ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ባይደን እና ትራምፕ በዋይት ኃውስ ተገናኙ


ባለፈው ሳምንት ምርጫውን ካሸነፉ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ወደ ዋሽንግተን የተመለሱት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋራ ዋይት ኃውስ ውስጥ ተገናኝተው እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።

ጆ ባይደን ትረምፕን ወደ ዋይት ኃውስ የጋበዟቸው ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ ሲሆን በዛም እንደደረሱ “ዶናልድ እንኳን ደስ አለህ” ብለዋቸዋል።

"መጪው ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ፣ እንኳን ደስ አልዎት። እንዳልነው በቀጣይ ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ በጉጉት እየጠበቅን ነው። የሚፈልጉትን ለማድረግ የምንችለውን እያደረግን ነው፣ እናም የተወሰነውን አሁን ለመነጋገር እድል እናገኛለን።"


ትራምፕ በበኩላቸው ባይደን ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነው፣ "በአንዳንድ ነገሮች የፖለቲካው ዓለም አስደሳች አይደለም። ዛሬ ግን አስደሳች ነው።

ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር መደርጉን አደንቃለሁ። ከዚህ በዋላ በሚቻለው ሁሉ የተረጋጋ ሽግግር ይሆናል። በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው። አመሰግናለሁ" ሲሉ ፖለቲካ አስቸጋሪ መሆኑን ግን ደግሞ በተደረገላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ትራምፕ  ዛሬ ጠዋት አውሮፕላናቸው ሜሪላንድ በሚገኘው ጆይንት ቤዝ አንድሩስ የአየር ኃይል ወታደራዊ ቅጥር ያረፈ ሲሆን፣ በካፒቶል የሚገኙ የሪፐብሊካን አባላትንም አግኝተው ንግግር አድርገዋል።

ትረምፕ ከአራት ዓመታት በፊት በምርጫው በተረቱበት ወቅት ባይደንን ወደ ዋይት ሃውስ አልጋበዙም። በባይደን በዓለ ሹመት ላይም አልተገኙም።

ህዳር 04 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አንድ ግለሰብ በደቡባዊ ቻይና በፈጸመው የመኪና ጥቃት ቢያንስ 35 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በደቡባዊ ቻይና በተፈጸመ የመኪና ጥቃት ቢያንስ 35 ሰዎች ተገደሉ። በአገሪቱ ባለፉት አሥርት ዓመታት በላይ በሕዝብ ላይ የተፈጸመ እጅግ አስከፊው ጥቃት እንደሆነ ይታመናል።

ክስተቱ በቻይና ብሔራዊ ቅሬታን የቀሰቀሰ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸው ወንጀል ፈጻሚው ግለሰብ "ከባድ ቅጣት" እንደሚጠብቀው ቃል ገብተው የተጎዱትን ለማከም "ሁሉን አቀፍ ጥረት" እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ ሰኞ ዕለት አንድ ግለሰብ ዙሃይ በሚገኘው ስታዲየም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎችን በመኪናው ገጭቷል።

“በአስከፊው እና በአሰቃቂው ጥቃት” አዛውንቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 45 ሰዎችም መቁሰላቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ፖሊስ እንዳለው ከሆነ የ62 ዓመቱ አሽከርካሪ ፋን እንደሚባልና ድርጊቱን የፈጸመው በፍቺው ውሳኔ ዙሪያ ደስተኛ ባለመሆኑ የተነሳ ይመስላል ።

ግለሰቡ ከዙሃይ ስፖርት ማዕከል ለመሸሽ ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን እና በራሱ ላይ ባደረሰው ጉዳት ኮማ ውስጥ እንደሚገኝ ፖሊስ በመግለጫው አክሏል።

ስለተገደሉት ሰዎች ዝርዝር መረጃ በባለሥልጣናት በኩል አልተገለጸም።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ነገ ማለዳ ወደ ኪንሻሳ የሚያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሀገር ቤት ልምምዳቸውን አጠናቀዋል።

ከታንዛንያ እና ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ላለበት የመጨረሻ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ብሔራዊ ቡድኑ በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እየተመራ ከጥቅምት 28 ጀምሮ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዝግጅቱን እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

በጉዳት ከስብስቡ ውጭ በሆነው ኪቲካ ጅማ ምትክ ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃንን የተካው ቡዱኑ ወደ ስፍራው ከማቅናቱ አስቀድሞ ዛሬ የሀገር ቤት የመጨረሻ ልምምዱን አገባዷል። ለሁለት ሰዓት በቆየው በዛሬው ልምምድ ሁሉን ያማከለ ታክቲካል ስራዎችን ሲከውኑ ተመልክተናል።

በዛሬው ልምምድ በሕመም ምክንያት ፍሬዘር ካሳ፣ በረከት ደስታ እና ቢኒያም ዐይተን በዛሬው ልምምድ አለመሳተፋቸውን አስቀድመን ካጋራናችሁ መረጃ ውጭ ሁሉም የቡድኑ አባላት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

ነገ ማለዳ ወደ ኪንሻሳ የሚያቀናው ቡድኑ ህዳር ሰባት ከታንዛኒያ ህዳር አስር ደግሞ ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር በዛው የኮንጎ ዲሪ. ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም ጨዋታውን የሚያከናውን ይሆናል።

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ በባቱ ከተማ የመጀመሪ ያ ደረጃ ትምህርት ቤት አስገንብቶ ለማህበረሰቡ አስረከበ

የመጠጥ አምራች ድርጅት ቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ በባቱ (ዝዋይ)ከተማ ያስገነባውን "የአባ ገዳ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት" በዛሬው እለት አስመርቆ ለባቱና አከባቢው ማህበረሰብ አስረክቧል።

የ ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄርቬ ሚልሃድ፣ ትምህርት ቤቱን ለማስገንባት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ብሏል።

ት/ቤቱ ፤ ለመማር ማስተማር አስፈላጊ ቁሳቁሶች የተሟሉላቸው ስምንት የመማሪያ ከፍሎችና ንጽህናቸውን የጠበቁ መፀዳጃ ቤት አለው ብለውናል ።

አቶ ሄርቬ ሚልሃድ፣ትምህርት ቤቱ በጠቅላላ በሁለት ጊዜ ፈረቃ ከ 6 መቶ በላይ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም አለው ያሉን ሲሆን ከኬጂ ጀምሮ እስከሶስተኛ ክፍል ትምህርት ይሰጣል ነው ያሉት፡፡

የባቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አህመዲን እስማኤል በበኩላቸው በከተማዋ አንዱ ችግር ዛሬ ተፈቷል ያሉ ሲሆን አሁን ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።

ሆኖም ይህ ትምህርት ቤት ለከተማዋ ብሎም ለሃገር የትምህርት መሠረተ ልማትን ከማስፋፋት በላይ ቢጂአይ ለማህበረሠቡ የሚያደርገውን ድጋፍ በጉልህ የሚያሳይ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ውጭ ድርጅቱ በአከባቢው አቅመደካማ ለሆኑ ከ500 በላይ ለሆኑ አባወራዎች የጤና መድህን ክፍያን በመሸፈን በማሳከም ላይ ይገኛል ተብሏል ።

ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ቢራና ወይን ጠጅ ምርት በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም በመሆን በሰባት ፋብሪካዎቹ ቢራና ወይን ጠጅ በማምረት ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የድርሻውን በመወጣት ይገኛል ።

ልኡል ወልዴ

ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከ3 ሺህ 5 መቶ በላይ ዜጎች የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና አግኝተዋል ተባለ

የኢትዮጵያ አይን ባንክ ከተመሰረተበት ጊዜ እስካሁን ድረስ ከ3 ሺህ 5 መቶ በላይ ዜጎች በተለያዩ የህክምና ማእከላት የብሌን ንቅለ ተከላ ተከናዉኖላቸዋል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ታዘበዉ በጤና ሚኒስቴር በተደረገ ጥናት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በአይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት የአይን ብርሀናቸውን አጥተው የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ እየተጠባበቁ ይገኛሉ ብለዋል።

ከ15ሺህ በላይ ወገኖች ከህልፈት በኋላ ብሌን ለመለገስ የቃል ኪዳን ሰነድ መፈረማቸዉ ተነግሯል ፡፡

ይሁን እንጂ ካለው ፍላጎት አንጻር ሲታይ የለጋሾች ቁጥር አናሳ መሆኑ ነው የተገለፀዉ፡፡

በመሆኑም ህዳር ወር አለም አቀፍ የአይን ብሌን ለጋሾች ወር በመሆኑ የብርሀን ስጦታ በመስጠት የወገኖቻችን ህይወት እንቀይር በሚል መሪ ቃል ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ይከበራል።

በዚህም የሀገር ከፍተኛ የመንግሥት አካላት ፡ታዋቂ ሰዎች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ጋዜጠኟች፣ የሀይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎችን ቃል በማስገባት ወሩን በሙሉ ይከበራል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኤለን መስክ የመንግሥትን ብቃት የሚገመግም መስሪያ ቤት ኃላፊነት ሹመት ተሰጠው

የተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ የጀርባ አጥንት የሆነው ቢሊየነሩ ኤለን መስክ የመንግሥትን ብቃት የሚገመግም አዲስ መስሪያ ቤት የኃላፊነት ሹመት ተሰጠው።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤለን መስክ ለሪፐብሊካን እጩ ፕሬዚዳንትነት ተወዳድረው ከነበሩት ቪቬክ ራምስዋሚ ጋር በጋራ ይህንን መስሪያ ቤት ይመራሉ ብለዋል።

መስሪያ ቤቱ በዋነኝነት የመንግሥት ቢሮክራሲን ለማስወገድ እና ወጪን በመቀነስ ላይ ከመንግሥታዊ ስራ ውጭ ምክር እና መመሪያ ይሰጣል ተብሏል።

መስሪያ ቤቱ መንግሥታዊ ሚና የለውም የተባለ ሲሆን ምን አይነት ቅርጽ እንደሚኖረው እስካሁን ግልጽ አልሆነም።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የፎክስ ኒውስ አቅራቢውን ፒት ሄግስትን የመከላከያ ጸሓፊ እንዲሁም ጆን ራትክሊፍን የብሔራዊ መረጃ ዳይሬክተር አድርገው መርጠዋል።

ኤለን መስክ በመንግሥት ብቃት እና የበጀት ቅነሳ ላይ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ተናግሮ ነበር።

የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው ኤለን መስክ የትራምፕ የስልጣን ሽግግርን የሙሉ ጊዜ ስራው እንዳደረገው ሪፖርቶች ወጥተዋል።

ተመራጩን ፕሬዚዳንት በካቢኔ ሹመት ላይ ከመምከር በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት በነበረው የትራምፕ እና የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ውይይት ተገኝቶ ነበር።

መስክ የትራምፕን ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ለማገዝ ወደ 200 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አውጥቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በህውሃት እና ጊዜዓዊ አስተዳደሩ መካከል  ለተፈጠረው አለመግባበት  መፍትሄው “የፌድራል መንግስቱ በጉዳዩ ጣልቃ መግባት ነው” ሲል የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ገለጸ

በህውሃት እና ጊዜዓዊ አስተዳደሩ መካከከል  በተፈጠረው አለመግባበት  የገፈቱ ቀማሽ  ህዘቡ በመሆኑ የፌድራል መንግሰት  ጣልቃ በመግባት ውሳኔ ይስጥበት ሲለ የትግራይ ዲሞክራሲዊ ፓርቲ (ትዴፓ)  ገልጿል::

የፓርቲው ማዓከላዊ ኮሚቴ አባል  አቶ ገ/ጊዮርጊስ ግደይ ለጣቢያችን  እንደተናገሩት  ከቅርብ ጊዜዓት ወዲህ የተፈጠረው የህውሃት እና የጊዜዓዊ አስተዳደሩ አለመግባባት መቋጫው “የፌድራል መንገስት ጣልቃ በመግባት ውሳኔ ማሳለፍ ብቻ ነው” ብለዋል፡፡

ሁለቱ አካለት ችግራቸውን  በውይይት ለመፍታት ያላቸው ቁርጠኝነት አናሳ ነው ያሉ ሲሆነ የሁለቱ አካላት አለመግባበት  የሚያመጣው ውጤት ህዝቡን ካለበት ሁኔታ በላይ  ሊጎዳው እንደሚችልም  ስጋታቸውን ነግረውናል፡፡

በመሆኑም  ህውሃትም ይሁን የክልሉ ጊዜዓዊ አስተዳደር   የገቡበትን አለመግባባት ለመፍታት ብቸኛው አማራጭ የፌድራል መንገስቱ ጣልቃ ገብነት ነው ሲል የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ገ/ጊዮርጊስ ግደይ ነግረውናል፡፡

ህወሃት እና ጊዜዓዊ አስተዳደሩ  በቅርቡ እንደተሸማገሉ በሰፊው  ቢገለጽም  ህውሃት ግን ውይይት እንዳደረጉ ቢያምኑም የተለወጠ ነገር እንደሌለ መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡

በአንጻሩ ደግሞ  ጊዜዓዊ አስተዳደሩ ትላንት ባወጣው መግለጫ “ህውሃት መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ጥረት ትትእያረገ ነው” ሲል መክሰሱ ይታወሳል፡፡

ለአለም አሰፋ

ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የቤተሰብ ጉዳይ አማካሪ ተቋማት በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የምክር አገልግሎችን እየሰጡ ስለመሆናቸው የሚከታተል ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት እንደሚዘረጋ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ። 


የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቤተሰብ የምክር እና የምክክር አገልግሎት ሰጪ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ እየመከረ ነው። 

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ የቤተሰብ ጉዳይ አማካሪ ተቋማት በተቀመጡ መስፈርቶች የምክር አገልግሎችን በመስጠት ማህበራዊ መሰረቱ ጠንካራ የሆነ ማህበረሰብ መፍጠር ላይ አተኩረው መስራት እንደሚገባቸው አስሳበዋል። 

የቤተሰብ ጉዳይ አማካሪ ተቋማት የምክርና የምክክር አገልግሎት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የመሰጠት ግዴታ አለባቸው ያሉት ሚንስትር ዴኤታዋ ይህንን የሚከታተል ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት እንደሚዘረጋም ተናግረዋል። 

በቁጥጥሩ ወቅት ተቋሙ ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት በማይሰሩ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም አስጠንቅቀዋል። 

ቤተሰብ ትውልድ የሚገነባበት የህብረተሰብ መሰረታዊ ተፈጥሯዊ መነሻና ትልቅ ማህበራዊ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል።

ቤተሰብ ችግር ላይ ከወደቀ ጉዳቱ የህብረተሰብ ብሎም የሀገር ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የቤተሰብ መሰረት እንዳይናድ የችግሩ ምንጭ በአግባቡ በመለየት በምክርና ምክክር መፍታት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

ቤተሠብ እንደሕብረተሰብ ዋነኛ መሠረት አቅሙ እንዲጎለብት፣ ደህንነቱ እንዲጠበቅና ሚናውንም በአግባቡ መወጣት እንዲችል ልዩ ጥበቃና ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች የቤተሰብ ደህንነት አደጋ ላይ የሚወድቅበትና አባላቱ የሚበተኑበት ችግር ሲፈጠር የቤተሰብ ጉዳይ አማካሪ ተቋማት ወደ መደበኛ ህይወታቸው ለመመለስ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ ሲሉም ተናግረዋል። 

የምክርና የምክክር ሂደት የተቀመጡ መስፈርቶች እና የታወቁ ቅደም ተከተሎች ያሉት በመሆኑ ያን መከተልና መተግበር ውጤታማ ያደርጋልም ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሩበን አሞሪም በካሪንግተን ተገኝተው ከተወያዩ በኋላ ሩድ ቫኔስትሮይ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እንደሚለያይ ታውቋል!

ባለፉት ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት የመራው ሩድ ቫን ኔስትሮይ በቀጣይ ከክለቡ ጋር እንደሚለያይ ተዘግቧል።

ሩድ ቫን ኔስትሮይ ባለፈው ክረምት የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን የቀያዮቹን ሴጣኖች የአሰልጣኝ ቡድን አባላት መቀላቀሉ ይታወቃል።

ቫን ኔስትሮይ የኤሪክ ቴንሀግን መሰናበት ተከትሎ ዩናይትድን በአራት ጨዋታዎች ሲመራ ሶስቱን በአሸናፊነት ተወጥቶ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ለሩድ ቫኔስተሮይ
አሁንም ለወደፊትም የማንቸስተር ዩናይትድ ሌጀንድ ሆኖ ይቀጥላል።

ለነበረው አስተዋጽኦ እና ስራውን ለከወነበት መንገድ ምስጋናችንን እንገልጣለን። ኦልድ ትራፎርድ እርሱን ለመቀበል ሁልጊዜም ዝግጁ ናት።

አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በካሪንግተን ተገኝተው ከተነጋገሩ በኋላ ቫን ኔስቶሮይ እንዲቀላቀላቸው እንደማይፈልጉ ማሳወቃቸው ተነግሯል።

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ወደ ዉጪ ሄደዉ ለሚታከሙ ሰዎች አስቀድሞ የመረጃ እና ክትትል አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡

ፎርቲስ ሆስፒታል በኢትዮጵያ የመጀመርያውን የመረጃ ማዕከሉን ወደ ዉጪ ሄደዉ መታከም የሚፈልጉ ዜጎች በተደራጀ መረጃ ህክምናቸዉን እንዲከታተሉ በማሰብ መክፈቱን በኢትዮጵያ የፎርቲስ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ማህደር ሐይለስላሴ ተናግረዋል፡፡

ሆስፒታሉ በኢትዮጵያ የመረጃ ማዕከሉን የከፈተው የውጭ ህክምና የታዘዘላቸው ተገልጋዮች ተጨባጭ የሆነ መረጃ አግኝተው ህክምናቸውን እንዲከታተሉ ለማስቻል መሆኑንም ነዉ የተናገሩት፡፡

ይህ የመረጃ ማዕከል ታካሚው ለህክምና ከመሄዱ በፊት ህክምናውን ከሚያደርግለት ሀኪም ጋር በቪዲዮ ስለህክምናው ሂደት ቀድሞ ማማከር የሚችልበት መሆኑም ተገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ታካሚዎች ምን ያህል ወጪ ማውጣት እንዳለባቸው እና ሙሉ የህክምና ሂደቱ ምን እንደሚመስል ከጉዞው በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የማዕከሉ ዶክተሮች የምክር አገልግሎት እንደሚሰጣቸውም ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

የመረጃ ማዕከሉ ውጪ ሄደው ለሚታከሙ ታካሚዎች ቪዛቸውን ማመቻቸት፣የሚያርፉበትን ሆቴል አስቀድሞ መያዝን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥም ነው የተገለጸው።

ሆስፒታሉ ታካሚዎች የውጭ ህክምናቸውን ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱም የህክምና ክትትል እንደሚያደርግላቸውም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ማዕከሉ ለኢትዮጵያዊያን ዶክተሮች በህንድ ተከታታይ ስልጠናዎች የሚሰጥም ሲሆን፤ ለታካሚዎችም እንደህክምና አይነታቸው ነጻ የማማከር አገልግሎት ለ6ወራት ያክል ለመስጠት ማሰቡንም ዶ/ር ማህደር ተናግረዋል።

ፎርቲስ በህንድ የሚገኝ ሆስፒታል ሲሆን፤በአገሪቱ ከ30 በላይ የተለያዩ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች አሉት፡፡

ሆስፒታሉ የልብ ህክምና፣የካንሰር እና የተለያዩ ንቅለ ተከላ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የንጥረ ነገር አጠቃቀም ችግር / Substance use disorder

በቅርቡ የተጠና ጥናት እንዳመለከተው በአለማችን ላይ በአመት 11.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በዚህ ችግር ምክንያት ለሞት እንደሚዳረጉ ነው፡፡

እንዲሁም 2 በመቶ የሚሆኑ የአለማችን ሰዎች የችግሩ ሰለባ እንደሚሆኑም መረጃው ያሳያል፡፡

በጉዳዩ ላይም ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የስነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት አቶ ልዑል አብርሀም ናቸው፡፡

Substance use disorder /የንጥረ ነገር አጠቃቀም ችግር ምንድን ነው?

አንድ ሰው በተለያየ ጊዜያቶች ለረጅም ጊዜ የተለያ አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም እራሱን ለከፋ የጤና ሁኔታ የሚዳርግ ከሆነ Substance use disorder /የንጥረ ነገር አጠቃቀም ችግር አለበት እንላለን ይላሉ፡፡

ሰዎች ይህ ችግር አለባቸው የሚባለው 3 ነገሮችን ሲያሳይ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

1. በቋሚነት የሚያደርገው ከሆነ
2. ለማቆም በሚሞክርበት ጊዜ የሚቸገር ከሆነ
3. በማቆሙ ምክንያት የሚመጡ የህመም ስሜቶች ካሉ

መንስኤው ምንድን ነው?

- የጓደኛ ተፅዕኖ
- አካባቢያችን ላይ አጋላጭ ሁኔታዎች ካሉ
- ብዙ ትርፍ ሰአት መኖር (ስራ ማጣት)
- አንዳንዴ ደግሞ በቤተሰብ ይሄ ችግር ካለ ሊተላለፍ ይችላል፡፡

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

- የምንጠቀመውን ነገር ሰአት ጠብቆ የፍላጎት ስሜት መሰማት
- ንጥረ ነገሩን ካልተጠቀምን የመነጫነጭ እና የድብርት ስሜት መኖር
- ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑን እየጨመሩ መሄድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የሚያመጣው ተፅዕኖ ምንድን ነው?

- እራስን መጠራጠር መጀመር
- ሀላፊነትን ለመቀበል መቸገር
- የቤተሰብ መረበሽ
- የኢኮኖሚ ውድቀት ሊያስከትል ይችላል፡፡

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

- ለማቆም የቆራጥነት ስሜት እንዲኖር ማድረግ
- ያለበት ደረጃ ከፍተኛ ከሆነ ንጥረ ነገሩን ከሰውነቱ እንዲወጣ ማድረግ
- በማገገሚያ ማዕከላት ለተወሰነ ጊዜ መቆየት
- የስነ ልቦና ህክምና መውሰድ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ነገር ግን ለዚህ ችግር ትልቁ ህክምና የሚጀምረው ከራሱ ከግለሰቡ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

በመጨረሻም ሱስ እንደማንኛውም በሽታ ስለሆነ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ተገቢውን ህክምና ማግኘት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ሐመረ  ፍሬው

ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ በሐዋሳ ከተማ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት የጨፌ ቆንቦዬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የማስፋፈያ ፕሮጀከት በዛሬው እለት አስመረቀ

ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ በሐዋሳ ከተማ የጨፌ ቆንቦዬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የማስፋፈያ ፕሮጀከት ዛሬ ኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም አጠናቅቆ ለማሕበረሠቡ አስረክቧል።

የቢጂአይ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ኸርቬ ሚልሃድ፤የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ የተሰራው በስድስት ወራት ውስጥ ነው ብለዋል።

ይህ የትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጄክት በአንድ ፈረቃ ከ 525 በላይ አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንዲያስተምር ይረዳል ብለዋል።

ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ 70 ሚሊዮን ብር በመመደብ በ2024 በአከባቢ ልማት፣ጤና እና የትምህርት ቤት ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ተብሏል ።


የሃዋ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው፤ዛሬ "በሐዋሳ ከተማ የተመረቀው ይህ ትምህርት ቤት የመጪውን ትውልድ ለመቅረፅ፣ የት/ቤቶችን አቅም ከማሳደግ አንፃር ሚናው የላቀነው ብለዋል።

በተጨማሪም በቀጣይ ትምህርት ቤቱን ሌሎች አስፈላጊ ለመማር ማስተማር የሚረዱ መሰረተ ልማቶቹን ለሟሟላት ይሰራል ብለዋል።

ቢጂአይ የኮምቦልቻና የዘቢዳር ት/ቤቶችን ግንባታቸው የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ለማህበረሰቡ የሚያስከረከብ ይሆናል ተብሏል ።

ኩባንያው በማህበረሰባዊ ኃላፊነት ረገድ አዎንታዊ ለውጥ የማረጋገጥ ተልዕኮውን በማስቀጠል መሠል የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶችን በተለያዩ የሃገራችን ከተሞች ላይ የሚቀጥል ይሆናል መባሉን ሰምተናል፡፡

ልኡል ወልዴ

ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አሕመድ ሺዴ ገልጸው ፡፡ ይህ የሆነውም ፍራንኮ ቫሉታ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ከፍ ብሉ በመታየቱ ነው ብለዋል፡፡

ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ ማድረጉን የተናሩት አቶ አሕመድ ሺዴ ነገር ግን ፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራው በመደበኛውና በትይዩ ገበያው መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ተቀራራቢ በማድረጉ የፍራንኮ ቫሉታ እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አክለውም መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉን እና በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም የንግድ ባንኮች ለመረሰታዊ ሸቀጦች የሚሆን በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዳላቸው ጠቅሰው በውሳኔው መሰረትም ከውጭ የሚመጡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ ብቻ እንዲገቡ መወሰኑንና ይህም ወደ ተግባር መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡

መንግስት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በጋምቤላ ክልል በሳምንት ከሶስት ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ይያዛሉ ተባለ፡፡

በክልሉ በተለያየ ጊዜ የሚከሰት ጎርፍ ለወባ ወረርሺኝ ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓል መባሉንም ሰምተናል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የጋምቤላ ክልል የወባ ፕሮግራም ባለሙያ የሆኑት አቶ በርሄ ካልአዩ፤ በሳምንት ዉስጥ ከሶስት ሺ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ እየተያዙ እንደሆነ ነግረዉናል፡፡

በዚህም በክልሉ 81ሺህ6 መቶ65 ሰዎች ወባ ተገኝቶባቸዋል ነዉ ያሉት።

ከፍተኛ የወባ ጭማሪ መታየቱን የሚያነሱት አቶ በርሄ፤ ማንኛዉም የትኩሳት ምልክት ያለበት ሰዉ ወደ ጤና ተቋማት ሄዶ የወባ ምርመር እንዲያደርግ ስራዎችን እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡

ወባ ከተገኘበትም መድሀኒት እንዲጀምሩ እየተደረገ መሆኑንም ነዉ አቶ በርሄ የነገሩን።

የመድሀኒት አቅርቦት አለ የሚሉት ባለሙያዉ፤ ችግር የሆነዉን ጎርፍ መሆኑንም ያነሳሉ፡፡

ለወባ ትንኝ መራባት ትልቁ ጉዳይ ጎርፍ ነዉ ያሉ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ ወረዳዎች በጎርፍ ተጠቂ መሆናቸዉንም አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም ከዚህ በኋላ መስፋፋቱ ከጨመረ ሁኔታዉ የከፋ ነዉ ያሉት አቶ በርሄ፤ የሚመለከታቸዉ አካላት በክልሉ ያለዉን የወባ ወረርሽኝ ለመቀነስ አስፈላጊዉን ድጋፍ ቢያደርጉልን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በካፒታል ገበያውን እና በኢንቨስትመንቱ ዙሪያ የተሻለ አቅም ለመፍጠር ያለመ አለም አቀፍ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

ይህ አለም አቀፍ ጉባኤም ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀን በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይም የብሔራዊ ባንክ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚዎች በመገኘት ንግግር አድርገዋል።

በተመሳሳይ ከውጪ ደግሞ የአለም ባንክ የአፍሪካ ልማት ባንክና ዩኤንዲፒ(UNDP) ጨምሮ ተወካዮች በመክፈቻው ተገኝተዋል።

የብሄራዊ ባንክ ገዢው ማሞ ምህረቱ ጉባኤው ለመጀመር ከጫፍ የደረሰውን የካፒታል ገበያው በቁጥጥር ረገድ እንዲጠነክር የሚያደርግ ይሆናል ብለዋል።


የገንዘብ ሚኒስትር ዴታው ዶር እዮብ ተካልኝ በበኩላቸው በጉባኤው መክፈቻው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አሁን ላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንዸሚገኝ አንስተው በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ደግሞ ግቡን እየመታ ይገኛል ብለዋል።

ሚኒስትር ዴታው በተጨማሪም እንደዚህ አይነት ጉባኤዎች ጤናማ የፋይናንስ ስርአት እንዲኖር ያስችላልም ብለዋል።


የካፒታል ገበያው ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተህክሉ በበኩላቸው በጉባኤው የሚነሱት ሀሳቦችና ልምዶች ለገበያው ጥንካሬና ቁጥጥር ሁነኛ ግብአት ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግረዋል።

ለዓለም አሰፋ

ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ቪሳም ቤን ዬደር በጾታዊ ጥቃት ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ በኋላ የታገደ ቅጣት ተቀብሏል።

የቀድሞው የሞናኮ አጥቂ በኒስ ፍርድ ቤት ቀርቦ በተሽከርካሪ ተሳፍሮ ሳለ የፆታዊ ጥቃት ክስ ቀርቦበታል።

አቃቤ ህግ በ 34 ዓመቱ የእግር ኳስ ተጫዋች ላይ የአስራ ስምንት ወራት የእስር ቅጣትን ጨምሮ የሁለት አመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ጠይቋል።

እንደ አርኤምሲ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ቤን ይደርን በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ብሎ ጥፋተኛ አድርጎታል እና በቅድመ ሁኔታ የሁለት አመት የነጻነት ቅጣት ወስኖበታል። የቀድሞ የሞናኮ ተጨዋች ለተጎጂው የሞራል ጉዳት 5,000 ዩሮ ካሳ እንዲከፍል እና 1,500 ዩሮ የሚደርስ የህግ ወጪን እንዲመልስ ይጠበቅበታል።

በተጨማሪም የፖሊስን ትዕዛዝ ባለማክበር ቤን ያደር የመንጃ ፈቃዱን ለስድስት ወራት ተሰርዟል እና 5,000 ዩሮ ተቀጥቷል።

እ.ኤ.አ. በነሀሴ 2023 ቤን ዬደር "አስገድዶ መድፈር፣ የአስገድዶ መድፈር ሙከራ እና የፆታዊ ጥቃት" ተመሳሳይ ክስ እንደገጠመው ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው።

በወቅቱ በ900,000 ዩሮ ዋስ ተለቀዋል። በተጨማሪም በዲሴምበር 27, እግር ኳስ ተጫዋቹ በቀድሞ ሚስቱ ላይ የሚደርሰውን ዛቻ እና የስነ-ልቦና ጥቃትን በተመለከተ ለፍርድ ይቀርባል

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዘንድሮ የብሔር ብሄረሰቦች ህዝቦች ቀን  በአርባምንጭ ከተማ ይከበራል ተባለ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፤ የኮምንኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን  ፤የዘንድሮ የብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች  ቀን’’የሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት ’’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዉናል፡፡

የዘንድሮ  የብሔር ብህሄረሰቦች ህዝቦች ቀን  ለ19ኛ ጊዜ በአርባምጭ ከተማ እንደሚከበር ነግረዉናል።

ወ/ሮ ሰናይት በዓሉን ለማክበር ወደ አርባምንጭ የሚመጡ  እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር እንዲሁም ከአከባቢዉ ማህበረሰብ ጋር ዉይይቶች መደረጋቸዉን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ሀላፊዋ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብለዉ በተለዩ ሆቴሎች፤በበዓሉን ለመታደም  በሚመጡት እንግዶች ላይ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ፤በአገልግሎት ጥራትና ይዘት እንዲሁም በሚሰጡት መስተንግዶ ዙሪያ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርጉና እርምጃ የሚወስዱ ኮሚቴ  ተዋቅሯል ብለዋል፡፡

የበዓሉ  አላማ በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው  የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፖብሊክ ህገ መንግሥት የጸደቀበት ቀንን ምክንያት በማድረግ ሁሉም በባህሉ አምሮ ደምቆ በእኩልነት የሚያከብረዉ ነዉ ፡፡

በመጨረሻም በበዓሉ አገር አቀፍ ሲምፖዚየሞች፣ ኤግዚቢሽኖች፣ ስልጠናዋች እና የባህል ልውውጦች  እንደሚካተቱ ተገልጿል ።

ልዑል ወልዴ

ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሳዑዲ አረቢያዉ ልዑል ማሐመድ ቢን ሰልማን በጋዛ እና በሊባኖስ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቁ።

ቢን ሳልማን ይህን ጥሪ ያቀረቡት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በአረብ ሊግ እና በእስልምና ትብብር ድርጅት የጋራ ጉባዔ ላይ ነው።

በጉባኤዉ መክፈቻ ላይ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እስራኤል በፍልስጤም ላይ የምትሰነዝረዉን ጥቃት እንድታቆም ቢን ሰልማን ጠይቀዋል።

ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረዉ የእስራኤል-ሃማስ ጦርነትን እና አካባቢዉ ላይ እየተባባሰ የመጣዉን ቀዉስ በተመለከተ ሪያድ ላይ የተሰበሰቡት የአረብ እና የሙስሊም መሪዎች አዲስ ለተመረጡት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ መልዕክት ለመላክ እድል እንደሆነም ተደርጎ ታይቷል።

«ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እስራኤል በፍልስጤምና በሊባኖስ ወንድሞቻችን ላይ የምትፈፅመዉን ጥቃት በአፋጣኝ ታቁም።

እንዲሁም እስራኤል የኢራንን እስላማዊ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነት እንድታከብር እና ግዛቶቿን ከማጥቃት እንድትቆጠብ እንዲያደር እና ዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን የማስጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናሰማለን።» ብለዋል፡፡

የአረብ ሊግ ከዓመት በፊት ተመሳሳይ ስብሰባዎችን በሪያድና በጅዳ ያካሄደ ሲሆን እስራኤል በጋዛ ላይ የፈፀመችው ጥቃት በጽኑ አውግዟል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

አባቱ መረቀ

ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በተሸከርካሪ አደጋ በ27 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የካፋ ዞን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የካፋ ዞን ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ዳዊት ደሳለኝ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን እንደገለፁት መነሻውን ቴፒ በማድረግ ወደአዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ሀበሻ ዘመናዊ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ኮድ 3-98954 ኢት ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከማለዳው 12፡30 በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ የብጦ ቀበሌ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰ አስታውቀዋል፡፡

በአደጋው በ16 መንገደኞች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው 13ቱ ሴቶች ሲሆኑ በ11 ተሳፋሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት ኢንስፔክተር ዳዊት ተጎጂዎች ቦንጋ ገብረፃዲቅ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

አደጋው የደረሰው መንገዱ ጠመዝማዛ መሆኑን አመልክተው የአደጋውን ምስኤ የትራፊክ ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ አመልክተው ተጎጂዎችን በማንሳት ወደ ህክምና በመውሰድ የተባበሩ የቀበሌው ነዋሪዎችን እና የጊምቦ ወረዳ ፖሊሶችን አመስግነው አሽርካሪዎች ፍጥነታቸውን ቀንሰው እንዲያሽረክሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡ ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽ ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ሁሉን ያሳተፈ ውይይት በአስቸኳይ እንዲደረግበት ተጠየቀ፡፡

በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይት ሳይደረግበት ወደ ቋሚ ኮሚቴ የተመራው የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የሕዝብንም ሆነ የባለድርሻ አካላትን ድምፅ በተገቢ ያለማካተቱ ተተችቷል፡፡

በሚዲያ ሕጉ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ አሳሳቢ ይዘት ላይ ከጋዜጠኞች የሙያ ማህበር እና ከሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በኩል መግለጫ ወቷል፡፤

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 19/2017 በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን ያስታወሰው መግለጫው

፤- በአዋጁ ከለላ ተሰጥቷቸው የነበሩ የቁጥጥርና ሚዛን መጠበቂያዎች በረቂቅ አዋጁ ሊሻሩ የሚችሉ መሆናቸው በእጅጉ እንደሚያሳስበው

፤- የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በሥራ ላይ የሚገኘውን የመገናኛ ብዙኃን ሕግ በርካታ አንቀፆች ይዘትና መንፈስን የሚቀይር በመሆኑ

፤-ረቂቅ ማሻሻያው የአካሄድና የይዘት ግድፈቶች በስፋት የሚስተዋሉበት በመሆኑ፤

፤- በረቂቁ ማሻሻያ ላይ ምንም ዓይነት የሕዝብ ውይይቶች ባለመከናወናቸው የሲቪል ማኅበረሰቡን፣ የሚዲያ ሙያተኞችን እንዲሁም የሌሎች መብቶች ተሟጋቾችንና የማኅበረሰብ ድምፆች እንዳይሰሙ የሚያደርግ በመሆኑ

፤- ማሻሻያውን ለማዘጋጀት የተሔደበት መንገድ ግልጽነትና አሳታፊነት የጎደለው በመሆኑ እንዲሁም የረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት በገለልተኛ አካል በተሠራ ጥናት ስለመለየቱ የቀረበ ማስረጃ ባለመኖሩ

ጉዳዩ አስችኳይ መፍትሔም ሊፈለግለት እንደሚገባው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበራቱ በወጡት የጋራ መግለጫ አሳስበዋል፡፡

ስለሆነም

፤-የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ በጥናት የተደገፈ ማስረጃ እንዲቀርብበት
፤- በባለድርሻ ወገኖች ሰፊ ውይይትና መግባባት እንዲደረስበት፣
፤-በጥናቱ እና ውይይቱ መሠረት ማሻሻያ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑ ከታመነበት፣ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ በምክር ቤቱ ከመፅደቁ በፊት ትርጉም ያለውና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት እንዲከናወን፣
፤- የውይይቶቹ ግብዓቶች በአግባቡ ተካትትው ረቂቁ እንዲዳብር፣ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ መንፈስ ዴሞክራሲን ከማስፈንና የመገናኛ ብዙኃንን ነጻነትን ከማረጋገጥ አንፃር የነበረውን አስቻይ የሕግ ማዕቀፍ የሚንድና ወደኋላ የሚጎትት እንዳይሆን ከታች ስማቸው የተዘረዘሩ ማህበራት በአጽንኦት ጠይቀዋል፡፡

1) የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD)
2) የህግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች (LHR)
3) የኢትዮጵያ ሰራተኞች መብቶች ተሟጋች (ELRW)
4) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (EHRCO)
5) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC)
6) የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅቶች ጥምረት (NEWA)
7) የኢትዮጵያ ሴቶች መብቶች ተሟጋች (EWRA)
8) የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር (EWLA)
9) ሴታዊት (Setaweet)
10) ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ (AHRE)
11) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር (EMMPA)
12) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት (CEHRO)
13) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማህበር (EMWA)
14) ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ (HRFE)


ህዳር 03 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዳኛ ዴቪድ ኩት በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን የተንቀሳቃሽ ምስል ቅጂ ተከትሎ መታገዳቸው ተገልጸ።

ዋና ዳኞው በተሰራጨው የቪዲዮ ቅጂ ሊቨርፑልን እና የቀድሞ አሰልጣኛቸውን የርገን ክሎፕን ሲሳደቡ እና ሲተቹ ተስተውለዋል።

አሁን ላይ የፕርሚየር ሊጉ ፕሮፌሽናል ዳኞች ማኅበር የ 49ዓመቱ ዳኛ ዴቪድ ኩት ማገዱን አስታውቋል።

ማህበሩ በዳኛው ላይ የሚያደርገውን ሙሉ ምርመራ መቀጠሉን እና በቀጣይ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የፖለቲካ ፓርቲዎችን የአመራር አቅም ለማሳደግ ያለመ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ

የጋራ ምክርቤቱ ስምምነቱን ያደረገው ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር እንደሆነም የጋራ ምክረ ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ለጣቢያችን ተናግረዋል

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢው አቶ ደስታ ዲንቃ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የመግባቢያ ስምምነቱ የፖለቲካውን የፖለቲከኛውን እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቅማቸውን እንዲያሳድጉ እንደሚረዳም ነግረውናል፡፡

ፓርቲዎችም በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚው የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እድል የሚያመቻች እንደሆነ የተነሳ ሲሆን የነበረውነን የፖለቲካ ባህል ለመቀየር እና ለማዘመን ታሳቢ የተደረገ ስምምነት እነደሆነም አቶ ደስታ ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዛዲግ አብርሃ እና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ ፈርመውታል።

ለአለም አሰፋ

ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ተቋም ኃላፊ ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ ኢራንን ይጎበኛሉ ተብሏል

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኑክሌር ቁጥጥር ተቋም ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ በሚቀጥለው ረቡዕ ኢራንን እንደሚጎበኙ ፣ በማግስቱም ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ምክክር እንደሚጀምሩ የመንግስት ዜና አውታሮች ዘግበዋል።

የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቋም ሃላፊ አከራካሪ በሆነው የኑክሌር መርሐ ግብር ዙሪያ ለመወያየት በመጪዎቹ ቀናት ወደ ኢራን ሊያቀኑ እንደሚችሉ ፤ ከተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋርም በትብብር ለመስራት እንደሚጠብቁ ረቡዕ ዕለት ተናግረዋል።

ቴህራን ከተቋሙ መርማሪ ቡድን የተላኩ የዩራኒያም ማበልጸግ ባለሙያዎችን መከልከሏ ፣ለዓመታት ባልተገለጹ ስፍራዎች የተገኙ የዩራኒየም ናሙናዎችን ምንጭ ለመግለጽ አለመስማማቷን ተከትሎ በተቋሙ ፣ በኢራን እና በምዕራብ ኃይላት መካከል ለረጅም ጊዜያት የቆዩ ችግሮች ተፈጥረዋል።

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአውሮፓዊያኑ የ2015ቱን፣ ኢራን የዩራኒየም ማብለጸግ እንቅስቃሴዋን እንደትቀንስ ከዓለም ኃያላን ጋር የገባችውን ስምምምነት በ2019 መሰረዛቸውን ተከትሎ ፣ ሀገሪቱ የኑክሌር እንቅስቃሴዋን አጠናክራለች ።

ቴህራን አቶሚክ ቦምብ ለመስራት ወደ ሚያስፈልገው 90 በመቶ የተጠጋ ፣60 በመቶ የንጥርነት አቅም ላይ የደረሰ ዩራኒየም እያበለጸገች መሆኑ ተሰምቷል ።

በዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቋም መሰረት ሀገሪቱ የማበልጸግ ሂደቷን ከቀጠለች አራት ያህል የኑክሌር ቦምቦችን ለማምረት የሚያስችል ከበቂ ከፍ ያለ የበለጸገ ዩራኒየም ይኖራታል።

ኢራን ለሲቪል ሃይል ፍጆታ ብቻ ዩራኒየምን እያበለፀገች መሆኑን በመግለጽ የኒውክሌር ቦምብ ፍላጎት እንደሌላት ስታስተባብል ቆይታለች ዘገባው የሮይተርስ ነው ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹ ቁጥር ከ 6 ሚሊየን በላይ መድረሱን ገለጸ፡፡

የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ወደ አገር ዉስጥ ገብቶ ስራ ከጀመረ በጥቅምት ወር 2ኛ ዓመቱን የያዘ ሲሆን፤የደንበኞቹ ቁጥርም 6.1 ሚሊየን ደርሷል ብሏል፡፡

ይህም በመስከረም ወር 2023 ከነበረዉ የደንበኞች ዉጥር የ47.3 በመቶ ጭማሪ እንዳለዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የ07 ኔትዎርክ እና አገልግሎት 46 በመቶ ሽፋን እንዳለዉ የተነሳ ሲሆን፤ ባለፈዉ ዓመት 12 ወራት በፊት 30 በመቶ ተደራሽ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

በመሰረተ ልማት ግንባታ ዙሪያ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸዉ የተገለጸ ሲሆን፤ በመላዉ አገሪቱ 3ሺህ የኔትዎርክ ሳይቶች መሰራታቸዉ ተነግሯል፡፡ ይህም ካለፈዉ ዓመት አንጻር የ 50 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የኤም-ፔሳ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 8.3 ሚሊየን መድረሱ ሲገለጽ፤ በመስከረም ወር 2023 ከነበረዉ የ1.2 ሚሊየን ተጠቃሚ ቁጥር 6 ዕጥፍ የበለጠ መሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በኤም-ፔሳ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ በኩል 6.4 ቢሊየን ብር ተንሸራሽሯል ነዉ የተባለዉ፡፡

የ4ጂ የዳታ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከፍ ማለቱ ሲገለጽ፤ አንድ የሞባይል ዳታ ተጠቃሚ በወር እስከ 6.6 ጌጋባይት እንደሚጠቀምም ተገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel