በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
የነገ የጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…ጤና ሚኒስቴር ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለሆስፒታሎች የተሽከርካሪ ድጋፍ ርክክብ አካሄደ
ጤና ሚኒስቴር ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለሆስፒታሎች የጤና አገልግሎት የሚውሉ አምቡላንሶችን ጨምሮ 260 ተሽከርካሪዎችን፣ 572 ሞተር ብስክሌቶችን፣ 2 ሺህ 700 ኮምፒዩተሮችን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ ድጋፍ አድርጓል።
የጤና ሚኒስትር ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ለተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች የተሽከርካሪ እና የህክምና ቁሳቁስ ርክክብ አካሂደዋል
የጤና ሚኒስትሮ በዝግጂቱ ላይ እንደገለጹት፥ የዜጎችን ጤንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል
የዛሬው የተሽከርካሪ እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የጤና ተቋማት የዜጎችን ጤንነት ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያጎለብት መሆኑንም አነስተዋል።
አቤል እሰጤፋኖስ
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
በዎላይታ ዞን ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጉዳት የ7 ወገኖች ሕይወት አለፈ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጉዳት የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ እንዳስታወቀው በካዎ ኮይሻ ወረዳ ላሾ እና 01 ቀበሌዎች የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ በሁለት ሰዎች እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ከዚህ ቀደም በዞኑ ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወቃል።
በክልሉ ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት መለፉም አይዘነጋም።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ በፓርላማ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ
ትናንት ፓርላማው ያፀደቀው የሚኒስትሮች ሹመት የአሠራር ጥያቄን በተመለከተ እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነገ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጡ ታወቋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
አሜሪካ 'አሰቃቂ’ ስትል በጠራችው የእስራኤል ጥቃት 93 ፍልስጤማዊን ተገደሉ
በሰሜን ጋዛ ቤይት ላሂያ ከተማ ላይ እስራኤል በፈጸመችው አየር ጥቃት ቢያንስ 93 ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ሲያስታውቅ፤ አሜሪካ በበኩሏ ‘አሰቃቂ’ ስትል ፈርጃዋለች።
የነፍስ አድን ሠራተኞች ባለ 5 ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ መመታቱን የገለጹ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩ ቪዲዮዎች ደግሞ በብርድ ልብስ የተሸፈኑ በርካታ አስከሬኖችን አሳይተዋል።
የእስራኤል ጦር “(ማክሰኞ) በቤይት ላሂያ አካባቢ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሚገልጹ ዘገባዎችን አውቋል” ብሏል። የአደጋው ዝርዝር ሁኔታ እየተጣራ መሆኑንም አክሏል።
የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ወረራ ባካሄደባቸው በሰሜን ጋዛ በተለይም በጃባሊያ፣ ቤይት ላሂያ እና በቤይት ሃኖን አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
በአቅራቢያው የሚገኘው የጃባሊያ ካማል አድዋን ሆስፒታል ዳይሬክተር የሆኑት ሁሳም አቡ ሳፊያ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ህጻናት በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን በሐኪሞች እና በመድሃኒት እጥረት ምክንያት ህሙማንን ለማከም እየታገሉ መሆኑን ገልጸዋል።
"ሠራዊቱ የሕክምና ቡድናችንን እና ሠራተኞቻችንን ካሰረ በኋላ ከመጀመሪያ እርዳታ መስጫዎች ውጭ በካማል አድዋን ሆስፒታል ውስጥ ምንም የቀረ ነገር የለም" ብለዋል።
ሆስፒታሉን የሐማስ ተዋጊዎች እየተጠቀሙበት ነው በማለት የእስራኤል ጦር ባለፈው ሳምንት ወረራ ፈጽሞበታል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
" ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ "ተቀራርቦ መነጋገርን የመሰለ ነገር የለም" በማለት ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በጋራ ከተነሱት ፎቶ ጋር በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጌታቸው፣ ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም በማለት ኹለቱን የሕወሓት ቡድኖች ለማገናኘት ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ አካላትን አመስግነዋል።
ጌታቸው ከደብረጺዮን ጋር በምን ጉዳዮች ላይ እንደተነጋገሩ፣ መቼና የት እንደተገናኙ ወይም የትኞቹ አካላት እንዳቀራረቧቸው ግን አልገለጡም።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች "ፋይዳ" መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ መሆኑን አስታወቀ
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ደንበኞች "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተቋሙ ባወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡
በመሆኑም ከህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ደንበኞች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ማሳሰቡን ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
ስትሮክ (stroke)
ማንኛውም ሰው በስትሮክ ህመም ሊጠቃ እንደሚችል ይነገራል፡፡
እድሜያቸው ከ55 አመት በላይ የሆኑ የማህበረተሰብ ክፍሎች በዚህ ህመም የመጠቃት እድላቸው ከሌላው ሰው ከፍተኛ መሆኑም ነው የሚነሳው ፡፡
በጉዳዩ ላይም ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የነርቭ ህክምና ክፍል መምህር እንዲሁም በላንሴት ሆስፒታል የነርቭ ህክምና ክፍል ሃላፊ እና ሃኪም የሆኑት ዶክተር ያሬድ ዘነበ ናቸው፡፡
ስትሮክ ምንድን ነው ?
ድንገተኛ የሆነ ወደ አንጎል የሚሄድ የደም ፍሰት በመቋረጡ ምክንያት አንጎል ውስጥ ያሉ ነርቮች በቂ ደም ሳያገኙ ሲቀሩ የሚፈጠር ነው ይላሉ ፡፡
መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
- የእድሜ መጨመር
- የአኗኗር ዘይቤ እና አመጋገብ ባህል
- ስኳር ህመም
- ማጨስ
- አልኮል ከመጠን በላይ መውሰድ
- የደም ግፊት
- የልብ እና የኩላሊት ህመም
- የአየር ብክለት ተጠቃሽ ናቸው
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
- የፊት መጣመም
- የአንድ እጅ መዛል /መደንዘዝ
- ሲያወሩ መንተባተብ መጀመር ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ያነሳሉ፡፡
መከላከያ መንገዶቹ ምንድን ናቸው?
- የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል(ውፍረት መቀነስ፣ቅባት የበዛበት ምግብ አለመመገብ፣የተመጣጠነ ምግብ መመገብ)
- ሲጋራ መጨስ ማቆም
- አልኮል መጠጦች ከመጠን በላይ መውሰድ መቀነስ
- የአካባቢ ብክለትን መቆጣጠር
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡
ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?
- የተከሰተበትን ሁኔታ መረዳት
- የሲቲስካን ምርመራ
- በደም ስር መዘጋት የመጣ ከሆነ ደም ስሩን የመክፈት ህክምናዎቸ ተጠቃሽ ናቸው ፡፡
በመጨረሻም ባለሙያው የጠቀሷቸውን ምልክቶች አንድ ሰው የሚያስተውል ከሆነ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም ሄዶ ተገቢውን ህክምና ማግኘት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሊከሰሱ ነው
የአትዮጵያ ህዘብ እንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት "ከክልሉ ጎን ለምን ተሳትፎ አላደረጋቸህም" በሚል ከስራቸው ተሰናበተው ለሁለት አመታት የቆዩት የፖሊስ ሰራዊት አባለት ምላሽ ባለማግኘታቸው ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደው አስታውቋል።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ጸሃዬ እምባዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አንደተናገሩት በሚቀጥሉት "አምስት ቀናት" ከጊዜዓዊ አስተዳደሩ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ጊዜያዊ አስተዳደሩን ፕሬዝዳንት እንደሚከሱ ተናግረዋል።
የአምስት ቀኑ ማስጠንቀቂያ ከጥቅምት 19 /02 /2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚቆጠር ነግረውናል፡፡
አቶ ጸሃዬ ፕሬዝዳነቱን የምንከሰው "አሰራሩ ስለሚያስገድድ እና ያሉበት የስራ ሃላፊ እሳቸውን የሚመለከት ስለሆነ እንጂ" ሌላ አላማ ኖሮን አይደለም ብለዋል።
በአሰራሩ መሰረት ፕሬዝዳነቱ ለክስ የሚቀርቡት ለትግራይ ክልል አቃቢ ህግ ቢሆንም አቃቢ ህጉ ደግሞ በክልል ጊዜዊ አስተዳደር ስር በመሆኑ ምክንያት አቃቢ ህጉ ሀላፊውን ለመክሰስ ስለማይችሉ ክሱ ለፌድራሉ ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንደሆነ ነግረውናል፡፡
ቅርንጫ ጽ/ ቤቱ የፖሊስ ሰራዊት አባለቱ ወደ ስራ እንዲመለሱ ውሳኔያቸውን እንዳሳለፉ የነገሩን አቶ ጸሃዬ ውሳኔው ከተወሰነ 33 ቀናት ቢያስቆጥርም እስካሁን ደረስ ምላሽ ባላመገኘቱ ምክንያት "የአምስት ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነው ወደ ክስ ለመግባት ተገደናል" ነው ያሉት።
ለአለም አሰፋ
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
ዳሽን ከፍታ የሶስተኛ ምእራፍ ስልጠናውን መስጠት ጀመረ፡፡
ሶስተኛው ምዕራፍ የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ቅድመ-ውድድር ሥልጠና በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናው በስራ-ፈጠራ፤በፅንሰ-ሃሳብ፤በፈጠራ ንድፈ ሃሳብ አዘገጃጀት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን በሥልጠናው የስራ-ፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ሃሳባቸውን በምን መልኩ ማቅረብና ወደ ሥራ መቀየር እንዳለባቸው የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡
ባንኩ ከውድድሩ በፊት ለሰልጣኞች ተግባራዊ ሥልጠና ለመስጠት በተለያዩ ከተሞች እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ዳሸን ባንክ አማካሪ ድርጅት ቀጥሮ ውጤታማ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የዳሸን ባንክ የቺፍ ስትራቴጅ ተወካይ አቶ ወልደማርያም ደረሰ አስታውቀዋል፡፡
ባንኩ የዳሽን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድርን ከማካሄዱ በፊት ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በባህር ዳር፣ ደሴ፣ መቀሌ፣አዳማ፣ድሬዳዋ፣ወላይታ፣ ሃዋሳና ጅማ ስልጠናውን ተደራሽ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ከስልጠናው በኋላ ሰልጣኞቹ የፈጠራ መነሻ ሃሳባቸውን በፅሁፍ በባንኩ ቅርንጫፎች በኩል እንዲያቀርቡ ይደረጋል ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት የተመረጡ ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ስልጠና ወስደውና በሌሎች ተያያዥ መርሃ ግብሮች እንዲሳተፉ በማድረግ እና የውድድሩ አሸናፊዎችን በመለየት ዕውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል፡፡
በተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
ባለፉት አመታት በተከናወኑት የዳሽን ከፋታ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች በባንኩ ፋይናንስ ተደርገው ስኬታማ ስራዎችን በማከናወን ለሌሎች ወጣቶች ጭምር የስራ ዕድል መፍጠር ችለዋል ሲል ባንኩ አስታውቋል፡፡
የውል ሰው ገዝሙ
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሠነድነት መጠቀም የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሠነድነት መጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ ለኢትዮጵያ) ናቸው፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ሥርዓቶቻቸውን በማቀናጀት ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሠነድነት መጠቀም ያስችላል ተብሏል።
በዚሁ መሠረት አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመሆን ምዝገባ ከመያዝ ጀምሮ እስከ መሳፈር ድረስ ያለውን የመንገደኞች አገልግሎት ባዮ ሜትሪክ መረጃን በመጠቀም ይበልጥ ለማቀላጠፍ ይሠራል ተብሏል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
ሰሜን ኮሪያ 10ሺህ ወታደሮቿን ወደ ሩሲያ መላኳ ተሰማ
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ሰሜን ኮሪያ ወታደሮቿን ወደ ሩሲያ ማስገባቷን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩት ፕዮንግያንግ ከሩሲያ ጎን ተሰልፋ ዩክሬንን ለመዉጋት እየተዘጋጀች ነዉ ብለዋል፡፡
አሜሪካ በበኩሏ ሰሜን ኮሪያ ዩክሬንን የምትወጋ ከሆነ ያልተገደበ የጦር መሳሪያ አቅርቦት ለኬይቭ እንደምታቀርብ አስታዉቃለች፡፡
ሰሜን ኮሪያ በበኩሏ ሩሲያን ለመርዳት ወታደሮቿን ብትልክ ህጋዊ እርምጃ እንደሚሆን ገልጻለች፡፡
ሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ የዩክሬኑ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ወታደራዊ ስምምነት በመፈራረም ጭምሮ ግንኙነታቸውን አጠናክረዋል።
ዩክሬን እና ምዕራባውያን ሀገራት ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ እያቀረበች ነው የሚል ክስ ሲያቀርቡባት ቆይተዋል።
አባቱ መረቀ
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ውስጥ 56 ከመቶ የሚሆኑት ከ1 ዓመት በላይ በተራዘመ የመፈናቀል ሁኔታ ዉስጥ ይገኛሉ- ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የአገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ሁኔታን አስመልክቶ ባወጣዉ ሶስተኛ ዙር ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ውስጥ 56 ከመቶ የሚሆኑት ከ1 ዓመት፤ 23 ከመቶ የሚሆኑት ከ2 እስከ 4 ዓመት እና 11 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከ5 ዓመት በላይ በተራዘመ የመፈናቀል ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ብሏል።
በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የሚከሰቱ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ በመንግስት እና በታጠቁ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ግጭቶች እንዲሁም በወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች ምክንያት የሚፈጠሩ ግጭቶች ከ68 በመቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ከመኖሪያ ቀያቸዉ ያፈናቀሉ መሆናቸዉንም ኢሰመኮ ገልጿል፡፡
ቀሪዎቹ እንደ ጎርፍ እና ድርቅ ባሉ ተፈጥሯዊ አደጋዎች እንዲሁም በልማት ፕሮጀክቶች እና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የተፈናቀሉ መሆናቸዉንም ኮሚሽኑ አስታዉቋል፡፡
ምርመራዉን በ8 ክልሎች በማከናወን በአጠቃላይ የ3መቶ33ሺህ8መቶ89 ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን መፈተሹንም ገልጿል፡፡
ተገቢው ጥበቃ የማይደረግላቸው እና የሲቪልነት ባሕሪን ያልጠበቁ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸው መጠለያ/ማቆያ ጣቢያዎች በመኖራቸው የተፈናቃዮች ያለሥጋት በደኅንነት የመኖር እና ከጥቃት የመጠበቅ መብት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም ነዉ ኢሰመኮ የገለጸዉ፡፡
በተለያዩ ጊዜያት ነዋሪዎችን ከመደበኛ የመኖሪያ ቦታቸው በኃይል በማፈናቀል የሰው ሕይወት እንዲጠፋ፣ ንብረት እንዲወድም፣ በሰዎች ላይ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ በሕግ እንዲጠይቁ አጥጋቢ እርምጃዎች አለመወሰዳቸው የሕግ የበላይነትን እና ተጠያቂነትን የማያረጋግጥ እንዲሁም የተፈናቃዮችን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚነፍግ ነው ሲል ገልጿል።
ይህም በሀገሪቱ በስፋት የሚስተዋለው ማንነትን መሠረት ያደረገ ሰዎችን በኃይል ማፈናቀል ተግባር ተባብሶ እንዲቀጥል አስተዋጽዖ አድርጓል ብሏል።
የሀገር ውስጥ መፈናቀል ሁኔታን በቅርበት የሚከታተለው ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት /IOM/ በግንቦት ወር 2024 ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር 3.3 ሚሊዮን ደርሷል ማለቱ ይታወሳል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም
ለሀገር ዉስጥ ገበያ የሚያቀርቡት የጨርቃ ጨርቅ አልባሳት የጥራት ጉድለት አለባቸው ተባለ።
ኢንደስትሪዎቹ ለሀገር ዉስጥ የሚያቀርቧቸዉ ምርቶች የሚኖራቸዉ የጥራት ደረጃን ለመጨመር የሚታይባቸዉ እንከን እንዳለባቸው ተነግሯል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ልማት ኢንስቲትዩት ተጠባባቂ ስራ አስፈፃሚ አቶ አላምረዉ አያልነህ ኢንደስትሪዎቹ ለሀገር ዉስጥ የሚያቀርብትን ምርት በጥራት ለማምራት የግንዛቤ ችግሮች አለባቸዉ ብለዋል።
"በምርቱ ላይ ጥራት መጨመር ወጪን ይጨምራል " የሚል እሳቤ እንዳለ የሚገልፁት አቶ አላምረዉ ኢንደስትሪዎቹ ለሀገር ዉስጥ እና ለዉጪ ገበያ ለይቶ የማምረት ችግሮች ስለመታየቱ ተናግረዋል።
ለሀገር ዉስጥ ፍላጎት የተለያዩ የጥራት መስፈርቶችን ሳያሟሉ ለገበያ ምርቶችን ማቅረብ ተፈላጊነትን ለመቀነስ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
በጥራት ማምረት ተጨማሪ ወጪ ያስወጣል የሚሉ አመለካከቶች አምራቾች ጋር ሊኖር አይገባም ያሉት አቶ አላምረዉ 85 በመቶ አሜሪካ መዳረሻ የሚያደረግ የዚህ ዘርፍ የዉጪ ንግድ ገበያ ለሀገር ዉስጥ ተጠቃሚ ጥራትን መጠበቅ ይገባዋል ይላሉ።
በኢንዱስትሪዎቹ ላይ የአቅም ግንባታ እና የክህሎት ክፍተቶች እንዳሉ የተገኙ ግምገማዎች ስለመኖራቸዉ ተነግሯል።
ይህንን ለመፍታት አምራች ኢንደስትሪዎች ሊመሩበት የሚገባ ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች መኖራቸውን አቶ አላምረዉ ለጣቢያችን ገልፀዋል።
በሀገሪቱ በአሁን ወቅት ከ395 በላይ ከፍተኛ እና መካከለኛ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንደስትሪዎች ያሉ ሲሆን 238 ያህሉ ሀገራዊ አምራቾች ናቸዉ ተብሏል።
ቁምነገር አየለ
ጥቅምት18 ቀን 2017 ዓ.ም
የማንችስተር ዩናይትድን ቀጣዩ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም!!!
