ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

🛑 ኮሬ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ለተፈጸመዉ ጥቃት ተጠያቂዉ ‹‹ፖሌ›› የተባለ የታጠቀ ቡድን መሆኑ ተገለጸ፡፡

ለደረሰዉ ጥቃትም እስካሁን ምንም የተሰጠ ምላሽ የለም ተብሏል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን የታጠቁ ሃይሎች ሚያዚያ 13 ቀን 2016 በፈጸሙት ጥቃት ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ ሶስት ህጻናትን ጨምሮ አንድ አርሶ አደር መገደላቸዉን ዞኑ አስታዉቋል፡፡

የኮሬ ዞን ሠላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶሮ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንደነገሩን በምዕራብ ጉጂ ዞን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ይህንን ጥቃት ሳይፈጽሙ አልቀረም ነዉ ያሉት፡፡

ባለፈዉ ዓመት ህዳር ላይ በኮሬ ማህበረሰብ እና በምዕራብ ጉጂ ዞን ማህበረሰብ መካከል ዕርቅ ተፈጽሞ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብሶችም ጥቃቱ እስከተፈጸመበት ቀን ድረስ ስራቸዉን ይሰሩ እንደነበር ነግረዉናል፡፡

‹‹ፖሌ›› የተሰኘዉ የታጠቀ ቡድን ከአንድ ወር በፊት በምዕራብ ጉጂ ዞን የምትገኘዉን ገላና ወረዳ  የቀበሌዉን መዋቅር ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩንም ነዉ የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በ16 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ቦሬ የምትባል ቀበሌ ላይ ቢሆንም ያለዉ እስካሁን ድረስ ግን ወደ ቦታዉ የገባ ምንም የመከላከያ ሃይል የለም ብለዋል፡፡

ለጥቃቱም የተሰጠ ምንም ምላሽ የለም ያሉት ሃላፊዉ አሁንም ምንም የተረጋጋ ነገር የለም በማንኛዉም ሰዓት ድጋሚ ጥቃት ሊፈጸም ይችላል ነዉ ያሉት፡፡

የወረዳዉም ሆነ የዞኑ አመራር ወደ ቦታዉ ገብቶ ችግሩን መፍታት የሚችልበት ሁኔታ ምቹ አይደለም ያሉት አቶ ተፈራ፤ዛሬም በቦታዉ ስጋት አለን ብለዉናል፡፡

የኮሬ ዞን አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ፥ ለንጹሐን አርሶ አደሮች ሞት ምክንያት ለሆነው ጥቃት "“በምዕራብ ጉጂ ዞን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ እና ፀረ-ሰላም” ሲል የጠራቸውን አካላት ተጠያቂ አድርጓል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያዊቷ የርቀት ሯጭ እና የኦሎምፒክ የፍጻሜ ተወዳዳሪ ዘርፌ ወንድምአገኝ በአበረታች መድሃኒት ክስ የ5 አመት እገዳ ተጣለባት።

ያለፈው አመት በቶኪዮ ኦሊምፒክ የ3000 ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ላይ የደረሰችው እና የአለም ሻምፒዮና መድረክን በጠባብ ልዩነት ያጣችው የኢትዮጵያ ሯጭ ሁለት የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች በሰውነቷ ዉስጥ መገኘቱ በመረጋገጡ ለአምስት አመታት እገዳ ተጥሎበታል።

Читать полностью…

EthioTube

የአማራ ክልል መንግሥት ለሕዝቡ ጥሪ አቀረበ።

የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን በወረራ ይዟል::

ይህንን ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአማራ ሕዝብ ዛሬም እንደትላንቱ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ከሰርጎ ገቦች ራሱን እና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል::

ሕዝቡ ከክልሉ መንግሥት እና በየአካባቢው ከሚገኙ አስተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቹ የከፈቱበትን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት የድርሻውን እንዲወጣ ነው ጥሪ ያደረገው::

የክልሉ መንግሥት ከአማራ ሕዝብ በተጨማሪ ለፌደራል መንግሥት እና ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ  ጥሪ አቅርቧል፤ ለፌደራል መንግሥት ባስተላለፈው ጥሪ የሕወሓት ታጣቂ ቡድን በወረራ ከያዛቸው ቦታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቆ እንዲወጣ እና ሕዝቡን ከጥፋት መታደግ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት መታደግ እንደሚገባ ጠቁሟል::

ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ደግሞ ሕወሓት በክልሉ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝ እና ከክልሉ ሕዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።

Читать полностью…

EthioTube

የአማራ ክልል አመራሮች በአሜሪካ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር መወያየታቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ኃላፊ የተመራ ልዑክ ቡድን በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ከተማ ከኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር መወያየቱ ተገለጸ።

አዲስ ማለዳ ከክልሉ ኮሚኬሽ ቢሮ ባገኘችው መረጃ መሰረት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ የተመራው ቡድን በኒውዮርክ ከተማ የሥራ ጉብኝት አድርጓል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሚሲዮን ጽሕፈት ቤት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ኢትዮጵታዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተወካዮች ጋር በአገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውንም ቢሮው አስታውቋል።

"የልዑክ ቡድኑ በሀገር ደረጃ እና ክልላዊ  የለውጥ ጉዞ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሔ መንገዶች ላይ" ውይይት አድርጓል የተባለ ሲሆን ክልሉን ወደ ተሟላ ሰላም ለማምጣት መንግሥት እያደረገ ስላለው ጥረትና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተደረገ ስላለው ጥረት ውይይት መደረጉ ተገልጿል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ስለክልሉ የሰላም ሁኔታ፣ የልማት ሥራዎችና ድህነት ቅነሳ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ፣ የሀገራዊ አካታች የምክክር መድረክ ላይ የአማራ ክልል ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ሥራ እና ለሥራ እድል ፈጠራ ያለውን ምቹ ሁኔታ የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተዋል ተብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በውድድሩ ከ10 ሺህ በላይ ግለሰቦች እንዲሁም ከ22 ክለቦች የተወጣጡ አትሌቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተመርተው ለዓለም አቀፍ ክለቦች የሚቀርቡ የስፖርት ትጥቆችን ማስተዋወቅ የሩጫው ዓላማ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

መርሐ ግብሩ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የውጭ ምንዛሬ ወጪን በማዳን ውጤት እያስገኘ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ያዘጋጁት ውድድሩ መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ አርብ የኢት ዜና - ሚያዝያ 11 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 19, 2024

👉በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው ፍተሻ

👉በአዲስ አበባ 32 ሺህ አባወራዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋልጠዋል

👉ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/mYYKWICAPM4

Читать полностью…

EthioTube

የአንድ አመት ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር ዋለ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን  ቤንች ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፒክተር አለማየሁ አማረ ለክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን እንደገለፁት በወረዳው ኮሶል ቀጭን መንደር ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረው  ፀብ ምክንያት የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

አዛዡ አክለውም በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ ፀብ እናት  የአንድ ዓመት ሴት ህፃን ልጅ ጥላ በመጥፋቷ ወላጅ አባት ቲቲዮስ ኪያግላስ የተባለው ተጠርጣሪ የአንድ ዓመት ህፃን ልጁ እያለቀሰች ስታስቸግረዉ በሁኔታው ተበሳጭቶ የአንድ አመት ልጁን  በህይወት ለመቅበር ጉድጓድ  ሲያዘጋጅ የተመለከቱ የአከባቢው ነዋሪዎች  ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣሉ፡፡

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪውን  ጉድጓድ እየቆፈረ እያለ በቁጥጥር  ስር እንዲውል በማድረግ ህፃኗን ጉዳት ሳይደርስባት መታደግ መቻሉንና በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ የህፃኗን ወላጅ እናቷን እያፈላለገ ሲሆን ህፃኗ በአሁን ሰዓት ሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ እንክብካቤ እያደረገላት እንደሚገኝ የገለፀት ፖሊስ አዛዡ በቤተሰብ መካካል አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ወቅት ችግሩን በመነጋገር መፍታት ይገባል ሲሉ ፖሊስ አዛዡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ፋስት መረጃ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን መረጃ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

Читать полностью…

EthioTube

ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ “በጸጥታ አካላት” ከተያዘ በኋላ ነው የተገደለው- የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት

ግድያው “ባልታወቁ ሰዎች” የተፈጸመ ነው- የኦሮሚያ ክልል መንግስት

አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የኦነግ የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ በቴ ኡርጌሳ መቂ ከተማ ውስጥ የተገደሉት ጸጥታ ኃይሎች ከሆቴላቸው ማክሰኞ እኩለ ሌሊት ላይ ከወሰዷቸው በኋላ እንደኾነ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ቡድኑ በቴ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በጥይት ረሽነዋቸዋል በማለትም ከሷል። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች፣ የሟቹ አስከሬን እንዳይነሳና የአስከሬን ምርመራ እንዳይደረግ ከልክለው እንደነበርም ቡድኑ ገልጧል።

በተያያዘ በቴ የተገደሉት የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ማክሰኞ ምሽት መቂ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ካዋሏቸው ከጥቂት ሰዓታት በኋላ መኾኑን ከምንጮቹ መስማቱን የፈረንሳዩ ዜና ወኪልም ዘግቧል።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በበኩሉ ግድያው “ባልታወቁ ሰዎች” የተፈጸመ ነው" ብሏል።

የክልሉ መንግሥት ግድያውን በማውገዝ ምርመራ እንደሚያደርግ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው ፥ " ኮሚሽኑ ከተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ በሁለቱም በኦሮሚያ ክልል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት አፋጣኝ፣ ገለልተኛ እና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ ይጠይቃል " ብለዋል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ ከትናንት በስተትያ ማክሰኞ ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉበት ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።

Читать полностью…

EthioTube

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

ውሳኔዎቹም፡-

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በመንግስት የአገልግሎትና አስተዳደር ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ መንግስት የሚያወጣቸውን ህጎች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመፈጸምና በማስፈጸም እንዲሁም የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደቱን በማፋጠን ረገድ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ተቋማት ሚና የጎላ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ፖሊሲው ሊፈታቸው እና በቀጣይ ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች በ7 ዋና ዋና ምሰሶዎች መሰረት በማድረግ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

እነዚህም ነፃና ገለልተኛ የሲቪል ሰርቪስ መገንባት ፤ብዝኃነትና አካታችነትን ያረጋገጠ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ማፋጠን፤ የመንግሥት አደረጃጀትና አስተዳደር ሥርዓትን ማሳለጥ፤ ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግሥት አገልግሎት አቅርቦት ሥርዓት መዘርጋት፤ የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት መገንባትና የማስፈጸም ዐቅምን ማሳደግ፤ የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት ቅቡልነት ያላቸው አገልግሎቶችንና ውሳኔዎችን ማቀላጠፍ፤ የሲቪል ሰርቪስ ገቢር ነበብነት (Pragmaticism) አመራር እና ተቋም ግንባታን ማፋጠን ናቸው፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ በኦነግ የፖለቲካ ሹም በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ "ሙሉ ምርመራ" እንዲደረግ ጠይቋል።

መስሪያ ቤቱ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ የግጭት አዙሪትን ለመቀልበስ ፍትህ እና ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚያስፈልግ ገልጧል።

ሂውማን ራይትስ ዎች በበኩሉ፣ የበቴ ኡርጌሳ ግድያ "ተዓማኒ ምርመራ" ያስፈልገዋል ብሏል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፣  የአቶ በቴ ኡርጌሳን ግድያ ዙሪያ ያለውን ሁኔታ በራሱ ማጣራት እንደሚያደርግ አመልክቶ፤ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ገለልተኛ እና ሚዛናዊ ምርመራ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአቶ በቴ ኡርጌሳን ግድያ በፅኑ እንደሚያወግዝ  ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ  ገልጻል፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ በኦነግ አመራር አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ መንግሥትን ተጠያቂ የማድረጉ ፕሮፓጋንዳ "በምንም መልኩ ተቀባይነት የለውም" ሲል ትናንት ባወጣው መግለጫ አጣጥሏል።

ምርመራ ባልተደረገበት ሁኔታና ወንጀል ፈጻሚው ገና ባልታወቀበት ሁኔታ  ክስተቱን ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ የሚጠቀሙ ኃይሎች መኖራቸውን በማመልከት አጥብቆ አውግዟቸዋል። "ከመንግስት ጋር የአቋም ልዩነት ስላላቸውና የፖለቲካ አቋማቸው ስለሚለይ ብቻ ግድያው በመንግሥት አካል እንደተፈፀመ ተደርጎ የሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ፥ " የፖለቲካ ኪሳራ የደረሰባቸው የፖለቲካ ኃይሎች መንግሥትን ለግድያው ተጠያቂ በማድረግ ይህንን ሁኔታ ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው " ሲል ወቅሷል። መንግሥት በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅም ባወጣው መግለጫ ቃል ገብቷል።

የፀጥታ ኃይሎች የግድያውን ፈፃሚ በህግ አግባብ መርምረውና አጣርተው እስካላሳወቁ ድረስ " ይህ አካል ነው ኃላፊነት የሚወስደው " ብሎ መናገር እንደማይቻል ጠቁሟል። ማህበረሰቡ ገና ውጤቱ ሳይታወቅ እየተካሄዱ ካሉት " እከሌ ነው የገደለው " ከሚሉ ፕሮፖጋንዳዎች ራሱን መጠበቅ አለበትም ብሏል።

 Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ማክሰኞ የኢት ዜና - ሚያዝያ 2 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 9, 2024

👉ችሎት በነ እስክንድር ነጋ ክስ አዲስ ነገር ብሏል
👉ጅቡቲ በ ጀልባ አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ሞቱ
👉ዛሬ ወደ ሞቃዲሾ የነበሩ በረራዎች ለምን ተሰረዙ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/MMTJi1bpYRE

Читать полностью…

EthioTube

ዛሬ ወደ ሞቃዲሾ ሊደረጉ የነበሩ በረራዎች ተሰረዙ

የአውሮፕላን በረራዎች የተቋረጡት፣ በሱማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በሞቃዲሾ ሰሞኑን አልሸባብ የሽብር ጥቃቶችን ሊፈጽም እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ማውጣቱን ተከትሎ ነው።

ኢምባሲው አገኘኹት ባለው መረጃ፣ በሞቃዲሾው ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ በወደቦች፣ በፍተሻ ጣቢያዎች፣ በመንግሥት መስሪያ ቤት፣ ሆቴሎች እና የገበያ መደብሮች ላይ የሽብር ጥቃቶች ሊፈጸሙ ይችላሉ በማለት ትናንት ባሠራጨው መረጃ አስጠንቅቋል።

ዛሬ ወደ ሞቃዲሾ ሊያደርጉት የነበረውን በረራቸውን ካቋረጡት አየር መንገዶች መካከል፣ የቱርክ እና ኳታር አየር መንገዶች ይገኙበታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አልሸባብ ትናንት ሌሊት በፕሬዝዳንታዊ ቤተመንግሥቱ ላይ የሞርታር ጥቃቶችን ፈጽሟል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ አዲስ ይዞት የመጣው የሊትየም ኤሌክትሪክ ሞተር ምን ይመስላል ?

ትናንት በሳይንስ ሙዚየም ያስተዋወቀው ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ ያቀረባቸውን አዳዲስ ሞዴል ሞተሮችን ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ ። 👇
https://youtu.be/30-Qwjy64gc

Читать полностью…

EthioTube

የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ነው።

ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ አልታየችም ፤ በመሆኑም የዒድ አልፊጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።

ነገ ማክሰኞ የረመዷን የመጨረሻው ሰላሳኛ ቀን ይሆናል።

Читать полностью…

EthioTube

በስልጤ ዞን የ10 ዓመት ታዳጊ ልጁን በቢላዋ  አርዶ የተሰወረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የ10 ዓመት  ታዳጊ ልጁን በቢላዋ አርዶ ተሰዉሮ የነበረዉ  ተጠርጣሪ ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር መዋሉን የስልጤ ዞን ፖሊስ አስታውቋል።

በዞኑ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረደ በሙጎ ከተማ ልዩ ስሙ ሀሊቾ ተብሎ በሚጠራዉ መንደር ነዋሪ የሆነዉ ተጠርጣሪ መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 4:30 ለጊዜው ምክንያቱ በግልፅ ባልታወቀ አኳኋን  ከራሱ አብራክ የተገኘን የ10 ዓመት ታዳጊ ሕፃንን ከመኖሪያ ቤቱ ጓሮ በመውሰድ መሬት ላይ አጋድሞ በቢላዋ አርዶት ድርጊቱን ከፈፀመ በኋላ ተሰዉሮ ነበር።

ወንጀል መፈፀሙ መረጃ የደረሰዉ የወረዳው ፖሊስ ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር በመሆን በተደረገ ክትትል ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሏል። ፖሊስ የሟቹን አስክሬን በማንሳት ወደ ወራቤ ኮምፕርሄኔሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመላክ አስክሬኑን በማስመርመር የሟች በድን ገላ በክብር እንዲያርፍ ለቤተሰቦቹ ተመላሽ መደረጉን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

Читать полностью…

EthioTube

" የቀሲስ በላይ ጉዳይ ከቤተክርስቲያኗ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርትያኗ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማስታወቋን ዶቸቬለ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግለሰቡ በቤተክርስቲያኗ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚያገለግሉ ቢሆንም፤ ተጭበርብሯል ከተባለው ሰነድ ጋር ግን ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኛት ምንም ነገር እንደሌለ አስታውቃለች፡፡

መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትሪያርክ ህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ክፍል ዋና ኃላፊ “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር በዋሉበት ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን የመከታተል ጥረት ላይ ትገኛለች ብለዋል።

ኃላፊው “እስካሁን በተደረገው ክትትል “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ እንደሌለና በግል ህይወታቸው ውስጥ የገጠማቸው ነገር እንደሆነ ነው የተረዳነው” ብለዋል።

መምህር ዶ/ር አካለወልድ አክለውም በቀጣይ ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ነገር አለው ወይ? የሚለው በህግ ክፍል በኩል ማጣራት እንዲደረግ ትዕዛዝ መተላለፉንም አመልክተዋል፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሰኞ የኢት ዜና - ሚያዝያ 14 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 22, 2024

👉ልጃቸው የተገደለባቸው አባ ገዳ ጎበና

👉የአማራ ክልል መንግስት ለህዝቡጥሪ አቀረበ

👉የአማራ ክልል አመራሮች በአሜሪካ ያለውን ማህበረሰብ አወያዩ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/svWhcygHKHg

Читать полностью…

EthioTube

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ አቆሙ

በሳውዲ አረቢያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ እና አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ በተለያዩ አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ ማቆማቸው ተጠቁሟል።

በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል ሪያድ፣ ዲሪያህ፣ ሁረይማላ ከዱርማ እና አል ቁዋይያህ ይገኙበታል ተብሏል።

የሀገሪቱ መንግስት እንዳስታወቀው ለጥንቃቄ ሲባል በአሲር፣ ናጅራን እና በሌሎች የተጎዱ አከባቢዎች የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል።

ኪንግ ካሊድ ዩኒቨርሲቲ እና ናጃራን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም የቢሻ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲዎች በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ የተነሳ ስራቸውን ማቆማቸውም ነው የተገለጸው።

የሀገሪቱ ሚቲዎሮሎጂ ማዕከል በአየር ሁኔታ ዘገባው በምስራቅ እና በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክልሎች በቀጣይ ቀናት ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ እንደሚጥል ተንብዮአል።

ከመካከለኛ እስከ ከባድ ነጎድጓዳማ ንፋስና በረዶ የታጀበ የአየር ሁኔታ በሪያድ ክልል እስከ ሰኞ ድረስ እንደሚቀጥልም ማዕከሉ ገልጿል።

በተጨማሪም ማዕከሉ በቀይ ባህር እና በአረብ ባህረ ሰላጤ ላይ ያለው የባህር ላይ የንፋስ ፍጥነት በሰአት እስከ 50 ኪ.ሜ እንደሆነና እና በነጎድጓድ ጊዜ ከፍታው ከሁለት ሜትር ሊበልጥ እንደሚችል ማስታወቁን ገልፍ ኒዊስ ዘግቧል።

Читать полностью…

EthioTube

አባ ገዳ ጎበና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መስማታቸውን ተናገሩ

የቱለማ አባ ገዳ የሆኑት አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።

ከአንድ ሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን መንግሥት ‘ሸኔ’ የሚለው ቡድን አባል ነው ያለው የአባ ገዳ ጎበና ልጅ “ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል” ብሎ ነበር። ይህን የዞኑ መግለጫን ተከትሎ በኦሮሞ ባሕላዊ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ትልቅ ስፍራ በሚሰጠው ገዳ ከፍተኛ ኃላፊነት ያላቸው የአባ ገዳ ጎበና ልጅ የመገደል ዜና ብዙዎችን ሲያነጋግር ቆይቷል።

የቱለማ አባገዳ እና የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ፀሐፊ የሆኑት አባ ገዳ ጎበና ሆላ፣ ፎሌ ጎበና የሚባለው ልጃቸውን መገደል የሰሙት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚሠራጨው ወሬ መሆኑን እና አስካሁን ምንም ማረጋገጫ እንዳላገኙ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግረዋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ፤ “የኦሮሞ ልጆችን ሕይወት ሲቀጥፍ የነበረው የአባ ገዳ ጎበና ሆላ ልጅ ላይ እርምጃ ተወሰዷል” ብሎ ነበር።

የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ጨምሮም፤ “ፎሌ ጎበና ሆላ የተባለው የአባ ገዳ ጎበና ሆላ ልጅ በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ ውስጥ የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት ለመቅጠፍ ሲንቀሳቀስ” እንደነበረ እና በፀጥታ ኃይሎች “እርምጃ እንደተወሰደበት” አመልክቷል። አባ ገዳ ጎበና የልጃቸውን ሞት ባያረጋግጡም በእርግጥ ልጃቸው መንግሥት ኦነግ-ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን አባል መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ልጃቸው ፎሌ ዕድሜው ወደ 33 ዓመት እየተጠጋ መሆኑን እና ከልጃቸው ጋር ከተያዩ ስድስት ዓመታት ማለፋቸውን አባገዳው ገልጸዋል። “ከስድስት ዓመታት በኋላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀናት በፊት ፎቶ ግራፉን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የተመለከትኩት።

“የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ውስጥ እንዳለ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ምንም ግንኙነት የለንም። የት እንዳለም አላውቅም። መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለሁ” ብለዋል።

የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ይህ የአባ ገዳው ጎበና ሆላ ልጅ በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር ግድያዎችን ሲፈጽም ቆይቷል ሲል ከሶታል። አባ ገዳ ጎበና ግን ልጃቸው ተገድሏል ከመባሉ በተጨማሪ መንግሥት ስለሚያቀርብበት ክስ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

“እኔ አባ ገዳ ነኝ አልዋሽም፤ ከልጄ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም። ስልክ አንደዋወልም። ከስድስት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፎቶግራፉን እንኳ የተመለከትኩት።” የአማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው እና የአባገዳው ሰባተኛ ልጃቸው የሆነው ፎሌ ጎበና ከቤት የወጣው የ26 ዓመት ወጣት ሳለ እንደነበረ አባቱ ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አባ ገዳ ጎበና ልጃቸው ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ መግባቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በተደጋጋሚ መኖሪያ ቤታቸው ላይ ብርበር ማድረጋቸውን ሲናገሩ ነበር።

ከጥቂት ወራት በፊት አባ ገዳ ጎበና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤታቸው ላይ ብርበራ በተደረገበት ወቅት ከወላጅ አባታቸው የወረሱት የጦር መሳሪያ መወሰዱን እና ክስተቱን ተከትሎ በቤተሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን ተናግረው ነበር።

አባ ገዳ ጎበና ከቀድሞ የቱለማ አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ መስከረም 20/2011 ዓ.ም. በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ የሆነውን ባሕላዊ ሥልጣንን መረከባቸው ይታወሳል። በገዳ ሥርዓት መሠረት አባ ገዳ ጎበና የቱለማ አባ ገዳ ሆነው እስከ 2019 ዓ.ም. ድረስ በስልጣን ላይ ይቆያሉ።

በአሁኑ ጊዜ ታጣቂ ቡድኖች ከሚንቀሳቀሱባቸው ክልሎች አንዱ በሆነው የኦሮሚያ ክልል ውስጥ የአባገዳው ልጅ አባል የሆነበት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ዋነኛው ነው። በተለያዩ የኦሮሚያ ክልፍሎች ውስጥ የሚንቀሳቀሰው እና መንግሥት ‘ሸኔ’ በማለት በሽብር ቡድንነት የፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሰላማዊ ሰዎች ላይ በሚፈጸሙ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ይከሰሳል።

ዳጉ ጆርናል

Читать полностью…

EthioTube

አፍሪካ ህብረት በአወዛጋቢው ቄስ በላይ መኮንን ላይ የመሰረተው የ6 ሚሊዮን ዶላር የማጭበርበር ክስ
-----
"The African Union has filed charges with the Federal Police Commission against Belay Mekonnen, a clergyman and deputy general manager at the Ethiopian Orthodox Church Patriarchate, following an alleged attempt to defraud the international organization of more than USD six million."

#AU #AfricanUnion #Ethiopia #EOTC

Full story:
https://www.thereporterethiopia.com/39751/

Читать полностью…

EthioTube

በአዲስ አበባ 32 ሺህ አባወራዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተባለ

የክረምት ወር መግባቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች 32 ሺሕ አባወራዎችና ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።በአሁኑ ሰዓት በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች በጥናት ተለይተው ታውቀዋልም ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ወ/መስቀል እንደተናገሩት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ፣ ልደታ፣ ቂርቆስና አራዳ ክፍለ ከተሞች በተደጋጋሚ ጎርፍ የሚያጠቃቸውና በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ናቸው ብለዋል፡፡

በመዲናዋ በወንዝ ዳር የሚኖሩ በርካታ ዜጎች መኖራቸውን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ዜጎችን ከአካባቢው በማንሳት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማዛወር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡መሥሪያ ቤታቸው ሰባት ከሚሆኑ ባለድርሻ መስራቤቶች አካላት ጋር በመሆን ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ በማድረግ ላይ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ ለጎርፍ አደጋ መባባስ ምክንያት ናቸው ያሏቸውን ችግሮች ሲገልጹ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ተቆፋፍረው ክፍት የተተዉ ጉድጓዶች፣ የውሃ መውረጃ ቦዮች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችና ወንዞች ላይ ተረፈ ምርቶችንና ቆሻሻዎችን መጣል በዋነኝነት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡እነዚህ ችግሮች በሁሉም አካባቢ በመለየት አሁን ላይ የስራ ክፍፍል ተደርጎ ቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው ፍተሻ

👉 ከሰሞኑ የሚደረጉ ፍተሻዎች የመዲናዋን እንቅስቃሴ የሚያዉኩ አካላትን ለመቆጣጠር የማደርገዉ ስራ ነው:-  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ ከተማን ለማወክ የሚደረጉ ጥረቶችን ከወዲሁ ለማስቀረት እና የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ በዋናነት ከሚደረገዉ የቁጥጥር ስራ በተጨማሪ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥርና ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በመዲናዋ የተለያዩ ለጥፋት ድርጊት የተሰማሩ አካላት መኖራቸውን የሚናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፤ ከተማዋን ከሽብርተኞች ለመከላከል ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር በ11ዱም ክፍለ ከተማ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመዲናዋ መግቢያ መውጫዎች እንዲሁም በየትኛውም አካባቢ ላይ ለሚደረገው የፍተሻ ስርዓት የማህበረሰቡ ትብብርና ፍቃደኝነት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

የከተማዋ እንቅስቃሴ ሰላማዊ ነዉ ያሉት ሃላፊዉ ሆኖም ማህበረሰቡ ሰላሙን ለማስጠበቅ ሀላፊነት ስላለበት አጠራጣሪ ነገሮችነን ሲመለከትም በአቅራቢያዉ ለሚገኝ የፖሊስ አካል እንዲጠቁም ጥሪያቸዉን አቅርበዋል፡፡
              
የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ በይፋ ከሚሰራው ስራ ውጪ ሚስጥራዊ ቁጥጥሮችን እና ክትትሎችን እያደረገ መሆኑን የሚያነሱት ሃላፊው በከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ የነዋሪዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ በመሆኑ የነዋሪው እገዛ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያስፈልግ አክለው ተናግረዋል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደሌለና ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት መሆኗን ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ተናገሩ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት” መሆኗን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደማይኖር እና ሶማሊያ ሉዓላዊነቷን ለድርድር እንደማታቀርብም ተናግረዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ ሞሐመድ ይህንን ያሉት የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ትናንት ረቡዕ ሚያዝያ 2/2016 ዓ.ም. ለአገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ነው።

“የኢትዮጵያ መሪዎች ወደ ቀልባቸው መመለስ አለባቸው” ያሉትን ሐሴን ሼህ፤ ግጭት እየፈጠረች ያለችው ኢትዮጵያ እንጂ ሶማሊያ እንዳልሆነች ለዓለም እየተናገሩ መሆኑን ገልጸዋል።

“እኛ የኢትዮጵያን አካል እንፈልጋለን አላልንም። ለኢትዮጵያን መንግሥት እውቅና አንሰጥም [አላልንም]፤ ከክልል መንግሥት ጋር ስምምነት እንፈጽማለንም አላልንም” ሲሉ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ግጭት እየፈጠረች አይደለም የሚለውን ሀሳባቸውን አስረድተዋል።

ሁለቱ ጎረቤት አገራት በጋራ ፍላጎቶቻቸው ላይ መሥራት ያላቸው “ብቸኛ አማራጭ” መሆኑን በንግግራቸው ላይ የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ “ሉዓላዊነታችንን፣ አንድነት እና ሙሉዕነታችንን ለድርድር የሚያቀርብ የጋራ ፍላጎት ሊኖረን አይችልም” ብለዋል።

ሐሰን ሼክ፤ “ለዓለም እየተናገርን ያለነው፤ እኛ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት እንዳልሆንን ነው። እነሱ ግን ናቸው። እናም ይህ እንዲፈጠር በፍፁም አንፈቅድም” ሲሉ ከኢትዮጵያ ተጋርጦብናል ያሉትን ስጋት ገልጸዋል።

ሶማሊያ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር ልታደርግ እንደማትችል እና ሉዓላዊነቷን ለድርድር እንደማታቀርብ የተናገሩት ሐሴን ሼክ፤ “ንግግርን ወይም ድርድርን እየተቃወምን አይደለም። ነገር ግን መሬታችን እንዲወሰድ ወይም ሉዐላዊነታችን ለድርድር እንዲቀርብ አንፈቅድም” ሲሉም ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንቱ፤ የኢትዮጵያ መሪዎች እየተከተሉት ያለው አካሄድ “እንደማይሠራላቸው” እና “ከዚህ መንገድ እንዲመለሱ እየመከሯቸው” መሆኑንም አንስተዋል።

ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ይህንን ንግግር ያደረጉት አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማቋረጥ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ካስተላለፈች ከቀናት በኋላ ነው። በአዲስ አበባ የሚገኙት የሶማሊያ አምባሳደርም ወደ ሞቃዲሾ እንዲመለሱ መታዘዛቸው ይታወሳል።

ሁለቱ አካላት ጥር ላይ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተፈፃሚነት ወደሚኖረው ስምምነት ተቀይሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ሁለቱ አካላት በተፈራረሙበት ዕለት ተገልጾ ነበር። ይሁንና የመግባቢያ ስምምነቱ ከተፈረመ አራት ወራት ቢያልፍም እስካሁን ድረስ ተፈፃሚነቱ የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ በይፋ የተነገረ ነገር የለም።

Читать полностью…

EthioTube

እንግሊዝ ዓለም ዓቀፉን በአበባ ንግድ ላይ የሚጣለዉን ታሪፍ ማንሳቷን አስታዉቃለች

በምስራቅ አፍሪካ ለሚገኙ የአበባ አምራቾች ዋጋዉን ለማርከስ እና ከእንግሊዝ ጋር የሚደረግ ግብይትም ቀላል እንዲሆን በማሰብ ለ2 ዓመታት ታሪፍ መጣል ማቆሟን ነዉ የገለጸችዉ፡፡

ከዚህ በኋላ ለሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ በምትልካቸዉ የአበባ ምርቶች ላይ ምንም ዓይነት ታሪፍ አይጣልባትም፡፡

ይህ ዉሳኔ ከአበባ አምራቹ አገር ቀጥታ ወደ እንግሊዝ ሲላክ ብቻ ሳይሆን በሌላ ሶስተኛ አገር ጭምር አበባዉ ወደ እንግሊዝ ቢገባ ምንም ዓይነት ታሪፍ እንደማይኖረዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ይህም በምስራቅ አፍሪካ ለሚገኙ የአበባ ምርታቸዉን ቀጥታ ወደ እንግሊዝ ሳይሆን በሌላ ሶስተኛ አገር ወደ እንግሊዝ ለሚያስገቡ አገራት ከፍተኛ ጥቅም አለዉ ተብሏል፡፡

ይህ ዉሳኔ ከምስራቅ አፍሪካ አምራቾች ጋር ያላትን ግንኙነት በማጠናከር በክልሉ ያላትን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነዉ የተባለ ሲሆን፤ ከዛ ባሻገር ለተጠቃሚዎችም በዋጋም፣ በአበባ ልዩነትም ምርጫ እንዲኖራቸዉ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የተነሳዉ የ8በመቶ ታሪፍ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚተገበር ቢሆንም ከፍተኛ አበባ አምራች ለሆኑት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ እና ኡጋንዳ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ከፍተኛ አበባ አምራች አገር ስትሆን ከሰብ ሰሃራን አፍሪካ ከሚላኩ የአበባ ምርቶች 23 በመቶዉን ድርሻ የምትይዝ ናት፡፡

በ2023 ከኢትዮጵያ 12.6 ሚሊየን ዩሮ የሚገመት የአበባ ምርት ወደ እንግሊዝ እንደተላከ ይታወሳል፡፡

ይህ ዉሳኔ ለሁለት ዓመታት ቀጣይነት ያለዉ ሲሆን ከዛሬ ሚያዚያ 11 2024 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 2026 ድረስ የሚተገበር ነዉ፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛ ኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ ኢድ ሙባረክ !

Читать полностью…

EthioTube

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የችሎት ውሎ ድምጽ ተቀድቶ በመሠራጨቱ ምክንያት በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የተከሰሱ ግለሰቦችን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታ እንደማይሰማ ፍርድ ቤቱ አስታወቀ።

ችሎቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተመለከተ አቤቱታ በጽሁፍ እንዲቀርብ ብይን መስጠቱን ከተከሳሾች ጠበቃ አንዱ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ብይኑን የሰጠው ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 1/2016 ዓ.ም. የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሕገ መንግሥት እና ሽብር ወንጀል ችሎት ነው።

ችሎቱ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙት ተከሳሾች ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ የሚያቀርቡትን የቃል አቤቱታ ለመስማት ነበር።

ባለፈው ሳምንት አርብ በነበረው የችሎት ውሎ ከ14ቱ ተከሳሾች መካከል አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዮሐንስ አቤቱታቸውን አቅርበው ነበር። ሁለተኛው ተከሳሽ አቶ ክርስቲያን ታደለ ደግሞ በከፊል አቤቱታቸውን ማቅረባቸውን ጠበቃቸው አስታውሰዋል።

አቶ ክርስቲያንን ጨምሮ ቀሪዎቹ 13 ተከሳሾች በዛሬው የችሎት ውሎ አቤቱታቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።
ሆኖም ግን ፍርድ ቤቱ የዛሬውን የችሎት ውሎ የጀመረው የዐቃቤ ሕግን አቤቱታዎች በመቀበል መሆኑን አቶ ሰለሞን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ዐቃቤ ሕግ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጸመ የተባለው አካል በሌለበት የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታ መቀበል ተገቢ አይደለም ስለዚህ አቤቱታው መቅረብ ያለበት በጽሁፍ ነው” የሚል ጥያቄ ማንሳቱን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ቀጣይ ቆይታ ላይም አስተያየት ሰጥቷል።
ዐቃቤ ሕግ “እኛ ሥራ የሚበዛብን ስለሆነ ቀጣይ ምርመራዎችም ስላሉብን የፌደራል [ፖሊስ] የወንጀል ምርመራ የጊዜያዊ ማቆያውን ስለምንፈልገው ወደ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩ” የሚል አቤቴታ ማቀረቡን አቶ ሰለሞን ገልጸዋል።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ዛሬ ችሎቱ የተቀጠረው፤ “የቀሪ ተከሳሾችን የሰብዓዊ መብት ጥሰት [አቤቱታ] ለመስማት” መሆኑን በማንሳት የደንበኞቻቸው አቤቱታ አንዲሰማ ጠይቀዋል።

ሆኖም ችሎቱ “በባለፈው ቀጠሮ የሰጠው ትዕዛዝ የቀሪ ተከሳሾችን አቤቱታ ለመስማት ቢሆንም ይኼን የሚያቋርጥ ነገር ተከስቷል” በሚል አቤቱታውን ላለመስማት አቋም ስለመያዙ አቶ ሰለሞን አስረድተዋል።

ችሎቱ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታውን የማንሰማበት ምክንያት ከዚህ በፊት የነበረው የችሎት ውሎ ተቀርጾ በመውጣቱ፣ ይህም የፍርድ ቤቱን ገለልተኝነት የሚጎዳ ሆኖ ስላገኘነው ይህንን ላለማስኬድ ችሎቱ አቋም ወስዷል” ማለቱን አቶ ሰለሞን አብራርተዋል።

ይህን ተከትሎም የሰብዓዊ መብት አያያዝን የተመለከተ አቤቱታ በጽሁፍ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ተከሳሾቹ የተከሰሱበት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ፍርድ ቤቶች ተከሳሾች ለሚያቀርቧቸው የመብት ጥያቄ ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው ያትታል።

የዳኝነት ሥልጣንን የሚያትተው አዋጁ ክፍል፤ “ፍርድ ቤቶች በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘው ሰው ወይም የተከሰሰው ሰው ከአያያዙ ጋር በተያያዘ በሚያነሳው የመብት ጥያቄ ቅድሚያ በመስጠት መመርመር እና ተገቢውን ማስተካከያ እንዲደረግ አግባብነት ላለው አካል ትዕዛዝ መስጠት አለባቸው” ሲል ይደነግጋል።

ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም “የድምጽ ቅጂው ከፍርድ ቤት ነው የወጣው አይደለም የሚለውን ለማጣራት ባለፈው ቀጠሮ የተከሳሾችን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን አቤቱታ የቀዳው ማሽን በፌደራል ፖሊስ ምርመራ አድርጎ ውጤቱን ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ” ሌላም ብይን ሰጥቷል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ ከዛሬ ጀምሮ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ በፍርድ ቤቱ ታዝዟል።
የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ሦስት ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾችን በተመለከተም ለ36ቱ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግ 40ኛ እና 51ኛ ተከሳሾችን ደግሞ ፖሊስ እንዲያቀርብ አዝዟል።


መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በሰሜናዊ ጅቡቲ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ የ38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አለፈ

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አልፏል።

በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ ጎዶሪያ በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ 60 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ትጓዝ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ 38 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን በጅቡቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮንም አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ የዒድ አልፈጥር ሰላት እስከሚጠናቀቅ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በከተማዋ የዒድ አልፈጥር ሰላት ተሰግዶ እስከሚጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም የይለፍ ፈቃድ ከሌላቸው ተሽከርካሪዎች በስተቀር ከሌሊት 10 ሰዓት ጀምሮ የዒድ ሰላት እስከሚጠናቀቅ

📍 ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ
📍 ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው  አጎና ሲኒማ ላይ
📍 ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
📍 ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ፡፡
📍 ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ
📍 ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ  22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ
📍 ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል  አጠገብ
📍 ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ  አቧሬ ሴቶች አደባባይ  ላይ
📍 ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
📍 ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ
📍 ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ
📍 ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎባ ቁጠባ አጠገብ
📍 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ
📍 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር  ወደ ብሔራዊ ቴአትር  ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ
📍 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ  የሚዘጉ ይሆናል።

በተያያዘ መረጃ የጸጥታና ደሕንነት የጋራ ግብረ ኃይል በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በመላው አገሪቱ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የአፍሪካ ኅብረት ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ የዘር ማጥፋትና የጅምላ ጭፍጨፋን ለመከላከል ልዩ መልዕክተኛ ሾመ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሌሎች ጅምላ ጭፍጨፋዎችን ለመከላከል ሴኔጋላዊውን አዳማ ዲዬንግ የመጀመሪያ የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ አድርገው ሾመዋል።

ልዩ መልዕክተኛው የተሾሙት በአፍሪካ አህጉር የጥላቻ እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ለመዋጋት የተያዘውን የህብረቱን አጀንዳ ለማስፈፀም ሲሆን ዲዬንግ በቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን የጅምላ ጭፍጨፋ መከላከል ልዩ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል ተብሏል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር መልቀቅ ማቆሙ ተሰምቷል

ንግድ ባንኩ ብድር ለማግኘት የተለያዩ ሂደቶችን አልፈው ፤ ብድሩ ተፈቅዶላቸው የመልቀቅ ሂደት ላይ ያሉትም እንዲቆም ነው ያዘዘው ። ባንኩ ይህን ትእዛዝ ያስተላለፈው ረቡዕ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ/ም መሆኑንም ሰምተናል ።

ንግድ ባንኩ በጊዜያዊነት ብድር መልቀቅ ከማቆሙ በስተቀር ባስተላለፈው ትእዛዝ ላይ ብድር መልቀቅ ያቆመበትን ምክንያት አልገለጸም። ሆኖም ከብድር መልቀቅ መለስ ያሉት የብደር ጥያቄ እና ሂደቶቹ አለመቆማቸውን ሰምተናል ።

መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ እስከ ዛሬ የሰጠው ብድርም ሆነ የሰበሰበው ቁጠባ ከአንድ ትሪሊየን ብር ያለፈ ብቸኛ ባንክ መሆኑ የሚታወቅ ነው ።

ባንኩ በቅርቡ በተገበረው የሲስተም ማሻሻያ ሳቢያ በተፈጠረ ስህተት 801 ሚሊየን ብር ለምዝበራ ተዳርጎበት እንደነበረ እና ከዚህ ውስጥ አብዛኛውን ገንዘብ ባደረገው ክትትል ማስመለሱን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ በሰጡት መግለጫ ተናግረው ነበር ። ባንኩ ገንዘቡን የማስመለስ አካል ነው ያለውን ባልተገባ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ ተሳትፈዋል ያላቸውን ደንበኞች ፎቶ ሳይቀር ለህዝብ ይፋ አድርጓል ። አሁን በጊዜያዊነት ብድር መልቀቅ ማቆሙ ከዚህ ጋር ይገናኝ አይገናኝ አልታወቀም ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው አመት ብቻ 151 ቢሊየን ብር ብድር የሰጠ ሲሆን ፤ በተመሳሳይ አመት 165 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ቁጠባን ደግሞ ሰብስቦም ነበር ።ሆኖም ይህ በጀት አመት ከገባ ግን የቁጠባ አሰባሰቡ ከእቅዱ ጋር እየሄደ አለመሆኑ ተሰምቷል ። ለአብነትም በዚህ በጀት አመት የመጀመርያ ስድስት ወራት የሰበሰበው ቁጠባ ከእቅዱ አንጻር ከግማሽ በታች መሆኑም ተዘግቧል ። ለዚህ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው ችግር እንደ ምክንያት ተጠቅሷል ። ምናልባትም የአሁኑ የባንኩ በጊዜያዊነት ብድር የማቆም ውሳኔ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከተፈጠረ የገንዘብ እጥረት ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ተዘግቧል።

ዋዜማ
 

Читать полностью…
Subscribe to a channel