ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

የነገ የታኅሣሥ 1ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአየር ብክለት ልቀትን በመቀነስ በኒሞንያ ህይወታቸው የሚያልፈውን 50 በመቶ  ህፃናትን  መታደግ ይቻላል ተባለ

በጤና ሚንስቴር የማህበረሰብ ተሳትፎና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዳኘዉ ታደሰ፤17 በመቶ በሃገራችን ከአምስት አመት በታች ህፃናት በሳንባምች ወይንም የኒሞንያ በሽታ ይሞታሉ ብለውናል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ለዚህ ለኒሞኒያ በሽታ መከሰት   የተለያዩ ምክኒያት አለ ያሉ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ በቤት ዉስጥና ከቤት ዉጭ ያሉ የአየር ብክለት ይጠቀሳሉ፡፡

ይሁን እና  በቤት ውስጥ እንደ ከሰል፣ኩበትና የእንጨት ጭስ ለእናቶችና ህፃናት ኒሞንያ ተጋላጭነት ምክንያተት መሆኑን ነግረውናል።

ከቤት ውጭ ደግሞ በተለይ በከተማ ውስጥ ከመኪናዎችና ከተለያዩ ተቋማት የሚለቀቁ በካይ ጋዞች፣በየቦታው የሚቃጠል ቆሻ፣ እንዲሁም ህንፃዎች ሲሰሩ የሚለቀቁ ኬሚካሎች ይጠቀሳሉ ብለውናል።

አቶ ዳኘዉ ፤የአየር ብክለትን በመቀነስ 50 በመቶ የሚሆነዉን  የኒሞኒያን በሽታ መቀነስ ይቻላል ያሉ ሲሆን ለዚህም የአየር ብክለት ልቀቱን ለመቀነስ መፍትሔ ነዉ ያሉትን  አጋርተውናል፡፡

ሆኖም ችግሩን ለመቅረፍ በገጠር አከባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች ጭስ አልባ ምድጃዎችን ሰርተው መጠቀም፣መኖሪያ ቤትን ከኩሽናው መለየትና ኩሽናቸው ከጭስ ነፃ መሆን ይኖርበታል ነው ያሉን።

በከተሞች ያለውን የአየር ብክለትን ለመቀነስ ደግሞ እፅዋትን መትከል፣ሳይክሎችን መጠቀም፣በእግር መንቀሳቀስ እንዲሁም 40 በመቶውን የአየር ብክለቱን ለመቀነስ የህዝብ ትራንስፖረትን ማበራከት ይገባል ተብሏል።

ልኡል ወልዴ

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ላለፉት አራት ወራት 2 ሺ 4መቶ 72 የሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ  እርምጃ ወስጃለሁ አለ።

ህገወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 2 ሺ 4መቶ 72 የሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ እስከ ማሸግ የሚደርስ እርምጃ መውሰዱን ቢሮው አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የገበያ ጥናት፤ መረጃ እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር እንዲሁም የኮሚኒኬሽን ተወካይ የሆኑት  አቶ ሙሰማ ጀማል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የማሸግ እርምጃ የተወሰደባቸው 6 መቶ 34 የንግድ ተቋማት ናቸው።

የዋጋ ዝርዝር በአግባቡ ሳይለጥፉ የተገኙ ነጋዴዎችም እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል እንደሆኑ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ጋር ያለው የሸመታ ስርአት መዘመን እንዳለበትም አንስተዋል።

ህገወጥ ንግድን ለመከላከል ህገወጥ የደላላ ስርአቱን ማስቆም እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

ቢሮውም ይህን ችግር ለመቅረፍ አምራቹ በቀጥታ ወደ አዲስ አበባ ገበያዎች መቶ ከህገወጥ ደላሎች ነፃ በሆነ መንገድ ምርቶቹን ሊያቀርብ የሚችልባቸው ሁኔታዎችን የማመቻቸት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ሐመረ ፍሬው

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሀገራዊ ምክክርን ለማካሄድ ፍጹም ሰላማዊ የሆነ ጊዜን መጠበቅ ግዴታ አይደለም ተባለ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክክር  ለማካሄድ ፍፁም ሰላም መሆን አለበት የሚል እምነት የለንም ሲል ገለፀ።

የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ይህን ምክክር ለማካሄድ በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶች የግድ ሙሉ በሙሉ መቆም አለብት ብሎ ኮምሽኑ እንደማያምን ተናግረዋል።

አቶ ጥበቡ በሀገራችን ግጭቶች በስፋት እንዳሉ ቢታወቅም  ምክክር ከማድረግ ግን አያግድም ብለዋል።

ምክክር  በግጭት ጊዜ ይካሄዳል የሚሉት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ በሌላ በኩል ፣ምክክር ግጭት ካለፈ በኋላም  መካሄድ እንደሚችል የሌሎች ሀገራትን ልምድ ማየት ይቻላልም ብለዋል።

ኮሚሽኑ አሁንም የታጠቁ አካላት በምክክር ሂደቱ  እንዲሳተፍ ጥረት እያደረገ ይገኛል፤ ሰላምን በማምጣት አሳታፊ የሆነ ምክክር ለማድረግ ቁርጠኛ ነው ሲሉም አቶ ጥበቡ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ለአለም አሰፋ

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን አስቆማለሁ አሉ ትራምፕ

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወላጆቻቸው በውጭ አገራት ቢወለዱም በአሜሪካ የተወለዱ ልጆቻቸው ዜግነት የሚያገኙበትን መብት እሽራለሁ አሉ።

ትራምፕ አስቆመዋለሁ የሚሉት በተለያዩ ምክንያቶች ተሰደው ወደ አሜሪካ የሄዱ ሰዎች የመኖሪያም ሆነ የዜግነት መብት ባያገኙም አሜሪካ ውስጥ የወለዷቸው ልጆች ዜግነትን ማግኘት የሚችሉበትን ነው።

ሆኖም በልጅነታቸው ወደ አሜሪካ የመጡ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ለመርዳት ከዴሞክራቶች ጋር እሰራለሁ ብለዋል።

በጥር ወር ወደ ዋይት ሃውስ የሚገቡት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣንን ከተቆናጠጡ በኋላ በስደተኞች፣ ኃይል እና ምጣኔ ኃብትን ጨምሮ በፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ ስር ነቀል ለውጦችን እንደሚያመጡ ከኤንቢሲ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ረዘም ያለ ቆይታ ቃል ገብተዋል።

ትራምፕ ወላጆቻቸው ሌላ ቦታ ቢወለዱም በአሜሪካ የሚወልዷቸው ልጆች የአሜሪካ ፓስፖርት የማግኘት መብት የሚሰጠውን በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት ለማስቆም ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ አስተላልፋለሁ ሲሉ ለኤንቢሲ ገልጸዋል።

በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት የአሜሪካ ህገ መንግሥት አንቀጽ 14ን መሰረት ያደረገ ነው።

''ማንኛውም አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ወይም ተገቢውን ግዴታዎች የተወጣ ሰው የአሜሪካ ዜጋ የመሆን ሙሉ መብት አለው'' ይላል።

"እኛ ይህንን መቀየር አለብን። ምናልባት ወደ ህዝቡ እንወስደዋለን። ነገር ግን ልናስቆመው ይገባል" ሲሉ ነው ትራምፕ የተናገሩት።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የቤተሰብ አባላት ያላቸውን ጨምሮ ህጋዊ ሰነዶች ያላሟሉ ስደተኞችን ከአገር ለማባረር የገቡትን ቃል ተግባራዊ አደርጋለሁ ብለዋል።

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

English premier League

አርሰናል እና  ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ሲጥሉ   ማንችስተር  ዩናይትድ እና ቶተንሀም ሸንፈተ አስተናግዱ!

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር አርሰናል ከፉልሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የፉልሀምን ግብ ሂምኔዝ ከመረብ ሲያሳርፍ ዊሊያም ሳሊባ አርሰናልን አቻ ማድረግ ችሏል።

አርሰናል በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ያለፉት አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ የማዕዘን ምት ግብ ማስቆጠር ችሏል።

አርሰናል ካለፈው የውድድር ዘመን ወዲህ 23  ግቦችን ከቆመ ኳስ ማስቆጠር ችሏል ::


ማንችስተር ሲቲ ከ ክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የማንችስተር ሲቲን ግብ ሀላንድ እና ሌዊስ ሲያስቆጥሩ 
ለክሪስታል ፓላስ ሙኖዝ እና ላክሮይክስ ከመረብ አሳርፈዋል።

ማንችስተር ሲቲ በዚህ አመት በሰባት ጨዋታዎች በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች ግብ የተቆጠረበት ቀዳሚው ክለብ ሆኗል።

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ 13ኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን አስቆጥሮ።

ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች

21ግቦች ተቆጥረውበታል
6 ጨዋታዎች ተሸንፈዋል እንዲሁም
1 ጨዋታ አሸንፈው
2  አቻ ተለያይተዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የኖቲንግሀም ፎረስትን የማሸነፊያ ግቦች ሚሌንኮቪች ፣ ክሪስ ውድ እና ጊብስ ዋይት አስቆጥረዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖቹን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ሆይሉንድ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከመረብ አሳርፈዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ ስድስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ኖቲንግሀም ፎረስት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድን በሊግ ጨዋታ ኦልድትራፎርድ ላይ አሸንፎታል።


ቼልሲ ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ3 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሰማያዊዎቹን የድል ግቦች ኮል ፓልመር 2x ፣ ኢንዞ ፈርናንዴዝ እና ጄደን ሳንቾ ከመረብ አሳርፈዋል።

ቶተንሀምን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ዶምኒክ ሶላንኬ ፣ ሰን እና ኩሉሴቭስኪ አስቆጥረዋል።

ቼልሲ ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ማጥበብ ችለዋል።

ኮል ፓልመር አስራ ሁለት ተከታታይ ፍፁም ቅጣት ምቶችን በማስቆጠር በሊጉ አዲስ ታሪክ ፅፏል።

በሌሎች ጨዋታዎች

- አስቶን ቪላ ሳውዝሀምፕተንን 1ለ0
- ብሬንትፎርድ ኒውካስል ዩናይትድን 4ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል ።
- ሌስተር ሲቲ ከብራይተን 2ለ2 ሲለያዩ
- በርንማውዝ ኢፕስዊች ታውንን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ከባድ አውሎ ንፋስ በመከሰቱ ምክንያት ሊደረግ የነበረው የመርሲሳይድ ደርቢ   ኤቨርተን ከ ሊቨርፑል ጨዋታ ለሌላ ቀን ተላልፏል።

የሊግ ደረጃቸው

1 ሊቨርፑል :- 35 ነጥብ
2 ቼልሲ :- 31 ነጥብ
3  አርስናል:-29 ነጥብ
4 ማንችስተር ሲቲ :- 27 ነጥብ
5 ኖቲንግሀም ፎረስት  :- 25 ነጥብ
11  ቶተንሀምን   :- 20 ነጥብ
13 ማንችስትር ዩናይትድ:- 19 ነጥብ

ጋዲሳ መገርሳ

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ         

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

መንግሥት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ባቀረበው የሠላም ጥሪ መሠረት የኦነግ ታጣቂ ኃይል አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በስፋት እየገቡ መሆኑ ይታወቃል። 

የታጣቂ  ቡድኑ አባላትን ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማጓጓዝ ስራ በስኬት እየተከናወነ ይገኛል። 

በዚህ መሀል ታጣቂዎቹ አዲስ አበባ ከተማን አቋርጠው ወደ ስልጠና ማዕከላት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እየጨፈሩና የደስታ ስሜት እያሰሙ ሲንቀሳቀሱ የተኩስ ድምጽ በማሰማታቸው በከተማው ነዋሪ ህዝብ ላይ ድንጋጤና መረበሽ ሊፈጠር መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።

ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ የጠየቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄና የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስታውቋል።

ኀዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ENTOTO PARK CBE RUN

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር። '' እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ''  ዛሬ  ተጀመሯል።

የመጀመሪያው የሩጫ ውድድር ዛሬ  ቅዳሜ ህዳር  28   ቀን 2017 ዓ ም  ክ ንጋቱ 12፡30 ጀምሮ በእጦጦ ፓርክ ተካሄዶል።


የሩጫ ውድድሩ እንድ አውሮፓዉያን አቆጣጠር ወር በገባ የመጀመሪያው ቅዳሜ በእንጦጦ  ፓርክ የሚድሪግ የ5KM ውድድር ሲሆን ከሩጫ ውድድርነት ባለፍ ብዙ እንድምታ ይኖረዋልም ተብሏል ።

ጋዲሳ መገርሳ

ኀዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት 940.7 ሚሊዮን ብር ማትረፍ ችያለው አለ።

ባንኩ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 940.7 ሚሊየን ብር ማትረፍ መቻሉን እና
ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀርም የ25 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አስታውቋል።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሒሳብ ዓመቱ  54 ቢሊየን ብር  ብድር መሰጠቱን እና ተመሳሳይ መጠን ያለው ከብድር ተመላሽ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉ ተጠቅሷል።

የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ዓቅም  3.1 ቢሊዮን ብር መድረሱ እና አጠቃላይ ሀብትም 43.1 ቢሊዮን ብር መሆኑን ጣቢያችን ሰምቷል።

በሒሳብ ዓመቱ  83 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ 35.6 ቢሊዮን ብር ማድረስ ተችሏልም ተብሏል::

ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ310 ሺህ በላይ አዳዲስ የባንክ ሒሳቦችን በመክፈት የአስቀማጭ ደንበኞቹን ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን በላይ ማድረሱን 20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት አስታውቋል ።

የዲጂታል እና የኤጀንት ባንኪንግ አገልግሎት ዘርፍ የተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 998,000 ከፍ ስለማለቱም ተነግሯል።

ተደራሽነት ከማሳደግ አንፃርም ባንኩ 18 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ለአገልግሎት በማብቃት እ.ኤ አ እስከ ሰኔ 30/2024 ድረስ አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 306 ማድረሱ ተነስቷል።

እንዲሁም  80 የገንዘብ መክፈያ ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖችን በተለያዩ አካባቢዎች በመትከል የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አገልግሎት ለማቀላጠፍ ጥረት እንደተደረገ ተገልጿል ።

ባንኩ ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያም በአጠቃላይ 6,365 ሰራተኞች እንዳሉት ተነግሯል።

ሐመረ ፍሬው

ኀዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

"ምንም የማውቀው ነገር የለም ፣ ጥሪም አልደረሰኝም በኃላፊነት ቦታ ሳይሆን በሙያዬ አግዛችኋለሁ ነው ያልኳቸው"  አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ

እስከ እኩለ ለሊት የቆየ ቀረፃ ጨርሼ ስልክ ስከፍት በርካታ ወዳጆቼ ተመረጥሽ የሚል ነገር ሰምተን ነው የሚል መልእክት ልከዋል።

በወዳጆቼ ጥቆማ ወደ ማህበራዊ  ሚዲያ ስገባ ተሰራጭቶ ያየሁት መረጃ  በፍፁም የማላውቀውና ከሌላው ሰው ዘግይቶ ነበር ያየሁት።

በግሌ በፕሮሞሽን፣ መድረክ መምራትና መሰል ጉዳዮች በሙያዬ እንዳግዝ በስልክ ተጠይቄ ፍቃደኛ ነኝ በሙያዬ አግዛችኋለሁ የሚል የስልክ ምላሽ ሰጥቻለሁ። መረጃ ዎች ላኪልን ስባልም በፍቃደኝነት ልኬያለሁ።

ከዚህ ውጭ ግዮን ሆቴል ተካሄደ ስለተባለ ስብሰባ የማውቀው ነገር አልነበረም፣ በቦታውም አልነበርኩም፣ ጥሪም አልደረሰኝም።

በጋዲሳ መገርሳ

ኀዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር) ከትግራይ ክልል አመራሮች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የፌዴራል መንግስትና የትግራይ ክልል አመራሮች በክልሉ የጸጥታና የፖለቲካ አስተዳደር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ፥ በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት በጋራ መፍታት እንደሚገባ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ በተለዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በጋራ ለመስራትና የክልሉ ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ መደረሱም ነው የተገለጸው፡፡

በተለይም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው የሚመለሱበትን ሁኔታና ታጣቂዎችን ወደ መደበኛ ህይወት የመመለስ ሂደት በትኩረት የሚሰራበት እና የሚሳለጥበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀም ህጋዊ  በሆነ አግባብ የህዝብንና የሀገርን ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሆን፣ ለህዝብ የሚቀርቡ የመንግስት አገልግሎቶች የሚሻሻሉበትና የህዝብን ፍላጎት የሚመጥኑ እንዲሆኑ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ስራ እንዲሰራ ተገቢው አቅጣጫ በውይይቱ መለየቱም ተጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም ጊዚያዊ አስተዳደሩ ክልላዊ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ያለበትን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ላይም አቅጣጫ ተቀምጧል ሲል ፋና ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋቾች እና  አስልጣኞች  እጩዎች ይፋ ይሆናል 

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ህዳር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ስምንት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

ማቲውስ ኩንሀ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ
ግራቨንበርች
ማርቲን ኦዴጋርድ
ጇ ፔድሮ
ቡካዩ ሳካ
መሐመድ ሳላህ
ዊሳ

የወርሀ ህዳር የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ሶስት እጩዎችም ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔል
አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር
አሰልጣኝ አርኔ ስሎት

በእጩነት መቅረብ ችለዋል።

በጋዲሳ መገርሳ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዙ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡ አቤቱታዎች በአመት 10ሺ አይሞሉም ተባለ

ይህ የተገለፀው በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጲያ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ አለም አቀፍ የፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀን "የሴትዋ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ ነው።

በፍትህ ሚኒስትር የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት ተረፈ ፤ በኢትዮጵያ ከፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዙ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡ አቤቱታዎች (ኬዞች ) በአመት 10ሺ አይሞሉም ብለዋል።

ይህ ማለት ግን ፆታዊ ጥቃቱ ቀንሶ ሳይሆን ጉዳዩን ወደ ህግ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት በተለያዩ ምክንያቶች አናሳ በመሆኑ ነው ሲሉ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

እንደ ምክንያት የሚነሳው ደግሞ አቤቱታዎች ጥቃቱ የደረሰባቸውን ሰዎችን ተከታትሎ ጉዳያቸውን ወደ ህግ ለማምጣት ሚያደርግ ተቋም አናሳ በመሆኑ እንደሆነም ተነስቷል።

ከፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ የህግ ስርአቱ ቢኖርም ትግበራው የጎላ አደለም የተባለ ሲሆን ይህንን ማስተካከል እንደሚገባ ተተግሯል።

ህጉ ክፍተት እንዳለው ቢሆንም የህጉ ትግበራው ግን መሻሻል አለበት ሲሉ በፍትህ ሚኒስትር የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት ተረፈ ተናግረዋል።

ብዙ ጊዜ አቤቱታ ለማቅረብ የሚደፍሩ ተጠቂዎች አናሳ ናቸው የሚሉት ወ/ሮ ምዕራፍ እሱን ከሚመለከተው አካላት ጋር በመሆን ማስተካከል እንዳለበት አንስተዋል።

በአለም ከሶስት ሴቶች በአንዷ ላይ የፆታዊ ጥቃት እንደሚደርስም የአለም አቀፍ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ለዓለም አሰፋ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዳሽን ባንክ ዘባንከር ሽልማት አሸነፈ፡፡

የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ የሚያሳትመው ዘባንከር መጽሔት ከኢትዮጲያ ዳሸን ባንክን የ2024 አሸናፊ አድርጎ መምረጡን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ህዳር 25-2017 ዓ.ም በእንግሊዝ ሎንዶን የተካሄደውን ሽልማት ተቀብሏል፡፡

ዳሸን ባንክ በዘርፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማቅረብ እና ከተለያዩ አለምአቀፍና አህጉራዊ ባለድርሻ አካላት ጋር የፈጠረው ውጤታማ ጥምረት ለሽልማት እንደበቃ ተገልፃል፡፡

ዘባንከር ሽልማት ባንኮች በየአመቱ ያስመዘገቡትን አፈፃፀም መሰረት በማድረግ የሚሰጥ ሽልማት ነው፡፡

ዳሸን ባንክ በምስራቅ አፍሪካ አካታች የፋይናንስ አገልግሎት በማቅረብና የላቀ አፈፃፀም ያሳየ ባንክ በሚል በአፍሪካ ባንክ 4.0 ጉባኤ መሸለሙን ባንኩ አስታውሷል፡፡

ለ 14ተኛ ጊዜ የተካሄደውን ዘባንከር ሽልማት አሸናፊ የሆነው ዳሽን ባንክ 6ተኛውን ስትራቴጂክ ዕቅድ በመተግበር ለደንበኞቹ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መልኩ ጥራት ያለውና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ጥረት እያደረገ መሆኑን ነው የገለፀው፡፡

ዳሸን ባንክ በ 880 በላይ ቅርንጫፎቹ መደበኛና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

የውልሰው ገዝሙ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዘምዘም ባንክ እና ሳንቲምፔይ ፋይናሻል ሶሊዩሽን የአጋርነት ፊሪማ በዛሬው እለት ተፈራርመዋል፡፡

የዘምዘም ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሊካ በድሪ ባንኩ የተቋቋመው በሃይማኖታዊ እምነት ወይም በሌሎች ምክንያቶች ከፋይናስ ስርዓቱ የራቀውን የህብረተሰብ ክፍል ልዩ ትኩረት በማድረግ የፋይናስ አካታችነትን ለማሳደግ ነው ብለዋል፡፡

ባንኩ በቀጣይ የወደፊቱን የዲጂታላይዜሽን ዘመን ከግምት በማስገባት እንዲሁም ጊዜንና ወቅቱን ያማከለ የፋይናስ ስርዓቶችን ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ዕቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፡፡

ወ/ሮ መሊካ ፤ዛሬ ከሳንቲምፔይ ፋይናንሺያል ሶልዩሽን አክሲዮን ማኅበር ጋር ያደረግነው የአጋርነት ስምምነት የክፍያ ሥርዓቱን ለማሳለጥ ይረዳናል ብለውናል።

የሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አ.ማ. ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ትንሳኤ ደሳለኝ በበኩላቸው ፤ሳንቲምፔይ ክፍያዎችን ለመፈጸምና ሌሎች አስፈላጊ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ የሚያስችል መጠነ ሰፊ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ የክፍያ መፈጸሚያ መንገድ ነው ብለዋል።

አቶ ትንሳኤ አሁን ላይ በክፍያ መፈጸሚያ ስረአቱ በአንድጊዜ የገንዘብ ዝውውር የሚያደርጉ ከ8 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ሳንቲምፔይ እያስተናገደ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ኩባንያው እስካሁን ቴሌ ብር፣ ሲቢኢ ብርን ጨምሮ ወደ አሥር ከሚሆኑ ባንኮች ጋር አብሮ እየሠራ መሆኑ አስታውቀዋል፡፡

በእዚህና በሌሎች የክፍያ አማራጮች ገንዘብ መክፈል የሚቻልበት ዕድል ስለተፈጠረ ሁሉንም ባንኮች በአንድ ላይ አያይዞ ለደንበኞች አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ዘምዘም ባንክ ዘመኑን የዋጀ ዲጂታል የክፍያ አማራጮችን ሺቶ ከእኛ ጋር በመስራቱ ደስብሎናል ሲሉ ተናግረዋል ።

ልኡል ወልዴ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ደቡብ ኮሪያ በፕሬዝዳንቷ ላይ የጉዞ ክልከላ ጣለች፡፡

የአገሪቱ መንግስት የወታደራዊ ህግን ተግግባራዊ ለማድረግ ሙከራ ማድረጉን ተከትሎ በፕሬዝዳንቱ ላይ የጉዞ እገዳ ተጥሏል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮል ከአገር እንዳይወጡ መደረጉን የፀረ ሙስና ቢሮዉ አስታዉቋል፡፡

የቢሮዉ ሃላፊ ኦህ ዶንግ ዉን ፕሬዝዳንቱ ወደየትኛዉም አገር እንዳይጓዙ እገዳዉን አስተላልፈናል ብለዋል፡፡

ዉሳኔዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩንና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን እንደማይመለከትም አብራርተዋል፡፡

ወታደራዊ ህግ ያወጁት የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል ለተግባራቸው ይቅርታ መጠየቃቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

ደቡብ ኮሪያ ዩን አስደንጋጩን ወታደራዊ ሕግ ማወጃቸውን ተከትሎ በፖለቲካዊ ቀውስ እና ትርምስ ውስጥ ገብታለች።

ፕሬዚዳንቱ ከሰሜን ኮሪያ ኮሚኒስት ኃይሎች አገራቸውን ለመጠበቅ ወታደራዊ ሕጉ አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናገረው ነበር።

ነገር ግን ወታደራዊ ሕጉ በታወጀ ሁለት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የፓርላማ አባላቱ ፕሬዚዳንቱን ተቃውመው በምክር ቤት ከተሰበሰቡ በኋላ አስቸኳይ ድምጽ በመስጠት ውሳኔውን አግደዋል።

አባቱ መረቀ

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሩሲያ ወዳጆቼን በመከራ ጊዜ አልከዳም አለች

ፑቲን በሽር አላሳድ በሞስኮ እንዲኖሩ መፍቀዳቸዉ ተሰምቷል

የሶሪያ አማጽያን ደማስቆ መግባታቸዉን ተከትሎ ወደ ሩሲያ የተሰደዱት በሽር አላሳድ በሞስኮ መኖር እንዲችሉ ፍቃድ አግኝተዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክተዉ ማብራሪያ የሰጡጥ የክሪሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ አሳድ በሩሲያ እንዲኖሩ ፍቃድ ተቸሯቸዋል ነዉ ያሉት፡፡

ፑቲንና አሳድ እስካሁን ባይገናኙም ነገር ግን በሞስኮ እንዲኖሩ ፍቃድ የሰጧቸዉ እራሳቸዉ ፑቲን ናቸዉ ብለዋል፡፡

አንጋፋዉ የሩሲያ ዲፕሎማት ሚካሂል ዩልያኖቭ በበኩላቸዉ ሩሲያ በመከራ ጊዜ ወዳጇን አትከዳም ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡

በአስቸጋሪ ጊዜ ወዳጅን መክዳት የሩሲያ ባህሪ ሳይሆን የአሜሪካ ነዉ ማለታቸዉን አርቲ ዘግቧል፡፡

አባቱ መረቀ

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የመንግስት ተቋማት የሚጠበቅባቸዉን የመረጃ ነፃነት ሪፖርት እያቀረቡ አይደለም ተባለ

ተቋማቱ በመረጃ ነፃነት አዋጁ ለሕዝቡ የሚጠበቅባቸውን መረጃ እንዲያደርሱ ቢቀምጥም ሪፖርቱን እያቀረቡ አለመሆኑ ተገልፆል።

የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሚቀርብለት የመረጃ ነፃነት ሪፖርት የዜጎች መረጃን የማግኘት መብት ግልጽነት እና ተጠያቂነት ለማምጣት እንደሆነ ይገልፃል ።

በኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የህግ ዝግጅት ክፍል ሀላፊ የሆኑት አቶ ተመስገን ኪዳኔ ተቋማቱ ላይ በተደረገ ግምገማ የመረጃ ነፃነት ሪፖርቶች አለመቅረባቸዉን ተመልክተናል ሲሉ ለኢትዩ ኤፍም ተናግረዋል።

መረጃዎች በተፈለገዉ ልክ ያለመላክ ክፍተት ተቋማቱ ላይ እንደሚታይ የሚገልፁት ሀላፊዉ ሆኖም አዋጁ የመንግሰት ተቋማት ሪፖርቱ እንዲቀርብ ግዴታ የሚጥል  ነዉ ይላሉ።

የህዝብ ግንኙነት እና የመረጃ ክፍል ባለሙያዎች ላይ ስለ መረጃ ነፃነት ሪፖርቱ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየሰራ መሆኑን የተቋሙ የህዝብ ዝግጅት ክፍል ሀላፊዉ ይገልፃሉ።

ይህንን የመረጃ ነፃነት ሪፖርት በትክክል ለማስፈፀም እንዲቻል አዋጁ ማሻሻያ ረቂቅ እንደተዘጋጀለት አቶ ተመስገን ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

በተጨማሪም ተሻሽሎ በረቀቀዉ የመረጃ ነፃነት አዋጅ ሪፖርቱን ማቅረብ ከመንግስት ተቋማት በተጨማሪ የግል ተቋማትን የሚጨምር እንደሆነ ተጠቅሷል።

ይህንን የተሻሻለ አዋጅ አፅድቆ ወደ ስራ በማስገባት የዜጎችን የመረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ እንዲቻል ምክር ቤቱ በትኩረት እንዲመለከተዉ ተጠይቋል።

ቁምነገር አየለ

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአዲስ አበባ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት "የሰው ህይወት ቀጥፏል" መባሉን መንግስት እንዲያጣራ ኢዜማ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት “የንፁሀን ዜጎች ህይወት መቀጠፉ እየተሰማ ነው” መሆኑን አሳውቋል፡፡


ፖርቲው ወደ ከተማም ሆነ ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት የሚገባ ታጣቂ ኃይል ሁሉ ትጥቁን ለሚመለከተው የጸጥታ አካል አስረክቦ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝቧል።

በመሆኑም በተለያዩ ቦታዎች ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ የጥይት ተኩስ ማድረጋቸው ንፁሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እና የስነ ልቦና ጫና የሚያሳድር፤ አግባብነት የሌለውም ተግባር መሆኑ ታውቆ በሁሉም ቦታዎች ላይ እንዲቆም አሳስቧል፡፡

ይህን ተከትሎም ትናንት ምሽት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የተሰማውን ተኩስ ተከትሎ ለዜጎች ድንጋጤ እና መረበሽ ይቅርታ ቢጠይቅም ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት የንጹሀን ዜጎች ህይወት ማለፉ እየተነገረ መሆኑን ፓርታው ጠቁሟል፡፡

"ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ሕግና ሥርዓትን በማክበር መሆኑ መዘንጋት አይኖርበትም" ሲልም አሳስቧል::

ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ትናንት ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በመጓዝ ላይ የነበሩ "የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን አባላት" በአዲስ አበባ በተለያዩ አከባቢዎች ላሰሙት ተኩስ የ አዲስ_አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይቅርታ መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሶሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ በሞስኮ ይገኛሉ ተባለ።

በአማፂያን ከ23 ዓመት የስልጣን መንበራቸው በሀይል የተገረሰሱት አሳድ  በሩሲያ ጥገኝነት እንደተሰጣቸው የክሬምሊን ምንጭ  ጠቅሱ TASS ዘግቧል ።

ኀዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሶሪያው ፕሬዚዳንት ዋና ከተማዋን አስረክበው ፈረጠጡ

የሶሪያ አማፅያን የአገሪቱን መዲና ደማስቆን በእጃቸው ማስገባታቸውን ተከትሎ  ፕሬዝዳንቱ መሸሻቸው ተነግሯል።

ደማስቆን መቆጣጠራቸውን ያወጁት አማፅያኑ  አሁን ከተማዋ ከአሳድ ነፃ ነች ብለዋል።

የአገሪቱ ጦርም ይሄንኑ አረጋግጧል ።

ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ከተማዋን ለቀው መሸሻቸውን አርቲ ዘግቧል ።


አባቱ መረቀ

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሳንቲምፔይ ፋይናሺያል ሶሊዩሽን መደበኛ ጉባዬውን በዛሬው እለት አካሄደ

የሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን  ሁለተኛ ዙር ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት፤ሀዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል።

ሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አ.ማ. በኢትዮጵያ የክፍያ ስርአት ኦፕሬተር ሆኖ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የክፍያ ስርዓት በአዋጅ ቁጥር 718/2011 በሃምሌ 2014 የተቋቋመ አክስዮን ማህበር ነዉ ተብሏል።

ኩባንያው ከጥሬ ገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆኑ የዲጂታልና የዘመናዊ ግብይት ሥርዓትን መዘርጋትን ዋናው ዓላማ አድርጎ ወደ ሥራ ከገባ ሁለት ዓመትን ሆኖታል፡፡ 

ሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን በ15 ባለአክሲዮኖች የተቋቋመና በ161 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተመሠረተ መሆኑንም ሰምተናል፡፡

ቦርዱ በዛሬው እለት የሁለተኛ መደበኛ ጉባዬው ላይ ለቦርድ አባሉቱ እንደገለፀው  በሳንቲምፔይ የክፍያ ስርዓት ስር የተመዘገቡ 15ሺህ 9መቶ60 አዲስ ደንበኞችን የቀላቀለ ሲሆን በድምሩ የደንበኞቹን መጠን ከ27ሺህ በላይ መድረስ ችለዋል ።

በገንዘብ ደረጃ በቀን ከ200ሺህ በላይ ጊዜ ከባንክ ወደባንክ እንዲሁም ከሰው ሰው ይለዋወጣሉ ያሉን ሲሆን በአጠቃል በአንድ አመት ውስጥ 44 ሚሊዮን ጊዜ ልዊውጥ መደረጉም ተነግሯል።

በዚህ መሰረት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በሳንቲምፔይ የክፍያ ስርዓት ከ16 ቢሊየን ብር በላይ ተንቀሳቅሷል ።

በአሁን ጊዜ ቁጥራቸው 12 ከሚሆኑ ባንኮች ጋር በአጋርነት እየሰራም ይገኛል።በቅርቡ የሚቀላቀሉ የመንግስትም የግል ድርጅቶች መኖራቸውም ተጠቁሟል።

አሁንላይ ተቋሙ ብራንቾቹን ለማስፋትና በሁሉም ክልል እና ስፍራ አሰራሩን ለማዳረስ እየሰራ ይገኛል ተብሏል ።


ልኡል ወልዴ

ኀዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ደረጃን መሰረት ያደረገ የምርት ሂደት በመከተል ከአለም ገበያ ጋር መዋሀድ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ ።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የአለም አቀፉን የጥራት ቀንን እያከበረ ይገኛል።

ፐድርጅቱ የጥራት መሰረተ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልፆል።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዳይሬክተር ኢ/ር መአዛ አበራ ምርት ለመጨመርና ለማሳደግ መስፈርቶች ከማሟላት ባሻገር ወደ ላቀ የአፈፃፀም ብቃት ለማደግ የጥራት እሳቤዎች ማሟላት ያስፈልጋል ብለዋል።

የኤክስፖርት ድርሻዉን ከፍ ለማድረግ ከዘላቂ የአካባቢ ደህንነት የጠበቀ አምራች ኢንደስትሪ መገንባት ያስፈልጋል ሲሉም ገልፀዋል

በቀኑን አስልክቶ ለሶስት ቀናት የሚቆይ አዉደ ርእይ ተከፍቷል። በአዉደ ርእዩ ጥራትን መሰረት ያደረጉ አምራች ኢንደስትሪዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጎበታል።

በአለምአቀፍ የገበያ ሰንሰለት ዉስጥ ለመሳተፍ እንዲሁም የተኪ ምርቶችን አቅም ለማሳደግ ጥራት ወሳኝ መሆን አለበት ተብሏል።

ጥራቱን የጠበቀ ምርት እና አገልገሎት ለማቅረብ የተስማሚነት ምዘና አቅምን ማሳደግ እንዲሁም በአምራች ኢንደስትሪ አመራር ላይ የመስፈርት ግንዛቤን ማስፋት እንደሚያስፈልግ ተገልፆል።

እንደ አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ያሉ ቀጠናዊ እና አህጉራዊ የኢኮኖሚ ማእቀፎች የሚፈጥሩትን የገበያ እድል ለዘርፉ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችሉ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል

ቁምነገር አየለ

ኀዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት ሆና የተመረጠችው አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን በቀጣይ ለመስራት ስላሰበችው እቅድ አብራርታለች።

“ምክትል ፕሬዝዳንት መሆኔን አልጠበቅኩም ነበር በዚህም በጣም ደስ ብሎኛል አዲስ አበባ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መስራች እንደመሆኗ አሁን ያለችበት ሁኔታ ደስ አይልም እና ዋናው ነገር ብዬ ማስበው ፋይናንስ ድጋፍ ያስፈልጋታል ስለዚህም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከኤምባሲዎች ጋር ጠንካራ የሆነ ስራን በመስራት ያስፈልጋል በተለይም አዲስ አበባ የኢትዮጲያ መዲና እንደመሆኗ ብዙ አምባሲዎች አሉ።

“ከእነርሱ ጋር አብሬ በመስራት Fund የመጠየቅ እንዲሁም ስፖንሰሮችን የማምጣት እቅድ አለኝ ሴቶችንም ለመደገፍ አስባለሁ እነሱ ሴቶችን በጣም ደስ እያላቸው ነው የሚደግፉት ከተለያዩ ባለሀብቶች እና ፋብሪካዎች ጋር በመስራት ጥሩ የሆነ ገቢን በማስገኘት እደግፋለሁ።”

“እግርኳስ በአለማችን ላይ ከ4 ቢሊዮን በላይ ተመልካቾች ያሉት የጨዋታ አይነት ነው እና ሁላችንም የምንወደው ሀገራችንን ማስጠራት የምንፈልግበት የስፖርት አይነት ስለሆነ ሁላችንንም ይወክላል ስለዚህ ሁሉም ሰው ደስ ብሎት የሚያግዘኝ ይመስለኛል።”   

የከተማዋን እግርኳስ በገንዘብ ለማገዝ ማቀዷንም አርቲስቷ ጨምራ ተናግራለች።

በጋዲሳ መገርሳ

ኀዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ እና ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት አ.ማ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ በሚል መጠሪያ በይፋ ተዋሃዱ።

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የማብሰሪያ እና ስራ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በግራንድ ኤሊያና ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በመርሐ-ግብሩ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የሚዲያው አመራሮች የድርጅቱ ሰራተኞች፣ ተባባሪ አዘጋጆች፣ የሚዲያው አጋሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ለተመሳሳይ ዓላማ የተቋቋሙት የሚዲያ ተቋማት ውህደት አንድ ግዙፍ እና ተደራሽ ሚዲያ ለመመስረት ያለመ ነው።

ውህደቱ የፋይናንስ፣ የሰው ሃይል፣ የቴክኖሎጂና የመሰረተ ልማት አቅምን በማቀናጀት የሃብት ብክነትን ማስቀረት እንደሚያስችል ተመላክቷል።
ከዚህ ባለፈም የማህበራቱ ውህደት ትርፋማነትንና ውጤታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ ሁለት የቴሌቪዥን ቻናሎች፣ ሶስት ሬዲዮ ጣቢያዎችና ሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይኖሩታል።

የውህደቱ ሒደት አስፈላጊውን ሕግና ሥርዓት ተከትሎ መፈጸሙም ተገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዳኝነት ክፍያ ማሻሻያው  የተጋነነ እና  ዝቅተኛውን የህብረተሰብ  ክፍልን  ያላገናዘበ ነው በሚል ቅሬታ ቀረበበት

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ ደንብ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ ሲሆን ጣቢያችን ያየው  ይህ የክፍያ ወሰን እስከ 5 እጥፍ  ጭማሪ ተገልጋዮች ላይ  የሚጥል ነው።

ደንቡን ማሻሻል ያስፈለገው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከዚህ ቀደም የሚጠቀሙበት የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል ለ72 ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት  የቆየ በመሆኑ ነው  መባሉም ተነስቷል፡፡

ታዲያ ጣቢያችን ያነጋገራቸው የህግ ባለሞያ እና ጠበቃ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ  ‘’የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ በዚህ ልክ መጨመሩ ከሳሽ ክሱን ወደ ፍርድ ቤት እንዳያመጣ እንቅፋት   እንዳይሆን”  ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተዘጋጀው ደንብ መሰረት የ10 ሚሊየን ክርክር ያለበት አንድ ተከራካሪ ወደ 1መቶ ሺ ብር አካባቢ እንደሚከፍል ያስታወሱት ባለሞያው በአሁኑ ጭማሪ ግን ወደ 5 መቶ ሺ ብር እንደሚያደርሰውም አንስተው ይህም መጋነኑን ያሣያል ብለዋል፡፡

በዚህም የፍትህ ስርዓቱን ወደ ኋለ እንዳይወስደው እንዲሁም የፍትህ መዘባት እንዳፈጠር የህግ ባለሞያው ስጋታቸውን አካፍለውናል፤፡

የህግ አማካሪው እና ጠበቃ አቶ ጥጋቡ "72ዓመታትን የቆየው የዳኝነት ክፍያ ማሻሻያ መደረጉ መልካም ቢሆንም ጭማሪው ተጋኗል" ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

የህግ ባለሞያው  በሃሳባቸውምመእንደዚህ ዓይነት ጭማሪዎች ሲደረጉ በቅድሚያ የኑሮ ውድነቱን ከግምት ማስገባት እንዳለበት  አስረድተዋል፡፡

ዜጎች ፍትህ የማግኘት ሙሉ መብት አላቸው የሚሉት ጠበቃው  መንግስት በበኩሉ ከአገልፈግሎት ሰጪ ተቋማት የሚገኘውን ገንዘብ እንደ የገቢ ግብር መሰብሰቢያ መመለክት እንደሌለበትም ጠቁመዋል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel