ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረጉ አብዛኛዎቹ በረራዎች በአስቸጋሪ የአየር ጸባይ ሳቢያ በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ አውሮፕላን ማረፊያዎች ተዘዋወሩ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረጉ አብዛኛዎቹ በረራዎች በአስቸጋሪ የአየር ጸባይ ምክንያት በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ አውሮፕላን ማረፊያዎች መዛወራቸውን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ ÷ ዛሬ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ጸባይ ምክንያት አብዛኛዎቹ በረራዎች በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም ፡፡

ይህን ተከትሎም አብዛኛዎቹ በረራዎች ወደ ሌሎች አውሮፕላን ማረፊያዎች መዛወራቸውን ነው የገለጸው፡፡

በመዲናዋ በተፈጠረው አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ምክንያት በመንገደኞች ላይ ለደረሰው መጉላላትም አየር መንገዱ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ህውሃት የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል ዶ/ር ደብረጽዮን

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።

አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን " አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም ” ብለዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " የህወሓት ሰዎች መመደብ አለባቸው " ብለው በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩን " ካቋቋሙ ወገኖች ጋር ውይይት ያስፈልጋል " ብለዋል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ከህወሓት በተጨማሪ የትግ ራይ ሠራዊት፣ ምሁራን እና ተቃዋሚው ባይቶና ድርሻ አላቸው።

በጉዳዩ ዙሪያ ከፌድራሉ መንግስት ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ፥ " እኛ ትግራይ ውስጥ ብቻ የምንጨርሰው አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።

EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በኬንያ ሚስቱን ጨምሮ 42 ሴቶችን ገድሏል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረው ተጠርጣሪ ከእስር ቤት ማምለጡ ተነገረ፡፡

በናይሮቢ የቆሻሻ መጣያ ስፍራ ላይ የሰውነት አካላቸው የተቆራረጠ የ6 ሴቶች አስክሬን በቆሻሻ ከረጢት ውስጥ መገኘቱን ተከትሎ ግለሰቡ በፖሊስ ተይዞ የፍርድ ሂደቱን በመከታተል ላይ ነበር፡፡

በወቅቱ በመላው ኬንያ ድርጊቱ ቁጣን ቀስቅሶ የነበረ ሲሆን በማህበራዊ ሚድያዎች ኬንያውያን ጥፋተኛው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ሰፊ ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበርም ይታወሳል፡፡

ኮሊንስ ጁማይሲ የተባለው ግለሰብ በፖሊስ ከተያዘ በኋላ ሴቶችን እየመረጠ ከ2022 ጀምሮ ሲገድል እንደነበር ቃሉን የሰጠ ቢሆንም ፍርድ ቤት በቀረበበት ጊዜ ድርጊቱን እንዳልፈጸመ ተናግሯል፡፡ 

የተጠርጣሪው ጠበቃ ግለሰቡ ሴቶችን ስለመግደሉ ለፖሊስ ያመነው በደረሰበት የምርመራ ማሰቃየት ነው ሲል ገልጿል፡፡
 የፖሊስ ቃል አቀባይ ርሲላ ኡንያንጎ እንደተናገሩት ግለሰቡን ጨምሮ በህ ገወጥ መንገድ የገቡ 12 ኤርትራውያን ትላንት አነጋጉ ላይ ጊጊሪ ከተባለው የፖሊስ ጣብያ እስር ቤት ማምለጣቸውን ተናግረዋል፡፡

 እስረኞቹ ማለዳ ላይ የታሳሪዎች ቆጠራ በሚከናወንበት ጊዜ እንዳመለጡ ፖሊስ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ፖሊስ አስራ ሶስቱን ከህግ ያመለጡ ሰዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ሰፊ አደን እና አሰሳ እያደረገ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ያልተለመዱ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከቱ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

ኮሊንስ ጆማይሲ የተባለው የ33 አመት ኬንያዊ ባሳለፍነው ሀምሌ ላይ የአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ እየተመለከተ በሚገኝብት ወቅት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ግለሰቡ ለመጨረሻ ጊዜ ከገደላቸው ሴቶች መካከል ከአንዷ ጋር ባደረገው የሞባይል ገንዘብ ልውውጥ ፖሊስ ባደረገው ማጣራት ሊያዝ ችሏል፡፡

አስክሬኖቹ ከተገኙበት አካባቢ 100 ሜትር ርቀት ላይ የሚኖር ሲሆን ፖሊስ በመኖርያ ቤቱ ውስጥ ባደረገው ፍተሻ 10 ሞባይል ስልኮችን ፣ ላፕቶፕ ፣ የሴቶች አልባሳት እና መታወቂያዎችን አግኝቷል፡፡

 በተጨማሪም የተለያየ መጠን ያላቸው የስለት መሳርያዎች እና የሟቾችን አስክሬን ከቆራረጠ በኋላ የሚጥልባቸውን በርካታ ከረጢቶች እንደተገኙ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ሟቾቹ ከ18 እስ 30 እድሜ የሚጠጉ ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም የተገደሉበት መንገድ አንድ አይነት ተብሏል፡፡

Via አል አይን

EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ከኢዜማ የወጡ የቀድሞ አመራሮች አዲስ ፓርቲ ማቋቋማቸው ተሰማ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አመራሮች ‹‹የንጋት ኮኮብ›› የተባለ አዲስ ፓርቲ ማቋቋማቸው ተነግሯል፡፡

የቀድሞ የፓርቲው ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋና ሃብታሙ ኪታባን ጨምሮ ሌሎች ፖለቲከኞች አዲስ ፓርቲ ሟቋቋማቸውን ከፊት አውራሪ የፓርቲው አደራጆች እና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምንጮቿ ማረጋገጥ ተችላል፡፡

ከቀድሞ የኢዜማ አመራሮች በተጨማሪ አዳዲስ ወጣት ፖለቲከኞች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ መምህራን በፓርቲው መካተታቸውን የገለጹልን ምንጮች ፓርቲው ከምርጫ ቦርድ የቅድመ ምዝገባ ፍቃድ ማግኘቱንም ነው የገለጹት፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀዋሳ ናቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀዋሳ ቆይታቸው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ጉብኝትና ሌሎችም ተያያዥ ፕሮግራሞች ይከናወናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ሚኒስትሮችና ሌሎች እንግዶች ሀዋሳ ሲገቡ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ዳግመኛ የህወሓት ሊቀመንበር ሆነዉ ተመረጡ

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ መመረጣቸው ተሰምቷል።

አቶ አማኑኤል አሰፋ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የፓርቲው የምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ህወሓት ሁለቱን የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ያደረገው ላለፉት ስድስት ቀናት በመቐለ ከተማ ሲያደርገው የነበረውን አወዛጋቢ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ሲያጠናቅቅ ነው። በዛሬው የጉባኤ ውሎ፤ ዘጠኝ አባላት ያሉበት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫም ተከናውኗል።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ፍኖተ-ካርታ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ሥራ መገባቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ገለጸ

ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሚኒስትሮች ም/ቤት የጸደቀውን የሸግግር ፍትሕ ፖሊሲ አፈፃፀም፣ ክትትልና ድጋፍ ሥርዓት የሚመራ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉ የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የዓለም አቀፍ ወንጀሎችን የሚደነግግ አዋጅ፣ የእውነት ምህረት እና ማካካሻ ኮሚሸን ማቋቋሚያ አዋጅ እና የሌሎች የሽግግር ፍትሕ አላባዎች ፈፃሚ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጆችን የማርቀቅ ሥራ እየተሳለጠ ነው ብሏል።

በተጨማሪም በሽግግር ፍትሕ ማእቀፍ የወንጀል ጉዳዮችን የሚያየው ልዩ ችሎት ስልጣንና አሰራርን የሚመሰርተው የሽግግር ፍትሕ ልዩ ችሎት አዋጅ ዝግጅት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስተባባሪነት እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

የሕግ ማዕቀፎቹ ዝግጅት በጉዳዩ ላይ በቂ እውቀትና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚካሄድ ነው ያለው ሚኒስቴሩ አጠቃላይ ሒደቱ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጿል።

የህግ ማርቀቅ ሥራው እንደተገባደደ ህዝቡና ባለድርሻ አካላት ዝርዝር አስተያየት የሚሰጡባቸው ሀገር-አቀፍ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች እንደሚዘጋጁም ተጠቅሷል፡፡

የነዚህ ሕጎች በፍጥነት መውጣት በፖሊሲው ላይ የተመላከቱትን ዓላማዎች ለማሳካት በተለይም የተለያዩ የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን በመጠቀም እውነት ለማውጣት፣ እርቅ የሚወርድበትን አሰራር ለመመስረት፣ የወንጀል ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ በቅድመ-ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ምህረትን ተግባራዊ ለማድረግ የማካካሻና ተቋማዊ ማሻሻያ ሥራዎችን ለማከናወን እና በአጠቃላይም የተሟላ ፍትህ ለማስፈን ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

የእኩልነት ድምፆች የማያቋርጥ ትግል

https://youtu.be/rNGWPj123MY

Читать полностью…

EthioTube

የቻይና መንግስት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር  ከሰሞኑ እየተናፈሰብኝ ነው ላለው ውዝግብ መግለጫ ሰጠ ።

ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ እንዳለው  ከሰሞኑ  ድርጅቱን በተመለከተ ህዝብን የሚያሳስት አሉባልታ እየተነሳ መሆኑን ለማወቅ ችሏል በመሆኑም  ድርጅቱ ነገሩን በጥልቅ መመርመሩን እና አሉባልታው ምንም መሰረት የሌለው እና የአሉባልታው ምንጭም የቀድሞ የድርጅቱ ሰራተኛ የነበሩት አቶ ሰን መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ሲል ተናግሯል።

በመሆኑም አቶ ሰን እያናፈሱት ያለው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን የድርጅቱን ደንበኞችም ሆነ ህዝቡ እንዲያውቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

በመጨረሻም  ድርጅቱን በተለመለከ የሚነሱ አሳሳች መረጃዎችንን ባለመስማት እና መጠየቅም ሆነ ማወቅ የሚፈልጉትን መረጃዎች በቀጥታ ድርጅቱን ማናገር እንደሚቻል በመግለፅ በጉዳዩ ላይ ዘርዘር ያለውን መረጃ በመግለጫው አካቷል።


ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል ☝️

Читать полностью…

EthioTube

#Update

⏲️ በአፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጨ ያለው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በርካታ ሰዎችን ለሞት እየዳረገ ነው

የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት እንደሆነ ካወጀ በኃላ ስዊድን የሚጀመሪያውን ኬዝ ማግኘቷን በቀደመው ዜናችን ማድረሳችን ይታወሳል። በቫይረሱ የተያዘው ሰው ወደ አፍሪካ የጉዞ ታሪክ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል ።

ፓኪስታንም በተመሳሳይ ሶስት በMpox ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ማግኘቷን ይፋ አድርጋለች።

3ቱም ቫይረሱ የተገኘባቸው ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ተጉዘው ፓኪስታን የገቡ እንደሆነ የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት ገልጸዋል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ቫይረሱ በተለይም አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳራጨ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜም በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ኬንያ ፣ በቡሩንዲ ፣  በሩዋንዳ ፣ በኡጋንዳ ተገኝቷል።

በቫይረስ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው Mpox በወሲባዊ ግንኙነት ፣ በቆዳ ንክኪ ፣ በቅርብ ርቀት ሆኖ ማውራት / መተንፈስ ፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ባለ የቅርብ ግንኙነት ይተላለፋል።
እንደ CDC Africa መረጃ እስካሁን በአፍሪካ ከ500 በላይ ሰዎች በበሽታው ሞተዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

አፍሪካ ልማት ባንክ የ40 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ድጋፍ ለዳሽን ባንክ አጸደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ለዳሸን ባንክ የ40 ሚሊዮን ዶላር የግብይት ዋስትና መስጫ ፋይናንስ ማፅደቁ ተገልጿል።

ድጋፉ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የንግድ ፋይናንስ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ድጋፉ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ፋይናንስ አቅርቦትን ያመቻቻል የተባለ ሲሆን ለአገር ውስጥ ኩባንያዎችም የገቢና ወጪ እንቅስቃሴን እንደሚያቀላጥፍ ተገልጿል።

ውጥኑ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AFCFTA)፤ በአፍሪካ ውስጥ ንግድን ለማስፋፋት ካለው ዓላማ ጋር የተጣጣመ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ግብርና እና ማኑፋክቸሪንግን የመሳሰሉ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎችን ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል።

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ በበኩላቸው ድጋፉ የባንኩን የንግድ እንቅስቃሴ ለማስፋት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በዳሸን ባንክ መካከል ያለው አጋርነት ኢትዮጵያ በአህጉራዊ እና አለምአቀፍዊ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያላትን ተሳትፎ ያጠናክራል የተባለ ሲሆን በተመሳሳይም የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት የሚደግፍ ስትራቴጂካዊ እርምጃ መሆኑ ተጠቁሟል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ከ6 አመት በላይ ጋምቤላ ክልልን ሲመሩ የቆዩት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ከስልጣናቸው ተነስተው አዲስ ፕሬዚዳንት ዛሬ ተሹሟል

የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድን የክልሉ ፕሬዜዳንት አድርጎ ሾሟል።

ወ/ሮ አለሚቱ የዛሬው ሹመት እስኪሰጣቸው በኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን አገልግለዋል።

በክልሉ ም/ቤት " የአመራር ለውጥ ያስፈለገበት ምክንያት በሠላም እና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ዘርፍ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም የተቀመጡ አቅጣጫዎች ውስንነቶች በመታየታቸው ነው " ተብሏል።

የቀድሞው ፕሬዜዳንት አቶ ኡመድ ሌላ የፓርቲ ተልዕኮ እንደሚሰጣቸውም ተሰምቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጋትሏክ ሮን (ዶ/ሮ) ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በሴቶች 3ሺ መሰናክል ማጣሪያ ሎሚ ሙለታ 5ኛ፣ ሰምቦ አለማየሁ 2ኛ ሆነው ከየምድባቸው በመጨረስ ለፍፃሜ አልፈዋል።
------
#OlympicGames in #Paris2024 - Women's 3000m Steeplechase Round 1 Heats

- Lomi Muleta 🇪🇹 (9:10.73) of #TeamEthiopia qualifies to the final after finishing 5th in Heat 1
- Meanwhile in Heat 2 Sembo Almayew 🇪🇹 (9:15.42) qualifies to the final after finishing 2nd

(📷: Getty Images)

Читать полностью…

EthioTube

የተለያዩ ባንኮች የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን።

#Birr #USDollar #ExchangeRate #Ethiopia

Читать полностью…

EthioTube

በሴቶች 800ሜ ማጣሪያ ጽጌ ዱጉማ እና ወርቅነሽ መሰለኛ ከየ ምድባቸው 1ኛ ሆነው በመጨረስ ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል።
-----
#OlympicGames in #Paris2024 - Women's 800m Round 1 Heats

Tsige Duguma 🇪🇹 (1:57:90), Worknesh Mesele 🇪🇹(1:58:07) #TeamEthiopia qualify to the final after finishing 1st in their respective heats

(📷: Getty Images)

Читать полностью…

EthioTube

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ገድላለች

በማዕከላዊ ኢራን " ዝድ ክልል "አስገድዶ መድፈር መፈጸሙ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት ግለሰብ ሞት ተቀጥቷል።

ግለሰቡ " በጥንቆላ ይተዳደራል " የተባለ ሲሆን ወደሱ የሚመጡ ሴቶችን በማታለል አስገድዶ ሲደፍር እንደነበር ተገልጿል፡፡

ከ12 በላይ የክስ መዝገቦች የተከፈቱበት ይህ ሰው አሱን ጨምሮ ከነ ረዳቱ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው በሞት ፍርድ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረትም ጥፋተኛ የተባሉት ሰዎች ታንቀው እንዲገደሉ ተደርጓል።

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉ ወንጀለኞች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚጥሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

via አል አይን

EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

መጠበቅም መታገዝም ያለባት እናት ናት !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨን እናትን በማግኘት አጽናንተዋል::

ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው እህታችን የፍትህ ሂደቱን ለመከታተል ፣ ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላት እና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በሙያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል::

የህፃን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋፅዖ ያለው ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ እና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል::

አሁንም ፍትህ እንፈልጋለን !

Читать полностью…

EthioTube

ከኢዜማ የወጡ የቀድሞ አመራሮች ፖርቲ አቋቋሙ መባሉን አስተባብለዋል

የቀድሞው የኢዜማ ሊቀ መንበር አቶ የሽዋዝ አሰፋ በማህበራዊ ገፃቸው ላይ እንዳጋሩት የጉዳዮ ባለቤቶችን በስልክ አነጋግሮ የተጠቀሰው ፓርቲ ምስረታ የእኛ አይደለም ማለታቸውን እና በቅርቡ ወደአገር ቤት ሲመለሱ በጉዳዩ ላይ በዝርዝር የደረስንበትን ሙሉ መግለጫ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል።

እስከዚያው በአገር ውስጥም፣ በውጭ አገርም ያላችሁ እና የእኛን ንቅናቄ የምትጠባበቁ ሁሉ መረጃዎችን በውስጥ እየተለዋወጥን ስለሆነ በትዕግስት ብንቆይ መልካም ይሆናል። የሚል መልዕክት በማህበራዊ ገፃቸው አስተላልፈዋል።

EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የታንዛኒያ የፖሊስ አዛዥ በቡድን ጾታዊ ጥቃት የደረሰባትን ሴት "የወሲብ ንግድ ሰራተኛ ናት" በማለታቸው ከኃላፊነት ተነሱ

በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዶዶማ በቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ደርሶባታል የተባለችውን ሴት ጉዳይ ከወሲብ ስራ ጋር በማያያዝ አወዛጋቢ አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አንዲት ወጣት ሴት ላይ ጾታዊ ጥቃት ሲደርስባት የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት​​​ተሰራጭቷል። በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ታንዛኒ ድርጊቱ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።አራት ሰዎች ሰኞ እለት በተጠረጠሩበት ጾታዊ ጥቃት ሰኞ እለት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ቢመሰረትባቸውም ወንጀሉን አለመፈፀማቸውን ተናግረዋል። እሁድ እለት በዋና ከተማዋ ዶዶማ የሚገኙት የፖሊስ አዛዥ የሆነችው ግለሰብ ለታንዛኒያ ጋዜጣ ጥቃት የደረሰባት ሴት የወሲብ ንግድ ሰራተኛ ነች ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንን አስተያየት ተከትሎ የታንዛኒያ ብሄራዊ የፖሊስ ሃይል ይቅርታ በመጠየቅ የፖሊስ አዛዧን ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወሩን ገልጿል። የብሔራዊ ፖሊስ ቃል አቀባይ ዴቪድ ሚሲሜ እንደተናገሩት የፖሊስ ሃይሉ በመገናኛ ብዙኃን በተሰራጨው መግለጫ የተናደዱትን ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ ይፈልጋል ብለዋል።ሚሲሜ አክለውም የዶዶማ ክልል የፖሊስ አዛዥ የሆነችው ቴዎፒስታ ማሊያ ለሃገር ውስጥ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት ተጎጂዋ የወሲብ ሰራተኛ ብትሆንም "እንዲህ አይነት ጥቃት ሊፈፀምባት አይገባም" ሲሉ መናገራቸው ቁጣን ፈጥሯል።

በማህበራዊ ድረ-ገጽ ኤክስ ላይ የፖሊስ አዛዧ ማልያ አስተያየት "ፖሊስ በሴቶች መብት ላይ ያለውን ጭካኔ የሚያሳይ ማስረጃ ነው" ሲሉ በርካቶች ተደምጠዋል። የህግ ባለሙያዋ እና ታዋቂዋ የመብት ተሟጋች ፋቲማ ካሩሜ በኤክስ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት በወሲብ ንግድ የሚሰማሩ ሰዎች ሊደፈሩ አይችሉም ማለት ነው ስትል ተናግራለች። ተጎጂዋ ጥቃት ሲደርስባት በሚያሳየው ቪዲዮ ላይ ተጠርጣሪዎቹ “አፋንዴ”ን ይቅርታ እንድትጠይቅ ሲያስገድዷት ይታያል። በታንዛኒያ "አፋንዴ" የሚለው ቃል ወታደርን ወይም የፖሊስ መኮንንን ለመጥራት ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።

በርካታ የመብት ተሟጋቾች እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ በፀጥታ ሀይሉ ትብብር ጾታዊ ጥቃት ሲፈፀም ቆይቷል በማለት ቁጣቸውን ገልፀዋል።ከስልጣን የተነሳችው የፖሊስ አዛዥ በንግግሯ በአልኮል እና በአደንዛዥ እፅ ተፅእኖ ውስጥ ያሉ ሰዎች ጥቃት ከፖሊስ ጋር አይያያዝም ተናግራለች። አክላም ጥቃት የደረሰባት ሴት በወሲብ ስራ ላይ የተሰማራች ትመስላለች ማለቷ የታንዛኒያን ህዝብ አስቆጥቷል።ቪዲዮው መቼ እንደተቀረፀ ግልፅ ባይሆንም ተጎጂው በሀገሪቱ የንግድ ዋና ከተማ ዳሬሰላም ውስጥ ነዋሪ እንደሆነች ተነግሯል።


Via , ዳጉ _ጆርናል

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት የደሴ ከተማን ከአዲስ አበባ  የሚያገናኘው ዋና አውራ ጎዳና በከፊል አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ተገለጸ

👉 ‹‹በከተማዋ 11 ቦታዎች ላይ የመሬት መንሸራተት አደጋ አጋጥሟል›› የደሴ ከተማ አስተዳደር

በደሴ ከተማ በ11 የተለያዩ አካባቢዎች በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ300 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተነግሯል፡፡

አደጋው ፊትበር፣ዶሮ ተራ፣ቄራን ጨምሮ 11 በሚሆኑ የከተማዋ አካባቢዎች የተከሰተ መሆኑን የገለጹት በደሴ ከተማ አስተዳደሩ የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ግርማ ከተማዋ ላይ በቀጣይ መሰል አደጋ ይከሰታል የሚል ስጋት እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

ከአደጋው ጋር ተያይዞ መኖሪያ ቤቶች በየቀኑ እየፈረሱ ነው የተፈናቃዮች ቁጥርም በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ ነው ያሉት ስራ አስፈጻሚው እየተደረገ ያለው ድጋፍ ግን አጥጋቢ ነው የሚባል እንዳልሆነ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

የደሴ ከተማን ከኮምቦልቻና ከአዲስ አበባ  የሚያገናኘው ዋና አውራ ጎዳና በአደጋው ምክንያት አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ፣ እርዳታ በተፈለገው ልክ ወደ ከተማዋ እንዳይገባ እንዳደረገውም አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ የተፈናቀሉ ዜጎችም በትምህርት ቤቶች ውስጥ በጊዚያዊነት ተጠልለው እነደሚገኙ የገለጹት ሃላፊው መጪው የትምህርት ዘመን ከመቃረቡ ጋር ተያይዞ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ሁሉም ዜጋ ለከተማዋ ድጋፍ እንዲያደርግ ትብብር ጠይቀዋል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ባወጣው የቅድመ ስጋት ሪፖርት በመሬት መንሸራተት አደጋ ተጋላጭ ናቸው ካላቸው የአገሪቱ አካባቢዎች ውስጥ ደሴ ከተማ አንዷ እንደነበረች አይዘነጋም።

Читать полностью…

EthioTube

በህፃን ሄቨን ጉዳይ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ይህን ብሏል

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከደቂቃዎች በፊት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ከህጻን ሔቨን ጋር ተያይዞ ባወጣው መግለጫ "የሚጠበቅብኝን ተወጥቻለሁ" ሲል ገልጿል።

- የህፃን ሄቨን ጉዳይ ለክልሉ ፖሊስ በተለይም ለባህርዳር ከተማ 8ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከዓመት በፊት ሐምሌ 25/ 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሪፖርት ከደረሰን ጀምሮ እስከ ፍርድ ቀን አብሮን የዘለቀ ጉዳይ ነው።

- በባሕር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ ቆጠጢና አካባቢ የ7 አመት ከ 8 ወር ታዳጊዋ ህጻን ሄቨን ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊትና ህልፈተ ህይወት መርምሮ ለፍርድ ለማቅረብ ከፍትህ ነጣቂዎች ጋር ታግለን መረጃና መስረጃ አሟልተን ለፍርድ አቅርበናል።

- ጉዳዩ ብዙ ሂደቶችን አልፎ ውሳኔ ከተሰጠ በኅላም ልዩ ትኩረት በመስጠት ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን በአማራ ፖሊስ ቴልቨዥን ፕሮግራም በተደጋጋሚ እንዲተላለፍ ተደርጓል።

- ከህፃን ሄቨን በተጨማሪ በክልሉ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ92 በላይ አስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተፈፅመዋል።

- ህፃን ሄቨንን በተመለከተ እንደ ተቋም ፖሊስ የሚጠበቅበትን ተወጥቷል ሲል አስታውቋል።

Читать полностью…

EthioTube

"ወንጀለኛው ጌትነት ከማረሚያ ቤት አምልጦ ነበር።" አቶ ተሻገር

<<የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር  በታዳጊዋ ሄቨን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን አሁንም በድጋሜ ይገልጿል::

ከተማ አስተዳደሩ *ሀምሌ 25 / 2015 ዓ.ም* በባሕር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ በ7 አመቷ ታዳጊ ህጻን ሄቨን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊትና ህልፈተ ህይወት በእጅጉ ማዘኑን ገልፆ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

በህጻናት ላይ የሚፈጸምን ማንኛውም ጥቃት መከላከል በዋነኛነት የመንግስት ሃላፊነት ሲሆን በሌላ በኩል የሁሉም አካል ተመሳሳይ ድርሻ ያለው መሆኑን የገለፀው ከተማ አስተዳደሩ እንደዚህ አይነት አስነዋሪና አሳፋሪ ድርጊት በከተማችን በመፈፀሙ በእጅጉ ዛሬም በድጋሜ አዝነናል ።

የባሕር ዳር ከተማ ህዝብ ሰው ወዳድ፣ ሁሉን አክባሪ፣ ባህሉን፣ ወጉንና ታሪኩን ጠባቂ አስተዋይ ጨዋ ህዝብ ነው ። በዚህ እሴትና ባህል በተገነባ ማህበረሰብ ውስጥ የተፈፀመው ድርጊት በፍፁም ነውረኛና የከተማውን ህዝብ የማይገልፅ ሁሉም ሰው ሊያወግዘው የሚገባ ዘግናኝ ተግባር ነው ።

ሁሉም እንደሚያስታዉስዉ ወንጀሉ እንደተፈፀመ  የከተማ አስተዳደሩ የሚመለታቸው ተቋማት በዋነኝነትም  ከፖሊስ ፣ ከጤና ተቋም ፣ ከፍትህ እንዲሁም ከተበዳይ ወገኖች ጋር በመቀናጀት ጉዳዩ በህግ እንዲያዝ በማድረግ ልዩ ትኩረትና ክትትል በማድረግ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ ተይዞ በ20/06/2016 ዓ.ም በከፍተኛ ፍርድ ቤት የ25 አመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበት ባህርዳር ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል። 

በዚህ አጋጣሚ ከተማ አስተዳደሩ የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ነፃነት የሚያከብር ቢሆንም ከተፈፀመው ዘግናኝ ድርጊትና የማህበረሰቡን ሞራልና ክብር ዝቅ ያደረገ ወጀል በፈፀመው ወንጀለኛ ላይ የተሰጠው ፍርድ አስተማሪነት የሚያንሰው መሆኑን አስተዳደሩ በፅኑ ያምናል ።

ከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩን በጥብቅ ለመከታተል ባለው ፅኑ አቋም ክልሉን ባጋጠመው ቀውስ ወንጀለኛው ከማረሚያ ቤት አምልጦ የወጣ መሆኑን እንዳወቀ  በልዩ ሁኔታ የፀጥታ ሀይሉ ክትትል እንዲያደርግ አመራር ተሰጦ ወንጀለኛው ተይዞ ድጋሜ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ወቅት ወንጀለኛው ይግባኝ የጠየቀ እንደሆነ እና ጉዳዩ ለጥቅምት 20/2017 ዓ.ም ፍ/ቤቱ ቀጠሮ የሰጠ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ያውቃል። የፍርድ ቤቱን ነጻነት በጠበቀ መልኩ ከህግ አኳያ የይግባኙን ሁኔታ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትኩረት የምንከታተለው እና ፍትህ እንዲረጋገጥ በፅናት የምንታገል እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን።

ከተማ አስተዳደሩ በልጃችን ህፃን ሄቨን  ለደረሰው ግፍ ፍትህ ሲጠይቅ ፣ ለጉዳዩ ለሰጠው ትኩረት እና እያደረገ ላለው ትግል ለመላው የህብረተሰብ  ክፍል   ምስጋና እያቀረብን በቀጣይም ለፍትህ መረጋገጥ ለምናደርገው ትግል ህ/ሰቡ ከጎናችን እንዳይለይ ጥሪያችን እያቀረብን በቀጣይም የህፃናት ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ስለሆነ በትብብር መስራት ይጠበቅብናል።>>
አቶ ተሻገር አዳሙ
በም/ከንቲባ ማዕረግ የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ዋና ስራ አስኪያጅ

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብርን ምላሾች እንዴት ተመለከታችሁት ?

ብዙዎችን እያነጋገረ ያለው የዛሬው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፓሪስን ኦሎምፒክ አስመልክቶ ይፋዊ ባልሆነ ጥሪ ለታደመው ጋዜጠኛ በማርዮት ሌግዥሪ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

👉 በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ምክንያቱ ባልተገለጸበት ሁኔታ አልተገኘችም።

ኦሎምፒክ ኮሚቴው ያቀረበውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን ሪፖርት ካቀረበ በኋላ ከጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል።

ዶክተር አሸብር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶክተር) ከሰጧቸው ምላሾች መሐከል ...

📌 ተሳትፎ ነው ላልነው ይቅርታ እንጠይቃለን ።ኦሎምፒክ ግን ተሳትፎ ነው።

📌 ከIOC ከመቶ ሺህ ዶላር በታች ነው የተሰጠን።

📌 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ያካሄደው ምርጫ ትክክለኛ ነው።

📌 የቀረበብን ክስ ሰምተናል ግን አንደነግጥም።

📌 አትሌቶችን ጥሩ ሆቴል አስቀምጠናል። ሆቴል ውስጥ ደግሞ አስረን አላስቀምጥናቸውም።

📌 የቦክስ ተወዳዳሪው በኦሎምፒክ ያልተሳተፈው ፓስፓርት ስለሌውና ስደተኞች መጠለያ ስለሆነ ነው።

📌 አትሌት ገዛኸኝ አበራ ሶስት ጉዞዎችን ሰርዞ በአራተኛው ጉዞ ነው ፓሪስ የመጣው። ያቀረበው ክስ ውሸት ነው። ዋሽቷል።

📌 አትሌት ፍሬህይወት ከፓሪስ የቀረችው በዶፒንግ ምክንያት ነው። ተገቢውን ምርመራ አድርጋ ውጤቷን ማሳወቅ አልተቻለም።

📌 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የጣሰው ምንም አይነት ደንብ የለም።

📌 የፌዝ ሪፖርት አላቀረብንም። የፌዝ ሪፖርት አቀረባችሁ በመባሉ ስሜታችን አይነካም።

🛑 ሥልጣን አልለቀም!

📌 እንደ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ሰልፍ ሳይ አልሮጥም። ኃይሌ በሰልፍ ወረደ በሰልፍ ሊመለስ ይፈልጋል ።

📌 የሚያግደን ምንም ኃይል የለም።

📌 ደሀ ስለሆንን አነስተኛ ልዑክ ይዘን የሄደነው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑክ ነው።

📌 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፌዴሬሽንን ያፈረሰው ኃይሌ ገ/ሥላሴ ነው።

📌 ለኃይሌ ስንል የሽግግር መንግስት እናቋቋም እንዴ? ...እኔ ከዚህ ጋ ብነሳ ኃይሌ በፍጹም እዚህች አይደርሳትም።

📌 “ ከሀላፊነት በመውረድ እና በመውጣት የሚመጣ ለውጥ የለም እግር ኳሱን ምሩ ብዬ ጥዬ ወጥቼ የመጣ ለውጥ የለም።

📌 ጉዳፍ ፀጋይን ለማግባባት ሞክረን ነበር ፣ ነገር ግን አቋሟ ጥሩ ስለነበር በሦስቱም ርቀቶች እወዳደራለሁ ስላለች ትተናታል።"

📌 እኔ ከኃላፊነት ብለቅ እንኳ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የሚገባበት መንገድ የለም።

📌 ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠብቅሃል ተብዬ ነበር ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው ፣ እንደ ኃይሌ ሰልፍ ሳይ አሮጥም።

📌የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከማንም በላይ ጉልበት አለው ፣ ጉባኤው ጠንካራ ነው።

📌 ሕግ ላይ አጥብቀን ስለምንሰራ ብዙ ጊዜ አልሸነፍም !

📌 የኔ ሸልማት የኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር ነው!

ጋዜጣዊ መግለጫ ተጠቃሏል።

በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ምክንያቱ ባልተገለጸበት ሁኔታ አልተገኘችም።

“ በህዝቡ ከኃላፊነት እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው ፣ በባንዲራው ስም ይልቀቁ!" ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር አሸብር “ ከኃላፊነት አለቅም “ ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

***
📌 "እኛ አንታገድም! የሚያግደንም ኃይል የለም!!"

📌 "ጥሎ መውጣት የወደቀ ካልኩሌሽን ነው"

🛑 የጋዜጠኛ ፍቃዱ አባይ #Befekadu Abayጥያቄዎች ለዶክተር አሸብር ...

«እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ልጠይቃችሁ፤ ስሜታችሁ ግን እንዴት ነው?... ሪፖርቱን የምር የተሻለ ነው ብላችሁ ነው እያቀረባችሁ ያላችሁት??

ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲ ስራ ማክሰር፤ እንደ ቡድን ሳይሆን እንደግል መንቀሳቀስ፤ አለመናበብ... ለቢዝነስ ቅድሚያ መስጠትን ከእናንተ ከሰማን በኃላ፤ ሪዛይን ለማድረግ ምን አይነት ሪፖርት ነው የሚጠብቁት?

በዲሞክራሲ የሚያምኑ ከሆነ ህዝብና አገር የሰጠንን ኃላፊነት መወጣት አልቻልንም ብሎ መልቀቅ የዲሞክራሲ መግለጫ አይደለም ወይ?

ስለእርስዎ አምባገነንነት ይነገራል፤ ኹሉም ስለእርስዎ አምባገነንነት ካነሳ ራስዎን ለማየት ዝግጁ አይደሉም ወይ?

የበጀት ብክነትም አይነተናል፤ አትሌቶች ቶሎ ይመጣሉ፤ እናንተ አካባቢ ሲቆዩ ግን አይታይም።

ከአትሌትክሱ ይልቅ ለእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የቀረቡ ጋዜጠኞችን፤ አትሌቲክስ ላይ የማይሰሩ በሁለት ኦሎምፒክ ላይ ይዛችሁ መሄድ በምን መስፈርት ነው? ምንድነው መለኪያዎቻችሁ?

በመጨረሻም የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ይጠይቃሉ?! "

***

🛑 የዶ/ር አሸብር ምላሽ

📌 «ሪፖርታችን የፌዝ አይደለም።

📌 አሸንፌ እግር ኳስን ጥዬ ወጥቻለሁ። የመጣ ለውጥ ግን አላየሁም ።

📌 እዛ ዋንጫ አምጥተን ውጤታማ ሆነንም ወጥተናል።

📌 ሪዛይን አላደርግም ልንገራችሁ!!

📌 ጥሎ መውጣት የወደቀ ካልኩሌሽን ነው። እየሰራችሁ ያላችሁት የወደቀ ካልኩሌሽን ነው።

📌 ሽያጭ ላይ የወደቀውን አትሌቲክስ ብሔራዊ አትሌት የፈረሰበትን መርምሮ መረባረብ ነው የተሻለ የሚሆነው።

📌 እየነገዱ ለሀገር እየሰሩ እንደሆነ መንጫጫት አያስፈልግም። እኔ ብለቅም ኃይሌ የሚገባበት አግባብ የለም። የትኛውም ፌዴሬሽን ስላልሆነ።

📌 ጋዜጠኛ በማደረጀት፣ ሰልፍ ኢንጆይ አደርጋለሁ በጣም መለመድ አለበት ። ኃይሌ በሰልፍ ሮጦ ወጣ [አሁን ደግሞ] በሰልፍ እመለሳለሁ ብሎ ያስባል።

የዚህ አይነት ነገር አይቻለሁ።

📌 እኛ አንታገድም! ... የሚያግደንም ኃይል የለም የምንታገደው በጉባኤያችን ነው። እየተናቀ ያለው ጉባኤ ስልጣን ከማንም በላይ አለው። እሱ ሲያባረን መባረር፤ ስሩ ሲለን እንሰራለን።

📌 ሽግግር ኮሚቴ እናቋቋም እንዴ? እንደዛ አይሆንም። ሕግን እናከብራለን»

📌 ኦሎምፒክ ተሳትፎ ነው ብዬ ለሰጠሁት ሀሳብ የቃሉ አውድ ለህዝባችን አዲስ ስለሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ ነገር ግን የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ፅነሰ ሀሳብ የአትሌቶች ተሳትፎ ነው በሚል ስለሚገልፅ ነው።

***

🛑 “ ለጠፋው ውጤት ሚድያው ኃላፊነትን ውሰዱ “

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በመግለጫው ላይ አጠቃላይ የፓሪስ ቆይታን በተመለከተ በቴኪኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ አጠር ያለ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም ካለፉት ሁለት ኦሊምፒኮች የተሻለ ውጤት መገኘቱ ገልጸዋል።

አቶ ቢልልቅ መቆያ :-

📌 ፓሪስን ልዩ የሚያደርገው በማራቶን የተገኘው ድል ነው ይህን ማድነቅ ይገባል።

📌 ሦስት ብር በአንድ ኦሎምፒክ አልመጣም ፣ መሳቅ አያስፈልግም ይሄን መናቅ ተገቢ አይደለም።

📌 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ብሔራዊ ቡድን / አትሌት አያቋቁም “ ሲሉ ተናግረዋል።

አቃቢ ንዋይ ዶ/ር ኤደን አሸነፊ በበኩላቸው ሚድያው በማህበራዊ ትስስር ገጽ የነበሩት ዘገባዎች አትሌቶች ውጤት ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን ገልፀው “ ለጠፋው ውጤት ሚድያው ኃላፊነትን ውሰዱ “ ብለዋል።

ምንጭ፦ ማህበራዊ ሚዲያዎች

Читать полностью…

EthioTube

‹‹ ለፍትህ ›› ኢትዮጵያዊ  ፊልም ፡ ትናንት ምሽቱን በዓለም ሲኒማ በድምቀት ተመርቋል ፡ የምርቃቱ ፕሮግራም ምን እንደሚመስል ይህን ቪዲዮ ተጋበዙ
https://youtu.be/DPuprrh5x4A

Читать полностью…

EthioTube

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የዓለም የህብረተሰብ የጤና ሥጋት ተብሎ ከተበየነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፍሪካ ውጪ በስዊድን በበሽታው የተያዘ ሰው መገኘቱ ሪፖርት ተደርጓል።

የሀገሪቱ የህብረተሰብ ጤና ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የተያዘው ግለሰብ በሽታው ሪፖርት በተደረገበት የአፍረካ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ሲሆን አሁን ላይ በስቶክሆልም የማገገሚያ ሥፍራ ክትትል እየተደረገለት ነው ተብሏል።

ይህ በስዊድን የተገኘው የMpox ዝርያ  በአፍሪካ ሀገራት ሥርጭቱ የጨመረው  ክላድ1 (Clade_1) ቫይረስ ዝርያ መሆኑ ተገልጿል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ዓለም አቀፍ የህዝብ ጤና ስጋት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ዓለም አቀፍ የህዝብ ጤና ስጋት መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስታውቀዋል።

የፈንጣጣ ወረርሽኝ በ ቡሩንዲ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተከሰተ ሲሆን በአህጉሪቱ 2,863 የሚቆጠሩ ሰዎች በበሽታው መጠቃታቸው እና 517 ሰዎችም መሞታቸው ተረጋግጧል።

ይህን ተከትሎ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል እየተስፋፋ የመጣውን የፈንጣጣ ወረርሽኝ አህጉራዊ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ሲል በይፋ አውጇል።

ጤና ሚንስትር በበኩሉ በኢትዮጵያ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ በሞያሌ እና ሌሎች የመግቢያ ቦታዎች የቁጥጥርና ማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

በሽታው ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ ሲሆን በበሽታው የተያዘ ሰው ከሚያሳያቸው ዋና ዋና ምልክቶች መካከልም፤ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የዕጢ እብጠት፣ የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣ ሽፍታ፣ የቆዳ ቁስለት እንዲሁም የአቅም ማጣት እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
    

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት እና ፕሬዘዳንቱ ላይ ሕጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተጠየቀ

👉 በቀረበው ሰነድ ዶክተር አሸብርን ጨምሮ የሥራ አስፈጻሚው ቦርድ አባላት የፈጸሟቸውን በደሎች በዝርዝር ተመልክቷል

👉አቤቱታው ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ጥሰትና ምዝበራ መካሄዱን ይገልጻል

👉 ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ያለ እሱ ፍቃድና ዕውቅና እየተቃወመ በግድ ምክትል እንዳደረጉት ተጠቅሷል።

👉 ረ/ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ያለ ምርጫ ለቦርዱ አመራርነት እንድታልፍ መደረጉም ተያይዟል።

በኢትዮጵያ ተመዝግበው ያሉ ሕጋዊ የስፖርት ፌዴሬሽኖች በሕጋዊ ወኪል ጠበቆቻቸው አማካኝነት፤ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ላይ አስዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ የሚጠይቅ ሰነድ በዛሬው ዕለት ለኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር አስገብተዋል።

አቤቱታ አቅራቢ ፌዴሬሽኖቹ በሰነዳቸው ላይ ካቀረቧቸው ምክንያቶች መሐል፦

👉ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ኮሚቴው ከፌዴሬሽኖቹ እውቅና ውጪ በድብቅ ጥሪ ተደርጎ በድብቅ የተፈጸመ ስብሰባ ማካሄዱን ይገልጻል።

👉አቤቱታ አቅራቢ ፌዴሬሽኖች ባልተጠሩበት፤ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ/ም በተደረገ ሕገወጥ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ምርጫ፤ ኮሚቴ ለሚፈልጋቸው ጥቂት አባላት ብቻ ጥሪ በማድረግ፤ መተዳደሪያ ደንቡ የማይፈቅድላቸውን በድምፅም ሆና ያለ ድምፅ የጠቅላላ ጉባኤው አባል ያልሆኑ ግለሰቦችን የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ አድርገዋቸዋል።

👉 ከዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ጋር የጥቅም ግንኙነት አላቸው ያሏቸውን የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጥበቡ ቸኮልን ኮሚቴው አስመራጭ በማድረግ ሕግ ተላልፏል ሲል በአቤቱታው ላይ ያስነብባል።

👉አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ዕውቅና እና ፍቃድ ድርጊቱን እየተቃወመ በሕገ ወጥ ምርጫው ላይ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ተደርርጓል የሚል አቤቱታም ይገኝበታል።

👉የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በጠቅላላ ጉባኤው ምርጫና አብላጫ ድምፅ እንደሚመረጡ መተዳደሪያ ደንቡ የሚደነግግ ቢሆንም ረ/ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ያለ ምርጫ እንድታልፍ መደረጉን በሰንዱ ተብራርቷል።

👉ለኮሚቴው ከረጂ ተቋማት የተሰበሰበ ከ300,000,000.00 (ከሦስት መቶ ሚልየን ብር) በላይ ምን ላይ እንደዋለ በኦዲት ሪፖርት እንደማያውቁት አቤቱታ አቅራቢዎቹ በሰነዱ ላይ ገልጸው በተጨማሪም ከስፖንሰር አድራጊዎች የተገኙ በውጭ ምንዛሪ ገቢ የተደረጉ ገንዘቦች ምን ላይ እንደዋሉ የሙያሳይ ግልጽ የኦዲት ሪፖርት አለመደረጉን አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጨምረው ዘርዝረዋል።

👉ሰነዱ የአትሌት ገዘኸኝ አበራንም ጉዳይም አያይዞታል።

👉 በአትሌቶች አመራረጥ ላይ ተደርጓል ስለተባለው አድሏዊ አሠራርም ተካቷል።

👉ለአገር ክብር ምልክት ከሆኑ አትሌቶች ይልቅ የአመራሮቹ ዘመድ አዝማዶች አገር ወክለው እንዲሄዱ መደረጉም ተነሥቷል።

👉 ሰነዱ የሥራ አስፈጻሚው ቦርድ አባላት የቅርብ ዘመዶች በኮሚቴው ያለ አግባብ ቅጥር እንዲፈጸምላቸው በማድረግ ምንም ዓይነት ሥራ ሳይፈጽሙ ገንዘብ በመመዝበር በርካታ የፋይናንስ ጥሰት መደረጉን ጨምሮ ይገልጻል።

እነዚህን እና ሌሎችንም አቤቱታዎች ያቀረቡት ፌዴሬሽኖች

👉ኮሚቴው አሻሻልኩት ያለው መተዳደሪያ ደንብ እንዲታገድ፤

👉ሰኔ 4 ተደረገ የተባለው ሕገ ወጥ ምርጫ እንዳልተደረገ ተደርጎ ቀሪ እንዲደረግላቸው፤

👉የተፈጸሙት ተግባራት ከባድ የሆነ የዲሲፕሊን ጥፋት ውጤት በመኾናቸው ቦርዱ ከኃላፊነት ታግዶ እንዲቆይ

👉 በገለልተኛ ኦዲተር ምርመራ እንዲደረግ፤ በመጠየቅ

👉ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ አስተዳደራዊ ርምጃ እንዲወሰድላቸው አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጠይቀዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን በውሃ ዋና የወከለችው ሊና አለማየሁ በ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ አዲስ የኢትዮጵያ ክብረወሰን አስመዝግባለች፡፡

ሊና አለማየሁ የመጀመሪያ ውድድሯን በአራተኛነት ማጠናቀቅ ችላለች። በዚህም በ50 ሜትር ሴቶች የነጻ ቀዘፋ ውድድር ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ሳትችል ቀርታለች።

በውድድሩ የገባችበት ሰዓት 31 ሴኮንድ ከ87 ማይክሮ ሴኮንድ ከዚህ በፊት በያኔት ስዩም ተይዞ የነበረውን የኢትዮጵያ ክብረወሰን እንድታሻሽል አስችሏታል።

በ2012 በለንደን ኦሊምፒክ ዋናተኛ ያኔት ስዩም በ50 ሜትር ይዛው የነበረው ክብረወሰን 32:41 ሰከንድ ነበር።

በቦጋለ አበባ

ሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓም

(ምንጭ፡ ኢፕድ)

#TeamEthiopia #Paris2024 #OlympicGames

Читать полностью…

EthioTube

በሪሁ አረጋዊ በወንዶች 10ሺ ሜ ከእልህ አስጨራሽ ፉክክር በኋላ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኘ። ወርቅ የኡጋንዳ ሆኗል።
-----

#OlympicGames in #Paris2024 - Men's 10,000m

Silver🥈for #TeamEthiopia

Berihu Aregawi 🇪🇹 (26:43:44)

(📸: Getty Images)

Читать полностью…

EthioTube

በሴቶች 5ሺ ማጣሪያ ጉዳፍ ፀጋይ 5ኛ፣ እጅጋየሁ ታዬ 6ኛ፣ መዲና ኢሳ 2ኛ ሆነው ከየምድባቸው በመጨረስ ወደ ፍፃሜ አልፈዋል።
------
#OlympicGames in #Paris2024 - Women's 5000m Round 1 Heats

Medina Eisa 🇪🇹 (15:00:82), Gudaf Tsegay 🇪🇹 (14:57:97), Ejgayehu Taye 🇪🇹 (14:57:97) of #TeamEthiopia qualify to the final after finishing 2nd, 5th and 6th from their respective heats

(📷: Getty Images)

Читать полностью…
Subscribe to a channel