ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

የህወሓት ቡድኖች እና የአስተዳደር አካላት የሚያስተባብሯቸው ሰልፎች በትግራይ እየተካሔዱ ነው
የትግራይ ክልል ከተሞች የህወሓት ሁለት ቡድኖች እና የአስተዳደር አካላት የሚያስተባብሯቸውን የድጋፍ እና የተቃውሞ ሰልፎች እያስተናገዱ ነው። በውቅሮ በነበረ ሰልፍ ላይ በተነሳ ግጭት ቁጥራቸው ያልታወቀ ወጣቶች መጎዳታቸው ተነግሯል። ለሁለት ዓመታት ከተካሔደ ኃይለኛ ጦርነት ባላገገመው ክልል የሚካሔዱት ሰልፎች ለነዋሪዎች ሌላ ሥጋት ፈጥረዋል። ዘገባው የጀርመን ድምጽ ነው።

#TPLF #Tigray #Ethiopia #GetachewReda #DebretsionGebremichael

Читать полностью…

EthioTube

የአክሱም የሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሂጃብ ክልከላን ወደ ፍርድ ቤት እንደወሰደው የትግራይ አጠቃላይ የእስልምና ጉዳዮች ምክርቤት አስታወቀ

ምክርቤቱ የቀረበው ጥያቄ አንድና አንድ መሆኑን እሱም ሴት ተማሪዎቹ ሂጃባቸውን ይለብሳሉ ትምህርታቸውን ይማራሉ የሚል እንደሆነ ገልፆል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት በአክሱም ከተማ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታይ ሴት ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የተጣለው ክልከላ ለማስነሳት ኃይማኖታዊ ብሎም አለም አቀፍ የሰው ልጆች መብት እንዲከበር በሚያስገድዱ አማራጮች ሁሉ ችግሩን ለመፍታት ተሞክሯል ብሏል።

ሆኖም ግን በክልሉ የትምህርት ቢሮ ከተሞከረው ያልተሳካ ሽምግልናና ሊያስፈፅመው ያልቻለውን የትዕዛዝ ደብዳቤ ከመፃፍ ውጭ ምንም ለውጥ ሊመጣ እንዳልቻለ ገልፆል።

የልጆቹ ጥያቄ የሁሉም እምነት ተከታይና የሌሎችን እምነት አክባሪ ትግራዋይ ጥያቄ ሆኖ ሳለ የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪዎች ከራሳቸው ሃይማኖታዊ ፍላጎት መብት በማደባለቅ ሴት ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት መዓድ እንዳይመለሱ አድርጓል ብሏል።

ጉዳዩ የከፋ የሚያደርገው ተማሪዎቹ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ መሆናቸው ነው ያለው ምክር ቤቱ በሂጃብ ምክንያት ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግባት እድላቸው እየተዘጋ ይገኛል ሲል አክሏል።

ምክር ቤቱ ትላንት አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫው ምንም አይነት ህጋዊ መሰረት በሌለበት የእስልምና እምነት ተከታይ ሴት ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታ የማገድ ተግባሩ በአፋጣኝ ካልተፈታ ጉዳዩን በህግ አግባብ እንዲታይ እናደርጋለን ባልነው መሰረት ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ወስደነዋል ብሏል።

ምክርቤቱ አክሎም ጉዳዩ የእስልምና እምነት ተከታይ ሴት ተማሪዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን በሴቶችና በሰው ልጆች የመማር መብትን የሚቃረን ነው በማለት ሁሉም ሰው በፍትሃዊው ጥያቄ ጎን እምዲቆም ጠይቋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ከጥቂት ከደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ 31 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ነው።


ዛሬ በተለያየ ሰዓት አምስት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የአሁኑ ለስድስተኛ ጊዜ የተከሰተው (በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካው ) በመጠን ከፍተኛው ነው።

ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ላይ በደንብ ተሰምቷል።

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3ኛውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ተረከበ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3ኛው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ከአዲሱ የፈረንጆቹ 2025 ዓመት ጋር በስኬት መቀበሉን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ምቹ እና ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ስራ ላይ በማዋል ለደንበኞቻችን ምርጥ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ በአቪዬሽን መስኩ በአፍሪካ ስኬታማ የሆንበትን መሪነት እና በዓለም ደርጃ ያለንን ተወዳዳሪነት አጠናክረን እናስቀጥላለን ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤር ባስ A350-1000 አውሮፕላን በፈረንሳይ ቱሉዝ ከኤርባስ ኩባንያ መረከቡ ይታወቃል፡፡

400 መቀመጫዎች ያሉት አውሮፕላኑ የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለትና Ethiopia land of origins የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

የመጀመሪያውን ተከትሎም ሁለተኛው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን (ET-BAX) በቅርቡ ተረክቧል። ይህም በአቪዬሽኑ ዘርፍ በአፍሪካ አህጉር አየር መንገዱ ያለውን የመሪነት ሚና የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ አየር መንገዱ 124 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

አትሌት በሪሁ አረጋዊ በ10 ኪሎ ሜትር አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ

በስፔን ማድሪድ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ አዲስ ክበረወሰን በማስመዝገብ ማሸነፍ ችሏል።

አትሌት በሪሁ ርቀቱን 26 ደቂቃ ከ32 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ክብረ ወሰን አሻሽሏል።

ኡጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ በአንድ ሰከንድ ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ስፔናዊው አዴል ሚካኤል ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

#Earthquake

ዛሬ ምሽትም 4:17 በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ላይ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ጠቁመዋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል።

በተለይም ደግሞ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል። ጠንከር ያለ እንደነበረም ጠቁመዋል።

ከጋርመንት፣ ጀሞ፣ አራብሳ፣ አያት ፣ ጎተራ፣ አያት 49 ፣ ጣፎ ፣ ኮዬ ... ሌሎችም አካባቢዎች በተለይ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ትግራይ ከንቲባ ጉዳይ ህዝቡን ለእንግልት እየዳረገ ነው ተባለ

''ከንቲባውን አገናኙኝ ብዬ ወደ ቢሮ ስልክ ስደውል 'የትኛውን ከንቲባ' ተብዬ እየጠየቃለሁ'' ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡

''በሕወሃት ፓርቲ መካከል በተፈጠረው ልዩነት ምክንያት ህዝቡ እየተንገላታ ነው'' ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተናግሯል፡፡በሕወሃት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ከተሞች ሁለት ከንቲባ እና አስተዳደሪ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ይህም ተገልጋዩ ለእንግልት ዳርጓል ብሏል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ፡፡

የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ እና አዲግራትን ጨምሮ በክልሉ ያሉ አንዳንድ ወረዳዎች በጊዜአዊ አስተዳደሩም እና በእነ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል(ዶ/ር) በሚመራው ህወሃትም ከንቲባ እና አስተዳዳሪ ይሾምላቸዋል ሲሉ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፀሃዬ አንባዬ አስታውሰዋል፡፡

ይህም አንዱ ለአንዱ ስለማይታዘዝ ተገልጋዩ ጉዳዩን የሚፈጽምለት አጥቶ ተቸግሮ ነው ያለው ሲሉ አቶ ጸሃዬ እንባዬ አስረድተዋል፡፡በተመሳሳይ ወረዳ እና ከፍለ ከተማ ላይ ያሉ የስራ ሃላፊዎች  አንዱ የመራውን ደብዳቤ ሌላኛው እኔ የእገሌን ትዕዛዝ አልፈጽምም ይላሉ ሲሉ አቶ ጸሃዬ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ራሱ የህዝብን አቤቱታ ለማስፈፀም መቸገሩን ነገሮናል፡፡በሕወሃት መካከል የተፈጠረው ልዩነት ከንቲባውን ፈልገን ስልክ ስንደውል እንኳን 'የትኛውን ከንቲባ' እየተባልን እየተጠየቅን ጉዳይ ለማስፈፀም ተቸግረናል ብሏል፡፡ “

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ሹመት‼️

የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ምክትል አዛዥ የነበሩት እና በቅርቡ ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የፈፀሙት አቶ ጃል ሰኚ ነጋሳ የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ ቢሮ ሐላፊ በመሆን በዛሬው መሾሙ ተዘግቧል።

Читать полностью…

EthioTube

ካናል+ ኢትዮጵያ ስርጭቱን ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን አስታወቀ።

#CanalPlus #Ethiopia

Читать полностью…

EthioTube

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እንዲሁም በአወዛጋቢው የኢትዮጵያ ምርጫ 97 ወቅት የምርጫ ታዛቢ የነበሩት ጂሚ ካርተር በ100 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

(📷: Getty Images/US Embassy)

Читать полностью…

EthioTube

21 ኩንታል ካናቢስ በመንግስት መኪና ሲያዘዋውር የነበረው ሹፌር በፅኑ እስራት ተቀጣ

21 ኩንታል ካናቢስ በመንግስት መኪና ሲያዘዋውር የነበረው ተከሳሽ ታምሩ ፍቅሬ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እና የአርባ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ መቀጣቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ተከሳሽ ታምሩ ፍቅሬ በእስራት ሊቀጣ የቻለው ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሆነው ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ ከተቋሙ ስምሪት በመውሰድ የስራ ኃላፊዎችን ከሜክሲኮ ወደ ኮዬ ፈጬ አድርሶ መመለስ ሲገባው ቀጥታ ወደ ሻሸመኔ በመጓዝ 21 ኩንታል ካናቢስ በመጫን ከሻሸመኔ በቱሉ ዲምቱ አድርጎ ዓለም ገና በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ አካባቢ በመኪናው ላይ እንዳስቀመጠው ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ግለሰቡ ሊያዝ ችሏል።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት በተከሳሹ ላይ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ከነ ኤግዚቢቱ እጅ ከፍንጅ ይዞ የምርመራ ሂደት በሚገባ ካጣራ በኋላ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመስርቶ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ ታምሩ ፍቅሬ ላይ 12 ዓመት ፅኑ እስራትና የአርባ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለዚህ መሰል የወንጀል ድርጊት እንዳይጋለጡ በተሽከርካሪዎቻቸው ላይ ጂፒኤስ በመግጠም የመኪናዎቻቸው እንቅስቃሴ መቆጣጠር እንዳለባቸውና በኬላ ጣቢያዎች ላይም ፍተሻ በሚገባ ማከናወን እንዳለባት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያሳስባል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት እንዲሰሩ ተወሰነ

በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት በመደበኛው ታሪፍ መሰረት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በመዲናዋ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ አስተዳደሩ ካቢኔ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በውሳኔው መሠረት አውቶቡሶች፣ ሚድ ባስ እና ሚኒ ባሶች መደበኛ በሚሰሩበት መስመርና ቀን ላይ በሚከፈለው ሕጋዊ ታሪፍ መሠረት እስከምሽቱ 4 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ ቢሮው አሳቧል፡፡

ስለሆነም የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ይህን በሚገባ በመረዳት እስከምሽቱ 4 ሰዓት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

የትራንስፖርት ቁጥጥር ሠራተኞች እንዲሁም የሚመለከታችሁ አካላት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተግባራዊነቱ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ሲል ጥሪ ቀርቧል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለበለጠ መረጃና ለትራንስፖርት ጉዳይ ጥቆማ ለመስጠት በነፃ የስልክ ጥሪ መስመር 9417 ላይ መደወል እንደሚቻልም ቢሮው አስታውቋል፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በግጭቱ ከ35 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

በሶማሌ ክልል ፋፋን ዞን ደአወሌይ ቀበሌ ትናንት ታህሳስ 16/ 2017 ዓ/ም "በአካባቢው አርብቶ አደሮች" እና በመንግስት ሚሊሻዎች መካከል በተቀሰቀሰ የትጥቅ ግጭት ከ35 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።

ግጭቱ ከዩአሌ ወረዳ የመጡ “ልዩ ፖሊስ እና ሚሊሻዎች” ደአወሌይ ቀበሌ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ  የተፈጠረ ነው ተብሏል።

በአካባቢው በሚኖሩ “ኢሳቅ እና የኦጋዴን ንዑስ ጎሳዎች” መካከል ለረጅም ጊዜ በቆየው የድንበር ግጭት የተነሳ ታህሳስ 10 ከተከሰው ግጭት የቀጠለ መሆኑንም ታውቋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ኢሰመጉ የአሰራር ጥሰት ፈፅሟል በሚል በመንግስት መታገዱ ተሰምቷል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን (ኢሰመጉ) ያገደው፣ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል በማለት መሆኑ ተነግሯል።

የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአመራሮቹና ሠራተኞቹ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጽሙ ለበርካታ ወራት ሲገልጽ የቆየው ኢሰመጉ፣ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚኹ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ በቅርቡ ተዘግቦ ተመልክተናል።

ባለሥልጣኑ በዲሞክራሲና መብቶች ዕድገት ማዕከል እና ጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኙት ሲቪል ማኅበራት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር በተመሳሳይ ምክንያት ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ፣ ድርጅቶች የተሰጧቸውን የማስተካከያ ርምጃዎቾ ተግባራዊ አላደረጉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ጥፋታቸውን ቀጥለውበታል በማለት በቅርቡ በድጋሚ እንዳገዳቸው ጠቅሶ ዋዜማ ዘግቧል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን በካዛክስታን ተከሰከሰ

ኤምብራየር 190 በተሰኘው አውሮፕላን ውስጥ 62 ተሳፋሪዎች እና 5 የበረራ ሰራተኞች እንደነበሩ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዘግቧል።

የመጀመሪያ ሪፖርቶች እንዳመላከቱት በህይወት ከተረፉ 25 ሰዎች መካከል 22ቱ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የካዛኪስታን የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአዘርባጃን አየር መንገድ የሚተዳደረው አውሮፕላኑ በአክታዉ ከተማ አቅራቢያ ለማረፍ ሲሞክር በእሳት የነደደ ሲሆን አሁን ላይ እሳቱን ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በብዛት ኢትዮጵያን የሚኖሩባት የካሊፎርንያ (ሎስ አንጀለስ) ግዛት ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ሰደድ እሳት ተከስቷል

ካሊፎርንያ ለእሳት አደጋ አዲስ አይደለችም። የእስካሁኑ በአብዛኛው ከከተማ ወጣ ብሎ የሚከሰት ነው። ከዚህ ቀደም ሆኖ በማያውቅ ሁኔታ ከፍተኛ የሆነውና፣ ከጫካው ይልቅ የከተማ መሰረተ ልማቶችና መኖርያ አካባቢወችን ያጠቃው የካሊፎርኒያ ሰድድ እሳት እስካሁን ከቁጥጥር ውጪ እንደሆነ ነው። ይሄው ሰደድ እሳት ደቡብ ካሊፎርኒያ፣ በተለይ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባት የሎስ አንጀለስ ከተማ አካባቢ ላይ ነው የተከሰተው።

እስካሁን ድረስ ከ105 ስኴር ኪሎሜትር (ከ11 ሺህ ሄክታር) በላይ አካባቢወች እየነደዱ ነው። እስካሁን አምስት ሰው ሞቷል፣ ከ70 ሺህ በላይ ነዋሪወች አካባቢወን ለቀው ወጥተዋል፣ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ቤቶች የኤክትሪክ ሃይል አቅርቦት አጥተዋል፣ ከ1000 በላይ ቤቶች፣ ህንጻወችና መሰረተ ልማቶችም ወድመዋል።

ይሄው ሰደድ እሳት ከፍተኛ ሃይል ባለው አውሎ ነፋስና በአካባቢው ከፍተኛ ድርቅ እየታገዘ እየተስፋፋ ነው። በዚህም ሳብያ 157 ሺህ የአካባቢው ነዋሪወች ባስቸኳይ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል። በርካታ ሰወች በታዘዙበት ወቅት ወድያው ከአካባቢው ለቀው ባለመውጣታቸው ጉዳት እየደረሰባቸው ነው። በዚህም ሳብያ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አካባቢውን ከፍተኛ የአደጋ አካባቢ በማለት አውጀው ከፌደራል መንግስት አስቸኳይ የእሳት አደጋ መከላከልና የእርዳት ድጋፍ እንዲሰጥ አዘዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ያልተጠበቀው የዛሬው የሊቨርፑል ከማንችስተር ዩናይትድ 2ለ2 የሆነ ውጤት በምስሎች።

የአርሰናል ደጋፊዎች ውጤቱን እንዴት አገኛችሁት? 😉

#PremierLeague #Liverpool #ManchesterUnited

Читать полностью…

EthioTube

"የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ችግር እልባት ያልተሰጠበት እና ወደባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው"--- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ለዘመናት የነበረባቸውን የእምነት ነፃነት፣ የመስገጃ ቦታ ችግር እና የቀብር ቦታ ችግር እልባት ያልተሰጠበት እና ወደባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው አለ።

ምክር ቤቱ ዛሬ መግለጫውን ያወጣው በከተማው የሚገኙ ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸውን አድርገው ትምህርት መከታተል እንዳልቻሉ ከሰሞኑ መሰማቱን ተከትሎ ነው።

"በዚህ ዘመን በጋራ እምነቶች ተከባብረው በሚኖሩበት አገር እሴቱን የሚሸረሽር ተግባር መፈፀሙን በፅኑ እናወግዛለን" ያለው ምክር ቤቱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መብቶች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ እንዲደረጉ እና መንግስትም ይህን እንዲያስፈፅም ጥያቄ አቅርቧል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ አዲስ የወጣ የአለባበስ መመርያም ሆነ ማስፈፀሚያ ደንብ እንዳልወጣ የጠቀሰበት ደብዳቤ ማውጣቱን ተመልክተናል።


Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች  በአድማ ብተና በፖሊስ እንዲመለሱ ተደርጓል ተባለ

በአንድ ታዳጊ ተማሪ ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰ እና ፣ በጉልበት ሂጃባቸውን ለመንጠቅም እንደተሞከረም ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል።

በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ በሂጃባቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ተማሪዎችን አስመልክቶ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ትላንት በፃፈው ደብዳቤ አዲስ የወጣ መመሪያ ባለመኖሩ ተማሪዎች በቀደመው አለባበሳቸው ይማራሉ ማለቱ ይታወሳል።

በዚህ መሰረት ተማሪዎቹ በዛሬው ዕለት ወደ ትምህርት ቤቱ ያቀኑ ቢሆንም በፀጥታ ሀይሎች እንዲበተኑ መደረጉን ሚዲያው ከስፍራው የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

የከተማው ትምህርት ቢሮ እና ከንቲባ ከክልል የተፃፈው ደብዳቤ እንደማይቀበሉት በመግለፅ  ተማሪዎቹን በፀጥታ ኋይሎች እንዲበተኑ እና ተማሪዎቹን ሒጃቦቻቸውን ለመቀማት እንደሞከሩ መረጃው ያመለክታል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በትምህርት ቢሮ የተፃፈው ደብዳቤ በሶስት ቀናት ውስጥ ተተግብሮ የሂጃብ ክልከላው በአዎንታዊ መልኩ ካልተፈታ በቀጣይ እንደ እስልምና ጉዳዮች ከህዝቡ ጋር በመመካከር የሚወሰዱ ሰላማዊ እርምጃዎች እንደሚያሳውቁ መግለፃቸውን ዘገባው አስታውሷል።

መረጃው የሀሩን ሚዲያ ነው


Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በኢትዮጵያ የወንድ የዘር ፈሳሽ ልገሳ፣  የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው።

ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት “ህዝቡ ያልተጠቀምበትን  አገልግሎት ይቆርጣል”  ሲሉ የምክር ቤቱ አባላት ተችተዋል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት  በበኩሉ  እንዚህን ችግሮች የሚያስቀሩ ሪፎርምች እየተደረጉ ናቸው፤ በቀጣይም ከደንበኞች አገልግሎት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች  እንደሚቀርፉም ገልጧል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋማት የስራ አፈጻጸምን በሚመለከት ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት  አድርጓል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት  የተደራሽነት ጥያቄን እንዲሁም የአገልግሎት አከፋፈል እና የስነምግባር ጥሰቶችንም መፍትሄ ሊበጅላቸው ይገባል ሲሉ አንስተዋል፡፡

በተለይም በድንገት ያልጠቀመንበትን የኤሌክትሪክ አገለግሎት 3 ሺ ይሁን 4 ሺ ድንገት ይቆርጣል ይህ ደግሞ ያለመዘመን ችግር ነው ሲሉ አባለቱ ወቅሰዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ችግሮች በክልል ብቻ ሳይሆን በዋና ከተማዋ አዲስ አበባም በስፋት አጋጥሞናል ሲሉ አባላቱ ተናግረዋል፡፡

ይህ ችግር ምንአለባት የቆጣሪ አንባቢዎችም ሊሆን ይችላል ወይም አገልግሎቱ  ነገር ግን አገልግሎቱ አሰራራሩን በማዘመን የህዝቡን እንግልት መሰማት ይገባዋል ብለዋለው፡፡

አባላቱ  የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነት  በሁሉመ ሃገሪቱ ተመሳሰይ  ይመስላል ያሉ ሲሆን እሱ ሊሰተካከል ይገባል ሲሉ አባለቱ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ከአባለቱ ከተነሱ ጥያቄዎች አንዱ የኤልከተሪክ ተዳራሽነትን  አገልግሎትን ለማረጋገጥ ምን ያህል በጀት አገልግሎቱ እንደሚያስፈልገው ግልጽ ማድረግ እንዳለበትም ተነስቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ሽፈራሁ ተሊላ ለቀረቡት ጥያቄዎች ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን ከደንበኞች አገልግሎት ተያይዞ ለተነሱ  ችግሮች  መሻሻል ያሉባቸውን ጉዳዮች እሰሩ እንደሚገኙም አንስተዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻማ ከዚህ  ባለፈም  በቀጣይም ከደንበኞች አገልግሎት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች  አሁን ባሉበት አይቀጥሉም ሲሉም ጠቁመዋል።

Читать полностью…

EthioTube

የማንችስተር ዩናይትድ የቁልቁለት ጉዞ እንደቀጠለ ነው።

#PremierLeague #ManchesterUnited #Newcastle

Читать полностью…

EthioTube

የሱማሌያው ኘሬዝዳን ከጂቡቲ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የኢትዮጵያን አየር ክልል ላለመጠቀም ወይም ለመሸሽ በሶማሌ ላንድ በኩል በማለፍቸው ሶማሌ ላንድ የአየር ክልሌ ተጥሷል በማለት ከሳለች

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሶማሌላንድን ሉዓላዊ የአየር ክልል ያለፈቃድ ጥሰው በመግባት ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና የሶማሊላንድን የግዛት መብቶች በመጣስ እየተካሰሱ ነው።

ፎከር 70 5Y-KBX በሚል ስም የተመዘገበ እና በኬንያ አየር መንገድ ስካይዋርድ ኤክስፕረስ የሚተዳደረው አውሮፕላኑ ከሶስት ሰአት በፊት የሶማሌላንድን የአየር ክልል አልፎ ወደ ሞቃዲሾ ሲመለስ የኢትዮጵያን ግዛት በመሸሽ ነው።

ሶማሊያላንዳዊያን<< ይህ ያልተፈቀደ ወረራ አፋጣኝ እርምጃ ይጠይቃል። አየር መንገዱ ይህንን ጥሰት በማቀላጠፍ ቅጣት ሊጣልበት ይገባል፤ ወደፊትም የሶማሊያ ባለስልጣናት የሶማሌላንድን የአየር ክልል እንዳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ መታገድ አለባቸው። የሶማሌላንድ አየር ክልል ሉዓላዊ ነው፣ እና ማንኛውም ያልተፈቀደ አጠቃቀም የራስ ገዝ ግዛቷን እና አስተዳደርን የሚነካ ነው። ብለዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

እሁድ ሌሊት ከደብረ ሲና 52 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

👉 በቅርብ ቀናት ከተከሰቱት ርዕደ መሬቶች በመጠኑ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል


ትናንት ምሽት ታህሳስ 20 ቀን 2017ዓ.ም 7:20 ላይ የተከሰተው ይህ ርዕደ መሬት 5.1 ሆኖ በሬክተር ስኬል እንደተመዘገበ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል፣ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ንዝረቱ እንደተሰማቸው እየጠቆሙ ይገኛሉ።

ይህ በቅርብ ቀናት ውስጥ በአብዛኛው አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ከተከሰቱት ርዕደ መሬቶች በመጠኑ ከፍተኛው እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ የተጠጋ ሆኖ ተመዝግቧል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

አፋር ክልል በመሬት መንቀጥቀጡ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደረሰባቸው

አፋር ክልል ጋቢ ረሱ ዞን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸው ነዋሪዎች ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ ማስገደዱ ተነግሯል።

በአዋሽ 7 ከተማ አሥተዳደር፣ በአዋሽ ፈንታሌ እና አሚባራ ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ገልጸዋል፡፡

በዚህም እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

ጉዳት በደረሰባቸውና ሌሎችም ሥጋት ባለባቸው መኖሪያ ቤቶች ያሉ ወገኖችን ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ቀለል ባለ ባህላዊ ቤት እንዲኖሩ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በሰው ላይ የተመዘገበ ጉዳት ባይኖርም በሰብል የተሸፈኑ ማሳዎች እና የመኪና መንገዶች ላይ የከፋም ባይሆን የመሰነጣጠቅ አደጋ መድረሱን ገልጸዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በኢትዮጵያ የታገዱ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ቁጥር አራት ደረሰ 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን “ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” ያላቸውን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) ከማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ አገደ። ባለስልጣኑ ባለፈው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያገዳቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ቁጥር አራት ደርሰዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሁለቱን ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያገደው፤ ከትላንት ረቡዕ ታህሳስ 16፤ 2017 ጀምሮ እንደሆነ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተመዘገቡበት ዓላማ መሰረት ስራቸውን ማከናወናቸውን የመከታተል እና የመቆጣጠር ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ ለድርጅቶቹ በትላንትናው ዕለት በላከው ደብዳቤ ለእግድ ያበቃቸውን ምክንያት ዘርዝሯል። 

ሁለቱም ድርጅቶች “ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ” እና “ኃላፊነት በጎደለው መልኩ” በመንቀሳቀስ እንዲሁም “ገለልተኛ ባለመሆን” በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ውንጀላ ቀርቦባቸዋል።

እነዚህ ውንጀላዎች ባለፈው ሳምንት በድጋሚ እንዲታገዱ በተደረጉት፤ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች (LHR) በተባሉት ድርጅቶች ላይም በምክንያትነት ተጠቅሷል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ሚና ተሰማርቶ በቆየው አትሚስ አተካክ ዙሪያ ድምጽ ለመስጠት እንደሚሰበሰብ ተገለጸ

ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ በስብሰባው ይሳተፋሉ ተብሏል

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ በሰላም ማስከበር ተግባር ተሰማርቶ በቆየው የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮን (አትሚስ) አተካክ ረቂቅ ውሳኔ ላይ ዛሬ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ተሰብስቦ ድምጽ እንደሚሰጥ ተገለጸ።

በምክር ቤቱ አሰራር ደንብ ቁጥር 37 መሰረት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በስብሰባው እንደሚሳተፉ ከጸጥታው ምክር ቤት ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮን (አትሚስ) የቆይታ ግዜ ከአራት ቀናት በኋላ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ቀጣይ በሶማሊያ ተልዕኮ ተሰጥቶት የሚሰፍረው ጦር ለ12 ወራት የሚቆይ ሲሆን ውሳኔው በአፍሪካ ህብረት የጸጥታው ምክር ቤት ጸድቆ በመንግስታቱ ድርጅት ተቀባይነት ማግኘቱ ተጠቁሟል።

ከታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በቀጣይ ተልዕኮ ተሰጥቶት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሀይል መለዮን ለብሶ በሶማሊያ የሚሰፍረው ጦር ብዛት አንድ ሺ የሚደርሱ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ በአጠቃላይ 12ሺ 626 መሆኑንም ተገልጿል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ በሶማሊያ የሰፈረው የአትሚስ ጦር አዋጪ ሀገራት “የትኛውም የድህረ አትሚስ ዝግጅት ከመወሰኑ በፊት፣ አስፈላጊ ጉዳዮችን በጥንቃቄ እና በጥልቀት መመርመር እንደሚያስፈልግ” ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወቃል።

ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚደረግ ማንኛውም ችኮላ የተሞላበት ስምምነት ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ እስካሁን የተገኙ ስኬቶችን አደጋ ላይ ይጥላል የሚል የጋራ ስጋት እንዳላቸው መግለጻቸውም ይታወሳል።

Читать полностью…

EthioTube

አዘርባጃን ብሔራዊ ሐዘን አወጀች

አዘርባጃን በትናትናው ዕለት በካዛኪስታን በተፈጠረ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ብሔራዊ ሐዘን ማወጇ ተነገረ፡፡

የአዘርባጃን 62 መንገደኞችንና አምስት ሰራተኞችን የጫነ አውሮፕላን በካዛኪስታን አክታው ከተማ አቅራቢያ መከስከሱ ይታወቃል፡፡ኢምብሬር 190 የተባለው የበረራ ቁጥር ጄ2-8243 የአዘርባጃን አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን በሩሲያ ቺቺኒያ ከባኩ ወደ ግሮዝኒ ሲበር እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ሆኖም በግሮዝኒ ጭጋግ ምክንያት ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲዞር የተደረገ ሲሆን፥ ቢያንስ በህይዎት የተረፉ ቢኖሩም ብዙዎችን ለህልፈት የዳረገ አደጋ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡በዚህም አዘርባጃን የሐዘን ቀን ማወጇን የዘገበው ዥኑዋ ነው፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትናትናው ዕለት ለ5 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ካሳለፈው ጊዜያዊ እግድ ጋር አይጋጭም ወይ የሚል ጥያቄን አስነስቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሚ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በዕግዱ ላይ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረውም ያትታል፡፡

የዕግዱ ምክንያትም ከጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረው "የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ" በመሻሻል ላይ በመሆኑ እንደሆነ ያነሳል፡፡የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ፤ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገቱን የሰጠው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ''ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመደንገግ በወጣው'' አዋጅ ቁጥር 1294/2015 መሠረት መሆኑን ይገልጻል፡፡

ኢቢሲ ጉዳዩን ለማጣራት አደረኩት ባለው ጥረት ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ በመሆኑ ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት ዕድገቱን የመስጠት መብት እንዳለው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምላሽ አግኝቷል፡፡
በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ:-
1. ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማሪያም…….  በስፔሻል ኒድስ ኤጁኬሽን
2. ዶ/ር አስራት ወርቁ ……………. በጂኦቴክኒክስ ኢንጂነሪንግ
3. ዶ/ር መኮንን እሸቴ ……………. በፕላስቲክ ሰርጀሪ
4. ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ ……………… በፐብሊክ ሄልዝ
5. ዶ/ር ተባረክ ልካ ………………. በዴቨሎፕመንት ጂኦግራፊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሠጥቷል።

Читать полностью…

EthioTube

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፈረንጆችን የገና በዓል ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመላው ዓለም የፈረንጆችን የገና በዓል ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓሉን ለሚያከብሩ በሙሉ፣ ለኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ወዳጆች፣ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ እና የዓለም ቤተሰብ መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብለዋል።

በዓሉ የደስታ፣ የሰላም እና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…
Subscribe to a channel