ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

በአዲስ አበባ ከተማ ደንበኞች የባንክ አካውንት ለመክፈት “ፋይዳ” የዲጂታል መታወቂያ በግዴታነት እንዲያቀርቡ ታዟል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከቀጣዩ ወር ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ደንበኞች የባንክ አካውንት ለመክፈት “ፋይዳ” የተሰኘውን የዲጂታል መታወቂያ በግዴታነት እንዲያቀርቡ አዘዘ።

ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ደንበኞች የትኛውንም የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ መገደድ እንደሚጀምሩ ባንኩ አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ፤ የ“ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በአስገዳጅነት ጥቅም ላይ እንዲውል ያዘዘው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ሕዳር 17/2017 ዓ.ም. ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ ነው።

እያንዳንዱ ሰው የሚለይበት ባለ 12-አሃዝ ልዩ መለያ ቁጥር እንዲያገኝ የሚያስችለው የ“ፋይዳ” መታወቂያ፤ የነዋሪዎች የባዮሜትሪክ መረጃዎችን በመውሰድ ምዝገባ የሚደረግበት ስርዓት ነው።

የጣት አሻራ፣ አይን አይሪስ ስካን እና የፊት ምስል ነዋሪዎች መታወቂያውን ለማግኘት የሚያቀርቧቸው የባዮማትሪክ መረጃዎች ናቸው።

እስካሁን ድረስም ከ10 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ይህንን የዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት እንደተመዘገቡ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም መረጃ ያመለክታል።

ይህ አስገዳጅ አሰራር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በተለያየ ጊዜ እንደሆነም ባንኩ ገልጿል።

የብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ እንደሚያስረዳው አዲሱ አሰራር ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በአዲስ አበባ ከተማ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በጊኒ ወደ 60 የሚጠጉ የእግር ኳስ ተመልካቾች ህይወታቸውን አጡ

በጊኒ ሁለተኛዋ ትልቋ ከተማ ዤረኮር በእግር ኳስ ሜዳ በተከሰተ ግጭት 56 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የሃገሪቱ መንግስት ተናግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ማማዱ ኡሪ ባህ በእሁዱ ጨዋታ በደረሰ ‹‹መረጋገጥ›› ብዙዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጸው በዚህ ወቅት የሚያስፈልገው መረጋጋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ሃኪም ለኤ.ኤፍ.ፒ ለዓይን የሚያታክት በርካታ አስከሬን በሆስፒታል መመልከቱን ተናግሯል፡፡

የአካባቢው ሚዲያ የእንግዳው ቡድን ደጋፊዎች በአርቢትሩ ውሳኔ ተበሳጭተው ወደ ሜዳ ድንጋይ መወርወራቸውን ተከትሎ ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙን ዘግቧል፡፡

‹‹አጨቃጫቂውን ውሳኔ ተከትሎ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ መግባታቸውን›› አንድ የዓይን እማኝ ለኤ.ኤፍ.ፒ ተናግሯል፡፡

ፖል ሳኩቮጊ የተባለ መቀመጫውን ዤሬኮር ያደረገ ጋዜጠኛ ለቢቢሲ እንደተናገረው በአካባቢው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲገደብ መደረጉን እና የሆስፒታል በሮች በሮች በፖሊሶች እየተጠበቁ መሆኑን ገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስት ባህ ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑትን ወገኖች ለማግኘት ምርመራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡ አጋጣሚውን ‹‹አሰቃቂ›› ብለው ገልጸው ላዘኑት መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

አቤል ጀቤሳ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሩሲያ የመከላከያ በጀቷን ክብረወሰን በሰበረ መልኩ አሳደገች

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑቲን የሀገሪቱ የመከላከያ በጀት እንዲያድግ ወስነዋል ።

ይህ አዲሱ በጀት ሞስኮ በዩክሬን ላይ እያደረሰችው ያለውን ጥቃት ተከትሎ ወታደራዊ ፍላጎቶችና ተጨማሪ ግብአቶችን ለማቅርብ እንደሚረዳ ተዘግቧል ።

ለ2025 በጀት ዓመት 13.5 ትሪሊዮን ሩብል ለሀገር መከላከያ ተመድቧል ።

ፑቲን የተጨማሪ በጀቱን ያፀደቁት የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ለዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጋር አጋርነታቸውን ለማሳየት ወደ ዩክሬን መጓዛቸውን ተከትሎ ነው ሲል AP ዘገቧል።

ልኡል ወልዴ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሊቨርፑል ማንችስትር ሲቴን አሽነፍ!

በአስራ ሶስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደርጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሽንፈዋል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ ሳላህ እና ኮዲ ጋክፖ ከመረብ አሳርፈዋል።

ማንችስተር ሲቲ አራተኛ ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

መሐመድ ሳላህ በውድድር አመቱ አስራ አንደኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ከመረብ አሳርፏል።

ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በውድድር አመቱ በሊጉ 17 የግብ ተሳትፎዎችን በማድረግ ቀዳሚው ተጨዋች ሆኗል።

ሊቨርፑሎች በፕርሚየር ሊጉ ያለመሸነፍ ግስጋሴያቸውን ወደ ዘጠኝ ጨዋታ ከፍ ማድረግ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው

1 ሊቨርፑል - 34 ነጥብ
2 አርስናል 25 ነጥብ
3- ቼልሲ 25 ነጥብ
4 ብራይትን 23 ነጥብ
5 ማንችስተር ሲቲ - 23 ነጥብ

ጋዲሳ መገርሳ

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሩድ ቫኔስትሮይ  በሌሲስተር ሲቲን ዋና አሰልጣኝነት ተሾመ።

በቅርቡ አሰልጣኝ ሴቲቭ ኩፐርን ያሰናበተው ሌስተር ሲቲ አዲስ አሰልጣኝ በሃላፊነት መሾማቸውን አስታውቀዋል።

ሌስተር ሲቲ ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ ሌስተር ሲቲ ማክሰኞ ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ቡድኑን በመምራት ስራውን የሚጀምር ይሆናል።

ጋዲሳ መገርሳ


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

5ኛው የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄዷል ።

በጠዋቱ መርሃግብር ላይ አጠቃላይ የ2014-2016 ዓ.ም የተከናወኑ አበይት ተግባራት ዝርዝር አፈፃፀም ሪፖርት በማህበሩ ጵ/ቤት ኃላፊ አትሌት ሙሉጌታ ደምሴ የቀረበ ሲሆን በጉባኤተኞቹ ለቀረቡት ጥያቄዎች በረዳት ኮሚሽነር አትሌት ማርቆስ ገነቲ ፣ በአትሌት መሰለች መልካሙ እና በጵ/ቤት አመራሮች ማብራሪያ እና መልስ ተሰጥቶባቸዋል ።

በመቀጠልም ለቀጣይ አራት ዓመታት በስራ አስፈፃሚነት የሚመሩት አባላት በጉባኤው ላይ ተመርጠዋል ።በዚህ መሰረት :-

አትሌት የማነ ፀጋይ- ፕሬዝዳንት
አትሌት ተመስገን ወርቁ
አትሌት መርሲት ገብረእግዚአብሔር
አትሌት በላይነሽ ኦልጂራ
አትሌት ግርማ ጥላሁን
አትሌት ባንቺአየሁ ተሰማ
አትሌት በሽንቄ እመሼ

ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ማርቆስ ገነቲ አዲስ ለተመረጡት የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ አባላት መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ማህበሩን የጀመረውን በጎ ተግባራት እንዲያስቀጥሉ አደራ ሰጥቷል ።

በመጨረሻም አዲሱ ስራ አስፈፃሚ ቃለ መሃላ በመፈፀም ከበፊቱ አመራር አደራውን ተቀብሎ ስራውን ለመስራት ቃል በመግባት ጉባኤውን አጠናቋል ።

ጋዲሳ መገርሳ


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትሯን ወደ ሰሜን ኮሪያ ላከች

የሩሲያዉ የመከላከያ ሚኒስትር አንድሪ ብሉሶቭ በሰሜን ኮሪያ ጉብኝት እያደረጉ ነዉ ተብሏል፡፡

ብሉሶቭ በሁለቱ አገራት የወታደራዊ ስምምነት ዙሪያ ከሰሜን ኮሪያ አቻቸዉ ኖ ክዋንክ ኮል ጋር መወያያታቸዉ ተነግሯል፡፡

ሁሉቱ ባላስልጣናት ፑቲንና ኪም ጆንግ ኡን በቅርቡ የፈረሙትን ስምምነተ ተግባራዊ በሚሆንበት ዙሪያ መነጋገራቸዉን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

የወታደራዊ አጋርነት ስምምነቱ ዋነኛ አላማ በሰሜን እስያ ያለዉን ዉጥረት ለማርገብ ነዉ ተብሏል፡፡

የሩሲያዉ የመከላከያ ሚኒስትር ወደ ፕዮንግያንግ ያመሩት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ዩክሬን ድንበር ላይ መስፈራቸዉን እነ አሜሪካ እየገለፁ ባሉበት ወቅት ነዉ፡፡

አባቱ መረቀ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሀዋሳ በህገ ወጥ የቤንዚን ንግድ የተሠማሩ ታሠሩ

የሲዳማ ክልል የነዳጅ ግብይትና ቁጥጥር ግብረሃይል ሁለት የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ባለሙያዎችን ጨምሮ “ ህገ ወጥ የቤንዚን ንግድ ሲያከናውኑ ደረስኩባቸው “ ያላቸውን 34 ሰዎች ማሠሩን አስታወቀ ፡፡

ግብሃይሉ እርምጃውን የወሰደዉ የከተማዋ ነዋሪዎች በነዳጅ ዘይት እጦት መቸገራቸዉን በሚያስታዉቁበት ወቅት ነው ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነርና የግብረ ሃይሉ አባል ካሳ ጩቦ እንዳስታወቁት ተጠርጣሪ ባለሙያዎችና አዘዋዋሪዎቹ የተያዙት ፖሊስ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ባደረገው ክትትል ነው ፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ እንዳሉት በሕገ ወጥ የቤንዚን ንግድ ተሰማርተዋል በሚል ጥርጣሬ ከታሠሩት 34ት ሰዎች መካከል ሁለቱ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ባለሙያዎች ናቸው “ ብለዋል ፡፡

በተጨማሪም ቤንዚን ተመላልሰው በመቅዳት ለጥቁር ገበያ ሻጮች ሲገለብጡ የነበሩ 22 ሞተር ሳይክሎች አጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የጠቀሱት ምክትል ኮሚሽነር ካሳ “ ከፋብሪካ ሥሪት ውጭ ተጨማሪ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋን አስበይደው ለመቅዳት የሞከሩ ሁለት አሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ለሕግ እንደሚቀርቡ ምክትል ኮሚሽነሩ አስታዉቀዋል።
የሐዋሳዉ ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ እንደዘገበዉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥቁር ገበያ ጫና ሥር የወደቀው የሀዋሳ ከተማ የነዳጅ አቅርቦት በአሽከርካሪዎችና በቀን ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎችን እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ ነዉ፡፡

ችግሩ ያሳሰበው የክልሉ መንግሥት በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ ግብረሃይል አቋቁሞ የተጠናከረ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ከቀናት በፊት አስታዉቋል ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አየርን ወደ ሳምባ የሚወስደው የአየር ቧንቧ መቆጣት (Bronchitis)

Bronchitis (አየርን ወደ ሳምባ የሚወስደው የአየር ቧንቧ መቆጣት) በጣም የተለመደ በሽታ ነው.፡፡በዚህ በሽታም በአለም ላይ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚያዙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣ ጨቅላ ሕፃናት እና ትንንሽ ልጆች ለአጣዳፊ ብሮንካይትስ ተጋላጭነታቸው ከሌሎች የዕድሜ ክልል ካሉ ሰዎች የበለጠ መሆኑ ይነገራል፡፡

በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ሥር በሰደደ ብሮንካይትስ ሊያዙ እንደሚችሉ እና ነገር ግን ከ 45 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ብዙ ጊዜ እንደሚከሰት ይጠቀሳል፡፡

ከሴቶች በበለጠ ወንዶችን እንደሚያጠቃም ይነሳል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ህክምና ክፍል ሀላፊ ፣የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስ እና የሳምባ እና ፅኑ ህሙማን ሰብስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አምሳሉ ቢተው ናቸው፡፡

አየርን ወደ ሳምባ የሚወስደው የአየር ቧንቧ መቆጣት (Bronchitis) በምን ይከታል?


- ኢንፌክሽን(በቫይረስ)
- ባክቴሪያ
- ኬሚካሎች
- የአየር መበከል ይህንን ህመም ሊያመጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

በብሮንካይትስ ህመም የተጠቃ አንድ ሰው ሊያሳይ ከሚችለው ምልክት መካከል ዋናው ተደጋጋሚ ሳል መሆኑን ያነሳሉ፡፡

የሚያመጣው ተፅእኖ ምንድን ነው?

እየቆየ ሲሄድ ትንንሾቹን የአየር ቧንቧ ሊጎዳ ይችላል፡፡ ይህም አየር የመያዝ እና ሳንባን የመወጠር ነገር ሊያስከትል ይችላል፡፡

ተደጋጋሚ ሳል ሲኖር ደግሞ የአየር ቧንቧዎች በሽታ የመከላከል አቅም ሊቀንስ ይችላል፡፡

መከላከያ መንገዶቹ ምንድን ናቸው?

- በማንኛውም ግዜ ሳል ሲጀምር ባለሙያ ማማከር
- ከሲጋራ ጭስ መራቅ
- አካባቢ ላይ ሽታ የሚያመጡ እና አብዋራ የሚያስከትሉ ነገሮችን በጥንቃቄ መያዝ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

- ማስታገሻ
- አንቲባዮቲክ ዋና ዋናዎቹ ናቸው

ከሁሉም በላይ ግን ሀኪምን ማማከር ጥሩ መፍትሄ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም በሽታዎች ብዙ ጊዜ ሲጀምሩ እንደቀላል ስለሚጀምሩ ማንኛውም ሳል ሲከሰት ችላ ማለት እንደማያስፈልግ እና ዝም ብሎ መድሃኒቶችን ገዝቶ ከመውሰድ ባለሙያ ማማከር እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አቶ መሃመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቁዩት አቶ መሃመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አቶ መሃመድ እድሪስ ከኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ጠቅላይ ሚስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር ) መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

አቶ መሃመድ እድሪስ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በደባርቅ ከተማ በጣለዉ ከባድ በረዶ ምክንያት ከ5መቶ በላይ አርሶ አደሮች መፈናቀላቸዉ ተገለጸ፡፡

በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ የኪኖ ከተማ አሥተዳደሪ አቶ ንጉሴ ጸጋ ፤ለጣቢያችን እንደተናገሩት፤በገጠር ቀበሌዎች በጣለው ከባድ በረዶ ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ገበሬዎች ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል ብለዋል፡፡

ህዳር 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ጀምሮ ለ30 ደቂቃ የጣለው ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በሶስት ቀበሌዎች ከ500 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ነግረዉናል፡፡

ጉዳቱ በተለያዩ የሰብል አይነቶች ላይ የደረሰ ሲሆን ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍና ጥራጥሬ ሰብሎች ይገኙበታል ብለዉናል።

ዋና አስተዳዳሪዉ እንደገለጹት፤ከ500 በላይ አርሶ አደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የደረሰው ጉዳት ከባድ በመኾኑ አርሶ አደሮች በበጋ መስኖ ሰብል ልማት ምርቱን እንዲያካክሱ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ ዋና አስተዳዳሪዉ ተናግረዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኡጋንዳ በደረሰ የመሬት መደርመስ ቢያንስ 13 ሰዎች መሞታቸዉ ተገለጸ፡፡

በምስራቅ ኡጋንዳ ከባድ ዝናብ በመጣሉ 13 ሰዎች ህይወታቸዉ እንዳለፈና ከ 40 የማያንሱ ቤቶች በጎርፍ መወሰዳቸዉ ተገልጿል፡፡

የኡጋንዳ ቀይ መስቀል ማህበር በጎርፉ 13 ሰዎች መሞታቸው ገልጾ፤ የሟቾች ቁጥር ወደ 30 ከፍ ሊል እንደሚችል አስታዉቋል፡፡

የዩጋንዳ ቀይ መስቀል ማህበር በኤክስ ገጹ ላይ የነፍስ አድን ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጿል።

በአብዛኞቹ የተገኙት አስከሬኖች ህጻናት እንደሆኑና ቁጥራቸዉ የማይታወቅ ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም ብሏል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በጣለው ከባድ ዝናብ ትምህርት ቤቶች፣ አብያተ ክርስቲያናት እና ድልድዮች መዉደማቸዉንና ብዙ ህዝብም ከመኖሪያ ቀየዉ እንደተሰደደ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል ተባለ፡፡

የሩስያ የአየር ላይ ጥቃት ወሳኝ የሆኑ የሀይል መሠረተ ልማት ተቋማትን በመጉዳቱ ዩክሬን ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ አባወራዎች ያለ ሃይል ቀርተዋል ሲሉ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልፀዋል፡፡

በኪዬቭ የሚገኘው የኢነርጂ ሚኒስቴር እንደገለጸው ይህ ሩሲያ በያዝነው አመት ብቻ በዩክሬን የኃይል አቅርቦት ላይ ለ11ኛ ጊዜ መጠነ ሰፊ ጥቃት ማድረሷን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ከቅርብ ወራት ወዲህ የቦምብ ጥቃቶች እየተባባሱ በመምጣቱ ዩክሬንን አስጊ ሁኔታ ላይ ጥሏታል ተብሏል፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፤የቦምብ ጥቃቱ ዩክሬን የአሜሪካን አቶሚክ ሚሳኤሎች ተጠቅማ ለምትፈፅመው ጥቃት ምላሽ ነው ሲሉ ተናግረዋል ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ስለ መንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም ያዉቃሉ?

የመንጋጋ አጥንት መገጣጠሚያ ቴምፖራል  ከተባለ የራስ ቅል አጥንት ጋር የሚያገናኝ ማጠፊያ ነው።

ይህም ማውራት ፣ ማኘክ እና ማዛጋት  እንዲችሉ ፤ መንጋጋን ወደ ላይና ወደ ታች እንዲሁም ከጎን ወደ ጎን እንዲያንቀሳቅሱ ያስችላል።

ይሁን እና በዚህ በመንጋጋ መገጣጠሚያ ላይ በሚደርስ ችግር በአለማችን ላይ ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባሉ ሰዎች እንደሚሰቃዩ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ይህ ህመም በጊዜ መታከም ካልተቻለ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል  የህመም አይነት ነዉም ተብሏል፡፡

በመንጋጋ መገጣጠሚያ ላይ ህመም እና መታወክን ሲኖር  የእለት ተእለት ስራን የሚያውክ ከባድ ችግር እንደሆነም ነዉ የተነገረዉ  ፡፡

ለመሆኑ የመንጋጋ ህመም ለመከሰቱ ምክኒያት ምንድነዉ ህክምናዉስ ስንል  በአዲሲ አበባ ዩኒቨረሲቲይ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፤የመንጋጋ፤ የአፍ ዉስጥና የፊት ቀዶ ህክም፤ እንዲሁም የጥርስ ህክምና ትምህርት ክፍል ሃላፊ  ዶክተር ዳንኤል ሹካሬን ጠይቀነል፡፡

የመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም በአብዛኛው ሴቶች ላይ እንዲሁም ወጣትና አረጋውያን ላይ ይከሰታል።

#የመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም ለመከሰቱ ምክንያቶቹ ;-
-በአብዛኛው በፊት ላይ በሚፈጸም ድብደባ
-አገጭ ላይ ምት ሲኖር ወይም ሌላ ጉዳት ሲኖር የሚሉት ይተቀሳሉ፡፡
-ኢንፌክሺኖች
-ጠንካራ ነገር ማኘክ ወይንም መጋጥ
-የተፈጥሮ የጥርስ አበቃቀል
-አብዝቶ ማሲቲካ ማኘክ አጋላጭ ምክንያት ናቸዉ የተባለሲሆን ፤

ከዚኅ ባለፈ እንደዚህ ዓይነት ህመሞች÷ የመገጣጠሚያ ጉዳት፣ በጡንቻ መቆጣት እንዲሁም በአጥንት ላይ  የሚደርስን ጉዳት ተከትሎ  ይከሰታሉ፡፡

እንዲሁም የጥርስ ሙሌት ከፍ ተደርጎ ሲሞላ፣ በትክክል ያልተሰራ ሰው ሠራሽ ጥርስ፣ የጥርስ መፋጨት፣ ጭንቀትና ድባቴ  ለመንጋጋ መገጣጠሚያ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡

#የመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም ምልክቶች፤-/

የዚህ ህመም ምልክት መገጣጠሚያ ላይ እንዲሁም ከመገጣጠሚያው ውጭ ሊታዩ ይችላል እንደ ባለሙያዉ ማብራርያ።

ከምልክቶቹ መካከል፤- አፍን እንደወትሮ ለመክፈት መቸገር፣ የመገጣጠሚያ ህመም መሰማት፣ ምግብ ሲታኘክ ድምፅ መሰማት፣ አፍ ተከፍቶ አልዘጋም ማለት፣ የመገጣጠሚያ አካባቢ እብጠት፣ የጆሮ መጮህ  እና ራስ ምታት ይጠቀሳሉ፡፡

በተጨማሪም የአገጭ መገጣጠሚያ  ህመም፣ የአንገት እንዲሁም የጭንቅላት ጡንቻ ህመም፣ እንቅልፍ የመተኛት ችግር፣ ጥርስን ማፋጨት የመንጋጋ ህመም  ምልክቶች ናቸው፡፡

#ለመንጋጋ ህመም የሚደረጉ ህክምና ፤-

ሕክምናው እንደ ህመሙ ደረጃ የሚወሰን ሲሆን፤
እንደ ህመሙ ሁኔታ እና ግለሰዎቹ ወደህክምና ተቋም እንደሄዱበት ፍጥነት የህክምና እርዳታ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ቀላል እና በጊዜ ወደ ህክምና ተቋም ከተኬደ ፤-የህመም ማስታገሻ፣ ጥርስ ላይ የሚደረግ መሸፈኛ፣ የመገጣጠሚያ እጥበት፤ፊዚዮ ቴራፒ ፤የመዳኒት ህክምና ይሰጣል፡፡

ከረፈደ ወደህክምና ለሚሄድ እና የህመሙ ሁኔታ ታይቶ  የቀዶ ጥገና ሕክምና ይሰጣል፡፡

#በመጨረሻም:-

የመንጋጋ፤ የአፍ ዉስጥና የፊት ቀዶ ህክም፤ እንዲሁም የጥርስ ህክምና ትምህርት ክፍል ሃላፊዉ  ዶክተር ዳንኤል ሹካሬ፤ማንኛውም የመንጋጋ ህመም ያጋጠመዉ ሰዎ በፍጥነት ወደ የአፍና የከፍተኛ ህክምና ባለሙያ መቅረብ እንዳለበት ተነግሯል።

ለመንጋጋ ህመም ያለው አመለካከት ሕመሙን በሚያስከትሉ መሠረታዊ ምክንያቶች ላይ የተመሠረተ ነው።

ህመሙ ችላ ቢባል ፤ምግብ  መብላት አለመቻልን ጨምሮ ንግግርን በማቋረጥ ከማህበራዊ ግንኙነት ይገድባል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የመንጋጋ በሽታ የሚያመጣው ህመም  ተባብሶ ለማከም የበለጠ አስቸጋሪ የሆነ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችልም ጠቁሟል፡፡

ልኡል ወልዴ

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ግብጽ ስለ ጋዛ የሰብዓዊ ድጋፍ ለመነጋገር የሚኒስትሮች ጉባዔ አዘጋጀች፡፡

አንድ መቶ ሶስት አገራትን እና ተቋማትን የወከሉ ልዑካን በጉባዔዉን ተገኝተዋል፡፡

በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ የተጀመረዉ ስብሰባ በጦርነት ለወደመችዉ ጋዛ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስብሰባዉ የተዘጋጀዉ በግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ተወካዮች እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታዉ ምክር ቤት ምክትል ሃላፊ አሚና መሐመድ ነዉ፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጋዛ ያለዉ የረሐብ ቀዉስ እጅጉን እየከፋ መጥቷል ያለ ሲሆን፤ ከጦርነቱ በፊት የነበረዉ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ አሁን ላይ ከ1ሺህ በመቶ በላይ መጨመሩን ነዉ የገለጸዉ፡፡

በጥቅምት 7 ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በጋዛ 44ሺህ ንጹሃን ህይወታቸዉ አልፏል፡፡ ከ1መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

እስራኤል እርዳታዎች እንዳይደርሱ በማድረግ የጋዛን ነዋሪዎች ለማጥፋት ሆን ብላ እየሰራች ነዉ በማለት የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ እያወገዛት ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ እና የቀድሞዉ የመከላከያ ሚኒስትር ዩአቭ ጋላንት በጦር ወንጀሎች ተጠያቂ ተብለዉ በዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸዉ ይታወቃል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በህውሃት እና በጊዜያዊው አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በሁለቱም በኩል የሚታይ ቁርጠኝነት የለም ሲሉ የህውሃት መስራች አቶ ገበሩ አስራት ተናገሩ

በትግራይ ክልል ያለው ፖለቲካዊ መካረርን ለመፍታት በሁለቱም ወገኖች መካከል ቁርጠኝነት የለም ሲሉ የህወሃት መስራችና የቀድሞ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ገብሩ አስራት ሊትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

የህውሃት መስራች እና አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ገብሩ አስራት ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ለችግሩ መነሻው ክልሉን እያስተዳደረ በሚገኘው ጊዜያዊ አስተዳደር እና በህወሓት መከከል የተፈጠረው የፖለቲካ ሽኩቻ የስልጣን ፍላጎት የፈጠረው ነው ብለዋል።

በተለይም ህውሃት ሰላምን ለማምጣት ፍላጎቱ እንደሌለው አንስተው እንደ አጠቃላይ ግን የቁርጠኝነቱ ጉዳይ በሁለቱም አካላት በኩል እንደማይታይ ተናግረዋል ፡፡

የትግራይ ሕዝብ ችግር የመላው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ችግር መሆኑን የሚናገሩት አቶ ገብሩ፤ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት የመመለስ እንዲሁም የወደሙ የመሰረተ ልማትቶችን መልሶ የማቋቋም ጉዳይ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ብቻ የሚተዉ አይደለም ብለዋል።

የፌድራል መንግስት መፍትሄ ለማበጀት መጣር እንዳለበት የሚያነሱት አቶ ገብሩ ነገር መካረሩ የአንድ ፓርቲ የመሰንጠቅ ችግር በመሆኑ የፌድራል መንግስቱ አሁን ላይ እርምጃ ለመውሰድ ይቸገራል ሲሉም ተናግረዋል።

ለአለም አሰፋ

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲጂታል የትምህርት ቤት ክፍያ ይፋ አደረገ።


ባንኩ ኢ-ስኩል ክፍያ የተሰኘ የዲጂታል የትምህርት ቤት ክፍያ አገልግሎት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።


የዲጂታል የክፍያ አገልግሎቱ ስህተቶችና ድጋሚ ክፍያዎች እንዳይፈፀሙ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።


የዲጂታል የክፍያ አገልግሎቱን በመጠቀም የግል እና የመንግስት ት/ቤቶች ክፍያዎችን መፈፀም ይችላሉ ነው የተባለው።


ከትምህርት ቤት ክፍያዎች በተጨማሪ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እንዲሁም መረጃዎችን ለማደራጀት ያስችላል ተብሏል።


መተግበሪያውን በመጠቀም ትምህርትቤቶች የራሳቸውን ማስተካከያዎች ማድረግ እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።


መተግበሪያው የትምህርት ቤት ክፍያዎች ጊዜያቸው እንዳያልፍም ለወላጆች  የፅሁፍ መልዕክት በመላክ የማስታወስ ስራ ይሰራል ተብሏል።


ከዚህ በተጨማሪ መተግበሪያውን በመጠቀም በየትኛውም ጊዜ የተፈፀሙ የክፍያ ሪፖርቶችን ማየት እንደሚቻል ተገልጿል።


ባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶቹን ለማስተዋወቅም አውደርእይ አዘጋጅቷል።


አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ በግንቦት ወር የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት የጀመረ ሲሆን ፤ አሁን ላይ ከ88ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ተገልጿል።


እሰከዳር ግርማ

ኀዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በዚሁ መሠረት ከታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ ተግባራዊ የሚደረግ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ታሪፍ አሁን እየተሰጠበት ካለው 10 ብር ወደ 20 ብር ማሻሻያ መደረጉን ቢሮው አስታውቋል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያው ከታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ታውቆ ተፈፃሚ እንዲደረግም ቢሮው አሳስቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በየዕለቱ ሊበር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኒውዮርክ ከተማ ሲያደርገው የነበረውን አራት ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ በእየዕለቱ ሊበር መሆኑን አስታውቋል።

አየር መንገዱ ከህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን እለታዊ በረራ እንደሚጀምር ገልጿል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለአራት አመት የሚቆይ የ6.5 ሚሊየን ፓውንድ የክትባት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።

በሦስት ክልሎች በአስራ ስድስት ወረዳዎች የሚተገበር የ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ የክትባት ፕሮጀክት ይፋ መሆኑን ሰምተናል።

ፕሮጀክቱ ለአራት ዓመት የሚቆይ ሲሆን፤ የሚተገበርባቸው ክልሎችም የክትባት ተደራሽነት የቀነሰባቸው ክልሎች ናቸው።

ፕሮጀክቱ ምንም አይነት ክትባት ያልወሰዱ እንዲሁም ክትባት ጀምረው ያቆሙ ሕጻናት ቁጥር በጥናት ልየታ የተደረገባቸው ወረዳዎች ላይ የሚተገበር መሆኑም ነው የተገለጸው።

ለዚህም የአማራ ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች መመረጣቸው ተገልጿል።

ፕሮጀክቱን ለማስጀመር በተደረጉ ጥናቶች ክትባት ላልወሰዱ ሕጻናት ቁጥር መጨመር እንደምክንያት የተጠቀሱት የክትባቶች እጥረት፣ የባለሙያዎች አለመኖር፣ የጤና ተቋማት ርቀት እና የግንዛቤ እጥረት የሚሉ ጉዳዮች ናቸው።

የፕሮጀክቱ ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይም የክትባቶችን ተደራሽነት ለማገዝ 52 የክትባት ማስቀመጫ ፍሪጆች ያሏቸው ሞተር ሳይክሎችና 50 የሞባይል ታብሌቶችን ሴቭ ዘ ችልድረን አስረክቧል።

ፕሮጀክቱ ሴቭ ዘችልድረን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን የሚተገብረው ነው።

ሊዲያ ደሳለኝ

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ስዊድን በባልቲክ ባህር አንድ የቻይና መርከብ በኬብሎች ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለመመርመር በይፋ የቻይናን ትብብር ጠየቀች።

ይ-ፔንግ ሶስት የተሰኘው የቻይና መርከብ አደጋዉ ሲደርስ በወቅቱ በአካባቢው እንደነበረ የሚታመን ሲሆን፤ከዚያን በኋላ በዴንማርክ አለም አቀፍ የውሃ ክልል ላይ ታይቶ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ቤጂንግ በኬብሎቹ መበላሸት ዙሪያ ምንም አይነት ተሳትፎ እንደሌላት በመግለጽ፤የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ግን ከስዊድን እና ከሌሎች አገራት ጋር ለመስራት ፈቃደኛ መሆኗን አስታዉቃለች፡፡

በስዊድን የጎትላንድ ደሴት እና በሉቲኒያ መካከል ያለው የአሬሊዮን ገመድ ጉዳት እንደደረሰበት ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም በፊንላንድ ዋና ከተማ ሄልሲንኪ እና በጀርመን የሮስቶክ ወደብ መካከል ያለው የሲ-ሊዮን 1 ገመድ እንደተቆረጠም ታዉቋል፡፡

መርከቧ ከ160 ኪ.ሜ (100 ማይልስ) በላይ መልህቅን በባህር ወለል ላይ በመጣል ገመዱን ሆን ብላ እንዳበላሸችው መርማሪዎች ያምናሉ ሲል ያስነበበዉ ዎል ስትሪት ጆርናል ነዉ፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ኀዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሰቆጣ ቃልኪዳን በዚህ ዓመት በተጨማሪ 94 አዳዲስ ወረዳዎች ላይ እየተተገበረ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአማራ እና ትግራይ ክልል በሚገኙ 40 ወረዳዎች የተጀመረዉ የቃልኪዳኑ የትግበራ ምዕራፍ እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ 2መቶ 40 ወረዳዎችን አዳርሶ ነበር፡፡

በዚህ ዓመት በተጨመሩት አዳዲስ 94 ወረዳዎች ቁጥሩ ወደ 3መቶ34 ከፍ ብሏል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የስርዓተ-ምግብ ማስተባበሪያ ቢሮ፤ የሰቆጣ ቃልኪዳን ማስተባበሪያ ዴስክ መሪ የሆኑት አቶ ዮናታን ማሞ ለጣቢያችን እንደገለጹት፤ አሁን በአገር አቀፍ ደረጃ በ3መቶ34 ወረዳዎች ላይ መቀንጨርን ለማስቀረት እየተሰራ ነዉ፡፡

በኢትዮጵያ የሚታየው የመቀንጨር ችግር ከግዜ ወደ ግዜ መሻሻሎች ቢያሳይም ፥ አሁንም የተለያዩ ችግሮች መኖራቸዉን አንስተዋል፡፡

ካለፈዉ ዓመት ጀምሮ እስከ 2018 ዓ.ም ይህን ፕሮግራም በ700 ወረዳዎች በማስፋት ከ5 ሚሊዮን በላይ ህፃናትን ከመቀንጨር ለመታደግ በዕቅድ ስለመያዙም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

አቶ ዮናታን በሰቆጣ ቃልኪዳን ከዚህ በፊት ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን ከመቀንጨር ለመታደግ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዉ፤ በ2030 ደግሞ ዕድሜያቸዉ ከ2 ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን የመቀንጨር ምጣኔ ዜሮ ለማድረስ እየተሰራ ነዉ ብለዉናል፡፡

ቃልኪዳኑ በሰቆጣ ከተማ በቀድሞዉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩት በአቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የከተማ ከንቲባዎች በተገኙበት በነሐሴ 2007 ዓ.ም ነበር የተፈረመው

እሰከዳር ግርማ

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ላምፓርድ የኮቨንትሪ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

የቀድሞው የእንግሊዝ እና የቼልሲ አማካይ ፍራንክ ላምፓርድ በሻምፒየንሺፕ የሚሳተፈው ኮቨንትሪ ሲቲ አሰልጣኝ ሆኖ የሁለት ዓመት ከመንፈቅ ርዝማኔ ባለው ኮንትራት ተሸሟል፡፡

የ46 ዓመቱ ላምፓርድ የተረከበው ከወራጅ ቀጠናው በሁለት ነጥብ ብቻ ከፍ ብሎ በሻምፒየንሺፑ 17ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠን ቡድን ነው፡፡

በክለቡ ረዘም ላለ ጊዜ ያገለገሉትን ማርክ ሮቢንስ ተክቶ ቦታውን ተረክቧል፡፡ አሰልጣኙ የተሰናበቱት ሰባት ዓመታት በክለቡ ቆይታ ካደረጉ በኋላ ነው፡፡

አቤል ጀቤሳ

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሕብረት ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ ከ74 ቢሊየን ብር በላይ ማለፉን ገለፀ።

ባንኩ ከታክስ በፊትም 3.08 ቢሊየን ብር ትርፍ አስመዝግቤያለሁ ብሏል።

ባንኩ በዛሬው ዕለት 27ኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።

በዚህ ወቅትም የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን 74.65 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጿል።

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጅነር ሳምራዊት ጌታመሳይ ፤ ተቀማጭ ገንዘቡ ባለፈው አመት ከነበረው መጠን ጋር ሲነፃፀር የ10.11 ቢሊየን ብር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል።

በተጨማሪም ባንኩ ከታክስ በፊት 3.08 ቢሊየን ብር ትርፍ ሲያስመዘግብ፤ ካለፈው አመት ትርፍ ጋር ሲነፃፀር የ22.57 ሚሊየን ብር ጭማሪ ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

የቦርድ ሰብሳቢዋ እንደገለፁት ፤ ከወለድ ነፃ ፋይናንስን ጨምሮ የባንኩ አጠቃላይ የብድር መጠን 68.89 ቢሊየን ብር ደርሷል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት የተለያዩ ችግሮች እንደነበሩ የገለፁት ኢንጅነር ሳምራዊት፤ ብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንኮች የሚሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ብድር የወለድ ምጣኔ ከፍ ማለት እንዲሁም የልማት ባንክ ቦንድ ግዢ ግዴታዎች ከችግሮቹ መሐል የሚጠቀሱ መሆናቸውን አንስተዋል።

በተጨማሪም የባንክ ሴክተሩ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት አመታት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ገጥሞት እንደነበርም ገልጸዋል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት ሕብረት ባንክ 25ኛ አመት የምስረታ በዓሉን አክብሯል።

እሰከዳር ግርማ

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

"የገና ስጦታ ለልብ ህሙማን ህጻናት "በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ይፋ ሆነ ።

በሀገራችን ብቻም ሳይሆን በተለያዩ ዓለማት በድምቀት የሚከበረውን የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ እስከ ገና በዓል የሚቆይ የገና ስጦታ ለልብ ህሙማን ህጻናት የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ዛሬ ህዳር 19 ቀን 2017 አ.ም መጀመሩን የኢትዮጲያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል አስታውቋል።

በዚህ የገና ስጦታ ለልብ ህሙማን ህጻናት የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች፥ ድርጅቶችና ተቋማት ከወትሮው በተለየ መንገድ ማዕከሉን በአይነትም ይሁን በገንዘብ እንዲያግዙ ለማስቻል የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል ።

እንዲሁም የልብ ህክምና ለማግኘት ወረፋ የሚጠብቁ ከ8 ሺ በላይ ህጻናት ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ማዕከሉ በልብ ህሙማን ህጻናት ስም ጥሪውን አቅርቧል ።

ለህክምና የሚውለው አብዛኛው ግብአት የሚመጣው ከውጪ በመሆኑም የሁሉም ህብረተሰብ ድጋፍ ስለሚያስፈልግ 6710 ላይ ok ብሎ በመላክ ሁሉም ሰው ንቅናቄው ላይ ቢሳተፉ የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ በሀገራችን ነፃ የልብ ሕክምና በመስጠት ላይ የሚገኝ ማዕከል እንደሆነ ይታወቃል።

ሐመረ ፍሬው

ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel