ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ምጥ ይዟት ወደ ሆስፒታል እየሄዱ የነበሩ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና አንድ ጎረቤትን ጨምሮ የ4 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከል መረጃና ስታቲክስ ክፍል ኃረፊ ኢንስፔክተር ታምራት ደሳለኝ  እንደገለፁት በሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ አስተዳደር ማዞሪያ ቀበሌ ሌሊት 11 ሰዓት 40 ከወላይታ ሶዶ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ፒካፕ መኪና በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዝ ባለሶስት እግር ባጃጅ ጋር ተጋጭቶ በውስጡ የነበሩ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት እና አንድ ጎረቤት በድምሩ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል።

በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።

ከሟቾቹ መካከል ምጥ ይዟት ወደ ሆስፒታል እያመራች የነበረች እናት እንደምትገኝበት ነው ኢንስፔክተር ታምራት የገለጹት። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም ኢንፔክተር ታምራት ጠቁመዋል።

Читать полностью…

EthioTube

የማህበረ ቅደሳን ኃላፊዎች ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት ተወሰዱ

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን ማህበረ ቅዱሳን ሚዲያ ገልጿል።

የሁለቱ አገልጋዮች መኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት አልታወቀም።

Читать полностью…

EthioTube

"በምዕራብ እና በሰሜን ትግራይ እንዲሁም ጸለምቲ የሚገኘው ሕገ ወጥ አስተዳደር እስከ ሰኔ 30 ድረስ ይፈርሳል"- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

"በምዕራብ ትግራይ" የሚገኘውን "ሕገ ወጥ" አስተዳደር የመበተን ስራ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 እንደሚያልቅ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ገለጹ።

ከሁለት ሳምንታት በፊት የጊዜያዊ አስተዳደሩ "በምዕራብ ትግራይ በፀለምቲ አካባቢ እና በደቡብ ትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች በአማራ ታጣቂዎች የተቋቋሙትን አስተዳደሮች ለማፍረስ" ከፌዴራል መንግስት ጋር መስማማታቸውን ገልፀው ነበር።

በትላንትናው ዕለት ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተሰጠው መግለጫ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ አስተዳደሮች "ከሰሜን ትግራይ ዞንና ጸለምቲ" አካባቢዎች እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ እንዲሁም "የምዕራብ ትግራይ" ቦታዎች ላይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ድረስ "በስምምነቱ መሰረት" ይፈርሳሉ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ባወጣው መግለጫ ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) “የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል” ማለቱ አይዘነጋም።

አዲስ ማለዳ

በዚሁ መግለጫ በእነዚህ አካባቢዎች ላይ የሚገኘው የክልሉ መንግስት መዋቅር የተቋቋመው "ህወሓት በለኮሰው" ጦርነት ሳቢያ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄያቸውን "በድል" ያገኙት መሆኑ ተገልጿል።

Читать полностью…

EthioTube

ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ እየተገኘ ነው ተባለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከዚህ ቀደም ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩና ሌሎች ወጣቶች በ2 ማኅበር ተደራጅተው በጀመሩት የዓሳ ማስገር ስራ ከህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ እየተገኘ መሆኑ ተገለፀ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ግድቡ ውሀ መያዝ ከጀመረ ወዲህ በተለይም ለዓሳ ምርት ምቹ መሆኑ ሲገር በ8 ወራት ውስጥ 1729 ቶን ዓሳ ምርት ከህዳሴ ግድብ መገኘቱን ዶይቼ ቨለ በዘገባው አመልክቷል።

ወጣቶቹ የተደራጁበት ማህበርም 56 የሚደርሱ ወጣቶችን ያቀፈ ሲሆን በግደቡ ዳርቻ በሚሰሩት የዓሳ ማስገር ስራ በቀን ከ2 እስከ 3 ኩንታል ዓሳ እንደሚኝና በአካባቢው የዓሳ ማስገር ስራውን በማህበሰረብ አቀም ለማድረግና ለማሻሻል ዘመናዊ ጅልባዎች ያስፈልጋሉ ተብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደርን አሰናበቱ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዡዩአንን አሰናብቷል።

በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

ኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ቻይና ያደረገችው ድጋፍ የሁለቱ አገራት የረዥም ዘመን ጠንካራ ወዳጅነት ሌላኛው ማሳያ ነው ያሉት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፣ በአምባሳደሩ የስራ ቆይታ ወቅት በቻይና መንግስት ድጋፍ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ መጠናቀቃቸውን አስታውሰዋል።

በሁለቱ አገራት ያለው ትብብር በወቅቶች የማይቀያየር ስትራቴጂዊ አጋራነት ደረጃ ላይ መድረሱ የሀገራቱ ግንኙነት ጠንካራና አርአያነት ያለው መሆኑን እንደሚያረጋጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

አቶ መልካሙ ፀጋዬ በአቶ ጣሂር መሀመድ ምትክ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾሙ

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ፥" ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራር የሆኑትን አቶ መልካሙ ፀጋዬ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በማድረግ ሹመዋል " ሲል አሳውቋል።

በዚህ ኃላፊነት ቦታ የነበሩት አቶ ጣሂር መሃመድ ከቦታው ተነስተዋል። ለምን በእሳቸው ምትክ ሌላ አዲስ ሰው እንደተሾመ / ከቦታው እንደተነሱ ፣ ለሌላ ሹመት እና ኃላፊነት ታጭተው እንደሆነ በግልጽ የተባለ ነገር የለም።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በኬንያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ በምትገኝ አንዲት ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ግድብ ተንዶ በትንሹ የ42 ሰዎች ህይወት አለፈ

ኃይለኛ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ለግድቡ መናድ ምክንያት ሲሆን በርካታ ቤቶችን ጠራርጎ መውሰዱን የአካባቢው ባለስልጣናት ዐስታውቀዋል።

በአደጋው በርካታ መንገዶች ተቆራርጠዋል፤ በህይወት የተረፉ ሰዎች ከተገኙ በሚልም የህይወት አድን ሰራተኞች በአካባቢው መሰማራታቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የኑኩሩ ግዛት አስተዳዳሪ ሱዛን ኪሂካ እንዳሉት  42 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል።

ነገር ግን አሁንም ድረስ በደለል ተውጠው ገና ያልተገኙ በርካታ ሰዎች በመኖራቸው የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ሊያሻቅብ ይችላል።

ኤል ኒኖ ያስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ በኬንያ በዚህ ዓመት በመጋቢት እና ሚያዝያ ወራት ከተለመደው የዝናብ መጠን በላይ እንዲዘንብ አስገድዷል። ኃይለኛ ዝናብ ባስተናገዱ አካባቢዎች በተከሰቱ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋዎች የሟቾችን ቁጥር ከ140 በላይ አድርሷል፤ ከ130 ሺ በላይ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል።

የጎርፍ መጥለቅለቁ በበርካታ አካባቢዎች መንገዶችን ጨምሮ በመሰረተ ልማቶች ላይም ብርቱ ጉዳት ማድረሱን ነው ዘገባው ያመለከተው። ይህንኑ ተከትሎ በእረፍት ላይ የነበሩ ትምህርት ቤቶች መከፈት ከሚገባቸው ቀን እንዲያስተላልፉ የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

Читать полностью…

EthioTube

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት የኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን አሳወቀ

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት በኅብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

በዚህም የህብረቱ ለአባል ሃገራት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ

- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ ተጠቁሟል።

- አባል ሀገራት ከአሁን በኋላ ከሁለት ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉም ተገልጿል።

- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛውን የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱም ተነግሯል።

በተጨማሪም፣ መደበኛው ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ተቀይሯል።

ይህ ውሳኔ የተወሰነው የህብረቱ ምክር ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት የሚቆዩ ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸውን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ሕብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት መለየቱ ተገልጿል፡፡

ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈቱ ፕላኑን የጠበቁ ዘላቂ የመፍትሄ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ጥሪ መቅረቡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

https://youtu.be/6oUKr0qE0Wc

Читать полностью…

EthioTube

ፑላ አድቫይዘርስ ለ 122 ሺህ አርሶአደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድህን ካሳ ክፍያ ፈፀመ

በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ፣ በአለም ምግብ ፕሮግራም እና በፑላ አድቫይዘር ጥምረት በኢትዮጵያ ትልቁን የሰብል መድህን ፕሮግራም የክፍያ ስርአት በትናንትናው እለት በሀያት ሪጀንሲ የጀመሪያውን ፕሮግራም አከናውኗል።

በኢትዮጵያ የሰብል መድህን ታሪክ ዉስጥ ትልቁ መሆኑ በተነገረለት ይህ ፕሮግራም የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ ለዚህ ፕሮግራም የመድህን ውል ሰጪ እና የካሳ ከፋይ ተቋም በመሆን አገልግሏል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ በተገለጸው በዚህ ስርዓት እንደመጀመሪያ በአማራ ክልል የሚገኙ አነስተኛ አርሶአደሮች ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን በቀጣይ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ለ 7.5 ሚሊዮን አርሶአደሮች ተደራሽ እንደሚሆንም ከፕሮግራሙ ለመረዳት ችለናል።

በመጨረሻም የመድህን ካሳ ክፍያ ቼክ አርሶ አደሮችን በመወከል ለተገኙ አርሷደሮን እና ለአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ተበርክቷል።

Читать полностью…

EthioTube

አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት' ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡

አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል።ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - ሚያዝያ 18 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 24, 2024

👉አሜሪካ ህጉን በፕሬዝዳንቷ በኩል አጽድቃዋለች
👉የኢትዮጵያ የኦዲት ተቆጣጣሪ ማንነት ግልጽ አይደለም ተባለ
👉የሱዳን ተፋላሚዎች ዛሬም ያረገበ ጦርነት
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/Xt8d1ZTx9TE

Читать полностью…

EthioTube

ፀድቋል

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቲክቶክ ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።

የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም ፣ ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን ፣ ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቶክ ከአሜሪካ እንዲሁም ከአውሮፓ ሀገራት ከካምፓኒዎች በሚያገኘው ገቢ ውጤታማ ሆኖ እራሱን እያሻሻለ እዚህ የደረሰ  ቢሆንም የቲክቶክ ባለቤት ለአሜሪካ ባለሀብቶች ቲክቶክን ለአሜሪካ አሳልፎ የማይሸጥ ከሆነ በአሜሪካ ሙሉ ለሙሉ መታገዱ አይቀርም ነው የተባለው።

ይህ ከሆነ ደግሞ ቲክቶክ ከአሜሪካ ካምፓኒዎች የሚያገኘውን የማስታወቂያ ገቢ ስለሚያጣ ኪሳራ ሊያጋጥመው ስለሚችል ቲክቶክ አደጋ ውስጥ መውደቁ አይቀሬ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ የአውሮፓ ሀገራትም ቲክቶክን ለመዝጋት እየተዘጋጁ ያሉም ስለመኖራቸው ተሰምቷል።

ከኬንያ እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ ጥቂት ካምፓኒዎች በስተቀር ቲክቶክ ከአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከማስታወቂያ ምንም የሚያገኘው ጥቅም የለም።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላትና ለእርሱም እየሰራች ነዉ ተባለ

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ተናግረዋል ።

የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ 2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ምን ያህል ዝግጁ ናት የሚለዉ ግን አጠያያቂ ነዉ።

Читать полностью…

EthioTube

ጸሎተ-ሐሙስ የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ

ዛሬ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክሃይማኖት መሪነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ።

በስነ ሥርዓቱ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ቆሞሳት ፣ ካህናትና በርካታ ምዕመናን ተገኝተው እንደነበር ከቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Photo Credit - TMC

Читать полностью…

EthioTube

ስካላይት ኢትዮጵያ ሆቴልየ ‘ገበታ ለሀገር’ ሎጆችን የማስተዳደር ኃላፊነት ተሰጠዉ

ገበታ ለሀገር’ ሎጆችን የማስተዳደር ኃላፊነት ለስካላይት ኢትዮጵያ ሆቴል መሰጠቱን የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታዉቋል። የተገነቡት ሎጆችን ስራ የማስኬድ ኃላፊነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስር ለሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል እንዲወስድ ስምምነት መፈረሙን ኢትዩትዩብ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን የተጠናቀቁት ሃላላ ኬላ ሎጅ ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ በስካይላይት ሆቴል የሚተዳደሩ ይሆናል። የጎርጎራ ፕሮጀክትም ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ተብሏል።

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠው ኃላፊነት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥበት እና ለዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል ስለሚፈጥር እንደሆነ የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመልክቷል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተከናወኑት የ'ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶች ከዛሬ ጀምሮ ለክልል መንግስታት ተላልፈው መሰጠታቸውን ተነግሯል።

ፕሮጀክቶቹ ለአማራ፣ ለኦሮሚያ እና ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ተሰጥተዋል።

Читать полностью…

EthioTube

በመጀመሪያው ዙር የቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ባየርን ሚዩኒክ በሜዳው ከሪያል ማድሪድ ጋር አቻ ተለያይቷል። ከሁለቱ ቡድኖች ለፍፃሜ ማን ያልፋል?

#UCL #ChampionsLeague #BayernMunich #RealMadrid

Читать полностью…

EthioTube

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ከአንድ ወር በፊት የኮሪደር ልማት ስራ ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አጠቃላይ ግምገማ አድርገን ነበር።

ዛሬ እንደገና ከአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች እና የኮሪደር ልማት ስራ መሪዎች ጋር በመገናኘት በስራዎቻችን ርምጃ ዙሪያ ጥልቀት ያለው ውይይት አድርገናል። 

እነኚህ ስራዎቻችን የግንባታ ብቻ ጉዳዮች አይደሉም፤ ይልቁንም ከተማችንን ወደ ላቀ ምቹ፣ ንቁ እና ዘላቂ የመኖሪያ ከባቢ የመለወጥ ጥረቶች ናቸው።

ሥነውበትን በማሳደግ፣ አረንጓዴነትን በማስፋት ብሎም መሰረተ ልማትን በማሻሻል የህዝባችንን ጤና መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የስራ ዕድሎችንም እየፈጠርን ነው።

በጋራ እነዚህ ጥረቶቻችን የአዲስአበባን አጠቃላይ ይዞታ በማላቅ እውነትም ለሁሉም ነዋሪዎቿ ፍላጎቶች የተመቸች ያደርጓታል።

Читать полностью…

EthioTube

ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው ስደተኛ በአሜሪካ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸናፊ ሆነ

ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው የላኦስ ተወላጁ ስደተኛ በአሜሪካ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሎተሪ ጃክፖት አሸናፊ ሆነ።የ46 ዓመቱ ቼንግ ሳፋን ፓወርቦል በተሰኘው የሎተሪ ጃክፖት ጨዋታዎች እድለኛ መሆኑን የውድድሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል።ቼንግ ዕድለኛ ያደረገውን የሎተሪ ቲኬት የገዛው በኦሪጎን ግዛት በፖርትላንድ ከተማ ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር።

ግለሰቡ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ ግብር ተቀንሶ 422 ሚሊዮን ዶላር ያህል የሚደርሰው ሲሆን ይህንንም ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር እኩል እንደሚካፈሉ አስታውቋል።“አሁን ቤተሰቤን አንበሻብሻለሁ። ለራሴም ጥሩ ዶክተር መቅጠር እችላለሁ” ሲል አስረድቷል።“ህይወቴ ተቀይሯል” ሲል ለሲቢኤስ አጋር የሆነው ኮይን የተናረው ቼንግ አምላኩ እንዲረዳው በጸሎት መማጸኑን አስረድቷል።

ቼንግ አክሎም ለቤተሰቡ ሲያልሙት የነበረውን ቤት መግዛት እንደሚፈልግ እና ፓወርቦል የሎተሪ ጃክፖት መጫወቱን እንደሚቀጥል ተናግሯል።“እንደገና እድለኛ ልሆን እችላለሁ” ሲል ተስፋውን አስረድቷል።ላለፉት ስምንት ዓመታት በኬሞቴራፒ ህክምና ውስጥ ያለው ቼንግ ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር በመተባበር ከ20 በላይ የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶችን መግዛታቸውን ተናግሯል።የሎተሪ ቲኬቶቹ አሸናፊ ቁጥሮች 22፣ 27፣ 44፣ 52፣ 69 እና ቀይ ፓወርቦል 9 ነበሩ ተብሏል።

በፓወርቦል ታሪክ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የገንዘብ ሽልማት መሆኑ የተነገረ ሲሆን እስካሁን ድረስ በከፍተኛ ደረጃ የተቀመጠው በ2022 አሸናፊ የነበረው የ2.04 ቢሊዮን ዶላር ሽልማት ነው።የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶች በ45 አሜሪካ ግዛቶች፣ በኮሎምቢያ እንዲሁም በፖርቶ ሪኮ እና በአሜሪካ የቨርጂን ደሴቶች እያንዳንዳቸው በ2 ዶላር ነው የሚሸጡት። የሎተሪ ቲኬቶች ዋጋ መጨመሩ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የቢሊዮን ዶላር ሽልማቶች በጣም የተለመዱ ሆነዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሰኞ  የኢት ዜና - ሚያዝያ 21 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 29, 2024

👉 አውሮፓ የኢትዮጵያውያንን ቪዛ አስመልክቶ እግድ አወጣች 

👉በመዲናዋ በዘነበው ከባድ ዝናብ ሰዎች ሞቱ 

👉ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልኡካኑ ጋር ኬንያ ለምን ጉዳይ ሄዱ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/pr_y-YDJMnw

Читать полностью…

EthioTube

በኮሪደር ልማት የተነሳው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ሕንጻ የመልሶ ግንባታ ሥራ ተጀመረ

በኮሪደር ልማት ምክንያት የተነሳው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ሕንጻ የመልሶ ግንባታ ሥራ ተጀመረ፡፡ በግንባታው ማስጀመሪያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የቤተ-ክርስቲያኗ እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የከተማ ፕላን እና ልማት እንዲጠበቅ ብሎም ከተማችን እንድትለማ፣ እንድትዘምን እና የተሻለ ዲዛይን እንዲተገበር በርካታ ትብብር አድርጋለች ነው ያሉት፡፡

ለዚህም በዛሬው ዕለት የመልሶ ግንባታ ሥራው የተጀመረው ሕንጻ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

አዲሱ ሕንጻም ከመሬት በታች ለፓርኪንግ ግልጋሎት የሚውል ወለል እንደሚኖረው እና ዘመናዊ ባለ አራት ወለል ሕንጻ ሆኖ እንደሚገነባም ነው የገለጹት፡፡

ይህም ከአካባቢው ልማት፣ ፕላን፣ በዙሪያው ካሉ ሌሎች ቅርሶች እንዲሁም ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ጋር የሚናበብ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቀን ለቤተክርስቲያኗ የምናስረክብ ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን አባቶች የልማት ኮሪደር ሥራውን በመደገፍ ከጎናችን ስለቆሙም እናመሰግናለን ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ናይሮቢ ኬንያ ገብተዋል።

ጉባኤው ማኅበሩ ደጋፊዎች እና ተባባሪ አካላት በአፍሪካ የልማት የገንዘብ ድጋፍ ቀዳሚ የትኩረት መስኮችን ለማመላከት እና አፅንዖት ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል።

የገንዘብ ድጋፍ አቅራቢዎች በ21ኛው የማኅበሩ ዘመን ድጋፋቸውን ለመጨመር በፅኑ እንዲያጤኑ የማሳሰብ አላማ ያነገበም መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ድጋፍ የአፍሪካን የልማት ተግዳሮቶች እና መልካም ዕድሎች በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የሰሜን ለንደን ደርቢ በአርሰናል አሸናፊነት ተጠናቀቀ። የዋንጫው ትንቅንቅ እንደቀጠለ ነው። የመጨረሻዋን ሳቅ የሚስቀው ማነው፥ አርሰናል ወይስ ሲቲ?

#PremierLeague #Arsenal #TottenhamHotspur

Читать полностью…

EthioTube

በናይጀሪያ ከባድ ዝናብ ባደረሰው ጉዳት ምክንያት ከ100 በላይ እስረኞች አመለጡ።

ባለፈው ረቡዕ ሌሊት የጣለው ከባድ ዝናብ በናይጀሪያ ዋና ከተማ አቅሪቢያ በሚገኘው የሱሌጃ እርስር ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ቢያንስ 118 እስረኞች ማምለጣቸውን የእስር ቤት አገልግሎት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ አዳሙ ዱዛ ሀሙስ እለት ባወጡት መግለጫ ለበርካታ ሰአታት የቆየው ከባድ ዝናብ ግርግዳውን እና በዙሪያው ያለውን ግንብ ጨምሮ የውስጠኛውን የእስርቤት ክፍል አፈራርሶታል ብለዋል።

የእስር ቤት አገልግሎቱ ከእስር ያለመጡትን እየፈለገ ሲሆን እስካሁን በሌሎች የጸጥታ አካላት ትብብር 10ሩ ተይዘዋል ተብሏል። 
ዱዛ "ያለመጡጥን ለመያዝ በእልህ እያሳደድን ነው" ብለዋል።

ያመለጡትን ለመያዝ መንግስት ከፍተኛ ክትትል እያደረገ ነው ያሉት ዱዛ ህዝቡ በፍለጋው እንዲተባበር እና አጠራጣሪ ነገሮችን ሲያይ በአቅራቢያው ላለ የጸጥታ አካል እንዲጠቁም ጠይቀዋል።

እስርቤቶች በተጨናነቁባት እና ልል የሆነ ጸጥታ ሁኔታ ባለባት ናይጀሪያ፣ እስርቤትን ሰብሮ ማምለጥ ዋና የጸጥታ ስጋት እየሆነ መጥቷል።

በቅርብ አመታት ውስጥ በደካማ መሰረተ ልማት እና በታጣቂዎች ጥቃት ምክንያት በሽዎች የሚቆጠሩ እስረኞች አምልጠዋል።

አይኤስ በ2022 ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት እስርቤት ላይ በፈጸመው ጥቃት 440 እስረኞች ነጻ መውጣታቸው በጉልህ የሚጠቀስ ነው።

እስር ቤቶቹ በቅኝ ግዛት ዘመን የተገነቡ በመሆናቸው ማርጀታቸውን እና ደካማ መሆናቸውን የገለጹት ቃል አቀባዩ እያንዳንዳቸው ሶስት ሺህ መያዝ የሚችሉ ስድስት እስርቤቶች ግንባታን ጨምሮ እስርቤቶችን ለማዘመን ጥድፊያ ላይ ነን ብለዋል።

Читать полностью…

EthioTube

የኤርትራ ጦር  ከዛላንበሳና አጎራባች ወረዳዎች ሰዎችን አግቶ እየወሰደ ነው ተባለ

የዛላ  አንበሳ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ በርሄ እንደተናገሩት ከምስራቃዊ ዞን  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ታግተዉ ተወስደዋል  ብለዋል፡፡

ከዛላ አንበሳ 26 ሰዎች፣ ከጉለም ወረዳ  50  እንዲሁም ከኢሮፕ 28 ሰው በኤርትራ ሰራዊት እንደተወሰደ  ገልፀው በዚህ ሳምንት ደግሞ ቁጥሩ መጨመሩን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ዛላንበሳ ከተማን ጨምሮ  ምስራቃዊው ዞን ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ማህብረሰቡም  ብዙ በደል እና ጥቃት እየደረሰበት ነዉ ብለዋል፡፡

የኤርትራ ጦር  የአካባቢዉን ነዋሪዎቹ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት  ኤርትራዊ እንደሆኑ በመግለጽ  በኃይል  እንደተቆጣጠረም ተሰምቷል፡፡

የፌድራል መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠንም የሚሉት አቶ ብርሀነ ዳግም ጦርነት አንፈልግም ግን ደግሞ ማንነታችንን እና ህልውናችንን ሊያስከብርልን ይገባል ብወዋል።

በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በጦሩ  ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ተነስቶ  በከተማው እንዲሁም በአካባቢው ያለው ነዋሪ ለከፋ ችግር እንደተጋለጠም ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ30ሺ በላይ ነዋሪ ተፈናቅሎ በመቀሌ፤ በአዲግራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኝ አቶ ብርሀነ ነግረውኛል ሲል የዘገበው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107·8 ነው፡፡

Читать полностью…

EthioTube

ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተገለጸ

ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል።

ይሁን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መሆኑ ተመልካቷል።

በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል። 

እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - ሚያዝያ 18 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 24, 2024

👉አሜሪካ ህጉን በፕሬዝዳንቷ በኩል አጽድቃዋለች
👉የኢትዮጵያ የኦዲት ተቆጣጣሪ ማንነት ግልጽ አይደለም ተባለ
👉የሱዳን ተፋላሚዎች ዛሬም ያረገበ ጦርነት

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/Xt8d1ZTx9TE

Читать полностью…

EthioTube

የሱዳን ጦር በዋና የጦር ማዘዣው ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ድሮኖችን መትቶ መጣሉን ገልጿል

የሱዳን ጦር በዛሬዉ እለት በሸዲ በሚገኘው ዋና የጦር ማዘዣው ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ድሮኖችን በጸረ-ጄት ሚሳይሎች መትቶ መጣሉን ሮይተርስ የአይን እማኞችን እና ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

የጦር ማዘዣው ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ቢሰነዘርበትም፣ የትኛውም ድሮን ኢላማውን መምታት እንዳልቻለ የሱዳን ጦር ምንጮች መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

የሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል አብደል ፋታህ አልቡርሃን ከካርቱም በሰሜን አቅጣጫ 180 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሸዲ ሰኞ እለት መድረሳቸውን የሱዳን ጦር ሚዲያዎች ዘግበው ነበር።

ጀነራሉ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በሸዲ ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር የለም።
የሱዳን ጦር ሰፊዋን የሰሜን አፍሪካ ሀገር ለመቆጣጠር ከተቀናቃኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር እየተዋጋ ይገኛል።

የማክሰኞው የድሮን ጥቃት በጦሩ ቁጥጥር ስር ባሉ ቦታዎች ላይ ሲደረግ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ተብሏል። የአትባራ ከተማ፣ የናይል ወንዝ ግዛት እና በምስራው የምትገኘው የገዳሪፍ ግዛት የድሮን ጥቃት ደርሶባቸዋል።

ከተቀሰቀሰ አንድ አመት በሆነው ጦርነት ውስጥ ሁለቱም ተፋላሚዎች ድሮን እየተጠቀሙ ናቸው።

አብዛኛውን የካርቱም ከተማ እና የሀገሪቱን ምዕራባዊ ክፍል የተቆጣጠረው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር ለእነዚህ ጥቃቶች ኃላፊት አልወሰደም።

አጋር በነበሩት የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን በሚመሩት ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ መካከል የተፈጠረው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን እንዲገደሉ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።

አል አይን

Читать полностью…

EthioTube

ዛሬ የብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ፤ በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከሩን አሳውቋል።

ይህ ተከትሎ ዘለግ ያለ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫ ፦
- ስለ ሀገራዊ ምክክር
- ስለ ሽግግር ፍትሕ
- ከመንግሥት ውጭ ታጥቀው ስለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች
- ስለ ተሃድሶ ኮሚሽን
- ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት
- ስለ ህወሓት ታጣቂዎች
- ስለ ተፈናቃዮች መመለስ

... ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተውበታል።

ምክር ቤቱ፥ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሀገረዊ ምክክር ኮሚሽን በክልል ደረጃ የምክክር መድረኮችን ማካሄድ ይጀምራል ብሏል።

ሀገራዊው የምክክር ጉባኤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ተስፋ ይደረጋል ሲል ገልጿል።

ም/ቤቱ፤ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ መፅደቁን አስታውሷል።

እንደ አግባብነቱ፦
° የወንጀል ምርመራ እና ክስ
° እውነት ማፈላለግ
° ዕርቅ
° በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት
° ማካካሻ እና ተቋማዊ ማሻሻያ እንደ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች በሀገራችን ተግባራዊ ይደረጋሉ ብሏል።

" የመንግሥት አንዱ መብት በብቸኝነት ኃይልን መጠቀም " መሆኑን ገልጾ በሀገራችን በተወረሰ የፖለቲካ ስብራት የተነሣ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋል ብሏል።

የሀገሪቱን ሰላም የጸና ለማድረግ፣ እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተው፣ የተሐድሶ ሂደት ውስጥ መቀላቀል አለባቸው ብሏል። " የፖለቲካ ጥያቄዎቻቸውንም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በመሳተፍ መፍታት ይችላሉ " ሲል ገልጿል።

ለዚህም የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል። ዓላማውም፦
° መሣሪያ ማስፈታት
° የትጥቅ ቡድኖችን ሰላማዊ ማድረግና ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ነው ብሏል።

መንግሥት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አተገባበር ከሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጋር የተናበበና የሚመጋገብ እንዲሆን ኃላፊነቱን ይወጣል ብሏል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ጦርነትን በፖለቲካዊ መፍትሔ የመቋጨት ባህል አምጥቷል ሲል ገልጿል።

የሰላም ስምምነቱ ለትውልድ የአሸናፊ ተሸናፊ ትርክትን ከቂም ጋር ላለማውረስ የተደረገ ውሳኔ እንደሆነ ገልጿል።

የሰላም ስምምነቱ እስካሁን ብዙ ውጤት እና እፎይታ ቢያስገኝም ቀሪ ሥራዎችም አሉ ብሏል።

በተለይ በስምምነቱ መሠረት " የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው " ሲል ገልጿል።

የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት ብሏል።

" ካለፈ ስሕተተ አለመማር የመጀመሪያውን ስሕተት ከመሥራት የባሰ ነው " ያለው ም/ቤቱ ፤ ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉ አሉ ሲል ጠቁሟል።

እነዚህን ሁሉም ተባብሮ አደብ ማስገዛት ይኖርበታል ብሏል።

" ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት ሕግ የማስከበር ሥራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባል" ሲል አሳስቧል።

ም/ ቤቱ ፤ መንግሥት በትግራይ ክልል አልፎ ቁስልን ለመሻር የሚያስችል ሥራ እየሠራ እንደሆነ ገልጿል።

" ይሄ ግን መንግሥታዊ ኃላፊነት እንጂ ፍርሃት ተደርጎ መወሰድ የለበትም " ብሏል።

" በፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነትና በሕገ መንግሥቱ መሰረት እንደ ሀገር የሚኖረው አንድ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ ነው ክልሎች በክልል ከፖሊስ እና ሚሊሺያ ያለፈ የታጠቀና የተደራጀ ሠራዊት ሊኖራቸው አይችልም፤ አይገባምም " ብሏል።

በዚህ መሠረት ትጥቅ መፍታትና ተያያዥ ሂደቶች በተሐድሶ ኮሚሽኑ ዕቅድ መሠረት በፍጥነት ሊተገበሩ እንደሚገባ አሳስቧል።

ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel