ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡም ወደ ዋይት ሃውስ ለመግባት ከሁለት ወራት በላይ መጠበቅ ይኖርባቸዋል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት በአሁኑ ወቅት በይፋ ፕሬዚዳንት ሆነው አልተሰየሙም።
የአሜሪካ የስልጣን ርክክብ ለምሳሌ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ካሉ አገራት የተለየ ነው።

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ኬይር ስታርመር ማሸነፋቸው በታወቀበት እና የምርጫው ጣቢያዎች በተዘጉበት በሰዓታት ውስጥ ነው በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾሙት።

በወቅቱ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እቃዎቻቸውን ሸክፈው አልወሰዱም ነበር።

ትራምፕ ሲመታቸው ከጥር 12/ 2017 ዓ.ም በፊት አይከናወንም። ጆ ባይደን ተግባራቸው የተገደበ ቢሆንም እስከዚያው ድረስ በስልጣን ላይ ይቆያሉ።

በምርጫው የተሸነፉት የዲሞክራት እጩ ካማላ ሃሪስ በበኩላቸው “በርካቶች ጨለማ ዘመን ውስጥ እየገባን እንደሆነ እየተሰማቸው ነው። ይህ እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ ተናገሩ።

በቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ሃዋርድ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ካማላ ሃሪስ “በጨለማ ውስጥ ነው ከዋክብትን ማየት የሚቻለው” ሲሉም ደጋፊዎቻቸውን አበረታትዋል።

ደጋፊዎቻቸው በአዎንታዊ መንፈስ እንዲቀጥሉም ጥሪ አድርገዋል።
ሃሪስ የአሜሪካ ህዝብ በተለይም የዲሞክራሲ ደጋፊዎችን “ተስፋ አትቁረጡ። አሁንም ኃይል አላችሁ” ብለዋል።

ምርጫው በትራምፕ አሸናፊነት መጠናቀቁን ተከትሎ “ሰዎች ትግላቸውን እንዳያቆሙም” ተናግረዋል።

አሁን እጃችንን አጣጥፈን የምንቀምጥበት ጊዜ አይደለም” ሲሉም ተደምጠዋል
ለነጻነት እና ለፍትህ እንዲሁም ሁላችንም በጋራ መገንባት እንደምንችል
ለምናውቀው የወደፊት ለመደራጀት፣ ለመቀስቀስ እና ለመሳተፍ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።

በተለይም ወጣት ደጋፊዎቻቸውን “ሁሉ ጥሩ ይሆናል” ሲሉ አጽናንተዋል።
ሃሪስ ለምትመለከቱኝ ወጣቶች ሲሉ በርካቶች ድጋፋቸውን በጩኸት የገለጹላቸው ሲሆን “ ማዘን እና መከፋት ምንም አይደለም። ነገር ግን ማወቅ ያለባችሁ ሁሉ ጥሩ እንደሚሆን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“አንዳንድ ጊዜ ትግሉ ጊዜ ይወስዳል ይህ ማለት አናሸንፍም ማለት አይደለም”
“ለአገራችን የሚደረገው ትግል ሁልጊዜም ዋጋ ያለው ነው” ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ ከህዳር 22 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንደያደርጉ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አዲሱ መመሪያ ከጥሬ ገንዘብ ንክኪ ነጻ የሆነውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በኢትዮጵያ ለማጎልበት እየተሰራ ያለውን ስራ ለማጠናከር እንደሚያግዝ እና የዲጂታል ግብይትን እየለመደ ያለውን ማህበረሰብ በይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ይህ ኢት ኪውአር ኮድ (EthQR Code) የሚል ሥያሜ የሚኖረው አሠራር ዓለምአቀፍ የአሠራር ልምዶችን መሠረት ያደረገ፣ የክፍያም ሆነ የግብይት ተዋናያንን ሙሉ መረጃ የሚይዝ ነገር ግን ከተወሰኑ አስፈላጊ መረጃዎች በቀር ሌሎቹን በምሥጢር የሚጠብቅ  ሥርዓት መሆኑ ተገልጿል።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የዲጂታል ክፍያ አገልግሎትና ግብይት የጥሬ ገንዘብን ዝውውር የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ፣ ሕብረተሰቡ ለሥርቆት፣ በእጁ ያለው ገንዘቡም ለእርጅና እንዳይጋለጥ፤ ከባንክ ውጭ የሚዘዋወር የገንዘብ መጠን እንዲቀንስ፣ ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ገንዘቡን ለማሳተም የሚወጣ ወጪን እንዳይጨምር ለማድረግ ይረዳል ብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኤርባስ  ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ ያደርጋል

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ  ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

"Ethiopia Land of Origin" የሚል ስያሜ በቅርቡ አዲስ አበባ  የገባው አውሮፕላኑ 400 መቀመጫዎች ያሉት ነው።

አባቱ መረቀ

ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አትሌት ታምራት ቶላ የ2024 ከስታዲየም ውጭ ውድድር የመጨረሻ እጩ ውስጥ ተካተተ

የዓለም አትሌቲክስ የ2024 ከስታዲየም ውጭ በተደረጉ ውድድሮች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ውስጥ ታምራት ቶላ የመጨረሻ እጩ ውስጥ ተካቷል፡፡

በወንዶቹ ዘርፍ የኦሊምፒክ አሸናፊው ታምራት ቶላ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሆኖ ለማሸነፍ ቅድመ ግምትን ያገኘ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆኗል።

የ33 ዓመቱ የረዥም ርቀት አትሌት ታምራት በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ 2:06:26 በመግባት በውድድሩ የተገኘውን ብቸኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሩ አስገኝቷል፡፡

👉🏾ከስር ባለው ሊንክ በመግባት ድምጽ እንድትሰጡት በአክብሮት እንጠይቃለን
👇👇

to vote 👉 bit.ly/3YxLVx8

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአክሱም ሐውልትን የጥገና ሥራ ሊጀመር ነው።

የአክሱም ሐውልት እና የነገስታት መቃብር ሥፍራን የጥገና ሥራ ወደ ተግባር ለማስገባት የጥገና ጥናት የውል ስምምነትና የቦታ ርክክብ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የአክሱም ሐውልት ቁጥር ሶስት እና በስሩ የሚገኙ የነገስታት መቃብር ሥፍራዎች ለማጥናት የማስጀመሪያ የፕሮጀክት ቦታ ርክክብ ዛሬ በአክሱም ከተማ አከናውኗል፡፡

ባለስልጣኑ ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር የአክሱም ሃውልት ቁጥር 3 እና የነገስታት መቃብር ሙዚዬም እንዲሁም ‘ብሪክ አርክ’ የጥገና ጥናት ሙሉ ለሙሉ የመከለስ ሥራ፣ የጥገና ሥራው ተጽዕኖ ግምገማ ሰነድ ዝግጅት እንዲሁም በተግባር ጥገና ሥራ ወቅት የማማከር እና ክትትል ተግባር ለማከናወን የሚያስችል የውል ስምምነት ነው ከኤምኤች ኢንጅነሪንግና ስቱድዮ ክሮቺ ጋር የተፈራረመው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

47ኛ የአሜሪካፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት መሪዎች የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት እየጎረፈላቸው ይገኛል።

የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ለዶናልድ ትራምፕ "የእንኳን ደስ አለዎ" መልዕክት አስተላልፈው ሀገራቸው ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ባሻገር ለሚገኙት ለሁለቱም ነጻነት እና ብልጽግና ለመፍጠር ከአሜሪካ ጋር መሥራቷን እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።

የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሱላ ፎን ዴር ላየን ትራምፕ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልካም ምኞታቸውን በኤክስ በኩል ገልጸዋል።

"የአውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ ከአጋር በላይ ናቸው። 800 ሚሊዮን ዜጎቻችንን አንድ በሚያደርግ እውነተኛ የሕዝቦች አጋርነት የተሳሰርን ነን" ብለዋል።

አውሮፓ እና አሜሪካ "ዘላቂ ኅብረት እና ታሪካዊ ትሥሥር እንዳላቸው የገለጹት የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ቻርለስ ሚሼል ተመሳሳይ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።

ትራምፕን "እንኳን ደስ አለዎ" ያሉት የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ የሩሲያ ጦርነት በዩክሬን ያበቃል የሚል ተስፋቸውን አያይዘው ገልጸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በጦርነት እና በድህረ ጦርነት አዉድ ዉስጥ ለሚገኙ ትምህርት ተቋማትን ለማቋቋም 4.6 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉ የተደረገላቸዉ የአማራ እና የአፋር ልማት ማህበራት ሲሆኑ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘዉ የዩስተን ኮሚኒቲ ትብብር የተሰበሰበዉ ይህ ድጋፍ በጦርነት ቀጠና ዉስጥ ሆነዉ ጉዳት ላጋጠማቸዉ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ነዉ ተብሏል።

በዛሬዉ እለት የገንዘብ ርክክቡን የፈፀመዉ ግሎባል አልያንስ የተሰኘ ድርጅት ነዉ።

የአፋር ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ እንደተናገሩት በክልሉ ከድህረ ጦርነቱ ባደረጉት ግምገማ በርካታ የማህበራዊ ግልጋሎት ተቋማት ዉድመት መድረሱን ገልፀዋል።

ዶ/ር ኮንቴ የትምህርት ተቋማትን በተመለከተ ድጋፎችን በማሰባሰብ በአፋር ሎጊያ ትምህርት ቤት መገንባት ተችሏል ይሄኛዉ ድጋፍ ለትምህርት ተቋሙ የቤተ መፅሀፍት ግንባታ ሊደረግበት መታቀዱን ተናግረዋል።

አያይዘዉም ክልሉ ላይ አገልግሎት በሚሰጥባቸዉ አካባቢዎች የባለሙያ እጥረት በመታየቱ ይህንን ክፍተት መሞላት ከገንዘብ ድጋፎች እኩል ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም የአማራ ልማት ማህበር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በጦርነት ቀጠናዎች ዉስጥም በሆኑ ሁኔታዎች ዉስጥ እየሰራ ይገኛል የተባለ ሲሆን ይሄኛዉ ድጋፍ በደቡብ ወሎ ቢስቲማ ትምህርት ቤት ለመገባት የሚዉል ነዉ።

ሆኖም እነዚህ ተቋማት ዘላቂ በሆነ መልኩ በቂ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚደረጉ የግጭት እና የጦርነት ሁኔታዎች ለቆሙ እንደሚገባ በርክክብ መድረጉ ተገልፆል።

ቁምነገር አየለ

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

5ኛው ሀገር አቀፍ የስራ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ተዘጋጀ።

300 የሚሆኑ ቀጣሪ ድርጅቶች በተገኙበት ከ30,000 በላይ የስራ እድሎች ለ20,000 ለሚሆኑ አዲስ ምሩቋን የተመቻቸበት 5ኛው አገር አቀፍ የሥራ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ጥቅምት 27 እና 28 ቀን 2017 ዓ.ም መዘጋጀቱን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህ ሀገር አቀፍ የስራ አውደርዕይ ደረጃ ዶት ኮም ፣ስራና ክህሎት ሚኒስቴር እንዲሁም ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በጋራ በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ ተልጿል።

በአውደርዕዮ ከ20ሺ በላይ የደረጃ ክህሎት ስልጠና የወሰዱ የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን ፣ከ300በላይ ከተለያዩ ዘርፍ የተውጣጡ የስራ አለማቸውን ከሚወስኑ ቀጣሪ ድርጅቶች ጋር የሚተዋወቁበት እና የስራ መረጃ የሚለዋወጡበት መድረክ መሆኑ ተነግሯል።


እንዲሁም ስራ ፋላጊዎች የስራ ዕድሎች የሚያገኙበት እና በሀገራችን ውስጥ ለሚታየው የስራ አጥነት ችግር እንደ መፍትሄ መሆኑን በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ላይ ተነስቷል።

ከሚገኙት ቀጣሪ ድርጅቶች መካከል  ovid construction, Rohobot Home Based Health Care Service Plc, Hybrid designs plc, East African Pharmaceuticals Plc እና Ethio Post ከፍተኛ የመቅጠር አቅም ያላቸዉን ትልልቅ ኩባንያዎች ያሳትፋል መባሉን ሰምተናል።

ሐመረ  ፍሬው

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዮአቭ ጋላንት ከስልጣናቸው ተነሱ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የመከላከያ ሚኒስትሩን ዮአቭ ጋላንትን አሰናበቱ


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የመከላከያ ሚኒስትራቸውን ዮአቭ ጋላንትን በአስደናቂ ሁኔታ ከስልጣናቸው ማባረራቸው ተሰምቱዋል ።

እርምጃው የተላለፈው ከሃማስ ጋር  የተቀሰቀሰው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት 14 ወራት ካለፈ በኋላ ነው።

በእርሳቸው እና በሚስተር ​​ጋላንት መካከል “የመተማመን ቀውስ” ተፈጥሯል ብለዋል ሚስተር ኔታንያሁ።

ሁለቱ በጋዛ ጦርነት አካሄድ  ላይ ብዙ ጊዜ ሲጋጩ ነበረም ተብሏል።

ልኡል ወልዴ

ጥቅምት 27 ቀን 2017

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤ350-1000 "Ethiopia land of origins" የሚል ስያሜ የተሰጠውን የመንገደኞች አውሮፕላንን በትናንትናው ዕለት ከኤር ባስ የአውሮፕላን ኩባንያ መረከቡ ይታወቃል። 

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኤ 350-1000 አውሮፕላን ለአየር መንገዱ ቀጣይ ዕድገት ትልቅ ስኬት ስለመሆኑ ተጠቅሷል። 

የኤ350-1000 አውሮፕላን 400 መቀመጫዎች አሉት።

አየር መንገዱ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2035 በዓመት 67 ሚሊዮን መንገደኞችን በማጓጓዝ 25 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት እየሰራ ይገኛል፡፡
 
በአሁኑ ወቅትም ባሉት 147 አውሮፕላኖች 139 ዓለም አቀፍ እና 22 የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል፡፡

የአየር መንገዱ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ አውሮፕላን እንድታገኝ ላደረጉ አጋር አካላት በተለይም ለኤርባስ ኩባንያ ምስጋና አቅርበዋል

አየር መንገዱ እዚህ ስኬት ላይ እንዲደረስ ሠራተኞቹ ላበረከቱት አስተዋጽኦም አመሥግነዋል።

አባቱ መረቀ

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሻምፒየንስ ሊግ በስፔን ቫሌንሽያ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ይታሰባሉ !

ዩኤፋ በሳምንቱ አጋማሽ በሚደረጉ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች በስፔን ቫሌንሽያ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንደሚታሰቡ ይፋ አድርጓል።

ይህንንም ተከትሎ በዚህ ሳምንት ከሚደረጉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች አስቀድሞ የህሊና ፀሎት እንደሚደረግ ተገልጿል።

በተጨማሪም በዚህ ሳምንት በሚደረጉ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በሚያዘጋጃቸው የክለብ ውድድሮች ተጎጂዎች እንደሚታሰቡ ተነግሯል።

በስፔን ቫሌንሽያ በተከሰተው አስከፊ የአውሎ ንፋስ እና ጎርፍ አደጋ እስካሁን ከ 230 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

02:45 | ፒኤስቪ ከ ጅሮና
02:45 | ስሎቫን ብራቲስላቫ ከ ዳይናሞ ዛግሬብ
05:00 | ቦሎኛ ከ ሞናኮ
05:00 | ሴልቲክ ከ RB ሌፕዚሽ
05:00 | ዶርትሙንድ ከ ስታሩም ግራዝ
05:00 | ሊል ከ ጁቬንቱስ
05:00 | ሊቨርፑል ከ ባየር ሊቨርኩሰን
05:00 | ሪያል ማድሪድ ከ ኤሲ ሚላን
05:00 | ስፖርቲንግ ሊዝበን ከ ማንችስተር ሲቲ

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የብር ኖቶች በማተም የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በአዳማ ከተማ በሀሰተኛ ደረሰኝ፣ በሀሰተኛ የብር ኖቶች እና ሠነዶች ህትመት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

ተጠርጣሪዎቹ አቶ አንዋር አለማየሁ እና አቶ ኢማም ሰይድ የተለያዩ የብር ኖቶች፣ ሀሰተኛ ሰነዶች፣ ህገ-ወጥ የተለያዩ ተቋማት ማህተሞች እና ለዚሁ ህትመት ተግባር የሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮችና ፕሪንተሮች ጨምሮ ተይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ ክ/ከተማ ኦዳ ወረዳ ኢምሩ በተባለ ህንፃ ላይ በተከራዩት ሱቅ ውስጥ ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር ሲያከናውኑ እንደነበረ ተደርሶበት በተጠርጣሪዎቹ ላይም የምርመራ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል፡፡

በዚሁ ክ/ከተማ በተመሳሳይ ቦታና ህንፃ ሌላ ሱቅ ከፍቶ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያትም የነበረ ግለሰብም በዚሁ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ እና 151 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሃብት ታግዶ የወንጀል ምርመራ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የኦዲት ግኝት የባለድርሻ አካላት የትብብር ፎረም ገለጸ፡፡

የሦስት ዓመታት የኦዲት ግኝት የባለድርሻ አካላት የትብብር ፎረም የጋራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ውይይት ትላንት ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተካሂዷል፡፡

ፎረሙ ባለፉት ሦስት ዓመታት ትግበራው፤ ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ እና 150 ሚሊዮን 504ሺህ ዶላር ያህል ሃብት እግድ እንዲወጣ ማድረጉን በሪፖርቱ አመልክተዋል፡፡

እንዲሁም 46 መኖሪያ ቤቶች እና አንድ ሕንጻ፣ 86 ተሽከርካሪዎች፣ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚያወጣ የአክሲዮን ብር ዋጋ ያለው፣ 81 ሺህ ገደማ ካሬ የመሬት ይዞታዎች እግድ እንደወጣባቸው ተመልክቷል።

ፎረሙ ባካሄደው ግምገማ በፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት በግኝት ከለያቸው መካከል የጥሬ ገንዘብ ጉድለት፣ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከአንድ ወር ጀምሮ 10 ዓመትና ከዚያ በላይ የቆየ መሆኑ፣ የመንግሥትን ገቢ በወጡ ሕጎች መሠረት አለመሰብሰብ፣ ሕግን ያልተከተሉ ክፍያዎች መፈጸም ይገኙበታል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ፍሊንትስቶን ሆምስ የተለያዩ ሽልማቶችን ለደንበኞቹ አበረከተ።
ሚያዚያ 16 እስከ ነሃሴ 19 ድረስ በቆየው የመተግበሪያ ማስተዋወቂያ ወቅት በመተገበሪያው ለተማዘገቡ ደንበኞች ከቤት እድሳት ጀምሮ ፣ የሆቴል ፓኬጅ ፣ ስማርት ስልኮች እንዲሁም የተለያዩ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን በዕጣው ተካቷል።

የዚህ የሽለማት  አላማው የፍሊንት ስቶንን ቤተሰቦችን ማበረታት አፕሊኬሽኑን ማከተዋወቅ ነው ተብሏል ።

ዛሬ በሚወጣው የፍሊንት ስቶን ሽልማት ዕጣ ውስጥ በመጀምሪያ ዕጣ የቤት እድሳት የባለ ዕድለኛው ቤት የሴራሚክ ወለል ንጣፍ የመታጠቢያ እና የማብሰያ ወለል ከግድግዳ ጋር የሴራሚክ ንጣፍ ሽልማት አበርክተዋል።

በመጨረሻም ቤት ሁሉም ሰው እቅድ ውስጥ ያለ ነገር በመሆኑ የመጀመሪያውን እጣ እጅግ ተፈላጊ ያደርገዋል ተብሏል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሐሰተኛ የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ በነበሩ 339 ህገ-ወጥ አካውንቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ።

ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በመመሳጠር የንግድ ሥርዓቱ እንዳይቀላጠፍ ሲሰሩ የነበሩ በየደረጃው የሚገኙ 136 ሠራተኞችና አመራሮች ላይም ቢሮው ሕጋዊ እርምጃ መውሰዱ ተገልጿል።

በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ሦስት ወራት የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችን አስመልክቶ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ፍስሐ ጥበቡ በሰጡት መግለጫ÷ የንግዱ ዘርፉ ፍትሃዊ፣ ተወዳዳሪና ተደራሽ እንዲሆን ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በ11ዱ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች የኦንላይን የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥን ቀልጣፋና ፈጣን ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

በዚህ ሂደት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥን የቴክኖሎጂ አሠራር ሥርዓት ለታለመለት ዓላማ እንዳይውል በሰባት ክፍለ ከተሞች 339 የሚሆኑ ህገ-ወጥ አካውንቶች በመክፈት አገልግሎት ሲሰጡ መገኘታቸውን አረጋግጠዋል።

በተከፈተው ሐሰተኛ አካውንት ግብር ሳይከፍሉ የንግድ ፈቃድ እድሳት፣ አዳዲስ የንግድ ፈቃድ፣ ዘርፍ መቀየርና የካፒታል ለውጥ አገልግሎት ሲሰጥ መገኘቱን ተናግረዋል።

በሐሰተኛ የኦንላይን አካውንት አገልግሎት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ የተሰጡ 430 አገልግሎቶች ሥራ ላይ እንዳይውሉ ተደርጓም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሕብረተሰቡ በተቋሙ ትክክለኛ አካውንት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚያገኝ አስረድተው፤ በተሳሳተ አካውንት የሚሰሩ ሰዎችንም እንዲያጋልጥ ጠይቀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሥራ ቦታቸው ወሲባዊ ግንኙነት ሲፈጽሙ የሚያዙ የመንግሥት ሠራተኞች “ከባድ እርምጃ” እንደሚጠብቃቸው የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንት አስጠነቀቁ።

ይህ የምክትል ፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው በመቶዎች የሚቆጠሩ የወሲብ ቪዲዮዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሰራጩ በኋላ ነው።

ቪዲዮዎቹ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን የሆነውን ባልታዛር ኢባንግ ኢንጎንጋ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ሚስቶችን ጨምሮ ከተለያዩ ሴቶች ጋር በቢሮው ውስጥ ወሲብ ሲፈጽም የሚያሳዩ ናቸው ተብሏል።

ኢንጎንጋ የአገሪቱ ብሔራዊ የፋይናንስ ምርመራ ኤጀንሲ ኃላፊ እና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዘመድ መሆናቸው ተነግሯል።

በጉዳዩ ላይ የተከሰሱት ባለሥልጣን አስተያየት እንዲሰጥ ቢቢሲ ጥያቄ አቀርቧል።

ኢንጎንጋ በፌስቡክ ገጹ ላይ የእሱን የአንዲት ሴትን እና የልጆችን ፎቶ በመለጠፍ “ቤተሰብ ሁሉም ነገር ነው” የሚል ጽሁፍ አስፍሯል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

47ኛ የአሜሪካፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት መሪዎች የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት እየጎረፈላቸው ይገኛል።

የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ለዶናልድ ትራምፕ "የእንኳን ደስ አለዎ" መልዕክት አስተላልፈው ሀገራቸው ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ባሻገር ለሚገኙት ለሁለቱም ነጻነት እና ብልጽግና ለመፍጠር ከአሜሪካ ጋር መሥራቷን እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።

የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሱላ ፎን ዴር ላየን ትራምፕ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልካም ምኞታቸውን በኤክስ በኩል ገልጸዋል።

"የአውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ ከአጋር በላይ ናቸው። 800 ሚሊዮን ዜጎቻችንን አንድ በሚያደርግ እውነተኛ የሕዝቦች አጋርነት የተሳሰርን ነን" ብለዋል።

አውሮፓ እና አሜሪካ "ዘላቂ ኅብረት እና ታሪካዊ ትሥሥር እንዳላቸው የገለጹት የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ቻርለስ ሚሼል ተመሳሳይ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።

ትራምፕን "እንኳን ደስ አለዎ" ያሉት የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ የሩሲያ ጦርነት በዩክሬን ያበቃል የሚል ተስፋቸውን አያይዘው ገልጸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩው ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ።

በፍሎሪዳ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር "የአሜሪካ ሕዝብ 47ኛው ፕሬዝደንት አድርጎ ስለመረጠኝ ላመሰግን እወዳለሁ" ያሉት ዶናልድ ትራምፕ "ለሁሉም ዜጋ" ለመታገል ቃል ገብተዋል።

“ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ታላቅ ድል ነው፤ አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ያስችለናል” ሲሉም የምርጫ ዘመቻ መፈክራቸውን በመጠቀም ተናግረዋል።

ትራምፕ ድላቸውን ለደጋፊዎቻቸው በተናገሩበት የፍሎሪዳ መድረክ “አገራችን እንድትድን እንረዳታለን” ብለዋል።

በድንበሮች ያሉ ጉዳዮችን እልባት እንደሚሰጡ ቃል ገብተው ፓርቲያቸው እና እሳቸው ታሪክ የሰሩት በምክንያት ነው ብለዋል።

ትራምፕ በዚህ የድል ንግግራቸው ይህችን ዕለት “በህይወታችሁ ጠቃሚ የምትባል ዕለት አድርጋችሁ እንደምትቆጥሯት” ተስፋ አለኝ ብለዋል።

“አሜሪካ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ስልጣን ሰጥታናለች” በማለት ፓርቲያቸው የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱን የበላይነት ከዲሞክራቶች በመውሰድ መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል።

ይህንን ተከትሉም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ የአሜሪካ 47ኛ ፕሬዝደንት ሆነው ለመመረጥ ለተቃረቡት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ፍሊንትስቶን ሆምስ የተለያዩ ሽልማቶችን ለደንበኞቹ አበረከተ።

ሚያዚያ 16 እስከ ነሃሴ 19 ድረስ በቆየው የመተግበሪያ ማስተዋወቂያ ወቅት በሙተገበሪያው ለተማዘገቡ ደንበኞች ከቤት እድሳት ጀምሮ ፣ የሆቴል ፓኬጅ ፣ ስማርት ስልኮች እንዲሁም የተለያዩ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን በዕጣው ተካቷል።

የዚህ የሽለማት ፕሮሞሽን አላማው የፍሊንት ስቶንን ቤተሰቦችን ማበረታት አፕሊኬሽኑን ማከተዋወቅ ነው ተብሏል ።

ዛሬ በሚወጣው የፍሊንት ስቶን ሽልማት ዕጣ ውስጥ በመጀምሪያ ዕጣ የቤት እድሳት የባለ ዕድለኛው ቤት የሴራሚክ ወለል ንጣፍ የመታጠቢያ እና የማብሰያ ወለል ከግድግዳ ጋር የሴራሚክ ንጣፍ ሽልማት አበርክተዋል።

በመጨረሻም ቤት ሁሉም ሰው እቅድ ውስጥ ያለ ነገር በመሆኑ የመጀመሪያውን እጣ እጅግ ተፈላጊ ያደርገዋል።

በመጨረሻም ፍሊንትስቶን ወደ ሪልስቴት ሲገባ የመጀመረያውን የቤት ግንባታ ከገበያው በተለየ ከብር ከ135,000  ጀምሮአል የመኖሪያ መደንደር ሰርቶ ያስረከበ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት በመሣል አዲስ አበባ ከተማ ጸና በዙሪያው ከሃያ ሶስት በላይ በሚሆኑ የግኀባታ ሳይቶች ላይ ቤቶችን በመገንባት ለቤት ገበያው የበኩሉን እያደረገ ይገኛል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በእንስሳት ኢንሹራንስ ዙሪያ ባንኮች በቂ ግንዛቤም ሆነ ዝግጅት እንደሌላቸው ተነገረ።

በዘንድሮዉ የእንስሳት ኢንሹራንስ ሽያጭ ባንኮች በቂ ዝግጅት አላደረጉም ተብሏል።

በተጨማሪም  የሰለጠነ የሰዉ ሃይል ችግር እንዳለባቸው ተሰምቷል።

በተያዘው የ 2017 ሩብ ዓመት በመጀመሪያ ዙር የእንስሳት መድህን ሽያጭ 23 ሺህ ያህል የመድህን ዋስትና መሸጥ መቻሉ ተገልፆል።

ይህም በመጀመሪያ ዙር እንዲሸጥ ከተቀመጠዉ 30 ሺህ አርብቶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ ከነበረዉ እቅድ አንፃር ተመጣጣኝ ነዉ ተብሏል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በግብርና ሚኒስቴር የአርብቶ አደር ማህብረሰብ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ጀማል አሊዪ የዚህ ዙር ሽያጭ ብዙ ችግሮች እንደነበሩበት አንስተዋል።

አቶ ጀማል እንደገለፁት ሽያጩ የአንድ ወር የጊዜ ወሰን የተቀመጠለት እና የቴክኖሎጂ ሂደቶችን እንዲከተል በመደረጉ ምክንያት ባንኮች በቂ ዝግጁነት እንዲሁም የሰለጠነ ባለሙያ  አልነበራቸዉም ብለዋል።

በዚህም በሽያጩ ቀነ ገደብ በመጠናቀቂያዉ ጊዜ ላይ በነበሩ መጨናነቆች ሳቢያ  ያልተስተናገዱ አርብቶ አደሮች የነበሩበት ቦታዎች እንዳሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በመጀመሪያ ዙር የመንግስት የክፍያ ፍጆታ አምና ከነበረዉ 80 በመቶ ወደ 70 በመቶ በመቀነሱ የአርብቶ አደሩ የገንዘብ ክፍያ መጨመር  እክል እንደነበር አንስተዋል።

እንዲሁም ኘሮጀክቱን የሚደግፈዉ የአለም ባንክ የኢንሹራንስ ድርጅቶች ከገንዘብ ማዳከም ሪፎርም ጋር ተያይዞ የአገልግሎት ክፍያዎቻቸዉ ላይ  ጭማሪ ማድረጋቸዉ ሌላኛው ስጋት ነበር ሲሉ አቶ ጀማል ተናግረዋል።

ሆኖም አርብቶ አደሩ የእንስሳት መድህን አገልግሎት ፋይዳ መገንዘብ ችሏል ሲሉ ሀሳባቸዉን አክለዋል።

የእንስሳት መድህን ዋስትና ሽያጭ በዚህ ዓመት ለ80 ሺ አርብቶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ የታቀደ ሲሆን በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር ባለባቸዉ 5 የሀገሪቱ ክልሎች ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ነዉ።

ቁምነገር አየለ

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ የመከላከያ ሚኒስትሩን ዮአቭ ጋላንትን ማባረራቸውን ተከትሎ በእስራኤል ተቃውሞ ተቀሰቀሰ።

ናታንያሁ በእሳቸው እና በመከላከያ ሚኒስትራቸው መካከል የተፈጠረው “የመተማመን ቀውስ” ወደዚህ ውሳኔ እንዳመራቸው ገልጸው በጋላንት ላይ ያላቸው እምነት በቅርብ ወራት ውስጥ “ተሸርሽሯል” ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትስ እሳቸውን እንደሚተኩ ገልጸዋል።

ጋላንት በበኩላቸው ከስልጣን የተነሱት በሶስት ጉዳዮች ላይ በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን ገልጸዋል። ከነዚህም መካከል እስራኤል የቀሩትን ታጋቾች ከጋዛ ለመመለስ ስምምነቶችን ለመቀበል መሸከም የምትችለው ስምምነት ውስጥ ልትገባ ይገባል የሚለውን ጨምሮ ነው።

አደባባይ ላይ የወጡ በርካታ ተቃዋሚዎች ናታንያሁ ከስልጣን እንዲወርዱ የጠየቁ ሲሆን አዲሱ የመከላከያ ሚኒስትር ታጋቾችን የማስለቀቅ ስምምነት እንዲያስቀድሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ናታንያሁ እና ጋላንት ለረጅም ጊዜ ልዩነት በተሞላበት የስራ ግንኙነት ቆይተዋል። እስራኤል በጋዛ ላይ በምታደርገው የተቀናጀ ጥቃት ላይ ልትከተለው ስለሚገባ የጦርነት ስልት ላይ ከፍተኛ አለመግባባት እንዳሉ ሪፖርቶች ወጥተዋል።

የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል አክራሪ የሚባሉ የይሁዲ እምነት ተከታዮች በውትድርና ከመሰማራት ነጻ መደረጋቸው መቀጠሉ ደስተኛ አልነበሩም።

የጋዛ ጦርነት ባለፈው ዓመት መስከረም መጨረሻ ከመጀመሩ ከወራት በፊት ናታንያሁ የመከላከያ ሚኒስትሩን በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት አባረዋቸው ነበር። ሆኖም ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞን ተከትሎ ወደ ኃላፊነት ስፍራቸው እንዲመለሱ ተደርገው ነበር።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን  አዲስ አበባ  መግባቱን ተከትሎ የአቀባበል መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

የኢትዮያ አየር መንገድ ከኤር ባስ ኩባንያ የገዛው ኤ350-1000 አውሮፕላን ከፈረንሳይ ቱሊስ ተነስቶ አዲስ አበባ ገብቷል።

አውሮፕላኑ "ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ" የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

አውሮፕላኑ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ  የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።


አባቱ መረቀ

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በዛሬው እለት በተነሳ የእሳት አደጋ የአንድ እናት እና ልጅ ህይወት አልፏል፡፡

በዛሬው እለት በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ-ከተማ በመስሪያና መሸጫ ሼድ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ነው አንድ እናት ከስድስት ወር ልጃቸው ጋር ህይወታቸው ሊያልፍ የቻለው፡፡

በእሳት አደጋዉ ስድስት የንግድ ሱቆችም ተቃጥለዋል ተብሏል ።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት አምቡላንሶች ከሰላሳ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ንግድ ሱቆች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል ሲል የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን አስታውቋል።

ከንግድ ሱቆቹ መካከል በአንደኛዉ ነዳጅ በፕላስቲክ ጠርሙስ በችርቻሮ የሚሸጥበት ሱቅ በመሆኑ ለሽያጭ የተዘጋጀዉ ነዳጅ ለቃጠሎ መከሰትና መባባስ ጉዳት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ከኮምሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ ያለፈችዉ እናት በእሳት አደጋዉ ከተቃጠሉት የንግድ ሱቆች ዉስጥ በአንደኛዉ ሱቅ የንግድ ስራ ላይ የነበረች መሆኗም ተጠቅሷል።


ነዳጅ መከማቸትም ሆነ መሸጥ ያለበት በተፈቀደለትና የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ባሟሉ የነዳጅ መሸጫ ጣቢያዎች ዉስጥ ብቻ ነው ያለው ኮምሽ፤
ስለሆነም በተለያዩ የንግድ ሱቆች ዉስጥ ነዳጅ ማከማቸትም ሆነ መሸጥ መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የንግድ ፈቃድ የሚሰጡ አካላትም ተገቢዉን ቁጥጥር ማድረግ ይኖርባቸዋል ሲሉ የኮምሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍኤም ገልጸዋል።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አርቱሮ ቪዳል ከፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሆነ ተገለፀ

ቺሊያዊው የመሐል ሜዳ ተጫዋች አርቱሮ ቪዳል በሀገሩ ቺሊ ከፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከአርቱሮ ቪዳል በተጨማሪም የክለቡ ኮሎ ኮሎ ተጨዋቾች ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።

አርቱሮ ቪዳል እና የቡድን አጋሮቹ ትላንት የክለባቸውን ድል ለማክበር እየተዝናኑ በነበረበት ምሽት ቤት ውስጥ የፆታዊ ጥቃት ክስ ሪፖርት እንደቀረበባቸው ተነግሯል።

አርቱሮ ቪዳል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ አስፈላጊውን የወንጀል ምርመራ መረጃ መስጠቱ እና በኋላም መለቀቁ ተገልጿል። ቺሊያዊው አማካይ አርቱሮ ቪዳል በአሁን ሰዓት በቺሊው ክለብ ኮሎ ኮሎ በመጫወት ላይ ይገኛል።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የ7 መቶ 38 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀች

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛው መደበኛ ስብሰባ የደቡብ ሱዳን የብድር ጥያቄ ተቀብሎ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ 738 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ብድር ስምምት ያጸደቀ ሲሆን ብድሩ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን ለማስተሳሰር የሚረዳ 220 ኪሎ ሜትር ለመንገድ ግንባታ የሚውል መሆኑ ተመላክቷል።

የብድር ስምምነቱ የአምስት አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ10 ዓመት የሚመለስ ሲሆን ብድሩ የሚመለሰው በካሽ ወይም እስከ ፖርት ሱዳን ድረስ በሚቀርብ ድፍድፍ ነዳጅ እንደሆነ ተገልጿል።

የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የሽግግር ህግ አውጪ ምክር ቤት የገንዘብ ስምምነቱን በሰኔ ወር 2016 አጽድቆ የነበረ ሲሆን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር በወቅቱ፤ የመንገድ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል እያደገ ያለውን ትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነት ግንኙነት የሚያሳይና የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የብድር ስምምነት የተፈራረሙት እ.ኤ.አ በግንቦት ወር 2023 ለድንበር ተሸጋሪ መንገድ ግንባታ ይውላል በሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ክራፍት ሶሉሽን ፋዉንዴሽን ያሰለጠናቸዉን ከ80 በላይ ወጣቶች አስመረቀ

ክራፍት ሶሉሽን ፋዉንዴሽን ከየካ ክ/ከተማ እና ከአቃቂ ክ/ከተማ የተወጣጡ ወጣቶችን በሶፍቶዌር ዲቨሎመንት እና በቢዝነስ ኢንተርነርሽፕ አሰልጥኗ አስመርቋል

በተጨማሪም ድርጅቱ በምርቃቱ ላይ በፀሀይ ብርሃን የሚሰራ ሶላር ፓወርድ ኮምፒዩተር ባስ አስተዋዉቋል ፡፡


ከአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር እና ከሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ጋር በመተባበር ወጣቶችን ከየወረደዉና ክ/ከተማ ተመልምሎ በሚቀርቡለት መሰረት ከ3-6  ወራት በነፃ አሰልጥኖ እያስመረቀ ይገኛል ፡፡

ተቋሙ ይህን ትምህርትና ስልጠና በኬንያ፣ በኡጋንዳ ፣በህንድ እና በኢትዬጲያ እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል

ክራፍት ሶሉሽን ፋዉንዴሽን መቀመጫዉን ኬኒያ ናይሮቢ ያደረገ ሲሆን በሴቶች ወጣቶች እና ህፃናትን በማስተማር እና በማሰልጠን ላይ የሚገኝ ተቆም ነዉ

አቤል እስጢፋኖስ

ጥቅምት 26  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel