በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
በአዲስ አበባ የሰብልና የፋብሪካ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ መቀነሱ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ፣ የንግድ ግብይት ማስፋፊ ዳይሬክቶሬት፣ በመንግሥት ገበያ ማዕከላት የሚቀርቡ የሰብልና የፋብሪካ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ዋጋው ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም የሚተገበር ነው ተብሏል፡፡
ዋጋው በመንግሥት የገበያ ማዕከላት የሚቀርቡ ምርቶችን ብቻ የሚመለከት ነው፡፡ ከዚህ በታች የዋጋ ዝርዝሮች የቀረቡ ሲሆን፤ በምርት አቅርቦትና ዋጋ ላይ ጥቆማ ለመስጠት በ8588 ነጻ የስልክ መስመር መጠቀም ይቻላል ተብሏል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ዶናልድ ትራምፕ ለፑቲን ስልክ ደዉለዉ ግጭት አንዲያረግቡ አሳሰቡ
ተመራጩ የአሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደዉለዉ ግጭቶችና ዉጥረቶች እንዲረግቡ አሳስበዋል ተብሏል፡፡
ትራምፕና ፑቲን በዉይይታቸዉ የዩክሬን ጦርነት በሚቆምበት ሁኔታ ላይ መክረዋል ነዉ የተባለዉ፡፡
ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ሲገቡ የመጀመሪያ ስራቸዉ የሚሆነዉ ጦርነቱን ማቆም እንደሆነም አንስተዋል፡፡
ከዩክሬን ጦርነት በጠጨማሪም የሁለቱ አገራት ግንኙነት በሚሻሻልበት ዙሪያ መምክራቸዉን ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል፡፡
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጆ ባደን በበኩላቸዉ ለዩክሬን የሚደረገዉ ድጋፍ እንዳይቀዘቅዝ ትራምፕን እያግባቡ ነዉ ፡፡
የትራምፕ ተቃዋሚ የሆኑት የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ተመራጩ ፕሬዝደንት ለሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የሚያሳዩት አቋም የተለሳለሰ ነው ሲሉ ይወቅሷቸዋል።
በዩክሬን ስላለው ጦርነት ያላቸው አቋምም ዩክሬን እጇን እንድትሰጥ የሚያደርግና ለአውሮፓ አደጋ ያለው ነው ይላሉ።
አባቱ መረቀ
ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም
በካፋ የሴቶች ቻምፒዮንሰ ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሽንፈት አስተናግዷል !
በካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ በምድብ ሁለት ላይ ተደልድሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ናይጄሪያው ኤዶ ኩዊንስ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።
የኤዶ ኩዊንስን የማሸነፊያ ሦስት ግብ ኢሜም ኢሴን ከዕረፍት በፊት ፎላሼድ ኢጃሚሉሲ እና ቹክዋማካ ኦሲግዌ ከዕረፍት መልስ አስቆጥረዋል።
የኢትዮጵያው ተወካይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ሽንፈት አስተናግዷል።
በምድብ ሁለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ሽንፈት ሲያጋጥማቸው ኤዶ ኩዊንስ እና ኤፍ ሲ ማሳር ድልን ተጎናጽፈዋል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምድብ ሁለት ማሜሎዲ ሰንዳውንስን በግብ እዳ በመብለጥ ከደረጃ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን ህሮብ ቀን 11:00 ሰዓት ላይ ከደቡብ አፍሪካው ተወካይ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።
ጋዲሳ መገርሳ
ህዳር 2 ቀን 2017
ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውላቸውን ለማቋረጥ የወጣው ማስጠንቀቂያ እስከ ህዳር 30 2017 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በሽያጭ ተላልፈው የቤት ባለቤቶች ውል የተዋዋሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ አሁን ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀመባቸው እና ለፀጥታ ስጋት እየሆኑ ይገኛል ማለቱ ይታወሳል።
በመሆኑም ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ኮርፖሬሽኑ እያስጠነቀቀ የነበረ ሲሆን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ህዳር30 2017አ ም እንደተራዘመ አስታውቋል።
ሆኖም በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ መሆኑን እና በእጣ እና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ የሚተላለፉ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል
ለዓለም አሰፋ
ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ላየን ኢትዮጵያ ሆቴል ቱሪዝምና ቢዝነስ ኮሌጅ 4 መቶ 50 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ኮሌጁ በሆቴል፣ በቱሪዝምና ቢዝነስ የትምህርት ምስኮች ያሰለጠናቸውን 4መቶ 50 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል ።
የኮሌጁ ባለቤት አቶ ሙሃመድ አወል ላየን ኢትዮጵያ የሆቴል፣ቱሪዝምና ቢዝነስ ኮሌጅ ላለፉት 20 ዓመታት ለዘርፉ ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉን አንስተዋል።
በቀጣይም የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ እየተደረገ ነው ብለዋል ።
በአገሪቱ የሚገኙ ሆቴሎችም በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች እንዲቀጥሩ መመሪያ ተሰጥቷል ነው ያሉት።
በዛሬው ዕለት የተመረቁት የኮሌጁ ተማሪዎች የ 2016 ዓ.ም ምሩቃን ናቸው ተብሏል ።
ላየን ኢትዮጵያ የሆቴል ፣የቱሪዝምና የቢዝነስ ኮሌጅ ከተመሠረተ 20 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ዛሬ ያስመረቀው 20 ኛ ዙር መሆኑ ታውቋል።
ኮሌጁ ባለፉት አመታት 15ሺህ ተማሪዎችን አስተምሮ ማስመረቁን የገለፀ ሲሆን ከፍለው መማር ለማይችሉም ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ አስታውቋል ።
ላየን ኢትዮጵያ የሆቴልና ፣ቱሪዝምና የቢዝነስ ኮሌጅ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፋ ከግል የትምህርት ተቋማት ፈር ሸዳጅ መሆኑን አሰምተናል ።
አባቱ መረቀ
ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ።
ከመጀመሪያው የሩሲያ አፍሪካ የሚኒስትሮች አጋርነት ፎረም ጎን ለጎን በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
የጋራ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ በሚያስችሉ የሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ትብብርን ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ናሽናል አቬሽን ኮሌጅ በልዩ ልዩ መረሃግብር ያሰለጠናቸውን ከ900 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ በድህረ-ምረቃ ፣ በቅድመ-ምረቃ፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም በሰርቲፊኬት ፕሮግራሞች ያስለጠናቸዉን 974 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።
ኮሌጁ በዛሬው እለት በድህረ ምረቃ 343፣በቅድመ ምረቃ 134፣በቴክኒክና ሙያ 242፣ሰርቲፊኬት 255 ተማሪዎችን በጥቅሉ 974 ተማሪዎችን በወዳጅነት አደባባይ አስመርቋል ።
ተቋሙ ዘንድሮ ሲያስመርቅ ለ11ኛ ዙር ነው ተብሏል።
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ የብሔራዊ ኢንቬስትመንት ግሩፕ አባልና የብሔራዊ አየር መንገድ እህት ኩባንያ ነው ተብሏል ።
ተቋሙ ኢትዮጵያን በአቪዬሽን፣ በሆቴልና ቱሪዝም እያደገ የመጣዉን የሰለጠነ የሰዉ ኃይል ፍላጎት ከማሟላት አኳያ በሚሰጣቸዉ መርሃግብሮች ብቁ ሙያተኞችን በማፍራት ለዘርፉ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ናሽናል አቭዬሽን ኮሌጅ ከሲቪል አቬሽን ባለስልጣን እውቅና ባገኘበት በአዉሮፕላን ጥገና ቴክኒሽያንነት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን የጀመረ ብቸኛ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ነው ተብሏል፡፡
ናሽናል አቭዬሽን ኮሌጅ በቅርቡ ናሽናል ዩኒቨርሲቲ የመሆን አላማ ሰንቆ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ሰምተናል::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኮሌጁ የስልጠና ዘርፎችን በማስፋት በጤናው ዘርፍ በነርሲንግና በፋርማሲ ስልጠና መስጠት መጀመሩም ተገልጿል፡፡
ልኡል ወልዴ
ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
በጋዛ ጦርነት ከሞቱት 70 ከመቶ የሚጠጉት ሴቶችና ህጻናት ናቸው – ተመድ
ባለፈው ዓመት በጋዛ ግጭት መሞታቸው ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል 70 በመቶ የሚጠጉት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ቢሮ ያወጣው ዘገባ አመልክቷል።
የመንግሥታቱ ድርጅት ዘገባ “ይህ የዓለም ዓቀፍ የሰብአዊ ህግ መሰረታዊ መርሆችን ስልታዊ በሆነ መንገድ የጣሰ ነው” ሲልም ድርጊቱን አውግዟል፡፡
የሟቾቹ ቁጥር፣ ከአንድ ዓመት በፊት በጀመረው የእስራኤል ሀማስ ጦርነት፣ የመጀመሪያዎቹን ሰባት ወራት የሚሸፍን መሆኑን ባለ 32 ገጹ የመንግሥታቱ ድርጅት ዘገባ አመልክቷል፡፡
በዚህ ሰባት ወር ጊዜ ውስጥ፣ በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ቢሮ የተረጋገጠው የሟቾች ቁጥር 8 ሺሕ 119 ሲሆን÷ ይህ የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት በ13 ወራት ግጭት ከ43ሺሕ በላይ ነው ሲሉ ከጠቀሱት ቁጥር በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡
ይሁን እንጂ የድርጅቱ ዘገባ በጦርነቱ ከተገደሉት መካከል አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ህጻናትና ሴቶች ናቸው የሚለውን የጤና ባለሥልጣናቱን ዘገባ ይደግፋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ቢንያም ፍቅሬ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ወደ ግብፁ ክለብ እስማኤሊያ የሚያደርገው ዝውውር ያልተሳካለት ቢንያምን ፍቅሬ ዳግም ወደ ሊጉ የተመለሰበትን ክለብ አግኝቷል።
የቀድሞ ወላይታ ድቻ የታዳጊ ቡድን ፍሬ በመሆን እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ያለፉትን ዓመታት መጫወት የቻለው አጥቂው ቢኒያም ፍቅሬ ከግብፁ ክለብ እስማኤሊያ ጋር ለመጫወት ያደረገው ስምምነት አለመሳካቱን ተከትሎ ወደ ሀገሩ መመለሱን አይዘነጋም።
ወደ ሀገር ቤት መመለሱን ያወቁ የተለያዩ የሊጉ ክለቦች ሲያነጋግሩት ቢቆዩም በስተመጨረሻም ማረፊያው ቅዱስ ጊዮርጊስ መሆኑ እርግጥ የሆነ ይመስላል።
ተጫዋቹ እና ክለቡ በአብዛኛው ድርድሮች ከስምምነት መድረሳቸው የታወቀ ሲሆን በቅርቡ ፊርማውን ለክለቡ እንደሚያኖር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ፈረሰኞቹ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ማጣቱን ተከትሎ ቢንያም ፍቅሬ ሁነኛ ተተኪ በመሆን ቡድኑን የማጥቃት አቅም ከፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሶከር ኢትዮጵያ
ጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የእንግሊዝ የፕርሚየር ሊግ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርጓል።
የኖቲንግሀም ፎረስቱ የፊት መስመር ተጨዋች ክሪስ ውድ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ ተገልጿል።
ተጨዋቹ በወሩ ባደረጋቸው ሶስት የሊግ ጨዋታዎች አራት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
አስረኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ አሰልጣኝን ይፋ አድርጓል።
በዚህም ፖርቹጋላዊው የኖቲንግሀም ፎረስት አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለው መመረጥ ችለዋል።
አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ክለባቸውን እየመሩ በወሩ ካደረጓቸው ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች ሁለቱን በድል ሲያጠናቅቁ በአንድ ጨዋታ ነጥብ ተጋርተዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
10ኛው የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
ከ2መቶ50 በላይ ኢንዱስትሪዎች በኤግዚቢሽኑ ይገኛሉ ተብሏል።
ከ30 አገራት በላይ የተውጣጡ ከ2መቶ50 በላይ የፋሽን ፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን የሚያቀርቡ ይሆናል።
የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት 10ኛ አመት ክብረ በዓሉን በማስመልከት በዝግጅቱ ላይ አለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና አዳዲስ ፈጣሪዎችን የሚያገናኝ ኤግዚብሽን ማዘጋጀቱ ነው የተገለፀው።
ከ60 አገራት በላይ የሚመጡ ከ7ሺህ በላይ የንግድ አቀላጣፊዎች ይገኛሉም ተብሏል።
የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በጨርቃጨርቅ ፣ በአልባሳት እና የቆዳ እሴት ሰንሰለቶች መካከል ንግድን በማመቻቸት በአህጉሪቱ የፋሽን መድረክ ሆኖ ቆይቷል ነው የተባለው።
10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት ከዛሬ ጥቅምት 29 ጀምሮ እስከ ህዳር 02 ቀን ለአምስት ቀናት በስካይ ላይት ሆቴል የሚቆይ ነው።
እስከዳር ግርማ
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
እገታን እና ዘረፋን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ 121 ግለሰቦችን በቀጥጥር ሥር ማዋሉን የአማራ ክልል ዋና ከተማ የባሕር ዳር ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሊጠናቀቅ በተቃረበው ጥቅምት ወር ብቻ መሆኑን የከተማው ፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ኮማንደሩ አክለውም በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው ከተያዙት ግለሰቦች መካከል ከ20 በላይ የሚሆኑት በእገታ ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው ብለዋል።
በግጭት እየታመሰ ባለው አማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እገታ፣ ዘረፋ እና ግድያ በተደጋጋሚ የሚከሰት አሳሳቢ ወንጀል መሆኑን የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የተለያዩ የተራድዖ ድርጅቶች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
ኮማንደር ዋለልኝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች በእገታ፣ በባንክ ዘረፋ እና በተለያዩ የስርቆት ወንጀሎች ተጠርጥረው በፖሊስ ሲፈለጉ የነበሩ ናቸው።
“የተያዙት 121 ናቸው። በእገታ ብቻ ሳይሆን በባንክ ዝርፊያ እና በልዩ ልዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ናቸው። ከ20 በላይ የሚሆኑት በእገታ ተጠርጥረው የተያዙ ናቸው” ይላሉ።
የባሕር ዳር ፖሊስ ኃላፊ እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ‘ኦፕሬሽን’ የተጀመረው በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ነው።
የከተማዋ ፖሊስ ካደራጀው ምርመራ እና ከሕዝብ ጥቆማ ተነስቶ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ማዋሉንም ኃላፊው ይናገራሉ።
“ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው ማስረጃዎች ተጠቅመን ነው በቁጥጥር ሥር ያዋልናቸው።”
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የተወሰኑቱ ገንዘብ ወደ ባንክ ገቢ ሲያደርጉ አሊያም ገቢ እና ወጪ ለማድረግ የተጠቀሙት የስልክ ቁጥር ምርመራ ተደርጎበት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ያስረዳሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ፑቲን ትራምፕ ደፋር ነዉ አሉ
የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተመራጩን የአሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንኳን ደስ አልዎት ብለዋቸዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕም ለፑቲን እደዉላለሁ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በሶቺ ቫልዳይ ጉባዔ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ፑቲን ትራምፕ ደፋር ሰዉ ነዉ ብለዋል፡፡
ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገረዉን ሁሉ ማመን ባይቻልም ነገር ግን ከዩክሬን ቀዉስ ጋር ተያይዞ ያነሳዉን ሀሳብ ትኩረት መስጠት ይገባል ነዉ ያሉት ፑቲን፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዶናልድ ትራም ደፋር ነዉ ያስገርመኛል ያሉት ፑቲን ከፖለቲካ ይልቅ የቢዝነስ ሰዉ በመሆኑ ብዙ ስህተቶችን ከዚህ ቀደም ይሰራ ነበር ሲሉም አንስተዋል፡፡
ሞስኮ ከዋሽንግተን ጋር ለመነጋገር በሯ ክፍት ስለመሆኑም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡
ኔቶን አስመልከተዉ ሲናገሩም የጦር ጎራዉ ጊዜዉን የሳተ ስብስብ ሲሉ ወርፈዋቸዋል፡፡
የትራምፕን መመረጥ ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ የተቀመጡት የአዉሮፓ አገራት መሪዎቸ አደጋ ዉስጥ ነን እያሉ ነዉ፡፡
አውሮፓ ካማላ ወይም ትራምፕ ስለተመረጡ ሳይሆን የራሱን እጣፈንታ የሚወስንበትን አቅም ሊገነባ ይገባል ብለዋል፡፡
ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ከአውሮፓ ጋር ከሚኖረው የንግድ ጦርነት አንስቶ ከኔቶ ለመውጣት እና ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት መሰረታዊ የሆነ የድጋፍ ለውጥ እንደሚያደርጉ ዝተዋል፡፡
ይህም በመላው አውሮፓ በሚገኙ ሀጋራት ላይ ከፍ ያለተጽዕኖ ሊያስከትል እንደሚችል ኤፒ ዘግቧል፡፡
አባቱ መረቀ
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን ደንብ መውጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህ ቢሮ አሳውቋል።
ይህ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ የወጣ ነው። ደንቡ " በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ ነው " ብሏል።
ከደንቡ የአለባበስ ስርአት ውስጥ ለአብነት ፦
ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፤
የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፤
ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ያስቀምጣል፡፡
ቢሮው " ደንብ ቁጥር 178/2017 በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም በከተማው የሚሰጠው የሆቴል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ ነው " ብሏል።
ይህ ደንብ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራ ባለሙያ በደንቡ በተደነገገው መሰረት አክብሮ እየሰራ ስለመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል ይደረጋል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል ነው የተባለው።
መረጃው ከየአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ የተገኘ ነው።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም
ወጋገን ባንክ በ ሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያ ላይ የጎላ ሚና እንዲኖረዉ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገለፀ።
ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅት ላይ ያለዉን የካፒታል ገበያ ተከትሎ ባንኩ አዲስ የኢንቨስትመንት ባንክ ማቋቋሙን ተናግሯል።
ይህ የኢንቨስትመንት ባንክ በቅርቡ የምዝገባ ስርአት እንደሚጀምር ታዉቋል።
ወጋገን ባንክ ይህን ያለዉ ዛሬ ባደረገዉ መደበኛ እና 15 ተኛ አስቸኳይ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነዉ።
ወጋገን ባንክ በዚህ የሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያ ዉስጥ ተሳትፎዉን ለማጉላት የአሰራር ስርአቶችን ለመዘርጋት ተዘጋጅቻለሁ ብሏል።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሽ ሁሴን በሰጡት ማብራሪያ የባንኩን መዋቅር እና ፖሊሲዎች ላይ ክለሳዎች እንደሚደረጉ አንስተዋል።
ለዚህም በባንኩ የቴክኖሎጂ ዝመና እና በቂ በገበያዉ ላይ የሰለጠኑ ባለሙያዎች እንዲኖሩት የቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተያይዞ ተነስቷል።
ዛሬ በተደረገዉ ጉባኤም የሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያ የሚፈልገዉን የኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሂሳብ አያያዝ ስርአት ተከትሎ የባንኩ አክሲዮኖችን ዲጂታል ማድረግ ላይ በመወያየት ፀድቋል።
በተጨማሪም ወጋገን ባንክ በ2016 በጀት አመት ገቢዉ ከፍተኛ የትርፍ መጠን ያለዉ እንደሆነ ያሳወቀ ሲሆን ይህም በንፅፅር ከባለፈው በጀት አመቱ ገቢ የ 40 በመቶ እድገት እንደታየ ተገልፆል።
በበጀት ዓመቱ ባንኩ ከታክስ በፊት ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበውን 2.2 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር የ86 በመቶ እድገት መኖሩን ሪፖርቱ አመላክቷል።
የቦርዱ ሰብሳቢ በአዲሱ የባንክ ስራ አዋጅ ጋር ባንኩ ራሱን በማሻሻል እንደሚሰራ ተናገረዋል።
ቁምነገር አየለ
ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ኦቪድ ሪል ስቴት ከራይድ ትራንስፖርት ጋር የራይድ ቤተሰብ መንደርን ለመገንባት ከተፈራረመ ከአንድ ወር በኋላ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ።
ኦቪድ ሪል ስቴት ለራይድ ሹፌሮች የሚሆን የራይድ ቤተሰብ መንደር በገላን ጎራ ከተማ ለመገንባት ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።
ራይድ ትራንስፖርት እና ሰዋሰው መልቲሚዲያ ለሚያስገነቡት ዘመናዊ የራይድ መንደር ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በገላን ጉራ ከተማ በይፋ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአማራጭ ቤቶች ልማት ፕሮግራም ዳይሬክተር ኢንጅነር ታምራት አክሊሉ፤በመንግስትና የግል አጋርነት ከሚሰሩ ፕሮጀክቶች መካከል ከኦቪድ ጋር በትብብር እየተሰሩ ካሉ ፕሮጀክቶች የራይድ መንደር ግንባታ አንዱ መሆኑን አንስተው፤ መንግስት ከመሬት አቅርቦት ጀምሮ ሌሎች አማራጮችንም በማቅረብ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።
ኦቪድ ሪልስቴት አዲስ እየተገነባ በሚገኘው የገላን ጎራ ከተማ ውስጥ ለራይድ አሽከርካሪዎች እና ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር ለተፈራረሙ አርቲስቶች በአጭር ጊዜ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ነው የተስማማው።
በዚህ ስምምነት ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር የተፈራረሙ አርቲስቶች በቅናሽ የቤት ባለቤት መሆን እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።
ኦቪድ ግሩፕ ከሚያደርገው የቤት ዋጋ ቅናሽ በተጨማሪ ሰዋሰው መልቲሚዲያ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ኦቪድ ግሩፕ ከ90 ሺህ በላይ ቤቶችን በተለያዩ ሳይቶች እየገነባ መሆኑን የገለፁት የኦቪድ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዮናስ ታደሰ፤ 60 ሺህ የሚሆኑት በገላን ጎራ ከተማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአማራጭ ቤቶች ልማት ፕሮግራም ዳይሬክተር ኢንጅነር ታምራት አክሊሉ፤ ኦቪድ ከሚሰራቸው ቤቶች 30 በመቶ ድርሻ እንዳለው ገልፀው ፤ 18 ሺህ ቤቶች የመንግስት መሆናቸውን አንስተዋል።
ዳይሬክተሩ መንግስት እነዚህን ቤቶች ለልማት ተነሺዎች ፣ ለቆጣቢዎች እና ለሌሎች የሚሰጥ መሆኑንም ገልፀዋል።
ኦቪድ ግሩፕ ከሁለቱ ተቋማት ጋር በገባው ስምምነት መሠረት 5 ሺህ ቤቶችን በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሰርቶ እንደሚያስረከብ አስታውቋል።
እሰከዳር ግርማ
ጥቅምት 30 ቀን ዓ.ም
ኤፍቢአይ በመላው አሜሪካ ለጥቁሮች የተላኩ ዘረኛ የጽሑፍ መልዕክቶች ላይ ምርመራ ጀመረ
በመላው አሜሪካ ለሚገኙ ጥቁሮች የተላኩ ዘረኛ የጽሑፍ መልዕክቶች ላይ ምርመራ መክፈቱን የአሜሪካው የፌደራል የምርመራ ቢሮ አስታወቀ።
የተላኩት የጽሑፍ መልዕክቶች በባርነት ዘመን እንደነበረው “ወደ ማሳ ሄደው ጥጥ ለቅመው ለጌቶቻቸው ሪፖርት” እንዲያደርጉ የሚጠቅስ ነው።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የዩኒቨርስቲ ጥቁር ተማሪዎችን ጨምሮ በአላባማ፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ቨርጂኒያ፣ ኒውዮርክ እና ፔንስልቬንያ ግዛቶች ነዋሪ የሆኑ ጥቁሮች እነዚህ የጽሑፍ መልዕክቶች ደርሷቸዋል ተብሏል።
“ኤፍቢአይ ለነዋሪዎች የተላኩትን አጸያፊ እና ዘረኛ የጽሑፍ መልዕክቶችን ያውቃል እናም በጉዳዩ ላይ ከፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከሌሎች የፌደራል ባለስልጣናት ጋር እየመከረ ነው” ብሏል የፌደራል ምርመራ ቢሮው
የጽሑፍ መልዕክቶቹ መላክ የጀመሩት አሜሪካ ካደረገችው ብሄራዊ ምርጫ ማግስት እንደሆነ ይታመናል።
አንዳንድ መልዕክቶች የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ቡድንን ቢጠቅስም ቡድኑ በበኩሉ ንክኪ የለኝም ሲል ውድቅ አድርጓል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
"የደመወዝ ማስተካከያው የጥቅምት ወር ክፍያን ታሳቢ በማድረግ ይከፈላል" የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)
ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ የጥቅምት ወር ክፍያን ታሳቢ በማድረግ እንደሚከፈል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ኮሚሽነሩ በማህበራዊ ትስስት ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፤ "የተፈቀደው የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ክፍያ ዘግይቷል፣ ቀርቷል የሚሉ ሃሳቦች እየተራመዱ ነው። በሲቪል ሰርቪስ በኩል የሚለቀቁ መረጃዎች ኦፊሴላዊና የሚተገበሩ መሆኑን መተማመን ጥሩ ነው።" ብለዋል፡፡
አክለውም፤ ቀደም ሲል የመንግሥት ሰራተኞችን የደመወዝ ስኬል በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚናፈሱ አሳሳች ወሬዎች ማህረሰቡ እንዳይሳሳት መልዕክት ማስተላለፋቸውን አስታውሰዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር የተጨማሪ ክፍያ በጀቱን ለሚመለከታቸው ተቋማት መፍቀዱን የገለጹት ኮሚሽነሩ፤ "በእኛ መስሪያ ቤትም በኩል የተስተካከለውን የጥቅምት ወር ደመወዝ ተከፍሏል። ሌሎችም እንደዚሁ የከፈሉ አሉ" ብለዋል።
የቀሩት ተቋማት ደግሞ ማስተካከያውን ለማድረግ የማጥራት ሥራ እየሰሩ ሊሆን እንደሚችል ያመላከቱም ሲሆን፤ "እነዚያም ዝግጅታቸውን ሲያጠናቅቁ የተስተካከለው የጥቅምት ወር ክፍያ ታሳቢ በማድረግ የሚከፍሉ ይሆናል።" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሽዴ ጥቅምት 09/2017 ዓ. ም በሰጡት ማብራሪያ አዲሱ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸው ነበር።
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ፤ ለደሞዝ ጭማሪው 91 ቢሊዮን ብር መመደቡን ገልጸው፤ ክፍያው ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ 200 የጋቦን ተማሪዎችን በአቪዬሽን ዘርፍ ሊታሰለጥን ነው፡፡
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ከጋቦን 200 ተማሪዎችን ተቀብሎ ሊያሰለጥን መሆኑን አስታውቋል።
ጋቦናውያን ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የአቪዬሽን ዘርፎች ትምህርታቸውን ይከታተላሉ ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የጋቦን ሪፐብሊክ አምባሳደር ሊሊ ስቴላ ንዶንግ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች ተማሪዎኡን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ማስገባት ሙሉ በሙሉ ተከለከለ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ለጉምሩክ ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ ፍራንኮ ቫሉታ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን ጠቅሷል፡፡
የብር የመግዛት አቅም በገበያው እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን እና የፀጥታ ተቋማት መሳሪያዎችን ሳይጨምር ሌሎች ምርቶችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ማስገባት ተፈቅዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይሁንና ከሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሲሰጡ የተፈቀደው ፍራንኮ ቫሉታ ሀብት ከሀገር እንዲሸሽ ምክንያት እየሆነ በመሆኑ ሊታገድ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ለተጠቀሱት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤም ከዚህ ቀደም በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ከውጪ ያዘዙ ካሉ ከዛሬ ጀምሮ በ2 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ግዢ የተፈፀመባቸው ህጋዊ ሰነዶችን ለጉምሩክ ኮሚሽን በማቅረብ ተቀባይነት አቅርበው የንግድ ሸቀጦቹ ወደ ሀገር እንዲገቡ ይደረጋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኩል ይደረግ የነበረዉ የሲሚንቶ ግብይት ትስስር ስራ ከዛሬ ጀምሮ እንዲቀር መደረጉ ተገለጸ
ከዚህ ቀደም በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኩል ይደረግ የነበረዉ የሲሚንቶ ግብይት ትስስር ሥራ ከዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቀር መደረጉን ሚኒስትሩ ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ አስታወቁ።
አምራቾች በራሳቸዉ ኃላፊነት በሚመርጧቸዉ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች በኩል ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ይችላለሁ የሚል ውሳኔ መተላለፉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ይህንን የመንግስት ውሳኔ ያስታወቁት የሲሚንቶ ምርት አቅርቦትና ፍላጎት ለማጣጣም እንዲቻል ከሲሚንቶ አምራቾች ጋር ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን ባካሄዱት ውይይት ወቅት ነው።
የግብይት ሥርዓቱም ሙሉ በሙሉ ከካሽ ክፍያ ነጻ ሆኖ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እንዲፈጸም አቅጣጫ መቀመጡንም አመላክተዋል።
አምራቾችም የሥራቸዉን የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲያቀርቡ እንደሚገደዱ አና በማያቀርቡ በማናቸዉም የሲሚንቶ አምራች ላይ ግን መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
አመታዊው የስሚንቶ አቅርቦቱ ከ7 ሚሊዮን ቶን አለመዝለሉን ያስታወቁት ሚኒስትሩ አምራቾች በአቅርቦት በኩል ያለዉን ማነቆ ለመፍታት የማምረት አቅማቸዉን ወደ 80 በመቶ በማድረስ 20 ሚሊዮን ቶን ሀገራዊ የሲሚንቶ ምርት ዓመታዊ ፍላጎትን ለማሟላት በትኩረት እንዲሰሩ በአጽንኦት ማሳሰባቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ አካቷል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በነገው እለት ሊያስመርቅ ነው፡፡
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከድህረ ጦርነቱ በኃላ ለሁለተኛ ጊዜ ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በነገዉ እለት ያስመርቃል፡፡
የመቀለ ዩኒቨርሲቲ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ትኮቦ ገ/ ስላሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲዉ ከድህረ ጦርነት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ሊያስመርቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲዉ ባለፈዉ አመት ከ ሁለት ሺ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወሳል።
ዩኒቨርስቲው ዘንድሮ በአንደኛ ፣በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ የትምህርት መርሃ ግብር ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ ይህ ለ30 ኛ ጊዜ ነው ተብሏል።
አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዉ ብዙ ችግሮችን እያሳለፈ ይገኛል ያሉት ዶ/ር ተክቦ የመምህራኖች የመኖሪያ ቤት ችግር ዋነኛ ፈተና ሆኖ መቀጠሉን እና በዚህ ከፍተኛ ችግር የተነሳ አንዳንድ መምህራን በተማሪዎች ዶርም ውስጥ ኑሯቸውን እንዳደረጉ ነግረውናል ፡፡
በተጨማሪም ለረዥም ወራቶች የዘለቀ የደሞዝ መቋረጥ ዩኒቨርስቲው ዛሬም ድረስ ያጋጠሙት ፈተናዎች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
በዘንድሮ የትምህርት ዓመት ሁለት ሺ ስምንት መቶ አዳዲስ ተማሪዎች ወደ ዩንቨርስቲዉ የተመደቡ ሲሆን በመጪው ጥር ወር አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎቹች ጥሪ የማድረግ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር ነግረውናል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የሸበሌ ወንዝ ሙላት በሶማሊ ክልል ሶስት ወረዳዎች የንብረት ውድመት አደረሰ
የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በሶማሊ ክልል ሸበሌ ዞን ስር በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች የንብረት ውድመት አደረሰ።
የጎርፍ አደጋው በሸበሌ ዞን ቀላፎ፣ ሙስታሂልና ፌርፌር ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በተለይም በቀላፎ ወረዳ ባሉ ሰባት ቀበሌዎች በንብረት እና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የክልሉ ሚዲያ ዘግቧል።
አደጋውን ተከትሎ በአከባቢው የሚኖሩ ዜጎች በአንስተኛ ጀልባዎች ቦታውን ለቀው እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን በጎርፉ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉና የተጎዱ ነዋሪዎችን ለማገዝ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የሸበሌ ወንዝ ሙላት በተደጋጋሚ በሸበሌ ዞን ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በነሐሴ ውር 2016 በተመሳሳይ ወረዳዎች በደረሰው የጎርፍ አደጋ ሁለት ሺ 827 አባወራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ሲፈናቀሉ፤ 6 ሺህ186 ሄክታር የሰብል መሬት ላይ ጉዳት ማድረስ ይታወሳል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት 45 ነጥብ 63 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።
በሩብ አመቱ ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረው ገቢ 54 ነጥብ 92 ቢሊዮን ብር እንደነበር ተጠቁሟል፤ በበጀት አመቱ 230 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ መያዙ ተገልጿል።
ቢሮው ከተማዋ ከምታመነጨው ሃብት መሰብሰብ ያለበትን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ የሚያስችል ስራ እያከናወነ መሆኑን የአስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ ተናግረዋል፡፡
ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ቢሮዎች፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ በፌዴራል ደረጃና በክልሎች ከሚንቀሳቀሱ 25 ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም በጋራ እየሰራ መሆኑምን ተጠቁሟል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሩብ ዓመቱ 96 ሺህ 415 አዲስና ነባር ግብር ከፋዮች ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እንዲወስዱ መደረጉን አስታውቋል፡፡
እንዲሁም ቢሮው በኮንትሮባንድ፣ በህገ ወጥ ንግድና በሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር 361 ህገ ወጥ ነጋዴዎች ተይዘው በህግ ተጠያቂ መደረጋቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
‹‹ቴግሬቶል›› የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ መድኃኒት ጨቅላ ህፃናት እንዳይጠቀሙት የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡
መድሃኒቱን ጨቅላ ህጻናት እንዳይጠቀሙት ባለስልጣኑ ማሳሰቡን የነገሩን፤ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በባለስልጣኑ የመድሀኒትና ደህንነት ድህረ ገበያ ክትትል ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተሽታ ሹቴ ናቸዉ።
ይህ የተጠቀሰው መድኃኒት በውስጡ በሚይዘው ንጥረ-ነገር መጠን ምክንያት ለጨቅላ ሕፃናት ማለትም ከ4 ሳምንታት በታች ለሆኑ ሕፃናት አልያም የመወለድ ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እንደማይመከር ገልጸዋል።
በዚህ ምርት ውስጥ ያለው የንጥረ ነገር መጠን ለጨቅላ ሕፃናት ከደህንነት ገደብ በላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ነዉ ያሉት ።
በዚህ ምርት ውስጥ ከሚገኙት ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው ‹‹ፕሮፓይሊን ግላይኮል›› ለምግብ እና ትንባሆ ምርቶች፤ እንዲሁም ለፋርማሲዩቲካል እና መዋቢያዎች በአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ደህንነቱ የተጠበቀ ምርት መሆኑ ቢገለጸም ፤ ለጨቅላ ህጻናት ግን የሚመከር አይደለም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ ተሽታ፤ ይህንን መድኃኒት ለጨቅላ ሕፃናት እና ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ መጠቀም ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች መድኃኒቱን ለተጠቀሱት የእድሜ ክልል ከማዘዝ እና ከማከፋፈል እንዲቆጠቡ ባለስልጣኑ ማሳሰቡን ተናግረዋል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ፊናፍ የአፋን ኦሮሞ ፊልም በቴሌቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ጀምሮ መታየት ይጀምራል ተባለ።
ፊናፍ ፊልም በቴሌቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለህዝብ መታየት እንደሚጀምር ተገለፀ።
በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የተሰራው ፊናፍ ፈልም ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት በግል እና በመንግስት ሲኒማ ቤቶች ለተመልካች እይታ ቀርቦ ነበር።
በወቅቱም ከተመልካች አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት የቻለ ተወዳጅ ፊልም ነው ተብሏል::
በቢቂላ አስፋው ተጽፎ የተዘጋጀው ፊናፍ ፊልም አንጋፋ እና አዳዲስ ተዋንያኖች ተሳትፈውበታል።
ፊናፍ የድራማ ዘውግ ያለው 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ፈልም ሲሆን እንግሊዘኛ ሰብታይትል እንዳለው አቶ ቢቂላ አስፋው ገልጸዋል።
በጉማ፣ ኦዳ እና ለዛ አዋርዶች እጩ መሆን የቻለው ይህ ፊልም በ9ኛው የጉማ አዋርድ ላይም ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ የውድድር ዘርፍ ብሩከ ግርማ ከፊናፍ ፊልም አሸናፊ መሆን ችሏል።
ቴሌቲቪ በኢግልላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያዉያን እዚሁ ሃገራችን ዉስጥ የበለጸገ ፕላትፎርም ነው። አሁን ላይ በቴሌቲቪ መተግበሪያ ፊናፍ ፊልምን ጨምሮ 8 የተመረጡ ሃገርኛ ፊልሞች ይገኙበታል።
አፎሚያ አሸናፊ
ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም