በፊሊፒንስ ለወንጀለኞች አዲስ የፊት ገጽታን በቀዶ ህክምና የሚሰጡ ሚስጥራዊ ሆስፒታሎች ተገኙ
በፊሊፒንስ የሚገኙ ሚስጥራዊ ሆስፒታሎች በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኞችን ለማስመለጥ የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል ።በግንቦት ወር ፖሊሶች በማኒላ ደቡባዊ ዳርቻዎች ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ሁለት ህገወጥ ሆስፒታሎች መያዛቸዉን የፖሊስ ቃል አቀባይተናግረዋል።
ከሁለት ወራት በፊት በፓሳይ ከተማ ውስጥ የፀጉር ንቅለ ተከላ መሳሪያዎች፣ የጥርስ ተከላ መሳሪያእና ቆዳን የሚነጣ መድኃኒት ተይዘዋል።
የፕሬዚዳንቱ ፀረ-የተደራጀ ወንጀል ኮሚሽን (PAOCC) ቃል አቀባይ ዊንስተን ጆን ካሲዮ “በእነዚያ ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ አዲስ ሰው መፍጠር ትችላለህ” ብለዋል።
በክትትል ላይ ያሉት ሁለቱ ህገወጥ ሆስፒታሎች በፓሳይ ከሚገኘው በአራት እጥፍ እንደሚበልጡ ይታመናል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል ።
ደንበኞቻቸው ከኦንላይን ቁማርተኚች የተውጣጡ፣ በፊሊፒንስ በህገ ወጥ መንገድ የሚሰሩትን ያካትታሉ ሲሉ ካሲዮ ተናግሯል።
የተያዙት ሶስት ዶክተሮችቹ ሁለቱ ከቬትናም እና አንድ ከቻይና ናቸዉ፡፡ቻይናዊ ፋርማሲስት እና አንድ የቪትናም ነርስ በፓሳይ ተይዘዋል፡፡አንዳቸውም በፊሊፒንስ ውስጥ ለመስራት ፈቃድ የላቸዉም፡፡
በአዲስ አበባ ከ50 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ
የንግድ ሥርዓቶችን ተላልፈው በተገኙ ከ50 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ገለጸ።
የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውነት አየለ፥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመዲናዋ በሚገኙ ከ400 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ተደርጓል።
በዚህም ልዩ ልዩ የንግድ ሥርዓቶችን ተላልፈው በተገኙ ከ50 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።
ከዚህ ውስጥ 21 ሺህ የንግድ ተቋማት እንዲታሸጉ፣ ምርታቸው ከገበያ እንዲሰበሰብና ሌሎች ተመሳሳይ እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ኢዜአ ዘግቧል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ፈረንሳይ የወንድ የዘር ፍሬ እጥረት ገጠመኝ እያለች ነው
👉 በጎ ፈቃደኛ ወንዶች እና ሴቶች የዘር ፍሬ እና እንቁላል እንዲለግሱ ጥሪ አቅርባለች
በፈረንሳይ ከበጎ ፈቃደኛ ሰዎች በተለገሰ የዘር ፍሬ ልጅ መውለድ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር በየዓመቱ እያሻቀበ ነው ተብሏል
የፈረንሳይ ባዮ ሜድሲን ኤጀንሲ እንደገለጸው በሀገሪቱ ያለው የወንድ የዘር ፈውሬ እና የሴት እንቁላል ከፍላጎቱ ጋር የማይጣጣም እንደሆነ አስታውቋል፡፡
እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ በሀገሪቱ ያለው የዘር ፍሬ እና እንቁላል ለጋሽ በጎ ፈቃደኞች እና ልጅ መውለድ የሚፈልጉ ሰዎች ብዛት የተጣጣመ አይደለም፡፡
ለአብነትም በፈረንጆቹ 2021 ላይ 20 ሺህ ሰዎች ከበጎ ፈቃደኞች በተለገሰ የዘር ፍሬ እና እንቁላል ልጅ ለመውለድ ያመለከቱ ሲሆን ይህ ፍላጎት በ2022 በሁለት ሺህ ጨምሯል ተብሏል፡፡
እንዲሁም በ2023 ይህ አሀዝ በ5 ሺህ ጭማሪ ሲያሳይ በተያዘው ዓመት ደግሞ የበለጠ እየጨመረ እንደሄደ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
አሁን ላይ በፈረንሳይ ከ7 ሺህ በላይ ሴቶች ልጅ ለመውለድ ከበጎ ፈቃደኞች የተለገሰ የወንድ ዘር ፍሬ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
ይሁንና የወንድ የዘር ፍሬ ለመለገስ ፈቃደኛ የሆኑ በጎ ፈቃደኛ ወንዶች ብዛት 676 ብቻ ናቸው የተባለ ሲሆን ፍላጎቱን ለማሟላት 1 ሺህ 400 በጎ ፈቃደኛ ወንዶች ያስፈልጋሉ ተብሏል፡፡
በአንጻሩ ከ26 ሺህ በላይ ሴቶች እንቁላላቸውን ለመለገስ በሂደት ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን አብዛኞቹ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆናቸው እንደሆኑ ተገልጿል።
በአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝ እና ሆላንድ ለግማሽ ፍፃሜ በማለፍ ስፔን እና ፈረንሳይን ተቀላቅለዋል። ዋንጫውን ማን ያነሳል?
#Euro2024 #England #Holland #Spain #France
ከሚሴ‼
የከሚሴ ዋና አስተዳዳሪ በጥይት ተመተው ተገደሉ
አማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ ዛሬ ከቀኑ 7:10 አካባቢ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።
አቶ አህመድ ኬሚሴ ረፋኡልረሽድ መስጅድ ጁሙዓ ሰላት ሰግደው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ ሰፈር አካባቢ እንደደረሱ በተተኮሰባቸው ጥይት ነው የተመቱት ተብሏል።
ወደ ህክምና ተቋም ቢወሰዱም በህይወት መትረፍ እንዳልቻለ የመረጃ ምንጮቹ ጠቁመዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አሰናበቱ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) አሰናብተዋል።
ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ.ም መሾማቸው ይታወሳል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ማሰናበታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አይነ ስውርና አካል ጉደተኛ የሆነው የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂያችን
"የአይቻልም እና የአይሆንም መንፈስን መስበር ከተቻለ የማይቻል ነገር የለም " ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ
ወጋየሁ በዩኒቨርሲቲያችን በአማረኛ ቋንቋ ስነ-ጽሑፍ እና ፎክሎር ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ እና የባለብዙ ተሰጥኦ ባለቤት ታታሪ ወጣት ነው። በፈተና የታጀበና በድል የተጠናቀቀ ጉዞ የማዕረግ ምሩቁን ሕይወት ይገልጻል።
የገጠሙት ፈተናዎች ለበርካታ ዓመታት ትምህርት እንዲያቋርጥ ቢያስገድዱትም ህልሙን ለማሳካት ዳግም ወደ ትምህርት አለም ተመልሶ ትምህርቱን በጥሩ ውጤት በድል ያጠናቀቀ የማዕረግ ተመራቂያችን ነው።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአካል ጉዳተኞች የበለጠ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በቅርቡ እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ዶላር ዋጋ ያላቸው 30 ዘመናዊ ዲጂታል ብሬሎችን ተደራሽ ማድረጉ ይታወሳል።
(ምንጭ፡ አአዩ)
የ2017 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ በሙሉ ድምፅ ጸደቀ!
የ2017 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ጸድቋል።
በጀቱን አስመልክቶ የምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ምክር ቤቱ በቀረበለት በጀት ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽፅ አጽድቆታል።
በጀቱ ከአምናው በጀት ጋር ሲነጻጸር የ169 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተመልክቷል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
"የሶማሊያ መንግስት እኛን ለመክሰስ ሀገር ለሀገር መሄድ አያስፈልገዉም ፤ አዲስአበባ መምጣት ይቻላል" ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ የዉይይት ጥሪ አቀረቡ
እየሻከረ መጥቷል የሚባለዉ የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት ላይ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ሃሳባቸዉን በዛሬዉ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ አመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ሃሳባቸዉን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ በሰጥቶ መቀበል መርህ የተፈራረሙትን የባህር በር ስምምነት ተከትሎ ሶማሊያ በአንድነቷ ላይ አደጋ የጣለ መሆኑን ስትገልጽ ቆይታለች። የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድም ወደተለያዩ ሀገራት እያቀኑ ሶማሊያ ድጋፍ እንድታገኝ ጥረት ማድረጋቸዉ ይታወቃል።
በዚህ የሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ግንኙት ላይ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ፤ የሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ህዝብ ወንድማማቾች ናቸዉ ያሉ ሲሆን የሶማሊያ መንግስት ችግሩን ለመፍታት የመረጠዉን መንገድ ግን ተችተዋል።
የሶማሊያ መንግስት ችግሩን በንግግር ከመፍታት ይልቅ በሰፈሩ እየዞረ እኛን መክሰስ መርጧል ብለዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ለሶማሊያ ምክር ብለዉ በለገሱት ሃሰብ ፥ የሚወጡ ወጪዎችን ተከትሎ የሶማሊያ መንግስት አንድ ት/ት ቤት ሞቃዲሾ ላይ ቢሰራ ይጠቀማል ማለታቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።
ከጎረቤት ሀገራት ምላሽ አጥተን በቆየንበት ሶማሊላንድ ፈቃደኝነቷን በመግለጿ እንጂ በሶማሊያ አንድነት ላይ አደጋ ለመፍጠር አስበን አይደልም ሲሉም አመላክተዋል። "እኛን ለመክሰስ ሀገር ለሀገር መሄድ አያስፈልግም ፤ አዲስአበባ መምጣት ይቻላል ለመነጋገር ዝግጁ ነን ሲሉ የዉይይት ጥሪ ማቅረባቸዉን ብስራት ሰምቷል።
ሶማሊያ እንድትጎዳ ልጆቻችንን አንልክም ነበር ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ የባህር በር ግን ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል የሚለዉን አስምረውበታል። ተባብረን አብረን ብንሄድ የቀጠናዉ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።
ኤርትራን ጨምሮ ለጎረቤት ሀገራት ባቀረቡት ጥሪም ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ በጋራ ተጠቃሚነት የባህር በር የምታገኝበትን መንገድ መመልከቷን እንደምትቀጥል አመላክተዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የተከበሩ አብርሃም በርታ ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ያቀረቡት ጥያቄ
"የመንግስት መዋቅር በሌቦች ተጠልፏል። መንግስት ሙሰኞችን ከመቅጣት ይልቅ ሹመት እየሰጠ ነዉ። የፋይናንስ ጥሰት እየተፈጸመ ነዉ። አፋጣኝ እና አስተማሪ እርምጃ ካልተወሰደ የሀገር ህልውናን መፈተኑ አይቀርም። መንግስቶ ይህንን ለመፍታት ቃል ከመግባት ባለፈ ምን ታስቧል"?
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የተወካዮች ምክር ቤት ህወሓት ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን የአዋጅ ማሻሻያ አጸደቀ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድ አዋጅ አጸደቀ። በ2011 ዓ.ም. የወጣውን “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን” የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በሁለት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው።
“በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ” የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው። ይህ የአዋጅ ማሻሻያ፤ “ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል” በሚል “ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ” የተደረገው ህወሓት በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል።
“አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል” ሲል ዛሬ የጸደቀው አዋጅ ደንግጓል።
Via Ethiopia insider
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ኢትዮጵያ፦ እለተ ሰኞ የኢት ዜና - ግንቦት 26 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - Jun 3 , 2024
👉 አብይ አህመድ ስለ ሽግግር መንግስት ምን አሉ
👉ሶማሊያ የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች አስጠነቀቀች
👉በሙቀት መጨመር ምክንያት ከ 50 በላይ ሰዎች ሞቱ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/61YRnzBbvXM
የቻይናው ሻንጋይ ጂአዎ ቶንግ ዩኒቨርስቲ አይነ ስውራንን መንገድ የሚመራ አዲስ የሮቦት ቴክኖሎጂ አስተዋውቋል።
ባለ 6 እግሩ ሮቦት መንገድ ጠቋሚ ሴንሰር፣ የሌዘር ራዳር ቴክኖሎጂ እና የናቭጌሽን ሲስተም የተገጠመለት ሲሆን ከሰው በሚሰጠው የድምጽ ትዕዛዝ ካሰቡት ቦታ ያለምንም ችግር ማድረስ የሚችል ነው ተብሏል።
ከቴክኖሎጂው ፈጣሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ጃው ፌንግ ሮቦቱ በተለይ ለጉዞ አይንን ተክቶ ማገልገል የሚችል ነው ብለውታል።
የትራፊክ መብራቶችን እና ሌሎች የደህንነት ማስጠንቀቂያዎችን ጠንቅቆ የሚያውቀው ሮቦት በተጨማሪም አስቸጋሪ የመንገድ ላይ ሁኔታዎችን በመለየት አይነስውራን በመንገድ ላይ ከሚያጋጥማቸው አደጋ ይከላከላል ተብሎለታል።
ሮቦቱ በሚኖርበት ከተማ ላይ ያሉ ቤተመጽሀፍቶች፣ የመንግስት ተቋማት፣ ቤተእምነቶችን እና ሌሎችንም በኢንተርኔት አማካኝነት መዝግቦ የሚያስቀምጥ ሲሆን ከሰዎች በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መጓዝ የሚችል ነው።
የቴክኖሎጂው ባለቤቶች ሮቦቱ የተገጠሙለት 6 እግሮች መሰናክሎችን እና የማይመቹ መንገዶችን እና ደረጃዎችን ያለ ችግር እንዲጓዝ የሚያደርጉት ነው።
ከዚህ ባለፈም በተመጠነ የጉዞ ፍጥነት በሰከንድ 3 ሜትሮችን መጓዝ የሚችል ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ባለቤቱ በሚፈልገው የጉዞ መጠን እንዲፈጥን አልያም እንዲዘገይ የሚነገረውን ትዕዛዝ ይቀበላል።
በተጨማሪም አይነ ሰውራን የጤና ችግር እና ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥማቸው በተገጠመለት አላርም የእርዳታ ጥሪን ማድረግ ይችላል።
እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ ከሆነ በቻይና 17.31 ሚሊየን አይነ ስውራን የሚገኙ ሲሆን በተለምዶ አይነ ስውራን ከሚጠቀሙት መንገድ ጠቋሚ በትር (ኬን) ባለፈ የሰለጠኑ ውሾችን ለመንገድ መሪነት ይጠቀማሉ፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት በቻይና የሚገኙት የሰለጠኑ ውሾች ቁጥር 40 ሺ ብቻ ነው።
እነዚህ ውሾች ለስልጠና እና ተያያዥ ጉዳዮች ከሚጠይቁት ወጭ አንጻር አዲሱ የሮቦት ቴክኖሎጂ ወደ ገበያ ሲገባ ተመራጭ እንደሚሆን ተነግሯል።
ሮቦቱ በአሁኑ ወቅት የመስክ ሙከራ ላይ ሲሆን ዩኒቨርስቲው ለገበያ ገና ባያቀርበውም 20 ትእዛዞችን መቀበሉን ገልጿል።
በአለም አቀፍ ደረጃ 50 ሚሊየን አይነ ስውራን እንዳሉ ይነገራል ከዚህ ውስጥ 85 በመቶዎች ቢያንስ በወር አንድ ግዜ የተለያዩ አደጋዎች ያጋጥሟቸዋል።
አል አይን
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
👉እንድታውቁት
በመንገድ ኮሪደር ልማትና በአስፓልት የማንጠፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
መዚህ መሰረት ፡-
- ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
- ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
- ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
እንዲሁም በውስጥ ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አየር መንገድ የሚወስዱ መንገዶች ከዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በየዕለቱ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:30 ሰዓት ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ይሆናሉ።
አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዳለባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
#AddisAbabaPolice
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በዚህ ሳምንት በመቀነት ፕሮግራም ምዕራፍ ሁለት ክፍል - 3 "መንግስት ይከሰሳል ፤ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሙግት " በሚል ርዕስ የምንዳስስ ይሆናል ::
ሙሉውን ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇
https://youtu.be/EzFzmce5uDk
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጦርነቱ በኋላ የሱዳን ጦር መሪዎች ዋና መቀመጫ ወደሆነችው ፖርት ሱዳን ከተማ ገቡ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት ጠዋት ሱዳን መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በትዊተር ገጹ አስታወቋል።
ጽ/ቤቱ እንደገለጸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጦርነቱ በኋላ የሱዳን ጦር መሪዎች ዋና መቀመጫ ወደሆነችው ፖርት ሱዳን ከተማ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ ለሱዳን ጦርነት ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ጥረታቸውን ይቀጥላሉ ብሏል ጽ/ቤቱ።
የሱዳን ጦርን በሚመሩት ጀነራል አልቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን በሚመሩት ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ መካከል ባለፈው አመት ሚያዝያ ወር አጋማሽ የተጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።
ኢትዮጵያ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ግጭቱን በንግግር እንዲፈቱ እንደምትፈልግ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ባወጣቻቸው መግለጫዎች መግለጿ ይታወሳል።
ግጭቱን በድርድር ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች እስካሁን አልተሳኩም።
በአሜሪካ እና በሳኡዲ አረቢያ አመቻችነት በጂዳ ተጀምሮ የነበረው ድርድር ያለውጤት መቋረጡ ይታወሳል።
በሱዳኑ ጦርነት በሺዎች የሚቅጠሩ ሲገደሉ ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።ተፋላሚ ኃይሎቹ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት በማድረስ ክስ ቢቀርብባቸውም፣ እርስበርሳቸው ከመወነጃጀል ውጭ ኃላፊት አልወሰዱም።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የእገታ ተግባር አወገዘች፣ የህግ የበላይነት እየተሸረሸረ ነው ስትል አሳስባለች
“ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በተደጋጋሚ በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች እየተፈጸሙ ያሉ የንጹሃን እገታዎች፣ የተራዘመ ግጭት ወንጀለኞች እንዲበረታቱ እና የህግ የበላይነትን እንደሚሸረሽር እንደሚያደርግ ማሳያ ነው” ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤሪቪን ማሲንጋ ገለጹ።
“ለገንዘብ ሲባል በተማሪዎች እና በንጹሃን ላይ የሚፈጸም እገታ ሊቆም ይገባዋል” ሲሉ አምባሳደሩ በኤምባሲው ይፋዊ የኤክስ ገጽ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አሳስበዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት ከ100 በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መታገታቸውን በአብነት ጠቅሰዋል።
ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በአውቶብሶች ሲጓዙ የነበሩ ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በታጣቂዎች መታገታቸው መዘገቡ ይታወሳል።
እገታው የተፈፀመባቸው በዋናነት የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲሆኑ ኢላማ የተደረገባቸው በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ መሆኑም በዘገባው ተካቷል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት “ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱን በንግግር ለመፍታት ዝግጁ አይደለችም” አሉ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የገቡበትን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በንግግር ለመፍታት ኢትዮጵያ ዝግጁ አይደለችም ሲሉ ተናገሩ።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም. በአገሪቱ ምክር ቤት የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ መንግሥታቸው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱን ለማርገብ ፍላጎት ቢኖረውም፤ በአዲስ አበባ ያለው መንግሥት ግን ለውይይት ዝግጁ አይደለም ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕምድ ከጥቂት ቀናት በፊት “የሶማሊያ መንግሥት እኛን ከማናገር፣ በየሰፈሩ እየዞረ እኛን መክሰስ መርጧል” ብለው ከተናገሩ በኋላ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሐሙስ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም. ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ ላይ ሰለሶማሊያ ጉዳይ ሲናገሩ፤ “እኛን ለመክሰስ አገር ለአገር መሄድ አያስፈልግም፤ አዲስ አበባ መምጣት ይቻላል። ለመነጋገር ዝግጁ ነን. . . ” ብለው ነበር።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ሁለቱ አገራት የገቡበትን ቀውስ ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግሥት ጨርሶ ሊያነጋግረን አልሞከረም ብለዋል።
“ኢትዮጵያ እንደ ጎረቤት አገር ወቅታዊ ጉዳዮችን በትብብር ለመፍታት አናግራን አታውቅም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በአንጻሩ “እየተዘዋወሩ ሽምግልና ይጠይቃሉ” ሲሉ ተደምጠዋል።
BBC
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በዚህ ሳምንት በመቀነት መሰናዶ ከባለፈው የቀጠለ ክፍል - 2 ፅኑዋ ሜላት | የአሲድ ጥቃት ያላስቆማት ብርቱዋ የሴቶች መብት ተሟጋች ሜላት ተሰማ የህይወት መንገድ
https://youtu.be/-uPTALKB0KM
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እየበረታባቸው የመጣውን የድጋሚ የምርጫ ፉክክር የማቋረጥ ጥሪ “የትም አልሄድም” ሲሉ አጣጣሉ
የ81 ዓመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሪፐብሊካኑ ተፎካካሪያቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር በቀጥታ ያደረጉትን ክርክር ተከትሎ ከአቋማቸው እና ከአእምሯቸው ጤነንት ጋር በተያያዘ ጫናዎች እየበረቱባው መጥተዋል።
ጆ ባይደን ባሳለፍነው ሳምንት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በቴሌቪዥን በቀጥታ ባደረጉት ክርክር ላይ ደካማ አፈጻጸም አሳይቷል ነው የተባለው።
ጆ ባይደን ድምጻቸው ደክሞ፣ በራስ መተማመናቸው ጠፍቶ፣ አቀርቅረው፣ ሃሳባቸው ተበትኖና አንደበታቸው ተሳስሮ ነበር ክርክሩን የጨረሱት።
ይህንን ተከትሎም የጆ ባይደን ፓርቲ የሆነው የዴሞክራት አባላት ፐሬዝዳንቱ በምርጫው ሊሸነፉ እንደሚችሉ ስጋታቸውን በመግለጽ ራሳቸውን በይፋ ከምርጫው እንዲያገሉ ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
ጆ ባይደን በትናንትናው እለት በተከበረ የነጻነት ቀን ላይ “ትግሉን ቀጥሉ” የሚል መፈከር ላሰሙ ደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር፤ የምርጫ ፉክክሩን የማቆም ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
በዋይት ሃውስ በተካሄደ ዝግጅት ላይ ንግግር ያደረጉት ባይደን “ተረድታችሁኛል፤ እኔ ወደየትም አልሄድም” ብለዋል።
“ስህተት ሰርቻለሁ” ያሉት ባይደን፤ “የ90 ደቂቃ የመድረክ ላይ ድክመቴን ሳይሆን ባለፉት 3 ዓመታት የሰራሁትን መልካም ስራዎች ተመልከቱ” ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ከምርጫው ራሳቸውን የማግለል ፍላጎት ባይኖራቸውም፤ ፓርቲያቸው ዴሞክራት ግን በምርጫው የማሸነፍ እድል ላይኖራቸው ይችላል በሚል ተተኪ በማዘጋጀት ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህን ተከትሎ ሮይተርስ ዶናልድ ትራምፕን ሊገዳደር የሚችሉ እጩዎች እነማን ሊሆኑ ይችላሉ? ሲል ጥናት አካሂዷል።
በጥናቱ የተሳተፉ አሜሪካዊያን መካከል የቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ባለቤት ሚሼል ኦባማ የተሻለ ድምጽ አግኝተዋል።
ከሚሼል ኦባማ በመቀጠል የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ በሁለተኝነት ሲጠቀሱ የካሊፎርኒያው ገዢ ጋቪን ኒውሶም ደግሞ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
አል አይን ኒውስ
ኢትዮ ቴሌ በዛሬው ዕለት ከ ኢግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በመሆን በአጋርነት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአይነቱ ልዩ የሆነ ቴሌቲቪ የተሰኘ ከቴሌብር ዲጂታል የክፍያ ሶሉሽን ጋር የተሳሰረ የኦንላይን ሲኒማ መተግበሪያ በጋራ አስጀምሯል፡፡
በዛሬው ዕለት በመዝናኛው ዘርፍ የፊልም አፍቃሪያን በእጅ ስልካቸው፣ በታብሌት፣ በስማርት ቴሌቪዥን እንዲሁም ኮምፕዩተር አማካይነት የፈለጉትን ሀገርኛ ፊልም በቀላሉ በቴሌብር ክፍያ በመፈጸምና በመከራየት ማየት የሚችሉበት አዲስ አሰራር ተጀምሯል፡፡
በዚሁ አጋጣሚ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ተወዳጅነት ያገኙትን “6 ሰዓት ከሌሊቱ” እና “ትዝታ” የተሰኙ ሁለት የአማርኛ ፊልሞችን ክፍያቸውን በቴሌብር በመፈጸም ካሉበት ቦታ ሆነው መመልከት የሚችሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
#Ethiotelecom #telebirr #TeleTV #DigitalAfrica #DigitalEthiopia
"ነብይ በሀገሩ ተከብሯል"
የገጣሚ ደራሲ እና ጋዜጠኛ #ነብይ_መኮንን ህልፈት አስመልክቶ ወደ ትውልድ ከተማው ናዝሬት (አዳማ) በብሔራዊ ቴአትር የአስክሬን ሽኝት ፕሮግራም!
https://youtu.be/1bwgDq2CKq0
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የሰብአዊ መብት ተቋማት እራሳቸዉን መገምገም እንዳለባቸው ተናገሩ
ጠቅላይ ሚኒሲትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት እንደገለፁት በሰበአዊ መብት ተሟጋች ስም የተቋቋሙት ድርጅቶች እራሳቸዉን ሊያጤኑ እና አሰራራቸዉን ሊፈትሹ ይገባል ብለዋል ፡፡
ለሰበአዊ መብት የተሰጠዉ ትርጓሜም መሰረቱ ከሆነዉ ግንድ ተለይቷል ነዉ ያሉት፡፡
በመሆኑ የሰበአዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚሉት ተቋማት ለተቋቋሙበት አላማ ሳይሆን ለፖለቲካ ማሳለጫነት እየተጠቀሙት ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ጎረቤት ሃገራት አንድም ዉስጣዊ ሰላም እያጡበት ያለዉ በእንዲህ አይነት አሰራር ምክንያት ነዉ ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒሲትሩ የኛም ሃገር የሰበአዊ መብት ተሟጓች ነኝ የሚሉት ተቋማት ለህዝብ ያመጡት ፋይዳ ሳይኖር ፤ በየሚዲያዉ የሚደረግ ዘመቻ ሊቆም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባል፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ምን አሉ?
ከአገራዊ ምክክር በፊት "እምነት መገንባት" ይቀድማል፤መንግስት በህዝብ ዘንድ አመኔታ አልፈጠረም ብለን እናስባለን፤ ለዚህም ማሳያው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ነው ሲሉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የፓርላማ አባሉ ተናግረዋል። በጅምላ የንጹሀን ግድያን ጨምሮ ዘረፋ፣ ውድመት፣ እገታ እና ሌሎችም ወንጀሎችና የመብት ጥሰቶች በአማራ ክልል ተንሰራፍቷል ብለዋል።
በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳቢያ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች፤ እንዲሁም ዜጎች በማንነት እየተለዩ እየታሰሩ ነው በማለትም የባልደረባቸውን ክርስቲያን ታደለ ጉዳይ በማንሳት የመንግስትን ሀብት ከምዝበራ የመጠበቅ ሀላፊነትን ወስዶ ሲሰራ የቆየን ሰው ለአንድ ዓመት ገደማ በእስር እየማቀቀ ነው ብለዋል። ከብልጽግና መንግስት ጋር አብረው እየሠሩ የሚገኙ ሰዎችም ስህተት አለ በማለታቸው ታስረዋል፤ ሀብታሙ በላይነህ የተባለው የአብን እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልም ለአራት ወራት የት እንዳለ የማይታወቅ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እንዲሰጡ እንማጸናለን ብለዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ኢትዮጵያ፦ እለተ ማክሰኞ የኢት ዜና - ግንቦት 27 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - Jun 4 , 2024
👉 የህውሃት ህጋዊ እውቅናን በተመለከተ አዲስ አዋጅ ፀደቀ
👉እስክንድር ነጋ ከመንግስት ጋር የጀመረው ድርድር
👉የትግራይ ታጣቂዎች በራያ አላማጣ እና በራጣ ባላ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/2y-chQKiru0
ፕሬዝዳንት ባይደን ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመግታት ጠንካራ ውሳኔ ይፋ ሊያደርጉ ነው
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ እና መጠነ ሰፊ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ዛሬ ማክሰኞ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
አዲሱ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በየዕለቱ ከሚመለከቱት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በላይ አመልካቾች ከቀረቡ ጥያቄያቸውን ሳይመለከቱ በቀጥታ ከአገር እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን ይሰጣል ተብሏል።
ይህም ድንበር ላይ ያሉ ባለሥልጣናት ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥርን እንዲገድቡ እንደሚያስችላቸው ሦስት ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጮች በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደን በሥልጣን ላይ በቆዩባቸው ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ከ6.4 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ ለመግባት እንደሞከሩ ተነግሯል። ይህ እስካሁን ከታየው ከፍተኛው ሲሆን፣ ለዳግም ምርጫ ዘመቻ ላይ ያሉትን ባይደን ፈተና ጋርጦባቸዋል።
የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡት እንዳለው ባይደን አሁን በ1952 የወጣውን በአሜሪካ ጥገኝነት የማግኘት ሥርዓትን ለመገደብ የሚያስችለውን ሕግ ለመጠቀም እያሰቡ ነው።
212(ኤፍ) በመባል የሚታወቀው ሕግ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የውጭ ዜጎች “ለአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም አስጊ የሚሆኑ ከሆነ” ፕሬዝዳንቱ “እንዳይገቡ ማገድ” የሚያስችለው ነው።
BBC Amharic
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በህንድ በከፍተኛ ሙቀት የተነሳ በሶስት ቀናት ውስጥ ከ50 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ
በህንድ ውስጥ ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ ከ50 የሚበልጡ ሰዎች በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በአስከፊ የሙቀት መጠን የተነሳ ህይወታቸውን አጥተዋል።
በሰሜናዊቷ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት ብቻ በሳምንቱ መጨረሻ በሙቀት ሳቢያ 33 ሰዎች ሞተዋል። በኦዲሻ ግዛት ደግሞ 20 የሚጠጉ ሰዎች በሙቀት መሞታቸውን አንድ ባለሥልጣኑ ለኤኤንአይ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ህንዳውያን ለጠቅላላ ምርጫ በመጨረሻው የድምጽ መስጠት ሂደት ላይ ሆነው ይህው የሞት ሪፖርት ይፋ ተደርጓል። የምርጫው ውጤት በነገው እለት ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል።
በየአምስት ዓመቱ ህንድ አጠቃላይ ምርጫዋን በሚያዝያ እና ግንቦት የበጋ ወራት ታካሂዳለች። ነገር ግን በዚህ አመት የሙቀት መጠኑ ኃይለኛና ረዘም ያለ የሙቀት ሞገዶች እያጋጠማት ይገኛል።
የህንድ ፌደራል ጤና ሚኒስቴር ከመጋቢት 1 እስከ ግንቦት 30 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 56 የተረጋገጡ በሙቀት ስትሮክ የሰዎች ህልፈት መመዝገቡን ይፋ አድርጓል ።በዚህ ወቅት 24 ሺ 8 መቶ 49 ያህል ሰዎች በሙቀት በተፈጠረ የጤና እክል ጉዳዮች ሪፖርት ተደርጓል። ሆኖም፣ ትክክለኛው የተጎጂዎች ቁጥር በጣም ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል ተመልክቷል። በኡታር ፕራዴሽ በርካታ በጎ ፈቃደኛ የፖሊስ አባላት፣ የምርጫ አስፈፃሚዎች፣ የጥበቃ ሰራተኞች እና የንፅህና አጠባበቅ ሰራተኞች ቅዳሜና እሁድ ከሞቱት መካከል ይገኙበታል።
የሀገሪቱ የምርጫ አስፈፃሚ ናቭዲፕ ሪንዋ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ለሟች የምርጫ ኮሚሽኑ ሰራተኛ ቤተሰቦች የገንዘብ ካሳ 1.5 ሚሊዮን ሩፒ ወይን 18,000 የአሜሪካን ዶላር እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።
ሪንዋ በተጨማሪም ድምጽ ለመስጠት ወረፋ ላይ የቆመ አንድ ሰው በሙቀት ምክንያት ራሱን ስቶ ወድቋል ብለዋል። መራጩ ወደ ጤና ተቋም ሲደርስ ህይወቱ ማለፉን ገልፀዋል።የኦዲሻ አውራጃ ባለስልጣናት ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ 99 ሰዎች በሙቀት ስትሮክ መሞታቸውን ሪፖርት አድርገዋል ። ከእነዚህ ውስጥ ግን 20 ብቻ ከሙቀቱ ጋር የተያያዘ ህልፈት መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ የኦዴሻ ልዩ የእርዳታ ኮሚሽነር በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል ።
ከሙቀት ጋር የሰዎች ህልፈት በቢሃር፣ማድያ ፕራዴሽ እና ጃርካሃንድ ግዛቶችም ተመዝግቧል። በሰሜን እና በመካከለኛው ህንድ እንዲሁም በአንዳንድ የምዕራቡ የሀገሪቱ ክፍል ያለው ሙቀት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ያለማቋርጥ የቀጠለ ሲሆን ከፍተኛው የሙቀት መጠን ከ45 እስከ 46 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ደርሷል። በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 50 ከፍ ብሏል። ይሁን እንጂ የሕንድ የአየር ሁኔታ ክፍል በመጪዎቹ ቀናት የሙቀት መጠኑ ሊቀንስ እንደሚችል ገልጿል።
በኤሌክትሪክ ፍጆታ መጨመር ምክንያት በርካታ ክልሎች ከፍተኛ የውሃ እና የመብራት እጥረት እያጋጠማቸው ነው። ከዋና ከተማው ዴልሂ የወጡ ቪዲዮዎች እንዳሳዩት ሰዎች ከውኃ ታንከሮች ውሃ ለማግኘት ሲጋፉ ያሳያሉ። በርካታ የመዲናዋ ክፍሎችም ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ እያጋጠማቸው ነው።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በሶማሊያ ሰላም በማስከበር ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች በቀጣዩ አመት ታህሳስ ተጠቃልለዉ እንዲወጡ ሶማሊያ ቀነገደብ አስቀመጠች
የሶማሊያ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሁሴን ማሊም በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች በቀጣዩ አመት ታህሳስ ተጠቃልለዉ ይወጣሉ ሲሉ ተናግረዋል።
የብሔራዊ ደህንነት አማካሪዉ ተናገሩት እንደተባለው ከሆነ በአፍሪካ ህብረት በሚመራዉ የሰላም አስከባሪ ሀይል ስር የኢትዮጵያ ጦር የግዳጅ ጊዜዉ የፈረንጆቹ አመት ሳይጠናቀቅ ወይንም በቀጣዩ አመት ታህሳስ ወር ላይ ይጠናቀቃል። ይህ ማብቃቱንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቅቆ ይወጣል ማለታቸውን ዘገባዎች አመልክቷል።
ሶማሊያ ከቀጣዩ አመት ጀምሮ አልሸባብን የሚዋጋ ሁለገብ ጦር ለማቋቋም ከአለማቀፍ አጋሮች ጋር እየተነጋገረች መሆኑንም ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ቱርኪዬ እና ሶማሊያ ወታደራዊ አጋርነታቸውን እያጠናሩ ሲሆን ሶማሊያ የቱርኪዬ የምስራቅ አፍሪካ ዋነኛ አጋር ለመሆን ሂደቶችን መጀመሯን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ከጥር ወር ጀምሮ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ በአራት ሀገራት ማለትም ከጅቡቲ ፣ ኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ብሩንዲ በሚወጣጡ ወታደሮች የሚመሰረት ሲሆን በዚህ መሰረት ከሆነ የኢትዮጵያ ጦር የጥምር ሃይሉ አባል እንደማይሆን ነዉ።
በሶማሊያ ከአፍሪካ ህብረት ጥምር ሀይሎች አበሰል ከሆኑት ዉጪ ተጨማሪ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሀገሪቱ ይገኛሉ መባሉን ነዉ።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ በቅርቡ የባህር በር ስምምነትን በሰጥቶ መቀበል መርህ ከተፈራረሙ በኋላ በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለዉ ግንኙነት መሻከር እያሳየ መጥቷል። ሶማሊያም ይህንን ተክትሎ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከክልሏ ለቅቀዉ እንዲወጡ መጠየቋ ይታወሳል።
በሶማሊያ በኩል የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሀገሪቱ ለቅቀዉ ይወጣሉ መባሉ ቢዘገብም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ አልሸባብን በመዋጋት ላይ ሲገኝ የህይወት መስዋዕትነት እንደከፈለም ይታወቃል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ሪያል ማድሪድ ለ15ኛ ጊዜ የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ሆነ።
#UCL #ChampionsLeague #RealMadrid #BorussiaDortmund #BVB
ኢትዮጵያ፦ እለተ አርብ የኢት ዜና - ግንቦት 23 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 31 , 2024
👉 የሚኒስትሮች ምክር ቤት የዛሬ ውሳኔዎች
👉ጳጳሱ የእስር ውሳኔ ተላለፈባቸው
👉የትግራይ ወታደሮች የአላማጣን ትምህርት ቤት ተቆጣጠሩ
ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/kSSqeCIJViI