ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሌ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ከህብረተሰብ ከተወካዮቹ ጋር መጠነ-ሰፊ ርዕይ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
አክለውም “ውይይታችን በልማት፣ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነበር” ብለዋል።
"ትናንት ብቻ ገደሉ 10 ጊዜ ያክል በታንክ ቢመታም ሊናድ አልቻለም"
👉 አንዳንድ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ የለቅሶ ስነ ስርዓት መፈፀማቸውንም ወረዳው አስታውቋል፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ወገል ጤና አካባቢ በማዕድን ቁፋሮ ላይ እንዳሉ ጉድጓድ ከገቡ 18ኛ ቀን የሆናቸውን ወጣቶች እጣፋንታ ለማወቅ የተደረጉ የህዝብና የመንግስት ጥረቶች እስካሁን እንዳልተሳኩ የደላንታ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ። አንዳንድ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ የለቅሶ ስነ ስርዓት መፈፀማቸውንም ወረዳው አስታውቋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ወጣቶቹን ከተቀበሩበት ጉድጓድ ለማውጣት በሰው ኃይል ሲያደርጉት የነበረው ሙከራ ባለመሳካቱ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር ለቁፋሮ እንቅፋት የሆነውን የአለት ክፍል በከባድ መሳሪያ ለማስወገድ የተለያዩ ሙከራዎች ሲደረጉ ቢቆይም የተገኘ ምንም ውጤት እንደሌለ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን ተናግረዋል፡፡
ሲደረግ የነበረውን ጥረት በተመለከተ ዋና አስተዳዳሪው፣ “በባባህላዊ መንገድ ቁፋሮዎች ለተከታታይ አንድ ሳምንት ያክል ሲካሄዱ ቆዩ፣ ግን ሌላ ናዳ በቆፋሪዎች ላይ ሊያስከትል የሚችል ስጋት በመፈጠሩ በሰው ጉልበት ሲደረግ የነበረው ቁፋሮ ቆመ ከዚያ ቀጥሎ ዞን፣ ክልልና ፌደራል መንግስት በጋራ ተነጋግረው በባለሙያዎች ተጠንቶ ተራራውን የሚንድ መሳሪያ እንዲመጣ ተደርጎ 35 ቶን የሚመዝን ተተኳሽ ተጠምዶ ተንጠልጣይ ቋጥኙን በፍንዳታ ለማስወገድ ቢሞከርም ሳይቻል ቀረ” ይላሉ አቶ አያሌው አክለው ዛሬም የአካባቢው የመከላከያ ኃላፊ፣ የዞን የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት ቋጥኙን በተለያዩ ተተኳሾች ለማስወገድ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ብለዋል፣ ትናንት ብቻ ቋጥኑ 10 ጊዜ ያክል በታንክ ቢመታም ቋጥኙን ማስወገድ አልተቻለም ብለዋል።
Via DW
ሚዛን አማን ድንገት በተነሳው እሳት የንብረት ውድማት ደርሷል
በሚዛን አማን ከተማ ህብረት ቀበሌ በተለምዶው ሀናን ካፌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
ዛሬ የካቲት 19/2016 ከንጋት ጀምሮ በተከሰተው የእሳት አደጋ የሃናን ካፌን ጨምሮ በአካባቢው ያሉ በርካታ ቁጥር ያሉት የንግድ ሱቆች መውደማቸው ታውቋል ።
የተከሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋን ለመቆጣጠር የአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ ሲያደርግ ማንጋቱን ነው ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን ድንገተኛ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና እና በሙያው የሰለጠኑ የሰው ሀይል ባለመኖሩ እሳቱን መቆጣጠር እንዳልተቻለ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት እሳቱ በቁጥጥር እየዋለ መሆኑን አቶ አብዱ ሙሃመድ በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል።
የአደጋው መንስኤና የደረሰ የውድመት መጠንም ገና አልታወቀም።
ፈረንሳያዊ ጋዜጠኛ እና አንድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባል መታሰራቸውን ሲፒጄ ገለጸ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አባል የሆኑትን በቴ ኡርጌሳን በስካይላይት ሆቴል ቃለ መጠይቅ በማድረግ ላይ የነበረው ፈረንሳያዊ ጋዜጠኛ መታሰሩን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ) አስታወቀ።
ጋዜጠኛው መቀመጫውን በፈረንሳይ ላደረገው 'አፍሪካ ኢንተለጀንስ' የተሰኘ የዜና ድህረ ገጽ ዘጋቢ ሲሆን የካቲት 14 ቀን 2016 ሲቪል በለበሱ ሰዎች መታሰሩን አዲስ ማለዳ ከሲፒጄ ድህረ ገጽ ተመልክታለች።
“እስሩ መሥረተ ቢስ እና ፍትሐዊ ያልሆነ ነው” ያለው ሲፒጄ “የአገሪቱ ባለስልጣናት ጋዜጠኛውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መልቀቅ አለባቸው” ሲል የመብት ተሟጋች ድርጅቱ አሳስቧል።
ይኽ እስር በአገሪቱ ያለውን "የፕሬስ ነጻነት አለመከበር ማሳያ ነው" ያለ ሲሆን በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች ስምንት ጋዜጠኞችም በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል ብሏል።
አንቷን ጋሊልዶ የተባለው ፈረንሳያዊ ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ በመጀመሪያ ቦሌ ሩዋንዳ የሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አስከትሎም ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መላካቸውን ጠቁሟል።
ቅዳሜ ዕለት በቦሌ ምድብ ችሎት ፊት የቀረበው ጋዜጠኛው “ከሁለቱ ታጣቂ ኃይሎች ማለትም በመንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በአማራ ክልል ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር በመሆን በመዲናዋ ሁከት እንዲፈጠር አሴሯል” በሚል መጠርጠሩ ተገልጿል።
የጋዜጠኛው ጠበቃ ክሶቹ ከባድ ቢሆኑም ፖሊስ እስካሁን ተጨባጭ ማስረጃዎችን ማቅረብ አሊያም ጋዜጠኛውን መክሰስ ነበረበት ማለቱን አንስቷል።
ጋዜጠኛው የዋስ መብቱን የጠየቀ ሲሆን ፖሊስ ሁለቱን ግለሰቦች ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ሲባል በእስር ላይ እንዲቆዩ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ለየካቲት 22 ቀን 2016 ቀጠሮ መስጠቱ ተገልጿል።
በዚህም ጋዜጠኛው እንዲሁም የኦነግ አባል የሆኑት በቴ ኡርጌሳ እስከ ቀጠሯቸው ቀን በእስር እንደሚቆዩ አዲስ ማለዳ ከዘገባው ተገንዝባለች።
ከአፍሪካ ህብረት ጀምሮ በኢትዮጵያ መሰንበቱ የተገለጸው ጋዜጠኛ ቪዛ ያለው እና በመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ስለ ቆይታው ያስታወቀ መሆኑ ተጠቁሟል።
ሲፒጄ በቅርቡ አደረኩት ባለው ቆጠራ መሰረት ስምንት ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት ሁለተኛዋ አገር ናት።
“በዝቋላ ገዳም አባቶች ላይ ለተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ከመንግሥት ፍትህን አንጠብቅም!”- እናት ፓርቲ
የካህናቱ ግድያ በገለልተኛ አካል ይመርመር- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
እናት ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዝቋላ ገዳም አባቶች ላይ ለተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ "ከመንግሥት ፍትህን አንጠብቅም" ሲል አስታወቀ።
“ብልጽግና መራሹ መንግሥት የእምነት ተቋማት በማይከበሩበት የሃይማኖት አባቶች እንደ ከብት በሚታረዱበት ወደፊት ታሪክ በጥቁር መዝገብ በሚጽፈው ዘመን ውስጥ የሕዝብን መከራ ማራዘሙን ተያይዞታል” ሲልም ፓርቲው ወቅሷል።
ዴሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶችን ማግኘት "እንደ ሰማይ እርቋል" የሚለው የእናት ፓርቲ መግለጫ ከሦስት አሥርት ዓመታት በላይ የዘለቀው የአብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎ፣ የክርስቲያኖችና የካህናት ግድያ ባለፉት አምስት ዓመታት "በተጠናከረና በተቀናጀ መልኩ" ቀጥሏልም ብሏል።
ፓርቲው ተጠናክሮ የቀጠለው የሃይማኖት አባቶቻችን አሰቃቂ ግድያ መሠረታዊ አገራዊ እሴቶቻችን ለመጣሳቸው ግልጽ ማሳያ ነው ማለቱን ኢትዮትዩብ ከመግለጫው ተመልክቷል።
በመሆኑም በአብዛኛው መንግሥት እየመራው የሚገኘው የአገራችን ፖለቲካ "አሻጥርን የተከተለ" በመሆኑ መንግሥትን ተስፋ አድርገን የምንጠይቀው ፍትህ ባይኖርም፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና የንጹሃን ደም ፍትሕ የሚያገኝበት ጊዜ እንደሚመጣ በእጅጉ ተስፋ እናደርጋለን ሲል ገልጿል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ካህናት ግድያ በገለልተኛ አካል ይጣራ ሲል ሌላኛው ተፎካካሪ ፓርቲ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ትላንት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
በመሆኑም ኦነግ "በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎችእና የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች በሁሉም መልኩ እንደሚያወግዝ" አመላክቶ "ጥፋትን በሌላ አካል ማላከክና ማጭበርበር ባለፉት አምስት ዓመታት የመንግስት የእለት ተግባሩ ቢሆንም ለዜጎች ግን ምንም አይነት ውጤት አላመጣም" ሲል ኦነግ መንግስትን ወቅሷል።
ኦነግ በመግለጫው "በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተፈጸመውን አሰቃቂ የአየርና የሰው አልባ አውሮፕላን ድብደባ እና የጅምላ ግድያ ቤተክርስቲያኒቱ ይህን አረመኔያዊ ድርጊት ከማውገዝ ተቆጥባለች ወይም መርጣ ተናግራለች" ብሏል።
በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን እንደ ሃይማኖታዊ ተቋም እጆቿን ከፖለቲካ እንድታስወጣና እንዲሁም በስልጣን ላይ ባለው ገዥ አካል እና በተቃዋሚዎቹ መካከል በሚከሰተዉ ግጭት ዉስጥ ከመግባት መቆጠብ አለባት ሲል ፓርቲው አሳስቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት መግቢያ ፊለፊት ላይ የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት እንደሚኖር ገልጿል።
ምኒሊክ አደባባይ የሚገኘው " የአፄ ምኒሊክ ሃይውልት ሊፈርስ ነው፤ ከቦታው ተነስቶ ወደ ሙዚየም ሊገባ ነው " የሚባለው ፍፁም ሀሰት ሲል ገልጿል።
የከተማው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰጡት ቃል ፤ " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎሜትር ፕሮጀክት የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊትለፊት ላይ ገና መግቢያው ላይ አለ፤ አዲስ ተጨምሮ። ያንን አዲስ የሚሰራ እንዴት ነው አሮጌውን የሚያፈርሰው ? ይሄ ያስኬዳል ? እንዴት ነው የበዓል ማክበሪያ ቦታ በዛ በኩል የሚደረገው ? " ሲሉ ተናግረዋል።
ከንቲባዋ ፤ " አፄ ምኒሊክ የራሱ ትክክል አይደለም የምንለው የሰራቸው ጥፋቶች አሉ ብለን እናምናለን። በዓድዋ ላይ ደግሞ የሰራቸው ትልልቅ ታሪኮች አሉ። አንድ የሆነ ጥፋት ካለ ሌላውን ሁሉ እውነት በዛ እንሸፍናለን ማለት አይደለም። የሆነ እውነት ካለ በጥፋቱ ሸፍነን እናያለን ማለት አይደለም። ታሪክን ጥፋትም ይኑር በጎ ገፅታውን ፣ መልካም ገፅታውንም እንዳለ እውነቱን ማስቀመጥ ነው ከእኛ የሚጠበቅ " ሲሉ ተናግረዋል።
" እኛ አልሰራነው፤ ለምን የአሁኑ ትውልድ መከራውን እንደሚያይ ብዙ አይገባንም። እኛ አልሰራነው ፤ ይሄ ትውልድ አልሰራው የጥፋቱንም የጀግንነት ፓርቱንም ይሄ ትውልድ አልሰራውም። ግን የራሱ ሃገር ታሪክ ነው፤ የራሱ ህዝብ ታሪክ ነው በመልካምነት የሚይዘውን ይኮራበታል፤ ይይዘዋል፤ ያሳይበታል። ትክክል አልነበረም የምንለውን አንደግመውም፤ በእኛ ዘመን መደገም የለበትም። " ብለዋል።
ከንቲባ አዳነች " አሮጌ አካባቢን ባደስን ቁጥር ቅርስ ፈረሰ ነው የሚባለው ይሄ አዲስ አበባ ላይ ትልቅ የልማት እንቅፋት ሆኖብናል " ሲሉ አክለዋል።
የ " ዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት ከጥቂት ቀናት በኃላ ለህዝብ ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግም፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 225 የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው አሳዳጊ የሌላቸው ሕጻናት ማዕድ ማጋራታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያ ፓስፖርቷን ወደ ዲጂታል ልትቀይር ነው ተባለ!
ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወደ ዲጂታል ሊቀየር እንደሆነ ተገልጿል፡፡የኢትዮጵያ የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በወረቀት የሚሰሩ ስራዎች ለሌብነት እና ሙስና ተገላጭ በመሆናቸው ወደ ዲጂታል አሰራር መቀየር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አገልግሎቱ ተቋማት ጋር ያሉ መረጃዎችን ማጣራት፤ የሰዎችን ማንነት ለመመርመር እንዲሁም ምዝገባዎች የሚያደርግበትን አሰራር ወደ ዲጂታል ለመቀየር እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ያሉ ሲሆን በዚህም የኢትዮጵያን ፓስፖርት ወደ ኢ- ፓስፖርት ወይም ዲጂታል ለመቀየር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም ይህንን ስራ ከሚሰራ የቴክኖሎጂ ተቋም ጋር ስምምነት በማድረግ እየሰራን ነው ያሉ ሲሆን በቅርብስራውን አጠናቀን ይፋ እናደርጋለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ለመቀነስ ፤አሰራሮችን በሙሉ ወደ ዲጂታል መቀየር ዋነኛው መፍትሄ መሆኑንም አክለዋል፡፡ የፓስፖርት ጉዳይ ሙስናን ጨምሮ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ይታዩበታል፡፡
ኢትዮጵያና ሶማሊያ ያደረጉት የመግቢያያ ስምምነት ህጋዊ አሳሪነት ባይኖረውም ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ነውጥ ያስነሳ መስሏል።
የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ የ20 ኪሎሜትር የባሕር ጠረፍ የሚያስገኝላት ሲሆን በምላሹም ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ ታገኛለች። የሶማሊላንድ ባለስልጣናት የስምምነቱ አንድ አካል ህጋዊ ዕውቅናን ከአዲስ አበባ ማግኘት ነው ቢሉም የኢትዮጵያ መንግስት የተግባቦት አገልግሎት ትናንትና ባወጣው መግለጫ ራሷን እንደነፃ አገር የምትቆጥረውን ሶማሊላንድን ዕውቅና እሰጣታለሁ ከማለት ተቆጥቧል። ከዚያ ይልቅ በጉዳዩ ላይ አቋም ለመያዝ የተጠና ምርመራ አደርጋለሁ ብሏል።
ሞቃዲሾ ግን ያለ እኔ ዕውቅና ከግዛቴ ጋር ድርድር ተደርጓል፥ የውሃ ድንበሬን ለመዝረፍ ተሞክሯል በሚል ቁጣዋን አሰምታለች። አምባሰደሯን ከመጥራትም በዘለለ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ መሃመድ አሁን አንድድሮው ደካማ አገር አይደለንም፤ ወሰናችንን ለመጠበቅ ሁሉንም ነገር እናደርጋለን የሚል ዛቻ የተቀላቀለበት ንግግር አድርገዋል። መንግስታቸው ኢትዮጵያን የፀብ አጫሪነት ድርጊት ፈፅማብናለች ሲሉም ወንጅለዋታል። ኢትዮጵያ በበኩሏ ከሶማሊላንድ ጋር ባደረገችው ንግግር የተጣሰ ህግ የለም ያለች ሲሆን ከዜናው በኋላ የተነሳውን ዲፕሎማሲያዊ አቧራ ለማርገብ በሚመስል ሁኔታ ባለስልጣናቷ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዲፕሎማቶችን ጠርተው ማብራሪያ እንዲሰጡ አድርጋለች።
ሶማሊያ በበኩሏ ወዳጆቿ ጋር በጉዳዩ ላይ ተከታታይ ውይይቶችን ያደረገች ሲሆን ከግብፅ እና ከአረብ ሊግ ከጎንሽ ነን የሚል ድጋፍን አግኝታለች። ካይሮ እና የአረብ አገራት ማኅበሩ ባወጧቸው መግለጫዎች የሶማሊያ የግዛት አንድነት መከበር እንዳለበት ወትውተዋል።
በሌላ በኩል ሁለቱም አገራት አባል የሆኑበት የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) አገራቱ ሰከን እንዲሉ ያወጣውን መግለጫ ሶማሊያ ለኢትዮጵያ ያደላ ነው ስትል አጣጥላዋለች። የድርጅቱ መሪ ኢትዮጵያ ምክትላቸው ደግሞ ሶማሊያዊ የሆኑበት ኢጋድ በሁለቱ አገራት ውጥረት አቋም ላለመውሰድ የጣረ ቢመስልም ሶማሊያ የግዛት አንድነቴ እንዲከበር አላሰሰበም፥ የኢትዮጵያን ድርጊትም አላወገዘም ስትል መግለጫውን እንዲሰርዝና መሪውም ይቅርታ እንዲጠይቁ አሳስባለች።
በዚህ መኃል የዲፕሎማሲያዊ ውጥንቅጡ ማዕከል የሆነችው ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት መከበር እንዳለበት የሚያሳስብ መግለጫ አውጥታለች። ሃርጌሳ በተባለችው ከተማዋ ነዋሪዎች ለስምምነቱ ያላቸውን ድጋፍ በሰልፍ የገለፁ ሲሆን በተቃራኒው በሶማሊያዋ መዲና ሞቃዲሾ ኢትዮጵያን የሚያወግዙ ሰልፈኞች አደባበይ መውጣታቸውን የአገሬው የብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።
የመግባቢያ ሰነዱ በትክክል ወደአስገዳጅ ውልነት ተቀይሮ በፊርማ የሚፀድቀው መቼ እንደሆነ ባይታወቅም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሊሆን እንደሚችል የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጠቆም አድርገዋል። ያኔ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ያህል ድርሻ ሶማሊላንድ ትወስዳለች፥ የይፋዊ ዕውቅናውስ ነገር ምን ይሆናል የሚለው ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።፥ እስከዚያው ድረስ ግን ውጥረቱ እያየለ የሚቀጠል መስሏል።
አሜሪካ ፤ በ 1960 ለተካለለዉ የሶማሊያ ድንበር እዉቅና ሰጣለሁ አለች
👉🏼በዚህ ድንበር መሰረት ሶማሊላንድ የሶማሊያ ግዛት ናት
ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተፈመዉ የወደብ አገልግሎትን የማግኘት ስምምነት ጉዳይ የአፍሪካ ህብረት ፣ የአረብ ሊግ እንዲሁም አጎራባች ሀገራት ጭምር ጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እየሰጡ አቋማቸዉንም እየገለጡ ነዉ።
የአረብ ሊግ ትናንት ማምሻዉን ባወጣዉ መግለጫ ለሶማሊያ ባደላ መልኩ ስምምነቱ ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ ሲል አጣጥሎታል። በአንጻሩ የአፍሪካ ህብረት ማለዳዉን ባወጣዉ መግለጫ ለየትኛዉም ጎራ ባልወገነ መልኩ ሁለቱ አካላት በንግግር ጉዳያቸዉን መፍታት እንዳለባቸዉ አሳስቦ ፤ የሶማሊያ ግዛት ግን ሊከበር ይገባል ብሎ ነበር።
በትናንትናው እለት የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ማቴዉ ፔሪ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ ሰሞነኛዉ የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ የወደብ ስምምነት ላይ አሜሪካ ያላትን አቋም ምን እንደሆነ እንዲያሳዉቁ ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ነበር።
ማቴዉ ፤ አሜሪካ የቀጠናዉ ሰላም እንደሚያሳስባት ተናግረዉ ሁለቱ ሀገራት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳያቸዉን በዲፕሎማሲያዊ ንግግር መፍታት አለባቸዉ ሲሉ መክረዋል።
አያይዘዉም አሜሪካ እ.ኤ.አ በ 1960 የተካለለዉ የሶማሊያ ግዛት እንዲከበር ትጠይቃለችም ብለዋል። አሜሪካ የሶማሊያ ሉዓላዊ ግዛት እዉቅና እንደምትሰጥም ተናግረዋል። በዚህም ድንበር መሰረት ሶማሊላንድ የሶማሊያ ግዛት መሆናን ዳጉ ጆርናል በወቅቱ ከተካለለዉ የድንበር ካርታ ላይ ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ የወደብ ስምምነት ዉዝግብ እያስነሳ ቢሆንም በሀርጌሳ እና አዲስአበባ መንግስታት በኩል ከዚህ በተቃራኒ በሆነ መልኩ ስምምነቱ ተፈጻሚ እንደሚሆን አስታዉቀዋል።
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ረቡዕ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 24 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 3 , 2024
👉 የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።
👉 ከቀጣይ አመት ጀምሮ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል የፈተና ምዝገባ የሚደረገው በዲጅታል መሆኑ ተገለፀ።
👉 በአሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጠችው የሶማሌ-አሜሪካዊቷ ከንቲባ ቃለ መሃላ ፈጸመች
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/pbx44B-Bc0A
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ ሰጡ
ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲላፕሎማሲው መስክ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት መካከል እያታየ ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።
ኢጋድ ሁኔታውን በንቃት እየተከታተለ መሆኑን እና በቀጠናው መረጋጋት ላይ ያለውን ተፅእኖ እንደሚገነዘብ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁኔታዎችን በሰላማዊ እና በመግባባት መንፈስ ለመፍታት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር ወርቅነህ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ስለተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ያነሱት ነገር የለም።
የሶማሊያ መንግሥት የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ እንዳበሳጨው ለመረዳት ተችሏል።
የሶማሊያ መንግሥት " የመግለጫው ሃሳብ ለኢትዮጵያ ያደላ ነው " በማለት ዶ/ር ወርቅነህ በአስቸኳይ ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ የይቅርታ መግለጫም በማውጣት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ ብሏል።
ሶማሊያ ፤ የኔ አንድ ግዛት ናት በምትላት ሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል የተረፈመው ስምምነት ያበሳጫት ሲሆን ስምምነቱ የግዛት አንድነቴን እና ሉዓላዊነትን የጣሰ ነው በማለት እየተቃወመች ትገኛለች።
የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዜዳንቱና ልኡካቸው ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት ሲደርሱ የሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ ባለስጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሁለቱም በኩል ያሉ ባለስልጣናት የንግድ ትብብርን በተመለከተና በድንበር የፀጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች (በሶማሌ ክልል እና በሶማሌላንድ) ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።
የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ከተማ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን እውን ያደርጋል የተባለለንትን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው አይዘነጋም።
ከቀጣይ አመት ጀምሮ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል የፈተና ምዝገባ የሚደረገው በዲጅታል መሆኑ ተገለፀ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከቀጣይ አመት ጀምሮ የፈተና ምዝገባ የማደርገው በዲጅታል ነው ብሏል።
አገልግሎቱ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በጋራ በሰጠው መግለጫ ነው ይሄን ያስታወቀው።
በየአመቱ በሃገር አቀፍ እና የክልል አቀፍ የፈተና ምዝገባዎች ሲደረጉ አገልግሎቱ በርካታ ሚሊየን ግብሮችን እንደሚያወጣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ተናግረዋል።
አሁን የፈተና አገልግሎቱ የፈተና ምዝግባዎችን በዲጅታል እንዲደረጉ የሚያደርግ በመሆኑ ይሄን ወጪ እንደሚያስቀር አንስተዋል።
ይህንንም ማሳካት እንዲቻል በተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ለዚህም ከ32 ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞች ተመልምለው ወደ ተለያዩ አከባቢዎች ተደልድለዋል ብለዋል።
ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን በ2015 ዓ.ም የሙከራ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ በሙሉ ኃይል ወደ አገልግሎት መግባቱን ገልጿል።
እስራኤልና ሃማስ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ።
የእስራኤልና ሃማስ አመራሮች ከኳታር እና አሜሪካ አደራዳሪዎች ጋር በተናጠል ግን በተመሳሳይ ከተማ (ዶሃ) እያካሄዱት ያለው ንግግር ተስፋ ሰጪ ነው ተብሏል።
እስራኤል እስከ ረመዳን ፆም መግቢያ የተኩስ አቁም ስምምነት ካልተደረሰ በራፋህ ጦርነት እጀምራለሁ ማለቷም ድርድሩ እንዲፈጥን ማድረጉ ተገምቷል።
"የብሄራዊ ደህንነት አማካሪዬ ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባችን ነግሮኛል፤ ያላለቁ ጉዳዬች ቢኖሩም እስከ ቀጣዩ ሰኞ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚደረስ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንት ባይደን።
የአሜሪካ አደራዳሪዎች እስከ መጋቢት 10 ድረስ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሶ የታጋች እና እስረኞች ልወውጥ እንዲጀመር ግፊት እያደረጉ ነው።
እስራኤልና ሃማስ ግን ለተኩስ አቁም ድርድሩ መጓተት እርስ በርስ መካሰስና የጋዛው ጦርነት መቀጠሉ አይቀሬ መሆኑን የሚያሳዩ ንግግሮችን ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የባንክ ሰራተኞች ወደ አውቶብስ ተርሚናል እንዳይገቡ ተባለ
የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መርካቶ አውቶቡስ ተርሚናል የተለያዩ ባንክ ሰራተኞች ሕብረተሰቡን አካውንት እናወጣለን በማለት ምክንያት የሕዝብ መገልገያ የሆነውን ወንበር ለብዙ ሰዓታት ሕዝብ እንዳይቀመጥበት በማድረግ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ ማንኛውም የባንክ ሠራተኛ ወደ ተርሚናሉ ገብቶ አካውንት ማስከፈት የማይፈቀድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን ብሏል።
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - የካቲት 18 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - February 26 , 2024
👉 ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ የኦነግን ባለስልጣን ኢንተርቪው በመስራቱ ታሰረ
👉 ከ20 በላይ ሰዎችን የቀጠፈው የመኪና አደጋ
👉 የመከላከያ ሰራዊት በባህር ዳር የፈፀመው
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/4rzUxGrqGQI
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በባሕር ዳር ከተማ እስከ “የጦር ወንጀል” ሊደርሱ የሚችሉ “ብርቱ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግ ጥሰቶች” መፈጸማቸውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምርመራ ውጤት ይፋ አደረገ።
የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ በሁለት የተለያዩ ወቅቶች የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአማራ ክልል ዋና ከተማ በትንሹ ዐሥራ ሁለት ሰዎች “ከሕግ ውጪ” መግደላቸውን የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ዛሬ ሰኞ የካቲት 18 ቀን፣ 2016 ይፋ አድርጓል።
በመስከረም 2016 እና ነሐሴ 2015 ተፈጽመዋል የተባሉ ግድያዎችን የሠነደው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምርመራ ውጤት “ከእኛ ጋር ሳይሆን ሊፋለሟቸው ከመጡት አካላት ጋር የሚዋጉ መስሎን ነበር” የሚል ርዕስ የተሰጠው ነው።
የድርጅቱ የአፍሪቃ ቀንድ ጽህፈት ቤት ባልደረባ ሱዓድ ኑር “ይኸ ርዕስ የ20 ዓመት ወንድ ልጇ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጭንቅላቱ ላይ ተመትቶ ከተገደለባት ለምለም ከተባለች እናት የወሰድንው ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ሱዓድ ኑር “እነዚህ ቃላት ከእርሷ ምስክርነት የተወሰዱ፣ ለዚህ ምርመራ ባነጋገርናቸው እና የማያውቁት ጦርነት ሰለባ የሆኑ በርካታ እማኞች የተደጋገሙ ናቸው” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል።
በአምነስቲ የምርመራው ውጤት መሠረት ነሐሴ 2 ቀን፣ 2015 በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ውስጥ በሚገኙት አቡነ ሀራ እና ልደታ የተባሉ አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት አባላት “ከሕግ ውጪ” ከተገደሉ ስድስት ሰላማዊ ሰዎች መካከል ወይዘሮ ይታጠቁ አያሌው ይገኙበታል።
ከልደታ አቅራቢያ በሚገኝ የመኖሪያ ቤታቸው እንጀራ በመጋገር ላይ የነበሩት ይታጠቁ ወታደሮች ወደ ቅጥር ግቢያቸው በተኮሱት ጥይት ተመትተው መገደላቸውን ዘመዳቸው ቢኒያም የተባለ የዐይን እማኝ ለአምነስቲ አስረድቷል።
በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት የ55 ዓመቱ አዛውንት አየነው ደፍረሽ በተመሣሣይ ቀን ካሳሁን እና አብርሐም ከተባሉ ሁለት ልጆቻቸው ጋር ከቤተ-ክርስቲያን በመመለስ ላይ ሳሉ እንደተገደሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምርመራ ውጤት ያሳያል።
አንድ የጥይት ድምፅ የሰማ የቤተሰቡ አባል ለአቶ አየነው ስልክ ደወሎ ለማናገር ሲሞክር የመከላከያ ሰራዊት ወታደር ሳይሆን አይቀረም ብሎ የጠረጠረው አንድ ግለሰብ ስልኩን አንሰቶ “የደረሰው አደጋ ትንሽ ነው” ብሎ እንደመለሰለት ለመርማሪዎቹ ተናግሯል።
የአየነው የቤተሰብ አባላት በስተመጨረሻ ሦስቱን አስከሬኖች ከጎዳና እንዳነሱ ሪፖርቱ ይጠቁማል። የዐይን እማኞች እና ቤተሰቦች እንደተናገሩት ሁሉም ሟቾች “ከቅርብ ርቀት በተተኮሰ ጥይት” መገደላቸውን ይኸው የምርመራ ውጤት አትቷል።
ግድያው በተፈጸመበት የነሐሴ ወር የመጀመሪያ ሦስት ቀናት የባሕር ዳር ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ብርቱ ውጊያ አስተናግዳለች። በባሕር ዳር በመከላከያ ሠራዊት “ከሕግ ውጪ” ተፈጸመ የተባለው ግድያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለይ በአማራ ክልል ተፈጻሚ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በደነገገ በጥቂት ቀናት ልዩነት የተከሰተ ነው።
በባሕር ዳር ዳግም ግጭት በተቀሰቀሰበት ወቅት ሰባት አሚት በተባለ የከተማዋ ክፍል መስከረም 29 እና 30 ቀን፣ 2016 አምስት ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች በመከላከያ ሠራዊት አባላት መገደላቸውን የአምነስቲ ምርመራ ይፋ አድርጓል። የምርመራው ውጤት እንደሚያሳየው ከሟቾቹ መካከል “በጤና ጣቢያ ውስጥ ከሕግ ውጪ የተገደለ ታካሚ ይገኝበታል።”
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ከ መስከረም መጀመሪያ እስከ ጥር ወር መጨረሻ ተፈፅሟል ያለውን ሰብአዊ ጥሰት በተመለከተ ያወጣው ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፤ በኦሮሚያ ክልል በተለይ ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት 2 ዓመታት ያደረገውን ክትትል እና ምርመራ መሠረት በማድረግ ከሕግ/ከፍርድ ውጪ የሆኑ እና በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ መሆናቸውን በማመላከት በተለይ የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጡ ጥሪ አድርጓል።
ይህን ጥሪ ያደረገው የሁለቱን ዓመታት ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ባለ 11 ገጾች ሪፖርት ነው።
ኢሰመኮ ፦
➡ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣
➡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” በመባል የሚጠራው)
➡ ኢ-መደበኛ የሆኑ የአማራ ታጣቂዎች ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎችን በመጣስ በግጭት ወይም በውጊያ ዐውድና ከውጊያ ዐውድ ውጭ በርካታ ሲቪል ሰዎችን ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን አረጋግጧል።
በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ለሚደርስ የመብቶች ጥሰት እንደ ዋነኛ ምክንያት የተገለጸው ፦
* በመንግሥት የጸጥታ አካላት በኩል " ለታጣቂ ቡድኖች መረጃ እና ሎጂስቲክስ ታቀርባላችሁ፤ የቡድኑ አባል ናችሁ " በሚል ምክንያት ነው።
* በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ "ኦነግ ሸኔ") በኩል " ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ በመንግሥት ጸጥታ ኃይል ውስጥ እያገለገለ ነው ወይም ከእኛ ጋር በመሆን አልታገላችሁም/ድጋፍ አላደረጋችሁም " በሚል ምክንያት ሲቪል ሰዎችን ማጥቃት፣ ማንገላታት፤ ማገት እና ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማድረግ ነው።
* በኢ-መደበኛ የአማራ ታጣቂዎች ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች በጅምላ " በኦነግ ሸኔነት " በመፈረጅ እና የክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን በማንሳት በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ዘረፋ እና ማፈናቀል እንደሚፈጸም ኮሚሽኑ ተገንዝቧል፡፡
(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)
ኢትዮጵያ፦ የእለተ አርብ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 25 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 5 , 2024
👉 ሰሞኑን በከተማዋ መነጋገሪያ የነበረውን ሚኒሊክን ሃውልት አስመልክቶ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያወጣው መረጃ
👉 ኢትዮጵያ ፓስፖርቷን ወደ ዲጂታል ልትቀይር ነው ስለመባሉ
👉 በዩናይትድ ስቴትስ አዮዋ ግዛት በሚገኝ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጀመሪያው የትምህርት ቀን አንድ ተማሪ ስድስት ሰዎችን በጥይት መትቶ እራሱን ማጥፋቱም ተሰምቷል
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/WIV4AlqSa4w
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አቅንተዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን በትናንትናው እለት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ማምራታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሚኒስትሩ ወደ መካከለኛ ምስራቅ ያመሩት በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተጀመረው ጦርነት ወደ ቀጣናው ይስፋፋል የሚል ስጋት ባየለበት ወቅት ነው።
ይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለሳምንት የሚቆየው ጉዞ፣ ሀማስ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ካደረሰበት ከፈረንጆቹ ጥቅምት 2023 ወዲህ ለአራተኛ ጊዜ ነው።
ሚኒስትር እስራኤል እና ዌስትባንክን ጨምሮ ጆርዳንን፣ ኳታርን፣ ሳኡዲ አረቢያን፣ አረብ ኢምሬትስን እና ግብጽን ይጎበኛሉ ተብሏል። ከጦርነቱ በኋላ ጋዛ እንዴት መተዳደር አለባት በሚለው አስቸጋሪ ጉዳይ መሻሻል መኖሩን የጠቀሱት ብሊንከን ተጨማሪ የሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል።
ብሊንከን ጉዞ ያደረጉት በሀማስ ምክትል የፖለቲካ መሪ ሳለህ አል አሮሪ ላይ የደረሰው ጉድያ፣ ግጭቱን ቀጣናዊ ያደርገዋል የሚል ስጋት ከተፈጠረ በኋላ ነው።
ከእስራኤል ጋር የተኩስ ልውውጥ እያደረገ ያለው በኢራን ይደገፋል የሚባለው የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ ዝቷል።
የእስራኤል እና ሀማስ ግጭት ወደ ቀይ ባህር ተስፋፍቶ መፋጠጥ ፈጥሯል። የሀማስ አጋር የሆኑት እና አብዛኛውን የየመን ክፍል የተቆጣጠሩት የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ 20 መርከቦች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል።
በጋዛ መጠነሰፊ ጥቃት እያካሄደች ያለው እስራኤል ጦርነቱ ለወራት ሊቆይ እንደሚችል ገልጻለች።
በዩናይትድ ስቴትስ አዮዋ ግዛት በሚገኝ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጀመሪያው የትምህርት ቀን አንድ ተማሪ ስድስት ሰዎችን በጥይት መትቶ እራሱን አጠፋ።
ፖሊስ እንዳለው በጥይት ከተመቱት ስድስት ሰዎች መካከል አንዱ ሕይወቱ አልፏል።
በፔሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ "በቀላሉ ተዘጋጅቶ" የተቀበረ ፈንጂ መገኘቱንም ፖሊስ ተናግሯል።
ጥቃት ከደረሰባቸው አምስቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አንደኛው የትምህርት ቤት አስተዳዳሪ ናቸው።
ህይወቱ ያለፈው ተማሪ የ11 እና 12 ዓመት ታዳጊዎች የሚማሩበት የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ነበር።
ጠዋት ላይ የተኩስ ጥቃት መኖሩ እንደተሰማ የመጀመሪያው የፖሊስ መኮንን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ቦታው መድረሱን ፖሊስ ተናግሯል።
የአዮዋ የወንጀል ምርመራ ዲቪዥን ረዳት ዳይሬክተር ሚች ሞርትቨ ከጥቃቱ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፖሊሶች ሲደርሱ ተጠርጣሪው ራሱን አቁስሎ አግኝተውታል።
ተጠርጣሪው ዲላን በትለር የተባለ የ17 ዓመት ተማሪ መሆኑ ታውቋል። ፖሊስ እንዳለው ትልቅ መሣሪያ እና ትንሽ የእጅ ሽጉጥ ታጥቆ ነበር።
ሞርትቨ አክለውም ተጠርጣሪው "ጥቃቱ በፈጸመበት ወቅት በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፎችን ለጥፏል" ብለዋል።
ከቆሰሉት መካከል አንዱ በአስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን አራቱ ደግሞ ጉዳታቸው ለሕይወታቸው አደጋ አይደለም ብለዋል የፖሊስ መኮንኑ።
የዳላስ ካውንቲ ሸሪፍ አደም ኢንፋንቴ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ጊዜው ጠዋት በመሆኑ “እንደ ዕድል ሆኖ በጣም ጥቂት ተማሪዎች እና መምህራን ነበሩ። ይህም የተጠቂዎችን ቁጥር አነስተኛ እንዲሆን አስተዋጽኦ አድርጓል ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሀሙስ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 24 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - January 4 , 2024
👉 ደብረ ብርሃን ግጭትን ማስተናገዷ ተዘገበ።
👉 አሜሪካ ፤ በ 1960 ለተካለለዉ የሶማሊያ ድንበር እዉቅና ሰጣለሁ አለች
👉 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኢትዮጵያና በሶማሌላንድ ስምምነት ጉዳይ ማምሻውን የሰጡት መግለጫ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/HDHr-yIt74M
ደብረ ብርሃን ግጭትን ማስተናገዷ ተዘገበ።
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን መዲና የሆነችውና ከአዲስ አበባ ከአንድ መቶ ሃምሳ ኪሎሜትር የማይበልጥ ርቀት ያላት ደብረብርሃን በታጣቂዎች እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መካከል ግጭትን ያስተናገደችው ትናንትና እንደነበረ ተዘግቧል። እስካሁን በግጭቱ ስለሞቱ ሰዎች ቁጥር በቁርጥ የታወቀ ነገር የለም። ይሁንና የተለያዩ የዓለምአቀፍ የብዙሃን መገናኛዎች ነዋሪዎችን ጠቅሰው እንደዘገቡት ታጣቂዎች ወደከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች መግባታቸውን ተከትሎ ነው ግጭቶቹ የተቀሰቀሱት። ትናንትና አመሻሽ ላይ ወደከተማዋ መረጋጋት ቢመለስም መደበኛ እንቅስቃሴዎች ግን ወዲያው አልቀጠሉም ነበር ተብሏል።
መንግስት በአማራ ክልል ከታጣቂዎች ጋር ፍልሚያ የጀመረው ካለፈው የክረምት አጋማሽ አንስቶ ነው። ከዚያም ወዲህ ክልሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር የሚገኝ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎትም ተቋርጦበታል። መንግስት አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት ወደክልሉ ተመልሷል ቢልም አሁንም ግጭቶች እና ጥቃቶች በተለይ በመጠን አነስ ባሉ ከተሞች መዘገባቸው አልቀረም።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ማምሻውን የሰጡት መግለጫ
በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የተፈጠረውን ውጥረት በቅርበት ሲከታተሉ እንደነበር የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ሌሊቱን በህብረቱ በኩል ባሰራጩት መግለጫ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መንግስታት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማርገብ መረጋጋት እና መከባበር እንዲኖር ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህ ረገድ ሁለቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በመካከላቸው ያለው መልካም ግንኙነት ወደ መበላሸት ከሚያመራ ከማንኛውም ተግባር እንዲታቀቡ አሳስቧል።
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ከሶማሌላንድ ጋር ስለተፈረመው የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሰነድ በዛሬው እለት ማብራሪያ ሰጥቷል።
በሰጠው ማብራሪያም፤
ስምምነቱ ለኢትዮጵያ በኤደን ባህረሰላጤ ላይ ዘላቂና አስተማማኝ የባሕር ኃይል ቤዝ እና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት በሊዝ የምታገኝበትን ዕድል የሚያስገኝ መሆኑን አስታውቋል፡፡
መንግሥት አስቀድሞ ይፋ ባደረገው አቋሙ መሠረት ሶማሌ ላንድን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሊዙ የሚታሰብ ድርሻ እንዲኖራት ያስችላል ብሏል መግለጫው።
ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል
በአሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጠችው የሶማሌ-አሜሪካዊቷ ከንቲባ ቃለ መሃላ ፈጸመች
በዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ ግዛት በሚገኘው የሴንት ሉዊስ ፓርክ ከተማ ምክር ቤት የ27 ዓመቷን ናዲያ መሀመድን ከንቲባ አድርጎ ቃለ መሃላ ፈፅሟል። በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሶማሌ-አሜሪካዊት ከንቲባ ሆና ከሁለት ወራት በፊት መመረጧ ይታወሳል።
ናዲያ መሀመድ ባለፈው ህዳር የተካሄደውን የከንቲባ ምርጫ 58 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት አሸንፋለች። በከተማዋ በእድሜ ትንሿ እና የመጀመሪያዋ ጥቁር ከንቲባ መሆን ችላለች። ከማንነቴ በላይ መታወቅ እፈልጋለሁ ስትል ተናግራለች።
ማንነቴ የታሪኬ አንዱ አካል ነው፣ እኔ ባለኝ ነገር ሁሉ እኮራለሁ፣ ነገር ግን ያ ብቸኛው ታሪኬ እንዲሆን አልፈልግም። ያ ሰዎች ንግግራቸውን የሚያቆሙበት እንዲሆን አልፈልግም ስትል ናዲያ መሐመድ ከተመረጠች በኋላ በሚኒያፖሊስ ለሚገኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግራለች። እንደ ከንቲባ ሆና ልታደርጋቸው ካቀዳቸው ቁልፍ ጉዳዮች መካከል የህዝብ ደህንነት እና ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ማቅረብ መሆኑን አንስታለች። ናዲያ ሞሃመድ የ23 ዓመት ወጣት እያለች በ2019 ለከተማው ምክር ቤት ተመርጣለች።
ቤተሰቦቿ በሶማሊያ ያለውን ጦርነት ሸሽተው በ10 ዓመቷ ከኬንያ ካኩማ የስደተኞች ካምፕ የገቡ ሲሆን ከዛም ወደ ሚኒሶታ አቅንተዌ። እ.ኤ.አ. በ2021 ዴቃ ዳልክ በሜይን ግዛት በደቡብ ፖርትላንድ ከተማ የምክር ቤት አባላት የመጀመሪያው ሶማሌ-አሜሪካዊ ከንቲባ ሆኖ መሾሙ ይታወሳል። ነገር ግን የናዲያ መሐመድ ምርጫ የሚለየው በሕዝብ የተመረጡ የመጀመሪያው ሱማሌ-አሜሪካዊት ከንቲባ ያደርጋታል።
ግብፅ በፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ቃል አቀባይ በኩል ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት ገልጻለች።
የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሼክ ሀሰን ሞሀሙድ ፤ ትላንት ምሽት ወደ አል ሲሲ ስልክ ደውለው ከሁለት ሳምንት በፊት ላሸነፉት ምርጫ " እንኳን ደስ አልዎት " ብለዋል። የስልክ ውይይቱን ተከትሎ የግብፅ ፕሬዜዳንት ቃል አቀባይ ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን ታሪካዊ ግንኙነታቸውን መሰረት በማድረግ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የጋራ ትብብርን ለማጎልበት መወያየታቸውን ገልጸዋል።
አል ሲሲ ግብፅ ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት መግለፃቸው ተነግሯል። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ከአል ሲሲ በተጨማሪ ለኳታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ስልክ ደውለው ነበር። ከኳታሩ ኤሚር ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችሉ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የጋራ ጥቅሞችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተሰምቷል።
አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ መግለጫ ሰጠ
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ አጭር መግለጫን ትላንት ምሽት አውጥቶ ነበር።
በዚህ መግለጫው፤ እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ የባህር በር አገልግሎት (በሊዝ) ማግኘት የሚያችላትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል ብሏል።
ቀጠል አድርጎ ፦ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት ፣ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተሮችን መሰረት በማድረግ የሶማሊያን አንድነትን ፣ ሉዓላዊነትን እና የግዛት አንድነትን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን ለማስታወስ እንፈልጋለን ብሏል።
ይህ ለመላው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላምና መረጋጋት ቁልፍ ጉዳይ ነው ሲል ገልጿል።