ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 22 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 2 , 2024
👉 ሶማሌያ በኢትዮጵያ ላይ ቁጣዋን ገለፀች ፤ በኢትዮጵያ የሚገኘውን አንባሳደሯንም በአስቸኳይ ጠርታለች
👉 የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ 5000 በላይ ሰዎችን አስሪያለሁ አለ ።
👉 በአርባምንጭ አካባቢ የተከሰተው ግጭት አሳሳቢ ደረጃ ስለመድረሱ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/l88HyRdgOpw
ፖሊስ በአዲስ አበባ በዚህ ወር ከ5000 ሰዎች በላይ አስሬያለሁ አለ።
በታህሳስ መጀመሪያ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ባካሄድኩት ዘመቻ ነው ሰዎቹን ያሰርኩት ብለዋል የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ትናንትና በጋራ በሰጡት መግለጫ። በርካታ ኤግዚቢቶችንም አብረን ይዘናል ሲሉ ሁለቱ የፀጥታ አካላት ገልፀዋል።
ታሳሪዎቹ የኅብረተሰብን ሰላም የሚያውኩ የቅሚያ፥ ዝርፊያ እና የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፀም ተጠርጠረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት እንደመግለጫው።
ከዚህም በዘለለ የቁማር ማጫዎቻ ቤቶች እና ሺሻ የሚሸጥባቸው ቤቶች ታሽገዋል፤ ከፍተኛ መጠን ያለው አደንዛዥ ዕፅም በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ።
ሕገ ወጥ የገንዘብ እና የጦር መሳርያ ዝውውርን በተመለከተ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም የፀጥታ አካላቱ የገለፁ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከመቶ በላይ ቁጥር ያላቸው ተንቀሳቃሽ ስልኮች በማስረጃነት ተይዘዋልም ተብሏል።
ከባንኮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ወደተላለዩ ሰዎች ስልክ እየደወሉ ያጭበረብሩ ነበሩ የተባለሉ ሰዎች እንዲሁም ባዕድ ነገሮችን ቀላቅለዋል ተብለው የተጠረጠሩም ከታሰሩት መካከል እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ፖሊስ በዘመቻ ያከናወነው ይህ እርምጃ ምን ያህል ዘላቂ ለውጥ እንደሚያመጣ ወደፊት የሚታይ ሲሆን በቅርብ ጊዜያት ግን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የአደገኛ ወንጀሎች መስፋፋት ስጋት እንደፈጠረባቸው ሲገልፁ መደመጣቸው ብርቅ አይደለም።
#Update
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ፤ ዛሬ በነበረው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ፊርማ ወቅት ፤ ኢትዮጵያ ከስምምነቱ በኃላ " ለሶማሌላንድ ነፃ ሀገርነት እውቅና የምትሰጥ የመጀመሪያዋ ሀገር እንደምትሆን " በምላሹ ደግሞ ሶማሌላንድ ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር እና የባህር ኃይል ቤዝ እንዲኖራት በቀይ ባህር በኩል 20 ኪሎ ሜትር የሆነ መሬት ለኢትዮጵያ በሊዝ እንደምትሰጥ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ኢትዮጵያ ግን የሶማሊላንድን የነፃ ሀገርነት እውቅና እንደምትቀበል በይፋ አላረጋገጠችም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሶማሌላንዱ ፕሬዜዳንት ይህን ጉዳይ ሲናገሩ ከጎን ተቀምጠው የነበረ ቢሆንም ንግግራቸውን አልተቃረኑም።
ከዚህ በተጨማሪ የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ፤ በስምምነቱ መሰረት ሶማሌለንድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ እንደሚኖራት ዝርዝር ነገር ሳይገልጹ ተናግረዋል።
አጠቃላይ የዛሬው ስምምነት ዝርዝር ጉዳይ በአንድ ወር ውስጥ ይፋ ይደረጋል።
ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ለሶስት አስርት ዓመታት ዓለማቀፍ እውቅና ማግኘት ያልቻለች ራስ ገዝ ስትሆን ሶማሊያ ደግሞ አንድ አንድ የራሷ ክልል ነው የምታያት።
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 22 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 1 , 2024
👉 ኢትዮጵያ የ BRICS አባልነቷን ዛሬ በይፋ ጀመረች ።
👉 በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ታጣቂዎች ሰው ገድለው ሁለት ባንኮችን መዝረፋቸው ተነገረ ።
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/TVMRzS88fzU
የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ምዘገባ አላቋረጥኩም ሲል የሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን በኤርትራ ስደተኞች ዙርያ ያወጣውን ሪፖርት ተችቷል።
ከስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጋር የሚከወኑ ሥራዎችን የመፈፀም እና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጠው አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ትናንትና በተጠናቀቀው የፈረንጆች 2023 በድምሩ ከ140 ሺህ በላይ ስደተኞችን መዝግቤያለሁ ብሏል። ባለቀው የፈረንጆች ዓመት ከ26,500 በላይ አዲስ የተወለዱ የስደተኛ ልጆችም ተመዝግበዋል ሲል አክሏል። ይሄንን ያለው ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለይ በአዲስ አበባ የኤርትራ ስደተኞች ምዝገባ መቋረጡ ለተለያዩ የመብት ጥሰቶች አስተዋፅዖ እያደረገ ነው በሚል ላወጣው መግለጫ በሰጠው ምላሽ ነው።
ኢሰመኮ ኤርትራዊያን ስደተኞች በቅርብ ጊዜያት ለዘፈቀደ እስር እና እንግልት እየተጋለጡ ነው ሲልም አክሎ ተናግሮ ነበር። የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ታዲያ ከጎረቤት አገራት ለሚገቡ ስደተኞች ምዝገባ የሚከናወንላቸው በድንበር አካባቢዎች እንጅ በአዲስ አበባ አይደለም ያለ ሲሆን ምዝገባው በመዲናይቱ እንደተቋረጠ ተደርጎ መገለፁ ተገቢ አይደለም ብሏል። በአዲስ አበባ ለሚገኙ ስደተኞች መታወቂያ እና የልደት የምስክር ወረቀት መስጠቴን ቀጥያለሁም ሲል ተናግሯል።
ከወራት በፊት ብሪክስ በሚል ስያሜ ወደሚጠራው በማደግ ላይ ያሉ አገራት ስብስብ የተጋበዘችው ኢትዮጵያ ይፋዊ አባልነቷን ዛሬ ትጀምራለች።
ስብስቤ በፈረንጆቹ 2000ዎቹ ነበር በአንድ ተጀምሎ መጠራት የጀመረው። በቅድሚየም የኢንቨስትመንት ፈንድ ለማቋቋም የፈለጉ ባንከኞች ነበሩ የአራት አገራትን የመጀመሪያ ሆሄያት በመውሰድ ብሪክ የሚል ስያሜ በኢመደበኛነት የፈጠሩት። ብራዚል፥ ሩሲያ፥ ህንድ እና ቻይና ቀዳሚዎቹ አባላትም ነበሩ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት አገር ሆና ቡድኑን ስትቀላቀል ብሪክ የነበረው መጠሪያ ወደብሪክስነት እደገ።
የቡድኑ አባላት ዓመታዊ ስብሰባን የሚያደርጉ ሲሆን ፕሬዚዳንትነትንም እየተቀያየሩ ይወስዳሉ። የዓለም ባንክን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት በምዕራብ አገራት ተፅዕኖ ስር ናቸው እያሉ የሚያማርሩት የብሪክስ አባላት የአዳጊ አገራት ተሳትፎ ከፍ እንዲል ይወተውታሉ።
ከወራት በፊት በደቡብ አፍሪካ በተደረገ ስብሰባው ተጨማሪ ማስፋፊያ ማድፈግን የወጠነው ብሪክስ ኢትዯጵያን ጨምሮ ለስድስት አባላት አገራት የተቀላቀሉን ግብዣ አቅርቦ ነበር። ግብፅ፥ ኢራን፥ ሳዑዲ አረቢያ፥ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና አርጀንቲና ሌሎቹ ጥሪው የደረሳቸው አገራት ነበሩ። አገራቱ በጥሪው ደስታቸውን ገልፀው የነበሩ ቢሆንም ከዚያ በኋላ በተደረገ ምርጫ ያሸነፉት አዲስ የአርጀንቲና ፕሬዚዳንት ሃቭየር ሜሊየ አገራቸው ጥሪውን እንደማትቀበል አሳውቀዋል።
አዳዲሶቹ ዕጩዎች ማኅበሩን አዲስ የምዕራባውያን ዓመት በተጀመረበት በዛሬው ቀን እንደሚቀላቀሉ ተነግሮ ነበር።
በግጭቶች እና በዓለም አቀፉ የኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ምጣኔ ኃብቷ ክፉኛ የደቀቀው ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባልነት ምን ያህል ጥቅም ልታገኝ ትችላለች የሚለው ገና ወደፊት የሚታይ ቢሆንም ባለስልጥኖቿ ማኅበሩን መቀላቀልን እንደትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል አድርገው ማቅረባቸው አልቀረም።
አዳዲሶቹ አባላት በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ በተደረገ የቅድመ ዝግጅት አድራጊ የባለሟሎች ስብሰባ ላይ የተሳተፉ ሲሆን ቀጥሎ በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ በሚደረገው አጠቃላይ ጉባዔ ላይ አገራቱ ሙሉ ተሳትፎ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከእንቅልፉ በድንገት የነቃው የእስራኤል ወታደር ጓደኞቹን ተኩሶ መምታቱ ተገለጸ
ለፍልስጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ ከ83 ቀናት በፊት በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ጦርነት መቀስቀሱ ይታወሳል።
እስራኤል በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ከ21 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ሲገደሉ ከ1ሺህ 200 በላይ እስራኤላውያንም ተገድለዋል።
ወደ ጋዛ እግረኛ ወታደሮቿን ያሰማራችው እስራኤል ከሀማስ ታጣቂዎች ጋር ከባድ ውጊያ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
በእርፍት ላይ የነበረ የእስራኤል ወታደርም ከእንቅልፉ ድንገት በመንቃት አብረውት እረፍት ላይ የነበሩ ወታደሮቹ ላይ መተኮሱን ጀረሰላም ፖስት ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ወታደሩ ከአስፈሪ ቅዠት በመንቃት አጋሮቹ ላይ ተኩሷል የተባለ ሲሆን እስካሁን ቁጥራቸው በይፋ ያልተገለጹ ወታደሮችን አቁስሏል፡፡
ወታደሩ ለቀናት በጋዛ ውስጥ በነበረው ከባድ ውጊያ ውስጥ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ከእንቅልፉ ድንገት በመንቃት ሊተኩስ የቻለው ከነበረበት ከባድ ጊዜ በሚገባ ባለማገገሙ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ይህ ወታደር ወደ አዕምሮ ህክምና ድጋፍ ማድረጊያ ማዕከል ገብቷል የተባለ ሲሆን ምርመራ እና ህክምና ከተደረገለት በኋላ በህግ ይጠየቅ አይጠየቅ የሚባለው ይወሰናልም ተብሏል፡፡
እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን ጦርነት እንድታቆም የተለያዩ ጫናዎች በመደረግ ላይ ሲሆኑ ኢራን እና የየመን አማጺዎች ደግሞ ጦርነቱ ካልቆመ ወደ ጎረቤት ሀገራት ሊስፋፋ እንደሚችል በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡
የሽግግር ፍትሕ ሂደት የጥቃት ሰለባዎችን ያማከለ መሆን አለበት ተባለ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዐዊ መብቶች ፅህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ ባወጡት የዘጠና ገፅ መግለጫ ነው ይሄንን ያሉት። መንግስት የሽግግት ፍትሕ ፖሊሲውን በዓለም አቀፍ የሰብዐዊ መብት ህግጋት ጋር እንዲያጣጥም፥ ለጥቃት ሰላባዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ፍትሕን ማስገኘትን ዓላማ እንዲያደርግ ሁለቱ ተቋማት በመግለጫቸው ጠይቀዋል።
ከሐምሌ 2014 እስካለፈው መጋቢት ድረስ ባለው ጊዜ የተደረጉ አስራ አምስት የማኅበረሰብ ምክክሮች ላይ ተመስርቶ ነው ሪፖርቱ የተጠናቀረው። ምክክሮቹም በትግራይ፥ በአማራ፥ በአፋር፥ በአሮሚያ፥ በሶማሊ፥ በሐረሪ ክልሎች እና በድሬዳዋ አስተዳደር ነው የተካሄዱት ተብሏል። ከስምንት መቶ የሚልቁ ግለሰቦችም ተሳትፈዋል።
በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱበት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ስምምነት ከተቋጨ እና ቢያንስ በትግራይ የጥይት ድምፅ ከቆመ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አለኝ ሲል ቆይቷል።
የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዐዊ መብት ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ከሰላም ስምምነቱ ጋር የሚስማማ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን ለማርቀቅ ተጨባጭ እርምጃ መውሰዷን በመልካምነት አነስተዋል። ነገር ግን ፖሊሲው ከዓለም አቀፍ የሰብዕዊ መብት ህግጋት ጋርም የሚጣጣም መሆን አለበት፤ የጥቃት ሰለባ የሆኑ ማኅበረሰባትን በተለይም ደግሞ ሴቶችን እና ታዳጊ ሕፃናትን ማዕከል ያደረገ ሊሆን ይገባዋል ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
ሪፖርቱ አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋሉ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሔ መስጠት እንዲሁም የተፈናቀሉ ዜጎችን ሰብዐዊ ክብራቸው በተጠበቀ መልኩ ወደቀያቸው መመለስ ትኩረት መስጠት ይገባል ሲል አክሏል።
የኢንተርኔት መዘጋት ከፍተኛ ኪሳራ ያደረሰባቸውን አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ትመራለች ተባለ።
በመጠናቀቀ ላይ ባለው የፈረንጆቹ 2023 የመጀመሪያ አጋማሽ በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ኢትዮጵያ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ አጥታለችም ተብሏል።
ይሄንን ያለው በዲሞክራሲ እና በመብቶች ጥበቃ ላይ የሚሰራው ሴንተር ፎር አድቫንስመትን ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዲሞክራሲ ወይንም በምህፃረ ቃል ካርድ እየተባለ የሚጠራው ተቋም ነው። ተቋሙ ለመረጃው በምንጭነት ቴክ ኔክስት የሚሰኝ በቴክኖሎጂ ዙርያ የሚሰራ ኅትመትን ጠቅሷል።
በዚሁ የጊዜ ክልል በዓለም ዙርያ በአስራ ሦስት አገራት ስድሳ አምስት ኢንተርኔትን የመጠርቀም እርምጃዎች ተወስደዋል ይላል ይህ ተቋም። ከዚህም የተነሳ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር የሚልቅ ኪሳራ አጋጥሟል።
ከፍተኛውን እጦት ያስመዘገበችው ኢትዮጵያ ስትሆን ህንድ እና ፓኪስታን ይከተላታል ተብሏል።
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካታ አጋጣሚዎች የኢንተርኔት አገልግሎትን ያቋረጠች ሲሆን ይህም በመረጃ ነፃነት ተሟጋች ተቋማት ጥርስ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። ካለፈው ክረምት አንስቶ ግጭት ውስጥ በሚገኘው እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት የአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ከተቋረጠ ወራት ተቆጥረዋል።
ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት መቀመጫውን በእንግሊዟ ለንደን ባደረገ ቶፕቴን ቪፒኤን የተባለ ተቋም ይፋ የሆነ ሪፖርት በጦርነት ምክንያት ኢንተርኔት ተቋርጦበት በነበረው ትግራይ ክልል የሚገኙ የንግድ ተቋማት ከ145 ሚሊዮን ዶላር የሚልቅ ገንዘብ በዚሁ ምክንያት ብቻ በአንድ ዓመት ማጣታቸውን ዘግቦ እንደነበር መገልፁ ይታወሳል።
16ዓመት ተፈርዶበታል
በሐዋሳዋ የዳሸን ባንኳ ሰራተኛ ፀጋ በላቸው ላይ የጠለፋ እና አስገድዶ መድፈር ወንጀል በመፈፀሙ የዋስትና መብቱ ተነፍጎ ከሐዋሳ ማረሚያ ሆኖ ችሎቱን ሲከታተል የነበረው እና የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ የሆነው ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደ ማሪያም በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዋለው የወንጀል ችሎት በተከሰሰባቸው ሁለቱም ወንጀሎች ጥፋተኛ ነው ተብሎ በቀን 04/04/2016 መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን በቀን 11/04/2016 የዋለው ችሎት ደግሞ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላ በዛሬው ዕለት ማለትም በ18/04/2016 ዓ.ም ተከሳሹን እጁ ከተያዘበት ጀምሮ በሚቆጠር በ16ዓመት ጽኑ እስራት የቀጣ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የምዕራብ አገራት ኤምባሲዎች በዲፕሎማቶች ላይ የደረሰው ጥቃት አሳስቦናል አሉ።
የአፍሪካ የልማት ባንክ ከፍተኛ ሹሞች የሆኑ ሁለት የውጭ አገር ዜጎች በፀጥታ ኃይሎች ታስረው መደብደባቸው ከተዘገበ እና ባንኩም ዓለምአቀፍ ሠራተኞችን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት ወስኛለሁ ካለ በኋላ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ሦስት የምዕራብ አገር ኤምባሲዎች በጉዳዩ ላይ ኃሳባቸውን ገልፀዋል። የዩኤስ አሜሪካ፥ የካናዳ እና የብሪታንያ ኤምባሲዎች አከታትለው ባወጧቸው መግለጫዎች ከጥቃቱ ጋር ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠይቀዋል።
ሁለቱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ሠራተኞች ለጥቃት የተጋለጡት ከስምንት ሳምንታት በፊት መሆኑ የተዘገበ ሲሆን የባንኩ ላዕላይ ኃላፊዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው እንዳስፈቷቸው በሰፈው መዘገቡ ይታወሳል። ሠራተኞቹም ወዲያውኑ አገር ለቅቀው ሄደዋል። ይሄንን ተከትሎ ባንኩ ከመንግስት በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚደረግና ጥቃቱን ያደረሱ አካላትም ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ቃል የተገባልኝ ቢሆንም ምርመራው ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የማውቀው ነገር የለም ብሏል። ከዚህም ባሻገር ለሠራተኞቼ ደህንነት ምንም ያህል ዋስትና የለኝም በማለት የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ሠራተኞቹ በሙሉ ኢትዮጵያን ለቅቀው እንዲወጡ ወስኗል።
ውሳኔው ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ቀጣይ ግንኙነት እንዲሁም በአገሪቷ ውስጥ ለጀመራቸው እጣ ፈንታ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነውም ተብሏል።
በጉዳዩ ላይ ኃሳቡን ያሰፈረው የአሜሪካ ኤምባሲ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ዙርያ በዓለም ዙርያ የሚተገበረውን እና የቪየና ቃል ኪዳን ተብሎ የሚጠራውን ስምምነት ማክበር እንደሚያስፈልግ አፅንፆት ሰጥቶ ተናግሯል። ጥቃቱ አሳስቦናል፤ ጥፋተኞችም ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባቸዋል ሲልም አቋሙን ገልጿል።
የአፍሪካ ልማት ባንክን በገንዘብ ከሚደጉሙት አገራት መካከል እንገኝበታለን ያለችው ብሪታንያ በበኩሏ በዓለም ዙርያ ያሉ ዲፕሎማቶች ተልዕኳቸውን እንዲወጡ የሚያስችለው የቪየና ቃል ኪዳን ሊከበር እና ሊጠበቅ ይገባዋል ብላለች። በጥቃቱ ዙርያ ጠለቅ እና ዘርዘር ያለ ምርመራ ያስፈልጋል ስትልም ጨምራ አሳስባለች።
የካናዳ መግለጫ ደግሞ ጥቃቱ እስካሁንም እንዳሳሰበን ነው ይላል። ጥቃት አድራሾቹ እስካሁን ተጠያቂ ያለመሆናቸው እጅጉን የሚያስቆጭ ነገር ነው ስትል አክላለች። ባንኩ የውጭ አገር ሰራተኞችን ማስወጣቱ አስደንግጦናል ስትልም ተናግራለች። ዓለም አቀፍ የጥበቃ ቃልኪዳን የሚጣስ ከሆነ ዲፕሎማቶች በአግባቡ መከወን አይችሉምም ብላለች።መግለጫዎቹ እንደሚያሳዩት ጥቃቱ የኢትዮጵያ ገፅታ ላይ ጥላሸት ያሳረፉ ይመስላል። ጥቃቱ ደብዛው ከጠፋቨ አምስት ሚሊዮን ዶላር ጋር የሚገናኝ እንደሆነ የጠቆሙ ዘገባዎች በቅርቡ መውጣታቸው ይታወሳል።
በሰሜን ኢትዮጵያ የቀደሙ ዘመናትን የሚያስታውስ ረሃብ ሊከሰት ይችላል ተባለ። መንግስት በበኩሉ ድርቅ ቢከሰትም ረሃብ የለም ይላል፤ ረሃብ እንዳለ የሚናገሩት ሌላ ዓላማ ያላቸው ወገኖች ነው ሲልም ይከሳል።
በጦርነት ደቅቃ ድርቅ የተደረበባት ትግራይ ክልል በመጓዝ ዘርዘር ያለ ዘገባ የሠራው የካናዳው ስመ ጥር ግሎብ ኤንድ ሜይል ጋዜጣ የረድዔት ድርጅት ሠራተኞችን በመጥቀስ ኢትዮጵያን መጥፎ ስም ያሰጧትን ከአስርት ዓመታት በፊት የተከሰቱትን የሚገዳደር ረሃብ አንዣብቧል ሲል አስጠንቅቋል።
አውዳሚው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ስምምነት ተቋጭቶ ቢያንስ በትግራይ ክልል የተኩስ ድምፅ መሰማት ያበቃ በመሰለባቸው አስራ አራት ወራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በምግብ እጥረት ህይወታቸው አልፏል ጋዜጣው እንደሚለው።
የጭላ በምትባለው ብዙ እርዳታ ጠባቂዎች በተሰባሰቡባት ትንሽ ከተማ በየዕለቱ ምንዱባን የተራድዖ እህል ማከማቻ መጋዘን አጠገብ ይሰባሰባሉ ሲል ያየውን የዘገበው ጋዜጣው አንዳንዶች ደግሞ ከአካባቢው መስተዳደር ፅህፈት ቤት በር ውጭ ይከማቻሉ፤ አንዳንዶቹ እንዲያውም አንዳች ነገር ጠብ ቢል በሚል እዚያው ያድራሉ ሲል አስነብቧል።
በ1977 ገደማ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው ረሃብ ክፉኛ ጡጫውን ካሳረፈባቸው የአገሪቷ አካባቢዎች መካከል አንደኛዋ ትግራይ እንደነበረች ያስታወሰው ዘገባው አሁን ያንዣበበው መዐት ከዚያም ሊከፋ ይችላል ብሏል። በጦርነት ምክንያት የክልሉ ሰብል ማምረቻዎች፥ የጤና ማዕከላት እና የመንግስት ፅህፈት ቤቶች ወድመዋል ወይንም ተዘርፈዋል ያለው ጋዜጣው መልሶ የመገንባት ጥረት ብዙም አይስተዋል ብሏል።
ረሃብን በማስመልከት ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚሰጠው ዘ ፋሚን ኧርሊ ዋርኒንግ ሲስተምስ ኔትዎርክ የተባለው የምርምር ተቋም ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚጀመረው የፈረንጆች 2024 የመጀመሪያ ወራት ረሃብ በትግራይ በሰፊው ሊሰራጭ ይችላል ይላል። የክልሉ ባለስልጣናት 3.5 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ያሻቸዋል የሚሉ ሲሆን ከመካለላቸውም የሚበዙቱ አርሶ አደሮች ናቸው።
የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ከ77ቱም የሚከሰት ረሃብ እየመጣ ነው ሲሉ ለጋዜጣው ነግረውታል፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤትም የቀድሞ ኃላፊም መረጃዎች በሙሉ የሚጠቁሙት ከአርባ ዓመታት ገደማ በፊት የተከሰተውን መዐት የሚገዳደር ቸነፈር እየመጣ መሆኑን ነው ይላሉ።
አንዲት ሴት ለጋዜጣው ዘጋቢ በአዝጋሚ ሞት ውስጥ ነው ያለነው ሲሉ ነግረውታል። ድርቁ እና የምግብ እጥረት በአጎራባች የአማራ ክልል ዞኖች እንደተከሰተም ይዘገባል።
የመንግስት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም ግን በቅርቡ ስለጉዳዩ ሲናገሩ ድርቅ ተከስቶ በርካቶችን ለምግብ እጥረት ቢዳርግም ረሃብ የለም ማለታቸው ይታወሳል። መንግስት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች እርዳታ ለማድረስ ከፍተና ገንዘብ መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እርዳታ ለማድረስ የሚደረግ ጥረትን ማደናቀፉንም ጨምረው ገልፀው ነበር።
የአማራ ክልል ያለመረጋጋት ለጣና ሐይቅም ስጋት ፈጥሮበታል ተባለ።
የክልሉ የኮምኒዩኬሽን ፅሕፈት ቤት የሐይቁ ህልውና ላይ አደጋን ፈጥሮ የነበረውን የእምቦጭ አረምን ለመከላከል ይደረጉ የነበሩ ጥረቶች በፀጥታ ስጋት ምክንያት መታወኩን ገልጿል።
የአገሪቷ ትልቁ ሐይቅ ጣና በወራሪው እምቦጭ አረም ምክንያት በተደጋጋሚ ስጋት የሚፈጥረበት ሲሆን የአካበቢ እና የፖለቲካ ሹማምንት የተለያዩ የማኅበረብ ክፍሎችን በማስተባበር አረሙን ለማጥፋት ሲጥሩ ነበር። ይሁንና እና ከክረምት ወር አንስቶ የተፈጠረው ያለመረጋጋት ይሄንን ማድረግን አዳጋች አድርጎታል።
ክልሉ ለስድስት ወራት በታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በተለይ በትንንሽ ከተሞች እና በገጠር ቀበሌዎች እስካሁንም በሚዘገቡ ግጭቶች ምክንያት ቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፈታኝ ሆኗል።
የክልሉ መንግስት አሁን እንደሚለው ባለፉት ጥቂት ወራት የመከላከል እርምጃ በበቂ ሁኔታ ባለመወሰዱ የእምቦጭ አረም ክፉኛ ተስፋፍቶ ይገኛል።
ሁኔታው አሳሰቢ ነው ያለው የክልሉ የኮምኒዩኬሽን ቢሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ አለባቸው ብሏል።
መነሻው ከወደ ደቡብ አሜሪካ ሳይሆን አይቀርም ተብሎ የሚጠረጠረው አምቦጭ በኢትዮጵያ የውሃ አካላትን ከሚወርሩ ከሰላሳ የሚልቁ አረሞች መካከል አንዱ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በጣና ሐይቅ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የውሃ አካላት ላይ ተስተውሎ እንደነበር ሲዘገብ ቆይቷል።
በቦረና ያቤሎ አጠቃላይ ሆስፒታል መንታ ልጆች ተጣብቀው መወለዳቸው ተገለፀ።
ቦረና በሚገኘው ያቤሎ አጠቃላይ ሆስፒታል ሁለቱም ወንድ የሆኑ መንትያ ልጆች ተጣብቀው መወለዳቸው ሲገለፅ የልጆቹ እናት በምስራቅ ቦረና የዋጪሌ ወረዳ ነዋሪ ናት ተብሏል።
ያቤሎ አጠቃላይ ሆስፒታል የጽንስና ማህፀን ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ዋርዮን ፥ የተወለዱት ህፃናት በልባቸው አካባቢ ተጣብቀው መወለዳቸውን የገለፁ ሲሆን የህፃናቱ የትኛው ክፍል መተሳሰሩን ለማጣራት ምርመራ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
ዶ/ር ዋርዮን የህፃናቱ ጉዳይ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ የሚሆን ከሆነ በሀገሪቱ በሚገኙ ትልልቅ የህክምና ሆስፒታሎች ሊታዩ እንደሚችሉ አስረድተዋል።
ተቃዋሚው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የመንግስት ኃይሎች እህል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ ሰላማዊያንን ገድለዋል አለ።
በውንጀላው ዙርያ ከመንግስት በኩል የተሰማ ነገር የለም። ኦነግ ግድያው ተፈፅሟል ያለው በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኘው በሆሮ ጉድሩ አካባቢ ሲሆን አካባቢው በአየር ጥቃት እና በከባድ መሳርያ ተደብድቧል ሲልም አክሏል። በሦስት ዙር ተከናውኗል ባለው ጥቃት ከንፁሃን ዜጎች በተጨማሪ እንስሳትም ተገድለዋል ፓርቲው እንዳወጣው መግለጫ። በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈ ስምንት ሰዎችን ለይተናል ያለው ኦነግ ተገድለዋል ያላቸውን እነዚሁ ሰዎች በስም አስቀምጧል። ከዚህም በተጨማሪ በጥቃት ቁስለኛ ሆነዋል ያላቸውን ሁለት ሰዎች ስምም ጨምሮ በመገለጫው አካትቷል።
ኦነግ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ኃላፊነት የጎደለው እርምጃ እየወሰዱ ነው ያለ ሲሆን ይህንንም በፅኑው አውግዛለሁ ብሏል። በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች በሰው ደም እየተጫወተ ነው ሲልም በመግለጫው የሰላ ትችትን ሰንዝሯል። በገዥው ብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት የንፁሃን ሰዎችን መብት መጣስን የቀን ተቀን ሥራው አድርጎታል ያለው ኦነግ በዚህም ምክንያት የንብረት ዝርፊያ፥ የጅምላ እስር፥ ግድያ እንዲሁም የቤቶች መቃጠል የሰርክ ተግባር ሆኗል ብሏል። የኦሮሞ ሕዝብ እና ሌሎችም ብሔር ብሔረሰቦች ጭቆናን መታገል አለባቸው የሚል ጥሪም አሰምቷል።
መንግስት ባልታጠቁ ሰዎች ላይ እርምጃ አዘውትሮ መውሰዱ የቀቢፀ ተስፋ ምልክት ነው ሲልም ገልጿል። በሆሮ ጉደሮ የድሮን ጥቃት ሳይደርስ እንዳልቀረ እና የአንድ ፕሮቴስታንት ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ ዜጎች የቤተ ክርስትያኗን እህል በመሰብሰብ ላይ እያሉ የጥቃት ሰለባ ስለመሆናቸው የዘገቡ የብዙሃን መገናኛዎች ነበሩ።
መንግስት ከዚህ የኦነግ መግለጫ ጋር በተያያዘ እስካሁን የሰጠው ምላሽ ባይኖርም ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት ያደርሳል በሚል የቀረቡበትን ውንጀላዎች እንዳጣጠለ አይዘነጋም። በኦሮሚያ ክልል ሸኔ እያለ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን ላይ ግን እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ይገልፃል።
ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው እና ከኦነግ ተሰንጥቆ የወጣ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ታጣቂ ቡድን በአገሪቱ ህግ በሽብርተኛነት የተፈረጀ ነው። ከቡድኑ ጋር መንግስት በታንዛኒያ በሁለት ዙር ድርድር ሲያደርገው የነበረው ድርድር ያለውጤት ከተበተነ በኋላ በኦሮሚያ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ግጭቶች መጠናከራቸው ይዘገባል። ቡድኑ ራሱ ካለፈው መስከረም አንስቶ ከመንግስት ጋር አድርጌያቸዋለሁ ያላቸውን ፍልሚያዎች የዘረዘረ ሲሆን በሕዳር እና በታህሳስ ወሮችም ግጭቶች እንደነበሩ ተናግሯል።
የአገር መከላከያ ሠራዊት በቅርቡ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ማለቱ አይዘነጋም። በእነዚህ እርምጃዎችም ቁጥራቸውን በግልፅ ያልጠቀሳቸውን የቡድኑን አባላት መግደሉን እና መማረኩን ተናግሯል። የግጭቶች መቀጠል በመኃል የሰላማዊ ዜጎችን ቁምስቅል ያበዛል የሚል ስጋት አይሎ አለ።
ሶማሊያ አምባሳደሯን ከኢትዮጵያ ጠራች።
ሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የተፈራረሙት ሰነድ ህጋዊ ቅቡልነት የሌለው እና የማይሰራ ነው ብላለች።
ኢትዮጵያ እና ራሷን እንደነፃ አገር የምትቆጥረው ሶማሊላንድ በባህር ዳርቻ አጠቃቀም ዙርያ የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረሙ በኋላ በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለው ግንኙነት በፍጥነት መበላሸት የያዘ ይመስላል። ሶማሊላንድን እንደራሷ ግዛት የምትቆጥረው ሶማሊያ ያለዕውቅና ማንም የውጭ አገር መንግስት ሊያናግራት አይችልም ባይ ናት።
ከዚህም በዘለለ ሃያ ኪሎ ሜትር ገደማ የባህር ዳርቻ ለኢትዮጵያ ያስገኛል የተባለው ስምምነት ሉዐላዊነትን እና የግዛት አንድነትን የሚጥስ ነው ብላለች። ዛሬ የአገሪቱ ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገ ሲሆን ከስብሰባው በኋላ መግለጫ የሰጡት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ የመንግስታቸውን አቋም ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ያፈጠጠ ያገጠጠ ፀብ አጫሪነት ፈፅማብኛለች ያለችው ሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትሯ የአገራቸው ሕዝብ እንዲረጋጋ ተማፅነዋል። በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ዕውቅና እንደምትሰጥ የሶማሊላንድ መንግስት ቢገልፅም በኢትዮጵያ በኩል ስለዚህ በግልፅ የተባለ ነገር የለም። ሶማሊያ ከዚህም በተረፈ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት በጉዳዩ ላይ እንዲመክሩ ጠይቃለች።
በአርባ ምንጭ ዙርያ የተከሰተው ግጭት ትኩረት ይሻል ሲል የሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን አስጠነቀቀ።
መንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ግጭት ተከስቷል፥ ውጥረትም ነግሷል ያለ ሲሆን ይህም ሳይባባስ በፊት አስቸኳይ እርምጃ ያሻል ብሏል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ሰብዐዊ እርዳታ ይሻሉ፥ ለነዋሪዎች ዘላቂ ሰላም መመለስ አለበት ሲልም ገልጿል።
ግጭት እና ውጥረት የተነሳው ከአስተዳደራዊ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ነው ያለው ኢሰመኮ በአካባቢው ዓመታትን ያስቆጠረ ውዝግብ መኖሩን አንስቷል። የአካባቢው ነዋሪዎች የአገሪቱን ገዥ ፓርቲ የሚፎካከር የፖለቲካ ፓርቲ በመምረጣችን ለሰብዐዊ መብት ጥሰት ይደርስብናል ሲሉም ያማረራራሉ ብሏል ኢሰመኮ። የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ የአካባቢ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ መንግስት ስፍራውን ማስተዳደር የለበትም በሚል ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ችግር እየፈጠሩ ናቸው ይላል።
ኢሰመኮ በአካባቢው እየተፈጸሙ ያሉ መብቶች ጥሰቶች ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገሩ፤ የተፈጠሩ አለመግባባቶች ሕጋዊና ሰላማዊ መንገድን ተከትለው እንዲፈቱ ለአካባቢው የመንግሥት አስተዳደር፣ ለአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች እና ለፖለቲካ ፓርቲዎች ምክረ ሐሳብ እያቀረብኩ ሁኔታው ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ ብሏል።
ይሁን እንጅ በተለይ ከወርሃ ጥቅምት አንስቶ የአንድ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ከዋለ በኋላ መሞቱን ተከትሎ ውጥረት ተባብሷል ብሏል የኢሰመኮ መግለጫ። ከዚህም በኋላ በግለሰቦች እና በቡድኖች በደረሱ ጥቃቶች የሙዝ እርሻዎች የመንግስት አገልግሎት ሰጭ መስሪያ ቤቶች ወድመዋል፤ በግለሰቦች እና በፀጥታ አካላት እርምጃዎች እየተወሰዱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል እንዲሁም ቆስለዋል እንደመግለጫው። ሪፖርት እስካጠናቀርኩበት ጊዜ ድረስ ውጥረት ቀጥሏል ያለው ኮሚሽኑ አፋጣኝ እርምጃ እንዲደረግ ተማፅኗል።
የኢትዮጵያ የወደብ ፊርማ በሶማሊያ ቁጣ ቀስቅሷል።
ኢትዮጵያና ራሷን ነፃ አድርጋ የምትቆጥረው ሶማሊላንድ አድርገውታል የተባለው የመግባቢያ ስምምነት ለኢትዮጵያ 20 ኪሎሜትር ገደማ የባህር ዳርቻ እንደሚያስገኝላት ከተሰማ በኋላ በርካታ የሶማሊያ ፖለቲኞች እና ስመ ጥር ግለሰቦች ቁጣቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
ሶማሊያ ሶማሊላንድን የግዛቴ አካል ናት ብላ የምትቆጥራት ሲሆን ያለ እኔ ዕውቅና ንግግር መደረጉ ሉዐላዊትን የሚጥስ ነው በሚል ነው በርካታ ሶማሊያውያን የተበሳጩት።
የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት እና በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቀዳሚ የስልጣን ዓመታት የቅርብ ወዳጃቸው የነበሩትን መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ኤክስ በተባለው የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሰነድ ለሶማሊያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ በጠቅላላ ስጋትን የሚፈጥር ነው ብለውታል። ፋርማጆ ቀጥለውም ሉዐላዊነትን እና የግዛት አንድነትን ማክበር የቀጠናዊ መረጋጋት እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙነት መሠረት ነው ያሉ ሲሆን የአገራቸው መንግስት በተገቢው አኳኋን ምላሽ እንዲሰጥ ጥያቄ ሰንዝረዋል።
የሶማሊያ ካቢኔ በበኩሉ ዜናው እንደተሰማ ብዙም ሳይቆይ ነበር አስቸኳይ ጉባዔ የጠራው።
ከካቢኔው አባላት አንዱ የሆኑት የአገሪቱ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ኃብት ሚኒስትር አብዲሪዛቅ መሃመድ “ሶማሊያ አትከፋፈለም፤ ሉዐላዊነቷ እና የግዛት አንድነቷ ለድርድር አይቀርብም” ሲሉ ቆጣ ያለ መልዕክት በዚሁ የማኅበራዊ የትስስር መድረክ ላይ አስፍረዋል። አክለውም ኢትዮጵያ ከክፍለ ሃገር መሪ ጋር ሰነድ መፈራረም እንደማትችል ጠንቅቃ ታውቃለች፤ የግዛት አንድነታችንን የመጣስ ፈቃድ የሰጣትም የለም ሲሉ አስፍረዋል።
ለወትሮው በተቃራኒ ወገን ቆመው የሚፋለሙት የአገሪቱ የመንግስት አካላት እና የታጣቂው ቡድን አል-ሸባብ በዚህ ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም ያንፀባረቁ መስሏል። በበርካታ አገራት በሽብርተኛነት የተፈረጀው አልሸባብ በቃል አቀባዩ በኩል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቱ ህገ ወጥ እና የማይሰራ ነው ማለቱን የአገሪቱ የብዙሃን መገናኛዎች ተናግረዋል። ታጣቂው ቡድን ጉዳዩን እንፋለማለን ሲል መዛቱም አብሮ ተዘግቧል።
ሶማሊያ በሶማሊላንድ ጉዳይ የሾመቻቸው ልዩ ወኪል አብዲካሪም ሁሴን ጉሌድ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና የህግ ማዕቀፍን በዘፈቀደ ጥሷል ሲሉ ወንጅለውታል።
ስምምነቱን እንደትልቅ ስኬት ተደርጎ በኢትዮጵያ በኩል ቢቀርብም ስለዝርዝር ይዘቱ ግን የተሻለ መረጃ የተገኘው ከሶማሊላንድ ወገን ነው። የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ እና የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የመግባቢያ ሰነዱ ኢትዮጵያ 20 ኪሎ ሜትር የሚዘረጋ የባህር ዳርቻን ለመጠቀም ለሃምሳ ዓመታት ያህል መከራየትን እንደሚጨምር ገልጿል። በምላሹ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ይፋዊ ዕውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሃገር ትሆናለች።
ሶማሊላንድ በአፍሪካ ኅብረትም ሆነ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋዊ ዕውቅና የላትም። ጉዳዩን ወደተባበሩት መንግስታት ድርጅት ብትወስድ እንኳ የራሷ ራስ ገዝ ግዛት ታይዋን ጋር ንትርክ ያለባት ቻይና እርምጃዋን ክፉኛ እንደምትቃወመውና ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ውድቅ እንደምታደርገው ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ዘርዘር አድርጋ ያለችው ነገር የለም። ብሉምበርግ የተባለው ዋነኛ ትከረቱን በንግድ ጉዳዮች ያደረገ የብዙሃን መገናኛ ኢትዮጵያ ከአየር መንገዷ ድርሻ እንደምታገኝ ቢገልፅም ስለዚሁ ጉዳይ በሶማሊላንድ መንግስት መግለጫ የተባለ ነገር የለም። ብሉምበርግ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ የሆኑትን ሬድዋን ሁሴንን ጠቅሶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዘርዘር ያለ ንግግር እንደሚደረግ ዘግቧል።
የመግባቢያ ሰነድ ህጋዊ አሳሪነት የሌለው ውል ሲሆን ወደተግባር እንዲገባ ህጋዊ ቅቡልነት ያለው ስምምነት መፈረም የግድ ይላል።
#ሰበር_ዜና
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል።
ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡
የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር እና የአጋርነት መግባቢያ ሠነድ በተለያዩ ዘርፎች በቀጣይ ለሚኖራቸው ግንኙነቶች ማዕቀፍ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽኅፈት ቤት ይፋ ባደረገው መረጃ አሳውቋል።
የመግባቢያ ሠነዱ ፦
* የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት ዕውን የሚያደርግ ፣
* የባሕር በር አማራጮቿን የሚያሠፋ
* የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ ፣ የዲፕሎማሲ ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናከር ነው ብሏል።
በተጨማሪም ሠነዱ ሀገራቱ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲው ዘርፍ የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚጎለብትበትን አካሄድ የሚያካትት መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጥቶ መቀበል መርኅ እና ሀገሪቷ ለጋራ ጥቅም ከጎረቤቶቿ ጋር የመሥራት ፍላጎት እና አቋሟን መልሶ የሚያጸና እንደሆነም አመላክቷል፡፡
ሠነዱ ፤ አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እና ለአፍሪካ ቀንድ ትሥሥር የላቀ ፋይዳ ያለው መሆኑን ጠቁሟል።
የሱዳን የሲቪሎች ጥምረት የበላይ እና የፈጥኖ ደራሹ ኃይል አለቃ በአዲስ አበባ ይገናኛሉ።
አገሪቱ በጦርነት መናጥ ከጀመረች በኋላ መላ ለማፈላለግ ከተወሰዱት እርምጃዎች አንዱ የሆነው የሲቪሎች ጥምረት በቀድሞው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ይመራል። በሐምዶክ እና ከሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች አንደኛው የሆነው የፈጥኖ ደራሹን ኃይል በሚመሩት ጄነራል ዳጋሎ መካከል የሚደረገው ስብሰባ መቀመጫ እንድትሆን አዲስ አበባ ተመርጣለች።
በጄኔራሉ እና በተፎካካሪዎች የሱዳን ጦር መሪ ጄኔራል አል ቡርሃን መካከል ከሰሞኑ በጅቡቲ ውይይት ይደረጋል ተብሎ የነበረ ሲሆን የጅቡቲ ባለስልጣናት የሁለቱ መሪዎች ግንኙነት መራዘሙን ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርገዋል። ይሄንን ተከትሎም ሃሜቲ በሚል ቅፅል ስማቸውም የሚጠሩት ጄኔራል ዳጋል በምስራቅ አፍሪካ ባሉ የተለያዩ አገራት እየተዘዋወሩ የአካባቢውን ፖለቲከኞች ማግኘት ላይ አተኩረዋል።
ወደካምፓላ አቅንተው የአገሪቱን መሪ ዩዌሪ ሙሴቪኒን ካገኙ በኋላ ወደኢትዮጵያ በመምጣት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተዋል። ከዚያም ወደጅቡቲ አምርተው ኢስማዔል ኦማር ጌሌ ጋር መክረዋል። አሁን ደግሞ ወደአዲስ አበባ ተመልሰው ከስልጣናቸው ከፈነቀሏቸው ሃምዶክ ጋር የሚወያዩ ይሆናል። ሃምዶክ የሱዳን ሕዝባዊ ተቃውሞ የአገሪቱ የረጅም ዘመን መሪ ኦማር አልበሽርን ከስልጣን ከገረሰሰ በኋላ የተቋቋመው የሲቪል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። ይሁንና አሁን በጠላትነት ጦር የተማዘዙት ጀኔራሎች ተባብረው ከስልጣን ካባረሯቸው በኋላ አገሪቷን ለሁለት ማስተዳደር ጀምረው ነበር። ባለፈው ዓመት አጋማሽ ገደማ ግን ጄኔራሎች አገሪቷ መከተል አለባት ብለው በሚያስቡት አቅጣጫ የተነሳ አልስማማ ብለው አገራቸውን ወደጦርነት እሳት ከትተዋል። ጄኔራል አል ቡርሃን የሱዳን የነፃነት ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ተቀናቃኛቸውን ጄኔራል ዳጋሎን እያስተናገዱ ያሉ የምስራቅ አፍሪካ አገራትን በአገራችን ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ነው ሲሉ ወርፈዋቸዋል።
ለወትሮውም ከአል ቡርሃን ጋር ጥሩ ግንኙነት የላትም የምትባለው ኢትዮጵያ ታዲያ ዳጋሎን ከሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ አስተናግዳቸዋለች። በሃምዶክ እና በሃሜቲ መካከል የሚደረገው ውይይት ሰላማዊ ዜጎችን ከጥቃት በመጠበቅ፥ የሰብዐዊ እርዳታ በአግባቡ እንዲሰራጭ በማስቻል እንዲሁም ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ የሚፈታበትን መንገድ በማፈላለግ ላይ እንደሚያተኩር የሲቪል ጥምረቱ ገልጿል። በሱዳን ጦርነት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከሰባት ሚሊዮን የሚበልጡት ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ይሄንንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት “የዓለማችን ትልቄ የመፈናቀል ቀውስ” ሲል ጠርቶታል።
በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ታጣቂዎች ሰው ገድለው ሁለት ባንኮችን ዘረፉ።
ዘረፋው የተፈፀመባቸው የአዋሽ እና የንግድ ባንኮች ሲሆኑ ፖሊስ ጣብያም መቃጠሉ ነው የተዘገበው ፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በክልሉ ምዥጋ ወረዳ ሰርገው በመግባት ጥቃት የሰነዘሩ ሲሆን ሶጌ በምትባል በወረዳው በምትገኝ ከተማ በደረሰው ጥቃት ቢያንስ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው አስተዳደር ገልጿል።
የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ የወረዳው ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ለጥቃቱ መንግስት ሸኔ ሲል የሚጠራውን በአብዛኛው በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀስ ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል ብሏል። ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሚለው ይሄው ቡድን ግን በጉዳይ ላይ እስካሁን ያለው ነገር ስለመኖሩ አልተዘገበም። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኛነት የተፈረጀው ይሄው ቡድን ከመንግስት ጋር በሁለት ዙሮች ያደርገው ድርድር ሳይሳካ መበተኑ ይታወሳል። ይሄንን ተከትሎም በተለይ በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች ተፋፍመዋል፤ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችም ዳግም አንሰራርተዋል።
ጥቃት ባስተናገደችው የቤንሻንጉል-ጉምዝ ከተማ አካባቢ ይገኙ የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች ለግዳጅ ወደሌላ ስፍራ መንቀሳቀሳቸውን ተክተሎ ታጣቂዎቹ ለመግባት ብዙም አልከበዳቸውን የተባለ ሲሆን ለሰዐታትም በከተማዋ ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብሏል። ከባንክ ዝርፊያ በተጨማሪም የፖሊስ ጣብያ እና በርካታ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውም አብሮ ተዘግቧል።
ታጣቂዎቹ ወደከተማዋ አርብ ዕለት ከገቡ በኋላ ብዙ ተኩስ በመኖሩ ሰላማዊ ነዋሪዎች ለሽሽት ተዳርገው የነበረ ሲሆን በማግስቱ ግን መረጋጋት መመለሱንና ይሄንንም ተከትሎ ነዋሪዎች መመለሳቸውን ዘገባው አመላክቷል።
መንግስት በተዳጋጋሚ በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌ አንፃራዊ መረጋጋት ተመልሷል ሲል ይደመጣል፤ ይሁንና መሰል ጥቃቶች አልፎ አልፎ መሰማታቸው አልቀረም።
ኢትዮጵያ፦ የእለተ አርብ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 19 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - December 29 , 2023
👉 የመብቶች ተሟጋቹ ኢሰመጉ በታጣቂዎች ለሚደርሱ ጥቃቶች መንግስት ተገቢ ትኩረት እየሰጠ አይደለም ሲል ከሰሰ።
👉 የሽግግር ፍትሕ ሂደት የጥቃት ሰለባዎችን ያማከለ መሆን አለበት ተባለ።
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/7DRPCvX1imI
የመብቶች ተሟጋቹ ኢሰመጉ በታጣቂዎች ለሚደርሱ ጥቃቶች መንግስት ተገቢ ትኩረት እየሰጠ አይደለም ሲል ከሰሰ።
በኦሮሚያ ክልል አርሲ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ተከስተዋል የተባሉ ጥቃቶችን አስመልክቶ መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥቃቶች ከግድያ እና ከአካል ጉዳት በተጨማሪ የንብረት ውድመትን፣ መፈናቀልን እንዲሁም ሌሎች “መጠነ ሰፊ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን” እያስከተሉ ነው ሲል ገልጿል።
ከተቋቋመበት 1984 ዓ.ም አንስቶ ኢሰመጉ ለ154ኛ ጊዜ ባወጣው በዚሁ መገለጫ በተለይ ማንነት ላይ ያነጠጠሩ ጥቃቶች ከሚደርሱባቸው ክልሎች አንዱ ኦሮሚያ ነው ብሏል። ለሚደርሱ ጥቃቶችም ዘላቂ መፍትሔ መሰጠት አልሰተቻለም፤ እንዲሁም መንግስት የዜጎችን ደህንነት በተገቢው ሁኔታ ማስጠበቅ ብሎም ሰብዓዊ መብቶቻቸውን ማስከበር አልቻለም ሲል ኢሰመጉ ይወነጅላል።
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በተለይም ጢጆ ለቡ፥ ሔላ ጢጆ ሴሮ እና በሮቤ እንደቶ ወደተባሉ ቀበሌዎች ባለሞያዎቼን አሰማርቼ ነበር የሚለው ኢሰመጉ በዚህም በወርሃ ሕዳር ሁለተኛ አጋማሽ የተከሰቱ የመብት ጥሰቶችን መርምሬያለሁ ብሏል በመገለጫው።
ይሁን እንጅ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሜ ወረዳ ማልኢኩ መንደር በሕዳር አጋማሽ የተከሰተ በወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ላይ ደርሷል የተባለን ጥቃት ለመመርመር ፈልጌ በፀጥታ ችግር ምክንያት ወደስፍራው ማቅናት ሳልችል ቀርቻለሁ ብሏል።
በአርሲ ዞን በደረሱት ጥቃቶች 53 ሰዎች ተገድለው የነበረ ሲሆን ሁለት ደግሞ ቆስለዋል ሲል ኢሰመጉ በምርመራው ደርሼበታለሁ ያለውን አስፍሯል። በጥቃት ህይወታቸውን ያለፈውን ሰዎች ስም እና ዕድሜ ዘርዝሮ አቅርቧል። ሪፖርቱን በፎቶዎችም ደግፏል። ከሟቾች እና ከቁስለኞች በተጨማሪ በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል ሲል አክሏል። ጥቃቶቹን በተመለከተ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት ኮሚሽን፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እንዲሁም ልዩ ልዩ የብዙሃን መገናኛዎች መዘገባቸው ይታወሳል።
በወቅቱ መንግስት ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በሚል የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን ወንጅሎ ነበር። መንግስት ሸኔ በሚል ስም የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በአገሪቱ ፓርላማ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀ ሲሆን ውንጀላውን አጣጥሎ ነበር።
ኢሰመጉ በቄለም ወለጋ ቤተ ክርስትያን ላይ በደረሰው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል ያላቸውን ዘጠኝ ስም ዘርዝሮ አቅርቧል።
የመብት ተሟጋቹ ከዚህም በዘለለ በኦሮሚያ ክልል አውራ ጎዳናዎች ላይ እና በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች እገታ እየተለመደ የመጣ የመብት ጥሰት ነው ያለ ሲሆን ይህንን አስመልክቶ በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ባሰማም መንግስት ለእዚህ ድርጊት ተገቢው ትኩረት እና ህጋዊ ዘላቂ መፍትሄ አልሰጠም፤ ይሄንን ተከትሎም ድርጊቱ በተጠናከረ መልኩ እየቀጠለ መገኘቱ የሚያሳስበው መሆኑን መግለጽ ይወዳል።
የኢሰመጉ መግለጫ ለክልሉ እና ለፌዴራል መንግስት ደህንነት ማስጠበቅ መብት እንዲያሰክብሩ፥ ጥቃት ያደረሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል። የመብት ጥሰት የተፈፀመባቸው አካላት ከፍትህም ባሻገር ካሳም ይሻሉ ሲል ጨምሮ ተናግሯል።
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሀሙስ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 18 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - December 28 , 2023
👉 የምዕራብ አገራት ኤምባሲዎች በዲፕሎማቶች ላይ የደረሰው ጥቃት አሳስቦናል አሉ።
👉 በሰሜን ኢትዮጵያ የቀደሙ ዘመናትን የሚያስታውስ ረሃብ ሊከሰት ይችላል ተባለ።
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/PLoluTYYFi0
ኤርትራዊያን ስደተኞች በዘፈቀደ እየታሰሩ ነው ተባለ።
የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በፀጥታ ኃይሎች ያለአግባብ እየተያዙ ሲሆን ባለፉት ሦስት ዓመታት በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ምዝገባ ያለመካሄዱ ለችግሩ አስተዋፅዖ አድርጓል ብለዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ዘገባ የሠሩት የዓለም አቀፍ የብዙሃን መገናኛዎች ያነጋገሯቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ኤርትራዊ ስደተኞች በፀጥታ ኃይሎች በዘፈቀደ የመያዝ ስጋት እንዳለባቸውና አንዳንድ ጊዜም በፖሊሶች ታስረው ከአጭር ጊዜ በኋላ እንደሚለቀቁ ተናግረዋል።
ኢሰመኮ የስደተኞች ምዝገባ በአስቸኳይ እንዲጀመር ማሳሳቢያ ያቀረበ ሲሆን የስደተኞች ጥበቃ አደጋ ውስጥ ገብተዋል ሲል ተናግሯል።
ኢትዮጵያ ለዓመታት ያህል በግዛቷ ለውጭ አገር ስደተኞች እና ጥገኝነት ፈላጊዎች አስተማማኝ ከለላ መስጠቷ የኩራት ምንጭ ሆኖላት ቆይቷል። ከጎረቤቶቿ በተለይም ከኤርትራ፥ ከሶማሊያ እና ከደቡብ ሱዳን የሚመጡ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞችን በልዩ ልዩ ካምፖች የምታስተናግድ ሲሆን ከስደተኞች መካከል የተወሰኑት ከካምፕ ውጭ ሆነው ከማኅበረሰብ ጋር በመቀላቀል እንዲኖሩ የሚያስችል አሰራር አላት። ከዚህ አሠራር ጋርም በተያያዘ ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን በልዩ በልዩ ከተሞቸ በተለይም በአዲስ አበባ እንደሚገኙ ይነገራል።
ይሁንና በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት የስደተኞች ደህንነት ላይ ስጋትን ጥሎ ቆይቷል። በትግራይ ክልል ውስጥ የነበሩ የኤርትራ ስደተኞች መቆያ ጣብያዎች ወደጎረቤት አማራ ለመዛወር የተገደዱባቸው አጋጣሚዎች ሲኖሩ ስደተኞች ለተወሰነ ጊዜ እርዳታ ተቋርጦባቸውም ቆይቷል።
ከዚህም ባለፈ የአስመራን መንግስት ወይንም አስገዳጅ የብሔራዊ ውትድርናን ሸሽተው ኢትዮጵያ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል የተወሰኑትን ተይዘው ወደኤርትራ መመለሳቸውም ተዘግቧል።
መቀመጫውን በፈርንሳይ መዲና ፓሪስ ያደረገው እና በኤርትራ መንግስት ላይ የቅዋሜ ድምፅ የሚያሰማው ሬዲዮ ኤረና በአዲስ አበባ የፀጥታ ኃይሎች በህጋዊ መልኩ ወደአገሪቱ የገቡ ኤርትራዊያንን ጭምር እያሰሩ ነው ሲል ይወነጅላል። በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ወገን የተሰማ አስተያየት ግን እስከ አሁን የለም።
በሰሜን ኢትዮጵያ የቀደሙ ዘመናትን የሚያስታውስ ረሃብ ሊከሰት ይችላል ተባለ።
መንግስት በበኩሉ ድርቅ ቢከሰትም ረሃብ የለም ይላል፤ ረሃብ እንዳለ የሚናገሩት ሌላ ዓላማ ያላቸው ወገኖች ነው ሲልም ይከሳል።
በጦርነት ደቅቃ ድርቅ የተደረበባት ትግራይ ክልል በመጓዝ ዘርዘር ያለ ዘገባ የሠራው የካናዳው ስመ ጥር ግሎብ ኤንድ ሜይል ጋዜጣ የረድዔት ድርጅት ሠራተኞችን በመጥቀስ ኢትዮጵያን መጥፎ ስም ያሰጧትን ከአስርት ዓመታት በፊት የተከሰቱትን የሚገዳደር ረሃብ አንዣብቧል ሲል አስጠንቅቋል።
አውዳሚው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ስምምነት ተቋጭቶ ቢያንስ በትግራይ ክልል የተኩስ ድምፅ መሰማት ያበቃ በመሰለባቸው አስራ አራት ወራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በምግብ እጥረት ህይወታቸው አልፏል ጋዜጣው እንደሚለው።
የጭላ በምትባለው ብዙ እርዳታ ጠባቂዎች በተሰባሰቡባት ትንሽ ከተማ በየዕለቱ ምንዱባን የተራድዖ እህል ማከማቻ መጋዘን አጠገብ ይሰባሰባሉ ሲል ያየውን የዘገበው ጋዜጣው አንዳንዶች ደግሞ ከአካባቢው መስተዳደር ፅህፈት ቤት በር ውጭ ይከማቻሉ፤ አንዳንዶቹ እንዲያውም አንዳች ነገር ጠብ ቢል በሚል እዚያው ያድራሉ ሲል አስነብቧል።
በ1977 ገደማ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው ረሃብ ክፉኛ ጡጫውን ካሳረፈባቸው የአገሪቷ አካባቢዎች መካከል አንደኛዋ ትግራይ እንደነበረች ያስታወሰው ዘገባው አሁን ያንዣበበው መዐት ከዚያም ሊከፋ ይችላል ብሏል። በጦርነት ምክንያት የክልሉ ሰብል ማምረቻዎች፥ የጤና ማዕከላት እና የመንግስት ፅህፈት ቤቶች ወድመዋል ወይንም ተዘርፈዋል ያለው ጋዜጣው መልሶ የመገንባት ጥረት ብዙም አይስተዋል ብሏል። ረሃብን በማስመልከት ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚሰጠው ዘ ፋሚን ኧርሊ ዋርኒንግ ሲስተምስ ኔትዎርክ የተባለው የምርምር ተቋም ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚጀመረው የፈረንጆች 2024 የመጀመሪያ ወራት ረሃብ በትግራይ በሰፊው ሊሰራጭ ይችላል ይላል። የክልሉ ባለስልጣናት 3.5 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ያሻቸዋል የሚሉ ሲሆን ከመካለላቸውም የሚበዙቱ አርሶ አደሮች ናቸው።
የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ከ77ቱም የሚከሰት ረሃብ እየመጣ ነው ሲሉ ለጋዜጣው ነግረውታል፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤትም የቀድሞ ኃላፊም መረጃዎች በሙሉ የሚጠቁሙት ከአርባ ዓመታት ገደማ በፊት የተከሰተውን መዐት የሚገዳደር ቸነፈር እየመጣ መሆኑን ነው ይላሉ።
አንዲት ሴት ለጋዜጣው ዘጋቢ በአዝጋሚ ሞት ውስጥ ነው ያለነው ሲሉ ነግረውታል። ድርቁ እና የምግብ እጥረት በአጎራባች የአማራ ክልል ዞኖች እንደተከሰተም ይዘገባል።
የመንግስት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም ግን በቅርቡ ስለጉዳዩ ሲናገሩ ድርቅ ተከስቶ በርካቶችን ለምግብ እጥረት ቢዳርግም ረሃብ የለም ማለታቸው ይታወሳል። መንግስት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች እርዳታ ለማድረስ ከፍተና ገንዘብ መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እርዳታ ለማድረስ የሚደረግ ጥረትን ማደናቀፉንም ጨምረው ገልፀው ነበር።
ኤርትራዊያን ስደተኞች በዘፈቀደ እየታሰሩ ነው ተባለ። የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በፀጥታ ኃይሎች ያለአግባብ እየተያዙ ሲሆን ባለፉት ሦስት ዓመታት በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ምዝገባ ያለመካሄዱ ለችግሩ አስተዋፅዖ አድርጓል።
በጉዳዩ ላይ ዘገበ የሠሩ የዓለም አቀፍ የብዙሃን መገናኛዎች ያነጋገሯቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ኤርትራዊ ስደተኞች በፀጥታ ኃይሎች በዘፈቀደ የመያዝ ስጋት እንዳለባቸውና አንዳንድ ጊዜም በፖሊሶች ታስረው ከአጭር ጊዜ በኋላ እንደሚለቀቁ ተናግረዋል።
ኢሰመኮ የስደተኞች ምዝገባ በአስቸኳይ እንዲጀመር ማሳሳቢያ ያቀረበ ሲሆን የስደተኞች ጥበቃ አደጋ ውስጥ ገልጿል ሲል ተናግሯል።
ኢትዮጵያ ለዓመታት ያህል በግዛቷ ለውጭ አገር ስደተኞች እና ጥገኝነት ፈላጊዎች አስተማማኝ ከለላ መስጠቷ የኩራት ምንጭ ሆኖላት ቆይቷል። ከጎረቤቶቿ በተለይም ከኤርትራ፥ ከሶማሊያ እና ከደቡብ ሱዳን የሚመጡ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞችን በልዩ ልዩ ካምፖች የምታስተናግድ ሲሆን ከስደተኞች መካከል የተወሰኑት ከካምፕ ውጭ ሆነው ከማኅበረሰብ ጋር በመቀላቀል እንዲኖሩ የሚያስችል አሰራር አላት። ከዚህ አሠራር ጋርም በተያያዘ ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን በልዩ በልዩ ከተሞቸ በተለይም በአዲስ አበባ እንደሚገኙ ይነገራል።
ይሁንና በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት የስደተኞች ደህንነት ላይ ስጋትን ጥሎ ቆይቷል። በትግራይ ክልል ውስጥ የነበሩ የኤርትራ ስደተኞች መቆያ ጣብያዎች ወደጎረቤት አማራ ለመዛወር የተገደዱባቸው አጋጣሚዎች ሲኖሩ ስደተኞች ለተወሰነ ጊዜ እርዳታ ተቋርጦባቸውም ቆይቷል።
ከዚህም ባለፈ የአስመራን መንግስት ወይንም አስገዳጅ የብሔራዊ ውትድርናን ሸሽተው ኢትዮጵያ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል የተወሰኑትን ተይዘው ወደኤርትራ መመለሳቸውም ተዘግቧል።
መቀመጫውን በፈርንሳይ መዲና ፓሪስ ያደረገው እና በኤርትራ መንግስት ላይ የቅዋሜ ድምፅ የሚያሰማው ሬዲዮ ኤረና በአዲስ አበባ የፀጥታ ኃይሎች በህጋዊ መልኩ ወደአገሪቱ የገቡ ኤርትራዊያንን ጭምር እያሰሩ ነው ሲል ይወነጅላል። በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ወገን የተሰማ አስተያየት የለም።
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ረቡዕ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 17 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - December 27 , 2023
👉 ተቃዋሚው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የመንግስት ኃይሎች እህል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ ሰላማዊያንን ገድለዋል አለ።
👉 የዚምባበዌ ፖሊስ አስራ ሦስት ህገ ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ተደብቀው ባሉበት ቤት ይዣለሁ አለ።
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/Wnefuvb9t1k
የዚምባበዌ ፖሊስ አስራ ሦስት ህገ ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ተደብቀው ባሉበት ቤት ይዣለሁ አለ።
ኢትዮጵያዊያኑ በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካይነት ወደአገሪቷ ያለፈቃድ ሳይገቡ አልቀረም ተብሎ እንደተጠረጠረ የአገሪቱ የብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል። ወደዚምባቡዌ የገቡትም በዛምቢያ አቋርጠው ነው ተብሏል።
በአንድ መሸሸጊያ ቤት ተጠልለው የነበሩትን ኢትዮጵያውያን የተመለከተ ጥቆማ ከማኅበረሰብ አባላት ደርሶት ፖሊስ እንደተንቀሳቀሰና በስፍራው የፖሊስ አባላት በስፍራው ሲደርሱም ያለጉዞ ሰነድ የተደበቁ ሰዎችን ማግኘታቸውን ዘገባዎች አመላክተዋል።
አስራ ሦስቱም ኢትዮጵያውያን ወንዶች ሲሆኑ በሃያ እና በአርባ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙም አብሮ ተጥቅሷል። ሰዎቹ በተያዙባት በአገረቷ ምዕራባዊ ክፍል በምትገኘው ቪክቶሪያ ፎልስ የተባለች ከተማ ህገወጥ ስደተኞችን በማሸጋገር የሚታወቁ አጓጓዦች አሉ ተብሏል። እንደዘገባዎቹ ከሆነ እነዚህ አጓጓዦች መዳረሻቸውን ደቡብ አፍሪካ ያደረጉ ህገ ወጥ ስደተኞችን ማሸጋገር ሥራቸው ነው። ኢትዮጵያውያኑ ፍርድ ቤት ቀርበው ያለፈቃድ ወደአገር ውስጥ በመግባት ወንጀል ክስ እንደሚመሰረትባቸው ይጠበቃል።
በርካታ ኢትዮጵያውያን አያሌ የአፍሪካ አገራትን በማቆራረጥ ደቡብ አፍሪካ ለመድረስ ጥረት እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህም ጋር በተያያዘ በልዩ ልዩ አገራት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር የመዋላቸው ዜና እንግዳ አይደለም።
አዲስ በተቋቋመው የማዕክላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ሠራተኞች ደምወዝ በአግባቡ ያለመከፈል ዜጎችን ከችግርም አልፎ ለእስር እያጋለጠ ነው ተባለ።
በዚሁ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአካባቢያዊ ገቢዎችን ማነስ እና ከፌዴራል ተልኮ የሚመጣ በጀት ለማደበሪያ ግዥ መዋሉን የአጥቢያ ሹማምንት በምክንያትነት ያነሳሉ። የደምወዝ ክፍያ ችግር ለጤና እና ትምህርት ተቋማት አገልግሎት መስተጓጎል ምክንያትም ሆኗል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በተለይ አዲስ በሚዋቀሩ ክልሎች ደምወዝ ያለመከፈል ወይንም ዘለግ ላለ ጊዜ የመዘግየት አጋጣሚዎች አሉ ሲል መግለፁ ይታወሳል።
ኮሚሽኑ ይህ መሰሉ አጋጣሚ ከተስተዋለባቸው ክልሎች መካከል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ነቅሶ ጠቅሷል። አሁን ደግሞ በተለይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያዋ የሆሳዕና አካባቢ የመንግስት ሠራተኞች ተገቢ ክፍያን ከማግኘትም ባለፈ ለእስር እየተዳረጉ ነው ሲሉ ልዩ ልዩ የብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።
በዚሁ አካባቢ የህክምና ባለሞያዎች ከደምወዝ ክፍያ ጋር በተገናኘ የስራ ማቆም አድማዎችን ስለማድረጋቸው መዘገቡ ይታወሳል። በዚሁ የሀድያ ዞን ከፖሊስ፥ ከፍርድ ቤት እንዲሁም ከፍትሕ ተቋማት ሰራተኞች በስተቀር አብዛኞቹ የመንግስት ሠራተኞች ካለፈው ዓመት ነሐሴ አንስቶ ለወራት እንዳልተከፈላቸው በስፍራው ተገኝቼ አረጋግጫለሁ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይሄም ለዘርፈ ብዙ የምጣኔ ኃብታዊ፥ ማኅበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ቀውስ ዳርጓቸዋል ብሏል።
ከደምወዝ ክፍያ ጋር በተገናኘ የትምህርት እና የጤና ተቋማት ስራ እያቋረጡ ወይንም ሙሉ በሙሉ ግልጋሎት እያልሰጡ እንደሆነ የተናገረው ኮሚሽኑ ይሄንን ተከትሎም የአካባቢው ማኅበረሰብ መሠረታዊ ግልጋሎት ፍለጋ ወደአካባቢው ለመሄድ ተገድድዋል ሲል አክሏል።
የከተማ እና የወረዳ አስተዳደሮች የችግሩን መኖር አምነውልኛል ይላል የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን። ለዚህም በምክንያነት ከሚያነሱት አንዱ የአካባቢያዊ ገቢዎችን ማነስ ነው። ከፌዴራል መንግስት ተምድቦ የሚመጣ በጀት ለሌላ ስራ የሚውልባቸው ጊዜያትም አለ ተብሏል። ከእነዚህም መካከል የማዳበሪያ ግዥ አንዱ ነው።
የመንግስት ሠራተኞች አንዳንድ ጊዜ ከደምወዟቸው ተቀንሶ እንደሚሰጣቸውም ኮሚሽኑ በሪፖርቱ የጠቀሰ ሲሆን ለቅጥረኛ ሠራተኞች በአግባቡ እና ሙሉ ሙሉ የደምወዝ ክፍያን ያለመፈፀም የመብት ጥሰት ነው ሲል አክሏል። ደምወዝን በመደበኛነት ያለመክፈል የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ስምምነት የሚጥስ ከመሆኑም ባሻገር የፌደራል የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ የሚፃረርም ነው ብሏል ኢሰመኮ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመስክ ምልከታ ባደረግኩባቸው ከተሞችና የወረዳ አስተዳደሮች ሁሉ የጤና ጣብያዎች እና የጤና ኬላዎች ሙሉ በሙሉ አገልግለት እየሰጡ ያለመሆኑን አይቻለሁም ብሏል ኢሰመኮ። አንደአብነትም ምስራቅ ባድዋቾ በሚባል ወረዳ አራት ጤና ጣብያዎች እና 22 የጤና ኬላዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም ሲል ያውን ገልጿል የሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን።
Comeback at Old Trafford!
ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው በአስቶን ቪላ በመጀመሪያው አጋማሽ 0 ለ 2 ሲመራ ቆይቶ፥ በሁለተኛው አጋማሸ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር 3 ለ 2 ያሸነፈበት አስገራሚ ጨዋታ በምስሎች።
#ManchesterUnited #AstonVilla #EPL #PremierLeague