ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ከ መስከረም መጀመሪያ እስከ ጥር ወር መጨረሻ ተፈፅሟል ያለውን ሰብአዊ ጥሰት በተመለከተ ያወጣው ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፤ በኦሮሚያ ክልል በተለይ ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት 2 ዓመታት ያደረገውን ክትትል እና ምርመራ መሠረት በማድረግ ከሕግ/ከፍርድ ውጪ የሆኑ እና በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ መሆናቸውን በማመላከት በተለይ የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጡ ጥሪ አድርጓል።

ይህን ጥሪ ያደረገው የሁለቱን ዓመታት ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ባለ 11 ገጾች ሪፖርት ነው።

ኢሰመኮ ፦

➡ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣

➡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” በመባል የሚጠራው)

➡ ኢ-መደበኛ የሆኑ የአማራ ታጣቂዎች ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎችን በመጣስ በግጭት ወይም በውጊያ ዐውድና ከውጊያ ዐውድ ውጭ በርካታ ሲቪል ሰዎችን ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን አረጋግጧል።

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ለሚደርስ የመብቶች ጥሰት እንደ ዋነኛ ምክንያት የተገለጸው ፦

* በመንግሥት የጸጥታ አካላት በኩል " ለታጣቂ ቡድኖች መረጃ እና ሎጂስቲክስ ታቀርባላችሁ፤ የቡድኑ አባል ናችሁ " በሚል ምክንያት ነው።

* በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ "ኦነግ ሸኔ") በኩል " ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ በመንግሥት ጸጥታ ኃይል ውስጥ እያገለገለ ነው ወይም ከእኛ ጋር በመሆን አልታገላችሁም/ድጋፍ አላደረጋችሁም " በሚል ምክንያት ሲቪል ሰዎችን ማጥቃት፣ ማንገላታት፤ ማገት እና ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማድረግ ነው።

* በኢ-መደበኛ የአማራ ታጣቂዎች ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች በጅምላ " በኦነግ ሸኔነት " በመፈረጅ እና የክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን በማንሳት በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ዘረፋ እና ማፈናቀል እንደሚፈጸም ኮሚሽኑ ተገንዝቧል፡፡

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ አርብ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 25 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 5 , 2024
👉 ሰሞኑን በከተማዋ መነጋገሪያ የነበረውን ሚኒሊክን ሃውልት አስመልክቶ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያወጣው መረጃ
👉 ኢትዮጵያ ፓስፖርቷን ወደ ዲጂታል ልትቀይር ነው ስለመባሉ
👉 በዩናይትድ ስቴትስ አዮዋ ግዛት በሚገኝ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጀመሪያው የትምህርት ቀን አንድ ተማሪ ስድስት ሰዎችን በጥይት መትቶ እራሱን ማጥፋቱም ተሰምቷል
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/WIV4AlqSa4w

Читать полностью…

EthioTube

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አቅንተዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አንቶኒዮ ብሊንከን በትናንትናው  እለት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ማምራታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሚኒስትሩ ወደ መካከለኛ ምስራቅ ያመሩት በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተጀመረው ጦርነት ወደ ቀጣናው ይስፋፋል የሚል ስጋት ባየለበት ወቅት ነው።

ይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለሳምንት የሚቆየው ጉዞ፣ ሀማስ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ካደረሰበት ከፈረንጆቹ ጥቅምት 2023 ወዲህ ለአራተኛ ጊዜ ነው።

ሚኒስትር እስራኤል እና ዌስትባንክን ጨምሮ ጆርዳንን፣ ኳታርን፣ ሳኡዲ አረቢያን፣ አረብ ኢምሬትስን እና ግብጽን ይጎበኛሉ ተብሏል። ከጦርነቱ በኋላ ጋዛ እንዴት መተዳደር አለባት በሚለው አስቸጋሪ ጉዳይ መሻሻል መኖሩን የጠቀሱት ብሊንከን ተጨማሪ የሰብአዊ  እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ብሊንከን ጉዞ ያደረጉት በሀማስ ምክትል የፖለቲካ መሪ ሳለህ አል አሮሪ ላይ የደረሰው ጉድያ፣ ግጭቱን ቀጣናዊ ያደርገዋል የሚል ስጋት ከተፈጠረ በኋላ ነው።

ከእስራኤል ጋር የተኩስ ልውውጥ እያደረገ ያለው በኢራን ይደገፋል የሚባለው የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ ዝቷል።

የእስራኤል እና ሀማስ ግጭት ወደ ቀይ ባህር ተስፋፍቶ መፋጠጥ ፈጥሯል። የሀማስ አጋር የሆኑት እና አብዛኛውን የየመን ክፍል የተቆጣጠሩት የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ 20 መርከቦች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል።

በጋዛ መጠነሰፊ ጥቃት እያካሄደች ያለው እስራኤል ጦርነቱ ለወራት ሊቆይ እንደሚችል ገልጻለች።

Читать полностью…

EthioTube

በዩናይትድ ስቴትስ አዮዋ ግዛት በሚገኝ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጀመሪያው የትምህርት ቀን አንድ ተማሪ ስድስት ሰዎችን በጥይት መትቶ እራሱን አጠፋ።

ፖሊስ እንዳለው በጥይት ከተመቱት ስድስት ሰዎች መካከል አንዱ ሕይወቱ አልፏል።
በፔሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ "በቀላሉ ተዘጋጅቶ" የተቀበረ ፈንጂ መገኘቱንም ፖሊስ ተናግሯል።

ጥቃት ከደረሰባቸው አምስቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አንደኛው የትምህርት ቤት አስተዳዳሪ ናቸው።
ህይወቱ ያለፈው ተማሪ የ11 እና 12 ዓመት ታዳጊዎች የሚማሩበት የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ነበር።

ጠዋት ላይ የተኩስ ጥቃት መኖሩ እንደተሰማ የመጀመሪያው የፖሊስ መኮንን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ቦታው መድረሱን ፖሊስ ተናግሯል።
የአዮዋ የወንጀል ምርመራ ዲቪዥን ረዳት ዳይሬክተር ሚች ሞርትቨ ከጥቃቱ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፖሊሶች ሲደርሱ ተጠርጣሪው ራሱን አቁስሎ አግኝተውታል።

ተጠርጣሪው ዲላን በትለር የተባለ የ17 ዓመት ተማሪ መሆኑ ታውቋል። ፖሊስ እንዳለው ትልቅ መሣሪያ እና ትንሽ የእጅ ሽጉጥ ታጥቆ ነበር።
ሞርትቨ አክለውም ተጠርጣሪው "ጥቃቱ በፈጸመበት ወቅት በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፎችን ለጥፏል" ብለዋል።

ከቆሰሉት መካከል አንዱ በአስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን አራቱ ደግሞ ጉዳታቸው ለሕይወታቸው አደጋ አይደለም ብለዋል የፖሊስ መኮንኑ።
የዳላስ ካውንቲ ሸሪፍ አደም ኢንፋንቴ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ጊዜው ጠዋት በመሆኑ “እንደ ዕድል ሆኖ በጣም ጥቂት ተማሪዎች እና መምህራን ነበሩ። ይህም የተጠቂዎችን ቁጥር አነስተኛ እንዲሆን አስተዋጽኦ አድርጓል ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሀሙስ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 24 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 4 , 2024

👉 ደብረ ብርሃን ግጭትን ማስተናገዷ ተዘገበ። 

👉 አሜሪካ ፤ በ 1960 ለተካለለዉ የሶማሊያ ድንበር እዉቅና ሰጣለሁ አለች

👉 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኢትዮጵያና በሶማሌላንድ ስምምነት ጉዳይ ማምሻውን የሰጡት መግለጫ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/HDHr-yIt74M

Читать полностью…

EthioTube

ደብረ ብርሃን ግጭትን ማስተናገዷ ተዘገበ።

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን መዲና የሆነችውና ከአዲስ አበባ ከአንድ መቶ ሃምሳ ኪሎሜትር የማይበልጥ ርቀት ያላት ደብረብርሃን በታጣቂዎች እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መካከል ግጭትን ያስተናገደችው ትናንትና እንደነበረ ተዘግቧል። እስካሁን በግጭቱ ስለሞቱ ሰዎች ቁጥር በቁርጥ የታወቀ ነገር የለም። ይሁንና የተለያዩ የዓለምአቀፍ የብዙሃን መገናኛዎች ነዋሪዎችን ጠቅሰው እንደዘገቡት ታጣቂዎች ወደከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች መግባታቸውን ተከትሎ ነው ግጭቶቹ የተቀሰቀሱት። ትናንትና አመሻሽ ላይ ወደከተማዋ መረጋጋት ቢመለስም መደበኛ እንቅስቃሴዎች ግን ወዲያው አልቀጠሉም ነበር ተብሏል።

መንግስት በአማራ ክልል ከታጣቂዎች ጋር ፍልሚያ የጀመረው ካለፈው የክረምት አጋማሽ አንስቶ ነው። ከዚያም ወዲህ ክልሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር የሚገኝ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎትም ተቋርጦበታል። መንግስት አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት ወደክልሉ ተመልሷል ቢልም አሁንም ግጭቶች እና ጥቃቶች በተለይ በመጠን አነስ ባሉ ከተሞች መዘገባቸው አልቀረም።

Читать полностью…

EthioTube

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ማምሻውን የሰጡት መግለጫ

በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የተፈጠረውን ውጥረት በቅርበት ሲከታተሉ እንደነበር የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ሌሊቱን በህብረቱ በኩል ባሰራጩት መግለጫ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መንግስታት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማርገብ መረጋጋት እና መከባበር እንዲኖር ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። 

በዚህ ረገድ ሁለቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በመካከላቸው ያለው መልካም ግንኙነት ወደ መበላሸት ከሚያመራ ከማንኛውም ተግባር እንዲታቀቡ አሳስቧል።

Читать полностью…

EthioTube

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ከሶማሌላንድ ጋር ስለተፈረመው የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሰነድ በዛሬው እለት ማብራሪያ ሰጥቷል።

በሰጠው ማብራሪያም፤

ስምምነቱ  ለኢትዮጵያ በኤደን ባህረሰላጤ ላይ ዘላቂና አስተማማኝ የባሕር ኃይል ቤዝ እና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት በሊዝ የምታገኝበትን ዕድል የሚያስገኝ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መንግሥት አስቀድሞ ይፋ ባደረገው አቋሙ መሠረት ሶማሌ ላንድን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሊዙ የሚታሰብ ድርሻ እንዲኖራት ያስችላል ብሏል መግለጫው።

ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል

Читать полностью…

EthioTube

በአሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጠችው የሶማሌ-አሜሪካዊቷ ከንቲባ ቃለ መሃላ ፈጸመች

በዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ ግዛት በሚገኘው የሴንት ሉዊስ ፓርክ ከተማ ምክር ቤት የ27 ዓመቷን ናዲያ መሀመድን ከንቲባ አድርጎ ቃለ መሃላ ፈፅሟል። በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሶማሌ-አሜሪካዊት ከንቲባ ሆና ከሁለት ወራት በፊት መመረጧ ይታወሳል።

ናዲያ መሀመድ ባለፈው ህዳር የተካሄደውን የከንቲባ ምርጫ 58 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት አሸንፋለች። በከተማዋ በእድሜ ትንሿ እና የመጀመሪያዋ ጥቁር ከንቲባ መሆን ችላለች። ከማንነቴ በላይ መታወቅ እፈልጋለሁ ስትል ተናግራለች።
ማንነቴ የታሪኬ አንዱ አካል ነው፣ እኔ ባለኝ ነገር ሁሉ እኮራለሁ፣ ነገር ግን ያ ብቸኛው ታሪኬ እንዲሆን አልፈልግም። ያ ሰዎች ንግግራቸውን የሚያቆሙበት እንዲሆን አልፈልግም ስትል ናዲያ መሐመድ ከተመረጠች በኋላ በሚኒያፖሊስ ለሚገኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግራለች። እንደ ከንቲባ ሆና ልታደርጋቸው ካቀዳቸው ቁልፍ ጉዳዮች መካከል የህዝብ ደህንነት እና ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ማቅረብ መሆኑን አንስታለች። ናዲያ ሞሃመድ የ23 ዓመት ወጣት እያለች በ2019 ለከተማው ምክር ቤት ተመርጣለች።

ቤተሰቦቿ በሶማሊያ ያለውን ጦርነት ሸሽተው በ10 ዓመቷ ከኬንያ ካኩማ የስደተኞች ካምፕ የገቡ ሲሆን ከዛም ወደ ሚኒሶታ አቅንተዌ። እ.ኤ.አ. በ2021 ዴቃ ዳልክ በሜይን ግዛት በደቡብ ፖርትላንድ ከተማ የምክር ቤት አባላት የመጀመሪያው ሶማሌ-አሜሪካዊ ከንቲባ ሆኖ መሾሙ ይታወሳል። ነገር ግን የናዲያ መሐመድ ምርጫ የሚለየው በሕዝብ የተመረጡ የመጀመሪያው ሱማሌ-አሜሪካዊት ከንቲባ ያደርጋታል።

Читать полностью…

EthioTube

ግብፅ በፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ቃል አቀባይ በኩል ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት ገልጻለች።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሼክ ሀሰን ሞሀሙድ ፤ ትላንት ምሽት ወደ አል ሲሲ ስልክ ደውለው ከሁለት ሳምንት በፊት ላሸነፉት ምርጫ " እንኳን ደስ አልዎት " ብለዋል። የስልክ ውይይቱን ተከትሎ የግብፅ ፕሬዜዳንት ቃል አቀባይ ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን ታሪካዊ ግንኙነታቸውን መሰረት በማድረግ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የጋራ ትብብርን ለማጎልበት መወያየታቸውን ገልጸዋል።

አል ሲሲ ግብፅ ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት መግለፃቸው ተነግሯል። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ከአል ሲሲ በተጨማሪ ለኳታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ስልክ ደውለው ነበር። ከኳታሩ ኤሚር ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችሉ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የጋራ ጥቅሞችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተሰምቷል።

Читать полностью…

EthioTube

አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ መግለጫ ሰጠ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ አጭር መግለጫን ትላንት ምሽት አውጥቶ ነበር።

በዚህ መግለጫው፤ እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ  የባህር በር አገልግሎት (በሊዝ) ማግኘት የሚያችላትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል ብሏል።

ቀጠል አድርጎ ፦ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት ፣ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተሮችን መሰረት በማድረግ የሶማሊያን አንድነትን ፣ ሉዓላዊነትን እና የግዛት አንድነትን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን ለማስታወስ እንፈልጋለን ብሏል።

ይህ ለመላው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላምና መረጋጋት ቁልፍ ጉዳይ ነው ሲል ገልጿል።

Читать полностью…

EthioTube

ሶማሊያ አምባሳደሯን ከኢትዮጵያ ጠራች።

ሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የተፈራረሙት ሰነድ ህጋዊ ቅቡልነት የሌለው እና የማይሰራ ነው ብላለች።

ኢትዮጵያ እና ራሷን እንደነፃ አገር የምትቆጥረው ሶማሊላንድ በባህር ዳርቻ አጠቃቀም ዙርያ የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረሙ በኋላ በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለው ግንኙነት በፍጥነት መበላሸት የያዘ ይመስላል። ሶማሊላንድን እንደራሷ ግዛት የምትቆጥረው ሶማሊያ ያለዕውቅና ማንም የውጭ አገር መንግስት ሊያናግራት አይችልም ባይ ናት።

ከዚህም በዘለለ ሃያ ኪሎ ሜትር ገደማ የባህር ዳርቻ ለኢትዮጵያ ያስገኛል የተባለው ስምምነት ሉዐላዊነትን እና የግዛት አንድነትን የሚጥስ ነው ብላለች። ዛሬ የአገሪቱ ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገ ሲሆን ከስብሰባው በኋላ መግለጫ የሰጡት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ የመንግስታቸውን አቋም ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ያፈጠጠ ያገጠጠ ፀብ አጫሪነት ፈፅማብኛለች ያለችው ሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትሯ የአገራቸው ሕዝብ እንዲረጋጋ ተማፅነዋል። በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ዕውቅና እንደምትሰጥ የሶማሊላንድ መንግስት ቢገልፅም በኢትዮጵያ በኩል ስለዚህ በግልፅ የተባለ ነገር የለም። ሶማሊያ ከዚህም በተረፈ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት በጉዳዩ ላይ እንዲመክሩ ጠይቃለች።

Читать полностью…

EthioTube

በአርባ ምንጭ ዙርያ የተከሰተው ግጭት ትኩረት ይሻል ሲል የሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን አስጠነቀቀ።

መንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ግጭት ተከስቷል፥ ውጥረትም ነግሷል ያለ ሲሆን ይህም ሳይባባስ በፊት አስቸኳይ እርምጃ ያሻል ብሏል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ሰብዐዊ እርዳታ ይሻሉ፥ ለነዋሪዎች ዘላቂ ሰላም መመለስ አለበት ሲልም ገልጿል።

ግጭት እና ውጥረት የተነሳው ከአስተዳደራዊ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ነው ያለው ኢሰመኮ በአካባቢው ዓመታትን ያስቆጠረ ውዝግብ መኖሩን አንስቷል። የአካባቢው ነዋሪዎች የአገሪቱን ገዥ ፓርቲ የሚፎካከር የፖለቲካ ፓርቲ በመምረጣችን ለሰብዐዊ መብት ጥሰት ይደርስብናል ሲሉም ያማረራራሉ ብሏል ኢሰመኮ። የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ የአካባቢ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ መንግስት ስፍራውን ማስተዳደር የለበትም በሚል ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ችግር እየፈጠሩ ናቸው ይላል።

ኢሰመኮ በአካባቢው እየተፈጸሙ ያሉ መብቶች ጥሰቶች ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገሩ፤ የተፈጠሩ አለመግባባቶች ሕጋዊና ሰላማዊ መንገድን ተከትለው እንዲፈቱ ለአካባቢው የመንግሥት አስተዳደር፣ ለአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች እና ለፖለቲካ ፓርቲዎች ምክረ ሐሳብ እያቀረብኩ ሁኔታው ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ ብሏል።

ይሁን እንጅ በተለይ ከወርሃ ጥቅምት አንስቶ የአንድ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ከዋለ በኋላ መሞቱን ተከትሎ ውጥረት ተባብሷል ብሏል የኢሰመኮ መግለጫ። ከዚህም በኋላ በግለሰቦች እና በቡድኖች በደረሱ ጥቃቶች የሙዝ እርሻዎች የመንግስት አገልግሎት ሰጭ መስሪያ ቤቶች ወድመዋል፤ በግለሰቦች እና በፀጥታ አካላት እርምጃዎች እየተወሰዱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል እንዲሁም ቆስለዋል እንደመግለጫው። ሪፖርት እስካጠናቀርኩበት ጊዜ ድረስ ውጥረት ቀጥሏል ያለው ኮሚሽኑ አፋጣኝ እርምጃ እንዲደረግ ተማፅኗል።

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ የወደብ ፊርማ በሶማሊያ ቁጣ ቀስቅሷል።

ኢትዮጵያና ራሷን ነፃ አድርጋ የምትቆጥረው ሶማሊላንድ አድርገውታል የተባለው የመግባቢያ ስምምነት ለኢትዮጵያ 20 ኪሎሜትር ገደማ የባህር ዳርቻ እንደሚያስገኝላት ከተሰማ በኋላ በርካታ የሶማሊያ ፖለቲኞች እና ስመ ጥር ግለሰቦች ቁጣቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

ሶማሊያ ሶማሊላንድን የግዛቴ አካል ናት ብላ የምትቆጥራት ሲሆን ያለ እኔ ዕውቅና ንግግር መደረጉ ሉዐላዊትን የሚጥስ ነው በሚል ነው በርካታ ሶማሊያውያን የተበሳጩት።

የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት እና በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቀዳሚ የስልጣን ዓመታት የቅርብ ወዳጃቸው የነበሩትን መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ኤክስ በተባለው የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሰነድ ለሶማሊያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ በጠቅላላ ስጋትን የሚፈጥር ነው ብለውታል። ፋርማጆ ቀጥለውም ሉዐላዊነትን እና የግዛት አንድነትን ማክበር የቀጠናዊ መረጋጋት እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙነት መሠረት ነው ያሉ ሲሆን የአገራቸው መንግስት በተገቢው አኳኋን ምላሽ እንዲሰጥ ጥያቄ ሰንዝረዋል።

የሶማሊያ ካቢኔ በበኩሉ ዜናው እንደተሰማ ብዙም ሳይቆይ ነበር አስቸኳይ ጉባዔ የጠራው።

ከካቢኔው አባላት አንዱ የሆኑት የአገሪቱ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ኃብት ሚኒስትር አብዲሪዛቅ መሃመድ “ሶማሊያ አትከፋፈለም፤ ሉዐላዊነቷ እና የግዛት አንድነቷ ለድርድር አይቀርብም” ሲሉ ቆጣ ያለ መልዕክት በዚሁ የማኅበራዊ የትስስር መድረክ ላይ አስፍረዋል። አክለውም ኢትዮጵያ ከክፍለ ሃገር መሪ ጋር ሰነድ መፈራረም እንደማትችል ጠንቅቃ ታውቃለች፤ የግዛት አንድነታችንን የመጣስ ፈቃድ የሰጣትም የለም ሲሉ አስፍረዋል።

ለወትሮው በተቃራኒ ወገን ቆመው የሚፋለሙት የአገሪቱ የመንግስት አካላት እና የታጣቂው ቡድን አል-ሸባብ በዚህ ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም ያንፀባረቁ መስሏል። በበርካታ አገራት በሽብርተኛነት የተፈረጀው አልሸባብ በቃል አቀባዩ በኩል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቱ ህገ ወጥ እና የማይሰራ ነው ማለቱን የአገሪቱ የብዙሃን መገናኛዎች ተናግረዋል። ታጣቂው ቡድን ጉዳዩን እንፋለማለን ሲል መዛቱም አብሮ ተዘግቧል።

ሶማሊያ በሶማሊላንድ ጉዳይ የሾመቻቸው ልዩ ወኪል አብዲካሪም ሁሴን ጉሌድ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና የህግ ማዕቀፍን በዘፈቀደ ጥሷል ሲሉ ወንጅለውታል።

ስምምነቱን እንደትልቅ ስኬት ተደርጎ በኢትዮጵያ በኩል ቢቀርብም ስለዝርዝር ይዘቱ ግን የተሻለ መረጃ የተገኘው ከሶማሊላንድ ወገን ነው። የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ እና የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የመግባቢያ ሰነዱ ኢትዮጵያ 20 ኪሎ ሜትር የሚዘረጋ የባህር ዳርቻን ለመጠቀም ለሃምሳ ዓመታት ያህል መከራየትን እንደሚጨምር ገልጿል። በምላሹ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ይፋዊ ዕውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሃገር ትሆናለች።

ሶማሊላንድ በአፍሪካ ኅብረትም ሆነ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋዊ ዕውቅና የላትም። ጉዳዩን ወደተባበሩት መንግስታት ድርጅት ብትወስድ እንኳ የራሷ ራስ ገዝ ግዛት ታይዋን ጋር ንትርክ ያለባት ቻይና እርምጃዋን ክፉኛ እንደምትቃወመውና ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ውድቅ እንደምታደርገው ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ዘርዘር አድርጋ ያለችው ነገር የለም። ብሉምበርግ የተባለው ዋነኛ ትከረቱን በንግድ ጉዳዮች ያደረገ የብዙሃን መገናኛ ኢትዮጵያ ከአየር መንገዷ ድርሻ እንደምታገኝ ቢገልፅም ስለዚሁ ጉዳይ በሶማሊላንድ መንግስት መግለጫ የተባለ ነገር የለም። ብሉምበርግ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ የሆኑትን ሬድዋን ሁሴንን ጠቅሶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዘርዘር ያለ ንግግር እንደሚደረግ ዘግቧል።

የመግባቢያ ሰነድ ህጋዊ አሳሪነት የሌለው ውል ሲሆን ወደተግባር እንዲገባ ህጋዊ ቅቡልነት ያለው ስምምነት መፈረም የግድ ይላል።

Читать полностью…

EthioTube

#ሰበር_ዜና

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል።

ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር እና የአጋርነት መግባቢያ ሠነድ በተለያዩ ዘርፎች በቀጣይ ለሚኖራቸው ግንኙነቶች ማዕቀፍ  እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽኅፈት ቤት ይፋ ባደረገው መረጃ አሳውቋል።

የመግባቢያ ሠነዱ ፦
* የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት ዕውን የሚያደርግ ፣
* የባሕር በር አማራጮቿን የሚያሠፋ
* የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ ፣ የዲፕሎማሲ ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናከር ነው ብሏል።

በተጨማሪም ሠነዱ ሀገራቱ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲው ዘርፍ የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚጎለብትበትን አካሄድ የሚያካትት መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጥቶ መቀበል መርኅ እና ሀገሪቷ ለጋራ ጥቅም ከጎረቤቶቿ ጋር የመሥራት ፍላጎት እና አቋሟን መልሶ የሚያጸና እንደሆነም አመላክቷል፡፡

ሠነዱ ፤ አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እና ለአፍሪካ ቀንድ ትሥሥር የላቀ ፋይዳ ያለው መሆኑን ጠቁሟል።

Читать полностью…

EthioTube

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሳችሁ ! መልካም የልደት በዓል !

Читать полностью…

EthioTube

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት መግቢያ ፊለፊት ላይ የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት እንደሚኖር ገልጿል።

ምኒሊክ አደባባይ የሚገኘው " የአፄ ምኒሊክ ሃይውልት ሊፈርስ ነው፤ ከቦታው ተነስቶ ወደ ሙዚየም ሊገባ ነው " የሚባለው ፍፁም ሀሰት ሲል ገልጿል።

የከተማው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰጡት ቃል ፤ " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎሜትር ፕሮጀክት የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊትለፊት ላይ ገና መግቢያው ላይ አለ፤ አዲስ ተጨምሮ። ያንን አዲስ የሚሰራ እንዴት ነው አሮጌውን የሚያፈርሰው ? ይሄ ያስኬዳል ? እንዴት ነው የበዓል ማክበሪያ ቦታ በዛ በኩል የሚደረገው ? " ሲሉ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ፤ " አፄ ምኒሊክ የራሱ ትክክል አይደለም የምንለው የሰራቸው ጥፋቶች አሉ ብለን እናምናለን። በዓድዋ ላይ ደግሞ የሰራቸው ትልልቅ ታሪኮች አሉ። አንድ የሆነ ጥፋት ካለ  ሌላውን ሁሉ እውነት በዛ እንሸፍናለን ማለት አይደለም። የሆነ እውነት ካለ በጥፋቱ ሸፍነን እናያለን ማለት አይደለም። ታሪክን ጥፋትም ይኑር በጎ ገፅታውን ፣ መልካም ገፅታውንም እንዳለ እውነቱን ማስቀመጥ ነው ከእኛ የሚጠበቅ " ሲሉ ተናግረዋል።

" እኛ አልሰራነው፤ ለምን የአሁኑ ትውልድ መከራውን እንደሚያይ ብዙ አይገባንም። እኛ አልሰራነው ፤ ይሄ ትውልድ አልሰራው የጥፋቱንም የጀግንነት ፓርቱንም ይሄ ትውልድ አልሰራውም። ግን የራሱ ሃገር ታሪክ ነው፤ የራሱ ህዝብ ታሪክ ነው በመልካምነት የሚይዘውን ይኮራበታል፤ ይይዘዋል፤ ያሳይበታል። ትክክል አልነበረም የምንለውን አንደግመውም፤ በእኛ ዘመን መደገም የለበትም። " ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች " አሮጌ አካባቢን ባደስን ቁጥር ቅርስ ፈረሰ ነው የሚባለው ይሄ አዲስ አበባ ላይ ትልቅ የልማት እንቅፋት ሆኖብናል " ሲሉ አክለዋል።

የ " ዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት ከጥቂት ቀናት በኃላ ለህዝብ ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

Читать полностью…

EthioTube

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግም፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 225 የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው አሳዳጊ የሌላቸው ሕጻናት ማዕድ ማጋራታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ ፓስፖርቷን ወደ ዲጂታል ልትቀይር ነው ተባለ!

ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወደ ዲጂታል ሊቀየር እንደሆነ ተገልጿል፡፡የኢትዮጵያ የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በወረቀት የሚሰሩ ስራዎች ለሌብነት እና ሙስና ተገላጭ በመሆናቸው ወደ ዲጂታል አሰራር መቀየር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አገልግሎቱ ተቋማት ጋር ያሉ መረጃዎችን ማጣራት፤ የሰዎችን ማንነት ለመመርመር እንዲሁም ምዝገባዎች የሚያደርግበትን አሰራር ወደ ዲጂታል ለመቀየር እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ያሉ ሲሆን በዚህም የኢትዮጵያን ፓስፖርት ወደ ኢ- ፓስፖርት ወይም ዲጂታል ለመቀየር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ይህንን ስራ ከሚሰራ የቴክኖሎጂ ተቋም ጋር ስምምነት በማድረግ እየሰራን ነው ያሉ ሲሆን በቅርብስራውን አጠናቀን ይፋ እናደርጋለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ለመቀነስ ፤አሰራሮችን በሙሉ ወደ ዲጂታል መቀየር ዋነኛው መፍትሄ መሆኑንም አክለዋል፡፡ የፓስፖርት ጉዳይ ሙስናን ጨምሮ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ይታዩበታል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያና ሶማሊያ ያደረጉት የመግቢያያ ስምምነት ህጋዊ አሳሪነት ባይኖረውም ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ነውጥ ያስነሳ መስሏል።

የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ የ20 ኪሎሜትር የባሕር ጠረፍ የሚያስገኝላት ሲሆን በምላሹም ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ ታገኛለች። የሶማሊላንድ ባለስልጣናት የስምምነቱ አንድ አካል ህጋዊ ዕውቅናን ከአዲስ አበባ ማግኘት ነው ቢሉም የኢትዮጵያ መንግስት የተግባቦት አገልግሎት ትናንትና ባወጣው መግለጫ ራሷን እንደነፃ አገር የምትቆጥረውን ሶማሊላንድን ዕውቅና እሰጣታለሁ ከማለት ተቆጥቧል። ከዚያ ይልቅ በጉዳዩ ላይ አቋም ለመያዝ የተጠና ምርመራ አደርጋለሁ ብሏል።

ሞቃዲሾ ግን ያለ እኔ ዕውቅና ከግዛቴ ጋር ድርድር ተደርጓል፥ የውሃ ድንበሬን ለመዝረፍ ተሞክሯል በሚል ቁጣዋን አሰምታለች። አምባሰደሯን ከመጥራትም በዘለለ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ መሃመድ አሁን አንድድሮው ደካማ አገር አይደለንም፤ ወሰናችንን ለመጠበቅ ሁሉንም ነገር እናደርጋለን የሚል ዛቻ የተቀላቀለበት ንግግር አድርገዋል። መንግስታቸው ኢትዮጵያን የፀብ አጫሪነት ድርጊት ፈፅማብናለች ሲሉም ወንጅለዋታል። ኢትዮጵያ በበኩሏ ከሶማሊላንድ ጋር ባደረገችው ንግግር የተጣሰ ህግ የለም ያለች ሲሆን ከዜናው በኋላ የተነሳውን ዲፕሎማሲያዊ አቧራ ለማርገብ በሚመስል ሁኔታ ባለስልጣናቷ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዲፕሎማቶችን ጠርተው ማብራሪያ እንዲሰጡ አድርጋለች።

ሶማሊያ በበኩሏ ወዳጆቿ ጋር በጉዳዩ ላይ ተከታታይ ውይይቶችን ያደረገች ሲሆን ከግብፅ እና ከአረብ ሊግ ከጎንሽ ነን የሚል ድጋፍን አግኝታለች። ካይሮ እና የአረብ አገራት ማኅበሩ ባወጧቸው መግለጫዎች የሶማሊያ የግዛት አንድነት መከበር እንዳለበት ወትውተዋል።

በሌላ በኩል ሁለቱም አገራት አባል የሆኑበት የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) አገራቱ ሰከን እንዲሉ ያወጣውን መግለጫ ሶማሊያ ለኢትዮጵያ ያደላ ነው ስትል አጣጥላዋለች። የድርጅቱ መሪ ኢትዮጵያ ምክትላቸው ደግሞ ሶማሊያዊ የሆኑበት ኢጋድ በሁለቱ አገራት ውጥረት አቋም ላለመውሰድ የጣረ ቢመስልም ሶማሊያ የግዛት አንድነቴ እንዲከበር አላሰሰበም፥ የኢትዮጵያን ድርጊትም አላወገዘም ስትል መግለጫውን እንዲሰርዝና መሪውም ይቅርታ እንዲጠይቁ አሳስባለች።

በዚህ መኃል የዲፕሎማሲያዊ ውጥንቅጡ ማዕከል የሆነችው ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት መከበር እንዳለበት የሚያሳስብ መግለጫ አውጥታለች። ሃርጌሳ በተባለችው ከተማዋ ነዋሪዎች ለስምምነቱ ያላቸውን ድጋፍ በሰልፍ የገለፁ ሲሆን በተቃራኒው በሶማሊያዋ መዲና ሞቃዲሾ ኢትዮጵያን የሚያወግዙ ሰልፈኞች አደባበይ መውጣታቸውን የአገሬው የብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።

የመግባቢያ ሰነዱ በትክክል ወደአስገዳጅ ውልነት ተቀይሮ በፊርማ የሚፀድቀው መቼ እንደሆነ ባይታወቅም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሊሆን እንደሚችል የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጠቆም አድርገዋል። ያኔ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ያህል ድርሻ ሶማሊላንድ ትወስዳለች፥ የይፋዊ ዕውቅናውስ ነገር ምን ይሆናል የሚለው ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።፥ እስከዚያው ድረስ ግን ውጥረቱ እያየለ የሚቀጠል መስሏል።

Читать полностью…

EthioTube

አሜሪካ ፤ በ 1960 ለተካለለዉ የሶማሊያ ድንበር እዉቅና ሰጣለሁ አለች

👉🏼በዚህ ድንበር መሰረት ሶማሊላንድ የሶማሊያ ግዛት ናት

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተፈመዉ የወደብ አገልግሎትን የማግኘት ስምምነት ጉዳይ የአፍሪካ ህብረት ፣ የአረብ ሊግ እንዲሁም አጎራባች ሀገራት ጭምር ጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እየሰጡ አቋማቸዉንም እየገለጡ ነዉ።

የአረብ ሊግ ትናንት ማምሻዉን ባወጣዉ መግለጫ ለሶማሊያ ባደላ መልኩ ስምምነቱ ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ ሲል አጣጥሎታል። በአንጻሩ የአፍሪካ ህብረት ማለዳዉን ባወጣዉ መግለጫ ለየትኛዉም ጎራ ባልወገነ መልኩ ሁለቱ አካላት በንግግር ጉዳያቸዉን መፍታት እንዳለባቸዉ አሳስቦ ፤ የሶማሊያ ግዛት ግን ሊከበር ይገባል ብሎ ነበር።

በትናንትናው እለት የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ማቴዉ ፔሪ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ ሰሞነኛዉ የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ የወደብ ስምምነት ላይ አሜሪካ ያላትን አቋም ምን እንደሆነ እንዲያሳዉቁ ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ነበር።

ማቴዉ ፤ አሜሪካ የቀጠናዉ ሰላም እንደሚያሳስባት ተናግረዉ ሁለቱ ሀገራት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳያቸዉን በዲፕሎማሲያዊ ንግግር መፍታት አለባቸዉ ሲሉ መክረዋል።

አያይዘዉም አሜሪካ እ.ኤ.አ በ 1960 የተካለለዉ የሶማሊያ ግዛት እንዲከበር ትጠይቃለችም ብለዋል። አሜሪካ የሶማሊያ ሉዓላዊ ግዛት እዉቅና እንደምትሰጥም ተናግረዋል። በዚህም ድንበር መሰረት ሶማሊላንድ የሶማሊያ ግዛት መሆናን ዳጉ ጆርናል በወቅቱ ከተካለለዉ የድንበር ካርታ ላይ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ የወደብ ስምምነት ዉዝግብ እያስነሳ ቢሆንም በሀርጌሳ እና አዲስአበባ መንግስታት በኩል ከዚህ በተቃራኒ በሆነ መልኩ ስምምነቱ ተፈጻሚ እንደሚሆን አስታዉቀዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ረቡዕ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 24 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 3 , 2024

👉 የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

👉 ከቀጣይ  አመት ጀምሮ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል  የፈተና ምዝገባ የሚደረገው በዲጅታል መሆኑ ተገለፀ።

👉 በአሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጠችው የሶማሌ-አሜሪካዊቷ ከንቲባ ቃለ መሃላ ፈጸመች  

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/pbx44B-Bc0A

Читать полностью…

EthioTube

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ ሰጡ

ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲላፕሎማሲው መስክ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት መካከል እያታየ ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ኢጋድ ሁኔታውን በንቃት እየተከታተለ መሆኑን እና በቀጠናው መረጋጋት ላይ ያለውን ተፅእኖ እንደሚገነዘብ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁኔታዎችን በሰላማዊ እና በመግባባት መንፈስ ለመፍታት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶክተር ወርቅነህ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ስለተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ያነሱት ነገር የለም።

የሶማሊያ  መንግሥት የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ እንዳበሳጨው ለመረዳት ተችሏል።

የሶማሊያ መንግሥት " የመግለጫው ሃሳብ ለኢትዮጵያ ያደላ ነው " በማለት ዶ/ር ወርቅነህ በአስቸኳይ ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ የይቅርታ መግለጫም በማውጣት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ ብሏል።

ሶማሊያ ፤ የኔ አንድ ግዛት ናት በምትላት ሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል የተረፈመው ስምምነት ያበሳጫት ሲሆን ስምምነቱ የግዛት አንድነቴን እና ሉዓላዊነትን የጣሰ ነው በማለት እየተቃወመች ትገኛለች።

Читать полностью…

EthioTube

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዜዳንቱና ልኡካቸው ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት ሲደርሱ የሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ ባለስጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሁለቱም በኩል ያሉ ባለስልጣናት የንግድ ትብብርን በተመለከተና በድንበር የፀጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች (በሶማሌ ክልል እና በሶማሌላንድ) ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ከተማ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን እውን ያደርጋል የተባለለንትን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው አይዘነጋም።

Читать полностью…

EthioTube

ከቀጣይ  አመት ጀምሮ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል  የፈተና ምዝገባ የሚደረገው በዲጅታል መሆኑ ተገለፀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት  ከቀጣይ አመት ጀምሮ የፈተና ምዝገባ የማደርገው  በዲጅታል ነው ብሏል።

አገልግሎቱ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር  በጋራ በሰጠው መግለጫ ነው ይሄን ያስታወቀው።

በየአመቱ በሃገር አቀፍ እና  የክልል አቀፍ የፈተና ምዝገባዎች ሲደረጉ አገልግሎቱ በርካታ ሚሊየን ግብሮችን እንደሚያወጣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ተናግረዋል።

አሁን የፈተና አገልግሎቱ የፈተና ምዝግባዎችን በዲጅታል እንዲደረጉ የሚያደርግ በመሆኑ ይሄን ወጪ እንደሚያስቀር አንስተዋል።

ይህንንም ማሳካት እንዲቻል በተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ  ገልጸዋል።

ለዚህም ከ32 ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞች ተመልምለው ወደ  ተለያዩ  አከባቢዎች ተደልድለዋል ብለዋል።

ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን በ2015 ዓ.ም የሙከራ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ በሙሉ ኃይል ወደ አገልግሎት መግባቱን ገልጿል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 22 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 2 , 2024

👉 ሶማሌያ በኢትዮጵያ ላይ ቁጣዋን ገለፀች ፤ በኢትዮጵያ የሚገኘውን አንባሳደሯንም በአስቸኳይ ጠርታለች

👉 የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ 5000 በላይ ሰዎችን አስሪያለሁ አለ ።

👉 በአርባምንጭ አካባቢ የተከሰተው ግጭት አሳሳቢ ደረጃ ስለመድረሱ 

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/l88HyRdgOpw

Читать полностью…

EthioTube

በቀጣይ ምዕራፍ ይጠብቁን !
https://youtu.be/v1ewbGSfZJ4

Читать полностью…

EthioTube

ፖሊስ በአዲስ አበባ በዚህ ወር ከ5000 ሰዎች በላይ አስሬያለሁ አለ።


በታህሳስ መጀመሪያ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ባካሄድኩት ዘመቻ ነው ሰዎቹን ያሰርኩት ብለዋል የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ትናንትና በጋራ በሰጡት መግለጫ። በርካታ ኤግዚቢቶችንም አብረን ይዘናል ሲሉ ሁለቱ የፀጥታ አካላት ገልፀዋል።

ታሳሪዎቹ የኅብረተሰብን ሰላም የሚያውኩ የቅሚያ፥ ዝርፊያ እና የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፀም ተጠርጠረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት እንደመግለጫው።

ከዚህም በዘለለ የቁማር ማጫዎቻ ቤቶች እና ሺሻ የሚሸጥባቸው ቤቶች ታሽገዋል፤ ከፍተኛ መጠን ያለው አደንዛዥ ዕፅም በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ።

ሕገ ወጥ የገንዘብ እና የጦር መሳርያ ዝውውርን በተመለከተ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም የፀጥታ አካላቱ የገለፁ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከመቶ በላይ ቁጥር ያላቸው ተንቀሳቃሽ ስልኮች በማስረጃነት ተይዘዋልም ተብሏል።

ከባንኮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ወደተላለዩ ሰዎች ስልክ እየደወሉ ያጭበረብሩ ነበሩ የተባለሉ ሰዎች እንዲሁም ባዕድ ነገሮችን ቀላቅለዋል ተብለው የተጠረጠሩም ከታሰሩት መካከል እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ፖሊስ በዘመቻ ያከናወነው ይህ እርምጃ ምን ያህል ዘላቂ ለውጥ እንደሚያመጣ ወደፊት የሚታይ ሲሆን በቅርብ ጊዜያት ግን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የአደገኛ ወንጀሎች መስፋፋት ስጋት እንደፈጠረባቸው ሲገልፁ መደመጣቸው ብርቅ አይደለም።

Читать полностью…

EthioTube

#Update

የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ፤ ዛሬ በነበረው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ፊርማ ወቅት ፤ ኢትዮጵያ ከስምምነቱ በኃላ " ለሶማሌላንድ ነፃ ሀገርነት እውቅና የምትሰጥ የመጀመሪያዋ ሀገር እንደምትሆን " በምላሹ ደግሞ ሶማሌላንድ ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር እና የባህር ኃይል ቤዝ እንዲኖራት በቀይ ባህር በኩል 20 ኪሎ ሜትር የሆነ መሬት ለኢትዮጵያ በሊዝ እንደምትሰጥ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያ ግን የሶማሊላንድን የነፃ ሀገርነት እውቅና እንደምትቀበል በይፋ አላረጋገጠችም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሶማሌላንዱ ፕሬዜዳንት ይህን ጉዳይ ሲናገሩ ከጎን ተቀምጠው የነበረ ቢሆንም ንግግራቸውን አልተቃረኑም።

ከዚህ በተጨማሪ የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ፤ በስምምነቱ መሰረት ሶማሌለንድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ እንደሚኖራት ዝርዝር ነገር ሳይገልጹ ተናግረዋል።

አጠቃላይ የዛሬው ስምምነት ዝርዝር ጉዳይ በአንድ ወር ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ለሶስት አስርት ዓመታት ዓለማቀፍ እውቅና ማግኘት ያልቻለች ራስ ገዝ ስትሆን ሶማሊያ ደግሞ አንድ አንድ የራሷ ክልል ነው የምታያት።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 22 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 1 , 2024

👉 ኢትዮጵያ የ BRICS አባልነቷን ዛሬ በይፋ  ጀመረች ።

👉 በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ታጣቂዎች ሰው ገድለው ሁለት ባንኮችን መዝረፋቸው ተነገረ ።

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/TVMRzS88fzU

Читать полностью…
Subscribe to a channel