በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያውን ሰብሰባውን በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት አድርጓል ።
በኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የሚመራው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን ኢንጅነር ጌቱ ገረመው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት እንዲሁም አትሌት መሰረት ደፋር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት በማድረግ መርጧል ።
ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጨምሮም የተለያየ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን :-
ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ አቃቤ ንዋይና የአስተዳደር ፋይናንስ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
አቶ ቢኒያም ምሩፅ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ወይዘሮ ሳራ ሀሰን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሃብት አሰባሰብ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
አቶ አድማሱ ሳጂ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የስነምግባርና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ዶክተር ኢፍራህ መሀመድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የህክምናና ፀረ አበረታች ቅመሞች ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
አትሌት በላይነሽ ኦልጂራ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል
አትሌት የማነ ፀጋይ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በማድረግ ስብሰባውን አጠናቀዋል ።
ጋዲሳ መገርሳ
ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…ኢራን ግዙፍ የጦር ልምምድ ላካሂድ ነዉ አለች
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ኃይል በቀጣዮቹ ቀናት በአይነቱ እጅግ ግዙፍ የጦር ልምምድ ማካሄድ እንደሚጀምር አስታዉቋል፡፡
የጦሩ ማዕከላዊ አዛዥ ሜጀር ጀነራል ጎላም አሊ ራሺድ መጠነ ሰፊ የጦር ልምም ለማድረግ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡
የጦር ልምምዱ የኢራንን የማጥቃትና የመከላከል አቅም የሚያሳድግ መሆኑንም አስታዉቀዋል፡፡
የጦር ልምምዱ በባሕር በአየርና በምድር ኃይል እንደሚታገዘም ተናግረዋል፡፡
የዚህ ጦር ልምምድ አላማ የኢራንን ጠላቶች አደብ ለማስገዛት እንደሆነም ፕሬስ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ወርቅ ለማዉጣት በሚል ክፍት የሚተው ጉድጓዶች ችግር እንደሆነበት የጋምቤላ ክልል የማእድን ልማት ዘርፍ ቢሮ ገለፀ።
በክልሉ ወርቅ አምራች ባለሀብቶች ወርቅ ፍለጋ በሚል የሚያደርጓቸዉ ቁፋሮዎችን ካጠናቀቁ በኋላ ጉድጓዶቹ ክፍት ትተዋቸዉ እንደሚሄዱ ተገልፆል።
በወርቅ ማወጣት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ባለሀብቶች ጉድጓዶቹን የመድፈን ግዴታዎች ቢጣልባቸዉም እየተገበሩ አይደለም ተብሏል።
የጋምቤላ ክልል የማእድን ልማት የፍቃድ አሰጣጥ ዘርፍ ባለሙያ አቶ ሙት ሎንግ ይህንን ለማተገበር አሰገዳጅ ህግ ቢቀመጥም ለመቆጣጠር እንደተቸገሩ ለጣቢያችን ገልፀዋል።
ቁፋሮዎቹ በአብዛኛዉ የማይታይ እና ተቆጣጣሪ አካል በማይደርስባቸዉ አካባቢዎች ሲደረጉ ይህ ችግር በስፋት መስተዋሉን አቶ ሙት ሎንግ አንስተዋል።
በአዋጅ ደረጃ ጉድጓዶቹን አፈር የማልበስ እንዲሁም የወደሙ ችግኖችን መልሶ መትከልን የሚያስቀምጥ ቢሆንም በባለሀብቶቹ ዘንድ ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆን እየታየ ነዉ ብለዋል።
የወርቅ ሀብት ካለባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች መካከል አንዱ የጋምቤላ ክልል ሲሆን 180 የሚደርሱ ፈቃድ የወሰዱ ባለሀብቶች በወርቅ ምርት ማውጣት ስራ ላይ መሆናቸዉን ነግረዉናል።
በክልሉ ወርቅ እና ግራናት በስፋት የሚገኝበት እንደሆነ ያነሱት ባለሙያዉ በተጨማሪ አይረን÷ ኒኬል ማእድናት ይኖራሉ ተብለዉ እንደሚገመት ጥናት አመላክቷል ሲሉ ገልፀዋል።
ቁምነገር አየለ
ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ወደ ሩሲያ እየበረረ የነበረ አዉሮፕላን መከስከሱ ተነገረ
ከካዛኪስታንተንስቶ ወደ ሩሲያ ሲጓዝ የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን መከስከሱ ተሰምቷል፡፡
ንብረትነቱ የአዘርባጃን አየር መንድ የኾነ አውሮፕላን 67 መንገደኞችን እንደያዘ በካዛኪስታን ተከስክሷል፡፡
አክታኡ በተሰኘ አካባቢ በእሳት እየጋየ ነበር አውሮፕላኑ ወደ መሬት የተከሰከሰው፡፡
የአደጋዉ መንሥኤም አልተረጋገጠም፡፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ዩኒቨርሲቲው ለ5 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ለአምስት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማሪያም……. በስፔሻል ኒድስ ኤጁኬሽን
2. ዶ/ር አስራት ወርቁ ……………. በጂኦቴክኒክስ ኢንጂነሪንግ
3. ዶ/ር መኮንን እሸቴ ……………. በፕላስቲክ ሰርጀሪ
4. ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ ……………… በፐብሊክ ሄልዝ
5. ዶ/ር ተባረክ ልካ ………………. በዴቨሎፕመንት ጂኦግራፊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል።
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ የሶማሊያ መንግስት ያቀረበባትን ክስ መሰረተ ቢስ ስትል አጣጣለች
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኃይሎች በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ላይ ጥቃት አድርሰዋል በሚል ያቀረበዉን ክስ አጣጥሏል፡፡
ድርጊቱ የተፈፀመዉ ኢትዮጵያ ኃይሎች ሳሆን የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማበላሸት በሚፈልጉ ሶስተኛ ወገኖች የተፈጸመ ነዉ ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ መሰል ትንኮሳዎችና የሁለቱን አገራት ግንኙነት የሚያበላሹ ድርጊቶችን ለመከላከል ቁርጠና መሆኗንም አረጋግጣለች፡፡
የሶማሊያ መንግስት ባወጣው መግለጫ ዱሎው በተባለችው የጁባላንድ ከተማ የኢትዮጵያ ኃይሎች ጥቃት ፈፅመዋል ሲል መዉቀሱ የሚታወስ ነዉ፡፡
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሶማሊያ አቻቸው ጋር መከሩ
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሶማሊያ አቻቸው አብዱላሂ ሞሃመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
አምባሳደር ሬድዋን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ፥ ሁለቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ችግሮችን በጋራ በሚፈቱባቸው ጉዳዮችና፣ ባሏቸው እድሎች እና የቀጣይ ጉዟቸው መወያየታቸው ተነግሯል፡፡
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን አሳወቁ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ጋር ስለመወያየታቸው ተሰምቷል፡፡
የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር እና የአንካራውን ስምምነት መተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል ተብሏል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር ይገባልም ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጻል፡፡
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢን ክሊንተን ሆስፒል መግባታቸዉ ተነገረ
የ78 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ክሊንተን ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ሆስፒታል መግባታቸውን ቤተሰቦቻቸዉ ተናግረዋል፡፡
ክሊንተን ለገና በዓል ሁለት ቀናት ሲቀሩት ወደ ሆስፒታል መግባታቸው ወዳጆቻቸዉን አስደንግጧል፡፡
42ኛው ፕሬዝዳንት ክሊንተን ተደጋጋሚ የጤና እክሎች ሲገጥማቸው እንደነበር ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡
ቢል ክሊንተን እ. ኤ.አ ከ1993 እስከ 2001 ድረስ አሜሪካን መምራታቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
በሃገራችን 54 ሚሊየን ሄክታር መሬት የተጎሳቀለ መሆኑ ጥናት አመላከተ
በኢትዮጵያ 54.1 ሚሊየን ሄክታር መሬት የተጎሳቀለ መሆኑን እና ከዛ ውሰጥም 11 ሚሊየን ሄክታር ሄክታር መሬት እንዲያገገም መደረጉ ሰምተናል፡፡
ይህ የተገለጸው የህዘብ ተወካዮቸ ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባው የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለማጽደቅ በመከረበት ወቅት ነው፡፡
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዋጁ ዙሪያ ባደረገው ውይይት ላይ ሲሆን አዋጁን ለማጽደቀ በተደረገው ጥናት ሲሆን በዚሀም በሃገሪቱ 54 ሚሊየን የሚሆነው መሬት የተጎሳቆለ እንደሆነ ጣቢያች ሰምቷል፡፡
ታዲያ ከዚህ ውስጥ 11 ሚሊየን የሚሆነው እንደሚያገግም መደረጉን አንስተው የሃገሪቱ ደን ሽፋንም 23 በመቶ መድረሱ ተገልጧል፡፡
ምክር ቤቱም የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አዋጁን 1361/2017 አድረጎ እንዲጸድቅ ሆኗል፡፡
ለዓለም አሰፋ
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
ለሩስያ ወግነው ይዋጉ ነበር የተባሉ ከ1 ሺህ በላይ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች መሞታቸውን
ለሩስያ ወግነው ይዋጉ ነበር የተባሉ ከ1 ሺህ በላይ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች መሞታቸውን አልያም መቁሰላቸውን ደቡብ ኮሪያ አስታወቀች።
ከስለላ ድርጅቴ አገኘሁት ብላ ደቡብ ኮሪያ ዛሬ ባሰራጨችው መረጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰሜን ኮሪያውያን ወታደሮች በዩክሬይን ጦርነት ከሩስያ ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው።
የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት ባሰራጨው መግለጫ በታህሳስ ወር ብቻ 100 የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በውግያ ተገድለዋል።
በአጠቃላይ ደግሞ 1 ሺህ 100 የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሞተዋል አሊያም ቆስለዋል ነው የተባለው።
ደቡብ ኮሪያ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች፣ የሚሳይል ማስወንጨፊያዎችና መድፎች ለሩስያ እንደምታቀርብ የገለጸው የስለላ ድርጅቱ፤ ተጨማሪ እግረኛ ወታደሮችን ወደ ሩስያ ለመላክ ዕቅድ እንዳላትም አትቷል።
ሰሜን ኮሪያና ሩስያ በአለፈው ሰኔ ወር የጋራ ወታደራዊ ድጋፍ ስምምነት መፈራረማቸውን ይታወሳል ሲል የዘገበው አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ከሩስያ በኩል እስከአሁን የተባለ ነገር የለም።
ታኀሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
ቡካዩ ሳካ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ለበርካታ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አረጋግጠዋል።
እንግሊዛዊው ተጨዋች ቡካዩ ሳካ አርሰናል ክሪስታል ፓላስን ባሸነፈበት ጨዋታ በጡንቻ ጉዳት ምክንያት ተቀይሮ መውጣቱ አይዘነጋም።
ሳካ ያጋጠመው ጉዳት ጥሩ አይመስልም ከታሰበው የከፋ ሊሆንም ይችላል ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
የፊት መስመር ተጨዋች ራሂም ስተርሊንግ በበኩሉ በጉዳት ምክንያት በተመሳሳይ ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ሚኬል አርቴታ ጠቁመዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
ታኀሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ ቻምበር የቀድሞ ስሙን ለመመለስ መሰረታዊ ስር ነቀል ሪፎርም እያደረገ መሆኑን አስታወቀ
የአዲስአበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት |አዲስ ቻምበር/ የቀድሞ ስሙን ለመመለስ መሰረታዊ ስር ነቀል ታሪካዊ ሪፎርም እያደረገ መሆኑን አስታዉቆል
ምክር ቤቱ ባደረገዉ ጥልቅ ዉይይት ዘመኑን እና የንግድ ህብረተሰቡ የሚመጥን አለመሆኑን በኦዲት ምርመራ እንዲጣራ ዉሳኔ በማስተላለፉ በተጨባጭም የንግድ ማህበረሰቡን የሚመጥን ቁመና ላይ አለመሆኑን ለማረጋገጥ መቻሉን ገልፆል
የዳሬክተሮች ቦርድ ባካሄደዉ ስብሰባ የንግዱ ማህበረሰብ ሀብት ባክኖል ፡ ቦርዱ የማያዉቃቸዉ የዉጭ ጉዙዎችና የተጋነኑ የዉጭ ምንዛሬ ተስተዉሏል እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች በምክር ቤቱ ተፈፅመዋል በሚል በቀረቡ ሃያ ሶስት ጥቆማዎች ሳቢያ የኦዲት ኮሚቴ ከቦርዱ በማዋቀር የኦዲት ምርመራ እንዲካሄድ መወሰኑን ተናግሮል
በዚህም ተቆማዊ ሪፎርሙ የሚመሩ ከቦርዱ የተዉጣጡና በምክትል ፕሬዝዳንት የተመራ ሶስት የስቲሪንግ ኮሚቴ አባላት እና ከፅ/ቤቱ ከተዉጣጡ ዘጠኝ የለዉጥ አመራሮች ሪፎርሙን እዉን ማደረጉ ተገልፆል::
አቤል እስጢፋኖስ
ታኀሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ወደ አስመራ መጓዛቸዉ ተነገረ
የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ መግባታቸዉ ታዉቋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አስምራ ሲደርሱም በአገሪቱ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደርጎላቸዋል ተብሏል፡፡
መሪዎቹ በሁለቱ አገራት፤በቀቀጠናዉና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪይ እንደሚመክሩ ታዉቋል፡፡
ሶማሊያ ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ መላኳ የሚታወስ ነዉ፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ወደ አስመራ መጓዛቸዉ ተነገረ
የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ መግባታቸዉ ታዉቋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አስምራ ሲደርሱም በአገሪቱ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደርጎላቸዋል ተብሏል፡፡
መሪዎቹ በሁለቱ አገራት፤በቀቀጠናዉና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪይ እንደሚመክሩ ታዉቋል፡፡
ሶማሊያ ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ መላኳ የሚታወስ ነዉ፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
በሳዑዲ አረቢያ ከሚኖሩ 7መቶሺህ ኢትዮጵያዊያን መካከል 4መቶ50ሺዎቹ መደበኛ ያልሆኑ ናቸዉ ተባለ፡፡
ከ2017 እስከ 2023 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ከ5መቶ61ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸዉ መመለሳቸዉም ተገልጿል፡፡
93ሺህ 5መቶ የሚሆኑ ዜጎች በ2022 በግዴታ ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል ነዉ የተባለዉ፡፡
በ2023 ደግሞ 43ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በግዴታ ወደ አገራቸዉ መመለሳቸዉን ዘ ፍሪደም ፈንድ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት አስታዉቋል፡፡
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፤1መቶ33 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከሳዑዲ መመለሳቸዉን የገለጸ ሲሆን፤ 46 የሚሆኑት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ነበሩ ብሏል፡፡
ህጻናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ 6ሺህ ኢትዮጵያዊያንም ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታዉቋል፡፡
ከሱዳን ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ ወደ 47ሺህ 8መቶ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል ያለዉ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ከየመን ከ4ሺህ በላይ ዜጎቻችን ተመልሰዋል ብሏል፡፡
በሁለት ዙር በተደረገ ስራ 2መቶ80ሺህ ዜጎች ወደ አገር መመለሳቸዉንም ሰምተናል፡፡
እስከዳር ግርማ
ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
በደላንታ ወረዳ የማዕድን ቁፋሮ ተከለከለ።
በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በባህላዊ መንገድ የማዕድን ቁፋሮ እንዳይካሄድ ለማድረግ እውቅና መነሳቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል
የደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የማዕድን ስራዎች ፈቃድ መስጠትና ማስተዳደር ቡድን መሪ አቶ በሪሁን አበረ ፤ በዞኑ ወደ ሰላሳ የሚደርሱ የተለዩ ቦታዎች እንዳሉ አንስተው ከዚህ ቀደም አደጋ የተከሰተበት ቦታ እና ሌሎቹም ባላቸው ተፈጥሮዓዊ አቀማመጥ ምክንያት ስራ እንዲያቆሙ መደረጉን ነግረውናል።
የአካባቢው ማሕበረሰብ ከዚህ ቀደም ከተፈጠረው አደጋ እንዲማር እና ከዚህ ቀደም የተከሰቱ አስከፊ አደጋዎች አንዳይከሰት በማሰብ ቁፋሮውን አንዲያቆሙ ተደርጓል ብሏል፡፡
በወረዳው ያለው ህዝብ ኑሮውን መሰረት ያደረገው ያለምንም መሳሪያ በባህላዊ መንገድ በሚደረግ የኦፓል መአድን ማውጣት ነው የሚሉት ሃላፊው አሁንም ግን ያለቆሙ መኖራቸውን መረጃዎች እንደሚያመለክቱም ተናግረዋል፡፡
ቦታው በኦፓል በማዕደን የበለጸገ በመሆኑ በቅርቡ ማእድን ሚኒሰተር እና የወሎ ዩንቨርስቲ በጋራ በመሆን በዘመናዊ መንገድ የቁፋሮ ስራዎችን ለመሰራት መሰማማታቸውንም ገልጸዋል፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በተለምዶ ቆቅ ውሀ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት በቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸውን ሰዎች ህይወት አካል እስካሁን ድረስ ምንም ፍንጭ አለመገኘቱንም ሃላፊው ጨምረው ነግረውናል፡፡
ለአለም አሰፋ
ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ዓለምዓቀፍ ሽልማቶችን ያገኘዉ ዶቃ ፊልም ለመቄዶንያ እርዳታ ማሰባሰብ ሊዉል ነዉ፡፡
ዶቃ ፊልም ከዛሬ ጀምሮ በሰይፉ የዩቲዩብ ቻናል ላይ መተላለፍ ይጀምራል፡፡ ከዛሬ ታህሳስ 16 ጀምሮ እስከ የካቲት 1 ቀን ድረስ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
ከፊልሙ ዕይታ የሚገኘዉ ሙሉ ገቢም ለመቄዶንያ የአረጋዊያን እና ህጻናት መርጃ ማዕከል የሚዉል ነዉ፡፡
እስከዳር ግርማ
ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የታኅሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…በሶሪያ የገና ዛፍ ያቃጠሎ ግለሰቦችን ማሰሩን አዲሱ ኢስላማዊ ቡድን አስታዉቋል፡፡
በሶሪያ የገና ዛፍ መቃጠሉን ተከትሎ በተቃዉሞ ወደ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ፤ አዲሶቹ ኢስላማዊ ባለስልጣናት ጥቂት ቁጥር ያላቸዉ ዜጎችን ለመጠበቅ እርምጃ እንዲወሰዱ እየጠየቁ ነዉ፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀ አንድ ቪዲዮ ክርስቲያን የሶሪያ ዜጎች በብዛት በሚገኙበት አንድ መንደር ዋና አደባባይ ላይ የተተከለ የገና ዛፍ ፊታቸዉን በጭምብል በሸፈኑ ሰዎች ሲቃጠል ያሳያል፡፡
የቀድሞዉን ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድን ከስልጣን ያስወገደዉ አዲሱ ኢስላማዊ ቡድን ፤ ዛፉን በማቃጠል ተግባር የተሳተፉ ግለሰቦችን ማሰሩን አስታዉቋል፡፡
ቡድኑ፤ በሶሪያ የሚገኙ በሃይማኖት እና በብሄር ቁጥራቸዉ አናሳ የሆኑ ዜጎችን መብት እና ነጻነት ለማስጠበቅ ቃል መግባቱም ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ሁለት ፊታቸዉን በጭምብል የሸፈኑ ወንዶች በሶሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች ገናን ለማክበር በዋዜማዉ ያዘጋጁትን ዛፍ ሲያቃጥሉ አንድ በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኝ ቪዲዮ ያሳያል፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ በተለቀቀ ሌላ ቪዲዮ ደግሞ፤ የኢስላማዊ ቡድኑ አባል በቦታዉ የተሰበሰቡ ክርስቲያኖችን ዛፉ በድጋሚ ተሰርቶ ከጠዋት በፊት እንደሚደርስ ሲያግባባቸዉ እንደነበርም ይታያል፡፡
ይህን ጥቃት የፈጸሙት ሶሪያዊያን ሳይሆኑ ፤ ከዉጭ የመጡ ሃይሎች ናቸዉ ሲል ኢስላሚስት ቡድኑ መግለጫ መስጠቱን ተከትሎ፤
‹‹ሶሪያ ነጻ ናት ፤ ሶሪያዊያን ያልሆኑ አገራችንን ለቀዉ ይዉጡ››ሲሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወደ አደባባይ ለተቃዉሞ የወጡ ሶሪያዊያን ድምጻቸዉን አሰምተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልልን አጀንዳ መረከቡን አስታወቀ
ላለፉት 9 ቀናት በአዳማ ሲያካሄድ የቆየውን የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ማጠናቀቁን ኮሚሽኑ አስታዉቋል፡፡
ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ከአምስቱ ባለድርሻ አካላት የተመረጡ 25 ወኪሎች አጀንዳዎቹን አደራጅተው ለኮሚሽነሮች አስረክበዋል ብለዋል፡፡
የአጀንዳ አሰባሰብ ምዕራፉ ነፃና ግልጽ ሆኖ መጠናቀቁን ተናግረዋል።
ልዑል ወልዴ
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ውጤታማ በሆነ መልኩ ያስችላል የተባለውን የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ።
በምክር ቤቱ 12ኛ መደበኛ ስብሰባ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጆ አዋጁን የተመለከተ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል።
አዋጁ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤታማና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመምራት በልዩ ፈንድ እንዲደገፍ የሚያስችል መሆኑ ተጠቅሷል።
አቶ ደሳለኝ ባለፉት ስድስት ዓመታት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የተጎሳቆለ መሬት እንዲያገግም ከማድረግ አኳያ ጉልህ ሚና ማበርከቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በደን ዘርፍ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ምንጮች የምታገኘውን ጥቅም ለማሳደግ ከማስቻል ባለፈ መንግስት ለመርሐ ግብሩ ተገቢውን በጀት እንዲመድብ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የሱዳኑን ጦርነት ሸሽተዉ ወደ አገር ዉስጥ የገቡ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ከ58 ሺህ በላይ መድረሱ ተነገረ
ከተመላሽ ኢትዮጵያዉያን በተጨማሪም ከ84 ሺህ በላይ ሱዳናዉያን መግባታቸዉንም የምዕራብ ጎንደር ዞን ለጣቢያችን አስታዉቋል
ዞኑ በፀጥታ ችግር ምክንያት የሰባዓዊ እርዳታ አቅርቦቱ መስተጓጎሉንም ተናግሯል፡፡
በምእራብ ጎንደር ዞን የአደጋ መከላከልና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ኃላፊ አቶ ዘላለም አበበ አሁንም ድረስ በየቀኑ ከሱዳን የሚገቡ ዜጎች እየገቡ ነዉ ብለዋል፡፡
በሁለቱ የሱዳን ጀነራሎች መከከል የተለኮሰዉን ጦርነት በመሸሽ ከ58 ሺ በላይ ኢትዮጵያዉያንና ከ84ሺህ በላይ ሱዳናዉያን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸዉንም ነግረ ዉናል፡፡
ሱዳናዉያንና የሶስተኛ ወገን ስደተኛ ዜጎችን የሚያስተዳደሩት የአለም አቀፍ ድርጅቶች መሆናቸዉን የሚናገሩት አቶ ዘላለም ተና ግረዋል፡፡
ነገር ግን ለተመላሽ ኢትዮጵያዉያን የሚደረገዉ ድጋፍ በመቆሙ ችግር እንደፈጠረባቸዉ አስታዉቀዋል፡፡
በሱዳን ካለዉ ግጭት በተጨማሪም በአካባቢ በተከሰተዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት የዞኑ ነዋሪዎች ከፍተኛ ችግር ዉስጥ እንደሚገኙ ሰምተናል፡፡
አብዛኞቹ ስደተኞችና ተመላሽ ኢትዮጵያዉያን ወደተለያዩ አካባቢዎች ቢሄዱም ነገር ግን ከ23ሺህ በላ የሚሆኑት አሁንም በመጠለያ ዉስጥ ናቸዉ ተብሏል፡፡
በመኆኑም የሚመለከታቸዉ አካላት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የሱዳኑን ጦርነት በመሸሽ አጠቀላይ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዜጎች ቁጥር ከ160 ሺህ በላይ መሆናቸዉንም ጣቢያችን ሰምቷል፡፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
አሜሪካ ዜጎቿ ከቤላሩስ በአስቸኳይ እንዲወጡ አዘዘች
በምስራቅ አዉሮፓዊቷ አገር ቤላሩስ የሚኖሩ የአሜሪካ ዜጎች አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል፡፡
የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣወ መግለጫ በቤለሩስ ያለዉ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አስጊ በመሆኑ ዉሳኔዉ ተላልፏል ብሏል፡፡
በተጨማሪም ወደ ቤላሩስ የሚደረግን ጉዞ የአሜሪካ መንግስት ክልከላ አድርጓል፡፡
በቤላሩስ የሚገኙ ዜጎች እንዲወጡ ትዕዛዝ ከመስጠቱ ባለፈ በየትኛዉም ቦታዎች ላይ እንዳይሰባሰቡ አስጠንቅቋል፡፡
አሜሪካ ይህን ዉሳኔ የወሰነችዉ ህዝባዊ አመፅ በሚኒስክ ይቀሰቀሳል በሚል ፍራቻ መሆኑን አርቲ ዘግቧል፡፡
ዋሽንግተን የፕሬዝዳንት አሌግዛንደር ሉኬሼንኮ መንግስት አምባገነን ነዉ በሚል ከ2 ዓመት በፊት ማዕቀብ መጣሏ የሚታወስ ነዉ፡፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት 12ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባው የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ ይሆናል ተብሏል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡
ታኀሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
በሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልዑክ ወደ አትዮጵያ እንደሚመጣ ተሰማ
በውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር አሊ ኦማር የተመራ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ የሶማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ይህ ጉብኝት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን ይህም በሁለቱም ሀገራት መሪዎች በተፈጠረው የአንካራ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
የልዑካን ቡድኑ በጋራ በመከባበር፣ በጋራ ጥቅም እና በትብብር ላይ የተመሰረተ አጋርነት ለመፍጠር የለውጥ ዕድሎችን በማሰስ ላይ ያተኩራል።
ታኀሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ዕድሜያቸው ለስራ ካልደረሱ ህፃናት አንድ አራተኛ የሚሆኑት በአማካይ 70 ሰዓት ይሰራሉ ተባለ።
በአዲስ አበባ 11 ሺህ የሚሆኑ ህፃናት በቤት ሰራተኝነት ስራ ውስጥ ይገኛሉም ተብሏል።
የእነዚህ ህፃናት የመቀጠሪያ አማካይ ዕድሜ 13 ዓመት መሆኑም ተገልጿል።
ዘ ፍሪደም ፈንድ የተባለ ዓለምአቀፍ የግብረሰናይ ድርጅት በመዲናዋ አምስት ክፍለከተሞች አደረግኩት ባለው ጥናት 11 ሺህ የሚሆኑ ህፃናት በቤት ሰራተኝነት እየሰሩ ይገኛሉ።
ለእነዚህ ልጆች የሚከፈለው በአማካይ 1ሺህ1መቶ17 ብር መሆኑንም ድርጅቱ ባደረግኩት ጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል።
ህጋዊ የመቀጠሪያ ዕድሜ 18 ዓመት በመሆኑ ብዙዎች ዕድሜያቸውን እየዋሹ እንደሚቀጠሩም በጥናቱ ይፋ ተደርጓል።
እነዚህ ልጆች በአማካይ በሳምንት 55 ሰዓት የሚሰሩ ሲሆን፤ ከጠቅላላዎቹ አንድ አራተኛ የሚሆኑት ደግሞ ከ70 ሰዓት በላይ ይሰራሉ ተብሏል።
40 በመቶ የሚሆኑት ምንም ዓይነት የዕረፍት ቀን እንደሌላቸውም ተገልጿል።
ምንም ዓይነት ክፍያ ከማይከፈላቸው እስከ 3 ሺህ ብር የሚከፈላቸው ህፃናት መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን፤ 27 በመቶዎቹ ብቻ ህጋዊ ስምምነት ያላቸው ናቸው።
ክፍያ ከሚያገኙ ህፃናት 68 በመቶ የሚሆኑት በቀጥታ ክፍያቸውን የሚያገኙ ሲሆን፤ 27 በመቶ የሚሆኑት ክፍያቸው ተቀንሶ አልያም ዘግይቶ የሚከፈላቸው ናቸው።
5 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ገንዘባቸው ቀጥታ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚላክ በጥናቱ ለማየት ተችሏል።
52 በመቶ የሚሆኑት ለህገወጥ የሰዎች ንግድ የተጋለጡ መሆናቸውም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የስራ ድንጋጌ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ምንም አይነት ስራ እንዳይሰሩ ፣ ከ15-17 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ደግሞ የምሽት የስራ ሰዓት ሳይኖር ለተወሰነ ሰዓት ብቻ እንዲሰሩ ይደነግጋል።
ነገርግን ዕድሜያቸው ከ12-14 ከሆኑ ህፃናት ሁሉም የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ተጠቂ ሲሆኑ፤ ከ15-17 ዓመት ክልል ውስጥ ከሚገኙት 87 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ረዥም ሰዓት በመስራት ለህገወጥ የጉልበት ብዝበዛ የተጋለጡ ናቸው ተብሏል።
እስከዳር ግርማ
ታኀሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም