ውድ ወላጆች!
👇👇👇👇👇👇👇
✍️✍️የሁለቱም ቅርንጫፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል የተማሪዎች ውጤት መግለጫ ካርድ የሚሰጠው ከሚኒስትሪ ውጤት ጋር ስለሚሆን በነገው ዕለት መምጣት አይጠበቅባችሁም፡፡ ነገር ግን ተሸላሚ ተማሪዎች እና ወላጆች እንዲገኙ እናሳስባለን፡፡✍️✍️
ት/ቤቱ!
ሰመር ካምፕ 2016
የሚወዱት ሰመር ካምፕ
በኢ ኤን ኤስ
📌እያንዳንዱ ተማሪ በሰመር ካምፕ ያለው ቆይታ እስከ 5 ሳምንት ሲሆን በተዘጋጁት 9 ዋና ተግባራት ተሳታፊ ይሆናል ጠዋት 2:30 የሚጀምር ሲሆን 6:00 ወደ ቤት የሚሄዱበት ሰአት ነው።
📌ተማሪዎቹ በቆይታቸው ክህሎታቸውን የሚያዳብሩ ሲሆን ደስተኛ ሆነው ያጠናቅቃሉ።
📌ተማሪዎች ደምብ ልብስ (uniform) መልበስ አይጠበቅባቸውም።
📌ለሰመር ካምፑ ተማሪዎቹ የሚያስፈልጉዋቸውን በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል።
📌ለኢትዮ ብሔራዊ ትምህርት ቤት ሁለቱም ቅርንጫፍ ላሉት ተማሪዎች የምንሰጥ ይሆናል።
📌እድሚያቸው 7 እስከ 12 አመት የሆኑ ተማሪዋች ተሳታፊ መሆን ይችላሉ። ወይም
-ዘንድሮ ተመራቂ የሚሆኑ ኬጂ 3
-ዘንድሮ 1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል የሆኑ ተማሪዋች ተሳታፊ መሆን ይችላሉ።
📌በ 5ኛው ሳምንት የተዘጋጀላቸውን ሰርተፍኬት ይቀበላሉ በተጨማሪም ተማሪዎቹ ያካበቱትን ክህሎት ለወላጆቻቸው ያዘጋጁትን አውደ ርዕይ ያቀርባሉ።
ክፍያ እና ምዝገባ
📌ክፍያዎን በአካውንት ቁጥር 10300 4178 7097 በብርሀን ባንክ ከከፈሉ በኃላ የከፈሉበትን ደረሰኝ በዋናው ግቢ (ኤክሰለንስ ቅርንጫፍ) በሚገኘው ከ1ኛ - 4ኛ ክፍል ባለው ርዕሰ መምህር ቢሮ በመገኘት ልጆን ያስመዝግቡ። ወይም በስልክዎ ከፍለው (Screen Shoot) አድርገው በቴሌግራም በዚህ አድራሻ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@ENS_SUMMER_CAMP_2016
መላክ ይችላሉ።
💵 አንድ ተማሪ 2500ብር ከፍሎ ይመዘገባል ክፍልም ይመደባል።
ጥያቄ ካለዎት
ኤፍሬም ዘውዱ
ሰመር ካምፕ አስተባባሪ
☎️ 0910 19 64 39 /
07 13 19 64 39
ውድ ወላጆች/ ህጋዊ አሳዳጊዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️🏆🏆🏆⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች ውጤት መግለጫ የሚሰጠው እንዲሁም በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዕውቅና ሰርተፊኬት የሚሸለሙበት ዕለት ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2016ዓ.ም መሆኑን በታላቅ አክብሮት እናሳውቃለን፡፡
🌟የሽልማት ስነስርዓቱ እንደተጠናቀቀ የተማሪዎች ውጤት መግለጫ በየመማሪያ ክፍላቸው የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በዚህም መሰረት
ሽልማቱ ከ2፡30-4፡00 ለኤክሰለንስ ቅርንጫፍበት/ቤቱ ትልቁ ቤተ-መፀሃፍት የሚሰጥ ሲሆን ለዊዝደም ቅርንጫፍ ደግሞ ሸገር በሚገኘው ግቢ ውስጥ የሚሰጥ ይሆናል::
የተማሪዎች ውጤት መግለጫ ካርድ ደግሞ ከ 4፡00-6፡30 ብቻ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ት/ቤቱ!
ጉዳዩ፡ የመጽሃፍት ክፍያ እና ስርጭትን ይመለከታል
ውድ ወላጆች/ ህጋዊ አሳዳጊዎች!
የማክበር ሰላምታችን እያቀረብን በ2017 ዓ.ም ከ1-8ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የመማሪያ መጽሐፍት ክፍያ እስከ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ብቻ በብርሃን ባንክ ሂሳብ ቁጥር 2500040004307 እንድትከፍሉ ማስታወሻ የላክን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በወላጆች ጥያቄ መሰረት የክፍያ ቀኑን እስከ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ያራዘምን መሆኑነ እንገልጻለን፡፡
በተጨማሪም ከት/ጽ/ቤት በተገለፀልን መሰረት እያንዳንዱ ተማሪ በክፍል ውስጥ መጽሐፍ ይዞ መገኘት ስላለበት ሁሉም ወላጆች መጽሐፍ መግዛት ስለሚኖርባቸው የምዝገባ ቀን ከመድረሱ በፊት ወላጆች ክፍያ ፈጽማችሁ የከፈላችሁበትን ማስረጃ በምዝገባ ወቅት ይዛችሁ በመቅረብ የምዝገባውን እና የመጽሐፍ ስርጭት ሂደት ቀልጣፋ እንዲሆን የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በአክብሮት ትጠየቃላችሁ፡፡
የመፅሃፈት ስርጭቱን በተመለከተ መጽሐፍቱን ከሚመለከተው ክፍል እንደተረከብን የስርጭት የጊዜ ሰሌዳ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የት/ቤቱ አስተዳደር!
ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች!
ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎቻችን የመንግስት መጽሐፍት ክፍያ ማሳወቂያ ቅጽ መላካችን ይታወቃል፡፡ ከፍያውንም መክፈል ያለባችሁ በብርሃን ባንክ ሂሳብ ቁጥር 2500040004307 ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በዚሁ መሰረት ለሒሳብ አሰራር አመቺ እንዲሆን እና የመጽሐፍት አቅርቦቱን ለማቀላጠፍ ይረዳ ዘንድ ይህንን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ብቻ እንድትጠቀሙ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡
እናመሰግናለን!
የት/ቤቱ አስተዳደር
ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማሪያ መፅሃፍት ግዢ የክፍያን መጠን
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ምዝገባ ከ 7ኛ እና 9ኛ ክፍል በስተቀር ከሰኔ 28 እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲካሄድ ወስኗል፡፡ ስለሆነም በሀገር ደረጃ ከአፀደ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ስርዓተ ትምህርት ባለፉት አመታት በተከታታይ ለውጥ የተደረገበት በመሆኑና ት/ቤታችን ደግሞ ይህንንም ሙሉ በሙሉ በመተግበር እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከስርዓተ ትምህርቱ ለውጥ ጋር ተያይዞ በዚህ በያዝነው የትምህር ዘመን ከፍተኛ የመፅሃፍት እጥረት የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ መንግስት በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ማለትም ለ2017 ዓ.ም የሚፈለጉ የተማሪ መፅሃፍቶችን አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ለሁሉም የግል ት/ቤቶች በግዢ ማዘጋጀቱን አሳውቆናል፡፡ ስለዚህ ከሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚኖረው የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ወቅት ለሁሉም ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው መማሪያ መፅሃፍት እንዲያገኙ እና ክፍል ውስጥ ይዘው መገኘት ስለሚገባቸው በዚህ ማስታወሻ ላይ ለመጻሕፍት መግዣነት የሚፈለገውን የገንዘብ መጠን በብርሃን ባንክ ሂሳብ ቁጥር 2500040004307 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ በማስገባት ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ት/ቤት ይዞ በመምጣት መፅሃፍቱን እንድትወስዱ እናሳውቃለን፡፡
የዋጋ ዝርዝር በየክፍል ደረጃው ለሁሉም ትምህርት ዓይነት
👉🏼G1= ብር 926.70 👉🏼G5= ብር1,489.10
👉🏼G2= ብር 988.20 👉🏼G6= ብር 1,352.69
👉🏼G3= ብር 1,164.56 👉🏼G7= ብር 2,040.25
👉🏼G4= ብር 1,277.18 👉🏼G8= ብር 2,106.94
የቅድመ መደበኛ እና የሁለተኛ ደረጃ መጻህፍት በህትመት ሂደት ላይ ስለሆነ ዋጋው እንደደረሰን እናሳውቃለን፡፡
ውድ ወላጆች!
የኢትዮ ብሄራዊ ትምህር ቤት ከስር የተዘረዘሩትን መረጃዎች ለ2017 የትምህርት ዘመን ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዲቻል የሚከተሉት የትኩረት ነጥቦች ላይ ግንዛቤ እንዲወሰድ በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
👉 ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከዊዝደም ቅርንጫፍ ወደ ኤክሰለንስ ቅርንጫፍ ምንም ዓይነት የተማሪዎች ዝውውር የማያከናውን መሆኑን:
👉ከኬጂ 2 ጀምሮ ያሉ የትኛውም የክፍል ደረጃ ላይ የሚገኙ አዳዲስ ተማሪዎች ምዝገባ የማያከናውን መሆኑ:
👉ለኬጂ 1 ተማሪዎች ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ምዝገባውን የምናከናውንበትን መንገድ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
👉በተማሪዎች በኩል የመጽሐፍት የዋጋ ዝርዝርና ወላጆች አረጋግጠው የሚፈርሙበት ቅጽ በነገው እለት ስለምንልክ ቅጹን ተከታትላችሁ ፈርማችሁ እንድትልኩልን እንጠይቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
👉ምዝገባ የሚከናወነው መንግስት ባስቀመጠው ቀነ ገደብ ብቻ ይሆናል፡፡
ት/ቤቱ!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ኢትዮ ብሔራዊ ትምህርት ቤት
ውድ ወላጆች!
የቲቶርያል መርሃ ግብር ግንቦት 30 ቀን 2016ዓ. ም ያጠናቀቅን መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን::
ማሳስቢያ: የ 12ኛ ክፍል ቲቶሪያል እስከ ሰኔ 14ቀን 2016ዓ. ም ድረስ የሚቀጥል ይሆናል::
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ለ2017 ዓ.ም የጀማሪ (ኬጂ-1) ተማሪዎች በት/ቤቱ የሚማሩ ወንድም / እህት ላላቸው ምዝገባ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በኢትዮ ብሄራዊ ት/ቤት ሁለቱም ቅርንጫፎች ልጆቻችሁን የምታስተምሩ በ2017 ዓ.ም የጀማሪ ህጻናትን ለማስመዝገብ በመጠባበቅ ላይ ላላችሁ ወላጆች በሙሉ!
ለ2017 ዓ.ም ላለን ውስን ቦታ ወላጆች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መረጃዎችን በመያዝ በተጠቀሰው ቀን ብቻ ልጆቻችሁ በሚማሩበት ቅርንጫፍ ይዛችሁ በመምጣት ዕጣ ለማውጣት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
👉🏼 ማክሰኞ፣ ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም የሚመዘገቡ ህፃናትን በአካል ይዞ መገኘት
👉🏼 ዋናውን የክትባት ካርድ
👉🏼 ዋናውን የልደት ካርድ ከወሳኝ ኩነቶች (ከወረዳ) ይዘው መገኘት ይኖርበታል፡፡
👉🏼 የህፃኑ/ኗ ዕድሜ መስከረም ወር ላይ ከ4 (አራት) ዓመት እስከ 4.3 (አራት ዓመት ከሶስት ወር) ብቻ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
✍️ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጣ ለማውጣት ይመዘገባሉ።
✍️ ዕጣው የሚወጣው ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ስለሚሆን በዕለቱ በተጠቀሰው ሰዓት በሚገኙት ወላጆች ፊት የእጣ ማውጣት ስነስርአት በሁለቱም ቅርንጫፍ የሚከናወን ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጪ የሚመጣ ማንኛውንም ወላጅ ት/ቤቱ የማያስተናግድ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
✍️የህጻኑ/ኗ ዕድሜ 4 ዓመት ካልሞላ ዕጣው ውስጥ መግባት አይችልም/አትችልም፡፡
✍️ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ያላሟላ ዕጣው ውስጥ መግባት አይችልም፡፡
ት/ቤቱ
ውድ ወላጆች!
ለ2017 ዓ. ም የትምህርት ዘመን መማሪያ መፅሃፍት ክፍያ እስከ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍላችሁ ደረሰኝ የምታመጡት እንዲሁም መፅሐፍቱን የመትወስዱት ምዝገባ ሲጀመር መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን::
ት/ቤቱ!
ውድ ወላጆች!
ዛሬ ከ1-7ኛ ክፍል ተማሪዎች በኩል የላክነውን የ2017 ዓ.ም መማሪያ መፅሃፍት ዋጋ ዝርዝር ማሳወቂያ ቅፅ ተመልክተው ማስታወሻው ላይ የተጠየቁትን ወሳኝ መረጃዎች ሞልተው እና ፈርመው ተማሪዎች ሰኞ ለማጠቃለያ ፈተና ሲመጡ ይዘው እንዲመጡ እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ጉዳዩ፡ የኢትዮ ብሄራዊ ት/ቤት የሁለቱም ቅርንጫፍ ወ.ተ.መ.ህ አባላት የጠሩትን አጠቃላይ የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
በቅድሚያ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን በ2016ዓ.ም ትምህርት ዘመን የተቋቋመውን የወ.ተ.መ.ህ አባላት ትውውቅ እንዲሁም የ2016ዓ.ም ትምህርት ዘመን በምን መልኩ እንደተከናወነ ለመገምገም እና ለ2017 ዓ.ም መቀጠል ያለባቸውን፣ መታረም ያለባቸውን እንዲሁም ሌሎች ከወላጆች የሚነሱ ሃሳቦችን ለመስማት እና የተሻለ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት ያስችል ዘንድ ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በመሆኑም በመጪው እሁድ ቀን ሰኔ 16፣ 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የሁለቱም ቅርንዓፍ ተማሪ ወላጆች በዋናው ግቢ በመገኘት የውይይቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል፡፡ በዕለቱ ሁሉም ወላጅ በሰዓቱ እንዲገኙ እናሳስባለን፡፡
የመጨረሻ ማስታወሻ
ቀሪ ያልተከፈለ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ክፍያን ስለማጠናቀቅ
የ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ያልተከፈለ ሁሉንም የትምህርት ክፍያ እና የሰርቪስ ክፍያ ያላጠናቀቃችሁ ወላጆች በተደጋጋሚ እንድታጠናቅቁ ማስታወሻ መላካችን ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የተወሰኑ ወላጆች እስካሁን ክፍያ ያልፈጸማችሁ እንደሆን የፋይናንስ መዝገባችን ያሳያል።
ስለሆነም ይህ የሚመለከታችሁ ውድ ወላጆች ውዝፍ ክፍያችሁን እስከ ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ. ም በማጠናቀቅ ክፍያ የፈጸማችሁበትን የባንክ ሰነድ ፋይናንስ ክፍል እንድታቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ ክፍያ በወቅቱ ባለመክፈል የሚፈጠረው መስተጓጎል ትምህርት ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድና ምንም አይነት መጉላላት በተማሪዎቻችን ላይ እንዳይከሰት ወላጆች ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡
ማሳሰቢያ: ከሰኞ ሰኔ 10 ቀን 2016ዓ. ም ጀምሮ ክፍያ ያላጠናቀቀ ተማሪ ክፍል የማይገባ መሆኑን በጥብቅ እናሳሰባለን::
ከማክበር ሰላምታ ጋር
የኢትዮ ብሔራዊ ት/ቤት አስተዳደር
ሰኔ 05 ቀን 2016