ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 8 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - December 18 , 2023

👉 በትግራይ ሽረ እንዳስላሰ መምህራን ከአንድ ዓመት ለሚልቅ ጊዜ ያልከፈላቸውን ውዝፍ ደምወዝ በመጠየቅ አደባባይ ወጡ።

👉 በድርቅ ክፉኛ የተጎዳው የዋግ ኸምራ ዞን አስር ሚሊዮን ብር ገደማ የሚያወጣ ድጋፍ አገኘ፤

👉 በአማራ ክልል የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱ 936 ተጠርጣሪዎች  ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቀሉ 

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/4ZDQxegfBVM

Читать полностью…

EthioTube

እስራኤል በጋዛ ድንበር አቅራቢያ ትልቁን የሃማስን ዋሻ ማግኘቷን አስታወቀች

የእስራኤል ጦር በጋዛ ውስጥ ትልቁን የሃማስ ዋሻ ቁልፍ በሆነው የድንበር ማቋረጫ አካባቢ ማግኘቱን ገልጻል።

የእስራኤሉ ባለስልጣናት ዋሻው ከ4 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝማኔ ያለው ሲሆን ከኤሬዝ ድንበር ማቋረጫ በመቶ ሜትሮች ርቀት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ሃማስ ለጥቅምት 7 ጥቃት ከተጠቀማቸው ዋሻዎች መካከል አንዱ ነው።

የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በዚህ ዋሻ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር መዋዕለ ንዋይ ፈሷል።
ይህንን መሿለኪያ ለመሥራት ሀማስ ዓመታት ፈጅቶበታል ተሽከርካሪዎች ለማንቀሳቀስ የሚያስችል እንደሆነም ገልፀዋል። የእስራኤል ጦር በጋዛ ካደረገው ጦርነት ዋና ዓላማዎች መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች የመሬት ውስጥ ዋሻዎችን ማሰናከል እንደሆነም ገልጿል።

በሌላ በኩል የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደተናገሩት የእስራኤል የአየር ጥቃት በጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ ላይ ቢያንስ 90 ፍልስጤማውያንን ገድሏል። በደቡባዊ ጋዛ በሚገኘው የናስር ሆስፒታል የእናቶች ክፍል ላይ የእስራኤል ጥቃት ቢያንስ አንድ ሕፃን ሲገድል ሌሎች ሦስት ሰዎች ቆስለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሰሜን ጋዛ በሚገኘው በካማል አድዋን ሆስፒታል ላይ የደረሰው ጥቃት አስደንጋጭ ነው ​​ብለዋል።

በሌላ በኩል እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኘውን የሂዝቦላ ፀረ ታንክ ሚሳኤል ማዕከል መትቻለው ስትል ሂዝቦላህ ግን በእስራኤል ወታደሮች ላይ ጉዳት አድርሻለሁ ብሏል። የሶሪያ የሰብአዊ መብት ታዛቢ ቡድን በበኩሉ እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በደማስቆ አቅራቢያ ቢያንስ ሁለት ሰዎችን ገድላለች ብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

በአማራ ክልል የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱ 936 ተጠርጣሪዎች ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቀሉ

በሰሜን ምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት 936 ተጠርጣሪዎች በሶስት ዙር ምክርና የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸውን ኮማንድ ፖስቱ ገለጸ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት በሰሜን ምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ለሁለተኛ ዙር በጮሪሳ ጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብት አያያዝ በመጎብኘት ከአመራሩም ጋር ውይይት አድርገዋል።

በጉብኝታቸውም የተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ መልካም መሆኑም ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።
በሰሜን ምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት በአራተኛ ዙር 152 ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ላይ እንደሚገኙም ተጠቁሟል።
የሰሜን ምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት የዘመቻ ሃላፊ ኮሎኔል መንገሻ ፈንታው እንደገለፁት፤ ኮማንድ ፖስቱ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እየሰራ ይገኛል።

በቀጣናው 779 ተጠርጣሪዎች በሶስት ዙር የተሃድሶ ስልጠና በወስደው እንዲሁም 157 ተጠርጣሪዎች በምክር ወደ ማህበረሰቡ የተቀላቀሉ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በአጠቃላይ 936 ተጠርጣሪዎች በሶስት ዙር የተሃድሶ ስልጠና በምክር ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ ዜሮ ለዜሮ ወተዋል። አርሰናል መሪነቱን ይዟል።

#EPL #PremierLeague

Читать полностью…

EthioTube

በዚህ ሳምንት በመቀነት መሠናዶ የምዕራፍ አንድ መጠናቀቁን አስመልክተን የነበረንን ቆይታ እናስቃኛቹሀን።

ሙሉውን ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/QSIW570LJbU

Читать полностью…

EthioTube

በዳውሮ 11 ኪሎ የሚመዝን ዕጢ በተሳካ ሁኔታ በቀዶ ሕክምና ተወገደ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ከተማ አጠቃላይ ሆስፒታል በተደረገ ቀዶ ሕክምና ከ65 ዓመት ወይዘሮ 11 ኪሎ የሚመዝን ዕጢ ማስወገድ መቻሉ ተገለጸ።

በሆስፒታሉ ለግለሰቧ የተደረገው ቀዶ ሕክምና ከ4 ሰዓታት በላይ መፍጀቱም ተነግሯል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ታካሚዋ በሆስፒታሉ ውስጥ ሆና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ ሆስፒታሉ መግለጹን የዳውሮ ኮሚንኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

Читать полностью…

EthioTube

ሃማስ አደገኛ የተባሉትን 35 አል ዛዋሪ ድሮኖች በእስራኤል ላይ አሰማርታለች

ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።

ሃማስ እስራኤል ላይ በሮኬት እንዲሁም ተዋጊዎቹ በፓራሹትና በተለያዩ መንገዶች ድንበር ጥሰው ገብተው ወረራ ያደረገ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም “አል-ዛዋሪ” የተባለ በድሮን ጥቃት እየሰነዘረ እንደሚገኝ አል አይን ዘግቧል።

ሃማስ የድሮን ጥቃት እየፈፀመ ያለው “አል-ዛዋሪ” የሚል መጠሪያ ባለው “ፈጣን እና አደገኛ” ድሮን መሆኑም ታውቋል :
“አል-ዛዋሪ”የርቀት መቆጣጠሪያ (ሪሞት ኮንትሮል) የሚሰራ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ሲሆን፤ ሃማስ ለውጊያ መሳሪያነት የሚጠቀምበት ፈጣኑ የጦር መሳሪያ ነው።

ድሮኑ እንደ ፈንጂ ያሉ የጦር መሳሪያዎችን በመታጠቅ የማቅረብ አቅም ያለው ሲሆን በእስራኤል ኢላማዎች ላይ ለማጥቃት ሲውል ቆይቷል። አል-ዞዋሪ የአጥፍቶ ጠፊ ድሮን በጠንካራው የእስራኤል የአየር መከላከያ ስርዓት “አይረን ዶም” ሊያቆመው አይችልም ተብሏል።

ሃማስ በሁሉም ግንባር 35 አል ዛዋሪ ድሮን ማሰማራቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ ድሮኖቹ በተለያዩ የእስራኤል ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል፣
ድሮኑ “አል-ዙዋሪ” የሚል ስያሜ ተሰጠው በፈረንጆቹ በ2016 በእስራኤል የስለላ ተቋም ሞሳድ በተገደለው በሐማስ ወታደራዊ ክንፍ መሪ መሐመድ አል-ዛዋሪ ስም ነው።


ምንጭ፦ አል አይን

Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 
Telegram: /channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ሦስተኛው ዙር የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት በሚቀጥለው ሳምንት በካይሮ ይካሄዳል

በታ
ላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል የሚደረገው ሦስተኛው ዙር የሦስትዮሽ ድርድር፤ በሚቀጥለው ሳምንት በካይሮ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በግድቡ ዙሪያ አለመግባባታቸውን ለመፍታት ካሳለፍነው ነሃሴ ወር ጀምሮ ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም በነሃሴ ወር ላይ የግድቡ ተደራዳሪ የቴክኒክ ባለሙያዎች በግብጽ ካይሮ ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን፤ ሁለተኛው ዙር የቴክኒክ ባለሙያዎች ውይይት ደግሞ ከኹለት ሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት በኹለተኛው ዙር ውይይት ላይ ሦስተኛው የአገራቱ ድርድር ጥቅምት ወር ላይ በግብጽ ካይሮ እንዲካሄድ ስምምነት ላይ መደረሱን  ተከትሎ፤ ድርድሩ የፊታችን ጥቅምት 11 እና 12/2016  በግብጽ መዲና ካይሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡



Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 
Telegram: /channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የዓለም አትሌቲክስ በ2023 ውድድር ውጤት መሰራት 11 ምርጥ ያለቸውን ሴት ዕጩዎች አትሌቶች ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ

ከአሥራ አንዱ ሴት ዕጩዎች አትሌቶች መካከል ሁለቱ ኢትዮጵያው ሲሆኑ እነሱም፡-
✳️አትሌት ትግስት አሰፋ እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 24/2023 በጀርመኗ በርሊን ከተማ በተካሄደ የማራቶን ሩጫ አሸናፊና የውድድሩ ከብረወሰን ባለቤት ፡፡

✳️አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የዘንድሮው የቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮና የ10,000 ሜትር አሸናፊ እና በሴብቴምበር 27/2023 በአሜሪካ ዩጂን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር 5,000 ሜትር የክብረወሰን ባለቤት በሴቶች ምድብ እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡


#EEF

Читать полностью…

EthioTube

የ14 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ሂመን በቀለ የታዳጊ ሳይንቲስቶች ሽልማት አሸናፊ ሆነ

በአሜሪካ ነዋሪ የሆነው የ14 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ሂመን በቀለ፤ የ2023 የታዳጊ ሳይንቲስቶች ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።

ታዳጊው ሽልማቱን ያገኘው የቆዳ ካንሰርን የሚከላከል ሳሙና ፕሮጀክት በማቅረብና በሱ ደረጃ ካሉ ታዳጊ ሳይንቲስቶች ጋር ተወዳድሮ በማሸነፉ ነው።

ሂመን ውድድሩን በማሸነፉ በታላላቅ ሳይንቲስቶች ሥር ሆኖ ከፍተኛ ስልጠና የሚያገኝበት ዕድል እንደሚመቻችለት ተገልጿል። ለቀጣይ ሳይንሳዊ ምርምሩ ሁለገብ ድጋፍ የሚያገኝበት ሁኔታ እንደሚፈጠርለትም ተነግሯል።

ሂመን ውድድሩን በማሸነፉ የ25 ሺሕ ዶላር ተሸላሚ ሲሆን፤ ‘ከፍተኛ የአሜሪካ ታዳጊ ሳይንቲስት’ የሚል ማዕረግም አግኝቷል።


ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ

Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 
Telegram: /channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመሰጠት ላይ ነው

በት
ግራይ ክልል በ2012 የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ የነበሩና መልቀቂያ ፈተናውን ሳይወሰዱ ለቀሩ ተማሪዎች የሚሰጠው የመልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ጀምሯል፡፡

በዚህም መሰረት በክልሉ 9 ሺሕ 514 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ከዚህም ውስጥ 6 ሺሕ 513 ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ሲሆኑ፤ 3 ሺሕ 1 የሚሆኑት ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መሆናቸውን ቢሮው ገልጿል፡፡

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ በመቀሌ፣ በአክሱም፣ በአዲግራት እና በራያ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡


Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 
Telegram: /channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ

በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል የተቀሰቀሰውን ከፍተኛ ጦርነት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ መታየቱ እየተዘገበ ይገኛል።

በዚህም እስራኤል በጋዛ ያለው ሁኔታ ከመካከለኛው ምስራቅ የሚነሳውን የነዳጅ አቅርቦት ሊያስተጓጉል ይችላል በሚል ስጋት፤ ዛሬ ሰኞ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ላይ በ 4 በመቶ ጭማሪ መታየቱ ተነግሯል።

ባለፉት ሳምንታት ወደ 96 ዶላር ደርሶ የነበረው የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ባለፉት ቀናት ጥሩ የሚባል ቅናሽ አሳይቶ የነበረ ሲሆን፤ ነገር ግን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኃላ የነዳጅ ዋጋ ዛሬ በ4 ነጥብ 53 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ፤ 88 ነጥብ 41 ዶላር መድረሱን ሲኤንቢሲ ዘግቧል።

የአሜሪካን የነዳጅ ዋጋ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰደው ዌስት ቴክሳስ ኢንትርሚዲየት የተሰኘው ተቋም አንድ በርሜል ነዳጅ በ4 ነጥብ 69 በመቶ ጨምሮ ወደ 88 ነጥብ 67 ዶላር ከፍ ማድረጉም ተነግሯል።

በእስራዔልና በፍልስጤሙ ሃማስ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ወደ ሙሉ ውጊያ ከተቀየረ ሁለተኛ ቀኑን ያያዘ ሲሆን፤ ጦርነቱ በደቡባዊ እስራዔል ሦስት ሥፍራዎች ተፋፍሞ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡


Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 
Telegram: /channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በፈተናው የማለፊያ ነጥብ ያመጡት 27 ሺህ 267 ተማሪዎች ወይም 3 ነጥብ 2 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ ውጤት ከተፈጥሮ ሳይንስ 649 በአዲስ አበባ ከተማ ሲመዘገብ÷ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 በደብረ ማርቆስ ከተማ ተመዝግቧል፡፡

አምስት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎችን በሙሉ ማሳለፋቸውን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

ከተፈጥር ሳይንስ ተፈታኞች ውስጥ 205 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን÷በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 15 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የፈተና መመሪያ እና ደንብ በመጣስ በግል 483 ተማሪዎች እንዲሁም በቡድን  376 ተማሪዎች መቀጣታቸውን አንስተዋል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

የኩላሊት ታማሚዋ ሜላት አስገራሚ ታሪክ | ጋሽ ፍቃዱ ተክለማርያም አትርፎኛል

ሙሉውን ቪዲዮ ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፦
https://youtu.be/IZVRQGWAY54?si=sS4b28iWBrVjEMpU

Читать полностью…

EthioTube

ሲፒጄ በኢትዮጵያ የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) በኢትዮጵያ በነሃሴ መጨረሻ እና በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙትን ሶስት ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የጠየቀ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የጋዜጠኞችን እስር እንዳሳሰበው ገልጿል።

አለማቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) የ"የኛ ቲቪ" እና "የምኒሊክ ቴሌቪዥን" የኦንላይን ሚዲያ አቅራቢ እና ፕሮግራም አዘጋጅ ቴዎድሮስ ዘርፉ ፤ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑትን ንጉሴ ብርሃኑ እና የትርታ ኤፍ ኤም የፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ የኋላሸት ዘሪሁን  መታሰራቸውን ገልጾ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል።

ኮሚቴው ሶስቱ ጋዜጠኞች መጀመሪያ በመዲናይቱ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጣቢያ ታስረው እንደነበር ገልጾ ፥ ከዛ በኋላ ጋዜጠኞቹ ከአዲስ አበባ 145 ኪ.ሜ ርቆ በሚገኘው አዋሽ አርባ ወታደራዊ የማቆያ ካምፕ መዛወራቸውን ገልጿል።

የአለማቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት የአፍሪካ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ ፥ "በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ጋዜጠኞችን ማቆየትና ግልፅ ያልሆነ የጋዜጠኞች እስር ኢትዮጵያ ለመገናኛ ብዙሃን ያላት የፕሬስ ነፃነት አሳሳቢ ያደርገዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

ተወካዩ "ጋዜጠኞቹ ቴዎድሮስ ዘርፉ፣ የኋላሸት ዘሪሁን እና አቶ ንጉሴ ብርሃኑ እንዲሁም ሌሎች ከፕሬስ ጋር በተያያዘ ሰበብ የታሰሩ እስረኞች ሊፈቱ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል።

ጋዜጠኞቹ ፍርድ ቤት ቀርበው በወንጀል መከሰሳቸውን እንደማይታወቅ ሲገለፅ ፥ ጉዳዩን አስመልክቶ የአለማቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) ለፌደራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ጄይላን አብዲ እና የፌደራል ፍትህ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዲሁም የመንግስት ቃል አቀባይ ለሆኑት አቶ ለገሰ ቱሉ በፅሁፍና በመልእክት መላላኪያ መተግበሪያ ጥያቄዎችን አቅርቦ ምላሽ አለማግኘቱን አሳውቋል።

Читать полностью…

EthioTube

በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ ልዑካን በሻንጋይ ከተማ የስራ ጉብኝት አደረገ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ የቻይና የንግድ ማዕከል በሆነችው በሻንጋይ ከተማ የስራ ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡

ልኡካን ቡድኑ በጉብኝቱ ዘመናዊ የከተማ መዋቅራዊ ፕላን እና አተገባበር፣ በመሰረተ ልማት ቅንጅትና ግንባታ ፣ በመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር እንዲሁም ዘመናዊ ከተማ አገነባብ ዙሪያ ከሻንጋይ ከተማ ፕላን እና የተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አመራሮች ጋር ውይይትና ጉብኝት አድርገዋል::

የሻንጋይ ከተማ በምትታወቅበት ዲጂታላይዝድ አገልግሎቶች እና በስማርት ሲቲ ግንባታ ሂደት ለሃገራችን ከተሞች ልምድ በምታጋራበት እና አብሮ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ከአዲስ አበባ አስተዳድ ከንቲባ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል::

በጉብኝቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ፣ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ፣ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳለማው፣ የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የከተሞች ባለሙያዎች መሳተፋቸውን መረጃው ጨምሮ ገልጿል::

Читать полностью…

EthioTube

በድርቅ ክፉኛ የተጎዳው የዋግ ኸምራ ዞን አስር ሚሊዮን ብር ገደማ የሚያወጣ ድጋፍ አገኘ።

በአማራ ክልል የሚገኘውና ከትግራይ የሚጎራበተው የዋግ ኸምራ ዞን ከተለያዩ ድጋፍ ሰጭዎች የተገኘ የምግብ እና የሌሎችም ቁሳቁሶች እርዳታ ደርሶታል። ድጋፉን ያስተባበረው የዋግ ኸምራ የልማት ማኅበር ሲሆን ከገንዘብ ደጓሚዎቹ መካከልም የአማራ ባንክ እና የመቄዶንያ የተራድዖ ድርጅት ይገኙበታል።

ድርቅ እጅጉን ከደቆሳቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች መካከል በርካታ የትግራይ ዞኖች እንዲሁም በአማራ ክልል የሚገኙት የዋግ ኸምራ እና የሰሜን ጎንደር ዞኖች ይገኙባቸዋል። በትግራይ ከድርቅ ጋር በተገናኘ በተፈጠረ የምግብ እጥረት እንዲሁም የምግብ እርዳታ በዓለም አቀፍ የረድዔት ድርጅቶች ከመቋረጡ ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት የሚናገሩ ሲሆን ባለፉት ጥቂት ወራት በዚሁ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር ከአንድ ሺህ ያስበልጡታል። በሰሜን ጎንደር እና በዋግ ኸምራ በአስርት የሚቆጠሩ ሰዎች በቅርቡ ህይወታቸው አልፏል ተብሏል። ከዚህም በላይ በሺህ የሚቆጠሩ ከብቶች ሞተዋልም ሲሉ ሹማምንት ይናገራሉ።
የዋግ ኸምራ ዞን አስቸኳይ ድጋፍ የማላገኝ ከሆነ ከፍተኛ ጥፋት ተጋርጦብኛል ሲል የአግዙኝ ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ዞኑ ላይ አተኩሮ የሚንቀሳቀሰው የልማት ማኅበር ጥሪውን መቀበሉን በተግባር አሳይቷል።

በዞኑ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር ከአንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ይልቃል። በዞኑ የሚገኙ አንዳንድ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ሊባል በደረሰ ደረጃ ነዋሪዎቻቸው እርዳታን የሚጠብቁ ሲሆን ድርቁ ተማሪዎችንም ከትምህርት ገበታ ማራራቁ ይዘገባል።
በኢትዮጵያ አንዳንድ ቦታዎች ለአራት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች በበቂ ሁኔታ ባለመዝነቡ እርዳታ ፈላጊዎች በዝተዋል፤ ድርቁ በምስራቅ አፍሪካ የታየው በአስርት ዓመታት ያልታየ የዝናብ እጥረት አካል ነው።

ሌሎች የአገሪቷ ክፍሎች በአንፃሩ ያለወቅቱ የመጣ ዝናብ መብዛት እንዲሁም ከእርሱም ጋር የተያያዘ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት በርካቶች መፈናቀላቸው ይታወቃል። ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት በምስራቃዊው ሶማሊ ክልል ሰዎችን መግደላቸውም ይታወሳል።

Читать полностью…

EthioTube

በትግራይ ሽረ እንዳስላሰ መምህራን ከአንድ ዓመት ለሚልቅ ጊዜ ያልከፈላቸውን ውዝፍ ደምወዝ በመጠየቅ አደባባይ ወጡ።

መምህራኑ ከዚህም በተጨማሪ የግብር ቅነሳ እና የብድር ወለድ ስረዛን ጠይቀዋል።
በትግራይ ጦርነት በተፋፋመባቸው ሁለት ዓመታት በርከት ላሉ ወራት በተለይ የመንግስት ተቀጣሪዎች ደምወዝ እንዳላገኙ ሲገለፅ የነበረ ሲሆን ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተፈርሞ ነገሮች ቀስ ቀስ ወደነበሩበት መመለስ ከጀመሩም በኋላ ያለፈ ክፍያቸውን እንዳላገኙ በመናገር ቅሬታ የሚያሰሙ ብዙሃን ናቸው።

በሽረ እንዳስላሰ ከተማ ለሰልፍ አደባበይ የወጡት መምህራን ቅሬታችንን ስሙ ካሉ ተቀጣሪዎች መካከል ይገኙባቸዋል። መምህራኑ የ2014 እና የ2015 ደምወዞቻችን ይከፈሉን፥ የግብር ዕዳ ይቃለልን፥ ከደደቢት ማይክሮፋይናንስ የወሰድነው ብድር ወለዱ ይሰረዝልን እና የመሳሰሉት ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን ይዘው ነው ለሰልፍ የወጡት።

የችግሮች መደራረብ ኑሯችንን አዳጋች አድርጎታል ሲሉ ምሬታቸውን ያሰሙት መምህራኑ የሚመለከታቸው አካላት መላ ሊሰጡን ይገባል ብለዋል ሲል ክልላዊው ትግራይ ቴሌቭዥን ዘግቧል።
የመምህራኑን ማኅበር በበላይነት የሚመሩት ተክላይ በላይ መምህራኑ ትግራይ ውስጥ የሚታዩ ችግሮች ሰለባ ናቸው ብለዋል ሲል የቴሌቭዥን ጣብያው ጨምሮ ዘግቧል።

በትግራይ የጦርነት መቆም የሚሊዮኖችን ሰቆቃ እጅጉን መቀነሱ የሚታወቅ ቢሆንም በክልሉ ከጦርነት ጠባሳዎች እንዲሁም ከአስከፊ ድርቅ ጋር በተገናኘ ብዙሃን የከፋ ህይወት ውስጥ እንደሚገኝ ይዘገባል። በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በክልሉ ያሉ ሲሆን ከድርቅ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የምግብ እጥረት ቁጥራቸው እያደገ ያለ ነዋሪዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው።

የክልሉ ምጣኔ ኃብት ከማገገም ብዙ ርቆ የሚገኝ ሲሆን በጦርነት የወደሙ በርካታ መሠረተ ልማቶችም ገና ዳግም አልተገነቡም። ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ከወደሙ መሠረተ ልማቶች መካከል ትምህርት ቤቶች ይገኙባቸዋል። ይህም የመማር ማስተማር ሒደትን ሙሉ በሙሉ ለማስቀጠል እንዳይቻል እንቅፋት ከፈጠሩ ምክንያቶች መካከል አንደኛው ሆኗል።

መምህራን እንደበርካታው የክልሉ ነዋሪ ከጦርነቱ ጥላ ለመውጣት የሚያደርጉት ጥረት በአስከፊ የምጣኔ ኃብት እውነታዎች ተተብትቧል።

የትግራይ ቴሌቭዥን የሽረ እንዳስላሰን የመምህራን ሰልፍ አስመልክቶ ያናገራቸው የከተማዋ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የተነሱትን ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ለመፍታት ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሐ-ግብር ያስተናገደው አንድ ክስተት

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ያሰለጠናቸውን እጩ መኮንኖችን ዛሬ ባስመረቀበት መርሐ-ግብር ላይ ተመራቂው ዕጩ መኮንን ተሞሽሯል።

(ምንጭ፡ መከላከያ)

Читать полностью…

EthioTube

ትኩስ ወግ - ክፍል - 3 የዚህ ሳምንት እንግዳችን ከ ቢንያም በለጠ (ዶ/ር) ጋር በሜቄዶንያ ማዕከል ቆይታ አድርገናል ።

https://youtu.be/coPPPQ8yDq0

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጎን እንድትቆም ጠየቀ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የኢትዮጵያ እና የእስራኤል የሺህ ዓመታት የቆየ ወዳጅነት በድጋሚ በማረጋገጥ ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጎን እንድትቆም ጠየቀ

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ከቀናት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከእስራኤል ጎን እንድትቆም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ «ከእስራኤል ፍልስጤም አንፃር ኢትዮጵያ የረጀም ጊዜ አቋም አላት፤ የአፍሪቃ ህብረትንም የሁለት መንግሥታት ዉሳኔን ትደግፋለች፤ በኢትዮጵያ በኩል በጉዳዩ ላይ ክትትል ይደረጋል ኤምባሲዉም የሚከታተለዉ ይሆናል» ሲል ገልጿል።

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ 445 ሚሊዮን ዶላር ባለ 62 ወለል ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ሊገነባ ነዉ

በአረንጓዴ ህንፃ የወርቅ ሰርተፊኬት ደረጃ እየተሰራ እንደሚገኝ የተነገረለት የተቋሙ ዋና መስሪያቤት ዲዛይን ከፀሐይ እና ከንፋስ ኃይል በማመንጨት ለህንፃው ፍጆታ ኃይል ማቅረብ የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እንደሚኖሩት ተነግሯል።

ሜክሲኮ በሚገኘዉ የተቋሙ ቅጥር ግቢ የሚገባዉ ባለ 62 ወለል ህንፃዉ በቀጣይ 4 ዓመታት ዉስጥ እንደሚጠናቀቅ እና ለዚህም 445 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ እንደሚደረግበት ተቋሙ አስታዉቋል።


Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 
Telegram: /channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የኩላሊት ታማሚዋ ሜላት ታሪክ ያልተነገሩ እውነቶቿ እና ያለፉት ውጣወረዶች

ሙሉውን ቪዲዮ ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ https://youtu.be/IZVRQGWAY54

Читать полностью…

EthioTube

🇮🇱 የእስራኤል እና 🇵🇸 የፍልስጤም ሀማስ ጦርነት ዛሬም ቀጥሏል

የአሁኑ ጦርነት ከመቼውም የከፋ ነው የተባለ ሲሆን በዚህ ጦርነት እስካሁን ከ 2ሺ በላይ ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል።

🇮🇱 እስራኤል ፦ 1,200 ሰዎች ሞተዋል። 3,418 ተጎድተዋል።

🇵🇸   ጋዛ ፦ 950 ፍልስጤማውያ ሞተዋል። 5,000 ተጎድተዋል።

በእስራኤል እና ጋዛ ድንበር ቅርብ ርቀት ላይ በነበረ አንድ የሙዚቃ ዝግጅ ላይ ሀማስ በፈፀመው ጥቃት የሞቱ ከ260 በላይ ሰዎች አክሬን መነሳቱ የተነገረ ሲሆን አሁንም ድረስ በሃማስ እጅ የሚገኙ ታፍነው የተወሰዱ ሰዎች አሉ።

ከእስራኤል እና ፍልስጤማውን ባለፈ የአሜሪካን ጨምሮ እስራኤል ውስጥ የነበሩ የሌሎች ሀገራት ዜጎች በሃማስ ጥቃት መገደላቸው ተነግሯል።

2 ሚሊዮን ህዝብ ባለበት በጋዛ ሰርጥ ውሃ፣ ምግብ፣ነዳጅ የለም ተብሏል። ሰዎች መሄጃ አጥተው ተቀምጠዋል።

ሃማስ በእስራኤል ላይ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ጀመርኩ ካለ በኃላ እስራኤል በተለይ በአየር እየወሰደችው ባለው አፀፋ በጋዛ የሚገኙ ህንፃዎች፣ ቤቶች ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።

አንድ የፍልስጤም ጋዜጠኛ ከዚህ ቀደም 6 ጊዜ ያህል በጋዛ የተካሄደ ጦርነት መዘገቡን ገልጾ ይኸኛው እጅግ በጣም የከፋውና ፍፁም ደም አፋሳሽ እንዲሁም ምንም ህግ የሌለበት ነው ብሏል።

እስራኤል በሃማስ ጥቃት ህፃናት እና ሴቶች ሳይቀሩ እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን የገለፀች ሲሆን ሃማስ በተመሳሳይ እስራኤል በምትፈፅመው ድብደባ በርካታ ህፃናት እና ሴቶች መገደላቸውን ገልጿል።

ሀገራት በጦርነቱ የተለያየ አቋም ይዘዋል። አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምዕራባውያን ሀገራት ሃማስን " አሸባሪ " ሲሉ አውግዘው ከእስራኤል ጎን መቆማቸውን ገልጸዋል። አሜሪካ ከድጋፍ ቃል በዘለለ ወታደራዊ ድጋፍም እያደረገች ነው።

ኢራን " እየሩሳሌም እና ፍልስጤም " ነፃ እንዲወጡ ከፍልስጤም ተዋጊዎች ጎን መሆኗን አስረግጣ ተናግራለች። እንደ ሩስያ እና ቻይና ያሉ ኃያላን ሀገራን ጦርነቱ እንዲበርድ ተኩስ እንዲቆም የሚል አቋም ይዘዋል። ቱርክ ይህ አስከፊ ጦርነት ይበርድ ዘንድ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አደርጋለሁ ብላለች።

ሌላው የእስራኤል ጎረቤት ከሆኑት ሌባኖስ (ሂዝቦላህ ቡድን) እንዲሁም ከሶሪያ አቅጣጫ እስራኤል ላይ መሳሪያ የተወረወረ ሲሆን ይህ ጦርነቱን ይበልጥ አስፋፍቶ ሌሎች ሀገራትም ገብተውበት የከፋ ሁኔታ እንዳይፈጠር አስግቷል።

ያም ሆነ ይህ ጦርነቱ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ እርስ በእርስ ከሚፋለሙት የታጠቁ ኃይላት ባለፈ እጅግ  በርካታ ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎችን እያረገፈ ይገኛል።

ምንም እንኳን ጦርነቱ መካከለኛው ምስራቅ ቢገኝም ዳፋው ለዓለም እንዳይተርፍ ይሰጋል። ከወዲሁ ነዳጅ ዋጋው እየናረ ነው።


ምንጭ፦ ቲክቫህ


Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 
Telegram: /channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

አፍጋኒስታን በቀናቶች ልዩነት ዳግም ርዕደ መሬት ተከሰተ

በአፍጋኒስታን ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸው ከተሰማ ከጥቂት ቀናት በኋላ በተመሳሳይ አካባቢ ዳግም ርዕደ መሬት ተከስቷል።

ሁለተኛው ርዕደ መሬት ዛሬ ርዕቡ ማለዳ የተከሰተ ሲሆን፣ የመጀመሪያው መንቀጥቀት ተከስቶ ከፍተኛ ጥፋት ያደረሰው ደግሞ ባለው ቅዳሜ ነበር። የመሬት መንቀጥቀጡ ዋነኛ ማዕከል ኼራት ተብላ ከምትጠራው ከተማ 28 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ ነው።

ዛሬ የተከሰተው የመሬት ነውጥ ያስከተለው የጉዳት መጠን እስካሁን አልታወቀም። ሆኖም በርካቶች በመጀመሪያው መንቀጥቀጥ ምክንያት ቤታቸው በመውደሙ ላለፉት ቀናት ከቤት ውጪ ለመተኛት መገደዳቸው ይታወቃል።

በተጨማሪም ቀደም ባለው ርዕደ መሬት ሳቢያ ለችግር ለተጋለለጡ አፍጋናውያን የሚሆን ብርድ ልብስ፣ የምግብ እና ሌሎች አቅርቦቶች እጥረትም ተከስቷል።የቅዳሜ ጠዋቱ ርዕደ መሬት ኼራት ከተሰኘችው ከተማ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ ዚንዱጃን በተባለች አካባቢ ነበር የተከሰተው።

ከዚንዱጃን የወጡ ምሥሎች እንደሚያሳዩት በአካባቢው ያሉ መኖሪያ ቤቶች የተከሰተውን አይነት ጠንካራን ርዕደ መሬትን መቋቋም የማይችሉ በመሆናቸው ሙሉ በሙሉ ፈራርሰው አሳይተዋል።



Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 
Telegram: /channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በመዲናዋ በሞተር ብስክሌት፣ በባለ አራት እግርና ባለሦስት እግር ባጃጅ እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በከተማዋ በሞተር ብስክሌተኞች፣ በባለ አራት እግር እና ባለሦስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ክልከላ ከዛሬ ማክሰኞ መስከረም 29/2016 ጀምሮ ማንሳቱን አስታውቋል።

ቢሮው ፍቃዱ የባጃጅ አሽከርካሪዎች በቢሮው እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው መስመርና ታፔላ ያላቸው እንዲሁም፤ የሞተር ሳይክሎች በአዋጁ መሰረት ሰሌዳ ወስደው፣ ሕጋዊ መንቀሻቀሻ ፍቃድና ጂፒኤስ(GPS) ያስገጠሙትን ብቻ የሚመለከት መሆኑን ገልጿል።

ከትራንስፖርት ቢሮው ሕጋዊ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሳስቧል።

Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 
Telegram: /channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የእስራኤል እና ፍልስጥኤም ግጭት ተከትሎ ሀገራት መግለጫን አውጥተዋል

🇺🇸የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሃገራቸው ለእስራኤል የምታደርገው ድጋፍ ጠንካራ እና የማይናወጥ ነው ብለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ መርከቦችን እና አውሮፕላኖችን ወደ አካባቢው በማሰማራት ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ወደ እስራኤል እንደምትልክ አስታውቀዋል።

🇬🇧የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ለቤንጃሚን ኔታንያሁ “ጽኑ ድጋፍ” እንዳላቸው ገልፀዋል። "እኛ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። ሽብርተኝነት አያሸንፍም" ሲሉ ተናግረዋል። የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ኢራን የፍልስጤማውያንን ራስን የመከላከል መብት እንደምትደግፍ ገልጸው እስራኤል ባለፉት ዓመታት አካባቢውን አደጋ ላይ በመጣል ተጠያቂ መሆን አለባት ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሃማስ በኢራን እንደሚደገፍ ተመላክቷል።

🇱🇧ሄዝቦላህ የተባለው ኃያል የታጠቀ ቡድን ሲሆን በኢራን ይደገፋል።እሁድ ዕለት ከሊባኖስ በመሆን ከእስራኤል ጋር መድፍ እና የሮኬት ተኩስ ልውውጥ አድርጓል። ይህው የተኩስ ልውውጥ በእስራኤል እና በተቃዋሚ ሀገራት መካከል ሰፊ ግጭት እንዳይፈጠር ስጋት ፈጥሯል።

🇨🇳ቻይና በበኩሏ ሁለቱ ወገኖች “ተኩስ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ” ጥሪ አቅርባለች። ቻይና የፍልስጤም ነጻ መንግስት መመስረትን ጨምሮ "የሁለት መንግስት መፍትሄ" ሀሳብን በድጋሚ አቅርባለች።

🇷🇺 የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "አፋጣኝ የተኩስ አቁም" እና "ሁሉን አቀፍ፣ ዘላቂ እና ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ሰላም" ለማምጣት ድርድር እንዲደረግ ጠቋል።

ምንጭ፦ ዳጉ ጆርናል

Instagram: https://instagram.com/ethiotube 
Twitter: https://twitter.com/EthioTube 
Facebook: https://facebook.com/EthioTube 

Читать полностью…

EthioTube

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ነገ ይጀመራል

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና ከነገ መስከረም 29/2016 ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

ፈተናውን በ2012 የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ የነበሩና መልቀቂያ ፈተናውን ሳይወሰዱ የቀሩ ከ11 ሺሕ በላይ ተማሪዎች እንደሚወስዱት፤ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ተማሪዎቹ በክልሉ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ45 ቀናት በላይ የማጠናከሪያ ትምህርት ሲወስዱ መቆየታቸውንም ቢሮው ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ነገ የሚጀመረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እስከ ጥቅምት 02/2016 ድረስ፤ በኣክሱም፣ በዓዲግራት፣ በመቐለና በራያ ዩኒቨርስቲዎች ብቻ እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡

በትግራይ ክልል በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና በክልሉ በተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ፈተናው ላለፉት ሦስት ዓመታት ሳይሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

Читать полностью…

EthioTube

This week's edition of #Setaweet #MeqenetShow - እውነትን መፈለግና ምላሽ መስጠት በሽግግር ፍትህ

#EthioTube #Ethiopia

https://youtu.be/NkQbhHIBW_g?si=CTzWoOibmAsOF-bK

Читать полностью…

EthioTube

በአቃቂ ቃሊቲ የውሃ ማሞቂያ ፈንድቶ የሦስት ሰዎች ሕይዎት አለፈ

በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የውሃ ማሞቂያ ፈንድቶ የሦስት ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተሰማ፡፡

አደጋው የተፈጠረው ዛሬ ከቀኑ 10:35 ሲሆን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የቀድሞ አቃቂ ጨረቃ ጨርቅ ጊቢ ዉስጥ በሚገኝ ሶሻል ሳሙናና ኘላስቲክ ፋብሪካ ዉስጥ ነው፡፡

በአደጋው የዉሃ ማሞቂያ ቦይለር ፈንድቶ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፥ ለጊዜዉ ቁጥራቸዉ ያልታወቀ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel