በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
የነገ የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከ9መቶ ጊዜ በላይ ጥሳለች ሲል የጋዛ መንግስት ከሰሰ፡፡
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ከጥር 19 ጀምሮ እስራኤል ስምምነቱን ከ9መቶ ጊዜ በላይ ጥሳለች ሲል አስታዉቋል፡፡
ስምምነቱ ተግባራዊ በሆነበት ወቅት እንኳን በተለያዩ የፍልስጤም ግዛቶች ዉስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማዊያን በእስራኤል ጥቃት ህይወታቸዉ እንዲያልፍ እና ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸዉ ሆኗል ነዉ ያለዉ፡፡
ጥቃቱ የአየር እና የከባድ መሳሪያ ድብደባ፣ የሰብዓዊ ድጋፎች እንዳይገቡ ማድረግ፣ በዜጎች ላይ ተኩስ መክፈት ፣ ቤቶችን እና መኪኖችን ማቃጠልን ያካተተ ነበር ሲል አስታዉቋል፡፡
በተጨማሪም ወደ ጋዛ ነዳጅ እንዳይገባ በማድረግ እና ከ2መቶ60 ሺህ በላይ ድንኳኖች እና መጠለያዎች እንዳይደርሱ በማድረግ ጭምር የተደረገ ነዉ ብሎታል፡፡
የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ እና አሸማጋዮች እስራኤል ጥቃት ማድረሷን እንድታቆም እና በተኩስ አቁም ስምምነቱ መሰረት የገባችዉን ሃላፊነት እንድትወጣ ጫና እንዲያደርጉባት ጠይቋል፡፡
የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር፤ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ በእስራኤል ጥቃት ህይወታቸዉ ያለፉ ፍልስጤማዊያን ቁጥር 1መቶ16 ደርሷል፤ የተጎጂዎች ቁጥር ደግሞ ከ4መቶ90 በላይ ሆኗል ሲል አስታዉቋል ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
አቢሲኒያ ባንክ የሴቶች የተሰጥኦ እና የስራ ፈጠራ ውድድር አዘጋጅቻለሁ አለ
አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን(ማርች 8) ምክንያት በማድረግ "እችላለሁ" በሚል መሪ ቃል ለ4ተኛ ጊዜ የሴቶች የተሰጥኦ እና የስራ ፈጠራ ውድድር መጀመሩን ባንኩ አስታውቋል ።
ውድድሩ ከየካቲት 24 እስከ መጋቢት 8 እንደሚቆይ ተነግሯል።
መርሐ ግብሩ በሙዚቃ (በድምጽ)፣ በቲክቶክ ቪዲዮ እና በሥራ ፈጠራ ውድድሮች ላይ ተሰጥዖ ያላቸው ሴቶች እንዲሳተፉ የሚጋብዝ መሆኑን ሰምተናል።
በሙዚቃ (በድምጽ) እና በአጭር የቲክቶክ ቪዲዮ አሸናፊ ሆነው ከ1ኛ-3ኛ ለሚወጡ እንስቶች ከብር 50,000 - 100,000 የሚደርስ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተነግሯል።
እንዲሁም በሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ ለሚሆኑ 50 ሴቶች ለሥራ ማስፋፊያ የሚሆን በአነስተኛ የወለድ ምጣኔ ካለመያዣ እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት እንደሚዘጋጅላቸው ተጠቅሷል።
ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ሥራ በባለሙያና በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የሕዝብ ድምጽ ተለይቶ አሸናፊዎች የሚለዩ መሆኑ ተነስቷል።
ለመወዳደሪያ የሚቀርቡ ነገሮች ይዘታቸው ሴቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው ተብሏል።
በሥራ ፈጠራ፣ በድምፅ እንዲሁም በቲክ ቶክ አጭር ቪዲዮ ተሰጥዖ ያላቸውን እንስቶች አወዳድሮ የሚሸልም መሆኑ ሴቶች ያላቸውን ተሰጥዖ እንዲያጎለብቱና ለሕዝብ በተሻለ እንዲደርሱ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።
ሐመረ ፍሬው
የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
በጋምቤላ ክልል ከ 10 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ ተባለ።
በክልሉ ባለፉት ሁለት አመታት በተፈጠረ ግጭት በሶስት ወረዳዎች ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸዉ መፈናቀላቸዉ ተነግሮናል።
በክልሉ ተከስቶ በነበረዉ ከፍተኛ ግጭት እና አለመረጋጋት ምክንያት በተለይ በጆር÷ ኢታንግ÷ አኮቦ ወረዳዎች ላይ 10 ሺህ 333 ሰዎች ተፈናቅለዋል።
በጋምቤላ ክልል የኑዌር እና አኝዋክ ብሄረሰቦች በሚገኙበት ኢታንግ ልዩ ወረዳ በባለፉት ሁለት አመታት ግጭት የ አስር ቀበሌ ነዋሪዎች ቅያቸውን ጥለዉ መሸሻቸዉ ተገልፆል።
ከኢትዩ ኤፍኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር አገልግሎት ዳይሬክተር ጃክ ጆይ በነባር ብሄረሰቦቹ መካከል መነሻ ሆኖ በነበረዉ ግጭት በዚህ ወረዳ ብቻ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት ሰዎች ተፈናቅለዉበታል ብለዋል።
በተጨማሪም ከዚህ ዉስጥ በጆር እና አኮቦ ወረዳ ዉስጥ በነበሩ 8 ቀበሌ ዎች ከ 5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃይ ነዋሪዎች አሉ ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በኢታንግ ልዩ ወረዳ ላይ በተወሰኑ ነዋሪዎች መካከል የተነሳዉ አለመግባባት ብሄርን መሰረት አድርጎ ወደ ዉጥረት መሸጋገሩን ኮምሽኑ ከነዋሪዎች መስማቱን በወቅቱ ገልፆ ነበር።
አቶ ጃክ በጋምቤላ ክልል የአመራር ለዉጡን ተከትሎ ሁለቱ ብሄረሰቦችን ዉይይት እንዲያደርጉ እና ተፈናቃዩችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
በሶስቱ ወረዳዎች የተፈናቀሉ አብዛኞቹ የአኝዋክ ብሄረሰቦች በመሆናቸዉ ወደ ቀያቸዉ እንዲመለሱ ከስምምነት መደረሱን ዳይሬክተሩ ለጣቢያችን ገልፀዋል።
ተፈናቃዮቹ አሁን ላይ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ባለ መጠለያ የሚገኙ ሲሆን የተቃጠሉ ቤቶቻቸዉን መገንባት እና መልሶ ማቋቋም እንዲቻል ለማድረግ ስራ መጀመሩን አቶ ጃክ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ጣቢያችን አነጋግሯቸዉ የነበረዉ የጋምቤላ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ሀላፊዉ አቶ ማበር ኮር አሁን ላይ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ስለመገኘቱ ነግረዉናል።
ቁምነገር አየለ
የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
ማንችስተር ዩናይትድ ከኤፌ ካፕ ውድድር በፉልሀም ተሰናበተ !
ፉልሀም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የኤፌ ካፕ አምስተኛ ዙር ጨዋታ በመለያ ምት 4ለ3 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።
ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
ግቦችን ለማንችስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እንዲሁም ለፉልሀም ካልቪን ባሴይ ማስቆጠር ችለዋል።
በመለያ ምት በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ቪክቶር ሊንድሎፍ እና ዚርኪዜ ሳይጠቀሙ ቀርተዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ነው።
በዓሉ "ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል" በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።
በበዓሉ አከባበር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር)፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ተገኝተዋል፡፡
በበዓሉ ላይ ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ ሌሎች የጸጥታ ሃይሎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መታደማቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል።
የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የትራምፕ እና የዜለንስኪ የዋይት ሐውስ ውይይት ወደ ኃይለ ቃል ልውውጥ ተቀየረ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋራ በዋይት ሐውስ ያደረጉት እና አሜሪካ ከዩክሬን ልዩ ማዕድናት ማግኘት የሚያስችላት ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለመችበት ውይይት ወደ ተጋጋለ ኃይለ ቃል ተቀይሮ፤ ትራምፕ "ስምምነት ላይ ትደርሳለህ አለዛ እኛ እንወጣለን" ሲሉ ለዜለንስኪን ነግረዋቸዋል።
ስብሰባውን ተከትሎ ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክትም "ስምምነቱ ተዘርዟል" ሲሉ አስታውቀዋል።
ትራምፕ በጹሑፋቸው "የአሜሪካ ተሳትፎ የሚቀጥል ከኾነ ፕሬዝደንት ዜለንስኪ ለሰላም ዝግጁ እንደማይሆን ወስኛለሁ። ምክንያቱም የኛ ተሳትፎ ለድርድር ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጠው ያምናል" ሲሉ ገልጸዋል።
"ዩናይትድ ስቴትስን እና የፕሬዝደንቱን ኦቫል ኦፊስ' አላከበረም።ለሰላም ዝግጁ ሲኾን መመለስ ይችላል" ብለዋል ፕሬዝደንቱ።
“ኦቫል ኦፊስ” በተሰኘው የፕሬዝደንቱ ጽሕፈት ቤት ውስጥ በርካታ አሜሪካውያን እና ዩክሬናውያን ጋዜጠኞች የተከታተሉት የተጋጋለ የቃላት ልውውጥ ወደ ኃይለ ቃል የተለወጠው ወደ 40ኛው ደቂቃ አካባቢ ዘለንስኪ ሩሲያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም ክሬሚያን መውረሯን ባነሱበት ወቅት ነው።
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ጄዲ ቫንስ ወዲያውኑ ዜለንስኪን "የፕሮፓጋንዳ" ወሬዎችን መጠቀሚያ በማድረግ ተችተዋቸዋል።
ቫንስ "ኦቫል ኦፊስ ውስጥ ኾኖ በአሜሪካ ሚዲያ ፊት ይህን ዐይነት ክስ ማንሳት ንቀት ነው" ነው ሲሉ ዜለንስኪን ተናግረዋቸዋል።
ቫንስ እና ትራምፕ የዩክሬኑ መሪ ዋሽንግተን ለሀገራቸው ላደረገቸው ርዳታ አመስጋኝ አለመኾናቸውን ገልፀውም ወቅሰዋቸዋል።
ዜለንስኪ ምላሽ ለመስጠት ቢሞክሩም ትራምፕ "ለመደራደሪያ የሚሆን አቅም እና ሥልጣን የለህም" በማለት አቋርጠዋቸው "በሚሊየን በሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ቁማር ትጫወታለህ። ከሦስተኛ ዓለም ጦርነት ጋራ ቁማር እየተጫወትክ ነው" ብለዋቸዋል።
ዜለንስኪ በታቀደው መሠረት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሳይሳተፉ ቀደም ብለው ከዋይት ሐውስ ወጥተዋል።
ውይይቱ በድንገት ከተጠናቀቀ በኋላ የዩክሬኑ መሪ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለአሜሪካ ሕዝብና መንግሥት መልዕት አስፍረዋል።
ኤክስ በተሰኘው የማኅበራዊ ገጽ ላይ "አመሰግናለኹ አሜሪካ" ሲሉ የጻፉት ዜለንስኪ፣ " የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት፣ የምክር ቤት አባላትንና የአሜሪካን ሕዝብ እናመሰግናለን።
ዩክሬን ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም ትፈልጋለች ፣ ያንን ለማግኘትም በሚገባ እየሠራን ነው" ብለዋል ሲል VOA ዘግቧል።
የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም
ረመዳን ሙባረክ🌙
የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ ነገ ቅዳሜ የረመዳን የመጀመሪያው ቀን ይሆናል።
ዛሬ የተራዊህ ሶላት የሚጀመር ሲሆን ነገ የረመዷን ጾም ይጀምራል።
የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
ትግራይ ክልል በ6 ወራት ዉስጥ ከቀረበልኝ 29 አቤቱታዎች 24ቱን መመልስ ችያለዉ ብሏል የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፡፡
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የመቀለ ቅርንጫፍ የጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ፀሀይ አምባዬ እንደተናገሩት ክልሉ በ2017 በጀት ዓመት 6 ዘር አፈፃፀም ተቋሙን የሚመለከት 29 አቤቱታወች መካከል 24 የሚሆነዉን መመለስቸዉንና 5 በሂደት ላይ እንደሉ ተናግረዋል።
ከቀረቡት የአቤቱታ መዝገቦች ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃውን የሚይዙት የሥራ ማጣት፣ ከሥራ መባረር እንዲሁም ቅጥርን የሚመለከቱ አቤቱታዎች ሲሆኑ፤ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ "አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም" የሚሉ አቤቱታዎች መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።
አሁንም ከተማዉ በሁለት ከንቲባ በመከፈሎ ምክንያት ህዝቡ መልስ የሚሰጠዉ አካል እያጠ እንደመጣ ተናግረዋል።
ሌሎች አቤቱታዎች የመሬት ይዞታና የጡረታ መብትን የሚጠይቁ መሆናቸውንና በተለይም በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችና ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በርካታ ቅሬታ እንዳላቸው መስተዋሉን ተናግረዋል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ዉስጥ 10 ከመቶ የሚሆነዉ ህዝብ ብቻ ነዉ የኤሌክትሪክ ሃይል በመጠቀም ምግብ የሚያበስለዉ ሲል የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬም ምግቡን የሚያዘጋጀዉ የማገዶ ቁሶችን በመጠቀም ነዉ ተብሏል ፡፡
ይህ የተገለፀዉ የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ሶላር ኢነርጅ ልማት እና ከኢትዮጵያ ጀርመን የኢነርጅ ትብብር ጋር በጋራ የሶላር ሃይል ቴክኖሎጂ የምክክር መድረክና ኤግዚቢሽን በተከፈተበት ጊዜ ነዉ፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የዉሃ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጅነር ሱልጣን ዋሌ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ቢኖራትም መጠቀም አልተቻለም ብለዋል
በዚህም የዉሃ እና ኢነርጅ ሚኒስተር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ ገልፀዉ ለአብነት ከአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ ከ 2 መቶ ሜጋ ዋት በላይ የሶላር ሃይል በኢትዮ ሱማሌ ክልል ማመንጨት እንደተቻለ ጠቅሰዋል ፡፡
መንግስት ያለውን ክፍተት ሙሉ ለሙሉ መሸፈን ስለማይችል የሃይል አቅርቦቱን ዘርፍ ለግሉ ባለሀብት ክፍት አድርጎታል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታዉ ተናግረዋል ፡፡
ለግሉ ባለሀብት የተሰጠዉን እድል ኢንቨስተሮች ሊጠቀሙበት እንደሚገባ በምክክር መድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
አቤል እስጤፋኖስ
የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አዲስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾመ
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የዳይሬክተሮች ቦርድ አቶ መርጊያ ባይሳን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾሟል።
አቶ መርጊያ በተቋሙ ውስጥ ከምስረታው ጀምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን፣ ለሰባት ዓመታትም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደነበሩ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ቦርዱ ወ/ሪት ቅድስት ስጦታውን በገበያና ግብይት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ እንዲሁም አቶ ታምራት ተሰማን በመጋዘንና ጥራት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾሟል ሲል ካፒታል ዘግቧል።
የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ባሳለፍነው ዕሁድ በተከናወነው 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሁም በፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በተላለፉ ወሳኔዎች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የአክሲዮን ማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ የኢትዮጵያን እግርኳስ ለማሳደግ እንደ አንድ አውራ ባለድርሻ አካል ከሁለት ዓመት በፊት ጥናት ከማስጠናት ጀምሮ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን እስከ ማምጣት ድረስ የተሰራውን ስራ አውስተው ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለማስተካከል ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና ክለቦች ጋር በመሆን የተዘጋጀውን የመቆጣጠሪያ ደንብ እንዴት ወደ ስራ እንደመጣ አብራርተዋል።
በቅድሚያም ከሊጉ ክለቦች የመጣውን የ6 ክለቦች እና የ25 ተጫዋቾች ጥቆማ ሲመረምር የቆየው ኮሚቴው ከፌዴራል ፖሊስ እና ከብሔራዊ የመረጃ እና መረብ ደህንነት ጋር በመሆን ሰፊ ማጣራት በማድረግ 4 ክለቦች እና 15 ተጫዋቾች ላይ ውሳኔ የተወሰነበትን እያንዳንዱ ሂደት ለጋዜጠኞች አብራርተዋል።
በመቀጠል መድረኩን የተረከቡት የአክሲዮን ማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የወጣውን ህግ ለማስፈፀም ተቋማቸው ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀው ከደንብ አወጣጡ ጀምሮ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ላሳያቸው ተመሳሳይ አቋም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሰብሳቢው አክለውም አሁን ከወጣው ውሳኔ ውጪ የሁሉም ክለቦች የዝውውር እንቅስቃሴ ማጣራት እየተደረገበት እንደሆነ አመላክተዋል።
አክስዮን ማህበሩ እንዳሳወቀው “ የተጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት አንከፍልም የሚሉ ክለቦች ከፕርሚየር ሊጉ ይሰናበታሉ “ ሲል አረጋግጧል።
እንዲሁም “ የተቀጡ ተጨዋቾችም ውሳኔውን አልፈፅምም ካሉ እስከመጨረሻው በየትኛውም ክለብ አይጫወቱም “ ሲል ነው አክስዮን ማህበሩ ያሳወቀው።
ቅጣት የተላለፈባቸው አካላት " ይገባኝ “ የማለት መብት አላቸው ብሏል ማህበሩ ።
እየተደረገ ባለው የምርመራ ሂደት ሶስት ጋዜጠኞች ስማቸው መገኘቱን አቶ ክፍሌ ገልፀዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የብልሹ አሰራር እና የሙስና ጥቆማ መስጫ ዲጂታል የሞባይል መተግበሪያ ስራ ላይ አዋለ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ በሚፈጠሩ የብልሹ አስራር እና የሙስና ችግሮች ላይ ደንበኞች የሚኖራቸውን ቅሬታ እንዲሁም አስተያየትና ጥቆማ በቀላሉ እንዲያቀርቡ የሚያስችል ዘመናዊ የሞባይል መተግበሪያ አገልግሎት ላይ ማዋሉን አስታውቋል።
ዲጂታል መተግበሪያው ደንበኞች በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ብልሹ አሰራር እና ተግባር ሲያጋጥማቸው በየትኛውም ቦታ ላይ ሆነው በእጅ ስልካቸው ጥቆማ የሚያቀርቡበት ቴክኖሎጂ ነው ተብሏል።
መተግበሪያው ደንበኞች በሚያመቻቸው አማራጮች ቅሬታቸውን እንዲያቀርቡ የቴሌግራም ቦት እና ድረ ገጽ የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉም አማራጮች የደንበኛው ማንነት ሚስጢራዊነቱ ተጠብቆ መገልገል የሚችሉበት መሆኑ ተገልጿል።
ደንበኞች የግል ስልክ ወይም ላፕቶፕ በመጠቀም ጎግል ላይ "eeuethics.et" ብለው በመግባት መተግበሪያውን በመክፈት የሚፈለጉ መረጃዎችን በተዘጋጀው ቅጽ መሰረት በጥንቃቄ ትክክለኛ መረጃዎችን መሙላት እንደሚጠበቅ ተነስቷል።
መተግበሪያው አማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን በመጠቀም ደንበኞች ጥቆማዎችን እንዲያቀርቡ የሚያስችል ሲሆን፣ በቀጣይ ሌሎች ቋንቋዎችን በማካተት አገልግሎቱን ለማስፋት ይሰራል ስለመባሉም ሰምተናል።
ሀመር ፍሬው
የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ሰሜን ኮሪያ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ሩሲያ መላኳን ደቡብ ኮሪያ አስታወቀች።
የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ጦር ግንባር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባት በኋላ ፤ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ሩሲያ እንደላከች የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ፒዮንግያንግ ወታደሮቿን በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ ወደ ሩሲያ የጦር ግንባር ወደ ሆነችዉ ኩርስክ ግዛት አሰማርታለች።
የደቡብ ኮሪያ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎት ፒዮንግያንግ በዚኛዉ ምንያክል መጠን ወታደሮችን በድጋሚ እንደላከች እያጣራ መሆኑን ብሔራዊዉ ‹ ዮንሃፕ የዜና› አገልግሎት ዘግቧል።
የሞስኮን ወረራ ለማጠናከር ፒዮንግያንግ ባለፈው አመት ወደ 11ሺህ የሚጠጉ ወታደሮችን መላኳንም ብሔራዊዉ የመረጃ አገልግሎት አስታዉቋል።
የጦር ተንታኞች እንደገለጹት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከሩሲያ ከፍተኛ የጦር ሃላፊዎች ጋር መገናኘት ባለመቻላቸውና ባላቸዉ አነስተኛ የዉጊያ ልምድ የተነሳ፤ በዩክሬን ድሮኖች እና የመድፍ ጥቃቶች በቀላሉ ኢላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
የብሔራዊ የመረጃ አገልግሎቱ እንዳመላከተዉ በጥር ወር፤ 300 የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሲገደሉ ፤2ሺህ 700 ቆስለዋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በበኩላቸዉ፤በዉጊያዉ ወቅት የሞቱ ወይንም የቆሰሉ የሰሜን ኮሪያውያን ቁጥር ከ4ሺህ ሊበልጥ እንደሚችልም ጠቁመዋል።
ሞስኮኖ እና ፕዮንጊያንግ በህዳር ወር የጋራ መከላከያ ስምምነት ማድረጋቸዉ የሚታወስ ነዉ ዘገባዉ የአልጄዚራ ነዉ፡፡
ልኡል ወልዴ
የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ኢራን ያልሄደው የሚደርስበትን ግርፋት ለመሸሽ ነው ተባለ።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዛሬ ከአል ናስር ጋር ወደ ኢራን ያልሄደውም የሚደርስበትን ግርፋት ለመሸሽ ስለመሆኑ ተነግሯል ::
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሁለት አመታት በፊት ወደ ኢራን ሄዶ ባጠፋው ጥፋት ምክንያት ድጋሜ ወደ ኢራን ከሄደ 99 ጊዜ ግርፋት እንደሚፈረድበት እየተዘገበ ይገኛል :
ነገሩ እንዲህ ነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከ2 አመታት በፊት ወደ ኢራን በሄደበት ወቅት አንዲት አካል ጉዳተኛ የሆነች እንስት በእግሯ ሮናልዶን በመሳል ውብ ምስል በስጦታ ታቀርብለታለች።
በዚህ የተደሰተው ሮናልዶም የፈረመበትን 7 ቁጥር ማልያውን በስጦታ ካበረከተላት በኃላ አቅፎ ጉንጯን ይስማታል።ታዲያ በኢራን ህግ ሚስቱ ያለሆነች ሴትን ጉንጯንም ቢሆን የሳመ ሰው እስራት እና 99 ጊዜ ግርፋት ይፈፅምበታል።
ይህ ህግ እንዳይፈፅምበት የፈራው ሮናልዶም ክለቡ አልናስር ወደ ኢራን ሲጓዝ መቅረትን መርጧል።
የክለቡ አሰልጣኝ ሮናልዶ ወደ ኢራን ያልተጓዘው በአካል ብቃት ችግር ነው ቢሉም እውነታው ግን ይህ እነደሆነ እየተዘገበ ነው።
የ40አመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣይ መጋቢት 7 በሳውዲ ፕሮ ሊግ አል ናስር ከ አልሸባብ ጋር ሲጫወት ወደ ሜዳ ይመለሳል ሲል Goal Sport ዘግቧል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ 18 በመቶ የሚሆኑ ዕድሜያቸዉ 5 አመት እና ከዛ በላይ የሆኑ ልጆች ለመስማት ችግር የተጋለጡ ናቸዉ ተባለ፡፡
ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ደግሞ የመጋለጥ ዕድላቸዉ 7 በመቶ ነዉ ተብሏል፡፡
በፈረንጆቹ 2023 በኢትዮጵያ የተደረገ በመስማት ችግር ተጋላጭነት ላይ ያተኮረ የዳሰሳ ጥናት፤ በኢትዮጵያ የመስማት ችግርን ለመቅረፍ መወሰድ ያለባቸዉ አፋጣኝ እርምጃዎች መኖራቸዉን ይጠቁማል፡፡
ቅድመ መከላከል፣ ቅድመ ልየታ ፣ የማገገሚያ ማዕከላት ችግሩን ለመከላከል መወሰድ ያለባቸዉ እርምጃዎች መሆናቸዉም በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገራት የሚኖሩ ዜጎች በተፈጥሮም ይሁን በሰዉ ሰራሽ ምክንያቶች ለመስማት ችግር የተጋለጡ መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡
በዚህ ችግር በአብዛኛዉ ተጠቂ የሆኑት ደግሞ ህፃናት ናቸዉ ተብሏል፡፡
የጆሮ ህመምን ለማከም፣ ቀድሞ ችግሩን ለመለየትና መፍትሄ ለማድረግ የሚያስችል የተሟላ የህክምና ተቋማት አለመኖር ሁኔታዉን ፈታኝ አድርጎታል ነዉ የተባለዉ፡፡
የዓለም የመስማት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ በአገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ 7ኛ ጊዜ ‹‹ለጆሮና ለማዳመጥ አቅም ጥንቃቄ ለማድረግ ራስን በዕዉቀት ማጎልበት ዕዉን ይሁን›› በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
ኢስት አፍሪካ የመስማት ድጋፍ ማዕከል የመስማት ችግርን ለመቅረፍ የሚያግዙ መሳሪያዎችን አምራች እና አቅራቢ ከሆነዉ ሜዴል ካምፓኒ ጋር በመተባበር ቀኑን አክብሯል፡፡
ማዕከሉ ከምስረታዉ 2002 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 15 ዓመታት መስማት ለተሳናቸዉ ዜጎች የተለያዩ አጋዥ መሳሪያዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
ከ1 ሺህ 5 መቶ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች የስራ ዕድል ፈጥሪያለሁ ሲል የአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ።
በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የሴቶች ተሳትፎ ማብቃትና ተጠቃሚነት ዳይሬክተር ወ/ሮ ስፍራሽ አልባው፤ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በከተማዋ ውስጥ በችግር ላይ ወድቀው ለነበሩ ለ1ሺህ 5መቶ77 ሴቶች የስራ እድል መፍጠራቸውን ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ወ/ሮ ስፍራሽ ቢሮዉ በዋናነት ሴቶች ከአልችልም ባይነት ወጥተው እራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲደግፉ የአመለካከትና ስብዕና ቀረፃ ላይ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሴቶች ስራ መፈጠር ሼዶችን በመስጠት ረገድ አብሮን እየሰራ ይገኛል ነዉ ያሉት፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ከ1መቶ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች ስልጠና መስጠታቸውንም ጠቁመዋል።
የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንፃር ደግሞ 1ሺህ 5መቶ77 ለሚሆኑት እንደየፍላጎታቸው የእንጀራ ፣የዳቦ መጋገሪያ እንዲሁም ሌሎች ማሽኞችን ገዝተው መስጠታቸውን ነግረውናል።
ድጋፉ ከተደረገላቸው ውስጥ 88 በመቶ ባሉበት አከባቢ በስራ ላይ መሰማራታቸውን በተደረገ ክትትል ማረጋገጣቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል ።
ልኡል ወልዴ
የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዓድዋ ከተማ በድምቀት ተካሂዷል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በኢትዮ ኤሌክትሪክ አሸናፊነት ፣ሸገር ከተማ በሁለተኝነት እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ተጠናቋል ።
አትሌት ያለምዘርፍ የኃላው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፤ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ ከሸገር ከተማ ሁለተኛ፣ እንዲሁም አትሌት አሳየች አይቸው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል ።
በደረጃቸው ቅደም ተከትል አትሌቶቹ የገንዘብ 40,000፣ 20,000 እና 15,000 ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ለክለቦች ደግሞ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል።
በውድድሩ ላይ ክልሎች ፣ ከተማ አስተዳደር እና ክለቦች ተሳትፈዋል ።
በአለም አትሌቲክስ ደረጃ ኮርስ የወሰዱ 60 ዳኞች ውድድሩን መርተዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም
ወልቂጤ ከተማ ክለብ በ ፊፋ የ 6 ነጥብ ቅነሳ ውሳኔ ተላለፎበታል።
ወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ክሊፍተን ሜይሶ አይሲ የተባለ ተጫዋችን በተመለከተ የተላለፈበትን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ቢገለፅም ተግባራዊ አለማድረጉን ተከትሎ የፊፋ የህግ ፖርታል የነጥብ ቅነሳ እንዲደረግበት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትዕዛዝ አስተላለፏል።
በዚህም መሰረት ወልቂጤ ከተማ እየተወዳደረበት በሚገኘው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከሰበሰበው ነጥብ ላይ የስድስት (6) ነጥብ ቅነሳ ውሳኔ ተላለፎበታል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
ከውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ጋር ተያይዞ እየተነሳበት ያለውን ቅሬታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈታ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚያመቻቸው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት እድል ለመጠቀም በተለያዩ የሙያ መስኮች የተለያዩ ስልጠናዎችን የወሰዱ ዜጎች በተቋሙ ላይ ተደጋጋሚ ቅሬታን ለ ኢትዮ ኤፍኤም አቅርበዋል፡፡
ቅሬታ አቅራቢ ዜጎች፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወደ ውጪ ሀገራት ለመላክ በሚያመቻቸው የስራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን በተለያዩ ዘርፎች ስልጠና ብንወስድም ቃል የተገባልን ሊፈጸም እና ሊልከን አልቻለም ሲሉ ቅሬታ ነግረውናል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት ሀላፊ አቶ ብርሀኑ አለቃ በጉዳዩ ላይ ለጣቢያችን ምላሽ እንዲሰጡበት ያደረግን ሲሆን በተለይ በሹፍርና የሙያ ብቃት ሰልጥነው እና ህጋዊ ማረጋጋጫ ይዘው ወደ ውጪ ሀገራት ለመሄድ ሚጠባበቁ 1 ሺ ዜጎችን እስካሁን ለመካል ችለናል ብለዋል፡፡
ነገር ግን በሹፍርናም ሆነ በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች አሁንም ቢሆን ዜጎችን ያለ ገደብ በተፈለገው ፍጥረት ለመላክ ክፍተቶች ማጋጠማቸውን ነግረውናል፡፡
ተቋሙ በሚያመቻቸው በዚህ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎችን የሚልኩ ኤጂንሲዎች ጋር ተነጋግረን ችግሩን ለመፍታት እየሰራን ነው ያሉት አቶ ብርሀኑ ህገወጥ ኤጀንሲዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ሂደት ስለመኖሩም ነግረውናል፡፡
ስልጠና አጠናቀው ወደ ውጪ ሀገራት ለመሄድ የሚጠባበቁ ዜጎችም ተቋሙ እስከ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንደሚኖረው አስታውቀዋል፡፡
የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት ሰባት ወራት ከ 2 መቶ 30 ሺ በላይ ዜጎች ወደ ውጪ ሀገራት ሄደዋል ሲል አስታውቆናል፡
የውልሰው ገዝሙ
የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የአራት ጨዋታዎች እና የ40,000 ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ተጣለባቸው !
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከቀናት በፊት በሰጡት አስተያየት ምክንያት ከቱርክ እግርኳስ ፌዴሬሽን ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ሞሪንሆ ከቀናት በፊት ከፌነርባቼው እና ጋላታሳራይ ጨዋታ በኋላ የቱርክ ዳኞች መርሐ ግብሩን ባለመምራታቸው ጨዋታው ያለብጥብጥ በሰላም ተጠናቋል ብለው ነበር።
አሁን ላይ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በሰጡት አስተያየት ምክንያት ከቱርክ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጆዜ ሞሪንሆን የአራት ጨዋታዎች እና የ40,000 ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
አሜሪካ እና ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ያለመ ውይይት በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ ዛሬ ቱርክ ኢስታንቡል ውስጥ ተደረገ ።
የሁለቱ ሃገራት ባለስልጣናት የዛሬው የኢስታንቡል ንግግር የኤምባሲ ጉዳዮችን ለመፍታት ያለመ ነው ተብሏል።
ዛሬ ኢስታንቡል ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ቆንስላ ጽ/ቤት ውስጥ የተደረገው የሃገራቱ ውይይት ለዩክሬኑ ጦርነት መቋጫ ለማበጀት ሳዑዲአረቢያ ውስጥ ከተደረገው ውይይት ቀጥሎ የተካሄደ ነው ።
ስድስት ሰዓታት ገደማ እንደወሰደ በተነገረለት የዛሬው ውይይት የሃገራቱን የግንኙነት ደረጃ ለማሳደግ የኤምባሲ ጉዳዮችን ለመፍታት ያለመ ከመሆኑ የዘለለ ከሁለቱም ወገን የተሰጠ መግለጫ አለመኖሩን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
በስብሰባው ላይ ከፍተኛ ባለስልጣናት መገኘታቸው ከመገለጹ ባለፈ ማን እንደተገኘ በዝርዝር የተባለ ነገር የለም። ነገር ግን ታስ የተሰኘው የሩስያ የመገናኛ ብዙኃን ከሩስያ ወገን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተሳታፊ እንደሆኑ መመልከቱን ዘግቧል።
የክሬምሊን ቃል አቃባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከአሜሪካ ጋር የተቆራረጡ ግንኙነቶችን በቦታው ለመመለስ ሂደት ይጠይቃል ።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው ወር የስልጣን ቆይታቸው የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም ብሎም ከሩስያ ጋር የነበረውን ዲፕሎማሲያዊ ግኑኙነት ለመመለስ የነበራቸውን ፍላጎት በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ ንግግር ማስጀመራቸው አይዘነጋም ።
የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
አለመግባባቶችን ለማስወገድ ደቡብ አፍሪካ ወደ አሜሪካ ልኡክ ልትልክ ነው።
ደቡብ አፍሪካ አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አሜሪካ በመላክ፣ በዲፕሎማሲ፣ ንግድ እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንደምትሻ ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ አስታውቀዋል።
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው የቡድን 20 ዓባል ሀገራት ጉባኤ ጎን የተናገሩት ራማፎሳ፣ ወደ አሜሪካ የሚላከው ቡድን በርካታ አለመግባባቶችን ለማስወገድ እንደሚወያይ አስታውቀዋል። በደቡብ አፍሪካው ጉባኤ የአሜሪካ ባለሥልጣናት አልተገኙም።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ደቡብ አፍሪካ ከነጮች ላይ መሬት ልትነጥቅ ነው በሚል የሀገሪቱን መንግሥት ተችተው የገንዘብ ድጋፍ አናቆማለን ብለው ነበር።
ትችቱ የመጣው ራሞፎሳ መንግሥት በሚወርሰው ንብረት ምትክ እንደ ሁኔታው ካሳ ላይከፍል እንደሚችል የሚያመለክተውን ሕግ ባለፈው ወር በፊርማ ማጽደቃቸውን ተከትሎ ነው።
“ወደ አሜሪካ የምንሄደው ምክንያት ለመደርደር ሳይሆን፣ በበርካታ መስኮች ከአሜሪካ ጋራ ትርጉም ያለው ስምምነት ለማድረግ ነው” ብለዋል ራማፎሳ።
ሕጉ አስፈላጊ የሆነው ሕዳጣን የሆኑት ነጮች የዘር መድልኦ ከተወገደ ከ30 ዓመታት በኋላም አብዛኛውን የእርሻ መሬት ይዘው በመቆየታቸውና እኩልነትን ማስፈን አስፈላጊ በመኾኑ እንደሆነ ተመልክቷል።
የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የ 22 ሚሊየን ብር ድጋፍ አገኙ።
ዳሸን ባንክ ከ22 ሚሊየን ብር በላይ በማወጣት ለ 31 ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
።
ባንኩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የጀመረበትን 7ኛ ዓመት ባከበረበት በዛሬው እለት ነው ድጋፉን ያደረገው።
ዳሸን ባንክ በወለድ ነፃ አገልግሎት ከደንበኞቹ በአደራ የሰበሰበውን ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ በተገኙበት በዛሬው እለት አስረክቧል።
በዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ መስፍን በዙ ባንኩ በሚሰጠው ከወለድ ነፃ አገልግሎት ብቻ በአሁኑ ወቅት ከ1 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ማፍራት መቻሉን አስታውቀዋል።
ድጋፊ የተደረገላቸው ሀገር በቀል ድርጅቶች የተቀመጡ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ባንኩ አስታውቋል።
ረጂ ድርጅቶቹ የወሰድትን ገንዘብ በተገቢው ለተቋቋሙለት ዓላማ ማዋላቸውን ባንኩ ክትትል እንደሚደረግም ተነግሯል።
ነህሚያ ኦትዝም ማእከል፣ምሉእ ፋውንዴሽን፣የአቢ -ዘር ማህበረሰብ አቀፍ የልማት ድርጅት እና ሌሎችም እያንዳንዳቸው ከ 5 መቶ ሺ ብር ጀምሮ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።
ዳሸን ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት (ሸሪክ) እ.ኤ.አ ህዳር 28 ቀን 2023 በባህሬን ማናማ በተካሄደው 9ኛው የኢስላሚክ ሪቴል ባንክ ሽልማት ላይ ጠንካራ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚሠጥ ባንክ በሚል ዕተውቅና ማግኘቱን አስታውሷል።
የውልሰው ገዝሙ
የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያና ሶማሊያ መሪዎች የርስ በርስ መተማመን መገንባት እንዳለባቸው ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር እንዳላቸው የጠቆመው መግለጫው፥ ሀገራቱ በዲፕሎማሲ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትብብራቸውን በማስፋት የርስ በርስ መተማመን መገንባት እንዳለባቸው መስማማታቸውን ተገልጻል፡፡
የዛሬው ምክክር ባለፉት ወራት ሀገራቱ ግንኙነታቸውን ለማደስ ያካሄዷቸውን ተከታታይ ውይይቶች ያጸና መሆኑን አመላክተዋል።
ሀገራቱ የጋራ እጣ ፈንታ ያላቸው ሉአላዊ ሀገራት መሆናቸውን በመጥቀስም ለቀጠናው መረጋጋትና እድገት በጋራ ለመስራት መሪዎቹ ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ነው የጠቀሰው የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ከውይይቱ በኋላ በጋራ ባወጡት መግለጫ የገለጹት ።
የሀገራቱን የህዝብ ለህዝብ ትስስር የሚያጠናክሩና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያጎለብቱ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት መስማማታቸውንም አብራርቷል።
መሪዎቹ የሀገራቱን ግንኙነት ለማሻሻል በቱርክ በተደረሰው ስምምነት መሰረት (አንካራ ዲክላሬሽን) የቴክኒክ ቡድን ንግግር መጀመሩንም ያደነቁ ሲሆን፥ ለገንቢ ንግግርና ትብብር ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዦች የደረሱት ስምምነትም በቀጠናው መረጋጋት ለማስፈን ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።
የሀገራቱ የጦር መሪዎች በቅርቡ ባደረጉት ምክክር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (አውሶም) ውስጥ እንዲሰማራ መስማማታቸው የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መሪዎች ለሀገራቱ የጋራ ፍላጎት፣ ሰላምና መረጋጋት በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውንም ባወጡት የጋራ መግለጫ አረጋግጠዋል።
የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
በከተሞች ባሉ የህንፃ ባለቤቶች ላይ የሊፍቶችን(አሳንሰሮችን) ደህንነት በየግዜው የማረጋገጥ ችግሮች አሉ ተባለ፡፡
ህንፃዎች ላይ የሚገጠሙ ሊፍቶች(አሳንሰሮች) ላይ ተገቢውን ፍተሻ እና ጥገና አለማድረግ በህንጻ ባለቤቶች ላይ የሚታይ ክፍተት እና ዋነኛው ለአደጋ አጋላጭ ምክንያት ነው ሲል የአዲስ አበባ አደጋ እና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ፤ የሊፍት አገልግሎት በሚሰጡ ህንፃዎቸ ላይ በቋሚነት ባለሙያ እንደሚያስፈልግ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ኤሌክትሪክ በተለያየ ምክንያት የሚጠፋባቸው አጋጣሚዎች ስለሚኖሩ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ይህንን ተክቶ የሚሰራ አውቶማቲክ ጀኔረተር እንደሚያስፈልጋቸውም ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ባሉት ግዜያት በሊፍት ምክንያት የሞት አደጋ አጋጥሞ እንደሚያውቅ አቶ ንጋቱ አስታውሰዋል፡፡
በሊፍት ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ የህንፃ ባለቤቶች ብቻም ሳይሆኑ ተጠቃሚዎችም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል፡፡
ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ለአደጋ የተጋለጡ ሊፍቶች ካሉ የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ እና ግን ደግሞ ሁሉንም ለማጣራት እንደሚቸገሩ አንስተዋል፡፡
ሐመረ ፍሬው
የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም