አቡነ ሉቃስ በ6 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወሰነ
የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምስራቅ አዉስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት የገዳማት መምሪያ የበላይ ሃላፊ ሊቀጳጳስ አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት “የቅስቀሳ ወንጀል” በ6 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወሰነ።
ከወራት በፊት የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ስር እና የወንጀል ህግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች አቅርቦባቸዋል።
በቀረበባቸው ክስ ላይ፤ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና በጵጵስና በማገልገል ላይ እያሉ ስለ ሰላም እና አንድነት የመስበክ ሃይማኖታዊ ግዴታቸዉን ወደ ጎን በመተዉ በታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገረ አሜሪካ ቴክሳስ እና አካባቢዉ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ታቦት ወጥቶ በቆመበት አዉደምህረት ላይ በመገኘት "የአመፅ ቅስቀሳ" ማድረጋቸውን ዐቃቤ ሕግ በዝርዝር ጠቅሷል።
በመሆኑም ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ሦስት የቅጣት ማክበጃ አስተያየቶች መካከል ፍርድ ቤቱ አንዱን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት በመያዝ እና ተከሳሹም የቀደመ የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መሆኑን መነሻ በማድረግ አንድ የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው ዛሬ በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል።
በዚህም መሰረት ተከሳሹ በሌሉበት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በእርከን 23 ሥር በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በሌሉበት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የደቡብ ሱዳን መንግሥት፣ አገሪቱን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኘውን ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ለመገንባት በኹለቱ አገራት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ከትናንት በስቲያ ለፓርላማው ማቅረቡን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ለመንገድ ግንባታው በጠቅላላው የሚያስፈልገውን 738 ሚሊዮን 264 ሺህ ዶላር ወጪ የምትሸፍነው ኢትዮጵያ እንደኾነች የአገሪቱ ባለሥልጣናት መናገራቸውን ዘገባዎቹ አመልክተዋል።
ደቡብ ሱዳን ከመንገድ ግንባታው ወጪ የሚደርስባትን ድርሻ የአምስት ዓመታት እፎይታ ከወሰደች በኋላ ባሉት ቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ በነዳጅ አቅርቦት ወይም በጥሬ ገንዘብ ለኢትዮጵያ እንደምትከፍል በስምምነቱ ላይ ተገልጧል ተብሏል።
ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል ጅቡቲ ወደብን የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ የገለጠች ሲኾን፣ ጅቡቲም የሸቀጥ ማካመቻ ቦታ ወደቡ ላይ እንደሰጠቻት አይዘነጋም።
ዋዜማ
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ንብ ባንክ ከአሥር በላይ የማኔጅመንት አባላቱ እንዲሰናበቱ ወሰነ
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክን በቺፍ ኦፊሰርነትና በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩትን ጨምሮ፣ ከአሥር በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት ከሥራ እንዲሰናበቱ ውሳኔ ማስተላለፉ ታወቀ፡፡
ባንኩ ውስጥ ረዥም ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት ከፍተኛ አመራሮች ከተጀመረው ሪፎርም ጋር ተያይዞ በተሰጠ ውሳኔ ከሥራ መሰናበታቸውን የሚገልጸው ደብዳቤ፣ ሰኞ ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደደረሳቸው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ለተሰናባቾቹ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የደረሳቸው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ከሥራ እንዲሰናበቱ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በዚህ ስብሰባ ባንኩ አሁን ለደረሰበት ችግር ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን አጣርቶ እንዲያቀርብ ቦርዱ አቋቁሞ በነበረው አጣሪ ቡድን ሪፖርት መሠረት ጥልቅ ውይይት በማድረግ፣ ሊወሰድ በሚገባው ዕርምጃ ላይ በቀረበ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔ ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በንብ ባንክ ላይ ባደረገውና እያደረገ ባለው ምርመራ አሁን ለደረሰበት ውድቀት የቀድሞ ቦርድና የባንኩ ማኔጅመንት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን፣ በባንኩ ላይ በውጭ ኦዲት ከተደረገው የምርመራ ግኝት አኳያ በባንኩ ከፍተኛ አመራርነት መቀጠላቸው ተገቢ ባለመሆኑ፣ ከግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ እንዲሰናበቱ እንደተወሰነ በዚሁ ደብዳቤ እንደተገለጸላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በቦርዱ ተወስኖ በአዲሷ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እመቤት መለሰ (ዶ/ር) ተፈርሞ በወጣው ደብዳቤ ከሥራ መሰናበታቸው የተገለጹት አመራሮች፣ በእጃቸው ያለውን የባንኩን ንብረት እንዲያስረክቡ ታዟል፡፡ ከሥራ መሰናበታቸው ከተገለጸላቸው ከፍተኛ አመራሮች መካከል አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ቦርድ ኃላፊነቱን ከተረከበ በኋላ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ መልካሙ ሰለሞን አንዱ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
አቶ መልካሙ ባንኩ አጋጥሞት ነበር ከተባለ ችግር ጋር ተያይዞ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ገነነ ሩጋን ካሰናበተ በኋላ፣ አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እስከተሰየሙበት ጊዜ ድረስ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ቀደም ብሎም የሒዩማን ካፒታል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ነበር፡፡
via ሪፖርተር
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ሜዲካል ቲምስ ኢንተርናሽናል የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ አማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ውስጥ የተገደለው የረድዔት ሠራተኛ ባልደረባው እንደሆነ አስታውቋል።
የረድዔት ሠራተኛው የተገደለው፣ የድርጅቱ ባልደረቦች በሚጓዙበት ተሽከርካሪ ላይ የታጠቁ አካላት በተኮሱበት ጥይት እንደኾነና በጥቃቱ ሌሎች የድርጅቱ ባልደረቦችም እንደቆሰሉ ድርጅቱ ገልጧል።
በክስተቱ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የጠቀሰው ድርጅቱ፣ ለጊዜው ጥቃቱ "ኾን ተብሎ የተፈጸመ" ነው ብሎ እንደማያምን አመልክቷል።
ድርጅቱ፣ በአማራ፣ ትግራይ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝና ሶማሌ ክልሎች ለተፈናቃዮችና ስደተኞች የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል።
ዋዜማ
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የኬንያው ፕሬዝዳንት የጫት ዕገዳን በመቃወም ምርቱን እንደሚያስፋፉ ተናገሩ
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አንዳንድ የአገሪቱ ግዛቶች በጫት ሽያጭ መጠቀም ላይ ያጣሉትን አወዛጋቢ ዕገዳ ውድቅ በማድረግ ምርቱ እንዲስፋፋ እንደሚያደርጉ አስታወቁ።
ኬንያ ውስጥ ጫት መቃም እየጨመረ ላለው የአእምሮ ጤና ችግር፣ ለወንጀልን መስፋፋት እንዲሁም ለተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች ምክንያት ነው ተብሎ ይታሰባል።
በኬንያ የባሕር ዳርቻ አካባቢ የሚገኙ ሦስት ግዛቶች ባለፈው ሳምንት ጫት መሸጥ እና መቃምን ካገዱ በኋላ ጫት በሚያምርቱ አካባቢዎች ቁጣን ቀስቅሷል።
የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ግን ጫት ሕጋዊ ምርት መሆኑን ጠቅሰው ሽያጩም መከልከል የለበትም በማለት የግዛቶቹን እርምጃ ተቃውመዋል።
ሙጉካ በመባል የሚታወቀው የጫት ዓይነት ርካሽ እና ጠንካራነቱ የሚነገርለት ሲሆን ሞምባሳ፣ ኪሊፊ፣ ታይታ ታቬታ እና ክዋሌ በተባሉት የባሕር ዳርቻ ግዛቶች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።
ባለፈው ሳምንት የሞምባሳ ግዛት አስተዳዳሪ አብዱልሰዋማድ ሸሪፍ ናሲር ሙጉኮ የተባለው የጫት ዓይነት በተለይ በወጣቶች ላይ ባለው ጎጂ ውጤት ምክንያት ወደ ግዛታቸው እንዳይገባ፣ እንዳይዘዋወር፣ አዳይሸጥ እና እንዳይቃም ከልክለዋል።
አስተዳዳሪው እንዳሉት ሞምባሳ ውስጥ በሚገኙ የሱስ መገገሚያ ማዕከላት ከሚታከሙት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የጫት ሱሰኞች ናቸው።
በተመሳሳይም የኪሊፊ እና ታይታ ታቬታ ግዛቶች አስተዳዳሪዎችም በጫት ሽያጭ እና አጠቃቀም ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ አሳውቀዋል።
ይህ የግዛቶቹ ውሳኔ ጫቱ በሚመረትበት ኢምቡ ግዛት ያሉ ገበሬዎችን እና ነጋዴዎችን ተቃውሞ ቀስቅሷል። ውሳኔው ተግባራዊ ሆኖ የሚቀጥል ከሆነ ሥራቸውን እንዲያቆሙ እንሚያስገድዳቸው ገልጸዋል።
ጫት ከሚመረትበት ግዛት የመጡ የማኅበረሰብ መሪዎች በጫት ላይ የተጣለውን ዕገዳ በተመለከተ ሰኞ ዕለት ከፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተወያይተዋል።
የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ “ጫት [ሙጉካ] በሕግ የታወቀ ነው፤ ስለዚህም ከአገሪቱ ሕግ ተቃራኒ የሆኑ ውሳኔዎች ተቀባይነት የላቸውም” ብሏል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ እንዳሉት ጫት በአገሪቱ ሕግ እንደ አንድ ምርት የሚታወቅ ሲሆን፣ በዚህ የበጀት ዓመት በአገሪቱ ያለውን የጫት ምርት ለማስፋት መንግሥታቸው 3.7 ሚሊዮን ዶላር እንደሚመድብ አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ ሁለት የመብት ተከራካሪዎች ግዛቶቹ በጫት ላይ ያጣሉትን ዕገዳ ተቃውመው ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል።
ሞምባሳ ውስጥ የተጣለው የጫት ዕገዳ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ ባለፈው አርብ ከ10 በላይ የጫት ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቧል።
ዕገዳው ከበርካታ የሃይማኖት ተቋማት ድጋፍ ያገኘ ሲሆን፣ በሞምባሳ ያሉ ሙስሊም መሪዎች ጫት ከተከለከሉ ዕጾች መካከል እንደመደብም እየጠየቁ ነው።
ምንም እንኳን የኬንያ ብሔራዊ ፀረ ዕጽ ተቋም በጫት ላይ ዕገዳ ባይጥልም፣ ቅጠሉ በውስጡ በያዛቸው ንጥረ ነገሮች ምክንያት ጎጂ ብሎ ለይቶታል።
ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የክልሎች ግንኙነት የጋራ መድረክ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው
የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የክልሎች ግንኙነት የጋራ መድረክ በሐዋሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ በጋራ ገቢ አስተዳደር፣ ክፍፍል እንዲሁም በብሔራዊ የግጭት መከላከልና ሰላም ግንባታ ስትራቴጂ ላይ ከፌደራልና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል።
በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ -ጉባዔ አገኘው ተሻገር፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ
የህወሓት ታጣቂዎች በራያ ወረዳዎችና በአላማጣ ከተማና ዙሪያውን የሚገኙ አካባቢዎችን በወረራ በመቆጣጠር በንፁሃን የአማራ ተወላጆች ላይ ግድያ እንደፈፀሙ፣ በብዙ አስር ሽህ የሚቆጠሩ ወገኖችን እንዳፈናቀሉ እና ከፍተኛ መጠን ያለው የህዝብ ሃብትና ንብረት እንደዘረፉና እንዳወደሙ፣ በገጠር ቀበሌወች የአርሶ አደሩን እህል ጭነው እንዳጓጓዙ ተረጋግጧል።
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የህወሓት ኃይል የፈፀመውን ጥቃት እና ያደረሰውን ጥፋት በማጋለጥ የፌዴራሉና የአማራ ክልል መንግስት የወራሪው ሃይል ወደ ነበረበት ቦታ እንዲመለስ፣ ለፈፀመው ጥፋት ሃላፊነት እንዲወሰድ፣ ወደፊትም ተመሳሳይ ድርጊቶችን ከመፈፀም እንዲቆጠብ እና የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ በግልፅና በጥብቅ አሳስቧል።
ነገር ግን በሀገርና ህዝብ እንዲሁም በመንግስት ላይ ጭምር የጥላቻ ስሜትና የንቀት አባዜ የተጠናወተው ህወሓት ሰፊ ወታደራዊ ዝግጂት ሲያደርግ ቆይቶ ከቀናት በፊት በአፋር አካባቢዎች እና ባሳለፍነው ሳምንንተ መጨረሻ በአለማጣ ከተማ ላይ የወረራ ጥቃት በመክፈት ኗሪዎችን እየገደለ፣ ንብረታቸውን እየዘረፈ እና እያፈናቀለ ይገኛል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ታጣቂዎቻቸው ከአለማጣ ከተማ ዙሪያ አካባቢዎች መውጣታቸውን በማህበራዊ ድረ-ገፃቸው ላይ ያሳወቁት በአለማጣ ከተማ ህዝብ ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ለማወጅና ለፈረንጅ ግብረ-አበሮቻቸው ይህንኑ ለማብሰር ጭምር ነበር!
ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም ምንም አይነት ተጨባጭ ርምጃ ካለመውሰዱም በላይ በጉዳዩ ዙሪያ አቋሙን በግልፅ አለማሳወቁ የህወሓት ታጣቂዎች ለሚፈፅሙት ጥቃት እና ለሚያደርሱት ጉዳት እንዲሁም ለራያ ህዝብ በህወሀት ለሚደርስበት ያልተቋረጠ መከራና ጉስቁልና ይሁንታ እንደሰጠ የሚያስቆጥር ነው። በተለይ የህወሓት አመራሮች ድርጊቱን የሚፈፅሙት በፌዴራል መንግስት ፈቃድ ተሰጥቷቸው መሆኑን ደጋግመው ከመግለፃቸው አኳያ ሲታይ ጉዳዩን እጅግ አሳሳቢና አደገኛ ጭምር ያደርገዋል። ይህም በመሆኑ በራያ አካባቢወች በህዝብ ላይ እየደረሰ ላለው ግድያ፣ መጠነ ሰፊ መፈናቀል፣ ውድመትና ዘረፋ መንግስት በዝምታ ያየው በመሆኑ፣ በህወሓት አመራሮች የሚደረግ የ"መንግስት ፈቅዶልን" ፕሮፓጋንዳ ዙሪያ ምንም ባለማለቱ ለሚጠፋው ሁሉ ተጠያቂ ይሆናል።
በሌላ በኩል በአማራ ህዝብ ስም እታገላለሁ የሚሉ በርካታ ሀይሎች በዚህ ቀጠና ያለው የአማራ ህዝብ ለተደጋጋሚ ጥቃት ሲዳረግ ካለማውገዛቸው ባለፈ እየደረሰ ያለው የህዝብ መከራ እንዳይነገር መፈለጋቸው ምን ያህል የፖለቲካና የሞራል ዝቅታ ላይ እንዳሉና በህወሓት ተፅእኖ ስር እንደወደቁ ማረጋገጫ ነው። ይህ ችግር በህልውና ትግሉ ወቅት ጭምር የታየ ገመና ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በተደራጃ አግባብ በግልፅ እየተፈፀመ ይገኛል።
በተጨማሪ ለዚህ ሁሉ ችግር ባልተናነሰ ደረጃ ሃላፊነት የሚወስደው በተለይ በችግሩ ዙሪያ ላለው የግልፅነት ጉድለትና በማህበረሰቡ ላይ ለሚደረሰው ያልተቋረጠ ጥቃት የክልሉ መንግስት መሆኑ መዘንጋት የለበትም።
ስለሆነም:-
1).የፌዴራል መንግስት የህወሓት ታጣቂዎችን በወረራ ከያዟቸው አካባቢዎች ባስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ እንዲያደርግ እና በተደጋጋሚ ወረራ እየተፈጸመበት ለከፍተኛ ችግር ለተጋለጠው ህዝብ አፋጣኝ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፤
2 ).የአማራ ክልል መንግስት ህዝቡን ከወረራና ጥቃት የመከላከል የሚበልጥ ኃላፊነት እንደሌለ በመገንዘብ ህዝቡን በማስተባበር ግንባር ቀደም ሃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን፤
3).መላው የአማራ ህዝብ የህወሓት ፖለቲካዊ ፍልስፍና እና የየዕለት ተግባራቱ በአማራ ህዝብ ህልውና ላይ አደጋ የሚጥል መሆኑን ለአፍታም ባለመዘንጋት በአንድነት እንዲቆም፤
4). አለማቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህብረሰብ በህወሓት አማካኝነች በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ያልተቋረጠ ግፍና ወረራ እያስከተለ ያለውን ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ቀውስ እልባት እንዲያገኝና ህወሀት ለፈፀመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ እንዲሆን ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃልን።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላን ባጋጠመው መንገጫገጭ 12 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ!
ከኳታር ዶሃ ወደ አየርላንድ ደብሊን ሲጓዝ በነበረ የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ባጋጠመ መንገጫገጭ 12 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ።
ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላን በመጥፎ የአየር ጸባይ ምክንያት መንገጫገጩ ያጋጠመው ቱርክ አየር ክልል ውስጥ ሳለ ነበር ተብሏል።
በአውሮፕላኑ መናወጥ 6 መንገደኞች እና 6 የበረራ አስተናጋጆች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 8 ሰዎች ተጨማሪ የሕክምና ድጋፍ አስፈልጓቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
አውሮፕላኑ በቱርክ የአየር ክልል ውስጥ ሳለ በሚነቀንቅ የአየር ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍም በመዳረሻው ያለ ችግር አርፏል ተብሏል።
የደብሊን አየር ማረፊያን የሚያስተዳድረው ዲኤኤ ቃል አቀባይ የአየር ማረፊያው ሠራተኞች ለኳታር አየር መንገድ እና ለተሳፋሪዎች አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠታቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል።
በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ መንገደኞች በረራውን እጅግ በጣም አስፈሪ እና የሚያስጨንቅ ነበር ሲሉ ገልጸውታል።
በተመሳሳይ ከጥቂት ቀናት በፊት ከለንደን ወደ ሲንጋፖር ሲጓዝ በነበረ የሲንጋፖር አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ባጋጠመው ከፍተኛ መንገጫገጭ የአንድ ተሳፋሪ ሕይወት ሲያልፍ 140 መንደኞች እና የበረራ አስተናጋጆች መጎዳታቸው ይታወሳል።
ከአምስት ቀናት በፊት ባጋጠመው ክስተት ከተጎዱት መካከል 20 የሚሆኑት አሁንም በጽኑ ሕሙማን ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል ።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ ለመገንባት ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ
ሞስኮ የነዳጅ ማደያውን ለመገንባት ያሰበችው በሱዳን ነው ተብሏል
ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ ለመገንባት ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ፡፡
በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ጎረቤት ሀገር ሱዳን ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ እንትገነባ ጥያቄ እንደቀረበላት አስታውቃለች፡፡
በሱዳን ጦር ውስጥ አመራር የሆኑት ጀነራል ሰር አል አታ እንዳሉት ሱዳን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማግኘት በሚል ከሩሲያ የቀረበላትን ጥያቄ እንደምትቀበል ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ይህን ስምምነት በቀርቡ ሊፈራረሙ እንደሚችሉ አል አረቢያ ጀነራል ያሰር አል አታን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ እስካሁን በሱዳን ጦር አመራር ይፋ ስለተደረገው የቀይ ባህር ነዳጅ ማደያ ግንባታ ዙሪያ በይፋ ያለችው ነገር የለም፡፡
ሩሲያ በቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር አስተዳድር ጊዜ በፖርት ሱዳን ወታደራዊ ማዘዣ ለመገንባት ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡
ፕሬዝዳንቱ በመፈንቅለ ስልጣን ከተወገዱ በኋላ ይህ ስምምነት ሳይተገበር እስካሁን የቆየ ሲሆን የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ስምምነቱን እየገመገመ መሆኑን በተደጋጋሚ አስታውቋል፡፡
ምንጭ ፦ አልአይን
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የመጀመሪያው አጋማሽ በተጠናቀቀበት የእንግሊዝ FA Cup ፍፃሜ ማንችስተር ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲን 2 - 0 እየመራ ይገኛል። ይህንን ጠብቃችሁ ነበር? 🙂
#FACup #ManchesterUnited #ManchesterCity
ተዋንያን አለማየሁ ታደሰ እና መስከረም አበራ #በስንቱ በተሰኘው ተወዳጅ ሲትኮም ባሳዩት ብቃት ያሸነፉበት 13ኛው የለዛ ሽልማት ፕሮግራም በሂልተን ሆቴል በድምቀት ተከብሯል።
ከስፍራው የተወሰዱ ምስሎችን ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ 👇👇👇👇
https://youtu.be/BawKsJg8Fmk
#LezaAward #Ethiopiamovie #LezaAward2016 #EthiopianMusic #Besintu #AlemayehuTadesse #MeskeremAbera #NewayDebebe #RahelGetu #Rophnan
አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ከ ግንቦት 16 ጀምሮ ይካሄዳል።
ዓለም አቀፍ ሙዚቀኞችን ያሳትፋል የተባለው አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ከግንቦት 16 - 18 በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ ይካሄዳል የተባለ ሲሆን፥ የአፍሪካ ቀን ክብረ-በዓልም በጋራ እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
አፍሪጎ ባንድ ከዩጋንዳ፣ ሴልሞር ቱኩድዚ ከዚምባብዌ፣ ማቲው ቴምቦ ከዛምቢያ የሚሳተፉ ሲሆን ከኢትዮጵያም አንጋፋዎቹን ዳዊት ይፍሩ እንዲሁም ግርማ በየነ ተሳታፊ ናቸው።
በተጨማሪም ጆርጋ መስፍን፣ ያሆ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ፣ መሐሪ ብራዘርስና ዮሃና ሳህሌ ሥራቸውን ያቀርባሉ የተባለ ሲሆን በልዩ ሁኔታ የጆርጋ መስፍን የአልበም ምርቃት ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ይኖራልም ተብሏል።
በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ ይካሄዳል የተባለው ይህ መርሐግብር ከ12 ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን መግቢያ ዋጋ 700 ብር ነው ተብሏል። ተሳታፊዎች የመግቢያ ትኬቱን በኦላይን አማራጭ መግዛት እንደሚችሉም ተጠቁሟል።
በፌስቲቫሉ ሁለተኛ ቀን ከ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ፕሮጀክትና፣ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በጋራ "የአፍሪካ ቀን" በጋራ እንደሚካሄድ ሰላም ኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡
በዕለቱም የአፍሪካ ሀገራት እ.አ.አ በ 2030 ከአጠቃላይ በጀታቸው 1% ያህሉን ለኪነጥበብ፣ባህልና ቅርስ ዘርፎች እንዲመድቡ ጥሪ ይቀርባል ተብሏል።
ሰላም ኢትዮጵያ መንግስታት ለዘርፉ የሚሰጡትን በጀት እንዲጨምሩና ዘርፉ ያለውን አቅም ለማሳየት ከመንግሥታት ጋር፤ ከምርምር ተቋማት/ዩኒቨርሲቲዎች ከአርቲስቶች እንዲሁም ዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታውቋል።
በ"103 ተቋማት ላይ ድንገተኛ ቁጥጥር ተካሄደ
የአዲስአበባ ከተማ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ፍቃድ ሰጥቶ የሚቆጣጠራቸው የጤና ተቋማት በምን አይነት ደረጃ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ለማወቅ ለ7 ቀናት ቁጥጥር ስራ አከናውኗል።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የጤና ተቋማት ቁጥጥር ዳሬክቶሬት ለማህበረሰቡ ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል አልሞ የቅርንጫፍና የማእከል የዘርፉ ባለሞያዎችን በማሰባጠር የዘመቻ ስራውን እንዳካሄደ ገልጻል።
በቁቁጥር ስራው ባለስልጣኑ ከሚቆጣጠራቸው 115 አጠቃላይ ሆስፒታል፣ሴንተር፣ላብራቶሪ፣ስቴሻሊቲ ክሊኒኮችን ጨምሮ 103 በሚሆኑት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩ ተካሂዷል።
በተካሄደው የዘመቻ ስራ በአብዛኛው ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበት ግንባታ (premises)ችግር ፣ጊዜ ያለፈባቸው የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች መገኝት፣የቆሻሻ አወጋገድ ችግር መኖር እንዲሁም በአንቡላንሶች ውስጥ መያዝ ያለባቸው የህክምና መሳሪያዎች አለሟሟት በቁጥጥር ስራው የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶች እንደሆኑ ተጠቁሟል።
ግኝቱ በተገኝባቸው ተቋማት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያስተካክሉ ግብረመልስ መስጠትና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እርምጃ እንደተወሰደ የዘርፉ ዳሬክተር አቶ ገልገሎ ኦልጅራ ገልጸዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ቦይንግ ኩባንያ የአፍሪካ ዋና ጽሕፈት ቤትን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው
ግዙፉ የአሜሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ የሆነው ቦይንግ የአፍሪካ ዋና ጽሕፈት ቤትን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው፡፡
ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የአቪዬሽን ጉባኤ ላይ እየተካፈለች ትገኛለች። በመድረኩ ላይ ኩባንያው በሚቀጥለው ዓመት ቢሮውን በአዲስ አበባ ለመክፈት ማቀዱ ተገልጿል፡፡
ኩባንያው ይህን ውሳኔ ያስታወቀው በአፍሪካ ከግዙፍ አየር መንገዶች መካከል ተጠቃሽ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 65 አውሮፕላኖቹን በቦይንግ እንደሚተካ ማስታወቁን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - ግንቦት 14፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 22 , 2024
👉የአማራና ትግራይ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል
👉 አማራ ክልል በወሰን ጉዳይ ቁርጥ ያለ ውሳኔ አስተላለፈ
👉 ከሰሙኑ በአማራ እና ትግራይ አዋሳኝ በርካታ ንፁሃን ተገድለዋል
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/sDOnYbw7J7Q
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበ አዋጅ ላይ ነው።
ከህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ እነዚህን አካላት ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የሚያስችል ስርዓት በነባሩ አዋጅ ላይ አልተካተተም። በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ እና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ መልሶ መመዝገብ የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ረቂቅ የአዋጅ ማሸሻያ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
2. በመቀጠልም ምክር ቤቱ የተወያየው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንብረት ማስመለስ አዋጅ ላይ ነው። የወንጀል ፍሬ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመያዝ፣ ለማገድ፣ ለመውረስ ወይም ለማስተዳደር የሚያስችል ግልጽና ዝርዝር የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ፤ በተለያዩ አዋጆች ውስጥ ተበታትነው ያሉትን የንብረት ማስመለስ እና አስተዳደር ድንጋጌዎች በአንድ ወጥ ሕግ ውስጥ በማካተት ለአፈጻጸም ምቹ የሆነ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
3. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አድርጎ ስለማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቀረበው አዋጅ ላይ ነው። በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀል የደህንነት ስጋት ከመሆኑ በተጨማሪ የፋይናንስ ስርዓቱ የተረጋጋ፣ ግልጸኝነት ያለው፣ ጤናማና ቀልጣፋ እንዳይሆን የሚያደርግ ነው።
ስለሆነም ይህን ወንጀል ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
4. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በቀረበው አዋጅ ላይ ነው። የነዳጅ ውጤቶች ካላቸዉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ አንጻር አቅርቦታቸውን፣ ክምችታቸውን፣ ስርጭታቸውን፣ ዋጋቸውን፣ ጥራታቸዉን እና ደህንነታቸውን መቆጣጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤ እንዲሁም ከአስመጪ ጀምሮ እስከ ተጠቃሚዎች ድረስ ያለው ግብይት ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ ፍትሐዊ እና ተደራሽ የሆነ የአቅርቦት ሰንሰለት እና የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - ግንቦት 22፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 30 , 2024
👉ንብ ባንክ ከ 10 በላይ የማኔጅመንት አባላቱን አባረረ
👉 ደላሎችን እና ዳኞች ያልተገባ ጥቅም እንዳያገኙ የሚያደርገው አዲስ አዋጅ
👉በአማራ ክልል የተገደለው የአለም አቀፍ ድርጅቱ ሰራተኛ ጉዳይ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/KOXp9VCYcTw
ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የመንግስት አስተዳደሮች፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም ያስቀራል የተባለለት አዋጅ ሊወጣ ነው።
በካሳ ክፍያ ሂደት የመንግስት አስተዳደር ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋናው የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ የተባለው መሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትን እና ተነሽዎች መልሰው የሚቋቋበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለማሻሻል ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።
በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንደተናገሩት ለመሰረተ-ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ መዘግየት ዋናውና ትልቁ ማነቆ የልማት ተነሺዎች የሚጠይቁት የተጋነነ የካሳ ክፍያ መሆኑን ገልጸው፤ ንብረት የሚገምቱ እና ካሳ የሚከፍሉ ተቋማት ወደ አንድ ሊመጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በማህበረሰቡም ፕሮጀክቶች ተገንብተው ከሚሰጡት ጥቅም ይልቅ፤ ከካሳ ክፍያ የሚገኘውን ጥቅም አስበልጦ የማየት አስተሳሰብ በመኖሩ፤ ትክክለኛ እና ወቅቱን ያገናዘበ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም የአዋጁ መሻሻል አስፈላጊነቱ የላቀ እንደሆነም ባለድርሻ አካላት አንስተዋል።
የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በበኩላቸው የአዋጁ መሻሻል በካሳ ክፍያ ሂደቱ በታችኛው እርከን የመንግስት አስተዳደር፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋና የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ማሻሻያ አዋጁ መሰረተ ልማቶች ሲገነቡ የንብረት ግመታው እና የካሳ ክፍያው በክልልና በወረዳ መዋቅሮች የሚፈጸም መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ዜጎች ቅሬታ ሲያነሱም በአቅራቢያቸው የፍትህ አገልገሎት እንዲያገኙ የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም
ኢትዮጵያ፦ እለተ ረቡዕ የኢት ዜና - ግንቦት 21፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 29 , 2024
👉አቡነ ማትያስ ዛሬ እውነታውን ተናገሩ
👉 በጊዜያዊ አስተዳደሩ እና በህውሃት መካከል ምን ተፈጠረ
👉የሰው ህይወት እንደቀልድ እያረገፈች ያለችው ድሮን ጉድ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/KD0IF87vIpc
ቤተክርስቲያኗ የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል አለች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል ብላለች፡፡ ቤተክርስቲያኗ ይህንን ያለችው ዛሬ በተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ነው፡፡
የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ብለዋል፡፡
ቤተክርስቲያኗ የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋልም ብለዋል፡፡
ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጎደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
Via:— EOTC
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ኢትዮጵያ፦ እለተ ሰኞ የኢት ዜና - ግንቦት 19፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 27 , 2024
👉የፈረንሳዩ አምባሳደሩ በቤታቸው ሞተው ተገኙ
👉 አብን ህውሃትን ወነጀለ ራያ ላይ የተፈጠረውን ተናገረ
👉አውሮፕላኑ በመንገጫገጩ 12 ሰዎች ጉዳት ገጠማቸው
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/gFNqrMybENI
በስሪላንካ የፈረንሳይ አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ሞተው ተገኙ፡፡
አምባሳደር ጂን ፓክቴት በፈረንጆቹ ጥቅምት 2022 ላይ ነበር በስሪላንካ እና ማልዴቪስ ፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው ወደ ኮሎምቦ የተጓዙት፡፡
የ53 ዓመቱ ዲፕሎማት በመኖሪያ ቤታቸው ህይወታቸው አልፎ እንደተገኘ ሲጂቲኤን የስሪላንካ ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ አምባሳደሩ ህይወታቸው ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረ የተገለጸ ሲሆን ተጨማሪ ምርመራዎች በመካሄድ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
በፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ለረጅም ጊዜ በውጭ ሀገራት የሚካሄዱ የፈረንሳይ ቋንቋ እና ባህል ማስፋፋት ላይ ሲሰሩ የቆዩ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማት ነበሩ ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በግሎባል ሄልዝ ተቋም ውስጥ የፈረንሳይ ተወካይ፣ በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት ወይም ኔቶ የፈረንሳይ ተወካይ እና በአሜሪካ የፈረንሳይ ኢምባሲ ውስጥ በተለያዩ ሀላፊነቶች ላይ እንደሰሩ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ቃል አቀባይነትን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ሀገራቸውን አገልግለዋልም ተብሏል፡፡
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር አሸነፉ
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር ሦስተኛውን ሽልማት አሸነፉ።
በቻይና ሼንዘን ከተማ በኮምፒውቲንግ ትራክ የተሳተፉት ሦስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሦስተኛውን ሽልማት ከማሌዢያ፣ ሜክሲኮ እና ኬንያ ቡድኖች ጋር ተጋርተዋል።
ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሦስት የውድድር ትራኮች ተከፋፍሎ የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በውድድሩ ከአርባ ምንጭና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙ ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ሽልማት አሸንፎ ዛሬ ወደ ሀገሩ መመለሱን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ሚኒስቴሩ የተማሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እድል የሚፈጥሩ ውድድሮች ላይ ተሳትፎውን በማሳደግ ከዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ÷ ውድድሩን ላሸነፉ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ማንችስተር ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲን 2 - 1 በማሸነፍ የFA Cup አሸናፊ ሆኗል። የዩናይትድ ደጋፊዎች እንኳን ደስ ያላችሁ።
#FACup #ManchesterUnited #ManchesterCity
በዚህ ሳምንት በመቀነት ፕሮግራም ምዕራፍ ሁለት ክፍል - 2 ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ ስለ " የመብቶች እንቅስቃሴዎች የአካል ጉዳተኛ ሴቶችን መብቶች አካትተዋል? " በሚል ጥያቄ አዘል ርዕስ የምንዳስስ ይሆናል ::
ሙሉውን ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇
https://youtu.be/OG7jUdFRlfs
ኢትዮጵያ፦ እለተ አርብ የኢት ዜና - ግንቦት 16፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 24 , 2024
👉ባለስልጣን መ/ቤቱ ድንገተኛ ቁጥጥር አካሄደ
👉 መከላከያ በፈፀመው ጥቃት ንፁሃን መሞታቸው ተዘገበ
👉 ባይደን ለኬንያው ፕሬዝዳት ያደረጉት ያልተጠበቀ አቀባበል
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/6ipbgWEqsmU
የጎረቤት ኬንያ ፕሬዜዳንት በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
እ.ኤ.አ ከ2008 ወዲህ ወይም ከ16 ዓመት በኃላ ነው ዋይት ሃውስ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ መሪ በዚህ ደረጃ ተቀብሎ እያስተናገደ የሚገኘው።
አሜሪካን እየጎበኙ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከፍ ያለ አቀባበል እና ከፍተኛ የቀድሞና የአሁን ባለስልጣናት በተገኙበት ልዩ እራት ግብዣ እንደተደረገላቸው ታውቋል።
ከፕሬዜዳንት ጆ ባይደንና ከሌሎች ባለልሰጣናት ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉም ሲሆን ሁነኛ ስምምነቶችም ከአሜሪካ መንግሥት ጋር መፈራረማቸው ተሰምቷል።
ሩቶ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማ ጋርም ተገናኝነትው መክረዋል።
በሌላ በኩል ፥ ኬንያ የሀገሪቱን የጸጥታ ስራዎች እና የሰላም ማስከበር ተልእኮዎቿን ለማሳደግ 16 በአሜሪካ የተሰሩ እጅግ ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች ልትቀበል እንደሆነ " ሲትዝን ቲቪ " ዘግቧል።
ይህ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በዋሽንግተን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ለኬንያ ካበረከቱት መልካም ነገሮች አንዱ ነው ተብሏል።
ሂሊኮፕተሮቹ እ.ኤ.አ ከ2024 እስከ 2025 መጨረሻ ናይሮቢ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋይት ሀውስ አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኬንያ በመስከረም ወር 150 " M1117 " የታጠቁ እጅግ ዘመናዊ የደህንነት ተሽከርካሪዎችን ትቀበላለች።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - ግንቦት 15፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 23 , 2024
👉የመሣሪያ ግምጃ ቤቱ ተዘረፈ
👉 ጎንደር አለምወጭ የስደተኞች መጠለያ አንድ ኤርትራዊት ተገደሉ
👉 ቦይንግ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቅርንጫፉን ሊከፍት ነው
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/IElzKFf7bhg
ኢትዮጵያ የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን ወደ ኤምባሲ ማሳደጓን የሶማሊላንድ ሚኒስትር ተናገሩ
ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ፣ ሃርጌሳ የሚገኘውን የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን ሙሉ አገልግሎት ወደሚሰጥ ኤምባሲ ማሳደጓን የሶማሊላንድ ሚኒስትር ገለጹ።
የሶማሊላንድ የመረጃ፣ የባህል እና የብሔራዊ መመሪያ ሚኒስትር አሊ ሐሰን መሐመድ (አሊ ማርሃን) ለቢቢሲ ሶማሊኛ ከቀናት በፊት ራሷን በነጻ አገርነት ያወጀችው የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ ቆንስላው ወደ ኤምባሲ ማደጉን አስመልክቶ የተናገሩትን አረጋግጠዋል።
“የኢትዮጵያ የቆንስላ ጽህፈት ቤት ሙሉ አገልግሎት ወደሚሰጥ ኤምባሲ ማደጉን አስመልክቶ ከፍተኛ ስፍራ በሚሰጠው ዕለት ፕሬዝዳንቱ ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል” ሲሉ ሚኒስትሩ ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ ሶማሊላንድ ነጻነቷን በማወጅ እንደ አገር የተመሠረተችበትን ዕለት ግንቦት 10/2016 ዓ.ም. 33ኛ ዓመት ስታከብር ሃርጌሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ወደ ኤምባሲ ማደጉን ለመጀመሪያ ጊዜ መናገራቸውን በሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መረጃ ያስረዳል።
የሶማሊላንድ ባለሥልጣናት የሰጡትን መረጃ አስመልክቶ ቢቢሲ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ የሆኑትን አቶ ነብዩ ተድላ የጠየቀ ሲሆን፣ ጉዳዩ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሳምንታዊ መግለጫ ላይ ሊነሳ እንደሚችል ጠቁመው በአሁኑ ሰዓት ይህንን በተመለከተ የሚሰጡት መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የሃይማኖት ተቋማት የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርታቸውን ለመንግሥት እንዲያቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ
ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡
" የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጅ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውንም ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው የሚደነግግ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
የሃይማኖት ተቋማቱ የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን እንደሚኖርበትና የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን እንዳለባቸውም ይገልጻል።
አንድ የሃይማኖት ተቋም በራሱ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ፣ ለዚሁ ሥራ የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ እንዳለበትም ተደንግጓል፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ ይኖርበታል ተብሏል።
በተጨማሪም የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስምና አድራሻ፣ የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነትና መጠን፣ እንዲሁም ስጦታው ወይም ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ የሃይማኖት ተቋማቱ ጨምርው ማሳወቅ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