ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube
አርቲስት እፀህይወት አበበ የዋዋ ዳይፐር ብራንድ አምባሳደር ሆና ተፈራረመች
በተዋናይነት ፣በሞዴሊንግ፣ በፕሮዲሰነርት፣ እንዲሁም የተለያዩ ቢዝነሶች ባለቤት የሆነችው አርቲስት እፀህይወት አበበ ከ12 አመታት ቆይታ በኃላ ክሊን ማቴሪያልስ ከሚያመርታቸው ምርቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን ዋዋ ዳይፐር ብራንድ አምባሳደር በመሆን በከፍተኛ ገንዘብ ተፈራርማ ወደ ኢንደስትሪው ብቅ ብላለች ።
ዋዋ ዳይፐር ክሊን ማቴሪያልስ ከሚያመርታቸው የህፃናት ዳይፐር አንዱ ሲሆን የሁለት ልጆች እናት የሆነችው አርቲስት እፀህይወት አበበ በአምባሳደርነት ሲመርጥ አርቲስቷ በምትታወቅበት የትወና እና የቢዝነስ ስራዎቿ ለስኬት የበቃችበትን ጠንክሮ የመስራት እና ህልሟን የማሳካት ጥረት ለብዙ እናቶች ተምሳሌት ይሆናል ብለን በማመን ነው ስትል የክሊን ማቴሪያልስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሀይረያ አህመድ ገልጻለች::
በብራንድ አምባሳደር ስምምነት ዝግጅቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን አርቲስቷ የዋዋ ዳይፐር አምባሳደር በመሆኗ እንደ እናት እንዲሁም እንደምርቱ ጥራት ካላት እውቅና ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን በመግለፅ ከድርጅቱ ጋር የበጎ አድራጎት ስራዎችን እንደምትሠራ በተዘጋጀው መድረኩ ላይ ገልፃለች።
አነጋጋሪው የባለሀብቱ Ambani ልጅ ሰርግ በህንድ
በህንድ ሀገር በሀብቱ ቀዳሚ የሆነው የቢሊየነሩ የambani ልጅ anant ambani pre wedding ወይንም የሰርግ ቅደመ ዝግጅት እየተካሄደ ነው
በዚህም የዓለማችን ቢሊዮነሮች ህንድ ገብተዋል
👉 የፊስቡክ መስራች ማርክ ከእነ ሚስቱ
👉 ቢል ጌትስ
😳 ለመዝፈን ብቻ 9 ሚሊዮን ዶላር ወጥቷል
ወደ ብር ሲመነዘር በባንክ
* 139 ሚሊዮን 142 ሺህ 701 ብር ከ89 ሳንቲም የተከፈላት ድምፃዊት ሪሀና
* የትራምፕ ልጅ ኢቫንካ
* ሻሩክ
* ሰልማን
እና ሌሎችም ሲሆን
ለዚህ ለሰርግ ቅድመ ዝግጅት ብቻ 120 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወደ ብር ሲመነዘር በባንክ ምንዛሬ:-
* 1 ቢሊዮን
* 855 ሚሊዮን
* 236 ሺህ
* 025 ብር
* ከ20 ሳንቲም
ወጪ እንደሚሆን ይገመታል
ይሄ ሁሉ ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ለሰርጉ ቅደመ ዝግጅት ሲሆን ሌላ ዋናው ሰርግ ደሞ ከዚህ በላይም ወጪ ሊያስወጣም ይችላል::
ብዙዎቹ የዓለማችን እደለኛዋ ሙሽሪት እያሏትም ይገኛል::
ከሸዋ ሮቢትና ከሚሴ በስተቀር የሰሜን ምስራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች፣ መቀሌ እና ሠመራ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል ተባለ
የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከባህር ዳር - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው መስመር ተበጥሶ ኃይል መቋረጡን አስታወቀ።
ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመበጠሱ በአካባቢዎቹ ኃይል ተቋርጧል የተባለ ሲሆን የመበጠሱ ምክንያት አልተገለጸም።
በተጨማሪም ከደብረ ብርሃን - ሸዋሮቢት - ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ በመበጠሱ ከሸዋ ሮቢትና ከሚሴ በስተቀር አብዛኛዎቹ የሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መብራት የለም ተብሏል።
በዚህም ሳቢያ ከኮምቦልቻ በባቲ በኩል ኤሌክትሪክ ኃይል የሚደርሳቸው የአፋር ክልል መዲና ሠመራና የተለያዩ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም በወልዲያ አላማጣ መስመር ኃይል የሚያገኙት የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ከተሞች ኃይል እንደተቋረጠባቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ረቡዕ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - የካቲት 20 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - February 28 , 2024
👉 ራያ ቆቦ የተገደሉት ባለስልጣናት
👉 በሩቶና አብይ ድንገት ሳይሰጥ የቀረው ጋዜጣዊ መግለጫ
👉 የታሰረው ጋዜጠኛ እውነት ፕሬዝዳንቱ ኬንያ ገብተዋ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/Iazv4i_r_rE
የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ኬንያ፣ ናይሮቢ ገቡ።
ፕሬዝዳንቱ ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ኤርፖርት ሲደርሱ የኬንያ ምክትል ፕሬዜዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ ተቀብለዋቸዋል።
ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ኬንያ የገቡት በኬንያ በሚካሄድ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ (UNEA-6) ስብሰባ ላይ ለመካፈል ነው።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም ለይፋዊ ስራ ጉብኝት ኬንያ እንደሚገኙ ይታወቃል።
በቅርቡ ከኢትዮ-ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ቅራኔ ውስጥ የገቡት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ናይሮቢ ውስጥ ተገናኝተው ይወያዩ እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም።
ኬንያ ሁለቱን መሪዎች ለማቀራረብ ጥረት እያደረገች እንደሆነም የሚታወቅ ነገር የለም።
የአፍሪካ ልማት ባንክ ስጋትና በናይጄሪያ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ናይጄሪያ፣ አንጎላ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ያለው የኃይል፣ የምግብ እና ሌሎች ሸቀጦች ዋጋ መናር በሀገራቱ ውስጥ አለመረጋጋት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠንቅቋል።
ባንኩ በዓመት ሁለት ጊዜ በሚወጣው የአፍሪካን ማክሮ ኢኮኖሚክ አፈጻጸምን በሚዳስሰው ህትመቱ በ2024 ምንም እንኳን አፍሪካ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ብታሳይም ከላይ በተጠቀሱት ሀገራት ከውጭ ምንዛሬ መውረድና የኑሮ ውድነት ምክንያት ግጭቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል።
የኑሮ ውድነት ያሰጋቸዋል ከተባሉት አንዷ በአፍሪካ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ናይጄሪያ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሰላማዊ ሰልፍ እያስተናገደች ነው። ሰልፉን የጠሩት የናይጄሪያ የሰራተኛ ማኅበር (Nigeria Labour Congress) ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ላይ የሚደረግ ነው ተብሏል።
እንደ ሀገሪቱ ስታስቲክስ ቢሮ መረጃ ከሦስት አስር ዓመታት በኋላ በናይጄሪያ የዋጋ ግሽበቱ 30% ሆኖ ተመዝግቧል። የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ከ12 ሚሊዮን በላይ ተጎጂዎችን ለመደገፍ ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ በትላንትናው ዕለት ገልጿል።
ምንጭ፦ ቲክቫህ
በአሰቦት ገዳም አካባቢ የተነሳው የሰደድ እሳት መጥፋቱን የገዳሙ ኃላፊዎች ገለጹ
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋን መቆጣጠር መቻሉ እና ገዳሙ በአሁን ሰዓት ከሰደድ እሳት ስጋት መውጣቱን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ማረጋገጥ ችሏል፡፡
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አካባቢ ለሁለት ቀናት በከፍተኛ ደረጃ የሰደድ እሳት እንደነበር የሜኢሶ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቃል፡፡የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ወንጀል መከላከል ክፍል ሀላፊ ኢንስፔክተር አህመዲን ከድር ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን እንደተናገሩት መሰሉ ሰደድ እሳት በአብዛኛው ከየካቲት እስከ ግንቦታ ባሉት ወራት በተደጋጋሚ የሚነሳ ሲሆን ዘንድሮም በተመሳሳይ መነሳቱን ገልጸዋል፡፡
ለሁለት ቀናት የቆየውን የሰደድ እሳት አደጋ ለመቆጣጠር የአካባቢው ማህበረሰብ የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በተለይ ወደገዳሙ እንዳይዛመት ባደረጉት ጥረት ሰደድ እሳቱን መቆጣጠር መቻሉን ኢንስፔክተር አህመዲን ጨምረው ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡
ቦታው ደረቃማ ሳሮች የተከበበ በመሆኑ በፍትጊያ እንዲሁም በአካባቢው ከሰል ለማክሰል በሚደረግ ጥረት የአሳት አደጋዎች በተደጋጋሚ እንደሚነሳም ተገልጻል፡፡አባ ገ/ሚካኤል የተባሉ የገዳሙ አገልጋይ ብስራት ሬድዮ እንዳነጋገራቸው በአሁኑ ሰዓት እሳቱን ጠፍቶ ከስጋት ነጻ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
👉 እንድታውቁት
በተለያዩ የዓለማችን አገራት ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት እድል አግኝተው ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ስለማጠናቀቃችሁ የተሰጣቸውን ማስረጃ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል በኩል ማረጋገጥ እንዳለባቸው ተገልጿል።
ከውጭ አገር የሚገባ የትምህርት ማስረጃ ይህን ካላሟላ አገር ውስጥ አገልግሎት ላይ የማይውል መሆኑን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደብዳቤ ማሳወቁን ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንባሲ ገጽ ላይ ተመልክተናል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ ሁኖ በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ተሰጠው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ ‘ሳልሳይ ወያነ ትግራይ’ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. መስጠቱን አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለሳልሳይ ወያነ ትግራይ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ እና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንደ ሰጠው ቦርዱ አመላክቷል።
ፓርቲው በበኩሉ በማህበራዊ ትስስር የፌስቡ ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ከአራት አመታት በፊት መሰረቱን ትግራይ ላይ አድርጎ የፖለቲካ ትግል መጀመሩን አውስቶ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከምርጫ ቦርድ እውቅና ተሰጥቶናል ብሏል።
ይህ እንዲሆን ያለሰለሰ ትግል ላደረጉት የፓርቲው አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎቹ በማመስገን እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ማክሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - የካቲት 19 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - February 27 , 2024
👉 ሸዋሮቢት ዛሬ ከባድ ተኩስ የተገደለው ሃላፊና ፖሊሶች
👉 ኤምባሲው ፊትለፊት ራሱን ያቃጠለው ወታደር
👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ምን ገጠመው
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/LX97nFtcuro
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ማክሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - የካቲት 19 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - February 27 , 2024
👉 ደብረ ማርቆስ በመከላከያ ላይ ጥቃት ተፈፀመ👉 ሚዛን ከባድ የእሳት አደጋ በርካታ ንብረት ወደመ
👉 ባይደን አይስክሬም እየበሉ ስለእስራኤል እና ሀማስ የተናገሩት
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/9UziP4let_o
እስራኤልና ሃማስ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ።
የእስራኤልና ሃማስ አመራሮች ከኳታር እና አሜሪካ አደራዳሪዎች ጋር በተናጠል ግን በተመሳሳይ ከተማ (ዶሃ) እያካሄዱት ያለው ንግግር ተስፋ ሰጪ ነው ተብሏል።
እስራኤል እስከ ረመዳን ፆም መግቢያ የተኩስ አቁም ስምምነት ካልተደረሰ በራፋህ ጦርነት እጀምራለሁ ማለቷም ድርድሩ እንዲፈጥን ማድረጉ ተገምቷል።
"የብሄራዊ ደህንነት አማካሪዬ ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባችን ነግሮኛል፤ ያላለቁ ጉዳዬች ቢኖሩም እስከ ቀጣዩ ሰኞ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚደረስ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንት ባይደን።
የአሜሪካ አደራዳሪዎች እስከ መጋቢት 10 ድረስ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሶ የታጋች እና እስረኞች ልወውጥ እንዲጀመር ግፊት እያደረጉ ነው።
እስራኤልና ሃማስ ግን ለተኩስ አቁም ድርድሩ መጓተት እርስ በርስ መካሰስና የጋዛው ጦርነት መቀጠሉ አይቀሬ መሆኑን የሚያሳዩ ንግግሮችን ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የባንክ ሰራተኞች ወደ አውቶብስ ተርሚናል እንዳይገቡ ተባለ
የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መርካቶ አውቶቡስ ተርሚናል የተለያዩ ባንክ ሰራተኞች ሕብረተሰቡን አካውንት እናወጣለን በማለት ምክንያት የሕዝብ መገልገያ የሆነውን ወንበር ለብዙ ሰዓታት ሕዝብ እንዳይቀመጥበት በማድረግ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ ማንኛውም የባንክ ሠራተኛ ወደ ተርሚናሉ ገብቶ አካውንት ማስከፈት የማይፈቀድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን ብሏል።
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - የካቲት 18 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - February 26 , 2024
👉 ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ የኦነግን ባለስልጣን ኢንተርቪው በመስራቱ ታሰረ
👉 ከ20 በላይ ሰዎችን የቀጠፈው የመኪና አደጋ
👉 የመከላከያ ሰራዊት በባህር ዳር የፈፀመው
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/4rzUxGrqGQI
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በባሕር ዳር ከተማ እስከ “የጦር ወንጀል” ሊደርሱ የሚችሉ “ብርቱ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግ ጥሰቶች” መፈጸማቸውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምርመራ ውጤት ይፋ አደረገ።
የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ በሁለት የተለያዩ ወቅቶች የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአማራ ክልል ዋና ከተማ በትንሹ ዐሥራ ሁለት ሰዎች “ከሕግ ውጪ” መግደላቸውን የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ዛሬ ሰኞ የካቲት 18 ቀን፣ 2016 ይፋ አድርጓል።
በመስከረም 2016 እና ነሐሴ 2015 ተፈጽመዋል የተባሉ ግድያዎችን የሠነደው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምርመራ ውጤት “ከእኛ ጋር ሳይሆን ሊፋለሟቸው ከመጡት አካላት ጋር የሚዋጉ መስሎን ነበር” የሚል ርዕስ የተሰጠው ነው።
የድርጅቱ የአፍሪቃ ቀንድ ጽህፈት ቤት ባልደረባ ሱዓድ ኑር “ይኸ ርዕስ የ20 ዓመት ወንድ ልጇ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጭንቅላቱ ላይ ተመትቶ ከተገደለባት ለምለም ከተባለች እናት የወሰድንው ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ሱዓድ ኑር “እነዚህ ቃላት ከእርሷ ምስክርነት የተወሰዱ፣ ለዚህ ምርመራ ባነጋገርናቸው እና የማያውቁት ጦርነት ሰለባ የሆኑ በርካታ እማኞች የተደጋገሙ ናቸው” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል።
በአምነስቲ የምርመራው ውጤት መሠረት ነሐሴ 2 ቀን፣ 2015 በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ውስጥ በሚገኙት አቡነ ሀራ እና ልደታ የተባሉ አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት አባላት “ከሕግ ውጪ” ከተገደሉ ስድስት ሰላማዊ ሰዎች መካከል ወይዘሮ ይታጠቁ አያሌው ይገኙበታል።
ከልደታ አቅራቢያ በሚገኝ የመኖሪያ ቤታቸው እንጀራ በመጋገር ላይ የነበሩት ይታጠቁ ወታደሮች ወደ ቅጥር ግቢያቸው በተኮሱት ጥይት ተመትተው መገደላቸውን ዘመዳቸው ቢኒያም የተባለ የዐይን እማኝ ለአምነስቲ አስረድቷል።
በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት የ55 ዓመቱ አዛውንት አየነው ደፍረሽ በተመሣሣይ ቀን ካሳሁን እና አብርሐም ከተባሉ ሁለት ልጆቻቸው ጋር ከቤተ-ክርስቲያን በመመለስ ላይ ሳሉ እንደተገደሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምርመራ ውጤት ያሳያል።
አንድ የጥይት ድምፅ የሰማ የቤተሰቡ አባል ለአቶ አየነው ስልክ ደወሎ ለማናገር ሲሞክር የመከላከያ ሰራዊት ወታደር ሳይሆን አይቀረም ብሎ የጠረጠረው አንድ ግለሰብ ስልኩን አንሰቶ “የደረሰው አደጋ ትንሽ ነው” ብሎ እንደመለሰለት ለመርማሪዎቹ ተናግሯል።
የአየነው የቤተሰብ አባላት በስተመጨረሻ ሦስቱን አስከሬኖች ከጎዳና እንዳነሱ ሪፖርቱ ይጠቁማል። የዐይን እማኞች እና ቤተሰቦች እንደተናገሩት ሁሉም ሟቾች “ከቅርብ ርቀት በተተኮሰ ጥይት” መገደላቸውን ይኸው የምርመራ ውጤት አትቷል።
ግድያው በተፈጸመበት የነሐሴ ወር የመጀመሪያ ሦስት ቀናት የባሕር ዳር ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ብርቱ ውጊያ አስተናግዳለች። በባሕር ዳር በመከላከያ ሠራዊት “ከሕግ ውጪ” ተፈጸመ የተባለው ግድያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለይ በአማራ ክልል ተፈጻሚ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በደነገገ በጥቂት ቀናት ልዩነት የተከሰተ ነው።
በባሕር ዳር ዳግም ግጭት በተቀሰቀሰበት ወቅት ሰባት አሚት በተባለ የከተማዋ ክፍል መስከረም 29 እና 30 ቀን፣ 2016 አምስት ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች በመከላከያ ሠራዊት አባላት መገደላቸውን የአምነስቲ ምርመራ ይፋ አድርጓል። የምርመራው ውጤት እንደሚያሳየው ከሟቾቹ መካከል “በጤና ጣቢያ ውስጥ ከሕግ ውጪ የተገደለ ታካሚ ይገኝበታል።”
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ማክሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - የካቲት 26 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 5, 2024
👉 የሰሜኑ አካባቢ ዛሬ የተፈጠረው ምንድነው
👉 ፈረንሳይን ያስፈነጠዛት አዲሱ ህግ ፀደቀ
👉 በአዲስ አበባ አነጋጋሪው የመንገደኞች ቅጣት
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/i0oXj8GJALw
በአዲስ አበባ ከተማ በጆሮ ማዳመጫ እያዳመጡ መንገድ ማቋረጥ 80 ብር ያስቀጣል ተባለ
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/ 2009 መሠረት በእግረኞች የሚፈፀሙ ጥፋቶች ላይ ቁጥጥር በማድረግ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ አስታውቋል ።ደንቡ ቀደም ባለው ጊዜ የወጣ ይሁን እንጂ በአፈፃፀሙ ዳተኝነት ሲታይበት ቆይቶ በአሁኑ ወቅት በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ስህተት ሳቢያ የሚከሰት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል ።
በዚህም መሠረት ደንቡን የሚተላለፉ እግረኞች ከ40 እስከ 80 ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጡ በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የዲጂታል ሚዲያ ከፍተኛ ባለሙያ አ/ቶ መኳንንት ምናሴ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
ከእግረኖች ደንብ መተላፎች መካከል ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ መንገድ ማቋረጥ ፣ ለተሽከርካሪ በተፈቀደ መንገድ ላይ ያለበቂ ምክንያት መቆም ፣ የእግረኛ መንገድ በሌለበት ቀኝ ጠርዝ ይዞ መጓዝ ፣ ለእግረኛ ተብሎ ከተከለለ መንገድ ውጭ መጓዝ እና በማንኛውም ሁኔታ ለእግረኞች እንቅስቃሴ እንቅፋት መሆን እያንዳንጃቸው በ40 ብር የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጡ ተጠቁሟል ።
በተጨማሪም ተለይተው የታጠሩ መንገዶችን ዘሎ ማቋረጥ ፣ በጆሮ ማዳመጫ እያዳመጡ መንገድ ማቋረጥ እንዲሁም እግረኞች እንዳያቋርጡ ክልክል በሆነ የማሳለጫ ወይም የቀለበት መንገድን ማቋረጥ እያንዳንዳቸው የ80 ብር ቅጣት እንደሚያስቀጡ አክለዋል ።
ሆኖም እግረኞች ይህን ተረድተው ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የተገለፀ ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ የገንዘብ ክፍያ መፈፀም ያልቻለ ሰው ፅዳትን ጨምሮ ተመጣጣኝ ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል ተብሏል ። የቁጥጥር ስራው በባለስልጣኑ 11 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል ።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
ጄፍ ቤዞስ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለሃብት ሆነ
ኤሎን መስክ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለፀጋነትን ተቀምቷል።
በዚህ ሣምንት የወጣው የምድራችን ባለ ፀጋዎች ዝርዝር ኤሎን መስክን ወደ ሁለተኛ ባለፀግነት አውርዶታል።
የአማዞኑ ባለቤትና መስራች ጄፍ ቤዞስ አሁን ላይ የምድራችን ባለፀጋ የሚለውን ማዕረግ መቀዳጀቱ ተሰምቷል።
ብሉምበርግ በሚያወጣው የምድራችን ቢሊየነሮች ዝርዝር ማሳያ መሰረት ቤዞስ በ200 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት ቀዳሚ ባለሃብት ሆኗል።
ኤሎን መስክ ደግሞ 198 ቢሊየን ዶላር ተከታዩን ደረጃ ይዟል።
መስክ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 31 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት ማጣቱን ያነሳው ሪፖርቱ ለዚህ ደግሞ በኩባንያዎቹ የሚታየው የአክሲዮን ድርሻና የገበያ መዋዠቅ ዋናው ምክንያት ነው ብሏል።
በአንጻሩ ጄፍ ቤዞስ በተጠቀሰው ጊዜ 23 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት ማግኘት መቻሉንም ዘገባው አስታውሷል።
በአዲስ አበባ ከተማ በግንባታ ተረፈ ምርት መደርመስ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ
በአያት ሪል እስቴት በሚያስገነባዉ የቤት ግንባታ ላይ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርት ተንዶ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።
በአዲስ አበባ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ በኮንስትራክሽን ስራ ላይ የዛሬዉን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በአዲስ አበባ ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሲኤምሲ ሚካኤል ከቀኑ 5:09 ሰዓት ላይ አያት ሪል እስቴት በሚያስገነባዉ የቤት ግንባታ ላይ የኮንስትራክሽን ተረፈምርት ተንዶ ዕድሜዉ ሀያ ዓመት የሆነ የድርጅቱ ሰራተኛ ወዲያዉ ህይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የወጣቱን አስከሬን ከፍርስራሽ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን የስራ ላይ አደጋ በአንድ ወር ዉስጥ የዛሬዉን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎችላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ብስራት መዘገቡ ይታወሳል፡፡
ጠ/ሚ ዐቢይ እና ፕሬዝዳንት ሩቶ ይሰጡታል የተባለ ጋዜጣዊ መግለጫ ሳይካሄድ ቀረ
👉 ለኢትዮጵማ ጠቅላይ ሚኒስትር ደማቅ አቀባበል ያደረገችው ናይሮቢ ዛሬ ረቡዕ የሶማሊያውን ፕሬዝንዳት ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድን እየጠበቀች መሆኑ ተሰምቷል።
ለይፋዊ ጉብኝት ኬንያ ናይሮቢ የሚገኙት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በጋራ ይሰጡታል የተባለው ጋዜጣዊ መግለጫ ሳይካሄድ የቀረው ጋዜጠኞች ሽፋን ለመስጠት እየጠበቁ ባሉበት ነው።
ለሁለት ቀናት በናይሮቢ የሚቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሁለቱ አገራት ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ከኬንያ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
ትናንት ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ኬንያ ናይሮቢ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ በፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት (ስቴት ሐውስ) አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዐቢይ፤ በአገሪቱ የክብር ዘቦች ታጅበው ወደ ስቴት ሐውስ የገቡ ሲሆን፣ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሶላቸዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በስቴት ሐውስ በፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አቀባበል ከተደርገላቸው የሁለቱ አገራት መሪዎች በጋራ ለጋዜጠኞች መግለጫ ለመስጠት ዕቅድ ይዘው ነበር።
ይሁንና ሁለቱ መሪዎች ወደ ውስጥ ከገቡ ከደቂቃዎች በኋላ “በዕቅድ ለውጥ ምክንያት” ጋዜጣዊ መግለጫው እንደማይኖር በቦታው ተገኝተው ሲጠባበቁ ለነበሩት ዘጋቢዎች ተነግሯል። የዕቅድ ለውጡ እንዲደረግ ምክንያት የሆነው ጉዳይ ግን አልተገለጸም።
ከዚህ ጋር በተያያዘ
ለኢትዮጵማ ጠቅላይ ሚኒስትር ደማቅ አቀባበል ያደረገችው ናይሮቢ ዛሬ ረቡዕ የሶማሊያውን ፕሬዝንዳት ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድን እየጠበቀች መሆኑ ተሰምቷል።
የሶማሊያ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዳውድ አዌስ እንደገለጹት፣ ሐሰን ወደ ኬንያ የሚያደርጉትን በረራ ጀምረዋል። ሐሰን ወደ ኬንያ ጉዞ ያደረጉት በተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው። ሰውዬው በእግረ መንገድ ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ወዲህ ካኮረፏቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ይገናኙ እንደሆን የተነገረ ነገር የለም።
128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል በድምቀት እንደሚከበር የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ ገለፁ።
የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችን ሪፖርት ያዳመጡት ጀኔራል አበባው÷ 128ኛው የዓድዋ ድል ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ወቅቱን በሚዘክር እና ክብሩን በሚመጥን መልኩእንደሚከበር አስታውቀዋል፡፡
በዓሉን ለማክበር በወጣው ዕቅድ መሠረት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡
የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችም የዓድዋ ጀግኖችን የሚዘክር የ34 ደቂቃ ዶክመንታሪ፣ ቢል ቦርድ፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ሎጎ፣ መሪ ቃል እና ሠራዊቱ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የሚወያይበት ጽሑፍ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
የካቲት 23 ቀን ወታደራዊ የሰልፍ ትርዒት እና ድሉን የሚያስታውሱ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡም ጠቁመዋል፡፡
ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ሥራ የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጪ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ዘገባ ለመስራት ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ለ37ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን አስታውሰዋል፡፡
ይሁን እንጂ ግለሰቡ የጋዜጠኝነት ሙያን ሽፋን በማድረግ አዲስ አበባ ከገባበት ቀን ጀምሮ ከመጣበት ዓላማ ፍጹም ተቃራኒ የሆኑ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የሚሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡
ይህም ከመጣበት አላማ ውጪ በተለይም የኢትዮጵያን ውስጣዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን የተመለከቱ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ሲሞከር እንደነበር አብራርተዋል፡፡
በዚህም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች እና አባላትን እንዲሁም የፖለቲካ ተሳትፎ አላቸው ያላቸውን ማህበራዊ አንቂዎችን ሲያነጋግር እንደነበር ገልጸዋል፡፡
ግለሰቡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ዋነኛ ዓላማ ውጪ በሀገሪቱ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት በማድረግ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ባደረገው ጥረት ተጠርጥሮ የካቲት 14 ቀን በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን አስገነዝበዋል፡፡
ግለሰቡ በ24 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረቡንም ነው ሚኒስትር ዴዔታዋ ያስረዱት፡፡
ለአፍሪካ ህብረት ዘገባ ፈቃድ የሚሰጠው ማንኛውም ጋዜጠኛ ከመጣበት ዓላማ ውጪ መስራት ህገ ወጥ እንደሆነ ጠቁመው÷ ይህም በየትኛውም ዓለም ያለ ሕግ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አንቷን ጋሊልዶ እና ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ በመጀመሪያ ቦሌ ሩዋንዳ የሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አስከትሎም ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መላካቸውንን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል።
በዚህም ፍርድ ቤት የቀረበው ጋዜጠኛው “ከሁለቱ ታጣቂ ኃይሎች ማለትም በመንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በአማራ ክልል ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር በመሆን በመዲናዋ ሁከት እንዲፈጠር አሴሯል” በሚል መጠርጠሩ ተገልጿል።
ፖሊስ ሁለቱን ግለሰቦች ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ሲባል በእስር ላይ እንዲቆዩ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ለየካቲት 22 ቀን 2016 ቀጠሮ መስጠቱ ይታወቃል።
ሲፒጄ በቅርቡ አደረኩት ባለው ቆጠራ መሰረት ስምንት ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት ሁለተኛዋ አገር ናት።
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: /channel/ethiotube
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በግማሽ አመቱ 23 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት (ኢባትሎድ) በባህር ትራንስፖርት ዘርፍ ፣ በጭነት አስተላላፊነት ፣ በወደብና ተርሚናል አገልግሎት እንዲሁም በኮርፖሬት አገልግሎት ዘርፍ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን በ2016 በጀት በግማሽ ዓመት 23 ነጥብ 46 ቢሊየን ብር ማግኘቱን አስታውቋል።
አዲስ ማለዳ ከድርጅቱ ካገኘችው መረጃ ይኼው ገቢ 17 ነጥብ 23 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 23 ቢሊየን ብር ማግኘቱን የገለጸ ሲሆን፤ ከግብር በፊት 3 ነጥብ 26 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል።
እንዲሁም የድርጅቱን መርከቦችና የኪራይ መርከቦችን በመጠቀም 1 ሚሊየን 886 ሺህ 399 ቶን ዕቃ ለማጓጓዝ ታቅዶ 2 ሚሊየን 214 ሺህ 156 ቶን ማጓጓዝ የተቻለ ሲሆን፤ የገቢና ወጪ ኮንቴይነር ፍሰት 197 ሺሕ 699 TEU ኮንቴይነር ለማድረስ ታቅዶ 204 ሺ 358 TEU ኮንቴነር ተስተናግዷል ብሏል፡፡
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አካባቢ የተነሳው ሰደድ እሳት ወደ ገዳሙ መቃረቡ ተነገረ
👉 " የገዳማውያኑን የእርዳታ ጥሪን በተጠንቀቅ ጠብቁ " - አባ ገ/ሚካኤል
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ የሰደድ እሳት የተነሳ ሲሆን ከትላንት ምሽት ጀምሮ ግን ወደ ገዳሙ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠጋ እንደሆነና እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተነግሯል ።
አባ ገ/ሚካኤል የተባሉ የገዳሙ አገልጋይ ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በሰጡት ቃል ፤ የእሳት ቃጠሎ መነሻው በሥርዓት ያልታወቀና የሰደድ እሳት እንደሆነ ገልጸዋል።
ከ3 ዓመታት በፊት ከፍተኛ እሳት ተከስቶ ለዘመናት የኖሩ የገዳሙን ብርቅዬ አራዊትና ደን ማውደሙን አስታውሰዋል።
በአሁኑ ሰዓት እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ፤ የእሳቱ አደጋ የሚከፋ ከሆነና መቆጣጠር ካልተቻለ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የገዳማውያኑን የእርዳታ ጥሪ በተጠንቀቅ ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊ የአፍሪካ አየር መንገዶች ቁጥጥር እንዲላላና የዋጋ ቅናሽ እንዲደረግ ጠየቁ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በአፍሪካ አህጉር የበረራ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ውድድርን ለመጨመር እና ለተጓዦች ወጪዎችን ለመቀነስ የአፍሪካ ሀገራት የአውሮፕላን በረራ ገደቦችን እንዲያላሉ የሚያስችለውን ስምምነት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የበረራ ገደቦች የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አየር መንገዶች መዳረሻቸውን ለማስፋት በሚያደርጉት ጥረት ላይ እንቅፋት ሆኗል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው 37 ሀገራት የአየር ቀጠናውን ነፃ የማድረግ ስምምነት በ2018 የፈረሙ ቢሆንም ነገር ግን የነጠላ አፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ቀጠና እስካሁን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሊሆን አለመቻሉን ተናግረዋል።
አቶ መስፍን ሌሎች አህጉራት የአየር በረራ ገደቦችን እንዳነሱት በአፍሪካ የሚንቀሳቀሱ አየር መንገዶች በአህጉሪቱ በሁለት ሀገራት መካከል ለመብረር የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት መፈረም ያለባቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአፍሪካ አህጉር የአየር ትራንስፖርት በኢኮኖሚ እድገት እና ሌሎች ምክንያቶች ፍላጎቱ እያደገ መሆኑ ቢገለፅም በአህጉሪቱ የሚደረጉት በረራዎች በአማካይ 70 በመቶ ያህል ብቻ ተሳፋሪ የሚይዙ መሆኑንና በበረራ ዋጋ ምክንያት ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛው መሆኑም ተመላክቷል።
በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን በአየር መንገዶች መካከል ጠንካራ ውድድር እንዲኖር፣ ለተጓዦች የትኬት ዋጋ እንዲቀንስ የአህጉሪቱ አየር መንገዶች የአየር ክልላቸውን በመክፈት አየር መንገዶች በነጻነት እንዲበሩ ማድረግ አለባቸው ማለታቸውን የዘገበው ፋይናንሺያል ታይምስ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሌ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ከህብረተሰብ ከተወካዮቹ ጋር መጠነ-ሰፊ ርዕይ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
አክለውም “ውይይታችን በልማት፣ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነበር” ብለዋል።
"ትናንት ብቻ ገደሉ 10 ጊዜ ያክል በታንክ ቢመታም ሊናድ አልቻለም"
👉 አንዳንድ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ የለቅሶ ስነ ስርዓት መፈፀማቸውንም ወረዳው አስታውቋል፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ወገል ጤና አካባቢ በማዕድን ቁፋሮ ላይ እንዳሉ ጉድጓድ ከገቡ 18ኛ ቀን የሆናቸውን ወጣቶች እጣፋንታ ለማወቅ የተደረጉ የህዝብና የመንግስት ጥረቶች እስካሁን እንዳልተሳኩ የደላንታ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ። አንዳንድ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ የለቅሶ ስነ ስርዓት መፈፀማቸውንም ወረዳው አስታውቋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ወጣቶቹን ከተቀበሩበት ጉድጓድ ለማውጣት በሰው ኃይል ሲያደርጉት የነበረው ሙከራ ባለመሳካቱ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር ለቁፋሮ እንቅፋት የሆነውን የአለት ክፍል በከባድ መሳሪያ ለማስወገድ የተለያዩ ሙከራዎች ሲደረጉ ቢቆይም የተገኘ ምንም ውጤት እንደሌለ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን ተናግረዋል፡፡
ሲደረግ የነበረውን ጥረት በተመለከተ ዋና አስተዳዳሪው፣ “በባባህላዊ መንገድ ቁፋሮዎች ለተከታታይ አንድ ሳምንት ያክል ሲካሄዱ ቆዩ፣ ግን ሌላ ናዳ በቆፋሪዎች ላይ ሊያስከትል የሚችል ስጋት በመፈጠሩ በሰው ጉልበት ሲደረግ የነበረው ቁፋሮ ቆመ ከዚያ ቀጥሎ ዞን፣ ክልልና ፌደራል መንግስት በጋራ ተነጋግረው በባለሙያዎች ተጠንቶ ተራራውን የሚንድ መሳሪያ እንዲመጣ ተደርጎ 35 ቶን የሚመዝን ተተኳሽ ተጠምዶ ተንጠልጣይ ቋጥኙን በፍንዳታ ለማስወገድ ቢሞከርም ሳይቻል ቀረ” ይላሉ አቶ አያሌው አክለው ዛሬም የአካባቢው የመከላከያ ኃላፊ፣ የዞን የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት ቋጥኙን በተለያዩ ተተኳሾች ለማስወገድ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ብለዋል፣ ትናንት ብቻ ቋጥኑ 10 ጊዜ ያክል በታንክ ቢመታም ቋጥኙን ማስወገድ አልተቻለም ብለዋል።
Via DW
ሚዛን አማን ድንገት በተነሳው እሳት የንብረት ውድማት ደርሷል
በሚዛን አማን ከተማ ህብረት ቀበሌ በተለምዶው ሀናን ካፌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
ዛሬ የካቲት 19/2016 ከንጋት ጀምሮ በተከሰተው የእሳት አደጋ የሃናን ካፌን ጨምሮ በአካባቢው ያሉ በርካታ ቁጥር ያሉት የንግድ ሱቆች መውደማቸው ታውቋል ።
የተከሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋን ለመቆጣጠር የአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ ሲያደርግ ማንጋቱን ነው ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን ድንገተኛ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና እና በሙያው የሰለጠኑ የሰው ሀይል ባለመኖሩ እሳቱን መቆጣጠር እንዳልተቻለ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት እሳቱ በቁጥጥር እየዋለ መሆኑን አቶ አብዱ ሙሃመድ በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል።
የአደጋው መንስኤና የደረሰ የውድመት መጠንም ገና አልታወቀም።
ፈረንሳያዊ ጋዜጠኛ እና አንድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባል መታሰራቸውን ሲፒጄ ገለጸ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አባል የሆኑትን በቴ ኡርጌሳን በስካይላይት ሆቴል ቃለ መጠይቅ በማድረግ ላይ የነበረው ፈረንሳያዊ ጋዜጠኛ መታሰሩን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ) አስታወቀ።
ጋዜጠኛው መቀመጫውን በፈረንሳይ ላደረገው 'አፍሪካ ኢንተለጀንስ' የተሰኘ የዜና ድህረ ገጽ ዘጋቢ ሲሆን የካቲት 14 ቀን 2016 ሲቪል በለበሱ ሰዎች መታሰሩን አዲስ ማለዳ ከሲፒጄ ድህረ ገጽ ተመልክታለች።
“እስሩ መሥረተ ቢስ እና ፍትሐዊ ያልሆነ ነው” ያለው ሲፒጄ “የአገሪቱ ባለስልጣናት ጋዜጠኛውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መልቀቅ አለባቸው” ሲል የመብት ተሟጋች ድርጅቱ አሳስቧል።
ይኽ እስር በአገሪቱ ያለውን "የፕሬስ ነጻነት አለመከበር ማሳያ ነው" ያለ ሲሆን በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች ስምንት ጋዜጠኞችም በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል ብሏል።
አንቷን ጋሊልዶ የተባለው ፈረንሳያዊ ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ በመጀመሪያ ቦሌ ሩዋንዳ የሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አስከትሎም ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መላካቸውን ጠቁሟል።
ቅዳሜ ዕለት በቦሌ ምድብ ችሎት ፊት የቀረበው ጋዜጠኛው “ከሁለቱ ታጣቂ ኃይሎች ማለትም በመንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በአማራ ክልል ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር በመሆን በመዲናዋ ሁከት እንዲፈጠር አሴሯል” በሚል መጠርጠሩ ተገልጿል።
የጋዜጠኛው ጠበቃ ክሶቹ ከባድ ቢሆኑም ፖሊስ እስካሁን ተጨባጭ ማስረጃዎችን ማቅረብ አሊያም ጋዜጠኛውን መክሰስ ነበረበት ማለቱን አንስቷል።
ጋዜጠኛው የዋስ መብቱን የጠየቀ ሲሆን ፖሊስ ሁለቱን ግለሰቦች ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ሲባል በእስር ላይ እንዲቆዩ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ለየካቲት 22 ቀን 2016 ቀጠሮ መስጠቱ ተገልጿል።
በዚህም ጋዜጠኛው እንዲሁም የኦነግ አባል የሆኑት በቴ ኡርጌሳ እስከ ቀጠሯቸው ቀን በእስር እንደሚቆዩ አዲስ ማለዳ ከዘገባው ተገንዝባለች።
ከአፍሪካ ህብረት ጀምሮ በኢትዮጵያ መሰንበቱ የተገለጸው ጋዜጠኛ ቪዛ ያለው እና በመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ስለ ቆይታው ያስታወቀ መሆኑ ተጠቁሟል።
ሲፒጄ በቅርቡ አደረኩት ባለው ቆጠራ መሰረት ስምንት ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት ሁለተኛዋ አገር ናት።
“በዝቋላ ገዳም አባቶች ላይ ለተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ከመንግሥት ፍትህን አንጠብቅም!”- እናት ፓርቲ
የካህናቱ ግድያ በገለልተኛ አካል ይመርመር- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
እናት ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዝቋላ ገዳም አባቶች ላይ ለተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ "ከመንግሥት ፍትህን አንጠብቅም" ሲል አስታወቀ።
“ብልጽግና መራሹ መንግሥት የእምነት ተቋማት በማይከበሩበት የሃይማኖት አባቶች እንደ ከብት በሚታረዱበት ወደፊት ታሪክ በጥቁር መዝገብ በሚጽፈው ዘመን ውስጥ የሕዝብን መከራ ማራዘሙን ተያይዞታል” ሲልም ፓርቲው ወቅሷል።
ዴሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶችን ማግኘት "እንደ ሰማይ እርቋል" የሚለው የእናት ፓርቲ መግለጫ ከሦስት አሥርት ዓመታት በላይ የዘለቀው የአብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎ፣ የክርስቲያኖችና የካህናት ግድያ ባለፉት አምስት ዓመታት "በተጠናከረና በተቀናጀ መልኩ" ቀጥሏልም ብሏል።
ፓርቲው ተጠናክሮ የቀጠለው የሃይማኖት አባቶቻችን አሰቃቂ ግድያ መሠረታዊ አገራዊ እሴቶቻችን ለመጣሳቸው ግልጽ ማሳያ ነው ማለቱን ኢትዮትዩብ ከመግለጫው ተመልክቷል።
በመሆኑም በአብዛኛው መንግሥት እየመራው የሚገኘው የአገራችን ፖለቲካ "አሻጥርን የተከተለ" በመሆኑ መንግሥትን ተስፋ አድርገን የምንጠይቀው ፍትህ ባይኖርም፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና የንጹሃን ደም ፍትሕ የሚያገኝበት ጊዜ እንደሚመጣ በእጅጉ ተስፋ እናደርጋለን ሲል ገልጿል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ካህናት ግድያ በገለልተኛ አካል ይጣራ ሲል ሌላኛው ተፎካካሪ ፓርቲ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ትላንት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
በመሆኑም ኦነግ "በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎችእና የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች በሁሉም መልኩ እንደሚያወግዝ" አመላክቶ "ጥፋትን በሌላ አካል ማላከክና ማጭበርበር ባለፉት አምስት ዓመታት የመንግስት የእለት ተግባሩ ቢሆንም ለዜጎች ግን ምንም አይነት ውጤት አላመጣም" ሲል ኦነግ መንግስትን ወቅሷል።
ኦነግ በመግለጫው "በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተፈጸመውን አሰቃቂ የአየርና የሰው አልባ አውሮፕላን ድብደባ እና የጅምላ ግድያ ቤተክርስቲያኒቱ ይህን አረመኔያዊ ድርጊት ከማውገዝ ተቆጥባለች ወይም መርጣ ተናግራለች" ብሏል።
በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን እንደ ሃይማኖታዊ ተቋም እጆቿን ከፖለቲካ እንድታስወጣና እንዲሁም በስልጣን ላይ ባለው ገዥ አካል እና በተቃዋሚዎቹ መካከል በሚከሰተዉ ግጭት ዉስጥ ከመግባት መቆጠብ አለባት ሲል ፓርቲው አሳስቧል።