ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

ከሀገራዊ ምክክሩ በኋላ በኦሮሚያ ክልል ያሉ ግጭቶች ይቆማሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ የአገራዊ ምከክረር ተሳታፊዎች ተናገሩ

ከኦሮሚያ ክልል 3 መቶ 56 ወረዳዎች የተወጣጡ ከ7 ሺህ 20 በላይ ተሳታፊዎች ከሀገራዊ ምክክር በኋላ በክልሉ ያሉ ያማያባሩ ግጭቶች፣አለመረጋጋቶች፣ስጋት እንዲሁም የፖለቲካ ስንጥቅ እንደ ሚሞላ ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የተሳታፊ ልየታ በገልማ አባ ገዳ መካሄዱ እንደቀጠለ ነዉ፡፡

ለሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ክልሉን እና ህዝቡን ይወክላሉ ባልናቸው ዋና ዋና ነጥቦች ላይ በቡድን ሆነው እየመከሩም ይገኛሉ።

ጣቢያችን ያነጋገራቸው እነዚህ ተሳታፊዎች ወደዚህ ምክክር የመጣነው የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት ሲያለቅስባቸው፣ሲሰደድባቸው፣ሲጨቆንበት እና ሲያከፋፍለው የኖሩ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ነውም ብለዋል።

ተሳታፊዎቹ የወከሏቸው የህብረተሰብ ክፍሎች፤ የመንግስት ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ወጣቶች፣ ሴቶችናተፈናቃዮች ይገኙበታል፡፡

ልዑል ወልዴ

ታኀሣሥ 9  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአፋር ክልል 22 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም ተባለ።

በክልሉ ተከስቶ በነበረው ጎርፍ እና በነበረው ግጭት ወደቀያቸው ያልተመለሱ ተፈናቃዮች በመኖራቸው 22 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በዘንድሮ 2017 በጀት አመት እቅድ ተይዞ ከነበረው 3 መቶ 16 ሺህ 7 መቶ ተማሪ ውስጥ 86.4 ፐርሰንቱ በአሁን ሰዓት በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ይገኛሉ፡፡

አዋሽ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ እና የጎርፍ አደጋ ብዙ ትምህርት ቤቶች ለጉዳት መዳረጋቸውንም አስታዉሰዋል።

በጦርነት እና በተፈጥሮ አደጋዎች የወደሙ ትምህርት ቤቶች ጥገና ተደርጎላቸው ወደ ስራ አለመመለሳቸው በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ትልቅ እንቅፋት መሆኑንም አንስተዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎችን ለመመለስ ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ ሀላፊው ተናግርዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ታኀሣሥ 9  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የታኅሣሥ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሩሲያ ለጄነራሉ ግድያ የዩክሬን አገዛዝ የእጁን ያገኛል አለች

የቀድሞዉ የሩሲያ ፕሬዝዳንትና የአገሪቱ የደህንነት ምክር ቤት ምክት ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬድቭ ለጄነራሉ ሞት የዩክሬን ባለስልጣናት ዋጋቸዉን ያገኛሉ ሲሉ ዝተዋል፡፡

ሩሲያ በቀሏን በቅርብ እንደምትወጣም ዲሚትሪ ሜድቬድቭ መናገራቸዉን ታስ ዘግቧል፡፡

የበቀል ጥቃቱ ከፍተኛ የዩክሬን ባለስልጣናትንና ወታደራዊ ኃላፊዎችን ጭምር ኢላማ እንደሚያደርግም ዝተዋል፡፡

የሩሲያ የኒዩክሌርና የኬሚካል መከላከያ ሃይል መሪው ሌተናል ጀነራል ኢጎር ኪሪሎቭ የተገደሉት በዩክሬን ልዩ ዘመቻ ነው ተብሏል።

የዩክሬን የደህንነት ተቋም ኤስቢዩ ጀነራሉ የተገደሉበትን ዘመቻ መምራቱንም ሬውተርስ ዘግቧል።

ምንጭቹ ኪሪሎቭ በጦር ወንጀል የሚፈለጉና ትክክለኛው ኢላማ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

አባቱ መረቀ

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

#የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ በ11ኛ ሳምንት እና በ1ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች ላይ የቀረቡትን ሪፖርቶች ተመልክቶ የቅጣት ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

የሲዳማ ቡናው ብርሀኑ በቀለ ቡድኑ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው ጨዋታ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታቱ ምክንያት በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱ ይታወቃል።

ተጫዋቹ የአራት ጨዋታዎች እና የሶስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥቶለበታል።

የመቀሌ 70 እንደርታው አጥቂ ያሬድ ብርሀኑ በበኩሉ ቡድኑ በስሁል ሽረ በተረታበት መርሐግብር ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የጨዋታውን ዳኛ አፀያፊ ስድብ ሰለመሳደቡ ሪፖርት ቀርቦበታል።

ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋትም ሶስት ጨዋታዎች እንዲታገድ እና ሶስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

በተጨማሪም መቀሌ 70 እንደርታ ስሁል ሽረን በገጠመበት ጨዋታ ላይ የቡድኑ አምስት ተጫዋቾች የቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ክለቡ አምስት ሺህ ብር ተቀጥቷል።

በተያያዘም የኢትዮጵያ ቡናው ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ እና የመቀሌ 70 እንደርታው ዋና አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ኮሚቴው ሊያነጋግራቸው ጥሪ አድርጎላቸዋል።


ጋዲሳ መገርሳ

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሶማሌ ክልል 450ሺህ ዕድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ክትባት አለመዉሰዳቸዉን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።

ዕድሜያቸዉ ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ክትባት ለማድረስ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነም ቢሮዉ አስታዉቋል።

በዚህም ሁለት መቶ ሺ ለሚሆኑ ህጻናት ክትባት መሰጠቱን እና የቀሩትም በቀጣይ ክትባቱን እንደሚያገኙ ገልጿል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ማህመድ መሃሙድ፤ 70 በመቶ የሚሆነዉ የክልሉ ነዋሪ አርብቶ አደር በመሆኑ እና ቋሚ የመኖሪያ ስፍራ ስለሌለዉ የጤና አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ተግዳሮት ሆኖብናል ብለዋል፡፡

ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ክትባት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ እቅዶችን መያዙንም ምክትል ሀላፊዉ ተናግረዋል።

አለም አቀፉ የረድኤት ድርጅት ሴቭ ዘ ችልድረን ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገዉ መረጃ ኦሮሚያ፣አማራና ሶማሌ ክልሎች ለየት ባለ መልኩ ክትባት ያልወሰዱ ህፃናት ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን አስታዉቆ ነበር፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኢሰመኮ ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ መያዝን በተመለከተ ካወጣዉ መግለጫ በኋላ ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር በደብዳቤ መነጋገሩን ገለጸ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መከላከያ ሚኒስቴርም በሁሉም ክልሎች የሚከናወኑ የሰራዊት አባላት ምልመላ ሥራዎች በሕግ በተቀመጡት መስፈርቶች መሠረት ብቻ የተከናወኑ ስለመሆናቸው በማረጋገጥ የሚረከብ መሆኑን ለኢሰመኮ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በደረሰው ደብዳቤ ስለመግለጹም አስታዉቋል፡፡

መከላከያ ሚኒስቴር በዚህ ዓመት እየተደረገ ያለውን ምልመላ አፈጻጸም ለመፈተሽ ከከፍተኛ ሙያተኛ መኮንኖች የተውጣጣ ከ7 እስከ 12 አባላት ያሉት ኮሚቴ አዋቅሮ በማጣራት መስፈርቶቹን የሚያሟሉትን ብቻ ለይቶ ወደ ማሰልጠኛ ተቋማት ማስገባቱን በደብዳቤዉ ማስታወቁን ኢሰመኮ ገልጿል፡፡

ይህ ከመሆኑ አስቀድሞ በክልሎች በተከናወነው የምልመላ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች ካሉ ግን ከክልሎች ጋር በመነጋገር ለማጣራት የሚቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ መግለጹንም ኢሰመኮ ለጣቢያችን በላከዉ ሪፖርት ለመመልከት ችለናል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ መያዛቸውን በተመለከተ ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

ከመከላከያ ሰራዊት መስፈርቶች ውጪ፣ “ለምልመላ” በሚል ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን በግዳጅ በመያዝ የተሳተፉ መኖራቸዉንም ደርሼበታለሁ ብሎ ነበር፡፡

በምርመራው ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ እና ከውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና አባላት ጋር ኅዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ምክክር ማካሄዱንም ኢሰመኮ ገልጿል፡፡

ኢሰመኮ ክልሉ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጥ እና በቀጣይ ተመሳሳይ ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ለማድረግ የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ የሚያደርገውን ጥረት እና ውትወታ እንደሚቀጥልም አስታዉቋል፡፡


ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የታኅሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በዩክሬን ጦርነት መግደላቸውን አሜሪካ አስታወቀች

የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያ ኩርስክ ድንበር አካባቢ ከዩክሬን ጦር ጋር በነበረ ፍልሚያ መገደላቸውን አሜሪካ ተናግራለች፡፡

በጥቅምት ወር ሰሜን ኮሪያ የሩሲያን ጦር ለማጠናከር ወደ 10ሺህ የሚጠጉ ወታደሮችን ልካለች።

ከነዚህም ውስጥ 2 ሺህ 600 የሚሆኑት ወታደሮች ዩክሬን በነሐሴ ወር ወደ ወረረቻቸው የሩሲያ ምዕራባዊ ከርስክ ግዛት እንደሚሰማሩ ሲገለጽ ነበር፡፡

የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ኤጀንሲ GUR በሳምንቱ መጨረሻ በተደረገው ጦርነት በትንሹ 30 የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ሲል ባሰራጨው መረጃ አሳውቋል።

ቢቢሲ ግን ይህንን በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም ብሏል፡፡

ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ በቅርብ ጊዜያት ጀምሩ ትብብራቸውን እያሳደጉ መጥተዋል።

የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች አንዳቸውም ከዚህ በፊት የውጊያ ልምድ የላቸውም ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡ይሆን እንጂ ወደ ሩሲያ ከተላኩ በኋላ በስልጠና ከዚያም በድጋፍ ሚናዎች ላይ የመጀመሪያዎቹን ሳምንታት እንዳሳለፉ ይታመናል።

ሩሲያ ግን የስሜን ኮሪያ ወታደሮች በአገሯ መገኘታቸውን ባታምንም አላስተባበለችም።


ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

# እንድታውቁት

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይኖሩ የነበሩ የህግ ታራሚዎች ገላን አካባቢ ወደ ተገነባው አዲስ ማረሚያ ቤት ሊዘዋወሩ ነው፡፡

በዚህ ምክንያት ከዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ደረስ የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ አገልግሎት እንደማይኑር የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አሳውቋል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሁሉም እንዲያወቀው ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ በአዲስ አበባ የህግ ታራሚዎች ቀደም ብለው ይኖሩበት ከነበረው አሮጌው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አዲስ ወደ ተገነባው ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም የማዘዋወር ስራ ይሰራል ብሏል፡፡

በመሆኑም በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ እንደሚቁይ አሳውቋል፡፡

ከዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2017 .ም ጀምሮ የሚቋረጠው አገልግሎት ከታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ መደበኛ ስራው የሚመለስ በመሆኑ አገልግሎቱ በአዲሱ የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ገላን አካባቢ በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው ማዕከል ማግኘት የሚቻል መሆኑን ገልጻል፡፡

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የመሠረቱት "የአዳም ፋውንዴሽን" የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ምሥረታውን ይፋ አድርጓል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመሩት "የአዳም ፋውንዴሽን"፤የመንግስት ባለስልጣናት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት በተገኙበት ይፋዊ የማብሰሪያ ሥነ ሥርዓቱን በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ልማትና እድገት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የገለፁት የፋውንዴሽኑ መስራች አቶ ደመቀ መኮንን፤ በተለይ ህፃናትና እናቶች ላይ በመስራት ብሎም መቀንጨርን በመዋጋት ደህንነቱ የተጠበቀ ትውልድ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

"በአፍሪካ መቀንጨርን መግታት" የሚል መሪ ሀሳብ ያለው ፋውንዴሽኑ፤ ከኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘው ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ እንደነበር ተገልጿል።

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በጆርጂያ 12 ሰዎች በካርቦን ሞኖክሳይድ ተመርዘዉ መሞታቸው ተገለጸ፡፡

በጆርጂያ በሚገኝ የበረዶ ሸርተቴ ሪዞርት 12 ሰዎች በካርቦንሞኖክሳይድ መርዝ ህይወታቸዉ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በቀድሞዋ የሶቪየት ህብረት አገር ጆርጂያ ዉስጥ በሚገኘዉ ትልቁ የበረዶ ሸርተቴ ሪዞርት በሆነው በጓዱሪ በሚገኝ አንድ ሬስቶራንት 12 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፎ መገኘቱ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

11 የውጭ ዜጎች እና አንድ የጆርጂያ ዜጋ በተኙበት በካርቦን ሞኖክሳይዱ መርዝ ታፍነዉ ህይወታቸዉ አልፎ ተገኝቷል፡፡

አስከሬኑ የተገኘው የህንድ ሬስቶራንት በሚገኝበት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ መሆኑንም የከተማዉ ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

ጓዱሪ በሁሉም ደረጃ ላሉ ጎብኚዎች የተለያዩ የክረምት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ለበረዶ መንሸራተት አድናቂዎች የቱሪስት መዳረሻ እንደሆነችም ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ ባልስልጣናቱ ምርመራ እንደተከፈተና ተጎጂዎች እስካሁን ማንነታቸዉ እንዳልታወቀ ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

እስራኤል በጎላን ኮረብቶች የሰፈራ ግንባታዎችን እንደምታስፋፋ አስታወቀች

የእስራኤል ካቢኔ ባሳለፈዉ ዉሳኔ በጎላን ኮረብቶች ተጨማሪ ግንባታዎች ይካሄዳሉ ብሏል፡፡

የእስራኤል ካቢኔ በትናትናዉ እለት በጎላን ኮረብቶች ዙሪያ ስብሰባ ተቀምጠዉ ነበር

በጎላን ኮረብቶች የሰፈራ ግንባታዎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ዉሳኔ ማሳሉን ሮይተርስና እየሩሳሌም ፖስት ዘግበዋል፡፡

ካቢኔዉ እቅዱን ለመደገፈም 11 ሚሊዮን ዶላር አፅድቋል፡፡

የእስራኤል ጦር አሁንም በሶሪያ ምድር እንደሚገኝ እየሩሳሌም ፖስት ዘግቧል፡፡

የእስራኤል አየር ሃይል በሶሪያዋ የወደብ ከተማ ታርጠስ የሚገኘዉን የጦር ሰፈር ማዉዳሙን የአረብ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነዉ

ኢራን በበኩሏ እስራኤልን ከሶሪያ ምድር ጠራርገን እናስወጣለን ብላለች፡፡

የአረቡ አለም አገራትም እስራኤል ከድርጊቷ እንድትቆጠብ እያሳሰቡ ይገኛሉ፡፡
የሶሪያ አማጽያን ግን ከእስራኤል ጋር መዋጋት አንፈልግም ብለዋል

የእስራኤል ጦር የሶሪያን የጦር ሰፈር መደብደቡን እንደቀጠለ ነዉ፡፡

የበሽር አላሳድ መንግስት መዉደቁን ተከትሎ የእስራኤል ጦር ወደ ሊባኖስ መግባቱ የሚታወስ ነዉ፡፡

አባቱ መረቀ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በየጊዜዉ የሚደረግ የስራ አመራሮች ለዉጥ  ለስራዬ እንቅፋት ሆኗል" ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ገለፀ።


በጋምቤላ ክልል የሚደረጉ ጊዜን የማይጠብቁ  የአመራር ለዉጦች እንዲሁም  ዝዉዉሮች ለተቋሙ የሚቀርቡ አቤቱታዎች መፍትሔ እንዳያገኙ እክል እንደሆነበት  ሰምተናል።


የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የጋምቤላ ቅርንጫፍ ለኢትዩ ኤፍአኤም እንደገለፀዉ በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ስር ያሉ መዝገቦች እየታዩ ባለበት ሂደት በየተቋማቱ ያሉ የግለሰቦች  መለዋወጥ የዉሳኔ   መጓተት መፍጠሩን አሰታዉቋል።


በኢትዩጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ጋምቤላ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተወካይ አቶ ግርማ መኩሪያ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ "ጉዳዩን የሚይዘዉ አሰፈፃሚ አካል በተለዋወጠ ቁጥር የአቤቱታ መዝገቦች  እንደ አዲስ የሚታዩ እንጂ ካቆሙበት የሚቀጥሉ አይሆኖም ብለዋል።


እንደ አዲስ እየታዩ ባሉ መዝገቦችም አዲሱ አመራር  መረዳት እንዲኖረዉ  ለማስቻል ባለ ሂደት የአቤቱታዉ ዉሳኔ መዘግየት እንዲታይበት አድርጓል ተብሏል።


በዚህም የአስፈፃሚ አካላት ይህንን ግንዛቤ ወስዶ በሀላፊነት የመስራት ዉስንነት መመልከታቸዉን  የክልሉ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተወካይ አቶ ግርማ መኩሪያ ገልፀዋል።

በጋምቤላ ክልል ተቋሙ በዘንድሮዉ በጀት አመት አጋማሽ 75 አቤቱታዎችን ለመቀበል አቅዶ 36 አቤቱታዎች ብቻ መቅረባቸዉን ለማወቅ ተችሏል።

ከነዚህ አቤቱታዎች ዉስጥ ከመልካም አስተዳደር ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ የታዩ መዝገቦች በቁጥር ከፍ ያለ መሆኑን ሰምተናል።

በጋምቤላ ክልል የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም እየሰራቸዉ ባሉ ስራዎች የክልሉን ህዝብ ተደራሽ ሆኖ ሀላፊነቱን ለመወጣት ከክልሉ መስተዳድር ጋር እየተወያየ ይገኛልም ተብሏል።

ቁምነገር አየለ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአሰልጣኞች ሰንበት በእንግሊዝ!

ሳውዝሀምፕተን አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲንን ከሀላፊነት ማሰናበቱ ይፋ ተደርጓል።

ክለቡ ካደረጋቸው አስራ ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ሲሆን በአስራ ሶስቱ ተሸንፏል።

ሳውዝሀምፕተን አሁን ላይ በሊጉ በአምስት ነጥቦች የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ።

ስኮትላንዳዊው አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲን ከአሰልጣኝ ስቲቭ ኩፐር ፣ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ እና ጋሪ ኦኔል በመቀጠል አራተኛው ተሰናባች የፕርሚየር ሊግ አሰልጣኝ ሆነዋል ።

ሳውዝሃምፕተን ካደረጋቸው አስራ ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ሲሆን በአስራ ሶስቱ ተሸንፏል።

ሳውዝሀምፕተን አሁን ላይ በሊጉ በአምስት ነጥቦች የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ።

በተጨማሪም በሜዳው በአዲስ አዳጊው ኢፒስዊች ታወን እና ያለፉትን አምስት ጫወታዎች በፕሪምየርሊጉ ሽንፈት ያስተናገደው ወልቨርሃምፕተንም አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔልን ማሰናበታቸውን ይፋ አድርገዋል::

ጋዲሳ መገርሳ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከታህሳስ 30 ጀምሮ ንግድ ፍቃድ ያላደሱ ነጋዴዎችን እንደሚቀጣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ንግድ ቢሮዉ 1መቶ 70 ሺህ ነጋዴዎች ንግድ ፍቃድ አለማደሳቸዉንም ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የገበያ ጥናት መረጃና ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሰማ ጀማል ለጣቢያችን እንደተናገሩት፤ አሁን ላይ 1መቶ70 ሺ የሚሆኑ ነጋዴዎች ንግድ ፍቃዳቸዉን አላደሱም፡፡

በሩብ ዓመቱ ምርት በማከማቸት፣ ዋጋ ባለመለጠፍ፣ደረሰኝ ባለመያዝ እና ካወጡት ንግድ ፍቃድ ውጭ ሲሰሩ የተገኙ 14 ሺህ 1መቶ31 ህገወጥ ነጋዴዎች መገኘታዉንም ገልጸዋል።

ከነዚህም ዉስጥ 11 ሺ የሚሆኑት ፍቃድ እንዲያወጡ መደረጉን የገለጹት አቶ ሙሰማ፤ የታሸጉ መኖራቸዉንም ተናግረዋል።

ከሀምሌ 1 እስከ ህዳር 30 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ 5 ሺህ 9መቶ23 ሰዎች ንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸዉ ሲነግዱ መገኘታቸዉ ተገልጿል፡፡

ከነዚህም ዉስጥ ወደ ህግ ስርዓቱ 4ሺህ7መቶ50 የሚሆኑ ነጋዴዎች ንግድ ፍቃድ አዉጥተዉ ስራቸዉን እየሰሩ እንደሆነ አቶ ሙሰማ ገልጸዋል።

ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ የነበሩ ባለሙያዎችና የንግዱ ማህበረሰብ ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ ገልጸዉ፤ ከስራ የተባረሩ፣ደሞዝ የተቀጡ፣የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸዉ እና በክስ ላይ ያሉ እንዳሉም ተናግረዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ታኀሣሥ 9  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ስንቄ ባንክ እና ዴሎይት ግሎባል  "የስንቄ ኢንቨስትመንት ባንክን" ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ይህ ስምምነትም የስንቄ ኢንቨስትመንት ባንክን ለማቋቋም  እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚደግፍ  እንደሆነም ተገልጿል።

የዴሎይት ግሎባል  በአለም አቀፍ የሚታወቅ ትልቅ የፋይናንስ አማካሪ መሆኑም ተገልጿል።

የስንቄ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ  አቶ ነዋይ መገርሳ፤  ስንቄ ባንክ ለ23 አመታት የኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ሆኖ ያገለግል እንደነበር አስታውሰው  ከሁለት አመት በፊት ባንክ ሆኖ መቋቋሙን ገልፀዋል።

ባንኩ 35 አጀንዳዎችን በ3 አመት ቆይታው ይዞ መነሳቱን የሚያነሱት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አሁን ላይ ሰላሳ ሶስቱን  አሳክቶ ከቀሩት 2 ደግሞ አንዱ የዛሬ ስምምነት ነው ብለዋል።

በዚህ  ስምምነት ስንቄ ባንክ   ወደ  ኢንቨስትመንት ባንኩ ለመግባትም ብዙ ጥናቶችን አድርገው ለውሳኔ እንደቀረቡም ተገልጿል።

ለዓለም አሰፋ

ታኀሣሥ 8  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ በተለምዶ ሿሿ የተባለውን የኪስ ስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

በለሚኩራ ክ/ከተማም በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት 3 ተጠርጣሪዎችን በክ/ከተማው ወረዳ 5 በሻሌ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል።

ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1 አአ 21727 AA የሆነ ሚኒባስ ታክሲን በመጠቀም የግል ተበዳይ ወደ አያት አደባባይ ለመሳፈር ቆመው ታክሲ እየጠበቁ እያለ ወዴት ነህ ብለው በመጠየቅ ወደ ታክሲው በማስገባት ከሾፌር ጀርባ ያለው ወንበር ላይ አስቀምጠዋቸው የተወሰነ ርቀት እንደተጓዙ ትራፊክ አለ ከፊት ትወርዳለህ ብለው ሲያስገድዷቸው የግል ተበዳይም ዞረው የተሳፋሪ ወንበርን ሲመለከት ምንም ተሳፋሪ ባለመኖሩ ተጠራጥረው የሱሪ ኪሳቸውን ሲዳብሱ ሳምሰግ ሞባይል ስልካቸው መሰረቁን እንደተረዱ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አስረድተዋል፡፡

የግል ተበዳይ ባሰሙት ጩኽት ተጠርጣሪዎቹ የተሽከርካሪውን በር በመክፈት ጥለውት ለማምለጥ ቢሞክሩም በአካባቢው ተመድበው የወንጀል መከላከል ስራ እየሰሩ በነበሩ የፖሊስ አባላት ከነተሽከርካሪው መያዛቸውን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹን ፈጣን ችሎት በማቅረብ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ እንደሚገኝ ያስታወቀው ፖሊስ ህብረተሰቡም በተለይ ትራንስፖርት ሲጠቀም ወዴት ነህ በማለት እየጠየቁ መሄጃ አቅጣጫውን ጠይቀው የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች ሲያጋጥሙት ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ አስታወቆ ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚል ለሚኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ ፈፃሚዎችን በመምረጥና ተጨማሪ መረጃ በመስጠት ማመልከት እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለሩሲያ ጦር ኃይል ከፍተኛ ጀኔራል ግድያ ዩክሬን ኃላፊነት ወሰደች

ሌተናንት ጀኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ የኒውክሌር፣ ባዮሎጂካል እና ኬሚካል መከላከያ ኃይል ኃላፊ በሞስኮ በቦምብ ጥቃት ሕይዎታቸዉ አልፏል፡፡

ጀኔራሉ ከመኖሪያ ቤታቸው ሲወጡ ስኩተር በተባለ መሽከርከሪያ ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ መሞታቸውን የሩሲያ መርማሪ ኮሚቲ አስታውቋል።

ከሥፍራው የወጡ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት የሕንፃው መግቢያ በፍንዳታ ክፉኛ የተጎዳ ሲሆን በፍንጥርጣሪ ምክንያት ግድግዳዎች እና መስኮቶች ፈራርሰዋል።

ከጥቃቱ በኋላ የሩሲያ መንግስት ምዕራቢያዊያንን ተጠያቂ አድርጎ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ጥቃቱ በዩክሬን አማካኝነት እንደተፈፀመ የኬይቭ መንግስት መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ባለፈው ጥቅምት እንግሊዝ ጀኔራል ኪሪሎቭ በዩክሬን ለተፈፀመው የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጥቃት ተጠያቂ ናቸው በማለት ማዕቀብ ጥላባቸው ነበር።

አባቱ መረቀ

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሮናልዶ ቀጣዩ ፕሬዝዳንት?

ብራዚላዊው ሮናልዶ ለሃገሩ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንትነት ሊወዳደር መሆኑ ተሰማ፡፡ የብሄራዊ ቡድኑን ‹‹ክብር ማስመለስ›› እንደሚፈልግም ተናግሯል፡፡

የ48 ዓመቱ የቀድሞ ኮከብ ለብራዚል ብሄራዊ ቡድን 98 ጨዋታዎችን አከናውኗል፡፡ የወቅቱን የብራዚል እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ኤድናልዶ ሮድሪጌዝ ለመተካት በሚደረገው ምርጫ በዕጩነት እንደሚቀርብ አሳውቋል፡፡

የአምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ብራዚል ለመጨረሻ ጊዜው ውድድሩን ያሸነፈችው በ2002 ነው፡፡

ከዚያ በኋላ ከሩብ ፍጻሜ መሸጋገር እንኳን አልቻለችም፡፡

ሮናልዶ ከግሎቦ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ ‹‹ለበርካታ አስርት ዓመታት የብራዚል እግር ኳስ ብራዚላዊውያን የእለት ተዕለት መከራቸውን የሚረሱበት አማራጭ ነበር፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ለብሄራዊ ቡድኑ ግድ የሌላቸው ሰዎች በርክተዋል፡፡ የፌደሬሽኔ ፕሬዝዳንት እንድሆን ካነሳሱኝ በርካታ ነገሮች ቀዳሚው የብሄራዊ ቡድኑንን ክብር ማስመለስ ነው›› ብሏል፡፡

የሮድሪጌዝ የስልጣን ዘመን በመጋቢት 2026 ይጠናቀቃል፡፡ ስለሆነም ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው 12 ወራት ቀደም ብሎ መከናወን ይኖርበታል፡፡

አቤል ጀቤሳ

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የቼልሲው ኮኮብ ሙድሪክ በአበረታች ንጥረ ነገር ምከንያት ከእግርኳስ ታገደ !

ዩክሬናዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ማይካሎ ሙድሪክ ያልተፈቀደ አበረታች ንጥረ በውስጡ መገኘቱ ተገልጿል።

የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ባደረገው ምርመራ " positive " ሆኖ መገኘቱ የተገለጸው ተጨዋቹ በጊዜያዊነት ከእግርኳስ መታገዱን ክለቡ አሳውቋል።

ማይካሎ ሙድሪክ እያወቀ የተከለከለ ንጥረ ነገር አለመውሰዱን ማረጋገጡን ቼልሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቀዋል።

ተጨዋቹ ያለፉት አምስት የክለቡ ጨዋታዎች እንዳመለጡት የሚታወስ ሲሆን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በህመም እንደሆነ ገልፀው ነበር።

ቼልሲዎች በመግለጫቸው በተጫዋቾቻችን ላይ ሁልጊዜም በሚደረገው መደበኛ ምርመራ ማይካሎ ሙድሪክ ያልተለመደ ንጥረነገር መጠቀሙን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

ይሆን እንጂ ተጨዋቹ እንዳለው ኤፍኤው ከእኔ በወሰደው ናሙና የተከለከለ ንጥረ ነገር ተጠቅመሀል ሲል መልዕክት ደርሶኛል ነገርግን እኔ ምንም አይነት ተጨማሪ ነገር ተጠቅሜ አላውቅም።


እኔ ምንም አይነት የእግርኳስ ህግጋትን ስላልጣስኩ ይህ አስደንጋጭ ሆኖብኛል ፤ በቅርቡ ወደ ሜዳ እንደምመለስ ተስፋ አደርጋለሁ ብሏል።

ጋዲሳ መገርሳ

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

“የውጭ ባንኮች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መፍቀድ የግል ባንኮች ይጥፉ ብሎ የመወሰን ያክል አይደለም ወይ” የምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

#የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ እያደረገ ያለው ውይይት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

“የንግድ ባንክን አዳ ወደ ህዘቡ ሲዞር ይህንን ታስቦ ነው” ያሉት የመንክር ቤቱ አባል ለግል ባንኮች ግን አቅማቸውን እንዲያደረጁ እንኳን ድጋፍ አልተደረገላቸውም ተብሏል፡፡

ዶ /ር ደሳለኝ የውጭ ባንኮችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ”የግሉ ባንከ ይጥፉ ብሎ እንደማሰብ አይቆጠርም ወይ” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የውጭ ባንኮች ወደ ሃገር ውስጥ መፈቀዱ አገልግሎቱን ከማሻሻል እና ካፒታል ከማምጣት ጥቅም ቢኖረውም የዝግጅት ማነስ ግን አንዱ ችግር ነው ብለዋል፡፡

በተለየም ሃገር ውስጥ የግል ባንኮች አጭር እድሜ ያስቆጠሩ ናቸው የሚሉት የምክር ቤቱ አባል ለአብነትም ብለው አማራ ባንከ፤ ስንቄ ባንክ እንዲሁም አሃዱን ባንክ አንስተዋል፡፡

በእንዚህ ባንኮች ውስጥ ደግሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አክሲዎኖች በስራቸው እንዳሉ አንስተው ጉዳዩ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባል ከዚህ ባለፈም በምን መልኩስ እንቆጣጠራቸዋልን ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ አያይዘውም የውጭ ባንኮች ምን አልባት ቢገቡ ሊያበድሩ የሚችሉት ከፍተኛ አቅም ላላቸው በመሆኑ ይህ ደግሞ አነስተና ገቢ ያላቸው እና ብድር የሚፈልጉትን እንደሚጎዳም ተናግረዋል፡፡›

ለአለም አሰፋ

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በባንኩ ዘርፍ ሲሰማሩ የሚያገኙትን ገቢ ከኢትዮጵያ ውጭ ማሰወጣት እንደማይችሉ በአዋጅ ቀረበ

ይህ የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ እያደረገ ባለው ውይይት ላይ ነው፡፡

በዚህም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ እና በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሰዎች በባንኩ ዘርፍ ሲሰማሩ የሚያገኙትን ገቢ በውጭ ምንዛሬ አማካኝነት ከሃገር ማስወጣት የማይችሉበት ድንጋጌን አስቀምጧል፡፡

በትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመ ድርጅትም ሆነ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በባንኩ ዘርፍ ሲሰማሩ የሚከተሉት የህግ ማዕቀፎች በብሄራዊ ባንክ በኩል ከዚህ ቀደም የተቀመጠ እንደሆነ ያነሳው ቋሚ ኮሚቴው፤ ነገር ግን ያገኘውን የኢንቨስትመንት ገቢ ከሃገር ማስወጣት እንደማይችል በአዲስ አንቀጽ መቀመጡን ጣቢያች ተመልክቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ይሄንን አዋጅ ማቀመጡ ያስፈለገው ማንኛውም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሃገር ውስጥ የባንክ ዘርፍ መሰማራት ሲፈልግ የሚታየው እንደሃገር ውስጥ ባለ ሃብት በመሆኑ የሚያገኙትን ማንኛውም ገቢ ከሃገር ማሰወጣት በህግ ተከለከለ መሆኑን ተገልጧል፡፡

ለአለም አሰፋ

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ተኛ ዓመት የስራ ዘመን በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል፡፡

በምክር ቤቱ፤ ቋሚ ኮሚቴው የብሄራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ሪፖርት ካቀረበ በኋላ የውሳኔ ሀሳቡን መርምር ረቂቁን አጽድቋል፡፡

በዚህም ረቂቁ አዋጅ ቁጥር 1359 /2017 በመሆን በሙሉ ድምጽ ጸደቋል፡፡

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ተገለፀ

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ከተወያየ በኃላ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

በነገው መደበኛ ስብሰባ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

ምክር ቤቱ፤ ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ሰኔ 18 ቀን ፣ 2ዐ16 ዓ/ም ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ የሚታወስ ነው፡፡

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የታኅሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኦሮሚያ ክልል በተጀመረው የምክክር ምዕራፍ የኦሮሞ ህዝብ ሲጠይቃቸው የኖሩ ጥያቄዎች አጀንዳ ሆነው እንዲቀረቡ አባገዳዎች ጠየቁ።

በኦሮሚያ በተጀመረው የምክክር ምዕራፍ የኦሮሞ ህዝብ ሲጠይቃቸው የኖሩ ጥያቄዎች አጀንዳ ሆነው እንዲቀረቡ አባገዳዎች የጠየቁት በምክክሩ ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ምርቃት ላይ ነው።

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ከ356 ወረዳዎች የተወከሉ ከ7 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች በምክክሩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

የምክክር ሂደቱ እስከ ታህሳስ 15 እንደሚቀጥል የተነገረ ሲሆን በዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ ይደረጋል ለተባለው ጉባዬ የኦሮሚያን ክልል እና የኦሮሞን ህዝብ ይወክላሉ የተባሉ አጀንዳዎች የሚለዩበት ነው።

በዚህ ምክክር ላይ ከአጀንዳዎች ውጭ በመጨረሻው ጉባዬ ላይ የሚሳተፉ የክልሉ ተወካዮች ይመረጣሉ ተብሎም ይጠበቃል።

በዚህ የምክክር መክፈቻ ላይ አባገዳዎች ባደረጉት ንግግር ላይ የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቃቸው የኖሩ የቋንቋ ፣የወሰን፣እና ሌሎች ጥያቄዎች በአጀንዳነት እንዲያቀርቡም ጥሪ አቅርቧል።

ልኡል ወልዴ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የተቋዋሚዎች የጋራ ምክር ቤት ለመመስረት ተገደናል ሲል የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ገለፀ።

የጋራ ምክር ቤቱ  በበኩሉ የፖለቲካ የጋራ ምክር ቤቱ በህጋዊ እና የቃል ኪዳን ሰነድን ሂደት በመከተል ጉባኤ አካሂዶ ስራ ላይ ይገኛል ብሏል።

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)   የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በስራ ላይ ይገኛል ብሎ እንደማያምን አስታውቋል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ  አብርሀም ሀይማኖት  "አሁን ላይ የጋራ ምክር ቤቱ ፈርሷል ብለለን እናምናለን" ያሉ ሲሆን እንደ መፍትሄም የተቋዋሚዎች የጋራ ምክር ቤት ለማቋቋም ማቃዳቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በምክር ቤቱ የተለያዩ የሕግ ጥሰቶች ነበሩ የሚሉት መጋቢ ብሉይ አብርሀም ሀይማኖት ፤ምክር ቤቱ አላግባብ ስልጣን ላይ በመቆየትና የምርጫ ጊዜውን በማራዘም  አሁን ያለበትን ቁመና ይዟል ብለዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ በምንፈልገው መንገድ ባለመሄዱና ጉዳዩንም ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመውሰድ ምክር ቤቱን እንዲያድነው ጥረት ቢደረግም መፍትሄ ሳይሰጥ ጠቅላላ ጉባኤው መካሄዱ እና አጀንዳ መመረጡም ተገቢ አይደለም አግባብነትም የለውም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም  የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱን በጉዳዩ ላይ የጠየቀ ሲሆን፤ ምክር ቤቱ የፓርቲዎችን ክስ አጣጥሏል።

የምክር ቤቱ አዲሱ ተመራጭ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አየለ  እንዳሉት፤ የምክር ቤቱን ህጋዊ እውቅና በማመን ችግሮችን በምክክር መፍታት ይገባል ብለዋል።

ምክር ቤቱ በተቋቋመበት የቃል ኪዳን ሰነድ አማካኝነት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል የሚሉት አቶ ሰለሞን፤ በዚህም የምክር ቤቱ አንዱ ስራ የሆነውን የጋራ አጀንዳ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አቅርበናል ብለዋል።

ለአለም አሰፋ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የታኅሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክሩ በቀጣይ  በአማራ ክልል ይካሄዳል ተባለ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮምሽን  በቀጣይ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል  የተሳታፊና አጀንዳ ልየታ እንደሚያደረግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት የዘገየውን የምክክር ተሳታፊዎች ልየታ በቀጣይ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

ኮሚሽነሩ አዝማሚያው ለምክክር መድረክ የማይጋብዝ ከሆነም ከሌሎች ክልሎች ባገኘነው ልምድ መሰረት እንደተደረገው ተሳታፊዎችን ወደ ሌሎች ቦታዎች ወስደን የምንወያይ ይሆናል ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በስኬት ማጠናቀቃቸውንም  ኮሚሺነሩ አንስተዋል፡፡

በዚህም በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ ከ8ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይገኙበታል የተባለው ሀገራዊ ምክክር ከነገ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሥምንት ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።

ተሳታፊዎች ወደ ምክክር ስፍራው እየገቡ መሆኑን ጣቢያችን ከቦታው ሆኖ ተመልክቷል።

ልዑል ወልዴ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel