ኢትዮጵያ፦ እለተ ማክሰኞ የኢት ዜና - መጋቢት 24 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 2, 2024
👉መራራ ጉዲና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ተቹ
👉የመንገዶች ባለስልጣን ሾፌር አደገኛ እጽ በማዘዋወር ተቀጣ
👉የ 12 አመቷን ህፃን ያገባት የ 63 ዓመቱ ጋናዊ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/acJX8nL_pXQ?si=B0RSpELK-sgIU9uR
የሐማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬ እህት በእስራኤል በቁጥጥር ስር ዋለች
የእስራኤል ፖሊስ በደቡብ እስራኤል ባደረገው ዘመቻ የ57 አመቷን የሃማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ እህት መያዙን አስታዉቋል።የእስራኤል ዜጋ የሆነችው ሳባህ አብደል ሳላም ሃኒዬህ በቴልሼቫ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን የእስራኤል የደህንነት ኤጀንሲ ሺን ቤትን ያካተተ የምርመራ ዘመቻን መደረጉን ተከትሎ ነዉ።የሃኒዬ እህት መሆኗን ያረጋገጡት የፖሊስ ቃል አቀባይ "ከሃማስ ኦፕሬተሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር እና ከድርጅቱ ጋር በመገናኘት በእስራኤል ውስጥ የሽብርተኝነት ድርጊቶችን በማነሳሳት እና በመደገፍ ተጠርጥራለች" ብለዋል፡፡
በቤቷ ውስጥ "በእስራኤል መንግስት ላይ ከባድ የደህንነት ጥፋቶችን የሚያሳዩ ሰነዶች፣ ሚዲያዎች፣ ስልኮች፣ ሌሎች ግኝቶች እና ማስረጃዎች"መያዙን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡በሌላ በኩል በፈረንሣይኛ ስያሜው ኤም ኤስ ኤፍ የሚታወቀው ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን፣ በአል አቅሳ ሆስፒታል የሚሠራው ስራ እሁድ ዕለት በእስራኤል የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ሥራ ማቆሙን እና ሽፋን እየፈለገ መሆኑን አስታዉቋል፡፡
"ቡድናችን በአቅራቢያው ከፍተኛ ፍንዳታ ሲሰማ ጥቃቱ ማለቁ እስኪረጋገጥ ድረስ በሆስፒታሉ ውስጥ የነበረንን ስራ አቁመናል" ሲሉ አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።ኤም ኤስ ኤፍ “አፋጣኝ እና ቀጣይነት ያለው” የተኩስ አቁም ጥሪውን በድጋሚ አቅርቧል።በጥቃቱ ቢያንስ አራት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 17 ሰዎች ቆስለዋል።
የጋዛ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው እስራኤል ወታደሮቿን እና ታንኮችን ከጋዛ አል-ሺፋ የህክምና ኮምፕሌክስ ዉስጥ አውጥታለች ብሏል።ሚኒስቴሩ በደርዘን የሚቆጠሩ አስከሬኖች ከፍርስራሽ ዉስጥ ተገኝተዋል ብሏል፡፡የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ከአል-ሺፋ ሆስፒታል የተገኙት ምስሎች “አስፈሪ እና አስደንጋጭ ናቸው” ብለዋል።‹‹ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ተቋማት ኃላፊነታቸውን ይወጡ ይሆን? የታወቁ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች የዚህን ግልጽ የጦር ወንጀል ስፋት በተመለከተ አለም አቀፍ ምርመራን ይደግፋሉ ወይንስ መራጭ እና አድሎአዊ ባህሪው ይቀጥላል? በማለት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ በኤክስ ገጻቸዉ ላይ አስፍረዋል፡፡
የእስራኤል ጦር በበኩሉ ከጥቅምት 7 ጥቃት ወዲህ የተገደሉበት ወታደሮች ቁጥር 600 መድረሱን አስታዉቋል፡፡
ዳጉ ጆርናል
የተፈጠረው የነዳጅ እጥርት እስከ ነገ ጠዋት ድረስ ይቀረፋል ፦የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ማስተዋል የተለመደ ሆኗል።
ይሄንንም ተከትሎ የረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ኢቢሲ ሳይበር የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትን አነጋግሯል፡፡
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ይስማ አለም ምህረቱ የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ጅቡቲ ላይ የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ድልድይ በመሰበሩ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ነዳጅ የጫነ አንድ የነዳጅ ቦቴ ተገልብጦ መንገድ መዘጋጋት በማስከተሉ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን አስረድተዋል፡፡
የ63 ዓመቱ ጋናዊ ቄስ የ12 ዓመት ታዳጊ ማግባታቸው ቁጣ ቀሰቀሰ
ኑሞ ቦርኬቴ ላዌህ ትሱሩ 33ኛ ቅዳሜ ዕለት በተካሄደ የሠርግ ሥነ-ሥርዓት ነው ታዳጊዋን ያገቡት። ምንም እንኳ በርካታ ትችት እየዘነበ ቢሆንም የማሕበረሰብ መሪዎች፤ ሰዎች በባሕል እና ወጋችን አያገባቸውም የሚል ምላሽ እየሰጡ ነው።
በጋና ከ18 ዓመት በታች ጋብቻ መፈፀም ሕጋዊ አይደለም። ምንም እንኳ በሀገሪቱ ያለዕድሜ ጋብቻ እየቀነሰ ቢመጣም አሁንም በአንዳንድ ሥፍራዎች ይህ ሲከናወን ይታያል።
ቅዳሜ ዕለት የነበረውን ፕሮግራም የሚያሳዩ ቪድዮዎች እና ፎቶዎች እንደሚጠቁሙት በርካታ የማሕበረሰብ መሪዎች ታድመዋል።
ቪድዮዎች እና ፎቶዎች ማሕበራዊ ሚድያዎች ላይ በስፋት መሰራጨታቸውን ተከትሎ ጋናዊያን ቁጣቸውን እያሰሙ ነው።
በሥነ-ሥርዓቱ ወቅት አንዲት ጋ በተሰኘው ቋንቋ ንግግር ያሰሙ ሴት፤ ታዳጊዋ ባሏን በሚማርክ መልኩ እንድትለብስ ሲመክሩ ይደመጣሉ።
አክለው የሚስት ተግባራትን ለመከወን እንድትዘጋጅ እና በስጦታ የተሰጣትን ሽቶ ተቀብታ ለባሏ ወሲብ ቀስቃሽ ሆና እንድትገኝ ሲናገሩ ይደመጣሉ።
ይህ ንግግር በጋናዊያን ዘንድ ያለውን ቁጣ እጅግ ያጋለው ሲሆን ጋብቻው እንዲሁ ለወግ ብቻ የተዘጋጀ አይደለም ማለት ነው የሚል ሐሳብ ጭሯል።
ብዙዎች መንግሥት ጋብቻውን እንዲያፈርስ እና ትሱሩን የተባሉትን ቄስ እንዲመረምር ጥያቄ እያቀረቡ ነው።
ታዳጊዋ እና ቄሱ አባል የሆኑበት ኑንጋ የተባለው ጥንታዊ ብሔረሰብ መሪዎች ከተቀረው የጋና ክፍል የቀረበባቸውን ትችት አስተባብለው ትችቱ “ካለማወቅ የመነጨ ነው” ብለዋል። ኒ ቦርቴ ኮፊ ፍራንክዋ 2ተኛ የተባሉ አንድ የማሕበረሰብ መሪ እሑድ ዕለት ታዳጊዋ የቄሱ ሚስት ሆና የምትጫወተው ሚና “ባሕላዊ እና ወጋዊ ብቻ ነው” ብለዋል።
ለሀገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ጅቡቲ ወደብ ደርሰዋል ተባለ
በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ጣና ሐይቅ ላይ ለሀገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ትላንት ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸው ተነግሯል።
ጅቡቲ የደረሱት "ጣና ነሽ ፪" የተሰኘችው የሰው ማጓጓዣና የመዝናኛ መርከብ እንዲሁም ሌላኛዋ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ ጀልባ ናቸው። ጣናነሽ ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣ እና የመዝናኛ መርከብ ስትሆን 38ሜ እርዝመት እንዳላት እና በአንድ ግዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላት ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያ፦ እለተ ሰኞ የኢት ዜና - መጋቢት 23 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 1, 2024
👉ህፃናቱን በመብላት ያስቸገረው ጅብ
👉በልበሊት በፋኖ እና በመከላከያ ሀይሎች ምን ተፈጠረ
👉 የነዳጅ ድጎማን በተመለከተ አዲስ ነገር ተሰምቷል
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/RSCnHPbvwgk?si=3WJ5T9S1zhww7K8L
በእስራኤል በቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተቃውሞ አሰሙ
በእስራኤል ያለው ጥልቅ የፖለቲካ ክፍፍል በአደባባይ ታይቷል። በጥቅምት 7 በሃማስ የተፈፀመው ጥቃት ያስከተለውንን ድንጋጤ እና ሀገራዊ አንድነት ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ ወደ አንድ ጎን ፖለቲከኞች ቆመው ነበር። ነገር ግን ከስድስት ወራት በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች እንደገና በእስራኤል ጎዳናዎች ላይ በመውጣት ልዩነታቸውን አሳይተዋል።
ጦርነቱ የእስራኤልን የረዥም ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከስልጣን ለማውረድ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይቷል። በእየሩሳሌም ፖሊሶች የከተማዋን ዋና የሰሜን-ደቡብ ሀይዌይ ቤጊን ቦሌቫርድ ዘግተው ተቃዋሚዎች ለመበተን ከውሃ መድፍ የተተኮሰ መጥፎ ሽታ ያለው ንጥረ ነገር ተጠቅመዋል። አሁንም በጋዛ ታግተው የሚገኙ 130 የሚደርሱ እስራኤላውያንን ለማስፈታት አፋጣኝ ስምምነት እንዲደረግ በመጠየቅ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ብሎም ምርጫ እንዲደረግ የሚጠይቁ መፈክሮች ባስፋት ተሰምተዋል።
በተቃውሞ ሰልፍ ላይ የነበሩ ሰዎች እንዳሉት ከታጋቾቺካከል ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሞቱ እንዳሉ ገልፀዋል። የተቃዋሚዎቹ ትልቅ ስጋት ጦርነቱ ያለ ስምምነት በቀጠለ ቁጥር ብዙዎች ይሞታሉ ይላሉ። እሁድ አመሻሽ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በእስራኤል ፓርላማ ዙሪያ ሰፊ መንገዶችን ዘግተው ታይተዋል።በሌላ በኩል የዓለም ጤና ድርጅት እስራኤል በመጋቢት 18 የአልሺፋን ሆስፒታል ከበባ ከጀመረች ወዲህ 21 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል። እስራኤል በበኩሏ ወታደሮቿን ከሆስፒታሉ እያስወጣች እንዳለም አስታውቃለች።
@አዲስ ሪፖርተር
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
ተጠባቂው የማን ሲቲ እና አርሰናል ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቀቀ። ሊቨርፑል መሪነቱን ተረክቧል። ዘንድሮ ዋንጫውን ማን ያነሳል?
#PremierLeague #ManCity #Arsenal
ኢትዮጵያ፦ እለተ አርብ የኢት ዜና - መጋቢት 20 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 29 , 2024
👉ጌታቸው ረዳ በራያ ጉዳይ ምን አሉ
👉አብን ውስጥ ምን ተፈጠረ መግለጫውን አልተስማሙበትም
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇https://youtu.be/nhSkeV-1CYE
ተገቢ ያልሆነ ዝቅተኛ የቅጣት ውሳኔ የሰጠ ዳኛ ከሥራ ታገደ
በአንዲት ሕጻን ክብረ ንጽህና ላይ ወንጀል መፈጸሙ በተረጋጠ ተከሳሽ ላይ የስድስት ወር ቀላል የእስራት ቅጣት የወሰነ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛን ከሥራ ማገዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ደብረዘይት ከተማ ታኅሣስ 2016 ዓ.ም ተክለአብ ገለታ የተባለ የ17 ዓመት ወጣት በሕጻኗ ክብረ ንጽህና ላይ የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በሕክምና ማስረጃ መረጋገጡን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ሰንበታ ቀጄላ ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ የወንጀሉ ክስ የቀረበለት የመተከል ዞን የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት÷ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በተከሳሹ ላይ የስድስት ወር ቀላል እስራት ቅጣት ወስኗ ብለዋል።
የዳኞች አሥተዳደር ኮሚቴ በበኩሉ የወንጀል ድርጊቱ እስከ 10 ዓመት ጽኑ እስራት ሊያስቀጣ እንደሚችል ጉዳዩን አጣርቶ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪፖርት አቅርቧል ነው ያሉት፡፡
ውሳኔው ሕዝቡ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ ሆኖ በመገኘቱ÷ ውሳኔውን ያሳለፈው ዳኛ ከመጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ እና ደመወዝ መታገዱን አስታውቀዋል፡፡
የወረዳው ዐቃቤ ሕግ በወንጀል ክሱ መዝገብ በተሰጠው የቅጣት ውሳኔ ላይ ለመተከል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቁንም ጠቁመዋል፡፡
ወንጀል ፈጸሚው 17 ዓመት ቢሆነውም የፍርድ ሂደቱ በመደበኛ የወንጀለኛ መቅጫ የሚታይ ሲሆን÷ ቅጣቱ የሚፈጸመው ደግሞ በወጣት ጥፋተኞች ማረሚያ ማዕከል መሆኑንም ነው ያብራሩት፡፡
በደቡብ አፍሪካ የ45 ሰዎች ሕይወት ካለፈበት አደጋ የ8 ዓመት ልጅ በሕይወት ተገኘች
በደቡብ አፍሪካ የ45 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ዓመት ልጅ በሕይወት መገኘቷ ተሰምቷል፡፡
ከቦትስዋና ዋና ከተማ ጋቦሮኔ ወደ ሞሪያ ከተማ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ የ45 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አደጋው የተከሰተው አውቶቡሱ 50 ሜትር ከፍታ ካለው ድልድይ ተገልብጦ ሲሆን÷ በርካቶችን ከቀጠፈው አደጋም የስምንት ዓመት ልጅ ከባድ ጉዳት ቢደርስባትም በሕይወት ልትገኝ ችላለች።
አደጋው የተከሰተው በሰሜን ምስራቅ ሊምፖፖ ግዛት ሲሆን÷ አውቶቡስ ከድልድዩ ወደ ታች ከተገለበጠ በኋላ ከመሬት ጋር ሲጋጭ በእሳት መቀጣጠሉን ዘገባው አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሀሙስ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - መጋቢት 19 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 28 , 2024
👉መንግስት በነ ዘመነ ካሴ ላይ የወሰደው እርምጃ
👉የጉምሩክ ሰራተኞች በአዲስ መልክ
👉የአማራ ክልል ለትግራይ የሰጠው ማስጠንቀቂያ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇https://youtu.be/U0Tpi0h1bi0?si=Zr-vIbSbecNquc5v
በዮሐንስ_ቧያለው፣ ክርስቲያን_ታደለ፣ እስክንድር_ነጋና ዘመነ_ካሴ ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ መመስረቱን ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ
ዮሐንስ ቧያለውና ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ፤ ክሱን የመሰረተው የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ነው።
በተከፈተው ክስ ዝርዝር ላይ እንደተገለጸው፤ ተከሳሾች የፖለቲካ ርዕዮትን በኃይል ለማስፈፀም በማሰብ የሚለው ይገኝበታል ያለው ዘገባው ተከሳሾች ያደራጁትን የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን ዓላማ ለማስፈፀም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሰብስበዉ በመደራጀት፤ የአማራ ሕዝብ “ሀገር ተወስዶበታል ርስቱን ተቀምቷል” የሚል አቋም በመያዝ የአማራ ርስት ናቸው የሚሏቸዉን መሬቶች በወታደራዊ ኃይል ለማስመለስና ሀገርን ‹‹በአማራ እሳቤ ብቻ መገዛት አለባት›› በሚል ስምምነት ላይ ደርሰዋል የሚል እንደሚገኝበት አስታውቋል።
ከ90 በላይ የመንግስት እና የግለሰቦች መኪኖች እንዲዘረፉ እና እንዲወድሙ እንዲሁም ለአርሶ አደር የሚከፋፈሉ ከ9 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ የዘረፉ እና እንዲዘረፉ ያደረጉ በመሆኑ የሚል ክስም እንደተመሰረተባቸው አመላክቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት “ዲሞግራፊ ለመቀየር” የሚካሄድ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተባበሉ
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ እና አካባቢ ልማት ፕሮጀክት፤ “ዲሞግራፊ ለመቀየር” አሊያም “ኦሮሞዎችን ወደ ከተማ ለመመለስ ነው” የሚሉ ወገኖችን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተቹ።
አዲስ አበባ ውስጥ “ከበቂ በላይ” የኦሮሞ እና የሌሎች ብሔር ተወላጆች መኖራቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የሌለ ሰው ኖሮ፤ ሰው ለማምጣት የምንቸገርበት አይደለም” ሲሉም አስተባብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራን ከሚያስፈጽሙ አመራሮች እና የስራ ኃላፊዎች ጋር ትላንት ረቡዕ መጋቢት 18፤ 2016 ባደረጉት ውይይት መሆኑን ዳጉ ጆርናል ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘገባ ተመልክቷል። እርሳቸው የሚመሩት መንግስት ከዚህ ቀደም ባከናወናቸው የግንባታ ስራዎች “ብዙ ስሞታዎች ነበሩ” ያሉት አብይ፤ ለዚህም የምኒልክ ቤተ መንግስት እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እድሳትን በምሳሌነት አንስተዋል።
“ይሄ ግቢ ሲቀየር ሀገራዊ ፖለቲካ ነበር። የእዚህን ግቢ እድሳትን እና ዩኒቲ ፓርክን ለመቃወም ሰዎች በጣም ብዙ ደክመዋል። በኋላ [የአዲስ አበባ ከተማ] ማዘጋጃ ቤት ሲጠናቀቅ፤ ‘ለምን ተሰራ’ ተብሎ ብዙ ተብሏል። አሁንም ብዙ አሉባልታዎች፤ ብዙ ወሬዎች ይሰማሉ። ‘ዲሞግራፊ ለመቀየር ነው’፤ ‘ኦሮሞዎች ለመመለስ ነው’ [የሚሉ] የተለያዩ ስሞች ይሰጣሉ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
Via Ethiopia Insider
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
ኢትዮጵያ፦ የእለተ ረቡዕ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - መጋቢት 18 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - March 27 , 2024
👉ህውሃት ራያ ላይ ጦርነት መክፈቱ ተሰማ
👉ንግድ ባንክ የመጨረሻ ያለውን ማስጠንቀቂያ ሰጠ
👉የአሜሪካ የሃይማኖት ተቋማት ስጋት የ3 ዓመት ህፃን የደፈረው ወንጀለኛ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/8FUcZa30K90?si=--kwq99Ng_H4G-Mq
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና ብልፅግና ፓርቲ በፕሪቶሪያ ውል መሰረት ፓለቲካዊ ውይይት ለመጀመር ተስማሙ
ህወሓት በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፁ ባሰራጨው መረጃ ፥ በብልፅግና ምክትል ፕረዚደንት አቶ አደም ፋራህ የሚመራ ቡድን ዛሬ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም በመቐለ ከህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ተወያይቷል።
የሁለቱም ፓለቲካዊ ፓርቲዎች የፓለቲካ ውይይት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ቀደም ብሎ መጀመር እንደነበረበት በመተማመን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውይይት እንዲጀምሩ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ህወሓት ገልጿል።
የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል፣ የሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል ዋና አዛዥ አድሚራል ቭላድሚር ካሳቶኖቭ የመሩት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ትናንት ምጽዋ መግባቱን የኤርትራ መንግሥት አስታውቀዋል።
የማነ፣ ልዑካን ቡድኑን የኤርትራ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ፊሊጶስ ወልደማርያም እንደተቀበሉት ገልጸዋል። የሩሲያ ባሕር ኃይል አንዲት ወታደራዊ መርከብ ከኤርትራ ባሕር ኃይል ጋር ለዘጠኝ ቀናት የሚቆይ ልምምድ በቀይ ባሕር ላይ ለማድረግ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ምጽዋ መድረሷ ይታወሳል።
12 ማዳበሪያ አደገኛ ዕፅ በማዘዋወር ጥፋተኛ የተባለ የመንገዶች ባለስልጣን የመኪና ሹፌር በጽኑ እስራት ተቀጣ
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የመኪና ሹፌር የሆነው ታምሩ ፍቅሩ የተባለ ተከሳሽ በታርጋ ቁጥር ኮድ 4 ኢት 15731 መኪና 12 ማዳበሪያ አደገኛ ዕፅ ሲያዘዋውር ተይዞ ጥፋተኛ መባሉን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ተከሳሹ በሸገር ከተማ ልዩ ቦታው በተለምዶ ዓለምገና ተብሎ በሚጠራው የመኖሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ 12 ማዳበሪያ 280 ሺህ 50 ግራም የሚመዝን ካናቢስ የተባለ አደገኛ ዕፅ በተሸከርካሪ ውስጥ ይዞ መገኘቱ ተጠቁሟል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎት አደገኛ ዕጾችን በማዘዋወር ወንጀል ተከሳሹን ያርማል በማለት በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ40 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር በዉይይቱ ያልተሳተፍነዉ “የለበጣ እና ከፎቶ ባለፈ ምንም ቁም ነገር እንደማያመጣ ሰለተረዳን ነዉ” ሲሉ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናገሩ
የአስራ አንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት (ሲኦፒ) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ለመወያየት የቀረበለትን ጥሪ ውድቅ ያደረገው መንግሥት በአገሪቱ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የመነጋገር ፍላጎት ስለሌለው መሆኑን ዳጉ ጆርናል መዘገቡ አይዘነጋም።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ከተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ሰኞ መጋቢት 23/2016 ዓ.ም. ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ የጥምረቱ አባላት ግን ሳይሳተፉም ቀርተዋል።
የጥምረቱ አባላት በውይይቱ ላለመገኘት የወሰኑት “መንግሥት አሳሳቢ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገር ስለማይፈልግ” መሆኑን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር መረራ እንዳሉት ውይይቱ “ዝም ብሎ የለበጣ እና ከፎቶ ባለፈ ምንም ቁም ነገር እንደማያመጣ ሰለተረዳን እና ተቃዋሚዎችን አናገርኩ የሚል የይምሰል በመሆኑ” ላለመሳተፋቸው ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ባለፉት ስድስት ዓመታት በአገር ውስጥ እንዲሁም ኔዘርላንድ እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በውጭ አገራት ከእሳቸውም እንዲሁም ከተወካዮቻቸው ጋር ድርድር ቢደረግም ፍሬ አላፈራም ብለዋል ፕሮፌሰሩ።
ከገዢው ፓርቲ ጋር በተደረጉ በርካታ ንግግሮችም የተረዱት መንግሥት “መሠረታዊ እና አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መደራደርም ሆነ መነጋገር አይፈልግም” ሲሉም ፕሮፌሰር መረራ አጽንኦት ይሰጣሉ።
እሳቸው መሠረታዊ ብለው ከሚያነሷቸው ጉዳዮች አንዱ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎችን ጨምሮ በአገሪቱ ለበርካታ ሰዎች እልቂት የእየሆኑ ያሉትን ግጭቶች እና ጦርነቶችን ነው። እነዚህ ጦርነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዴት ይቋጭ? በሚለው ጉዳይ ላይ “መንግሥት መነጋገርም ሆነ ወደ መደራደር አይሄድም” ይላሉ።
በአገሪቱ ውስጥ የሰፈነው “የመገደደል ፖለቲካን ማቆም” ዋነኛ እና መሠረታዊ ጉዳይም እንደሆነም ነው የሚገልጹት።
ሌላኛው ፖለቲከኛው የሚጠቅሱት ጉዳይ አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገው ሽግግር መክሸፉን በመጥቀስ፤ ይህንን የአገሪቱ የዲሞክራሲ የመቀልበስ ሂደት ላይም ገዢው ፓርቲ መወያየት አይፈልግም ይላሉ።
“መነጋገር ደግሞ ውል እና ማሰሪያ ያለው ነገር ይዞ መሠረታዊ ነገሮችን አንስተን ሰጥቶ በመቀበል ፖለቲካ ችግሮችን መፍታት ካልቻልን ንግግሩ ብዙም ትርፍ ስለሌለው ሕዝቡንም ላለማሳሳት ያደረግነው ነው” ብለዋል።
አገሪቷን እየናጧት ያሉ ግጭቶችንም ሆነ ሌሎች መሠረታዊ ያሏቸውን ጉዳዮች ፊት ለፊት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በማንሳት መነጋገር አይቻልም ነበር ወይ? በሚል ቢቢሲ ፕሮፌሰር መረራን ጠይቋቸዋል።
እሳቸውም ከዚህ በፊት የተደረጉ በርካታ ንግግሮች ፋይዳ እንዳልነበራቸው እና ወደየትም ያልተራመዱ መሆናቸውን በመጥቀስ ምላሽ ሰጥተዋል።
“ጦርነቱን ማስቆም አልተቻለም። መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ካልተወያየን ከፎቶ ባለፈ ምንም ቁም ነገር ስለማያመጣ መሳተፍን አልመረጥንም እንጂ መነጋገርንም ሆነ መደራደርን ጠልተን አይደለም” ሲሉም መልሰዋል።
አክለውም “በእነዚህ ንግግሮች የመጣ ለውጥ፣ የምናስተካክለው ነገር ወይም የምንፈይደው ነገር ስለሌለ ነው። ሕዝቡን በማይሆን መንገድ እየተነጋገርን ነው፤ በውይይይ እየተፈታ ነው የሚል አጉል ተስፋ ላለመስጠት እኛ የመሰለንንን እርምጃ ወስደናል” ብለዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረውን ውይይት ግብዣ ላለመቀበል የመወሰናቸው እርምጃ ዋጋ የሚያስከፍላችሁ አይመስላችሁም ወይ በሚልም ቢቢሲ የጠየቃቸው መረራ “ከዚህ በላይ ዋጋ ከፍለናል” ብለዋል።
ኢትዮጵያ ባለፈው ባደረገችው ምርጫ የእሳቸው ፓርቲ እና ኦነግ “ተገፍተው” ከምርጫው እንደወጡ በመጥቀስ የከፈሉት ዋጋ መሆኑን አንስተዋል።
ኦፌኮ ብቻ ሳይሆን በምርጫው ተሳታፊ የነበረው አብን አንዳንድ አመራሮች ለእስር መዳረጋቸውንም ያነሱት ፕሮፌሰር መረራ “ሌሎቹም አልተጠቀሙም” ይላሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉት የአንድ ቀን ውይይት ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ላይ አስተያየቶችን እና ትችቶችን ለማሰባሰብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
መንግሥት እያከናወናቸው ያሉ ልማቶችን በተመለከተ ለተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ገለጻ መደረጉም ተጠቅሷል።
መረራ በበኩላቸው በእነዚህ ልማቶች ላይ ጥያቄ በማንሳትም “የሚለማው ሕዝብ ነው መሬት አይደለም። ይሄንን ገዢው ፓርቲ እንዲረዳ ካልፈለገ? ምን ማድረግ ይቻላል?” ሲሉም ይጠይቃሉ።
ሁለቱ ሰፊ የኢትዮጵያ ክልሎች የድሮኖችን ጥቃት ጨምሮ ሰፊ እልቂት እና ጦርነት እያስተናገዱ እንደሆነም የሚያነሱት መረራ፤ እነዚህን እልቂቶች “ወደ ጎን ትቶ ይሄ ህንጻ ተሠራ፣ መንገድ ተሠራ በማለት ያለውን የሕዝብ ትግል ዝቅ ማድረግ ተገቢ አይደለም” ብለዋል።
አክለውም “በግልጽ ለመንግሥት፣ ለገዢው ፓርቲም ሆነ ለሕዝቡ እያልን ያለው እየተካሄደ ያለው ጨዋታ የትም አያደርስም። ኳሱ ያለው በገዢው ፓርቲ ነው እኛ ጋር አይደለም” ብለዋል።
በዚህ ውይይት ላይ ለፖሊሲ ግብዓት አስፈላጊ የሆኑ እርማቶች እና ማስተካከያዎች ተለይተው ወደፊት ለመቀጠል በሚያስፈልጉ የትብብር ዓይነቶች ላይ ምክክር መካሄዱንም የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
ከሁለት ዓመታት ገደማ በፊት የተመሠረተው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦጋዴን የነጻነት ግንባር፣ ህብር ኢትዮጵያ፣ አረና ትግራይ ፓርቲ፣ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የአፋር ሕዝቦች ፓርቲን የያዘ ሲሆን ከዚህ ቀደምም አንዳንድ የመንግሥት ውሳኔዎችን በመቃወም ይታወቃል።
በአማራ ክልል እንዲሁም በሌላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንደ አስፈላጊነቱ ተግባራዊ ይሆናል የተባለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘም ተቃውሞም መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
ሴኔጋል በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ቀዳማዊ እመቤቶች ይኖራታል።
አዲሱ የሀገሪቱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲማዩ ፋየ ዛሬ ቃለመሃላ ፈጽመው ወደ ቤተመንግስት የሚገቡት ከሁለት ሚስቶቻቸው ጋር ነው።
የ44 አመቱ ፋየ ከ15 አመት በፊት ካገቧት ማሪያ ሆን አራት ልጆችን ወልደዋል።
አብሳ ፋየንም ባለፈው አመት ማግባታቸውን የሚገልጹት ተመራጩ ፕሬዝዳንት በሁለቱም ሚስቶቻቸው ደስተኛ መሆናቸውን በምርጫ ቅስቀሳቸው ሲገልጹ ተደምጠዋል።
በየምርጫ ቅስቀሳ መድረኩ ከሁለት ሚስቶቻቸው ጋር መታየታቸውም የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት መሳቡና የሴኔጋላውያን መነጋገሪያ ርዕስ እንደነበር ፍራንስ 24 አስታውሷል።
“ከውብ ሚስቶቼ ቆንጆ ልጆች አግኝቻለሁ፤ በጣም ቆንጆዎች ናቸው፤ ሁሌም ከጎኔ ስለሆኑም ፈጣሪዬን በጣም አመሰግነዋለሁ” ሲሉ ነው ፋየ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገሩት።
የአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ንግግር እና በየአደባባዩ ከሚስቶቻቸው ጋር መታየታቸው ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ነውር አለመሆኑን ለማመላከት ያለመ ነው ይላሉ ጂቢ ዲያሄት የተባሉ የማህበረሰብ አጥኝ።
በሴኔጋል ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በተለይ በገጠሪቱ ክፍል የተለመደና ቤተሰብን ለማብዛት አንደኛው መንገድ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።
የሀገሪቱ ስታስቱክስ ተቋም በ2013 ያወጣው ጥናትም ከጠቅላላው ጋብቻ 32 ነጥብ 5 በመቶው በዚሁ መንገድ የተከናወነ መሆኑን ያሳያል። በርካታ ሚስቶችን የማግባቱ ልማድ በሴኔጋላውያን ወንዶች ቢደገፍም ሴቶች ግን ባል ሁሉንም ሚስቶቹን እኩል ማየት ስለማይችል መድልኦ መከሰቱ አይቀርም፤ ጋብቻው ሊታገድ ይገባል ሲሉ ይደመጣል ብሏል የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ በ2022 ባወጣው ሪፖርት።
አል አይን
ፑንትላንድ የሶማሊያን ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ተቃወመች!
የሶማሊያ ፓርላማ ‘አንድ ሰው አንድ ድምጽ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ እንደሚከተል ማስታወቁን ተከትሎ፣ ራስ ገዟ ፑንትላንድ ለፌዴራል ተቋማት እውቅና እንደማትሰጥ አስታውቃለች።
ሞቃዲሹ ከሚገኘው ማዕከላዊ መንግስት ጋራ ያላትን ተቃውሞዎች በተደጋጋሚ በመግለጫ ስታስታውቅ የከረመችው ፑንትላንድ፣ ዛሬ እሁድ ባወጣችው መግለጫ፣ በትናንትናው ዕለት በርካታ ሕገ መንግስታዊ ማሻሻዮችን ያደረገው የሶማሊያ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔዎችም ውድቅ አድርጋለች።
“በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም” ብሏል መግለጫው።
ሕዝበ ውሳኔ የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራትም አስታውቃለች፡፡ውስብስብ የሆነውንና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ሶማሊያ ከአምሣ ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡
ትናንት የተሰበሰበው የሶማሊያ ፓርላማ ‘አንድ ሰው አንድ ድምጽ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ተከትሎ፣ በፑንትላን የሚገኙ ባለሥልጣናት ቁጣቸውን ገልፀዋል።በተፈጥሮ ሃብቶች እና በቦሳሶ ወደቧ በመተማመን፣ ፑንትላንድ በእ.አ.አ 1998 ራስ ገዝ መሆኗን አውጃለች፡፡
ከመጋቢት 30 ጀምሮ ለሚኒባሶች የሚደረገው የነዳጅ ድጎማ ሙሉ በሙሉ እንደሚቋረጥ ተገለጸ
ከዚህ ቀደም የነዳጅ ድጎማ ሲደረግላቸው የነበሩ የሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ከመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ድጎማው እንደሚቋረጥ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።
መንግሥት ለረጅም ጊዜ ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ መጠን የለው ድጎማን ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጽ ይህንን ለማስቀረት በሂደት የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ ባወጣው ዕቅድ መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
ቀስ በቀስም መንግስት በነዳጅ ምርት ላይ የሚያደርገዉ ድጎማ የማቋረጥ እቅድ እንዳለዉ ይታወቃል፡፡
በሚኒባስ ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረገዉ መንግስት ድጎማን የማስቀረቱ አንዱ አቅድ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ሆኖም የድጎማ ስርአቱን የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች ማህበረሰቡን በሚገባ እያገለገሉ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሰልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሄኖስ ወርቁ ከዚህ ቀደም 170ሺ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርአት ውጪ መደረጋቸዉን ተናግረዋል።
ተሽከርካሪዎቹ ነዳጅ ድጎማን በስርዓት ባለመጠቀማቸው ከድጎማው ውጪ እንዲደረጉ ምክንያት መሆኑ አመላክተዋል።
ከፊታችን መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጅምሮ በነዳጅ ድጎማው ስርአት የሀገር አቋራጭና የከተማ አውቶቢስ ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀው እነዚህም ተሽከርካሪዎችን እስከሚቀጥሉት 5 አመታት ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡
በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በኩል ከመጋቢት 30 2016 ዓ.ም በኃላ ድጎማዉ ከሚኒባስ ተሸከርካሪዎች ላይ እንደሚያነሳ የተወሰነ ቢሆንም ተግባራዊ የሚደረገዉ ግን የነዳጅ አገልግሎት ስርጭትን በተመለከተ ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክ፤ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከሌሎች ባላድርሻ አካላት የተዉጣጣዉ ኮሚቴ ዉሳኔዉን ሲያሳልፍ መሆኑን አመላክተዋል፡፡መንግስት በ5 አመታት ዉስጥ በነዳጅ ላይ የሚያደርገዉን ድጎማ ሙሉ በሙሉ እንደሚያቋርጥ ይታወቃል፡፡
መረጃው የመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ነው
ዛሬ በማን ሲቲ እና በአርሰናል መካከል በሚካሄደው ወሳኝ የፕሪምየር ሊግ ፍልሚያ ማን ያሸንፋል? ወይስ እኩል ይወጣሉ?
#PremierLeague #ManCity #Arsenal
አካል ጉዳተኞችን የተመለከተ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊወጣ መሆኑ ተሰማ
አካል ጉዳተኞች መብታቸው እንዲጠበቅ ለመብታቸው መጠበቅም ምላሽ የሚሰጥ ተፈጻሚነቱን የሚከታተል ባለቤት ያለው አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊወጣ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
ኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞችን መብት ምላሽ የሚሰጥ ጥቅል አዋጅ የላትም የተባለ ሲሆን ያን ለማድረግ የአካል ጉዳተኞች ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ወደ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መላኩ ተገልጿል።
ይህ የአካል ጉዳተኞች አዋጅ ፥ ያሉትን ህጎች ተከታትሎ የሚያስፈፅም፣ ካልተፈፀሙም ተጠያቂ የሚሆን ተቋም እንዲኖር ለማስቻል ፣ የህግ ክፍቶችም እንዲስተካከሉ ያደርጋል ተብሏል። አዋጁ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተልኮ አስፈላጊ አስተያየት ከተሰጡበት በኋላ ወደ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መላኩ ነው የተገለፀው።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው በማለት ትናንት ከቻይናው ሲጂቲኤን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
ያለፈው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት አልነበረም ያሉት ጌታቸው ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና የትግራይ ሕዝብ ድጋሚ ጦርነት እንዳያገረሽ የተቻላቸውን ጥረት ኹሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
ጌታቸው ይህን ያሉት ፣ በአላማጣ አቅራቢያ በትግራይ ኃይሎች እና ባካባቢው ሚሊሻዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በተደረገ ማግስት ነው መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል።
አቶ ጌታቸዉ ይህንን ይበሉ እንጂ አብን፣ ሕወሃት ለአዲስ ዙር ጦርነት ቅስቀሳ እያደረገ ነው ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት የሕወሃት ተዋጊዎች ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ሳይፈቱና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጸጥታ ለማስከበር ሳይሠማራ ሕወሃት ለሌላ ዙር ጦርነት ፕሮፓጋንዳ በመለፈፍ ተጠምዷል ብሏል።
የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥታት የሕወሃትን የጠባጫሪነት ቅስቀሳ በትኩረት እንዲከታተሉና በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት "በንግግር" እና "ድርድር" እንዲፈታም አብን ጠይቋል። የአማራ ሕዝብ ሕወሃት ሊያደርስበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል በአንድነት እንዲቆም የጠየቀው ፓርቲው፣ የትግራይ ሕዝብም ራሱን ከሕወሃት ቀንበር እንዲያላቅቅ ጥሪ አድርጓል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክርትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል
በሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ዛሬ ከቀኑ 09 ሰዓት ከ46 ደቂቃ ጀምሮ ከባህር ዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ሲል የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
ኢትዮትዩብ ከተቋሙ ባገኘችው መረጃ የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ መጀመሩን ገልጿል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ
በቅርብ ጊዜያት በርካታ ቅሬታዎችን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉምሩክ የስራ ክፍል፤ ሰራተኞች በአዲስ መልክ እንደሚደራጁ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።
ከብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በ2016 ስምንት ወራት ውስጥ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
ኮሚሽኑ በሰራተኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ "ረጅም ጊዜ" የወሰደ ጥናት መካሄዱ ታውቋል።
በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል።
በመጋቢት መጀመሪያ "በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ አሉባልታዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከእውነት የራቁ ናቸው" በማለት የብሔራዊ የአየር ትራንስፖርት ፋሲሊቲ ኮሚቴ መግለጫ ቢሰጥም አየር መንገዱ በበኩሉ በቅሬታዎቹ ላይ ምርመራ መጀመሩን እንዳስታወቀ ከዚህ ቀደም የመረጃ ምንጫችን መዘገቡ ይታወሳል ።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
የአማራ ክልል ይፋዊ ምላሽ ሰጠ
* " የዛቻና የጠብ አጫሪነት የሆነውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ ተመልክተነዋል " - የአማራ ክልል
የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ሀሙስ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል " ብሏል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ስርዓትን በማጣቀስ " የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል " ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳችና የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ ነው ሲል ገልጿል።
በትናንትናው እለት ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደልና በማሰቃየት ላይ ይገኛል ሲል የአማራ ክልል ከሷል።
(ሙሉው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሰጠ የሀዘን መግለጫ !
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በባህር ዳር ከተማ በመጫወት ላይ ይገኝ የነበረው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወቱ ተሰምቷል።
አለልኝ አዘነ በተደጋጋሚ ለብሔራዊ ቡድናችን ተመርጦ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ እና በአሁኑ ወቅት በእግር ኳሳችን ላይ ምርጥ አቋማቸውን እያሳዩ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀስ ተጫዋች ነበር።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአለልኝ አዘነ አስደንጋጭ እና ልብ ሰባሪ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ ፣ ለወዳጅ ዘመድ ፣ ለሙያ አጋሮቹ እና መላው የእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መጽሃፍ ቅዱስ መሸጥ ጀመሩ።
ትራምፕ በራሳቸው ማህበራዊ ትስስር ገጽ (ትሩዝ ሶሻል) ደጋፊዎቻቸው “ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” የሚል ስያሜ ያለውን መጽሃፍ ቅዱስ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።
“ወደ ፋሲካ በዓል እየተቃረብን ነው፤ ‘ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ’ መጽሃፍ ቅዱስን በመግዛት አሜሪካ ዳግም እንድትጸልይ እናድርጋት” ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።
ሁሉም አሜሪካውያን በቤታቸው መጽሃፍ ቅዱስ ሊኖራቸው እንደሚገባም ነው ያነሱት።
ትራምፕ ዝርዝር ውስጥ መግባት ባልፈልግም መጽሃፍ ቅዱስ በህይወቴ ውስጥ ልዩ ቦታ አለው ብለዋል።
“ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” መጽሃፍ ቅዱስ GodBlessTheUSABible.com በተሰኘ ድረገጽ በ59.9 ዶላር ለገበያ ቀርቧል ተብሏል።
ድረገጹ መጽሃፍ ቅዱስ በትራምፕ መተዋወቁ “ምንም አይነት ፖለቲካዊም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ” አላማ የለውም ማለቱንም አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት መጽሃፍ ቅዱሱን የሚያሳትመው ኩባንያ ባለቤት አለመሆናቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ዝናቸውን ተጠቅመው ለሰሩት የማስተዋወቅ ስራ ሊያገኙት ስለሚችሉት ገቢ የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድንም ሆነ መጽሃፍ ቅዱስ የሚሸጠው ኩባንያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ዋይትሃውስ ዳግም ለመግባት ከባይደን ጋር የሚፎካከሩት ትራምፕ በቀረቡባቸው አራት ክሶች የገጠማቸውን የገንዘብ እጥረት ለመሙላት ባለፈው ወር በስማቸው የተሰየሙ ስኒከር ጫማዎችን ማስተዋወቃቸው ይታወሳል።
አዲሱ የመጽሃፍ ቅዱስ ግዙ ቅስቀሳም በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ትራምፕ በቀጣዩ ምርጫ ክርስቲያን ደጋፊዎቻቸውን ለማብዛት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተገልጿል።