በመዲናዋ የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ
በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜ መስከረም 26/2016 የሚከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።
በዓሉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የገለጸው ፖሊስ፤ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙም አሳስቧል፡፡
በዚህም መሰረት ከአርብ መስከረም 25/2016 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ፦
• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ
• ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ
• ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
• ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
• ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ
• በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ
• ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ
• ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ አትላስ ሆቴል አካባቢ
• ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
• ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ
• ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ
• ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ ያሉት መንገዶች፤ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እንዲሁም 011-1-26- 43-59፣ 011- 5- 52- 63-02/03 ፣ 011-542-40-77፣ 011-5-54-36-81 የስልክ መስመሮች መጠቀም እንደሚችልም ፖሊስ አስታውቋል።
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች አስመረቀ
በኢፌዴሪ አየር ኃይል አካዳሚ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ላለፉት ስድስት ወራት መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ምልምል ወታደሮችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ ሌሎች የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመርኃ ግብሩ በ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዓመት በበረራና ቴክኒሻን የሙያ ዘርፎች ትምህርትና ሥልጠናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ ሠልጣኞች የትከሻ ምልክት (ፍላግ) የማልበስ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
ጃማይካ ውስጥ ከሃሺሽ የተሠራ ከረሜላ የበሉ ከ60 በላይ ተማሪዎች ሆስፒታል ገቡ
ጃማይካ ውስጥ ሃሺሽ (ካናቢስ) ያለበት ከረሜላ የበሉ ከ60 በላይ ልጆች ሆስፒታል መግባታቸውን የአገሪቱ የትምህርት ሚኒስትር አስታወቁ።
ሚኒስትሯ ፋይፋል ዊሊያምስ በኤክስ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ (ትዊተር) ላይ እንዳሰፈሩት፣ ልጆቹ ከጃማይካ ዋና ከተማ ኪንግስተን 80 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ናቸው።
ልጆቹ ከረሜላውን ከበሉ በኋላ ማስታወክ እና መቃዠት አጋጥሟቸው እንደነበር ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
ነገር ግን ከተማሪዎቹ መካከል አንዳቸውም ከባድ የጤና ችግር አልተከሰተባቸውም ነው የተባለው።
“ሐኪሞች እና ዶክተሮች ተማሪዎቹ እንዲሻላቸው የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው” ሲሉ የገለፁት ሚኒስትሯ አብዛኞቹ ተማሪዎች በሐኪም ቤት ውስጥ በደም ስር የሚሰጥ ጉሉኮስ እንደተደረገላቸው አስፍረዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
" እስካሁን ውጤት አልተገለፀም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እስካሁን አልተገለፀም ሲል አሳውቋል።
ተፈታኞችና መላው የትምህርት ማህበረሰብ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።
ከሁለት ሳምንት በፊት በፀጥታና ሌሎች ምክንያቶች ፈተና ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ፈተናቸውን መውሰዳቸው ይታወቃል።
የነዚህ ተማሪዎችን ፈተና ውጤት በሐምሌ 2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች ጋር አብሮ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ቀደም " እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል " የአገልግሎቱ ከፍተኛ ኃላፊ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ ከምሽት አንስቶ ለሶስት ቀናት በክልል ደረጃ የሀዘን ቀን ሆኖ ይውላል
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደር በምክትል ፕሬዜዳንት ማዕረግ የፀጥታ እና ደህንነት ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ከጥቅምት 2 ጀምሮ የሀዘን ቀን እንደሚታወጅ ይፋ አድርገዋል።
" 3 የብሄራዊ ሀዘን ቀን ይኖሩናል " ያሉት ጄነራል ታደሰ ይህ ሁሉንም ትግራዋይ የሚመለከት ሀዘን ነው ብለዋል።
" ሁሉም ትግራዋይ በትግራይ ውስጥ ሆነ በመላው ኢትዮጵያ ፤ እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኘው ለሰማዕታት ክብር የሚሰጥበት የሃዘን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ጄነራል ታደሰ የሃዘን ቀኑ ጥቅምት 2 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ ከምሽት ጀምሮ ይከናወናል ብለዋል።
ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የሃዘን ቀን የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ፣ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ሰማዕታትን የተመለከቱ መልእክቶች እንደማያስተላልፉ ተነግሯል።
የክልሉ ጊዜያዊ አስተደር ይህን የሀዘን ሂደት የሚያውክ ማንኛውም ነገር የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ ነው ሲል አስጠንቅቋል።
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
ላሊበላ ከተማ አቅራቢያ በመከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መካሄዱ ተሰማ
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ አቅራቢያ ትናንት እሁድ መስከረም 20/2016 በመከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ሲካሄድ መዋሉን የአይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
ከላሊበላ ከተማ 32 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ብልብላ ጊዮርጊስ አካባቢ ከትናንት ጠዋት ጀምሮ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ እንደነበረ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በዚህም የከባድ መሳሪያው ድምጽ በፈጠረው አለመረጋጋት በላሊበላ ሱቆችና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
በጦርነቱ ወቅት የታሰሩ ወታደሮች የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለፀ
በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በተካሄደው ጦርነት በኹለቱም ወገኖች የታሰሩት ተዋጊዎች የት እንዳሉ እስካሁን እንደማይታወቅ ተገለጸ።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የሕግ አማካሪ ፍስሃ ተክሌ፤ በእስር ላይ የሚገኙ የፌደራል መንግሥቱ እና የሕወሓት ወታደሮች እንዲሁም በየአካባቢው በጦርነቱ ተሳትፋችዋል ተብለው ያለክስ የታሰሩ የሚሊሻ አባላት የት እንዳሉ አይታወቅም ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
በሁለቱ ኃይሎች መካከል በተደረገው ጦርነት የት እንዳሉ ከማይታወቁት ከታሰሩት ተዋጊዎች በተጨማሪ እስካሁን ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱም በፌደራል መንግሥቱም ይሁን በሕወሓት በኩል ይፋ የተደረገ ቁጥር የለም ተብሏል፡፡
በፌደራል መንግሥቱና በሕወሓት መካከል በነበረው የሰላም ድርድር የአፍሪካ ህብረት የሰላም ድርድር ዋነኛ መሪ የነበሩት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ፤ በሰሜኑ ጦርነት ከ600 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጄንሲ ባለፈው ህዳር ወር ባወጣው ዘገባ፤ ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ከ70 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ ወደ ሱዳን ተሰደዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
#FootballTransfers:
ጁድ ቤሊንግሃም ወደ ማድሪድ። የ19 አመቱ እንግሊዛዊ ከጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ወደ ሪያል ማድሪድ የተዛወረ ሲሆን፥ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ሽያጭ የተካሄደበት ቁጥር አንድ እንግሊዛዊ ተጫዋች ሆኗል።
#judebellingham #RealMadrid #dortmund
የሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን ለመፍታት የአራት ሀገር መሪዎች ከካርቱም ተቀናቃኞች ጋር እንደሚወያዩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) አስታውቋል።
ኢጋድ የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ደቡብ ሱዳንን መሪዎች ያካተተ የአራትዮሽ ስብስብ ከጀነራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃንና ከጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ጋር ይወያያሉ ብሏል።
መሪዎቹ በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ በአካል እንዲወያዩ መወሰኑንም አስታውቋል።
በ14ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ አባል ሀገራት ቀጣናዊ ተቋሙ በምስራቅ አፍሪካ እየሰጠ ያለውን ምላሽ ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
ዝዋይ (ባቱ) በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በ"ሸኔ" ታጣቂዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ (ዝዋይ) ከተማ እሁድ ሰኔ 4/2015 ዕለት ከሌሊቱ አምስት ሰዓት አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራውና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ ተብሎ በአሸባሪነት በተፈረጀው ታጣቂ ቡድን መካከል በተደረገ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልኛል ስትል አዲስ ማለዳ ዘግባለች።
ከሟቾቹ መካከል አንዲት ሴትን ጨምሮ ሦስቱ የመንግሥት የጸጥታ አካላት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አንዱ ደግሞ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባል ነው ተብሏል።
የተገደለው የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባል እግሩን ተመትቶ መሸሽ ባለመቻሉ፤ የታጣቂ ቡድኑ አባላት መረጃ እንዳያወጣ በማለት ገድለውት እንደሸሹ ተጠቁሟል።
ለተከታታይ ሁለት ሰዓታት በላይ ሲደረግ ነበር የተባለው የተኩስ ልውውጥ፤ ዓላማው እስረኛ ለማስፈታት እንደሆነ ተገልጿል።
እስር ቤቱ በተለምዶ ሀይቅ ዳር ወይም የቀድሞ ጤና ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደሚገኝ እና ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደምም በእስር ቤቱ የታሰረባቸውን አባል ለማስፈታት ጥረት ሲያደረጉ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎቹ አውስተዋል።
የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ቡልቡላ እና ቱሉ መካከል በተለምዶ ኦኢቱ በምትባል ስፍራ መሽገው እንደሚገኙ የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ እስረኞቻቸውን ለማስፈታትም የዝዋይን ሀይቅ በጀልባ እየቀዘፉ መጥተው ጀልባቸውን ጦጣ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ እንዳቆሙ አብራርተዋል፡፡
አክለውም፤ እሁድ ሌሊት በተካሄድው የተኩስ ልውውጥ የታሰሩ የታጣቂ ቡድኑን አባላት ለማስፈታት የተደረገው መኩራ አለመሳካቱን በመጥቀስ፤ "የታጣቂ ቡድኑ አባላት አሉ ወደተባለበት ኦኢቱ አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ አካላት በተደጋጋሚ ቢያቀኑም በሕይወት ተርፈው የሚመለሱት ጥቂቶች ናቸው።" ሲሉም መደመጣቸውን አዲስ ማለዳ ዘግባለች።።
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ
ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ፡፡
ሌተናል ጄነራል ይልማ የቀድሞ የአየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄን በመተካት ነው የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢነት የተሾሙት፡፡
ሌተናል ጄነራል ይልማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡
ግርማ ዋቄ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
ማንችስተር ሲቲ የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ።
- Premier League ✅️
- FA Cup ✅️
- Champions League ✅️
ትሬብል ተፈፀመ።
#UCLFinal
#ሰበር፡
ለሜቻ ግርማ - የ3000 ሜ. መሰናክል የአለም ክብረ ወሰን ለኢትዮጵያ!
WORLD RECORD
🇪🇹's Lamecha Girma clocks 7:52.11 and breaks the 3000m steeplechase world record* 🔥
#DiamondLeague #Ethiopia
*Subject to the usual ratification procedures
ዛሬ አንዋር መስጊድ ጁመዓ በሰላም ተጠናቋል።
ነገር ግን መርካቶ የንግድ ሱቆች የባለፈው አይነት ችግር ይከሰታል በሚል ፍራቻ በርካታ ሱቆች ተዘግተው ተስተውለዋል። በስፍራው ምንም የሚያሰጋ የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ምንጮች አድርሰውናል።
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
“ህዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን በማጠናከርና በዱዓ በመበርታት መደበኛ የጁምዓ ሰላቱን ብቻ እንዲያከናውን ጥሪ እናቀርባለን።”-ኡስታዝ አቡበክር አህመድ
በሁሉም መሳጂዶች ከቁኑት ዱዓ ውጪ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊ ባለመሆናቸው ህዝበ ሙስሊሙ የተለመደ ታዣዥነቱን በማሳየት የጁምዓ ሰላቱን ሰግዶ ብቻ መመለስ እንዳለበት ኡስታዝ አቡበክር አህመድ አሳስበዋል።
ኡስታዝ አቡበክር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አመራሮች ሼይኽ ሁሴን ጨምሮ የፕሬዝዳንቱ አማካሪዎች ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ፣ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እንዲሁም ከኦሮሚያ መጅሊስ ሼይኽ ሚስባ እና ሌሎች አመራሮች ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚኬኤል ጋር በትናንትናው ዕለት ውጤታማ ውይይት መካሄዱን ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ የፈደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እና ከፍተኛ የፀጥታ ሐይሉ አመራሮች መካፈላቸውን አስታውቀዋል። በውይይቱ ላይ በሸገር ከተማ የፈረሱ መስጂዶችን ተከትሎ በኹለት ጁምዓዎች በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተወሰዱት ኢ ሰብዓዊ እና ከልክ ያለፉ የኃይል እርምጃዎች ተቀባይነት የሌላቸው እና ህዝበ ሙስሊሙን እጅግ ያሳዘነ መሆኑም ተገልጿል።
አገር ወዳድ እና ሰላማዊ ለሆነው ህዝበ ሙስሊም ህጋዊ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ በማቅረቡ በምላሹ በፀጥታ ኃይሉ የተወሰደው የኃይል እርምጃ በምንም መመዘኛ የሚገባው እንዳልነበር እና ጥፋት እንደሆነ ለፀጥታ አመራሮቹ ማብራሪያ መሰጠቱንም ገልጸዋል። በፀጥታ ኃይሉ በኩልም የሙስሊሙን ሕጋዊ ጥያቄ ሽፋን በማድረግ የራሳቸው አጀንዳ ለማራመድ የሞከሩ ኃይሎች መኖራቸውን መረጃ እንዳላቸው በማንሳት የነበራቸውን ስጋት መግለጻቸውም ተነግሯል።
በውይይቱ መቋጫ ላይም በኹለቱ ጁምዓዎች በተወሰደው የኃይል እርምጃ በእስር ላይ የሚገኙት ሙስሊሞች በሙሉ ከእስር በሚፈቱበት አግባብ ላይ ከስምምነት ላይ መድረስ መቻሉንም ኡስታዝ አቡበክር በመልዕክታቸው ያስታወቁ ሲሆን፤ ከሕግ አግባብ ውጪ የኃይል እርምጃ የወሰዱ የጸጥታ ሀይሉ አባላትም በሕግ አግባብ እንዲጠየቁ ኮሚቴ ተዋቅሮ የማጣራቱ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ መገለጹን ተናግረዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ ያቀረባቸው ሕጋዊ ጥያቄዎቹ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት በኩል መፍትሄ ለመስጠት ቃል በመገባቱ እና ይህም መፍትሄ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ህዝበ ሙስሊሙ በተለመደው ጨዋነቱ በትዕግስት በመጠበቅ ከመሪ ድርጅቱ መጅሊሱ ጎን በመቆም በተቋሙ የተሰጡትን መመሪያ እና የመፍትሄ አቅጣጫ በመተግበር እና በዱዓ በማገዝ የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል።
ስለሆነም፤ “በቀጣይ ባሉ ጁምዓዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ህዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን በማጠናከር እና በዱዓ በመበርታት መደበኛ የጁምዓ ሰላቱን ብቻ እንዲያከናውን ጥሪ እናቀርባለን።” ሲሉ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።
እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ትናንት ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።
አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል።
ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ።
አስፈላጊ #መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/
አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
መዲናዋ ሶስት ሀገራዊ ፣ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ሁነቶችን እንደምታስተናግድ ተገለጸ
አዲስ አበባ ከተማ ሶስት ሀገራዊ ፣ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ሁነቶችን እንደምታስተናግድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
መድረኮቹ በመጪው ቅዳሜ ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ጎን ለጎን እንደሚከናወኑም ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ እናት አለም መለሰ፣ መስከረም 24 እና 25 የሚካሄደው የአፍሪካ ከንቲባዎች የሊደርሽፕ ኢኒሼቲቭና የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች የእርስ በእርስ መማማሪያ መድረክ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
መስከረም 28 እስከ 29 የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም የልህቀት ማዕከልን ለማቋቋም የአለም አቀፍ የምክክር መድረክ እንዲሁም ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም የሀገር አቀፍ መሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ ናቸው ተብሏል።
በመድረኮቹ ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ተሳታፊዎች ይካፈሉበታል።
እነዚህን ሶስት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው መድረኮች በሰፊው የምትጠቀም ይሆናል ተብሏል።
ምንጭ፦ ኢፕድ
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ጦርነት ምክንያት ያዘገየውን የ680 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለመልቀቅ ቃል ገባ
የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ጦርነት ምክንያት ያዘገየውን የ680 ሚሊየን ዶላር የባለ ብዙ ዘርፍ ዓመታዊ ድጋፍ ለመልቀቅ የሚያስችል ስምምነት ከገንዘብ ሚኒስትር ጋር ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱ በአውሮፓ ኅብረት የዓለም ዓቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን እና በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ መካከል የተደረገ ሲሆን፤ ድጋፉ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ ትብብር ይበልጥ የሚያጎለብት እንደሚሆን ተመላክቷል።
የተደረገው የ650 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን ቦታዎች ለመገንባትና የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያን ለማናከናወን እንደሚጠቅም አመላክተዋል።
ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን በበኩላቸው፤ ድጋፉ በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ለመልሶ ግንባታና ለተለያዩ የልማት ሥራዎች እንደሚውል ተናግረዋል።
ድጋፉ በፈረንጆቹ 2024 እስከ 2027 ለአራት ዓመታት እንደሚቆይም ተነግሯል፡፡
የአውሮፓ ህብረት በጥር ወር 2021 ለኢትዮጵያ ሊያደርገው የነበረውን የበጀት ድጋፍ በትግራዩ ጦርነት ምክንያት አቋርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መንግስት መስጠት ያቋረጠውን ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ ለመቀጠል፤ አሁንም መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ አስታወቀ።
ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ወደ ነበረበት ለመመለስ “የደረጃ በደረጃ አካሄድን” እንደሚከተል ገልጿል።
ሃያ ሰባት አባል ሀገራትን በስሩ ያቀፈውን የአውሮፓ ህብረትን አቋም ያሳወቁት፤ የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ዩታ ኡርፒላይነን ናቸው።
ኮሚሽነሯ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጋር ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 22፤ 2016 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል ውይይት ካደረጉ በኋላ፤ የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን አሁንም እንደ “ስትራቴጂካዊ አጋር” እንደሚመለከታት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት፤ በጥቅምት 2013 በትግራይ ክልል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ወዲህ ተቀዛቅዞ ቆይቷል። ህብረቱ በጦርነቱ ምክንያት ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን 90 ሚሊዮን ዩሮ ከሚጠጋው የበጀት ድጋፍ ማገዱ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ በተመሳሳይ ምክንያት ለኢትዮጵያ ያዘጋጀውን አንድ ቢሊዮን ዩሮ የልማት እርዳታ ሳይያጸድቅ ቀርቷል።
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን ቀጥተኛ በጀት እንደገና ለመልቀቅ አስቦ እንደው ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጥያቄ የቀረበላቸው ኮሚሽነሯ፤ ይህ የገንዘብ ድጋፍ ከመደረጉ በፊት በኢትዮጵያ በኩል መሟላት የሚገባቸው “ፖለቲካዊ ሁኔታዎች” እንዳሉ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
በኢትዮጵያ ለተከሰተው የ1977ቱ አስከፊ ረሃብ እርዳታ እንዲውል በገንዘብ ማሰባሰቢያነት ከ38 ዓመታት በፊት የተዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት ዳግም ወደ መድረክ ሊመጣ ነው
‘ላይቭ ኤይድ’ የሚል ስያሜ የተሰጠው እና በርካታ ሙዚቀኞችን ያሰባሰበው የሙዚቃ ዝግጅት በዝነኛነቱ አሁንም ዓለማችን ከምታወሳቸው አንዱ ነው።
በቀጥታ የተላለፈው የሙዚቃ ዝግጅትም ተዘጋጅቶ በመድረክ ሙዚቃነት በሚቀጥለው ዓመት በለንደን ይቀርባል።
የመጀመሪያው የሙዚቃ ዝግጅት በአውሮፓውያኑ ሐምሌ 13/1985 በዌምብሌይ ስታዲየም የቀረበ ነው።
ታዋቂው ሙዚቀኛ ቦብ ጌልዶፍ እና ሚጅ ዩሬ ናቸው ከ38 ዓመታት በፊት የነበረውን ኮንሰርት ያዘጋጁት።
‘ጀስት ፎር ዋን ደይ’ በሚል ስያሜ ወደ መድረክ የሚመለሰው ይህ የሙዚቃ ቅንብር ኩዊን፣ ሰር ኤልተን ጆን፣ ሰር ፖል ማካርቲኒ እና ስቲንግ የተጫወቷቸው ዘፈኖችን አካቷል።
በለንደን ኦልድ ቪክ ቲያትር ከጥር አጋማሽ እስከ መጋቢት የሚቀርብም ይሆናል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ
በስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ እየተሰተፈ የሚገኘው ብሔራዊ ባንክ ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በግል ባንኮች ላይ አለ ስለተባለው የገንዘብ እጥረት ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል።
የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ እንዳሉት "በኢትዮጵያ በግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል እሚባለው መረጃ ሀሰት ነው" ብለዋል።
የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል የተባሉት አምስት ባንኮች ናቸው መባሉን ሰምተናል ፣ "ነገር ግን በሶስት ባንኮች ላይ የተወሰነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሞ ነበር፣ ብሔራዊ ባንክ እና ሌሎች ተቋማት በወሰዷቸው ማስተካከያዎች አሁን ላይ ከአንድ ባንክ በስተቀር የጥሬ ገንዘብ እጥረት ያጋጠመው ባንክ የለም" ሲሉም ምክትል ገዢው አክለዋል።
በኢትዮጵያ የገንዘብ አቅርቦቱ እና ፍላጎቱ የተጣጣመ አይደለም ያሉት አቶ ሰለሞን አሁን ያጋጠመው ክስተትም ጦርነት ውስጥ በነበርንበት የቆመው የፋይናንስ እንቅስቃሴ አሁን የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የፋይናንስ ፍላጎቱ በመጨመሩ ብቻ የተፈጠረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎቶችን ለዓለም አቀፍ ተቋማት በሯን ክፍት ማድረጓን ተከትሎ ይህ ሂደት የት ደረሰ? በሚል ለምክትል ገዢው ለቀረበላቸው ጥያቄም " ስራው ሰፊ ዝግጅቶችን የሚጠይቅ ነው፣ ከዓለም ባንክ ጋርም አብረን እየሰራን ነው በአንድ ዓመት ውስጥም ስራውን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው" ብለዋል።
ስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው ይህ ትኩረቱን በካፒታል ማርኬት ላይ ያደረገ ሲሆን የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶች እና ውይይቶች እየተደረጉበት ይገኛል። በጉባኤው ላይ የባንክ ስራ አስኪያጆች፣ ባለሙያዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች ተሳትፈውበታል።
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagra://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
በአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ኃይሎች የሕግ አግባብ በሌለው መልኩ የመንገድ ላይ ፍተሻዎች እስሮች፣ ማዋከቦች እና እንግልቶችን በዜጎች ላይ እየፈጸሙ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ።
ኢሰመጉ እነዚህ እስሮች እና እንግልቶች በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉት የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባ ከተማ ተከታታይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እንደሚያደርግ ማስታወቁን ተከትሎ እንደሆነ ሰኔ 07/ 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
የጋራ ግብረ ኃይሉ በአዲስ አበባ ከተማ “የተለያዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የተዘጋጁ ኃይሎች እንዳሉ ደርሼባቸዋለሁ” ሲል ግንቦት 30/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ግብረ ኃይሉ በእነዚህ ኃይሎች ላይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ለማካሄድ እንዳቀደ አስታውቆ ማኅበረሰሰቡ “ፀጉረ ልውጦችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥ” እና እንዲተባባርም ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።
አምስት አካላትን የያዘው የፀጥታ እና ደኅንነት ግብረ ኃይል ሰላም እና ፀጥታን ለማስከበር እየሰራ ባለው ተግባር በአንዳንድ አካባቢዎች ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም መስተዋሉን ኢሰመጉ ጠቅሷል።
የጋራ ግብረ ኃይሉ “ከመደበኛው የሕግ ሥነ ሥርዓት ከፍ ያለ ሥልጣን እንዳለው በማሰብም” በአንዳንድ አካባቢዎች ሥልጣንን አላግባብ ለመጠቀም ምክንያት መሆኑም ከኢሰመጉ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜላት መሀመድ ትላንት ሰኔ 5/2015 ዓ.ም ቀትር ላይ በሁለት ተሽከርካሪ በመጡ ግለሰቦች 'መጠለፏን' ቤተሰቧቿ ተናግረዋል።
የ14 ዓመት ከ 8 ወር ታዳጊዋ ሜላት ከትምህርት ቤት ወደ መኖሪያ ቤቷ በመመለስ ላይ እያለች አግተው እንደወሰዷት ተሰምቷል።
የሜላት የአክስት ልጅ የሆነችው ትዕግስት ብስራት ስለሁኔታው ስታስረዳ እሷና እናቷ ለቅሶ ላይ በነበሩበት ሁኔታ ነው እናቷ ከምትሰራበት አነስተኛ ምግብ መሸጫ የቤት ቁልፍ ወስዳ ስትሄድ ከመንገዷ በሁለት ዳማስ [መኪና] የነበሩ ግለሰቦች አፍነው ያስገቧት በማለት ከጥበቃቸው የሰማችውን መረጃ የተናገረችው።
እናት በህይወት ባለመኖሯቸው ምክንያት ሜላት ከአክስቷ ጋር ማደግ የጀመረችው ከ 3 አመቷ ጀምሮ ነዎ።
ትዕግስት ሀዋሳ ከተማ ውስጥ አነስተኛ ምግብ ቤት ያላት ሲሆን ፤ የአጋቾቹን ማንነት ለማጣራት ባደረገችው ሙከራ እሷ ጋር ምግብ የሚመገቡ ልጆች መሆናቸውን አመልክታለች።
ትዕግስት " ጠላፊውን " እንደምታወቀውና ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው የገለፀች ሲሆን ይህ የምግብ ቤት ደንበኛዋ የተለየ ምንም ነገር እንደማያሳይ ተናግራለች።
" ከሜላትና ከልጆቼ ጋር ያለኝ ነገር ያውቃሉ። " ያለችው ትዕግስት " ሲናገሯቸው እንኳን በጣም ነው የምቆጣው። አይደፍሩም. . . ሙሉ ቤተሰብ ለቅሶ ላይ ስለነበር አለመኖራችንን አይቶ ነው [ይህንን ያደረገው]” ብላለች።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
አነጋጋሪዋ የ 76 ዓመት አዛውንቷ ቤላ ምንቶያ
ኢኳዶራዊቷ የ76 ዓመት ቤላ ሞንቶያ ሞተዋል ተብሎ ሊቀበሩ ሲሉ እስትንፋሳቸውን አሰምተዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት በስትሮክ ምክንያት መሞታቸው የተነገረው አዛውንቷ የሬሳ ሳጥን ውስጥ ተከተው ሥርዓተ ቀብራቸው ሊፈጸም ሲል ነው በሕይወት እንዳሉ የታወቀው።
ዘመዶቻቸው ልብሳቸውን ቀይረው ለግብዓተ መሬት እያዘጋጇቸው በነበረበት ሰአት እስትንፋሳቸውን ሰምተው ነው ወደ ሆስፒታል የወሰዷቸው። አዛውንቷ አሁን በጽኑ ሕሙማን ማቆያ ነው የሚገኙት።
የኢኳዶር ጤና ሚኒስትር ጉዳዩን የሚመረምር ኮሚቴ አዋቅሯል። ድንገተኛ የልብ መቆምና ትንፋሽ መቋረጥ (cardiorespiratory arrest) ገጥሟቸው ስለነበር ሐኪሞች ሞተዋል ብለው እንደደመደሙ ተገልጿል።
በስትሮክ ህመም ህይወታቸው ማለፉን ያረጋገጠው ሀኪምና ሆስፒታሉ ምርምራ እንዲደረግባቸው የኢኳዶር ጤና ጥበቃ ሚኒሲቴር አስታውቋል።
ሞንቶያ ልባቸው መምታት፣ በሰው ሰራሽ መሳሪያም መተንፈስ አቁመው እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፥ ሊቀበሩ ሲሉ የመንቃታቸው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል።
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ያነጋገረው ልጇ ጊልበር ሩዶልፎ፥ እናቱ ጤናቸው እንዲመለስ በመጸለይ ላይ መሆኑን ገልጿል።
ክስተቱ ህይወታቸው ማለፉ ተነግሮ በፍጥነት ወደ አስከሬን ሳጥን የተወረወሩና የሚያደምጣቸው አጥተው ነፍሳቸው ሳይወጣ የተቀበሩ ሰዎች ቁጥር ቀላል እንደማይሆን ያሳያል ተብሏል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
ከእስር ተለቀቀ
ባሳለፍነው አርብ ሰኔ 2/2015 ምሽት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው የፊልም ባለሙያ እና የጉማ የፊልም ሽልማት አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ መዋ ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር መፈታቱ ታውቋል።
ዮናስ አርብ ምሽት ከጉማ የፊልም ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በኋላ ሲቪል በለበሱ የመንግሥት ደኅንነት ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል።
በማግስቱ ቅዳሜ ጠዋት ፍርድ ቤት የቀረበው ዮናስ በአምስት ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ በፍርድ ቤት ቢወሰንለትም፤ በተመለዶ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ ወደሚጠራው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መዘዋወሩም ተገልጾ ነበር።
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ "20ሺህ ሰራተኞችን ሊቀጥር ነዉ"በሚል እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን አስታወቀ
በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እየተሰራጨ የሚገኘዉ "ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 20 ሺህ ሰራተኞችን ሊቀጥር ነዉ" የሚለዉ መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ሀላፊ ወ/ሮ ተወዳጅ እሸቱ ተናግረዋል።
እንደ ወ/ሮ ተወዳጅ ገለጻ ኩባንያዉ 20 ሺህ ሰራተኞቻችን ለመቅጠር የያዘዉ እቀድ የለም ያሉ ሲሆነወ የተጠቀሰዉ ቁጥርም ግነት ያለዉ መሆኑን ገልጸዋል።
እየተሰራጨ በሚገኘዉ መረጃ ኩባንያዉ " በሶማሌ ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች ነዉ የተጠቀሰውን ቁጥር ያህል ሰራተኛ ይቀጥራል የተባለዉ"።
ኩባንያዉ የዚህን ያህል ቁጥር ሰራተኛ ለመቅጠር የያዘዉ እቀድ እና ዝግጅት እንደሌለ ጠቅሰዉ ፤ በኩባንያዉ ስም ከተከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት የተሰራጨ መሆኑን ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
ለእስር ተዳርጓል
የጉማ አዋርድ በተለያዩ ጊዚያት አነጋጋሪ አለባበሶችን ሲያስተናግድ ቆይቷል። በፊልም ኢንዱስትሪያቸው ትልቅ የተባሉ ሀገራት በሚያካሂዱት ጥበባዊ የሽልማቶች መድረክ ላይ ትልልቅ ሀሳቦች ይሰንዘሩበታል ስለ ዘረኝነት ስለእኩልነት ስለ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከያኒያን ሀሳባቸውን ይገፁበታል።
በትላንትናው እለት በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው 9ኛው የጉማ የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ "ልጅ ማኛ " ጥበባዊ በሆነ መንገድ አፈናና ሞትን በሚገልፅ መልኩ ፊቷ ላይ በተሰራችው የገፅቅብ ሀሳቧን ገልፃለች። የጉማ ዋና አዘጋጅ ዮናስ ብርሀነ መዋም ለእስር እንደተዳረገ ተገልጿል።
#GummaAwards
በአሰሪዋ ተደብድባና ተደፍራ ያረገዘችው ኢትዮጵያዊ ወጣት ከ 9ሚሊዮን ብር በላይ እንዲከፈላት በፍርድ ቤት ተወሰነላት
በባህሬን አንዲት ወጣት 4 ዓመት ሙሉ ስትሰራበት የነበረበት ቤት ውስጥ በአሰሪዋ በመደፈር፣ በመደብደብ እና የመግደል ዛቻ ሲደርስባት በመቆየቱና የድረሱልኝ ጥሪዋን በማሰማቷ ምክንያት፤ በባህሬን የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በጋራ በመሆን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማመልከት ፍትሕ እንድታገኝ መደረጉ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ አሰሪዋ “አልደፈርኩም” ብሎ የሕክምና ወረቀት በማቅረብ ጉዳዩ ትኩረት እንዳያገኝ በማድረግ ወጣቷን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም፤ ጽ/ቤቱና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ከ6 ወራት በላይ በመከራከርና የDNA ምርመራ በማስደረግ በተገኘው የምርመራ ውጤት መሰረት፤ ወጣቷ የስድስት ወር እርጉዝ መሆኗና የእርሱም ልጅ እንደሆነ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተነግሯል።
በዚህም መሠረት፤ የወጣቷን እና የልጇንና መብት በማስከበር 64 ሺሕ 800 የባህሬን ዲናር (9 ሚሊዮን 344 ሺሕ 886 ብር) በየአራት ዓመት ክፍያ እንዲከፍል አሰሪው የተስማማ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ አራት ዓመት የሚሆን ቅድመ ክፍያ 14 ሺሕ 200 የባህሬን ዲናር (2 ሚሊዮን 47 ሺሕ 799 ብር) በመቀበል ፍርድ ቤት ፈርሞበት ወጣቷ ፍትህ እንድታገኝ መደረጉን በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አስታውቋል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
በሱሉልታ ከተማ በሸኔ ታጣቂዎች ቁጥራቸው በውል ያልታውቁ ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸው ተገለጸ
በቅርቡ በተዋቀረው የሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኘው የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ከአንድ ሳምንት በፊት በአንድ ምሽት ብቻ ከሱሉልታ ክፍለ ከተማ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አካባቢ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ቁጥራቸው ከ20 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በሸኔ ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ጠቅሶ አዲስ ማለዳ ዘግቧል።
ሰዎቹ በተወሰዱበት ዕለትም ምንም አይነት የመሳሪያ ድምጽ ባለመሰማቱ የጸጥታ አካላት ደርሰው ሊያስጥሏቸው እንዳልዳቻሉ ጠቅሰዋል።
ረቡዕ ግንቦት 30/2015 እንዲሁ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ምሽት ላይ ታግተው መወሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡
የተወሰዱት ሰዎችም እስካሁን ድረስ ያሉበት አይታወቅም የተባለ ሲሆን፤ አጋቾችም ይህን ያህል ብር አምጡና እንለቃቸዋለን በማለት እየተደራደሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ነዋሪዎቹ ታጣቂ ቡድኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአካባቢው እና በሌሎች አዋሳኝ ወረዳዎች በስፋት እንደሚንቀሳቀስ የተናገሩ ሲሆን፤ ትግሉም ከሌላ አካል ጋር ሳይሆን ንጹሃን ዜጎችን እያፈነ ገንዘብ መጠየቅ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube
በቦረና ዞን አንድ እናት ነብርን አላምደው አብረው እየኖሩ መሆኑ ተሰማ
በቦረና ዞን የዲሎ ወረዳ ቃዲም ኦላ ጫጩ ገልገሎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ጂሎ ጃተኒ የዱር እንስሳት የሆነውን ነብርን በማላመድ አብረው እየኖሩ መሆኑ ተዘገበ፡፡
ወ/ሮ ጂሎ በዞኑ ድርቅ ተከስቶ በነበረበት ወቅት ለከብቶች ሳር ለመፈለግ ወደ ዱር ባቀኑበት ጊዜ የነብር ግልገል አግኝተው ነዎ ይዘው የገቡት፡፡
ወይዘሮዋ እንደገለፁት ግልገሏን እነርሱ የሚመገቡትን ምግብ በመመገብ እያሳደጉት ሲሆን ግልገሏም ተላምዶ ከፍየሎች እና ህፃናት ጋር ቦርቃ እያደገች ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ OBN
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:/channel/ethiotube