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ከሁለት አመታት በፊት ክለባቸው ስፖርቲንግ ሊስበንን ከ 19ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ እንዲያሳካ ረድተዋል።
የባለፈው የውድድር አመት ተጨማሪ የሊግ ዋንጫ ለክለባቸው ማሸነፋቸው በታላላቅ ክለቦች አይን ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ስፖርቲንግ ሊስበንን እየመሩ ያደረጓቸውን ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች በማሸነፍ በሀያ ሰባት ነጥቦች ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ።
በዘንድሮው የውድድር ዘመን ስፖርቲንግ ሊስበን በዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ሰላሳ ግቦችን በተጋጣሚዎቹ ላይ ሲያስቆጥሩ የተቅጠሩበት ሁለት ግቦች ናቸው።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በ 3-4-3 እንዲሁም 3-4-2-1 የጨዋታ አሰላለፍ እንደሚመርጡ ያላቸው ቁጥራዊ መረጃ ያስረዳል።
አሰልጣኙ ኳስ የሚቆጣጠር ፣ ተለዋዋጭ የማጥቃት ባህሪ ያለው እና ጠንካራ የመከላከል መሰረት ያለው ቡድን በመገንባት እንደሚታወቁ ተገልጿል።
አሰልጣኙ በስፖርቲንግ ሊስበን ቆይታቸው ኑኖ ሜንዴዝ ፣ ኑኔስ ፣ ማኑኤል ኡጋርቴ እና ፓልሂንሀን የመሳሰሉ ባለተሰጥኦ ተጨዋቾችን ማብቃት ችለዋል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን ከተረከቡ ከቡሩኖ ፈርናንዴዝ እና ማኑኤል ኡጋርቴ ጋር ዳግም አብረው የሚሰሩ ይሆናል።
በአውሮፓ ስድስቱ ታላላቅ ሊጎች ያለፈው የውድድር አመት ከተጀመረ ጀምሮ እንደ ስፖርቲንግ ሊዝበን ብዙ ጎሎች ያስቆጠረ አንድም ቡድን የለም 126 ጎሎች !
በተመሳሳይ ካለፈው የውድድር አመት ጀምሮ በስድስቱ ታላላቅ ሊጎች እንደ ስፖርቲንግ ሊዝበን ብዙ ጨዋታ ያሸነፈም ቡድን የለም 38 ጨዋታዎች !
ሩበን አሞሪም በማን ዩናይትድ ታሪክ በእድሜ ትንሹ አሰልጣኝ ነዉ 39 አመት ።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል መጠነ ሰፊ የፆታዊ ጥቃት እየፈፀመ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት ገለፀ
ድርጅቱ በሪፖርቱ የቡድኑ ታጣቂ ሀይሎች ሴቶችን በማሰር የቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች ፈፅመዋል ይህም የጦር ወንጀል ተደርጎ ተወስዷል ብሏል።
ሪፖርቱን ያቀረበዉ የድርጅቱ አጣሪ ቡድን የሱዳን ጦር ሀይሎችንም የሚመለከት መሆኑን አያይዞ ቢገልፅም አብዛኞቹ የአስገድዶ መድፈር እና ሴቶችን የወሲብ ባርነት ስር በማድረግ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ታጣቂዎች የደረሱ መሆናቸዉን አረጋግጧል።
ከፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ዉጪ ያሉ ተቃዋሚዎች ለመቅጣት የሚደረግ ስልት ነዉ ሲል ሪፖርቱ አስረድቷል
እነዚህ ጥቃቶች በአብዛኛው በካርቱም÷ ዳርፉር እና አልጃዚራህ ግዛቶች ላይ በሰፊዉ እየተፈፀመ መሆኑ ተገልጿል።
የቡድኑ ሊቀመንበር መሀመድ ኦትማን በተለይም በዳርፉር ጾታዊ ጥቃት በ ጭካኔ እንደሚፈጸም ገልጿል፤ ይህም አብዛኛውን ጊዜ በጦር መሳሪያ፣ ቢላዋ እና አለንጋ ተጎጂዎችን በማስፈራራት ይፈፀማል ብለዋል
ተጎጂዎች በጾታ እና በጎሣቸው ተመስርተው በተደጋጋሚ ኢላማ ይደረጋሉ በዚህም ለጾታዊ ጥቃት እና የግድያ ዛቻዎች መዳረጋቸውን አሳዉቋል።
ሊቀመንበሩ ገለልተኛ የጥበቃ ሃይል በአስቸኳይ እንዲሰማራ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያስችሉ መንገዶች መፈጠር አለባቸው ብለዋል ።
አሁን ሱዳን ውስጥ ምንም አስተማማኝ ቦታ አለመኖሩን አያይዘው ገልፀዋል።
ቁምነገር አየለ
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ለአገራት የብድር መክፈል አቅም ደረጃ የሚያወጣው ዓለማቀፉ ፊች ሬቲንግስ፣ የኢትዮጵያን ብድር የመክፈል አቅም ከቀድሞው ደረጃ "ሲሲሲ ማይነስ" ወደ "ሲሲሲ ፕላስ" አሻሽሎታል።
ተቋሙ የኢትዮጵያን ብድር የመክፈል አቅም ደረጃ ያሻሻለው፣ በአገሪቱ ላይ የነበረው የገንዘብ ጫና በመቃለሉ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት በመፈጠሩና በሂደት ላይ ያሉ የእዳ ሽግሽግ ድርድሮች ከኢትዮጵያ ብር ጋር ያልተያያዙ በመኾናቸው እንደኾነ ገልጧል።
በተያዘው በጀት ዓመት የመንግሥት የአገር ውስጥ ብድር ከአጠቃላይ አገራዊ ምርት አንጻር ወደ 0 ነጥብ 5 በመቶ ይወርዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተቋሙ ገልጧል።
ባለፈው በጀት ዓመት የመንግሥት የአገር ውስጥ ብድር ከአጠቃላይ አገራዊ ምርት አንጻር 1 ነጥብ 7 በመቶ ደርሶ ነበር።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ 2 ነጥብ 6 ትሪሊዮን መድረሱን አስታውቋል።
ባንኩ፣ በሩብ ዓመቱ ውስጥ 121 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱንም ገልጧል።
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ባንኩ 640 ሚሊዮን የገንዘብ ዝውውር በዲጂታል አማራጮች መካሄዱንና ይህም ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ46 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አውስቷል።
በባንኩ የዲጂታል የክፍያ አማራጮች የ3 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር ግብይት እንደተፈጸመም ተገልጣል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የነገ የጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…እስራኤል በሊባኖስ ባደረሰችዉ ጥቃት ከ60 በላይ ሰዎች ተገደሉ፡፡
እስራኤል በሊባኖስ ቤካ ሸለቆ በአንድ ሌሊት ባደረሰችዉ ጥቃት ከ60 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉ እንዳለፈ ተገልጿል፡፡
እስራኤል ካለፈው ወር ጀምሮ የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ላይ ያነጣጠረ ነዉ ያለችዉን ጥቃት አጠናክራ መቀጠሏ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ የሊባኖስ ባለስልጣናት፣ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የተጎዱ የከተሞች ነዋሪዎች ጥቃቱ ያለ ልዩነት የሚፈጸም ነዉ ይላሉ፡፡
በአንድ ሌሊት በደረሰዉ ጥቃት 67 ሰዎች ሲገደሉ ከ1መቶ20 በላይ ሰዎች ቆስለዋል የተባለ ሲሆን ፤የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር ይችላል ተብሏል ።
በጥቃቱ ዙሪያ እስካሁን ከእስራኤል የተሰጠ አስተያየት የለም።
በጋዛ ካለዉ ጦርነት ጎንለጎን በሊባኖስ የእስራኤል ጦር እና ሄዝቦላህ ከአንድ አመት በፊት በጀመሩት የተኩስ ልውውጥ ከ2 ሺህ 7 መቶ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
ከዚህ የሟቾች ቁጥር ዉስጥ ሁለት ሶስተኛው የሚሆኑት እስራኤል የቦምብ ጥቃት ዘመቻዋን ባጠናከረችበት ባለፉት አምስት ሳምንታት ውስጥ የተገደሉ ናቸዉ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
እስራኤል የተባበሩት መንግሥት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲን አገደች
የእስራኤል ፓርላማ የተባበሩት መንግሥት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ በእስራኤል እና እስራኤል በምትቆጣጠረው ምስራቅ እየሩሳሌም እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ አዋጅ አፅድቋል።
በውሳኔው መሠረት በተለምዶ ኡንርዋ የተባለው የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ በሶስት ወራት ውስጥ አካባቢውን ለቆ መውጣት አለበት።
በኤጀንሲው እና በእስራኤል ባለሥልጣናት መካከል የሚደረገው ግንኙነት የሚቋረጥ ሲሆን ድርጅቱ በጋዛ እና በዌስት ባንክ መንቀሳቀስ ሊያዳግተው ይችላል።
የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ የሚያስኬደውን መንገድ ስለሚቆጣጠር ኤጀንሲው ያለጦሩ ፈቃድ ወደ ጋዛ ሰርጥ መግባት አይችልም። ኤጀንሲው በአካባቢው እየተንቀሳቀሰ ያለ ብቸኛው የተባበሩት መንግሥታት ተቋም ነው።
የኡንርዋ ሠራተኞች እስራኤል ውስጥ ለመሥራት የነበራቸው ፈቃድ የሚሰረዝ ሲሆን ምስራቅ እየሩሳሌም የሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤትም ይዘጋል።
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አዲሱ ሕግ “በእስራኤል እና ፍልስጤም መካከል እንዲሁም በቀጣናው ሊፈጠር የሚገባውን ሰላም እና ፀጥታ የሚያጨልም ነው” ያሉ ሲሆን የኡንርዋ ኃላፊ ፊሊፔ ላዛሪኒ በበኩላቸው “የፍልስጤማዊያንን ስቃይ የበለጠ የሚጨምር” ውሳኔ ነው ብለዋል።
ዩናይትይት ስቴትስ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ጀርመን በእስራኤል ውሳኔ የተሰማቸውን ስጋት ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት ከ2 ሚሊዮን በላይ በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ፍልስጤማዊያን እርዳታ የሚያገኙት በኤጀንሲው በኩል ነው።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ “በሽብርተኝነት ተግባር ላይ የተሰማሩ የኡንርዋ ሠራተኞች ተጠያቂ ሊሆን ይገባል” ብለው ነገር ግን በጋዛ ሰብዓዊ እርዳታ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።
በኤክስ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት “የእስራኤልን ደኅንነት በጠበቀ መልኩ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ተባብረን ለጋዛ ሰላማዊ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳት ለማድረስ ዝግጁ ነን” ሲሉ ፅፈዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን።
እስራኤል ኡንርዋ በጋዛ በመንቀሳቀሱ ያላትን ተቃውሞ ለዓመታት ስታሰማ ብትቆይም በተለይ በቅርብ ዓመት የበለጠ ቅዋሜዋ ጠንክሯል።
እስራኤል እንደምትለው የኡንርዋ ሠራተኞች በጋዛ ከሐማስ ጋር ይሠራሉ፤ አልፎም 19 የኡንርዋ አባላት ሐማስ ባለፈው ዓመት መስከረም ባደረሰው ጥቃት ላይ እጃቸው አለበት ስትል ትወቅሳለች።
ኡንርዋ በእስራኤል ክስ መሠረት ምርመራ ከፍቶ ወቀሳ የቀረበባቸውን 9 የኤጀንሲውን አባላት ያባረረ ቢሆንም እስራኤል ጠለቅ ያለ ማስረጃ አላቀረበችም ሲል ተችቷል።
ኤጀንሲው እንደሚለው ከሐማስ ጋር የሚተባበረው የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ብቻ ነው።
ኡንርዋ ለበርካታ አስርት ዓመታት በጋዛ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ፍልስጤማዊያን የሰብዓዊ እርዳታ ጨምሮ የጤና አገልግሎት እና ትምህርት ሲያቀርብ ቆይቷል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
ምክር ቤቱ የ5 ሚኒስትሮችን ሹመት አጸደቀ
ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ነው የምኒስትሮችን ሹመት ያጸደቀው።
ሹመታቸው የጸደቀላቸው ሚኒስትሮችም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጤሞቲዎስ
የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያ ሥላሴ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ናቸው
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
የአገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ባለመመዝገባቸዉ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር ሆኖብኛል ሲል በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሽረ ቅርንጫፍ ገለጸ፡፡
በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ ከዞን እና ወረዳዎች የመጡ የተለያዩ ተፈናቃዮች መኖራቸዉ ሲገለጽ ፤ ተገቢዉ ምዝገባ ባለመደረጉ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ሽረ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሌ አብርሃ ፤ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፤በከተማዋ ከምዕራብ ትግራይ የመጡ የአንድ ዞን ነዋሪዎች ተፈናቅለዉ እንደሚገኙ ነግረዉናል፡፡
በተለያዩ ከተማዎችም በኤርትራ በኩል ያልተመለሱ እንዲሁም ተጨማሪ ሌሎች ከሶስት ወረዳዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መኖራቸዉንም አንስተዋል፡፡
ይህ የተፈናቃይ ቁጥር ከሌሎች መደበኛ ነዋሪዎች ጋር ያልተመዘገበ በመሆኑ መድሃኒት አቅርቦት ላይ ችግር ፈጥሮብናል ብለዉናል፡፡
ለተመዘገበ ነዋሪ የሚላከዉ የመድሃኒት ኮታ ቢኖርም ያልተመዘገቡ ተፈናቃዮች በመኖራቸዉ ግን መድሃኒቱን በበቂ ሁኔታ ማከፋፈል አልተቻለም ነዉ ያሉት፡፡
የአገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ጉዳይ አሁንም ችግር ሆኖ ቀጥሏል የሚሉት ስራ አስኪያጁ፤ በተቻለን መጠን በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት እየሞከርን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ችግሩ በመንግስት ባይፈታም እኛ ተግባብተን ለመፍታት እየሞከርን ነዉ ያሉት አቶ ሙሌ፤ ወረዳዎች መድሀኒት ሲጠይቁ ተፈናቃዮችንም ከቁጥር አስገብተዉ እንዲጠይቁ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ይህ ችግር የአገልግሎቱም ሆነ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ሳይሆን የአገሪቱ ችግር ይመስለኛል ያሉት ስራ አስኪያጁ ፤ ከመንግስት መፍትሄ ባይገኝም ከወረዳዎቹ ጋር ግን በመተባበር ለመፍታት እየሞከርን ነዉ ብለዋል፡፡
እስከዳር ግርማ
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
‹‹በዘፈቀደ የሚሰጡ ሹመቶች ከባድ ቅጣትን ያስከትላሉ›› የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር
ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፍቃድና እውቅና ውጪ የሚደረጉ ሹምሽሮች እስከ በጀት መገደብ የሚደርስ ቅጣት ሊጣል ይችላል ሲል በጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር አስጠንቅቋል፡፡
ጊዚያዊ አስተዳደሩ በአቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ ተፈርሞ ባሰራጨው መመሪያ ፤ " የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች ማደናቀፍ እና በዘፈቀደ ህጋዊ ያልሆነ ሹመት መስጠትና መንሳት የበጀት ቅጣትና የህግ ተጠያቂነት ያስከትላል " ሲል ነው ማስጠንቀቂያ የሰጠው።
መንግስታዊ ስልጣን እና ሃላፊነት የሌለው ' ቡድን ' በማለት የተጠቀሰው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የሚሰጠው ሹመት የመሻርና ሹመት የመስጠት ተግባር ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
በመሆኑም ቡድኑ የሚያካሄዳቸውን ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት እንዲቆም ይህንን የጊዚያዊ መንግስቱ መመሪያ በመቀበል ፍርድ ቤት ጨምሮ የዞን እና የወረዳ የመንግስት መዋቅሮች ህጋዊ አሰራር እንዲከተሉና ህግ በሚጥስ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንዲሁም በክልሉ በየመዋቅሩ ያሉ ምክር ቤቶች ጊዚያቸው ያለፈ እና ህጋዊ መሰረታቸው ያበቃ መሆኑን በመቀበል ሹመት ከመስጠትና ከመሻር እንዲቆጠቡ ሲል ነው ያሳሰበው፡፡
ላለፉት ወራት የዘለቀው የህወሃት አመራሮች ፍትጊያ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን እኔ ብቻ ነኝ እውቅና ያለኝ የሚለው የሁለቱ ቡድኖች መካረርም ምንም አይነት መፍትሄ አላገኘም፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተሰናበቱ
ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ከሀላፊነት ማሰናበታቸውን ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ አረጋግጧል።
ማንችስተር ዩናይትድ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምትክ ሩድ ቫኔስትሮይን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት እንደሚሾሙ ተገልጿል።
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን በሀላፊነት እየመሩ በሊጉ ደካማ ጉዞ በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም
ግምቱ 1 መቶ 55 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ህገወጥ የመድሃኒት ምርት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ፡፡
የኢትዮጲያ ምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አጠቃላይ ግምቱ ከ1 መቶ 55 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ህገ-ወጥ የመድኃኒት ምርት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ በቃሉ አረጋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከአምስት ክልሎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት በኦሮሚያ ክልል ወደ 15 ሚሊዮን፣ በደቡብ ምዕራብ 6 ሚሊዮን፣በቤኒሻንጉል ጉሙዝ 500 ሺ ፣በጋምቤላ 26 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ እና በማእከላዊ ኢትዮጲያ ደግሞ 1 መቶ 7.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ህገወጥ መድሀኒቶች መያዛቸውን ነው የጠቀሱት፡፡
ይህን ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙ አካላት ላይ ከተወሰደባቸው እርምጃዎች መካከል የማሸግ ፣የእገዳ፣ የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ እና ፍቃድ የመሰረዝ እርምጃዎች እንደሚገኙበት ነግረውናል፡፡
በቁጥጥር ስራው የተገኙት ህገ-ወጥ መድሃኒቶችም የህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ የማስወገድ እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው አንስተዋል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ጥቅምት18 ቀን 2017 ዓ.ም
ኢራን ለእስራኤል የመልስ ምት እንደምትሰጥ አስታወቀች
የኢራኑ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዝሽኪያን ምንም እንኳን ጦርነት ባንፈልግም እስራኤል ግን መቀጣቷ አይቀሬ ነዉ ብለዋል፡፡
እስራኤል ለፈጸመችዉ ፀብ አጫሪ ድርጊት ትክክለኛና ተመጣጣን ቅጣት እንደሚጠብቃት ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡
የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካህሚኒ በበኩላቸዉ የእስራኤል ጥቃት የሚጋነንና ያነሰ ባይሆንም እርምጃ እንደሚወስዱ ግን አረጋግጠዋል፡፡
የእስራኤሉ ጥቃት ከሰዓታት በፊት የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባቃይ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ከጥቃቱ በኋላ ወደ ጦር ሰፈራቸው ሲመለሱ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር አንቀጽ 51 ላይ እንደተገለጸው ራስን የመከላከል መብት እንዳላቸው አመልክቷል።
መግለጫው ኢራን ለውጭ ጥቃቶች ምላሽ የመስጠት መብት እና ግዴታ እንዳለባት ታምናለች ብሏል።
አገራት ለሚሰነዘርባቸው ጥቃት ምላሽ ካልሰጡ እንደ ደካማ እና ስጋት እንዳልሆኑ እንደሚታዩ ካመኑ ተከታታይ ዙሮችን እና የአጸፋ ጥቃቶችን ማቆም ከባድ ነው። ጦርነቶች ከቁጥጥር ውጪ የሚወጡትም በዚህ ምክንያት ነው።
አሁን ጥያቄው ኢራን ቢያንስ በዚህ የጦርነቱ ደረጃ ለእስራኤል አጸፋ እንደማትመልስ የመጨረሻውን ቃል ለመስጠት ተዘጋጅታለች ወይ የሚለው ነው።
አባቱ መረቀ
ጥቅምት18 ቀን 2017 ዓ.ም