ethiop_pdf | Unsorted

Telegram-канал ethiop_pdf - Ethiopian pdf

983

ይህ channel የትምህርት መጽሀፍ እና አንዳንድ ልቦለድ መጽሐፍቶችን የምታገኙበት ምርጥ eBook store ነው ማንበብ ሰው ያደርጋል!!! ለማናገር ከፈለጉ👇 @ethiopdf1bot (Student book @ethiopdf2bot ) Group @eniteyayek

Subscribe to a channel

Ethiopian pdf

/channel/kinfemichael_petross

Читать полностью…

Ethiopian pdf

@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

/channel/kinfemichael_petross

Читать полностью…

Ethiopian pdf

@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

📖አርማጌዶን
✍በደራሲ ዶ.ር ጆን ኤፍ ዋልቮርድ
📍ትርጉም:-በሰለሞን ደጀኔ
📌የነዳጅ ዘይትና የመካከለኛው ምስራቅ ውዝግብ
📌መፅሀፍ ቅዱስ ስለ መካከለኛው ምስራቅና የምዕራብ ስልጣኔ ማብቂያ የሚነግረን ነገር
@ethiop_pdf
@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

ዮቶድ
Join and share
@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

🗓ርእስ:- 🔗በቀልና ፍንጥ ርጣሪው

ደራሲ✍ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ
join and share
ⒺⓉⒽⒾⓄⓅⒾⒶⓃ ⓅⒹⒻ

@ethiop_pdf
@ethiop_pdf
አስተያየትና ጥያቄ
@ethiopdf1bot
ለተማሪዎች መፅሀፍ
@ethiopdf2bot

Читать полностью…

Ethiopian pdf

🎽🎽🎽🎽🎽🎽🎽🎽🎽🎽🎽🎽
➊ ምን ጊዜም ለስዎች አሰፈላጊያቸው እንጂ ፈላጊያቸው አትሁን! ከቻልክ ለችግራቸው ደራሽ ሁን ለችግርህ ውይንም ለጥቅምህ ግን አትፈልጋቸው፡፡

➋ ስው ወሬ አያጣም/ ደግ ፡ብትሆንለት~ተርፎት ነው :
ብትቀርበው~ልምምጥ ነው ፡ዝም ብትል~ነገርኛ ነው ፡ ብትረሳው ~ትቢተኛ ነው እያለ ያወራብሀለ፡፡

➌ ቅጠረን ይሉኛል ፡ስዎች ሳይገባችው ትርፍ ቦታ የለም ብለሽ ንገሪያቸው ተንስራፍተሸበት በ አእምሮዬ ጓዳ አንቺን ዬት አድርጌ ልቀበል እንግዳ

➍ ሚስት ማግባት ትዝ የሚልህ ልጆችን ስታይ ከሆነ ሚስትህን የምትፈልጋት ለርቢ ነው ማለት ነው

➎ በአንድ ምክንያት የሚወድክ ስው ፡ በሌላ ምክንያት ይርቅካል ለምን እንደሚውድክ ማያቅ ግን ሁሌም ይወድሀል

➏ ከሠዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ ተነሣህበት ተመለስ!
ከፈጣሪ ጋር መሮጥ ጀምር የኔ ካስብክበት ሣይሆን ያስበልክ ቦታ ትደርሣለክ!!!

➐>በመራራቅ ውስጥ በጣም የሚያስፈራው ነገር ይናፍቁህ ወይ ይርሱህ አለማወቅህ ነው

➑ ችክ አትበልበተት
❤️ስትውደው😏 ከጠላክ : ስትነገረው ካልስማህ ፡ ስስጠው ፊትህን ፡ ከስጠህ ጅርባውን ፍፁም ካልተረዳው አስተሳስብህን ችክ አትበልበት አትለማመጠው ወዳጅ አይሆንህም በግድ ያስጠጋኸው


❤️መልካም ቀን❤️
Share 4 ur friends👩‍🎤👨‍🎤
@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

ርዕስ 📕:-መግባትና መውጣት ቁ.3
ደራሲ✍️ :-በውቀቱ ስዩም
ዓ. ም:- 2005
ብዛት📑:-175

@ethiopdf2bot

Читать полностью…

Ethiopian pdf

ርዕስ 📕:-መግባትና መውጣት ቁ1
ደራሲ✍️ :-በውቀቱ ስዩም
ዓ. ም:- 2005
ብዛት📑:-175

@ethiop_Pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

አቢሲኒያ 24 (ኤፍ ኤም66.6)
ለወዳጆ ያጋሩ

@ethiopdf2bot
@ethiopdf1bot 👉አስተያየት

join and share
@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

መቆያ አጫጭር ልብ ወለዶች እና ግጥሞች
ደራሲ :- አበራ ለማ

@ethiopdf2bot
@ethiopdf2bot

Читать полностью…

Ethiopian pdf

📒 "ደማሙ ብዕረኛ"
✍ መንግስቱ ለማ


@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

/channel/Mickey_Bimerew

Читать полностью…

Ethiopian pdf

@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

አሌክስ አብርሀም
@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

🌿የምትሰድበው እራስክን ነውና ምላስክን ሰብስባት!

አሁን አሁን ስድብ ከአስነዋሪነቱ አልፎ መግባቢያና የመዝናኛ መንገድ ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በተለይ እኛ ወጣቶች ስንገናኝ የመጀመሪያ ቃላቶቻችን የእግዜር ሰላምታ መሆኑ ቀርቶ ዘመን አመጤው አራድነት ያለበሰን የስድብ ቃላቶች ናቸው፡፡ ፊልሞቻችን ለማሳቅና ለማዝናናት ከጥልቅ ጥበባዊ ድርጊት ይልቅ ተከፍቶ ካደረ አፍ የሚወጡ፤ የሰውን ማንነትና ስብዕና ዝቅ የሚያደርጉ ስድቦችን ይመርጣሉ፡፡

አንድ የማይገባኝ ነገር አለ፤ በእየቀኑ ሙልጭ አድርጎ እየተሳደበ 'ለቀልድ' ነው የሚል ሰው አለ፡፡ ለምሳሌ አንድ ወጣት ጓደኛውን በእየቀኑ 'አንተ ደንጋይ ና እስኪ' ብሎ ሲጠራው እንዲህ ተብሎ የሚጠራው ሰው ቀስ በቀስ ስሙን እረስቶ፤ ሰዋዊ ባህሪውን እረስቶ ድንጋያዊ ባህሪን ተላብሶ ነው ቁጭ የሚለው፡፡

አንድ ታሪክ ላካፍላችሁ አባት ልጃቸውን "አንተ ውርንጭላ ና" ይሉታል፡፡ ይህ ህፃን #ውርንጭላ ምን ማለት እንደሆነ ማውቅ ፈለገና አንድ ቀን ሰዎች በተሰበሰቡበት አባቱን ጠርቶ "አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ" ይለዋል፡፡ አባትም ይፈቅድለታል፡፡

ልጅም "ውርንጭላ ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃል፡፡ አባት ሆዬ እንደዛ ብሎ መሳደቡን ዘንግቶ "ውርንጭላማ የአህያ ልጅ ነው" ብሎ ይመልሳል፡፡ በዚህ ወቅት ልጅ "አንተ አህያ ነክ ማለት ነዋ" ብሎ ይናገራል፡፡

✍️እናም ሁሌም ቃላቶች እኛን፣ ማንነታችንን ይገልፃሉ፡፡ ሰዎችን ስንሳደብ በቅድሚያ እራሳችንን ነው የምንሰድበው፡፡ የሰውን እናት ስንሰድብ በቅድሚ 9 ወር በሆዷ ተሸክማ አምጣ የወለደችንን እናታችንን ሰድበን ነው፤ ስለዚህ PLS ስድብን ማቆም እንለማመድ፡፡ በተለይ "እናትህ እንዲህ ትሁን" ብሎ ስድብ እጅግ ያማልና እንተወው፡፡

ደግ ደጉን እናስብ፤ ደግ ደጉን እንናገር፤ ደግ ደጉን እንተግብር፤ ምክንያቱም መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና፡፡/channel/ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

ህዝቡ አያነብም!!!
👇👇👇👇👇👇

"....ብዙ ኢትዮጵያውያን ጉጉታቸው ነዳጅ ተቆፍሮ አልወጣም ነው። እኔ ደግሞ ነዳጅ ተቆፍሮ ከመውጣቱ በፊት ንዴታችንን ይውጣ እላለሁ። ብስጩ ህዝብ፣ እልኸኛ ህዝብ፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለው ህዝብ፣ የማይግባባ ህዝብ... ነዳጅ ቢያወጣ የመኪና ፋብሪካ ሳይሆን የሚያቋቁመው፥ ሰይጣን #የክብሪት_ፋብሪካ ያቋቁምለታል፤ ክብሪት ያቃብለዋል።
.
አጼ ኃ/ሥላሴን ስንገለብጥ እኮ ሌባ ብለን አባርረናቸው ነበር፤ ቀጥሎ ለመጣ መንግስትም ስናጨበጭብ ነበር፤ ህዝቡ ደርግ ሲመጣ እኮ ሶሻሊዝም እግዚአብሔር የለም ለማለት እኮ ቄሱ ነው አስቀድሞ ካድሬ የሆነው። ይሄ መንግስት ሲመጣም በብሔር በቋንቋ ይደራጅ ሲባል ህዝቡ አጨብጭቦ ነው የተቀበለው፤ ነገም ሌላ ቢመጣ ለማጨብጨብ የኢትዮጵያ ህዝብ ለምን እንደሚያጨበጭብ
የሚጠይቀው አጨብጭቦ እጁ ከተላጠ በኋላ ነው። በጣም ችግር አለ። ምክንያቱም #አያነብም። ህዝባችን የጥቂት ፓለቲከኞች #የሀሳብ_መስጫ ሳጥን ነው የኢትዮጵያ ህዝብ። ጥቂት ፓለቲከኞች ሀሳባቸውን ያራግቡበታል።"
......
|| ☞ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማዮህ በአንድ ወቅት ከተናገሩት/channel/ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

🔎🗂ከድንቃ ድንቅ አለም ትንሽ እንንገራችሁ
📍ስናስነጥስ ልባችን ለ 1 ሴኮንድ ቀጥ ትላለች::
📍የሰጎን አይን ከ አንጎሏ ይበልጣል::
📌ቀጭኔ ልጇን የምትገላገለው ቆማ ነው::
📌ፈረሰ እና ላም ቆመው እንቅልፍ ይወስዳቸዋል::
📌ከወንዶቹ አይን ይልቅ የሴቶች አይን በሁለት እጥፍ ይርገበገባል::
📌የዝንብ እድሜ ከ2-3 ቀን ብቻ ነው::

Читать полностью…

Ethiopian pdf

💥ኢሉሚናቲ 666

join and share
@ethiop_pdf
@ethiop_pdf

discussion Group👇
@eniteyayek

Читать полностью…

Ethiopian pdf

📒📒መርበብት📒📒
ምእራፍ-ሰባት
ክፍል ሁለት
ደራሲ:-አለማየሁ ዋሴ እሸቴ
አቅራቢ👉ዘካሪያስ ገ/ሕይወት

...በጊዜው የአደራው ክብደት ስላልታየው ነገሩን ቸል ብሎ ከቄሱ የተቀቀለውን ሳጥን በጥንቃቄ አስቀምጦ ወደ መደበኛው ስራው አተኮረ። ወጣቱ መሐንዲስ በወቅቱ የመንገድ ስራው ተጠናቆ ጣልያንና ህዝቦቿ ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጥቅም በማመንጨት ተጨማሪ ብልፅግና መፍጠር ለማስቻል ሀገሩ የጣለችበት አደራ በመሆኑ ያ ድልድይ ስራው ላይ አተኮረ።

አዲሲቷንና የተስፋይቱን ምድር ሞሶሎኒ በሮም አደባባይ ላይ <እንደልባችሁ ፀሀይ የምትሞቁባት ሀገር በምስራቅ አፍሪካ እሰጣችኋለሁ> ብሎ ያቅራራባትን ኢትዮጵያን በመሠረተ ልማት በማበልጸግ ለታላቋ ጣልያን እንዱስትሪዎች የጥሬ እቃ ማቅረቢያ በሥራ ለደከሙ ጣልያናውያን የእረፍት ማሳለፊያ የፀሀይ መሞቂያ ሀገር ለመፍጠር የመሐንዲሶች ቡድን ቀን ከሌት መስራት ቀጠለ።

ቅድም እንዳልኩህ በአምሥት አመት ጊዜ ውስጥ ተከናወነ ተብሎ ለመገመት የሚያዳግት የመንገድ ግንባታ ከአስመራ በአድዋ አድርጎ ጎንደር ከዚያም የአባይን በረሃ አቋርጦ አዲስ አበባ ማድረስ ቻሉ። በዚህ የትጋትና የምህንድስና ጥበብ ሥራ ፋታ ያልነበረው ያ ወጣት መለንዲስ እንደተመኘው የመንገድ ሥራው ተሠርቶ አዲስ አበባ ቢደርስም የሀገሩ ፋሺስት መንግስት በአውሮፓ ከገጠመው ቀውስ ጋር ተዳምሮ በኢትዮጵያውያን ፅኑ ተጋድሎ ኢትዮጵያ የተስፋ ምድራቸው ሳትሆን የውርደትና የሽንፈት እንባ ሆናባቸው በምራል ክስረትና በአካል ጉዳት ወደ ሀገሩ መመለስ ግዴታ ሆነበት" አሉና ተከዝ አሉ።

ሚስተር ኢስጢፋኖ በተከዙበት ቅፅበት ቀሕሊናቸው ከሲሳይ ሰውረው የሚከተለውን እያነበነቡ ነው።

"የሰው ልጅ ግብዝ ነው። ስለራሱ ወገን ብልፅግና ስለ ራሱ ሀገር እድገት ሲያስብ የሌላውን በመጉዳት ላይ መሆኑን እያወቀ እንኳን በሀገሩ ፍቅር ብቻ ታውሮ ድርጊቱን በትጋት ይሠራል። የሌላውን ሀገርና ህዝብ በድሎ የራሱን ሀገር ለማበልፀግ ፈጣሪውን ይማፀናል። ፈጣሪ የእርሱን ሀገር ብቻ የሰራ የእርሱን ወገን ብቻ የፈጠረ ይመስል። ፈጣሪ የሁሉም ፍጥረታት ብሔራት አህጉራት ፈጣሪ መሆኑን ዘንግቶ የግፍ ስራው ተባባሪ ሊያደርገው ይማፀነዋል። የረሳነው ነገር ግን ፈጣሪ ሁሉንም ሀገር በልዩ ልዩ ጸጋ ሁሉንም ሕዝብ ቀልዩ ልዩ ክብርና ስጦታ የፈጠረ በመሆኑ በመሆኑ አንዱ ሌላውን መዝረፍና መንጠቅ ተገቢ አልነበረም። እግዚአብሔር ያለፀጋ ያለአቅም የፈጠረው ሕዝብና ሀገር የለምና።"

ብቻቸውን እያወሩ እንደሆነ ትዝ ሲላቸው እንደመባነን አሉና "እያዳመጥከኝ ነው አይደል?" አሉት።

ሲሳይም አንገቱን እየነቀነቀ "አዎን በደንብ እንጂ" አለ።

ከዚያው ሳይወጡ "ፋሺስቶች የውስጥ ድቃታቸውን በሀገር ፍቅርና በብሔራዊ ስሜት ማር ለውሰው የሀገራቸውን ህዝብ በእብሪነት ስሜት አሳብደዋል። የሞሶሎኒን የሮም አደባባይ ዲስኩር የሰሙ ወይዛዝርት የጆሮ ጌጣቸውን የእጅ አምባራቸውን ሌላው ቀርቶ የጋብቻ ቀለበታቸውን ለጦርነቱ ማስፈፀሚያ ለግሰዋል። እንደምታውቀው በየትኛውም ሀገርና ህዝብ ታሪክ ውስጡ ብዙ የሚያሳፍርና የሚያስጸጽቱ ክስተቶች ሊፈጸሙ ይችላሉ። በእኛም የሆነው እንደዚያው ነው። እስከ ዛሬ አዋቂዎቻችን ከሚያፍሩባቸው ክስተቶች ውስጥ አንዱ በዚያ ጦርነት ወቅት የካቶሊክ ካህናትና ካሪዲናሎች። ዘማች ሰራዊቱንና የጦር መሳሪያውን ቅዱስ ጦርነት ብለው ባርከው መሸኘታቸው ነበር። እንዲያውም የእናንተ ሀገር ምሁራንም ሀገራችን ጣልያንን እስከ አሁን ድረስ ካሳ ከሚጠይቁባቸው ወቀሳዎች አንዱ በወቅቱ የቶራኖ ሊቀ ጳጳስ የተናገሩትን በመጥቀስ ነው። መቼም ይህንን ታውቃለህ አይደል?" አሉት።

ሲሳይም "በጨረፍታ እሰማለሁ። ቃል በቃል ግን ምን እንዳሉ አላቅም" አለ።

ያሉትን እኔ ልንገርህ አሉና። የቶራኖ ሊቀ ጳጳስ ያሉት:-
<በኢትዮጵያ ላይ የታወጀው ጦርነት ለካቶሊክ እምነት አልገዛም ያለችውን አፈንጋጯን ኢትዮጵያን በሯን የሚያስከፍት ቅዱስ ጦርነት ነው።> የሚል ነበር።
በጊዜው አሁን እንደምናገርለት ባለታሪክ መሐንዲስ ያሉ ወጣቶችንም ማማለልና ማሳለፍ የቻሉ ቢሆንም የኋላ የኋላ የፍትህና የእውነት ፀሀይ ስትወጣ ጨለማ ግብራቸው ሲገለጥ ግን አሳፋሪ ታሪካዊ ስሕተት ሆኖ መታየቱ አልቀረም።

ይገርምሃል በዘመናት ታሪኳ ለአጭር ጊዜም ቢሆን የኢትዮጵያን ባንዲራዋን ያወረደው ሞሶሎኒም መጨረሻው አላማረም። የሁለተኛው የአለም ጦርነትን ማብቃት ተከትሎ ሽንፈቱን ተቀብሎ ጣልያንን ለቆ ወደ ሲዊዘርላንድ ሲሸሽ ተይዞ በዘጠኝ ጥይት ተደብድቦ ከተገደለ በኋላ አስክሬኑ ሚላን አደባባይ ላይ ተጥሎ ሲረገጥና ሲረገም ዋለ። ከዚያም እንደገና አስክሬኑ ቁልቁል ተዘቅዝቆ እንዲሰቀል ተደረገና ሕዝብ ሲዘባበትበት ከዋለ በኋላ ባልታወቀ መናኛ ስፍራ እንዲቀበር ተደረገ። ከዓመት በኋላ በፋሺስት ደጋፊዎች በስርቆቶ ቡድኑ ተቆፍሮ በስውር በክብር እንዲያርፍ ተደረገ። ይሁን እንጂ ወሬው ከወቅቱ ባለስልጣናት ጆሮ በመድረሱ ከአራት ወራት በኋላ በድብቅ ከተቀበረበት ስፍራ አንድ እግሩ ጎሎ የተገኘ ቢሆኖም እንደገና በስውር መናኛ ስፍራ እንዲቀበር ተደረገ። ከዐሥራ አንድ አመት በኋላ በብዙ ልመና ቅሪት ዐፅሙ በቤተሰቡ መካነ መቃብር እንዲያርፍ ተደርጓል። ሞሶሎኒ በቁሙ ውርደት ብቻ ሳይሆን ሞቶም በድኑ በእጅግ ተንከራቷል። ሞሶሎኒን ለዚህ እብሪትና እብደት ያበቃው ጨብጥ(syphilis) የተባለ የአባላዘር በሽታ በአእምሮው ላይ በፈጠረው ችግር ነው በሚል መላምት ከመከረኛው አስክሬን ጭንቅላቱ ተከፍቶ የአንጎሉ ክፋይ ለምርመራ ወደ አሜሪካ እንዲላክም በኅብረቱ ጦር ተደርጎ ነበር" አሉና በረጅሙ ተነፈሱ። ሲሳይም ከሰማው ታሪክ ተነስቶ በተራው በሐሳብ ማነብነብ ጀመረ።

"አንዳንድ ሀገሮችም ሳትበድላቸውና ሳትደርስባቸው ከዚያ በፊትና በኋላ ከኢትዮጵያ መከራዎች ሁሉ ጀርባ እጃቸውን በቀጥታም በተዘዋዋሪም አስገብተው ነበር። አምላኳ አይተዋትምና የእጃቸውን አግኝተዋል። ያገኛሉም። በሰፈሩት ቁና ሲሰፈር ብትንትናቸው ሲወጣ ተመልክታለች። ተመልከት ኢራቅን ሶሪያን ሊቢያን ሶማሊያን ሱዳንንና የመንን። የሳዑዲ አረቢያ የግብፅና የቱርክ ደግሞ ጊዜው ሲደርስ ይታያል ወይም ይታረሙ ይሆናል። ከዋና ዋናዎቹ የኢትዮጵያ ጦርነት ጀርባ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሽ የነበረችው ቱርክ አሁን አሁን አበዳሪና ኢንቨስተር ሁና ሽር ብትን እያለች ነው። ዘመን ኢትዮጵያን ወይ ሊክሳት ነው አለበለዚያም እያባበላት ነው።

ያም ሆነ ይህ የኢትዮጵያ አምላክ ይታገሳል እንጅ አያንቀላፈም።
ግፍ ሞልቶ እስኪፈስ ዝም ይል እንደሆን እንጅ እንድትጠፋ ፈጽሞ የማይተዋት መሆኑ ታሪክ ምስክር ነው" አለ ለራሱ።

አዛውንቱ ኢስጢፋኖም የሲሳይን በሐሳብ መወሰድ ከተመለከቱ በኋላ"በል ታሪኩን ልጨርስልህ" በማለት አትኩሮቱን ወደርሳቸው መለሱት።...
.
.
.
................ይቀጥላል.................


join, like and share
@ethiop_pdf
@ethiop_pdf
አስተያየትና ጥያቄ
@ethiopdf2bot

Читать полностью…

Ethiopian pdf

የአዲስ አበባ ውሾች
በደራሲ ዳንኤል ክብረት

@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

ርዕስ 📕:-መግባትና መውጣት ቁ.2
ደራሲ✍️ :-በውቀቱ ስዩም
ዓ. ም:- 2005
ብዛት📑:-175

@ethiop_Pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

📒📒መርበብት📒📒
ምእራፍ-ሰባት
ክፍል አንድ
ደራሲ:-አለማየሁ ዋሴ እሸቴ
አቅራቢ👉ዘካሪያስ ገ/ሕይወት

..."አሁን የምነግርህ ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ወጣት ስለነበረ ስለ አንድ ጣልያናዊ መሐንዲስ ነው። ልብ ብለህ እንድታዳምጠኝ ፈልጋለሁ" አሉ ኢስጢፋኖ ኢቶሬ።

ሲሳይም ከድንጋጤው መንፈስ በትንሽ መለስ አለ።
"ይህ መሀንዲስ በወጣትነት ዘመኑ በጣሊያን ጦር ሃይሎች ውስጥ የጦር መሀንዲስ ሆኖ አገልግሏል። በዚህ ሙያውም ጣልያን በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን ስትወርር ወደ ኢትዮጵያ ከዘመተው የፋሺስት ሠራዊት ጋር አብሮ ዘምቷል።

ከኤርትራ በአድዋ በኩል በሽሬ አድርጎ የተከዜን ወንዝ ተሻግሮ ወደ ጎንደር ካቀናው የጦር ክፍል ጋር መሐንዲስ ሆኖ የሠራዊቱን እግረኛ እንቅስቃሴ ከሚመሩት ወጣት ወታደራዊ መሀንዲሶች ውስጥ አንዱ ነበር።

የወቅቱ የጣልያን ፋሽስት መንግስት የኢትዮጵያን ማእከላዊ መንግስት በጦር አሸንፎ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ የሀገሪቱን ቅኝ ተገዥነት ያረጋገጠ ሲመስለው ወደ መሠረተ ልማት ግንባታ ፊቱን አዞረ። ወጣቱ መሀንዲስም ከአስመራ በአድዋ ጎንደር ሥራ በተለይም ጎንደር አከባቢ የነበረው የሥራ ክፍል ውስጥ ተዛወረ። በዚያ ወቅት የፈታኙንና አስደናቂውን የሊማሊሞ ጠመዝማዛ መንገድ ቅየሳ ሥራና ግንባታ ላይ ከተሣተፉ ወጣት መሀንዲሶች ውስጥ እንደነበር ሲገለፅም ታላቅ ኩራት ይሰማዋል።

የመንገድ ሥራው ተጧጡፎ ከጎንደር ወደ ጎጃም ብሎም ወደ አዲስ አበባ ለማድረስ ጣልያኖች የኢትዮጵያን አርሶ አደር ጉልበት በካኪ ቁምጣ እያባበሉ እንዲያም ሲል በኃይል እያስገደዱ ቀን ተሌት ይሠሩ ነበር።

ይህ ወጣት ከጎንደር ወደ ባህርዳር በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ እንፍራዝ ከተማ አቅራቢያ <እንፍራዝ> ከሚባለው ወንዝ ላይ የሚሠራ ድልድይ ተቆጣጣሪ መሀንዲስ ሆኖ ሲሰራ እስከ አሁን ድረስ የሚያስጨንቀውን ምሠጢራዊ አደራ የሚቀበልበት አጋጣሚ ተፈጠረ።

የጣልያን ፋሽስት ጦር ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለስደት ቢዳረግም እንዲሁም የመንግስቱ ጦር መበታተን ቢችልም የኢትዮጵያን አርበኞች ቅስም ሰብሮ በሌሎች ሀገር እንዳደረገው የጣልያንን ቅኝ ገዥነት አሜን ብሎ የሚቀበል ሀገርና ህዝብ መፍጠር አልተቻለውም ነበር። የሀገራችሁ አርበኞች በቡድን በቡድን በመሆን በደፈጣ ውጊያ ሲያስፈልግም በግንባር በመግጠም ፋታ ነሥተውት ነበር። ይህንን አይበገሬነታችሁን ለመስበር የጣልያን ወታደሮች እጅግ ጭካኔ የተሞላበት ተግባር በአርበኞችና በሕዝቡ ላይ ቢፈጽሙም የሚቀየር ነገር አልነበረም።

በእንደዚህ አይነት የነፃነት ትግል ውስጥ የኢትዮጵያ ቅኝ ተገዥነት አይቀሬ ነው በሚል ተስፋ የጣልያን መንግስት በየቀኑ በተለያዩ ቦታዎች ዜጎቹን መሥዋዕት እያደረገ መሠረተ ልማቱን ማስፋፋቱን ተያያዘው። እንደ እውነቱ ከሆነ እናንተ እንደምታዩት ባላውቅም በአምስት አመት ጊዜ ተከናወነ ብሎ ለመቀበል የሚያዳግት የዋሻ ውስጥ መተላለፊያ ያላቸው በተራራዎች ላይ የሚጠማዘዙ ረጃጅም መንገዶችና ድልድዮችን እንዲሁም በከተሞች ደግሞ ውብ ውብ ሕንፃዎችን መሥራት ተችሎ ነበር።" ሲሉ ሲሳይ ቀበል አድርጎ:- "እውነት ነው! ሥራው አስደናቂ ሊባል የሚችል ነው" አለ።

እርሳቸውም ወጋቸው እንዳይናጠብ በመፈለግ ስሜት ከአፋ ቀበል አድርገው ታሪኩን ቀጠሉ።

"ይኸውልህ ሚስተር ሲሳይ! አንድ ቀን ከሰዓት በርከት ያሉ የጣልያን ወታደሮችና ሲቪሎች በኢትዮጵያ አርበኞች የደፈጣ ውጊያ አደጋ ደረሰባቸው። ሙትና ቁስልኛ ሆነውም ይህ ወጣት መሀንዲስ ወዳለበት የመንገድ ሥራ ካምፕ ይደርሳሉ።

የሞቱት ተቀብረው ቁስለኞቹ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ ወታደሮቹ ወደ እናት ጦር ክፍላቸው ሲላኩ ከመካከላቸው አብሮ የነበረ አንድ የካቶሊክ ቄስ ከመንገድ ሥራው ካምፕ ሕክምና እየተደረገለት እንዲቆይ ተወሰነ።

የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ የሆነው ይህ ወጣት መሀንዲስ ይህንን ቄስ በተቻለው መጠን ሁሉ ይንከባከበውና ከቁስሉ እንዲድን ያጽናናው ነበር። ይሁንና እግሩ ላይ ባቱ አከባቢ የገባው ጥይት መመረዝ ወይም ኢንፌክሽን ፈጥሮ ሰውነቱ በሙሉ ተመረዘና የመዳን ተስፋው ተመናመነ።

መሞቱ የማይቀር መሆኑን የተረዳው ቄስም በርኅራኄ የሚያስታምመውን ወጣቱን መሐንዲስ ለብቻው አስጠርቶ እጅግ በተዳከመ ድምፅ እንዲህ አለው:- "ሞቴ... የማይቀር ነው ሐዘኔም... ከባድ ነው። ሐዘኔ የከበደው የምሞት... መሆኔን በማወቄ አይደለም።...ይልቁንም በጴጥሮስ መንበር ...የተሰየመችውን የቫቲካን ቤተክርስቲያንን ክብር... የቅዱሳን ፖፕ... አደራ ሳልወጣ... በመቅረቴ ነው" አለ ትንፋሹ እየተቆራረጠ።

"የምን አደራ ነው?" አለ ወጣቱ መሐንዲስ እየተጨነቀ። ቄሱ ሰውነቱ በላብ ተዘፍቆ ዐይነቹን መግለጥ እየተሳነው በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እያጣጣረ እንደሆነ ሲረዳ እርሱም በእጅጉ ተጨነቀ።
"ምንድን ነው? የምን አደራ ነው?" አለ ደጋግሞ።
"ከቦ.ርሳ.ዬ ው.ስጥ ያለ..ውን ሣጥ.ን አውጥ..ተህ ውስ.ጡ ያለ..ውን መልእ..ክት አንብ..በህ ፈ..ጽመው አ.ደ.ራ!" አለው እጁን ጨበጥ አድርጎ።

"ምንድን ነው የሚሉኝ?" አለ እየተርበተበተ። ግን መልስ አልነበረም። ቄሱ ወዲያው አንደበቱ ተዘግቶ በሰዓታት ውስጥ እስከ ወዲያኛው አሸለበ።

ቄሱ እስከ ቁስሉ ወደ ካምፕ ሲመጣ በጀርባው አዝሎት የነበረውን ቦርሳ ከፍቶ ሲያይ አንድ መጽሀፍ ቅዱስ አንድ የጸሎት መጽሐፍና የብረት ሣጥን አገኘ።...
.
.
.
..............ይቀጥላል...................

join, share and like
@ethiop_pdf
@ethiop_pdf
ለጥያቄዎና አስተያየቶ
@ethiopdf1bot
ለተማሪ መፅሀፍ @ethiopdf2bot

Читать полностью…

Ethiopian pdf

📒📒መርበብት📒📒
ምእራፍ-ስድስት
ክፍል ሁለት
ደራሲ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ
አቅራቢ👉ዘካሪያስ ገ/ሕይወት

...ትንሽ ቆዩና ደግሞ "ተከዜ ተፋሰስ ውስጥ ዝቋላ አከባቢም እኮ የብረት ማእድን ክምችት አለ። ምን ተደረገ? አሉ።
"ኧረ እንደውም ስለሱ ሰምቼ አላውቅ" አለ አንገቱን አቀርቅሮ በውስጡ ደግሞ "ምንድነው ለሆድ ጥሩ ምግብ አቅርቦ ሲያበቃ አእምሮ ማሸማቀቅ? ምናለ ቢተውኝ" በልቡ እያለ።

የማእድን ክምችቶችን የፋብሪካ የእርሻና የመንገድ የመሳሰሉትን በርካታ የፕሮጀክት ሐሳብ እያነሱ ሲጠይቁት ቆዩ። ሲሳይም ብዙውን <አልተሰራም> እና ትንሽ <አዎን ተሰርቷል> የሚሉ መልሶችን እየተሸማቀቀ ሲመልስ ቆየ።

ይህን የታዘቡት አዛውንቱ ኢስጢፋኖም በመሐል ሳያስቡት:-
"ለነፃነት ሲል መተኪያ የሌላት ህይወቱን በጀግንነት የሚገብር ሕዝብ እንዴት ለልማትና ለብልፅግና ዕውቀቱንና ጉልበቱን ይሰስታል?!" ብለው አጉረመረሙ።

"ሕዝቡ ለግሞ ሳይሆን የሥራ እቅድና ስልት የሚነድፍ ባለሙያ ያንንም የሚያስተባብር እውነተኛ ጠንካራ አመራር መጣት ይመስለኛል" አለ ሮቤርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣልቃ ገብቶ።

"ሆኖ ነው እንጂ" አሉ ኢስጢፋኖ አንገታቸውን በአዎንታ እየነቀነቁ።
ትንሽ ጎረስ ጎረስ አደረጉና ደግሞ:-

"ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ አንፍራዝ ወንዝ ላይ ያለው ድልድይ እስካሁን አለ?" አሉት።

በልቡ "ወይ አበሳዬ!" አለና "እ...በጣልያኖች የተሰራው ድልድይ ከዐሥር ዓመት በፊት ፈርሷል። ከዚያ ወዲህ አንድ የብረት ድልድይ ተሰርቶ እርሱም ፈርሶ አሁን የኮንክሪት ድልድይ ተሠርቶበታል" አለ ሲሳይ።

"እ... ስንት አመት አገለገለ ማለት ነው?..." አሉና ራሳቸውን ጠይቀው ራሳቸው መልስ እንደመፈለግ ወደ ጣሪያው ሲያዩ ቆይተው:-

"አ ወደ ሰባ አመት አገልግሏል ማለት ነው። ደኀና ነው። የታሰበው እኮ ለ ሀምሳ አመት ነበር" አሉ። አሁንም እንዴት እንዳወቁ ሲሳይ ግራ ገባውና ዝም አለ። በሀሳቡም "ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ማወቅ የሚገባን ያህል ባይሆን እንኳን ቢያንስ ባእዳን ስለ እርሷ ያላቸውን ዪክል ግንዛቤ አለመያዛችን ያሳዝናል" አለ።

ትንሽ ቆይቶ ፈገግ አለና:-
"አንዲያው ይቅርታ ያድርጉልኝና ስለኢትዮጵያ ከእኔ በላይ የሚያውቁ እንደሆነ ተረድቻለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ኑረዋል እንዴ?" አለ ሲሳይ በትህትና።

ሚስተር ኢስጢፋኖ ለጥያቄው መልስ ሳይሰጡ አይን አይኑን ትኩር ብለው እያዩ ፈገግ አሉና በትዝታ የተሳቡ መስለው ለትንሽ ጊዜ ፈዘው ቀሩ።

ራት አልቆ የምግብ ማንሸራሸሪያ ቀርቦ ስለነበር ድንገት ቀና ብለው ወደ እነ ሮቤርቶ ዞር ብለው:-

"እራቱ እንደተመቻችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። እናንተ ተጫወቱ እኔና ሚስተር ሲሳይ የምንወያየው ጉዳይ ስላለ ወደ ቤተ መጻሕፍት ልንሄድ ነው" አሉና ተነስተው ሲሳይ እንዲከተላቸው በእጃቸው ጭምር ጋብዘው በስተምስራቅ በኩል ባለው ግድግዳ በኩል አንድ በር ከፍተው ገቡ።

የሚስተር ኢስጢፋኖ ቤተመጻሕፍት ጣራው ግድግዳውና ወለሉ <ማሆጎኒ> ከተባለ እንጨት በጌጠኛ መልክ ተጠርቦ የተሰራ ነው። መሃል ላይ የፋርስ ምንጣፍ ተነጥፎበታል። አንድ ትልቅ መስኮትና በር ሲቀር በስተቀር ከጣራው እስከ ወለሉ ድረስ ከዚህ እንጨት በተሰራ የመጻሕፍት የተሞላ ነው። የመጻሕፍቱ ብዛት እኚህ ሰው ዕድሜ ልካቸውን ሲያነቡ ለመኖራቸው ምስክር ነው። የሚያብረቀርቅ ትልቅ ጠረጴዛ ጎን ሲሳይ እንዲቀመጥ ጋብዘውት እርሳቸው በአንድ በኩል የቆዳ ወንበር ስበው ቁጭ አሉ።

ሲሳይ ፍርሃት በውስጡ ቢታገለውም የመጻሕፍቱ አደረጃጀትና የሚስተር ኢስጢፋኖ ሁኔታ ግን የሚያረጋጋ ሆነለት።

"ሚስር ሲሳይ! ለረጅም ዘመን ሳልፈፅመው የቀረሁት ከእኔ ጋር የሚኖር አደራ አለብኝ። ይህን አደራ እንድፈጽም እኔ የተጠየኩ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አልቻልኩም። ዕድሜዬ እየገፋ ሲሄድ ደግሞ አደራው ለእኔ መሆን እንደሌለበት የሞራል ጥያቄ ፈጠረብኝ" አሉና ዝም ብለው በሐሳብ ሰጠሙ።

ሲሳይ እንደገና የፍርሃት ስሜት ሲቀሰቀስበት ታወቀው።
"እናም ይህን አደራ መወጣት ያለበት ኢትዮጵያዊ ነው ብዬ ካመንኩ ቆየሁ። ይሁንና ታማኝ ሰው ለማግኘት በእኔ በኩል የማይቻል ሆነብኝ። ለቤተሰብ ሐሳቡን ባማክርም የሚያቀርቡልኝ ሐሳብ ከእኔ ሞራል ጋር አብሮ የሚሄድ አልሆነም" አሉና ዝም አሉ። ቆይተው:-

"ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን ወንድሜና ወዳጄ ሮቤርቶ ካገራችሁ ኢንቨስት ለማድረግ መወሰኑን ስረዳ ይህንኑ የቤት ስራ እንዲሰራልኝ በማለት የሚታመን ሰው እንዲያፈላልግልኝ ጠይቄው ነበር። አሉ።
ፍርሃት አሁን ስሜት ሳይሆን ጥፍርና ጥርስ አውጥቶ የሲሳይን አእምሮ ይቧጥጠው ጀመር። ቢሆንም ምንም ቃል ሳይተነፍስ ማዳመጥ መረጠ።

"እናም አደራዬን ሊወጣ የሚችል ሰው አንተ ልትሆን እንደምትችል ጠቆመኝ። በዚህ የተነሳ መምጣትህን በጉጉት ስጠብቅ ቆይቻለሁ። ከመሞቴ በፊት በመምጣትህ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ" አሉ ፈጣሪን እንደማመስገን እጆቻቸውን ከዓይኖቻቸው ጋር ወደ ላይ አንሥተው።
"የ..ምን አ..ደራ እንደሆነ አል..ገባኝም?" አለ ሲሳይ እየተንተባተ። "ግዴለም! እርሱን በዝርዝር አስረደሃለሁ" ብለው ዝም ብለው ቆዩና መተረክ ጀመሩ...
.
.
.
...............ይቀጥላል..................


@ethiop_pdf
አስተያየት ጥያቄ
@ethiopdf1bot
የተማሪዎች መፅሀፍ
@ethiopdf2bot

Читать полностью…

Ethiopian pdf

መንገድ ስጡኝ ሰፊ
ገብረ ክርስቶስ ደስታ

@ethiop_pdf

Читать полностью…

Ethiopian pdf

join and share
@ethiop_pdf
@ethiop_pdf

አስተያየት ጥያቄ
@ethiopdf1bot


የተማሪዎች መፅሀፍ
@ethiopdf2bot.
@ethiopdf2bot

Читать полностью…
Subscribe to a channel