ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

"የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ ካልቀየረ መንግሥት ተመጣጣኝ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ"

#Ethiopia #Africa #EU

Full story:
https://www.ethiopianreporter.com/129449/

Читать полностью…

EthioTube

" መቀነት " ምዕራፍ ሁለት በአዳዲስ ሀሳቦች ወደ እናንተ ለመድረስ ዝግጅታችንን ጨርሰናል ። በቅርብ ቀን በኢትዮ ትዩብ ይጠብቁን ።

https://youtu.be/STobMO0mZ-Q

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ላንድ የፖሊስ ስልጠና ፕሮግራም የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ በሶማሊ ላንድ አዲስ የፖሊስ ኃይሎችን ማሰልጠን ያሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊላንድ ጋር ፈጸመች።

የሶማሊ ላንድ ፖሊስ ኃይል  ትላንት ሐሙስ በፌስቡክ ገፁ ላይ፤ የፖሊስ ኃይል ስልጠና ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መስፍን አበበ እና የሶማሊላንድ ፖሊስ ኃይል የስልጠና ኃላፊ ጄነራል አብዲ አህመድ ቲር በአዲስ አበባ መፈራረማቸውን ገልጿል።

ይሁን እንጂ ስለ ስምምነቱ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

ስምምነቱ የተደረገው የሶማሊላንድ ፖሊስ ኃላፊ ሞሃመድ አደን ሳቃዲ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ መሆኑን የሶማሊ ላንድ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚገኙ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ ጠየቀች

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤  በአሜሪካ ተቀምጠው “የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት የሚያውኩ ተፈላጊዎችን” አሳልፎ በመስጠት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን ትብብር እንዲያደርጉ ጠየቁ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአሜሪካው የፌዴራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አምባሳደሩ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱም ኮሚሽነር ጀነራል ጥሪ ማቅረባቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጀ አመላክቷል፡፡

ኮሚሽናር ጀነራሉ ጥያቄውን ያቀረቡት አምባሳደሩን በቢሯቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡

አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው፤ በአሜሪካን መንግሥት የሚፈለጉ ወንጀለኞችን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አሳልፎ በመስጠት ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተመሳሳይ ድጋፎችን እንድታደርግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ  መናገራቸውም ተገልጿል፡፡

 
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በሰኔ ወር ወደ አክሱም በረራ ይጀመራል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣይ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም መጀመሪያ ሳምንት ወደ አክሱም መደበኛ የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታወቀ።

በአክሱም የሚገኘው የአጼ ዮሐንስ አራተኛ አየር ማረፊያ በትግራዩ ጦርነት ጉዳት ደርሶበት አገልግሎት መስጠት አቁሞ እንደነበር ይታወሳል።

በአየር ማረፊያው ላይ ሲካሄድ የነበረው ጥገና የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ አየር መንገዱ ወደ አክሱም የሚያካሂደውን መደበኛ በረራ በሰኔ ወር መጀመሪያ ሳምንታት ላይ ይጀምራል ሲሉ የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ሃላፊ ለማ ያደቻ በስልክ እንደገለጹለት የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

አየር መንገዱ ወደ አክሱም መደበኛ በረራ አለመጀመሩ በከተማዋ ይፈስ የነበረውን ቱሪስት እንደገደበው ዘገባው አመላክቷል።

ወደ አክሱም ከተማ የሚደረግ መደበኛ በረራ አለመኖሩ የቱሪስት ፍሰቱን እንደገደበው ዘገባው አመላክቷል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ከዛሬ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ፣ ናይሮቢና ጅቡቲ እንደሚያቀኑ ተገለጸ።

ወደ ናይሮቢ በማቅናት ከኬንያ ባለስልጣናት ጋር በጋራ ቀጠናዊ ተግዳሮቶች ላይ ይመክራሉ።

ልዩ መልዕክተኛ ሀመር በአዲስ አበባ  ከአፍሪካ ህብረት፣ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት እና ከትግራይ ጊዚያዊ መስተዳድር ጋር በፕሪቶሪያ የጦርነት ማቋረጥ ስምምነትን አፈፃፀም እና አስቸኳይ ጉዳዮችን በፖለቲካዊ ውይይት መፍታት እና ወደ ግጭት መመለስን በማስወገድ  ዙሪያ እንደሚነጋገሩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ አስታውቋል።

ልዩ መልዕክተኛ ሀመር በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም በሚደረገው ውይይት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ሪፖርቶችን ማጣራት እንዳለበትም እንደሚወያዩ የገለጸው መስሪያ ቤቱ በጅቡቲም፣  ልዩ መል ዕክተኛው ከጅቡቲ መንግስት ባለስልጣናት ጋር በክልላዊ እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ አስታውቋል።

U.S. Embassy Addis Ababa

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የኢሮብ እና ጉሎ መኸዳ ነዋሪዎች “ኤርትራዊነት በግድ እየተጫነብን ነው” ማለታቸው ተሰማ

ዜግነታቸው በኀይል እንዲቀየሩ እየተገደዱ እንደሆነ የገለጹ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ አዋሳኝ ወረዳ ነዋሪዎች፣ በስጋት የተሞላ ሕይወት በመምራት ላይ እንዳሉ መናገራቸውን ምንጮች ነግረውናል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ከትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ወረዳዎች መውጣቱ ሕዝቡን ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ እንደከተተው የሚያስረዱት ነዋሪዎች እና አስተዳዳሪዎች፣ “ኤርትራውያን እንድንሆን በኀይል እየተገደድን ነው” ሲሉ አመልክተዋል፡፡

በአንጻሩ፣ በኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የወጡ ጽሑፎች፣ የኤርትራ ወታደሮች በኤርትራ ልዑላዊ መሬት ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል። በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኘው የኢሮብ ብሔረሰብ ተወላጆች ጊዜያዊ ኮሚቴ፣ “የመጥፋት አደጋ አንዣብቦበታል’’ ባሉት የብሔረሰቡ ህልውና ጉዳይ፣ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ጋራ ባለፉት ሳምንታት ተገናኝተው መወያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ሪያል ማድሪድ ባየርን ሙኒክን 2-1 በማሸነፍ ለቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አልፈዋል። በፍፃሜው ቦሩሲያ ዶርትሙንድን የሚገጥሙ ይሆናል።

#championsleague #realmadrid #BayernMunich

Читать полностью…

EthioTube

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የትራንስፎርሜሽናል ዕቅድ ዝግጅት ወርክ ሾፕ መካሄድ ጀመረ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የትራንስፎርሜሽናል ዕቅድ ዝግጅት ወርክ ሾፕ መካሄድ መጀመሩን የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት፤ በወርክሾፑ አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በሚያስችሉ በተመረጡ ስድስት አጀንዳዎች ላይ በዓለም አቀፍ የዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና ይሰጣል።

በተጨማሪም የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዝግጅት እንደሚከናወንም ጠቁመዋል።

"ሃገራችንን ለማበልጸግ በሁሉም ዘርፍ ያለ እረፍት መስራታችን ተጠናክሮ ቀጥሏል"  ብለዋል ከንቲባዋ በመልዕክታቸው።

Читать полностью…

EthioTube

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ጀሉ ዑመር (ዶ/ር)÷ ዩኒቨርሲቲውን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ ሙሉ ራስ ገዝ ለማስገባት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርኃ ግብር መስጠት ለመጀመር መወሰኑን ነው ያነሱት።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ሲሆን÷ መርሐ ግብሩ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ እንደሆነም አስታውቀዋል።

የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው በሁሉም ዘርፎች ላይ እንደሚሰጥ ጠቁመው÷ ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም ፕሮፌሽናል ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በነቀምት ከተማ በተዘጋጀ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለመታደም ነቀምት ከተማ ገቡ

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ፣
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም በድጋፍ ሰልፍ ላይ ለመታደም ነቀምቴ ከተማ ገብተዋል፡፡

በስፍራው የተገኙት "ወለጋ የሰላምና የብልፅግና ምድር" በሚል በተዘጋጀ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለመታደም ነው ተብሏል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ማክሰኞ የኢት ዜና - ሚያዝያ 29 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 7 , 2024

👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ በበረራው የገጠመው

👉ከተደረመሰው ህንፃ እስከ አሁን 5 ሰዎች ሞተዋል

👉የሱዳን ፈጥኖ ደራሽና ህውሓት በጋራ ስለመስራታቸው

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/twdCrTcxvrM

Читать полностью…

EthioTube

የኢጋድ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በጅጅጋ እየመከሩ ነው

የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋን ጨምሮ የኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳና ጅቡቲ የውሃ ሚኒስትሮች ጂግጂጋ መግባታቸው ተገለጸ።

ሚኒስትሮቹ ጂግጂጋ የገቡት በቀጠናው ሀገራት መካከል የሚኖሩ ዜጎችን ታሳቢ ያደረገ ድንበር ተሻጋሪ የከርሰምድር ውሃ አጠቃቀም ላይ ለመምከር መሆኑ ተጠቁሟል። የቀጠናው ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በተጨማሪ የዩኒሴፍ የአለም ባንክና ሌሎች አጋር ድርጅቶች በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ሚኒስትሮቹ ጅግጂጋ ሲደርሱ የሶማሌ ብሔራዊ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ መሀመድ በጅጅጋ ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

"ከውሸት ፣ ከክፋት ፣ ከመወነጃጀል ነጽተን ትንሣኤውን በእውነትና በፍቅር እናክብር " ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በዓለ ትንሣኤን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ትንሣኤ ማለት ሕዝበ ክርስቲያኑ በጠቅላላ አምኖ የሕይወትን ትንሣኤ ስናከብር ነው በማለት የገለጹ ሲሆን አያይዘውም በዓለማችን ላይ የ ትንሣኤ ሕይወትን የሚለማመድ እና በሞት ጥላ ስር የሚኖሩ አሉ በመሆኑም በሞት ጥላ ለሚኖሩት ትንሣኤ የሚባል ነገር የለም ነገር ግን በሕይወት ትንሣኤ ስንኖር ዛሬ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ትንሣኤ ነው በማለት ምክራቸውን ለግሰውናል።

ምድራችን ሁል ጊዜ በበሽታ ላይ ነው ያለችዉ በሕመም ላይ ነው ያለችው ስለዚህ ትንሣኤ ዛሬ ነው ካልን  ከውሸት ፣ ከክፋት ፣ ከመወነጃጀል ነጽተን ትንሣኤውን በእውነትና በፍቅር እናክብር በዓሉም የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት ይሁንልን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Via: ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

Читать полностью…

EthioTube

ክሪስታል ፓላስ ማንችስተር ዩናይትድን 4-0 አደባይቶታል። ዩናይትድ በሜዳው በቀጣይ ጨዋታ አርሰናልን ይገጥማል። አርሰናል በኦልድ ትራፎርድ ድል ይቀናዋል ወይስ ነጥብ ይጥል ይሆን? 🤔

#PremierLeague #ManchesterUnited #CrystalPalace

Читать полностью…

EthioTube

አርሰናል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የነበረውን ወሳኝ ጨዋታ 0-1 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን ከማንችስተር ሲቲ ተረክቧል። ዋንጫ ያነሳ ይሆን?

#PremierLeague #ManchesterUnited #Arsenal

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ አርብ የኢት ዜና - ግንቦት 2፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 10 , 2024

👉 የኢትዮጵያ እና ሶማሊ ላንድ አዲስ ስምምነት

👉ለተሻለ ኑሮ ስደትን የመረጡ የአፍሪካ ዶክተሮች ጉዳይ አስደንጋጭ ሁኔታ

👉በትግራይ የተቀበሩት ቦንቦች የንፁሃን ህይወት እየቀጠፈ ነው

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/9bfkCLbRh28

Читать полностью…

EthioTube

አፍሪካ የጤና ባለሙያዎች እጥረት እንዳለባት የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል

ድርጅቱ በናሚቢያ ዋና ከተማ ፤ ዊንድሆክ በዚህ ሳምንት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የጤና ባለሞያዎች ፎረም ላይ ነው ይህን ያሳወቀው።

ፎረሙ ላይ የናሚቢያ የጤናና የማህበራዊ አገልግሎት ሚኒስትር ካሉምቢ ሻንጉላ ፥ " አፍሪካ ያጋጠማት የጤና ባለሙያዎች እጥረት አህጉሪቱ እ.አ.አ በ2030 ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ለማግኘት የያዘችውን እቅድ እንዳታሳካ እንቅፋት ይሆናል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" የተሻለ ህይወት ፍለጋ አህጉሩን ጥለው የተሰደዱ አፍሪካውያን ቁጥር የሚስደነግጥ_ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህን ጉዳይ የአፍሪካ መንግስታትም ሆኑ ታሪካዊ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ተለውጠው ማየት የሚሹ በሙሉ ቅድሚያ ሰጥተው ሊፈቱት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ አስረድተዋል።

የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳይሬክተር ጀነራል ጂን ካሳያ እንዳስታወቁት፣ እ.አ.አ በ2030 ለመድረስ የታቀደውን ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ለማሳካት አፍሪካ ተጨማሪ 1.8 ሚሊየን የጤና ሰራተኞች ያስፈልጓታል።

በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ 1.55 የጤና ባለሙያዎች ለአንድ ሺህ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ፣ ይህም ለ1 ሺህ ሰዎች 4.55 የጤና ባለሙያዎች እንደሚያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው ገደብ በታች ነው።

እ.አ.አ በ2023 ብቻ አፍሪካ " 166 ወረርሽኞች "ን  መመዝገቧን ያመለከቱት ካሳያ ፤ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት እ.አ.አ በ2030 ሁለት ሚሊየን የቋማዊ የማህበረሰብ የጤና ሠራተኞችን እንዲመለምሉ እንዲያሰለጥኑና ወደ ስራ እንዲያሰማሩ የተወሰነውን ውሳኔ ለማሳካት በጣም ወደኃላ መቅረታቸውንም አመልክተዋል።

ምንጭ፦ ቲክቫህ

Читать полностью…

EthioTube

በአፋር ክልል በሶስት ወረዳዎች ከኢሳ ጎሳዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ ከ38 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተጠቆመ

በአፋር ክልል ከኢሳ ጎሳዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ምክንያት በክልሉ ሶስቱ ወረዳዎች ከ38 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ከቀረበለት ሪፖርት መረዳት መቻሉን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

በአፋር ክልል “አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶች” ዘለቄታዊ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በክልሉ እያጋጠሙ ያሉ ግጭቶችና በግጭቱ ምክንያት በተፈጠረው አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው በአፋር ክልል ሦስት ወረዳዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመመልከት ከክልሉ ምክር ቤት አፈ -ጉባኤ፣ ከክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ማስተባበሪያ እንዲሁም ከክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል ።

በውይይቱም በክልሉ ሦስት ወረዳዎች በኢሳ ጎሳዎችና በአፋር ክልል ሦስት ወረዳዎች በሚያጋጥመው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች የዘላቂ የሰላም ግንባታ ተከናውኖ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ነው የተከበሩ ፈትሂ (ዶ/ር) ያሳሰቡት።

በግጭቱ ምክንያት በሦስቱ የአፋር ወረዳዎች ከ38 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ከቀረበለት ሪፖርት መረዳት መቻሉን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - ግንቦት 1፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 9 , 2024

👉  ታዬ ደንድአ ላይ  ዛሬ የተላለፈባቸው ውሳኔ

👉ኤርትራ የትግራይን መንደሮች እያስጨነቀች ነው

👉የአየርመንገዱ ሰራተኞች በጅምላ የህመም ፍቃድ ጠየቁ


ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇


https://youtu.be/LZ-4qou1MMs

Читать полностью…

EthioTube

የህንድ አየር መንገድ የበረራ  ሰራተኞች በጅምላ የህመም ፍቃድ መጠየቃቸዉን ተከትሎ በርካታ በረራዎች ተሰረዙ

የአር ኢንዲያ ኤክስፕረስ በርካታ የበረራ ቡድኑ አባላት በመጨረሻው ደቂቃ ታመው ለበረራ መድረስ እንደማይችሉ ማሳወቃቸዉን ተከትሎ በደርዘን የሚቆጠሩ በረራዎችን አየር መንገዱ ለመሰረዝ ተገዷል። አየር መንገድ ሐሙስ ዕለት 85 በረራዎችን መሰረዙን አስታውቋል::የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት የበረራ ሰራተኞቹ የጅምላ የህመም ፈቃድን ያቀረቡት ካላቸዉ ቅሬታ ጋር በተያያዘ ነዉ ሲሉ ለንባብ አብቅተዋል፡፡

የበረራዉ መስተጓጎሉ የጀመረው ማክሰኞ እለት ሲሆን ኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ ከ90 በላይ በረራዎች ለመስተጓጎልና ለመሰረዝ ቢገደዱም ዝርዝሩን ግን ከመግለጽ አየር መንገዱ ተቆጥቧል።በዋና ከተማው በኒው ዴሊ የሚገኘው አየር ማረፊያ ላይ መንገደኞች ሲስተጓጎሉ የሚያሳዩ ምስሎች በስፋት ተሰራጭተዋል።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሎክ ሲንግ እንደገለፁት ከ 100 በላይ ሠራተኞች የህመም ፍቃድ ይሰጠን ሲሉ ደዉለዉልናል በማለት ተናግረዋል፡፡የኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ ቃል አቀባይ አየር መንገዱ "በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ተገቢ እርምጃዎችን ወስዷል" ቢሉም ተጨማሪ ዝርዝር መረጃን ግን አልሰጡም፡፡ ይህ የሰራተኞች የህመም ፍቃድ በሺዎች ለሚቆጠሩ መንገደኞች ከባድ ችግር ፈጥሯል ብለዋል ።የሕንድ ብሮድካስቲንግ ኤንዲቲቪ እንደዘገበው 300 የሚጠጉ ሠራተኞች ታመው ከደውሉ በኃላ ስልካቸውን አጥፍተዋል።

ኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ ከ2,000 በላይ የበረራ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ወደ 31 የሀገር ውስጥ እና 14 አለም አቀፍ መዳረሻዎች ይበራል። ከ 70 በላይ አውሮፕላኖች እንዳሉት መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Читать полностью…

EthioTube

አቶ ታዬ ደንደአ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን ተሰጠ

የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደአ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን ተሰጥቷል፡፡

ዋስትና ላይ የግራ ቀኝ ክርክር መርምሮ ብይኑን የሰጠው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገመንግስትና ህገመንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሪክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ታዬ ደንደአ ላይ ሦስት ክሶችን ማቅረቡ ይታወሳል።
ይኸውም ክስ፥ ተከሳሹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 251/ሐ እና አንቀጽ 257/ሰ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና የጦር መሳሪያ አዋጅን መተላለፍ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስት እና የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ፣ ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው ፀረ-ሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ መልዕክቶችን በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ነው፡፡

በተጨማሪም ተከሳሹ ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ አዋጁን በመተላለፍ በታኅሣስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ላይ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽንኮቭ ከሁለት የክላሽንኮቭ ካዝና ከ60 ጥይት ጋር ይዞባቸዋል የሚል ነው።

አቶ ታዬ ከጠበቆቻቸው ጋር ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ ከደረሳቸውና በንባብ ከተሰማ በኋላ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ ቀርቧል።

በዐቃቤ ሕግ በኩል የዋስትና ጥያቄያቸው በሰበር ሰሚ ችሎት ዋስትናን በልዩ ሁኔታ ሊከለክል የሚችልባቸው ነጥቦችን ማለትም በተደራራቢ ክስ መከሰሳቸውንና የተከሰሱበት ድንጋጌ ከፍ ያለ ቅጣት የሚያስጥል ከሆነ ዋስትና ሊያስከለክል ይችላል በማለት ተከራክሯል።

በተከሳሽ ጠበቆች በኩል ሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀመጣቸው ዋስትናን ሊያስከለክሉ የሚችሉ ድንጋጌዎች ተከሳሹ ላይ በቀረበው ክስ የሚመለከቱ አለመሆናቸው ጠቅሰው መልስ ስጥተዋል።

በተጨማሪም ህጻን ልጃቸውን ጥለው መታሰራቸውን ጠቅሰው፥ በህገመንግስቱ የተቀመጠው የህጻናት መብት ታሳቢ ተደርጎ በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ያቀረቡትን የዋስትና የመብት ጥያቄን መርምሮ ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ታዬ በወ/መ/ስ/ህ ቁጥር 67 መሰረት በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን ሰጥቷል።

አቶ ታዬ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ላይ ዛሬ ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ አስተያየቱን በጽሁፍ የሰጠ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱም የክስ መቃወሚያው ላይ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ረቡዕ የኢት ዜና - ሚያዝያ 30 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - May 8 , 2024

👉 መከላከያ ወልቃይትን መቆጣጠሩ ተሰማ

👉የሱማሌላንድ እና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ

👉ከ 10 አመት በኋላ ከኮማ የነቃው ቻይናዊ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/K17-mxx02bM

Читать полностью…

EthioTube

በቻይና ለ10 አመታት ኮማ ውስጥ የነበረው ግለሰብ በሚስቱ ጥረት እና እገዛ ነቅቷል

በምስራቃዊ ቻይና አንሁይ በተባለችው ግዛት ነዋሪ የሆነችው ሰን ሆንግሻይ ባሏ በ2014 በገጠመው ድንገተኛ የልብ ድካም ኮማ ውስጥ ይገባል።

በአጭር ጊዜ ከኮማ ይወጣል፤ የቤተሰቡም ስጋት ይወገዳል ተብሎ ቢጠበቅም ምን እየተካሄደ እንደሆነ በውል መረዳትና መግለጽ የማይችለው ባል 10 አመታት ኮማ ውስጥ ይቆያል።

ከሰሞኑ ግን ሰን ለድፍን አስር አመታት በተስፋ የጠበቀችው፤ በብዙ የደከመችለት ጉዳይ ፍሬ አፍርቶ የምትወደውና የሁለት ልጆቿ አባት ነቅቷል።

ያለፉትን አመታት እንዴት እንዳሳለፈች በእምባ ታጅባ ስትነግረው የሚያሳይ ምስልም ተለቋል። 

“ምንም እንኳን በጣም ቢደክመኝም ቤተሰባችን ወደቀድሞው ደስታው እንዲመለስ የተከፈለ መስዋዕትነት አድርጌ እወስደዋለሁ” ስትልም ዳዋን ለተሰኘው የቻይና መገናኛ ብዙሃን ተናግራለች።

የሰን ባል ረጅም አመት ኮማ ውስጥ መቆየቱን ተከትሎ የሚስቱ ድጋፍ እጅግ ወሳኝ ነበር።
የሰውነት አካሉን ማዘዝ ስለማይችል አይንቀሳቀስም፤ ይህም ካለሚስቱ ድጋፍ መጸዳዳት እንኳን እንዳይችል አድርጎታል።

አይኑ በሂደት በከፊል መገለጥ መጀመሩ ተስፋየን እያለመለመው ሄደ የምትለው ሰን ከጊዜ ወደ ጊዜ ህመሙ እየበረታ ፈተናዋን ቢያበዛባትም እስከህይወቱ ፍጻሜ አብራው ለመቆየት ቃል ለገባችለት ባሏ ሙሉ ጊዜዋን ሰጥታ ያለመሰልቸት ተንከባክባዋለች።

የ84 አመቱ የታማሚው አባትም የዚህ ምስክር ናቸው።“ሰን የልጄ ሚስት ብትሆንም ከሴት ልጄ የተሻለች ልዩ ሰው ናት፤ ከእርሷ ጋር ማንም አይወዳደርም” ሲሉ ለልጃቸው ያሳየችውን ወደር የለሽ ፍቅር እና እንክብካቤ አድንቀዋል ብሏል ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት በዘገባው።

ለ10 አመት የባሏን ህመም የተጋራችውና ፍቅሯን በተግባር ያሳየችው ቻይናዊት ሚስት ለልጆቿ አርአያ ሆናለች። ከኮማ ከወጣ ባሏ ጋር የተነሳችው ምስልም በቻይና ማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እየተዘዋወረ ነው።

በርካቶች “እውነተኛ ፍቅር ማለት ይህ ነው” እያሉ አድናቆታቸውን እየገለጹላት ይገኛሉ።

አል አይን

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ፑቲን ለአምሥተኛ ጊዜ ሩሲያን ለመምራት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአምሥተኛ ጊዜ ሩሲያን ለመምራት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡

ፑቲን ከሥስት ሳምንት በፊት በተካሄደው ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነው ለቀጣዮቹ ሥድስት ዓመታት ሃገራቸውን ለመምራት ቃለ መሐላ የፈጸሙት፡፡

ከፈረንጆቹ 1999 ጀምሮ ሩሲያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እና በፕሬዚዳንትነት እየመሩ ይገኛል።

በክሬምሊን ቤተ መንግስት በተከናወነው ስነ ሥርዓት፥ "ሩሲያ አስቸጋሪውን ጊዜ በጥንካሬ እና አሸናፊነት ትሻገረዋለች" ብለዋል።

"ጠንካራ አንድ ህዝቦች ነን" ያሉት ፑቲን፥ "በጋራ ሁሉንም እናልፈዋለን፤ እናሸንፋለንም" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ ጉዳይ አዲስ ነገር ምን አለ ?

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ ራስ ገዝ የአገርነት እውቅና የመስጠት ሃሳብ እንደሌላት ለዲፕሎማቶች መግለጣቸውን ጠቅሰው የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የሶማሊላንድ ባለሥልጣናት፣ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረሰው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ተግባራዊ ሊኾን እንደተቃረበና በሁለት ወራት ውስጥ የመጨረሻው ስምምነት ሊፈረም እንደሚችል በቅርቡ መግለጣቸው አይዘነጋም።

ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሌላንድ በኩል ለሚሰጡ መግለጫዎች በይፋ የሰጠው ማረጋገጫ ወይም ማስተባበያ የለም።

ምንጭ፦ ዋዜማ

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በደቡብ አፍሪካ ህንፃ ተደርምሶ የአምሥት ሰዎች ህይወት አለፈ

በደቡብ አፍሪካ በተከሰተ የህንፃ መደርመስ አደጋ የአምሥት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

በሀገሪቱ ዌስተርን ኬፕ ግዛት ጆርጅ ከተማ በመገንባት ላይ ያለ ባለ 5 ወለል ህንጻ ተደርምሶ በስራ ላይ ከነበሩ አጠቃላይ 75 ሰዎች አምሥቱ ህይወታቸው ሲያልፍ 24 ሰዎችን ከፍርስራሹ ማውጣት ተችሏል ተብሏል።

ከፍርስራሹ ስር ይገኛሉ የተባሉ 50 ያክል ሰዎችን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል።

በነፍስ አድን ስራው ከመቶ በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከአነፍናፊ ውሾች ጋር እንደተሰማሩ ዘገባው ጠቁሟል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ የታየ ጭስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ዛሬ ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ የታየ ቢሆንም አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገዶኞቻችንን ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ወርደዋል።

በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ውድ ደንበኞቹን ይቅርታ ይጠይቃል፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

በመላው ዳውሮ ዞን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ

በምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ዛሬ ጠዋት 1:30 ላይ ቤቶችን ሳይቀር ያንቀጣቀጠ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ማጋጠሙ ተዘግቧል።

የዳውሮ ዞን ፖሊስ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ብርሀኑ ጠንክር እንደተናገሩት የመሬት መንቀጥቀጡ መላው ዳውሮን ያዳረሰ ነው ብለዋል።

በዞኑ ከዚህ በፊት በዚህ ልክ የሚሆን የመሬት መንቀጥቀጥ ደርሶ እንደማያውቅ ምክትል ኢንስፔክተር ተናግረዋል።

ጠዋት በዞኑ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቤቶች ጭምር የነቀነቀ እንደነበረም ገልጸዋል።

የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ ታርጫ ጨምሮ በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች አደጋው መድረሱን ነው የተገለጸው።

በተፈጠረው የመሬት መንሸጥቀጥ እስካሁን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት አልታወቀም ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም

EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ኢትዮጵያ፦ እለተ ሀሙስ የኢት ዜና - ሚያዝያ 24 ፣ 2016 | #Ethiopia: Et News : አንኳር - Ethiopian Daily News Digest - April 2 , 2024

👉 የማህበረ ቅዱሳን የሥራ ኃላፊዎች ታሰሩ

👉ታደሰ ወረደ በአማራ ተቋቁሟል ያሉት ህገ-ወጥ አስተዳደር ጉዳይ

👉የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ተገደሉ

ሌሎችንም መረጃዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/2-sYnzsFqMQ

Читать полностью…
Subscribe to a channel