ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

ህፃናት የሚሉት አላቸው፤እናዳምጣቸው" በሚል መሪ ቃል የህፃናት ቀን በነገው ዕለት ይከበራል።

በዓለም ለ35ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ አለም አቀፉ የህፃናት ቀን እንደሚከበር የአዲስ አበባ ሴቶች፣ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።

ዕለቱ ሲከበር በአራት ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የገለፁት የቢሮው ምክትል ሃላፊ እና የህፃናት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ ናቸው።

እነዚህ አራት ጉዳዮች ተብለው የተዘረዘሩትም የህፃናት መብቶችን ማሳደግ፣ አለምአቀፋዊ ተግዳሮቶችን መሞገት፣ የመንግስት እርምጃዎችን ማበረታታት እና ህፃናትን ማብቃት የሚሉ ናቸው።

ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች አብዛኛውን ጊዜ በቅርብ ቤተሰብ የሚከሰቱ መሆናቸውን ያነሱት በቢሮው የህፃናት መብት ደህንነት እና ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አንዱአለም ታፈሰ ናቸው።

ዳይሬክተሩ ከቤት ውጪ በትምህርት ቤቶችም ጥቃቶች መበራከታቸውን በማንሳት ፤ በ2016 ዓ.ም በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በመዲናዋ ከሚገኙ ከ1 ሺህ በላይ የመንግስት ት/ቤቶች አንዱም ከህፃናት ጥቃት ነፃ አይደለም ስለመባሉም ተናግረዋል።

በመዲናችን በዚህ ሩብ ዓመት ከ15ሺህ 6መቶ በላይ ህፃናት የልደት ምዝገባ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የዓለም የህፃናት ቀን ነገ ህዳር 11 ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

እስከዳር ግርማ

ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በ6 አመትውስጥ በኢትዮጵያ  ከ1 ሚሊየን በላይ ቤቶች ተገንብተዋል ተባለ

በኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ  ባሉት ስድስት አመታት ከአንድ ሚሊየን በላይ ቤቶች መገንባታቸውን መንግስት ገለፀ።

የኢትዮጵያን ያለፈውን የኢኮኖሚ ሁኔታ እና የአሁኑ የኢኮኖሚ ደረጃ እየተገመገመ ባለበት ወቅት የቤት ችግርን ለመፍታት ከአንድ ሚሊየን በላይ ቤቶች ተገንብተዋል ተብሏል።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶር ፍፁም አሰፋ ባቀረቡት ንግግር ላይ ጣቢያችን እንደሰማው በ18 አመት ውስጥ ወደ 400 መቶ ሺ ኮንዶሚኒየም ብቻ መገንባታቸውን ያስታወሱ ሲሆን፤

በስድስት አመት ውስጥ ግን  ከግሉ ዘርፍ ጋር በቅንጅት በመሆን ከ1 ሚሊየን በላይ ቤቶች ተገንብተዋል ብለዋል።

በዚህም ወደ 71 ሺ የሚጠጉት ቤቶች ግንባታቸው የተደረገው በመንግስት ድጋፍ መሆኑን ገልፀው የተቀረው ግን በግሉ ዘርፍ ትብብር ነው ይለዋል።

የቤቶቹ የግንባታ  እድገት የታየውም በግሉ ዘርፍ ጥምረት መሆኑም ተገልጿል።



ለዓለም አሰፋ

ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር  ጠቅላላ ጉባኤውን በማድረግ አዳዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት  መምረጡን ገለፀ።

በዚህም ክላዊው የሆነው የከፋ አረንጋዴ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አየለ የጋራ ምክር ቤቱን ለሁለት ዓመታት በሰብሳቢነት እንዲመሩ መመረጣቸውን ሰምተናል።

የቀድሞው የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ደስታ ዲንቃ ደግሞ ፀሀፊ በመሆን ተመርጠዋል።

በሌላ በኩል አንድ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ አባል ለምርጫው ጥቆማ ሳይደረግ፣ ምርጫም ውስጥ ሳይገቡ በቀጥታ የሥራ አስፈፃሚ አባል ሆነው እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የጋራ መድረክ ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሑድ ህዳር 7 እና 8  ለሁለት ቀናት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤን ባካሄደበት ጉባኤው ነው ምርጫውን የተከናወነው።

የጋራ ምክር ቤቱ በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው የሥራ ዘገባ ቀርቦለት መርምሮ በመወያየት፤ ቀጣይ የሥራ ዕቅድ ላይ በመነጋገር እንዲሁም የጋራ ምክር ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ማጽደቁንም የጋራ ምክር ቤቱ ለጣቢያችን ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የምክር ቤቱ አባላት የሆኑ ስድስት ፓርቲዎች አስቀድመው ምርጫው ትክክል አይደለም፤ በሚል ቅሬታ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።

በዚህ ጉዳይም የቀድሞዎ የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እና የአሁኑ ፀሀፊ የሆኑት አቶ  ደስታ ዲንቃ ለጣቢያችን እንደተናገሩት  ምክር ቤቱ በንግግር የሚያምን ቢሆንም ፓርቲዎች ግን በዚህ አለማመናቸውን አሳይተዋል ሲሉ ነግረውናል።

በመሆኑም ምክር ቤቱ በመመሪያ እና ደንቡ መሰረት ያራሱን ዉሳኔ ይወሰናል ብለውናል።

ለዓለም አሰፋ


ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የማሕፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በአገር አቀፍ ደረጃ መጀመሩን  የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ዛሬ የተጀመረው የክትባት ዘመቻ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሕጻናትን ለማዳረስ ያለመ ነው። 

በአማራ ክልል ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት እንደሚከተቡ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አመልክቷል።

ክትባቱ ባሕር ዳር ከተማ ድል ችቦ አጠቃላይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ሲጀመር በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትሯ የክትባት ፕሮግራሞች አማካሪ አቶ ዮሐንስ ላቀው ተገኝተው ክትባቱ ዕድሜያቸው ከዘጠኝ እስከ14 ለሆነ ሕፃናት ለአምስት ተከታታተይ ቀናት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።


በሀገር ደረጃ ዘመቻው በሁሉም አካባቢዎች መጀመሩን በመጠቆምም፣ 7,500,000 ሕፃናትን ለመከተብ መታቀዱንም አመልክተዋል።

የማሕፀን በር ካንሰር በየዓመቱ የስምንት ሺህ እናቶችን ሕይወት እንደሚነጥቅ የገለጹት አቶ ዮሐንሰ ክትባቱን በመውስድ ወጣት ሴቶችንና እናቶችን ከመሞት ማትረፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሳውድ አረቢያ በያዝነው የፈረንጁቹ ዓመት ከአንድ መቶ በላይ የውጭ ሃገራት ዜጎችን በሞት መቅጣቷ ተነገረ።

በሞት ከተቀጡት መካከል ሰባት ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል።

የፈረንሳይ የዜና ወኪል AFP እንደዘገበው ከኢትዮጵያውኑ በተጨማሪም 21 የፓኪስታን፣ 20 የየመን፣ 14 የሶርያ፣ 10 የናይጀሪያ፣ ዘጠኝ የግብፅ እና ስምንት የዮርዳኖስ ዜጎች የሞት ቅጣቱ ተፈጽሞባቸዋል።

በቅርቡም ማለትም  ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ ዕለት የሞት ቅጣት አደንዛዥ ዕጽ በሕገወጥ በማዘዋወር ጥፋተኛ በተባለ የየመን ዜጋ ላይ መፈጸሙን ሳውዲ ፕረስ መዘገቡንም ተጠቅሷል።

ይህም በዚህ የፈረጁቹ ዓመት ሳውድ አረቢያ በሞት የቀጣቻቸው የውጭ ዜጎች ቁጥርን 101 አድርሶታል።

ባለፈው የፈረንጁቹ ዓመት 2023 የሳውዲ መንግሥት በሞት የቀጣቸው የውጭ ዜጎች 34 እንደነበሩና የዘንድሮው በሦስት እጥፍ ገደማ ከፍ ማለቱን መቀመጫውን በርሊን ጀርመን ያደረገው የአውሮጳ ሳውዲ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ሳውድ አረቢያ የሞት ቅጣት በተደጋጋሚ ከሚፈጸምባቸው ሃገራት አንዷ ናት።

የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የሞት ቅጣት እንዲቀር በየጊዜው ያሳስባሉ።

ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዓለም አቀፍ የአንተርፕሪነርሺፕ ሳምንት ተጀምሯል

የዘንድሮ የስራ ፈጣሪዎች ሳምንት "ኢንተርፕሪነርሽፕ ለሁሉም " በሚል መሪ ሐሳብ ከህዳር 9 እስከ 17/2017 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደረጃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል ተብሏል ፡፡

የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀሰን ሁሴን፤ዜጎችን ለማነፅ፣ችግሮች በመቅረፍ፣ሀገርን ለመገንባትና የስራ እድልን ለመፍጠር አጋዥ ነው ብለዋል።

ይህንም እንዲያግዝ በበጀት አመቱ 310 ስልጠናዎችን መስጠት መቻላቸውን ጠቁመዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፤ በበኩላቸው በፈጠራ ላይ የተመሰረተ ትውልድ ለመፍጠርና የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

የተሻለ ኢኮኖሚና ዘላቂነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ ምቹ ምህዳር በመፍጠር ስራ ፈጣሪዎችን ማገዝና መሰናክሎችን ማስወገድ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል ።

ያደጉ ሃገራት ለማደጋቸው ምክንያቱ ምቹ ምህዳር በመፍጠራቸው እና በዚህ ዘርፍ ላይ አተኩረው በመስራታቸው ነው ያሉ ሲሆን ከስራና ክህሎት ሚስቴር ጋር በመሆን ከፖሊሲ ጀምሮ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ዶ/ር በለጠ ሞላ።

የሥራና ክህሎት ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እንደገለጹት፤ሳምንቱ በሃሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባር በማስደገፍ ጭምር ነው ብለዋል።

ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ሀገሪቱ ያላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም ሁሉንም ማህበረሰብ በማካተት ተሳታፊ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፤
እኛም እታች ድረስ በመውረድ የግንዛቤና ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረግን ነው አሁንም እንቀጥላለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ ይህን አለም አቀፍ የኢንተርፕሪነርሺፕ ሳምንትን በማዘጋጀት ከአለም 16ኛ ከአፍሪካ በ3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች 47 ኩነቶች በማዘጋጀት።

ይህ አለም አቀፍ የስራ ፈጣሪዎች ቀን በየዓመቱ በህዳር ወር የግንዛቤ ማስጨበጫና መረጃ ሰጭ በሆነ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከበር ተነግሯል ፡፡

ሁነቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩትና ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተዘጋጀነው ተብሏል።

ልዑል ወልዴ

ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የጨዋታ ቀን

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ የምድብ 5ተኛ ጨዋታቸውን ከታንዛኒያ ጋር ያደርጋሉ።

በጊዜያዊ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመሩት ዋልያዎቹ የማለፍ ጠባብ እድል ይዛ ጨዋታዎቹን የምታደርግ ሲሆን ሁለቱንም ቀሪ ማጣሪያ ብታሸንፍም ለማለፍ የታንዛንያን እና የጊኒን መሸነፍ ለመጠበቅ ትገደዳለች።

በምድብ 8 የምትገኘው ኢትዮጵያ እስካሁን ካደረገቻቸው 4 ጨዋታዎች በ3ቱ ተሸንፋ በአንዱ አቻ በመውጣት በ1 ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች ።

ጨዋታውን አራት ደቡብ ሱዳናውያን ዳኞች በጋራ በመሆን እንዲመሩት በካፍ መመረጣቸው በይፋ ተገልጿል።

ሪንግ ኒየር አኬች ማሎንግ ጨዋታውን በመሐል አልቢትርነት ሲመሩት ሮበርት ዱዉኪ ሮበርት ሄነሪ እና ጋሲም ማዲር ዴሂያ በረዳትነት እንዲሁም አንቶኒ ኪሪ ኢማኑኤል ዳውድ በአራተኛ ዳኝነት ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

በጨዋታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ እንዲሁም የታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን ቢጫ በሰማያዊ ማልያ በመልበስ ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።

ብሄራዊ ቡድኑ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በኮንጎ ኪንሻሳ ከታንዛኒያ ጋር ወሳኝ ጨዋታውን ታደርጋል፡፡

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሴቶች በትምህርት ዘርፍ ለሚያመጡት ዉጤት ማበረታቻ እና ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ተገለፅ።

በተለያዩ የትምህርት ደረጃወች የሚገኙ እና በትምህራታቸዉ የተሻለ ዉጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪወችን ለማበረታታትና እዉቅና ለመስጠት መርሀ ግብር መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ማህበራዉ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል

የቢሮው ሀላፊ  የሆኑት ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን  ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በ2016 ዓም የ12 ክፍል ብሔራዉ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገቡትን እና በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸዉን ላጠናቀቁ ሴት ተማሪወች እዉቅና ተሰጥቷል ብለዋል፡፡


እንዲሁም እውቅና ከመስጠት ባለፈ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ትምህራታቸዉን ያጠናቀቁ ተማሪወች ልምዳቸዉን ያጋሩበት መድረክ መሆኑን ነግረውናል።

ሴት ተማሪወችን የማበረታታት   ስራዉ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ እንደነበር እና ሴቶች ካለባቸዉ ጫናና ሃላፊነት አንፃር በከፍተኛ ጥረት ለሚያመጡት ዉጤት ማበረታታት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በቀጣይ ለሚደረጉ መሰል መርሀ ግብሮችም በግል የትምህርት ተቋማት ያሉ እንዲሁም  መካከለኛና ዝቅተኛ  ዉጤት ያላቸዉ ተማሪወችንም የማበረታታት ስራው የሚቀጥል መሆኑን አንስተዋል።

በመጨረሻም የእዉቅና መርሀ ግብሩ ሌሎች ሴት ተማሪወችን የሚያነሳሳ እና ለተሻለ ዉጤት እንዲተጉ  የሚያደርግ ማበረታች ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

ሊዲያ ደስአለኝ

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄዷ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሶማሊላንድ ህዝህብ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄዱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ሚኒስቴሩ የሶማሊላንድ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄዱ የሚያስመሰግን ነው ብሏል።

ይህ ሂደት የሶማሊላንድን የአስተዳደር እና የዲሞክራሲ ሥርዓት ብስለት ያሳያል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ህዳር 06 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ደብብ አፍሪካ  ህገ ወጥ ማእድን አውጪዎችን እያሰሰች ነው፡፡

ደቡብ አፍሪካ በሺዎች ለሚቆጠሩ ህገ-ወጥ ማዕድን  አውጪዎች ማንኛውንም አይነት አቅርቦት እንደማትሰጥ  እና ህገወጥ ያለቻቸውን ዜጎች በመፈለግ ላይ ስለመሆኗ ታውቋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ወደ 4,000 የሚጠጉ ህገወጥ የወርቅ ማዕድን አውጪዎች  እንደሚኖሩ ሲገመት እነዚህን ማእድን አውጪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል እንቅስቃሴ መጀመሩ ተነግሯል፡፡

ይሁን እንጂ ከ 4 ሺ በላይ የሚገመቱት ህገወጥ ማአድን አውጪዎች ከመሬት በታች ተደብቀው እንደሚገኙ የቢቢሲ አፍሪካ ዘገባ አመላክቷል፡፡

እነዚህ   ማዕድን ቆፋሪዎች በሰሜናዊ    ምዕራብ ግዛት  ውስጥ  በሚገኝ   የማዕድን ማውጫ ስፍራ    ለአንድ ወር ያህል ተደብቀው  ቆይተዋል ተብሏል።

ከሀገሪቱ    ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር   ፈቃደኛ አልሆኑም  የተባሉት  እነዚህ ህገወጥ ማእድን አውጪዎች    አንዳንዶቹ ሰነድ የሌላቸው እና  እንደ ሌሶቶ እና ሞዛምቢክ ካሉ ጎረቤት አገሮች የመጡ  ስመሆናቸው ተሰምቷል፡፡

ዛማ ዛማ  በመባል የሚታወቁት እነዚህ  ህገወጥ  የማአድን አውጪዎች    ህገ ወጥ ማዕድን በማውጣት የደቡብ አፍሪካን መንግስት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ለኪሳራ እንደሚዳርጉት ዘገባው አመላክቷል

የውልሰው ገዝሙ

ህዳር 06 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሱዳን በተከሰተው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ 60 ሺ በላይ ሰዎች መሞታቸውን አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

በሱዳን ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከተገለጸው በእጅጉ ጨምሮ መገኘቱን ነው ቢቢሲ ይዞት የወጣው አዲስ ጥናት ያመላከተው ፡፡

ጦርነቱ ባለፈው አመት በተጀመረበት በካርቱም ግዛት ከ61,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውን በለንደን የሚገኝ የሱዳን የምርምር ቡድን ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል ።

ከነዚህም መካከል 26,000 ሰዎች በሁከቱ በቀጥታ ተገድለዋል ያለው ሪፓርቱ በሱዳን ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከፍተኛ የሞት ቁጥር እየተመዘገበ ያለውም በበሽታና በረሃብ መሆኑን ጠቁሟል።

በሀገሪቱ በተለይም በምዕራባዊው የዳርፉር ግዛት ብዙ ሰዎች የሞቱ ሲሆን በአሰቃቂ ጭፍጨፋ እና በዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ የሆኑ ዜጎችም ስለመሆናቸው መረጃው ጠቅሷል ።

በሱዳን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለርሃብ አደጋ ተጋልጠዋል እንደሚገኙ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች አረጋግጠናል እንዳሉት 20,000 ሰዎች በረሀብ ምክንያት ሞተዋል፡፡

ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለናሙና ወደ ውጪ የተላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸውን ተሰማ

ከማዕድን ዘርፉ እና ከማዕድን አምራቾች በቂ ገቢ እየተሰበሰበ አለመሆኑን የተገለፀ ሲሆን ለናሙና ወደ ውጪ የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸውን በተደረገው የኦዲት ግኝት መረጋገጡ ተገልጿል።

በማዕድን ሚኒስቴር ከማዕድን የሚገኝ ገቢን ማሳደጉን እና መሰብሰቡን በተመለከተ የተከናወነዉን የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው በሚኒስቴር መ/ቤቱ ላይ የህግ ማዕቀፍ ክፍተት እንዳለበት በመጥቀስ ለአብነትም የአለኝታና የአዋጭነት ጥናቶች በአግባቡ አለመደረጋቸው ይገኙበታል ብሏል።

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዳለዉ ለናሙና ወደ ውጪ የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸው እና በተቋሙ በኩል ግን የተሰጠው ምላሽ አጥጋቢ አይደለም ሲል አስታውቋል

ይህም ለሀብት ብክነት የሚዳርግ ነዉ ያለዉ ቋሚ ኮሚቴዉ ማዕድናቱ የሚመለሱበትን ስርአት መዘርጋት ይገባል በማለት አሳስቧል እንደ ካፒታል ዘገባ።

በማዕድን ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዮስ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በክዋኔ ኦዲት የታዩ ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችል አዲስ አደረጃጀትና አሰራር እንዲሁም የአዋጅ ማሻሻያ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ታዋቂው ኢራናዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የኢራንን መንግሥት በመቃወም ራሱን አጠፋ።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኪያኖሽ ሳንጃሪ አምባገነን ነው ያለውን የኢራኑን የአያቶላ አሊ ኻሚኒ አስተዳደር በመቃወም ራሱን አጥፍቷል።

አራት የፖለቲካ እስረኞች እስከ እሮብ ምሽት ከእስር ካልተለቀቁ ራሱን እንደሚያጠፋ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስታውቆ ነበር።ሕይወቱ ማለፉን አጋሮቹ የሆኑ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አስታውቀዋል።

“አንድ ቀን ኢራናውያን ነቅተው ባርነትን ያሸንፋሉ” ሲል ራሱን ከማጥፋቱ አስቀድሞ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ጽፏል።የኢራንን መንግሥት አጥብቶ በመተቸት የሚታወቀው ኪያኖሽ ሳንጃሪ ለዴሞክራሲ ሲታገል ቆይቷል።

ከመሞቱ በፊት “ማንም ሰው ሐሳቡን በመግለጹ ምክንያት መታሰር የለበትም። መቃወም የሁሉም ኢራናውያን መብት ነው” ብሏል።

ፋትሚ ሰፕሀሪ፣ ናስሪን ሻክራሚ፣ ቶማጂ ሳሊህ እና አርሻም ረዛይ ከእስር ቤት የማይለቀቁ ከሆነ “የኻሚኒን መንግሥትና አጋሮቹን በመቃወም ራሴን አጠፋለሁ” ሲል በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ጽፎ ነበር።

አራቱም የታሰሩት የ22 ዓመቷ ማሳ አሚኒ መገደሏን ተከትሎ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ በመደገፋቸውና በመሳተፋቸው ነበር።

እአአ በ2022 ማሳ አሚኒ በኢራን የሞራል ፖሊስ ከታሰረች በኋላ መሞቷን ተከትሎ በኢራን ሕዝባዊ ቁጣ ተነስቶ እንደነበር ይታወሳል።

ኪያኖሽ ለኢራን የአገር ውስጥ መገናኛ እንደገለጸው የኤሌክትሪክ ንዝረት እንዲሁም ከአልጋ ጋር እስራት ተፈጽሞባል። በርካታ መድኃኒቶችም ተሰጥተውታል።

የንግግር ነጻነት ተሟጋቹ ሁሴን ሮናጊ በኤክስ ገጹ ላይ “ኪያኖሽ ሳንጃ ስም ብቻ አይደለም። የዓመታት ስቃይ፣ አይበገሬነትና የነጻነት ትግል ምልክት ነው” ሲል ጽፏል።

ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ባለፉት ስድስት አመታት 10 ቢሊየን ዶላር እዳ  ከፍለናል ሲል መንግስት ገለፀ

ይህንን ያሉት የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍፁም አሰፉ ናቸው።

የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሁኔታ በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተደረገ ባለው ውይይት ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት አመታት 10 ቢሊየን ዶላር  ብድር  መክፈሏን ተናግረዋል።

የተወሰዱት ብድሮች በአጭር ጊዜ እንዲከፈሉ የሚደረግ እና ከፍተኛ ወለድ ያለቸው እንደነበሩም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

"ብድር መበደር ቀላል ቢሆንም ለሚመጣው ትውልድ እዳ ትቶ ላለማለፍ አንድም ብር ሳንበደር እዳችንን ከፍለናል " ሲሉም ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ገልፀዋል።

የተወሰደው ብድር አላግባብ ቦታ ላይ በመዋሉ እንዲሁም ብድሩን የወሰዱ ድርጅቶች ውጤታማ አለመሆኑም ለብድሩ መበላሸት ምክንያት እንደሆነም ተናግረዋል።


ለዓለም አሰፋ

ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ካፒታል የገንዘብ ቁጠባ እና ቡድር ተቋም ከኦቪድ ሪል ስቴት እንዲሁም ከኦቪድ ቤቶች ባንክ  ጋር የ500 ቤቶች ግዢ  እንዲሁም የአንድ መቶ ሚሊየን ብር የአክሲዮን ስምምነት  ተፈራረመ።

ምስረታውን ካደረገ አንድ አመት ያለፈው ካፒታል  የገንዘብ ቁጠባ  እና ብድር  ተቋም ከኦቪድ ቤቶች ባንክ (በምስረታ ላይ) እና ከኦቪድ ሪል ስቴት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱም ከኦቪድ ቤቶች ባንክ (በምስረታ ላይ) ጋር 1መቶ ሺህ አክስዬኖች ግዚ ስምምነት እንዲሁም ከኦቪድ ሪል ስቴት ጋር ደግሞ የ500 ቤቶች ግዚ የጋራ መግባቢያ ስምምነት አድርገዋል።

የአንድ መቶ ሺ አክሲዎኖች ስምምነት  በገንዘብ ሲተመን ወደ 1 መቶ ሚሊየን  ብር የሚጠጋ  መሆኑም ተገልጿል።

የመግባቢያ ስምምነቱ ዋና አላማ  የአባላቶቹን
የቤት ፍላጎት ለመቅረፍ በማሰብ መሆኑም  ተገልጿል።

ለዓለም አሰፋ

ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት አገኘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025 የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት ማግኘቱን አስታወቀ።

ይህ የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከተረጋገጡ ጉዞዎች፣ ከበረራ በኋላ ከመንገደኞች በተሰጡ ድምፆች መሰረት የሚበረከት ሽልማት መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሽልማቱ በአቪዬሽኑ ዘርፍ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው አለም አቀፍ ዕውቅና መሆኑም ተመላክቷል።


ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሮድሪጎ  ቤንታንኩር   እገዳ  ተጥሎበታል

ዩራጓዊው  የቶተንሀም  አማካይ  ሮድሪጎ  ቤንታንኩር  በቅርቡ  ለመገናኛ  ብዙሃን   በሰጠው  አስተያየት ምክንያት  ከእንግሊዝ  ኤፍ ኤ  ቅጣት  እንደተጣለበት  ይፋ  ሆኗል።


ተጨዋቹ ከመገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ በቡድን አጋሩ ላይ ያልተገባ ነገር ተናግሯል በሚል ክስ እንደቀረበበት ይታወሳል።

ሮድሪጎ ቤንታኩር አሁን ላይ የሰባት ጨዋታዎች እገዳ ቅጣት እና የ 100,000 ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ሮድሪጎ ቤንታኩር ከዩራጓይ መገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ የሰን ሁንግ ሚን ማልያ ማገኘት ከተቻለ ሲጠየቅ “ ምናልባት የአጎቱን ልጅ ምክንያቱም ሁሉም ይመሳሰላሉ “ ሲል ተናግሮ ነበር።

ተጨዋቹ ከእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ውድድሮች ውጪ በሚደረጉ ውድድሮች መሳተፍ እንደሚችል ተነግሯል።

ቤንታንኩር  አሁን  ለቶተንሃም   የሚከተሉትን  ጨዋታዎች  የሚያመልጥ  ይሆናል።

ቅዳሜ:   ማን ሲቲ
ዲሴምበር 1፡  ፉልሃም
ዲሴምበር 5፡  በርንማውዝ
ታህሳስ 15፡ ሳውዝሃምፕተን
ታህሳስ 19፡  ማን  ዩናይትድ ( - ኢኤፍኤል ዋንጫ)
ታህሳስ 22፡  ሊቨርፑል

ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከአክሱም ከተማ ጠፍተው የነበሩትን የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ተባለ

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጦርነት እና አለመረጋጋት በነበረበት ወቅት 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው እንደተረጋገጠ የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታወቀው ነበር፡፡

ታዲያ አሁን ላይ ቅርሶችን ለማግኘት ምን ተሰራ ሲል ጣቢያችን የጠየቀ ሲሆን ኃላፊው በምላሻቸውም የተዘረፉት እና የጠፉትን 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ብለዋል።

የጠፉትን ቅርሶች ማን እንደወሰዳቸው ማወቅ እንዳልተቻለ የገለፁት ኃላፊው እነዚህን ቅርሶች የማስመለስ ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን እንደገለጹልን፣ ጽሕፈት ቤታቸው በዋናነት ቅርሶችን ለማግኘት ከፌደራል እና ከክልል ፖሊሶች ጋር በጥምረት በመሆን ቢሰራም እስካሁን ፍንጭ እንኳን አለመገኘቱን ተናግረዋል።፡

ኃላፊው ጨምረው፣ የነዚህ ቅርሶች መጥፋት በከተማዋ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
ለአለም አሰፋከአክሱም ከተማ ጠፍተው የነበሩትን የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ተባለ


በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጦርነት እና አለመረጋጋት በነበረበት ወቅት 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው እንደተረጋገጠ የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታወቀው ነበር፡፡

ታዲያ አሁን ላይ ቅርሶችን ለማግኘት ምን ተሰራ ሲል ጣቢያችን የጠየቀ ሲሆን ኃላፊው በምላሻቸውም የተዘረፉት እና የጠፉትን 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ብለዋል።

የጠፉትን ቅርሶች ማን እንደወሰዳቸው ማወቅ እንዳልተቻለ የገለፁት ኃላፊው እነዚህን ቅርሶች የማስመለስ ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን እንደገለጹልን፣ ጽሕፈት ቤታቸው በዋናነት ቅርሶችን ለማግኘት ከፌደራል እና ከክልል ፖሊሶች ጋር በጥምረት በመሆን ቢሰራም እስካሁን ፍንጭ እንኳን አለመገኘቱን ተናግረዋል።፡

ኃላፊው ጨምረው፣ የነዚህ ቅርሶች መጥፋት በከተማዋ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ለአለም አሰፋ

ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኤሌክትሪክ አደጋን መቀነስ የሚችሉ የማከፋፈያ ምርቶችን ወደ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ነዉ ተባለ።

ይህን ያለዉ የቻይናዉ ኤፍ ኤንድ ቲ የኤሌክትሪክ እቃዎች አምራች ድርጅት ነዉ

ከአራት ወራት በፊት በኢትዩጵያ ስራ የጀመረዉ ኤፍ ኤንድ ቲ የተሰኘዉ የቻይና ካንፓኒ ከኤሌክትሪክ የጥራት ጉድለት ጋር በተያያዙ የሚፈጠሩ አደጋዎችን ችግር ለመፍታት በማለም ስራ ጀምሯል።

ድርጅቱ አዲስ ባስተዋወቀዉ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ምርት ላይ በሰጠዉ መግለጫ በሁለት አይነት የምርት አቀራረብ ለገበያ እንደሚቀርብ ገልፆል።

በተለያየ ይዘት ዩኤስቢ እንዲሁም ታይኘ ሲ ገመድ ቻርጀሮችን መቀበል የሚያስችል እንደሆነ  የድርጅቱ ተወካይ ተናግረዋል።

ከአንድ ወራት በኋላ ገበያዉን ይቀላቀላል የተባለዉ ምርቱ ገበያዉ ላይ እየታየ ያለዉ እጥረት እና የጥራት ጉድለት ይሸፍናል ተብሎ የታመነበት ነዉ ተብሏል።

አዲሱ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ምርት ሁለት ሺህ አምስት መቶ ዋት የሀይል መጠን ያለዉ ነዉ።

ኤፍ ኤንድ ቲ የኤሌክትሪክ ገመዶች እና ኬብሎች አምራች ድርጅት አዲሱ ምርቱን በወር ሀምሳ ሺህ ያህል የማምረት እቅድ እንዳለዉ ገልፆል።

የሚያመርተውን ምርት በተመለከተ ከተሰጠዉ ተጨማሪ ማብራሪያ  ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ተፈላጊውን ጥራት የሚኖራቸዉ  የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኬብል ምርቶችንና የኬብል ምርት ውጤቶችን ማምረት የጀመረ መሆኑ ተነስቷል።

ቁምነገር አየለ

ህዳር 07ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ማይክ ታይሰን በጄክ ፖል ተረታ !

የአለማችን የምንጊዜም ታላቁ ቦክሰኛ ማይክል ታይሰን ከ 19ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ገነነበት የቦክስ ፍልሚያ ተመልሶ በ 31ዓመታት ከሚያንሰው ጄክ ፖል ጋር ተፋልሟል።

በመላው አለም በርካቶች በተመለከቱት ፍልሚያ የ 27ዓመቱ ጄክ ፖል በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ካደረጋቸው 56 ፕሮፌሽናል የቦክስ ግጥሚያዎች በ 50 ድል የተቀዳጀው ማይክ ታይሰን ዛሬ ሰባተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ወጣቱ ጄክ ፖል በበኩሉ የዛሬውን ጨምሮ ካደረጋቸው 11 ፕሮፌሽናል ግጥሚያዎች በ 10 ድል መቀዳጀት ችሏል።

ማይክ ታይሰን ከፍልምያው በኋላ “ ፖል ጠንካራ ተፋላሚ እንደሆነ አውቅ ነበር በደንብ ተዘጋጅቷል ለማንም ማሳየት ያለብኝ ነገር የለም ባደረኩት ነገር ደስተኛ ነኝ ብሏል።

ጄክ ፖል በበኩሉ “ ከማይክ ጃክሰን ጋር መፋለም ክብር ነው ፤ እንደጠበቅኩት በጣም ከባድ ፍልሚያ ነበር የቻልኩትን ሁሉ አድርጌያለሁ።"በማለት ተናግሯል።

ግጥሚያውን ያሸነፈው ጄክ ፖል የ 40 ሚልዮን ዶላር አሸናፊ ሲሆን ተሸናፊው ማይክ ታይሰን በበኩሉ 20 ሚልዮን ዶላር እንደሚያገኝ ተገልጿል።

ተጠባቂውን የሁለቱ ቦክሰኞች ፍልሚያ 4.9 ሚሊዮን ሰዎች በቀጥታ ስርጭት መመልከት ችለዋል።

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለቀድሞው ፖሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፤ በኃላፊነታቸው ላይ ሳሉ ላከናወኗቸው ስራዎች የምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል ።

ይህን መርሃ ግብር ያዘጋጁት በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሰባት ሀገር በቀል እና አለም አቀፍ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ናቸው።


የመርሃ ግብሩ ዋና አላማ የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት በሴቶች አመራር ረገድ ላከናወኗቸው ስራዎች በሴቶች አማካኝነት ምስጋና ለማቅረብ ነው ተብሏል።

በሽኝት መርሃግብሩ ላይ የተገኙት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለተሰጣቸው ክብርና ዕውቅና አመሰግነዋል።

በቀጣይ በሴቶች ዙሪያ የጀመሯቸውን ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግርዋል ።

በስልጣን ዘመናቸው ለሀገራቸው በተለይም ሴቶቾን ከማብቃት አኳያ ላደረጉት አስተዋጽኦ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

በዝግጅቱ ላይ አምባሳደሮችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

አባቱ መረቀ

ህዳር 06 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ካዛንቺስን ከሚያለሙ ባለሀብቶች ጋር መከሩ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ካዛንቺስ አካባቢ ካሉ ባለሀብቶች ጋር አካባቢውን በትብብር መልሶ ለማልማት መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

ሁለተኛው የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡንና ባለሀብቱን በማሳተፍ በጥራትና በፍጥነት ይጠናቀቃል ብለዋል።

በውይይቱ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለማድረግ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ እንደ መጀመሪያው ሁሉ የሁለተኛውን የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡንና ባለሀብቱን በማሳተፍ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት የካዛንቺስ አካባቢ ባለሀብቶች በበኩላቸው በኮሪደር ልማትና በመልሶ ማልማት ስራ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ የከተማው ጽዳትና ውበት ለኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ በመሆኑ ገልጸዋል።

ባለሃብቶቹ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር አካባቢውን እንደሚያለሙ ቃል በመግባት ያላቸውን የልማት ጥያቄዎች በማቅረብ ለመልሶ ማልማት ስራው በቀረበላቸው ጥሪ ደስተኛ መሆናቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


ህዳር 06 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ የቀድሞውን ቲውተር የአሁኑን X መጠቀም ማቆሙን ገለፀ።

የብሪታንያ ዕለታዊ ጋዜጣ ዘ ጋርዲያን ፅሁፎቹን በኤክስ ላይ መለጠፍ አቆማለሁ ብሏል። ጋዜጣው X ኤሎን ማስክ "ፖለቲካ ለመቅረጽ" የሚጠቀምበት "መርዛማ" መድረክ ነው ብሏል ።


የብሪታንያ ዕለታዊ ጋዜጣ ዘ ጋርዲያን ረቡዕ እለት በቀድሞ ትዊተር ተብሎ በሚጠራው የማህበራዊ ሚዲያ X ላይ ይዘትን መለጠፍ እንደማይችል ተናግሯል።ጋዜጣው ውሳኔውን የሚያብራራ መግለጫ በድረ-ገጹ ላይ አውጥቷል።

መግለጫው "በኤክስ ላይ መገኘት ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች ይልቅ ከአሉታዊ ጎኖቹ የበለጠ እና ሀብቶቻችንን ጋዜጠኝነትን በሌላ ቦታ ለማስተዋወቅ ይጠቅማል ብለን እናስባለን ብሏል።

ዘ ጋርዲያን “የቀኝ ዘመም የሴራ ንድፈ ሃሳቦችን እና ዘረኝነትን ጨምሮ በመድረኩ ላይ የሚንፀባረቀው  ይዘት የሚረብሽ  እና አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል ብሏል።,ይህም በቅርብ ወራት ውስጥ የበለጠ እየጨመረ ነው።በተለይም የ X ባለቤት ኤሎን ማስክ ለዶናልድ ትራምፕ ወደ ኋይት ሀውስ እንዲመለስ ግፊት ካደረገ ወዲህ።

"ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ያገለገለው X መርዛማ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ መሆኑን እና ባለቤቱ ኤሎን ማስክ የፖለቲካ ንግግሮችን ለመቅረጽ ተጽኖውን ሊጠቀምበት ችሏል."ብሏል ዘጋርዲያን።


ጋዜጣው X ን መጠቀም ቢያቆምም  ተጠቃሚዎች ግን አሁንም ከዕለታዊ ጋዜጣ የወጡ መጣጥፎችን ቀደም ሲል ትዊተር ተብሎ በሚጠራው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ  መድረክ ላይ ማጋራት ይችላሉ ብሏል::

ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አልሸባብን የማዳከም ስራ እንደሚቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ

በሶማሊያ የሚገኘውን አሸባሪ ቡድን አልሸባብ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥጋት እንዳይሆን "በየትኛውም ሁኔታ አሸባሪ ቡድኑን የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል" ሲል መንግሥስት አስታወቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠራዊት በአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ውጪ መሆኑን ባለፈው ሳምንት በይፋ ማስታወቋን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም ሲጠየቁ ነው ይህንን ያሉት።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ "የማይነጣጠሉ ሕዝቦች እንደመሆናቸው ጊዜያዊ ችግሮችን የመባባስ ፍላጎት የለንም" ያሉት ቃል አቀባዩ የሶማሊያ ማንግሥት ይፋ ላራመደው አቋም አልሸባብን እናዳክማለን ከማለት በቀር ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተካረረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ እና የራስ ገዟ ሶማሊላንድ «የባሕር በር እውቅና» የመግባቢያ ስምምነት እስካሁን በሂደት ላይ መሆኑ ሲገለጽ በአንድ በኩል፣ አልሸባብን በመዋጋት ለዓመታት የጋራ ግብ እና ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ሆድና ጀርባ አድርጎ ከቃላት ያለፈ የዲፕሎማሲ ውጥረት ውስጥ ከቷቸዋል።

ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አቢሲኒያ  ባንክ አጠቃላይ የተቀማጭ የገንዘብ መጠኑን ከ158.54 ቢሊዮን ብር ወደ 192.51 ቢሊዮን ማድረስ ችያለው አለ፡፡

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ አመት 4 .23 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

በበጀት አመቱ የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ21.43 በመቶ ወይም የ33 ቢሊዮን ብር እድገት ማሳየቱ ተገልጧል፡፡

የባንኩን ብድር እና ቅድመ ክፍያዎች መጠን ከወለድ ነፃ የተሰጡ ብድሮችን አካቶ 167.74 ቢሊዮን መድረሱ ተነግሯል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት አመት የተገኘው የውጭ ምንዛሬ መጠን 424 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን ሰምተናል፡፡

ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ቅናሾች ማሳየታቸው ተነስቷል፡፡

እንዲሁም ያለፈው አመት የባንኩ ጠቅላላ ገቢ 27.75 ቢሊዮን መድረሱ ተጠቅሷል፡፡

ባንኩ በአጠቃላይ 15 ንኡሳን ቅርንጫፎችን ጨምሮ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 930 ከፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel