ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

የሳንባ እብጠት (lung Abscess)

የሳንባ እብጠት በታዳጊ ሀገሮች ላይ የተለመደ በሽታ መሆኑ ይነገራል፡፡

የሳንባ እብጠት በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊከሰት እንደሚችል ይነሳል፡፡ነገር ግን ይህ ችግር በልጆች ላይ የመከሰት እድሉ አነስተኛ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡

እንዲሁም ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ በብዛት እንደሚታይ ባለሙያዎች ያናገራሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ህክምና ክፍል ሀላፊ ፣የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስ እና የሳንባ እና ፅኑ ህሙማን ሰብስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አምሳሉ ቢተውን ናቸው፡፡

የሳንባ እብጠት ምንድን ነው?

ሳንባ ላይ ከተለመደው ሌላ የሰውነት ክፍል መስሎ የሚታይ ነገር ካለ የሳንባ እብጠት እንለዋለን ይላሉ፡፡

መንስኤው ምንድን ነው?

- የባክቴሪያ ኢንፌክሽን
- ቲቢ(የሳንባ ነቀርሳ)
- የፈንገስ ኢንፌክሽን
- የሳንባ መቆጣት ህመሞች
- የሳምባ ካንሰር ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

አንዳንድ የሳንባ እብጠቶች ምልክት ላይኖራቸው እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡

እብጠቱ እያደገ ሲሄድ ግን ከሚታዩ ምልክቶች መካካል

- ውጋት
- ሳል
- ሀክታ
- ድካም
- የደረት ውጋት
- ትንፋሽ ማጠር ሊኖር ይችላል

መከላከያ መንገዶቹ ምንድን ናቸው ?

- የስራ ተጋላጭነትን መቀነስ(ፋብሪካ፣ኮንስትራክሽን እና ብናኝ ያለበት ቦታ የሚሰሩ ሰዎች)
- ሲጋራ ማጨስ ማቆም
- የአየር ብክለት መቀነስ
- አላስፈላጊ ስሜት ሲሰማን ክትትል ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

- መንስኤው ምን እንደሆነ ማጣራት
- ራጅ፣ ሲቲስካን፣ደም ምርመራ
- የሳንባ ናሙና

መንስኤው ከታወቀ በኃላ እንደየ መንስኤው ህክምናው ይሰጣል፡፡

በመጨረሻም ሰዎች እንደዚህ አይነት ችግር ሲገጥማቸው መደናገጥ ሳይሆን ወደ ህክምና ተቋም ሄዶ ተገቢውን ህክምና ማድረግ እንደሚያስፈልግ ዶ/ር አምሳሉ ተናግረዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ የደቡባዊ ሊባኖስ ነዋሪዎች ወደቄያቸው እየተመለሱ ነው ተባለ

በሄዝቦላና በእስራኤል መካከል የተኩስ አቁም መታወጁን ተከትሎ የደቡባዊ ሊባኖስ ነዋሪዎች ወደቄያቸው እየተመለሱ ነው ተብሏል ።

የእስራኤል ጦር ሌሎች ተጨማሪ መመሪያ እስኪሰጥበት ድረስ የሊባኖስ ህዝብ ወደ ስፍራው ከመመለስ እንዲቆጠብ ሲል እያስጠነቀ ይገኛል።

ይሁን እንጅ በርካታ ነዋሪዎች ወደ መኖሪያ መንደራቸዉ በመመለስ ላይ መሆናቸዉን ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

በሊባኖስ ያለዉን ቀዉስ ለማስቆም በአሜሪካ አደራዳሪነት ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ መድረሳቸዉ ይታወቃል፡፡

ልዑል ወልዴ

ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ እስካሁን አንድም ትምህርት ቤት ያልተከፈተባቸው 17 ወረዳዎች መኖራቸውን መግለጡን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ትምህርት ቢሮው ዘንድሮ ከቅድመ አንደኛ እስከ ኹለተኛ ደረጃ ድረስ 7 ሚሊዮን 71 ሺሕ 933 ተማሪዎች ለመመዝገብ አቅዶ፣ እስካሁን የመዘገበው 2 ሚሊዮን 543 ሺሕ 128 ተማሪዎችን ብቻ እንደኾነና ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች አኹንም ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደኾኑ ገልጧል ተብሏል።

ትምህርት ቤቶች በታጠቁ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና የመምህራን ግድያ መኖሩም በትምህርት ላይ ጫና እንዳሳደረ ቢሮው መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

8ተኛውን ኦዳ አዋርድ ህዳር 27 ይካሄዳል ተባለ

8ተኛው የኦዳ አዋርድ የፊታችን ህዳር 27 2017ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል ሊካሄድ መሆኑን አዘጋጆቹ አስታውቋል ፡፡

የኦዳ አዋርድ አለማ በሃገራችን በሁለም ቋንቋዎች የሚሰሩ የኪን ጥበብ ስራዎች እኩል እድል አግኝተው እንዲበረታቱና ለኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲወጡ ለማስቻል እንደ ሆነ ተገልጿል::

በእለቱ ከተለያዩ የጥበብ ዘርፎች የተወጣጡ ከ60 በላይ እጩዎች ይቀርባሉ የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ተለይተው ይሸለማሉ ተብሏል።

በዝግጅቱ ከሀገራችን የኪነ ጥበብ ስራዎች ባሻገር ከምስራቅ አፍሪካ ስምንት ሀገራት ለተወጣጡ ኮኮብ ሙዚቀኞች እውቅና እንደሚሰጠም ሰምተናል::

በዚህም ኢትዮዽያውያን ጥበበኞች ከአፍሪካውያን አቻቸው ጋር ተቀራርቦ ለመሰራት መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል መባሉም ተገልጿል::

ለዚህ አመት ለሽልማት የሚበቁ እጩ ስራዎች በ2016ዓ.ም ከመስከረም 1 እስከ ጳጉሜ 5 የተሰሩ ብቻ ይሆናሉ፡፡

ይህ ኦዳ አዋርድ የተሰኘው የሽልማት መረሃግብር የተዘጋጀው በበሻቱ ቶሌ ማሪያም መልቲ ሚዲያና ከኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ጋር በመተባበር ነው ተብሏል።

አቤል እስጢፋኖስ

ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የጤና መድህን ታካሚዎች የላብራቶሪ ምርመራ ላይ በቂ አገልግሎት እያገኙ አይደለም ተባለ

በአዲስ አበባ ከተማ የጤና መድህን ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎች ለህክምና ምርመራዎች በቂ አገልግሎት ለማግኘት ይቸገራሉ ተብሏል።

የጤና መድህን ታካሚዎች በህክምና ተቋማት ላይ የላብራቶሪ ምርመራ ማግኘት ባለመቻላቸዉ ለተጨማሪ ወጪ መዳረጋቸዉን በቅሬታ አንስተዋል።

ጣቢያችን በ ጉዳዩ ላይ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለን ያነጋገረ ሲሆን በጤና ተቋማቱ ላይ የማሽን መበላሸት ÷ የግብአቶች እጥረት እና መቆራርጥ ምክንያት ታካሚዎች ከዉጪ እንዲያሰሩ ይደረጋል ብለዋል።

ሆኖም ይህ የምርመራዉ መስተጓጓል በመደበኛዉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጫና ፈጥሮብናል ሲሉ ተናግረዋል።

በከተማዋ ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ላይ ያሉ ትልልቅ ማሽኖች ያሉ ቢሆንም ፤ለላብራቶሪ ምርመራው የሚያስፈልጉ ግብአቶች አለመገኘት ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል።

ሆኖም በጤና ተቋማቱ ታካሚዎች በብዛት የሚፈልጓቸዉ በአማካኝ ሊይዟቸዉ የሚገቡ ምርመራዎችን መለየት እና ማሻሻል እንዲቻል ለ ማድረግ እየተሞከረ ነዉ ተብሏል

ጤና ቢሮዉ ከጤና ሚኒስትር ጋር በመሆን ይህንን ክፍተት ለመሙላት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ዶ/ር ሙሉጌታ የተጠቃሚ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከግል ተቋማት ጋር ተነጋግሮ ለመስራት እየታቀደ ነዉ ብለዋል።

ከተቋማቱ ጋር ለሚደረጉ ስምምነቶች መመሪያዎች እየተዘጋጀ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

በተያያዘም የመድኃኒት አቅርቦት እጥረትን ለመቀነስ ቢሮዉ ከከነማ መድሀኒት ቤቶች ጋር ከስምምነት ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህ አመት በጤና መድህን አገልግሎት ሽፋን 380 ሺ እማወራ እና አባወራ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል።

ቁምነገር አየለ

ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ምክር ቤቱ 582 ቢሊየን ብር ተጨማሪ የፌደራል መንግስት በጀት አድርጎ አፀደቀ

ለምክር ቤቱ የቀረበው ተጨማሪ የፌደራል መንግስት በጀት አልበዛም ወይ የሚል ጥያቄም መቅረቡ ተሰምቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በገበያው ውስጥ የዋጋ ግሽበትን አያስከትልም ወይ? ከተጨማሪ በጀት ውስጥ 282 ቢሊየን ብር ከግብር የሚሰበሰብ ከሆነ በግብር ከፋዮች ላይ ጫና አያሳድርም ወይ? የሚሉት ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

የፀደቀው ተጨማሪ በጀት ለውጭ እና ለሀገር ውስጥ ዕዳ ክፍያ፣ ለማህበራዊ በጀት ድጎማ (ለማዳበሪያ፣ ለመድሐኒት፣ ለምግብ ዘይትና ሌሎች)፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፋፊያ፣ ለማህበራዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም እና ለመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ማሻሻያ እንደሚውልም የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ በጀቱ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያካሄደቸውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ የሚገኘው በጀት በመጨመሩ ምክንያት መሆኑን የመንግስት ተጠሪዉ አስረድተዋል፡፡

ለ2017 በጀት አመት ከቀረበው 582 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪ 393 ቢሊየን ብር፣ ለካፒታል ወጪ 70 ቢሊየን ብር፣ ለወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ 119 ቢሊየን ብር መሆኑም ተገልጿል፡፡

ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ የቀረበው ተጨማሪ በጀት 120 ሚሊየን ህዝብ ላላትና በኢኮኖሚ በማደግ ላይ ላለች ሀገር ብዙ የሚባል እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡

የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ከጨመረ በቀጣይ በጀት አመት ከዚህ የበለጠ በጀት ሊቀርብ እንደሚችልም ነዉ የተናገሩት፡፡

ተጨማሪ በጀቱ ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ ከሚገኝ ገቢ የሚሸፈንና ዝቅተኛ ተከፋይ ለሆኑ የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም ለሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የሚውል በመሆኑ በዋጋ ግሽበቱ ላይ ለውጥ እንደማያመጣም አቶ አህመድ ሺዴ አብራርተዋል፡፡

ምክር ቤቱ የፌደራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅን አዋጅ ቁጥር 1355/2017 አድርጎ በሶስት ተቃውሞ እና በአምስት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቆታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

"የምዕራቡ ዓለም ቁጣ አጫሪ ተግባር ሩሲያ ምላሽ እንድትሰጥ እያስገደዳት ነው፣ ይህም ዓለም በኒውክሌር ለመጥፋት አፋፍ ላይ መሆኖን አመላካች ነው"ተባለ

የቀድሞ የአሜሪካ የስለላ መኮንን ስኮት ሪተር ከአንድ ታዋቂ የዩቲዩብ ፔጅ ጋር ባደረገው ንግግር ፤የምዕራቡ ዓለም ቁጣ አጫሪ ተግባር ሩሲያ ምላሽ እንድትሰጥ እያስገደዳት ነው፣ ይህም ዓለም  በኒውክሌር የምትጠፋበትን ቀን  እያቀረበው ነው ሲል ተናግረዋል።

የቀድሞ የአሜሪካ የስለላ መኮንን በዚሁ በርካቶች ባለስልጣናትን ለውይይት በሚያቀርበው የዩቲዩብ ቻናል ላይ ፤" ትንሽ የኒውክሌር ልውውጥ የሚባል ነገር የለም፤ዝቅተኛ ገደቦች የኒውክሌር ጦርነት የሚባል ነገርም የለም፤እነዚያ ኒውክሌር አንዴ ከፈነዱ በፍጥነት ከቁጥጥር ውጭ ይሆናሉ " ነው ያለው።

ይህ ደግሞ"አንዴ ኒውክሌር ፈነዳ ማለት ከ72 ደቂቃዎች በኋላ ሁላችንም እንሞታለን፤ ይሄም አሁን ያለንበትን ቦታን አመላካች ነው በመሆኑ በቶሎ መላ ሊበጅለት ይገባል ሲል ተናግሯል።ከመቼውም ጊዜ ይልቅ  ወደ ኒውክሌር ግጭት ተቃርበናል"ብሏል።

እንደ ሪትተር ገለጻ፣ በአሜሪካና በሩሲያ መካከል ትንሽ "የኒውክሌር ልውውጥ" ሀሳብን ማቅረብ ለሞት የሚዳርግ ስህተት ነው።

"ይህ ልውውጥ" ማለት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሞቱ መልቀቅም ነው ሲል አሳስበዋል ።


በመሆኑ ቁጣ አጫሪ ከሆነው እርምጃ ሊቆጠቡ ይገባል ሲል ገልጿል ።



ልዑል ወልዴ

ኀዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን ለ19ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ከዛሬ ጀምሮ ይከበራል።

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን በአገራችን ለ19ኛ ጊዜ “የሴቷ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ህዳር 16 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚከበር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ ሂክማ ሄይረዲን፤ የቀኑ አከባበር አጠቃላይ ዓላማ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች አስከፊነት ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር ፆታዊ ጥቃት እንዲቀንስ እና እንዲወገድ ለማድረግ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ጥቃት የደረሰባቸውንም ዜጎች ለመደገፍ ታስቦ እንደሚከበር ገልጸዋል።

በቀጣይ ለ16 ተከታታይ ቀናትም በሁሉም ዩንቨርስቲዎችና ትምህርት ቤቶች፣ በሀይማኖት ተቋማት፣ በመስሪያ ቤቶች እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት ጥቃትን እንዲከላከሉና እንዲያወግዙ የንቅናቄ ዘመቻ የማድረግ እና ሀብት የማሰባሰብና ድጋፍ የማድረግ ስራዎች እንደሚሰሩም አንስተዋል።

በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፤ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የአገልግሎት ሥርዓትን በመዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ በተጎጂዎች ላይ የሚደርሰውን የጤና፣ ማህበራዊና ሥነ - ልቦናዊ  ክፍተቶችን ለመቅረፍ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው፤ ወደፊትም ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም ሚኒስትር  ድኤታዋ ሁላችንም ጥቃትን ለመከላከል እና ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም በጋራ መረባረብ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ኀዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለአክሱም ፅዮን ማርያም ክብረ በዓል  1 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶች እንደሚገኙ ይጠበቃል ተባለ

የአክሱም ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገብረ መድህን ፍፁም ብርሀን  ለዓመታዊው የአክሱም ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል 1 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶች እንዲሚጠበቁ ተናግረዋል።

የቱሪዝም ፅ/ ቤቱ ለጣቢያችን እንደገለፀው  በህዳር 21 በሚከበረው የንግስ በአል ላይ  5 ሚሊዮን ብር ገቢ ይገኛል የሚል ዕቅድ መያዙን ገልጿል።

ቢሮው የከተማውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከሚደግፉ ነገሮች አንዱ የአክሱም ፂዮን የንግስ በአል እንደሆነ ገልፆ  በዚህም የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙም አንስቷል።

ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ተቀዛቅዞ የነበረውን የከተማዋን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለመመለስ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

  የአየር መንገዱም እድሳት ትልቅ ግብአት እንደሆነም ተመላክቷል።

ለበኡሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል የከተማ አስተዳደሩ ከከተማው ህዝብ ጋር በመሆኑ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙም አሰምተናል ።

ለአለም አሰፋ

ኀዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

1ሺህ ቤቶችን እየገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪልእስቴት ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።

ከተመሰረተ ሁለት አመታት ያስቆጠረው ሪልእስቴት  ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት አምባሳደር  አድርጎ መርጧል።

በአማራ ክልል ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪልእስቴት የቤት ፈላጊዎችን ምርጫ ያሟላና ዘመናዊ መንደር እየፈጠረ የሚገኝ ተቋም መሆኑ ተነግሯል።

በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ከተማ በ230ሺህ ካሬ ሜትር ላይ እየገነባ ያለው ግዙፍ የመኖርያ መንደር 1ሺህ ቤቶችን እየገነባ እንደሚገኝ አስታውቋል።


እንዲሁም አለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት በማሰብ እና ከኢትዮጵያ ደንበኞች በተጨማሪም በሰሜን አሜሪካና ካናዳ እንዲሁም እንግሊዝ ፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በስፋት እንዲቀሳቀስ ያመቸው ዘንድ ነው እጸገነት ይልማን አምባሳደር አድርጎ የመረጠው።

ሊዲያ ደስአለኝ

ኀዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አዋሽ ባንክ  አ.ማ  11 ቢሊዮን ብር የተጠጋ ትርፍ ማስመዝገቡን ገለፀ

ይህ የተገለፀው ባንኩ 29ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን  ባካሄደበት ወቅት ነው።

አዋሽ ባንክ አ.ማ በዚህ   በ2023/24 እ አ አ የሂሳብ ዓመት 10.8 ቢሊዮን ብር  ትርፍ ማስመዝገቡ   የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጉሬ ከምላ ለጉባኤው አጠቃላይ ዓመታዊ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ተመላክቷል።

በዚህም በዓመቱ ውስጥ ባንኩ 45,1 ቢለዮን ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡንና ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ24 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት የባንኩ የብድር መጠን ካለፈዉ ዓመት  ወቅት አንፃር 21.6 ቢሊዮን ብር  ወይም በ13.3 በመቶ ዕደግት ያሳየ ሲሆን የባንኩ አጠቃላይ የብድር መጠንም 183.5 ቢሊየን ብር አድርጓል።

በሂሳብ ዓመቱ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ 36.58 ቢሊየን  ብር ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ7.77 ቢሊየን ብር  ወይም የ27 በመቶ ዕድገት ማሳየቱም ተገልጿል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በተመለከተ ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ 1.52 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡን እና ይህም በግል ባንክ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛው መሆኑም ተመላክቷል።


 ለዓለም አሰፋ

ኀዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከልን (ካርድ) አገደ

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን፣ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) "ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆን ሲገባው፣ ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርን ጥቅም የሚጎዱ ተግባራት ላይ መሰማራቱ” በመረጋገጡ ከሥራው መታገዱን አስታወቀ።

ከካርድ በተጨማሪም ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ (AHRE) የተሰኘ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት በባለስልጣኑ መታገዱ ተገልጿል።

ካርድ ለመታገድ የተሰጠው ምክንያት “ከእውነታው የራቀ መሆኑን” አበክሮ በመግለጽ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ እግዱን ለመጣል እንደ ምክንያት የገለጸው የምርመራ ሒደት ስለመከናወኑ ድርጅቱ ምንም ዓይነት መረጃ ያልነበረው ከመሆኑም ባሻገር፣ ውሳኔው አስፈላጊ የሆኑትን ሕጋዊ አካሄዶችን አለተከተለም ሲል ቅሬታ አሰምቷል።

ኀዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው የኤሮ ክበብ ተመሰረተ

በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው የኤሮ ክበብ (AERO Club)የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከመወዳ ትምህርት ቤት ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው እለት መስርተዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጌታቸው መንግስቴ፤በአለም እያደገ ባለው የአቬሽን ኢንዱስትሪ የስራ ሃይል ሃብትን በጥራትና በብዛት ማምረት ተገቢ ነው ብለዋል።

በመሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤሮ ክለብን በየሀገሩ በትምህርት መስጫ ተቋማት ለማቋቋም በሂደት ላይ ነን ያሉት አቶ ጌታቸው የመወዳ ትምህርት ቤት ለዚህ አላማችን ፈርቀዳጅ በመሆን ለሌሎች ሞዴል ይሆናል ብለዋል።

ሼህ አብዱልመጂድ ሁሴን የመወዳ ትምህርት ቤት ሃላፊና ባለቤት በበኩላቸው፤የመወዳ ትምህርት ቤት በትምህርት ዘርፍ አንጋፋ ሆኖ የዘለቀና በተለይም ተማሪዎች በሚወዱት የሙያ ዘርፍ ከልጅነታቸው ጀምሮ ድጋፍ እግኝተው እንዲያድጉ እየሰራ ያለ ተቋም ነው ብለዋል።

ይህንም የልጆችን የወደፊት ህልም ለማሳካትም በተቋቋሙ የተለያዩ የሙያ ክበባትን በመፍጠር ጠንካራ እንቅስቃሴ እያደረግን ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡

ሼህ አብዱልመጂድ ሁሴን በዛሬው እለትም  ከዘርፎቹ አንዱ በሆነው የአቪዬሽን ዘርፍ ህፃናት ከመሰረቱ በእውቀት የታገዘ ድጋፍ አግኝተው እንዲያድጉ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ጋር በጋራ ለመስራት ከስምምነት የደረስነው ብለዋል፡፡

ስምምነቱ ተማሪዎች በአቪዬሽን ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችሉ የተለያዩ ማዕቀፎች ያሉት ነው።

በመሆኑም ይህ ስምምነት በትምህርት ዘርፍ ብቻ ሳይሆን እያደገ በመጣው የአቬሽን ኢንዲስትሪ እንደሀገር ብቁ  ሰራተኛን ከስር መሰረቱ ከማፍራት አንፃር የሚኖረው ፋይዳው የጎላ ነው መባሉን ጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምትዋል።

የመወዳ ትምህርት ቤት ከኬጂ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በመረጡት በተለያዩ ዘርፍ የሚያስተምር  ሲሆን ከተመሰረተ17ኛ አመት ሆኖታል ተብሏል ።

ልኡል ወልዴ

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሃማስ ባለስልጣናት ቡድኑ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለጹ፡፡

በእስራኤል እና ሄዝቦላህ የተደረሰዉ የተኩስ አቁም ስምምነት መልካም ነዉ ፤ ተመሳሳይ ስምምነት በጋዛ ይካሄዳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

በግብጽ፣ ኳታር እና ቱርክ ለሚገኙ አሸማጋዮች የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ሃማስ ዝግጁ መሆኑን ገልጸናል፤ በተጨማሪም እስረኞችን ለመለዋወጥም ስምምነት ላይ ለመድረስ ተዘጋጅተናል ሲሉ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግረዋል፡፡

ትናንት ምሽት የተደረሰዉ የተኩስ አቁም ስምምነት እስራኤል፣ ሄዝቦላህን እና የሊባኖስ መንግስትን ያካተተ ነበር፡፡

እስራኤል እና ሄዝቦላህ ካለፈዉ ዓመት ጥቅምት 8 ጀምሮ በየዕለቱ በሚባል ደረጃ ተኩስ ሲለዋወጡ ቆይተዋል፡፡ ሄዝቦላህ የፍልስጤሙን ሃማስን በመደገፍ እስራኤል ላይ በተደጋጋሚ ሮኬቶችንም ሲያስወነጭፍ ቆይቷል፡፡

በጋዛ በሃማስ እና እስራኤል መካከል የሚደረግ የተኩስ አቁም ስምምነት እና የታጋቾች ልዉዉጥ ለወራቶች የተዘጋ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ኳታር በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ስታደርግ የነበረዉን ማሸማገል ማቆሟን ገልጻ፤ሃማስ እና እስራኤል ፍቃደኝነታቸዉን ካሳዩ ግን የማሸማገል ስራዋን እንደምትቀጥል አስታዉቃለች፡፡

እሰከዳር ግርማ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት እየፈፀሙ ያሉ አካላት ተጠያቂ እንዲደረጉ ኢሰመጉ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)  የፌደራል እና የክልል መንግስታት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም ተግባራዊ እንቅስቃሴ አለማድረጋቸዉን ገልፆል።

ለዚህም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በየእለቱ እየባሰ እና አሳሳቢ ወደ ሆነ ደረጃ መጥቷል ብሏል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ግጭት ሊያስከትሉ የሚችሉ ድርጊቶች ተጠያቂነት እንዲኖራቸዉ በቀረበዉ ጥሪ ተገልፆል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ላይ የተፈፀመው ግድያ ተከትሎ እየተሰራጬ ያሉ ተግባራት የሚመለከተው የመንግስት አካል በቂ ትኩረት እንዲሰጠዉ ኢሰመጉ ጠይቋል።

እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችና የሚዲያ አካላት ግድያውንና ተከትሎ
እየተሰራጨ ያለውን ግጭት ቀስቃሽ ድርጊት ማውገዝ ይገባቸዋል ተብሏል

በተጨማሪም ተግባሩን የፈጸሙና እየፈጸሙ ያሉ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲደረጉ የውትወታ ስራ እንዲሰሩ ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል።

ኢሰመጉ በበኩሉ በጉዳዩ ላይ  በልዩ ሁኔታ ክትትልና ማጣራት እያደረገ እንደሆነ አሳዉቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

መንግስት ከታክስ ለመሰብሰብ ያቀደዉ 282 ቢሊዮን ብር የንግድ ዘርፉን በይበልጥ አለመረጋጋት ዉስጥ ሊከተዉ እንደሚችል ተነገረ

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ሲጠበቅ የነበረውን የ 2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ 582 ቢሊዮን ብር በጀት አፅድቋል።

ከዚህ በጀት ዉስጥ 282 ቢሊዮን ያህሉ ከግብር እንደሚሰበሰብ የገለፀ ሲሆን ይህም የንግድ ዘርፉን በይበልጥ አለመረጋጋት ዉስጥ እንደሚከተዉ እና የኑሮ ዉድነቱን ሊያባብሰዉ እንደሚችል ከምክርቤት አባላት ጥያቄ አስነስቷል ።

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት እንደተናገሩት " ይህ ከፍተኛ ታክስ በነጋዴው ላይ ጫና እፈጠረ ከመሆኑ በላይ የንግዱ ማህበረሰብን መደናገር" ዉስጥ በይበልጥ እየከተተው መሆኑን አስረድተዋል ።

ገቢን ለመጨመር በሚል የታክስ ጫናዉን ከልክ በላይ መለጠጥ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል እነዚሁ የምክርቤት አባላት ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴም በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ የተደረገው " ከማሻያው በፊት ባለው መቀጠል የሀገርን ኦኮኖሚ እያደሙ መቀጠል እና ወደ ለየለት የኢኮኖሚ ውድቀት የሚያመራ በመሆኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም ጊዜውን የጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል ሲል ካፒታል ዘግቧል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣ አዲሱን ራሳቸውን የሚቆጣጠሩ ድርጅቶች የዕውቅና አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ፍትሕ ሚንስቴር እንዳጸደቀለት አስታውቋል።

አዲሱ መመሪያ፣ ባለሥልጣኑ የተወሰኑ ሥልጣንና ኃላፊነቶቹን እውቅና ለተሰጠውና ራሱን በራሱ ለሚቆጣጠር ድርጅት በውክልና ለመስጠት እንደሚያስችለው ተገልጧል።

መመሪያው ባግባቡ ቁጥጥር የሚደረግበት የካፒታል ገበያ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር፣ ፍትሃዊ ውድድርን ለማስፈንና የባለሥልጣኑን የቁጥጥር ሃላፊነት በመቀነስ ጉልህ ሚና ሊጫወት ይችላል ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጵያ 47 በመቶ የሚሆነው የሃይል መቆራረጥ ችግር የሚከሰተው ከዛፎች ጋር በሚፈጠር ንክኪ ነው፣ በመሆኑም ዛፎችን የማፅዳት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” - አገልግሎቱ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀገሪቱ “47 በመቶ የሚሆነው የሃይል መቆራረጥ ችግር የሚከሰተው ከዛፎች ጋር በሚፈጠር ንክኪ መሆኑ አረጋግጫለሁ፣ ለሃይል መቆራረጥ መንስዔ የሆኑ ዛፎችን የማፅዳት ስራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ” ሲል አስታወቀ። 

“ዛፎች ሲተከሉ ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በሶስት ሜትር መራቅ እንዳለባቸው” መመሪያ ቢኖርም ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም ሲል የገለጸው ተቋሙ “በአብዛኛው አካባቢዎች በመኖሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲሁም ከግቢ ውጭ ለኃይል መቆራረጥና ለአደጋ መንስኤ የሆኑ ዛፎችን ከመሰረተ ልማቱ በእጅጉ ተቀራርበው ይገኛሉ ሲል አመላክቷል።

ተቋሙ ይህን ችግር ለመቅረፍ ብሎም በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ ለሃይል መቋረጥ መንስዔ የሆኑ ዛፎችን የማፅዳትና የቅድመ-መከላከል ስራ እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቁሟል።

በምዕራብ አዲስ አበባ፣ በወልዲያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በሆሳና ሪጅኖች ስር በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከ193 ኪሜ በላይ የኤሌክትሪክ መስመር የዛፍ ማፅዳት ስራ አከናውኛለሁ ሲል በማህበራዊ ትስስር የፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ የኢንተርፕርነር ሺፕ ፖሊሲ አበረታች አደለም ተባለ

የኢንተርፕርነር ልማት ኢንሲቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ቦሩ ሸና፤ወጣቶች የሚያመጧቸውን የሥራ ፈጠራ ሀሳቦች ማስተናገድ የሚችል የፖሊሲ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

በወጣቶች የሚመጡ የሥራ ፈጠራ ሀሳቦች ኢኮኖሚውን መደገፍ ወደሚያስችል አቅም እንዲያድጉ ለማድረግ የሥራ ፈጠራዎቻቸውን የሚያግዝ መሰረት መጣል ያስፈልጋል ነው  ያሉት።

በመሆኑ  በሁሉም ዘርፎች የተሰማሩ ወጣቶች የሚያመጧቸውን ሀሳቦች ማስተናገድ የሚችል የፖሊሲ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። 

አቶ ቦሮ ፤የወጣቶችን ሀሳብ በመቀበል ለሥራ ፈጣሪዎችና አዳዲስ ሀሳቦቻቸው ምቹ ሥነ-ምህርዳር መፍጠር ያስፈልጋልም ብለዋል። 

ሀገሪቷ ባላት አቅም የሥራ ፈጠራን ለመደገፍና ለማበረታታት ጥረት እየተደረገ መሆኑም ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ሁለንተናዊ ድጋፎችንና የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማመቻቸት የሐብት ምንጭ ለማድረግ  የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ መውሰድ ይገባልም ነው ያሉት።

ልዑል ወልዴ

ኀዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የድህረ-ምርት ብክነት አለ ተባለ።

በኢትዮጵያ ከተመረቱ በኋላ የሚባክኑ ምርቶች መጠን ከፍተኛ መሆኑን ሰምተናል።

ከምንመገበው የምግብ መጠን 30 በመቶው እንደሚጣል እና ከአትክልትና ፍራፍሬ ደግሞ 50 በመቶው ለብክነት እንደሚጋለጥ የኢትዮጵያ ሥርዓተ ምግብ መሪዎች ኔትዎርክ አስታውቋል።

በጅማ ዩኒቨርስቲ የሥርዓተ -ምግብ ፕሮፌሰር እና ከኔትዎርኩ መስራቾች አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ተፈራ በላቸው፤ ከመንዝ የመጣ ድንች ለምግብነት ሳይበቃ 70 በመቶው እንደሚጣል እና ከአርባምንጭ የሚመጣ የሙዝ ምርት ደግሞ 50 በመቶው እንደሚባክን በቅርቡ የተሰራ ጥናት ማመልከቱን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በምንም አይነት ቴክኖሎጂ ብናመርት የሚባክነውን ያህል መልሶ የማምረት አቅም የለንም ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ ማህበረሰቡ የአመጋገብ ዕውቀት ሊኖረው ይገባል ብለዋል።

ከ6 ዓመት በፊት የፀደቀው የምግብና ሥርዓተ -ምግብ ፖሊሲ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር፣ የድህረ-ምርት ብክነት ቅነሳ ላይ እና የአመጋገብ እውቀትን ለማስፋት እየተሰራበት መሆኑንም ገልጸዋል።

ስድስተኛው የኢትዮጵያ ሥርዓተ-ምግብ መሪዎች ኔትዎርክ አመታዊ ጉባኤውን ቅዳሜ ዕለት አካሂዷል።

የዚህኛው ዓመት ጉባኤ "የሥርዓተ-ምግብ አመራር በአየር ንብረት ለውጥ ለማይበገር የሥርዓተ - ምግብ ትግበራ በኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።


እስከዳር ግርማ

ኀዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጲያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ከ54.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ምርቶች ላይ እርምጃ ወስጃለው አለ፡፡

ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላለቀሉ እና ህገወጥ የምግብ ምርቶችን ለመለየት በተሰራ የቁጥጥር ስራ ከ252 ሺ ኪግ በላይ ወይም ከ54.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ምርት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

በተለያዩ የምግብ ምርቶች ላይ፣ በምግብ ገበያ ማዕከላት እና የምግብ ችርቻሮ ድርጅቶች ላይ እንዲሁም በተለዩ የምግብ ዓይነቶች ላይ በ10 ዙር ቁጥጥር መካሄዱን ጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ቁጥጥሩ ከተደረገባቸው የምግብ አይነቶች ውስጥ የዱቄት ወተት፣ የምግብ ዘይት፣ የበቆሎ ዱቄት፣ የጤፍ ዱቄት፣የለውዝ ቅቤና ፕላምፕኔት ዋናዎቹ መሆናቸው ተገልጸል፡፡

የቁጥጥር ስራው ከተካሄዳባቸው አካባቢዎች መካከል ደግሞ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ ተጠቃሽ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

የቁጥጥር ስራው የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በተጠቀሱት አካባቢዎች ከሚገኙ  የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የተሰራ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ኀዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዓባይ ባንክ  ጠቅላላ ገቢውን  ከ8.4 ቢሊዮን ብር በላይ አድርሻለው አለ።

ባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 52.6 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን አስታውቋል ።

ይህም ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር 26 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።

ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት 3.2 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉም ተጠቅሷል ።

ባንኩ በበጀት ዓመቱ ገቢን ከማሳደግ እና ወጪዎችን ከመቆጣጠር እንፃር ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ከግብር በፊት  1.9 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተገልጿል ።

የዓባይ ባንክ አጠቃላይ የሀብት መጠን 66.4 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተነስቷል፡፡

ከአጠቃላይ የባንኩ የገንዘብ እንቅስቃሴ ውስጥ 54 በመቶ የሚሆነው በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች በኩል መንቀሳቀሱን ጣቢያችን ሰምቷል።

ዓባይ ባንክ የደንበኞቹን ቁጥር 3.5 ሚሊዮን ማድረሱን እና ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ42 በመቶ ዕድገት በማሳየቱ ተነግሯል ።

ዓባይ ባንክ በአሁኑ ወቅት 548 በደረሱ ቅርንጫፎቹ ከ19,000 በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዳሉት ተገልጿል።

ሐመረ ፍሬው


ኀዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የፑቲን ማስጠንቀቂያ እንደ አዉሮፓ መሪዎች ወሬ ብቻ ሳይሆን በተግባር የሚታይ ነዉ ሲሉ የሃንጋሪዉ መሪ አሳስቡ

የሃንጋሪዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ፑቲን የሰጡትን ማስጠንቀቂ ትኩረት ሰጥተን መመልከት አለብን በለዋል፡፡

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካና አጋሮቿ ለዩክሬን ረጅም ርቀት የሚምዘገዘጉ ኪሳኤሎችን ማስታጠቃቸዉን ተከተሎ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የሃንጋሪዉ ጠቅላይ ሚኒስትር የፑቲን ማስጠንቀቂያ እንደ አዉሮፓ መሪዎች ወሬ ብቻ አይደለም ነዉ ያሉት፡፡

ይልቁንም ፑቲን የተናገሩትን ሚተገብሩ በመሆኑ ጥንቀቄ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ኦርባን የአዉሮፓ መሪዎች ከሚናገሩት 20 በመቶዉን ብቻ ነዉ የሚተገብሩት ቀሪዉ 80 በመቶ ወሬ ብቻ ነዉ ሲሉም ወርፈዋቸዋል፡፡

ቪክቶር ኦርባን ከሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር መልካም ግንኙነት ያላቸዉ የአዉሮፓ መሪ ናቸዉ፡፡

በዚህም የፑቲን ቀኝ እጅ ናቸዉ በሚል በህብረቱ አባል አገራት ይወቀሳሉ፡፡

ሃንጋሪ የዩክሬኑ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ ተደጋጋሚ ጥረቶችን ስታደርግ መቆየቷ የሚታወስ ነዉ፡፡

አሁንም በምዕራቡ አለምና በሩሲያ መካከል እንደ አዲስ ያገረሸዉን ዉጥረት ማርገብ እንደሚገባ ኦርባን እያሳሰቡ መሆናቸዉን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

አባቱ መረቀ

ኀዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel