ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ሴኔጋል በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ቀዳማዊ እመቤቶች ይኖራታል።

አዲሱ የሀገሪቱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲማዩ ፋየ ዛሬ ቃለመሃላ ፈጽመው ወደ ቤተመንግስት የሚገቡት ከሁለት ሚስቶቻቸው ጋር ነው።

የ44 አመቱ ፋየ ከ15 አመት በፊት ካገቧት ማሪያ ሆን አራት ልጆችን ወልደዋል። 

አብሳ ፋየንም ባለፈው አመት ማግባታቸውን የሚገልጹት ተመራጩ ፕሬዝዳንት በሁለቱም ሚስቶቻቸው ደስተኛ መሆናቸውን በምርጫ ቅስቀሳቸው ሲገልጹ ተደምጠዋል።

በየምርጫ ቅስቀሳ መድረኩ ከሁለት ሚስቶቻቸው ጋር መታየታቸውም የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት መሳቡና የሴኔጋላውያን መነጋገሪያ ርዕስ እንደነበር ፍራንስ 24 አስታውሷል።
“ከውብ ሚስቶቼ ቆንጆ ልጆች አግኝቻለሁ፤ በጣም ቆንጆዎች ናቸው፤ ሁሌም ከጎኔ ስለሆኑም ፈጣሪዬን በጣም አመሰግነዋለሁ” ሲሉ ነው ፋየ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገሩት።

የአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ንግግር እና በየአደባባዩ ከሚስቶቻቸው ጋር መታየታቸው ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ነውር አለመሆኑን ለማመላከት ያለመ ነው ይላሉ ጂቢ ዲያሄት የተባሉ የማህበረሰብ አጥኝ። 

በሴኔጋል ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በተለይ በገጠሪቱ ክፍል የተለመደና ቤተሰብን ለማብዛት አንደኛው መንገድ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

የሀገሪቱ ስታስቱክስ ተቋም በ2013 ያወጣው ጥናትም ከጠቅላላው ጋብቻ 32 ነጥብ 5 በመቶው በዚሁ መንገድ የተከናወነ መሆኑን ያሳያል። በርካታ ሚስቶችን የማግባቱ ልማድ በሴኔጋላውያን ወንዶች ቢደገፍም ሴቶች ግን ባል ሁሉንም ሚስቶቹን እኩል ማየት ስለማይችል መድልኦ መከሰቱ አይቀርም፤ ጋብቻው ሊታገድ ይገባል ሲሉ ይደመጣል ብሏል የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ በ2022 ባወጣው ሪፖርት።

አል አይን

Читать полностью…

EthioTube

ፑንትላንድ የሶማሊያን ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ተቃወመች!

የሶማሊያ ፓርላማ ‘አንድ ሰው አንድ ድምጽ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ እንደሚከተል ማስታወቁን ተከትሎ፣ ራስ ገዟ ፑንትላንድ ለፌዴራል ተቋማት እውቅና እንደማትሰጥ አስታውቃለች።

ሞቃዲሹ ከሚገኘው ማዕከላዊ መንግስት ጋራ ያላትን ተቃውሞዎች በተደጋጋሚ በመግለጫ ስታስታውቅ የከረመችው ፑንትላንድ፣ ዛሬ እሁድ ባወጣችው መግለጫ፣ በትናንትናው ዕለት በርካታ ሕገ መንግስታዊ ማሻሻዮችን ያደረገው የሶማሊያ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔዎችም ውድቅ አድርጋለች።

“በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም” ብሏል መግለጫው።

ሕዝበ ውሳኔ የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራትም አስታውቃለች፡፡ውስብስብ የሆነውንና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ሶማሊያ ከአምሣ ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡

ትናንት የተሰበሰበው የሶማሊያ ፓርላማ ‘አንድ ሰው አንድ ድምጽ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ተከትሎ፣ በፑንትላን የሚገኙ ባለሥልጣናት ቁጣቸውን ገልፀዋል።በተፈጥሮ ሃብቶች እና በቦሳሶ ወደቧ በመተማመን፣ ፑንትላንድ በእ.አ.አ 1998 ራስ ገዝ መሆኗን አውጃለች፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ከመጋቢት 30 ጀምሮ ለሚኒባሶች የሚደረገው የነዳጅ ድጎማ ሙሉ በሙሉ እንደሚቋረጥ ተገለጸ

ከዚህ ቀደም የነዳጅ ድጎማ ሲደረግላቸው የነበሩ የሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ከመጋቢት 30 ቀን  2016 ዓ.ም ጀምሮ ድጎማው እንደሚቋረጥ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።

መንግሥት ለረጅም ጊዜ ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ መጠን የለው ድጎማን ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጽ ይህንን ለማስቀረት በሂደት የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ ባወጣው ዕቅድ መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

ቀስ በቀስም መንግስት በነዳጅ ምርት ላይ የሚያደርገዉ ድጎማ የማቋረጥ እቅድ እንዳለዉ ይታወቃል፡፡

በሚኒባስ ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረገዉ መንግስት ድጎማን የማስቀረቱ አንዱ አቅድ መሆኑ ተመላክቷል፡፡  ሆኖም የድጎማ ስርአቱን የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች ማህበረሰቡን በሚገባ እያገለገሉ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሰልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሄኖስ ወርቁ ከዚህ ቀደም 170ሺ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርአት ውጪ መደረጋቸዉን ተናግረዋል።

ተሽከርካሪዎቹ ነዳጅ ድጎማን በስርዓት ባለመጠቀማቸው ከድጎማው ውጪ እንዲደረጉ ምክንያት መሆኑ አመላክተዋል።

ከፊታችን መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጅምሮ በነዳጅ ድጎማው ስርአት የሀገር አቋራጭና የከተማ አውቶቢስ ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀው እነዚህም ተሽከርካሪዎችን እስከሚቀጥሉት 5 አመታት ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡
                 
በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በኩል ከመጋቢት 30 2016 ዓ.ም በኃላ ድጎማዉ ከሚኒባስ ተሸከርካሪዎች ላይ እንደሚያነሳ የተወሰነ ቢሆንም ተግባራዊ የሚደረገዉ ግን የነዳጅ አገልግሎት ስርጭትን በተመለከተ ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክ፤ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከሌሎች ባላድርሻ አካላት የተዉጣጣዉ ኮሚቴ ዉሳኔዉን ሲያሳልፍ መሆኑን አመላክተዋል፡፡መንግስት በ5 አመታት ዉስጥ በነዳጅ ላይ የሚያደርገዉን ድጎማ ሙሉ በሙሉ እንደሚያቋርጥ ይታወቃል፡፡

መረጃው የመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ነው

Читать полностью…

EthioTube

ዛሬ በማን ሲቲ እና በአርሰናል መካከል በሚካሄደው ወሳኝ የፕሪምየር ሊግ ፍልሚያ ማን ያሸንፋል? ወይስ እኩል ይወጣሉ?

#PremierLeague #ManCity #Arsenal

Читать полностью…

EthioTube

አካል ጉዳተኞችን የተመለከተ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊወጣ መሆኑ ተሰማ

አካል ጉዳተኞች መብታቸው እንዲጠበቅ ለመብታቸው መጠበቅም ምላሽ የሚሰጥ ተፈጻሚነቱን የሚከታተል ባለቤት ያለው አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊወጣ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞችን መብት ምላሽ የሚሰጥ ጥቅል አዋጅ የላትም የተባለ ሲሆን ያን ለማድረግ የአካል ጉዳተኞች ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ወደ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መላኩ ተገልጿል።

ይህ የአካል ጉዳተኞች አዋጅ ፥ ያሉትን ህጎች ተከታትሎ የሚያስፈፅም፣ ካልተፈፀሙም ተጠያቂ የሚሆን ተቋም እንዲኖር ለማስቻል ፣ የህግ ክፍቶችም እንዲስተካከሉ ያደርጋል ተብሏል። አዋጁ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተልኮ አስፈላጊ አስተያየት ከተሰጡበት በኋላ ወደ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መላኩ ነው የተገለፀው።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው በማለት ትናንት ከቻይናው ሲጂቲኤን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ያለፈው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት አልነበረም ያሉት ጌታቸው ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና የትግራይ ሕዝብ ድጋሚ ጦርነት እንዳያገረሽ የተቻላቸውን ጥረት ኹሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

ጌታቸው ይህን ያሉት ፣ በአላማጣ አቅራቢያ በትግራይ ኃይሎች እና ባካባቢው ሚሊሻዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በተደረገ ማግስት ነው መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል።

አቶ ጌታቸዉ ይህንን ይበሉ እንጂ አብን፣ ሕወሃት ለአዲስ ዙር ጦርነት ቅስቀሳ እያደረገ ነው ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት የሕወሃት ተዋጊዎች ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ሳይፈቱና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጸጥታ ለማስከበር ሳይሠማራ ሕወሃት ለሌላ ዙር ጦርነት ፕሮፓጋንዳ በመለፈፍ ተጠምዷል ብሏል።

የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥታት የሕወሃትን የጠባጫሪነት ቅስቀሳ በትኩረት እንዲከታተሉና በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት "በንግግር" እና "ድርድር" እንዲፈታም አብን ጠይቋል። የአማራ ሕዝብ ሕወሃት ሊያደርስበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል በአንድነት እንዲቆም የጠየቀው ፓርቲው፣ የትግራይ ሕዝብም ራሱን ከሕወሃት ቀንበር እንዲያላቅቅ ጥሪ አድርጓል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክርትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል

በሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ዛሬ ከቀኑ 09 ሰዓት ከ46 ደቂቃ ጀምሮ ከባህር ዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ሲል የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

ኢትዮትዩብ ከተቋሙ ባገኘችው መረጃ የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ መጀመሩን ገልጿል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ

በቅርብ ጊዜያት በርካታ ቅሬታዎችን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉምሩክ የስራ ክፍል፤ ሰራተኞች በአዲስ መልክ እንደሚደራጁ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በ2016 ስምንት ወራት ውስጥ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

ኮሚሽኑ በሰራተኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ "ረጅም ጊዜ" የወሰደ ጥናት መካሄዱ ታውቋል።

በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል።

በመጋቢት መጀመሪያ "በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ አሉባልታዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከእውነት የራቁ ናቸው" በማለት የብሔራዊ የአየር ትራንስፖርት ፋሲሊቲ ኮሚቴ መግለጫ ቢሰጥም አየር መንገዱ በበኩሉ በቅሬታዎቹ ላይ ምርመራ መጀመሩን እንዳስታወቀ ከዚህ ቀደም የመረጃ ምንጫችን መዘገቡ ይታወሳል ።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የአማራ ክልል ይፋዊ ምላሽ ሰጠ

* " የዛቻና የጠብ አጫሪነት የሆነውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ ተመልክተነዋል " - የአማራ ክልል

የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ሀሙስ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል " ብሏል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ስርዓትን በማጣቀስ " የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል " ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳችና  የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ ነው ሲል ገልጿል።

በትናንትናው እለት ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደልና በማሰቃየት ላይ ይገኛል ሲል የአማራ ክልል ከሷል።

(ሙሉው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

Читать полностью…

EthioTube

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሰጠ የሀዘን መግለጫ !

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በባህር ዳር ከተማ በመጫወት ላይ ይገኝ የነበረው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወቱ ተሰምቷል።

አለልኝ አዘነ በተደጋጋሚ ለብሔራዊ ቡድናችን ተመርጦ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ እና በአሁኑ ወቅት በእግር ኳሳችን ላይ ምርጥ አቋማቸውን እያሳዩ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀስ ተጫዋች ነበር።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአለልኝ አዘነ አስደንጋጭ እና ልብ ሰባሪ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ ፣ ለወዳጅ ዘመድ ፣ ለሙያ አጋሮቹ እና መላው የእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

Читать полностью…

EthioTube

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መጽሃፍ ቅዱስ መሸጥ ጀመሩ።

ትራምፕ በራሳቸው ማህበራዊ ትስስር ገጽ (ትሩዝ ሶሻል) ደጋፊዎቻቸው “ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” የሚል ስያሜ ያለውን መጽሃፍ ቅዱስ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።

“ወደ ፋሲካ በዓል እየተቃረብን ነው፤ ‘ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ’ መጽሃፍ ቅዱስን በመግዛት አሜሪካ ዳግም እንድትጸልይ እናድርጋት” ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

ሁሉም አሜሪካውያን በቤታቸው መጽሃፍ ቅዱስ ሊኖራቸው እንደሚገባም ነው ያነሱት።


ትራምፕ ዝርዝር ውስጥ መግባት ባልፈልግም መጽሃፍ ቅዱስ በህይወቴ ውስጥ ልዩ ቦታ አለው ብለዋል።

“ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” መጽሃፍ ቅዱስ GodBlessTheUSABible.com በተሰኘ ድረገጽ በ59.9 ዶላር ለገበያ ቀርቧል ተብሏል።

ድረገጹ መጽሃፍ ቅዱስ በትራምፕ መተዋወቁ “ምንም አይነት ፖለቲካዊም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ” አላማ የለውም ማለቱንም አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት መጽሃፍ ቅዱሱን የሚያሳትመው ኩባንያ ባለቤት አለመሆናቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ዝናቸውን ተጠቅመው ለሰሩት የማስተዋወቅ ስራ ሊያገኙት ስለሚችሉት ገቢ የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድንም ሆነ መጽሃፍ ቅዱስ የሚሸጠው ኩባንያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ዋይትሃውስ ዳግም ለመግባት ከባይደን ጋር የሚፎካከሩት ትራምፕ በቀረቡባቸው አራት ክሶች የገጠማቸውን የገንዘብ እጥረት ለመሙላት ባለፈው ወር በስማቸው የተሰየሙ ስኒከር ጫማዎችን ማስተዋወቃቸው ይታወሳል።

አዲሱ የመጽሃፍ ቅዱስ ግዙ ቅስቀሳም በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ትራምፕ በቀጣዩ ምርጫ ክርስቲያን ደጋፊዎቻቸውን ለማብዛት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተገልጿል።

Читать полностью…

EthioTube

የአንበሳ እና ሸገር ከተማ አውቶቡሶች የመገልገያ ትኬት ከነገ ጀምሮ የሚቀየር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።

ትኬቶችን የመቀየር ስራ የመዲናዋ የትራንስፖርት ቢሮ በኪሎ ሜትር ባወጣው የትራንስፖርት ታሪፍ መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አስታውቋል። በመሆኑም አውቶቡሶቹ ከዚህ ቀደም ሲጠቀሙበት የነበረው ትኬት በባለ 5፣ 10፣ 15፣ 20 እና ባለ 25 ብር ይቀይራል ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሁለቱም ድርጅቶች የተቀየረው አዲስ ቲኬት ሙሉ በሙሉ ሥራ የሚጀምር ሲሆን በአዲስ መልክ ስራ ላይ የሚውለው ትኬት ከነባሩ የተለየ ቀለም፣ ወጥ የሆነ ዋጋ፣ ምስጢራዊ መለያ ያለው መሆኑን የዘገበው ኢዜአ ነው።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ህልፈተ ሕይወቱ ዛሬ መጋቢት 18/2016 ዓ.ም ንጋት ላይ የተሰማው የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ስብስብ ጋር ያልነበረ ሲሆን በትውልድ ቦታው አርባ ምንጭ ሌሊቱን በድንገት ማረፉ ተሰምቷል።

በቅርቡ የተሞሸረው አለልኝ አዘነ፤ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት መስጠቱ ይታወሳል።

ሥርዓተ ቀብሩ ዛሬ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ እንደሚፈፀም ታውቋል።
***

#ethiotube በተጫዋቹ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ  ማክሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - መጋቢት 17 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 26 , 2024

👉አርሲ 2 አገልጋዮች ከነቤተሰቦቻቸው ተገደሉ
👉ንግድ ባንክ የተወሰነ ብሩ ተመለሰለት ቀሪውስ
👉አሜሪካ በፈረሰው ድልድይ በርካታ መኪኖች የገቡበት አልታወቀም

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/wvNrMb6S5Xk?si=S2URZvXzpg_JxP7E

Читать полностью…

EthioTube

በአሜሪካ ቁልፍ የሚባለው የባልቲሞር ድልድይ መፈራረሱ ተሰማ

የሜሪላንድ ትራንስፖርት ባለስልጣን (ኤምቲኤ) ክስተቱን አስመልክቶ ዛሬ ማለዳ ብሎ በ ኤክስ ገፁ ላይ በምስል አጋርቷል። "አይ-695 የሚባለው ቁልፍ ድልድይ ክፉኛ መውደሙን በመግለፅ አሽከርካሪዎች በፓታፕስኮ ወንዝ ላይ ያለውን መንገድ ከመጠቀም እንዲቆጣቡ።

በሁለቱም አቅጣጫ ያሉት መንገዶች ተዘግተው የትራፊክ እንቅስቃሴው ተስተጓጉሎ ውሏል።በዩናይትድ ስቴትስ ባልቲሞር ከተማ የሚገኘው ይህው የፍራንሲስ ስኮት ቁልፍ ድልድይ በመርከብ ከተመታ በኋላ ፈርሷል ሲል ባለስልጣኑ አክሏል።

አደጋው ከጠዋቱ 1፡30 ላይ ሲደርስ መርከቧ ድልድዩን ከመምታች በኃላ በእሳት ተቃጥላ የሰጠመች ሲሆን በርካታ ተሽከርካሪዎች ውሃ ውስጥ መውድቃቻውን የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ባለሥልጣናቱ ክስተቱን "የጅምላ ጉዳት" ብለውታል

የባልቲሞር ከንቲባ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታው እንዳሉ እና የነፍስ አድን ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጭዎች ቢያንስ ሰባት ሰዎች በውሃ ውስጥ አሉ ተብለው መገመታቸውን እና እየተፈለጉ ነበር ሲል የባልቲሞር የእሳት አደጋ መከላከያ ዲፓርትመንት የግንኙነት ዳይሬክተር ኬቨን ካርትራይት ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል። አደጋው ሲደርስ የትራክተር ጎታችን ጨምሮ በርካታ ተሽከርካሪዎች በድልድዩ ላይ ነበሩ። ካርትራይት "አሁን ትኩረታችን እነዚህን ሰዎች ለማዳን እና መልሶ ለማግኘት መሞከር ነው" ብለዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሰኞ የኢት ዜና - መጋቢት 23 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 1, 2024

👉ህፃናቱን በመብላት ያስቸገረው ጅብ 

👉በልበሊት በፋኖ እና በመከላከያ ሀይሎች ምን ተፈጠረ

👉 የነዳጅ ድጎማን በተመለከተ አዲስ ነገር ተሰምቷል 


ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/RSCnHPbvwgk?si=3WJ5T9S1zhww7K8L

Читать полностью…

EthioTube

በእስራኤል በቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተቃውሞ አሰሙ

በእስራኤል ያለው ጥልቅ የፖለቲካ ክፍፍል በአደባባይ ታይቷል። በጥቅምት 7 በሃማስ የተፈፀመው ጥቃት ያስከተለውንን ድንጋጤ እና ሀገራዊ አንድነት ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ ወደ አንድ ጎን ፖለቲከኞች ቆመው ነበር። ነገር ግን ከስድስት ወራት በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች እንደገና በእስራኤል ጎዳናዎች ላይ በመውጣት ልዩነታቸውን አሳይተዋል።

ጦርነቱ የእስራኤልን የረዥም ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከስልጣን ለማውረድ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይቷል። በእየሩሳሌም ፖሊሶች የከተማዋን ዋና የሰሜን-ደቡብ ሀይዌይ ቤጊን ቦሌቫርድ ዘግተው ተቃዋሚዎች ለመበተን ከውሃ መድፍ የተተኮሰ መጥፎ ሽታ ያለው ንጥረ ነገር ተጠቅመዋል። አሁንም በጋዛ ታግተው የሚገኙ 130 የሚደርሱ እስራኤላውያንን ለማስፈታት አፋጣኝ ስምምነት እንዲደረግ በመጠየቅ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ብሎም ምርጫ እንዲደረግ የሚጠይቁ መፈክሮች ባስፋት ተሰምተዋል።

በተቃውሞ ሰልፍ ላይ የነበሩ ሰዎች እንዳሉት ከታጋቾቺካከል ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሞቱ እንዳሉ ገልፀዋል። የተቃዋሚዎቹ ትልቅ ስጋት ጦርነቱ ያለ ስምምነት በቀጠለ ቁጥር ብዙዎች ይሞታሉ ይላሉ። እሁድ አመሻሽ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በእስራኤል ፓርላማ ዙሪያ ሰፊ መንገዶችን ዘግተው ታይተዋል።በሌላ በኩል የዓለም ጤና ድርጅት እስራኤል በመጋቢት 18 የአልሺፋን ሆስፒታል ከበባ ከጀመረች ወዲህ 21 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል። እስራኤል በበኩሏ ወታደሮቿን ከሆስፒታሉ እያስወጣች እንዳለም አስታውቃለች።

@አዲስ ሪፖርተር

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube

Читать полностью…

EthioTube

ተጠባቂው የማን ሲቲ እና አርሰናል ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቀቀ። ሊቨርፑል መሪነቱን ተረክቧል። ዘንድሮ ዋንጫውን ማን ያነሳል?

#PremierLeague #ManCity #Arsenal

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ አርብ የኢት ዜና - መጋቢት 20 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 29 , 2024

👉ጌታቸው ረዳ በራያ ጉዳይ ምን አሉ
👉አብን ውስጥ ምን ተፈጠረ መግለጫውን አልተስማሙበትም

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇https://youtu.be/nhSkeV-1CYE

Читать полностью…

EthioTube

ተገቢ ያልሆነ ዝቅተኛ የቅጣት ውሳኔ የሰጠ ዳኛ ከሥራ ታገደ

 
በአንዲት ሕጻን ክብረ ንጽህና ላይ ወንጀል መፈጸሙ በተረጋጠ ተከሳሽ ላይ የስድስት ወር ቀላል የእስራት ቅጣት የወሰነ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛን ከሥራ ማገዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ደብረዘይት ከተማ ታኅሣስ 2016 ዓ.ም ተክለአብ ገለታ የተባለ የ17 ዓመት ወጣት በሕጻኗ ክብረ ንጽህና ላይ የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በሕክምና ማስረጃ መረጋገጡን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ሰንበታ ቀጄላ ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ የወንጀሉ ክስ የቀረበለት የመተከል ዞን የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት÷ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በተከሳሹ ላይ የስድስት ወር ቀላል እስራት ቅጣት ወስኗ ብለዋል።

የዳኞች አሥተዳደር ኮሚቴ በበኩሉ የወንጀል ድርጊቱ እስከ 10 ዓመት ጽኑ እስራት ሊያስቀጣ እንደሚችል ጉዳዩን አጣርቶ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪፖርት አቅርቧል ነው ያሉት፡፡

ውሳኔው ሕዝቡ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ ሆኖ በመገኘቱ÷ ውሳኔውን ያሳለፈው ዳኛ ከመጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ እና ደመወዝ መታገዱን አስታውቀዋል፡፡

የወረዳው ዐቃቤ ሕግ በወንጀል ክሱ መዝገብ በተሰጠው የቅጣት ውሳኔ ላይ ለመተከል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቁንም ጠቁመዋል፡፡

ወንጀል ፈጸሚው 17 ዓመት ቢሆነውም የፍርድ ሂደቱ በመደበኛ የወንጀለኛ መቅጫ የሚታይ ሲሆን÷ ቅጣቱ የሚፈጸመው ደግሞ በወጣት ጥፋተኞች ማረሚያ ማዕከል መሆኑንም ነው ያብራሩት፡፡

Читать полностью…

EthioTube

በደቡብ አፍሪካ የ45 ሰዎች ሕይወት ካለፈበት አደጋ የ8 ዓመት ልጅ በሕይወት ተገኘች

በደቡብ አፍሪካ የ45 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ዓመት ልጅ በሕይወት መገኘቷ ተሰምቷል፡፡

ከቦትስዋና ዋና ከተማ ጋቦሮኔ ወደ ሞሪያ ከተማ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ የ45 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አደጋው የተከሰተው አውቶቡሱ 50 ሜትር ከፍታ ካለው ድልድይ ተገልብጦ ሲሆን÷ በርካቶችን ከቀጠፈው አደጋም የስምንት ዓመት ልጅ ከባድ ጉዳት ቢደርስባትም በሕይወት ልትገኝ ችላለች።

አደጋው የተከሰተው በሰሜን ምስራቅ ሊምፖፖ ግዛት ሲሆን÷ አውቶቡስ ከድልድዩ ወደ ታች ከተገለበጠ በኋላ ከመሬት ጋር ሲጋጭ በእሳት መቀጣጠሉን ዘገባው አመላክቷል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሀሙስ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - መጋቢት 19 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 28 , 2024

👉መንግስት በነ ዘመነ ካሴ ላይ የወሰደው እርምጃ
👉የጉምሩክ ሰራተኞች በአዲስ መልክ
👉የአማራ ክልል ለትግራይ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇https://youtu.be/U0Tpi0h1bi0?si=Zr-vIbSbecNquc5v

Читать полностью…

EthioTube

በዮሐንስ_ቧያለው፣ ክርስቲያን_ታደለ፣ እስክንድር_ነጋና ዘመነ_ካሴ ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ መመስረቱን ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ

ዮሐንስ ቧያለውና ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ፤ ክሱን የመሰረተው የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ነው።

በተከፈተው ክስ ዝርዝር ላይ እንደተገለጸው፤ ተከሳሾች የፖለቲካ ርዕዮትን በኃይል ለማስፈፀም በማሰብ የሚለው ይገኝበታል ያለው ዘገባው ተከሳሾች ያደራጁትን የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን ዓላማ ለማስፈፀም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሰብስበዉ በመደራጀት፤ የአማራ ሕዝብ “ሀገር ተወስዶበታል ርስቱን ተቀምቷል” የሚል አቋም በመያዝ የአማራ ርስት ናቸው የሚሏቸዉን መሬቶች በወታደራዊ ኃይል ለማስመለስና ሀገርን ‹‹በአማራ እሳቤ ብቻ መገዛት አለባት›› በሚል ስምምነት ላይ ደርሰዋል የሚል እንደሚገኝበት አስታውቋል።

ከ90 በላይ የመንግስት እና የግለሰቦች መኪኖች እንዲዘረፉ እና እንዲወድሙ እንዲሁም ለአርሶ አደር የሚከፋፈሉ ከ9 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ የዘረፉ እና እንዲዘረፉ ያደረጉ በመሆኑ የሚል ክስም እንደተመሰረተባቸው አመላክቷል።

Читать полностью…

EthioTube

የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት “ዲሞግራፊ ለመቀየር” የሚካሄድ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተባበሉ

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ እና አካባቢ ልማት ፕሮጀክት፤ “ዲሞግራፊ ለመቀየር” አሊያም “ኦሮሞዎችን ወደ ከተማ ለመመለስ ነው” የሚሉ ወገኖችን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተቹ።

አዲስ አበባ ውስጥ “ከበቂ በላይ” የኦሮሞ እና የሌሎች ብሔር ተወላጆች መኖራቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የሌለ ሰው ኖሮ፤ ሰው ለማምጣት የምንቸገርበት አይደለም” ሲሉም አስተባብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራን ከሚያስፈጽሙ አመራሮች እና የስራ ኃላፊዎች ጋር ትላንት ረቡዕ መጋቢት 18፤ 2016 ባደረጉት ውይይት መሆኑን ዳጉ ጆርናል ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘገባ ተመልክቷል። እርሳቸው የሚመሩት መንግስት ከዚህ ቀደም ባከናወናቸው የግንባታ ስራዎች “ብዙ ስሞታዎች ነበሩ” ያሉት አብይ፤ ለዚህም የምኒልክ ቤተ መንግስት እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እድሳትን በምሳሌነት አንስተዋል።

“ይሄ ግቢ ሲቀየር ሀገራዊ ፖለቲካ ነበር። የእዚህን ግቢ እድሳትን እና ዩኒቲ ፓርክን ለመቃወም ሰዎች በጣም ብዙ ደክመዋል። በኋላ [የአዲስ አበባ ከተማ] ማዘጋጃ ቤት ሲጠናቀቅ፤ ‘ለምን ተሰራ’ ተብሎ ብዙ ተብሏል። አሁንም ብዙ አሉባልታዎች፤ ብዙ ወሬዎች ይሰማሉ። ‘ዲሞግራፊ ለመቀየር ነው’፤ ‘ኦሮሞዎች ለመመለስ ነው’ [የሚሉ] የተለያዩ ስሞች ይሰጣሉ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

Via Ethiopia Insider

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ረቡዕ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - መጋቢት 18 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 27 , 2024

👉ህውሃት ራያ ላይ ጦርነት መክፈቱ ተሰማ
👉ንግድ ባንክ የመጨረሻ ያለውን ማስጠንቀቂያ ሰጠ
👉የአሜሪካ የሃይማኖት ተቋማት ስጋት የ3 ዓመት ህፃን የደፈረው ወንጀለኛ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/8FUcZa30K90?si=--kwq99Ng_H4G-Mq

Читать полностью…

EthioTube

የ3 አመቷን ህጻን አስገድዶ በመድፈር ገድሎ ተሰውሮ የነበረ ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ።

ቢሊሱማ መሃመድ የተባለችን የ3 አመት ህጻን የእንጀራ ልጁን አስገድዶ በመድፈር ገድሎ ተሰውሮ የነበረ ተጠርጣሪ ግለሰብ በድሬዳዋ ከተማ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የድሬዳዋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሟቿ ህጻን እናት ከባለቤቷ ጋር በትዳር መቀጠል ባለመቻላቸው ምክንያት ከተለያዩ በኃላ ወደ ሀሮማያ ከተማ በመሄድ ሌላ ባል አግብታ ህጻኗም ከእናቷ እና እንጀራ አባቷ ጋር ትኖር ነበር፡፡

ተከሳሹ የእንጀራ አባቷ ግለሰብ ለ15 ቀን በትዳር ከቆየ በኃላ ገና ምንም ነፍስ እንኳን ያላወቀችውን ህጻን አስገድዶ ደፍሮ መግደሉ ተገልጿል።

ለ11 ወራት ያህል ተሸሽጎ የቆየው ተጠርጣሪው መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ጠዋት ከተሸሸገበት ወጥቶ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ  በቁጥጥር ስር ውሎ ለሀሮማያ ከተማ ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ ተጠቁሟል።

ግለሰቡ ለምን ይችን ገና ነፍስ እንኳን ያላወቀች፣ ክፉ ደጉን የማትለይ ህፃን አስገድዶ እንደደፈረና እንደገደለ ሲጠየቅ " ሰይጣን አሳስቶኝ ነው " ማለቱን ከፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Читать полностью…

EthioTube

በአሜሪካ የሚኒሶታ የሀይማኖት ተቋማት ፆታ የሚቀይሩ ሰዎችን የመቅጠር የህግ ግዴታ እንዳይጣልባቸው ጠየቁ

በአሜሪካ ሚኒሶታ የካቶሊኮች፣ ሉተራኖች፣ አይሁዶች እና ሙስሊሞች የሃይማኖት ጥምረት ቡድን የሃይማኖት ድርጅቶች እና ትምህርት ቤቶች ሀይማኖታዊ እሴቶችን የሚጥሱ ጾታ ቀያሪ ግለሰቦችን ከመቅጠር ግዴታ ነፃ እንዲሆኑ የሚያደርገውን የሚኒሶታ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ እንዲሻሻል ጠይቀዋል።

ባለፈው አመት ህግ አውጪዎች የሚኒሶታ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ላይ በፆታ ማንነት ላይ የተመሰረተ መድልዎን የሚከለክል ህግ ማውጣታቸው ሲገለፅ የሀይማኖት ተቋማቱ ግብረ ሰዶማውያንን በተቋሞቻቸው የመቅጠር ግዴታ እንዳይኖርባቸው ቢደረግም ፆታን የሚቀይሩ ዜጎች ላይ የተቀመጠ አመልካች ህግ አልነበረም።

አሁን ላይ እንዲፀድቅ የተጠየቀው አዲስ ድንጋጌ ሁሉም የሃይማኖት ድርጅቶች እና ተቋማት ከፆታ ማንነት ጋር በተገናኘ ጾታ ቀያሪዎችን በግዴታ የመቅጠር ፖሊሲውን ከመከተል ነፃ ለማድረግ ያለመ ነው ሲባል የሀይማኖት ተቋማቱ ያለ ህዝባዊ የመብት ሙግት ጾታ ቀያሪ ሰዎችን መቅጠር መተው እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

Читать полностью…

EthioTube

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ገንዘብ የወሰዱ ደንበኞች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ

Читать полностью…

EthioTube

በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከአምስት ዓመት በላይ የተከማቸ ዝቃጭ ቆሻሻ መኖሩ ተገለጸ

በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ 5 ዓመት በላይ የተከማቸ ዝቃጭ ቆሻሻ መኖሩን ያስታወቀው መረጃው ከፓርኩ ወደ ሀዋሳ ሐይቅ የሚገባ ፍሳሽ አለ መባሉንም ጠቁሟል።

ከሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በተጨማሪ ከቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ እርሻ ማሳ የሚገባ ፍሳሽ መኖሩም በኦዲት ሪፖርቱ መመለካቱን አስታውቋል።

ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተጠናላቸው አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ውጪ በሆኑ ዘርፎች ሲሰማሩ ተገቢው ጥናት አልተደረገም ተብሏል።

በምርት ሂደት የሚጠቀሙባቸውን ኬሚካሎች ይዘት ለኮርፖሬሽኑና ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚያሳውቁበት መመሪያ አለመኖሩ ተገልጿል።

Читать полностью…

EthioTube

ንግድ ባንክ ባጋጠመው ችግር የተመዘበረው 801.4 ሚሊዮን ብር መሆኑን አስታወቀ

👉 እስካሁን 622.9 ሚሊዮን ብር ማስመለስ ችሏል


ንግድ ባንክ ሰሞኑን አጋጥሞት በነበረው ችግር ያለአግባብ የተወሰደበት የገንዘብ መጠን 801.4 ሚሊዮን ብር መሆኑን አስታወቀ።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ዛሬ ረፋዱ ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የተፈጠረውን ችግር በመጠቀም ከተወሰደ ገንዘብ ውስጥ እስከ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ባለ ሪፖርት 622.9 ሚሊዮን ብር ማስመለስ መቻሉን ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ ተሳትፎ የነበራቸው 9,281 ያህል ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ብር 223.47 ሚሊዮን ብር በፈቃደኝነት ሙሉ በሙሉ መልሰዋል ያሉት የባንኩ ፕሬዝዳንት ፣ በጉዳዩ ላይ ተሳትፎ የነበራቸው 5,160 ያህል ግለሰቦች ደግሞ የወሰዱትን ገንዘብ በከፊል ማለትም ብር 149.02 ሚሊዮን ብር በፈቃደኝነት መመለሳቸውን አስታውቀዋል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel