ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

ዕድሜያቸዉ ከ5ዓመት በታች ለሆኑ ከ6መቶሺህ በላይ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ለመስጠት ዘመቻ ተጀመረ፡፡

በመዲናዋ ሁለተኛው ዙር የልጅነት ልምሻ /ፖሊዮ/ ክትባት መሰጠት ተጀምሯል።

በዚህኛዉ ዙር ከ6መቶ92ሺህ በላይ ህጻናትን ለመከተብ በዕቅድ መያዙም ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያ ዙር በተካሄደዉ ዘመቻ ከ6 መቶ 28 ሺህ በላይ ዕድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን ለመከተብ ታቅዶ፤ ከ6መቶ91 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህጻናት ክትባቱ መሰጠቱን ሰምተናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ ፤የህፃናት ልምሻ ለሞትና ለዘላቂ ጉዳት የሚዳርግና ከዘር ወደ ዘር የሚተላለፍ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዚህም ለሁለተኛ ጊዜ በሚደረገዉ የክትባት ዘመቻ ከ6መቶ92 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህጻናት ክትባት ለመሰጠት መታቀዱን ተናግረዋል።

እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት በሙሉ ከዛሬ ታሕሳስ 03 እስከ 06/2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤት፣ በማቆያ እና በማሳደጊያ ቦታዎች እንዲሁም በሌሎች ሕጻናት በሚገኙበት ሁሉ በአፍ ጠብታ ክትባቱ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የፖሊዮ በሽታ የሕጻናትን የእግር እና የእጅ ጡንቻ በማልፈስፈስ ለሽባነት እና ለከፋ የጤና ችግር የሚዳርግ በመሆኑ፤ ወላጆች ከዚህ በፊት ክትባት የወሰዱም ሆነ ያልወሰዱ ዕድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናትን ልጆቻቸዉን እንዲያስከትቡ ቢሮው ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ታህሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አካል ጉዳተኞች የንብረት ታክስ መክፈል የለባቸውም” ሲል የኢትዮጵያ ምሁር አይነስውራን ሴቶች ማህበር ገለፀ፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴር በበኩሉ፤ “አካል ጉዳተኛ ሁሉ ድሃ ስላልሆነ የንብረት ታክስ አይክፈሉ የሚለው ክርክር አያስኬድም ብሏል፡፡

የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም የኢትዮጵያ ምሁር አይነስውራን ሴቶች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር በቀለች ጥሩዬ “ከአካል ጉዳተኞች ላይ የንብረት ታክስ መውሰድ አግባብ አደልም” ሲሉ በምክር ቤቱ ተናግረዋል፡፡

ደ/ር በቀለች አካል ጉዳተኞች በኢትዮጵያ ያሉበት ሁኔታ የሚታወቅ ነው ያሉ ሲሆን በተለየም ፋይናንሻሊ ራሳቸውን እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

ከ89 በመቶ በላይ በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ትምህርት አንዳላገኙ የትምህርት ሚኒስትር ጥናት ያመላክታል የሚሉት ዶ/ር በቀለች ይህ ደግሞ ራሳቸውን በጊቢ እንዳያደረጁ አድርገዋል ብለዋል፡፡

አካል ጉዳተኞች ፤ አካል ጉዳተኛ ካለሆኑ ሰዎች በእጥፍ ለወጪ የተጋለጡ ናቸው የሚሉት ዶ/ር በቀለች እንደውም እንደውጪው አለም ሊደጎሙ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በዚህም አካል ጉዳተኞች ከንብረት ታክስ ክፍያ ነጻ መሆን አለባቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ምሁር አይነስውራን ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንቷ በተደረገው የምክክር መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡

በምክር ቤቱ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስተር ከፍተኛ ሃላፊ አቶ ዋሱሁን አበበ በበኩላቸው “አካል ጉዳተኛ ስለሆነ ታክስ አይክፈል የሚለው አግባብነት የለውም” ሲሉ አስርድተዋል፡፡

አቶ ዋሲሁን “አካል ጉዳተኛ እንደ ማንኛውም ህብረተሰብ ክፍል ዝቅተኛ ገቢ ካለው የንብረት ታክስ አይቆረጥበትም ነገር ግን አካል ጉዳተኛ ሁሉ ደሃ ነው ማለት ግን ልክ አደልም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አካል ጉዳተኞች ጥያቄዓቸው መሆን ያለበት ግን ታክስ ከፍለው ለአካል ጉዳተኛ የሚሆን መሰረተ ልማት ካልተሰራ እሱን መጠየቅ ነው ያለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ለአለም አሰፋ

ታህሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ድርድር በስኬት ተጠናቀቀ

በቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ተጠናቀቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያና የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ በባህል እና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን አንስተው አገራቸው ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የባህር በር በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ለቀጣናው ምጣኔ ሃብታዊ እና ማህበራዊ ትስስር የጎላ ሚና እንደሚጫወት አንስተዋል

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃሙድ በበኩላቸው ለሁለቱ ሃገራት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሰላም ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተው ከኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

መንግስታቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም መጠበቅ የከፈሉትን መስዋዕትነት እንደማይዘነጋው እና በቀጣይም ሰላምን ለማፅናት ለሚረገው ጥረት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን:- ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት የስምምነት ሰነድ ትብብርን፣ ምጣኔ ሃብታዊ ልማትን እና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ታህሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሳውዲ አረቢያ የ2034  የአለም ዋንጫ አስተናጋጅ ሆነች!
ሳውዲ አረቢያ የ 2034ቱን አለም ዋንጫ ውድድር ለማዘጋጀት በብቸኝነት ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
ዛሬ በነበረ የፊፋ ጉባኤ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ሳውዲ አረቢያ ማሸነፏን አረጋግጠዋል።
ለብዙዎች የሳዑዲ ዓለማቀፍ ዋንጫ ማፅደቁ ሀገሪቱ አሁን በስፖርታዊ ጨዋነት የምትጠቀምበት ኃያልነት የመጨረሻ መግለጫ እና ከዚ ጋር ተያይዞ የመጣው ዕድል፣ መቋረጥ እና ውዝግብ ይሆናል።
እ.ኤ.አ. ከ2021 ጀምሮ መንግሥቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ ኢንቨስት አድርጓል። መንግሥቱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፎርሙላ 1ን፣ የእግር ኳስ የስፓኒሽ እና የጣሊያን ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታዎችን፣ የዓለም ክለቦች ዋንጫን እና ከፍተኛ ደረጃ ቦክስን፣ ጎልፍን፣ የፈረስ እሽቅድምድም እና ቴኒስን አስተናግዷል።

የሀገሪቱ የህዝብ ኢንቬስትመንት ፈንድ የተለየውን   አራት የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ክለቦችን ተቆጣጥሮ ኒውካስል ዩናይትድን ገዝቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ የዴንማርክ ድርጅት ፕሌይ ዘ ጨዋታ ባወጣው ዘገባ ሳዑዲ አረቢያ ከ900 በላይ የስፖንሰርሺፕ ስምምነቶችን መፈራረሟን ገልጿል፣ ውጪያዊ እና በደርዘን የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖችን በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ተጽእኖዋን እያሰፋች ትገኛለች።

በግንቦት እና በሴፕቴምበር መካከል፣ አማካኝ የየቀኑ የሙቀት መጠን ከ27C እስከ 43C በውስጥ አካባቢ፣ እና በባህር ዳርቻዎች ከ27C እስከ 38C መካከል ይደርሳል።

የሳውዲ ስፖርት ሚኒስትር ልዑል አብዱልአዚዝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዘጋጆቹ በበጋው ዝግጅት ይቻል እንደሆነ በእርግጠኝነት እያጠኑ ነው።

"በበጋው ወቅት ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለምን አትታይም? በበጋም ሆነ በክረምት ለኛ ምንም ለውጥ አያመጣም, እንደዚህ አይነት ክስተት ለማስተናገድ ትክክለኛውን ከባቢ አየር እንደሰጠን እስካረጋገጥን ድረስ." በማለት ተናግሯል።
የአለም ዋንጫው እየተስፋፋ ሲሆን ከ2026 ጀምሮ 48 ቡድኖች ይሳተፋሉ። ይህም በኳታር ከተወዳደሩት 32 ጭማሪዎች ነው።

ጋዲሳ መገርሳ

ታኀሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የታኅሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በየትኛውም የሥራ መስክ ለሚሰማሩ የዲጂታል ፋይናንሺያል ክህሎት ወሳኝ ነው ተባለ

በየትኛውም የሥራ መስክ ለተሰማሩና ለሚሰማሩ የዲጂታል ፋይናንሺያል ክህሎት ወሳኝ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ ፤በ2025 የድጅታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት በማድረግ የማህበረሰቡን የድጅታል ክህሎት የሚያጎለብት ሁለተኛ ዙር የዲጂታል ፋይናሽያል ክህሎት ሥልጠና በዘመቻ መጀመሩን ገልፀዋል።

ዶክተር ይሽሩን በዘመቻው ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት በየትኛውም የሥራ መስክ ለተሰማሩና ለሚሰማሩ ሁሉ የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና ወሳኝ ነው ።

በዚህም ለትግበራ ቴክኒካል ኮሚቴ በማዋቀር በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እንዲሁም በመምህራን የታገዘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተጀምሯል ብለውናል ።

ሚኒስትር ዴታው በመጀመሪያ ዙር ከ40 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች በዘመቻ መልክ ተሰጥቷል ነው ያሉት።

በዚህም በሁለተኛ ዙር የዲጂታል ፋይናንሺያል ክህሎት 50ሺህ የሚሆኑት ለመድረስና በዘመቻ መልክ በከተማ እንዲሁም በክልል ከተሞች ላሉት ከአርሶአደር ጀምሮ በተለያዩ የሙያ መስክ ላይ ለተሰማሩ የማህበረሰብ ክፍል ከገፅ ለገፅ የስልጠና አሰጣጥ ጀምሮ በሁሉም የሚዲያ አማራጮች ይሰጣል ተብሏል ።

ዘመቻውን ያስጀመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ከUNCDFና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው።

ልዑል ወልዴ

ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ብቻ ከ 71 ሺህ በላይ የወባ ህሙማን ሪፖረት ተደርጎል ተባለ

ባሳለፍነው ሳምንት ከ 71 ሺህ በላይ አዳዲስ የወባ ህሙማን ሪፖርት መደረጉን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሰታውቆል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንከር ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከሌሎች ሳምንታት አንፃር 4.2 በመቶ የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቷል ፡፡

በበጀት አመቱ ከ 1 ሚለዮን 1መቶ 46 ሺህ በላይ የወባ ህሙማን ሪፖርት መደረጉንም አንስተዋል፡፡

ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ አመት ጋር ሲነፃፀር የ67 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

ስርጭቱን ለመቆጣጠር ጤና ጣቢያ መር ማህበረሰብ አቀፍ አካባቢ ቁጥጥር ስራ አየተሰራ መሆኑ ተገል ጧል

በዚህም ከ 6 መቶ በላይ በሆኑ ጤና ጣቢያዎች ማህበረሰብ አቀፍ አካባቢ ቁጥጥር ስራዎች መስራት መጀመሩን የፕሮግራም አስተባባሪው ተናገረዋል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢንተርኔት አገልግሎት ውስንነት እና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ለተጠቃሚዎች ችግር ሆኗል ተባለ።

የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂን በማሳካት ሂደት ተገልጋዮች ችግር እያጋጠማቸው መሆኑንም ተገልጿል።

የቴክኖሎጂውና የተጠቃሚው ያለመተዋወቅ እንዲሁም የሲስተም ችግር ተጠቃሚውን ለእንግልት እንደዳረገው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

የኢንተርኔት አገልግሎት ውስንነት፣ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ፣ የሀይል አቅርቦት እጥረት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት ማነስ እና ቴክኖሎጂን ገዝቶ ለመጠቀም የኢኮኖሚ አቅም አነስተኛ መሆን በኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንን ለማስፋፋት እንቅፋት እንደሆኑ ተገልጿል።

የተለያዩ ችግሮች እንደሚያጋጥሙ የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ ሲስተም በሚበላሽበት ወቅት ችግሮችን ለማስተካከል በጋራ መስራት እንደሚጠበቅም አንስተዋል።

የዲጂታል መሰረተ ልማትን በማስፋት በ2025 ኢትዮጵያን ሙሉለሙሉ ወደ ዲጂታል አለም ለመለወጥ እየተሰራ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

አፎሚያ አሸናፊ

ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጨዋቾች ጥሪ አቅርበዋል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ማጣርያ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታውን ታኅሣሥ 13 እና 16 ሊቢያ ቤንጋዚ ላይ ያደርጋል።

የብሔራዊ ቡድናችን ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረጉ ሲሆን ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል በመሰባሰብ ሐሙስ ታኅሣሥ 3 ለጨዋታዎቹ የሚያደርገውን ዝግጅት ይጀምራል።

ጋዲሳ መገርሳ

ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ማሻሻያ ተደርጎበታል ሊጉ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ይምጣ ይሆን !

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬደዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መርሃ ግብሩን እስከ 13ኛ ሳምንት በድሬደዋ ለማካሄድ ፕሮግራም ቢወጣም በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ላለበት የቻን የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ምክንያት ሊጉ ከ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ ይቋረጣል።

ነገር ግን የአንደኛ ሳምንት ተስተካካይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 06/2017 በድሬዳዋ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

ከ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ጀምሮ ያለውን የ2017 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  በአዳማ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ከታህሳስ 25/2017 በኋላ ያለውን መርሃ ግብር በቀጣይ ቀናት የምናሳውቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ

ጋዲሳ መገርሳ

ታኅሣሥ 1 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዪት 350 የሚሆኑ ደረጃዎችን ማፅደቁን ገለፀ

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዪት 40ኛ እና 41ኛ ጉባኤውን ባዘጋጀበት ወቅት ነው 350 የሚደርሱ ደረጃዎችን ማፅደቁን የገለፀው።

የፀደቁት ደረጃዎች በ6 ዘርፎች እና በ23 ቴክኒክ መንገዶች 207 አዲስ 143 የተከለሱ ደረጃዎች መሆናቸውን ተገልጷል።

በደረጃዎቹም በግብርና እና ምግብ 16 አዲስ 24 የተከለሱ እንደሚገኙበትም ተገልጿል።

ከተሰጡት ደረጃዎች ብዙዎቹ አስገዳጅ እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን ጥንቃቄን ከመምረጥ አኳያ እንደሆነም ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት እስካሁን 12ሺ የሚጠጉ ደረጃዎች እንዳሉትም ተገልጿል።

ለዓለም አሰፋ

ታኅሣሥ 1 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተውን ድንገተኛ በሽታ እሰካሁን ሊታወቅ አልቻለም፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እና የአፍሪካው የጤና ተቋም ሲዲሲ በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተውን ድንገተኛ በሽታ መመርመር ጀምረዋለ።

በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ከ 4 መቶ ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የአለም ጤና ድርጅት እና የአፍሪካው ሲዲሲ የበሽታውን ምንነት ለማወቅ ምርመራ መጀመራቸው ታውቋል።

በኮንጎ በደቡባዊ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኘው ክዋንጎ ክፍለ ሀገር ውስጥ የተከሰተው ይህ በሽታ እስካሁን ከ 4 መቶ በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፉል።

ከእነዚህም አብዛኞቹ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው።

ሳል፣ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ እና የመሳሰሉ ምልክቶች አሉት የተባለው በሽታው የተከሰተበት አካባቢ ከከተማ መራቅ ለጤና ተደራሽነቱን አስቸጋሪ እንዳደረገው ተነግሯል ሲጂቲኤን አፍሪቃ ዘግቧል፡፡

የውልሰው ገዝሙ

ታኅሣሥ 1ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

እስራኤል ለምን ጦሯን ወደ ሶሪያ አስገባች?

የቂጣዉን ጦርነት የደመደመዉ የ1974ቱ ስምምነት ዛሬ አፈር ድሜ በልቷል አሉ የእስራኤሉ አለቃ ቢቢ፡፡

ሰዉየዉ ዛሬም የጦርነት ጥማቱ አልቆረጠለትም እንዴ ሲሉ የፋርሶቹና የአረቡ አለም ሰዎች ይጠይቃሉ፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጦራቸዉ ደቡባዊ ሶሪያን እንዲቆጣጣር ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡

ማዲናት አል ባዝ እና ሃደር የገባዉ የእስራኤል ጦር ወደ ቁኔትራ እየገፋ ነዉ፡፡

ወትሮዉም አላሳድ ደማስቆ ተቀምጠዉም የሃያላኑ ምቹ መፋለሚያ የነበረችዉ አገረ ሶሪያ ሰዉየዉ ወዳጄ ፑቲን ሆይ አስጠልለኝ ብለዉ ወደ ሞስኮ ሲፈረጥጡ በ7 ግንባሮች አገረ እስራኤል ጦርነት ተከፍቶባታል ሲሉ የነበሩት ቢቢ የጎላን ኮረብቶችን ተሸግረዉ ወደ ሶሪያዋ ዳኣራ ከተማ ጦራቸዉ እየገፋ ነዉ ሲል ፕሬስ ቴለቪዥን ዘግቧል፡፡

አሁን የኣሳድ ስራዉ መንግስት ተገርስሶ ሰዉየዉን ግዞተኛ አድርጎ ወደ ሩሲያ ሸኝቷል፡፡

ግን ዛሬም አገረ ሶሪያ እጣፈንታዋን አላወቀችም፡፡
ምክንያቱም የአማጽያኑ ዉሳኔ እንዳለ ሆኖ አለመታት በሁለት ጎራ ተከፍለዉ ጥንታዊቱን ከተማ ደማስቆን፤ አሌፖን ፤ ሃማን ዳራንና ኢድሊብን ሲያወድሙ የነበሩ ሃያላን አገራት ቀጣይ ዉሳኔ ምን ሊሆን ይችላል የሚለዉ ተጠባቂ ነዉና፡፡

አሁን የነጩ ቤተመንግስት፤ የብረሰልስ፤ የክሪሚሊን፤ የሰዳባድና የቤት አግዮን አለቆች አይናቸዉን ደማስቆ ላይ ተክለዋል፡፡

የእስራኤል አለቆች ግን ማፍጠጥ ብቻም ሳይሆን ጦር እስከማዝመት ደርሰዋል፡፡

ይህ ደግሞ የገላን ምድርን ብቻም ሳይሆን መከረኛዉ መካከለኛቀዉ ምስራቅን ለዳግም ዉጥረት ዳረጎታል፡፡

ለመሆኑ እስራኤል ስለምን የእግረኛ ጦሯን ወደ ሶሪያ ምድር አሰገባች የሚለዉ የብዙዎች ጥያቄ ነዉ፡፡

ዮም ኩፑር በተባለዉ የእስራኤል ብሔራዊ በዓል ዕለት ጥቅምት 1973 የተጀመረዉ ዉጊያ የእስራኤል ጦር ካይሮን አልነካም።

የሲና በረሐንም በከፊል ለቆ በሶሪያ ግንባር ግን ከ1967 ጀምሮ እስራኤል በኃይል በያዘችዉ በጎላን ኮረብታ ላይ የሰፈረ ጦሯን አጠናክራ ደማስቆን በመድፍ፤ሚሳዬሏ የርቀት ቀለበት ዉስጥ አስገባቻት።

ከዚያ ሁሉ እልቂት በኋላ አገረ ሶሪያና እስራኤል ስምምነት ላይ ደርሰዉ ነበር፡፡
ዛሬ ግን ያ አፈር ድሜ መብላቱን ኔታንያሁ በቦታዉ ተገኝተዉ ለአለም አሰሙ፡፡
ከፈረንሳይ ነጻ ከወጣች ከ1946 ጀምሮ የመካከለኛው ምስራቅ ትኩሳት የሚንጣት፤ ውስጣዊና ውጪያዊ ቀውሶች የሚያምሳት አገር ነች።

ከሳምንት በፊት የጀመራት ትርምስ ግን የሀገሪቱን ቀጣይ ዕድል ዕጣ ፈንታ ከሚወስንበት ምዕራፍ የተጠጋ መስሏል ተብሎ ይሄዉ የተፈራዉ ሆኗል።

ሶሪያ በ1967 ከግብጽ ወግና እስራዔል ላይ ብረት ካነሳችና በተሽናፊነት በእጇ የነበረውን የጎላንን ኮረብታ ካጣች ወዲህ በምዕራቡ ዓለም ጥቁር መዝገብ ላይ በደማቁ ተቀምጣለች።

ለእስራዔል የጎን ውጋት በመሆን ሃማስንና የሊባኖሱን ሂዝቦላ በማስታጠቅ በመልዕክተኞች በቀሏን እየተወጣች ተብላ ትከሰሳለች።

በቀጠናው የእስራዔል ቀንደኛ ባላንጣ ሆኗ የተሰለፈችው ሶሪያ በሊባሎስ የውስጥ ጉዳይ በእጅ አዙር ጣልቃ እየገባች የፈለገችው ፖለቲካኛን ስታሾም፤ ያልፈለገችውን ስታሽርና ስታስገድል እየተባለችም ትወነጀላለች።

ወታደሮቻቸው ወደ ሶሪያ ዘልቀው በመግባት የወታደራዊ ነጻ ቀጠና እንዲወሩ ትዕዛዝ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ፣ የበሻር አል አሳድን ስርዓት መውደቅ ለመካከለኛው ምስራቅ ታሪካዊ ቀን ብለውታል።

የደማስቆው አምባገነን ሥርዓት መገርሰስ ትልቅ ዕድል ያመጣል፤ ግን ደግሞ የሚጠበቅ አደጋም አለው ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በማብራሪያቸው እሰራኤል የአሳድ ዋነኛ አጋር የሆኑትን ሄዝቦላህ እና ኢራንን በማጥቃቷ ስርዓቱ እንዲወድቅ ትልቅ ሚና መጫወቷን ገልጸዋል።

በዚህም ከእስራኤል ጋር በሰላም መኖር ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የሰላም መልክት ልከናል ብለዋል።

አሁን ሶሪያ ውስጥ ዘልቀው የተቆጣጠሩት አካባቢ በጊዜያዊነት የተያዘ እና በሶሪያ የመንግሥት ሥርዓት እስኪዘረጋ የሚቆይ መሆኑን ገልጸዋል።

ለአንድ ዓመት ያህል ጦርነት ውስጥ የነበረችው እስራኤል በቂ የጦር ግንባሮች ተፈጥረውላታል።
ነገር ግን በሰሜን በኩል የምትጎራበታት ሶሪያ ሁኔታም ሌላኛው አሳሳቢ ጉዳይ ነው።

መከላከያ ሰራዊቷ ቀድሞ ወደ ጎላን ተራራዎች ገብቶ ወሯል።
እስራኤል በተለይ በሻር አል አሳድ አከማችተውታል የሚባለው የኬሚካል መሣሪያ በማን እጅ ሊወድቅ ይችላል የሚለው በእጅጉ ያሳስባታል።
የሶሪያ አማጺያን መሪ አቡ ሞሃመድ አል- ጃውላኒ ናቸው።

የቤተሰቦቻቸው የዘር ሃረግ በእስራኤል ቁጥጥር ከሚገኘው የጎላን ተራሮች የሚመዘዝ ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ሰፋሪዎች ከ20 ሺህ ሶሪያውያን ጋር ተቀላቅለው ይኖሩበታል።

እስራኤል ያንን አካባቢ የመስጠት ፍላጎት የላትም። ይልቁንም በዚያ የሰፈሩ ዜጎቿን መጠበቅ ትፈልጋለች።

በአውሮፓውያኑ 2011 የሦሪያ አመጽ ሲፋፋም ምንም እንኳን በሻር አል አሳድ ከጠላቶቿ ሄዝቦላህ እና ኢራን ጋር ወዳጅ ቢሆኑም ከእርሳቸው በኋላ ከሚመጣው ስርዓት ይልቅ አሳድ ይሻሉኛል የሚል ስሌት ነበራት።

አሁን ደግሞ በሶሪያ ምን ሊመጣ ይችላል የሚለውን ታሰላለች።
የሚሆነውን በግልጽ ማወቅ አይቻልም፤ እንደሌላው ተመልካች ሁሉ ስሌቷን ልትሰራ የምትችለው በግምት ብቻ ነው።

የሶሪያው አመጽ የተጀመረው በእርግጥ የበሽር አላሳድ መንግስት እንዲፈርስ ለመጠየቅ ባለመ መልኩ አልነበረም።

እንደ ሊቢያዋ ቤንጋዚ፤ የሶሪያዋ ደቡባዊ ከተማ ዳራ ተቃውሞ ሲጀምር ከባዝ ፓርቲ ጋር እኩል ዕድሜ የያዘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ፤ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ለመጠየቅ ነበር።

በወቅቱ ሰሜን አፍሪካን እያመሰ የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ መሪዎችን እያፈናቀለ ነበርና በሽር አላሳድም ስጋት ገብአቶቸው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርጉ ወዲያውኑ አስታወቁ።

እንደበሽር እንደመንግስታቸው እምነትና ተስፋ ከቃል ያልዘለው፤ ወደ ተግባር ያልተለወጠው ውሳኔአቸው፤ ለተቃውሞ የወጣውን ህዝብ ወደ ቤቱ ይመለስ ነበር። ግን አልሆነም።

የአሁኑ መሪ አባት ሃፊዝ አላሳድ በ1982 እ.ኤ.አ ሃማ በተሰኘች ከተማ የሱኒ ሙስሊሞች ያነሱትን ተቃውሞ በሃይል ከደፈጠጡና 20 ሺህ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ አንድ ቀን ሊፈነዳ የሚችል የሱኒዎች አመጽ ይጠበቅ ነበር።

ይሄዉ ቀኑ ደርሶ አላሳድን ግዞተኛ አደርጎ እስራኤልና መንግስት አልበዋን ሶሪያን ዳግም ለዉጥረት ዳርጓል፡፡

በርግጥ አማጽያኑ ከእስራኤልም ሆነ ከሌሎች የቀጠናዉ ገራት ጋር ሰላም እንደሚፈልጉ አሳዉቀዋል፡፡

የእስራኤሉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳርም ሶሪያ ምድር ጦር ያስገባነዉ በጊዚያዊነት ነዉ ብለዋል፡፡

ግን ከቂጣዉ ጦርነት በኋላ በጎላን ተራራ ደም ሰለ አለመፍሰሱ ምንም ዋስትና የለም፡፡

አባቱ መረቀ

ታኅሣሥ 1ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጵያ ከ20 በመቶ በላይ የሚሆነዉ ህዝብ ከተለያዩ አካል ጉዳቶች ጋር አብሮ እንደሚኖር ተገለጸ፡፡

የዓለም የአካል ጉዳተኞች ቀን ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጰያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ ተከብሯል፡፡

ከኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር ዉስጥ ከ20 በመቶ በላይ የሚሆነዉ ህዝብ ከተለያዩ አካል ጉዳቶች ጋር እንደሚኖርም ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዝደንት ወይንሸት ግርማ(ዶ/ር)፤በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው አንስተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ እነዚህን ችግሮች ለመቀነስ የመንግስትም፣ የግለሰብም ሀላፊነት ነዉ ብለዋል፡፡

በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ ከግንዛቤ ማስጨበጥ ጀምሮ ሌሎች የተሻሻሉ አሰራሮች መኖራቸዉ የተገለጸ ሲሆን፤ አሁንም የሚቀሩ እና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ ተብሏል፡፡

አካል ጉዳተኞች በሁሉም የስራ መስክ መካተት እንዳለባቸዉም ተነስቷል፡፡

በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ የሚሰሩ አካላት እርስ በእርሳቸው መስራት ቢችሉ ችግሮችን ለማወቅና ለመፍታት አንድ ዕርምጃ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ታኅሣሥ 1ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የታኅሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የበሻር አል አሳድን አስተዳደር የገረሰሱት የሶሪያ አማጺያን የቀድሞውን ፕሬዝዳንት አባት ሐፊዝ አል አሳድን የቀብር ቦታን በእሳት አወደሙ።

አማጺያኑ የመንግሥት ወታደሮችን በማሸነፍ ዋና ከተማዋን ሲቆጣጠሩ ከአገር የኮበለሉት የፕሬዝዳንት በሻር አል አሳድ አባት ሶሪያን ለ29 ዓመታት ገዝተዋል።

በአውሮፓውያኑ 2000 ሐፊዝ አል አሳድ ሲያርፉ ልጃቸው በሻር መንበሩን ተረክበው ለ24 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ሶሪያን በፈላጭ ቆራጭነት ሲመሩ ቆይተው ነው በአማጺያኑ ከሥልጣን የተባረሩት።

አማጺያኑ ያወደሙት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ሐፊዝ አል አሳድን የመቃብር ቦታ ብቻ ሳይሆን በመላዋ አገሪቱ ያሉ የሐፊዝ እና የልጃቸውን በሻር ሐውልቶች አፍርሰዋል እንዲሁም ፖስተሮችን አውርደዋል።

ከሃምሳ ዓመታት ሶሪያን አንቀጥቅጠው የገዙት አባት እና ልጅ የአሳድ ቤተሰብ በበርካታ ሶሪያውያን ላይ ከፍተኛ ግፍ እና ጭፍጨፋ መፈጸማቸው ይነገራል።

ከዚህም የተነሳ አማጺያኑ ፕሬዝዳንት አሳድ በሽሽት ቢያመልጧቸውም የአባታቸውን የመቃብር ስፍራ በእሳት አቃጥለውታል።

በሰሜናዊ ምሥራቅ ሶሪያ ውስጥ በምትገኘው ቃርዳህ የሐፊስ አል አሳድ አስከሬን ያረፈበት ሳጥን በእሳት ሲነድ የሚያሳዩ በርካታ ቪዲዮዎች ተጋረተዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ ረጅም ዘመናት በሥልጣን ላይ ከቆዩ አገዛዞች መካከል የሚጠቀሱት የአሳድ ቤተሰቦች ምንም እንኳን ንጉሣውያን ባይሆኑም አባት እና ልጅ ሥልጣን ተቀባብለው ከ50 ዓመታት በላይ አገሪቱን ገዝተዋል።

ሐፊዝ አል አሳድ ለሁለት ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን፣

ከአውሮፓውያኑ 1971 ጀምሮ እስከ እስከ 2000 ድረስ በሥልጣን ላይ ቆይተው ሲያርፉ ሁለተኛ ልጃቸው በሻር ሥልጣኑን ተረክቧል።

የሐፊስን የመሪነት መንበር የታላቅ ልጃቸው ባሴል ይይዛል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም፣ በመኪና አደጋ ሕይወቱ ሲልፍ ሁለተኛ ልጅ የሆኑት በሻር ወደ መሪነት መጥተዋል።

በሻር መሪ ሲሆኑ ጨቋኙን የአባታቸውን ሥርዓት ያሻሽሉታል ተብሎ የተጠበቀ ሲሆን፣ እሳቸውም በሶሪያ ፖለቲካዊ ለውጥ ለማምጣት ቃል ገብተው ነበር።

ነገር ግን በአባታቸው የአስተዳደር መንገድ በመቀጠል በአምባገነን መሪነት ለ24 ዓመታት በሥልጣን ላይ ቆይተዋል።

ከ13 ዓመታት በፊት የአረቡን ዓለም ያንቀጠቀጠው የፀደይ አብዮት ሲቀጣጠል በሶሪያም የበሻር አል አሳድን መንግሥት ለመጣል ከፍተኛ ተቃውሞዎች የተካሄዱ ሲሆን፣ ወታደሮቻቸውን እና ታንኮቻቸውን በከተሞች አሰማርተው በወሰዱት ጭካኔ የተሞላባቸው እርምጃ ሕዝባዊውን አመጽ አዳፍነውታል።

ነገር ግን ሕዝባዊው ተቃውሞ ወደ የትጥቅ አመጽ ተሸጋግሮ ለ13 ዓመታት ሲካሄድ ቆይቶ አሳድ በሩሲያ እና በ ሄዝቦላህ ድጋፍ ታጣቂዎቹን ለመቆጣጠር ችላ ነበር።

ነገር ግን ከሳምንታት በወዲህ የአማጺያኑ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ሰፊ የአገሪቱን ቦታዎች እና ትላልቅ ከተሞችን በፍጥነት በመቆጣጠር ዋና ከተማዋ ደማስቆን ተቆጣጥረው አሳድን ከሥልጣን አባረዋል።

ታህሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውች

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በስድስተኛ ጨዋታ አርሰናል ፣ ባርሴሎና እና ጁቬንቱስ ድል ማድረግ ችለዋል።

አርሰናል ከሞናኮ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በቡካዩ ሳካ ሁለት እና ካይ ሀቨርትዝ ግቦች 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ጁቬንቱስ በበኩሉ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ በቭላሆቪች እና ማኬኔ ግቦች 2ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ ካለፉት አስር ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ነው።

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 መርታት ችሏል።

የባርሴሎናን ግብ  ፊራን ቶሬስ ሁለት እና ራፊንሀ ሲያስቆጥሩ ሴርሁ ጁራሲ ለዶርትመንድ ሁለቱንም አስቆጥሯል።

በሌሎች  የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች

ኤሲ ሚላን 2-1 ክሬቬና ዝቬዝዳ

ቤኔፊካ 0-0 ቦሎኛ

ፌይኖርድ 4-2 ስፓርታ ፓግራ

ስቱትጋርት 5-1 ያንግ ቦይስ

ጋዲሳ መገርሳ

ታኀሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዩክሬን ወደ ሩሲያ ሚሳኤል መተኮሷ ተሰማ

የዩክሬን ጦር ወደ ደቡባዊ ሩሲያ ሚሳኤል ማስወንፉን ሞስኮ አስታውቃለች ።

ሚሳኤሎቹ የተወነጨፉት በሮስቶቭ ግዛት ወደምትገኘው ታጋኖርግ ከተማ መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።


ከተማዋ በደቡብ ሩሲያ በአዞቭ ባህር ዳርቻ ላይ የምትገኝ ነች።

በሚሳኤል ጥቃቱ የተጎዳ ሰው ባይኖርም በኢንዱስትሪ ተቋማት ላይ መጠነኛ ጉዳት አድርሶል ነው የተባለው ።

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ዩክሬን በተደጋጋሚ የሚሳኤል ጥቃት እየፈፀመች መሆኑን አርቲ ኒውስ አስታውሷል።

በተለይም የምዕራባውያንን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎች መጠቀም መጀመሯ ሞስኮን ክፉኛ አስቆጥቷል።

አባቱ መረቀ

ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሚኒስክ እንደ ሃቫና

አሌግዛንደር ሉኬሼንኮም እንደ ካስትሮ የሆኑበት ዘመን እየተፈጠረ ነዉ፡፡

የኩባዉን የሚሳኤል ቀዉስ የወለደዉ የቀዝቃዛዉ ጦርነት ነዉ

https://ethiofm107.com/2024/12/11/ሚኒስክ-እንደ-ሃቫና/

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

እስራኤል በ48 ሰዓታት ውስጥ 4 መቶ 80 ጥቃቶችን በሶሪያ ላይ መፈፀሟ ተነገረ

የእስራኤል ጦር ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 4 መቶ 80 ጥቃቶችን መፈፀሙ ተነግሯል ።
ጥቃቶችን የፈፀመችው በአየር ከባህርና ከየብስ ነው ተብሏል ።

እስራኤል ሶሪያን እየደበደበች ያለችው የኬሚካል ጦር ሠሳሪያዎች በአማፅያን እጅ እንዳይገቡ ነው።

ይህንን ተከትሎ በመላው ሶሪያ የአየር ጥቃቶችን አጠናክራ ቀጥላለች።


ከዚህ ቀተጨማሪም እስራኤል ጦሯን ወደ ደቡባዊው ሶሪያ ማስገባቷ ይታወቃል።

አባቱ መረቀ

ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሶሪያ ጊዚያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር መርጣለች

በሽር አላሳድን ከስልጣን ያስወገደችዉ አገረ ሶሪያ ሞሃመድ አልበሽርን ጊዚያዊ  ጠቅላይ ሚኒስትር  አድርጋ ሾማለች፡፡

አልበሽር  የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

በበሽር አላሳድ የስልጣን ዘመን  ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ ያገለገሉት ሙሃመድ አል ጃላሊ  የሽግግር መንግስቱን  እንደሚደግፉ ቃል ገብተዋል፡፡

ጊዚያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሖነዉ የተመረጡት  ሞሃመድ አልበሽርም  አገሪቱን ለማረጋጋት በሚደረገዉ ጥረት ሁሉም አጋርነቱን እንዲያሳይ ጠይቀዋል፡፡

አባቱ መረቀ

ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

እንጀራ በአፍሪካ ደረጃ ስታንዳርድ ሊወጣለት እንደሆነ ተሰማ።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት እንጀራን በአፍሪካ ደረጃ ስታንዳርድ ለማውጣት ከአፍሪካ የደረጃዎች ቡድን ጋር በመሆን ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ጣቢያችን ሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ደ/ር መሰረት በቀለ እንደተናገሩት እንጀራን ደረጃውን በጠበቀ እና የሁሉንም የአፍሪካ እና የአለም ሃገራት ስታንዳርድ ታሳቢ ባደረጉ መልኩ ደረጃ ለማውጣት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የውጭ የምግብ አቀነባባሪ ኩባንያ ፍላጎት በማሳየቱ የሽሮ ወጥ ደረጃ መዘጋጀቱ መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡

ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን መሠረት በማድረግ የምግብ ይዘታቸው ላይ ጥናት ተደርጎባቸው ደረጃቸው ወጥቷል የተባሉ ምርቶች ሽሮ፣ በርበሬ፣ በሶ እና ጠጅን ያካትታል ማለቱ ይታወሳል።

ታዲያ አሁን ደግሞ አንጀራን ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ በአፍሪካ ደረጃው ለማውጣት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ በዋናነት ትኩረት አድርጎ ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ የኢትዮጵያ ደረጃዎችን ማዘጋጀት ፣ በተዘጋጁ ደረጃዎች ላይ የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ እና ስልጠና መስጠት እንዲሁም ጥናት እና ምርምር ስራዎችን መስራት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ለአለም አሰፋ

ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጲያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል በቀን በአማካይ ከ20-30 የሚሆኑ ታማሚዎች ይሄዳሉ ተባለ።

በማዕከሉ በአመት እስከ 1 ሺ 3 መቶ የልብ ህሙማን ሊመጡ እንደሚችሉም የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል አስታውቋል ።

የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር እንዲሁም የህፃናት እና የታዳጊ ልጆች ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ኤሌዘር ሀይሌ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ተቋሙ አሁን እየሰራ ያለው እስከ 600 የሚሆኑትን ብቻ ነው።

ከሚመጣው የታማሚ ቁጥር አንፃርም እየተሰራ ያለው በቂ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ህክምናውን ለማድረግ የሚረዱ የግብአት እጥረቶች በመኖራቸው እንደሆነ ነግረውናል።

እንዲሁም በዘርፉ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ውስን መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
ይህንን ችግር ለመቅረፍም ባለሙያዎችን የማስተማር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

አንገብጋቢው ችግር ግን የግብአት እጥረት ስለሆነ የመስራት አቅማችንን ውስን ያደርገዋል ብለውናል።

በመጨረሻም ሁሉም ማህበረሰብ በማዕከሉ የሚሰጠውን ነፃ አገልግሎት እንዲደግፉ እና 6710 ላይ ok ብሎ በመላክ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የሚል ጥሪያቸውንም አቅርበዋል ።

ሐመረ ፍሬው

ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የቤት ሽልማት ይዞ የመጣው የገና ባዛር ከታህሳስ 4 ጀምሮ ይከፈታል ተባለ።

ለ 24 ቀናት የሚቆየው አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንደሚከፈት ሰምተናል።

በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል እና በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው ይህ ባዛር ከ5 መቶ በላይ ነጋዴዎች ምርታቸውን የሚያቀርቡበት ነው ተብሏል።

በዚህ ባዛር ላይ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሸማቾች እና ጎብኚዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።

የተጋነነውን የዋጋ ንረትን ለማስቀረት ሸማቹ ምርቱን ቀጥታ ከአምራች እና አስመጪዎች ላይ የሚገበያይ ይሆናል ተብሏል።

ሸማቹ ለበዓል ብቻ ሳይሆን በየዕለቱ የሚጠቀማቸውን እንደ ስኳር፣ ሩዝ፣ ዱቄት እና ዘይት ያሉ የምግብ ግብዓቶችን በፋብሪካ ዋጋ ትራንስፖርት ጨምሮ መግዛት ይችላል ነው የተባለው።

የባዛሩ መግቢያ ከ1መቶ ብር እስከ 2መቶ ብር ድረስ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የመጀመሪያዎቹን ቀናት በመቶ ብር የበዓሉ ወቅት ሲቃረብ ያሉትን ቀናት ደግሞ በ2 መቶ ብር በመግባት መገበያየት ይችላሉ ተብሏል።

በተጨማሪም የባዛሩ መጠናቀቂያ ዕለት በሚወጣ ዕጣ ሸማቾች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጋር በዕጣ አወጣጡ ዙሪያ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ይህን ኤግዚቢሽን እና ባዛር ሮበስት ቢዝነስ ግሩፕ እና ሠላሳ መልቲሚዲያ በጋራ አዘጋጅተውታል።

እስከዳር ግርማ

ታኅሣሥ 1 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሙዓለ ነዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ በመሆን ፍቃድ ያገኘው የግል ድርጅት የራሱን አስተዋጾ ለማበርከት እንደተዘጋጀ ገለጸ።

በቅርቡ ከካፒታል ገብያ ባለስልጣን የማማከር ፍቃድ የተሰጠው አይ ካፒታል ኢንስቲትዩት በካፒታል ገያበው የሚመጡ ኢንቨስተሮችን በማማከር እና ወደ ገበያው እንዲመጡ ለማድረግ የበኩልን ድርሻ እንደሚወጣ ለጣቢያችን ገልጧል፡፡

አይ ካፒታል ኢንስቲትዩት በካፒታል ገበያው የሙዓለ ነዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ በመሆኑ ምን ያስገኝለታል ሲል ጣቢያችን ድርጅቱን ጠይቋል።

ኢንስቲትዩቲ በምላሹ ከፊቱ ሰፊ ስራ እንደሚጠብቀውና ለኢንቨስተሩም የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱንም ዶ/ር ገመቹ ግልጸዋል።

የአይ ካፒታል ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ገመቹ ዋቅቶላ በሀገር ቤት የመጀመርያው ሀገር በቀል አማካሪ ለመሆን አዋጁ የሚያስቀምጠኣቸው መስፈርቶች ከባድ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በኢትዮዽያ በተለያየ የቢዝነስና የካፒታል ገበያ ለመሳተፍ ለግለሰብም ሆነ ለፋይናንስ ተቋማተት እንዲሁም፣ ለድርጅቶች የኢንቨስትመንት ምክር ለመስጠት ፈቃድ ያገኙት ድርጅቶች ሶስት ናቸው።

አይ ካፒታል ኢንስቲትዩት በየዓመቱ በፋይናንስና አካባቢው ሰፊ የፋይናንስ ጉባኤ በማዘጋጀት የሚታወቅ ተቋም ነው፡፡

ለአለም አሰፋ

ታኅሣሥ 1ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የታኅሣሥ 1 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሀገሪቱ ያሉትን አንበሶች ከመጥፋት መታደግ ይገባል ተባለ።

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የአንበሳ እና የስጋ በል እንስሳት ተመራማሪ የሆኑት አቶ ካህሳይ ገብረ-ትንሳይ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያሉት አንበሶች ቁጥር ከ9መቶ እስከ 1 ሺ ካለው ቁጥር አይበልጡም ሲሉ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።

በሃገሪቱ አሁን ላይ አንበሶች ያሉበት ሁኔታ ለማወቅ ጥናት ማድረጋቸውን የገለፁልን ተመራማሪው በአዋሽ እና በመካከለኛው አዋሽ በተደረገው ጥናት መሰረት ያለው ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም አሁንም ግን ሁሉም ርብርብ ካላደረገ አንበሶቹን ልናጣ እንችላለን ብለዋል፡፡

ተመራማሪው እንደሚሉትም ህገወጥ የነዋሪዎች ሰፈራ፣ የደን ጭፍጨፋ መኖር፣ የእርሻ ስራ እና ግጦሽ መበራከት አንበሶቹ የሚፈልጉትን ምግብ እንዳያገኙና በምግብ ሰንሰለት ውስጥ ችግር እንዲፈጠር ብሎም ለህገወጥ አደን በስፋት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የባህል መድኃኒት ቀማሚዎች ፊታቸውን ወደ አንበሳ አጥንት ማዞራቸው እንስሳቶቹን ለህገወጥ አደን ይበልጥ ተጋላጭ እንዲሆኑና ቁጥራቸው እንዲመናመን ማድረጉን በባለስልጣኑ ተመራማሪው ይናገራሉ።

ቀጣይነት ያለው ጥናት በመላ ሃገሪቱ ለማድረግ ማቀዳቸውን የገለጹልን ተመራማሪው የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ርብርብንም ጠይቀዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር በባህልም ይሁን በሌላ ሰፊ ቁርኝት እንዳለው የሚነገረው አንበሳ ከመንገስትም ይሁን ከማህበረሰቡ ከፍተኛ ትኩረት ካልተደረገለት የአንበሳ ስሙ ብቻ ሊቀር እንደሚችል እና አንበሳ የሚባል ነገር ታሪክ ሊሆን ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ለጣቢችን አሳስበዋል፡፡

ለአለም አሰፋ

ታኅሣሥ 1ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሶሪያ ውስጥ ግዛት የማስፋፋት እቅድ የለንም ሲሉ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ተናገሩ

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን፤ ቱርክ በሶሪያ ውስጥ ተደራሽነትን ለማስፋት እንደማትፈልግ ተናግረዋል ።

ቱርክ መዳረሻዋን ወደ ሶሪያ የማስፋት ፍላጎት የላትም፣ ከሰሞኑ የተደረገውም የድንበር ተሻጋሪ ተግባሯ ሀገሪቱን ከ"ሽብር ጥቃት" ለመከላከል ብቻ ያተኮረ ነበር ሲሉ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ገልፀዋል።

“ቱርክ የሌላ አገር ግዛትን ለመቀራመት አስባ አታውቅም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ፤የድንበር ተሻጋሪ ዘመቻችን ብቸኛ አላማ አገራችንን ከአሸባሪዎች ጥቃት ማዳን ነው” ሲልው ተናግረዋል።

ልኡል ወልዴ

ታኅሣሥ 1ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel