ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ኢትዮጵያ  የሶማሊያ መንግስት ያቀረበባትን ክስ መሰረተ ቢስ ስትል አጣጣለች

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኃይሎች በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ላይ ጥቃት አድርሰዋል  በሚል ያቀረበዉን ክስ አጣጥሏል፡፡

ድርጊቱ የተፈፀመዉ ኢትዮጵያ ኃይሎች ሳሆን የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማበላሸት በሚፈልጉ  ሶስተኛ ወገኖች የተፈጸመ ነዉ ብሏል፡፡

ኢትዮጵያ መሰል   ትንኮሳዎችና  የሁለቱን አገራት ግንኙነት  የሚያበላሹ ድርጊቶችን ለመከላከል ቁርጠና መሆኗንም አረጋግጣለች፡፡

የሶማሊያ መንግስት  ባወጣው መግለጫ ዱሎው በተባለችው የጁባላንድ ከተማ የኢትዮጵያ ኃይሎች ጥቃት ፈፅመዋል ሲል መውቀሱ  የሚታወስ ነዉ፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ስብሰባ መጀመራቸውን ጽ/ቤቱ አስታወቀ ።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ምን እየተባባሉ ይመስላችኋል? 🤔

#AbiyAhmed #EmmanuelMacron #Ethiopia #France

Читать полностью…

EthioTube

አሜሪካ አዲሱን የሶሪያ መሪ ለመያዝ መድባ የነበረውን የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ሰረዘች

አሜሪካ የሶርያውን መሪ አህመድ አል-ሻራ በቁጥጥር ስር ለማዋል ለመያዝ መድባው የነበረውን የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ከከፍተኛ ዲፕሎማቶች እና ከሃያት ታህሪር አል ሻም (ኤችቲኤስ) ተወካዮች ጋር ውይይት ካደረገች በኋላ ነው የሰረዘችው።

ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባርባራ ሌፍ ከሻራ ጋር የተደረገው ውይይት "በጣም ውጤታማ ነበር" ካሉ በኋላ እርሱም "ለመወያየት ዝግጁ" ሆኗል ብለዋል።


የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ዋና ከተማዋ ደማስቆ የደረሰው የኤች ቲ ኤስ ታጣቂዎች የበሽር አል አሳድን መንግሥት ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ካስወገዱ በኋላ ነዉ።

ዋሽንግተን አሁንም አማፂ ቡድኑን በአሸባሪነት እንደ ፈረጀች ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ዲፕሎማቶቹ በአሜሪካ የሚደገፍ "የሽግግር መርሆዎች" ላይ፣ ቀጠናዊ ሁኔታዎች እንዲሁም አይኤስን የመዋጋት አስፈላጊነት ላይ መወያየታቸውን አረጋግጠዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም፣ ባለሥልጣናቱ በአሳድ አገዛዝ ዘመን ስለጠፉት አሜሪካውያን ዜጎች፣ በ2012 በደማስቆ የተጠለፈውን ጋዜጠኛ ኦስቲን ቲስ ፣ እና በ2017 የጠፋውን ሳይኮቴራፒስት ማጅድ ካልማዝ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን አስታውቀዋል።

ጉብኝቱ ከአስር ዓመታት ወዲህ በደማስቆ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ መደበኛ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ነው።

ይህ ጉብኝት በሶሪያ የአሳድ ከስልጣን መወገድን ተከትሎ የታየ ድንገታዊ ለውጥ ሲሆን፣ አዲስ ስልጣን የሚረከበውን መንግሥት የአረብ አገራት ድጋፍ ተጨምሮበት አሜሪካ እና አውሮፓ ተጽዕኖ ለማሳረፍ የወሰዱት እርምጃ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም

Читать полностью…

EthioTube

አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፃፉት ደብዳቤ ከስራቸው ተሰናበቱ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ሆነው ላለፉት ስድስት አመታት ያገለገሉትን አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀትን ከስራቸው ማሰናበታቸው ተሰምቷል።

አቶ ሰርፀ ከስራቸው የተነሱት በከንቲባዋ ህዳር 23/2017 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ሲሆን ምክንያቱ ግን በደብዳቤ ላይ አልተገለፀም።

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ስር በሚገኙት 4 ቴአትር ቤቶች ማለትም የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ፣ ሀገር ፍቅር፣ ራስ ቴአትር እና ሕጻናትና ወጣቶች ቴአትር በስራቸው 800 ሰራተኞች አሉ።

ከእነዚህ ሰራተኞች 50 ከመቶው እንዲቀነሱ እንደተወሰነ የደረሰን መረጃ የሚጠቁም ሲሆን በምትካቸው ማለትም 50 ከመቶ የሚሆኑ ከተለያዩ የክልል አካባቢዎች በመጡ ሰዎች በቴአትር ቤቶቹ ምደባ ተከናውኗል ተብሏል።

ይህን ውሳኔ ያልተቀበሉ ላይ ወይም ተቃውሞ ያሰሙ ሰዎች ላይ ከስራ የማንሳት እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን የአቶ ሰርፀ ጉዳይም ከዚህ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

መረጃው የመሠረት ሚዲያ ነው ።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ጋዜጠኛዋ ከስራ መታገዷ ተሰማ

ሰሞኑን የኢሳት ቴሌቪዥን የዜና አንባቢ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቆሴ ወረዳ የተመለከተ ዜና ስታነብ ቆሴ የሚለውን ስም ለመጥራት ሲያስቸግራት ያለውን ቪዲዮ በቲክቶክ ገጿ ላይ መለጠፏ የተለያዩ ትችቶችን አስነስቶባታልተ

ኢሳት ቴሌቪዥን ይህን ተመልክቶ ዜና አንባቢዋን እና የተቆረጠውን ቪዲዮ አሳልፎ የሰጣትን ባልደረባ ከስራ ማገዱን ፋስት መረጃ ከጣቢያው መስማቱን አስነብቧል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በዶ/ር ደብረፂዮን የሚመራው ህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በመቀሌ ስብሰባ ተቀምጧል።

የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው  የሰላማዊ ፖለቲካ ትግል ስትራቴጂዎች ከከፍተኛ አመራሩ ጋር ለመወያየት ነው ተብሏል።

እነዶ/ር ደብረፂዮን  ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በብዙ ጉዳይ ባለመግባባት ላይ መሆናቸው በስፋት ይነገራል። በቅርቡም በመቀሌ ሰልፍና ስብሰባ ተከልክሎ እንደነበርም ይታወቃል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የበርካታ ባለሐብቶች የባንክ ሂሳብ እየታገደ እንደሆነ ታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተሻለ ቢዝነስ ያንቀሳቅሳሉ የሚመባሉ የበርካታ ባለሐብቶች የባንክ ሂሳብ እየታገደ እንደሆነ መሠረት ሚዲያ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

እነዚህ በአብዛኛው የአማራ ተወላጅ የሆኑ ባለሀብቶች እየተመረጡ ተንቀሳቃሽ ሒሳባቸው በህግ እየታገደ ወይም Legal Restriction እየተደረገባቸው እንደሆነ ፐ ተናግረዋል።

በአማራ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር በተያያዘ ለታጣቂዎች ድጋፍ ሊያደርጉ ይችላሉ የተባሉ ሁሉ 'ከላይ በመጣ ትእዛዝ) በሚል በጥርጣሬ ባንካቸው እየታገደባቸው ይገኛል።

ንግድ ባንክ ላይ ብቻ ቢያንስ 200 የሚሆኑ የእነዚህ ባለሀብቶች አካውንቶች እንደታገዱ ታውቋል ፣ የግል ባንኮች ላይ በተመሳሳይ ቁጥራቸው ያልታወቀ እገዳዎች መደረጋቸው ታውቋል።

"አብዛኞቹ የፍርድ ቤት እግድ እንኳን የሌለባቸው ናቸው፣ በጥርጣሬ በሚል በርካታ አካውንቶች ተዘግተዋል" ያሉት ምንጫች ሁኔታው የዛሬ ሶስት እና አራት አመት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት የትግራይ ባለሀብቶች ላይ ከተደረገው ጋር ተመሳሳይነት አለው ብለዋል።

በዚህ ዙርያ አካውንታቸው የታገደባቸውን አንድ ነጋዴ "አካውንቱ መታገዱን የሰማሁት ከቢሮዬ ተደውሎ ክፍያ መፈፀም አልቻልንም ሲሉኝ ነው" ብለዋል።

እኚህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነጋዴ ወደ ንግድ ባንክ ሄደው ሲያጣሩ "ለግዜው እንቅስቃሴ እንዳያደርግ እግድ ተጥሎበታል ተባልኩ፣ ሌላው ቀርቶ በወረቀት ላይ የተፃፈ ማብራርያ ወይም ለእግዱ ማረጋገጫ አልሰጡኝም" በማለት አስረድተዋል።

በተመሳሳይ እርሳቸው የሚያውቋቸው የአራት የአማራ ተወላጅ የቢዝነስ ባለቤቶች አካውንታቸው እንደታገደባቸው እንደሰሙ ጠቅሰው ወንጀል ባልፈፀሙበት እና ክስ እንኳን ባልቀረበበት ጉዳይ ለ40 አመት የሰሩበትን የንግድ ስራ እንዲያቆሙ እንደተገደዱ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ዙርያ ከብሄራዊ ባንክም ሆነ ከሌላ የመንግስት አካል የተሰጠ መግለጫም ሆነ ማብራርያ የለም።

መረጃው የመሠረት ሚዲያ ነው

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የመሠረቱት ፋውንዴሽን ይፋ ሆነ

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የመሠረቱት "የአዳም ፋውንዴሽን" የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ምሥረታውን ይፋ አድርጓል።

አቶ ደመቀ መኮንን በቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመሩት "የአዳም ፋውንዴሽን" ፤ የመንግስት ባለስልጣናት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት በተገኙበት ይፋዊ የማብሰሪያ ሥነ ሥርዓቱን በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ልማትና እድገት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የገለፁት የፋውንዴሽኑ መስራች አቶ ደመቀ መኮንን፤ በተለይ ህፃናትና እናቶች ላይ በመስራት ብሎም መቀንጨርን በመዋጋት ደህንነቱ የተጠበቀ ትውልድ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

"በአፍሪካ መቀንጨርን መግታት" የሚል መሪ ሀሳብ ያለው ፋውንዴሽኑ፤ ከኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘው ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ እንደነበር ተገልጿል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ኃይል ጠቅላይ አዛዥ ጀነራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ ጋር ተወያይተዋል።

Читать полностью…

EthioTube

በዛሬው ተጠባቂ የማንችስተር ደርቢ ማን ያሸንፋል? ሲቲ? ዩናይትድ? ወይስ እኩል ይወጣሉ?

የሊቨርፑል፥ የቸልሲ እና አርሰናል ደጋፊዎች ምን አይነት ውጤት ትመኛላችሁ? 🙂

#PremierLeague #ManchesterCity #ManchesterUnited

Читать полностью…

EthioTube

አርቲስት መሠረት መብራቴ በሎስአንጀለስ ሲቲ ካውንስል ተሸለመች !

በተለያዩ ፊልሞች ፣ ቴአትሮች እና በማስታወቂያ ስራዎቿ አድናቆት የተቸራት ፤ ጎን ለጎንም በምታበረክተው የበጎ አድራጎት አገልግሎት የበርካቶችን አክብሮትና ፍቅርን የተጎናፀፈችው አርቲስት መሠረት መብራቴ በሎስአንጀለስ ከተማ Los Angeles city council እና U.S Africa institute በጋራ ባዘጋጁት “Humanitarian award” የካውንስሉ አባላት በተገኙበት የእውቅና እና የክብር ሽልማት ተበርክቶላታል።

ካውንስሉ አርቲስቷ ለኢትዮጵያ የህፃት የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል በበጎ ፈቃድ አምባሳደርነት እየሰጠች ያለውን አገልግሎት በማክበር በተለይም በአሜሪካን ሀገር የነበራትን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር በመጥቀስ የተለየ እውቅና እንደሚሰጠውና ለዚህ አገልግሎቷም አክብሮት እንዳለው በመግለፅ የእውቅናና የክብር ሰርተፊኬት አበርክቶላታል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ይህ ጉዳይ ወዴት እያመራ ነው ?

ማህበራዊ ሚዲያዎቻችን የዚህ ሳምንት አነጋጋሪ ጉዳይ አድርገውት ሰንብተዋል።

አሁንም ድረስ መልስ የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑም እሙን ነው !

ሚዲያዎቻችን ይዘውት የሚመጡት ማህበራዊ ጉዳዮች በደንብ ተመርምረው ለተመልካች መቅረም እዳለባቸው የሚያሳይ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ፕሮግራም ነው ።

እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ከዚህ ቀደም በ ሰይፉ ፕሮግራም ላይ መቅረቡ የሚታወስ እና የቅርብ ጊዜ ትውስታ ጭምር ነው ።

ሁለት ጥንዶች በዚህ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ጉዳይ ለቧለቤቷ በመለገሷ እና ብዙ የጭንቅ ጊዜያቶችን አብረው በማሳለፋቸው ከዛም በስተመጨረሻ ያሰቡት ተሳክቶ ንቅለ ተከላውን አከናውነው ወደ ሀገር መመለሳቸውን አይተን ተደንቀን አመስግነን አልፈናል ።

በዚህኛው ፕሮግራም ደግሞ በተመሳሳይ ታሪክ ተመልካች ደስታውን ሳያጣጥም ፕሮግራሙ በተላለፈ ማግስት የተባለው ሁሉ ውሸት እንደሆነ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ሀብታሙ በ tiktok መንደር ብቅ ማለቱ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ላይ ጭምር ትልቅ ነጥብ በማስጣል አነጋጋሪነቱን ቀጥሏል ።

ይህ ጉዳይ ከ ሩሐማ ይልቅ ለማን ያመዝናል ? የሚለውን በጥልቀት ማየት ይኖርብናል ፤  ባለጉዳዩ እና ሊደነቅ የሚገባው ሀብታሙ ሆኖ ሳለ እሷ በዛ ፕሮግራም ላይ ብቻዋን የመቅረቧ ምክንያት ምንድነው ? ሀብታሙ በፕሮግራሙ ላይ ያለመገኘቱ ምክንያት በትክክል ተጠቅሷል ወይ ? እሱንስ ለማናገር የሞከረ አካል አለ ወይ? እነዚህና መሠል ጥያቄዎችን  በዚህ ሾው አዘጋጆች ላይ ያስነሳል !

በርግጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰይፉ ምንም አይነት መረጃው እንደሌለው እሙን ቢሆንም ፤ ነገር ፕሮግራሞቻችንን በምን ያህል ትኩረትና ጥልቀት መመርመርና ማቅረብ እንዳለብን ትልቅ ትምህርት ይሰጣል ።

በቂ መረጃ ካልተገኘ ደግሞ ማዘግየት ካልሆነም ማስቀረት ይዞ ከሚመጣው መዘዝ የተሻለ አማራጭ ነው ።

በዚህ ጉዳይ የጉዳዩ ባለቤት የሆነችው ሩሐማን ጨምሮ ሰይፉ ሾው  ፕሮግራሙ  መልስ ሊሰጡበት ይገባል ።

ከዚህ በማስቀጠል ሀብታሙ አሁን ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የስነ ልቦና እርዳታ ሊደረግለት ያስፈልጋል። ቀድሞ ካለበት ማንነቱ ወጥቶ አሁን ያለበትን ማንነት የያዘው እንዲሁም በተለያዩ ሱሶች ተዘፍቆ የሚገኝበት ምክንያት እሷ እንደሆነች በይፋ በ YouTube ሚዲያ ቀርቦ የተናገረ ሲሆን ማህበራዊ ሚዲያ በሆነው tiktok ጭምር እሱም በቀጥታ ስርጭት live በማስገባት እንዲሁም አንዲት የሱ የወንድሙ ሚስት ነኝ የምትል ቤተሰቡን ጨምሮ ተመሳሳይ የሆነ ሀሳብ ሲያነሱ ተመልክተናል ።

ስለዚህ የዚህን ጉዳይ እውነት ለማወቅ እነዚህ ሰዎች ይቅርታ ተጠያይቀው ህይወታቸውን በጋራ መቀጠል የሚችሉበት ሁኔታ ካልሆነም በሰላማዊ መንገድ ተለያይተው የየራሳቸውን ህይወት እንዲኖሩ እና ሀብታሙም ወደ ቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስ የተቻለው ሁሉ መደረግ አለበት ። 

በዚህ ሳምንት የሰይፉ ሾው ፕሮግራም ይህን ጥያቄ ይመልሳል ወይንስ አይመልስም ?

እናንተስ ምን ሀሳብና አስተያየት ይኖራቹሀል ?

Читать полностью…

EthioTube

የቃላት ጦርነቱን በይፋ ጀምረውታል !

ኢትዮጵያና ኤርትራ ከሠላም ስምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባለላቸውን የመነቃቀፍ መንገድ በይፋ ጀምረውታል ።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሰሞኑን በራሳቸው ሚዲያ በኩል በአንደበታቸው ስለኢትዮጵያ እና በቀጠናው ስላሉ አለመስማማቶች በተለይም ግብፅና ሱማሊያ ላይ ትኩረት አድርገው የተናገሩት ኢትዮጵያን የመቃወም እንዲሁም በውስጥ ጉዳዮቿ ለምሳሌ ያህል ህገመንግስቷን አንስተው የሰነዘሩትን የትችት ንግግር  የኢትዮጵያን መንግስት በእጅጉ ያሳቀ እና ያስገረመ ጉዳይ መሆኑን በመንግስት ሚዲያ በሆነው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የቴሌቪዥን መስኮት የተላለፈው ትንታኔ በግልፅ ሲናገር ተመልክተነዋል ።

በርግጥ የሁለቱም መንግስታት አለመግባባት ከተጀመረ ውሎ ቢያድርም  ሁለቱም በይፋ ይህን ነገር ባለማሳወቃቸው ምክንያት በሠላም እና በፍቅር መኖር የሚፈልገውን የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ግራ ሲያጋባ የቆየ ጉዳይ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ።

በተለይም ኤርትራ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳይ ስታነሳው የነበረው ክስ እና የስልክ ግንኙነትን እስከማቋረጥ እንዲሁም በረራዎች እንዲቋረጡ ያደረጋትን ሁኔታ የሁለቱም ሀገራት መንግስታት የሚያውቁበት ሌላ የተለየ ምክንያት እንዳለ ብንጠረጥርም በተለይም ኢትዮጵያ አሁን ላይ አለመግባባቶች ውስጥ ከገባችባቸው ሱማሊያ እና ግብፅ ጋር የኤርትራው መንግስት ያላቸው የጠበቀ ግንኙነት ከማስታረቅና ከማስማማት በተቃራኒው መሆኑ ጉዳዮን የእውነት መቃቃር እንዳላቸው በግልፅ የሚያሳይ ጉዳይ ሆኖ አይተነዋል ።

ሰሞኑን የኤርትራው መንግስት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የሰጡትን አስተያየት መሠረት በማድረግ "የራሷ እያረረባት " በሚል የስላቅ ቃላት በፋና ብሮድካስት የተሰጠው ትንታኔ ሁለቱም የቃላት ጦርነቱን በይፋ ስለመጀመራቸው ማረጋገጫ ሆኖ አጊንተነዋል።

ሁለቱም በመገናኛ ብዙሃኖቻቸው የሰጡት አንዱን በአንዱ የማጣጣል እና የማንቋሸሽ ንግግር ሁለቱም ከመስማማት እና ህዝቡን አንድ ከማድረግ ይልቅ የራሳቸውን መንገድ የመረጡበት ሁኔታ እና ከዚህም በላይ ሊባባስ እንደሚችል ይታመናል።

በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግስት በግልፅ በራሱ አንደበት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቀጠናውና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች በሰጧቸው ሀሳቦች ላይ መልስ ምት ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን።

Читать полностью…

EthioTube

ሱሌማን አብደላ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱ ተዘገበ

በሳዑዲዓረቢያ መቀመጫዉን በማድረግ በማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎችን በማቅረብ የሚታወቀዉ ሱሌማን አብደላ ለበርካታ ጊዜያት በሀገሪቱ መንግስት በቁጥጥር ስር ዉሎ በእስር ላይ ይገኝ ነበር።

ሱሌማን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለይም በአረብኛ ቋንቋ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን አቋም ሲያንጸባርቅ የነበረ ሲሆን በሳዑዲዓረቢያ መንግስት ተይዞ እስር ላይ ቆይቷል።

ሱሌማን ከትናንት በስቲያ ለኢትዮጵያ መንግስት መሰጠቱን መሠረት ሚዲያ ዘግቧል። ሱሌማን በኢትዮጵያ ምን እንደሚጠብቀዉ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። እስካሁንም የኢትዮጵያ መንግስት ሱሌማን አብደላን መረከቡን አላሳወቀም።

Via መሠረት ሚዲያ

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ምሽት 4:41 ላይ ከመተሐራ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አመልክቷል።

መሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ መሆኑን አመልክቷል።

ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ "ህመማቸው እንደባሰባቸው" ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ለከፍተኛ ሕመም" መዳረጋቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ።

አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ "የማያቋርጥ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው" ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ቤተሰባቸው ነግረውኛል ሲል ቢቢሲ በዘገባው ጠቁሟል።

አንድ የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ "ቁስሉም አልደረቀም እና ደግሞ ደም እየፈሰሳቸው ነው፤ ሐኪሞቹም ተናግረዋል፤ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም እንደሚችል እና ይህ ሲያጋጥምም እንድታመጧቸው ብለው ነበር" ብለዋል ያለው ዘገባው ነገር ግን ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ወደ ሆስፒታል አለመወሰዳቸውን ነግረውኛል ብሏል።

ሕክምናውን ተከትሎ ለሚከሰተው የደም መፍሰስ ማስታገሻ እንደተሰጣቸው ያስታወሱት የቤተሰብ አባላቱ "ሕመሙን ለማስታገስ ቶሎ ቶሎ እየወሰዱት ስለነበር የተሰጣቸው የማስታገሻ መድኃኒትም አልቆባቸዋል። " ሲሉ ተናግረዋል ።

የአቶ ዮሐንስ ቤተሰብ አባል፤ "ትላንት ማስታገሻ ይዘን ስንሄድ መግባት አትችሉም ተባልን፤ ለምንድን ነው ስንል? ሊቀየሩ ነው አሉን። እስከ ትናንት ግን እነሱ አይሄዱም ብለውን ነበር። ትናንት በድንገት ተነስተው ሊወጡ ስለሆነ ምንም ምግብ ማስገባት አትችሉም መድኃኒትም አይገባም ብለው ከለከሉን" ማለታቸውንም ዘገባው አካቷል።

የአቶ ክርስቲያንም የቤተሰብ አባል በተመሳሳይ "ትላንትና ምግብም ማስታገሻም ይዘን ስንሄድ የሚያስገባን ስለሌለ ተመለስን" ሲሉ መናገራቸውን አስታውቋል።

Читать полностью…

EthioTube

ማንችስተር ሲቲ ከአስቶን ቪላ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ጆን ዱራን እና ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶንቪላ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል ፤ ፎደን የማንችስተር ሲቲን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።

የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ማንችስተር ሲቲ ካደረጋቸው የመጨረሻ አስራ ሁለት ጨዋታዎች በአስራ አንዱ ቢያንስ ሁለት ግቦች አስተናግዷል።

ማንችስተር ሲቲ ካለፉት አስራ ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጨዋታ ነው ዘጠኙን በሽንፈት አጠናቋል።

Читать полностью…

EthioTube

በኢነርጂ ፍጆታ እና በልዩ ልዩ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ

ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ በሚጠቀሙ ደንበኞች የፍጆታ ሂሳብ ላይ እና አዲስ ደንበኛ ማገናኘትን ጨምሮ ደንበኞች በሚፈፅሟቸው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ የ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ  መደረጉን በላከልን መግለጫ ተናግሯል፡፡

በዚህ መሠረት ደንበኞች ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ በሚከፍሉበት ወቅት የፍጆታ መጠናቸው ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ ከሆነ እላፊ የመጣው የፍጆታ መጠን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተሰልቶ ሂሳባቸው ላይ የሚደመር ይሆናል ብሏል፡፡

ተቋሙ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ ያደረገው ከህዳር ወር የክፍያ የደረሰኝ ጀምሮ ሲሆን፤ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለባቸውን የኋላ ክፍያ በታህሳስ ወር በሚወጣው ቢል ላይ ተጨምሮ የሚከፍሉ ይሆናል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኖችም ከመስከረም ወር ጀምሮ ባላቸው የፍጆታ መጠን መሠረት የኋላ ክፍያ በቀጣይ ይከፍላሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ደንበኞች ለተቋማችን በሚከፍሉት ልዩ ልዩ ክፍያዎች ላይም ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( ኢቢሲ )ን የቴሌቭዥን አገልግሎት ክፍያ በወርሃዊ በደንበኞች የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ላይ በመጨመር እንዲከፍሉ ሲያደርግ መቆየቱን ተቋሙ አስታውሷል፡፡

በመሆኑም ወርሀዊ የኤሌክትሪክ የፍጆታ መጠናቸው ከ50 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ የሆኑ ደንበኞች 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ጋር የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ እየከፈሉ ይገኛሉ ሲል በመግለጫው አካቷል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት   ቭላድሚር ፑቲን  ተመራጩን የአሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምን ለማግኘት ዝግጁ ነኝ ብለዋል፡፡

ከትራምፕ ጋር የምገናኝበትን ጊዜ  ባላዉቀዉም ግን በፈለገበት ጊዜ ለመነጋገር ተዘጋጅቻለሁ ነዉ ያሉት፡፡

ትራምፕ የት እንድንገኛኝ  እንደሚፈልግ  አልነገረኝም ያሉት ፑቲን እኔ ግን የትም ይመቸኛል ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡

ላለፉት አራት አመታት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር አዉርተዉ እንደማያዉቁም ፑቲን አንስተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን   የ2024  አመት  ከመጠናቀቁ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር  የመጨረሻዉን ቃለ ምልልስ ማድረጋቸዉን ታስ ዘግቧል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ  በዩክሬኑ ጦርነት ዙሪያ ለመምከር ከፑቲን ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉ መናገራቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

ይሁን እንጂ ለበዓለ ሲመታቸዉ የቻይናዉን ፕሬዝዳንት ሲጋብዙ  ፑቲንን አልጠሯቸዉም፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ49 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ የኮንጎ አየር መንገድን ስራ ማስጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በጋራ በመሆን “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ በይፋ ስራ ማስጀመሩን አስታወቀ።በይፋ ስራውን በጀመረው የኮንጎ አየር መንገድ የሀገሪቱ መንግስት 51 በመቶ የሚሆነውን አብላጫውን ድርሻ መያዙ የተገለጸ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ 49 በመቶ ድርሻ በመያዝ አየር መንገዱን እንደሚያስተዳድር ተጠቁሟል።

ኤር ኮንጎ በሁለት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ሰባት ኤርፖርቶች በረራ በማድረግ አገልግሎት መጀመሩን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮንጐ ዜጎችን በአብራሪነት፣ በበረራ ሰራተኝነት፣ በሽያጭና አገልግሎት ሰራተኞች እና በቴክኒሻንነት አሰልጥኖ ለማብቃት በስምምነቱ ላይ መካተቱን መረጃው አመላክቷል።

ይህ ጥምረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራዕይ 2035 አንዱ አካል መሆኑን የጠቆመው መረጃው ከዚህም በፊት በሎሜ አስካይ አየር መንገድ፣ በሊሎንግዌ የማላዊ አየር መንገድ እንዲሁም በሉሳካ የዛምቢያ አየር መንገድን በጋራ ማቋቋሙን አስታውሷል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በሁሉም ክልሎች ዋና ዋና ከተሞች የሰላም ኮንፍረንስ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

''ኃይማኖት ለሰላም ለአንድነትና ለመከባበር'' በሚል መሪ ሃሳብ አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ እንደሚያካሂድ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔው ገልጿል።

ኮንፍረንሱ በሁሉም ክልል ዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ ስቴዲየሞች እንደሚካሄድም ጠቁሟል፡፡

ይህን ተከትሎ የመጀመሪያው የሰላም ኮንፍረንስ በድሬዳዋ ከተማ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ታኅሳሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አመላክቷል።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ አካላት የሰላም ጥሪውን እንዲቀበሉ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑንም ገልጿል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ያወደሰው ተቋሙ ስምምነቱን ለማጽናትና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ አካላት የሰላም ጥሪውን እንዲቀበሉ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑንም አስታውቋል።

በተጨማሪም መላው የአገሪቱ ሕዝብ ለሰላም ያለውን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይበት፣ አብሮነቱን የሚያጠናክርበትና ለሰላም ግንባታ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ የሚያጎላበትን መድረክ ለማመቻቸት እየሰራ ስለመሆኑም ገልጿል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በሞስኮ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሩሲያ የኒውክሌር ኃይል አዛዥ ተገደሉ

ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ አንድ አፓርትመንት ሕንፃ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፤ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ከረዳታቸው ጋር መገደላቸው ተገልጿል፡፡

ኢጎር እና ረዳታቸው የተገደሉት ከክሬምሊን በስተደቡብ ምስራቅ 7 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው የመኖሪያ አፓርትመንታቸው ውጭ በደረሰ ፍንዳታ ነው ተብሏል።

ጄነራሉ የተገደሉት በመኖሪያ ቤታቸው መግቢያ ላይ በኤሌክትሪክ ስኩተር ላይ በተጠመደና ቤት ውስጥ የተሰራ ቦንብ መሆኑን በሩሲያ መንግሥት የሚተዳደረው ታስ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር፤ በኮስትሮማ ከፍተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የኬሚካል መከላከያ ትምህርት ቤት ወታደራዊ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ ከፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር 2017 ጀምሮ የጦር ኃይሉን እንዲመሩ ተሹመዋል።

ጄኔራሉ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ጨምሮ ከአደገኛ ፈንጂዎች ጋር በተዛመደ በሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ውስጥ በተለያዩ ሚናዎች አገልግለዋል። በትላንትናው ዕለት የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ዩክሬን ውስጥ የተከለከለ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ሲል ጄኔራል ኢጎርን ከሶ ነበር፡፡የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት በኪሪሎቭ መሪነት ሩሲያ 5 ሺሕ ያህል የኬሚካላዊ መሳሪያዎችን ተጠቅማለች ሲል ተናግሯል።

ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር "በዩክሬን በሩሲያ ጦርነት ላይ አውዳሚ ኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ተጠቅመዋል" በሚል በብሪታኒያ፣ ካናዳ እንዲሁም በሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ማዕቀብ ተጥሎባቸው ቆይቷል።

Читать полностью…

EthioTube

በመቐለ ከተማ ከንቲባነት ዙርያ ያለው ውዝግብ ወደ ግጭት እንዳያመራ ስጋት መኖሩ ተሰማ

በአሁኑ ሰዓት የመቐለ ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት በፀጥታ ሀይሎች እየተጠበቀ ስለመሆኑ ከአከባቢው የደረሱ መረጃዎች ያሳያሉ።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከዚህ ቀደም የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ ይትባረክ አምሃን ከሀላፊነት በማንሳት አቶ ብርሀነ ገብረየሱስ ከሾመ ሁለት ሳምንት ገደማ ተቆጥሯል።

ታድያ አዲሱ ተሿሚ አቶ ብርሀነ በዛሬው ዕለት ስራቸውን ይጀምራሉ ተብሎ የነበረ ቢሆንም ዘገባው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ግን ከንቲባው ስራቸውን ስለመጀመራቸው የተባለ ነገር የለም።

በአንፃሩ አዲሱ ተሿሚ ወደ ስራ እንዳይገቡ የከተማ አስተዳደሩ ፅህፈት ቤት በፀጥታ ሀይሎች ጥበቃ እየተደረገለት ስለመሆኑ ሰምቷል።

በዚህም ነገሮች ተባብሰው ወደ ግጭት እንዳያመሩ ስጋት መጣሉን ነው ከመረጃ ምንጮች ለመረዳት የተቻለው ።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የማንችስተር ዩናይትድ አዲሱ አሰልጣኝ ሩብን አሞሪም የመጀመሪያቸውን የማንችስተር ደርቢ በሲቲ ሜዳ በድል አጠናቀዋል።

የሊቨርፑል፥ የቸልሲ እና አርሰናል ደጋፊዎች የዩናይትድን ድል እንዴት አገኛችሁት? 🙂

#PremierLeague #ManchesterCity #ManchesterUnited

Читать полностью…

EthioTube

በተከለከለ አየር ክልል በረራ አድርገዋል የተባሉ የኢትዮጵያንና የ ኢትሃድ አየር መንገዶችን በአሜሪካ መቀጣታቸው ተሰምቷል።

የአሜሪካ የትራንስፖርት ክፍል የኢትዮጵያ አየር መንገድን 425,000 ዶላር እና የኢትሃድ አየር መንገድን 400,000 ዶላር  መቅጣቱ ተገለጸ። 

አየር መንገዶቹ የተቀጡት ያለፍቃድ በተቀከለከለ አየር ክልል በረራ ማከናወናቸው በደንበኞች ጥበቃ አቪየሽን ቢሮ ምርመራ መደረጉን ተከትሎ ነው ተብሏል።

ምርመራው እንዳመለከተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጎርጎሮሳውያኑ 2020 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ እና በጂቡቲ መካከል የተባበሩት አየር መንገድ መለያ ኮዶችን የያዙ በረራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

አየር መንገዱ ከሀምሌ 2022 እስከ ሚያዚያ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ጄትብሉ አየር መንገድን (B6) ኮድን በመጠቀም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና አሜሪካ መካከል በረራዎችን አካሄዷል ሲል የአቪየሽን ድረገጾች ዘግበዋል።

የአሜሪካ የትራንስፖርት ክፍል እነዚህ በረራዎች በአሜሪካ ደንቦች መሠረት ተገቢ ፈቃድ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸ ሲሆን ምርመራው አየር መንገዶቹ ቀደም ብሎ ማሳወቂያ ቢሰጣቸውም በራራዎቹ መቀጠላቸውን ከአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ተመልክተናል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የሰጥቶ መቀበል ድርድር ማድረጋቸውን ቱርክ ገለጸች።

(ምንጭ፡ ኢፕድ)

Читать полностью…

EthioTube

የሱሉልታ ወረዳ ፖሊስ አዛዥና የፀጥታ አካላት የተገደሉበት ጥቃት

እጃችንን ለመንግሥት መስጠት እንፈልጋለን ያሉ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት መሆናቸውን የገለጹ ታጣቂዎች ትናንት ሱሉልታ ወረዳ ጫንጮ ከተማ አቅራቢያ ሊቀበሏቸው በሄዱ ባለሥልጣናት ላይ በከፈቱት ተኩስ የወረዳውን ፖሊስ አዛዥና የፀጥታ አካላትን መግደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና የዓይን ምስክሮች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

በወቅቱ በተከፈተው የተኩስ እርምታ ከተገደሉት በተጨማሪ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊና ታጣቂዎቹን ለመቀበል በስፍራው የተገኙ ሌሎች ሰዎችም መቁሰላቸውን የዓይን ምስክሮቹ ተናግረዋል።

ስለ ጥቃቱ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ የሰጠው ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ የለም።

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ፣ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ደረስኩበት ባለው ስምምነት የተቀበላቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ላይ መሆናቸውን አስታውቋል።

ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባና  በሌሎች ከተሞች ወደ ተሃድሶ ማዕካላት የሚያመሩ በተባሉ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች የተከፈተ የተኩስ እሩምታ ድንጋጤ መፍጠሩን የየከተማዎቹ ነዋሪዎች ተናግረው ነበር።


ምንጭ፦ DW

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 በላይ የአካባቢው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፀጥታ አባላት በፋኖ ሀይሎች መገደላቸው ተሰማ ።

በዞኑ ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ኅዳር 26/2017 ዓ.ም. ለሁለት ወራት ለመንግሥት "መረጃ እና ድጋፍ ሰጪ" በሚል ተጠርጥረው በፋኖ ሀይሎች ተይዘው የነበሩ በርካታ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት "መረሸናቸው" ታውቋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ የአካባቢው ነዋሪዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዋለ አለማየሁ 20 ከሚሆኑ የወረዳው ካቢኔዎቻቸው ጋር የግድያው ሰለባ መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።

መስከረም መጨረሻ በአካባቢው "ከባድ ውጊያ" መደረጉን ተከትሎ መስከረም 29/2017 ዓ.ም. ወረዳው በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መግባቱን እና የመንግሥት ኃይሎች ወረዳውን ለቀው መውጣታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ይህንንም ተከትሎ "[መከላከያ] የሚሊሻ፣ የፖሊስ አባላትን እንዲሁም ካቢኔዎችን በሙሉ መስመር ላይ ነው ጥሏቸው የሄደው" ሲሉ አንድ ነዋሪ፤ 'ባልተለመደ ሁኔታ' የወረዳው አስተዳደር ከተማዋ ውስጥ መቅረቱን ገልጸዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ዓለም 20 የሚሆኑ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች መከላከያ ሠራዊት "ለስምሪት" አካባቢውን ለቆ ሲወጣ "ተቆርጠው" መቅረታቸውን ተናግረዋል።

በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩት የአካባቢ አመራሮች "ፈረስ ቤት ሚካኤል" በተባለ የከተማው መውጫ ላይ ተወስደው መረሸናቸውን ሦስት ነዋሪዎች እና የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

Via BBC Amharic

Читать полностью…

EthioTube

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

👉 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጓል።

" ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ማድረጉን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት / የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አሳውቋል።

በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ይሰራል ተብሏል።

በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ተጠቁሟል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት ብቻ እንደነበር ይታወሳል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel