ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲን 2ለ0 በሆነ ውጤት በመርታት መሪነቱን በ9 ነጥብ አስፍቷል።

ዋንጫው ዘንድሮ ወደ አንፊልድ ያመራ ይሆን?

#PremierLeague #Liverpool #ManchesterCity

Читать полностью…

EthioTube

አርሰናል ዌስት ሀምን 2ለ5 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ደረጃውን ወደ 2ኛ አሻሽሏል።

#PremierLeague #WestHam #Arsenal

Читать полностью…

EthioTube

በአዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በዚሁ መሠረት ከታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ ተግባራዊ የሚደረግ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ታሪፍ አሁን እየተሰጠበት ካለው 10 ብር ወደ 20 ብር ማሻሻያ መደረጉን ቢሮው አስታውቋል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያው ከታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ታውቆ ተፈፃሚ እንዲደረግም ቢሮው አሳስቧል፡፡

ድርጅቱ ከሰሜን ወደ ደቡብ (ከጊዮርጊስ - ቃሊቲ) እና ከምስራቅ ወደ ምዕራብ (ከአያት - ጦር ኃይሎች) የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት በየቀኑ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞችን እንደሚያጓጉዝ ተገልጿል፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

አቶ ብናልፍ አንዷለም ከሰላም ሚኒስቴር ሀላፊነታቸው ተነሱ

👉አቶ መሃመድ እድሪስ ተክተዋቸዋል

በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ  የቁዩት አቶ መሃመድ እድሪስ  የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አቶ መሃመድ እድሪስ ከኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ  የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር  ሆነው እንዲያገለግሉ ጠቅላይ ሚስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር ) መሾማቸውን  የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም የት እንደተመደቡ ለማወቅ አልተቻለም፡፡

በፓርላማ ጭምር ከፍተኛ ነቀፌታ የሚቀርብበትና ‹‹ አስፈላጊነቱ ላይ ›› ጥያቄ የሚነሳበት ሰላም ሚኒስቴር በጀቱ ሁሉ ታጥፎ ለሌሎች ተቋማት እንዲውል ተጠይቆ ነበር፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

#Update

የጁባላንድ መንግሥት ከሶማሊያ ፌዴራሉ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ይፋ አደረገ

የጁባላንድ ካቢኔ ስብሰባ ካደረገ በኃላ ይፋ እንዳደረገው  " ሙሉ በሙሉና በይፋ ከሶማሊያ የፌዴራል መንግሥት ጋር ያለውን የስራም ሆነ ማንኛውንም ግንኙነት " አቋርጧል።

የጁባላድ መንግሥት ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድን ፦
- ኃይላቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም
- የእርስ በእርስ ጦርነት በማነሳሳት
- ሰራዊትን በማውደም
- በሙስና ... ከሷል።

ሕገመንግስቱን በማጣስ ወንጅሎም " በፌዴራል መንግሥት የተደረጉ የሕገመንግስት ማሻሻያዎችን አንቀበልም " ሲል አሳውቋል።

ቀደም ሲል ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ በጁባላንድ ፕሬዝዳንት አሕመድ ማዴቦ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።

የጁባላንድ መንግሥት በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ እንዲታሰሩ የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል።

በፌዴራል መንግሥቱ እና በጁባላንድ መንግሥት መካከል ውጥረቱ መባባሱ ተሰምቷል።

NB. ባለፈው አመት የፑንትላንድ መንግሥት ከማዕከላዊው የሶማሊያ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ምንጭ ፦ ቲክቫህ

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ 251 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ መስማማቱ ተገለጸ

ተቋሙ  ብድሩን ለማጽደቅ የተስማማው፣ የድርጅቱ የባለሙያዎች ቡድን ከኅዳር 3 እስከ 17 በአዲስ አበባ ተገኝቶ ሁለተኛውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ግምገማ ማድረጉን ተከትሎ ነው።

የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፣ የብድር መልቀቅ ስምምነቱን በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ እንደሚያጸድቀውም ይጠበቀቃል ተብሏል ።

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቀረፈና በመደበኛውና በትይዩው ምንዛሬዎች መካከል ያለው ልዩነት ከ10 በመቶ በታች መውረዱን የጠቀሰው ድርጅቱ፣ መንግሥት ጥብቅ የገንዘብና ፊስካል ፖሊስ መከተሉን እንዲቀጥልም መክሯል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር እየተዘጋጀሁ ነው አለ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማርና ሌሎች ተግባራትን በላቀ ደረጃ ለመፈፀምና ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ለመሸጋገር የሚያስችለውን ዝግጅት እያከናወነ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ አስራት አጸደወይን (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር የሚያስችለውን 13 የሚደርሱ መመሪያዎችና ፖሊሲዎችን እያዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ስራውን በተሳለጠ ሁኔታ ለማከናወንም አንድ ዐብይና 13 ንኡሳን ኮሚቴዎች በማቋቋም ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፤ ስትራቴጂክ ፕላን በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላትና ለዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ማቅረቡን ገልፀዋል፡፡

ስትራቴጂክ ፕላኑ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ህግ አውጪን፣ የተማሪዎች የመግቢያ ፖሊሲን፣ የኢንዶውመንትና የሪሶርስ ሞብላይዜሽ ፖሊሲ ማቋቋሚያ አዋጅና ደንቦችን ማካተቱን ጠቁመዋል፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ ፣ የእስላማዊ አገራት ትብብር ድርጅት አባል ለመኾን ከድርጅቱ ጋር ንግግር ጀመረች

ኢትዮጵያ፣ የኦርጋናይዜሽን ኦፍ እስላሚክ ኮፕሬሽን (የእስላማዊ አገራት ትብብር) ድርጅት አባል ለመኾን ከድርጅቱ ጋር ንግግር መጀመሯ ተሰምቷል።

ተቀማጭነቱ ጅዳ የሆነውና 58 አባል አገራትን ያቀፈው ድርጅቱ፣ በዓለም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀጥሎ በአባላት ብዛት ትልቁ የበይነ መንግሥታት ማኅበር ነው።

ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመሆን ንግግር የጀመረችው፣ ከድርጅቱ በቀረበላት ግብዣ መሠረት እንደኾነ ታውቋል።

ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመሆን፣ የቱርክን፣ ፓኪስታንንና የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶችን ድጋፍ አግኝታለች።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ጥፋተኛ በተባለችበት የኮምፒዩተር ወንጀል እስር ተፈረደባት

ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ከሦስት ሳምንት በፊት ጥፋተኛ በተባለችበት የኮምፒውተር ወንጀል ክስ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈርዶባታል።

ፍርድ ቤቱ በመስከረም ላይ የእስር ቅጣት ያሳለፈው በጣቢያዋ ባስተላለፈቻቸው ሁለት ፕሮግራሞች ፈጸመችው በተባለው በኮምፒውተር ተጠቅሞ በኅብረተሰቡ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት የመሞከር ወንጀል መሆኑም ተነግሯል።

ፍርድ ቤቱ የእስር ቅጣቱን ባስተላለፈበት ችሎት ላይ መስከረም በአካል እንዳልተገኘችም ነው የተነገረው።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሸለመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ 25 የአለማችን ግዙፍ አየር መንገዶች ሕብረት የሆነው “ስታር አላያንስ” የ2024 ምርጥ የአየር መንገዶች ህብረት በሚል ተሸልሟል፡፡

“ስታር አላያንስ” ውድድሩን ሲያሸነፍ ይህ ለ5ኛ ተከታታይ ዓመት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የዘንድሮው የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብር በፖርቹጋል ማዲዬራ መካሄዱንም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ሊቨርፑል ሳውዝሀምፕተንን 2ለ3 ማሸነፉን ተከትሎ መሪነቱን በ8 ነጥብ አስፍቷል። በሚቀጥለው ሳምንት በሜዳው 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ማንችስተር ሲቲን ይገጥማል።

የሊቨርፑል ደጋፊዎች ዋንጫው ዘንድሮ የማን ነው?

#PremierLeague #Liverpool

Читать полностью…

EthioTube

የፔፕ ጓርዲዮላ ማንችሰተር ሲቲ በሜዳው 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በቶተንሃም ሽንፈትን ተከናንቧል። ሲቲ በሁሉም ውድድሮች በተከታታይ 5 ጊዜ የተሸነፈ ሲሆን፥ ይህ ለጓርዲዮላ በአሰልጣኘነት ታሪካቸው የመጀመሪያቸው ነው።

ዋንጫውን ማን ይበላዋል? የሊቨርፑል እና የአርሰናል ደጋፊዎች ምን ትላላችሁ? 🤔

#PremierLeague #ManCity #Tottenham #Liverpool #Arsenal

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይበር ኦፕሬሽን ዋና ዳይሬክቶሬት እና የጣሊያን የመከላከያ ሳይበር ክፍል በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

የመከላከያ ሳይበር ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ኮሎኔል ሀገር አስቻለ እንዳሉት ስምምነቱ በሳይበር ዘርፍ በትብብር ለመስራትና የሙያተኞችን አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

የተቋሙን የሳይበር ጥቃት ለመከላከልና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት ስምምነቱ ጠቃሚ ነው ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል በመጠቀም ዩክሬን ላይ ጥቃት ፈፀመች

ሩሲያ በዩክሬን መካከለኛው ምስራቅ በምትገኘው ዲኒፕሮ ከተማ ላይ ያነጣጠረ አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል በመጠቀም ጥቃት ስለመክፈቷ ዩክሬን አስታውቃለች።

ይህ ጥቃት ከተረጋገጠ ሞስኮ በጦርነቱ ውስጥ እንዲህ አይነት ሚሳኤል ስትጠቀም የመጀመሪያዋ ይሆናል ተብሏል።

የዩክሬን አየር ኃይል ትክክለኛውን የሚሳኤል ዓይነት ባይገልፅም፤ በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ በሰጠው መግለጫ ሚሳኤሉ የተወነጨፈው ከካስፒያን ባሕር ጋር ከሚዋሰነው ከሩሲያ አስትራካን ክልል ነው ብሏል።

በዲኒፕሮ ከተማ ከሌሎች ስምንት ሚሳኤሎች ጋር አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል የተተኮሰ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የዩክሬን ጦር ከእነዚህ ውስጥ ሥድስቱን መምታቱንም አስታውቋል።

በጥቃቱ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውንና በኢንዱስትሪ ተቋማት እና የአካል ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል ሲል የዘገበው ኤፒ ነው።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

አያት 49 አንድ የባንክ ጥበቃ ተገደለ

በለሚኩራ ክ/ከተማ አያት 49 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  40/60 ሳይት 3 አያት 49 ግሎባል ባንክ ዘበኛው ዛሬ ጠዋት በጥይት ተመትቶ መገደሉ ታውቋል።

ግድያው የተፈጸመው ጠዋት አንድ ሰዓት አካባቢ ነው ያሉት ምንጮች ሌላኛው በጥይት የተመታው ጥበቃ ሠራተኛ ጓደኛ እንደቆሰለ አስረድተው፣ ገዳዩና አቁሳዩ በሌላ ብራንች የሚሰራ የጥበቃ ሠራተኛ ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመዋል።ፓሊስ ምርመራ መጀመሩ ተሰምቷል።

ምንጭ ፦ ዋሱ

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የመጀመሪያ አጋማሽ፡ ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲን 1ለ0 እየመራ ነው።

ጨዋታው ስንት ለስንት ያልቃል?

#PremierLeague #Liverpool #ManchesterCity

Читать полностью…

EthioTube

ቄራው ስህተቱን ካላረመ ከቦታው እንዲነሳ በፍርድ ቤት ተወሰነ

ከ30 ዓመታት በላይ አካባቢ ሲበክልና ለሰው ጤና ጎጂ የሆነ በካይ ፍሳሽ ቆሻሻ በዘፈቀደ ሲለቅ  ነበር የተባለው የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ብክለቱን ማቆም ካልቻለ ከቦታው እንዲነሳ በፍርድ ቤት ተወሰነበት፡፡

ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በፍርድ ቤት ተቋሙን ላይ ክስ በመመስረትና ለ5 ዓመታት በመሞገት የተጠቀሰው ውሳኔ እንዲሰጥ ምክንያት የሆነው ‘’ቁም ለአካባቢ’’ የተሰኘ  መንግስታዊ  ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡

በጎ ፈቃደኛ የህግ ባለሞያዎች የአካባቢ ብክለትን በተመለከተ መሰል ስራዎችን የሚከውነው ቁም ለአካባቢ፤ ከዚህ ቀደምም በ7 ተቋማት ላይ ተመሳሳይ  ውሳኔ በፍርድ ቤት መገኘቱን ነግሮናል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ብክለቱተን ማቆም ካልቻለ አሁን ካለበት ቦታ ተነስቶ ሌላ ቦታ ላይ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የእንስሳት እርድ የሚከውነበት ቦታ እንዲያዘጋጅ በፍርድ ቤት ተወስኖበታል፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

አክሱም ከተማ ከአራት አመታት በፊት በነዋሪዎቿ ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ዘከረች

በ ትግራይ ክልል ከአራት አመታት በፊት የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ በአክሱም ከተማ የተፈጸመው የንጹሃን ጭፍጨማ የሚዘክር መረሃ ግብር ትላንት ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል።

በክልሉ ለሁለት ዓመት በተካሄደው ጦርነት በመጀመሪያ ወር ላይ በኤርትራ ኃይሎች የተገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቤተሰቦች እና ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች ተሰብሰበው ዘክረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተፈጸመውን የጅምላ ግድያን መጠንን በተመለከተ ሪፖርት አውጥተዋል። ሪፖርቶቹ የኤርትራ ኃይሎች በአክሱም ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ስልታዊ በሆነ መንገድ መግደላቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ያልታጠቁ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ ሆን ተብሎ የቤት ለቤት ግድያን ጨምሮ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን አስታውቀዋል።

ትናንት ሐሙስ በተካሄደው መርሃግብር ላይ ከጥቃቱ የተረፉና የከተማዋ ነዋሪዎች ፍትህ እንዲረጋጋጥ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ለሰላም ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ፎቶ፡ ድሚጺ ወያነ

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት።

አንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ነው የሾመው።

ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስራቃዊ ዞን ፅ/ቤት በፃፈው የሹመት ደብዳቤ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዓለም አረጋዊን የከተማይቱ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

አቶ ዓለም የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል።

" ጊዜያዊ አስታዳደሩ በተቋቋመበት ህግ እና አሰራር መሰረት ወደ ስራ ገብቻለሁ አሁን ላይ በፅ/ቤት ስራ ርክክብ እያደረኩ ነው " ብለዋል።

ትናንት ደግሞ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ዓዲግራት ከተማ በተካሄደ የም/ቤት ጉባኤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩትን ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

አቶ ረዳኢ ሹመቱን አረጋግጠዋል።

" TPLF ተወዳድሮ በተመረጠበት ትግራይ እስካሁን ያለው የTPLF ም/ቤት አባላት ናቸው ፤ እኔም እንደ TPLF አንድ አካል ተወካይ ሆኜ ነው የቀረብኩት " ሲሉ ሹመቱ በም/ቤት እንደፀደቀላቸው ተናግረዋል።

አቶ ዓለም ስለ ረዳኢ ሹመት የማውቀው የለም ብለዋል።

" በምክር ቤት ስለተደረገው ሹመት በማህበራዊ መገናኛ ነው ያየሁት በይፋ በመንግሥት መዋቅር አልሰማሁም " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ረዳዒ ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ሹመት ምንም ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።

" ሹመት እንደተሰጠው ሰምቻለሁ ያው ትግራይም ኢትዮጵያም ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አካሄዳችን የአንድ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አስተዳደር የራሱ ምክር ቤት አለው ምክር ቤቱ ነው ከንቲባም ፣ የወረዳ አስታዳዳሪም ፣ ካቢኔም የሚያፀድቀው በዚህ ም/ቤት ያላለፈው ከንቲባ ወይም አስተዳዳሪ የመሆን እድል የለውም " ብለዋል።

" እንደ ድርጅት ከምክር ቤት ውጭ ከመጣ ተቀባይነት አለው ብዬ አላምንም እንደ ህወሓት አቋማችን ይሄው ነው " ያሉት ረዳኢ ከምክር ቤት ውጭ ማንም ሰው ደብዳቤ እየፃፈ የሚሾመው ተቀባይነት የለም ሲሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሰጠውን ሹመት አጣጥለዋል።

ከትናንት በስቲያ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ የወረዳና የከተማ ም/ ቤቶች አብላጫው መቀመጫ በህወሓት በመያዙ ከባለፈው ጉባኤ በኃላ የአመራር ማስተካከያ እያደረግን ነው ብለው ነበር።

የጊዛያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመመራው ቡድን ጊዜያዊ አስታዳደሩን ስራ አላሰራ እንዳለና የወረዳና የከተሞች ም/ቤቶችን በመጠቀም በመንግሥት የተመደቡ አስተዳዳሪዎች እንዲነሱ እያደረገ መሆኑን ይህም መፈንቅለ መንግሥት እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

የዚህ መረጃ ባለቤት ቪኦኤ ሬድዮ ነው።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አራተኛ ፓትርያርክ የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው ።

በሰዓሊና ቀራጺ ቡዝዬ ካሰሽ በስሜን አሜሪካን የተሰራው መታሰቢያ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል አቡነ መርቆርዮስ አጽማቸው ባረፈበት ስፍራ እንዲቆም ይደረጋል።

ሰዓሊና ቀራጺ ቡዝዬ ካሰች በሀገራችን ታዋቂ የሆኑ የመታሰቢያ በርካታ ሐውልቶችን እና ፓርትሬቶችን በመስራት ይታወቃል ።

Via- Befekadu Abay

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በሶማሊያ የፌዴራል መንግሥት እና በክልላዊው ጁባላንድ መሪዎች መካከል ያለው ውጥረት አንዱ በአንዱ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥተዋል

የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት የጁባላንዱ ፕሬዝደንት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የእስር ትዕዛዝ ያወጣ ሲሆን፣ በተመሳሳይ የጁባላንድ መንግሥት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።

በዋና ከተማዋ የሞቃዲሾው የሚገኘው ባናዲር ክልላዊ ፍርድ ቤት የጁባላንዱ ፕሬዝደንት አሕመድ ማዶቤን በሀገር ክህደት ከሷቸዋል።

የጁባላንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ሕገ-መንግሥቱን በመጣስ እና አመፅ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆነዋል ሲል ክስ አቅርቧል።

በባናዲር ክልላዊ ችሎት በአሕመድ ማዶቤ ላይ የወጣው የእስር ማዘዣ ፍርድ ቤቱ የሶማሊያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክስ እና የይታሰሩ ጥያቄን ከተቀበለው በኋላ ነው።

በእስር ትዕዛዙ መሠረት የሶማሊያ ብሔራዊ ፖሊስ አዛዥ የጁባላንዱን ፕሬዝደንት አሕመድ ሞሐመድ ኢስላም አሊያም በቅፅል ስማቸው አሕመድ ማዶቤን በቁጥጥር ሥር አውሎ ፍርድ ቤት እንዲያቀረብ ታዟል።

የክስ መዛግብት እንደሚያሳዩት ማዶቤ በብሔራዊ አንድነት እንዲሁም በሶማሊያ ሉዓላዊነት ላይ ወንጀል ፈፅመዋል የሚሉ ክሶች ቀርበውባቸዋል።

ማዶቤ ከሀገር ክህደት በተጨማሪ ምሥጢራዊ የሚባሉ መረጃዎችን ለሌሎች ሀገራት አሳልፈው በመስጠት ከሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት እና ሕግ ውጪ የሆነ ድርጊት ፈፅማል ተብለው ተከሰዋል።

ይህ በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ ራስገዝ አስተዳደር መሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ምክንያቱ በአገሪቱ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየውን ክልላዊ የውክልና ምርጫ በማስቀረት አገራዊ ምርጫ እንኪካሄድ የፌደራል መንግሥቱ መወሰኑን ተከትሎ ነው።

የጁባላንድ መሪዎች ግን ይህ ውሳኔ የአገሪቱን ሕገ መንግሥት የሚጥስ ነው በማለት በተናጠል ክልላዊ ምርጫ ለማድረግ በመወስን ከቀናት በፊት በተካሄደው ምርጫ አሕመድ ማዶቤ ለሦስተኛ ጊዜ በመሪነት ተመርጠዋል።

ይህን የእስር ትዕዛዝ ተከትሎ የጁባላንድ ቴሌቪዥን ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማዘዣ ወጥቷል ከማለት ውጭ ያለው ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።



via BBC

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

መንግስት ከታክስ ለመሰብሰብ ያቀደዉ 282 ቢሊዮን ብር የንግድ ዘርፉን በይበልጥ አለመረጋጋት ዉስጥ ሊከተዉ ይችላል ተባለ

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ሲጠበቅ የነበረውን የ 2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ 582 ቢሊዮን ብር በጀት አፅድቋል።

ከዚህ በጀት ዉስጥ 282 ቢሊዮን ያህሉ ከግብር እንደሚሰበሰብ የገለፀ ሲሆን ይህም የንግድ ዘርፉን በይበልጥ አለመረጋጋት ዉስጥ እንደሚከተዉ እና የኑሮ ዉድነቱን ሊያባብሰዉ እንደሚችል ከምክርቤት አባላት ጥያቄ አስነስቷል ።

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት እንደተናገሩት " ይህ ከፍተኛ ታክስ በነጋዴው ላይ ጫና እፈጠረ ከመሆኑ በላይ የንግዱ ማህበረሰብን መደናገር" ዉስጥ በይበልጥ እየከተተው መሆኑን አስረድተዋል ።

ገቢን ለመጨመር በሚል የታክስ ጫናዉን ከልክ በላይ መለጠጥ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል እነዚሁ የምክርቤት አባላት ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴም በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ የተደረገው " ከማሻያው በፊት ባለው መቀጠል የሀገርን ኦኮኖሚ እያደሙ መቀጠል እና ወደ ለየለት የኢኮኖሚ ውድቀት የሚያመራ በመሆኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም ጊዜውን የጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል ሲል ካፒታል ዘግቧል ።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክርቤት ፕሬዝደንት እና የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን ወደ ኤርትራ አቅንተዋል

የሽግግር ምክርቤቱ ጀነራሉ በሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ዋና መቀመጫ ካደረጓት ፖርት ሱዳን ሲሸኙ የሚያሳይ ምስል ለቋል።

አል ቡርሃን በኤርትራ በሚኖራቸው ቆይታ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር ወይይት ያደረጋሉ ብሏል ምክር ቤቱ።

ጀነራል አልቡርሃን ወደ ኤርትራ ያቀኑት የባህልና ሚዲያ ሚኒስትሩን ካሊድ አል አሰር እና የደህንነት ኃላፊውን አውል አህመድ ኢብራሂም ሞፋዚልን አስከትለው ነው።

በሱዳን፣ ጀነራል አልቡርሃን እና ጀነራል ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ በሚመራቸው ጦሮች መካከል የተጀመረው ጦርነት 2 1/2 በላይ አመት አስቅጥሯል።

ጀነራሎቹ ወደ ጦርነት የገቡት ከአልበሽር ውድቀት በኋላ የሱዳንን ሽግግር ይመራሉ ተብለው በተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳለ ሀምዶክ ላይ መፈንቀል መንግስት ካደረጉ በኋላ ነበር።

በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች
መገደላቸውን እና ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ በሀገር ውስጥ አለያም ድንበር አቋርጠው ወደ ሌሎች ሀገራት መሰደዳቸውን አለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) መግለጹ ይታወሳል ሲል አል ዓይን ዘግቧል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ መውረጃ  ላይ በደጃች ውቤ ሰፈር የእሳት አደጋ  ተከስቷል።የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት እርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ለአክሱም ፅዮን ማርያም ክብረ በዓል 1 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶች እንደሚገኙ ይጠበቃል ተባለ

የአክሱም ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገብረ መድህን ፍፁም ብርሀን  ለዓመታዊው የአክሱም ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል 1 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶች እንዲሚጠበቁ ተናግረዋል።

የቱሪዝም ፅ/ ቤቱ እንደገለፀው  በህዳር 21 በሚከበረው የንግስ በአል ላይ 5 ሚሊዮን ብር ገቢ ይገኛል የሚል ዕቅድ መያዙን ገልጿል።

ቢሮው የከተማውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከሚደግፉ ነገሮች አንዱ የአክሱም ፂዮን የንግስ በአል እንደሆነ ገልፆ  በዚህም የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙም አንስቷል።

ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ተቀዛቅዞ የነበረውን የከተማዋን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለመመለስ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

የአየር መንገዱም እድሳት ትልቅ ግብአት እንደሆነም ተመላክቷል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የማንችስተር ዩናይትድ አዲስ አሰልጣኝ ሩብን አሞሪም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከኢፕስዊች ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ጀምረዋል።

የዩናይትድ ደጋፊዎች ጨዋታውን እንዴት አገኛችሁት?

#PremierLeague #ManchesterUnited #Ipswich

Читать полностью…

EthioTube

የሚኒስትሮች ምክር ቤት 581.98 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት በማጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ

የሚንስትሮች ምክር ቤት ትናንት ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል በፌደራል መንግስት የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ይገኝበታል።

የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያው የተሻሻለውን የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ማስፈጸም በሚያስችል መልኩ የመንግስት የፋይናንስ አቅምና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም የተጨማሪ በጀት ታሳቢዎችንና የወጭ ታሳቢዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት መዘጋጀቱን ከጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚሁ መሰረት ለመደበኛ ወጪዎች እና የወጪ አሸፋፈን ለማስተካከል የሚውል 581.9 ቢሊዬን ብር ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ማስተካከያ ረቂቅ አዋጁ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ያፀደቀው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት አመት አንድ ትሪሊየን ብር የሚጠጋ በጀት ካፀደቀ ከአምስት ወራት በኋላ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህም የ2017 ዓ.ም አጠቃላይ በጀት ከ1.5 ትሪሊየን ብር በላይ እንደሚያደርገው ተመላክቷል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የሀሴት ገዳይ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ

በአዳማ ከተማ እቴቴ ሆቴል ሀሴት ደርቤ የተባለችን ሴት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በስለት የገደላትን ወንጀለኛ የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት አስተላልፎበታል ፡፡

የአዳማ ፖሊስ አብረሃም ዳዊት የተባለውን ወንጀለኛ ከተደበቀበት ወለንጪቲ ከተማ በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ዛሬ ጠዋት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ተቃውሞ መነሳቱ ተሰማ።

ተማሪዎቹ ይህንን የተቃውሞው ድምፅ ያሰሙት በህዝባችን ላይ ግድያ ይቁም በሚል ምክንያት ሲሆን ተማሪዎቹ ቁርሳቸውን ሳይበሉ ነው ወደ ተቃውሞ የወጡት።

ተቃውሞው እንዳይባባስ የፀጥታ ሀይሎች ጥረት አድርገዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች

ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ነው፡፡ ተጠርጣሪዋ በደላላ አማካኝነት በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በሶስተኛው ቀን ቆይታዋ የግል ተበዳይ ወደ ስራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንዲሁም የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦችን ሰርቃ በመሰወሯ የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተዋል፡፡

ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ቤት ለሦስት ወራት ተከራይታ በነበረበት ቤት ተደብቃ በክትትል የፖሊስ አባላት ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት

* የተለያዩ የሴትና የወንድ ጫማዎች
* 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ
* የተለያዩ የወርቅና ልዩ ልዩ  ጌጣጌጦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን ከክ/ከተማው የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በተጨማሪም በሁለት የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያ እንደተገኘባትም ተገልጿል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አበበ እንደገለፁት የግል ተበዳይ ተጠርጣሪዋን ለስራ ሲቀጥሯት ያቀረበችው የተያዥ ፎርም የራሷን ፎቶ በትክክል እንዳይለይ አድርጋ የለጠፈች ሲሆን የግል ተበዳይም ይህንን ሳያረጋግጡ በእምነት የቀጠሯት መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛ በአጋዥነት መቅጠሩ ተገቢ ቢሆንም በህጋዊ መንገድ በቂ ተያዥ በማስቀረብ የተያዣቸውን አድራሻና ማንነት በአግባቡ በማጤን መቅጠር እንደሚገባና ውድ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ በማስቀመጥ በተገቢው ሊቆጣጠሩና ንብረታቸውን ከስርቆት ወንጀል ሊታደጉ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አዲስ አበባ ፖሊስ

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…
Subscribe to a channel