ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በትግራይ ክልል 40 በመቶ ህጻናት የመቀንጨር ችግር እንዳጋጠማቸው ተነገረ

በትግራይ ክልል እናቶች እና ህጻናት ያሉበትነ ሁኔታ ለማወቅ ያስችላል የተባለለት ጥናት ክልሉ መካሄዱን ጣቢያችን ሰምቷል፡፡

በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የ ስነ-አመጋገብ ጉዳይ ቡድን አስተባባሪ አቶ መንገሻ ባህረሥላሴ ህጻናቱ ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ የሚለውን ለማየት ዩኒሴፍ በሚያስተባብረው የስነ ምግብ ጥናት እንዳተካሄደ ተናግረዋል ፡፡

በጥናቱ መሰረት መካከለኛ እና የከፋ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ህጻናት ቁጥር 17.9 በመቶ እንደሆነ አንስተዋል ።

አቶ መንገሽ ባህረስላሴ እንዳሉት ጥናቱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በሚያስተዳድራቸው 73 ወረዳዎች ብቻ የተሰራ ነው ።

አሁን ላይ ያለው ሁኔታ ከባድ እንደሂነ የሚናገሩት አቶ መንገሻ በክልሉ የሚታየው የህጻናት መቀንጨር በሀገር አቀፍ ከሚታየው ምጣኔ ከፍ ያለ ነውም ብለዋል።

በትግራይ ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ቁጥር 9 መቶ ሺህ እንደሚሆኑ ፣የሚያጠቡ እናቶች ቁጥር ደግሞ ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ 3.4 በመቶ እንደሚይዙ ይገመታል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ከ 8 ወራት በፊት ከ ትግራይ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጋር በመተባበር በጋራ አካሄድኩት ባለው ጥናት 28 % የክልሉ ህጻናት መካከለኛ እና አጣዳፊ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው አረጋግጦ ነበር።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 26  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አርሰናል እና ጋኤዱ ጋስፐር ይለያያሉ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ብሬዚላዊ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤዱ ጋስፐር ከክለቡ ጋር ለመለያየት መወሰናቸውን ተገልጿል ።

ኤዱ ጋስፐር መድፈኞቹን የሚለቁት በኖቲንግሀም ፎረስት ባለቤት ኢቫንጄሎስ ማሪናኪስ ከሚተዳደሩ ክለቦች ጋር የመስራት እድል አግኝተው መሆን ተነግሯል።

ስፖርቲንግ ዳይሬክተሩ ከአምስት አመታት በላይ ከቆዩበት አርሰናል ለመልቀቅ የወሰኑት በአዲስ ሀላፊነት መሆኑ ተገልጿል።

ግሪካዊው ባለቤት ኢቫንጄሎስ ማሪናኪስ ከኖቲንግሀም በተጨማሪ ኦሎፒያኮስ እና የፖርቹጋሉን ክለብ ሪዮ ኤቭ በባለቤትነት ያስተዳድራሉ።

ዘ አትሌቲክ

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኦፔክ ሀገራት በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የነዳጅ ምርት ቅነሳን እስከ 2025 ማራዘማቸዉን ገለጹ፡፡

ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፣ ኩዌት እና ኦማንን ጨምሮ 8 የኦፔክ ፕላስ አገራት በፈቃደኝነት የነዳጅ ምርት ቅነሳዉን እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ለማራዘም ተስማምተዋል፡፡

ስምንቱ የኦፔክ ፕላስ አገራት ሳዑዲ አረቢያ፣ ሩሲያ፣ ኢራቅ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኩዌት ፣ ካዛኪስታን፣ አልጄሪያ እና ኦማን በ2023 ያደረጉትን የነዳጅ ምርት ቅነሳ ማስተካከያን እስከ 2024 መጨረሻ ለማራዘም መስማማታቸዉ ተዘግቧል፡፡

በዚህም ለቀጣይ አንድ ወር በቀን 2.2 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ለማምረት ተስማምተዋል፡፡

የኦፔክ አገራት ከህዳር 2022 ጀምሮ በቀን ወደ 3.6 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ምርትን ሲቀንሱ ቆይተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አባል አገራቱ ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ በግላቸዉ የተለያየ መጠን የነዳጅ ምርት ሲቀንሱ መቆየታቸዉ የተገለጸ ሲሆን፤ ከሰሞኑ ካወጡት መግለጫ በኋላ ቅነሳዉ እስከዚህኛዉ ዓመት መጨረሻ ድረስ እንደሚቀጥል አስታዉቀዋል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ከዚህ በፊት በቀን ታመርት ከነበረዉ 11 ሚሊየን በርሜል ፤ አሁን ላይ 10 ሚሊየን በርሜል እያመረተች ትገኛለች፡፡

የነዳጅ ምርት ቅነሳዉ እስከ ታህሳስ መጨረሻ የተራዘመበት ምክንያት ይፋ ባይሆንም፤ በዚህ ሳምንት የሚደረገዉ የአሜሪካ ምርጫ ምናልባት ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 25  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማን ጨምሮ በሰባት ወረዳዎች ላይ የወባ በሽታ መከሰቱ ተገለጸ

በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማን ጨምሮ በሰባት ወረዳዎች ላይ የወባ በሽታ መከሰቱን የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዳመነ ደባልቄ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የወባ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ልየታ በማድረግ እና ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ በማድረግ አስፈላጊውን ሕክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።

የመከላከያ ኬሚካል በሀገር ውስጥ መመረት በመቆሙ ምክንያት እጥረት መኖሩን ገልጸው በአራት ወረዳዎች ላይ ርጭት ተደርጓል ብለዋል። ተጨማሪ ኬሚካል እና አጎበሮች እንዲላክ ለጤና ሚኒስቴር ጥያቄ መቅረቡን አክለው ገልጸዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት አዲስ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ከታህሳስ 23፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ7.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን እና ከእነዚህም መካከል 1,157 ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ወባ አሁንም አሳሳቢ የጤና ስጋት ሲሆን 75 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ መሬት እና 69 በመቶ የሚሆነው በነዚህ አከባቢዎች የሚኖረው ህዝብ በተለይም ህጻናት ለከፍተኛ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁሟል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶች ቁጥር 74 በመቶ መድረሱ ተገለፀ፡፡

በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ያገኙ እናቶችን 74 በመቶ ማድረስ መቻሉን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ ይህን ያሉት፤ የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትን ለማጠናከር ያለመ ውይይት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነዉ፡፡

ሚኒስቴሩ የቤተሰብ ጤና ልማትን እንደ ዋና ስትራቴጂክ ዓላማ ይዞ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ጤንነቱ የተጠበቀና አምራች ዜጋ እንዲኖር በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በበኩላቸዉ÷ የእናቶችና ህጻናት፣ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶችን ጤና በሚፈለገዉ ልክ ለማሻሻል በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀትን እንደገና ለማጠናከር የሚረዳ ሀገር አቀፍ መመሪያ መዘጋጀቱን መግለፃቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዲሞክራቷ እጩ ካማላ ሐሪስ “የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አሉ።

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26/ 2015 ዓ.ም ከሚደረገው የአሜሪካ ምርጫ በፊት የመጨረሻ ቅስቀሳቸውን እያደረጉ ያሉት ካማላ ሃሪስ በሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርስቲ ተገኝተው ነው ይህንን ያሉት።

የአረብ አሜሪካውያን ከፍተኛው ህዝብ በሚገኝበት ሚቺጋን ግዛት ውስጥ ተገኝተው ነው ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት።

የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከፍተኛ የአረብ ህዝብ በሚኖርባት የዲርቦርን ከተማ በሳምንቱ መጨረሻ ተገኝተው ቅስቀሳ አድርገዋል።

ዲሞክራቶች ጦርነቱን የያዙበት መንገድ እንዲሁም እስራኤል በጋዛ ላይ በምታደርገው የተቀናጀ እና የማያባራ ጥቃት የባይደን አስተዳደር የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ላይ አረብ አሜሪካውያንን ያለባቸውን ቁጣ ለዚህ ቅስቀሳ ተጠቅመውበታል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በተወሰኑ ቦታዎች የመጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ

በዚሁ መሰረት፦
1. መገናኛ ውስጥ ተርሚናል ላይ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ
• ከመገናኛ - ቃሊቲ
• ከመገናኛ - ሳሪስ እና
• ከመገናኛ - ጋርመንት የመጫኛና ማውረጃ መስመሮች መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት፤

2. ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ተርሚናል ላይ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ
• ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና
• ከመገናኛ - ኮዬ ፈቼ የመጫኛና ማውረጃ መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ)፤

3. ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ተርሚናል ላይ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ
• ከመገናኛ - ገርጂ
• ከመገናኛ - ጎሮ
• ከመገናኛ - አያት እና
• ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና ማውረጃ መስመሮች ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጁ ጊዜያዊ ተርሚናሎች በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ቢሮው አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የመጀመሪያው የፓን አፍሪካ የሴቶች አመራርና ለውጥ ላይ የሚመክር ጉባኤ ተካሄደ ።

ጉባኤው ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

የዘንድሮ የፓን አፍሪካ "ሳውቦና" ጉባኤ፤ አፍሪካ በምታደርገው ጉዞ የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎና አመራር በምን መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግ ምክክር ተደርጎበታል።

ከዚህ በተጨማሪ በአፍሪካ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎን እንዴት ማንፀባረቅ ፣ ማሰብ እና ማቀድ ይቻላል በሚለው ላይም መክሯል።

ጉባኤው ሴቶች ፍትሃዊ እና አካታች አመራርን እንዴት መገንባት እና ማበርታት አለባቸው የሚለውንም ያሳየ መሆኑ ነው የተገለጸው።

በጉባኤው የሴቶች መብት ተሟጋቾች ፣ በአመራር ደረጃ ያሉ ሴቶች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ዓለም አቀፍ መሪዎች እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነውበታል።

በብዛት የህዝባቸው ቁጥር ወጣት ከሆኑ 20 አገራት መካከል 18ቱ በአፍሪካ የሚገኙ ቢሆንም፤ በወጣቶች አመራር ላይ ግን አለመሰራቱ ተነስቷል።

በ2030 በአፍሪካ ከሚኖሩ ዜጎች 42 በመቶው ወጣት እንደሚሆንም በጉባኤው ተገልጿል።

ወጣቶች እና ሴቶችን ወደ መሪነት ማምጣት እንደሚገባም ነው የተገለጸው።

ከአፍሪካ ሩዋንዳ 63 በመቶ የሚሆነው የመንግስት ስልጣን በሴቶች የተያዘ መሆኑ ሲገለፅ፤ አገሪቱን ለሴቶች የመሪነትን ድርሻ በመስጠት በመጀመሪያ ደረጃ እንድትቀመጥ አድርጓታል።

ይህንን ጉባኤ " አኪና ማማ ዋ አፍሪካ" የተሰኘ በሴቶች ላይ የሚሰራ ድርጅት ከአፍሪካ ልማት እና ኮሚኒኬሽን እና ከታንዛኒያ የፆታ ጉዳይ ትስስር ጋር በጋራ አዘጋጅተውታል።

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 22  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በቅርቡ ሥራ የጀመረው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከትናንት ጀምሮ ምርቱን ለገበያ እያቀረበ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ፋብሪካው የማምረት ሥራውን በፍጥነት እንዲጀምር የተደረገው ምርቱን በቶሎ ወደ ገበያ በማቅረብ በሀገር ደረጃ ያለውን የሲሚንቶ ገበያ ለማረጋጋትና እንደሀገር የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፋብሪካው ምርቱ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ከግብዓት ምርት ጀምሮ ዘመናዊና የተደራጀ ላቦራቶሪ ገንብቶ ባለሙያ መድቦ በብቃት እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ምርቱ ከሚመለከተው አካል የጥራት መስፈርት ያሟላ መሆኑንም ከፋብሪካው ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በበጀት አመቱ 72 ያህል ኘሮጀክቶች በኢንደስትሪዉ ዘርፍ ስራ ይጀምራሉ ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬዉ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ የኢንደስትሪ ዘርፍን ከነበረበት 59 በመቶ አቅም ወደ 67 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ተናግረዋል።

ከጠቀሳቸዉ አዳዲስ የኢንዱስትሪ አምራች ኘሮጀክቶች ዉስጥ በጨርቃጨርቅ 9 ኢንዱስትሪዎች በምግብ እና መጠጥ 41 ኢንዱስትሪ በኮንስትራክሽን እና ኬሚካል ግብአት አቅራቢ 4 ኢንደስትሪዎች ÷ በቴክኖሎጂ 15 ኢንደስትሪዎች እንዲሁም የወታደራዊ ግብአት ፋብሪካ 3 ወደ ስራ ይገባሉ ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የወርቅ ÷ የብረታብረት እና የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ ምርት እንደሚጠበቅባቸዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ የሀገር ዉስጥ ባለሀብቶች ለማሳተፍ ተደርጓል በተባለዉ ስራ 50 በመቶ ያህሉ አሳታፊ ለማድረግ መቻሉ ተነግሯል።

በዘንድሮዉ በጀት አመት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዉስጥ የኢንደስትሪዉ ዘርፍ 12.8 ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።

ቁምነገር አየለ

ጥቅምት 21  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በዘንድሮው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል ተባለ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሰጡት ማብሪያ በዘንድሮው በጀት ዓመትም 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ መታቀዱን ተናግረዋል ፡፡

ከዚህም ውስጥ ከግብርና 6 ነጥብ 1 በመቶ ፤ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

በጅምላ የሚገዛውን የመዳበሪያ አቅርቦት ትክክል አልነበረም ያሉት ጠቅላይ ምንስትሩ የምርት ጥራት እና ምርት እንዲጨምር እንዲያስችለን እያንዳንዱ መሬት የሚስማማውን አይነት ማዳበሪያ እናዘጋጃለን ብለዋል።

በዚህም በዘንድሮ አመት 30 ቶን ስንዴ ወይንም 300 ሚሊዮን ስንዴ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

ልዑል ወልዴ

ጥቅምት 21  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሩብ አመቱ  11 ቢሊየን ብር ገቢ ማስገባቱን ገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2017 የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀሙ ከሀይል ሽያጭ እንዲሁም ከአዳዲስ ደንበኞች ወደ11.5  ቢሊየን ብር ለማስገባት አቅዶ
11 ቢሊየን ብር ገቢ ማስገባቱን ገልጿል።

የተቋሙ ህዝብ ግግንኙነት ሀላፊ አቶ መላኩ ታዬ እንደገለፁት  ተቋሙ የሩብ አመት የአፈፃፀሙን እቅድ ወደ 97በመቶ አሳክቷል ብለዋል።

ገቢው የተገኘው ከሀይል ሽያጭ ከቋሚ ንብረቶች እንዲሁም ከአዳዲስ ደንበኞች የተገኘ ገቢ እንደሆነም ተገልጿል።

አቶ መላኩ ታዬ  የተገኘው ገቢ አዲሱን የታሪፍ ማሻሻያ ታሳቢ ያላደረገ እንደሆነም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ተቋሙ  ወደ 120 ሺ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ  አቅዶ  ወደ 90 ሺ ሰዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ አድርገናል ብሏል።

በዚህም የእቅዱን 75በመቶ ማሳካቱን አንስቷል።

በአዲሱ ሩብ አመት የዲሲፒሊን ግድፈትከ20 በላይ የተቋሙ ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱንም ገልጿል።

በሩብ አመቱ የሀይል መቆራረጥ እና የደንበች ቅሬታ አሁንም አለመቀረፉን ሀላፊው አንስተዋል።

ተቋሙ አሁን ላይ አጠቃላይ ደንበኛችንም ወደ 4ሚሊዮን ገደማ ማድረሱ ተሰምቷል።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 26  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከእዉነታ መራቅ (Dissociative disorder)

ይህ ችግር በአለማችን ላይ 1.5 በመቶ የሚሆነውን የማህበረሰብ ክፍል የሚያጠቃ የአዕምሮ ህመም መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በልጅነታቸው ፆታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ልጆች ለዚህ የስነ ልቦና ችግር የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል ፡፡

እንዲሁም ድንገተኛ አደጋ የሚያጋጥማቸው ሰዎችም ለዚህ ችግር ተጋላጭ መሆናቸው ይነሳል፡፡

ለዚህ ችግር ከሴቶች በበለጠ ወንዶች ተጋላጭ መሆናቸዉም ነዉ የሚገለጸዉ፡፡
በጉዳዩ ላይ ሙያዉ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የስነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት አቶ ልዑል አብርሀም ናቸዉ።

ከእውነታ መራቅ(Dissociative disorder) ምን ማለት ነዉ?
ዕለት ከዕለት ከሚያጋጥሙን እውነታዎች መነጠል አልያም ከአደጋ በኋላ ያጋጠሙንን ነገሮች መርሳት ማለት መሆኑ ይገለጻል፡፡

አልፎ አልፎ ደግሞ የምንወዳቸውን ሰዎች ስናጣ አዕምሯችን የምንወዳቸውን ሰዎች ማጣታችንን መቀበል ስለማይፈልግ ለዚህ ችግር ሊዳርገን እንደሚችልም ይነገራል፡፡

መንስኤዉ ምንድን ነዉ?
- እራሳችን ላይ የሚያጋጥም አደጋ ወይም የምንወደውን ሰዉ በድንገት ማጣት
- ያየነውን ወይም የሰማነውን ነገር መቀበል ባለመፈለጋችን ለመሸሽ መሞከር
- የአስተዳደግ ሁኔታ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ምልክቶቹም ምንድን ናቸዉ?
- አደጋ ከተፈጠረ በኃላ ሙሉ ለሙሉ ከነበሩበት ባህሪይ ወጥቶ አዲስ ባህሪይ ማሳየት
- ነገሩን ሙሉ ለሙሉ አለማስታወስ
- አልያም በወቅቱ የተፈጠረዉን ጥቂት ነገር አስታዉሶ ቀሪዉን ደግሞ ፈጽሞ መርሳት
- ከእዉነታው ርቆ አዕምሯችን በፈጠረዉ ነገር መኖር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የሚያመጣው ተፅዕኖ ምንድን ነው?
- አብሮን ከሚኖሩ ሰዎች ጋር መስማማት አለመቻል
- ከስራ ባልደረባ ጋር ለመግባባት መቸገር
- እዉነት የሆነዉንና ያልሆነዉን ነገር መለየት አለመቻልን ሊያስከትል ይችላል፡፡


በመጨረሻም የስነ-ልቦና ባለሙያዉ አብዛኛዉን ጊዜ እንደዚህ አይነት የስነ ልቦና ችግሮች የመከሰት እድላቸው ያነሰ ቢሆንም በሚከሰትበት ወቅት ግን ወደ ህክምና ተቋማት መሄድ እንደሚያስፈልግ ነግረዉናል፡፡

በተጨማሪም አቶ ልዑል በልጅነት የሚከሰቱ ጥቃቶች ለችግሩ እንደመንስዔ እንደሚነሱ አስታዉሰዉ ፤ ህፃናት ልጆች ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ እንዳይሆኑ በቂ ክትትል እና እንክብካቤ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 26  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል የኔትዎርክ ተደራሽነቱን ማስፋቱን ገለጸ፡፡

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ቀብሪበያ፣ ደጋሃቡር፣ ዋጃሌ እና አዉባሬ ከተሞች እንዲሁም በመሃል ያሉ ከተሞች ላይ የኔትዎርክ ተደራሽነቱን ማስፋቱን አስታዉቋል፡፡

የኔትዎርክ ማስፋፋያ ስራዉ ተቋሙ በግንኙነት እና ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ያለዉን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነዉ ተብሏል፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄልፑት ፤ የኔትዎርክ ተደራሽነት መስፋፋቱ በሶማሌ ክልል ለሚገኙ ግለሰቦችም ሆነ የቢዝነስ ተቋማት ተደራሽነትን በማስፋት አዳዲስ እድሎችን ይዞላቸዉ የሚመጣ ነዉ ብለዋል፡፡

እንደ ጎዴ ባሉ ቦታዎች ላይ የኔትዎርክ ተደራሽነትን ማስፋታችን ሰዎችን ከሰዎች ጋር፣ ሰዎችን ከእዉቀት ጋር፣ እንዲሁም ሰዎችን ከተለያዩ ዕድሎች ጋር ለማገናኘት ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዉ፤ ነዋሪዎች እና ከተማዋን የሚጎበኙ ሰዎች በ4ጂ ኔትዎርክ በመጠቀም የፈለጉትን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ነዉ ያሉት፡፡

አስተማማኝ የሆነ ኔትዎርክ ከማቅረባችን በተጨማሪ ፤ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በኤም-ፔሳ በኩል አቅበናል ሲሉም ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ተናግረዋል፡፡

የኤም-ፔሳ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት በሶማሌ ክልል በፍጥነት ተቀባይነት ማግኘቱን ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚዉ፤ በኢትዮጵያ ካሉ ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ነዉ የገለጹት፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኔትዎርክ ማስፋፊያ ስራዉን በስፋት እና በቅርበት ለመከታተል በጅግጅጋ የክልል ቢሮ እንደሚከፈት የተገለጸ ሲሆን፤ ቢሮዉ የስራ ዕድልም እንደሚፈጥር ተነስቷል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 25  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ታዳጊ ሀገራት ፍላጎታቸውን ያማከለ ውክልና በተባበሩት መንግስታት ድርጀት (ተመድ) ውስጥ ሊኖራቸው እንደሚገባ ኢትዮጵያ አስገነዘበች።

ኢትዮጵያ በሩሲያ ካዛን ከተማ የተካሄደውን 16ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ውጤት አስመልክቶ ጀኔቫ የሩሲ ፌደሬሽን ቋሚ መልዕክተኛ በተዘጋጀው ማብራሪያ መድረክ ላይ ተሳትፋለች፡፡

በመድረኩ የተሳተፉት በተመድ የጄኔቫ ቢሮ የኢፌዲሪ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጸጋአብ ክበበው እንዳሉት፤ ዓለም አቀፍ ተቋማት የአስተዳደር መዋቅራቸው እንዲሻሻል እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው።

በተለይም ታዳጊ ሀገራት በተመድ ውስጥ ፍላጎታቸው ያማከለ ውክልና ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።

ዓለም አቀፍ ግንኙቶች የታዳጊ ሀገራት ድምጽ እንዲሰማባቸው በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

በጄኔቫ የሚገኙ የብሪክስ አባል ሀገራት ቋሚ መልዕክተኞች፤ በሰብኣዊ መብቶች፣ በንግድ፣ በጤና፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፍ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን የቋሚ መልዕክተኛ ቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በጋዛ እና በሊባኖስ የነበረን ዘመቻ አጠናቀናል - የእስራኤል ወታደራዊ መሪዎች

የእስራኤል ወታደራዊ መሪዎች ሀገሪቱ በጋዛ እና ሊባኖስ በወታደራዊ ዘመቻዎች ማከናወን የፈለገቻቸውን አላማዎች በሙሉ ማሳካቷን አመልከተዋል፡፡

ሲኤንኤን እንደዘገበው ከሆነ፤ መሪዎቹ በይፋ ባይሆንም ወታደራዊ ዘመቻዎቹ መጠናቀቃቸውን እና ጦሩ ከዚህ በኋላ በሁለቱ ስፍራ መቆየቱ እምብዛም ጥቅም እንደሌለው እየተናገሩ እንደሚገኝ ዘግቧል፡፡

በወታደራዊ ኃይል የምትችለውን ሁሉ እንዳሳካች የገለጹት አዛዦቹ÷ ፖለቲከኞች ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜው አሁን መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የእስራኤል ጦር ከፍተኛ ጄነራል ከሰሞኑ በሰሜናዊ ጋዛ ከሚገኙ መኮንኖች ጋር ወቅታዊ የጦርነቱን ሁኔታ ለመገምገም በነበራቸው ስብሰባ፤ የግጭቱ ከዚህ በኋላ መቆየት እምብዛም ጥቅም የለውም ማለታቸው ነው የተሰማው፡፡

የሀገሪቱ ኢታማዦር ሹም ሄርዚ ሄልቪ በበኩላቸው “በጋዛ የሰሜን ጋዛ ብርጌድ አዛዥን ብንገድል ለቡድኑ ሌላ ውድቀት ነው፤ ነገ ምን እንደሚገጥመን አላውቅም፤ ነገር ግን ይህ ጫና ወደ ተጨማሪ ስኬቶች እንድንቀርብ ያደርገናል” ብለዋል፡፡

በሊባኖስ ሄዝቦላህ ላይ እየተካሄደ በሚገኝው ጦርነት አሁን በሚገኝበት ደረጃ አንድ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ እድሉ አለ ነው ያሉት ኢታማዦር ሹሙ፡፡

ከዚህ በፊት የእስራኤል የቀድሞ ጄነራሎች በተመሳሳይ የሀማሱ መሪ ያህያ ሲንዋር ግድያን የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የኔታንያሁ አስተዳደር እንዲጠቀምበት መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ወልቂጤ ከተማ በ2017 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚወዳደር ይሆናል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከ2017 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተሰረዘው ወልቂጤ ከተማ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የሚጠይቀውን መስፈርት በማሟላት እንዲወዳደር ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም መሠረት ወልቂጤ ከተማ በ2017 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ላይ ተደልድሎ የሚወዳደር ይሆናል።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 22  ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሩብን አሞሪም የማንቸስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ በመሆን መሾሙ ይፋ ሆኗል ።

ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከሀላፊነት ያሰናበተው ማንችስተር ዩናይትድ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ፖርቹጋላዊውን የስፖርቲንግ ሊስበን አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በሀላፊነት መሾማቸውን አስታውቀዋል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ከ international break ጨዋታዎች በኃላ በቋሚነት ስራዉን ይጀምራል !

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለተጨማሪ አንድ አመት የመቆየት አማራጭ ያካተተ የሶስት አመት ውል መፈረማቸው ተገልጿል።

ሩድ ቫኒስትሮይ ዩናይትድ ከቼልሲ ፣ ፓኦክ እና ሌስተር ሲቲ ጋር የሚደረጉትን ጨዋታ በአሰልጣኝነት ቡዱንን ይመራል !

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 22  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀለ ከተማ በተመረጡት ትምህርት ቤቶች ሲሰጠው የነበረው የህፃናት አትሌቲክስ (kids's Athletics) ስልጠና አጠናቀዋል ።

ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡት አጠቃላይ ስልሳ ህፃናት እና አሰልጣኞችን በህፃናት አትሌቲክስ (Kids' Athletics ) ንድፈ ሀሳብ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

በኢ.አ.ፌ. ስልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ እና ኢ.አ.ፌ ስልጠና ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጊዜ አድነው በጋራ በመሆን በህፃናት አትሌቲክስ ዙሪያ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት የተግባር ስልጠና በመስጠት አጠናቀዋል ።

የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ /ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ማሙ ለተሰጠው ስልጠና የላቀ ምስጋና በማቅረብ ድጋፍ እና ክትትል እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስልጠና ጥናት እና ምርምር ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ የክልሉ ፌዴሬሽን ላደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን በመጥቀስ ቀጣይም ተግባሩ ጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል ።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 22  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ክቡር ዶክተር ማሕሙድ አሕመድ ከመድረክ ሊሰናበት ነው ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያደረገው ጋሽ ማህሙድ አህመድ ማይኩን ሊሰቅል መሆኑ ተገልጧል፡፡

ጋሽ ማሐሙድ ለአገራችን የሙዚቃ ዕድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የክቡር ዶክተር ማዕረግን መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

በአገራችን የሙዚቃ ዘርፍ ስመጥር የሆነውን የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም ለማሰናበት ወይም ማይኩን ሊሰቅል ሲዘጋጅ እጃችንን አወዛውዘን መሸኘት አግባብነት የለውም በሚል በጆርካ ኢቨንት አዘጋጅነት ሽኝቱን በደመቀ እና በታሪክ ማስታወሻነትም ለማስቀመጥ መታሰቡን ሰምተናል፡፡

በዚህም ጥቅምት 22 ቀን ከጋሽ ማሕሙድ ኮሚቴ በመረከብ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚለኒየም አዳራሽ ደረጃውን የጠበቀ የድምጻዊው የመጨረሻ የህይወት ዘመን ስንብት ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ተነግሯል ፡፡

በእለቱም የክቡር ዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ላይ የተዘጋጀ መፅሀፍ እንደሚመረቅም ተነስቷል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኢራን ከአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት እስራኤልን እንድትመታ አያቶላህ ትእዛዝ መስጠታቸዉ ተሰማ

ኢራን ከኢራቅ ሆና እስራኤልን እንደምትመታም ነዉ የተነገረዉ፡፡

በኢራን የተገዙ እስራኤላዉያን የእስራኤልን ባለስልጣናት ለመግደል እየሰሩ ነዉ የሚል መረጃም ወጥቷል

የእስራኤል ጦር የኢራንን ጥቃተ ለመመከት አስፈላጊዉን ዝግጅት አድርጊያለሁ ማለቱም ተሰምቷል

አሜሪካ በበኩሏ ምርጫየነ በሰላማዊ መንገድ እንዳደርግ እባካችሁ የተኩስ አቁመ ስምምነት ላይ ድረሱልኝ ስትል እየተማጸነች ነዉ

የእስራኤል የጦር አመራሮችም እኛ በጋዛና በሊባኖስ የጀመርነዉን የቤት ስራ ጨርሰናል የመስማማቱ ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ነዉ እያሉ ነዉ፡፡

70 በመቶ የሚሆነዉ የሄዝቦላህ የድሮን መሰረተ ልማት ሙሉ በሙሉ መዉደሙን ጦሩ አስታዉቋል

ሄዝቦላህ የሊባኖሱ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ 95 የእሰራኤል ወታደሮችን ገድያለሁ 9 መቶ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ብሏል

በአሜሪካ የምርጫ ዋዜማ ላይ የኢራን የመልስ ምት ብዙዎችን እያሳጋ ነዉ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከ5ሺህ በላይ የንግድ ጎብኚዎችን እንደሚያስተናግድ የሚጠበቀው አውደ ርዕይ ተከፈተ

13ኛው ኢትዮ የዶሮ እርባታ ኤክስፖ (ETHIOPEX) እና 9ኛው የአፍሪካ የእንስሳት እርባታ አውደ ርዕይ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል።

ከጥቅምት 21 እስከ 23 በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ ከ17 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ ዓለምዓቀፍ የቴክኖሎጂ እና ግብዓት አቅራቢዎች እንዲሁም ገናና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ይሆናል።

አውደ ርዕዩ በእንስሳት መኖ፣ በእንስሳት ጤና፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት፡ በስጋ በእንቁላል እንዲሁም በንብ እና በአሳ ሃብት ልማት ዘርፎች ለይ ትኩረት እንዸሚያደርግም ተገልጿል።

የዚህ አውደ ርዕይ ዋና አላማም የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ በዘርፉ ተዋንያን መካከል ለመቀርረብ ምቹ መድረክ በመሆን፤ ልምድና ተሞክሮ ማጋራት እንደሆነም ተመላክቷል።

በአውደ ርዕዩ ከ5ሺህ በላይ ጎብኚዎች እንደሚስተናገዱም ይጠበቃል።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 21  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በቡና ምርት በዚህ ዓመት 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ይገኛል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ

በያዝነዉ በጀት ዓመት ከ4መቶ50 እስከ 5 መቶ ሺህ ቶን ቡና ለማምረት በዕቅድ መያዙንም ገልጸዋል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነዉ፡፡

ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያም እየሰጡ ይገኛል፡፡

በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቡና ምርትን አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ፤ ባለፈዉ ዓመት የተገኘዉን ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ በዚህ ዓመትም ለማስቀጠል መታሰቡን አንስተዋል፡፡

በዚህ ዓመት ከቡና ምርት የ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት በዕቅድ መያዙንም ገልጸዋል፡፡

ከቡና ባሻገር በሻይ ምርትም ከፍተኛ ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በቂ ባይሆንም 20 የሻይ ማቀነባበሪያ ለመትከል መታቀዱንም ለምክር ቤቱ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከ8.2 ሚሊየን በላይ መሬት በስንዴ ምርት እንደሚሸፈን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፤ 300 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ምርት እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

በዚህ ዓመት የግብርናዉ ሴክተር 6.1 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ መታቀዱንም ገልጸዋል፡፡

በዚህም ሰብል፣ ጥጥ እና የሆርቲካልቸር ዘርፉ በ 30 ሚሊየን ሄክታር ላይ ወደ 1.4 ቢሊየን ኩንታል ምርት እንደሚያስገኝም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 21  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በጎዳና ተዳዳሪነት ላይ ያሉ ዜጎችን ማቋቋም ቢቻልም በርካቶች የስራ ቦታ ለማግኘት ይቸገራሉ ተባለ።

አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በክልል ዋና ዋና ከተሞች በጎዳና የሚኖሩ ዜጎችን ለማንሳት እና ለማቋቋም ጥረቶች ቢኖሩም በድጋሚ ወደ ጎዳና የሚወጡ እንዳሉ ተነግሯል።

በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 21 ከተሞች ዜጎችን ከጎዳና ለማንሳት የሚያግዘው ፕሮጀክት ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ ሰምተናል፡፡

በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር በማህበራዊ ዘርፍ የልዩ ድጋፍ አገልግሎት የኘሮጀክቱ አማካሪ አቶ ገመቹ ተርፋሳ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደገለፁት እነዚህ ዜጎች ከ3 እስከ 6 ወር በአገልግሎት ማእከሉ ያላቸውን ቆይታ ሲያጠናቅቁ ለቀጣይ ህይወታቸው የሚደረጉ ድጋፎች ቢኖሩም በተለያዩ ምክንያቶች በድጋሚ ወደ ጎዳና ላይ እንደሚመለሱ አቶ ገመቹ ይገልፃሉ።

ከማእከሉ ቆይታ በኋላ ከ20 እስከ 30 ሺህ ብር የስራ ማስጀመሪያ ድጋፎች እንደሚመደቡላቸው አንስተዋል፡፡

ሆኖም በአንዳንድ ከተሞች በሚሰማሩባቸዉ የስራ መስኮች የመስሪያ ቦታዎችን አለማግኘት አንዱ ችግር ነዉ ያሉት አማካሪዉ ከከተማ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ጥቂቶች ቦታ እንዲያገኙ ቢደረግም አብዛኞቹ የተረጋጋ ቦታ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

በአለም ባንክ እና በከተማ ልማት ሴፍቲኔት ትብብር ዜጎችን ከጎዳና ላይ ለማንሳት እየተተገበረ ባለው ፕሮጀክት በሁለተኛዉ ዙር ትግበራ 14 ሺህ ያህል የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለማንሳት እቅድ ይዟል ተብሏል።

ኘሮጀክቱ ያቅፋቸዋል ተብለዉ የተለዩት በጎዳና ላይ ያሉ እናቶች ÷ ህፃናት ÷ ወጣቶች እና አረጋውያንን ናቸው፡፡

ፕሮጀክቱ 50 በመቶ የሚሆነዉ ሽፋን በ አዲስ አበባ ከተማ የሚሸፍን ይሆናል፡፡

ቁምነገር አየለ

ጥቅምት 20  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel