ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2024 ዓለም አቀፍ ዓውደ ርዕይና ሲምፖዚይም ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል።

የአየር ንብረት ለውጥ እየፈጠረው ያለውን ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ መቋቋም የሚችል ዘላቂና አስተማማኝ አረንጓዴ ልማት መፍጠር ያስልጋል ብለዋል የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዬ ታገሰ ጫፎ።

ኢትዮጵያ አረንጓዴ ሞቢሊቲን ሊደግፍ የሚችል እምቅ ታዳሽ ኃይል ባለቤት ናት ያሉት አፈ-ጉባዔው ይህን አቅም በመጠቀም የአረንንዴ ትራንስፖርት ፈር ቀዳጅ ለመሆን እየሰራች ነው ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አስመጪዎች የተለያዩ ማበረታቻ ድጋፎች እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰው ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ የበለፀገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ፖሊሲ አውጪዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው አረንጓዴ ትራንስፖርት ኢትዮጵያ ዘላቂነት ያለው አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታደርገው ጥረት አካል ነው ብለዋል።

አዲስ አበባ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማዕከልነቷን ለማስጠበቅ የተጀመሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በአረንጓዴ ትራንስፖርት ለመደገፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተሽከርካሪ መሰረተ ልማት ባለፈ የሳይክልና የእግረኛ መንገዶችን በማስፋት ከነዳጅ ጥገኝነት ለመላቀቅ፣የበካይ ጋዝን ለመቀነስና ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

አውደ ርዕዩና ሲምፖዚየሙ እስከ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ኀዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ህብረተሰቡ ሪሊፍ (RELIEF) የተባለ ህገ ወጥ መድሃኒት ከመጠቀም እንዲቆጠብ የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አስጠነቀቀ፡፡

ባለሥልጣኑ RELIEF የሚባል ሕገወጥ መድኃኒት በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው ስለሚገመትና ለጤና ጎጂ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ስላለ መድሃኒቱ ጥቅም ላይ መዋል እንደሌለበት አስጠንቅቋል፡፡

መድሃኒቱ በኢትዮጵያ ገበያ በስፋት እየተዘዋወረ መሆኑን ጠቁሞ፤ መድኃኒቱ በሕጋዊ መንገድ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ በመሆኑ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ አይታወቅም ሲል አስገንዝቧል።

በተጨማሪም የዚህ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ድካም፣ የእይታ መዛባት፣ መፍዘዝ፣ ራስ ምታት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመርና ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል የኩላሊት ጉዳትን እንደሚያመጣም ተመላክቷል፡፡

ይህንን መድኃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል በጥናት መረጋገጡንም የባለስልጣኑ መረጃ ገልጿል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን መድኃኒት ከመጠቀም እንዲቆጠብ እና መድኃኒቱን ጥቅም ላይ ሲውል ከተገኘ በነጻ ስልክ ቁጥር 8482 በመደወል ለባለስልጣኑ ወይም ለክልል ጤና ተቆጣጣሪ አካላት እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርቧል።

አባቱ መረቀ

ኀዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የምዕራባዉያን ኢምፔሪያሊዝም እብደት ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ ማዱሮ ተናገሩ

የቬንዙዌላዉ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ አሜሪካ መራሹ የኢምፔሪያሊዝም አስተሳሰብ እብደት ደረጃ ላይ በመድረሱ አለምን ለስጋት ዳርጓል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ማዱሮ አሜሪካና አጋሮቿ ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን በማስታጠቅ እህታችን ሩሲያን መምታት ጀምረዋል ብለዋል፡፡

ይህም የምዕራባዉያን ኢምፔሪያሊዝም ወደ ከፋ ደረጃ መድረሱን አመላካች ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በካራካስ ንግግር ያደረጉት ማዱሮ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ወንጀለኛዉ ናዚ ሲሉ ወርፈዋቸዋል፡፡

አገራቸዉ ቬንዙዌላ ከሩሲያ ጎን እንደምትቆምም አስታዉቀዋል፡፡

አባቱ መረቀ

ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለ 614 ጫኝ እና አውራጆች ፍቃድ ተሰቷል።

በከተማዋ 614 የጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት ህጋዊ ፍቃድ አግኝተዋል ተባለ።

በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ የምሬት ምንጭ ሆኖ የቀጠለዉ የጫኝ እና አዉራጅ አደረጃጀት ህጋዊ አካሄድ እንዲኖረዉ እየተደረገ ነዉ ተብሏል።

ከአንድ አመት ወዲህ የጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት መመሪያ ህግ እንዲወጣ መደረጉ ተነግሯል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ የከተማዋ መታወቂያ አላቸዉ የተባሉ 7228 ወጣቶችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ሰምተናል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እየመራዉ ነዉ በተባለዉ መመሪያ በእያንዳንዱ እቃዎች የመጫን እና የማዉረድ ሂደት ላይ የገበያ ጥናት የተደረገበት የዋጋ ተመን ማዉጣቱን የቢሮዉ ምክትል ሀላፊው አቶ ሚደቅሳ ተናግረዋል።

ሆኖም በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ተነሺዎችን ተከትሎ የሚጠየቁ የጫኝ እና አዉራጅ የዋጋ ተመን ክፍያዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ ተነስቶበታል።

ቢሮዉ በዚህ ዙሪያ ያሉ የቁጥጥር ክፍተቶችን ለማስተካከል ምን እየሰራ ነዉ ብለን ላነሳንላቸዉ ጥያቄ " ህጋዊ ማህበራቱ ለባለንብረቶች ንብረት ሀላፊነት እንዲወስዱ በማስገደድ እንዲሁም የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ክትትል እያደረኩ ነዉ" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በከተማዋ አራብሳ እና ከከተማዋ መውጫ ላይ የሚገኙ ሰፈሮች ህገወጥ የጫኝ እና አዉራጅ አደረጃጀቶች በስፋት መታየታቸዉ ሰምተናል።

ይህንን ተከትሎ ማህበረሰብ ለአገልግሎቱ ህጋዊ ደረሰኝ እንዲጠይቅ ያስፈልጋል ተብሏል።

ሆኖም ህብረተሰቡ ንብረቱን ከጫኝ እና አዉራጅ አካላት ዉጪ በራሱ አቅም የማዉረድም ሆነ የመጫኝ ሙሉ ፍቃዱ ተሰቶታል።

ማህበረሰብ ይህን ያልተከተሉ ማህበራት በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊሲ ኮምሽን ነፃ የስልክ መስመሮችን በመጠቀም ጥቆማዎችን መስጠት የሚችሉ መሆኑን ቢሮዉ አሳዉቋል።

ቁምነገር አየለ

ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ጣሊያን፣ ካናዳና እንግሊዝ ኔታኒያሁ ወደ ግዛታችን ዝር ቢል ይቀፈደዳል አሉ

የጣሊያን፣ የካናዳና የእንግሊዝ ከፍተኛ ባለስልጣናት የአለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ውሳኔ ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁን ለመያዝ ቃል ገብተዋል።

የጣሊያን መከላከያ ሚኒስትር ጊዶ ክሮሴቶ፤ሮም ኔታንያሁና ጋላንት ጣሊያን ከደረሱ ውሳኔውን ለማክበር ትገደዳለች ብለዋል።

ክሮሴቶ አክሎም ፤ኔታንያሁ እና ጋላንት የአይ.ሲ.ሲ ውሳኔ ስህተት ነው ብለው ያምናሉ ምክንያቱም ደግሞ በጥቅምት 7 ቀን 2023 በእስራኤል ላይ ለደረሰው “አሳፋሪ ጥቃት” ተጠያቂ ከሆኑት ጋር “በተመሳሳይ የክስ ደረጃ” በመጠየቃቸው ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እንዳሉት፤ ካናዳ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለኔታንያሁ እና ጋላንት የሰጠውን የእስር ማዘዣ ታከብራለች።

ዘ ታይምስ ጋዜጣ የዩኬ የጠቅላይ ሚንስትር ኬይር ስታርመርን ቢሮ ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደዘገበው ዩናይትድ ኪንግደም ኔታንያሁ እና ጋላንት ወደ አገሩ ከገቡ በቁጥጥር ስር አውላቸዋለሁ ብለዋል።

ትእዛዙ በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ከፀደቀ በኋላ ስታርመር የICCን ውሳኔ እንደሚያከብር ቃል አቀባዩ አክለዋል።

ባለፈው ሐሙስ ቀደም ብሎ አለም አቀፉ የወንጀለኞች ህግ ለኔታንያሁና ለቀድሞው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በጋዛ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የእስር ማዘዣ ማውጣቱ የሚታወስ ነው።

ይህ ቢሆንም የኔታንያሁ ፅህፈት ቤት በእለቱ በሰጠው መግለጫ የአይ.ሲ.ሲ ፍርድ ፤እስራኤልን ያገለለና በእስራኤል ላይ ሽብርተኝነትን የሚያበረታታ ነው ሲል ከሰዋል Sputnik ዘግቧል ።

ልኡል ወልዴ
ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኦሮሚያ ክልል መንግስት አሸባሪና ጽንፈኛ ቡድኖች በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙትን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንደሚያወግዝ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሰጡ በተባለው መግለጫ ላይ በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የሚወገዝ ድርጊት ነው ብለዋል።

የሸኔ አሸባሪ ቡድንና ጽንፈኛው ቡድን የተለያየ ቋንቋ ይናገሩ እንጂ ድርጊታቸው ተመሳሳይ ነው በማለት ገልጸው÷ ቡድኖቹ በህዝቡ መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር አስነዋሪ ድርጊቶች እየፈጸሙ መሆኑን ተናግረዋል።

አሸባሪ የሸኔ ቡድን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሚፈጽመው ድርጊት የህዝብ ደህንነት አደጋ ላይ እንዲወድቅና ልማት እንዲደናቀፍ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

ራሱን ፋኖ እያለ የሚጠራው ጽንፈኛው ቡድን የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች በንጹሀን ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በመግለጫቸው አንስተዋል ።

የክልሉ መንግስት በቡድኖቹ የሚፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ድርጊትን በማውገዝ የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የህግ ማስከበር እርምጃ እየወሰደ መሆኑን መጠቆማቸው የዘገበው ኢዜአ ነው።

በአሸባሪው ሸኔ ላይም ተከታታይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቅሰው÷ የሰላም መንገድ የመረጡት የቡድኑ አባላት እጃቸውን እየሰጡ ነው ብለዋል።

ህዝቡ አሸባሪና ጽንፈኛ ቡድኖችን ለማስወገድ በጋራ እንዲቆምም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኢትዮጵያዊው ማርሻል አርት ተወዳዳሪ ሳቦም ኤልያስ 3 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አሸናፊ ሆነ

በ ሀገረ አሜሪካ በተደረገ የ አለም አቀፍ ማርሻል አርት ፌስቲቫል ኢንተርናሽናል ውድድር ኢንስትራክተር ሳቦም ኤልያስ ኩመል አሸናፊ ሆኗል።

በሀገረ አሜሪካ ፍሎሪዳ ከተማ በአለም አቀፍ ማርሻል አርት ፌስቲቫል ውድድር 17 ሀገራት የተውጣጡ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ ተሳትፈዋል።

ከ ኢትዮጵያ ብቸኛ ተወዳዳሪ የሆነው ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም ኤልያስ ኩመል በሦስት ውድድሮች በመሳተፍ አንድ ወርቅና ሁለት የብር ሜዳሊያ በማግኘት የኢትዮጲያን ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲታይ አድርጓል።

ኢንተርናሽናል ኢንስትራክር ሳቦም ኤልያስ ኩመል በመጀመሪያ ደረጃ የፖተርን ውድድር የወርቅ ሜዳልያ፣ በነፃ ፍልሚያ ውድድር የብር ሜዳልያ፣ በሁለተኛ ደረጃ የፖተርን ውድድር የብር ሜዳልያ አግኝቷል።

ኢንስትራክተር ሳቦም ከዚህ ቀደም ለ 3 ተከታታይ አመታት (2022-2024) በአሜሪካን ሀገር በተደረገ ኢንተርናሽናል ማርሻል አርት ውድድር አሸናፊ ነው።

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዩክሬን በብሪታንያና ፈረንሳይ ስቶርም ሻዶ ሚሳኤል ሩሲያን መደብደብ ጀመረች

አሜሪካ ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን አሳልፋ መስጠቷን ተከትሎ ሁለቱ አገራት ፍቃድ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ዩክሬን ስቶርም ሻዶ በተሰኙ ሚሳኤሎች ሩሲያን ማጥቃት ጀምራለች ተብሏል፡፡

ሩሲያም የእጃችሁን ታገኛላችሁ ስትል እየዛተች ነዉ፡፡

የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ በሰጡት ምላሽ አገራቸው ዩክሬን ለምትጠቀማቸው ለእነዚህ ሚሳኤሎች ተገቢውን ወታደራዊ ምላሽ ትሰጣለች ብለዋል።

ለዩክሬን ተሰጠ የተባለው ‘ዘ ስቶርም ሻዶ’ የረጅም ርቀት ሚሳኤል ከዚህ በፊት የለንደንና እና የፓሪስ አየር ኃይሎች በባሕረ ሰላጤው አካባቢ በኢራቅ እና በሊቢያ ውስጥ ጥቅም ላይ አውለውታል።

የጦር አውድማ ላይ ሩሲያ የበላይነቷን እያሳየች ትገኛለች። የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬንን ግዛቶች እየተቆጣጠሩ ወደፊት በመገስገስ ላይ ናቸው።

አባቱ መረቀ

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሽንት ቤት ዉጭ መንገድ ላይ ይፀዳዳል ተባለ ፡፡

በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ጥራቱን ከጠበቀ ሽንት ቤት ዉጭ መንገድ ላይ ይፀዳዳል ተብሏል ፡፡

በጤና ሚኒስቴር አካባቢ ጤና ፕሮግራም ዴስክ ሃላፊ አቶ አለሙ ቀጀላ በአለም ጤና ድርጅት እና በዩኒሴፍ በ2022 በተደረገ ጥናት 17 ፐርሰንት የሚሆነዉ የኢትዬጲያ ህዝብ ከመፀዳጃ ቤት ዉጭ መንገድ ላይ ይፀዳዳል ብለዋል ፡፡

በዚህም ህዝቡ ለኮሌራ እና መሰል በሽታዎች ተጋላጭነቱ እንደጨመረ ተነግረዋል ።

ጤና ሚኒስቴር የተለያዩ ስትራቴጅዎችን ቀርጾ ህዝቡ መሰረታዊ መፀዳጃ ቤት እንዲጠቀም እየሰራ መሆኑ አቶ አለሙ ቀጀላ ገልፀዋል ፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረዉ የእጅ መታጠብ እና መፀዳጃ ቤት ቀን በኢትዮጵያ ለ ስምንተኛ ጊዜ በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች እየተከበረ ይገኛል ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

13ኛው የአፍሪካ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ተጀምሯል።

ጉባኤው አጣዳፊ የኢንተርኔት እና የዲጂታል ስራዎችን ለመፍታት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን የሚያሰባስብ ሲሆን በፖሊሲ ጉዳዮች፣ ከአፍሪካ ዲጂታል የወደፊት የጋራ ራዕይ ጋር የተጣጣሙ የህዝብ ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ የሚያስችሉ ጉዳዮች እንደ የሚዳሰሱበት እንደሆነም ተጠቁሟል ፡፡

የሳይበር ደህንነት እና የሳይበር ወንጀል፣ ኢመርጅንግ ቴክኖሎጂ፣ የኢንተርኔት አስተዳደርና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፤ የዲጂታልና ሰብአዊ መብቶች፣ ዘላቂነት፣ ሁለንተናዊ ተደራሽነትና ትርጉም ያለው አሀጉራዊ ግንኙነት እንዲሁም በሌሎችም የዘርፉ አጀንዳዎች ዙርያ በፎረሙ ውይይት ይደረጋል ተብሏል ፡፡

የዘንድሮ 13ኛ የአፍሪካ በይነመረብ አስተዳደር ጉባኤ “ዲጂታል አፍሪካን እውን ለማድረግ ጠንካራ ባለድርሻ አካላትን መገንባት ያስፈልጋል” በሚል መሪ ቃል ነው በዛሬው ዕለት ከፓርላማ አባላት ጋር ወይይት እየተደረገ የሚገኘው።

በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፤ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተሰኘውን አገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ መተግበር ከጀመረች አምስት አመት አስቆጥረናል ብለዋል።

የዚህ የስትራቴጂው ትግበራ፤ የቴሌኮም ዘርፉን ነፃ ለማድረግ ያስቻለን ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ከ130 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ወዳለበት ትልቅ ገበያ መቀላቀል ተችሏል ነው ያሉት።

ይህም ኢትዮጵያ ከ80 ሚሊየን በላይ የሞባይል ድምጽ ተመዝጋቢዎች በመያዝና ከ50 ሚሊዮን በላይ የዳታና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በመያዝ ከአፍሪካ 2ኛዋ ትልቋ ገበያ እንድትሆን አስችሏታል ሲሉም ዶ/ር ነገሪ ለንጮ ተናግረዋል።

በመሆኑ በአፍሪካ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ የኢንተርኔት ተደራሽነትን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው ለዚህም ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።

ኢንተርኔትን በከተሞች ብቻ ሳይሆን በገጠር ላለው የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በመጨረሻም አብሮ መስራቱ ከዳታ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን ለመለየትና መፍትሄዎችን ለማዘጋጀት ይህንን መድረክ መጠቀም አለብን ሲሉም አሳስበዋል።

ልኡል ወልዴ

ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሶማሊላንድ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ አሸነፉ

በሶማሊላንድ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው መሐመድ አብዱላሂ ኢሮ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲን ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ ማክሰኞ አስታወቀ፡፡

ገለልተኛ ታዛቢዎች ምርጫውን "ሰላማዊ "ሲሉ ገልጸውታል፡፡

የብሔራዊ ፓርቲው የዋዳኒ ፕሬዚደንታዊ እጩ አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ (ኢሮ) 63 ነጥብ 92 ከመቶውን የመራጭ ድምጽ ያገኙ ሲሆን ፕሬዚደንት ቢሂ 34 ነጥብ 81 ከመቶ፡ ሦስተኛው እጩ 0 ነጥብ 74 ከመቶውን ማግኘታቸውን የሶማሊላንድ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሴ ሀሰን ዩሱፍ ሐርጌሳ ላይ ይፋ አድርገዋል፡፡

የ69 ዓመቱ ኢሮ ለአምስት ዓመት ሶማሊላንድን ሊመሩ እ አ አ ታሕሳስ 13 ቀን ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ፡፡

ብሐራዊ የምርጫ ኮሚሽኑ የምርጫውን ውጤት እንዲያጸድቅ ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ እንደሚያቀርበው ተመልክቷል፡፡

የሶማሊላንድ ምርጫ እአአ በ2022 ዓም ሊካሂድ ታቅዶ የነበረ ሲሆን በፖለቲካ ልዩነቶች የተነሳ እስካሁን ዘግይቷል፡፡

እአአ በ2017 በተካሄደው በቀደመው ምርጫ የዋዳኒ ፓርቲውን መሪ አሸንፈው ስልጣን የያዙት ቢሂ የምርጫውን ውጤት አከብራለሁ ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለተመራጩ ፕሬዚደንት የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላልፉል፡፡

ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

#የሳንባ እብጠት (lung Abscess)

የሳንባ እብጠት በታዳጊ ሀገሮች ላይ የተለመደ በሽታ መሆኑ ይነገራል፡፡

የሳንባ እብጠት በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊከሰት እንደሚችል ይነሳል፡፡ነገር ግን ይህ ችግር በልጆች ላይ የመከሰት እድሉ አነስተኛ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡

እንዲሁም ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ በብዛት እንደሚታይ ባለሙያዎች ያናገራሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ህክምና ክፍል ሀላፊ ፣የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስ እና የሳንባ እና ፅኑ ህሙማን ሰብስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አምሳሉ ቢተውን ናቸው፡፡

የሳንባ እብጠት ምንድን ነው?

ሳንባ ላይ ከተለመደው ሌላ የሰውነት ክፍል መስሎ የሚታይ ነገር ካለ የሳንባ እብጠት እንለዋለን ይላሉ፡፡

መንስኤው ምንድን ነው?

- የባክቴሪያ ኢንፌክሽን
- ቲቢ(የሳንባ ነቀርሳ)
- የፈንገስ ኢንፌክሽን
- የሳንባ መቆጣት ህመሞች
- የሳምባ ካንሰር ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

አንዳንድ የሳንባ እብጠቶች ምልክት ላይኖራቸው እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡

እብጠቱ እያደገ ሲሄድ ግን ከሚታዩ ምልክቶች መካካል

- ውጋት
- ሳል
- ሀክታ
- ድካም
- የደረት ውጋት
- ትንፋሽ ማጠር ሊኖር ይችላል

መከላከያ መንገዶቹ ምንድን ናቸው ?

- የስራ ተጋላጭነትን መቀነስ(ፋብሪካ፣ኮንስትራክሽን እና ብናኝ ያለበት ቦታ የሚሰሩ ሰዎች)
- ሲጋራ ማጨስ ማቆም
- የአየር ብክለት መቀነስ
- አላስፈላጊ ስሜት ሲሰማን ክትትል ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

- መንስኤው ምን እንደሆነ ማጣራት
- ራጅ፣ ሲቲስካን፣ደም ምርመራ
- የሳንባ ናሙና

መንስኤው ከታወቀ በኃላ እንደየ መንስኤው ህክምናው ይሰጣል፡፡

በመጨረሻም ሰዎች እንደዚህ አይነት ችግር ሲገጥማቸው መደናገጥ ሳይሆን ወደ ህክምና ተቋም ሄዶ ተገቢውን ህክምና ማድረግ እንደሚያስፈልግ ዶ/ር አምሳሉ ተናግረዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ኀዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

26 የገጠር ከተሞችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አድርጊለሁ አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በተጠናቀቀው የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት 26 የገጠር ከተሞችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በማድረግ የዕቅዱን 84 በመቶ ማሳካት ችያሁ ብሏል፡፡

ተቋሙ 120 ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ 90 ሺህ 573 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ተናግሯል፡፡

በተጠናቀቀው ሩብ አመት ከልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 11.15 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ከኢነረጂ ሽያጭ 8.2 ቢሊዮን ብር እና ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ 183 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጻል፡፡

ተቋሙ ካሉት የድህረ ክፍያ ደንበኞች ውስጥ 87.1 በመቶ የሚሆኑ ደንበኞች በተዘረጉ ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸውን እየከፈሉ እንደሚገኙም አሳውቋል፡፡

በሩብ አመቱ 40 ሺህ 634 ስማርት ቆጣሪዎችን ለመግጠም ታቅዶ 38 ሺህ 435 ስማርት ቆጣሪዎችን በመግጠም 92.56 በመቶ ተሳክቷል፡፡

የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት፣ የሃይል ብክነት፣ የወሰን ማስከበር ችግር፣ የግብዓት እቃዎች ዋጋ መናር፣ የኤሌክትክ መሰረተ ልማት ስርቆት፣ የፕሮጀክቶች አፈጻፀም መጓተት እና የሃይል ማከፋፈያ ጣቢዎች መሙላት በሩብ አመቱ የታዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶች እንደነበሩም ገልጻል ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ይጠቁሟል፡፡

ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አለም በአሜሪካ ምክንያት የኒዉክሌር ጦርነት እንደተደቀነባት ኪም ተናገሩ

የሰሜን ኮሪያዉ መሪ ኪም ጆንግ ኡን አለም በተለይም የኮሪያ ልሳነ ምድር ከመቼዉም ጊዜ በላይ የኒዉክሌር ጦርነት እንደተጋረጠባት ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ የምትባል አገር አርፈዉ የተቀመጡ መንግስታትን እየነካካች በአለም ላይ አዉዳሚ ጦርነት እንዲቀሰቀስ እየጣረች ነዉ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

በዚህም የኮሪያ ልሳነ ምድር ብቻም ሳትሆን አለም የኒዉክሌር ጦርነነት ዋዜማ ላይ እንደምትገኝ አስታዉቀዋል፡፡

ፕዮንግያንግ ሰላምን ፈልጋ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ልዩነት ለማጥበብ ብትሞክርም ሳይሳካ እንደቀረም አንስተዋል፡፡

አለም ላይ እየተካሄዱ ላሉ ጦርነቶች በአሜሪካ ምክንያት የተቀሰቀሱ መሆናቸዉን ኪም ተናግረዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ ሉአላዊነቷ አደጋ ዉስጥ የሚወድቅ ከሆነ ኒዉክሌር እንደምትጠቀምም ማስጠንቀቃቸዉን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

አባቱ መረቀ

ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከ አምስት መቶ ሰማንያ ቢሊየን በላይ ብር  ለተጨማሪ በጀት እና ለወጪ አሸፋፈን አፀደቀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔን አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል  በፌዴራል መንግስት የተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ አዋጅን የተመለከተው አንደኛው ነው፡፡

በዚሁ መሰረት ለመደበኛ ወጪዎችና የወጪ አሸፋፈን ለማስተካከል የሚውል /አምስት መቶ ሰማንያ አንድ ቢሊዮን፤  ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሁለት ሚሊዮን፤ ሶስት መቶ ዘጠና ሺህ አንድ መቶ አስራ ሰባት ብር/ ተጨማሪ በጀት ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የተጨማሪ በጀትና የወጪ ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

የተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያው የተሻሻለውን የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ማስፈጸም በሚያስችል መልኩ የመንግስት የፋይናንስ አቅምና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ፣ የተጨማሪ በጀት ታሳቢዎችንና የወጭ ታሳቢዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ተዘጋጅቷል ሲል ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የቼልሲው ጄምስ አዲስ ጉዳት አጋጥሞታል

ሪስ ጄምስ ባጋጠመው ቀለል ያለ ጉዳት ምክንያት ከሌስተርሲቲው ጨዋታ ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ አረጋግጠዋል ።

የቼልሲው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በጉዳት ላይ፡ "አንድ የተጎዳ ተጫዋች ብቻ ነው ያለን እሱም ሬስ ጄምስ ትንሽ ነገር ተሰምቶት ነበር እናም ምንም አይነት ስጋት ልንወስድ አንፈልግም።
"በእርግጠኝነት የተጎዳው እሱ ብቻ ነው። የተቀሩት፣ አንዳንዶቹ የተሻሉ ናቸው፣ አንዳንዶቹ አሁንም ጥርጣሬዎች ናቸው፣ ማየት አለብን።

"የጡንቻ ችግር ነው እና ምንም አይነት አደጋ መውሰድ አንፈልግም።" ማሬስካ ለአጭር ጊዜ የሚደርስ ጉዳት መሆኑን ገልጿል።

ጋዲሳ መገርሳ

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአለም አቀፉ የወንጀኞች ፍርድ ቤት በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል፡፡

የአይሲሲ ፍርድ ቤት ኔታንያሁ እና ጋላንት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ጥፋተኛ አድርጓቸዋል፡፡

ይህም ረሃብን እንደ የጦር መሳሪያ መጠቀም ፣ ግድያ፣ ስደት እና ኢሰብአዊ ድርጊቶች መፈጸምን ይጨምራል።

ቢቢሲ በሰበር ዜናው እንዳለው ይህ ማለት ኔታንያሁ እና ጋላንት የሮም ስምምነት ፈራሚ የሆኑትን 120 ሀገራት መጎብኘት አይችሉም ።


ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስወረድና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ዛሬ ተጀምሯል

የመጀመሪያው ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝድ በማድረግ ወደ ስልጠና ማእከላት የማስገባት ስራ በመቐለ ከተማ ነው በይፋ የተጀመረው፡፡

በመጀመሪያ ዙር በክልሉ 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ስልጠናና የማቋቋምያ ገንዘብ በመስጠት ወደ ህብረተሰቡ የማቀላቀል ስራ ይሰራል።

በአሁን ሰዓት ታጣቂዎች የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የትግራይ ክልል የፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ አመራሮች ፣ የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪዎች እና ሚድያዎች ፊት የታጠቁትን ቀላል መሳሪያ እያስረከቡ ነው።

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በትግራይ ክልል ያለው ማህበራዊ ቀውስ ከጊዜ ጊዜ ወደ ከፋ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው ተባለ

ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ በትግራይ ያለው ማህበራዊ ቀውስ እና የመልካም አስተዳደር ችግር ከጊዜ እየተባባሰ መጥቷል ሲሉ ትዴፓ ገልጿል።

የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ገብረ ጊዮርጊስ ግደይ፣ በክልሉ ያለው የመልካም አስተዳደር ችግር የተራዘመ የማህበራዊ ቀውስ ችግር እንዲኖር አድርጓል ብለዋል።

በተለይም በክልሉ የሚገኙ የጊዜያዊ አስተዳደሩም ይሁን የህውሀት እና ትጥቅ ያልፈቱ አካላት በማህበረሰቡ ላይ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ ብለዋል።

የክልሉ ነዋሪ በኑሮ ውድነት ተፈትኗል ስደትን የመጨረሻ አማራጭ አርጎ እየተሰደደ እንደሚገኝ ያነሱት አቶ ገብረጊዮርጊስ በክልሉ ወጥቶ ሰርቶ መግባት ቅንጦት ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ያለውን ቀውስ ለመፍታት "ሁሉንም ያማከለ አካታች ውይይት ሊኖር ይገባል" ሲሉ ገልፀዋል።

በሌላ መልኩ ከጣቢያች ጋር ቆይታ የነበራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፀሀዬ እምባዬ ከክልሉ ነዋሪ የተለያዩ ቅሬታዎች እንደሚደርሴቸው ተናግረዋል።

ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ሂደት በመንግስት መስሪያ ቤት የሚገኙ ሀላፊዎ እንቅፋት እንደሆኑም አንስተዋል ።

ለአለም አሰፋ

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሩብ አመቱ ከ168.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ህገወጥ የመድሃኒት ምርቶች ተገኝተዋል ተባለ፡፡

ባለፈው 3 ወር ውስጥ ከ168.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ህገወጥ የመድሃኒት ምርቶች ከ127 ተቋማት በመሰብሰብ የተለያዩ እርምጃዎች መውሰዱን የኢትዮጲያ ምግብ እና መድሀኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

በኮንሶ፣ ጅማና አዲስ አበባ ከተማ ከጉምሩክ ኮሚሽን፣ ከክልልና ፌዴራል ፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን በተካሄደ የቁጥጥር ስራ የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ እና ተመሳስለው የተሰሩ ከ39.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የወባ መድኃኒቶች መያዛቸውን ጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ከ8.4ሚሊዮን ብር በላይ የሚወጣ ምርት መወገዱንም ተነግሯል፡፡

በ10 የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አምራች ተቋማት ላይ የቁጥርር ስራውን ማከናወን መቻሉን እና በተመሳሳይ በ219 የመድኃኒት አስመጪ እና አከፋፋዮች፣ በ18 ጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ የሚያመርቱ ድርጅቶች ላይ ስጋት ተኮር ክትትል ተካሂዷል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አሜሪካ በኪዬቭ የሚገኘውን ኤምባሲዋን በጊዜያዊነት ዘጋች

አሜሪካ ሩሲያ በዩክሬን የአየር ጥቃት ልታደርስ ትችላለች በሚል ፍራቻ በኪዬቭ የሚገኘውን ኤምባሲዋን በጊዜያዊነት መዘጋቷን አስታውቃለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ዛሬ ሩሲያ በኪዬቭ  የአየር ጥቃት ልታደርስ እንደምትችል ተጨባጭ መረጃ እንዳገኘ እና ኤምባሲው በጊዜያዊነት እንደሚዘጋ አስታውቋል።

በኪዬቭ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ፣ ኤምባሲው የሚዘጋበት ምክንያት ለቅድመ ጥንቃቄ ሲባል እንደሆነ እና የኤምባሲው ሰራተኞችም የአየር ማስጠንቀቂያ በሚሰጥበት ጊዜ ከአደጋ መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ ማሳሰቡን አይሪሽ ኤግዛማይነር ዘግቧል።

ልኡል ወልዴ

ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የትግራይ ክልል ነጋዴዎች ጥያቄ ፓለቲካዊ ውሳኔ እንዲሰጥበት ተጠየቀ፡፡

የትግራይ ነጋዴዎች አቤቱታ ፖለቲካዊ ዉሳኔ እንዲያገኝ የፊርማ ማሰባሰቢያ እየተደረገ ነዉ ፡፡

ይህ ፊርማ ማሰባሰቢያ በትግራይ የሚገኙ ነጋዴዎች እና ባለሀብቶች በጦርነቱ ወቅት ያልከፈሏቸዉ ብድሮችን ከነወለዱ እንዲከፍሉ በባንኮች መገዳደቸዉን ተከትሎ ነዉ።

የትግራይ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት እና የግሉ የንግዱ ዘርፍ ማህበረሰብ በጋራ በመሆኑ በክልሉ በሚገኙ 40 ያህል ከተሞች ላይ ያሉ ነጋዴዎች የፊርማ ማሰባሰቢያ መደረጉን ኢትዮ ኤፍኤም ሰምቷል።

ጣቢያችን ያነጋገራቸዉ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ የትግራይ ንግድ እና ዘርፍ ማህበር ባለሙያ እንደገለፁት ይህ አቤቱታ ለክልሉም ሆነ ለፌደራሉ መንግስት ቢቀርብም መፍትሄ አልተሰጠበትም ብለዋል።

ስለሆነም ጉዳዩ በባንኮቹ አቅም ሊፈታ የማይችል በመሆኑ ፖለቲካዊ ዉሳኔ ማስፈለጉን ባለሙያዉ ነግረዉናል።

ይህ የፊርማ ማሰባሰቢያ ሂደት የሚመለከተዉ የፊደራሉ መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት ፍትሀዊ ምላሽ እንዲሰጣቸዉ ለማድረግ ነዉ ተብሏል።

ባንኮች እና የንግዱ ማህበረሰብ አድርገዉት በነበረዉ ስምምነት የብድር ወለድ መክፈያ ጊዜን 1 አመት ከ6 ወር አድርጓ እንደነበር የተገለፀ ቢሆንም ለስራ ማስኬጃ ይሰጣችኋል የተባለዉ ብድር አለመሰጠቱ ተነግሯል።

ባለሙያዉ በአሁኑ ወቅት ለነጋዴዎቹ የተቀመጠዉ የመክፈያ ጊዜ ሁለት ወራት እንደቀሩት ተናግረዋል።

ነጋዴዎች ዳግም ወደ ስራቸዉ ለመመለስ የሚችሉበት ሁኔታ ያልተፈጠረ በመሆኑ ለጉዳዩ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየተሰራ መሆኑን ሰምተናል።

ቁምነገር አየለ
ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ .ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የራፋኤል  ናዳል  የመጨረሻ  ስሜቶች

ጡረታ የወጣው ድንቅ ኮከብ ራፋኤል ናዳል በአስደናቂ ህይወቱ የመጨረሻ ውድድር ላይ ስፔን የዴቪስ ዋንጫን እንድታሸንፍ በማሰብ በስሜታዊነት አይዘናጋም ብሏል።

የ22 ጊዜ የግራንድ ስላም ሻምፒዮን የሆነው ናዳል ሀገሩን ወክሎ በማላጋ በሚካሄደው የወንዶች ቡድን ውድድር ከቴኒስ ጡረታ ይወጣል።

ስፔን  በሩብ ፍፃሜው ከኔዘርላንድስ ጋር ትጫወታለች ነገርግን የ38 አመቱ ናዳል በቂ ሚና መጫወት ይችል እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

የቀድሞው የአለም ቁጥር አንድ ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት የተለያዩ ጉዳቶችን ካስተናገደ በኋላ በዚህ አመት ሰባት ውድድሮችን ብቻ አድርጓል። 

ባለፈው ወር እዚህ ለመልቀቅ ማሰቡን ያስታወቀው ናዳል "እኔ ለጡረታ አልመጣሁም። እዚህ የመጣሁት ቡድኑ እንዲያሸንፍ ለመርዳት ነው" ብሏል።
"የቡድን ውድድር ነው እና በጣም አስፈላጊው ነገር ሁላችንም ማድረግ ያለብን ነገር ላይ ማተኮር ነው - ይህ ቴኒስ በመጫወት እና በጥሩ ሁኔታ መስራት ነው።  ናዳል ለሀገሩ በአምስት የዴቪስ ካፕ ድሎች ትልቅ ሚና የተጫወተ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ስራውን ለመጨረስ ትክክለኛው መንገድ ነው።
ስፔን ኔዘርላንድስን ካሸነፈች አርብ ከጀርመን ወይም ካናዳ ጋር ወደ ግማሽ ፍፃሜ ትገባለች።

የመጨረሻው እሁድ ይካሄዳል

ስፔን በፈረንሳይ ኦፕን እና የዊምብልደን ሻምፒዮን ካርሎስ አልካራዝ የሚመራ ጠንካራ ቡድን አላት ፣ ከሮቤርቶ ባውቲስታ አጉት ፣ ፔድሮ ማርቲኔዝ - ሁለቱም በኤቲፒ ነጠላ 50 ምርጥ ውስጥ ተቀምጠዋል - እና ድርብ ስፔሻሊስት ማርሴል ግራኖለርስ ቡድኑን ያጠናቀቀ።

ከአለም 154ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ናዳል ሀሙስ ማላጋ የገባ ሲሆን ባለፉት ሶስት ቀናት ከሌሎች የቡድኑ አባላት ጋር ልምምዱን ሲሰራ ቆይቷል።
የስፔናዊው ካፒቴን ዴቪድ ፌረር በነሀሴ ወር መጀመሪያ ላይ በፓሪስ ኦሊምፒክ የረዥም ጊዜ ተቀናቃኙ ኖቫክ ጆኮቪች ከደረሰበት አስከፊ ሽንፈት በኋላ ያልተጫወተው ናዳል ዝግጁ ከሆነ “እስካሁን አላውቅም” ብሏል።

"ነገን ታውቃለህ። ለጊዜው የሚጫወቱትን ተጫዋቾች አልወሰንኩም" ሲል ፌሬር ተናግሯል።
ብዙ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች በጉዞ አሰልጣኝ ላይ ሲወጡ በኮስታ ደ ሶል ውስጥ የታወቀ ነው።

ይህ ግን ለናዳል የስንብት ትዕይንት መጀመሪያ ወደ Fuengirola ልዩ የማለዳ ጉዞ ነበር።
ፌደረር እና ናዳል እ.ኤ.አ. በ2022 የስዊዘርላንዱ ኮከብ በላቨር ካፕ ጡረታ ሲወጣ እጅ ለእጅ ተያይዘው አለቀሱ።

የቢቢሲ ስፖርት

ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel