ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ሩስያ የግብረሰዶምን እንቅስቃሴ በሽብር ድርጊት ውስጥ አካተተች

ከዚህ ቀደም ማንኛውም አይነት የግብረሰዶም እንቀስቃሴን ሕገወጥ እና ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን የአክራሪነት እና የሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ አካታዋለች።

በዚህም ማንኛውም ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ በሩስያ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።

ውሳኔው የተደረሰው የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ የግብረሰዶም ተከራካሪዎች አክራሪ እና አሸባሪ ተብለው እንዲጠሩ በህዳር ወር ላይ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ነው።

በቅርቡ የሩስያ ፍርድ ቤት በ " አክራሪ ድርጅት " ውስጥ ሚና አላቸው በሚል በመወንጀል ሁለት የመጠጥ ቤት / ባር ሰራተኞችን በእስር ቤት እንዲቆዩ እና እዛው እስር ቤት ሆነው ፍርዳቸውን እንዲከታተሉ ወሷል።

የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከዚህ በፊት ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም የአደባባይ እንቅስቃሴን " ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዶ ነበር።

በወቅቱም የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦

የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)

የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች

የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ አካሂደው ተጠርጣሪዎችን አስረው እንደነበር ይታወሳል።

በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና የለውም።

በሩሲያ ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በመንገድ ግንባታ ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን  እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

                     
ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ  የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ  የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር በተለይም በስራ መግቢያ እና መውጪያ ሰዓት አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጪ  መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
• ከ4 ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
• ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከባሻወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ እና ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቋል፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የሩሲያ ጎዳናዎች በሐዘን ተውጠው መዋላቸው ተገለጸ

በሩሲያ አርብ በተፈጸመው የአሸባሪዎች ጥቃት 133 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታውጇል፡፡

በትናንትናው እለት በሽብር ጥቃቱ የሞቱ ዜጎች በሻማ ማብራት ሥነ-ሥርአት ሲዘከሩ ውለዋል፡፡

በርካታ ሩሲያዊያን የሽብር ጥቃቱ በተፈጸመበት አቅራቢያ በተዘጋጀው መታሰቢያ ላይ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡

የሐዘን መግለጫዎችን የሚያሳዩ ፎቶ እና ጽሑፎችም በግዙፍ ስክሪኖች ሲተላለፉ መዋላቸው ታውቋል፡፡

በሀገሪቱ የመዝናኛ እና የስፖርት ዝግጅቶች መሰረዛቸውን፤ የቴሌቪዥን ዜና አንባቢዎችም በጥቁር ልብሶች መታየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሞስኮ በሚገኘው ኮርኩስ ሲቲ ሆል አዳራሽ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 133 መድረሱ ተመላክቷል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

በጦርነት ሳቢያ ሥራ አቋርጦ የቆየው የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ መመለሱ ተገለጸ


የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ምርት ሂደት መመለሱን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑን ዋና ስራ አስፈጽሚ ዋቢ ያደርገውን ዘገባ አዲስ ማለዳ የተመለከተች ሲሆን በሰሜኑ ግጭት ምክንያት ሥራ አቋርጦ የቆየው የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በከፍተኛ ርብርብ ዛሬ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል።

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ከዚህ ቀደም ያመርቱ የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እና አዳዲስ ኢንቨስተሮች እንዲገቡ ጥሪ ቀርቧል።

የቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎቻቸውን እያጠናቀቁ የሚገኙ አልሚዎች መኖራቸውን ያስታወቀው ኮርፖሬሽኑ፤ ኩባንያዎቹ ወደ ምርት ሂደት እንዲገቡ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ238 ሄክታር መሬት ላይ ተገንብቶ በፈረንጆች 2017 ሥራ የጀመረ ሲሆን 15 የማምረቻ ሼዶች እና የለማ መሬት ይገኝበታል።

Читать полностью…

EthioTube

ሐኪሞች 30 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው እባብ መሳይ ፍጥረት ከአንድ ሰው ሆድ ውስጥ በቀዶ ጥገና አስወገዱ፡፡

የ34 ዓመቱ ቬትናማዊ ሆዱን በተደጋጋሚ ቁርጠት ህመም ሲሰማው እና ማስታገሻዎችን ቢወስድም መሻሻል ባለማየቱ ነበር ወደ ሆስፒታል ያመራው፡፡

ያመራበት ሐኪሞች ባደረጉለት ምርመራም በሆዱ ውስጥ መጠኑ ባልተለመደ መልኩ ከፍ ያለ ተንቀሳቃሽ አካል መኖሩን ይነግሩታል፡፡

ቀጥሎ በተደረገለት የቀዶ ህክምና መሰረትም 30 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው እባብ መሳይ ፍጥረት ከሆዱ ውስጥ እንደወጣለት ተገልጿል፡፡

ከነ ህይወቱ በቀዶ ጥገና የወጣው ይህ አባብ መሳይ ፍጥረት የታካሚውን አንጀት ሲጎዳው እንደቆየ፣ ለቁርጠት እና ሌሎች ህመሞች ሲዳርጉት ነበር ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

በራሱ ጭንቅላት ላይ ቀዶ ጥገና ያደረገው ሩሲያዊ
ይህን መያህል መጠን ያለው አካል እንዴት በሆድ ውስጥ ሊኖር ቻለ የሚለው ጥያቄ እስካሁን ያልተመለሰ ሲሆን ምን አልባት ይህ እባብ መሳይ ፍጥረቱ በግለሰቡ መቀመጫ በኩል ሊገባ እንደሚችል ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀስ በቀስም ወደ አንጀቱ እና ሆድ እቃው ውስጥ ሊንቀሳቀስ እና ሊኖር እንደቻለም ሐኪሞቹ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ግለሰቡ አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ ነው የተባለ ሲሆን ተጨማሪ የሆድ እቃ ጉዳት መኖር አለመኖሩን ክትትል እየተደረገለት ነውም ተብሏል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

የጥቁር አንበሣ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሀሰተኛ የሜዲካል ቦርድ ሰነድ በማዘጋጀት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ሲፈፅም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ

ጌቱ ደጀን ወልደአረጋይ የተባለ የጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ሠራተኛ የሆስፒታሉን ሀሰተኛ የሜዲካል ቦርድ ሰነድ በማዘጋጀት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀሎችን ሲፈፅም በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

ግለሰቡ ወደ ውጭ ሀገር በሕገ-ወጥ መንገድ ለሚሰደዱ ኢትየጵያውያን በህመም ምክንያት ከሀገር ውጭ ሄደው እንዲታከሙ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቦርድ ወስኗል የሚል ሀሰተኛ ደብዳቤ በማዘጋጀት ፣ ከኢምባሲው ስለ ትክክለኛነቱ የይጣራ ጥያቄ ሲቀርብ ሰነዱ ትክክለኛ ነው የሚል ምላሽ በመስጠት እና ባንኮች የውጭ ምንዛሬ በሀሰት ታማሚ ለተባሉ ግለሰቦች በመስጠት እንዲተባበሯቸው የሚገልፅ ደብዳቤ በመጻፍ ሕገ-ወጥ የገንዘብ እና የሰዎች ዝውውር ወንጀል ሲፈጽም እንደነበረ ፖሊስ ደርሼበታለሁ ብሏል።

ተጠርጣሪው በሀሰተኛ ስም ዶ/ር አባይ ገብረስላሴ በመባል የሚጠራ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ሀገራት መሄድ ፍላጎት ያላቸውን ግለሰቦች በማፈላለግ በህመም ምክንያት ከሀገር ወጥተው እንዲታከሙ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቦርድ አመራር ወስኗል የሚል ሀሰተኛ የጥቁር አንበሣ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ደብዳቤ በማዘጋጀት ተጠርጥሮ ከመጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡

ፖሊስ የፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ አውጥቶ በተጠርጣሪው ቢሮ ውስጥ ባደረገው ብርበራ ግለሰቡ ያዘጋጃቸው ሀሰተኛ፦
1. የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክብ ማህተም፣

2. Addis Ababa university faculty medicine ክብ ማህተም፣

3. የጤና ሣይንስ ኮሌጅ የሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ክብ ማህተም፣

4. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ክብ ማህተም

5. የጤና ሚኒስቴር ክብ ማህተም፣

6. Addis Ababa university dep’t of surgical medical faculty ክብ  ማህተም፣

7. የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የራዲዮቴራፒ ሕክምና ማዕከል ክብ ማህተም፣

8. የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አ.አ.ዩ ህክምና ፋካልቲ የጥቁር አንበሣ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክብ  ማህተም፣

9. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና የመድሃኒት እንክብካቤ አሰተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ክብ ማህተም፣

10. የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የአጥንት ቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ክብ ማህተም፣

11. የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ኬዝ ቲም 11 ክብ ማኅተም

12. ጤና ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የዜጎች ጤና ለሀገር ብልፅግና የሚል ክብ ማህተም፣

13. HILINA TADESSE TIYO (MD) Medical service General Directorate Director General የሚል ቲተር፣ በተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የተዘጋጁ የራስጌ ማህተሞችን ፖሊስ በኤግዚቢትነት መያዙን አስታዉቋል።

ከዚህም ባሻገር ተጠርጣሪው ያዘጋጃቸው የጥቁር አንበሣ ሆስፒታል የህክምና ቦርድ የታካሚዎች ሀሰተኛ ሰነዶች፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ ባንኮች ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጁ ሀሰተኛ ሰነዶች እና የተለያዩ የግለሰቦች ፓስፖርት እና ሌሎች የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶች በተደረገው ብርበራ የተገኙ መሆኑን ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሀሙስ  ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - መጋቢት 12 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 21 , 2024

👉 የኦሮሚያ መንግስት በድጋሚ  የላከው የሰላም ጥሪ 

👉ትግራይ የወንድ የዘር ፈሳሽ የሚለግሱ ሰዎች የ10ሺ ስጦታ

👉 አጣዬ ዛሬም ቀጥሏል ፤ ሴቶችና ህፃናት ለቀው እየወጡ ነው

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/DvFVcQI1WJY

Читать полностью…

EthioTube

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በድጋሜ የድርድር ጥሪ አቀረበ

"የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ያለበት ተጨባጭ የትግል ምዕራፍ ለትጥቅ ትግል የሚያነሳሳም አይደለም" ሲል የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ሕዝብ ሲታገልላቸው የነበሩ "ዋና ዋና ጥያቄዎች" ተመልሰዋል ብሎ የቀሩትም በሂደት እየተፈቱ ይገኛሉ ሲል አስታውቋል።

"ከለውጡ" ወዲህ የትላንቱን የፖለቲካ ኋላ ቀርነት ለማስወገድ እና ሰላምን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ያለው የክልሉ መንግስት፤ የሰላም በሮችን ክፍት አድርጓል ማለቱን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።

"የተለያዩ አካላት ነጠላ ትርክት እየተከተሉ የትናንቱ ኋላ ቀርነት አብሮን እንዲቀጥል እየሠሩ ነው" ያለው መግለጫው፤ እስካሁን ከ3 ሺህ 500 በላይ "የሸኔ" ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ ተቀብለው 1 ሺህ 500 የሚሆኑት ተዋጊዎች የመልሶ ማቋቋም ስልጠና ወስደው ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቅለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ በመግለጫው "ለኦሮሞ ሕዝብ የሚበጀው የተገኘውን ድል ተባብሮ በመጠበቅ ለተሻለ ነገ በሕብረት መሥራት እንጂ እርስ በርስ መፋለም እና መጠፋፋት አይደለም" ብሎ መጠፋፋትና መጠላለፍ "እንደአገር ያገኘነውን ድል" ለማስቀጠል ፈተና ሆኗል ብሏል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራ ውስጥ ከስድስት ዓመታት ገደማ በፊት የተፈራረሙት ስምምነትን ተከትሎ ወደ አገር ወስጥ የገባው ታጣቂ ቡድን ወደ ኦሮሚያ ክልል ከገባ በኋላ ላለፉት ዓመታት የግጭት ቀጠና ሆኗል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)ን ጨምሮ ሌሎችም የፖለቲካ ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ያላባራ እና ያልተቋረጠ በመሆኑ ከፍተኛ ውድመት እና የሰው ህይወት መጥፋት እያስከተለ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገልጻሉ።

Читать полностью…

EthioTube

እንዲህም ሆኗል

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መ/ኮ/ሰ / ሆስፒታል የተያያዙ መንታዐልጆች አንዲት እናት ትናንት ተገላግላለች

Hilal Tube / ሂላል ቲዩብ

Читать полностью…

EthioTube

Picture of the Day

4 ኪሎ : 4 Kilo

📷: Nat Nael via Bored Cellphone Addis Ababa

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮ ቴሌኮም በከተማዋ የመልሶ ማልማት ስራዎች ሳቢያ የኔትዎርክ መቆራረጥ ሊያጋጥም ይችላል ሲል አሳስቧል 

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ባለው የመንገድ ኮሪደር ልማት እና ሌሎች የመልሶ ማልማት ሥራዎች ምክንያት የፋይበር፣ የታወር እና የተለያዩ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች እየተነሱ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

በዚህም የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ግንባታ በማከናወን አገልግሎት ለማስቀጠል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመግለጽ፤ የኔትዎርክ መቆራረጥ ወይም የአገልግሎት ጥራት መቀነስ ሊያጋጥም ይችላል ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች አገልግሎት ሳይቆራረጥባቸው በተቻለ ፍጥነት እና ጥንቃቄ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን በማዘዋወር፤ እንዲሁም አዳዲስ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ግንባታ በማከናወን አገልግሎት ለማስቀጠል ጥረት እያደረግኩ ነው ብሏል።

ይሁን እንጂ ኩባንያው የአገልግሎት ጥራት የሚኖርባቸው የተለዩ አካባቢዎችን አልጠቀሰም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ እንደገለጹት በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ግንባታ በስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል።

Читать полностью…

EthioTube

" እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ገንዘቡን ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እናሳውቃለን - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ከ " ቢቢሲ ኒውስ ዴይ " ጋር በነበራቸው ቆይታ ባንኩ የሲስተም ብልሽት ባጋጠመው ወቅት የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ደንበኞች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ገንዘቡን ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።

" በዲጂታል ነው ዝውውር የፈጸሙት። ደንበኞቻችን ስለሆኑ እናውቃቸዋለን። " ያሉት የባንኩ ፕሬዜዳንት ፤ " የፈጸሙት ተግባር በሕግ ያስጠይቃቸዋል። ለፖሊስ ማንነታቸውን እናሳውቃለን " ብለዋል።

" አሶሼትድ ፕሬስ " ባንኩ አርብ መጋቢት 6 ለሊት የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት የተወሰደበት ገንዘብ 2.4 ቢሊዮን ብር (40 ሚሊዮን ዶላር) መሆኑን ዘግቧል።

ይህ ወጥቷል የተባለው ገንዘብ ትክክለኛ ነው ወይ ? ተብለው የተጠየቁት የባንኩ ፕሬዝዳንት ፤ " የኦዲት ምርመራው ባለመጠናቀቁ የተወሰደውን ገንዘብ መጠን አሁን ላይ አይታወቀም " ብለዋል።

" ገና ኦዲት እየተደረገ ነው። ዝውውሩ ውስብስብ ነው። ጤናማ የሆነ ዝውውር የፈጸሙ እንዳሉ ሁሉ፤ የሌላቸውን ገንዘብ ያወጡም አሉ። ስለዚህ ማጣራት ይጠይቃል። ይህ ደግሞ ጊዜ ይፈልጋል። ምናልባት በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንጭርሳለን ብለን እንጠብቃለን "ብለዋል።

አቶ አቤ ፤ 10 ሺህ የሚሆኑ ግለሰቦች የገንዘብ ዝውውር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አርብ ሌሊት ከ490 ሺህ በላይ " ጤናማ እና ጤናማ ያልሆኑ " የገንዘብ ዝውውሮች መከናወናቸውን መናገራቸው ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

Читать полностью…

EthioTube

#አጣዬ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ትናንት ጀምሮ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ተኩስ መኖሩን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። ህዝቡም መውጫ አጥቶ ቤቱ ቁጭ ብሏል ብለዋል።

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት  አጎራባች ከሆነው የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን የመጡ ታጣቂዎች ጭምር በተኩሱ ተሳታፊ ናቸው ብለዋል።

ተኩሱ በማን መካከል እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

Читать полностью…

EthioTube

" የትግራይ ጡረተኞች ክፍያው እንዲፈፀምላቸው ተወስኗል " - ዶ/ር እዮብ ተካልኝ

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት የጡረታ ገንዘብ ያልተከፈላቸው ጡረተኞች፤ በፖለቲካ ውሳኔ መሰረት ደሞዝ እንዲከፈላቸው መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታና የጡረታ ፈንድ የቦርድ አባል ዶክተር እዮብ ተካልኝ ማሳወቃቸውን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ዶ/ር እዮብ ፤ የጡረታ መዋጮ ባልተሰበሰበበት ሁኔታ ጡረታ እንዲከፈል የሚፈቅድ አሰራር አለመኖሩን ጠቅሰው፤ ውሳኔው ፖለቲካዊ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

በዚህም ከፕሪቶሪያው ስምምነት በፊት ክፍያ ተቋረጦባቸው የነበሩ ጡረተኞች፤ በሚቀጥሉት ሳምንታት ክፍያ ይፈፀምላቸዋል ብለዋል። አሰራሩ በመንግስት ተቋማት እና በግል ድርጅቶች ይሰሩ የነበሩ ጡረተኞችን እንደሚመለከት ጠቁመዋል።

ከትግራይ ጡረተኞች ክፍያ ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲነሳ እንደነበር ጠረተኞችም ሰላማዊ ሰልፍ እስከመውጣት መድረሳቸው ይታወሳል።

ከቀናት በፊት ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ ክልል ከመጡ የህዝብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ የጡረተኞች የደሞዝ ክፍያ አልተፈጸመም የሚል ቅሬታ ቀርቦ ነበር።

ጠ/ሚኒስትሩ ፤ " ከሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግሬ በአጭር ጊዜ ምላሽ ይሰጣል " የሚል ምላሽ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል።

በተደረሰው ፖለቲካዊ ውሳኔ በጦርነቱ ምክንያት ያለተከፈለ የጡረተኞች ደሞዝ ተሰልቶ ይከፈላቸዋል ተብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

በሸዋሮቢት ከተማ ዙሪያ ባሉ ወረዳዎች በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ወታደሮች መካከል ግጭት ቀጥሏል

👉🏼 በሸዋሮቢት ከተማ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከተቋረጠም ከ 20 ቀናት በላይ እንደሆነ ሰምተናል


በሸዋሮቢት ከተማ ዙሪያ ባሉ ወረዳዎች ላይ አሁንም ግጭት ያለባቸው መኖራቸውን ከከተማዋ ነዋሪዎች ሰምቷል። ላለፉት አራት ቀናት በቆጥ፣ ሞላሌ እና ዋጮ ቀበሌ ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች ላይ መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን እና የሰው ህይወት መጥፋቱንም ተገልጿል።

በሸዋሮቢት ከተማ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከተቋረጠ ከ 20 ቀናት በላይ እንደሆነ እና ከደብረብርሃን እንዲሁም ከደሴ ምንም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አለመኖሩንም ዳጉ ጆርናል ተረድቷል።

የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎችም ትራንስፖርት እንቅስቃሴ በመቋረጡ ምክንያት የኑሮ ውድነቱ መቋቋም አለመቻላቸውን እንዲሁም የስራ እንቅስቃሴዎች የተቋረጠባቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎችም ለአስፈላጊ ነገሮች ሲንቀሳቀሱ ሲኖትራክ እንዲሁም ተመሳሳይ ፍቃድ ያላቸውን የትራንስፖርት አገልግሎቶች እየተጠቀሙ እንደሆነ ይህም በቀላሉ የሚገኝ እድል አለመሆኑን አንስተዋል። በተጨማሪም ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በዚህም መሰረታዊ የሚባሉ ነገሮችንም ወደ ከተማዋ ለማስገባት እና ለመንቀሳቀስ ከባድ እንደሆነባቸውም አንስተውልናል።

ነጋዴዎች ቀድመው ያስገቡትን እቃዎች በውድ ዋጋ በመሸጥ ላይ መሆናቸው የነገሩን ሲሆን በዚህም ሽንኩርት ኪሎ እስከ 135 ብር ፣ ቶማቲም 50 ብር፣ ስኳር በትንሹ አንድ ኪሎ ከ150 ብር ጀምሮ እየተሸጠ እንደሚገኝ ነግረውናል።

በመሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች በኑሮ ውድነቱ መማረራቸውን በከተማው ያለው የስራ እንቅስቃሴም መቀዛቀዙ እንዳሳሰባቸው እና ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ እንደሆነም ገልጸዋል ። ጉዳዩ በተመለከተ ዳጉ ጆርናል ምን ዓይነት መፍትሄ ሊሰጥ እንድታሰበ እና ትራንስፖርት እንቅስቃሴውን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ ቢሞክርም ምላሽ ማግኘት አልቻለም።

Читать полностью…

EthioTube

የመጀመሪያዎቹ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሠሩ  የህዝብ ማመላለሻ  አውቶብሶች በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
       
አውቶብሶቹን ወደ ስራ ያስገባው በቅርቡ 20 በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሠሩ ሚኒባሶችን  ወደ ስራ ያስገባው የበላይነህ ክንዴ እህት ድርጅት ቬሎሲቲ ኤክስፕረስ ነው።

ዛሬ ስራ የጀመሩት አውቶብሶች መነሻቸው ቦሌ ሲሆን መዳረሻቸው በእስጢፋኖስ አራት ኪሎ  ስድስት ኪሎ ሽሮ ሜዳ ነው።

Читать полностью…

EthioTube

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከሱዳኑ ጄኔራል አኮል ኩር ኩች ጋር መከሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሱዳኑ ጄኔራል አኮል ኩር ኩች ጋር ዛሬ ጠዋት ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸው በምስራቅ አፍሪካ መረጋጋትን እና ልማትን በማረጋገጥ የጋራ ግቦች ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ  አርብ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - መጋቢት 13 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 22 , 2024

👉ኮሪያ በ AI የሚሰራ ዜና አንባቢ ቀጠረች 

👉ተማሪዎቹ ተጨነቁ የንግድ ባንክን ገንዘብ አጥፍተውታል

👉ሳውዳረቢያ በስቃይ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/IIgITthEInA

Читать полностью…

EthioTube

ከንግድ ባንክ በወሰዱት ገንዘብ ላፕቶፕ እና ዘመናዊ ስልኮችን የገዙ ተማሪዎች ገንዘቡ መመለስ አለበት መባሉን ተከትሎ ጭንቅ ላይ ናቸዉ ተባለ

ቢቢሲ በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ያሉ ተማሪዎችን በማናገር ባገኘው መረጃ መሠረት በርካታ ተማሪዎች ከአስር ሺዎች እስከ መቶ ሺዎች የሚቆጠር የራሳቸው ያልሆነ ብር ከባንኩ ለመውሰድ ችለው ነበር።

ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ባንኩ ከዩኒቨርስቲዎች እና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ገንዘቡን ለማስመለስ እያደረገ ባለው ጥረት፣ ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች በእጃቸው ላይ የቀረውን ብር መመለሳቸው ቢነገርም ለተለያዩ ጥቅም ያዋሉት ግን ግራ በመጋባት በቀጣይ የሚመጣውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ በተፈጠረው ችግር የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ የወሰዱ ተማሪዎች ሂደቱን “ሥራ” በሚል ቃል ነበር የገለጹት። ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪም “እኔ ወደ 150 ሺህ ብር ሠርቻለሁ። 300 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ የሠሩ ተማሪዎች አሉ። . . . ቀድሞ የሰማ [የሲስተም ብልሽቱን] ብዙ ሠርቷል” ብሏል።

ተማሪው አክሎም በዕለቱ “150 ሺህ ብር ‘ሠርቼ’ ነበር። ሁሉንም ብር ተመላሽ አድርጊያለሁ። ወደ ሌላ ባንክ ያዘዋወሩ ጓደኞቼ ግን ጭንቀት ላይ ናቸው” ሲል የተፈጠረውን ሁኔታ መግለጹን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። ንግድ ባንክ በገንዘብ ዝውውር ሥርዓቱ ላይ ብልሽት ከማጋጠሙ በፊት በሂሳቡ ውስጥ የነበረው ከ5 ሺህ ብር በታች እንደነበረ የሚገልጸው ይህ ተማሪ፣ የተፈጠረውን ክፍተት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ 150 ሺህ ብር መውሰዱን አምኗል። ባንኩ ችግሩ መከሰቱን ተከትሎ ያላግባብ ብር የወሰዱ ደንበኞቹ ተመላሽ እንዲያደርጉ ባሳሰበው መሠረት እና ከዩኒቨርስቲው በኩል በወጣው ማስጠንቀቂያ ምክንያት ተማሪው ገንዘቡን መመለሱን ተናግሯል።

በድንገት እጃቸው ላይ የገባውን ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ የተለያዩ እቃዎች የገዙበት ወይም ከንግድ ባንክ አካውንታቸው ወደ ሌላ ባንክ ገንዘብ ያዘዋወሩ ተማሪዎች ደግሞ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ይገኛሉ።

ተማሪው እንደሚለው የሲሰተም ብልሽት ባጋጠመበት ወቅት ካላቸው ገንዘብ በላይ ወደ ሌላ ባንክ ገንዘብ ያዘዋወሩ ተማሪዎች የባንክ ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ በመደረጉ ገንዘቡን ለመመለስ ባለመቻላቸው በግራ መጋባት ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ ብሏል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲው ተማሪ እንደሚለው ብዙ ጓደኞቹ በወሰዱት ገንዘብ የተለያዩ ውድ ነገሮችን በመግዛታቸው ገንዘቡን መልሰው ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ስላሉ ጭንቀት ላይ ይገኛሉ ይላል።

በተለይ ላፕቶፕ እና ዘመናዊ ስልኮችን የገዙ ተማሪዎች ጥቂት አለመሆናቸውን የሚጠቅሰው ተማሪው “100ሺህ ብር የሠራ አንድ ልጅ በሁለተኛው ቀን ላፕቶፕ እና ስማርት ስልክ ገዝቷል” በመግዛቱ እጁ ላይ የሚመልሰው ገንዘብ እንደሌለ ገልጿል።

Via ቢቢሲ አማርኛ

Читать полностью…

EthioTube

የኮሪያዋ ጄጁ ግዛት መንግስት በሰውሰራሽ አስተውሎት AI የምትሰራ ዜና አንባቢ ቀጠረ

የዜና አቅራቢዎች ለረዥም ጊዜያት በስራ ላይ የቆዩና ጥሩ ስራን የሰሩ ቢሆንም የመንግስትና የግል ድርጅቶች ሰዎችን በመተካት እና ገንዘብ ለመቆጠብ ይረዳቸው ዘንድ ሰውሰራሽ አስተውሎትን ምርጫቸው እያደረጉ ነውም ተብሏል።

በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የጄጁ ደሴት አውራጃ መንግስት ጄጁ ሳምንቱን የተሰኘ ሳምንታዊ የዩቲዩብ ፕሮግራም ያለው ሲሆን ለቀድሞ ሰራተኞቹ ይከፍለው ከነበረዉ ገንዘብ እጅግ በጣም ባነሰ ክፍያ የሰውሰራሽ አስተውሎት AI ዜና አቅራቢ መቅጠሩን ነው የተነገረው። ይህቺ  ጄ-ና የሚል መጠርያ የተሰጣትና በሰውሰራሽ አስተውሎት የበለፀገች ዜና አቅራቢ ምንም እንኳ በወጣትነት ዕድሜዋ እምትገኝ እንስት መስላ ብትታይም በሥራዋ በጣም ልምድ ያላት ናት ተብላለች።

ጄ-ና ዜና ለማንበብ በስክሪኑ ላይ በምትሰየምበት ሰዓት እንደ ChatGPT ባሉ የ AI ቋንቋ ሞዴሎች የተፈጠረ ስክሪፕት ነው የምታነበው። ከቀድሞዉ አሰራር በተለየ ወደ በሰውሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ዜና አቅራቢ መቀየሩ በጣም ርካሽ አማራጭ ነውም የተባለ ሲሆን ጄ-ና በወር 600,000 የኮሪያ ዎን ወይም $ 450 ዶላር ብቻ እንደሚከፈላት ነው የተገለፀው።

አንድ የጄጁ ደሴት ባለስልጣን ለኮሪያ ሄራልድ እንደተናገሩት "መደበኛ የዜና አዘጋጆችን መቅጠር ከፍተኛ ወጪን ይጠይቃል፣ ስለዚህ ጄ-ናን መርጠናል" ሲል ተናግሯል። ምንም እንኳን አሁን ጄ-ና ዜናውን በዩቲዩብ ላይ ብቻ እምታቀርብ ቢሆንም ይህን የሰውሰራሽ አስተውሎት ውጤት በጥራትም ሆነ በዋጋ አንፃር ተመራጭ መሆኑን ተከትሎ በመደበኛ የቴሌቪዥን ጣብያዎች ላይም ተግባራዊ ሊደረግ ይችላልም ተብሏል። ቀደም ባሉት ጊዜያት እንደ ቻይና እና ደቡብ ኮሪያ ባሉ አገሮች በዋናነት እንደ ቴክኖሎጂ ማሳያዎች የሰውሰራሽ አስተውሎት ዜና አቅራቢዎች በሙከራ ደረጃ ቀርበው እንደነበር አይዘነጋም።

በሐገራችንም በሰውሰራሽ አስተውሎት የተሰራች ኢትዮጲያ የተሰኘች ዜና አንባቢ በሙከራ ደረጃ ተዋዉቃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነጋገሪያ ሆና እንደነበር አጥዘነጋም፡፡ የዜና አንባቢዋ በሙከራ ደረጃ ከተዋወቀች በኃላ በጋዜጠኞች ስራ ላይ አደጋ ልትደቅን ትችላለች የሚል ስጋት ጭሮም ነበር፡፡

Читать полностью…

EthioTube

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 70 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደአገራቸው ሊመለሱ ነው

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሦስተኛ ዙር የስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ሂደት በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚጀመር አስታወቀ።

ስደተኞቹን ለመመለስ የተዋቀረውን ኮሚቴ የሚመሩት የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንደገለጹት 70 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅት እንዲደረግ አሳስበዋል።

አዲስ ማለዳ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባገኘችው መረጃ ሂደቱ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ አልተጠቀሰም። ይኹን እንጂ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት እና የክልል መንግስታት ከ15 ቀናት በኋላ ለሚጀመረው ስደተኞችን የመመለስ ተግባር አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ተብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

የኬንያ ሰራተኞች ለድሀ ዜጎች የቤት መገንቢያ የሚውል የ 1.5 በመቶ ተጨማሪ ግብር ሊከፍሉ ነው ተባለ

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ከያዝነው ወር ጀምሮ የኬንያ ሰራተኞች ለደሀ እና አቅመ ደካሞች የቤት መገንቢያ የሚውል የ 1.5 በመቶ ተጨማሪ ግብር እንዲከፍሉ የሚያደርገውን ህግ ስራ ላይ እንዲውል ፈርመውበታል ሲሉ የኬንያ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።

ህጉ በኬንያ ከያዝው ወር ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚሆን ሲገለፅ ሰራተኞቹ ከወር ደሞዛቸው ላይ የ1.5 በመቶ ተጨማሪ ግብር እንዲከፍሉ እንደሚደረግ እና ይህ ህግ በኢ መደበኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ የሀገሪቱን ሰራተኞች እንደማያካትት ተጠቁሟል።

አዲሱ የግብር ክፍያ በሀገሪቱ የህግ አውጪዎች እና የምክርቤት አባላት እውቅናን አግኝቷል የተባለ ሲሆን ነገር ግን በተቃዋሚዎች እና በብዙ ግብር ከፋዮች ዘንድ ነቀፋ እና ትችትን እያስተናገደ መሆኑም ነው የተገለፀው።

Читать полностью…

EthioTube

አቶ ነብዩ ተድላ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ

አቶ ነብዩ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለ22 ዓመታት በዋናው መስሪያ ቤት እና ሚሲዮን ጽህፈት ቤቶች ሲሰሩ ቆይተዋል።
በተጨማሪም በምክትል ቃል አቀባይነት መስራታቸውም ተገልጿል።

አቶ ነብዩ በኒዮርክ፣ ሪያድ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሌሎችም ሀገራት እና ከተሞች በዲፕሎማትነት ማገልገላቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። አቶ ነብዩ በዛሬው ዕለት ከውጭ ጉዳይ ቋሚ ዘጋቢዎች ጋር ተዋውቀዋል።

Читать полностью…

EthioTube

በትግራይ ፤ የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) ለሚለግሱ ሰዎች 10ሺ ብር ስጦታ ይሰጣል ተባለ

'አዶ' በሚል ስም እሚታወቅ አንድ የግል የህክምና ማዕከል በተፈጥሮአዊ መንገድ ፅንስ ለመቋጠር ላልቻሉት ልጅ እእዲኖራቸው ለማድረግ እየሰራሁት ነው ባለው ስራ ሴት እንስቶች 'እንቁላል' ወንዶች ደግሞ 'የዘር ፍሬ (ስፐርም) እንዲለግሱ ጥሪውን አቅርቧል።

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ መቀመጫውን ያደረገው 'አዶ' የእናቶች፣ ሕጻናት እና የነቃ ሕይወት ሕክምና ማዕከል ይህንን ሕክምና ለመስጠት ዝግጅት የጀመረው ከትግራይ ጦርነት በፊት እንደሆነና ህክምናውን ለመጀመር የተደረገው ጥረት በጦርነቱ ምክንያት ቢቋረጥም ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ግን ሂደቱ መቀጠሉን ይገለፃል።

ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት ታድያ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በመከወን ስፐርም እና እንቁላል ለመለገስ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን እየጠበቀ ነውም መባሉን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል። የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ዶ/ር ሳምሶን ሙልጌታ እንዳሉት ከሆነም ለጋሾችን እየጠበቅን ነው ነገር ግን ሁሉም ሰው የወንድ የዘር ፍሬ ወይም እንቁላል መለገስ አይችልም።  ከሁለቱም ፆታዎች ፈቃድ በተጨማሪ የብቃት መስፈርቶች አሉ ብለዋል።

የወንድ ዘር ለጋሾች የዘር ፍሬያቸው መጠን ከ 1.5 ሚ/ሊ በላይ መሆን አለበት፣በአንድ ሚ/ሊ ስፐርም ውስጥ ከ15 ሚሊዮን በላይ የወንድ የዘር ህዋስ (sperm cells) መኖር አለበት በተጨማሪም ለጋሾች ለኤችአይቪ፣ ለሄፐታይተስ ቫይረስ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ምርመራ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል።

እንቁላል ለሚለግሱ ሴቶች የእድሜ ገደብ እንዳለና እንቁላል ለመለገስ ብቁ የሆኑ ሴቶች በ 20 እና 30 አመት መካከል ናቸው በተጨማሪም ሴት ለጋሾች ቀደም ብለው የወለዱ መሆን አለባቸው ይላሉ ዶ/ር ሳምሶን። ይህ መስፈርት የተቀመጠው ለምን እንደሆነ ሲገልጹም “[የወለዱ ሴቶች] እንቁላሎቻቸው ተፈትነዋል ብለዋል።

የሕክምና ማዕከሉ ባለቤት እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉ ለጋሾች ከድርጅቱ ጋር በስምምነት መስራት እንደሚችሉም የገለፁ ሲሆን ከስምምነቱ አንዱ የተበረከተው የወንድ ዘር ወይም እንቁላል ለማን እንደሚሰጥ አለመገለፅ ነው ብለዋል።

በዚህ ልገሳ ለሚሳተፉ ሰዎች ማለትም ስፐርም ለሚለግሱ ወንዶች 10ሺ ብር ስጦታ እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ምንም እንኳ ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት ከትግራይ ምግብና መድሓኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ፍቃድ ተሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ኢንስፔክሽን፣የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ይህ በትግራይ ጤና ቢር በኩል ተሰጠ ስለተባለው ፍቃድ እሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ረቡዕ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - መጋቢት 11 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 20 , 2024

👉 አጣዬ ከትናንት ጀምሮ ህዝቡ ተጨንቋል 

👉ንግድ ባንክ ለተዘረፈበት ገንዘብ አዲስ ማስጠንቀቂያ

👉 ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የነፃ ንግድ 6 ሺህ እቃዎች ታሪፍ ወጣላቸው

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/gcT2uRX7OcE

Читать полностью…

EthioTube

5 የአውሮፕላን ማረፊያዎችን እየገነባሁ ነው- የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አምስት ተጨማሪ የሀገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አየር መንገዱ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን ለማስፋት እየሰራ ነው።

የሚያበራቸውን አውሮፕላኖች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ አየር መንገዱ 136 ዓለም አቀፍ እንዲሁም 22 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዳሉት ገልጸዋል።

አየር መንገዱ ተጨማሪ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን ለማስፋት የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ በአሁኑ ወቅት አምስት የሀገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን ተናግረዋል።

ኤርፖርቶቹ የሚገነቡት ሚዛን ቴፒ አማን፣ ነጌሌ ቦረና፣ ያቤሎ፣ ጎሬ መቱና ደብረ ማርቆስ መሆናቸውን ገልጸው፤ አራቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

ይህም በሀገር ውስጥ ያሉ ደንበኞች ፍላጎትን ተከትሎ የሚተገበር ሲሆን፤ በቀጣይም ሌሎች መዳረሻዎች ጥናት ላይ በተመሠረተ መልኩ ግንባታ የሚቀጥል ይሆናል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ጉዳት የደረሰባቸው የአክሱምና የቀብሪደሃር ኤርፖርቶች እድሳት እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገቡም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

አየር መንገዱ በቀጣይም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን ለማስፋት በትኩረት እንደሚሰራም ዋና ስራ አስፈጻሚው ጨምረው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2035 ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ለማድረግና በዓመት 67 ሚሊየን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ራዕይ አስቀምጦ እየሰራ ይገኛል።

Читать полностью…

EthioTube

የህዳሴ ግድብ 5 ተርባይኖች በመጪዎቹ ሳምንታት ሀይል ማመንጨት ይጀምራሉ ተባለ

ግንባታው ባይጠናቀቅም በ 2 ተርባይኖች ሀይል ማመንጨት ጀምሯል የተባለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በመጪዎቹ ሳምንታት 5 ሀይል አመንጪ ተርባይኖች ስራ እንደሚጀምሩ የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መግለፁን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ 13 ተርባይኖች ሀይል ማመንጨት ሲጀምሩ አጠቃላይ የግድቡ ስራ የሚጠናቀቅ መሆኑን የገለፁ ሲሆን 5 ሀይል አመንጪ ተርባይኖች በቀጣይ ሳምንታት ስራ እንደሚጀምሩ ገልፀዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ለጅቡቲ፣ ለሱዳን እና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል እየተሸጠ መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር አረጋዊ፤ ለታንዛኒያ እና ለደቡብ አፍሪካ ለመሸጥ ታቅዶ ንግግር ተጀምሯል ብልዋል፡፡ ለተገባደደው የግድቡ ስራ አሁን የሚቀሩት በአብዛኛውም ከውጭ የሚገቡ የመካኒካል እና ኤሌክትሪካል ግብአቶች መሆናቸውና አጠቃላይ ግንባታውም፤ በ1 ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መገመቱም ነው የተገለፀው።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ማክሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - መጋቢት 10 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 19, 2024

👉 ሸዋሮቢት ፋኖና መከላከያ መካከል ያለው ውጥረት ቀጥሏል
👉የቲቪ ጣቢያዎች ለሚለቁት ሙዚቃ ክፍያ ሊፈጽሙ ነው
👉 የመሬት ዞታና ካሳን በተመለከተ ዛሬ የቀረበው ረቂቅ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/1pZTm9buZYw

Читать полностью…

EthioTube

የአውሮጳ ህብረት እና ግብፅ ስደትን ለመግታት የ8 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ

የአውሮጳ ህብረት እና ግብፅ በንግድ እና በፀጥታ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንዲሁም ወደ አውሮጳ የሚደረገውን የስደተኞች ፍሰት ለመግታት ያለመ የ7.4 ቢሊዮን ዩሮ ወይም የ8 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱ የአውሮፓ ህብረት ከግብፅ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ ያደርገዋል።

የግብፅን የኢኮኖሚ ውድቀት ለመደገፍ በሚቀጥሉት ሶስት አመታት እርዳታ፣ብድር እና ሌሎች ድጋፎችን ያገኛከል ።የሀገሪቱ ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ ቀውስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ግብፃውያን ወደ አውሮፓ በተለይም በሊቢያ በኩል ለመሻገር ይሞክራሉ፡፡ባለሥልጣናቱ ከግብፅ ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ የሚወስደውን መንገድ ዘግተዋል፡፡

ግብጽ ወደ አውሮፓ የሚደረገውን መደበኛ ያልሆነ ስደት ለመግታት እንደምትሰራም አስታዉቃለች፡፡የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ "ይህ በልማት ላይ ያተኮሩ መፍትሄዎችን በመጠቀም የችግሩን መንስኤ መፍታት እና መደበኛ የስደት መስመሮችን ማሻሻልን ያጠቃልላል" ብለዋል ።

የአውሮፓ ህብረት ቀደም ባሉት ጊዜያት ቱኒዚያ፣ ሊቢያ እና ሞሪታንያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ለሚደረጉ መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰት ታዋቂ መንገዶች ከሚሆኑት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ተመሳሳይ ስምምነቶችን ተፈራርሟል።

Читать полностью…

EthioTube

ምክር ቤቱ 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል

በስብሰባውም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ /ማሻሻያ/ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Читать полностью…
Subscribe to a channel