ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የችሎት ውሎ ድምጽ ተቀድቶ በመሠራጨቱ ምክንያት በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የተከሰሱ ግለሰቦችን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታ እንደማይሰማ ፍርድ ቤቱ አስታወቀ።

ችሎቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተመለከተ አቤቱታ በጽሁፍ እንዲቀርብ ብይን መስጠቱን ከተከሳሾች ጠበቃ አንዱ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ብይኑን የሰጠው ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 1/2016 ዓ.ም. የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሕገ መንግሥት እና ሽብር ወንጀል ችሎት ነው።

ችሎቱ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙት ተከሳሾች ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ የሚያቀርቡትን የቃል አቤቱታ ለመስማት ነበር።

ባለፈው ሳምንት አርብ በነበረው የችሎት ውሎ ከ14ቱ ተከሳሾች መካከል አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዮሐንስ አቤቱታቸውን አቅርበው ነበር። ሁለተኛው ተከሳሽ አቶ ክርስቲያን ታደለ ደግሞ በከፊል አቤቱታቸውን ማቅረባቸውን ጠበቃቸው አስታውሰዋል።

አቶ ክርስቲያንን ጨምሮ ቀሪዎቹ 13 ተከሳሾች በዛሬው የችሎት ውሎ አቤቱታቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።
ሆኖም ግን ፍርድ ቤቱ የዛሬውን የችሎት ውሎ የጀመረው የዐቃቤ ሕግን አቤቱታዎች በመቀበል መሆኑን አቶ ሰለሞን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ዐቃቤ ሕግ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጸመ የተባለው አካል በሌለበት የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታ መቀበል ተገቢ አይደለም ስለዚህ አቤቱታው መቅረብ ያለበት በጽሁፍ ነው” የሚል ጥያቄ ማንሳቱን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ቀጣይ ቆይታ ላይም አስተያየት ሰጥቷል።
ዐቃቤ ሕግ “እኛ ሥራ የሚበዛብን ስለሆነ ቀጣይ ምርመራዎችም ስላሉብን የፌደራል [ፖሊስ] የወንጀል ምርመራ የጊዜያዊ ማቆያውን ስለምንፈልገው ወደ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩ” የሚል አቤቴታ ማቀረቡን አቶ ሰለሞን ገልጸዋል።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ዛሬ ችሎቱ የተቀጠረው፤ “የቀሪ ተከሳሾችን የሰብዓዊ መብት ጥሰት [አቤቱታ] ለመስማት” መሆኑን በማንሳት የደንበኞቻቸው አቤቱታ አንዲሰማ ጠይቀዋል።

ሆኖም ችሎቱ “በባለፈው ቀጠሮ የሰጠው ትዕዛዝ የቀሪ ተከሳሾችን አቤቱታ ለመስማት ቢሆንም ይኼን የሚያቋርጥ ነገር ተከስቷል” በሚል አቤቱታውን ላለመስማት አቋም ስለመያዙ አቶ ሰለሞን አስረድተዋል።

ችሎቱ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታውን የማንሰማበት ምክንያት ከዚህ በፊት የነበረው የችሎት ውሎ ተቀርጾ በመውጣቱ፣ ይህም የፍርድ ቤቱን ገለልተኝነት የሚጎዳ ሆኖ ስላገኘነው ይህንን ላለማስኬድ ችሎቱ አቋም ወስዷል” ማለቱን አቶ ሰለሞን አብራርተዋል።

ይህን ተከትሎም የሰብዓዊ መብት አያያዝን የተመለከተ አቤቱታ በጽሁፍ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ተከሳሾቹ የተከሰሱበት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ፍርድ ቤቶች ተከሳሾች ለሚያቀርቧቸው የመብት ጥያቄ ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው ያትታል።

የዳኝነት ሥልጣንን የሚያትተው አዋጁ ክፍል፤ “ፍርድ ቤቶች በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘው ሰው ወይም የተከሰሰው ሰው ከአያያዙ ጋር በተያያዘ በሚያነሳው የመብት ጥያቄ ቅድሚያ በመስጠት መመርመር እና ተገቢውን ማስተካከያ እንዲደረግ አግባብነት ላለው አካል ትዕዛዝ መስጠት አለባቸው” ሲል ይደነግጋል።

ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም “የድምጽ ቅጂው ከፍርድ ቤት ነው የወጣው አይደለም የሚለውን ለማጣራት ባለፈው ቀጠሮ የተከሳሾችን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን አቤቱታ የቀዳው ማሽን በፌደራል ፖሊስ ምርመራ አድርጎ ውጤቱን ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ” ሌላም ብይን ሰጥቷል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ ከዛሬ ጀምሮ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ በፍርድ ቤቱ ታዝዟል።
የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ሦስት ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾችን በተመለከተም ለ36ቱ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግ 40ኛ እና 51ኛ ተከሳሾችን ደግሞ ፖሊስ እንዲያቀርብ አዝዟል።


መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በሰሜናዊ ጅቡቲ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ የ38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አለፈ

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አልፏል።

በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ ጎዶሪያ በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ 60 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ትጓዝ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ 38 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን በጅቡቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮንም አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ የዒድ አልፈጥር ሰላት እስከሚጠናቀቅ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በከተማዋ የዒድ አልፈጥር ሰላት ተሰግዶ እስከሚጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም የይለፍ ፈቃድ ከሌላቸው ተሽከርካሪዎች በስተቀር ከሌሊት 10 ሰዓት ጀምሮ የዒድ ሰላት እስከሚጠናቀቅ

📍 ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ
📍 ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው  አጎና ሲኒማ ላይ
📍 ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
📍 ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ፡፡
📍 ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ
📍 ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ  22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ
📍 ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል  አጠገብ
📍 ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ  አቧሬ ሴቶች አደባባይ  ላይ
📍 ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
📍 ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ
📍 ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ
📍 ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎባ ቁጠባ አጠገብ
📍 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ
📍 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር  ወደ ብሔራዊ ቴአትር  ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ
📍 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ  የሚዘጉ ይሆናል።

በተያያዘ መረጃ የጸጥታና ደሕንነት የጋራ ግብረ ኃይል በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በመላው አገሪቱ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የአፍሪካ ኅብረት ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ የዘር ማጥፋትና የጅምላ ጭፍጨፋን ለመከላከል ልዩ መልዕክተኛ ሾመ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሌሎች ጅምላ ጭፍጨፋዎችን ለመከላከል ሴኔጋላዊውን አዳማ ዲዬንግ የመጀመሪያ የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ አድርገው ሾመዋል።

ልዩ መልዕክተኛው የተሾሙት በአፍሪካ አህጉር የጥላቻ እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ለመዋጋት የተያዘውን የህብረቱን አጀንዳ ለማስፈፀም ሲሆን ዲዬንግ በቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን የጅምላ ጭፍጨፋ መከላከል ልዩ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል ተብሏል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር መልቀቅ ማቆሙ ተሰምቷል

ንግድ ባንኩ ብድር ለማግኘት የተለያዩ ሂደቶችን አልፈው ፤ ብድሩ ተፈቅዶላቸው የመልቀቅ ሂደት ላይ ያሉትም እንዲቆም ነው ያዘዘው ። ባንኩ ይህን ትእዛዝ ያስተላለፈው ረቡዕ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ/ም መሆኑንም ሰምተናል ።

ንግድ ባንኩ በጊዜያዊነት ብድር መልቀቅ ከማቆሙ በስተቀር ባስተላለፈው ትእዛዝ ላይ ብድር መልቀቅ ያቆመበትን ምክንያት አልገለጸም። ሆኖም ከብድር መልቀቅ መለስ ያሉት የብደር ጥያቄ እና ሂደቶቹ አለመቆማቸውን ሰምተናል ።

መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ እስከ ዛሬ የሰጠው ብድርም ሆነ የሰበሰበው ቁጠባ ከአንድ ትሪሊየን ብር ያለፈ ብቸኛ ባንክ መሆኑ የሚታወቅ ነው ።

ባንኩ በቅርቡ በተገበረው የሲስተም ማሻሻያ ሳቢያ በተፈጠረ ስህተት 801 ሚሊየን ብር ለምዝበራ ተዳርጎበት እንደነበረ እና ከዚህ ውስጥ አብዛኛውን ገንዘብ ባደረገው ክትትል ማስመለሱን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ በሰጡት መግለጫ ተናግረው ነበር ። ባንኩ ገንዘቡን የማስመለስ አካል ነው ያለውን ባልተገባ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ ተሳትፈዋል ያላቸውን ደንበኞች ፎቶ ሳይቀር ለህዝብ ይፋ አድርጓል ። አሁን በጊዜያዊነት ብድር መልቀቅ ማቆሙ ከዚህ ጋር ይገናኝ አይገናኝ አልታወቀም ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው አመት ብቻ 151 ቢሊየን ብር ብድር የሰጠ ሲሆን ፤ በተመሳሳይ አመት 165 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ቁጠባን ደግሞ ሰብስቦም ነበር ።ሆኖም ይህ በጀት አመት ከገባ ግን የቁጠባ አሰባሰቡ ከእቅዱ ጋር እየሄደ አለመሆኑ ተሰምቷል ። ለአብነትም በዚህ በጀት አመት የመጀመርያ ስድስት ወራት የሰበሰበው ቁጠባ ከእቅዱ አንጻር ከግማሽ በታች መሆኑም ተዘግቧል ። ለዚህ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው ችግር እንደ ምክንያት ተጠቅሷል ። ምናልባትም የአሁኑ የባንኩ በጊዜያዊነት ብድር የማቆም ውሳኔ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከተፈጠረ የገንዘብ እጥረት ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ተዘግቧል።

ዋዜማ
 

Читать полностью…

EthioTube

ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን ነጥብ ማስጣሉን ተከትሎ አርሰናል መሪነቱን ተረክቧል። የዋንጫው ትንቅንቅ በማን አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ይመስላችኋል?

#PremierLeague #ManUnited #Liverpool

Читать полностью…

EthioTube

31 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማላዊ ታግተው ለማስለቀቂያ ከቤተሰቦቻቸው 1ሺ ዶላር መጠየቃቸው ተጠቆመ

የማላዊ ባለስልጣናት በህገወጥ መንገድ ወደ  ሀገሪቱ የገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተው ለማስለቀቂያ በነፍስ ወከፍ 1ሺ ዶላር እየተጠየቀባቸው እንደነበር አረጋግጫለሁ ማለቱን ኒያሳ ታይምስ የተሰኘው የሀገሪቱ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

የሀገሪቱ የደህንነት ባለስልጣን ኬን ዚክሃሌ ንጎማ በሊሎንግዌ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አህመድ ሙሀመድ እና ዲሞራህ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ጥንዶች 31 ኢትዮጵያውያን አግተው ኢትዮጵያ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ለማስለቀቂያ 1ሺ ዶላር እየጠየቁ እንደነበር መረጋገጡን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ወደ ማላዊ ለመግባት 200 ዶላር እንደሚከፍሉ ባለስልጣኑ የገለፁ ሲሆን ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎቹ ጥንዶች ለረዥም ጊዜ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ንግድ ተሰማርተው እንደቆዩ አብራርተዋል። ይህ ድርጊታቸው ከታወቀ በኋላ ከሀገሪቱ እንዲባረሩ ሲደረግ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ስላሉበት ሁኔታ የተጠቀሰ ነገር የለም።

Читать полностью…

EthioTube

በአሶሳ ከተማ በትዳር አጋሩ ላይ ከባድ የመግደል ሙከራ የፈጸመው የፖሊስ አባል በእስራት ተቀጣ ተቀጣ

በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ በትዳር አጋሩ ላይ በድምፅ አልባ መሳሪያ ከባድ የመግደል ሙከራ ወንጀል የፈጸመው የፖሊስ አባል በፅኑ እስራት መቀጣቱ ተነግሯል ።

ተከሳሽ ዋና ሳጅን ማስረሻ ፈንታዬ  በከተማ አስተዳደሩ ወረዳ አንድ  በተለምዶ ጤና ቢሮ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ነዋሪ ሲሆን ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሆን ብሎ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ከባለቤቱ ጋር በነበረው አለመግባባት በመነሳሳት እና ቂም በመያዝ ወንጀሉን መፈፀሙ ተገልጿል ።

በዚህም ተከሳሽ በያዘው ድምፅ አልባ መሳሪያ ጩቤ ጭካኔ እና ነውረኝነት በተሞላበት ሁኔታ የግል ተበዳይን በጀርባዋ ላይ ስድስት ጊዜ ፣ ግንባሯ ላይ አንድ ጊዜ በመውጋት እንዲሁም በሳንባዋ ላይ በስለት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተጠቁሟል ።

ሆኖም መረጃው የደረሰው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተከሳሹን በቁጥጥር ስር አውሎ  የወንጀል ምርመራ በማጣራት መዝገቡን ለዓቃቤ ህግ መላኩን በከተማ አስተዳደሩ የወረዳ አንድ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር በላቸው ፈረደ ከብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ።

የምርመራ መዝገቡ የደረሰው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ዓቃቤ ህግ በሰውና በህክምና ማስረጃ አስደግፎ ተከሳሽ በፈጸመው ከባድ የሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ክስ መስርቶበታል። በዚህ መሠረት የክስ መዝገቡን ሲመለከት የቆየው የወረዳው ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል ።

ፍርድ ቤቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ማሳለፉን ምክትል ኮማንደር በላቸው ፈረደ ጨምረዉ ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
     

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - መጋቢት 26 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 4, 2024
👉ሶማሊያ የኢትዮጵያን አንባሳደር አባረረች
👉ዲጂታል መታወቂያ የሌለው ነጋዴ አዲስ ህግ
👉በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ያልረገው ጦርነት

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/weYzrMg3_6k

Читать полностью…

EthioTube

የአሳማ ኩላሊት የተለገሰው ግለሰብ ከሆስፒታል አገግሞ መውጣቱ ተሰማ

ለመጀመሪያ ጊዜ የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላ የተደረገለት ግለሰብ ከሆስፒታል አገግሞ መውጣቱ ተሰምቷል፡፡

የኩላሊት ህመም በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙዎችን ሕልም ያጨለመና በርካቶችን ለህልፈት የዳረገ እና እየዳረገ የሚገኝ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ኩላሊት ሥራውን በአግባቡ ለመከወን ሲሰንፍ የኩላሊት ህመም ተከስቷል ይባላል፤ ህመሙ በጊዜ ከተደረሰበት በንቅለ ተከላ የሚታከም ቢሆንም ኩላሊት ማግኘት ግን ፈታኝ ጉዳይ ነው፡፡

አሁን ላይ በአሜሪካ ማሳቹሴትስ አጠቃላይ ሆስፒታል የተሰማው አዲስ ሕክምና የብዙዎችን ጭንቀት ወደ እፎይታ የቀየረና ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በሆስፒታሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓሳማን ኩላሊት ለሰው ልጅ በንቅለ ተካላ በመተካት ውጤታማ ሕክምና ማድረግ መቻሉ ተሰምቷል፡፡
የ62 ዓመቱ የዕድሜ ባለጸጋ ሪቻርድ ስሌይማን የኩላሊት ህመም እንዳለባቸውና በአፋጣኝ የኩላሊት ንቅለተከላ ማድረግ እንዳለባቸው ተነግሯቸው ዲያሊሲስ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ሆኖም ግለሰቡ የዓሳማ አካል ከአካላቸው ተስማምቶ ወደጤናቸው እንደሚመለሱ እርግጠኛ መሆን አልቻሉም ነበር ፤ይሁን እንጂ ሕክምናው በባለሙያዎች ታግዝ እውን ሆኗል፡፡
ከአሁን በፊት ተሞክሮ ያልተሳካው የዓሳማ ኩላሊት ንቅለ-ተከላ ጊዜው ደርሶ በዘርፉ ሊቆች ታግዞ የግለሰቡን ሕይዎት ማትረፉም በብዙዎች ዘንድ አግራሞትን ጭሯል፡፡

የንቅለ-ተከላ ሂደቱ አራት ሰዓታት እንደፈጀ የተናገሩት ሃኪሞች ፥ በአሁኑ ወቅት የዓሳማው ኩላሊት ከግለሰቡ ተዋህዶ በአግባቡ እየሰራ መሆኑን በማረጋገጥ ከሆስፒታል እንዲወጣ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ስሌይማን በበኩላቸው ፥ ህክምናው ተሳክቶ ወደቤቴ መሄዴ የሕይወቴ ትልቁ ደስታ ነው ማለታቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
ታካሚውከአሁን በፊት ያደረጉት ንቅለተከላ ከሰው በተለገሳቸው ኩላሊት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ፥ ሆኖም ትንሽ ቆይቶ መስራት ማቆሙ ተነግሯል፡፡

ይሁን እንጂ ሕክምናው ሃኪሞች ባነሱት የዓሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ሙከራ መሳካቱ ነው የተነገረው፡፡

የዓሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምነው “እኔን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን በሕይወት ለመትረፍ ንቅለ ተከላ ለሚያስፈልጋቸው በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ተስፋ የሚሰጥ መንገድ ሆኖ አይቸዋለሁ” ሲሉም ገልጸዋል።

ምንጭ፦ FBC

Читать полностью…

EthioTube

በቀጣይ ዓመት ብሔራዊ መታወቂያ የሌላቸው ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት አያገኙም ተባለ

በሚቀጥለው ዓመት የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት ለማግኘት ብሔራዊ መታወቂያ ያስፈልጋል በማለት በቀጣይ ዓመት ብሔራዊ መታወቂያ የሌላቸው ነጋዴዎች አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ደንበኞች በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው በኦንላይን አገልግሎት እያገኙ ነው ሲባል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ከሌሎች ተቋማት ጋር የሚያገናኘው በመሆኑ ከተቋማቱ ጋር ሲስተም የማናበብ ስራ በፋይዳ መለያ የሚሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።

ስለዚህ የንግዱ ማህበረሰብ ከ2017 በፊት ብሔራዊ መታወቂያ በማውጣት ራሱን ለነገሮች ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የላይሰንሲንግ እና ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጅራታ ነመራ ተናግረዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በመዲናዋ በመፍረስ ላይ ያሉ ቤቶች "በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት ያላሟሉ" ናቸው - የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ከአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በመዲናዋ በኮሪደር ልማት ስራ ምክንያት የሚፈርሱ ቤቶች "በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት የሚያሟሉ ባለመሆናቸው" ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በመዲናዋ የቅርስ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁሉ የተመዘገቡ መኖራቸውን አስታውሰው፤ በተዘጋጀው መስፈርት መሰረት በአዲስ መልክ የቅርስ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በፊት የተመዘገቡ በቅርስነት የሚቀጥሉ ሲኖሩ በመመሪያው መሰረት መስፈርቱን የማያሟሉ ደግሞ የማይቀጥሉ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከቀናት በፊት ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ የመልሶ ግንባታና ኮሪደር ልማት የቅርስ መስፈርት የማያሟሉ ቤቶችንና አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት የቀደመ ስያሜና አገልግሎታቸው እንዲቀጥል እንደሚደረግ ማስታወቁን ፕሬስ ድርጅት መዘገቡ ይታወሳል።

ቤቶቹን በቅርስነት ለመመዝገብ ያላቸው ታሪክ፣ አሁን ያሉበት ውጫዊ እና ውስጣዊ ገፅታ፣ እድሜያቸው፣ አርክቴክቸርን ጨምሮ በርካታ መስፈርቶች መቀመጣቸውን ገልጸዋል። በተቀመጡት መመዘኛዎች መሰረት ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጣ በቅርስነት እንደሚመዘገብ እና በአንጻሩ ከ50 በታች የሆነ ቤት ቅርስ ተብሎ ሊመዘገብ እንደማይችል ጠቁመዋል።

ለየሀገር ከፍተኛ ትርጉም ያላቸውን ቅርሶችን መጠበቅና መንከባከብ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር በኮሪደር ልማቱ የሚፈርሱ ቤቶች ላይ የክትትልና የቁጥጥር ስራ እየሰራ ይገኛል ማለታቸውን ተገልጿል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ረቡዕ የኢት ዜና - መጋቢት 25 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 3, 2024

👉ሕወሓት ዕውቅናው እንዲመለስለት ያቀረበውን ጥያቄ👉በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ
👉ከ8ሺህ በላይ የሆኑ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ተባረዋል

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/ZkqKQfdsqx8

Читать полностью…

EthioTube

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን የሚወስን አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱ ተነገረ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በከተማዋ የሞተር ሳይክል ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላትን በአሰራርና በተደራጀ ሁኔታ ለመምራት የሞተር ሳይክል እና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ለመወሰን አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ማድረጉን ተናግሯል፡፡

በመመሪያውም ከአሽከርካሪው ውጪ ሌላ ሰው መጫን እንደማይቻልና ለእቃ ማመላለሻ ብቻ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ፣ ከኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ውጪ አዲስ የአገልግሎት ፍቃድ እንደማይሰጥ፣ ከ250 አባላት ጀምሮ በማህበር በመደራጀት ፍቃድ እንደሚሰጥ ተጠቅሷል፡፡

አሁን በስራ ላይ የሚገኙ የሞተር ሳይክሎች ቢሮው በሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ መነሻነት ወደ ኤሌክትሪክ የሞተር ሳይክል መለወጥ እንደሚገባ ቢሮው አሳስቧል፡፡

ቢሮው ባወጣው መመሪያ መሰረት አገልግሎቱን የማይሰጡ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች በመመሪያው መሰረት እንደ ጥፋቱ እርከን ቅጣት እንደሚጣልባቸውም አሳስቧል፡፡

አዲሱ መመሪያ ወደ ተግባር እንዲገባ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች እንዲሁም የሚመለከታችው ሁሉ አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ ሲል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጠይቋል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የኒሻን ሽልማት ተረከበች

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የወርቅ ጨረር ያለው የኒሻን ሽልማት ተረከበች።

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በስፖርት ዲፕሎማሲ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ቀደም ሲል ከጃፓን መንግስት የክብር ኒሻን ሽልማት እንደተበረከተላት ይታወሳል።

በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል ካበረከተችው የስፖርት ዲፕሎማሲ በተጨማሪ ለአትሌቲክስ ዕድገት እና ለሀገር ሰላም ላበረከተችው አስተዋፅኦም ነው ሽልማቱ የተበረከተላት።

ሽልማቱን ከኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ መረከቧን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ዛሬ ወደ ሞቃዲሾ ሊደረጉ የነበሩ በረራዎች ተሰረዙ

የአውሮፕላን በረራዎች የተቋረጡት፣ በሱማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በሞቃዲሾ ሰሞኑን አልሸባብ የሽብር ጥቃቶችን ሊፈጽም እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ማውጣቱን ተከትሎ ነው።

ኢምባሲው አገኘኹት ባለው መረጃ፣ በሞቃዲሾው ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ በወደቦች፣ በፍተሻ ጣቢያዎች፣ በመንግሥት መስሪያ ቤት፣ ሆቴሎች እና የገበያ መደብሮች ላይ የሽብር ጥቃቶች ሊፈጸሙ ይችላሉ በማለት ትናንት ባሠራጨው መረጃ አስጠንቅቋል።

ዛሬ ወደ ሞቃዲሾ ሊያደርጉት የነበረውን በረራቸውን ካቋረጡት አየር መንገዶች መካከል፣ የቱርክ እና ኳታር አየር መንገዶች ይገኙበታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አልሸባብ ትናንት ሌሊት በፕሬዝዳንታዊ ቤተመንግሥቱ ላይ የሞርታር ጥቃቶችን ፈጽሟል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ አዲስ ይዞት የመጣው የሊትየም ኤሌክትሪክ ሞተር ምን ይመስላል ?

ትናንት በሳይንስ ሙዚየም ያስተዋወቀው ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ ያቀረባቸውን አዳዲስ ሞዴል ሞተሮችን ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ ። 👇
https://youtu.be/30-Qwjy64gc

Читать полностью…

EthioTube

የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ነው።

ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ አልታየችም ፤ በመሆኑም የዒድ አልፊጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።

ነገ ማክሰኞ የረመዷን የመጨረሻው ሰላሳኛ ቀን ይሆናል።

Читать полностью…

EthioTube

በስልጤ ዞን የ10 ዓመት ታዳጊ ልጁን በቢላዋ  አርዶ የተሰወረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የ10 ዓመት  ታዳጊ ልጁን በቢላዋ አርዶ ተሰዉሮ የነበረዉ  ተጠርጣሪ ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር መዋሉን የስልጤ ዞን ፖሊስ አስታውቋል።

በዞኑ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረደ በሙጎ ከተማ ልዩ ስሙ ሀሊቾ ተብሎ በሚጠራዉ መንደር ነዋሪ የሆነዉ ተጠርጣሪ መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 4:30 ለጊዜው ምክንያቱ በግልፅ ባልታወቀ አኳኋን  ከራሱ አብራክ የተገኘን የ10 ዓመት ታዳጊ ሕፃንን ከመኖሪያ ቤቱ ጓሮ በመውሰድ መሬት ላይ አጋድሞ በቢላዋ አርዶት ድርጊቱን ከፈፀመ በኋላ ተሰዉሮ ነበር።

ወንጀል መፈፀሙ መረጃ የደረሰዉ የወረዳው ፖሊስ ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር በመሆን በተደረገ ክትትል ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሏል። ፖሊስ የሟቹን አስክሬን በማንሳት ወደ ወራቤ ኮምፕርሄኔሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመላክ አስክሬኑን በማስመርመር የሟች በድን ገላ በክብር እንዲያርፍ ለቤተሰቦቹ ተመላሽ መደረጉን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

Читать полностью…

EthioTube

የቦይንግ አውሮፕላን የሞተር ሽፋን በበረራ ላይ ተገንጥሎ መውደቁን ተገለጸ

የአሜሪካው የሳውዝዌስት አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን በበረራ ላይ እያለ የሞተሩ ሽፋን ተገንጥሎ መውደቁ ተነገረ።

135 መንገደኞችንና 6 የበረራ አባላት ያሳፈረው አውሮፕላን ዴንቨር ለማረፍ ከመደገጉ በፊት 10 ሺህ 300 ጨማ ከፍታ ላይ እየበረረ እንደነበረም ነው የተገለጸው።


ችግሩ ማጋጠሙን ተከትሎ የአሜሪካ የአየር መንግድ ተቆጣጣሪዎች አፋጣኝ ምርመራ እያደረጉ መሆኑም ተነግሯል።

የአሜሪካው የሳውዝዌስት አየር መንገድ በቦይንግ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ላይ ያጋጠመውን ችግር የአየር መንገዱ የጥገና ቡድን እንደሚመረምረው አስታውቀዋል።

አየር መንገዱ ለእንደዚህ አይነት ክፍሎች ጥገና ኃላፊነት እንዳለበት አረጋግጧል።

ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን የተመረተው በፈረንጆቹ በ2015 መሆኑን የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ) መረጃ ያመለክታል።

ቦይንግ ኩባንያ የአሜሪካው የሳውዝዌስት አየር መንገድ በቦይንግ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ላይ ባጋጠመው ችግር ዙሪያ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።

የዓለማችን ግዙፍ የአቪየሽን ኩባንያ የሆነው ቦይንግ ካሳለፍነው ጥር ወር ጀምሮ በ737 ማክስ 9 አውሮፕላን መስኮቱ ተገንጥሎ መውደቁን ተከትሎ ትችቶችን እያስተናገደ ይገኛል።

ከዚህ ጊዜ በኋላ ተደጋጋሚ የምርት ጥራት ችግሮች የተከሰቱ ሲሆን የአሜሪካ አቪዬሽን አስተዳድር በኩባንያው ላይ የቴክኒክ ጥራት ምርመራዎችን አድርጓል።

ኩባንያው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ምርቶች ላይ ካከናወናቸው 89 የጥራት ምርመራዎች ላይ በ33ቱ ጉድለት እንደተገኘበት መገለጹም ይታወሳል።

ይህ አውሮፕላን በተለይም የኤሮ ሲስተሙ ሲፈተሸ የጥራት ደረጃውን ያሟላው ከ13 ነጥቦች በስድስቱ ብቻ አልፏል ተብሏል።

የኩባንያው የቴክኒክ ባለሙያዎች ስለ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በቂ እውቀት እንዳላቸው በተደረገው ምርመራ የሚገባውን ያህል ያውቃሉ የሚለውን ኩባንያው ማስረዳት እንዳልቻለም ተገልጿል።

አል አይን

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ አርብ የኢት ዜና - መጋቢት 27 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 5, 2024

👉አለም ባንክ የፈቀደችው አዲስ ብድር
👉የሶማሊና የኢትዮጵያ ጉዳይ እየከረረ መጥቷል
👉በባለቤቱ ላይ የመግደል ሙከራ የፈፀመው የፖሊስ አባል
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/6UrueGKPzvE

Читать полностью…

EthioTube

የሶማሊላንድ እና  ፑንትላንድ ባለሥልጣናት ሶማሊያ መንግስት የ ኢትዮጵያ ቆንስላ ለመዝጋት የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አደረጉ

የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሮዳ ኤልሚ፤ የሶማሊላንድ የመረጃ፣ የባህልና ብሔራዊ መመሪያ ሚኒስትር አሊ ሀሰን ሞሃመድ እና የፑንትላንድ የመረጃ ሚኒስትር ማህሙድ አይዲድ ዲሪር የሶማሊያ መንግስት በሶማሊላንድ መዲና ሃርጌሳ እና በፑንትላንድ ጋሮዌ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤቶች እንዲዘጉ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አድርገዋል።

በትላንትናው ዕለት የሶማሊያ መንግስት በ ሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሃመድ ዋሬ  በ72 ሰዓት ውስጥ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ ያዘዘ ሲሆን ሲሆን በተጨማሪም በኢትዮጵያ የሚገኙትን አምባሳደሩን ለምክክር በሚል መጥራቱን አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም፤ የሶማሊያ መንግስት በሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሀርጌሳ እና በፑንትላንድ ጋሮዌ ከተማ የሚገኙትን ቆንስላ ጽ/ቤቶች በሰባት ቀናት ውስጥ ይዘጋሉ ብሏል።

ይሁን እንጂ አምባሳደር ሮዳ ከቪኦኤ ሶማሊ ጋር ባደረጉት አጭር ቃለ መጠይቅ፤  (የሶማሊያ) ውሳኔው፤ "በህልም" ላይ የተመሰረተ እና "ጥቅም የሌለው" ነው ብለዋል።

የሶማሊላንድ የመረጃ፣ የባህልና ብሔራዊ መመሪያ ሚኒስትር አሊ ሀሰን ሞሃመድ በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ፤ በሶማሊላንድ “የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሶማሊ ላንድ ከመነሻው በሶማሊያ ፍቃድ አይደለም  የተከፈተው፤ ስለዚህ ሞቃዲሾ ባለመፈቀዷ አይዘጋም” ሲሉ ለሶማሊያ ምላሽ ሰጥተዋል።

በተመሳሳይ መልኩ፤  የፑንትላንዱ ማህሙድ አይዲድ የሶማሊያ መንግስት በጋሮዌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ ለመዝጋት "የሚያስችል ስልጣን የለውም" ብለዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊየን ዶላር የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊየን ዶላር የድጋፍ እና የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡የብድር እና የድጋፍ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የሚውሉ ስድስት ፕሮጀክቶችን ለመተገበር እንደሚውል ተገልጿል፡፡የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተፈራርመውታል፡፡

ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 300 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው በገጠር አካባቢዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ማሳለጥ ለሚያስችል የመንገድ መሰረት ልማት ግንባታ እንደሚውል ተገልጿል፡፡200 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘውን የሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ለማጠናከር እና ለማስፋፋት እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ ከተሰጠው ብድር ውስጥ 340 ሚሊየን የሚሆነው በኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል እንደሚውል ተጠቅሷል፡፡

522 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚሆነው ደግሞ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ተደራሽነትን ለማስፋት እና ታዳሽ ሃይል ማመንጨት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመደገፍ እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡275 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው ደግሞ በኢትዮጵያ ከተሞች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን እና ተደረሽነትን ለማስፋት እንዲሚውል ተገልጿል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 70ሺህ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ሁኔታዎችን የሚያመቻች የመንግሥት ልዑክ በቀጣይ ቀናት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ እንደሚያቀና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የሚመራው ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች የተካተቱበት የልዑካን ቡድኑ የሚያቀናው ከሳዑዲ አቻው ፣ በሪያድ እና ጂዳ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ጋር በመተባበር
መሆኑን ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ልዑኩ በሳዑዲ በሚኖረው ቆይታ አስፈላጊውን ዝግጅት ካጠናቀቀ በኋላ በፍጥነት ዜጎችን የመመለስ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጸዋል።

መንግሥት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተለያዩ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ከ50 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉንም አቶ ነብዩ አስታውሰዋል።

መንግሥት በአሁኑ ወቅት ዜጎችን ከመመለስ ባሻገር ሕጋዊ የሥራ ሥምሪት ለማመቻቸት እየሠራ መሆኑን ተቅሰው፤ እስካሁን ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች፣ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ከሊባኖስ እና ዮርዳኖስ ጋር ሕጋዊ የሥራ ሥምሪት መፈራረሙን አብራርተዋል።

ከኩዌት ፣ከባሕሬን እና ኦማን ጋርም ሕጋዊ የሥራ ሥምሪት ስምምነት ለመፈራረም በሂደት ላይ መሆኑን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የፍልሰተኞች መነሻ ብቻ ሳትሆን ከ1 ሚሊዮን በላይ ከተለያዩ ሀገር የመጡ የውጭ ሀገር ፍልሰተኞችን አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በፍልሰተኞች አያያዝ እያደረገችው ላለው ሥራ ዓለም አቀፉ ማኀበረሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

(EBC)

Читать полностью…

EthioTube

ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገሯ ማባረሯን ገለጸች።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከአራት ወራት በፊት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።

ይህ ስምምነት ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣንና እና ተቃውሞን ማስከተሉም አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎም ሶማሊያ የተለያዩ ዲፕሎማያው እርምጃዎችን ስትወስድ የቆየች ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገሯ ማባረሯን ሮይተርስ ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ሶማሊያ በሞቃዲሾ የኢትዮጵያን አምባሳደር ያባረረች ሲሆን ለውሳኔው መነሻ የሆነው ደግሞ ከሶማሊላንድ ጋር ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ባደረገችው የወደብ ስምምነት ምክንያት ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችንም ዘግቻለሁ ብላለች።

አል ዐይን አማርኛ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢዩ ተድላ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

በተያያዘ ዜና የፑንትላንድ ገንዘብ ሚንስትር መሀመድ ፋራህ የመሩት ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ፑንትላንድ በገንዘብ ሚንስትሯ መሀመድ ፋራህ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉን ተናግረው ይህ የአዲስ አበባ ጉብኝት ከሰሞኑ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር የማይገናኝ እንደሆነ እና የጉብኝት ፕሮግራሙም የቆየ ቀጠሮ ነው ሲሉ በዛሬው ሳምንታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባደረጉት የወደብ መግባቢያ ስምምነት ምክንያት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት እንዲሻክር ምክንያት ሆኗል።

ስምምነቱን ተከትሎም የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግስት በኢትዮጵያ የሚገኙትን የሀገሪቱን አምባሳደር አብዱላሂ መሀመድ ወርፋን ለምክክር ወደ ሞቃዲሾ መጥራቱን ይታወሳል።

Читать полностью…

EthioTube

43 አገራት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የቀጠሉ ግጭቶችና የመብት ጥሰቶች አሳስቦናል አሉ

43 አገራት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የቀጠሉ ግጭቶችና የመብት ጥሰቶች በጣም እንዳሳሰቧቸው ትናንት ለተካሄደው 55ኛው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ባስገቡት መግለጫ ላይ ገልጸዋል።

አገራቱ፣ ሁሉም የግጭቶች ተሳታፊ ወገኖች በንግግር ሰላምን እንዲሽቱና በአገራዊ የውይይት ሂደቱ እንዲሳተፉ ጠይቀዋል። አገራቱ፣ በኢትዮጵያ ሰላምና እርቅ ለማስፈን ተዓማኒነት ያለው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲና ተጠያቂነት አስፈላጊ መኾኑንም አውስተዋል።

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፉ፣ እውነተኛ ተጠያቂነትን፣ እውነት አፈላላጊነትን፣ ካሳ እና ጥሰቶች ድጋሚ ላለመፈጸማቸው ማረጋገጫ መስጠትን ማካተት እንዳለበትም አገራቱ አሳስበዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ትዝታ ስራ አገኘች

ትዝታ ገረመው አዲሱን ስራዋን በኢትዬጲያን ቢዝነስ ሪቪዊ Ethiopian Busines Review የመረጃ ጥንቅር እና ምርምር ኦፊሰር (Data Researcher) ሆና ሚያዝያ 1 ሥራ ለመጀመር የቅጥር ደብዳቤ ዛሬ ተቀብላለች።

ቢሮ ተገኝታ ከቅርብ አለቃዋ የEthiopian Business Review ዋና አዘጋጅ ወይዘሪት ኤደን ተሾመ፣ እንደዚሁም የአስተዳደር እና ፋይናንስ ኃላፋዋ ወይዘሪት ሃና ፈቃዱ ጋር ስለ አዲሱ ስራዋ እና የድርጅቱ የሥራ መመሪያ በዝርዝር ገለፃ ተደርጎላታል። ከተቀሩት የድርጅታችን ሰራተኞች ጋርም ትውውቅ አድርጋለች።

ቅዳሜ ዕለት ያቀረብነውን የትብብር ጥያቄ ተቀብላችሁ አድራሻዋን በመስጠት እንድንገናኝ ላገዛችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።

ምንጭ፡ አማን ይሁን በፌስቡክ

Читать полностью…

EthioTube

በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ

ላለፉት ሦስት ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረው የመሬት አገልግሎት ካለፈው ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናው የመዋቅር ጥናት መሠረት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ ከጥር  21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦስት ወራት ታግዶ የቆየው የመሬት አገልግሎት፣ የዜጎችን መብት የጣሰ እንደነበር በመናገር  ተገልጋዮች ሲያማርሩ ቆይተዋል።

አስተዳደሩ እንደገለጸው አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከቀን ከመጋቢት 23 ቀን2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን አስታውቋል።

Читать полностью…

EthioTube

ከ8ሺህ በላይ የሆኑ የብልፅግና ፓርቲ አባላት  ተባረዋል ተባለ፡፡

በዘንድሮው የበጀት ዓመት በስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ላይ  በተደረገ ግምገማ ከ8 ሺህ በላይ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)  ይህን የገለፁት በትላንትናው  ዕለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ከፓርቲዎች በብልሹ አሰራር ዙሪያ ለተነሳላቸው ጥያቄ  ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት የብልፅግና ፓርቲ አባላት  እንደ ስራቸው አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰድ በተጨማሪ እስከ ማባረር የደሰረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡መጋቢት 2015 ዓ.ም ፓርቲው ባካሄደው ጉባዔ ላይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ ፓርቲው በኢትዮጵያ ታሪክ ከዚህ በፊት ከነበሩ ፓርቲዎችና ድርጅቶች በቁጥርም፥ በአደረጃጀትም፥ በሀሳብም የተለየ ፓርቲ መሆኑንም መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡

በወቅቱ  ፓርቲው በመላው ሀገሪቱ ከ11 ሚሊየን በላይ አባላት እንዳው በመግለፅ፤ ሁሉም ብሄሮች በሚገባቸው ልክ የተወከሉበት ፓርቲ መሆኑንም አስታውቀዋል።ገዢው ፓርቲ ብልፅግና ባለስልጣናት  መካከል የክህሎት፣ የመቀራረብና  የአስተሳሰብ አንድነት ያመጣል የተባለ ስልጠናና ውይይት በሁሉም ክልሎች ማካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ዛሬ የመጨረሻ ቀን ነው ‼

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያላግባብ ከ121 ሺህ እስከ 95 ሺህ ብር ወስደው ያልመለሱ ደንበኞቹን ማንነት የሚገልጡ የፎቶግራፍና ሌሎች መረጃዎችን ትናንት ምሽት ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።

ባንኩ እስከ ትናንት ድረስ ያላግባብ ገንዘቡን የመለሱ ደንበኞቹ ብዛት ከ10 ሺህ በላይ መድረሱን አስታውቋል።ባንኩ ለደንበኞቹ የሰጠው የገንዘብ መመለሻ ተጨማሪ ቀነ ገደብ ዛሬ ያበቃል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…
Subscribe to a channel