ethiohumanity | Education

Telegram-канал ethiohumanity - ስብዕናችን #Humanity

30703

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Subscribe to a channel

ስብዕናችን #Humanity

በአረም የተወረረ እርሻ አትሁን!

አንዳንድ ሰው የአረም እርሻ ነው። ብዙ የማይጠቅሙ ሃሳቦችን ተሸክሞ ይዞራል፣ አንተ ግን የማይጠቅሙ ሃሳቦችን ከአእምሮህ ጓዳ ቶሎ ቶሎ አጽዳ!

በረከቶችህን እንጂ ጉዳቶችህን አትቁጠር፣አእምሮ ሰነፍ ጮማ ስጋ ነው። መጥፎም ይሁን ደግ የተነገረውን ለቀም ነው።ለአእምሮህ የምትነግረው ደግ ደጉን ይሁን። አለዚያ መጥፎ ሃሳብ ከሰጠኸው ያንን ይዞ ይመርዝሃል።

አዘውትረህ የምታስበው ሃሳብ በውስጥህ ይደድራል። ውሎ አድሮም ይገዝፋል፣ ሃሳብ ለአእምሮ፣ ስፖርት ለጡንቻ እንደሆነው ነው።መጥፎ ምግብ ሰውነትን ይመርዛል።መጥፎ ሃሳብ አእምሮን ይመርዛል።በመጨረሻም ሰውየውን ገላፈቻ (ከጥቅም ውጭ) ያደርገዋል።

መጥፎ ሃሳብን አታመንዥክ የጥላቻ ሃሳብን አታመንዥክ። ይልቅስ መጥፎ ሃሳቦችን ከአእምሮህ እያጸዳህ በመልካም ሃሳቦች ተካቸው፣ስለሰው ስታስብ የሰውየውን መልካም ጎን ለይተህ ለማሰብ ሞክር፣ ችግርን ተጋፈጥ። መልካም ሃሳብን ዝራ፣ መጥፎን በመልካም ሃሳብና ድርጊት ተዋጋ።

ይህ ሁሉ ሆኖ ከመጥፎነት አልመለስ ለሚሉ በመጥፎ ሃሳባቸው እንዳትጠመድ ከእነርሱ ራቅ። ሁሌም ደግ ደጉን እናስብ። ደግ ደጉን እንሥራ። መልካምነት ሌላው ቢቀር የአእምሮ ሰላም ይሰጣል። ከጨጓራ ህመም ያተርፋል።

ነገ ሲነጋልህ፣  ተነስና በረከቶችህን ቁጠር። ለጤናህ ፈጣሪህን አመስግን። ለቀጣዩ ቀን ውሎህ ሰላምና ስኬት ፈጣሪህን በጥበባዊ ጸሎት ለምን። በዚህ ምን ትጎዳለህ? የተሻለ ምርጫስ አለህ?

የቀን ውሎህን አቅድ። ለሥራህ ተዘጋጅና ቆፍጠን ብለህ ውጣ። ፈገግታ ከፊትህ አይጥፋ! ጎበዝ ገበሬ ሁን! የጎበዝ ገበሬ እርሻ ከአረም የጸዳ መልካም ቡቃያ ነው።

✍ Getu k toughe

ውብ ጊዜ❤️

@EthioHumanity

@EthioHumanityBot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💎 ለመቶ ሚሊየን ሰው 1 ፀሀይ ነው የምትወጣው እንጂ ለሁሉም የተለያየ ፀሀይ አይወጣም፡፡ ፀሀይ ስራዋ መውጣት ነው መሞቅ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ አዲሷ ፀሀይ አዲስ እድል አዲስ ተስፋ አዲስ ስኬት ይዛ በማለዳው ህይወትህን ልታሞቀው ስትወጣ አንተ ዛሬም በትላንት መጥፎ ታሪክህ በእንባ ጥላ ተጠልለህ ትደበቃታለህ፡፡ ሳታሞቅህ ዜናዋን ሳታበስርህ ትገባለች፡፡

💡ተፈጥሮ ሁሌም ለሁሉም እኩል ናት ፡፡ ለሁሉም አንድ ፀሀይ ነው የሚወጣው ዛሬም በፍቅር ከመኝታህ ተነስ የዛሬዋን ፀሀይ በተስፋ ሙቃት አትደበቃት ከውድቀትህ እንቅልፍ እራስህን ቀስቅስ፣ብርሃን የድምቀት መገለጫ ነው ፣ደማቅ ቀን በብርሃን ውስጥ ደግሞ ደጋግሞ ያበራል። የሚሰጠህ ውስጣዊ ስሜት በፈጠርከው ብሩህ ቀን ይወሰናል ተግባር የእምነት ፍሬ ናትና ።

💎 ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። ስኬትህ የመንገድህ ጥግ ላይ ነው፣ ከምታስበው በላይ ቀርብ ነህ፣ ትንሽ መዘግየቱ የሚመጣው ነገር ስለሚበልጥ ነው፣ ትንሽ ታገስህ መንገድህን ቀጥል ፣ ድልህ ቅርብ ይሆናል።

💡አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገሰህ ተራመድ ፤ የህይወትህ ፀሀይ መውጣቷ አይቀርም! ከጨለማው ምሽት በኋላ ሁል ጊዜ ፀሀይ ትወጣለች፣ አንተም በውስጥህ ያለውን ጥንካሬ ሰብስበህ ቀጥል።

ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🔴 ሕይወት በሚታይና በማይታይ ማዕበል የተከበበች ናት!

ሰው ሃሳቡ በግንባሩ ላይ ቢጻፍ ማን ማንን ቀና ብሎ ያያል? ደግነቱ በውስጣችን ያለውን ማንም አያውቅብንም። የምናስበውን አስበን፤ የፈለግነውን አሳውቀን የምንደብቀውን ደብቀን የመኖር ጥበቡ ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ ጥበብ ነው። ልብ በሃዘን ደምቶ ፊት በፈገግታ ሲፈካ ፤ ግንባር ኮስተር ብሎ ልብ በሃሴት ሲሞላ ፤ ጉልበት ተንበርክኮ ልብ በትዕቢት ሲቆም ፤ አፍ እንደ ማር ጣፍጦ ልብ እንደ እሬት ሲመር ፤ ማን ማንን ያውቃል ያሰኛል?!

የሰው ልጅ በሚታየውና እና በማይታየው ማዕበል ውስጥ ያልፋል፤ የሚታየው ማዕበል ሌሎች የሚረዱት እና የሚያዩት ችግራችን ሲሆን፤ የማይታየው ማዕበል ደግሞ ከሌሎች ደብቀን ለብቻችን የምንጋፈጠው ችግር ነው”።

ሌሎች የማውቁት ምን አይነት ጭንቀት ይሆን እያንዳንዳችን በውስጣችን ያለው? ምን አይነት የማይታይ ማዕበል እየተጋፈጥን ይሆን?

🔷አዎ በሰው ፊት እንስቃለን ለብቻችን ግን እንባችንን በገዛ መዳፋችን ያለማቋረጥ እናብሳለን። ከሰው መሃል ደምቀን ለብቻችን ስንሆን መግቢያ እናጣለን። ከህዝብ ፊት ከብረን በቤታችን ግን የሰው ያህል የሚቆጥረን የለም። ጠንካራ መስለን፤ ልባችንን ግን በክህደት ስብርብሩ ወጥቷል። ከላይ ሰላም የሰፈነብን እንመስላለን፤ ውስጣችን ግን በተስፋ መቁረጥ ማዕበል ይተራመሳል። ከውጪ ሲታይ ቤታችን የደመቀ ቢመስልም ውስጡ ግን እንደ ዋሻ ቀዝቅዟል። ተለቀም አነሰም ሁላችንም ለሌሎች የማይታይ ለብቻችን የምንጋፈጠው ማዕበል አለን።

🔵እናም በየመንገዳችን ስንተላለፍ ልብ እንበል፤ ሌላው ከኛ ያነሰ ትግል የሚታገል እየመሰለን ፊት አንንሳው፤ እየረገጥን አንለፈው። የኔ ችግር እና ጭንቀት ከሌላው ይበልጣል የሚል አስተሳሰብ ሲኖረን ለሌሎች የምንዘረጋው እጅ ያጥረናል። ትኩረታችን ሁሉ የራሳችን ችግር ላይ ሲሆን ይበልጥ እናማርራለን፤ ሌሎች ለብቻቸው የሚገፈጡትን ማዕበል ስለማናይ “ምነው እኔን ብቻ” እያለን የሃዘናችንን ጉድጓድ ይበልጥ ወደታች እንቆፍረዋለን።

♦️ከትዳር አጋራችን ጋር ክንድ ተንተርሰን እያደርን፤ እርስ በርሳችን የምንፋለመውን ትግል አናውቅም። ለዚህ ነው ጭቅጭቅ ሲነሳ መሸናነፍ እና እርቅ ማውረድ የሚከብደን፤ ማን የማንን ማዕበል ያያልና? እናም በየመንገዳችን የሚያጋጥሙን ሰዎች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ታሪክ አላቸው፤ በጫማቸው ሳንቆም አንፍረድ። በደቂቃ ውስጥ ያየነውን ምግባራቸውን ተንተርሰን አንፍረድ።

🔴ሌላውም እንደኔ ስሜት አለው የሚል አስተሳስብ መያዝ ስንጀምር፤ የሌላው ህመም ይሰማናል እናም ብዙ ስህተቶችን ከመፈጸም እንድናለን። ምናልባት ለብቻሽ/ ለብቻህ የምትጋፈጠው ማዕበል ካለህ በርታ… አጋዥ የለኝም ብለህ አትስጋ ፈጣሪ የማትችለውን ችግር አይሰጥህም። አንተ/አንቺ ብቻ ከሰው የተለየ መከራ አልተሰጠሽም/አልተሰጠህም እንደየአቅማችን ለሁላችንም የታደለን ነው እንጂ……ከምንም በላይ ግን እርስ በርሳችን እንተጋገዝ፤ እየተገፈታተርን መተላለፉን እናቆም ምክንያቱም ሁላችንም ለየብቻችን በምንጋፈጠው ማዕበል ደክመናልና።

                      ✍ሚስጢረ አደራው

            ውብ አሁን ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍@EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🔱 እርግጠኛ ነሽ አርግዘሻል?

ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ፡፡ ከሶስት ወራቶች በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝሆኗ እንዳረገዘች ከስድስት ወር በኋላ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች ፣ ዘጠኝ ወር ደግሞ ሌሎች ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡ የእርግዝና ስርዓቱ ቀጠለ ፡፡ ውሻዋ በየሦስት ወሩ መውለዷን ቀጠለች።

በአሥራ ስምንተኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች ፣

✨“እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ? አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? ምክንያቱም በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነናል ብለን ነበር፣ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ እና አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል ፣ ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ ምን እየሆነ ነው?

ዝሆኗም “እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፣ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው ፡፡ እኔ በሁለት ዓመት ውስጥ አንዱን ብቻ እወልዳለሁ፡፡ የምወልደው ግን ተራ እንስሳ ስላልሆነ ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል ፣ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ይንቀጠቀጣል፣ የኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን ይስባል ፡፡

✨ሌሎች እንደ መቅስፈት በሚመስል ጊዜ ነገራቸው ሲቀየርና የተሳካላቸው ሲመስልህ በነሱ አትቅና፣ እምነትህም አይጥፋ በፍጹምም ተስፋ አትቁረጥ፣ ምክንያቱም የአንተም ጽንስ የሚወለድበት ጊዜ ይመጣል፣ ምንም ጊዜ ወስዶ የማይመጣ ቢመስልም የተሻለው መምጣቱ የማይቀር ነው፣ እናም ሲመጣ ሰዎችን ሁሉ የሚያነጋግርና የሚያስደንቅ ይሆናል! የዘገየው የተሻለ ስለሆነ ነውና የራስህን ጉዞ ከሌላ ከማንኛውም ሰው ጋር አታነፃፅር !

ውብ የስኬት ጊዜ❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

✍@Ethiohumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

📍ፈጣሪ ለምን ፈጠረኝ ብለህ አስበህ ታውቃለህ?

❣እኛ የሰው ልጆች ፈጣሪ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ አናውቅም!! እሱ በጣም ድንቅ አንጎል እና ስሜት ያለበት አፍቃሪ ልብ ሰጥቶናል፣ለመናገር እና ስሜታችንን ለመግለጽ በሁለት ከንፈሮች ባርኮናል፣ ውበትን የሚያዩ ሁለት ዓይኖች፣ በሕይወት መንገድ ላይ የሚራመዱ ሁለት እግሮች፣ ለእኛ ሁለት የሚሠሩ እጆች፣ እና የፍቅር ቃላቶች የሚሰሙ ሁለት ጆሮችን ሰጥቶናል።

ፈጣሪ ሰውን ሲፈጥር የራሱን ትክክለኛ ባህሪ እንዲላበስ ነው ፤ የፈጣሪ ባህሪ ርህራሄ ቸርነት ፣ ይቅርታ ፣ ፍቅር እና ደስታ ናቸው። እኛም እሱ እንደፈጠርን ሰው ሆነን መኖር ይገባናል።

♦️ሰው ሁኖ መኖር ማለት፦ ከራስ አልፎ ለሌሎችም ማሰብ መቻል ነው፡፡ ሰው ሁኖ መኖር ማለት ሰውን መግደልና መግፋት ሳይሆን ማዳንና መደገፍ ፣ ማበረታታትና ማረጋጋት ነው፡፡ ሰዎችን ገንዘብንና ስልጣንን ፣ ጉልበትንና ጊዜን ተጠቅመው መከራ የሚያሳዩ ሰዎች ሰው ሁነው ተፈጥረው ዳሩ ግን ሰው ሁነው መኖር ያልቻሉ ወገኖች ናቸው፡፡

♦️ሰው ያለሰው ፤ ሰው ያለዙሪያው ህይወትን ሙሉ በሙሉ ሊኖራት አይችልም። ሰው ስንል ግዴታ በአንድ ጣሪያ ስር የሚኖርን ወዳጅ አይደለም፤ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ እንጂ። እኛ ከአለም ውጪ አለም ከእኛ ውጪ አንደኛችም መኖራችን አይረጋገጥም ። ለሰው ማሰብ አለመቻል ኅሊና ማጣት ነው፡፡ አንተ ያስፈለገኽና የሚያስፈልግኽ ለሌሎች የማያስፈልጋቸው የሚመስልህ ከሆነ ራስህን ፈትሽ።

ሰው አድርጎ መፍጠር የፈጣሪህ ድርሻ ሲሆን ሰው ሁኖ መኖር ግን ያንተ ድርሻ ነው፣ ማንነትን የመርሳት መድሀኒቱ ፈጣሪ ስለሆነ በምንችለው መንገድ ሁሉ ወደእርሱ በመቅረብ ማንነትን ከመርሳት በሽታ እንፈወስ!

ውብ አዳር ❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

✍@Ethiohumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

❤️ትዳርና ኃላፊነት

ትዳር ፍቅር ብቻ አይደለም። ትዳር ኃላፊነትም ነው።

🔺በትዳር ውስጥ ብዙ የሚገመቱም የማይገመቱም ጉዳዮች ሊያጋጥሙ ይችላል። ያልጠበቃችሁት እና የሚያናድዳችሁ ጉዳይ ቢያጋጥማችሁ እንዴት ታስተናግዱታላችሁ? ትቆጣላችሁ? ትጣላላችሁ? ታግሳችሁ በዝምታ ታልፋላችሁ? በይቅርታ እና እርቅ ታልፋላችሁ? ወይንስ ወደ ፍቺ ትሄዳላችሁ?

በትንሽ በትልቁ ወደ ፍቺ የሚሮጡ ባለትዳሮች በመንፈስና በአስተሳሰብ ያልበለጸጉና ራስ ወዳዶች ናቸው። አንዳንዶች ተጋብተው አንድ ዓመት እንኳ ሳይቆዩ ወደ ፍቺ ይሄዳሉ። ይሄ ልዩነትን መሸከም አለመቻል ነው፣ አለመብሰል ነው። ልዩነትን ማስተናገድ ሳትችሉ ወደ ጋብቻ አትሩጡ።

🔺ትዳር ስትመሰርቱ ኃላፊነት ያለው አኗኗር ውስጥ መግባታችሁን አስቡ። ትዳር የራሳችሁን ፍላጎት ለሌላው ማስገዛት መሆኑን እወቁ። ትዳር በሌላ ሰው ቁጥጥር ስር ራስን ለማስገዛት መፍቀድ መሆኑን ተረዱ። ትዳር ውስጥ ስትገቡ ነጻነታችሁን በተወሰነ ደረጃ እንደምትተዉ እመኑ።

🔺ትዳር ውስጥ ልጆች ይመጣሉ። ልጆች በነጻነትና በደስታ እንዲያድጉ የራስን ስሜት መግዛትና እኔ ያልኩት ብቻ ይሁንልኝ ከማለት ራስን ማቀብ ያስፈልጋል፣ልጅ ወልዶ የራሱ ጉዳይ ብሎ በትኖ የሚሄድ ከእንሰሳም ያነሰ ሰብዕና ያለው ነው። ፍሬ ለማፍራት ስንዴዋ እንኳ ራሷ እንዴት እንደምትፈርስ አታዩምን? ታድያ ከስንዴ እንኳ ታንሳላችሁ?

ኃላፊነትን ለመቀበል ካልተዘጋጃችሁ ወደ ትዳር አትግቡ፣ ትዳርን ቸኩሎ ኃላፊነትን ለመሸከም ብቁ ሳይሆኑ መያዝ አይገባም። ትዳር የዕቃ ዕቃ ጨዋታ አይደለም። ትዳር የፉክክር ቤትም አይደለም ፣ ትዳር ራስን አሳልፎ መስጠት ቢጠይቅም፣ በጥበብ ከተያዘ ደግሞ ፈተናዎች ሁሉ ቀላል ናቸው።

♦️ትዳር በህይወት የሚከሰቱ ለውጦችን የማስተናገድ አቅም ይጠይቃል። ህመም፣ የኢኮኖሚ ችግር፣ እስር ጥጋብ፣ ውስልትና፣ ንዴት፣ ጦርነት፣ ግጭት፣ ሹመት፣ ማግኘት፣ ማጣት፣... ትዳርን ይፈትናሉ። ግን ላወቁበት፣ ለበሳሎችና ኃላፊነት ለሚሰማቸው ትዳር ለማፍረስ ምክንያት አይሆኑም።

ትዳር ለመያዝ ማናችንም የመጀመሪያም ይሁን የመጨረሻም ሰዎች አይደለንም። ትዳር ውስጥ ያለ አለመግባባትም ያለና የነበረ የሚኖርም ነው። እናንተ ያጋጠማችሁ በሌሎችም የደረሰ እንጂ አዲስ አለመሆኑን እወቁ። ቁም-ነገሩ ችግርን መፍታት እንጂ ችግርን ማውራት አለመሆኑን ተገንዘቡ። ችግርን ታግሳችሁ ፍቱ።

🔺ከትዳር በፊት ሁለት ዓይናችሁን፣ ከቻላችሁም ሦስተኛውን ከፍታችሁ በደንብ እዩ፣ ፈትሹ፣ በአእምሮ ተዘጋጁ፣ ለኃላፊነት ተዘጋጁ። ትዳር ውስጥ ከገባችሁ በኋላ ግን አንድ ዓይን ብቻ ይበቃችኋል። ትዳር ውስጥ ሁሉን ካልሰማሁ ሁሉን ካላወቅሁ አትበሉ። ሁሉን ማወቅ አይጠቅማችሁም።

🔺መጀመሪያ አይታችሁና አምናችሁ ለኃላፊነት ተዘጋጅታችሁ አግቡ። እንደተጋባችሁ ለመውለድ አትቸኩሉ። ምንም ምንም ምንም ቢሆን ግን ወልዳችሁ አትፋቱ፣ ከፀሓይ በታች አዲስ ነገር የለም! ወልዶ የሚፋታ ግለሰብ ፣ ቤተሰቡን ብቻ ሳይሆን አገር ያፈርሳል።

✍Getu k. Toughe

         ውብ ምሽት❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

✍@Ethiohumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💚  ንቁ የሃሳብ ሰው ስንሆን ምንሰራው ዓለም ነው ለዚህ ደሞ የስብዕና ግንባታ ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል ቻናላችን. . . ታድያ ሁሉን አልፈን አብረን ተያይዘን ዛሬን  ረግጠናል. . .

💛ከጎናችን በመሆን አጋርነታቹን እደምሰሶ ላፀናቹልን ቤተሰቦቻችን ልባዊ ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ !!

❤️. . እደትላንቱ ዛሬም ታስፈልጉናላቹ ፣ የእናንተ ሃሳብና አስተያየት ያርመናል ያጠነክረናል.
ሁላችሁም ስለቻናሉ የሚሰማችሁን እዚች ላይ ፃፍፍ አርጉልን
👉 @EthiohumanityBot
👉 @EthiohumanityBot

✍ሁሉም የለንምና በእናንተ ሀሳብ  
           የጎደለውን እንሞላለን!!

ስላላችሁልን ከልብ እናመሰግናለን❤️

@EthioHumanityBot @EthioHumanityBot
 

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ቃል አልባው ቃል ኪዳን!

✨እውነተኛ ጓደኝነት ያስደምመኛል! እንደዛሬው ማህበራዊ ድረ ገፁ "ጓደኛ" የሚለውን ቃል ሳያልከሰክሰው በፊት ...ጓደኝነት ቀለል ተደርጎ የሚወሰድ ግን ደግሞ እጅግ ጥልቅ የሆነ የመንፈስ ትስስር ያለውን ግንኙነት መግለጫ ቃል ነበር! ጓደኝነት መሠረቱ ውበት አይደለም ፣ ጥቅም አይደለም፣ ወሲብ አይደለም፣ ማህላና ቃል ኪዳን አይደለም፣ ተስፋም አይደለም! ከፍቅረኝነት  በላይ የሚያስደምም ነገር አለው!

✨ጓደኞች በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ንፁህ የነፍስ መዋደድ ብቻ ነው! አንዱ ለሌላኛው መቆም ነው! ላልከዳህ ላልከዳሽ የሚል ማህላ የለበትም! ከመሀላ የጠነከረ ያለመካካድ እና የእድሜ ልክ አብሮነት ግን በውስጡ አለ! ጓደኝነት ፆታ ፣ ባህል፣ እምነት፣ ርቀት የኑሮ ደረጃ አይወስነውም! አንዱ ለሌላው ህይወትን እስከመክፈል የሚደርስ ፍቅር በጓደኝነት ስሜት ውስጥ አለ!

✨ጓደኝነት ብዙ ያልተዘፈነለት፣ ብዙ ያልተገጠመለት ብዙ ያልተፃፈለት ብዙ ፊልም ያልተሰራለት ግን ደግሞ በህግ ያልታጠረ እውነተኛ ፍቅር የተሞላበት ስሜት ነው! ጓደኝነታችሁን አታፍርሱ! ቃል አልባ ቃልኪዳን ነውና ለጓደኞቻችሁ ሚስጥርና ሁለንተናዊ ደህንነት ታምናችሁ አብሮነታችሁን አጠንክሩ!

✍ አሌክስ አብርሃም

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@Ethiohumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

📍ወዳጄ ሆይ መቆም ከፈለክ ሌሎችን አትጣል

💡የምትሔድበት የስኬት መንገድ ሺህ ጊዜ ይርዘም እንጂ ቶሎ ለመድረስ ብለህ አቋራጭ መንገድ አትጠቀም። ልብህ በእውነት ላይ ተረማምደው በሰዎች ትከሻ ላይ ተንጠልጥለው ፣ በአቋራጭ ባደጉ ሰዎች እንዳይቀና! የግፍንም እንጀራ እንዳትበላ ተጠንቀቅ ፣ትግስትን ገንዘብህ አድርጋት አምላክ ለአንተ ያዘጋጀዉ ነገር አለውና። በዕውነት ፣ በሃቅና በራስ አገዝ አዋጭ መንገድ ከተራማድክ እመነኝ በያንዳንዱ እርምጃህ ስኬትህን እየገነባህ ነው።

ሀሴትህ በቀናነትህ መጨምር ይበዛል፣ ከክፋት ትርፍ አይሰበሰብም፡፡ የምትሆነው ብታጣ እንኳ ጨካኝነትን ብቸኛው ምርጫህ አታድርግ፡፡ የሚመረጥ ስላጣህም የማይመረጥ አትምረጥ ፣ የምትመርጠው ከሌለ አለመምረጥም ጥሩ ምርጫ ነው፡፡ ማስተዋልህን ባለማስተዋል አትጠቀምበት፡፡

ወዳጄ ሆይ

ከብረህ ሳለም ቀለህ መኖርን አትውደድ፡፡ በከፍታ እንጂ በዝቅታ እያሰቡ መኖር አይመጥንህም ጭካኔ የሕሊና ሰላምህን ያቀነጭራል፡፡ የውስጥህንም ሰላም ያመክናል፡፡ጊዜአዊ እንጂ ዘላለማዊ የዚህች ምድር ነዋሪ አይደለህምና በደጉ ጊዜህ መሰልህን አትበድል፡፡

📍ነገ የአንተ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን በውል አታውቅምና ነግ በእኔ ማለትን እወቅ፡፡ በቁንጮነት ዘመንህ የፍጡራንን መብት አትግፈፍ፡፡ የሌላው ውድቀት የአንተን መቆም አያረጋግጥምና ፣ መከራ በታጨቀባት በዚህች ጠፊ ዓለም መልካምነትን የመሰለ ሰላም ሰጪ ተግባር የለም፡፡ በመሆኑም ዛሬህ ላይ ነገ የማትፀፀትበትን ምግባር አብዛ፡፡

ነፃ የሆነ ነፃነት እንዲሰማህ ፤ በጭንቀት የታጨቀ ኑሮህን በቅንነት ቀይር፡፡ ከሁካታ እርካታ አይመነጭም እፎይታ ለሚሰጡህ ተግባሮች ራስህን ስጥ፡፡
✍ ሐዋዝ

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity

@Ethiohumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

☮ሁለት ሱፊዎች በመንገድ ላይ ሲሄዱ ይገናኙና በመተቃቀፍ ተሳስመው አንዱ የቋጠረውን ስንቅ በጋራ ሊመገቡ ተቀመጡ ። ይኸንን ትዕይንት ለአፍታ የተመለከተው የክርስቲያን ልዑል ወደሁለቱ ሰዎች ተጠግቶ ስለትውውቃቸው ጠየቃቸው ።

💟 መመገባቸውን ሳያቋርጡ አንዱ ቀና ብሎ ፦
"ካለዛሬ አይቼው አላውቅም ..." አለው ።
" ምናልባት የአንድ ሀገር ልጆች ትሆኑ ...?" ሲል ጠየቀ ልዑሉ ።
"ሀገሩንም አላውቅም ..." አለ ሰውየው አሁንም መመገቡን ሳያቋርጥ ።
"ታዲያ ለምንድ ነው እንዲህ ዓይነት ፍቅር ያሳየኸው...?" አለ ልዑሉ ተደንቆ
"በእኔ መንገድ ላይ ሲጓዝ ስላገኘሁት ነው" አለው ።

☯ልዑሉም ተደንቆ ዝም ብሎ አልሄደም ። በዚያ ቦታ ለሱፊዎች ማረፊያ የሚሆን ትልቅ አዳራሽ ሰራ ። ዛሬ አዳራሹ ዘመናዊ መልክ ተገንብቶ የሱፊዎች መፍለቂያ "ዩኒቨርስቲ" ሆኗል ።

📖ጥበብ ከጲላጦስ

☯ሰው መሆን እኮ እንዲህ ነው ፣ በሀይማኖት ተለያይቶ ፣ በደም ሳይተሳሰሩ ፣ በባህል ሳይገናኙ ፣ ነገር ግን ለመረዳዳት ፣ አብሮ ለመብላት ፣ እንደሰው ተያይቶ አብሮ ችግርን መካፈል ማለት ነው ፣ ባጠቃላይ በፍቅር ለመኖር ሰው መሆንና እንደ ሰው ማስተዋል ብቻ በቂ ነው ።

መልካም ቀን💜
☮☯☮☯☮☯☮☯☮☯
@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

እምወድሽዋ!❤ቅዳሜዋ!❤ሸጋዬዋ❤

እቴ!❤'ለነገ ብለሽ ፊት የምትነሺው ትላንት አለ'

ደባሪውን ትላንትን ካስተያየሺው ፤ፊት ከሰጠሺው ይጎትትሻል። ንፍጣም ነው ቀሚስሽን ይዞ አያራምድሽም ፤ላባብለው ካልሽ ዝርክርክ ነው አይፅናናም ።አይጠራም ያጨማልቅሻል ነገሽን ፤ህልምሽን ፤ሳቅሽን ያንገራግጨዋል ።

ዛሬሽን ይኮረሽምብሻል ። ውበት እና እድሜሽ ከሚኮረሸሙት ዋነኛቹ ናቸው።

እና የትላንት ጎታች ፊት ነስተሽ ነገ ላይ መንጠራራት ይበልጣል ትላንት ላይ ከማጎንበስ viva ነገ💪🏾💪🏾💪🏾✌️

ድምቅምቅ ያለች ቅዳሚት!❤

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለጁምኣችን!
💚

«ሌባው» የመስጂድ ኢማም


ባልና ሚስት ከረመዷን ወራት ባንዱ በሰፈራቸው የሚገኙትን ታዋቂ የመስጂድ ኢማም ለፊጥራ ጋበዟቸው። ኢማሙም ግብዣውን በክብር ተቀበሉ። የቤቱ እማወራ የምግብ ማዕዱን ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ እያለች ሳለ ገንዘቧን ጠረጴዛው ላይ ጥላ ወደ ኩሽና አመራች። ፊጥራው ተጠናቀቀ። ኢማሙም ሄዱ። ሚስት ገንዘቧ እንደጠፋ አስተዋለች። «ገንዘቡን የሰረቀው ማን ነው?» ተብሎ አይጠየቅ ነገር ባልና ሚስት ልጆች የሏቸውም። በወቅቱ ወደቤት የመጡት የመስጂዱ ኢማም ብቻ ናቸው። ውስጧ በጥርጣሬ ተናጠ። ታሪኩን ለባለቤቷ አጫወተችው። የመስጂዱን ኢማም እንዲያማክራቸውና ጉዳዩን እንዲያረጋግጥ ጠየቀችው። «ኧረ ነውር ነው ፤ ባይሆን ከኢማሙ ጋር የፈጠርነውን ስር የሰደደ ግንኙነት አቋርጠን ፋይሉን እንዘጋለን እንጂ እንዲህ አይነት ጥያቄ ማንሳት የማይታሰብ ነው» በማለት መለሰላት።

ቀናት በንፋስ ፍጥነት ከነፉ። ቀጣዩ ረመዷን ገባ። ባል ከሚስቱ ጋር ተቀመጠ። «እንግዲህ የእዝነት እና የይቅርታ ወር ስለገባ ያለፈውን መርሳት አለብን። እንደምታውቂው ኢማሙም ቤተሰብ የላቸውም። የኛው ስለሆኑ ዘንድሮም ቢሆን ፊጥራ ልንጋብዛቸው ይገባል» በማለት ሚስቱን አማከራት። ሚስት ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ «በሃሳብህ እስማማለሁ፤ ነገር ግን የማስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ ይኖራል። እርሱም የባለፈው ዓመት ረመዷን ላይ ስለተሰረቀው የገንዘብ ጉዳይ በግልጽ እንድታወሩ እፈልጋለሁ» አለችው። ባቀረበችው ሃሳብ ተስማማ።

የመስጂዱ ኢማም ግብዣውን ተቀብለው ከቤት መጡ። ፊጥራውን ከጨረሱ በኋላ የቤቱ አባወራ ጉዳዩን በይፋ አነሳው። ስለ ገንዘቡ ሁኔታ በቀጥታ ጠየቃቸው። ከፍተኛ የሀፍረት ስሜት ተሰማቸው። እንባቸው በጉንጮቻቸው ላይ ተንኳለለ። ካቀረቀሩበት ቀና አሉ። አይኖቻቸው የእንባ ቋጠሯቸውን እንደፈቱ ነው። ሚስት ፈጠን ብላ «ኢማም ሆይ! ምን ሆነው ነው የሚያለቅሱት ?» በማለት ጠየቀቻቸው። «አዎ! ገንዘቡን ያነሳሁት እኔ ነኝ። ያስቀመጥኩትም የመጽሃፍት መደርደሪያው ላይ ከተቀመጠው ብቸኛ ቁርኣን ውስጥ ነው። እንባዬ የፈሰሰውም ረመዷንን ጨምሮ ለ 365 ቀናት ያህል የአላህን መጽሃፍ ገልጣችሁ አንድ ፊደል እንኳ ባለመቅራታችሁ ውስጤን ተሰምቶት ነው» በማለት ምላሽ ሰጡ። በዚህ ጊዜ የቤቱ አባወራ በፍጥነት መደርደሪያው ላይ ወደተቀመጠው ቁርኣን አመራ። ገንዘቡንም የቁርኣኑ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ምዕራፍ መሃል ላይ ተቀመጦ አገኘው። ሚስት እንባዋ ግድቡን ጥሶ ፈሰሰ። ኢማሙን በክፉ በመጠርጠሯም ይቅርታ ጠየቀቻቸው። «ልጄ ሆይ! እኔ ደካማ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ ይልቅ አመቱን ሙሉ ቁርኣኑን ችላ በማለትሽ ይቅርታና ምህረት ከአላህ ጠይቂ» በማለት መከሯት።

👉 እኛስ መቼ ይሆን ለመጨረሻ ጊዜ የአላህን (የፈጣሪን) ቃል ከፍተን ያነበብነው ? ነፍሳችንን ሳንዋሽ እውነቱን ለራሳችን እንገረው‼‼‼
ወገኖቼ የአላህ (የፈጣሪ) ቃል እየጠራን ቢሆንም ችላ ብለነዋል።

ሸጋ ጁምኣ!💚

📝መሀመድ አህመድ

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለውብ ቀን!
🖤

አብሮ መጨፈርን ሰጥቶ፣ አብሮ ማልቀስን ማን ነጠቀን?



ሁሉም ከሳሽ ፤ሁሉም ምሁር ፤ሁሉም ጨዋ፤ ሁሉም ወቃሽ ፤ሁሉም ሊቅ፤ ሁሉም አዛኝ፤ ሁሉም አቅጣጫ ጠቋሚ ፤ ሁሉም አውሪ ፤ሁሉም ብያለው ባይ ፤ ሁሉም ጆሮ አልባ ነው።

ተመሳሳይ ሃሳብ፤ ተመሳሳይ ምልከታ፤ ተመሳሳይ ህልም ፤ተመሳሳይ ዜና ፤ተመሳሳይ ክስ ፤ተመሳሳይ ውዳሴ ፤ተመሳሳይ አቋም ፤ተመሳሳይ ድጋፍ ፤ተመሳሳይ ሙግት ።

የቡድን ጀግና፤የቡድን ተቆርቋሪ ፤የቡድን ተከራካሪ ፤የቡድን ተከላካይ ፤ቡድናም እይታ ፤የቡድን ጭብጨባ ፤ የቡድን ሳቅ ፤የቡድን ሙሾ ፤ የቡድን ሙግት ፤የቡድን መልስ ። የቡድን ጩኸት

ሃላፊነት የሚወስድ አንድም የለም ። ዝቅጠት ላይ አስተዋፅዖ እንደ አበረከተ የሚያወራ ።አንድም የለም። ሁሉም ጣት ቀሳሪ ፤ ሁሉም ዳር -ነኝ ባይ ነው ።



ሃይማኖታችን ጥንጥ ሞራል ፤ጥንጥ ርህራዬ ትንሽ መተዛዘን ካልፈጠረልን ምን ይሰራልናል ???

የሃይማኖት ስፍራዎች ለምን ግንባቸው ተሸንሽኖ ቤት አልባ ሰዎች አይኖሩበትም??

መስበኪያ ስፍራዎች ለምን ወደ መበየጃ ወደ መሸመኛ ፤ወደ መጥለፍያ ቦታዎች አይቀየሩም ።

እምነት አልባ ህዝብ ውስጥ ይሄ ሁላ ማምለክያ ግንብ ምን ይረባል !!

በዚህ ደረጃ እርስ በእርስ ተጠያይፈን እርስ በርስ ተጨካክነን እርስ በእርስ እየተሳደድን ምን ያስተሳስረናል ???

እርስ በእርስ በሚበላላ ህዝብ ውስጥ ያለች አገርን እንደምን ማፍቀር ይቻላል? ?? ምኗ ይናፍቃል ??

ከዚህ በኋላ የትኛው አገዳደል ፤የትኛው አበዳደል ፤የትኛው ግፍ ያስበረግገን ይሆን ??
የቱም !

ይታክታል!!! እውነት ይታክታል!!!!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

☯“The most beautiful people we have known are those who have known defeat, known suffering, known struggle, known loss, and have found their way out of the depths.

💜These persons have an appreciation, a sensitivity, and an understanding of life that fills them with compassion, gentleness, and a deep loving concern. Beautiful people do not just happen.”

✍Elisabeth Kübler-Ross

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ቃላት ስሜትን መሸከምም ሆነ መግለጥ አቅቷቸዋል!!!💚💛❤

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹


🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹


እንኳን ደስ አለን!!!!💚💛❤💚💛❤💚💛❤

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

✨ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444'ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

📍ወዳጄ ሆይ

ብሩህና መልካም ነገር አስብና! ተነስ
ወደፊት ስለሚሆነው አትጨነቅ ሁሉንም ነገር እንደ ችግር አትመልከት። በራስህ ችግር አትፈጠር። እያንዳንዱ ፈተና ታርሞ ውጤት እንደሚሰጠው ሀሉ ያንተም ችግር እንደተጋፈጥቀው መጠን ለስኬትህ ግብአት እንደሆነ አስብ፣ ስኬት የተለያዩ ደረጃዎች እንዳሉት እወቅ።

📍የስኬት መጨረሻ የውድቀት መጀመሪያ እንደሌለ እወቅ ፣ ስኬት በተገኘ ነገር ላይ በመርካት እንደሚለካ አስብ። ስኬትን ከአእምሮ እርካታ ጋር እንጂ ከቁስ ጋጋታ ጋር አታዛመድ፣ የሰው ልጅ እራሱን ሊያስደስት የሚችለው በመልካም ባህሪውና በሚሰራው ጥሩ ሥራ እንጂ የሚያምር መልክና አቋም ወይንም በርካታ ሀብት ስላለው አይደለም ... የሚያምር አቋምህና ሀብትህ ምድር ላይ ቀሪ ናቸው ..መልካም ስራህ ግን ለነገ ስንቅ ይሆንሐል ! ባለህበት የህይወት ደረጃ መርካት ከቻልክ በራሱ ስኬት እንደሆነ እወቅ።

እናም ወዳጄ

🔑 ሰውን ለመርዳት ጥግ አትያዝ እራስህን ሆነህ ደግ ስራ። በዚህ ምድር ትልቁ ነገር ሰው ሁኖ መፈጠር ሳይሆን ሰው ሆኖ መገኘት ነው ፣ ባለህ ነገር ተደሰት ፣ ተጨማሪ ቁሰ የአኗኗር አማራጭ እንጂ የህይወት ግዴታ እንዳልሆነ እወቅ። ማግኘት የምትችለውን ቁስ እንጂ አንተን የሚፈጥርህ ቁስ ለማግኘት አትጨነቅ ፣  እጅና እግሮችህ ሀብት እንደሆኑ እወቅ ፣ ህልውናህ ብቻውን ስኬት እንደሆነም ላፍታ አትዘንጋ፣ ሁሉም ነገር ሚሆነው አንተ ስትኖር ነው፣ ስለዚም በህይወት ሳለህ ወሳኝ" እና "ጠቃሚ" ሰው ሁነህ ተገኝ ሰዎችን እርዳ። መልካም ሰው መሆን በተግባር  እንጂ በትንታኔ ወይም በምላስ አይገለፅምና ፣በምትኖረው ህይወት ቁም-ነገር ያለው ጥሩ ነገር ሰርተህ እለፍ።

            ውብ ጊዜ ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

❤️እኛ ኢትዮጵያውያን

🔶ኢትዮጵያዊያን የሰው ክብረቱ ስራ እና አእምሮ መሆኑን ገና አላወቅንም። ሰርዐት የሌለው ህዝብ የደለደለ ሀይል የሌውም። ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው።  የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው።

ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!
                   ✍  በዓሉ ግርማ

🔷 ያለፈው ታሪክ የድሮውም የአሁኑም ኑሮዋችን እጅግ ያሳዝናል። በመላው አለም ላይ ሰላም ሲሰፋ አእምሮም ሲበረታ እኛ በጨለማ እንኖራለን። እርስ በእርሳችን መጠራጠርን አልተውነም። ህዝቦች ሁሉ እርስ በርሳቸው በፍቅር ተቃቅፈው ስለ ልማታቸው ሲደክሙ እኛ አንድ ዘርና ወንድማማች መሆናችን ገና አልተገለፀልንም። እርስ በርሳችን መፋጀት እስከ ዛሬ ጀግንነት ይመስለናል።

♦️ዘወትርም በስምምና በፍቅር አድረን ብንሆን እስከ ዛሬ ድረስ ብዙውን ትልልቅ ነገር መፈፀም እንችል እንደነበር ጥርጥር የለውም። ፈጣሪ ብዙ በረከት ሰጥቶናል ፣ ካለመስማማታችን የተነሳ ግን ሌሎች ህዝቦች በአእምሮና በጥበብ እየበረቱ ሲሄዱ እኛ ወደ ኋላ ቀረን። እንደ አረመኖች እስኪቆጥሩን ድረስ።

♦️ምነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንቅልፍህ መቸ ትነሳለህ? በአለም ላይ የሚደረገውን ነገር ለማየትስ ዓይንህን መቸ ትከፍታለህ? ለውጥንስ መቸ ትናፍቃለህ?

✍ ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ

      ውብ አዳር ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💔 ወርቃማው ጥገና!

በጃፓን ሃገር ውስጥ ለብዙ መቶ አመታት የከረመ ልምምድ አለ፡፡ ጃፓኖች አንድ ከሸክላ የተሰራ እቃ ሲሰበርባቸው እንደገና የመጠገኑን ስራ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) ብለው ይጠሩታል፡፡

ይህ ቃል የሁለት የጃፓንኛ ቃላት ጥምረት ነው፡ “ኪን” (Kin) ማለት ወርቃማ ማለት ሲሆን፣ “ሱጊ”(Tsugi) ማለት ደግሞ ጥገና ማለት ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቃላት ጥምረት የሚሰጣቸው ይህ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) የተሰኘ አንድ ቃል ትርጉም አንድ ነገር ከተሰበረ በኋላ እንደገና በወርቅ መጠገንን የሚያመለክት ነው - ወርቃማ ጥገና!

ከዚህ ልምምዳቸው የተነሳ አንድ የተሰበረ የሸክላ እቃ እንደገና ሲጠገን ይህ የጥገና ሂደቱ በእቃው ታሪክ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ እቃው በመሰበሩ የተነሳ እንደገና ሲጠገን በሶስት መልኩ የላቀ ሆኖ ይወጣል፡- 1) ጥንካሬው ይጨምራል 2) ዋጋው ይጨምራል፣ 3) ውበቱ ይጨምራል፡፡

በሕይወታችሁ ልባችሁን ሰብሮና ስሜታችሁን አቁስሎ የነበረ ያለፈ ልምምድ ካለ፣ አሁንም ተመሳሳይ ልምምድ ውስጥ በማለፍ ላይ ካላችሁና ወደፊትም በሚሰብር ልምምድ ውስጥ ስታልፉ ይህንን የጃፓኖችን የጥገና ሂደት አትዘንጉ፡፡ በሁኔታው ተስፋ በመቁረጥና ተሰብራችሁ ለመቅረት ራሳችሁን ካልጣላችሁ በስተቀር እንደገና ትጠገናላችሁ፡፡ ከተጠገናችሁ በኋላ ግን ከበፊቱ ይልቅ ጠንካራ ሰዎች፣ ዋጋችሁ የከበረና ከበፊቱ ይልቅ እጅግ ውብ ሆናችሁ ነው የምትወጡት፡፡

✨ሆኖም፣ ጥገና ጊዜን እንደሚፈልግ አትዘንጉ፡፡ ጥገና ያለፈውን ረስቶ ፈጣሪን በመታመን ወደፊት የመገስገስን ቆራጥነትም እንደሚፈልግ አትርሱ፡፡

Beauty can be found in imperfection.

✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ

ውብ አዳር ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

♦️ለመኖር የመጓጓታችንን ያህል መኖራችን ውስጥ የተሰጠንን ፀጋ ምን ያክል እናስተውላለን? ከውልደት እስከ ሞት የሚዘረጋው የስብዕናችን ተረክስ ሁነኛ ልኩ ምንድነው?

የህይወት ዳርቻ ስትደርስ ጨለማውን ታየዋለህ።  ተስፋ ካልተለየህ ጭላንጭሏ ላይ ታተኩራለህ። እሷ እንዳታመልጥህ ትታገላለህ።  ካመለጠችህ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መውደቅህን ታውቃለህ ፣ ሰው አንዳንዴ የተስፋው ጭላንጭል ስትሟጠጥ እና የህይወቱ ገመድ ተገዝግዛ ልትበጠስ ስትደርስ የመጨረሻው ንቃት ላይ ይደርሳል፣ ታድያ በዚች ቅፅበት ጨለማውን የሚገፍ የተስፋ ብልጭታና እንደገና ጨብጦ የሚወጣበት የምርጫ ገመድ ሲያገኝ የሚፈጠረው ለውጥ አቻ አይኖረውም።

🔷ዛሬ ብንሞትስ ብለህ አስብ እስኪ
ለነገ ያሳደርካቸው ብዙ ሀሳቦች አብረውህ ይሞታሉ  ፣ ለነገ ያቆየሀቸው ስንት ግቦች መቃብር ይወርዳሉ  ፣ዛሬ ሳታወጣው የደበቅከው ተሰጥኦህ አብሮህ ይቀበራል ሳይፈነጥቁ የቆዩ ብዙ ተስፋዎች ይቀጫሉ ፣ ለሰዎች ያላሳየሃቸው ስንት ደግነቶች አፈር ይበላቸዋል ያልተነገሩ ስንት ይቅርታዎች ይሞታሉ ነገ እደሰታለሁ ብለህ ቀን ስትጠብቅ ቀኑ ይጨልምብሀል  ስለዚህ አስብ እየአንዳንዷን ቀን እንደ መጨረሻ ቀን ቁጠራት ማድረግ ያለብህን ዛሬ እያደረክ ተደሰት።

🔶መኖር ጥሩ ነው።  ሌላው ትርፍ ነው።አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' አይምሰልህ ፣ ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ለህይወትህ በይበልጥ ዋጋ የምትሰጠው ልክ የአንበሳ መንጋጋ ገብቶ በተአምር እንደ ተረፈ ነብይ ወይም ጻድቅ ነው። 

🔷ከክፉ በሽታና ከሞት ጥግ መመለስ ራሱ ጽድቅ ነው፣ የደረሰበት ብቻ ያውቀዋል፣  ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ዋናው ነገር ለተሰጠህ ለምታውቀውም ለማታውቀውም በረከት ፈጣሪህን አመስግን ፣ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!

              ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

✍@Ethiohumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💡ፀጥታህ በጩኸት መሃል ካሌለች፤ ሰላምህም በግርግር ካልተገኘች፤ ተመለስ አልደረስክም!

ሰማዩን ተመልከተው ፀሓዩዋን እያት፣ ዛፎቹን እያቸው። ነፋሱን አስተውል። በመንገድ የሚጓዙትን የሚተምሙትን መኪኖችና ሰዎች ልብ በል። ወፎቹን አዳምጥ። ሌሎች እንሰሳቶችንም ተመልከት። ምን ይሰማኃል?
ልክ እንደ ጨቅላ በሀሴት ተሞሽረህ ምናብህን ስታበረታ ሁሉም ነገር በቀና ይሄዳል፣ ሰከን በል! ተረጋጋ! አስተውል፣ ወደውስጥ ስትገባ አንተነትህ ሁሌም አዲስ ሆኖ የሚታደስ ድንቅ ፍጥረት ሆኖ ይታይሃል፡፡ የተፈጥሮ አካል አንድ ህዋስ ነህ፡፡

💎ወዳጄ ዓለም እና የሰው ልጅ ተፈጥሮ በብዙ ስንክሳር የተሞሉ ናቸው። ባሳለፍከው ህይወት ብዙ ክስተቶች ታይተዋል። የሚያሳዝንም የሚያስደስቱም ሁኔታዎች የህይወት ገጾች ናቸው። ሁሉ ይመጣል፣ ሁሉም ይሄዳል። ያለፈውና የሚሄደውን በሰላም ሸኘው። አሁን ካለው ጋር በሰላም ተከባብረህና ተሳስበህ ኑር። ታመን፣ እመንም። የሚመጣውን በልከኛ ተስፋ ተቀበለው። ዘልዓለማዊ ክስተት የለም፣ ለውጥ እንጂ።ባንተ ጭንቀት አንዲቷ ችግርህ አትፈታም፡፡ ባንተ ማስተዋል ግን የሁሉ ሰንሰለት ይበጠሳል፣ የራስህ ሳይሆን የብዙሃን ነፃ አውጪ ነህ፣ ከሁኔታዎች በላይ መሆንን እወቅበት። መረጋጋት መልካም ነው።

💡ይህ ሁሉ ሲሆን፣ ነገሮች ሲለዋወጡ ህይወትን በእርጋታ ማጣጣም የቻሉ ግን ጥቂቶች ናቸው። ህይወትን ለማጣጣም ሀብት የግድ አይደለም፣ ቢኖር ግን ጥሩ ነው፣ ግን በልክ። ህይወትን ለማጣጣም ዘመድና ጓደኛ ቢኖሩ ጥሩ ነው፣ግን በልክ። ህይወትን ለማጣጣም ጊዜ ማግኘት አስፈላጊ ነው። ጊዜህን መጠበቅና መቆጣጠርን እወቅበት።

ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

✍@Ethiohumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💚  ንቁ የሃሳብ ሰው ስንሆን ምንሰራው ዓለም ነው ለዚህ ደሞ የስብዕና ግንባታ ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል ቻናላችን. . . ታድያ ሁሉን አልፈን አብረን ተያይዘን ዛሬን  ረግጠናል. . .

💛ከጎናችን በመሆን አጋርነታቹን እደምሰሶ ላፀናቹልን ቤተሰቦቻችን ልባዊ ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ !!

❤️. . እደትላንቱ ዛሬም ታስፈልጉናላቹ ፣ የእናንተ ሃሳብና አስተያየት ያርመናል ያጠነክረናል.
ሁላችሁም ስለቻናሉ የሚሰማችሁን እዚች ላይ ፃፍፍ አርጉልን
👉 @EthiohumanityBot
👉 @EthiohumanityBot

✍ሁሉም የለንምና በእናንተ ሀሳብ  
           የጎደለውን እንሞላለን!!

ስላላችሁልን ከልብ እናመሰግናለን❤️

@EthioHumanityBot @EthioHumanityBot
 

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

❤️ከስሞች ሁሉ ምርጥ ስም  ከሰው ልጅ ከናፍራት ከወጡ ውብ ቃላት አንዱ " እናት" ነው ።

❣የጥሪዎች ሁሉ ምርጡ  ጥሪ " እማ" ቃላቱ በፍቅር , እና ተስፍ የተሞላ ነው ፣የምትጣፍጥ ቃል ከሰው ልጅ ጥልቅ ልብ የወጣች ናት።እናት ሁሉ ነገር ናት ፣ በችግር ሰአት አማካሪያችን ናት በጭንቀት ሰአት ተስፍችን ናት በድክመት ሰአት ጥንካሪያችን ናት እሷ እኮ የፍቅር , የእዝነት , የርህራሄ, ምንጭ ናት።

❣ እናት እንደ መሬት ሁሉን ቻይ ናት። ብትረገጥ ታግሳ ለወግ ማረግ ታበቃለች። ብትነቀፍና ብትተችም ፈገግታዋ አይከስምም። የዘሩባትን መልካም አድርጋ እንደምታበቅል እርሻ ልበ ንፁሁ እንዲሁም መልካም ፍሬ እንደምታፈራ ዛፍ አብራኳ ለምለም የሆነ የውበት የምጨረሻዋ ምእራፍና የመጨረሻዋ እውነተኛ ዓረፍተ ነገር ነች እናት። ልቧ ከፍቅር ድርና ማግ የተሸመነ ነውና ምን ቢያስቀይሟት የጥላቻ ጥርስ አትነክስም። ፊት ቢነሷት ፊት አትነሳም ።

❤️ሰው የመሆን የመጨረሻው ደረጃ ነው። ቅድስና በእናትነት መንገድ የሚደረሰበት የህሊና ንቃት ነው። እናት  የፍጥረት ሁሉ የመጅመሪያ ምሳሌ ናት ሙሉ የሆነ ውበት እና ፍቅር ተምሳሌት ናት ከሁሉም በላይ እናት የሚተመንላት ዋጋ የላትም፡፡ ከዋጋ በላይ ናትና።

የእናት ፍቅር የመጨረሻዋ የፅድቅ ፅዋ ነች።

ውብ የእናቶች ቀንን ተመኘን❤️
                  
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💫ራሳችሁ ላይ ስሩ!

✨ከአንድ ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት በቤተሰብ አባልነት፣ በጓደኝነት፣ በፍቅር ግንኙነት፣ በትዳርም ሆነ በሌሎች የቅርብ ወዳጅነት ዘርፎች ይሁን፣ ለዚያ ግንኙነት የሚመጥን ቅርበትንና ትኩረትን የመስጠታችሁ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ከእነሱ በሚነሳ አጉል ባህሪይ ወይም የትኩረት መለዋወጥ ምክንያት በቶሎ እንዳትደናገጡ ከፈለጋችሁ ራሳችሁ ላይ ስሩ፡፡ እነሱ እንዶለወጡ መጠበቅ ትክክለኛ ቢሆንም፣ አስተማማኙ መንገድ ግን ራስ ላይ መስራት ነው፡፡

💫ራስ ላይ መስራት ማለት ለእነሱ የምትሰጡትን መሰረታዊ ፍቅርና አክብሮት ሳትቀንሱ ራስን በመቀበል መደላደል፣ የግልን ዓላማ በማወቅ መንቀሳቀስ፣ አልፎ አልፎ ከእነሱ ውጪ የግል ጊዜን በመውሰድ ራስን ማድመጥና የመሳሰሉትን ልምምዶች ማዳበር ማለት ነው፡፡ ከሰዎች ጋር ምንም ያህል ብትቀራረቡና ራሳችሁን ብትሰጧቸውም እንኳን ማንነታችሁን መካድ ግን አትችሉም፡፡

✨ከእነሱ ጋር መቀራረብ ማለት ከራስ ጋር መራራቅ ማለት አይደለም፡፡ እነሱን መደገፍ ማለት ራስን መጣል ማለት አይደለም፡፡ ይህንን መርህ መከተል የሚጠቅማችሁ ከእነሱ የማትጠብቁትን ጎጂ ነገር ስታገኙ ወይም የምትጠብቁትን መልካም ነገር ስታጡ ከልክ ባለፈ መልኩ ከመጎዳትና ግራ ከመጋባት ራሳችሁን ትጠብቃላችሁ፡፡

✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ

የሰላም እንቅልፍ ይሁንላችሁ!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

✨ስብዕና(Personality)

💛በዶ/ር ወዳጄነህ ማህርነ

፨ የሰዓት ፍጆታ፦ 25 ደቂቃ
፨ ሳይዝ የቦታ ይዞታ፦ 6.0MB

ውብ ቅዳሜ❤️
✨✨✨✨✨✨✨✨✨

🔆ምርጫችሁ ስለሆንን ስናመሰግኖት ከልብ ነው !!!
@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ነገ ሸጋዋ ቅዳሚት ነች !


የ20❤+ዓመታት የሙዚቃ መልክ!!

ኤልያስ የሙዚቃው ሊቅ ተወርዋሪው ኮከብ....እንቅልፉን ሰጥቶን ሙዚቃውን በሰረገላ ከፍ አድርጓት ከሔደ ዛሬ ዓመት ከመንፈቅ ሆነው።

ኩልል ያለ የጠራ ንፁህ ውበት!!

የልማድን ቅጥር እንደመናድ...በአምክንዮ ነባራዊውን እውነታ እንደመጋፈጥ...
ደፈር ተባ ብሎ የይሉኝታን እስራት እንደመበጠስ... የጥላቻን ገደል ደፍኖ የፍቅር ድልድይ እንደማነፅ... የባርነትን ቀንበር ሰብሮ የነፃነት ብርሃን እንደመፈንጠቅ...በቅንነት ቀና ብሎ በፅድቅ መንገድ በኩራት እንደመራመድ... ከጃጀ ቀኖና አፈንግጦ ቅቡል ተአማኒ ስርዓት እንማፅደቅ...
የተዛባን ፍርድ አቃንቶ ፍትህን በሰው ልጆች ሁሉ እንደማስፈን..
እንደዚህ ሁሉ...ማነው..? ኤልያስ መልካ!!!

ከኤልያስ መልካ ስራዎች እጅግ በጣም የምወደው ሁሌም ሰርክ አዲስ የሚያስገርመኝ አንዱ "መልክሽ አይበልጥሽም" ሙዚቃ ተጋበዙልኝ!!

ሰላም እደሩልኝ!❤ ለኢትዮጵያችን ናካይታ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ይፈለጋል !

ዝም የሚል የማይጠይቅ ፤ ሲነገረው አሜን አሜን የሚል፤ የግንኙነት ድንበር የማያበጅ፤ሲናቅ የማይቆረቁረው ፤ የበዛ ይሉንተኛ ፤ከቦታ ቦታ የሚለያይ አቋም የሚያንፀባርቅ ፤ ልምጥምጥ ፤ አቋሙን ፈርጠም ብሎ የማይናገር፤ ሳያስቀው የሚስቅ ፤ አላምንበትም የማይል ። ማብራርያ የማይጠይቅ። ቅሬታውን የማይናገር ፤ሸንጋይ ፤በየቦታው የሚያጨበጨብ ።ይገባኛል(ሲጠብቅ) የማይል ፤ ስለመብት እና ግዴታ የማይዘበዝብ
በጣም ነው የምንፈልገው !¡¡

በነገራችን ላይ

የምንፈልገው ልንገለው ነው¡¡¡¡


@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

:
ጌታ ሆይ - ክፍትም ብሆን
የባለጌ ልቃቂ
ኮረት እንኳ ባልሆን
የአሸዋ ዝርያ ድቃቂ
ቤት ለእንግዳ በለኝ 'በምስራቅ በር' --

አንተ በሌለህበት ቦታ
ሰማይ ተቀዶ ብሰፋ - እንኳን ልሾም የማልከበር --
የሰጠኸኝ ሁሉ ምሉዕ ነው
ግን እኔን የሚያብሰከስከኝ
እጄ የማይደርስበት ጀርባዬ - ባልበላሁት እያሳከከኝ
አወከኝ
:

አያ ሙሌ ❤️
[ጌታ ሆይ ነፍሴን ባርካት]

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለውብ ቀን!
💚

ሰዉ ዉበቱን እንጂ ቁንጅናዉን ሊፈጥር አይችልም።

ተፈጥሮ የሰጠንን አጣጥበን ከመዉጣት በዘለለ ቁንጅናን ልንፈጥረዉ አንችልም።

ማቆንጀት የምንችለው አስተሳሰባችንን ነው!

ውብ ቀን!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

የድል ቀን!
💚💛❤️💪

እግርኳስ ከስፖርት በላይ ነው !

አንድነትን ይፈጥራል ፣ ሰላምን ያሰፍናል በጥላቻ ውስጥ ገብቶ ፍቅርን ይገነባል ።

ከ14 አመት በፊት ዲዲየ ድሮግባ የዛሬ ተጋጣሚያችን ለአምስት አመታት የቆየውን እርርስ በርስ ሲጨረሱ ጎል አስቆጥሩ በመማፀን ብቻ ጦርነቱን አስቁሞ ነበር ። ይሄ ሁሉ የሆነው በእግርኳስ ነው !

እግርኳስ ከሴክስ በላይ አስደሳች ነው ይለናል የባርሴሎናው የመሀል መሀንዲሱ ሰርጂዮ ቡስኬትስ ልክ 2010 አለም ዋንጫን ባነሱባት ቅፅበት ደስታውን ሲገልፅ ።

በ1915 እኤአ በእንግሊዝና ጀርመን መካከል በነበረው ጦርነት ለአዲስ አመት ሰላም ያሰፈኑበት ወታደሮቹ እግርኳስን በመጫወት ነው ። ለዚ ነው ከሱስም በላይ ነው ምንለው !!

አሁን የኛም ህዝብ በውስጡ ብዙ ነገሮች አሉበት በብዙ ነገር አንዱ ከአንዱ ተለያየቷል አድነታችን ከምንጊዜውም በላይ እየሻከረ የመጣበት ወቅት ነው 120 ሚሊየን ህዝብን በ90 ደቂቃ ተጋድሎ አንድነት ፍጠሩለት !!🙏🙏🙏

እውቁ ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ እሁድ እለት እንዲህ ሲል መልእክቱን ለጥቁር አንበሳዎቹ እንዲህ ሲል አድርሷል....

"ስራው አልተጠናቀቀም። እናንት ውድ የሃገራችን ልጆች ዛሬ ጨርሱትና #ፖለቲካ የረበሸውን ህዝባችሁን በእግሮቻችሁ ምትሃት ሰብስቡት፤ ሁሉም ያያችኋል፤ አንድነትን አሳዩት፤ የረሳውን ህብረት አስታውሱት፤ ችግሩን አስረሱት፤ ቁስሉ ባይሽር እንኳን ማስታገሻ ሁኑለት፤ የወዲያኛውን ሠፈር ከዚህኛው ሠፈር ጋር ቀላቅላችሁ ወደ ህብረቱ መልሱት፤ በጋራ የሚደሠትበትን ዕድል ስጡትና እግርኳስ ከስፖርትም በላይ መሆኑን አስተምሩት።"


ድል ያለ ድል ለሃገሬ ዛሬ ሁላችንም የምንደሰትበት በጋራ ስለ ኢትዮጵያችን የምንዘምርበት ካጠላብን ጥላ ትንሽም እንኳን ቢሆን ገፈፍ የሚልበት የድል ቀን!!
💚💛❤

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…
Subscribe to a channel