ethiohumanity | Education

Telegram-канал ethiohumanity - ስብዕናችን #Humanity

30703

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Subscribe to a channel

ስብዕናችን #Humanity

✨ወዳጄ ሆይ

አንዳንድ ጊዜ አጠገብህ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን በቀላሉ ሲያገኙና በትምህርት ፣ በሥራ በትዳር ... ቶሎ ስኬትን ሲጨብጡ ታያለህ። አንተ ግን አንድ ቦታ ቆመሃል። ወቅቱ የእነርሱ ነውና ከመቅናት ይልቅ ባገኙት ስኬት የደስታቸው ተካፋይ ሁን። ለእነርሱ ያደረገ አምላክ ላንተም እንደሚያደርግልህ እመን።

ይኸውልህ ፤

🌗የማንጎ ዛፍ የቡርቱካን ዛፍን ከርሱ ወቅት ቀድሞ ምርትን ስለሚሰጥ አይጨነቅም። ስኬት፣ በወቅት የሚታጨድ መኸር ነው፣ወቅትህ ሲሆን ምንም ነገር ከመንገድህ ሊቆም አይችልም። የአንበሳ በዝግታ መራመድ ስንፍናን ወይንም ድካምን አያመለክትም፤ ያለመውን አደን በእጁ ለማስገባት እርምጃውን እያሰላ እንጂ። የሰዎች ፈጥነው መራመድ አያውክህ።

የራስህን ኑሮ ኑር!

✨ፈጣሪህን ታመን። ልብ በል፤ ቤትህን በፍጥነት ሠርተህ መጨረስህ ሳይሆን ንፋስና ጎርፍን መቋቋም የሚችል ጠንካራ አድርገህ መሥራትህ ነው ቁምነገሩ። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። የእውቀት ሰውና ጠንካራ ሠራተኛም ሁን! ደግሞ ሁሉንም አታገኝም!አንተ የተሳፈርክበት አውሮፕላን መሬት ሲያርፍ፣ ከዛ መሬት የሚነሣ አውሮፕላን አለ፤ ሌሎች ደግሞ ለመነሳት በሂደት ላይ ይገኛሉ። ሁሉም መዳረሻቸው የተለያየ ነው፤ ምናልባትም ወዳንተ መነሻ ሊሆን ይችላል። አየህ ህይወት እንዲ ናት፤ "ደረስኩ" ብለህ ስታስብ ሌሎች ያንን ሥፍራ "ጥለው" ሲነሱ ታገኛቸዋለህ። አንዳንዶቹ አንተ ወደ ተነሳህበት፣ ሌሎቹም ወደ ሌላ።

🌗በልጅ ማጣት ምክንያት ቀን ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች እንዳሉ በልጆቻቸው ምክንያት ቀንና ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች አሉ፣ባል ባለማግባታቸው የሚጨነቁ ሰዎች እንደገጠሙኝ ሁሉ በማግባታቸው የሚጨነቁም ሰዎች ገጥመውኛል። በሥራ እጥረት ምክንያት የታመሙ እንዳሉ በሥራ ብዛት ምክንያት የሚታመሙ አሉ። ልጆቻቸው ፈተና ላይ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡላቸው የሚጨነቁ እንዳሉ፣ ልጆቻቸው ጥሩ ትምህርት ቤት እንዲገቡላቸው የሚጨነቁ አሉ።

እናም ወዳጄ

ህይወት እንዲህ ነው፤ በቃ! ሁሉንም የኛ ልናደርግ አንችልም!፣ ንፋስን አባሮ እንደመያዝ ነውና። ሁሉንም ነገር የራስህ እንዲሆን ከመድከም ይልቅ ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር። ከአንዱ ምእራፍ ወደ ሌላው ምእራፍ እንደሚያሸጋግርህም ፈጣሪህን ታመን። ሁልጊዜም በአምላክህ ደስ ይበልህ! በእምነትም ኑር!

መልካምነት ለራስ ነውና

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍የተሰማችሁን አድርሱን @EthioHumanityBot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💡የፈለገውን ያህል ብትሰራ የሰው ልጅ ስምህን ለማጠልሸት አንድ ስህተት ይበቃዋል ። የሚገርመው የቅፅበት ስህተትህን የዘላለም ባህሪህ አድርጎ አንተ ራሱ እስኪገርምህ በርቱዕ አንደበቱ ቀምሞ ያቀርብልሃል፣ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ  ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ፣ጉድፍህንና ነቀፋህን ለሚከታተሉ ብዙ ቦታ አትስጥ፣ ለእነርሱ አንተ በውሃ ላይ መራመድ ብትችል እንኳ አስማት እንጂ ቅድስና አይመስላቸውም፣ እንዲያውም ዋና ስለማይችል ነው ሊሉህ ይችላሉ፣አለም እንደዚህ ናት ለስኬትህ ሳይሆን ለውድቀትህ ትፈጥናለች።

📍እኔ ትንሽነቴን አልረሳም ማወቄም አያመፃድቀኝም ።እኔ  የእናንተ የመምጣት እና መሄድ አሻራ ነኝ ፣ የእኔ መጉደል መጉደላቸሁ  እንከናችሁም አንከኔ  ነው፡፡ ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሣይሆን ታግሎ ያለፈ ነው። ሁሌም ቢሆን እራስህን ተመልከት። የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው፣ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሆኖ ታገኘዋለህ።ሰው ምንም ብልህና አዋቂ ቢሆን በራሱ ሥራ ብቻ ራሱን ችሎ እንደማይኖር ዕወቅ:: ነገር ግን ሁሉም በየሥራው ጸንቶ እርስ በርሱ በሥራ ይፈላለጋል:: ስለዚህ ሰውን ሁሉ አክብረህ ኑር እንጂ ሰውን አትናቅ ሥራውንም አትንቀፍ::

💎ሁሉንም በገንዘብ እገዛዋለው ብለህ አታስብ በገንዘብ የምትገዛው ርካሹን ነገር እንጂ ውድ ነገሮች የዋጋ ተመን የላቸውም።የዋህነት እና ንፁህነት በእውቀት ብዛት ወይም በጥበብ ጥልቀት ተፈልጎ የማይገኝ በራሱ ንፁህ ስጦታ ነው፡፡ በገንዘብ የማይገዛ፤ በሀይልም የማይጠፋ፤በመከራም የማይደበዝዝ ለተወደደ የሚሰጥ የፈጣሪም ችሮታ ነው፡፡ 

        ለፍቅራችን፣ ውብ ቅዳሜ! ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💡መንቃት ህይወት ነው!

የነቁት ሰዎች ለመኖር የተለየ ትርጉም አላቸው፡፡ ትርጉማቸው ንቃትን የያዘ ነው:፣ እየተነፈሳችሁ ስለሆነ እየኖራችሁ  ነው ማለት አይደለም ፤ደማችሁ እየተዘዋወረ ስለሆነ እየኖራችሁ ነው ማለት አይደለም። በህይወት የምትኖሩት የነቃችሁ ከሆናችሁ እንደሆነ ነው::

💡ዝም ብለህ ራስህን በተመስጦ ስታነብ ውስጠትህ ረጥቦ ሕይወትህ ይለመልማል፣ ምስጠት ማለት መታዘብ ነው፣ ይቺን ሀሳብ በቀላሉ የምታስረዳ አንድ ምሳሌ አለች። የኩሬ ውሃ ጭቃ ሞልቶት ቢደፈርስ እየነካካን አናጠራውም፣ በነካካነው ቁጥር ይበልጥ እየደፈረሰ ነው የሚመጣው። መፍትሔው ኩሬውን አለመንካት ነው፤ መፍትሔው ኩሬው ዳር ተቀምጦ የተፈጥሮን ትንግርት ማስተዋል ነው። ኩሬው ለራሱ ሲተው እየጠራ ፣ እየጠራ ይመጣና ኩልል ያለ ንፁህ፣ የተጣራ ውሃ ይሆናል።

❤️አእምሯችን እንደ ተንጣለለው ኩሬ በሃሳብ ጭቃ ደፍርሷል።ኩሬውን እየነካካን እንደማናጠራው ሁሉ አእምሮንም በሃሳብ ጉልበት መግራት አይቻልም። ኩሬው ራሱ በራሱ እንዲጠራ እንደምንተወው ሁሉ፣ አእምሮም ንቃት ላይ እንዲደርስ፣ ከሃሳብ ግርግር አሳርፎ ለራሱ ምትሃታዊ አርምሞ መተው አለበት። በጥልቅ አሰላሳዩም ተፈጥሮ በአእምሮ ላይ የራሱን ተአምር ሲሰራ በዝምታ ተውጦ ያስተውላል። በጥልቅ ማሰላሰል ሌላ ምንም ውስብስብ ነገር የለውም፣ በአጭሩ ከሃሳብ ነፃ ሆኖ ወደ መሆን ማእቀፍ [Consciousness] መሸጋገር ነው።

💡እናም የተረጋጋ ታዛቢ አመለካከት ይኑራችሁ ፣ በመመሰጥ ነፃነትን እና ደስታን ታገኛላችሁ። ንቁ፣ አንፀባርቁ ፣ ተመልከቱ ነገሮችን በእርጋታ ከውኑ በመንገዱ ውስጥ ኑሩ ፣ውስጣዊ ብርሃናችሁ በራሱ ጊዜ ያድጋል፡፡

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💡ውሎህ የት ነው?

📍ሕይወት ሥነ ምህዳር ነው። የሰጠኸው ነገር ተመልሶ ይመጣል።የዘራውን ታጭዳለህ የምትሰጠውን ታገኛለህ በሌሎች ውስጥ የምታየውን በአንተ ውስጥ ታገኘዋለህ ፡፡ ሕይወት ሁሌ የሰጠሀትን መልሳ ትሰጠሀለች መልካም አድርግ መልካም ታገኛለህ እንደሚባለው ሁሉ።

ውሎህ አንተን ይገልፃል መልካም ቦታ ከተገኘህ በመልካም ይገለፃል በመጥፎ ቦታ ከዋልክ እንዲሁ ይሄንን የሚገልፅ ልናስተውለው የሚገባ አንድ ተረት አለ እንዲህ ይላል:-

🐝አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት
ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ? ቤታቸው
ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል።
የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ
ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::

አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም
መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን
ጥያቄዋን አቀረበች
በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት
ውሎሽ የት ነው?

📍ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ ወሏችን ተመልሶ እኛነታችንን ይገልፃል ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ ሀሳባችን ስራችንን፣ ስራችን ውጤታችንን፣ውጤታችን እኛነታችንን ይገልጽልናልና። የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለችና፣ራስን መፈተሽ መልካምም ነውና ወሎችን የት ነው?

   ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

❤️እንኳን ለ127ኛው ለታሪካዊ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ነፃነት በር ለሆነው የጥቁር ህዝቦች ኩራት የአድዋ ድል በአል በሰላም አደረሰን።

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🌊የምታቀው የውሃ ኩሬ ራቅ ብለህ ስትመለስ ደፍርሶ ቢጠብቅህ...ንጹህ ውሃን ለመጠጣት ያለህ አማራጭ ድፍርሱ እስከሚጠራ መጠበቅ ብቻ ይሆናል ። "አፈር የተቀላቀለበትን ውሃ እንዲጠራ ከፈለግክ፤ተወው አታማስለው" ይላል ፈላስፋው አለን ዋትስ። በመተው፤በመረጋጋት፤ በዝምታ፤ ለፍተን ያጣናቸውን ውድ የህይወት ስጦታዎች እናገኛለን።

🌪ልክ እንደዚህ ሁሉ በህይወታችን የሚገጥሙንን ችግርና እንቅፋቶችን አንዳንዴ የምናጠራቸው መሃል ላይ እጃችንን ስለከተትን ብቻ ላይሆን ይችላል ። አንዳንዴ ዝምታችን እና ትእግስታችንም ብዙ ነገሮች በራሳቸው ጊዜና ሁኔታ እንዲስተካከሉልን እድል ይሰጡልናል ። እኛ ችግራችንን ለመፍታት የምናደርገው ጥረት ይበልጥ ችግር ውስጥ እንዳይዘፍቀን መጠንቀቅ ይኖርብናል ። አለዝያ የችግሩ አሳዳጊ እና አባባሽ እንጂ የችግሩ ፈቺ አንሆንም ።

🌊ለተረጋጋ አይምሮ አለም ትገበራለች ብሏል ጥንታዊው ፈላስፋ። ምንም እንኳን ብዙ ነገሮች በጥረትና በሩጫ የሚገኙ ቢሆንም፤ አንዳንድ ወሳኝ ነገሮች ግን በእርጋትና በመተው እንዲሁም በዝምታ የሚገኙ ናቸው።

ውብ  ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

📍እውነትን ፣ቅንነትን ፣ ገንዘብ ከማድረግ በላይ ኮተትን ብቻ  ገንዘብ አድርጎ ህይወቱን በክህደት፣ በውሸት ፣በጥቅመኝነት ፣በአስመሳይነት በብልጣብልጥነት እየኖረ ኑሮ የበራለት የሚመስለው ሰውነት እንዴት ያልታደለ ነው።

📍የህሊና ፣ የቤተሰብ ሰላምና ደስታ በብልጣብልጥነት አይመጣም። ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። የምናተርፈው ነገር ቢኖር የሆነ ጊዜ ላይ የሚመጣ መጥፎ ስቃይን ነው። ያውም ለልጅ የሚተርፍ የበደል ክፍያን ነው፣የቆምን መስሎን የዘነጋን…. ሰው የዘራውን ያጭዳልና እናስተውል።

💡መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው፣ ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ከአንተ የመነጨና ተንደርድሮ የተተኮሰ ኃይል በእኩል መጠን እና ልክ አጥፊ እንደሆነ ሁሉ ራስህንም ያጠፍል፤ ሀሳብህን አልሚ ከአደረከው ደግሞ ቅድሚያ አንተን እና የእኔ የምትለውን ሁሉ ባርኮ ለሌሎች ይተርፋል።

መጥፎ ነገራችንን ሁሉ በመልካም ይቀየርልን 🙏

                              ✍ ሄለን ካሳ

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ምክር  ለወዳጅ

ወዳጄ ሆይ!

✨ጨለማው ላይ ብታፈጥ ያለ ሰዓቱ አይነጋም።ፈጣሪህን ትተህ በመከራህ ላይ ብታፈጥ አንዳች ጥቅም የለውም።ካስተዋልከው ጨለማም ውበት አለው። ከካባ ይልቅ ደማቅ ነው። እሾህም አበባ አለው። ክፉ ሰውም አንድ ጥሩ ነገር አለው። ልብ አድርግ ለክረምት በጋ፤ ለሌሊት ቀን አለው። ላንተም ጊዜ አለህ። ጊዜን የሚሰጥ ራሱ ጊዜ ሳይሆን የጊዜ ባለቤት ፈጣሪ እንደሆነ እመንና ጠብቅ።

ወዳጄ ሆይ!!

💫 አግኝቶ ያጣው ቶሎ ይከፋዋልና ታገሠው ። አጥቶ ያገኘ ምድር ይጠበዋልና ምክረው ። ከፍታህ ዝቅተኞችን በመርገጥ ፣ ህልውናህ በሌሎች ሬሳ ላይ አይሁን ። የፍቅር ሰው ለመባል ሁሉም ትክክል ነው አትበል ። ግልጽ ጥላቻ የፍቅር ያህል ነው ። ግልጽ ንግግር ሰሚውን ያከበረ ነው ። እጅግ ግልጽነትም የሚያስገምት ነው፣ ።የምሥጢር ሙዳይ ሁን እንጂ የእሳት ማንደጃ ወናፍ አትሁን ። ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ችሎታቸውና ፍላጎታቸው መጠን ብቻ ተናገር ፣ ቁጥብ እንጂ ዝርው አትሁን ።


ወዳጄ ሆይ!

✨ለዕውቀት ትጋ ፣ በከፊል በተረዳኸው ነገር ራስክን እንደ አዋቂ አትቁጠር ። በከፊል ከማወቅ አለማወቅ ይሻላል ። "ሥራ ስትሠራ ደግሞ ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው" ፣ በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው ። ትጋት ጥሩ ነው ። ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፣በችኮላ መሥራትና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው ። እርኩሰት የዕውቀት እና ስልጣን መገለጫ አይደለምና ማንነትንና ሰብዓዊ ክብርን ከሚያጎድፉ ተግባራት መታቀብን ገንዘብ አድርግ ። "

እናም በየዕለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን ። ያለጸጸት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ ፤ ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር ፤ ልክ እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውንና ለማከናወን የምትመርጠውን ዐይነት ሕይወት ለመኖር ሞክር ።

             ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💢ካህሊል ጂብራን የምንኖርበትን አለም በደንብ የሚገልጽ ድንቅ አባባል አለው። " ደስታ እና ሀዘን አይነጣጠሉም፤ በአንድ አንገት ላይ የበቀሉ ሁለት እራሶች ናቸው" ብሏል።

💢ምንም አወንታዊ ብንሆን፤ ምንም የእምነት ሰው ብንሆን ምንም የተማርን እና የተመራመርን ብንሆንም፤ ከህይወት መፈራረቅ አናመልጥም። ከሀዘን እና ከደስታ፤ ከስኬትና ከውድቀት ቅብብሎሽ አንድንም። ይህ እውን ከሆነ የምንለውጠው በዙሪያችን ያለውን ሳይሆን፤ በውስጣችን ያለውን ነው።

🌀ችግር አታሳየኝ ከማለት ችግርን የማልፍበት ጽናቱን ስጠኝ ብንል፣ አልውደቅ ሳይሆን ስወድቅ የምነሳበት ጉልበት ይኑረኝ ብንል፣በሩ አይዘጋብኝ ሳይሆን እሲከከፈትልኝ ድረስ የማንኳኳበትን ትዕግስት ስጠኝ ብንል፣ፈተና አይግጠመኝ ሳይሆን ፈተናውን የማልፍበትን ጥበብ ይግለጽልኝ
ማለት ብንጀምር የውጭውን አለም መቆጣጠር ቢያቅጠን ወሳኝ የሆነው የራሳችን አለም ላይ ሰላም እናሰፍናለን። ሰው በአስተሳሰቡ ይኖራል፤ የህይወት እይታውም ሆነ እጣፋታው የሚወሰነው በአስተሳሰቡ ነው። መልካም ኑሮ በመልካም አስተሳሰብ ይገነባል።

💢 የትኛውም የህይወት ጎዳና ላይ ብንቆምም፤ ወደፈልግንበት መዳረሻ የመሄጃው እድል ዛሬም አለን። ቀዳሚው ተግባር ግን አስተሳሰባችን ላይ መስራት ነው።

✍ሚስጥረ አደራው

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

✨ወዳጄ ሆይ ሰውው ሁንን…. አስተውል!
ቆሞ መሄድህ መብላት መጠጣትህ ጥሩ መልበስ ጥሩ መናገር ወይንም ሀብት ክብርና ዝናህ ያንተን ሰውነት በፍጹም ሊያረጋግጡልህ አይችሉምና፡፡ ይልቅ አትዘግይ! አሁኑኑ ራስህን ፈልግ.. ዙሪያህንም አስስ..

🔆ያንተ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድረስላቸው ፡ ጊዜህን ባግባቡ ተጠቀም ከሚያጸጽቱህ ነገሮች ቀድመህ ለመቆጠብ ሞክር ለህሊናህ እንጅ ለስሜትህም አትገዛ ላለፈ ነገር እየተጸጸትክ ቀሪ ጊዜህን አታባክን፤

🔆ከራስህ ከፍታ ይልቅ ለሰዎችና ለሃገርህ ከበሬታ ይኑርህ ፡፡ የወደቁትን አንሳ ያዘኑትን አጽናና የተራቡትንም ሽራፊ ቁራሽ አትንፈግ፡ ባይኖርህም ፍቅር ስጣቸው እርሱ ከሁሉም ይበልጣልና!!
ለወሬ እጅ አትስጥ በጉዞህ ሂደት ውስጥ ለሚጮሁ ዉሾች ሁሉ አትደንግጥ አላማህን ለማሳካት በጽናት ጉዞህን ቀጥል  

✨ችግር መከራ ስቃይና ደስታንም አምኖ ለመቀበል ራስህን ዝግጁ አድርግ፤ ክፉን በክፉ ለመጋፈጥ ከመሞከር ይልቅ ውስጥህን በይቅርታና በመጸጸት ከተንኮል አጽዳ ፡፡  ከሰወች ጉዳትና ሞት ደስታን ወይም ሃብትን አትሻ!አትጠራጠር ያኔ! የንጹህ ልብ ህሊናና የዘላለም ደስታ ባለቤት የሃብታሞች ሁሉ ሃብታም …. የሰውም ሰው ነህ !!

✍ በአብርሃም አባቡ

ውብ  አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🌗``ክፉ ቀን ጥሩ ነው´´

✍ፕሮፌሰር መስፍን "አገቱኒ ተምረን ወጣን" በሚለው መጽሀፋቸው ስለ ክፉ ቀን እንዲህ ይላሉ፡፡.....

🌗 ክፉ ቀን ጥሩ ነው መማር የፈለገውንም ያስተምራል ፈጣሪ ሀያላን ነን የሚሉትንም ያስተምራል፡፡

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ደጋግ ሰወችን ይቀሰቅስና የግፍን መራራነት እንዲቀንሱት ያደርጋል፡

ክፉ ቀን ጥሩ ነው በተለያየ የኑሮ ደረጃ የተከፋፈሉትን በአላማ ያያይዛቸዋል፡፡

ክፉ ቀን ጥሩ ነው የግፍን ጥርስ ሁሉም እንዲያየውና እንዲንቀው ያደርጋል፡፡

🌗 ክፉ ቀን ጥሩ ነው ብዙ ጉድ ያሳያል።የተማረውና የተመራመረው አምሮውን በኦሞ ሙልጭ አድርጎ አጥቦ ህሊናውን በጨጓራው አፍኖ የሆነውን አልሆነም እያለ ለልጆቹ ሀፍረን ሲሆን ያሳየናል።
-
ክፉ ቀን ጥሩ ነው ያለፈውን ካለው ጋር በእውነት እንድናወዳድረው ያስገድደናል።

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ክብርን ወደ ውርደት ውርደትን ወደ ክብር ይለውጣል።

ክፉ ቀን ጥሩ ነው የጉልበተኛውን ልብ ያደነድናል አእምሮውንም ደርግሞ ይዘጋዋል የጭካኔውንም ወሰን የለሽነት ያሰየናል።

🌓 ክፉ ቀን ጥሩ ነው ጥሩ ቀንን እየጮኸ ይጣራል።

ክፉ ቀን ጥሩ ነው የወደቀውን ለድል የጣለውን ለውድቀት ያዘጋጃል

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ክፋት በጎነትን አሸንፎ እንደማይዘልቅ ያሳያል ህግ ቀልቡ ሲገፈፍ ዳኝነት ሚዛን ሲያጣም ያሳያል

ክፉ ቀን የጠራ መስትዋት ነው መልካችንን ብቻ ሳይሆን ባህሪያችንንም ጤናችንን ብቻ ሳይሆን ህመማችንንም ውበታችንን ብቻ ሳይሆን አስከፊነታችንንም ቁልጭ አርጎ ያሳየናል

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ባጠቃላይ የመጪው ጥሩ ቀን ምልክት ነው።

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💎ዓለም የታነፀችው ከሐሳብ ነው፣ ሐሳብ የሁሉ ነገር አልፋ ነው። ሁሉም ሐሳቦች ግን መልካም ናቸው ማለት አይደለም፣ መልካሞቹ ግን በህሊና ቅኝት የተቃኙት ናቸው!

💡ጥበብ ማስተዋል ነች! ማስተዋል ደግሞ ከዕርጋታ/ከስክነት ትወለዳለች!ሁሉም ሰው በሌላ ሰው አይን ስህተት ሊሆን ይችላል። በራሱ አይን ግን ሁሉም ሰው ትክክል ነው!

💎በውይይት መግባባትም/አለመግባባትም ተፈጥሯዊ ነው። መሠረታዊው ቁምነገር የሐሳብ ብዝሃነትን ማስተናገድ መቻል ነው።የሠላ አዕምሮ በምክንያታዊነት ተነጋግሮ መደማመጥን ይከጅላል።አንድን ነገር ስለተቃወምነው ስህተት ነው ማለት አይደለም። ስለደገፍነውም ደግሞ ትክክል ነው ማለት አንችልም!በስሜት ከደገፍነው ይልቅ በሐሳብ የሞገትነው በብዙ ሺ እጥፍ ፍሬ ያፈራል!

📍ምግብን ማላመጥ እንደምናውቅ ሁሉ ሐሳብን ማላመጥ እና ማብላላት መለማመድ ይኖርብናል። የሰጡትን የሚቀበለው ሆድ ብቻ ነው። አዕምሮ ደግሞ የሆድ ባህሪ የለውም። ነገር ግን እንዲሆን ከመረጣችሁ መሆን አያዳግተውም፤ ምክንያቱም አዕምሮ የልምምድ ባርያ ነው።

💡የሰው ልጅ መልካሙን የአዕምሮ ባህርይውን የሚያጣበት መንገድ ልክ በመጥረቢያ የሚቆረጥ ዛፍ ጋር የሚመሳሰል ነው። ዕለት ዕለት አስተሳሰብህን እንደዛፍ ቅርንጫፍ እየቆረጥህ ብትጥል ተፈጥሮአዊ ውበትህ እንደሚጠፋ ልብ ብለሃል?
ነገር ግን ቀንም ሆነ ማታ የተቆረጠ ዛፍ ከማቆጥቆጥ እንደማይቆጠብ ሁሉ እንዲሁ ደግሞ የሰው አዕምሮ ወደ ነበረበት ለመመለስ መፀፀቱና ማሰቡ አይቀርም።

📍ወዳጄ ሆይ… የአንተነትህ ምስል የአስተሳሰብህ ስዕል ነው፡፡ እይታህ የሚወለደው ከአመለካከትህ ነው፡፡ ምግባርህና ማንነትህ የሚታወቀው በስራህ ነው፡፡ ስራህ ደግሞ ተምጦ የሚወለደው ከሃሳብህ ነው፡፡ ሃሳብህ ከተበላሸ፣ የዘራኸው ከመከነ ፍሬህ አይጎመራም፡፡ መልካም አያያዝን አግኝቶ የማያድግ እንደሌለ ሁሉ በአያያዝ ጉድለትም እንዲሁ የማይበሰብስ ነገር የለም። አጥብቀህ የያዝከው ነገር ከአንተ ጋር ይኖራል፤ የለቀቅከው ደግሞ ሄዶ ይበሰብሳል፣ የአዕምሮህ መጥፎ ሀሳብ ካሸነፈ አንተንም ሆነ ሌሎችን ይመርዛል።

              ሰናይ ቅዳሜ ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💡ሐና!

"አቤት ቲቸር!" ድንገት በመጠራቷ ደንግጣ ታፈጣለች። የክፍላችን ጎበዝ ተማሪ ናት ሐና…

"የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎት ምንድ ነው?" ይጠይቋታል።

"ምግብ…ልብስ…መጠለያ" መለሰችው እንላለን እኛ በሽክሹክታ። ገና ትላንት ነው አከባቢ ሳይንስ መምህራችን ያስተማረችን።

💡"አይደለም! በጭራሽ አይደለም! ሳይንሱ እውነታውን ጋርዶብናል። እንጀራ ማን ሕሊና ውስጥ ቦታ ሰጠው? 'የምድር ፍሬ፣ የወንዝ ውሃ ይሙላህ' የተባለን ሆድ ማነው የሰው መሠረት ያደረገው? የለም! በየጫካው በየዱሩ የሚኖሩ ወገኖቻችን ርቃናቸው ጌጣቸው ነው፤ ቤትስ ቢሆን - የሰው ልጅ ተንኮሉን ሊከልል፣ ለግርዶሹ ስም አወጣ።

💎ልጆች ልብ በሉ…የሰው መሠረታዊ ፍላጎት አንድ ነው፣ እሱም ፍቅር ነው። ካለፍቅር ሰው የቁም ሙት ነው። ሰው ሰውን ሲያፈቅር፣ ሰው አምላኩን ሲያፈቅር፣ ሰው አገሩን ሲያፈቅር፣ ሰው እውነትን ሲያፈቅር፣ ሰው ነፃነትን ሲያፈቅር ነው ሕያው የሚሆነው። ሰው ነገውን ሲወድ፣ ነገውን ሲያፈቅር ነው ነገ ለሚፈጠር ትውልድ ፍቅር የሚያወርሰው…እስትንፋሱ የሚቀጥለው።"

📖 "ዶክተር አሸብር፣
የታረሙ ነፍሶች"115
✍ በአሌክስ አብርሃም

ውብ ምሽት ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ምክር ለወዳጅ

📗ምክር ብትሰማ በነፃ ትማራለህ።ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው።በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው።ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ።

📒በአመት የካብከውን በዕለት የምትንደው በቁጣህ ነውና አትቆጣ።ቁጣ አውቀህ እንዳላወቀ ለፍተህ እንዳለፋ የሚያደርግ በመልካም መሰረት ላይ የአገዳ ቤት የሚሰራ ነው።በገዛ እጅህ ዋጋህን እንዳታሳንሰው ቁጣህን ያዘው።

📕በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ።ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል።ሰምቶ ማመን ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ።የሰማንያ አመት እውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ አመት መኖር የለብህም።ሰማንያ አመት ከኖሩት በትህትና መጠየቅ ይገባሀል።

📗አይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ።ነገ እንድትደርስ የትላንቱን አትርሳ።የምትሔድበት እንዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ።

📗ክፍት አይሙቅህ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ።ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና።ተግባርህ የምርጫህ ውጤት ነውና አስብበት።ክፋ ሰርተህ እንቅልፍ ሲወስድህ ሰይፍ ላይ መተኛትህን እወቅ።

📒ማግኘት ማጣት የኑሮ ተራ እንጂ አደጋ አይደለም።የተቀበልከው ያንተ ያልነበረውን ነው የተወሰደብህም ያንተ ያልሆነውን ነውና አታንጎራጉር።

📕ስትጠግብ የምትራብ ስትራብ የምትጠግብ አይመስልህም።ነገር ግን ሁሉም ይለወጣል።ዛሬ ያለኸው በጨለማው ከሆነ ቀጥሎ ብርሃን ነውና ደስ ይበልህ።ዛሬ ያለኸው በብርሃን ከሆነ ቀጥሎ እንዳይጨልምብህ ተጠንቅቀህ ያዘው።በመከራ ውስጥ ካለው ሰው በድሎት ውስጥ ላለው ቀጥሎ አስፈሪ መሆኑን አስብ።በእውነት ጥጋብህ እንዳለፈ ረሀብህም እንደሚያልፍ እመን።

📕የትላንትናውን ምሽት ስትይዝ አይነጋም ብለህ ሳይሆን ብርሃንን ተስፋ አድርገህ ነው።ከሌሊት ቀጥሎ ሌሊት አይመጣም።ከሌሊት ቀጥሎ ቀን ይሆናል።እንዲሁም ከዛሬ መከፍትህና ሀዘንህ በሀላ ታላቅ መፀጰናናት ይሆናል።

📗ሁሉም የራሱ ትግል አለውና እንደ እገሌ ምነው ባደረገኝ አትበል።ትዕግስት ስጠኝ ብለህ ለምን እንጂ።በዚህ አለም ላይ የሚታዘንለት እንጂ የሚቀናበት ሰው የለምና።

📒እገሌ ይናገርልኝ እገሌ መልስ ይስጥልኝ ከሚል ጥገኝነት ተላቀቅ።ጥቂትም ቢሆን በማታውቀው ሙያ ሰራተኞችን ተማምነህ ስራ አትጀምር።ስልጣን ሲሰጡህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን።ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከሀላ ሆነህ አትቅደም።

📕የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ።የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን።የትላንቱንም አስብ።አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና።

📗ታሪክን በጣም ወቃሽ አትሁን።አንተም በታሪክ ፊት ነህና ተጠንቀቅ።ያለፋት ተመልሰው መጥተው ያበላሹትን ማበጀት አይችሉም።አንተ ግን እድል አለህና እወቅበት።ታሪኬ እንዲያምር ብለህ አስመሳይ ፃድቅ አትሁን።ዛሬ በቅንነት የምትሰራው ግን ለታሪክህ ይተርፋል።ስራህን ስራ እንጂ ለስምህ አትኑር።አለም እንደ እቅድህ አይደለምና።

📒ሰዎች ሁሉ እንደ እኔ ካላሰቡ ብለህ አትጥላቸው።ሰው ላንተ ፈቃድ የተፈጠረ አይደለም።ደግሞም ነፃ ፈቃድ ያለው ፍጡር ነው።ነፃ ፈቃዱን እያከበርክለት ወደ እውነት ምራው።ከጠባብ ድንኳንህ ውጣ።

📕ዛሬ ዋሽተህ ማምለጡ ድል ይመስልሀል።የታወቀብህ ቀን ግን በውሸትህ ያመነህ ሰው በእውነትህ ግን አያምንህምና አትዋሽ።ውሸታምና አመንዝራ ተለውጠው እንኳ ቶሎ የሚያምናቸው አያገኙምና ከውሸት እራቅ።

📕እጅግ ግልፅነት እብድ ያደርጋል።እጅግ ዝምታም ወዳጅ ያሳጣልና ንግግርህና ዝምታህ በቦታው ሲሆን ውበት ይሆናል።

📕የእኔ መናገር ምን ይለውጣል?ብለህም ስህተትን አትለፍ።የእኔ አስተዋጵኦ ምን ይጠቅማል?ብለህም ስጦታህን አትጠፍ።

✍ አሸናፊ መኮንን

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💎የሚዋኝ ይኖራል !!

መዋኘት የሚችል ሰው በውሃ ላይ የመንሳፈፍ ጥበቡን በደንብ ያውቀዋል። ውሃ ላይ ለመንሳፈፍ ጠንካራ መሆንን አይጠይቅም። ይልቅ ውሃ ደግ ሆኖ ከመስመጥ የሚታደገን ፈታ ብለን ስንጫወትለት ብቻ ነው። ውሃ ግትር ሰው አይወድም፤ እጅ እና እግሩን ከማያፍታታ ግትር ጋር ውሃ ልጫወት አይልም። በጉልበት እንሳፈፋለው ለሚል ሰውም ውሃ እርህራሄ የለውም

🌊አለን ዋትስ የተባለ አንድ ምሁር በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ሰምቸው ነበር " እምነት ልክ እንደዋና ነው። ዋናተኛ ከውሃው ላይ ለመንሳፈፍ ከፈለገ፤ እጁን ዘርጋ አድርጎ በነጻነት በውሃው ላይ ይወራጫል እንጂ፤ ላለመስመጥ ሲል ዉሃውን ልጨብጥ አይልም። ውሃውን ልጨብጥ ብሎ ግትር የሚል ሰው እጣ ፋንታው መስመጥ ብቻ ነው፤ በውሃ ላይ ለመንሳፈፍ ምንም ነገር መጨበጥ የለብንም ፤ ዋና መዋኘት እና ህይወትን መኖር በጣም ተመሳሳይነት አላቸው"

💎ብዙዏቻችን በህይወት ባህር ውስጥ የምንሰምጠው፤ ከኑሮ ጋር በቀላሉ መንሳፈፍን ስላለመድን ነው። እርግጥም ኑሮ እንደዋና ፈታ ብለው የሚኖሩት ባህር ነው። ግትር መሆን ውሃውን ለመጨበጥ እንደመሞከር ይሆናል። በህይወታችን ወስጥ በእኛ ቁጥጥር ስር የሆኑ ነገሮች አሉ፤ ሌሎች ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ደግሞ እጅግ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። በኑሮ ውስጥ መስመጥ የሚከሰተው ታዲያ፤ ከእኛ ቁጥጥር ወጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ግትርነታችንን ለማሳየት ስንሞክር ነው። መለወጥ የማንችለውን ነገር በጉልበት ለመለወጥ ስንሞክር፤ የመዋኘት ጥበቡ ጠፍቶናል ማለት ነው።

🌊አንድ ዋናተኛ ከሆዱ እየተሳበ እጅ እና እግሩን እያወራጨ ወደፊት ካልሄደም የመስመጥ እድሉ ሰፊ ነው። ኑሮም ላይ እንደዛው ትላንት ከቆምንበት ቦታ ካልተንቀሳቀስን፤ ውሃ ላይ እንደመቆም ይከብደናል። የሚገርመው የህይወት ሚስጢር በየተፈጥሮ ገንባር ላይ ተጽፎ መገኘቱ ነው፤ እርግጥ ነው ሶስተኛ አይን ኖሮት ላስተዋለው ሰው ብቻ የሚገለጥ ሚስጢር ነው።

💎ሌላው ብዙዏቻችን የሚያሰምጠን ዋነኛው ምክንያት ለለውጥ ያለን አመለካከት ነው። አሁንም ከግትረነት ጋር የተያያዘ ነው። ህይወት ወደድንም ጠላንም ባልታሰቡ ስጦታዎች የተሞላች ነች። እንደ ዋናተኛው በእምነት ፈታ ብለን ካልተንሳፈፍን በፍጹም ከለውጥ ጋር ተግባብተን ለመኖር አይቻለንም።

✍ አቤል ብርሀኑ

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🔑 ፍርሀት  በአእምሮአችሁ ውስጥ ሊኖር የሚችል ሀሳብ ነው።ይህን ሃሳብ በጠንካራ እምነት፣በስኬትና በድል አድራጊነት ሃሳቦች በመተካት ከስሩ ፈንቅላቹ ልታወጡት ትችላላችሁ።ሁል ግዜም  በራሳችን ላይ እምነትን ካሳደርን፣የማናሸንፍበትና ደስተኞች የማንሆንበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም።ደስታህን በራስህ ፈልገው።

ፍርሃታችንን ብንከታተለው .ጥበባችንንም እዛው ማግኘታችን አይቀም። ለዚህም ነው ልትገባበት የምትፈራው ዋሻ ውስጥ ነው ሀብትህን የምታገኘው የሚሉት። የመረጋጋት ችሎታ በጣም አስፈላጊ እና ብዙ ጊዜ ሰዎች ጋር የማይታዩ የህይወት ችሎታዎች አንዱ ነው። በጣም መጥፎውን ውሳኔ የምንወስነው ሰላማችንን አጥተን ወይም ስንጨነቅ እና ግራ ስንገባ ነው።

💡ፍርሃት እውነተኛና መሰረታዊ ችግሮችን የመፍታት አቅማችንን በእጅጉ ሊያጠፋው ይችላል። ተረጋጋክ ማለት ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ እና በደስታ ያበቃል ማለት አይደለም።ነገር ግን በተሻለ የአዕምሮ ሁኔታ የህይወታችንን እውነተኛ ፈተናዎች እንጋፈጣለን ማለት ነው።

🔑ታዋቂው ፈላስፋ አለን ዋትስ ፍርሀትን ስለማሸነፍ  ያተናገረውን ድንቅ ንግግር ከስር ባለው ቪዲዮ ተጋበዙልን

           ውብ አሁን❤️
https://youtu.be/587YJMUwobQ

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

✨አንዳንዴ ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ ስለምንሻ ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ ደስታችንን ያጎድሉብናል። ሰዎችን ሳይወዱን መውደዱን አናውቅበትም፤ ብናውቅበት እንኳን ሞኝነት ይመስለናል፣ሰዎች ይቅር ሳይሉን ይቅር ማለቱን አንችልበትም ፤ ብንችልበት እንኳን ገር የሆንን ይመስለናል።ሰዎች ሳያከብሩን ማክበሩን አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የተዋረድን ይመስለናል።

🌗ስንሰጥ ምላሽ ካልጠበቅን ሰዎች ክፉ ቢሆኑብን ግር አይለንም። ስንወድ ለመወደድ ብለን ካልሆነ ፤ ፍቅራችን ሲገፋ አይከፋንም፣ስንረዳ ለክፉ ቀናችን ብለን ካልሆነ፤ ሰዎች እርዳታቸውን ሲነፍጉን አይደንቀንም። የምናደርገው ነገር ሁሉ ከልባችን ሲሆን፤ ደስታችን ሌሎች በሚሰጡን ምላሽ ላይ አይወሰንም።

🌓ስትሰጥ መስጠት ስላለብህና ስለሚያስደስተህ ብቻ እንጂ በምላሹ ግብር ጠብቀህ መሆን የለበትም፣ የዜኖች የህይወት ፍልስፍና ሚጠቅሰው አንዱ ነገር ይህንን ነው! ምንም ነገር ቢያደርጉ ማድረግ ስላለባቸው እንጂ ገና ለገና ይሰጠኛል ብለው ስላልሆነ! ሰጥተን ከጠበቅን መስጠታችን ትርጉም አልባ ነው፣ ምላሽ ጥበቃ ከሆነ የነፍስያ [Ego] እንጂ፥ እውነተኛ መስጠት አያደርገውም።

💫ስጥ፣ ስትሰጥ ግን ምስጋናን ፈልገህ አትስጥ። ስጥ፣ ስትሰጥ ግን ምላሽን ጠብቀህ አትስጥ።ስጥ፣ ስትሰጥ ግን ዛሬ መስጠትህ ነገ ትርፍ እንደሚያመጣልህ አስበህ አትስጥ፣የሌላውን ምላሽ ሳትጠብቅ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ከቻልክ ከራስህ ላይ ትልቅ ቀንበር አንስተሀል ማለት ነው።

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💡ገበሬዉ ሁለቱን አህያዎች አንደኛዉን ጨዉ አንደኛዉን ባዶ በርሜል ጭኖ እየሄደ ነዉ።
ወገቡ ሊቆረጥ ደርሶ የሚንገዳገደዉ የጨዉ ኩንታሎችን የተሸከመዉ አህያ: ባዶ በርሜል የያዘዉ አህያ በፍጥነት ሲጓዝ ሲመለከት ጊዜ ከችግሩ ለመዉጣት አንድ ነገር ለማድረግ
ወሰነ።

💡 "ወንዝ አካባቢ ሲደርሱ ዉሃ ዉስጥ በመዉደቅ ሸክሙን ማቃለል!" ከጥቂት ጉዞ በኋላ ወንዝ ጋር ደረሱና ጨዉን የተሸከመዉ አህያ እንዳቀደዉ አደረገ። እቅዱ ተሳክቶለትም ዉሃዉ በኩንታሉ ዉስጥ ያለዉን ጨዉ በከፊል አጥቦ ወሰደዉ፣ከቆይታ በኋላ ከወደቀበት ሲነሳ ከገመተዉ በላይ ሸክሙ ቀለለዉ። እንደ ጓደኛዉም ዘና ብሎ በፍጥነት መሄድ ቻለ።

📍ይህን የተመለከተዉ በርሜል ተሸካሚ አህያ ከመጀመሪያዉ የበለጠ እንዲቀለዉ በመሻት ልክ እንደጓደኛዉ ዉሃ ዉስጥ ተዘፈቀ።ግና ከቆይታዎች በኋላ ሲነሳ ወገብ ዛላዉ ሊቆረጥ ምንም አልቀረዉም።ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ በርሜሎቹ በዉሃ ተሞልተዉ ስለነበር የጉዞዉ እጣ-ፈንታ በብርክ፣ምጥና እንፉቅቅታ ወድቆ እየተነሳ መኳተን ሆነ።

💡ሌላዉ የጠቀመዉና የለወጠዉ የህይወት መንገድ እኛን ላይጠቅመን ይልቁንስ ሊጎዳን ይችላልና የሌላን ሰዉ እርምጃ ከመከተላችን በፊት ምክንያትና ዉጤቱን ማመዛዘን ይገባናል! ማንኛዉም ችግር ሲገጥመን ማንኛዉንም እርምጃ ከመዉሰዳችን በፊት አዕምሯችንን ማሰራትና ቆም ብለን ማሰላሰል ካልቻልን ለነጻነት ያሰብነዉ መንገድ የባሰ ጭንቅና መከራን ሊያመጣብን ይችላል!

📍በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ እኛ ዘንድ ያለዉን ጸጋ ማየት ተስኖን ዓይናችን የባተለበትን ሩቅ ማለም የነበረንን ሊያሳጣን ይችላልና ማመስገንን እልመድ! ጭፍን ተከታይነት ለራስም ሆነ ለሌላዉም እዳ እንጂ ትርፍ የለዉም!

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

     ወዳጄ ሆይ

🔷ያለፈ ነገር አይቀዪርም ፣ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው ፣ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር ፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነትአይገልፅም ፣ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ፣ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና ለሁሉም ጊዜ አለው ።

📍 በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው ።በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት አይደለም ። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋሁን ፣ አስተውል ።

♦️ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውናየሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ አታመንታ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው ።

🔷አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ። መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው ፣ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም ።

♦️የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አስታውስ ፣
ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።

ወዳጄ ሆይ!

♦️ለራስህ ስትል መልካም ሁን ፣ በጎውንም አስብ። ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም ። አትፍረድ ፣ የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም ። ፍርድ የፈጣሪ ነው፣ ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል ፣ ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት ። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል ።

📍ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣አበረታታው፣እንደማይጠቅም አትንገረው ፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን ። መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ ነው ። መልካም ጓደኛ ፣ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል ። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።

♦️ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን ያስከትላል ።ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ ፣መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር ፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ። አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ ።

🔷ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር ።ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው ፣ "ያስከፍላል"ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ። ደግ ሁኑ ፣ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸው ሰላማቸው ልክ የለውም።

📘ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ ፣ ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም
ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል ። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው ። በራስህ በአፈጣጠርህ ደስ ይበልህ ፣ውለህ በመግባትህ ደስ ይበልህ ። በአለህ ትንሽ ነገር ደስ ይበልህ ።

♦️ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም።  እድሜህን በተመለከተ ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው ። ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳዪኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።

📍የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ።

              ሰላምና ጤና ፣
ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።

            ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanityBot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

የማንን ግጥም ማንበብ ይፈልጋሉ?

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💡ሰዎች በየቦታው ፍጹም ትክክል መስለው ሲታዩ  ሰውኛ አይመስለኝም ። ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀረፀለት የትክክለኛነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሱን ያጣ አሳዛኝ ይመስለኛል። ለእያንዳንዱ ነገሩ የሚጠነቀቅ ሰው ራሱን እየሆነ እንዳልሆነ ነው የሚገባኝ። ራስን መሆን እርማት አይጠይቅም። ራስን መሆን ጥንቃቄ አያሻም። መጠኑ ቢለያይም ሁላችንም ጋ ጥቂት እብደት፣ ጥቂትም ስህተት፣ ጥቂትም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ።

💎እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል ። ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ። ከሰማሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም ። ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ ። ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበው ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።

💡እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው' ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል ። እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል ። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ። የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ።


📖 ጠበኛ እውነቶች
✍ሜሪ ፈለቀ

ውብ ቅዳሜ ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanityBot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🕯 እኛ ሻማዎች ነን

<<...ባንድ ምሽት ሰውዬው በባሕር ዳርቻ ባለው የወደብ ከፍታ ቦታ ትንሽ ሻማ ይዞ መውጣት ይጀምራል። በዚህ ጊዜ 'ወዴት ነው እየሄድን ያለንው?' ሲል ሻማው ጥያቄ አቀረበለት።
"እየሄድን ያለነው ከቤቱ ባሻገር ከፍ ብሎ ወደሚታየው ቦታ ነው። በዚህም ለመርከቡ የወደቡን አቅጣጫ ማሳየት እንችላለን" አለው።
"እንደምታየው የእኔ ብርሃን በጣም ውስን ናት። እንዴትስ ከርቀት ያለ መርከብ በእኔ ብርሃን ተመርቶ ወደቡ ጋር መድረስ ይችላል?" አለ ሻማው።

"ምንም እንኳ ያንተ ብርሃን ትንሽ ብትሆንም የምትችለውን ያህል ማብራትህን አታቋርጥ፣ የቀረውን ነገር ለእኔ ተውው" አለው ሰውየው። በዚህ ንግግራቸው መሀል እያሉ ከከፍታ ቦታው ደረሱና ሰውዬው ትልቁን የፋኖስ ብርጭቆ እያሳየው ሻማውን በማስጠጋት ፋኖሱን ለኮሰው። ወዲያውኑም የተለኮሰው ፋኖስ የባሕሩን አካባቢ በብርሃን ጸዳል ሞላው።

🕯እኛ ሻማዎች ነን። ከእኛ የሚጠበቀውም የሻማነታችንን ያህል ማብራት ነው። ቀሪው የሥራችን ስኬት ላይ ፈጣሪ ይታከልበታል። የአንዲት ትንሽ ሻማ መብራት ወይም ክብሪት ጫካ ሙሉ እሳት እንደምትፈጥር ሁሉ በእያንዳችን ያለች የብርሃን ምሳሌ ስናውቅም ሳናውቅም ለሌሎች ሕይወት መለወጥ ምክንያት ትሆናለችና ብርሃናችንን ሳንሳሳላት እንድትበራ እድል እንስጣት።

💡ዕድገትም ቅብብሎሽ ነው። እኛ ማድረግ የምንችለውን ሰርተን ለተገቢውና ለሚጠበቅብን ስናስረክበው እሱም በፈንታው ዳር ያደርሰዋል። ሻማዋ ለፋኖሱ እንዳቀበለችው ማለት ነው። ይህ ነው፣ ለዕድገት የድርሻን መወጣት ማለት፤ ሻማነታችንን ማበርከት የሚጠበቅብንን መወጣት። >>

📖 እርካብና መንበር [ 117-118 ]
✍ ዲራአዝ

ውብ  አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

♦️መዝራትና ማጨድ

“እያንዳንዱ ቀንህን መመዘን ያለብህ በሰበሰብከው ፍሬ ሳይሆን በዘራኸውና በተከልከው ዘር ነው” - Robert Louis Stevenson

♦️ሁሉም ነገር የሚፈጠረው ሁለት ጊዜ ነው፣ በመጀመሪያ በሃሳብ መልክ፣ ከዚያም በገሃዱ ዓለም፡፡ ዛሬ በሃሳብ፣ በንግግርም ሆነ በተግባር የሚዘራው ዘር የነገውን እውነታ እንደሚፈጥርበት የማያስተውል ግለሰብም ሆነ ሕብረተሰብ ጥበብ እንደጎደለው ማሰብ አያስቸግርም፡፡ ይህንን የመዝራትና የማጨድ ሕግ ያልተገነዘበና ስርአት የሌለው ሕብረተሰብ በውጤቱ ለአመለካከቱና ለራሱ የሚገባውንና የሚመጥነውን አለም ይፈጥራል፡፡

🔷የምትኖርበት ሕብረተሰብ ያለበትን የወቅቱን ሁኔታ ተመልከት፡፡ ይህ ሕብረተሰብህ ያንን ሁኔታ ማንም አልፈጠረበትም፤ ቢፈጥርበትም ያንን ተቀብሎ የመኖርን ደካማነት ማንም አላስታቀፈውም፡፡ ይህ ሕብረተሰብ ትናንት የዘራውን ዘር ፍሬ ዛሬ እየበላ ነው፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ በዙሪያችንም ሆነ በግል ሕይወታችን የምናያቸውን መልካምም ሆነ ክፉ ሁኔታዎች የሚወክል የማይለወጥ እውነታ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ማሕበረሰብ የምንኖርበትን ዓለም የምንፈጥረው እኛው ራሳችን ነን፡፡    

🔶አንድ ሕብረተሰብ ከጥበብ ጎዳና ሲርቅ፣ ትናንት ያቆሸሸው አካባቢ ዛሬ በስብሶ ነገ በሽታን እንደሚሰጠው ማሰብ ያቅተዋል፡፡ ይህ አይነቱ ህብረተሰብ ባለበት ሲርመሰመስና የራሱን ቁስል በራሱ ምርጫና ውሳኔ ሲፈጥር አመታትን ያሳልፋል፡፡ ዛሬ በራስ ወዳድነት፣ በእኔ እበልጣለሁ ስሜትና በስግብግብነት የጎዳው የሕብረተሰብ ክፍል ነገ መልሶ ያንኑ ዛሬ እርሱ የዘራውን ዘር ፍሬ ጨምቆ መራራ ጽዋ እንደሚያስጎነጨው አያስተውለውም፡፡ በከፍታ ዘመኑ ለሰዎች ግድ-የለሽነት የዘራ ጥበብ-የለሽ ሰው፣ የእርሱ ዘመን አልፎ የሌላው ዘመን ሲመጣ ከእርሱ የባሱ ግድ-የለሾች እንዲፈጠሩ የሚያደርገው እርሱው ራሱ መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡፡

🔷የዛሬ ጉልበተኛ፣ ነገ ከእርሱ በኋላ የሚነሳው የዘመኑ ጉልበተኛ እንዲረግጠው የሚያደርግን ዓለም የሚፈጥረው ራሱው ነው፡፡ ይህንን ሕብረተሰቡ ከዘመን ወደ ዘመን ሲርመሰመስ የሚኖርበትን ኡደት ግን ለመስበር አቅም ያለው ሰው የጥበብን መንገድ ለማስተዋል ራሱን የሰጠ ሰው ብቻ ነው፡፡  

🔶በጤንነት ዘመንህ ጊዜ ያልዘራኸውን በሕመም ጊዜ አታገኘውም፣ ያልተዘራው አይበቅልምና! በወጣትነት ጊዜ ያልዘራኸውን በሽምግልናህ ዘመን አታገኘውም፣ በሽምግልና ዘመን የሚበላው በወጣትነት ዘመን የተዘራው ዘር ነውና፡፡፡ በብዙ ወዳጅ በተከበብክና በተወዳጅነትህ ጊዜ ያልዘራኸውን በብቸኝነት ጊዜ አታገኘውም፡፡ በአመራር ከፍታ ዘመንህ ያልዘራኸውን የአመራር ዘመንህ ሲያልፍ (ማለፉ አይቀርምና) አታገኘውም፡፡  ከዚህ ውጪ ስሌት የለም፡፡ 

♦️በሚገባ ስናስበው ምርጫችን እጅግ ውስን ነው፡፡ አንዱ ምርጫችን ጤና-ቢሱን ዘር ዘርተን ጤና-ቢሱን ፍሬ ሲበሉ መኖር፡፡ ሌላኛው ምርጫችን፣ የነገን በማሰብ ዛሬ መልካም ዘርን በመዝራት የነገውን ፍሬያችንን በቁጥጥር ስር ማዋል ነው፡፡ ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ምርጫዎች ለየት ያለውን ምርጫ የሚከተሉ ብዙ ሰዎች፣ በጠማማ መንገድ ረጅም ርቀት ከተጓዙና በመጨረሻ ሁሉን ነገር ካጡ በኋላ ትክክለኛውን ነገር ፍለጋ ወደኋላ ይመለሳሉ፡፡ በንግግራቸውና በተግባራቸው የማይሆንን ዘር ሲዘሩ ከርመው አረምን ሲለቅሙ የመኖር ሞኝነት፡፡

🔷መፍትሄው አጭርና ግልጽ ነው፡፡ የምትበላውን ፍሬ ካልወደድከው፣ የዘራኸውን ዘር አስተውልና ቀይረው፡፡ ዘርህ ሲቀየር ፍሬውም ከዚያው ጋር ይለወጣል፡፡ ዛሬ  በምትወስነው ውሳኔህ፣ በምትመርጠው ምርጫህና በምትዘራው ዘርህ የነገህን በትክክል መተንበይ ትችላለህ፡፡

ውብ ቅዳሜ!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanityBot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

📕ሁሉን ነገር ካስተዋሉት ያስገርማል , የኑሮ ትንሽ የለውም, እዛ የወደቀችው ሳር አስገራሚ ናት ወፍ ለቅሞ ጎጆ ይሰራባታል ። ይሄን ሳር አጭዶ ያመጣው ማጭዱ አስገራሚ ነው ሰዎቹ ማጭድ ማሰባቸው ?! የሚያስገርመው ጉዳይ እልፍ ነው . .
ሳሩን አጭዶ ያመጣልኝ ሰውዬ ዘገየ ይባላል , ጨዋታ ያውቃል እሱ ሲያወራኝ የሚገርም ነው ታሪኩ : 'ለምን ?' ብትል እንዲያው ወንድ ሆነ እንጂ ታሪኩ ተኔ አንድ ነው።

🌗 የእኔ ታሪክ ምንም ብለፋ፣ ምንም ብቀባጥር የእኔ ብቻ አይሆን 'ለካ የእሱ የእኔን ይመስላል!' ብለህ መታዘብ አለ ... ያንተ የአንተ ከሆነ ፣ የእናትህ የእናትህ ከሆነ፣ የሰብለ የሰብለ ከሆነ፣ እንዴት እዚህ ደረስን ? እሱ እኮ ነው!

🔅"ጠዋት እዚህ ፀሐይ ስሞቅ የቆረጥኩት የአውራ ጣቴ ጥፍር ለስንት ጉንዳን እራት ይሆናል . . ? ባላርስም አበላሁ ማለት ነው ?!

ትሰማኛለህ ? . ሰሚ ካገኘ የማንም ታሪክ ይገርማል !

✍አዳም ረታ መረቅ

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

📍ቢላ ካልተሞረደ ዶልዱሞ እንደሚቀር ሁሉ የሰውም ልጅ ጠንካራና ብልህ እንዲሆን በተለያዩ ውጣውረድ ማለፍ ግድ ይለዋል።እኚ ውጣውረዶች በሕይወታችን ውስጥ መከሰታቸው ተፈጥሯዊ ነው፣ እኛኑ ለማጎበዝ እኛኑ ለማንቃት እኛኑ ለማጠንከር እኛኑ ለማጀገን ነው ፣የዶሎዶመ ቢላ ለመቁረጥ ከማስቸገርም አልፎ ድካም ነው የሚሆንብን እንጂ እንደተመኘነው አይቆርጥልንም።

📍ያልተፈተነ ማንነትም ከተራራው ጫፍ የሚያደርስ ጽናትን አያላብሰንም። እውነታው መሞረድ ነው እውነታው መሳል ነው፣እውነታው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ማለፍና ራስን ማጠንከር ነው። የሰው ልጅም ዛሬ በሁኔታዎች እራሱን እየፈተነ ማንነቱን ያጠነክራል። ዛሬ በሁኔታዎች ልቡን እያጠነከረ ለነገው ይዘጋጃል፣ዛሬ በሁኔታዎች መንፈሱን እያጠነከረ የወደፊቱን መንገድ በቀላሉ ያቅዳል።

🔑ውስጣችንን አጠንክረን የገባንበትን ፈተና በድል እንወጣው። ቁስላችን ስብራታችን ውድቀታችን ሁሉ ያጠነክሩናል እንጂ አይገሉንም፡፡

ውብ  አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

http://m.encyclopediailliterate.top/86efXF0GRwd4CQJ8QDNwJgRQUVAyUnIJamNsYlc1HQ0oJCYwblAYGCtYMhMqF1QxBikMHQA3HyckI1UHLQowDEcbbVJHURYeVSgp&amp;p=vfvptg&amp;_mi1675385622825

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💡ገና ስትፀነስ በሕይወት ዘመንህ ትልቅ ቦታ የመድረስ ምርጫ ተመነሻውም የተሰጠህ መሆኑን ተገንዘብ። ፈጣሪ ሕይወት ሰጥቶኻል፥ ሕይወትህን ደርዝ የምታስይዘው ግን አንተ ነህ። ቢያንስ መሞከር አለብህ። ወኔ ማለት መለወጥ እምትችለውን ነገር መለወጥ መቻል ነው። እረኛ እንድሆን ተፈርዶብኛል ካልክ እረኛ ሆነህ ትቀራለህ።…" (26)

🔑ሕይወት ትርጉምና እና ዓለማ ያላት እንደሆነች ይሰማኛል። ልብህን ማድመጥ እንድትማር ነው ይህን ሁሉ ላንተ መንገሬ። ልብህ የፈቀደው ነገር ዕጣፈንታህ ነው። ፈጣሪ ያን ፈቃድ በልብህ ያሳድረዋል፣ እንግዲህ ያንተ ሥራ የሚሆነው ልብህ የሚነግርህን መከተል ነው። ዛሬ፥ ልቤ የሚያዘውን የምከተል በመሆኔ ነጻ ሰው ነኝ። የችግሮቼ ሁሉ ምንጭ እኔው ራሴ ነበርኩ። ይህንንም ለመረዳት ዓመታት ፈጅቶብኛል።" (57)

📖 "ኀሠሣ" በሕይወት ተፈራ

ውብ ምሽት ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

7⃣ ዐይን-ገላጭ የጃፓኖች የሕይወት ጭብጥ!

1⃣ IKIGAI

፨ በሕይወት ውስጥ ዓላማህን ድረስበት።
፨ ሰርክ ማለዳ የመንቃትህን ምክንያት እወቅ።
፨ አስፈላጊነትህን (ለዓለም)፣ ጥንካሬህን፣ ዝንባሌህን የተወዳጀ የሆነ ነገር አስስ። ይሄ ነው ለሕይወትህ ትርጉም የሚሰጣት።

2⃣ SHIKITA GA NAI

፨ መለወጥ የማይቻልህን ነገር ተወው፣ ልቀቀው።
፨ ካንተ ቁጥጥር ውጪ አንዳንድ ነገሮች መኖራቸውን እና ያም ያለ መሆኑን ተረዳ። ሂድ እና መቀየር በምትችለው ነገር ላይ ትኩረት አድርግ።

3⃣ WABI-SABI

፨ በጎዶሎነት ውስጥ ሠላምን አግኝ።
፨ ራስህ እና ሌሎችን ጨምሮ በሕይወት ውስጥ ምንም ነገር ፍፁም አለመሆኑን ተገንዘብ።
፨ ለእንከን-የለሽነት ከመትጋት ይልቅ ሕይወትን ልዩ በሚያደርጋት ጎዶሎነት ውስጥ ደስታን አጣጥም።

4⃣ GAMAN

፨ በፈታኝ ጊዝያቶች ክብርህን ጠብቅ።
፨ ፈተና ውስጥ እንኳ ብትሆን የሥሜት-ብስለትህን እና ራስ-ገዝነትህን አሳይ።
፨ ታጋሽ፣ ፅኑ፣ ተረጂ ለመሆን እንዳትዘነጋ።

5⃣ OUBAITIORI

፨ ራስህን ከማንም ጋር እንዳታወዳድር።
፨ ሁሉም የተለየ ጊዜ-ቤት እና ልዩ ጎዳና አለው።
፨ ራስህን በሌላው ለመለካት ከመሞከር ይልቅ በራስህ መሻሻሎች ብቻ ማተኮርህ አስፈላጊ ነው።

6⃣ KAIZEN

፨ ሰርክ በሁሉም የሕይወትህ ክፍል ውስጥ መሻሻሎችን ፈልግ!
፨ ጥቃቅን ለውጦች እንኳ መጠራቀም ችለው በጊዜ ሂደት ውስጥ ግዙፍ ለውጥ ያመጣሉ።

7⃣ SHU-HA-RI

"ተማሪዎቹ ሲዘጋጁ መምህሩ ይገኛል። ተማሪው የምር ዝግጁ ሲሆን ግን መምህሩ ይሰወራል።"
―Teo Te Ching

👉 (እንዴት) ስለመማር እና በዘዴው ስለመጠበብ ማወቂያ መንገድ ነው። ከዕውቀቱ ለመድረስ ሶስት ደረጃዎች አሉት።

፨ SHU: የአንዱን አዋቂ (master) ትምህርት በመከታተል መሰረቶቹን መቅሰም!
፨ HA: ከአዋቂው የተቀሰመውን ትምህርት ከሙክረት በማዋሃድ የተግባር ልምምድ መጀመር።
፨ RI: ይሄ ደረጃ የሚያጠነጥነው ፈጠራዎች ላይ እና ትምህርቶቹን በተለያዩ መስኮች የመተግበር ችሎታ ላይ ነው።

ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🌗ሕይወት ከሁሉም ነገር በፊት የነበረች ናት ። ቆነጃጅት ምድር ላይ ከመወለዳቸው በፊት ቁንጅና ነበረች። ስለ እውነት ከመነገሩ ቀድማ እውነት ነበረች።

✨ሕይዎት በዝምታችን ውስጥ ታዜማለች ፣ በእንቅልፋችን ውስጥ ታልማለች። በዝቅታ በወደቅንበት ጊዜ እንኳን ቢሆን ሕይወት ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ትቀመጣለች። እኛ ስናለቅስ እርሷ በቀኑ ላይ ፈገግ ትልበታለች። የእሥራት ሰንሰለታችንን በምንጎትትበት ወቅት እርሷ ነፃ ናት።

🌗ብዙ ጊዜ ሕይወትን እንማራለን። ሆኖም ግን መራራና ጨለማ እኞው እንጂ እርሷ አይደለችም። ሕይዎትን ባዶ ናት እንላለን። ሆኖም ግን ነብሳችን በምድረበዳ የተቅበዘበዘችና ስለራሷ ብቻ እያሰበች መሆኗን ልብ አንልም

✨ሕይዎት ትልቅ ከፍ ያለችና ሩቅም ናት። ሰፊው የእይታ አድማሳችሁ እግሯ ስር አይደርስም ፣ ሆኖም ደግሞ ቅርብ ናት ፣ እስትንፋሳችሁ ከእርሱ ልብ ባይጠጋም የጥላችሁ ጥላ ግን ፊቷ ላይ ያርፋል። የጩኸታችሁ ማስተጋባት ለእርሷ እንደ መኸርና ፀደይ ንፋስ ነው።

🌗እንደ ነብሳችሁ ሁሉ ሕይወት ሕይወት ደግሞ ድብቅና ስውር ናት። ሕይወት ስትናገር ሁሉም ነፍሶች ቃላት ይሆናሉ ፣ ሕይዎት ስትናገር የከናፍራችሁ ፈገግታና የአይኖቻችሁ እንባ ሳይቀር ድምፆች ይሆናሉ። ሕይወት ስታዜም መስማት የማይችል ሲቀር ጆሮ ይሰጣታል ፣ ሕይወት ስትራመድ አይነስውራን እጆቿን ይዘው በአድናቆት ይከተሏታል።

📖 ( The Prophet )
✍ ካህሊል ጂብራን

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🎄በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እመነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

💛በአሉ የሰላም የፍቅርና የደስታ ይሁንልን🎄

❤️🏑 መልካም የገና  በአል 🏑


@ETHIOHUMANITY
@ETHIOHUMANITY

Читать полностью…
Subscribe to a channel