ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው ስደተኛ በአሜሪካ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸናፊ ሆነ

ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው የላኦስ ተወላጁ ስደተኛ በአሜሪካ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሎተሪ ጃክፖት አሸናፊ ሆነ።የ46 ዓመቱ ቼንግ ሳፋን ፓወርቦል በተሰኘው የሎተሪ ጃክፖት ጨዋታዎች እድለኛ መሆኑን የውድድሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል።ቼንግ ዕድለኛ ያደረገውን የሎተሪ ቲኬት የገዛው በኦሪጎን ግዛት በፖርትላንድ ከተማ ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር።

ግለሰቡ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ ግብር ተቀንሶ 422 ሚሊዮን ዶላር ያህል የሚደርሰው ሲሆን ይህንንም ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር እኩል እንደሚካፈሉ አስታውቋል።“አሁን ቤተሰቤን አንበሻብሻለሁ። ለራሴም ጥሩ ዶክተር መቅጠር እችላለሁ” ሲል አስረድቷል።“ህይወቴ ተቀይሯል” ሲል ለሲቢኤስ አጋር የሆነው ኮይን የተናረው ቼንግ አምላኩ እንዲረዳው በጸሎት መማጸኑን አስረድቷል።

ቼንግ አክሎም ለቤተሰቡ ሲያልሙት የነበረውን ቤት መግዛት እንደሚፈልግ እና ፓወርቦል የሎተሪ ጃክፖት መጫወቱን እንደሚቀጥል ተናግሯል።“እንደገና እድለኛ ልሆን እችላለሁ” ሲል ተስፋውን አስረድቷል።ላለፉት ስምንት ዓመታት በኬሞቴራፒ ህክምና ውስጥ ያለው ቼንግ ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር በመተባበር ከ20 በላይ የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶችን መግዛታቸውን ተናግሯል።የሎተሪ ቲኬቶቹ አሸናፊ ቁጥሮች 22፣ 27፣ 44፣ 52፣ 69 እና ቀይ ፓወርቦል 9 ነበሩ ተብሏል።

በፓወርቦል ታሪክ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የገንዘብ ሽልማት መሆኑ የተነገረ ሲሆን እስካሁን ድረስ በከፍተኛ ደረጃ የተቀመጠው በ2022 አሸናፊ የነበረው የ2.04 ቢሊዮን ዶላር ሽልማት ነው።የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶች በ45 አሜሪካ ግዛቶች፣ በኮሎምቢያ እንዲሁም በፖርቶ ሪኮ እና በአሜሪካ የቨርጂን ደሴቶች እያንዳንዳቸው በ2 ዶላር ነው የሚሸጡት። የሎተሪ ቲኬቶች ዋጋ መጨመሩ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የቢሊዮን ዶላር ሽልማቶች በጣም የተለመዱ ሆነዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሰኞ  የኢት ዜና - ሚያዝያ 21 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 29, 2024

👉 አውሮፓ የኢትዮጵያውያንን ቪዛ አስመልክቶ እግድ አወጣች 

👉በመዲናዋ በዘነበው ከባድ ዝናብ ሰዎች ሞቱ 

👉ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልኡካኑ ጋር ኬንያ ለምን ጉዳይ ሄዱ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/pr_y-YDJMnw

Читать полностью…

EthioTube

በኮሪደር ልማት የተነሳው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ሕንጻ የመልሶ ግንባታ ሥራ ተጀመረ

በኮሪደር ልማት ምክንያት የተነሳው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ሕንጻ የመልሶ ግንባታ ሥራ ተጀመረ፡፡ በግንባታው ማስጀመሪያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የቤተ-ክርስቲያኗ እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የከተማ ፕላን እና ልማት እንዲጠበቅ ብሎም ከተማችን እንድትለማ፣ እንድትዘምን እና የተሻለ ዲዛይን እንዲተገበር በርካታ ትብብር አድርጋለች ነው ያሉት፡፡

ለዚህም በዛሬው ዕለት የመልሶ ግንባታ ሥራው የተጀመረው ሕንጻ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

አዲሱ ሕንጻም ከመሬት በታች ለፓርኪንግ ግልጋሎት የሚውል ወለል እንደሚኖረው እና ዘመናዊ ባለ አራት ወለል ሕንጻ ሆኖ እንደሚገነባም ነው የገለጹት፡፡

ይህም ከአካባቢው ልማት፣ ፕላን፣ በዙሪያው ካሉ ሌሎች ቅርሶች እንዲሁም ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ጋር የሚናበብ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቀን ለቤተክርስቲያኗ የምናስረክብ ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን አባቶች የልማት ኮሪደር ሥራውን በመደገፍ ከጎናችን ስለቆሙም እናመሰግናለን ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ናይሮቢ ኬንያ ገብተዋል።

ጉባኤው ማኅበሩ ደጋፊዎች እና ተባባሪ አካላት በአፍሪካ የልማት የገንዘብ ድጋፍ ቀዳሚ የትኩረት መስኮችን ለማመላከት እና አፅንዖት ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል።

የገንዘብ ድጋፍ አቅራቢዎች በ21ኛው የማኅበሩ ዘመን ድጋፋቸውን ለመጨመር በፅኑ እንዲያጤኑ የማሳሰብ አላማ ያነገበም መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ድጋፍ የአፍሪካን የልማት ተግዳሮቶች እና መልካም ዕድሎች በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የሰሜን ለንደን ደርቢ በአርሰናል አሸናፊነት ተጠናቀቀ። የዋንጫው ትንቅንቅ እንደቀጠለ ነው። የመጨረሻዋን ሳቅ የሚስቀው ማነው፥ አርሰናል ወይስ ሲቲ?

#PremierLeague #Arsenal #TottenhamHotspur

Читать полностью…

EthioTube

በናይጀሪያ ከባድ ዝናብ ባደረሰው ጉዳት ምክንያት ከ100 በላይ እስረኞች አመለጡ።

ባለፈው ረቡዕ ሌሊት የጣለው ከባድ ዝናብ በናይጀሪያ ዋና ከተማ አቅሪቢያ በሚገኘው የሱሌጃ እርስር ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ቢያንስ 118 እስረኞች ማምለጣቸውን የእስር ቤት አገልግሎት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ አዳሙ ዱዛ ሀሙስ እለት ባወጡት መግለጫ ለበርካታ ሰአታት የቆየው ከባድ ዝናብ ግርግዳውን እና በዙሪያው ያለውን ግንብ ጨምሮ የውስጠኛውን የእስርቤት ክፍል አፈራርሶታል ብለዋል።

የእስር ቤት አገልግሎቱ ከእስር ያለመጡትን እየፈለገ ሲሆን እስካሁን በሌሎች የጸጥታ አካላት ትብብር 10ሩ ተይዘዋል ተብሏል። 
ዱዛ "ያለመጡጥን ለመያዝ በእልህ እያሳደድን ነው" ብለዋል።

ያመለጡትን ለመያዝ መንግስት ከፍተኛ ክትትል እያደረገ ነው ያሉት ዱዛ ህዝቡ በፍለጋው እንዲተባበር እና አጠራጣሪ ነገሮችን ሲያይ በአቅራቢያው ላለ የጸጥታ አካል እንዲጠቁም ጠይቀዋል።

እስርቤቶች በተጨናነቁባት እና ልል የሆነ ጸጥታ ሁኔታ ባለባት ናይጀሪያ፣ እስርቤትን ሰብሮ ማምለጥ ዋና የጸጥታ ስጋት እየሆነ መጥቷል።

በቅርብ አመታት ውስጥ በደካማ መሰረተ ልማት እና በታጣቂዎች ጥቃት ምክንያት በሽዎች የሚቆጠሩ እስረኞች አምልጠዋል።

አይኤስ በ2022 ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት እስርቤት ላይ በፈጸመው ጥቃት 440 እስረኞች ነጻ መውጣታቸው በጉልህ የሚጠቀስ ነው።

እስር ቤቶቹ በቅኝ ግዛት ዘመን የተገነቡ በመሆናቸው ማርጀታቸውን እና ደካማ መሆናቸውን የገለጹት ቃል አቀባዩ እያንዳንዳቸው ሶስት ሺህ መያዝ የሚችሉ ስድስት እስርቤቶች ግንባታን ጨምሮ እስርቤቶችን ለማዘመን ጥድፊያ ላይ ነን ብለዋል።

Читать полностью…

EthioTube

የኤርትራ ጦር  ከዛላንበሳና አጎራባች ወረዳዎች ሰዎችን አግቶ እየወሰደ ነው ተባለ

የዛላ  አንበሳ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ በርሄ እንደተናገሩት ከምስራቃዊ ዞን  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ታግተዉ ተወስደዋል  ብለዋል፡፡

ከዛላ አንበሳ 26 ሰዎች፣ ከጉለም ወረዳ  50  እንዲሁም ከኢሮፕ 28 ሰው በኤርትራ ሰራዊት እንደተወሰደ  ገልፀው በዚህ ሳምንት ደግሞ ቁጥሩ መጨመሩን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ዛላንበሳ ከተማን ጨምሮ  ምስራቃዊው ዞን ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ማህብረሰቡም  ብዙ በደል እና ጥቃት እየደረሰበት ነዉ ብለዋል፡፡

የኤርትራ ጦር  የአካባቢዉን ነዋሪዎቹ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት  ኤርትራዊ እንደሆኑ በመግለጽ  በኃይል  እንደተቆጣጠረም ተሰምቷል፡፡

የፌድራል መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠንም የሚሉት አቶ ብርሀነ ዳግም ጦርነት አንፈልግም ግን ደግሞ ማንነታችንን እና ህልውናችንን ሊያስከብርልን ይገባል ብወዋል።

በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በጦሩ  ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ተነስቶ  በከተማው እንዲሁም በአካባቢው ያለው ነዋሪ ለከፋ ችግር እንደተጋለጠም ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ30ሺ በላይ ነዋሪ ተፈናቅሎ በመቀሌ፤ በአዲግራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኝ አቶ ብርሀነ ነግረውኛል ሲል የዘገበው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107·8 ነው፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተገለጸ

ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል።

ይሁን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መሆኑ ተመልካቷል።

በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል። 

እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - ሚያዝያ 18 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 24, 2024

👉አሜሪካ ህጉን በፕሬዝዳንቷ በኩል አጽድቃዋለች
👉የኢትዮጵያ የኦዲት ተቆጣጣሪ ማንነት ግልጽ አይደለም ተባለ
👉የሱዳን ተፋላሚዎች ዛሬም ያረገበ ጦርነት

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/Xt8d1ZTx9TE

Читать полностью…

EthioTube

የሱዳን ጦር በዋና የጦር ማዘዣው ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ድሮኖችን መትቶ መጣሉን ገልጿል

የሱዳን ጦር በዛሬዉ እለት በሸዲ በሚገኘው ዋና የጦር ማዘዣው ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ድሮኖችን በጸረ-ጄት ሚሳይሎች መትቶ መጣሉን ሮይተርስ የአይን እማኞችን እና ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

የጦር ማዘዣው ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ቢሰነዘርበትም፣ የትኛውም ድሮን ኢላማውን መምታት እንዳልቻለ የሱዳን ጦር ምንጮች መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

የሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል አብደል ፋታህ አልቡርሃን ከካርቱም በሰሜን አቅጣጫ 180 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሸዲ ሰኞ እለት መድረሳቸውን የሱዳን ጦር ሚዲያዎች ዘግበው ነበር።

ጀነራሉ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በሸዲ ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር የለም።
የሱዳን ጦር ሰፊዋን የሰሜን አፍሪካ ሀገር ለመቆጣጠር ከተቀናቃኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር እየተዋጋ ይገኛል።

የማክሰኞው የድሮን ጥቃት በጦሩ ቁጥጥር ስር ባሉ ቦታዎች ላይ ሲደረግ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ተብሏል። የአትባራ ከተማ፣ የናይል ወንዝ ግዛት እና በምስራው የምትገኘው የገዳሪፍ ግዛት የድሮን ጥቃት ደርሶባቸዋል።

ከተቀሰቀሰ አንድ አመት በሆነው ጦርነት ውስጥ ሁለቱም ተፋላሚዎች ድሮን እየተጠቀሙ ናቸው።

አብዛኛውን የካርቱም ከተማ እና የሀገሪቱን ምዕራባዊ ክፍል የተቆጣጠረው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር ለእነዚህ ጥቃቶች ኃላፊት አልወሰደም።

አጋር በነበሩት የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን በሚመሩት ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ መካከል የተፈጠረው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን እንዲገደሉ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።

አል አይን

Читать полностью…

EthioTube

ዛሬ የብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ፤ በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከሩን አሳውቋል።

ይህ ተከትሎ ዘለግ ያለ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫ ፦
- ስለ ሀገራዊ ምክክር
- ስለ ሽግግር ፍትሕ
- ከመንግሥት ውጭ ታጥቀው ስለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች
- ስለ ተሃድሶ ኮሚሽን
- ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት
- ስለ ህወሓት ታጣቂዎች
- ስለ ተፈናቃዮች መመለስ

... ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተውበታል።

ምክር ቤቱ፥ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሀገረዊ ምክክር ኮሚሽን በክልል ደረጃ የምክክር መድረኮችን ማካሄድ ይጀምራል ብሏል።

ሀገራዊው የምክክር ጉባኤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ተስፋ ይደረጋል ሲል ገልጿል።

ም/ቤቱ፤ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ መፅደቁን አስታውሷል።

እንደ አግባብነቱ፦
° የወንጀል ምርመራ እና ክስ
° እውነት ማፈላለግ
° ዕርቅ
° በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት
° ማካካሻ እና ተቋማዊ ማሻሻያ እንደ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች በሀገራችን ተግባራዊ ይደረጋሉ ብሏል።

" የመንግሥት አንዱ መብት በብቸኝነት ኃይልን መጠቀም " መሆኑን ገልጾ በሀገራችን በተወረሰ የፖለቲካ ስብራት የተነሣ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋል ብሏል።

የሀገሪቱን ሰላም የጸና ለማድረግ፣ እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተው፣ የተሐድሶ ሂደት ውስጥ መቀላቀል አለባቸው ብሏል። " የፖለቲካ ጥያቄዎቻቸውንም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በመሳተፍ መፍታት ይችላሉ " ሲል ገልጿል።

ለዚህም የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል። ዓላማውም፦
° መሣሪያ ማስፈታት
° የትጥቅ ቡድኖችን ሰላማዊ ማድረግና ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ነው ብሏል።

መንግሥት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አተገባበር ከሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጋር የተናበበና የሚመጋገብ እንዲሆን ኃላፊነቱን ይወጣል ብሏል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ጦርነትን በፖለቲካዊ መፍትሔ የመቋጨት ባህል አምጥቷል ሲል ገልጿል።

የሰላም ስምምነቱ ለትውልድ የአሸናፊ ተሸናፊ ትርክትን ከቂም ጋር ላለማውረስ የተደረገ ውሳኔ እንደሆነ ገልጿል።

የሰላም ስምምነቱ እስካሁን ብዙ ውጤት እና እፎይታ ቢያስገኝም ቀሪ ሥራዎችም አሉ ብሏል።

በተለይ በስምምነቱ መሠረት " የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው " ሲል ገልጿል።

የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት ብሏል።

" ካለፈ ስሕተተ አለመማር የመጀመሪያውን ስሕተት ከመሥራት የባሰ ነው " ያለው ም/ቤቱ ፤ ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉ አሉ ሲል ጠቁሟል።

እነዚህን ሁሉም ተባብሮ አደብ ማስገዛት ይኖርበታል ብሏል።

" ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት ሕግ የማስከበር ሥራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባል" ሲል አሳስቧል።

ም/ ቤቱ ፤ መንግሥት በትግራይ ክልል አልፎ ቁስልን ለመሻር የሚያስችል ሥራ እየሠራ እንደሆነ ገልጿል።

" ይሄ ግን መንግሥታዊ ኃላፊነት እንጂ ፍርሃት ተደርጎ መወሰድ የለበትም " ብሏል።

" በፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነትና በሕገ መንግሥቱ መሰረት እንደ ሀገር የሚኖረው አንድ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ ነው ክልሎች በክልል ከፖሊስ እና ሚሊሺያ ያለፈ የታጠቀና የተደራጀ ሠራዊት ሊኖራቸው አይችልም፤ አይገባምም " ብሏል።

በዚህ መሠረት ትጥቅ መፍታትና ተያያዥ ሂደቶች በተሐድሶ ኮሚሽኑ ዕቅድ መሠረት በፍጥነት ሊተገበሩ እንደሚገባ አሳስቧል።

ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

የግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ ከሳሃራ በረሃ በተነሳ ብርቱካናማ አቧራ መሸፈኗ ተሰማ

ከሰሃራ በረሃ የተነሳ አቧራ ብርቱካናማ ጭጋግ በአቴንስ ከተማ ላይ መሸፈኑ ተሰምቷል።

ከ 2018 ጀምሮ በግሪክ ከተከሰቱት በጣም አስከፊ ክስተቶች መካከል አንዱ መሆኑን የመንግስት ባለስልጣናት ገልፀዋል። በመጋቢት ወር መጨረሻ እና በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ግሪክ በተመሳሳይ ጭጋግ ተሸፍና ነበር ፤ በተመሳሳይ የስዊዘርላንድ እና የደቡብ ፈረንሳይ አካባቢዎችን ይሸፍኑ ነበር።

የግሪክ የአየር ሁኔታ አገልግሎት እስከ ሩዕቡ ምሽት ሰማዩ ይጸዳል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል። በበርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች የአየር ጥራት ብክለት የተመዘገበ ሲሆን እሮብ ጠዋት በአቴንስ የከተማዋ ምልክት የሆነው አክሮፖሊስ በአቧራ ምክንያት አይታይም ነበር። ደመናው እስከ ተሰሎንቄ በስተሰሜን ክፍል ድረስ ሸፍኗል።

የአተነፋፈስ ችግር ያለባቸው ግሪካውያን ከቤት ውጭ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲገድቡ፣የመከላከያ ጭንብል እንዲጠቀሙ እና አቧራው እስኪያጠራ ድረስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከማድረግ እንዲቆጠቡ የመንግስት ባለስልጣናት አሳስበዋል። የሰሃራ በረዓ በዓመት ከ60 እስከ 200 ሚሊዮን ቶን የማዕድን አቧራ ይለቃል።

አብዛኛው አቧራ በፍጥነት ወደ ምድር ይመለሳል። ነገር ግን አንዳንድ ጥቃቅን ቅንጣቶች ብዙ ርቀት ሊጓዙ የሚችሉ ሲሆን አንዳንዴም አውሮፓ ይደርሳሉ። በተለይ በደቡባዊ ግሪክ ያለው ከባቢ አየር ከአቧራ እና ከከፍተኛ የሙቀት መጠን ጋር ይመዘገብበታል። የሜትሮሎጂ ባለሙያው ኮስታስ ላጎውቫርዶስ የአየር ሁኔታውን ከማርስ ፕላኔት ጋር አወዳድሮታል።

የእሳት አደጋ መከላከያ አገልግሎት እንዳስታወቀ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 25 ሰደድ እሳት ተፈጥሯል።አንድ የእሳት አደጋ በቀርጤስ ደሴት የባህር ኃይል ሰፈር አቅራቢያ ያጋጠመ ሲሆን የሙቀት መጠኑ ከ 30 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ከፍ ብሏል ።ነዋሪዎች ከቤታቸው ለቀው እንዲወጡ መደረጉን የአካባቢው ዘገባዎች ያመላክታሉ።

Читать полностью…

EthioTube

ቀሲስ በላይ መኮንን ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ! የ8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ተፈቀደ።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ የ3 ግለሰቦችን ጊዜ ቀጠሮ መዝገብን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልክቷል።

ቀሲስ በላይ ከአንድ ሳምንት በፊት በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሂሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ለማዘዋወር ለባንኩ ጥያቄ በመቅረቡና የያዙት የክፍያ ሰነድ ሀሰተኛ መሆኑ መረጋገጡን ተከትሎ በአፍሪካ ህብረት የጥበቃ ሃይሎች ተይዘው ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ በፍርድ ቤት በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ለ7 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ሲከናወንባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱ በቀሲስ በላይ መኮንን፣ ያሬድ ፍስሃ እና ጣባ ገናና በተባሉ 3 ተጠርጣሪዎች ላይ ለምርመራ ማጣሪያ ለፖሊስ በሰጠው 7 ቀን የምርመራ ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ ስራዎችን ተመልክቷል፡፡

መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው የ7 ቀን ጊዜ ውስጥ የምስክሮችን ቃል መቀበሉን፣ በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለሚመለከተው ተቋም መጠየቁን፣ የቴክኒክ ምርመራ እንዲሰጠው በደብዳቤ መጠየቁን፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለአፍሪካ ህብረት የሰነድ ማስረጃዎች እንዲሰጠው መጠየቁን፣ ተጠርጣሪዎቹ በስማቸው የሚገኙ ሂሳቦችን ለማጣራት ማረጋገጫ እንዲሰጠው በደብዳቤ መጠየቁን፣ በወቅቱ የነበረ የካሜራ ቅጂ መጠየቁን፣ ለወንጀል ተግባር የዋለ ተሽከርካሪ ማረጋገጫ ከሚመለከተው ተቋም መጠየቁን፣ በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ብርበራ ማድረጉንና በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ  እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ቀረኝ ያላቸውን ስራዎችን ማለትም ከተለያዩ ተቋማት የሰነድ ማስረጃ መሰብሰብ፣ ተጨማሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል፣ ግብረአበሮችን ተከታትሎ መያዝ፣ ተጨማሪ ሀብት የማፍራት ተግባሮች ላይ የማጣራት ስራ መስራት እንደሚያስፈልገው እና በተቀናጀና በቡድን የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት ጥላሸት የሚቀባ ተግባር መሆኑን ጠቅሶ ምርመራውን በተጠናከረ መንገድ በስፋት ለማከናወን ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጾ መርማሪ ፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

ተጠርጣሪው ቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ ሌሎቹም ተጠርጣሪዎች በ6 ጠበቆች ተወክለው ችሎት የቀረቡ ሲሆን÷ ጠበቆቻቸው ፖሊስ ያቀረበው ጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ምክንያቶች ደንበኞቻቸውን ተጨማሪ በእስር ለማቆየት የሚያስችል አይደለም በማለት ተከራክረዋል።

በደንበኛቸው ቀሲስ በላይ የተገኘው የጦር መሳሪያ ህጋዊ መሆኑን በመጥቀስ ሀብት ማፍራት ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር ሊገናኝ አይገባም በማለት የመከራከሪያ ነጥብ አንስተዋል።

የሃይማኖት አባት መሆናቸውን፣ የልማት ስራ አስተባባሪ በመሆናቸውና ቋሚ አድራሻ እንዳላቸው በመጥቀስ ቢወጡ ከመንግስት ተቋማት የሚመጡ ማስረጃዎችን የማጥፋት አቅም የላቸውም በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ጠበቆቻቸው በማህበራዊ ሚዲያና በመገናኛ ብዙሃን የቤተሰቦቻቸውንና የሳቸውን የከበረ ስም በሚያጎድፍ መልኩ ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ እየቀረበባቸው ነው የሚል አቤቱታም አቅርበዋል።

ቀሲስ በላይ በበኩላቸው÷ ወንጀል አለመፈጸማቸውን ገልጸው፤ ለሀገር እና ለፖሊስ ተባባሪ መሆናቸውን እንዲሁም ምሽት ላይ እቤቴ እየሄድኩ ጠዋት ልምጣላችሁ በማለት ፖሊስን መጠየቃቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል።

አብረዋቸው የታሰሩት ሹፌራቸውና አጃቢያቸው መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ምንም የወንጀል ተሳትፎ  በሌለበት ሁኔታ ላይ ከኔ ጋር ተጨማሪ ጊዜ በእስር ማቆየት ተገቢ አይደለም በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

የመርማሪ ፖሊስ በጠበቆች ለተነሱ መከራከሪያ ነጥቦች ላይ መልስ የሰጠ ሲሆን÷በዚህም ምርመራው ተጠናቋል ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ አይገባም ለሚለው የጠበቆች መከራከሪያ በሚመለከት ፖሊስ ሰፊ ምርመራ ስራ እንደሚቀረው ግብረአበሮችንም የመያዝ ስራ ገና እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ተግባሮች መኖራቸውን ጠቅሶ፤ በተደረገ ብርበራ ተጨማሪ ማስረጃ ማግኘቱንና ማስረጃውን ተከትሎ ምርመራውን እያሰፋ እንደሚያጣራ ተናግሯል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ ቢወጡ ማስረጃ ሊሰወር ይችላል በማለትም የዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

ዘገባው የፋና ነው።

Читать полностью…

EthioTube

ከየመን ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ተገልብጣ የ16 ኢትዮጵያውያን ሕይወት አለፈ

ትናንት ምሽት ከየመን የባሕር ዳርቻ ልዩ ስሙ ‘አራ’ ከተባለ ቦታ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ-ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ጎዶሪያ አካባቢ ተገልብጣ የ16 ወገኖች ሕይወት አለፈ፡፡

እንዲሁም አብረው በጀልባዋ ተሳፍረው የነበሩ 28 ኢትዮጵያውያን እስካሁን አለመገኘታቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል 33 ፍልሰተኞች በሕይወት ተርፈው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኤምባሲው የተሰማውን ሐዘን ገልጾ÷ ከጂቡቲ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የሚደረጉ ሕገ-ወጥ ጉዞዎች እጅግ አደገኛ ከመሆናቸውም በላይ በየጊዜው የዜጎችን ሕይወት እያሳጡ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ዜጎቻችን በሕገ-ወጥ ደላሎች የሐሰት ስብከት በመታለል ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ሲል አሳስቧል፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ተባለ

ሕወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገ – ወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑን  ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች አሰባስቤ ሰራሁት ያለችዉ ዘገባ ያመለክታል። ከሁለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፈረመው ሕወሓት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን ብልፅግናን በመቀላቀል በሀገራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት መስማማቱን ቢገልፅም ፓርቲውን ለመቀላቀል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።

ከብልፅግና በፊት የነበረው ኢሕአዴግ እኩል የስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውክልና ያላቸው አራት ንዑስ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሆን ብልፅግና ግን አንድ ወጥ ፓርቲ ነው። የብልፅግና የፓርቲ ውክልና በህዝብ ብዛት የሚወሰን እንጂ እንደ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እኩል ውክልና አይኖራቸውም።

አሁንስ እየተደረገባቸው ባለው ድርድር ሕወሓት የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-ደንብ ተሻሽሎ በፓርቲ ውስጥ አባል ድርጅቶች እኩል የማዕከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ ውክልና እንዲኖራቸው ይፈልጋል።

ብልፅግና ግን ሕወሓት የተናጠል ህልውናውን አክስሞ ብልፅግናን እንዲቀላቀልና ውክልናውም በትግራይ ህዝብ ቁጥር ልክ የሚወሰን መሆኑን ይገልፃል።

የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር የጀመሩት ሲሆን ከሁለት ሳምንት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው በጉዳዩ ላይ በስፋት ተነጋግረዋል።

በሕወኋት በኩል ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው …አስፈላጊም አይደለም” ብለው የሚያምኑ አመራሮች ቢኖሩም ፣ ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው፣ በተለይም የትግራይን ፀጥታና ደህንነት ለመስጠበቅ ከብልፅግና ጋር አብሮ መቆም አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑም አሉ።

Via ዋዜማ

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

አቶ መልካሙ ፀጋዬ በአቶ ጣሂር መሀመድ ምትክ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾሙ

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ፥" ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራር የሆኑትን አቶ መልካሙ ፀጋዬ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በማድረግ ሹመዋል " ሲል አሳውቋል።

በዚህ ኃላፊነት ቦታ የነበሩት አቶ ጣሂር መሃመድ ከቦታው ተነስተዋል። ለምን በእሳቸው ምትክ ሌላ አዲስ ሰው እንደተሾመ / ከቦታው እንደተነሱ ፣ ለሌላ ሹመት እና ኃላፊነት ታጭተው እንደሆነ በግልጽ የተባለ ነገር የለም።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በኬንያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ በምትገኝ አንዲት ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ግድብ ተንዶ በትንሹ የ42 ሰዎች ህይወት አለፈ

ኃይለኛ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ለግድቡ መናድ ምክንያት ሲሆን በርካታ ቤቶችን ጠራርጎ መውሰዱን የአካባቢው ባለስልጣናት ዐስታውቀዋል።

በአደጋው በርካታ መንገዶች ተቆራርጠዋል፤ በህይወት የተረፉ ሰዎች ከተገኙ በሚልም የህይወት አድን ሰራተኞች በአካባቢው መሰማራታቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የኑኩሩ ግዛት አስተዳዳሪ ሱዛን ኪሂካ እንዳሉት  42 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል።

ነገር ግን አሁንም ድረስ በደለል ተውጠው ገና ያልተገኙ በርካታ ሰዎች በመኖራቸው የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ሊያሻቅብ ይችላል።

ኤል ኒኖ ያስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ በኬንያ በዚህ ዓመት በመጋቢት እና ሚያዝያ ወራት ከተለመደው የዝናብ መጠን በላይ እንዲዘንብ አስገድዷል። ኃይለኛ ዝናብ ባስተናገዱ አካባቢዎች በተከሰቱ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋዎች የሟቾችን ቁጥር ከ140 በላይ አድርሷል፤ ከ130 ሺ በላይ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል።

የጎርፍ መጥለቅለቁ በበርካታ አካባቢዎች መንገዶችን ጨምሮ በመሰረተ ልማቶች ላይም ብርቱ ጉዳት ማድረሱን ነው ዘገባው ያመለከተው። ይህንኑ ተከትሎ በእረፍት ላይ የነበሩ ትምህርት ቤቶች መከፈት ከሚገባቸው ቀን እንዲያስተላልፉ የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

Читать полностью…

EthioTube

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት የኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን አሳወቀ

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት በኅብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

በዚህም የህብረቱ ለአባል ሃገራት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ

- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ ተጠቁሟል።

- አባል ሀገራት ከአሁን በኋላ ከሁለት ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉም ተገልጿል።

- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛውን የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱም ተነግሯል።

በተጨማሪም፣ መደበኛው ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ተቀይሯል።

ይህ ውሳኔ የተወሰነው የህብረቱ ምክር ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት የሚቆዩ ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸውን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ሕብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት መለየቱ ተገልጿል፡፡

ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈቱ ፕላኑን የጠበቁ ዘላቂ የመፍትሄ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ጥሪ መቅረቡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

https://youtu.be/6oUKr0qE0Wc

Читать полностью…

EthioTube

ፑላ አድቫይዘርስ ለ 122 ሺህ አርሶአደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድህን ካሳ ክፍያ ፈፀመ

በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ፣ በአለም ምግብ ፕሮግራም እና በፑላ አድቫይዘር ጥምረት በኢትዮጵያ ትልቁን የሰብል መድህን ፕሮግራም የክፍያ ስርአት በትናንትናው እለት በሀያት ሪጀንሲ የጀመሪያውን ፕሮግራም አከናውኗል።

በኢትዮጵያ የሰብል መድህን ታሪክ ዉስጥ ትልቁ መሆኑ በተነገረለት ይህ ፕሮግራም የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ ለዚህ ፕሮግራም የመድህን ውል ሰጪ እና የካሳ ከፋይ ተቋም በመሆን አገልግሏል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ በተገለጸው በዚህ ስርዓት እንደመጀመሪያ በአማራ ክልል የሚገኙ አነስተኛ አርሶአደሮች ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን በቀጣይ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ለ 7.5 ሚሊዮን አርሶአደሮች ተደራሽ እንደሚሆንም ከፕሮግራሙ ለመረዳት ችለናል።

በመጨረሻም የመድህን ካሳ ክፍያ ቼክ አርሶ አደሮችን በመወከል ለተገኙ አርሷደሮን እና ለአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ተበርክቷል።

Читать полностью…

EthioTube

አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት' ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡

አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል።ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - ሚያዝያ 18 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 24, 2024

👉አሜሪካ ህጉን በፕሬዝዳንቷ በኩል አጽድቃዋለች
👉የኢትዮጵያ የኦዲት ተቆጣጣሪ ማንነት ግልጽ አይደለም ተባለ
👉የሱዳን ተፋላሚዎች ዛሬም ያረገበ ጦርነት
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/Xt8d1ZTx9TE

Читать полностью…

EthioTube

ፀድቋል

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቲክቶክ ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።

የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም ፣ ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን ፣ ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቶክ ከአሜሪካ እንዲሁም ከአውሮፓ ሀገራት ከካምፓኒዎች በሚያገኘው ገቢ ውጤታማ ሆኖ እራሱን እያሻሻለ እዚህ የደረሰ  ቢሆንም የቲክቶክ ባለቤት ለአሜሪካ ባለሀብቶች ቲክቶክን ለአሜሪካ አሳልፎ የማይሸጥ ከሆነ በአሜሪካ ሙሉ ለሙሉ መታገዱ አይቀርም ነው የተባለው።

ይህ ከሆነ ደግሞ ቲክቶክ ከአሜሪካ ካምፓኒዎች የሚያገኘውን የማስታወቂያ ገቢ ስለሚያጣ ኪሳራ ሊያጋጥመው ስለሚችል ቲክቶክ አደጋ ውስጥ መውደቁ አይቀሬ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ የአውሮፓ ሀገራትም ቲክቶክን ለመዝጋት እየተዘጋጁ ያሉም ስለመኖራቸው ተሰምቷል።

ከኬንያ እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ ጥቂት ካምፓኒዎች በስተቀር ቲክቶክ ከአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከማስታወቂያ ምንም የሚያገኘው ጥቅም የለም።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላትና ለእርሱም እየሰራች ነዉ ተባለ

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ተናግረዋል ።

የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ 2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ምን ያህል ዝግጁ ናት የሚለዉ ግን አጠያያቂ ነዉ።

Читать полностью…

EthioTube

"የሚሊሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት" አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተላለፈ ያለው መልዕክት ሀሰተኛ ነው" :- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት 

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት አወጣ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲተላለፍ የነበረው "የሚሊሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት" የተመለከተ ደብዳቤ በሐሰት የተቀናበረ መሆኑን የአማራ ክልል አስታውቋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ተጻፈ የተባለው ደብዳቤ ከመስሪያ ቤታቸው የወጣ አለመሆኑን እና የተቀነባበረ መሆኑን ገልጸዋል።

ክልሉ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የሚሊሻ ኃይሉን የማጠናከር ስራን እየሰራ ይገኛል ያሉት ሃላፊው፤ የርዕሰ መስተዳድሩን ጽ/ቤት የደብዳቤው ይዘትም ሆነ ቅርጽ ሀሰተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

Читать полностью…

EthioTube

የአሜሪካ ሴኔት በመላው አሜሪካ " ቲክቶክ" ን ሊያግድ የሚችል አዋጅ ትላንት ለሊት አጽድቋል።

ከቀናት በፊት የተወካዮች ምክር ቤት " ቲክቶክ " እንዲታገድ ረቂቅ ሕግ ማጽደቁ ይታወሳል።

ትላንት ለሊት የአሜሪካ ሴኔት ተሰብስቦ " ቲክቶክ " ከቻይና ካልተፋትና ድርሻው በ9 ወር ውስጥ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ አሜሪካ ውስጥ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚያግድ አዋጅ አጽድቋል።

ቀጣዩ ሂደት ፕሬዜዳንቱን ይመለከታል።

ይህ አዋጅ ወደ ፕሬዝዳንት ጆ  ባይደን የተመራ ሲሆን እሳቸው ቀደም ሲል " ይህ አዋጅ እኔ ጋር ይድረስ እንጂ ፊርማዬን አኑሬበት ሕግ ሆኖ ይተገበራል " ብለው ነበር።

አሁን አሜሪካ ውስጥ 170 ሚሊዮ ተጠቃሚዎች ያሉት " ቲክቶክ " የመታገዱ ነገር እውን እየሆነ የመጣ ሲሆን ሂደቱ ረጅም ወራትን ሊወስድ ይችላል።

በሌላ በኩል ፥ ሴኔቱ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅል አፅድቆታል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ማክሰኞ የኢት ዜና - ሚያዝያ 15 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 23, 2024

👉ህውሃትና ብልጽግና ሊቀላቀሉ ነው
👉ደቡብ ጎንደርና ኮሬ በርካታ ንፁሃን ተገደሉ
👉ታይዋን በድጋሚ በተከታታይ ከባድ ርዕደ መሬት ተመታች
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/-n8gduhYVdE

Читать полностью…

EthioTube

ታይዋን በድጋሚ በተከታታይ ከባድ ርዕደ መሬት ተመታች


ታይዋን 17 ሰዎችን ለህልፈት ከዳረገው ርዕደ መሬት አደጋ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ በድጋሚ ለሰዓታት ከባድ በሆነ ተከታታይ ርዕደ መሬት መመታቷ ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 5 ሆኖ የተመዘገበ ሰኞ ምሽት በደሴቲቱ ምስራቃዊ ሁዋሊን ግዛት የደረሰውን ርዕደ መሬት ተከትሎ አነስተኛ መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተመላክቷል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 0 እንዲሁም 6 ነጥብ 3 ሆነው የተመዘገቡ የርዕደ መሬት አደጋዎች መከሰታቸውን የደሴቲቱ የአየር ሁኔታ አስተዳደር የርዕደ መሬት ማዕከል አስታውቋል፡፡

በፈረንጆቹ ሚያዝያ 3 በደረሰው ርዕደ መሬት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሕንፃዎችም ከዛሬ ጠዋቱ ክሰተት በኋላ በከፊል መውደቃቸውን የሁዋሊን ግዛት ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የማዕከላዊ የአየር ንብረት አስተዳደር የርዕደ መሬት ማዕከል በአደጋው የተጎዱ ሰዎች እንደሌሉና በሁዋሊን ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ እንደተላለፈ ማስታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡

ቀደም ሲል የደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ በታይዋን ከ25 ዓመታት በፊት በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 ሆኖ ከተመዘገበውና 2 ሺህ 400 ሰዎችን ለህልፈት በመዳረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ህንፃዎችን ካወደመው ርዕደ መሬት በኋላ ከባዱ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ከአላማጣ እና የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን ተመድ አስታወቀ

ግጭት ከተነሳባቸው የአላማጣ ከተማ፣ ዛታ እና ኦፍላ የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ተፈናቃዮቹ የተጠለሉባቸውን የዞን ባለሥልጣናት ዋቢ አድርጎ ጽህፈት ቤቱ ሰኞ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት መሠረት ከተፈናቃዮቹ መካከል 42 ሺህ የሚሆኑ በሰሜን ወሎ በምትገኘው ቆቦ ከተማ እንዲሁም 8300 የሚሆኑት ደግሞ በሰቆጣ እና ዋግ ኽምራ ዞኖች ተጠልለዋል ብሏል።

በአብዛኛው ሴቶች፣ ህጻናት፣ ታዳጊዎች እና አረጋውያንን ያሉበት ተፈናቃዮች በማኅበረሰቡ ባሉ ቤቶች ለመጠለል እየሞከሩ እንደሆነ ገልጾ፣ ሌሎች ደግሞ ከቆቦ ከተማ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኝ ጋራ ሌንጫ በተሰኘው የኢንዱስትሪ መንደር ክፍት ቦታ ላይ ተጠልለው ይገኛሉ ተብሏል።

በዚህ ስፍራ የተጠለሉ ተፈናቃዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ለበልግ ዝናብ መጋለጣቸውን የጠቀሰው የመንግሥታቱ ድርጅት መግለጫ የተወሰኑትን ተፈናቃዮች ወደ ሌላ ስፍራ ለማዘዋወር እየተሞከረ እንደሆነ መሬት ላይ ያሉ አጋሮቹን ዋቢ አድርጓል ጠቅሷል።

የፌደራል ኃይሎች ጣልቃ መግባታቸውን ተከትሎ በአላማጣ፣ ወልዲያ እና ቆቦ ከተሞች አካባቢ ከትናንትና ሚያዝያ 14/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የፀጥታው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑም ተገልጿል።

ከአላማጣ ወደ ቆቦ የሚወስደው እንዲሁም ከአላማጣ ወደ ማይጨው የሚወስዱ መንገዶች ለትራንስፖርት ክፍት መሆናቸውን እንዲሁም ባንክን የመሳሰሉ ሕዝባዊ አገልግሎቶች እንደገና ሥራ መጀመራቸው ተጠቁሟል።

በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ወደ አማራ ክልል እንዲጠቃለሉ በተደረጉ የአላማጣ ከተማ እና ራያ ወረዳዎች እንደ አዲስ የተቀሰቀውን ግጭት ተከትሎ በአዲስ አበባ መቀመጫቸውን ያደረጉ የካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካ ኤምባሲዎች ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ አቅርበዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…
Subscribe to a channel