ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

ኢትዮጵያ ከካርበን ሽያጭ ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያስችል የህግ ማእቀፍ በዝግጅት ላይ ነዉ ተባለ።

ኢትዮጲያ በዚህ የካርበን ንግድ ግብይት የሚገባትን ለማግኘት እና ለመጠቀም እየቻለች አይደለም ተብሏል።

ሀገሪቱ ለሚኖራት የካርበን ሽያጭ ተጠቃሚ ለማድረግ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት የሚጠናቀቅ የህግ ማእቀፍ እንደተዘጋጀ ሰምተናል።

ይህ የህግ ማእቀፍ ኢትዩጲያ በዚህ የካርበን ግብይት በምን ያክል የሽያጭ መጠን  እና ለማን የሚሉ ጥያቄዎችን የሚመልስ ነዉ ተብሏል።

ከኢትዩ ኤፍም ጋር ቆይታ ያደረጉት በኘላን እና ልማት ሚኒስተር የአየር ንብረት ለዉጥ ስምምነት ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መንሱር ደሴ የካርበን ሽያጭ ለመፈጸም በርካታ መስፈርቶችና ረዥም ሂደት የሚጠይቅ መሆኑን ይገልፃሉ።

የካርበን ገበያ ተሳታፊ ሆኖ እንድትጠቀም ለማስቻል ኘላን እና ልማት ሚኒስትር የስትራቴጂክ እቅዶች እንዳሉት ገልፆል።

የብሄራዊ የካርበን ገበያ ስትራቴጂ መጀመሩን የሚገልፁት አቶ መንሱር ከተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለዉጥ ፅህፈት ቤት ድጋፍ እየተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል።

የበካይ ጋዝ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት ለመጥቀም ይደረጋል የሚባለዉ ግብይቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ደንን በማልማት እና በመንከባከብ የሚገኙትን የካርበን መጠን በመለካት ገቢ የሚያገኙበት ነዉ።

ከዚህ ጋር ተያይዞ አዲሱ የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ደንብ የኢትዮጵያ የካርበን ሽያጭ በህግ እንዲመራ የሚያደርግ እንደሆነ መገለፁም የሚታወስ ነዉ።

ቁምነገር አየለ

ታኀሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ፑቲን ከአሜሪካ ጋር መታረቅ እንደሚፈልጉ አስታወቁ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአሜሪካ ጋር ያለውን ውዝግብ በሠላማዊ መንገድ ማስቆም እንፈልጋለን ብለዋል::

ፕሬዝዳንቱ የሩሲያ ብሔራዊ ጥቅም ከተጠበቀ ሁሌም ለመነጋገርና ሰላም ለማውረድ ዝግጁ መሆናቸው አረጋግጠዋል ።

ፑቲን አሜሪካ መራሹ አለም ከቀድሞው የሩሲያ ደካማ መሪዎች ጋር ተባብረው ሩሲያን አፈራርሰዋታል ሲሉ በቁጭት ተናግረው ከዚህ በኋላ ግን አንፈቅድላቸውም ነው ያሉት።

በዩክሬኑ ጦነት ዙሪያም ከተመራጩ ፕሬዝዳንት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውንም ታስ ዘግቧል።

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን እና የሩሲያ ልዩ መልዕክተኛ ኪት ሎግ በሚቀጥለው ወር ኪቭን ከጎበኙ በኋላ ወደ ሞስኮ ለመጓዝ ማቀዳቸውን ብሉምበርግ ከሰሞኑ አስነብቧል።

ምንምእንኳን እቅዱ በውሳኔ ደረጃ ባይጎለብትም ኪሎግ ወደ ሩሲያ የሚያቀኑ ከሆነ የተለየ ፖሊሲ ማስተግበር ላይ ከማተኮር ይልቅ በሞስኮ በኩል የሚነሱ ሀሳቦችን መረጃ በማሰባሰብ ላይ ሊያተኩሩ እንደሚችል ብሎምበርግ አስነብቧል፡፡

አባቱ መረቀ

ታኀሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በናይጄሪያ የገና ገጸበረከት ለመቀበል የወጡ ሰዎች ተረጋግጠው የ32 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በናይጄሪያ የገና ስጦታ በማከፋፈል ላይ በነበሩ በሁለት በጎ አድራጎት ዝግጅቶች ላይ በተከሰተ መረጋገጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ13 ወደ 32 ማሻቀቡን የሀገሪቱ ፖሊስ ዛሬ እሁድ አስታውቋል።

በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከከፋ የኑሮ ውድነት ቀውስ ጋር እየታገለች ባለችው ናይጄሪያ የምግብ እርዳታዎችን ለመቀበል ሰዎች በሰፊው ወጥተው የነበረ ሲሆን፤ በትንሹ አራት ህጻናትን ጨምሮ ብዙዎች ህይወታቸው አልፏል።

ከሟቾቹ 22ቱ በደቡብ ምሥራቅ አናምብራ ግዛት ኦኪጃ ነዋሪዎች ሲሆኑ፤ ትላንት ቅዳሜ አንድ ገባሬ ሰናይ ተቋም በዓሉን በማስመልከት ምግብ ለማከፋፈል ባዘጋጀው መርሃግብር ላይ ጉዳቱ መከሰቱን የአካባቢው ፖሊስ ቃል አቀባይ ቶቹቹኩ ኢኬንጋ ተናግረዋል ሲል አልጃዚራ ዘግቧል።


ታኀሣሥ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ድጋሚ በተሰጠው ድምፅ ዶ/ር ትዕዛዙ ሞሴ ከአዲስ አበባ በወንዶቹ ምድብ አራተኛው የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

በስራ አስፈፃሚነት ለመቀጠል ፍላጎት በነበራት ደራርቱ ቱሉ ዙሪያ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባደረገው ስብሰባ እሷን ጨምሮ የስራ ዘመናቸውን የጨረሱትን አትሌት መሰለች መልካሙ፣ አትሌት ማርቆስ ገነቴ እና ወ/ሮ ፎዚያ እንድሪስ የዕድሜ ልክ የክብር አባል ሆነው እንዲቀጥሉ ለጉባኤው ሀሳብ ቀርቦ ተቀባይነትን አግኝቷል።

ምስጋናው ታደሰ

ታኀሣሥ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አትሌት ስለሺ ስህን 11 ድምፅ በማግኘት አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆኗል።

ገ/እግዚአብሔር 9 ድምፅ አግኝቷል።

ምስጋናው ታደሰ

ታኀሣሥ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የመን በሃይፐርሶኒክ ባለስቲክ ሚሳኤል ቴል አቪቭን ደበደበች

የየመን ጦር ሃይል ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሬ ፤የአረብ መንግስት ጦር ቴል አቪቭን በሃይፐርሶኒክ ባለስቲክ ሚሳኤል መምታቱን አስታውቋል።

ሳሬ በሰጡት መግለጫ የየመን ጦር በጃፋ ፍልስጤም-2 በተሰኘ ሃይፐርሶኒክ ባሊስቲክ ሚሳኤል ወታደራዊ ኢላማ መምታቱን ተናግሯል።

ሚሳኤሉ ዒላማውን በትክክል መቷል የተባለ ሲሆን ፅዮናዊያኑ ጥቃቱን መመከት አልቻሉም ተብሏል።

የጽዮናዊው አገዛዝ ጥቃት እስኪቆምና በጋዛ ሰርጥ የተከበቡ ስፍራዎች እስኪለቀቁ ድረስ የአረብ መንግስት ለፍልስጤም የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥልም ቃለአቀባዩ አጽንኦት ሰጥተዋል። 

ከጥቅምት 7 ቡኋላ በጋዛ ላይ አውዳሚ ጦርነት ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ የየመን ነዋሪዎች ፍልስጤምን በእስራኤል ወረራ ላይ ለሚያደርጉት ትግል በብርቱ እያገዙ ይገኛሉ።

የየመን ጦር ኃይሎች፤ለ27 ሺህ 948 ሰዎች ሞትና  ለ67 ሺህ 459 ግለሰቦች መቁሰል ምክንያት የሆነው የእስራኤል ያልተቋረጠ የመሬትና የአየር ላይ ጥቃት እስካልቆመ ድረስ በማንኛውም መንገድ እስራኤልን ማጥቃት እንደ ማያቆሙ ተናግረዋል ።

አሜሪካና ብሪታንያ እስራኤልን ለመደገፍ በየመን ላይ ወታደራዊ ጥምረት ማድረጋቸውም ታውቋል።

ልኡል ወልዴ

ታኀሣሥ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአፍሪካ የወታደራዊ ሰፈር መቆናጠጫ መሬት እያጣች የመጣችው ፈረንሳይ በጂቡቲ ያላትን የጦር ሰፈር ማጠናከር እንደምትፈልግ አስታውቃለች።

የፈረንሳዩ ፕረዚደንት ማክሮን ዛሬ በጅቡቲ ባደረጉት ጉብኝት ከጅቡቲው ፕረዚደንት ኢስማኢል ጉሌህ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን እዛው የሚገኘውን የሃገሪቱን የጦር ሰፈርም ጎብኝተዋል።

ማክሮን ከፕረዚደንት ኢስማዒል ጉሌህ በነበራቸው ቆይታ ጅቡቲ የሚገኘው የፈረንሳይ ጦር ሰፈር የኢንዶፓስፊክ የንግድ ግኑኝነት መስመር ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

ፈረንሳይ በኢንዶ ፓስፊክ ያላትን ስትራተጂያዊ ጥቅም በጅቡቲ ካለው የጦር ሰፈሯ ውጭ የማይታሰብ እንደሆነም አክለዋል።

ፈረንሳይ ጅቡቲ በሚገኘው የጦር ሰፈሯ 1,500 ወታደሮች ያላት መሆኑን ይታወቃል።

ፈረንሳይ፤ በማሊ፣ ኒጀርና ቡርኪናፋሶ የነበራት ጦር እንደጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2022 እና 23 በየሃገራቱ ሥልጣን በተቆናጠጡ ወታደራዊ ሁንታዎች የፈረንሳይ ወታደሮች አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማድረጋቸው ይታወቃል።

በቻድ ያለው ወታደራዊ ሁንታም ከፈረንሳይ መንግስት ጋር የነበረውን  ወታደራዊ ግኑኝነት ማቋረጡን ተከትሎ የፈረንሳይ ወታደሮች በቅርብ ሳምንታት ሐገሪቱን ለቀው ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመሆኑም ፈረንሳይ በአፍሪካ ያላትን ወታደራዊ የመቆናጠጫ ቦታ ሙሉ በሙሉ ላለማጣት ከጅቡቲ ጋር ያላትን ግኑኝነት ማጠናከር እንደምትፈልግ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ታኀሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

ዛሬ ከቀኑ 5 ሠዓት ከ20 ላይ በፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡

ከአሁን ቀደም የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰትበት በነበረው ፈንታሌ አካባቢ ዛሬም ክስተቱ መስተዋሉን በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ገልጸዋል፡፡

በሬክተር ስኬልም 4 ነጥብ 3 መመዝገቡን አረጋግጠዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ያደረሰው ጉዳት መኖሩ ወይም አለመኖሩ በቀጣይ እንደሚገለጽም መናገራቸው ፋና ዘግቧል፡፡

ታኀሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ማህበረሰቡ ጥራታቸው ያልተረጋገጠ የፀረ-ወባ መድሀኒትቶችን ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳሰበ

ባለስልጣኑ በገበያ ላይ የሚገኙ አንዳንድ የፀረ-ወባ መድሀኒቶች ጥራታቸው ያልተረጋገጠና ለጤና ጎጂ በመሆናቸው ማህበረሰቡ ከመጠቀም አዲቆጠብ አሳስቧል፡፡

ደህንነትና ጥራታቸው በባለስልጣኑ ያልተረጋገጡ መድሀኒቶች ለጤና ጎጂና የከፋ ችግር የሚያስከትሉ በመሆናቸው ማንኛወም ማህበረስበ መድናቶችህን ከመወሰድ ተጠብቆ ጤናወን እንዲጠብቅ አሳስቧል፡፡

እንዚህን መሰል መድሀኒቶች ከመግዛት እንዲቆጠቡ እንዲሁም በቤት ውስጥ የሚገኝ ከሆነም ማህበረሰቡ በአፋጣኝ እንዲያሶግድ  ባለስልጣኑ መመሪያ አስተላልፏል፡፡


ታኀሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከ18 አመት በታች የሆኑ ወጣት ታዳጊዎች ብቻ የሚሳተፉበት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውድድር  ሊካሄድ ነው

ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት የሆነው  ሲያትል አካዳሚ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዘጋጅነት በጄኔቫ በሚካሄደው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውድድር ላይ ለመሳተፍ መመረጡን ገልጧል፡፡

በዚህም ተቋሙ   በሀገር አቀፍ ደረጃ የአሸናፊዎች አሸናፊን ለመምረጥ ከኢትዮጽያ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ጋር  በመተባበር በኢትዮጵያ ሳይስንስ ሙዚየም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውድድር እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል።

የአካዳሚው መስራች የሆኑት መንግስቱ ወዳጄም የሰው ሰራሽ አስተውሎት በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ጠቀሜታ በማስታወስ በተለይ ወጣቱ ክፍል ተሳትፎውን ማጠናከር እንደሚገባው ገልጸዋል።

በየሁለት አመቱ ይካሄዳል የተባለው ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውድድር ላይ ኢትዮጵያን እንድወክል ሀላፊነት ተሰጥቶኛል ያለው ሲያትል አካዳሚ ኢትዮጵያ በመሰል ውድድሮች መሳተፍ እንዳለባትም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

ይህ አለም አቀፉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውድድር በዚህ አመት የአደጋ ምላሽ ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን ወጣቶች ችግር ፈቺ በሆኑ የፈጠራ ስራዎች እንዲሳተፉ እድል የሚሰጥ ነው ተብሏል።

የኤአይ ፎር ጉድ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ማኔጀር  የሆኑት ሄለን አቢ በበኩላቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለመልካም ነገሮች ለመጠቀም እንድንችል መሰል ውድድሮች መንገድ ከፋች ናቸው ብለዋል።

ለዓለም አሰፋ

ታኀሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አሜሪካ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ለተከሰተው ድርቅ እና የምግብ እጥረት ምግብ እየተላከ መሆኑን አስታወቀች

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የተከሰተውን ድርቅ እና የምግብ እጥረት ተከትሎ እርዳታ ወደ ስፍራው እየተላከ መሆኑን አስታውቋል።

ኤምባሲው በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው በወረዳው እንደተከሰተ ከሰሞኑ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች ላይ ክትትል አድርጓል።

"የኢትዮጵያ ህዝብን ለመደገፍ አጋሮቻችን ምግብ እና አልሚ ምግቦችን ወደተጠቁት ስፍራዎች እየላኩ ነው" ያለው ኤምባሲው ሁኔታውን በቀጣይም በመከታተል ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰራ አስታውቋል።

ታኀሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያ ግንዛቤን ለማስፋት ያግዛል የተባለ የዲጂታል ስርዓት ይፋ ሆነ።

በቅርቡ ወደ ስራ የሚገባዉ  የሰነደ መዋለ ንዋዩች ገበያ ላይ  የሚኖሩ የእዉቀት  ዉስንነቶችን የሚቀንስ የዲጂታል አካዳሚ  ስራ መጀመሩን ሰምተናል።

የዲጂታል አካዳሚዉ ይፋ ከተደረገበት በ 24 ሰአት  ዉስጥ 1 ሺህ 8 መቶ ተመዝጋቢዎች እንዳገኘ ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ የሰነደ መዋለ ንዋዩች ዲጂታል አካዳሚን ለመጀመር ሲሰራ የቆየዉ ኤፍ ኤስ ዲ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ሲሆን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሂክመት አብዱላሂ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ ከሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያ ጋር እየሰራ እንደቆየ ገልፀዋል።

ይህ የዲጂታል አካዳሚ በገበያዉ የሚኖሩ የባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የፋይናንስ ባለሙያዎችን  እዉቀት እና ግንዛቤን  ለመጨመር የሚያስችል ነዉ ብለዋል።

ህብረተሰቡ ስለ ሰነደ መዋለ ንዋዪች ገበያ ሊያዉቋቸዉ የሚፈልጓቸው ጉዳዩች ካሉ  የመጀመሪያ አስር ኮርሶችን በነፃ መዉሰድ የሚችሉ መሆኑን  የኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሂክመት አብዱላሂ ገልፀዉልናል።

ይህ የዲጂታል አሰራር ስለ ካፒታል ገበያም ሆነ ስለ ሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያዎች መረዳት እንዲቻል የተዘጋጁ የተለያዩ የስልጠና ይዘቶች እንዳሉት ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመጪው ጥር ወር መጀመሪያ ጅማሮዉን ስለማድረጉ መገለፁ የሚታወስ ነዉ።

ቁምነገር አየለ

ታኀሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሁቲዎች ከእስራኤል ጋር ረጅም ጦርነት ለማድረግ ዝግጁ ነን አሉ

የጋዛው ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ አጋርነታቸውን ለፍልስጤማውያን እያሳዩ የሚገኙት የየመኖቹ ሁቲዎች ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል ።

የሁቲ ጦር ቃል አቀባይ የብርጋዴር ጀነራል ያህያ ሳሪ  ከእስራኤል ጋር የተራዘመ ጦርነት ውስጥ ለመግባት ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል።


ጦሩ ወደ እስራኤሏ መዲና ቴል አቪቭ በተሳካ ሁኔታ የሚሳኤል ጥቃት ማድረጉንም አስታውቋል ።

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ሁቲዎች የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ወደ እስራኤል ማስወንጨፍ መጀመራቸው የሚታወስ ነው።

እስራኤል በበኩሏ ሁዳዬዳህ የመሳሰሉት የየመን ከተሞችን በጄት ትደበድባለች።

ሁቲዎች ጥቃቱን የሚያቆሙት  እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን ጦርነት ስታቆም ብቻ መሆኑን በተደጋጋሚ መናገራቸው የሚታወስ ነው ዘገባው የፕሬስ ቴሌቪዥን ነው።

አባቱ መረቀ

ታኀሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ፋስት ፔይ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ውስጥ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ

ፋስት ፔይ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ የገንዘብ መላላኪያ ስርዓት ማስጀመሩን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል ።

የፋስት ፔይ ኢቲ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍፁም ተስፋዬ ፤ ይህ ስርዓት ቁጭት የፈጠረው ነው ብለዋል።

እሱም በውጪው አለም ተሰራጭተው የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ቀደም ገንዘብ ወደሃገር ውስጥ ለመላክ ከፍተኛ ችግር ይገጥማቸው ነበር ብለዋል።

ይህም አንድ ጊዜ ገንዘብ ለመላክ ከ5 እስከ 10 በመቶ ኮምሽን መቆረጥ፣በፈለጉበት ጊዜ መላክ አለመቻል፣ለገንዘብ ዝውውሩ ቀናት መፍጀት፣ከፍተኛ ሰልፍ ፣ ቴክኒካል ችግሮች ይገጥማቸው እንደ ነበር ጠቁመዋል።

አቶ ፍፁም ይህን መጉላላትና እንግልትን የስቀረ ፣ለገንዘብ ዝውውር ምንም አይነት ኮምሽን የማያስከፍልና በአንድ ደቂቃ ውስጥ ወደ ፈለጉት መላላክ እንዲችሉ የሚያደርግ መተግበሪያ ዛሬ አስጀምረናል ብለዋል።

ተጠቃሚዎች በፋስት ፔይ ኢቲ ሲጠቀሙ ከዕለቱ የባንኮች ምንዛሪ ከፍ ያለውን ማቅረቡ መተግበሪያውን ከሌሎች የመላላኪያ ዘዴዎች ልዩ ያደርገዋልም ተብሏል።

ማንኛው አካል ወይንም ተቋም ፤ለተቋማት ወይንም ለግለሰብ ድጋፍ ማድረግ ቢፈልጉ መተግበሪያውን በመጠቀም በቀላሉና በቀጥታ ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉም ብለውናል።

ፋስት ፔይ ኢቲአሁን ሀገሪቱ ውስጥ ካሉት 31 ባንኮች ጋር የተሳሰረ ሲኾን ይህም ተጠቃሚዎች ካሉበት ሀገር ኾነው ወደ የትኛውም የኢትዮጵያ ባንኮች በቀላሉ ሞባይልን በመጠቀም ገንዘብ ማስተላለፍ የሚችሉበት መተግበሪያ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ፋስት ፔይ ኢቲ/ FastpayEt በዩናይትድ ስቴት አሜሪካና በኢትዮጵያ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦና ፈቃድ አውጥቶ ወደሥራ የገባ የቴክኖሎጂ ተቋም መሆኑን ተነግረዋል፡፡

ልዑል ወልዴ

ታኀሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አልቤኒያ ቲክቶክን አገደች፡፡

ቲክቶክ ግጭት ቀስቃሽ እና ሕፃናትን የሚያሸማቅቁ ቪዲዮች የሚሰራጭበት በመሆኑ ለአንድ አመት እንደምትዘጋው አስታውቃለች፡፡

የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ ቲክቶክ እንዲታገድ ውሳኔ ያስላለፉት በቲክቶክ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ኅዳር ወር አጋማሽ ላይ አንድ ታዳጊ፣ በሌላ ታዳጊ በስለት መገደሉን ተከትሎ መሆኑን ተዘግቧል፡፡

ቲክቶክ በተመሰረተበት ቻይና "በተሻለ ሁኔታ እንዴት ማጥናት እንደሚቻል፣ ተፈጥሮን እንዴት መንከባከብ እንደሚቻል እና የመሳሰሉትን በጎና የተለዩ መልዕክቶች ናቸው የሚተላለፉት" ሲሉ የአልቤኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራማ ተናግረዋል። ራማ ቲክቶክ እንዲዘጋ ያሳለፉትን ውሳኔ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አልተቀበሉትም።


ይህ ውሳኔ የመጣው የአልቤኒያ ባለሥልጣናት ከ1 ሺሕ 300 መምሕራንና ወላጆች ጋራ ውይይት ካደረጉ በኃላ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት የተጠየቀው ቲክቶክ ቅዳሜ ዕለት በሰጠው የኢሜል ምላሽ፣ በስለት ተወግቶ ስለተገደለው አዳጊ የአልቤኒያ መንግሥት በአስቸኳይ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቋል። "የደረሱኝ ብዙ ሪፖርቶች እንዳረጋገጡት ወደ አደጋው እንዲያመራ ምክኒያት የሆነው ቪዲዮ የተሰራጨው በሌላ የትስስር ገጽ ላይ እንጂ በቲክቶክ አይደለም" ብሏል።

አልቤኒያ ውስጥ ከቲክቶክ ተጠቃሚዎች ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሕፃናት መሆናቸውን የሀገር ውስጥ ጉዳዮችን የሚያጠኑ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

ልጆች ቲክቶክ ላይ በሚያዩዋቸው ግጭት ቀስቃሽ ቪዲዮዎችና የሚፈጠሩ አለመግባባቶች ወደ ትምሕርት ቤት በሚሄዱበት ጊዜ እንደ ቢለዋ ያሉ ስለት ነገሮችና ሌሎች ቁሳቁሶችን እየያዙ መሄድ በመጀመራቸው ወላጆችን ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል ሲል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡።

ታኀሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአውሮፓ ህብረት መሪዎች የኔቶን መከላከያ ወጪን ለመጨመር ቁርጠኛ መሆናቸውን የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ

የኔቶ አገሮች ከ2 በመቶ በላይ የኤኮኖሚ ግኝታቸውን ለመከላከያ ሃይላቸው ሊያውሉት እንደሚያስፈልግ ጠንቅቀው ያውቃሉ  ሲሉ የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሪያኮስ ሚትሶታኪስ ተናግረዋል ።

ይህ  አዲሱ የታቀደው አሃዝ በሚቀጥለው ዓመት በኅብረቱ አባላት መካከል ውይይት ከተደረገ በኋላ ግልጽ ይደረጋልም ብለዋል።

ሚትሶታኪስ ይህን ያሉት በሰሜን ፊንላንድ የአውሮፓ ህብረት በአውሮፓ ደህንነት ፣መከላከያና ፍልሰት ላይ በካሄደው  ስብሰባ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት “ከ2 በመቶ በላይ መመደብ እንዳለብን ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን ብለዋል።

አሁን ላይ በአሃዙ እርግጠኛ አይደለሁም ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ "ከአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር ከተገናኘን በኋላ ጭማሬው ምንያህል ይሁን የሚለውን በኔቶ ውስጥ ተስማምተን የምናሳውቅ ይሆናል ሲሉም ጠቁመዋል።


ልኡል ወልዴ

ታኀሣሥ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በስራ አስፈፃሚነት ለመቀጠል ፍላጎት በነበራት ደራርቱ ቱሉ ዙሪያ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባደረገው ስብሰባ እሷን ጨምሮ የስራ ዘመናቸውን የጨረሱትን አትሌት መሰለች መልካሙ፣ አትሌት ማርቆስ ገነቴ እና ወ/ሮ ፎዚያ እንድሪስ የዕድሜ ልክ የክብር አባል ሆነው እንዲቀጥሉ ለጉባኤው ሀሳብ ቀርቦ ተቀባይነትን አግኝቷል።

ምስጋናው ታደሰ

ታኀሣሥ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለቀጣዮቹ 4 ዓመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በስራ አስፈፃሚነት የሚመሩት 8 ሰዎች ተለይተው ታውቀዋል። በዚህም መሰረት፦

በሴቶች
1ኛ. አትሌት መሰረት ደፋር - ከአ/አ (18 ድምፅ)
2ኛ. ወ/ሮ ሳራ ሀሰን ከኦሮሚያ (16 ድምፅ)
3ኛ. ክብርት ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ ከአማራ (13 ድምፅ)
4ኛ. ዶ/ኤፍራህ መሀመድ ከሶማሌ (12 ድምፅ) በመሆን ተመርጠዋል።

በወንዶቹ
1ኛ. አቶ ቢኒያም ምሩፅ ከ ትግራይ (10 ድምፅ)
1ኛ. ተመስገን ነቤ ከኦሮሚያ (10 ድምፅ)
3ኛ. ኢ/ር ጌቱ ገረመው ከድሬዳዋ (9 ድምፅ)
4ኛ. አቶ ተፈራ ሞላ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ (8 ድምፅ)
4ኛ. ዶ/ር ትዕዛዙ ሞሴ ከአዲስ አበባ (8 ድምፅ)
4ኛ. ዶ/ር ዘላለም መልካሙ ከአማራ (8 ድምፅ) ወጥተዋል።

በመሆኑም የመጀመሪያዎቹ ሶስት አትሌቶች በቀጥታ እንዲያልፉ ተደርጎ እኩል 8 ድምፅ አግኝተው አራተኛ በሆኑት አትሌቶች ላይ በድጋሚ ድምፅ እየተሰጠ ይገኛል።



ምስጋናው ታደሰ

ታኀሣሥ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

እርቅ የፈፀሙ የኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል የሀገራዊ ምክክር ላይ መሳተፍ ጀመሩ።

በቅርቡ ከመንግስት ጋር እርቅ በመፈፀም የገቡ የኦሮሚያ ክልል ታጣቂ ኃይሎች በክልሉ እየተካሄደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ላይ እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮምሽን ኮምሽነር አምባሳደር ሞሀመድ ድሪ የራቁት ቀርበዋል፣የቀረቡትም ገብተዋል፣የገቡት እዚሁ እንዲቀሩ አበክሮ መስራት ይገባል ብለዋለል።

አባሳደር ባስተላለፉት መልእክት "አንድ ቤት ለመስራት የሚጣደፉ ሰዎች ለቤቱ ግብአት የሚሆን ቁሳቁስ አይሰራረቁም" ነው ያሉት።

በመሆኑ የምንሰራው፣የምንገነባው አንድ ቤት ነውና በሃሳብ ተለያይታቹ በጫካ ውስጥ ያላቹ አሁንም ቅረቡልን ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮምሽን ዋና ኮምሽነር ፕ/ር መስፍን አርዐያ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣
የመንግስት ተወካዮች ለሀገር የሚሆነውን ሁሉ እንደምትሰጡን እናምናለን ብለዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ በተከፋፈለ ሳይሆ አንድ ሆናቹ፤ ለኦሮሞ ህዝብና ክልል እንዲሁም ለኢትዮጵያ የሚበጃትን ሃሳብና ምክር እንድት ሰጡን እንፈልጋለን ብለዋል።

ለሀገር እድገትና ሁለንተናዊ ልማት የናተ ተፅኖፈጣሪዎች ሚና ላቅ ያለ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህ መድረክ የተመረጡ የህብረተሰብ ወኪሎች፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት ተወካዮች፣ የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች እንዲሁም የማህበራትና ተቋማት ወኪሎች ተገኝተዋል።

በመጨረሻም በሶስት ቀናት ውይይት ውስጥ ለሀገራዊ ምክክር ጉባዬው ተወካዮቻቸውን እና አጀንዳዎቻቸውን እንደሚያስረክቡ ተነግሯል ።


ልኡል ወልዴ

ታኀሣሥ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአሜሪካ ሴኔት ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታደገውን በጀት አጸደቀ

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የአሜሪካ መንግሥትን እስከ መጋቢት የሚያቆየውን በጀት አጸደቀ።

በሪፐብሊካን ተመራጮች ብዙኅን ድምፅ ስር ያለው የሕግ መምሪያ ምክር ቤት እና በዲሞክራት አብላጫ ቁጥጥር ስር ያለው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት፣ ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታገደውን በጀት ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ አጽድቀዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የበጀት ረቂቁን እንደሚደግፉና ሕግ እንዲሆን እንደሚፈርሙ ትላንት ዐርብ ተናግረው ነበር።

የጸደቀው በጀት ሕግ ኾኖ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ፣ መንግሥቱን እስከ መጪው መጋቢት የሚያቆየው በጀት ይኾናል።

100 ቢሊዮን ዶላር ለአደጋዎችና ለርዳታ፣ 10 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ለገበሬዎች በበጀቱ ተይዟል።

የጸደቀው በጀት የፌደራል መንግሥቱን የዕዳ ጣሪያ ከፍ እንዲል አያደርግም።

ታኀሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዓለም ባንክ፣ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር የሚውል የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል።

ከብድሩ 90 በመቶው የንግድ ባንክን ሒሳብ ለማስተካከልና ባንኩን መልሶ ለማዋቀር እንደሚውል ዓለም ባንክ ገልጧል።

ከፊሉ ብድር ለብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማጠናከሪያና መዋቅራዊ ማሻሻያ እንደሚሰጥ ባንኩ ጠቅሷል።

ብድሩ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚለቀቀው፣ የባንኮቹ አፈጻጸም፣ የደንቦችና የመዋቅሮች ማሻሻያ ሂደት እየታየ የሚለቀቅ ነው።

የብድሩ ዓላማ፣ የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግና ተደራሽነቱን ለማስፋት ያለመ እንደኾነም ባንኩ ባሠራጨው አጭር መግለጫ አንስቷል።

ታኀሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ናቸው


ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የፈረንሳይ ፕሬዜዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ተቀብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማክሮንን " ወንድሜ እና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ " ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

" በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖር እምነታቸውን ገልጸዋል።

የማክሮንን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ ዋና ዋና የአዲስ አበባ መንገዶች ላይ የተተከሉ የማስታወቂያ ስክሪኖች " ፕሬዜዳንት ማክሮን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በሰላም መጡ " የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፈባቸው ነው።

ማክሮን ፤ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት ሲመጡ በ6 ዓመታት ይህ ሁለተኛቸው ነው።


ታኀሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አሜሪካ አዲሱን የሶሪያ መሪ ለመያዝ መድባ የነበረውን የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ሰረዘች


አሜሪካ የሶርያውን መሪ አህመድ አል-ሻራ በቁጥጥር ስር ለማዋል ለመያዝ መድባው የነበረውን የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ከከፍተኛ ዲፕሎማቶች እና ከሃያት ታህሪር አል ሻም (ኤችቲኤስ) ተወካዮች ጋር ውይይት ካደረገች በኋላ ሰረዘች።

ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባርባራ ሌፍ ከሻራ ጋር የተደረገው ውይይት "በጣም ውጤታማ ነበር" ካሉ በኋላ እርሱም "ለመወያየት ዝግጁ" ሆኗል ብለዋል።


የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ዋና ከተማዋ ደማስቆ የደረሰው የኤች ቲ ኤስ ታጣቂዎች የበሽር አል አሳድን መንግሥት ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ካስወገዱ በኋላ ነዉ።

ዋሽንግተን አሁንም አማፂ ቡድኑን በአሸባሪነት እንደ ፈረጀች ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ዲፕሎማቶቹ በአሜሪካ የሚደገፍ "የሽግግር መርሆዎች" ላይ፣ ቀጠናዊ ሁኔታዎች እንዲሁም አይኤስን የመዋጋት አስፈላጊነት ላይ መወያየታቸውን አረጋግጠዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም፣ ባለሥልጣናቱ በአሳድ አገዛዝ ዘመን ስለጠፉት አሜሪካውያን ዜጎች፣ በ2012 በደማስቆ የተጠለፈውን ጋዜጠኛ ኦስቲን ቲስ ፣ እና በ2017 የጠፋውን ሳይኮቴራፒስት ማጅድ ካልማዝ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን አስታውቀዋል።


ጉብኝቱ ከአስር ዓመታት ወዲህ በደማስቆ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ መደበኛ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ነው።

ይህ ጉብኝት በሶሪያ የአሳድ ከስልጣን መወገድን ተከትሎ የታየ ድንገታዊ ለውጥ ሲሆን፣ አዲስ ስልጣን የሚረከበውን መንግሥት የአረብ አገራት ድጋፍ ተጨምሮበት አሜሪካ እና አውሮፓ ተጽዕኖ ለማሳረፍ የወሰዱት እርምጃ ነው።


ታኀሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የቅድመ ደሞዝ ብድር ለማግኘት ያስችላል የተባለ ለት "አቦል ደሞዜ " የተሰኘ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ

ቡና ባንክና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ስርቪስ የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ "አቦል ደሞዜ የተሰኘ የዲጅታል ብድርና ቁጠባ አገልግሎት በዛሬው እለት በይፋ አስጀምረዋል ።

የቡና ባንክ ቺፍ ባንኪንግ ኦፊሰር እቶ መንክር ሀይሉ፤ "አቦል ደሞዜ የተሰኘው ስርዓት ለሰራተኞች የደሞዝ መደረሻ የገንዘብ ፍላጎትን ለመሙላት የተዘጋጀ የቅድመ ደመወዝ ብድር አገልግሎት መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ መንክር ሰራተኞች ከከፍያ ቀናቸው በፊት በሚገጥማቸው የገንዘብ እጥረት ወቅት የወር ደሞዛቸውን የተወሰነ ክፍል ያለምንም ማስያዣ በብድር እንዲያገኙ የሚያስችል የፋይናንሺያል አገልግሎት ነውም ብለዋል።

በዚህ አዲስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የደመወዛቸውን 33 ወይም 50 በመቶ በቀላሉ ካሉበት ሆነው በካቻ የሞባይል አፕሊኬሽን ማግኘት ይችላሉ የተባለ ሲሆን  የአከፋፈል ዘዴውም በሚቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት ብድራቸውን መክፈል የሚያስችል ነው ተብሏል።

ሰራተኞች አገልግሎቱን ለማግኘት የቡና ባንክ ወይም የካቻ ደንበኞች መሆን እንደሚጠበቅባቸው እቶ መንክር ሀይሉ ገልፀዋል ።

አገልግሎቱን ያበለፀገው የካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ጥላሁን በበኩላቸው ፤ካቻ በተለመደው የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልነበረውን ሰፊ የህብረተሰብ ክፍል ለማገልገል የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን እንደ አማራጭ ይዞ የመጣ ኩባንያ መሆኑን ገልፀዋል።

ስራ አስኪያጁ ከቡና ባንክ ጋር በመቀናጀት ይህንን የደሞዝ መዳረሻ ብድር እገልግሎትን ሲያቀርብ ታላቅ ኩራትና ክብር ይሰማናል ብለዋል።

ልኡል ወልዴ

ታኀሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም!

የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ1ኛ እስከ 11ኛ ሳምንት በድሬደዋ ከተማ መደረጉ ይታወቃል።

ከ12ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት ያለው የአንደኛ ዙር መርሃ ግብር በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ከታህሳስ 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ያሳውቃል።

ጋዲሳ መገርሳ

ታኀሣሥ 11 ቀን 2017ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ቴክኖ ሞባይል አጋዥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የተካተተበት መተግበሪያ አስተዋወቀ

ቴክኖ በቅርቡ ለዓለም ዓቀፍ ገበያ ያስተዋወቀው የቴክኖ ኤ አይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በትናንትናዉ እለት አስተዋውቋል፡፡

አዲሱ የቴክኖ ኤ አይ አጋዥ ቴክኖሎጂ የዕለት ተዕለት ኑሮን የሚያቀል ነዉ ተብሏል።

ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ የተለያዩ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየር እና መሰል ተያያዥ ስራዎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመከወን የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

የቴክኖ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሊክ ቴክኖ ኢትዮጵያ በሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ቁልፍ ሚናን እየተጫወተም እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ቴክኖ ኢትዮጵያም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን እንዲሁም ማህበረሰቡ አለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ እኩል እንዲራመድ መትጋቱን እንደሚቀጥል ማናጀሩ አያይዘ ገልፀዋል።

ቴክኖ ከአለም የቴክኖሎጂ ገበያ ጋር ተወዳዳሪ የሆኑ እና ከፍ ያለ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ወደ ተጠቃሚ ማድረሱን እየቀጠለ ነዉ የተባለ ሲሆን አሁን ደግሞ በኤይ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለተጠቃሚዎች አጅግ ቀላል እና ዘመናዊ የምርት ውጤትን ለመስጠት እየተጋ መሆኑ ተገልፆል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ታኀሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጵያ 92 በመቶ የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ6 ወር በላይ ያሉ ህፃናት ምግብ አይጀምሩም ተባለ።

ዕድሜያቸው ከ6 ወር በላይ ከሆኑ ልጆች 8 በመቶዎቹ ብቻ ከእናት ጡት ወተት ውጪ ተጨማሪ ምግቦችን እንደሚጀምሩ ሰምተናል።

61 በመቶ የሚሆኑ እናቶች ብቻ ልጆቻቸውን እስከ 6 ወር ድረስ ጡት እንደሚያጠቡም ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የተለያዩ ማስታወቂያዎች እና የተጋነኑ መረጃዎች እናቶች ልጆቻቸውን ጡት እንዳያጠቡ አድርጓል ነው የተባለው ።

በአዲስ አበባ 57 በመቶ የሚሆኑ እናቶች በተለያዩ ማስታወቂያዎች ምክንያት ልጆቻቸውን ጡት አያጠቡም ተብሏል።

ከ6 ወር በላይ ለሆናቸው ልጆች የሚሰጥ ምግብ ላይ የስኳር እና የቅባት መጠን አነስተኛ መሆን ያለበት ቢሆንም በጥናት የታየው ግን የዚህ ተቃራኒ መሆኑም ተገልጿል።

በአገራችን ዕድሜያቸው 6 ወር እና ከዛ በላይ የሆኑ ህፃናት 31 በመቶ ለጤናቸው ተስማሚ ያልሆኑ ጣፋጭ መጠጦችን የሚጠቀሙ ሲሆን ፤ 15 በመቶዎቹ  ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችን ይመገባሉ።

74 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ምንም ዓይነት አትክልትና ፍራፍሬ እንደማይመገቡ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

በሶማሌ ክልል ዕድሜያቸው ከ6 ወር በላይ የሆኑ 91 በመቶ ህፃናት ምንም ዓይነት አትክልት እና ፍራፍሬ አያገኙም።

በአጠቃላይ በከተማ 50 በመቶ የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ6 ወር በላይ የሆኑ ህፃናት ለጤናቸው ተስማሚ ያልሆኑ ጣፋጭ መጠጦችን የሚወስዱ ሲሆን፤ በገጠር ከሚገኙት ደግሞ 23 በመቶዎቹ ይህን እንደሚጠቀሙ ተገልጿል።

እስከዳር ግርማ

ታኀሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ፋስት ፔይ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ውስጥ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ

ፋስት ፔይ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ የገንዘብ መላላኪያ ስርዓት ማስጀመሩን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል ።

የፋስት ፔይ ኢቲ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍፁም ተስፋዬ ፤ ይህ ስርዓት ቁጭት የፈጠረው ነው ብለዋል።

እሱም በውጪው አለም ተሰራጭተው የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ቀደም ገንዘብ ወደሃገር ውስጥ ለመላክ ከፍተኛ ችግር ይገጥማቸው ነበር ብለዋል።

ይህም አንድ ጊዜ ገንዘብ ለመላክ ከ5 እስከ 10 በመቶ ኮምሽን መቆረጥ፣በፈለጉበት ጊዜ መላክ አለመቻል፣ለገንዘብ ዝውውሩ ቀናት መፍጀት፣ከፍተኛ ሰልፍ ፣ ቴክኒካል ችግሮች ይገጥማቸው እንደ ነበር ጠቁመዋል።

አቶ ፍፁም ይህን መጉላላትና እንግልትን የስቀረ ፣ለገንዘብ ዝውውር ምንም አይነት ኮምሽን የማያስከፍልና በአንድ ደቂቃ ውስጥ ወደ ፈለጉት መላላክ እንዲችሉ የሚያደርግ መተግበሪያ ዛሬ አስጀምረናል ብለዋል።

ተጠቃሚዎች በፋስት ፔይ ኢቲ ሲጠቀሙ ከዕለቱ የባንኮች ምንዛሪ ከፍ ያለውን ማቅረቡ መተግበሪያውን ከሌሎች የመላላኪያ ዘዴዎች ልዩ ያደርገዋልም ተብሏል።

ማንኛው አካል ወይንም ተቋም ፤ለተቋማት ወይንም ለግለሰብ ድጋፍ ማድረግ ቢፈልጉ መተግበሪያውን በመጠቀም በቀላሉና በቀጥታ ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉም ብለውናል።

ፋስት ፔይ ኢቲአሁን ሀገሪቱ ውስጥ ካሉት 31 ባንኮች ጋር የተሳሰረ ሲኾን ይህም ተጠቃሚዎች ካሉበት ሀገር ኾነው ወደ የትኛውም የኢትዮጵያ ባንኮች በቀላሉ ሞባይልን በመጠቀም ገንዘብ ማስተላለፍ የሚችሉበት መተግበሪያ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ፋስት ፔይ ኢቲ/ FastpayEt በዩናይትድ ስቴት አሜሪካና በኢትዮጵያ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦና ፈቃድ አውጥቶ ወደሥራ የገባ የቴክኖሎጂ ተቋም መሆኑን ተነግረዋል፡፡

ልዑል ወልዴ

ታኀሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel