ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ማክሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 16 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - December 26 , 2023

👉 ሚኒስትር ድዔታው አገር ጥለው መኮብለላቸው መነጋገሪያ ሆኗል

👉 ኢትዮጵያ እዳዋን የመክፈያ ተጨማሪ ቀናቶቿን ሳትከፍል አጠናቃለች ቀጣይ እጣፈንታዋ ምን ይሆን

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/fEo-sGeSiB8

Читать полностью…

EthioTube

የመከላከያ ሠራዊት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በታጣቂዎች ላይ እየወሰድኩት ባለው እርምጃ ድል እየቀናኝ ነው አለ።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን መንግስት ሸኔ እያለ በሚጠራው እና ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እያለ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን ላይ በተወሰደ እርምጃ “ጥቂት የማይባል” የቡድኑ አባላት ተመትተዋል ያለው የአገር መከላከያ ሠራዊት በተመሳሳይ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በሚንቀሳቀሱ እና ፅንፈኛ ባላቸው ኃይሎች ላይም ከስድሳ በላይ ታጣቂዎች “ከጥቅም ውጭ” አድርጌያለሁ ብሏል።

በሁለቱ ክልሎች የሚገኙ አንዳንድ ዞኖች ግጭቶችን ማስተናገዳቸውን የቀጠሉ ሲሆን ግጭቶቹ አንዳንድ ጊዜ በከባድ መሣርያ እንዲሁም በድሮኖች የታጀቡ እንደሆኑ ዘገባዎች ያትታሉ። ይህም ከሰሜኑ ጦርነት ጦስ ገና ጨርሳ ላልወጣቸው አገር ምጣኔ ኃብት ድቀት ከሚኖረው ጫና በተጨማሪ የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

የሠራዊቱ የማኅበራዊ መገናኛ የትስስር ገፅ በምዕራብ እዝ የአንድ ክፍለ ጦር አዛዥ የሆኑትን ኮሎኔል መሃመድ ሙሳን ጠቅሶ እንደዘገበው በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ እንዲሁም በኢቨንቱ ሀሮ ሊሙ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ላይ ነው እርምጃ ወስዷል።

የታጣቂ ቡድኑ አባላት በአካባቢው ዝርፊያ እና ግድያዎች ሊፈፅሙአ እየተዘጋጁ ነበር ሲልም ዘገባው አክሏል። ሠራዊቱ በታጣቂዎቹ ላይ እርምጃ የወሰደው ከኅብረተሰቡ ጥቆማ ደርሶት ነው ያለው ዘገባው “ጥቂት የማይበሉ” የቡድኑ አባላት ተገድለዋል፤ ሌሎች ደግሞ ተማርከዋል ሲል ገልጿል። የተገደሉትን ታጣቂዎች ቁጥር ግን በግልፅ አላስቀመጠም። ሰላማዊ አማራጭን ትቶ በጉልበቱ እየዘረፈ መኖርን ምርጫው አድርጓል በሚል በዘገባው በተጠቀሱ አንድ መኮንን የተወነጀለው ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ መወሰዱ ይቀጥላልም ተብሏል።

በኢትዮጵያ ህግ በሽብርተኛነት የተፈረጀው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በጉዳዩ ላይ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ያለው ነገር የለም።

በኢትዮጵያ መንግስት እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል በሁለት ዙሮች በታንዛኒያ የተደረጉ ድርድሮች ያለውጤት መበተናቸው አይዘነጋም። ይሄንን ተከትሎም በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እና ጥቃቶች መዘገባቸውን ቀጥለዋል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ አካባቢ ግዳጅ ላይ በነበረ አንድ አሃድ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከሩ ታጣቂዎች ሙከራ ከሽፏል ሲል የሠራዊቱ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ በሌላ ዘገባ አትቷል። ጥቃቱን የፈፀሙት የህዝብን እና የመንግስትን ንብረት የመዝረፍ አባዜ የተጠናወተው ፅንፈኛ ቡድን ነው ብሏል።

የታጣቂው ቡድን አባላት “ክፉኛ” ተመትተዋል ያለው ዘገባው በቁጥር ስድሳ የሚሆኑ ታጣቂዎች “ከጥቅም ውጭ ሆነዋል” ያለ ሲሆን ይህንን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ አላብራራም። ይሁን እንጅ ታጣቂው ቡድን “ቁስለኛውን እያንጠባጠበ” ከአካባቢው ሸሽቷል ሲል አክሏል። ይህንን በተመለከተ ከሌላ ወገን የተገኘ ማረጋገጫ የለም።

አማራ ክልል ካለፈው ክረምት አንስቶ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር የሚገኝ ሲሆን የመንግስት ባለስልጣናት አንፃራዊ መረጋጋት ተመልሷል ይላሉ። ይሁን እንጅ አሁንም ግጭቶች መሰማታቸው አልቀረም።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ መሳብ የቻለችው የውጭ ኢንቨስትመንት ከፍተኛ ማሽቆልቆል ታይቶበታል ተባለ።

ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንቷ ባለፉት ዓመታት ከነበረው ጋርም ሆነው በአቅራቢያዋ ካሉ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ጋር ሲተያይ የቁልቁል ተጉዟል ተብሏል። ይሄን ያለው በዓለም ላይ ከፍተኛ ከሚባሉት አራት የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (አካውንቲንግ) ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ኧርነስት ኤንድ ያንግ ወይንም ኢዋይ ነው።

በአንድ ወቅት ለቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ተመራጭ የነበረችው ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ዓመትት መሳብ የቻለችው መጠን ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ወደስድስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ክፉኛ ዝቅ ብሏል። በፈረንጆች አቆጣጠር በ2019 በአገሪቷ ውስጥ ሰላሳ አራት ያህል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፕሮጄክቶች የነበሩ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2022 ወደስድስት ዝቅ ብሏል።

ይህን ካመጡት ምክንያቶች መካከልም የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት፥ የኮቪድ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እና የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ግጭቶች እና ጦርነት ይገኙበታል ሲል የአካውንቲንግ ኩባንያው ገልጿል።
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ልዩ የቀረጥ ተጠቃሚነት (አጎዋ) መቀነሷ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬን የተመለከቱ የደንብ ማነቆዎች ሌሎች ምክንያቶች ናቸውም ተብሏል።

በምስራቅ አፍሪካ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከጨመረላቸው አገራት መካከል ኡጋንዳ እና ኬንያ ይገኙበታል። ኡጋንዳ በፈረንጆች 2022 አስር ቢሊዮን ዶላር ገደማ የውጭ ምንዛሬ አግኝታለች ተብሏል። በዚህም ከ6300 የሚለቁ ዜጎቿ ስራ አግኝተዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ውይይት በቴሌግራም ከዘጠኝ ሞት ደራሲ እና አዘጋጅ ዳዊት ተስፋይ ጋር 👇🏾

/channel/Cinemagallery11?videochat

Читать полностью…

EthioTube

ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ዛቻ መሰንዘሯን ቀጥላለች።

በያዝነው ዓመት ብቻ በአራት ዙሮች የተካሄደው የህዳሴው ግድብ ድርድር ያለውጤት መበተኑን ተከትሎ የግብፅ ባለስልጣናት ዛቻ የቀላቀሉ ንግገሮችን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል። በቅርቡ አስተያየታቸውን የሰጡት የአገሪቱ የመስኖ እና የውሃ ኃብት ሚኒስትር የአገራቸው የውሃ ደህንነት አደጋ የሚጋረጥበት ከሆነ “ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ” እንወስዳለን ሲሉ ተሰምተዋል። ይህ እርምጃ ምን እንደሆነ ግን ዘርዝረው አልገለፁም።

አራተኛው ዙር ድርድር ያለውጤት ባለፈው ሳምንት እንደተቋጨ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን በአቋሟ ግንችር ብላ ስምምነት ላይ እንዳይደረስ አስቸግርላች የሚል ክስ ሰንዝሮባት ነበር። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም በበኩሉ ይህ የግብፅ መግለጫ ዓለም አቀፍ መርኆዎችን የጣሰ ነው ሲል አጣጥሎታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አክሎም ግብፅ የቅን ግዛት ዘመን አስተሳሰብ ላይ ቆማ ቀርታለች ሲል ወርፏታል።

የካይሮው የመስኖ እና ውሃ ኃብት ሚኒስትር ሃኒ ሰዋሊም በሳምንቱ የእረፍት ቀናት ወቅት አል-አራቢያ በተባለ የቴሌቭዥን ጣብያ ቀርበው ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ በተጠየቁበት ወቅት ኢትዮጵያ በግድቡ ያላት ፍላጎት የኤልክትሪክ ኃይል ከማመንጨትም አልፎ ፖለቲካዊ የበላይነት የመያዝ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያኑ በግድቡ የገነቡት የውሃ ቋት እናመነጨዋለን ለሚሉት የኤሌክትሪክ ኃይል ከሚያስፈልገው እጅግ የበለጠ ነው ሲሉ የተሰሙት ሚኒስትሩ እንደዚህ የተጋነነ ሐይቅ ለመገንባት የፈለገችው ኢትዮጵያ ሌላ ድብቅ ፍላጎት ስላላት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በግድቡ ሐይቅ ግንባታ ላይ ብቻም ሳይሆን ለድርድሩ ይዛው በምትቀርበው አቋም እንዲሁም የግድቡ ባላት አስተያየት ከኤሌክትሪክ ኃይል የሚሻገር ዓላማ እንዳላት ግልፅ ነው ሲሉም አክለዋል።

“የህዳሴው ግድብ የፖለቲካ ጥቅም ይኖረዋል፤ ኢትዮጵያ የናይል ውሃን እንድትቆጣጠር እና የበላይነት እንዲኖራት ግብፅ አትፈቅድም” ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ግብፅ በግድቡ ዙርያ ዛቻ የተቀላቀለበት ንግግር ስታደርግ ይህ የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም። ተደጋጋሚ ድርድሮችም ባለፉት ዓመታት ተከናውነዋል። ይሁንና ውጤት ሲያስገኙ አላስተዋለም። ኢትዮጵያም የግብፅን ማስፈራሪዎች ችላ ብላ ከታሰበበት ጊዜ እጅጉን ዘግይቶም ቢሆን ግድቡን ለማጠናቀቅ ተቃርባለች።

በግጭቶች ክፉኛ በደደቀችው ኢትዮጵያና ከዓለም ትልልቅ የጦር ኃይሎች የአንዱ ባለቤት በሆነችው መካከል ቀጥተኛ ጦርነት ይጫራል ተብሎ ባይታሰብም ዲፕሎማሲያዊ ቁርሿቸው ሌሎች የፀጥታ እና የምጣኔ ኃብት መዘዞችን ሊያስከትሉ ግን ይችላሉ።

Читать полностью…

EthioTube

በአሜሪካዋ አላባማ ሁለት ማህፀን ያላት እናት በሁለት ቀናት ውስጥ ሁለት ልጆችን ወለደች።

ከአንድ ሚሊዮን እርግዝና በአንድ እናት ላይ በሚከሰተው በዚህ በሁለት ማህጸን እርግዝና፤ እናት 20 ሰዓታትን በምጥ አሳልፋለች ነው የተባለው።

የ32 ዓመቷ ኬልሲ ሃትቸር ማክሰኞ የመጀመሪያዋን ሴት ልጅ ወለደች፣ ሁለተኛዋን ደግሞ ረቡዕ እለት በአላባማ ዩኒቨርሲቲ በበርሚንግሃም ሆስፒታል በሰላም ተገላግላለች።

እናት ኬልሲ ሃትቸር በማህበራዊ ትስስር ገጿ ላይ ተዓምርኞቹ ስትል የጠራቻቸው ልጀቿ ቤተሰቧን መቀላቀላቸወውን ያታወቀቸወ ሲሆን፤ የህክምና ባለሙያዎችን "አስደናቂ" በማለት አሞካሽታለች።


በሁለቱም ማህጸን ማርገዝ ማለት በቀላሉ ሁለት የተለያየ እርግዝና ተከስቷል እንደማለት ነው የሚሉት የሃቸርን እርግዝና የሚከታተሉት ዶክተር ሪቻርድ ዴቪስ፥ በዚህም ጽንሶቹን መንትያ ማለት እንደሚያስቸግር ይናገራሉ።

በአላባማ ነዋሪ የሆነችው ኬስሊ ሃቸር ከ17 አመቷ ጀምሮ ሁለት ማህጸን እንዳላት የወቀች ሲሆን፤ በአላባማ ዩኒቨርሲቲ በበርሚንግሃም ሆስፒታል እንዲህ አይነት ክስተት 0.3 በመቶ ሴቶች ላይ ሊከሰት እንደሚችል አስታውቋል።

እንደ ሃቸር ሁለት ማህጸን ኖሯቸው ሊፈጠሩ የሚችሉት ከ1 ሺህ ሴቶች ሶስቱ ብቻ ናቸው።
በሁለቱም ማህጸን የመጸነስ እድሉም ከ1 ሚሊየን ሴቶች በአንደኛዋ ይሳካል ተብሎ እንደመታመንም በአላባማ ዩኒቨርሲቲ በበርሚንግሃም ሆስፒታል ገልጿል።

አል አይን

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሀሙስ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 11 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - December 21 , 2023

👉 ኤርትራ ከአውሮፓ ህብረት ለቀረበባት ወቀሳ ምላሽ ሰጠች

👉 በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፈረስ ቤት በተባለች ከተማ እና በአቅራቢያዋ ከሰሞኑ ከፍተኛ የሚባል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ተዘገበ

👉 በርካታ የኦነግ ሸኔ አባላት እጅ መስጠታቸው ተነገረ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/uXtaj1HlIEg

Читать полностью…

EthioTube

እስራዔል ኢትዮጵያዊ ዝርያ ያላቸው ዜጎቿን በቴክኖሎጂ ዘርፍ የበለጠ ለማሰማራት የሚያስችል ውጥን ነድፌያለሁ አለች።

የአገሪቱ የሥራ ሚኒስትር እና የስነ ፈጠራ ባለስልጣን በጋራ እንደገለፁት በአገሪቱ የረቂቅ ቴክኖሎጅ (ሃይቴክ) ዘርፍ ውስጥ ቤተ እስራዔላዊያኑ እንዲሰማሩ የሚያስችሉ መርኃ ግብሮችን በፋይናንስ ለመደገፍ ዕቅድ ተይዟል።

ከፍልስጤማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገኘው እና ከበርካታ ንፁሃን መገደል ጋር ተያይዞ ዓለም አቀፍ ጫና እየበረታባት ያለችው እስራዔል በቴክኖሎጂ ዘርፍ መሪ ከሚባሉት ተርታ ትመደባለች። ከአገሪቷ ዓመታዊ አጠቃላይ ምርት ውስጥ እስከ አስራ ስምንት በመቶ የሚሆነው ከዚሁ ዘርፍ እንደሚገኝ ሪፖርቶች ያመላክታሉ። ከቴክኖሎጅ ጋር በተገኘ አዳዲስ ኩባንያዎች ብቅ ከሚሉባቸው አስር አገራት ውስጥ የምትገኘው ቴል አቪቭ ይህም ጥቂት የሕዝብ ቁጥር ይዛ በዝርዝሩ ውስጥ የተገኘች ብቸኛ አገር ያደርጋታል። ከዚህ ጋር ተያይዞም “የአዳዲስ ኩባንያዎች አገር” ወይንም “ስታርታፕ ኔሽን” በሚል ስያሜ ትጠራለች።

ይሁንና የአገሪቱ ዜጋ የሆኑ ቤተ እስራዔላዊያን እና ሌሎችም በአገሪቱ የሚኖሩ ጥቁሮች በቆዳቸው ቀለም ምክንያት መገለል እንዲሁም መዋከብ ይደርስባቸዋል የሚሉ ውንጀላዎች በብዛት ይደመጣሉ።

አሁን ታዲያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለበትን የሰው ኃይል እጥረት እንዲሁም በዘርፉ የቤተ እስራዔላዊያንን ተሳትፎ ዝቅ ያለ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ሦስት መርኃ ግብሮች ተመርጠው በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አምስት መቶ ሰዎችን ለማሰልጠን ድጋፍ አግኝተዋል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከወንድ ቤተ እስራዔላዊያን መካከል በቴክኖሎጅ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙት አምስት በመቶ እንኳ አይሞሉም። ከሴት ቤተ እስራላዔላዊያን ደግሞ ይህ ቁጥር 2̄.3 በመቶ ብቻ ነው። ይህን ከቀረው የአገሬው ሕዝብ ዝቅ ያለ ቁጥር ነው ተብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

አደንዛዥ ዕፅ አምርተው ለሽራጭ ሊያቀርቡ የነበሩ አርሶአደሮች ተያዙ።

በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ላዮትርጋ ቀበሌ ውስጥ ተመርቶ ሲዘዋወር የነበረ የአደንዛዥ እፅ ምርት በፖሊስ ሀይል በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

አደንዛዥ ዕጹ በአርሷ አደር አቶ እንድሪያስ ኢልጎ አማካኝነት ለሽያጭ በከተማ ሲያዘዋውር በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ምርቱን ብቻውን እንዳላመረተና ሌሎች አርሶ አደሮች አብረውት እንዳሉ የእምነት ቃሉን መስጠቱን ተከትሎ ሌሎች 4 አርሶአደሮችም ተይዘዋል።

በዚህም ፖሊስ የፍርድ ቤት ብርበራ ትዕዛዝ በማውጣት በእያንዳንዳቸው የእርሻ ማሳ ተዘርቶ በቅሎ የደረሰው ምርት በመንቀል ዕጹ በቁጥጥር ሥር መዋሉን አስታውቋል።

የመጀመሪያ ተጠርጣሪው ዘሩን ከከተማ ማንነቱ ካልታወቀ ግለሰብ ተቀብሎ ማምረት እንደጀመረና ምርቱን ወደ ከተማ በማዘዋወር ላይ እንዳለ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ረቡዕ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 10 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - December 20 , 2023

👉 ኢትዮጵያ የአልሸባብ ታጣቂዎች የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ ሲሰናዱ ያዝኩ አለች።

👉 ሠራተኞቼ በፀጥታ ኃይሎች ተደብድበዋል ያለው የአፍሪካ የልማት ባንክ የውጭ አገር ባለሞያዎቹን ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ ለማስወጣት ወሰነ።

👉 በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ወጥነው የነበሩ የውጭ አገር ኩባንያዎች ፍላጎት ተቀዛቅዟል ተባለ።

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/eA4UvbXzgdU

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ የአልሸባብ ታጣቂዎች የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ ሲሰናዱ ያዝኩ አለች።

በቁጥር አስራ አራት ይሆናሉ የተባሉት ታጣቂዎች በምስራቃዊው የሶማሌ ክልል ነበር ጥቃት ሊያደርሱ ያሰቡት ተብሏል። ጥቃቱም ያነጣጠረው የክልሉ መዲና ጅግጅግና ከተማ እና በዙርያዋ ያሉ አካባቢዎች ናቸው ሲል የደህንነት እና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ተናግሯል።

ስለተባለው እስር በዋናነት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን አልሸባብ ያለው ነገር የለም። አልሸባብ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገራት በሽብርተኛነት የተፈረጀ ቡድን ሲሆን ለዓመታት ይዞታውን በሶማሊያ ሲያስፋፋ ቆይቷል።

በቅርብ ወራት ግን የሶማሊያ መንግስት በተለያዩ ዙሮች በከፈታቸው ዘመቻዎች የአልሸባብ ይዞታዎችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ ነው። የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል አገሪቷን ለቅቆ የሚወጣበት ጊዜ ከመቃረቡ ጋር ተያይዞ የአገሪቱ ጦር ራሱን ለማጠናከር ብሎም በታጣቂ ቡድኑ ላይ የበላይነትን ለመያዝ እየታተረ ይመስላል።
ልዕለ ኃያሏ አሜሪካ የተመረጡ የአልሸባብ ዒላማዎች ላይ የድሮን ጥቃቶችን በማድረስ እገዛዋን እያሳየች ነው። አልሸባብ በከተሞች የሽብር ፍንዳታዎች መፈፀሙን መቀጠሉ ግን ይዘገባል። ከጥቂት ወራት በፊት የአልሸባብ ታጣቂዎች ለኢትዮጵያው ሶማሌ ክልል ጠጋ ብለው በሚገኙ አካባቢዎች ዘመቻዎችን ለማድረግ መሞከራቸው አይዘነጋም።

በሶማሌ ክልል ጥቃት ሊያደርሱ ነበር የተባሉት የአልሸባብ አባላት መሪ አሊ አብዲ በሚል ስም እንደሚጠራ የግብረ ኃይሉ መግለጫ አሳውቋል። መግለጫው አክሎም ይሄው የቡድኑ መሪ በሞያሌ በኩል ሰርጎ ለመግባት ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል ብሏል። ህገ ወጥ የጦር መሣርያዎችን እንዲሁም ሰነዶችንም አብሬ ይዣለሁ ብሏል።

ለሽብር ተግባሩ ሊውሉ የነበር የተባሉት የጦር መሣርያዎቹም በጅግጅግና በዋርዴር እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በተደረጉ እርምጃዎች ተይዘዋል ብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

በሕዳሴው ግድብ ዙርያ ሲደረግ የነበረው ንግግር ያለውጤት ተበተነ።

ግብፅ ኢትዮጵያን ለስምምነት አሻፈረኝ ብላለች በማለት ስትወነጅላት፥ ኢትዮጵያ በበኩሏ ግብፅን የቀኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብ ተጣብቷታል ስትል ወቅሳታለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ አል ሲሲ ተገናኝተው በግድቡ ዙርያ ተቋርጦ የነበረውን ድርድር ለማስቀጠል እንዲሁም በአፋጣኝ አንዳች ዓይነት ስምምነት ላይ ለመድረስ መወሰናቸውን ከተናገሩ በኋላ ነበር ሦስቱ አገራት ወደጠረጴዛ የተመለሱት። ከዚያም በተለያዩ ጊዜያት በግብፅ መዲና ካይሮ እና በአዲስ አበባ ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፤ በዚህ ሳምንትም አራተኛው ዙር ውይይት መጀመሩ ተዘግቦ ነበር። ይሁንና ንግግሩ ያለውጤት መጠናቀቁን ሁለቱ አገራት በየፊናቸው ባወጧቸው መግለጫዎች አሳውቀዋል። በግጭት የምትታመሰው ሱዳን ግን በጉዳዩ ላይ ብዙም ያለችው ነገር የለም።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቴክኒካዊ እና ህጋዊ ጉዳዮች ላይ አቋሟን ላላ በማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያ አበክራ አሻፈረኝ ብላለች ሲል ውንጀላውን አስደምጧል። በዚህም ሳይወሰን ግብፅ የዓለም አቀፍ ደንቦችን እና ስምምነቶችን በመከተል ውሃዋን እንዲሁም ብሔራዊ ደህንነቷን ከጉዳት የመከላከል መብቷን የሚነካባት የለም ሲል ፈርጠም ብሎ ተናግሯል።


የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩሉ ካይሮን በቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ላይ ተቸንክራ ስምምነት ላይ እንዳይደረስ እንቅፈት መጋረጥ ይዛለች ሲል ወርፏታል። የፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርኆን በመከተል የአሁንም ሆነ የወደፊት ትውልዶች የሚኖሯቸውን ፈተናዎች ለመጋፈጥ ውሃዋን የመጠቀም መብቷን እውን እንደምታደርግ እጅጉን ግልፅ ማድረግ እንፈልጋለንም ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ።

ግንባታው ስድስት ዓመታትን ይወስዳል ተብሎ አስራ ሁለተኛ ዓመት የደረሰው የህዳሴው ግድብ የውሃ ቋቱ ቢሞላም እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጭት ቢጀምርም ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ በሙሉ አቅሙ ኤሌክትሪክ የመስጠት ደረጃ ላይ አልደረሰም።

ግብፅ እና ሱዳን ከአባይ ውሃ የምናገኘው ውሃ በግድቡ ምክንያት ችግር ውስጥ ሊገባ ይችላል የሚል ስሞታን ለዓመታት ሲያሰሙ ቆይተዋል። ግድቡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቼ ብርሃን እንዲያገኙ የማደርገው ጥረት አንድ አካል ነው የምትለው ኢትዮጵያ ግን ማንንም የመጉዳት ኃሳብ የለኝም ትላለች።

በየጊዜው በርከት ያሉ ድርድሮች ሲካሄዱ ቢቆዩም አንዳችው ህጋዊ አሳሪነት ያለው ስምምነትን ለማስገኘት አልተቻላቸውም። በበርካታ ጉዳዮች ላይ መግባባት መደረስ መቻሉን ግን ተደራዳሪዎች ሲናገሩ ይደመጣሉ። ይሁንና በተለይ ድርቅ በሚኖርባቸው ጊዜያት ውሃውን እንዴት ነው የምንጠቀመው እንዲሁም የውሃውን ፍሰት መቆጣጠር የሚቻለው እንዴት ነው በሚሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት ሊደረስ እንዳልቻለ እንዲሁም ጉዳዮቹ አጨቃጫቂ ሆነው መቀጠላቸው ይገለፃል።

በአዲስ አበባ ሲከናወን የቆየው የአሁኑ ንግግር ያለ ፍሬ ከተበተነ በኋላ ቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎችን በተመለከተ የጠራ መረጃ ባይኖርም የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት መግለጫ ድርድሮቹ ዳግም እንደሚቀጥሉ ተስፋ አለኝ ብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ማክሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 9 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - December 19 , 2023

👉 ኢትዮጵያ ያለባት እዳ ሳይከፈል ሌላ ብድር ልትጠይቅ እየተዘጋጀች ነው

👉 ቴዎድሮስ አድሃኖም በአማራ እና በትግራይ ጉዳይ የተናገሩት ምንድነው ?

👉ደቡብ አፍሪካ የቀጣችው ኢትዮጵያዊ ።

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/lOfbpAosEpk

Читать полностью…

EthioTube

ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል አካባቢ አንድ ሰው በጥይት ተመቶ ተገድሏል።

ድርጊቱ የተፈፀመው ቦሌ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ በሚገኝ አንድ የመዝናኛ ስፍራ አካባቢ ነው።

ምሽት አራት ሰዓት ገደማ ሟች አባተ አበበ በአንድ መሳሪያ በታጠቀ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል።

አባተ አበበ ተወልዶ ባደገበት ፣ በሚኖርበት አካባቢ እንዲሁም ደግሞ በስራ ህይወቱ በመልካም ስነምግባሩና በተግባቢነቱ በርካቶች እንደሚያውቁት ለመረዳት ችለናል።


ገዳይ እንዳልተያዘ ለመረዳት ተችሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ በሰጠው ቃል፤ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ ምርመራ ላይ መሆኑን ገልጾ ሲጠናቀቅ በሚዲያ ለህዝቡ ይፋ ይደረጋል ብሏል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ የጎደለ በጀቷን ለመደጎም ከአይ ኤም ኤፍ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በብድር ለማግኘት እየተጣጣረች ነው።

እስከፈረንጆች 2028 ድረስ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት ያጋጥማታል ተብሏል።

ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ጋር ድርድር ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ ክፉኛ የተራቆተ ፋይናንሷም ለማለምለም አይኤምኤፍ ከተለመደው የተለየ የብድር ዕድል እንዲሰጣት ነው ጥያቄ ያቀረበችው።

በጉዳዩ ላይ ዘገባ ያስነበቡ ዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች እንደሚሉት ድርድሩ የምጣኔ ኃብቱን መናወጥ በመቀነስ መረጋጋትን መፍጠርን ዓላማ ያደረገ የማሻሻያ መርኃ ግብር ላይ የሚያጠነጥን ነው።

ኢትዮጵያ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ በሚጀመረው የፈረንጆች 2024 የመጀመሪያ ሦስት ወራት ከገንዘብ ተቋሙ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ውጥን ይዛለች።

ከአይኤምኤፍ ከጠየቀችው የ3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር በተጨማሪ ከዓለም ባንክ ያንኑ የሚያህል የበጀት ድጋፍም ጠይቃለች ኢትዮጵያ።

የውጭ ብድር ጫናቃዋ ላይ ተጭኖ ያጎበጣት እና ግጭቶች ያተራመሷት አገር ከሰሞኑ የብድር ክፍያ አራዝሙልኝ እና የቦንድ ወለድ ቀንሱልኝ ጥያቄዎችን ለተለያዩ አካላት በማቅረብ ተጠምዳለች።

ለቦንድ ገዥዎች የሚጠበቅባትን የ33 ሚሊዮን ዶላር የወለድ ክፍያ ለመፈፀም እንዳልቻለች ባለፈው ሳምንት የተዘገበ ሲሆን በጉዳዩ ላይ አቋሙን የገለፀው የገንዘብ ሚኒስትር የወለድ ክፍያው ያልተፈፀመው መክፈል ስለተሳነን ሳይሆን ሁሉንም አበዳሪዎች በእኩል ደረጃ መመልከት ስለምንፈልግ ነው ማለቱ ይታወሳል። ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት ግን ከቦንድ ያዥዎች ሰማነው ብለው እንደዘገቡት ኢትዮጵያ በድንገት ነው ክፍያውን መፈፀም እንደማትችል ያሳወቀችው።

ይሄንን ተከትሎም በእፎይታ ጊዜዋ የመጨረሻ ሳምንት ላይ የምትገኝ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ክፍያው የማይፈፀም ካልሆነ ወይንም ደግሞ አንዳች ዓይነት ስምምነት ላይ ለመድረስ ካልተቻለ ዕዳ መክፈል የማይችሉ አገራት ተርታ የመፈረጅ ዕጣ ይገጥማታል። ይህም ዓለም አቀፍ ብድርን ወይንም የፋይናንስ ድጋፍን ለማግኘት እንዲቸግራት ያደርጋል የሚል ስጋት አንዣብቧል።

ከሁለቱ የቻይና አበዳሪ ተቋማት የቻይና ኤግዚም ባንክ እና የቻይና ልማት ባንክ ጋር ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሚቆይ ጊዜ ያህል የብድር ክፍያ ፋታ ለማግኘት ስምምነት ላይ መድረሷ ለምጣኔ ኃብቷ እንደበጎ ነገር ታይቷል። ከአበዳሪዎችም ጋር የ1 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ እፎይታን ብታገኝም ይህ እፎይታ ግን ከአይኤምኤፍ ጋር ስምምነት ላይ በመድረሷ ላይ የተንጠለጠለ ነው።

ኢትዮጵያ እንደፈረንጆች ቆጠራ በ2021 ጂ20 እየተባሉ በጅምላ ከሚጠሩት ባለፀጋ አገራት የብድር እፎይታ ጠይቃ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ተፋፍሞ የነበረው ጦርነት እንዲሁም ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ይደመጡ በነበሩ የመብት ጥሰት ውንጀላዎች ምክንያት ንግግሮቹ ምንም ውጤት ላይ ሳይደርስ ቀርቷል።

የጦርነቱ በሰላም ድርድር መቋጨት እንደበጎ እምርታ ቢታይም በሁለት ክልሎች ግጭቶች መቀጠላቸው፥ የሰላም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግም የታየው ዳተኝነት በብድር እፎይታ ጥያቄዎች ላይ ደንቃራ ሆኖ ቆይቷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የአገሪቷ ምጣኔ ኃብት በውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲሁም ከከፍተኛ የዋጋ ንረት ወዲያ ወዲህ መላጋት ይዟል። በግጭቶች ምክንያት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ መቸገሯም የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሬ ድርቅ አባብሶታል።

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በየትኛዉም መልክ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም።

ከሰሞኑ የሮማዉ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ቤተክርስቲያኗ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ቡራኬ እንዲሰጡ ፈቃድ መስጠታቸዉን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ መግለጫ አዉጥቷል።

ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ጋር የሚጻረር ወይንም ዉዥንብርን ሊፈጥር የሚችል ስርዓተ አምልኮን ያወግዛል ብሏል። ሆኖም የጳጳሱ መልዕክት በተቃራኒው ተወስዷል የሚል ሃሳብ ያለዉን መግለጫ ያወጣ ሲሆን ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ጋብቻን ግን ጳጳሱ ፈቃድ አልሰጡም ብሏል።

አክሎም የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስን በማስቀመጥ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በየትኛዉም መልክ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም ፤ አታጸድቅምም ማለቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከመግለጫው ተመልክቷል።

ቤተክርስቲያኒቱ ሀጢያትን አትባርክም ታወግዛለች እንጂ ያለዉ መግለጫዉ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ የኢትዮጵያ ባህል እና እሴትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት እንደማይኖረዉም በመግለጫው አስታዉቋል።

Читать полностью…

EthioTube

ሚኒስትር ድዔታው አገር ጥለው መኮብለላቸው ተነገረ።

አንደኛው ሚኒስትር ድዔታው ከኃላፊነት የተነሱበት እና ወዲያውም ለእስር የተዳረጉበት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አሁን ደግሞ ሌላኛው ድዔታው ጥለውት ከአገር መውጣታቸው ተዘግቧል።

ባለፈው ሳምንት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ድዔታ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ታየ ደንደዓ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ገልፀው ሲያገለግሉት የነበረውን መንግስት እንዲሁም የፓርቲያቸውን መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጠንከር ባሉ ትችቶች ነቅፈው ነበር።

ብዙም ሳይቆይ ግን የፀጥታ ኃይሎች በወንጀል እንደጠሯቸውና ገልፀው በቁጥጥር ስር አውላቸዋል። ታየ ከፀጥታ አደፍራሽ ታጣቂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው፥ ከሰዎች መታገት ጋርም ይያያዛሉ ተብለው ነው በፀጥታ ኃይሎች የተጠረጠሩት።

አሁን ደግሞ ሌላኛው የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ድዔታ ዶክተር ስዩም መስፍን አገር ጥለው መኮብለላቸው ተዘግቧል።

ስዩምም እንደታየ ሁሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ጠንከር ያለ ትችትን አባል ሆነው ሲያገለግሉት በቆዩት ገዥው ፓርቲ ላይ አዝንበዋል። ፓርቲውን “መንግስታዊ ባህርይን ያልተላበሰ” ነው ያሉት ሲሆን አባላቱን በሴራ ፖለቲካ ተጠምደው የሚራኮቱ ናቸው ብለዋቸዋል። ገዥውን ፓርቲ ከዚህም በዛ ያለውን የአገሪቱን ክፍል በቅጡ እያስተዳደረ አይደለም ያሉት ሲሆን የራሱ አባላት እንኳ እምነት የማይጥሉበት ነው ብለውታል። በግሌ በህዝብ ላይ ያደርስኩት በደል ባይኖርም፥ የመንግስት አካል ሳለሁ በሕዝብ ላይ ለደረሰው በደል ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል።

ከስዩም አስተያየት በኋላ ገዥው ፓርቲ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር ስለመኖሩ አልተሰማም።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ እዳዋን የመክፈያ ተጨማሪ ቀናቶቿን ሳትከፍል አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ የ33 ሚሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ ብድር ወለድ ትናንት በቀነ ገደቡ ሳትከፍል መቅረቷን ብሉምበርግ ዘግቧል።

የወለዱ መክፈያ ዋናው ቀነ ገደብ ያለፈው ከሁለት ሳምንት በፊት ሲሆን፣ ቀነ ገደቡ የ14 ተጨማሪ የእፎይታ ቀናት ነበረው።

መንግሥት የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ብድር ወለዱን ከሁለት ሳምንት በፊት ያልከፈለው፣ ሁሉንም አበዳሪዎች በእኩል ለማስተናገድ እንደሆነ መግለጡ ይታወሳል።

የወለድ መክፈያው የእፎይታ ጊዜ ትናንት ማብቃቱን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ የውጭ ዕዳዋን መክፈል ያልቻለች አገር ሆናለች።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ የእለተ ሰኞ ኢትዮትዩብ አንኳር አጫጭር ዜናዎች - ታህሳስ 15 ፣ 2016 | #Ethiopia: EthioTube Ankuar : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - December 25 , 2023

👉 የአፍሪካ ልማት ባንክ የውጭ አገር ሰራተኞቹን ጠቅልሎ ከኢትዮጵያ እንዲያስወጣ ካስገደደው ጥቃት ጀርባ ዘርዘር ያሉ መረጃዎች ተሰምተዋል

👉 ተፈናቃዮች ሳንፈልግ ሸሽተነው ወደመጣነው ቦታ ተመለሱ እየተባልን ነው አሉ

👉 ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ዛቻ መሰንዘሯን ቀጥላለች።

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/lGtNQiDy5SY

Читать полностью…

EthioTube

የአንጋፋዋ ጋዜጠኛ ዓይናለም ባልቻ የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈጸመ

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ፕሮግራም ላይ ሰፊ አገልግሎት ከሰጡና ተጽኗቸው ከላቀ ጋዜጠኞች አንዷ የነበረችው ጋዜጠኛ ዓይናለም ባልቻ የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በቤቴል ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

ዓይናለም ባልቻ ሐምሌ 21 ቀን 1961 ዓ.ም የተወለደች ሲሆን የልጅነት ጊዜዋን በህፃናት አምባ አሳልፋለች። የከፍተኛ ትምህርቷን በቡልጋሪያ ቀጥላ በጋዜጠኝነት ትምህርት በማስተርስ ተመርቃለች።

ጋዜጠኛ ዓይናለም በ1988 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን የተቀላቀለች ሲሆን በጣቢያው ለ25 ዓመት ያህል አገልግላለች። ከ25 ዓመት በተቋሙ የሥራ ቆይታዋ ውስጥም ረዥሙ የሆነውን የሥራ ክፍል ያሳለፈችበትን ማለትም 15 ዓመትን የሰራችበት የህፃናት ክፍልን ወደ መጨረሻ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሥራ ቆይታዋ እስከ ዳይሬክተር በመሆን አገልግላለች። 

ጋዜጠኛ ዓይናለም ባልቻ ባደረባት የጤና እክል ምክንያት ከሥራዋ ተገላ ለረጅም ዓመት በሕመም ቆይታ ነበር። ከጥቂት ወራት በፊት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የአዲስ ዓመት ፕሮግራም ለአንጋፋዋ ጋዜጠኛ ዓይናለም ይፋዊ የዕውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት አበርክቶላታል።

ጋዜጠኛ ዓይናለም ባልቻ የአንዲት ሴት ልጅ እናት እና የሁለት የልጅ ልጆች አያት ነበረች። ኢትዩትዩብ ለቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ይመኛል።

Читать полностью…

EthioTube

ተፈናቃዮች ሳንፈልግ ሸሽተነው ወደመጣነው ቦታ ተመለሱ እየተባልን ነው አሉ።

ተፈናቃዮቹ ለደህንነታችን ዋስትና የለንም ቢሉም መንግስት በግዳጅ የሚመለስ ተፈናቃይ የለም ይላል።

በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ምዕራባዊ የወለጋ ዞኖች በተለያየ ጊዜያት ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች የሚገኙ ሰላማዊያያን ናቸው በግዳጅ ተመለሱ እየተባልን ነው ያሉት። ተፈናቃዮቹ ለልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ የብዙሃን መገናኛዎች እንደተናገሩት ጥለዋቸው ወደመጡት የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ከስጋት አንፃር የመመለስ ፍላጎት የላቸውም፤ ይሁንና በአጭር ጊዜ ውስጥ መመለሳቸው እንደማይቀር የአካባቢው ሹማምንነት ነግረዋቸዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ፅህፈት ቤት ተፈናቃዮቹን ወደቀያቸው የመመለስ ስራ የሚከናወነው በፈቃድ ላይ ተመስርቶ መሆኑን እና ተፈናቃዮቹ የሚመለሱትን የፀጥታ ሁኔታቸው አስተማማኝ ወደሆኑ አካባቢዎች መሆኑን ይሞግታል።

ጉዞው በዚህ ሳምንት መባቻ ላይ እንደሚጀምር እንደተነገራቸው የገለፁት ተፈናቃዮች ወደተፈናቀሉባቸው አካባቢዎችን መመለስን አስፈሪ የሚያደርግባቸው በክልሉ ምዕራባዊ ክፍሎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ የማያስተማምን እና የማይገመት በመሆኑ ነው።

ባሉባቸው የጊዜያዊ ማቆያዎች በቂ ድጋፍ እያገኙ ያለመሆኑን የሚናገሩት እነዚሁ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ የማይፈለጉ ከሆነ ከማቆያዎቹ በግዳጅ እንዲወጡ ሊደረጉ እንደሚችሉ ፍርሃት ገብቷቸዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተናቃዮችን ቁጥር አስተናግዳለች።

በቅርብ ይፋ የሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃዎች እንደሚያሳዩትም በአሁኑ ጊዜ ከአራት ሚሊዮን የሚልቁ ተፈናቃዮች በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ስፍራዎች በጊዜያዊ ማቆያ ጣብያዎች ይገኛሉ። ይህም አገሪቷን ከፍተኛ የተፈናቃዮች ቁጥር ካለባቸው የአፍሪካ አገራት ተርታ ያስቀምጣታል። ግጭቶች ዋነኛ የመፈናቀል ምክንያት ሆነው ቀጥለዋል።

የመንግስት ባለስልጣናት ከተፈናቃዮች ጋር በተያያዘ የሚሰጧቸው መፍትሔዎች በአብዛኛው ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው መመለስ ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ ይህ ግን በተለይ የማንነት ተኮር ጥቃቶች ሰላባዎች በሆኑ እንዲሁም በግጭቶች ምክንያት ቤት አልባ በሆኑ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ሲያገኝ አይስተዋልም።

Читать полностью…

EthioTube

ኤርትራ ከያዘቻቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች ለቅቃ ትውጣ ሲል የእውሮፓ ኅብረት ያወጣውን መገለጫ “የለየለት ቅጥፈት” ስትል አጣጣለች።

የአገሪቱ የመረጃ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ ወኪሎች ወደኢትዮጵያው ትግራይ ክልል በማቅናት የኤርትራ ጦር በክልሉ እንዳለ በመግለፅ የለየለት ቅጥፈትን እንደበቀቀን አነብንበዋል ሲሉ ምሬታቸውን ገልፀዋል። እንዲህ ዓይነት የአውሮፓ ኅብረት ውንከላ የተለመደ እየሆነ መጥቷል ሲሉ የመረጃ ሚኒስትሩ አክለው በፅሁፋቸው አትተዋል።

የማነ ይህን ያሉት ሰሜናዊውን የኢትዮጵያ ክልል ትግራይን የጎበኙ የአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ ልዑካን የኤርትራ ጦር ከያዛቸው የትግራይ አካባቢዎች ለቅቆ መውጣት አለበት ማለቱን ክልላዊው ቴሌቭዥን ከዘገበ በኋላ ነው።

የኤርትራ ጦር በሁለት ዓመቱ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ፌዴራላዊውን መንግስት ወግኖ ስለመሳተፉ ብዙ የተዘገበ ሲሆን በወቅቱም የመብት ጥሰቶችን ፈፅሟል ተብሎ ተወንጅሏል። ይሁናን ለጦርነቱ መቆም ምክንያት የሆነው የሰላም ስምምነት ሲደረግ በውይይቱ ያልተካተተ ሲሆን እስካሁንም የያዛቸው አካባቢዎች አሉ እየተባለ ይታማል። ይሁንና አስመራ ይሄንን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው ስትል ታጣጥለዋለች።

Читать полностью…

EthioTube

መንግስት ከአንድ ሺህ አምስት መቶ የሚልቁ ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባላት ወደሰላማዊ ህይወት ተመልሱ አለ።

መንግስት “ሸኔ” እያለ የሚጠራውና በኢትዮጵያ ህግ በሽብርተኛነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሲሰጥ አልተሰማም።

የታጣቂ ቡድኑ አባላት ስልጠና ወስደው ወደሰላማዊ ህይወት መመለሳቸውን ነው ለመንግስት ቀረብ የሚሉ የብዙሃን መገናኛዎች የዘገቡት።

አስቸኳይ አዋጅ ጋር በተገናኘ ታስረው የነበሩ በርካታ ወጣቶች ስልጠና ወስደው ወደኅብረተሰቡ ተቀላቅለዋል ተብሎ መዘገቡ ይታወሳል።

ስልጠናቸውን ጨርሰዋል የተባሉት የኦሮሚያ ታጣቂዎች ቃለ መሃላ የፈፀሙ ሲሆን የይቅርታ መርኃ ግብርም ተከናውኖላቸዋል ተብሏል። የይቅርታ እና የቃለ መሃላ ስርዓቱ የተፈፀመው በቢሻን ጉራቻ ከተማ በሚገኝ ቶጋ የተሰኘ ካምፕ መሆኑም አብሮ ተዘግቧል። ሰልጣኞቹ በቃዳቸው እጃቸውን ለመንግስት የሰጡ እና የተማረኩ ናቸውም ተብሏል። የመንግስት የብዙሃን መገናኛዎች ሰልጣኞቹ ወደትጥቅ እንቅስቃሴ የገቡት በስህተት መሆኑን አምነው በጥፋታቸው እንደተፀፀቱ፥ ዳግመኛም በተመሳሳይ ተግባር ላለመሳተፍ ቃል እንደገቡ ተናግረዋል።

በመንግስት እና በታጣቂው ቡድን መካከል በሁለት ዙር ድርድር በምስራቅ አፍሪካዊቷ ታንዛኒያ ሲከናወን የነበረ ሲሆን ድርድሩ ያለውጤት መበተኑ አይዘነጋም። በተለይ ከሁለተኛው ዙር ድርድር ያለውጤት መበተን በኋላ በሁለቱ ወገኖች መካከል ቃላት መወራወር በርትቶ ተስተውሏል። ከእርሱም ባሻገር ግጭቶች በኦሮሚያ ጠንከር ብለው የታዩ ሲሆን በሰላማዊ ዜጎች ላይም ጥቃቶች ተመዝግበዋል።

ሌላ ዙር ድርድር ሊኖር የመቻል እድል እንዳልተሟጠጠ በቅርቡ ዘለግ ያለ ቃለ መጠይቅ የሰጡት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጠቆም ማድረጋቸው ይታወሳል።

Читать полностью…

EthioTube

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፈረስ ቤት በተባለች ከተማ እና በአቅራቢያዋ ከሰሞኑ ከፍተኛ የሚባል የተኩስ ልውውጥ በታጣቂዎች እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መካከል መደረጉ ተዘገበ።

በሌላ በኩል የክልሉ መንግስት ከሰሞኑ ለታጠቂዎች የቀረበውን በሰላም ግቡ ጥያቄ በርካቶች እየተቀበሉ ነው ብሏል።

ቢያንስ ለሁለት ቀናት የዘለቀው የፈረስ ቤት ውጊያ ከፍተኛ የሚባል እንደነበር ከነዋሪዎች ሰምቻለሁ ሲል ዘገባ ያሰራጨው የጀርመን ድምፅ የአማርኛ አገልግሎት የፋኖ ታጣቂዎች ከተማዋን ይዘዋት እንደነበርም ጨምሮ ገልጿል። የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ከተማዋን ለማስለቀቅ ከፍተኛ ዘመቻ ከፍቶ ነበርም ሲሉ ነዋሪዎች መናገራቸውን የሬዲዮ ጣብያው ዘገባ ያመላክታል። ውጊያው በከባድ መሳርያዎች የታገዘ ሲሆን ይህም ለነዋሪዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳስን አዳጋች አድርጎታል። ይሁንና በውጊያው ስለደረሰ ጉዳት እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎች ስለገጠማቸው ዕጣ ብዙም የተባለ ነገር የለም።

በአማራ ክልል የፀጥታ መደፍረስን ለማሻሻል ያግዛል በሚል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተደነገገ ወደአምስት ወር እየተጠጋ ቢሆንም አሁንም ውጊያዎች እና ጥቃቶች መዘገባቸውን ቀጥለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መንግስታት ለንፁሃን ዜጎች ከለላ እንዲደረግ ሲማፀኑ ቢቆዩም በተለይ ሰው ሰብሰብ ብሎ በሚኖርባቸው ከተሞች አካባቢዎች የሚደረጉ ፍልሚያዎች ስጋት መጋረጣቸውን ቀጥለዋል። ከዚህ ቀደም የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዐዊ መብቶች ፅህፈት ቤት በአማራ ክልል ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ በሰላማዊ አካባቢዎች ላይ ያነጣጠሩ የድሮን ጥቃቶች እንዲሁም የመኖሪያ ስፍራዎች ላይ ያረፉ የከባድ መሳርያዎች የንፁሃንን ነብስ እየቀጠፉ ነው ሲል መናገሩ ይታወሳል። በክልሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ከተቋረጠ ወራት የተቆጠሩ መሆናቸው በምስል የተደገፉ እና ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን ማግኘትን አዳጋች አድርጎታል።

የክልሉ መንግስት እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጠቅላይ መምሪያ በበርካታ አካባቢዎች በአንፃራዊነት የተሻለ የፀጥታ መሻሻል መኖሩን ይናገራሉ፤ ይሁን እንጅ አለ ከተባለው መሻሻል ጋር ተያይዞ አዋጁ ይነሳ ስለመሆኑ እንዲሁም የኢንተርነት አገልግሎት ስለመመለሱ ብዙም ሲናገሩ አይደመጡም።

በቅርቡ በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በሰላም ተመልሱና ወደማኅበረሰቡ ተቀላቀሉ የሚል ጥሪ የቀረበላቸው ሲሆን መጀመሪያ ለሰባት ቀናት ያህል ቀርቦ የነበረው ጥሪ ለተጨማሪ ቀናት እንደተራዘመም ተገልጿል። ይህንን ተከትሎ በርካቶች የትጥቅ እንቅስቃሴን ይቅርብን ብለው ወደሰላም እየተመለሱ ነው ብሏል የክልሉ መንግስት። የአማራ ክልል የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንገሻ ፈንታው በዚህ ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጥሪ ተቀብለው ተመልሰዋል ያሏቸውን ታጣቂዎች ቁጥር ከአምስት ሺህ የሚበልጥ ነው ብለዋል። ሕዝቡ ለሰላም ጥሪው ያሳየው ተነሳሽነት የሚደነቅ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ወደሰላም ለመጡት ታጣቂዎች የመከላከያ ሠራዊት ጥበቃ እያደረገ ነው ያሉት የክልሉ ቃል አቀባይ ታጣቂዎቹን ለማስገባት ስራ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የመንግስት የብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል። ይሁንና እርሳቸው ያቀረቡትን ቁጥር በተመለከተ ከገለልተኛ ወገን የተገኘ ማረጋገጫ የለም።

የአርሶ አደሮች ምርታማነት እና የምጣኔ ኃብታዊ ተፎካካሪነት እንዲኖር ለሰላም ዋጋ መክፈል ያስፈልጋል ሲሉ ቃል አቀባዩ አሳስበዋል።

በተያያዘ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በሚገመግም አንድ መድረክ ላይ ተገኝተው “አንፃራዊ ሰላም” እንዳለ እና ያንን በዘላቂነት ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። የሰላም ጥሪ ከቀረበ በኋላ “በርካቶች” ሲሉ የገለጿቸው ታጣቂዎች ወደሰላም መጥተዋል ሲሉ ተናግረው እነርሱን እያሰለጠንን ወደማኅበረሰብ እንመልሳለን ሲሉ ተደምጠዋል።

የክልሉ ሹማምንት እንደዚህ ይበሉ እንጅ አሁንም ግጭቶች መደመጣቸው አልቀረም። የውጭ አገራት ለዜጎቻቸው በሚያወጧቸው ማሳሰቢያዎች ክልሉ አሁንም ግጭት ማስተናገዱን መቀጠሉን እየጠቀሱ ከጉዞ እንደቆጠቡ ያስጠነቅቃሉ።

Читать полностью…

EthioTube

በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ወጥነው የነበሩ የውጭ አገር ኩባንያዎች ፍላጎት ተቀዛቅዟል ተባለ።

ለዚህም አንዱ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያውና ብቸኛው የግል የቴሌኮም ኩባንያ የሆነው ሳፋሪኮም ወደሥራ ለመሰማራት ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ የገጠሙት ተግዳሮቶች እና ውጣ ውረዶች ናቸው ተብሏል።

ሮይተርስ የዜና ወኪል በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የዘርፉን ባለሞያዎች አነጋግሬ እንደተረዳሁት ፈተና ሆነው ከታዩት ጉዳዮች መካከል የህግ ማሻሻያዎች፥ በአገሪቱ የሚታዩት የፀጥታ ችግሮች እንዲሁም ለአስርት ዓመታት ያህል በከፍተኛ ሁኔታ ተጠንቅሮ የቆየውን ዘርፍ በመክፈት ረገድ መንግስት የታሰበውን ያህል ትጋት ያለማሳየቱ ይገኙባቸዋል ብሏል።

ይህም መቶ ሃያ ሚሊዮን ገደማ ሕዝብ ይዛ ከፍተኛ የገበያ እምቅ አቅም አላት በሚል የቴሌኮም ዘርፍ ኩባንያዎች በከፍተኛ ፍላጎት ሲመኟት የነበረችውን ኢትዮጵያ ገበያ አሁን ደፍሮ ለመግባት ብዙም ተነሳሽነት የለም ሲል ዘገባው አክሏል።

ስለገጠሙት ውጣውረዶች ብጠይቀውም ሳፋሪኮም ኢትየጵያ ምላሽ አልሰጠኝም ያለው ሮይተርስ በዘርፉ ላይ ጥናት ሰርተው መፅሐፍ ያሳተሙ አንድ ባለሞያ ግን የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለው ነገር ውዥንብር የሚፈጥር ነው ብለውኛል ብሏል። “የኢትዮጵያ መንግስት ምን እያደረገ እንዳለ እርግጠኛ መሆን አይቻልም” ሲሉ ምሁሩ ነግረውኛል ያለው ሮይተርስ አንድ ጊዜ ገበያውን ሲከፋፍት ይታይና ወዲያው ደግሞ ሁሉንም ነገር መልሶ ይወስዳል ሲሉ ኃሳባቸውን ገልፀዋል ብሏል።

መንግስት በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት እንደሌለ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት መቀመጫውን ፈረንሳይ ያደረገው ኦሬንጅ የተባለ የቴሌኮም ኩባንያ የመንግስታዊውን ኢትዮቴሌኮም አርባ አምስት በመቶ ድርሻ ልገዛ አስቤ የነበረውን ትቼዋለሁ ሲል ራሱን ማግለሉን መግለፁ ይታወሳል።

Читать полностью…

EthioTube

ሠራተኞቼ በፀጥታ ኃይሎች ተደብድበዋል ያለው የአፍሪካ የልማት ባንክ የውጭ አገር ባለሞያዎቹን ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ ለማስወጣት ወሰነ።

ለሰራተኞቼ ደህንነት ዋስተና መተማመኛ የለኝም ሲል ገልጿል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሁለት የውጭ አገር ሠራተኞቼ በፀጥታ ኃይሎች ተወስደው ታስረዋል፥ ያላግባብ ተዋክበዋል እንዲሁም አካላዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል ያለው ከኢትዮጵያ የፋይናንስ ደጋፊዎች መካከል አንዱ የሆነው የአፍሪካ ልማት ባንክ ክስተቱን እንደ ዲፕሎማሲያዊ ጥሰት እንደሚቆጥረው ገልፆ ነበር።

ምንም እንኳ በወቅቱ ባንኩ ታሰሩና ተደበደቡ የተባሉ የውጭ አገር ሰራተኞቹን ማንነት ገልፆ ያልነበረ ቢሆንም የተለያዩ ዘገባዎች ግን የባንኩን የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ እንደሚጨምር ገልፀው ነበር።

የአፍሪካ ልማት ባንክ የወቅቱ መግለጫ ሰዎቹን ከእስር ማስፈታት የቻለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ንግግር በማድረግ እንደሆነም ተናግሮ ነበር።

አሁን ከባንኩ ፕሬዚዳንት እና የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወዳጅ እንደሆኑ ከሚነገርላቸው ከናይጄሪያዊው ከአኪናዋ አዴሲና የተፃፈ መመሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የባንኩ የውጭ አገር ሠራተኞች ጓዛቸውን ጠቅልለው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። የባንኩ ተቀጣሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ግን እዚሁ ይቀራሉ፤ ከሥራ ገበታቸውም አይቀነሱም ይላል ይሄው መልዕክት።

ከሳምንታት በፊት የተከሰተውን ጥቃት ተከትሎ በባንኩ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደአዲስ አበባ ልከን የኢትዮጵያ ሹማምንትን እንዲሁም የባንኩን ሠራተኞች አነጋግረን ነበር ያለው የአፍሪካ ልማት ባንክ በግምገማችን የደረስንበት ድምዳሜ ጉዳዩ አጥጋቢ በሆነ መልኩ እንዳልተፈታ፥ ሠራተኞቻችን በልበ ሙሉነት ደህንነት ተስምቷቸው ስራቸውን ለመከወን እንዲሁም ከቦታ ቦታ ምንም ትንኮሳ ሳይደርስባቸው ለመንቀሳቀስ የሚያስችል ሁኔታ እንደሌለ ገብቶናል ብሏል።

በወቅቱ ከተፈፀመውና “እጅግ የከፋ ጥሰት” ካለው ክስተት ጋር በተገናኘ የፀጥታ ኃይሎች እያደረግን ነው ያሉትን ምርመራ ውጤት እስካሁንም አላሳወቁንም ያለው ባንኩ የሠራተኞቼን ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲሁም መብታቸውን ለማስከበረ የማልፈነቅለው ድንጋይ የለም ሲል ተናግሯል።

የአፍሪካ የልማት ባንክ ኢትየጵያ ውስጥ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ስምንት ፕሮጄክቶች ያሉት ሲሆን የውጭ አገር ባለሞያዎቹን ጠቅልሎ በማስወጣቱ ስራዎቹ ላይ ሊኖር ስለሚችል መስተጓጎል ምንም ያለው ነገር የለም።

መንግስት በወቅቱ በክስተቱ ማዘኑን ገልፆ ምርመራም እንደሚደርግ ቃል ገብቶ የነበረ ሲሆን ከአሁኑ የባንኩ ውሳኔ ጋር ተያይዞ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።

Читать полностью…

EthioTube

ድንቅ መልዕክት !

እውነቱን ለመናገር እኛ ሀገር ውድ መኪና ለመንዳት ሞራሉም አይመጣልህም ፤ ከቤት ወትተህ የሆነ ቦታ ደርሰህ ስትመለስ መንገድ ላይ ስንት የተቸገረ ታያለህ መሰለህ ፤ ቤት አጥቶ መንገድ ዳር የተኛ ታያለህ ፤ የሚበላው አጥቶ የሚለምን ታያለህ ፤ ይህን እየተመለከትክ ውድ መኪኖች አሉኝ ብለህ እዚህ ህዝብ ላይ እራስህን ለማሳየት መሞከር በዚህ ህዝብ ላይ ራስህን መቆለል ምን ያደርጋል ? ፤ ምን ይባላል መሰለህ ‹‹ ብዙ ደሃ ባለበት ሀገር ውስጥ ሁሉም ሀብታም ደሃ ነው ›› ስለዚህ ማን ላይ ነው ራስህን የምታሳየው ? ፤ ውድ መኪና እየነዳህ ውድ ልብስ ለብሰህ ራስህን የምትቆልለው ፤ ያንተው ህዝብ ናቸው ወንድም እህትህ ናቸው ፤ የተቸገረ ህዝብ ላይ ራስህን መቆለል ትክክል አይደለም ፡፡
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

Читать полностью…

EthioTube

ደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያንን ወደግዛቴ በህገ ወጥ መልኩ አስገብቷል ያለችውን የጭነት መኪና ሾፌር ቀጣች።

በአገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ግዛት ባለች ምባቶ የተሰኘች ከተማ ያለ ፍርድ ቤት ነው የ39 ዓመት ዕድሜ አለው የተባለውን የጭነት መኪና ሾፌር የገንዘብ ቅጣት ያከናነበው።

ሾፌሩ በጭነት መኪናው ወደአገሪቷ ያስገባቸው ኢትዮጵያውያን በቁጥር አስራ ስምንት ሲሆኑ ዕድሜያቸውም በአስራ ስምንት እና በሃያ የዕድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል። በአገሪቱ የሚታተሙ ጋዜጦች እንደዘገቡት ኢትዮጵያውያኑ ተገቢ ሰነዶች የሌሏቸው ሲሆን በመኪናው የዕቃ መጫኛ ክፍል ታጉረው ተገኝተዋል ተብሏል።

ሾፈሩ ኢትዮጵያውያኑን የያዘው ከዛምቢያዋ መዲና ሉሳካ አንስቶ ወደንግድ ከተማዋ ጆንሃንሰበርግ ሊያደርሳቸው በመጓዝ ላይ እያለ ነው በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋለው።

ኢትዮጵያኑ በጆሃንስበርግ ከተማ ያሉ ዘመዶቻችን ስራ እንፈልግላችኋለን ብለውን ነው ወደዚያው የምናቀናው ማለታቸውም አብሮ ተዘግቧል።

Читать полностью…

EthioTube

የዓለም የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የትግራይ እና የአማራ ክልል ቀውሶች አሳስበውኛል አሉ።

ኢትዮጵያዊው ዶክተር ቴድሮስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘጋቢ ጋዜጠኞች ማኅበር ፊት ቀርበው ባደረጉት ንግግር ነው የሁለቱን ክልሎች ሁኔታ ያነሱት። በትግራይ ክልል የሰላም ስምምነት ተደርጎ ጦርነት ቢቆምም የሰብዐዊ መብት ጥሰቶች ቀጥለዋል ያሉት ቴድሮስ በክልሉ ከጦርነት ጋር ተያይዞ የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃት ሰለባዎች ፍትሕ ያለማግኘታቸው አስቆጭ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሴቶች እና ታዳጊዎች በጦርነቱ ወቅት ፆታዊ ጥቃቶች እንደተፈፀመባቸው የተለያዩ ዘገባዎች ያመላክታሉ። በቅርቡ ይፋ የሆነ አንድ ጥናት የጥቃት ሰላባ የሆኑ ሴቶች ቁጥር ቀድሞ ከታሰበውም እጅጉን የላቀ ሳይሆን እንደማይቀር ማመላከቱ ይታወሳል።

ከጥቃቶቹ እንዲሁም ከሌሎች ተፈፅመዋል የተባሉ የሰብዐዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተገናኘ ተጠያቂነትን የማስፈን ስራ እንደሚከናወን ቃል ሲገባ የሚደመጥ ሲሆን እስካሁም ፆታዊ ጥቃትን ፈፅመዋል በሚል ፍርድ ቤት የቀረቡ ተጠርጣሪዎች ስለመኖራቸው በይፋ የተገለፀ ነገር የለም።

በክልሉ የተፈፀመው ፆታዊ ጥቃት ብዛት እጅጉን ሰቅጣጭ ነበር ያሉት ዶክተር ቴድሮስ በሙያ ሕይወታቸው በዚህ ልክ የደረሰ ጥቃት እንደማያውቁም ጨምረው ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ በቂ የብዙሃን መገናኛዎች ዘገባ ያለመኖሩ እንደሚያሳዝናቸውም አልደበቁም። የፆታ ጥቃት ሰለባዎች ተገቢ የሆነ የህክምና ድጋፍ የማግኘት መብት አላቸውም ሲሉ ተደምጠዋል።

ሬፊውጂ አንተርናሽናል የተባለ በስደተኞች ላይ የሚሰራ ተቋማ በትግራይ ካሉ ሴቶች ምናልባትም ከአርባ እስከ ሃምሳ በመቶ የሚሆኑት አንዳች ዓይነት የፆታ ጥቃት እንደደረሰባቸው ጥናትን በማጣቀስ ፅፎ ሳነብ ልቤ ተሰብሮ ነበር ያሉት ዶክተር ቴድሮስ ትግራይ ሆነ ኮንጎ፥ ሄይቲ ሆነ እስራዔል ወይም ሱዳን አስገድዶ መድፈርን እንደጦር መሳርያ መጠቀም ዘግናኝ እና በሰብዐዊነት ላይ የተለደፈ ቆሻሻነት ነው ብለዋል።

ዶክተር ቴድሮስ በአማራ ክልል ለወራት ያህል የቀጠለው ግጭት የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት አድርሷል ሲሉ በዚሁ መድረክ ላይ የገለፁ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት አንድ አምቡላንስ በድሮን ተደብድቦ አምስት ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህም ባሻገር በሁለቱ ክልሎች አስከፊ ድርቅ ተከስቶ ቀድሞም የነበረውን የምግብ እጥረት አባብሶታል፤ እናም አሁን ሚሊዮኖች ረሃብ ተጋርጦባቸዋል ብለዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ዘለግ ባለው ንግግራቸው ከኢትዮጵያም ባሻገር ጋዛን፥ ምስራቅ ኮንጎን እንዲሁም ሱዳንን በማንሳት ትልቅ የጤና ዘርፍ ቀውስ በግጭቶች ምክንያት ተከስቷል ብለዋል።

Читать полностью…

EthioTube

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ


ባለፈው ክረምት መልቀቂያ ያስገቡትም የቀድሞዋን ዳኛ እና የተቃውሞ ፖለቲካ መሪ ብርቱካን ሚደቅሳን ለመተካት ሰብሳቢ ሲያፈላልግ የከረመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ወይዘሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን ሾሟል። ሹመቱ ላይ ተወያይቶ እንዲያፅድቅ የቀበረለት የታችኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ ሹመታቸውን አፅድቆላቸዋል። የሜላተወርቅ የአንድ ሰው ድምፀ ተዐቅቦ ብቻ ገጥሞታል።

በመንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ የትምህርት እና የሥራ ተሞክሯቸው በምክር ቤቱ የተነገረላቸው ሜላተወርቅ በቦርዱ ውስጥ ሲያገለግሉ የቆዩ ባለሞያ ሲሆኑ ለሦስት ዓመታት ያህል የቦርዱ የፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። ሜላተወርቅ በምክር ቤቱ ተገኝተው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel