ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ዛሬ አይርላንድ ፣ ኖርዌይ እንዲሁም ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አስታወቁ።

" የዛሬው ቀን ለፍልስጤም እጅግ ታሪካዊ ቀን ነው " ተብሏል።

የአየርላንድ ጠ/ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ " ዛሬ አየርላንድ ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና ሰጥተናል። ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ እያንዳንዳችን ማንኛውንም አይነት ብሔራዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " በሚቀጥሉት ሳምንታት ተጨማሪ ሀገራት ይህን ጠቃሚ እርምጃ ለመውሰድ ከእኛ ጋር እንደሚተባበሩ እርግጠኛ ነኝ " ሲሉ አክለዋል።

የአይርላንድ መንግሥት ይህ የሀገርነት እውቅና የሁለት ሀገር መፍትሄን እንደሚደግፍና ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኢስፔን ባርት ኢይድ ሀገራቸው ከግንቦት 28 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አሳውቀዋል።

የስፔኑ ጠ/ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፥ " ምንም እንኳን ከአሸባሪው ቡድን ሃማስ ጋር የሚደረገው ውጊያ ህጋዊ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለፍልስጤም የሰላም ፕሮጀክት የላቸውም " ብለዋል።

የኖርዌይ ጠ/ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስቶር በበኩላቸው ፥ " እውቅና ከሌለ (የፍልስጤም) በመካከለኛው ምስራቅ ምንም ሰላም ሊኖር አይችልም " ብለዋል።

" ሽብር የተፈፀመው በሃማስና የሁለት ሀገር መፍትሄን በማይቀበሉ እንዲሁም የእስራኤልን መንግሥት በማይደግፉ ታጣቂ ቡድኖች ነው። " ሲሉ አክለዋል።

" ፍልስጤም ነጻ አገር የመሆን መሠረታዊ መብት አላት " ብለዋል።

የፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና መስጠት በይፋ ከተሰማ በኃላ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኖርዌይ እና በአይርላንድ የሚገኙ አምባሳደሮችን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል እንዲመለሱ አዘዋል።

ሚኒስትሩ፤ " የዛሬው ውሳኔ ሽብርተኝነት እንደሚከፍል ለፍልስጤማውያን እና ለዓለም መልእክት ያስተላለፈ ነው " ብለዋል።

መረጃው የስካይ ኒውስ ነው።

Читать полностью…

EthioTube

በትግራይ ክልል 227 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ገቡ

በትግራይ ክልል 227 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች በመተካት እና ወጪ ንግድን በመደገፍ የውጪ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል፡፡

3 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ግምት ያላቸው 2 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን ጠቁመው በዚህም 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ማዳን መቻሉን አንስተዋል፡፡

10 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦት በማቅረብ የጨርቃ ጨርቅ፣ ምግብና - ብረታ ብረት ፣ የቆዳና ሌጦ ኢንዱስትሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውንም መግለጻቸውን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

107 ሺህ ቶን ምርቶች ወደ ውጪ ሀገራት ተልከው 202 ሚሊየን ዶላር እንደተገኘም ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት ተናግረዋል፡፡ 20 ቢሊየን ብር ግምት ያለው የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ እንተቻለ ጠቅሰዋል፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ስለ ብራና ኢፒ አልበም የተሰጠ መግለጫ | | ዕብነ ሐኪም | Bana records

ሙሉውን ለመመልከት

https://youtu.be/A4X0sio4E0A

#Bana #EbneHakim #Brana #Music #EthiopianMusic #AfricanMusic #AmharicMusic #sonymusic

Читать полностью…

EthioTube

ጓደኛቸውን በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ከአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ በመሆኑ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል። በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ ቴዎድሮስ ታከለ እና ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል ተብሏል፡፡

ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ ወለቴ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት በማረጋገጥ መኪናው ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የክትትል እና የምርመራ ስራው የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የከተማችንን እና የነዋሪዎቿን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆ በከተማችን የተፈጸሙ አንዳንድ ወንጀሎችን መነሻ በማድረግ የበሬ ወለደ ይዘት ያላቸውን የተዛቡ እንዲሁም የተጋነኑ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦችና ተቋማት መኖራቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ የከተማችንን የፀጥታ ጉዳይ በተመለከተ ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛ ምንጭ የማግኘት ልምድን ሊያዳብር እንደሚገባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፎ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ፖሊስ ጨምሮ አሳስቧል።

Читать полностью…

EthioTube

የአዲስ_አበባ ከተማ ወረዳዎች በነጋዴዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ያላቸው ሥልጣን ተገደበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ፤ ወረዳዎች በከተማዋ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የነበራቸው ሥልጣን ላይ ገደብ አስቀመጠ።

በአዲሱ አሠራር መሠረት ወረዳዎች በራሳቸው ውሳኔ የንግድ ቦታዎችን ማሸግ የሚችሉት ከንግድ ፈቃድ ጋር በተያያዙ ሁለት ጥሰቶች ተፈፅመው ሲያገኙ ብቻ እንደሆነ አዲስ ባወጣው በመንደር የንግድ ቁጥጥር የአሠራር ሥርዓት መመሪያ” ገልጿል።

መመሪያው፤ የከተማዋ ንግድ ቢሮ፣ ክፍለ ከተሞች ወይም የወረዳ ጽህፈት ቤቶች በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች አሠራር ላይ የሚያደርጉትን የቁጥጥር ሥራ ተፈጻሚነት ያለው እንደሆነ አስፍሯል።

“በተለይ ከእርምጃ አወሳሰድ ፍትሐዊነት ጋር ተያይዞ እና ጤናማ ሂደቱን ከመጠበቅ ጋር ተያይዞ እዚህም እዚያም የሚታዩ ችግሮች አሉ። ‘አላግባብ ታሸገብን፣ አላግባብ ተከፈተ’ የሚሉ ቅሬታዎች ይነሳሉ” ሲሉ ቢሮው ከእርምጃ አወሳሰድ ጋር በተያያዘ ቢሮው የተመለከታቸውን ችግሮች አብራርተዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በቻይና አገጭን በገመድ በማንጠልጠል የነርቭ ጫናን ለመቀነስ በሚደረግ እንቅስቃሴ የአንድ ግለሰብ ህይወት አለፈ

አንድ ቻይናዊ በቅርቡ በነርቭ ላይ የሚደርሰውን ጫና በመቀነስ የአንገት እና የአከርካሪ ህመምን ለማስታገስ በአገጭ ብቻ በገመድ መሰቀልን የሚጠይቅ አወዛጋቢ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲያደርግ ህይወቱን አጥቷል።

ባለፉት አስር ዓመታት እና ከዚያ በላይ፣ በቻይና ውስጥ አንድ በዓለም ዙሪያ ያልተለመደ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በርካቶች እየተጠቀሙበት ይገኛል።

በቆዳ በተሰራ የአገጭ ማሰሪያ ገመድ ብቻ በመታገዝ በአየር ላይ ተንጠልጥሎ ሰውነትን ማወዛወዝ እንቅስቃሴው ያካትታል። ይህው እንቅስቃሴ እ.ኤ.አ. በ2017 አካባቢ በሼንያንግ ግዛት ተወላጅ  በሆነው ሰን ሮንግ ቹን ተስፋፍቷል ተብሎ ይታመናል።

የጀርባ ህመምን ለማስታገስ እንደ ተፈጠረ የተነገረለት፣ የአንገት መወዛወዝ በፍጥነት በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ መናፈሻዎችና የውጪ ጂሞች ዘንድ የታወቀ ሆኗል።

ምንም እንኳን በአየር ላይ በአገጩ ላይ ማንጠልጠል በአለም ላይ የተለመደ ባይሆንም የቻይማ ፓራክቲስቶች ለአንገት እና ለጀርባ ህመም መፍትሄ ነው ብለው ይናገራሉ። ያም ሆኖ ግን ዶክተሮች አንገትን ማንጠልጠል የሚያስከትለውን ጉዳት ከፍተኛ ነው በማለት ለዓመታት ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።

በቅርብ ጊዜ የተፈጠረ አሳዛኝ ክስተት እንደሚያመለክተው ይህ ዓይነቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በስህተት ሲከውን የነበረው ግለሰብ ለሞት ተዳርጓል።

ባለፈው ሳምንት የ57 ዓመቱ ቻይናዊ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቱን አጥቷል።ከቤት ውጭ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን በቼንግዚ ከተማ ሲሰራ ነበር። ፖሊስ ግለሰቡ በአንገቱ ተሰቅሎ መሞቱን ያረጋገጠ ሲሆን ሰውነቱ ከማወዛወዙ በፊት  አገጩ ላይ ገመዱን ማድረግ ሲገባው አንገቱ ላይ ማድረጉን የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ሌላ እማኝ በበኩሉ ሰውነቱን ሲያወዛወዝ ብዙ ሃይል ተጠቅሞ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል። ስህተቱ ምንም ይሁን ምን ገዳይ እንቅስቃሴ ነው ሲል አክላል።

የቲያንጂን የባህል ህክምና ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ተባባሪ ሆስፒታል ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ዣኦ ኪያንግ ምንም እንኳን ጽንሰ-ሀሳቡ በክሊኒካዊ መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ቢሆንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ባልተገባ ሁኔታ ጥሩ አይደለም ብለዋል ። ነርቭን እና የአከርካሪ አጥንትን አልፎ ሊጎዳ ይችላል።

በአንገትዎ ላይ ገመድ ማንጠልጠል አይመከርም ለጤናም ሆነ ለ አከርካሪው ምንም አይነት ጥቅም አይኖረውም ሲሉ እክለዋል።ይህ አሳዛኝ ሁኔታ አብዛኛዎቹን አንገት በማወዛወዝ ህክምናውን ለሚጠቀሙ ሰዎች ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው። ይህንን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመለማመድ ላይ ያሉትን አደጋዎች እና የአንገትን ማወዛወዝ በትክክል እንዴት እንደሚጠቀሙበት የመማር አስፈላጊነትን ይጠይቃል ተብሏል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሰኞ የኢት ዜና - ግንቦት 12፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 20 , 2024

👉 አብርሃም በላይ ስልጣናቸውን ቀየሩ

👉 ፕሬዝዳንቱ በሂሊኮፍተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ

👉 ታደሰ ወረደ የፌደራል መንግስቱን በተመለከተ የተናገሩት

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/aCA9Mag9hIE

Читать полностью…

EthioTube

በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከባድ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ተደረገ

የተሳካና ከባዱ ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገው ባልተለመደ መልኩ የሰውነት ክፍሉ ከመደበኛው በተቃራኒው ሆኖ ለተወለደው የ 9 ዓመት ታዳጊ ነው፡፡

በኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል የህፃናት እና የአዋቂዎች የልብ ቀዶ ጥገና ሀኪም የሆኑት ዶክተር ሺቢቆም ታመነ፣ ለ9 ዓመት ታዳጊ ባልተለመደ መልኩ ልቡ በቀኝ በኩል ሆኖ ለተወለደው ታዳጊ በተሳካ ሁኔታ ቀዶ ጥገና መከናወኑን ተናግረዋል።

ለቀዶ ጥገና ህክምናው 5 መቶ ሺህ ብር መከፈሉ የተገለፀ ሲሆን፤ በውጭ ሀገር ቢሄድ ለቀዶ ለጥገናው ብቻ በትንሹ ከ 15 እስከ 20 ሺህ ዶላር እንደሚያስከፍል  ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ የሚያገኙትን የህክምና አገልግሎት ለማስቀረት ከ7 ዓመት በፊት ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን በሚል የልብ ቀዶ ጥገና በሀገር ውስጥ መሰጠት መጀመሩንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ  ለህክምና የሚያወጡትን ከፍተኛ ወጪ እና እንግልት ለማስቀረት ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር  የህክምና ባለሞያዎች፣ ወደ ውጭ ሀገር የሚያስኬዱ ህክምናዎችን በሀገር ውስጥ  እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡

ሆስፒታሉ በዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች በመታገዝ በአዋቂዎች እና በህፃናት የልብ ቀዶ ጥገና የሚሰጥ ሲሆን፤ በ8 ወራት ውስጥ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ የቀዶ ጥገና አገልግሎት መሰጠቱ ተመላክቷል።

ማህበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አንፃርም 300 ለሚሆኑ ህፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና መስጠቱን በመግለጫው ላይ ተነስቷል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም

https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ዶክተር አብርሃም በላይ የሃላፊነት ቦታ ቀየሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዛሬው እለት ሹመቶች ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት፡-

1. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር፣

2. አብረሃም በላይ (ዶ/ር) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚንስትር፣

3. መሀመድ እንድሪስ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ከግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተሹመዋል::

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ማንችስተር ሲቲ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ4 ተከታታይ አመታት ሻምፒዮን ሆነዋል። አርሰናል ልክ እንደ አምና በሁለተኛ ደረጃ አጠናቋል።

#PremierLeague #ManCity #Arsenal

Читать полностью…

EthioTube

በዚህ ሳምንት በመቀነት ፕሮግራም ምዕራፍ ሁለት ክፍል - 1  ስለ የመብቶች እንቅስቃሴዎች የአካል ጉዳተኛ ሴቶችን መብቶች አካትተዋል? በሚል ጥያቄ አዘል ርዕስ የምንዳስስ ይሆናል ::

ሙሉውን ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇

https://youtu.be/msBN3NVzTqI

Читать полностью…

EthioTube

Sony Music Africa የተሳተፈበት የዕብነ ሐኪም ብራና የተሰኘው ኢፒ አልበም ተለቀቀ

Ebne Hakim - Brana EP Album Out Now!

#EbneHakim #Brana #Music #EthiopianMusic #AfricanMusic #AmharicMusic #SonyMusic

Watch:
https://youtu.be/-d7hDFSYNTc

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ አርብ የኢት ዜና - ግንቦት 9፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 17 , 2024

👉 ተማሪዋን የገደለው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

👉 274 ሺህ የትግራይ የሠራዊት አባላት ትጥቅ ይፈታሉ ተባለ

👉 ቢጂአይ እና ፐርፐዝ ብላክ በመሃከላቸው የተፈጠረው ችግር ፈቱ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/lSMWFO2FOSE

Читать полностью…

EthioTube

#Update

ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።

ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም ደግሞ አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መስፍን ጣሰዉ  ፥ " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መቃጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ " ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር " ET154 " ሚያዝያ 29/2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን እና አውሮፕላኑ በሰላም ቦሌ ኤርፖርት ማረፉን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል።

የዚህ መረጃ ባለቤት ካፒታል ጋዜጣ ነው።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በሐመር ወረዳ በአንድ ቀን ውስጥ ሶስት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሟል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሐመር ወረዳ ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት ላይ ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ያጋጠመ ሲሆን በአንድ ቀን ውስጥ ሶስት ጊዜ መከሰቱ ተነግሯል ።

ሶስት ጊዜ ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ውስጥ ሁለቱ መጠነኛ ሲሆኑ ከምሽቱ 6 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ላይ ያጋጠመው እና ለ20 ሴኮንዶች የቆየው ክስተት ግን ከፍተኛ እንደነበረ የሐመር ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አ/ቶ አወቀ ንጋቱ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በዚህ ክስተት በሰው እና በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም የተመዘገበውን የልኬት መጠን በሬክተር ስኬል 5 መሆኑን ገልፀዋል ። ከአሁን ቀደም በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም በወረዳው በዲመካ ከተማ በአንድ ወር ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ማጋጠሙን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል ።

በተለይም የአሁኑ ክስተት ባለፈው ከተከሰተው ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አ/ቶ አወቀ በአካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ የሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ ትኩረት እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል ።

በሌላ በኩል ሰምኑን እየጣለ ባለው ዝናብ አማካኝነት ከተራራማ ሸንተረሮች የሚመጣ ጎርፍ እና ውሃ ሙላት በንብረትና በሰብሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ተገልጿል ። በዚህም ምክንያት በአሲሌ፣ በኤርቦሬ ጎንደሮባ ፣ በጨርቀቃ እና  ዘገርማ ቀበሌዎች ባልደረሱ የአገዳ ሰብሎች፣ ተሰብስበው በተከመሩ እህሎችና መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል ።

በተለይም እየጣለ በሚገኘው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የሚከሰተው ጎርፍ እና ውሃ ሙላት ለከተማው ማህበረሰብም ጭምር ስጋት እየደቀነ መምጣቱ ተመላክቷል ። በተለይም የወይጦ ወንዝ ምልቶ መደበኛ የመፍሰሻ ቦታውን ለቆ እየፈሰሰ በመሆኑ በሰውና በንብረት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ማህበረሰቡ ከወዲሁ መጠንቀቅ እንደሚገባ ተገልጿል ።

Читать полностью…

EthioTube

ነገ በተወሰኑ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል

ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደሚቋረጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

በዚህም በቦሌ አትላስ፣ ደሳለኝ ሆቴል፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ ፊጋ፣ ላምበረት፣ አንቆርጫ፣ የተባበሩት፣ ፍየል ቤት፣ ገዳመ እየሱስ ቤተ ክርስቲያን፣ ጭላሎ፣ ኮካ፣ አዲሱ ገበያ እና አካባቢዎቻቸው የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉና በከፊል ይቋረጣል ተብሏል።

በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ደንበኞች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በቀጣዮቹ 10 ቀናት ከባድ ዝናብ እንደሚጠጥል ተነገረ

የኢትዮጰያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው በቀጣዮቹ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እንደሚያመላክቱን በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናት ሰፊ ቦታዎችን ያካተተና የተጠናከረ ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተስፋፋ ዝናብ የሚኖር ሲሆን እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የኢትዮጲያ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ከኢትዮጰያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአጠቃላይ በሚቀጥሉት ቀናት ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፤ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፤ ነአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞኖችን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች  ላይ የተሻለ የዝናብ ስርጭት ይኖራቸዋል፡፡

በሌላ በኩል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ ፣ በአዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ እና ሃረር ላይ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጥል ይጠበቃል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳድር ከትናንት በስቲያ ሌሊት በራያ ዓዘቦ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ ወገኖች " በግፍ ተጨፍጭፈው መገደላቸውን " ገለጸ።

አስተዳደሩ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉና ግድያ የተፈጸመበትን ልዩ ስፍራ በተመለከተ በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም ድርጊቱን " ዘግናኝ ወንጀል " ብሎታል።

" ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት ከዓፋር አከባቢ የመጡ ናቸው " ብሎ " ማንነታቸውን በሚመለከት ጥብቅ ክትትል እያደረግን ነው " ሲል አሳውቋል።

የአፋር ክልል መንግስትና የፌደራል ፖሊስም ወንጀለኞችን ተከታትለው በመያዝ ወንጀል ወደ ፈፀሙበት አከባቢ መጥተው ይዳኙ ዘንድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፤ " የራያ ዓዘቦ ወረዳ ህዝብ እና አስተዳደር ሁኔታውን ለማረጋጋት እና ለመቆጣጠር ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት  እጅግ የሚበረታታ ነው " ብሏል።

ወንጀለኞችን በመያዝ እና ለሕግ ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ለህዝቡ አሳውቋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ማክሰኞ የኢት ዜና - ግንቦት 13፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 21 , 2024

👉የዲላን ከተማን ያስቸገረው የጅብ መንጋ

👉 ወረዳዎች በነጋዴዎች ላይ ያለቸው ስልጣን ተነሳ

👉 75 አመራሮች ሃሰተኛ የት/ት ማስረጃ ተገኘባቸው

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/VE6MvF5qM_M

Читать полностью…

EthioTube

ዲላን የጅብ መንጋ አስቸግሯታል

በዲላ ዙሪያ ወረዳ የጅብ መንጋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ መጠጥ ቤቶች እስከ 12 ሰዓት ብቻ እንዲሰሩ ፖሊስ አስጠነቀቀ።
ከዚህ በፊት ባልተለመደው መልኩ በዲላ ዙሪያ ወረዳ አንዳንድ አከባቢዎች የጅብ መንጋ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የገለጹት የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ም/ኢ/ር መሰለ ወንዱ ጀጎ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ም/እ/ር ይህንን ያሉት በሽጋዶ ቀበሌ ልዮ ቦታ ባፋኖ ተብለው በሚጠራበት አከባቢ ነዋር የሆኑት አቶ አለማዬሁ ጎበና የተባሉ ግለሰብ ግንቦት 11/2016 ዓ/ም አምሽተው ወደ ቤታቸው ስመለሱ በጅብ መንጋ መበላታቸውን በገለጹበት ወቅት ነው፡፡

አቶ አለማየሁ ወደ ቤት ሳይመለሱ በመቅረቱ ቤተሰቦች ፍለጋ በወጡበት ወቅት በመንገድ ላይ ልብስ ጫማና የተለያዩ የሰውነት ክፍል የቀሩ ስጋና አጥንት በማግኘታቸው ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ባደረጉት ምርመራ ባገኙት ምልክቶች ግለሰቡ በጅብ መበላታቸውን ማረጋገጣቸው የገለጹት አዛዡ በአከባቢው ከፍተኛ የጅብ ጩሄት እንደነበረው ከአከባቢው ማህበረሰብ ማረጋገጥ መቻሉን አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ የትኛውን ማህበራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ከገበያ በሚመለሱበት ወቅት በጊዜ ወደ የቤታቸው መመለስ እንዳለበት በመግለጽ በም/ቤቱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ማነኛውም መጠጥ ቤቶች እስከ ምሽቱ 12:00 ስዓት ብቻ መሆኑን ገልጸው ከዚህ ውጭ በሆኑ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግሯል፡፡

የጅብ መንጋ እንቅስቃሴ ስጋት በመጨመሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በጊዜ ወደየ ቤታቸው መግባት እንደለበትና ልጆች የቤት እንስሳትን ስጠብቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ወደ ጫካ ውስጥ እንዳይሄዱ አሳስቧል።

በመጨረሻ በአካባቢው ለረዥም ጊዜያት ጅብ እንደነበሩ የገልጹት ም/እ/ር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በአጎራባች ቀበሌያት መሠል ጥቃት መድረሱን በማንሳት ማህበረሰቡ በጊዜ በመግባት የሚሰጠዉን የጥንቃቄ መልእክት በአግባቡ እንዲተገብርም ጠይቀዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ድምፃዊት ራሄል ጌቱ ሰረቅ የተሰኘውን ተወዳጅ ሙዚቃዋን በTecno Camon 30 Pro ስልክ ምረቃ በሸራተን አዲስ እንዲህ ነበር የተጫወተችው | LIVE Performance: Rahel Getu - Sereq

ለማየት፦
youtu.be/gBXUngdqFWA

#RahelGetu #EthiopianMusic #AfricanMusic #TecnoMobile

Читать полностью…

EthioTube

በኢራን ፕሬዝዳንት ህልፈት ሊባኖስ የሶስት ቀናት የሀዘን አዋጅ አወጀች

👉 በአደጋዉ ህይወታቸዉን ያጡት ኢማም አል-ሃሽም ከፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ጋር ለመገናኘት ለአንድ ሰዓት ያህል ሞክረዉ ነበር

የሊባኖስ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ማካቲ በሄሊኮፕተሩ ላይ በነበሩት ራይሲ እና ሌሎች ሰዎች ሞት የሶስት ቀናት የሃዘን አዋጅ አውጀዋል።"በሀዘን ወቅት በሁሉም የህዝብ አስተዳደሮች፣ ተቋማት እና ማዘጋጃ ቤቶች ሰንደቅ ዓላማቸዉ በግማሽ ብቻ ከፍ ብለው ይውለበባሉ" ሲል የኤንኤን የዜና ወኪል ዘግቧል።የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በኢራን ፕሬዝዳንት ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው ራይሲን "በአክብሮት እና በታላቅነታቸዉ" እንደሚያስታውሷቸው ተናግረዋል።"ብዙ ጊዜ እንዳደረግነው በእነዚህ አስቸጋሪ እና አሳዛኝ ጊዜያት ከጎረቤታችን ኢራን ጎን እንቆማለን" ሲሉ በኤክስ ላይ አጋርተዋል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኢራን ፕሬዝዳንት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞት ታላቅ ሀዘኔ ነዉ ሲሉ ለኢራን መንፈሳዊ መሪ ካሜኔይ ሀዘናቸውን ልከዋል ።ፑቲን በመልዕክታቸዉ "ሰይድ ኢብራሂም ራኢሲ ሙሉ ህይወቱን እናት አገሩን ለማገልገል ያደረ ድንቅ ፖለቲከኛ ነበር" ሲሉ ፑቲን ጽፏል። "የሩሲያ እውነተኛ ወዳጅ እንደመሆኗ በሀገራቱ መካከል መልካም ጉርብትና ግንኙነት እንዲጎለብት በማድረግ የማይናቅ ግላዊ አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡ ወደ ስልታዊ አጋርነት ደረጃ ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ነበር በማለት አሞካሽተዋል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

በቤንች ሸኮ ዞን የወባ ወረርሽኝ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን የወባ ወረርሽኝ መጠን 74 በመቶ መድረሱን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን አስታወቁ፡፡ ችግሩ በጣም አሳሳቢ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሔ እንደሚያሻው ጠቁመዋል፡፡

የወባ የዞኑ ትልቅ ፈተና ሁኗል ሲሉ ለኢፕድ የገለጹት አቶ ሀብታሙ፤ አንድ ሰው እስከ 20 ዙር ድረስ በወባ በሽታ እየተያዘ መሆኑን አመላክተዋል።

አካባቢው ሦስት ዓመት ሙሉ በወባ ወረርሽኝ ውስጥ መቆየቱንና የወባ ወረርሽኙ እየጨመረ እና ዝርያውን ቀይሯል የሚል መረጃ እየወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ሀብታሙ ገለጻ፤ ስርጭቱን በማህበረሰብ ንቅናቄ ለመቆጣጠር ሙከራ ቢደረግም ነገር ግን ስርጭቱን መቀነስ አልተቻለም፡፡ የኬሚካል ርጭት ለማድረግ አቅርቦት ውስንነት እንዳለ የጠቆሙት አቶ ሀብታሙ፤ ዞኑ በወረርሽኝ ውስጥ እንደመሆኑ መጠን ችግሩን ታሳቢ ያደረገ ኬሚካል አቅርቦትና ስርጭት ሊኖር እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የኢራን ፕሬዚዳንት በ ሄሊኮፍተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ

የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ተሳፍረውባት በነበረው ሄሊኮፕተር በደረሰው አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

ይህንንም የሀገሪቱ የመንግሥት አረጋግጧል።

ከሳቸው በተጨማሪ በሂሊኮፕተር ውስጥ አብረው የነበሩት የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አሚር አብዶላሂያን እና ሌሎች በርካታ ሰዎች ሞተዋል።

ሮይተርስ በአደጋው ፕሬዚዳንቱ ሲጓዙባት የነበረችው ሄሊኮፕተር ሙሉ_በሙሉ መቃጠሏን " አንድ የኢራን ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

" የፕሬዜዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሄሊኮፕተር በአደጋው ሙሉ በሙሉ ተቃጥላለች።

በኢራን የሂሊኮፕተር አደጋ የሞቱት

- የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ
- የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂያን
- የተብሪዝ መስጂድ ኢማም አያቶላህ አልሃሸሚ
- የምስራቅ አዘርባጃን ግዛት አስተዳዳሪ ማሊክ ራህማቲ
- የፕሬዝዳንቱ ጥበቃ ኃላፊ ማሄዲ ሙሳቪ
- የሄሊኮፕተሩ አብራሪ፣
- የሂሌኮፕተሩ ረዳት አብራሪ
- ቦዲጋርድ
- የበረራ አስተናጋጅ በትላንቱ የሂሊኮፕተር አደጋ ሞተዋል።

የፕሬዜዳንት ራይሲን ሞት ተከትሎ ምክትል ፕሬዜዳንቱ ሞሀመድ ሞክበር በ50 ቀናት ውስጥ በምርጫ አዲስ ፕሬዜዳንት እስኪመረጥ ድረስ የፕሬዜዳንቱን ቦታ ተክተው ይሰራሉ።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ሳይሽ እሳሳለሁ የተሰኘውን ተወዳጅ ሙዚቃውን በTecno Camon 30 Pro ስልክ ምረቃ በሸራተን አዲስ እንዲህ ነበር ያቀረበው | LIVE Performance: Michael Belayneh - Sayesh Esasalehu

ለማየት፦
https://youtu.be/a0EbqsA07zg

#MichaelBelayneh #EthiopianMusic #AmharicMusic #AfricanMusic #TecnoMobile #TecnoCamon30 #AddisAbaba

Читать полностью…

EthioTube

ድምፃዊት ራሄል ጌቱ ጥሎብኝ የተሰኘውን ተወዳጅ ሙዚቃዋን በTecno Camon 30 Pro ስልክ ምረቃ በሸራተን አዲስ እንዲህ ነበር የተጫወተችው | LIVE Performance: Rahel Getu - Tilobign

ለማየት፦
https://youtu.be/_v-Pba71CAY

#RahelGetu #EthiopianMusic #AmharicMusic #AfricanMusic #TecnoMobile #TecnoCamon30 #AddisAbaba

Читать полностью…

EthioTube

የወጣቱ ድምፃዊ ዕብነ ሐኪም ኢፒ (ግማሽ)  "ብራና" የተሰኘው የሙዚቃ አልበም ትናንት ምሽት በ ሉና ላውንጅ ይፋ ሆነ

በSony Entertainment Africa አጋርነት የተዘጋጀው የኢትዮጵያዊው ዘፋኝ ዕብነ ሐኪም  ኢፒ "ብራና" ይፋ ሆኗል

አለም አቀፉ Sony Entertainment Africa ጋር አብሮ በመስራት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሆነው ወጣቱ ሙዚቀኛ ዕብነ ሐኪም የመጀምሪያ ኢፒ "ብራና"  ትናንት ምሽት ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በ ሉና ላውንጅ ምሽቱን ተመርቋል።  

አልበሙ በብራና ሪከርድስ የቀረበ ሲሆን አቀናባሪ ኑሂ በአቀናባሪነት ፤ ሙዚቀኛ ዕብነ ሐኪም በሙዚቃ ግጥም ጻሀፊነት እንዲሁም ሌሎች ወጣት እና አንጋፋ ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል።

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ስልትን ከዘመናዊ ስልቶች ጋር በማጣመር የተዘጋጀው ይህ አልበም "ብራና" ፤  ሙዚቀኛው የሚያዘነብልበትን የኢትዮ-ፊዩዥን ስልት ተከትሏል ተብሏል ።

ሙዚቃዊ ጭብጦቹን በቅኔያዊ ትረካዎች አማካኝነት የሚዳስሰው አልበሙ በውስጡ ስድስት ያህል ዘፈኖችን የያዘ ሲሆን የዘፋኙ የህይወት እና ሙዚቃ ጉዞ ጥልቅ ስሜቶች የተንፀባረቀበት ነው።

ሙዚቀኛ ዕብነ ሐኪም ስለ አልበሙ ለጋዜጦኞች በሰጠው ማብራሪያ  ‘’ብራና ለልቤ በጣም የቀረብ ስራ ነው። ሙዚቃውን የሚያደምጥ ሁሉ ተመሳሳይ ስሜት እንደሚሰማው ተስፋ አደርጋለሁ’’ ብሏል ።

የባና ሪከርድስ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ብሌን መኮንን ‘’ባና ረከርድስ የተመሰረተው የኢትዮጵያን ሙዚቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ነው። በዚህም ታላቅ ኅላፊነት እንዲሁም ኩራት ይሰማናል’’ ስትል ገልፃለች ።

የሙዚቃ አቀናባሪው ኑሂ  እንደተናገረው "ብራና" ሙሉ አለም ሲሆን ከልብ የተሰሩ ግጥሞችን፣ እርስ በርስ የተሳሰሩ ትረካዎችን እና በስሜት ልዩ የሆኑ የሙዚቃ ቅንብሮችን አስተሳስሮ የሚሄድ የሕይወት መንገድ ይህን ህልም ሕያው ለማድረግ ከዕብነ ሐኪም  ጋር በመስራቴ እና ለህዝብ በማቅረቤ እጅግ ደስ ይለኛል ‘’ ሲል ስለ አልበሙ ያለውን ስሜት አጋርቷል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሰኞ የኢት ዜና - ግንቦት 5፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 13 , 2024

👉 ትናንት የተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀትቀጥ

👉ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባህርዳር ተገኝተው ለፋኖ ጥሪ አቀረቡ

👉አየር መንገዱ ለተፈጠረው ጭስ ማብራያ ሰጠ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/4w_-chdbth0

Читать полностью…

EthioTube

“ስለ አማራ መብት እንቆረቆራለን በሚል ጫካ የገባችሁ ወንድሞች ከክልላችሁ መንግስት ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ ጥሪ አቀርባለሁ”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)   

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባህርዳር የተገነባው የዓባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ ስለ አማራ መብት እንቆረቆራለን በሚል ጫካ የገባችሁ ወንድሞች ከክልላችሁ መንግስት ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ስለ አማራ ዲሞክራሲ የሚታገል ማንኛውም ግለሰብ እና ቡድን ሰክኖ በማሰብ ሕዝቡን እና ክልሉን መጥቀም በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

ስለ አማራ መብት፣ ልማት እና ዲሞክራሲ እንቆረቆራለን በሚል ጫካ የገባችሁ ወንድሞች ለዚህ ግዜው ባለመሆኑ ከክልላችሁ መንግስት ጋር አብራችሁ ልትሰሩ ይገባል፤ ሞት ይበቃል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ብልጽግና በኢትዮጵያ ልክ የሚሰራ፣ ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚመጥን ስራ የሚሰራና በቃሉ የሚገኝ ፓርቲ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ብልጽግናን እንመኛለን ስንል በንግግር ያልተገነዘቡን ሰዎች በዚህ ድልድይ ብልጽግና ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲረዱ እፈልጋለሁ ብለዋል።
 
የብልጽግና ራዕይና ተልእኮ ያሳከውን ድልድይ ላይ ቆሜ ይህ ንግግር በማድረጌ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የዓባይ ወንዝ ድልድይ በሀገሪቱ ግዙፍ ከሚባሉ ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ የሚገባትን፣ የአማራ ሕዝብ የሚገባውን፣ ለባሕር ዳርም ውበት የሚመጥን ታላቁን ሥራ በጋራ ለማስመረቅ በቅተናል ሲሉም ተናግረዋል።  

በሕዝቦች መካከል በተፈጠሩ አልባሌ ትርክቶች ምክንያት እየላላ ያለውን ትስስር ሊያጠናክር የሚችል የትርክት ድልድይ መገንባት እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል፡፡

እንደመንግስት ሁለት ድልድይ ለመገንባት እንፈልጋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የመጀመሪያው ልማትን የሚያሳልጥ ድልድይ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ህዝብን የሚለያይ ግድግዳ በማፍረስ የአንድነት ድልድይ መገንባት ነው ብለዋል፡፡ 
 
ይህ ሁለት ዓይነት ድልድይ ኢትዮጵያን በርቀት ያሻግራል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ 

ኢትዮጵያን የሚመጥን ድልድይ በውቧ ባህር ዳር ከተማ ማስቀመጥ ለቻሉ ባለሙያዎች እና መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ለእናቶች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትም አስተለልፈዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው የዓባይ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት ያለው በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ መሆኑ ተገልጿል።

Читать полностью…

EthioTube

የአሳማ ኩላሊት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰው ግለሰብ ህይወቱ አለፈ

በዘረመል ምህንድስና የተሻሻለ የአሳማ ኩላሊት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰው ግለሰብ ከህክምናው ሁለት ወራት በኋላ ህይወቱ ማለፉን ሆስፒታሉ አስታወቀ።

የ62 ዓመቱ ሪቻርድ "ሪክ" ስላይማን ቀዶ ህክምናውን በመጋቢት ወር ከማድረጉ በፊት በከፋ የኩላሊት ህመም ይሰቃይ ነበር።

ህይወቱ ያለፈው በንቅለ ተከላው ምክንያት ስለመሆኑ ምንም ምልክት የለም ሲል የማሳቹሴትስ አጠቃላይ ሆስፒታል (ኤምጂኤች) እሑድ ዕለት አስታውቋል።

በዘረመል ምህንድስና ከተሻሻሉ አሳማዎች የተገኙ ክፍሎችን ሌሎች የመተካት ሙከራ ቀደም ሲል አልተሳካም ነበር። የስላይማን ቀዶ ህክምና ግን ታሪካዊ ምዕራፍ ነው ተብሎ ተወድሷል።

ከኩላሊት ህመም በተጨማሪ ስላይማን የስኳር በሽታ እና የደም ግፊት ነበረበት።
እአአ በ 2018 የሰው ኩላሊት ንቅለ ተከላ ቢያከናውንም ከአምስት ዓመታት በኋላ መሥራት ማቆሙ ተነግሯል።

የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላውን ተከትሎ፤ አዲሱ ኩላሊቱ በጥሩ ሁኔታ እየሠራ በመሆኑ የኩላሊት እጥበት (ዳያሊሲስ) እንደማያስፈልገው ዶክተሮቹ አረጋግጠው ነበር።

"ስላይማን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ህሙማን የተስፋ ብርሃን ፈንጣቂ ሆኖ ይታያል።

‘የዜኖትራንስፕላንቴሽን’ መስክን ወደፊት እንዲራመድ ላሳየው እምነት እና ፍቃደኝነት በጣም እናመሰግናለን" ሲል ሆስፒታሉ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ዜኖትራንስፕላንቴሽን ህይወት ያላቸው ሴሎችን ወይም የአካል ክፍሎችን ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላ ዝርያ መተካት ነው።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…
Subscribe to a channel