ውድ ወላጆች፣
በነገው ዕለት ማለትም ግንቦት 1 ቀን 2016ዓ.ም ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ መምህራን የሞያ ፈቃድ ምዘና ስላለባቸው በቶታል ኤክሰለንስ ቅርንጫፍ ያሉ ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ትምህርት አይኖራቸውም።
ማሳሰቢያ
👉 ዊዝደም ከኬጂ እስከ 8ኛ ክፍል እንዲሁም ቶታል ኤክሰለንስ ከኬጂ እስከ 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች መደበኛ ትምህርት ይኖራቸዋል።
የት/ቤቱ አስተዳደር
እንኳን ለትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ!
በዓሉ የደስታ እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን::
መልካም በዓል!
ኢትዮ ብሔራዊ ትምህርት ቤት
የልዕቀት ማዕከል
የ4ኛውን ሩብ ዓመት የክፍያ ጊዜ ስለማሳወቅ
ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች፡
የ2016 ዓ.ም የ4ኛው ሩብ ዓመት ክፍያ የሚከፈለው ከሚያዚያ 15 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የት/ቤቱ አስተዳደር
ውድ ወላጆች፣
የሸዋል ወር አዲስ ጨረቃ ባለመታየቷ የኢድ አልፊጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ፣ ሚያዝያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
ነገ መደበኛ ትምህርት የሚቀጥል ይሆናል።
ከወዲሁ በአሉን ለምታከብሩ የት/ቤታችን የእስልምና እምነት ተከታይ ወላጆች፣ ተማሪዎቻችና መምህራን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።ኢድ ሙባረክ‼️
ውድ ወላጅች
ለተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ይቅርታ እየጠየቅን:
ድንገተኛ በሆነ መመሪያ የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ቀን መርሀ-ግብር ቆይተው እንዲፈተኑ ትእዛዝ ከትምህርት ጽ /ቤት በመምጣቱ ምክንያት የተፈጠረ የመረጃ ክፍተት መሆኑን እያሳወቅን የጥናት ፕሮግራም ያላቸው ተማሪዎች እስከ 8:00 የሚቆዩ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን::
ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች፤
👉🏼ከቱሉዲምቱ፣ ቅሊንጦ እንዲሁም ሲዳሞ አዋሽ አካባቢ ለሚመጡ ተማሪዎች ዛሬ በሚኖረው ሰልፍ ምክንያት ትራንስፖርት ማቅረብ እንዳልተቻለ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ወደትምህርት ቤት መምጣት ያልቻሉ ተማሪዎቻችን ዛሬ የሚሰጠው ትምህርት እንዳያመልጣቸው በነገው ዕለት የማካካሻ ትምህርት የሚሰጣቸው መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ!