ethiotube | Unsorted

Telegram-канал ethiotube - EthioTube

-

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other platforms: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Subscribe to a channel

EthioTube

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በጎፋ ዞን የመሬት ናዳ አደጋን ተከትሎ የዜጎች ህይወት በማመለፉ ሀዘናቸውን ገለጹ

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላፉት መልእክት፤  “ከኢትዮጵያ በሰማውት ዜና እና በመሬት ናዳ ሳቢያ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ህልፈት አሳዝኖኛል” ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት ቡድን አፋጣኝ የጤና አቅርቦት ድጋፍ ለማቅረብ ወደ ስፍራው መሰማራቱንም አስታውቀዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 229 መድረሱ ተገልጿል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

#Update

በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የሟቾች ቁጥር ከ150 በላይ ደረሰ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል በትላንትናው እለት ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመሬት ናዳ የሟቾች ቁጥር ከ150 በላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡

በቀበሌው ናዳው ከደረሰ በኋላ የሠው ህይወት ለመታደግ ወደ በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን  የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ለእርዳታ የመጡ ነዋሪዎች በቀበሌው በርካቶች በመሆናቸው በቀበሌው የነዋሪዎች ቁጥር በውል እንደማይታወቅ ነው የተነገረው በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልፆል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ለአደጋ ተጋጭ ናቸው ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና ቀበሌዎች የማጓጓዝ ስራ እየተሰራ ነው፡፡

የአስከሬን ፍለጋ ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው የተባለ ሲሆን በቀጣይ የሞቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል   ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና ምክትላቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ!

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት  ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ታምራት ታገሰ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።የሥራ ኃላፊዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስናና በሃብት ምዝበራ ተጠርጥረው መሆኑን ፋና ዘግቧል።ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በዩኒቨርሲቲው የሀብት ምዝበራ ላይ ያተኮረ የምርመራ ዘጋቢ ፊልም ማቅረቡ የሚታወስ ነው።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት በየመፈተሻ ኬላዎች ገንዘብ እየተጠየቅን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ከደሴና መቀሌ ጭነቶችን በመያዝ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት በየመፈተሻ ጣብያዎች ገንዘብ ካልከፈላችሁ አታልፉም በሚል እንግልት እየገጠማቸው መሆኑን የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን ለአሐዱ አቅርበዋል፡፡

በተለየ ሁኔታ ሸቀጣ ሸቀጥና መሰል ጭነቶችን በመያዝ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት የሚያስቸግሩ ቦታዎች እንዳሉ በተለይም ለገጣፎ፤በኬ፤ሸኖ፤ለገዳዲ፤ እና 44 ማዞርያ በእነዚህ አካባቢ ያሉ ፍተሻዎች የጭነት ተሸከርካሪዎችን ለረጅም ሰአት በማስቆም ገንዘብ ካልከፈላችሁ አታልፉም የሚባልበት ሁኔታ እንዳለም ቅሬታ አቅራቢዎቹ አንስተዋል፡፡

ከእነዚህ ቦታዎች መካከል በተለየ ሁኔታ ሸኖ አካባቢ የሚደረግ ፍተሻና ጥበቃ  በግዳጅ ገንዘብ እንድንከፍል በተደጋጋገሚ እንጠየቃለን ሲሉ ገልጸው የጭነት አገልግሎት ለመስጠትም ስጋት ላይ መሆናቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ጉዳዩን በሚመለከት አሐዱ የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ይሁንና ግን መንግስት መሰል ችግሮችን መፍታት እንዳለበት ነው ቅሬታ አቅራቢዎቹ በአጽንኦት የገለጹት፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ትናንት ምሽት ጥቁር አደይ ፊልም በሸራተን አዲስ በድምቀት ተመርቋል ። እነማን በምርቃቱ ተገኙ ጥንዶቹ ምሽቱን አድምቀውታል ? 👇 ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ

https://youtu.be/5TWH-ZmVITI

Читать полностью…

EthioTube

የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

በዚህም፡-
1. አቶ ያብባል አዲስ – የትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ
2. ወ/ሮ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ – የቤቶች  ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ
3. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ – የአረንጓዴና ውበት ቢሮ ሀላፊ
4. አቶ ማሾ ኦላና – በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ
5. ወ/ሮ አንድነት ብዙ ሰው እና አቶ ሁሴለታ ዋቅጅራ – የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ኦዲተሮች ሆነው ተሹመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሿሚዎችን የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ከምክር ቤቱም የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶች ከተሰጡ በኋላ ነው ሹመቱ በሙሉ ድምፅ የጸደቀው ፥ ተሿሚዎቹም ቃለ መሐላ ፈጽመዋል ።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በአዲስ አበባ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት፤ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው፡፡

በከተማዋ ጠዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።

ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል ያሉት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ሁነት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያሌው እቴሳ ናቸው፡፡

እቅዱ በ2 እና በ3 ወር ጊዜ ውስጥ፤ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካራች በፈረቃ አንዲንቀሳቀሱ  ይደረጋል ተብሏል፡፡

የኦሮሚያንና የፌዴራልን ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755,000 በላይ ናቸው ያሉት አቶ አያሌው ከእነዚህ ውስጥ የበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጠዋትና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በትናንትናው እለት በተካሄደው የሩዋንዳ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፖል ካጋሜ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፋቸው ተሰምቷል።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን እስካሁን ከተቆጠረው 79 በመቶ ድምጽ ካጋሜ 99 ነጥብ 15 በመቶውን ማግኘታቸውን ይፋ አድርጓል።

የ66 አመቱ ፕሬዝዳንት በስልጣን ላይ ለ29 አመት የሚያቆያቸውን ድምጽ ማግኘታቸው የሚጠበቅ ነበር የሚለው ሬውተርስ ዲያን ርዊጋራን ጨምሮ ሶስት ብርቱ ተቀናቃኞቻቸውን ከምርጫ ፉክክሩ ውጭ መሆናቸውን ያወሳል።

በምርጫው የተሳተፉት የአየር ንብረት ጥበቃ ተሟጋቹ ፍራንክ ሃቢኔዝ እና ጋዜጠኛና ደራሲው ፊሊፕ ምፓይማና 1 በመቶ እንኳን መራጭ አለማግኘታቸውንም በመጥቀስ።

እስካሁን በተካሄደው የድምጽ ቆጠራ ሃቢኔዝ 0.53 በመቶ፤ ምፓይማና ደግሞ 0.32 በመቶ መራጭ ማግኘታቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን መግለፁን አልዓይን ዘግቧል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ዶናልድ ትራምፕ መትረፌ ተዓምር እንደሆነ ያከመኝ ዶክተር ነግሮኛል ሲሉ አሳወቁ

ከግድያ ሙከራ ያመለጡት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሙከራው ለሞት የመጣ ቢሆንም “በእርግጥ በህይወት የተገኘ ልምድ” ሲሉ ተናግረዋል።ትራምፕ ለሪፐብሊካን ብሄራዊ ስብሰባ ወደ ሚልዋውኪ ሲያቀኑ ለኒውዮርክ ፖስት እንደተናገሩት “እዚህ መሆን አልነበረብኝም ፣ ሞቼ ነበር” ብለዋል ።

ትራምፕ ቀኝ ጆሮአቸዉን የሚሸፍን ነጭ ማሰሪያ አድረገዉ የነበረ ሲሆን ነገርግን ረዳቶቻቸዉ ምንም አይነት ፎቶግራፍ እንዲነሱ ፍቃድ አልሰጡም ሲል ኒዉዮርክ ፖስት ዘግቧል። ትራምፕ አክለው በሆስፒታሉ ውስጥ ያለው ዶክተር እንደዚህ አይነት ነገር አላየሁም ተአምር ነዉ ብሎኛል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የቀድሞ የኤፍቢአይ ልዩ ወኪል ኬን ግሬይ እንደተናገሩት ጥቃት አድራሹ ይህን ያህል በመቅረብ ጥቃት ማድረስ መቻሉ "በደህንነት ላይ ውድቀት" መኖሩን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል፡ ኤፍቢአይ ለዚህ አይነት ሰልፍ በቂ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ላይ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ከዝግጅቱ በፊት የደህንነት ጥበቃ የሚጀምረው ከየት ሊመጡ እንደሚችሉ እና አንድን ሰው ከህዝቡ መካከል እንዴት ነጥሎ ማውጣት እንደሚችሉ የሚያስገነዝብ የዳሰሳ ጥናት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ጡረተኛው የቀድሞ የኤፍቢአይ ወኪሉ ትራምፕን ከቦታው ለማራቅ ለደህንነት መሥሪያ ቤቱ የፈጀውን “አስፈሪ ረጅም ጊዜ” በመተቸት ሁለተኛ ተኳሽ ቢኖር በድጋሚ በጥይት ሊመቱ ይችል እንደነበር ተናግረዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ኦፌኮ በአቶ በቀለ ገርባ ምትክ አቶ ሙላቱ ገመቹን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ

የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) በአቶ በቀለ ገርባ ቦታ አቶ ሙላቱ ገመቹን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡን አስታወቀ፡፡

የፓርቲው ዋና ጸሐፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ እንደተናገሩት አቶ በቀለ ገርባ ሃገር ውስጥ በነበሩበት ወቅት እርሳቸውም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ጫና ሲደርስባቸው እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡

አቶ በቀለ ለፓርቲያቸውም ሆነ ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸው ታማኝነት እስከ መጨረሻ አልተቀየረም ያሉት አቶ ጥሩነህ  መንግስት በተደጋጋሚ በሚደርስባቸው ጫና ምክኒያት ሃገር ለቀው ለመሄድ ተገደዋል ብለዋል፡፡

በተለይም ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ በሚያሳልፉበት ወቅት የግድያ ሙከራ ሲደረግባቸው እንደነበር አስረድተዋል፡፡

አቶ በቀለ በሰላማዊ መንገድ መታገልን የሚያስቀድሙ ቢሆንም በሃገሪቱ ስልጣን የያዘው አካል ግን ስለ ሰላማዊ ትግል ግድ የማሰጠው በመሆኑና ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባል ሆኖ ለመኖር ያለው እድል አናሳ በመሆኑ ከፓርቲው አመራርነት ለመልቀቅ በጠየቁት መሰረት ፓርቲው አምኖበት ጥያቂያቸውን እንደተቀበላቸው አቶ ጥሩነህ አስታውሰዋል፡፡

የኦፌኮ ዋና ጸሐፊ አክለውም አቶ በቀለ በደረሰባቸው ጫና ምክኒያት ከሃገር ከወጡ በኋላ ፓርቲያቸውንም ሆነ ህዝባቸውን በሚፈለገው ልክ በቅርበት ማገልገል የማይችሉ በመሆኑ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አምኖበት ጥያቄያቸውን በመቀበሉ፤ የእርሳቸው ቦታ ክፍት ሆኖ መቆየቱን አስረድተው በዚህ ቦታ ላይ አቶ ሙላቱ ገመቹ እንዲተኩ ተደርጓል ብለዋል፡፡

Читать полностью…

EthioTube

በአማራ ክልል በ17 ከተሞች ከ11 ወራት በኋላ ኢንተርኔት ተለቀቀ።

የኢንተርኔት አገልግሎቱ ዳግም ከተጀመረባቸው ከተሞች መካከል ባህር ዳር፣ ደሴ፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ ወልዲያ፣ ከሚሴ፣ ባቲ እና ሰቆጣ ይገኙበታል ብሏል ኢትዮ ቴሌኮም።

አል አይን ያነጋገራቸው የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች የኢንተርኔት አገልግሎቱ ፍጥነት ከቀድሞው አዝጋሚ ቢሆንም ለጊዜው አዳዲስ መረጃዎችን ለመከታተልና የተቋረጡ ግንኙነቶችን ለማስቀጠል እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።

በአማራ ክልል ከባለፈው አመት ሀምሌ ወር ጀምሮ በመንግስት እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር በክልሉ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠው።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በ2017 ዓ.ም የቤት ለቤት የፓስፖርት አገልግሎት ሊጀመር ነው

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2017 ዓ.ም ፓስፖርታቸውን ቦታው ድረስ ሂደው መውሰድ ለማይችሉ ግለሰቦች የቤት ለቤት አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል።

በበጀት ዓመቱ በተሰራ ገቢ የማሰባሰብ ሥራ 14 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡንም ገልጿል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ ከተሰበሰበው ብር ውስጥ 148 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው በውጭ ምንዛሪ የተሰበሰበና አገልግሎቱ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪን ከማስገኘት አንፃር ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

በዘርፉ የነበረውን ውስንነትና ችግር ለመቅረፍ ሪፎርም ተቀርፆ ሲሰራ መቆየቱንም በማንሳት በዚህም አመርቂ ውጤቶች መመዝገቡን ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የፓስፖርት ቡክሌት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት መቻሉን የጠቀሱት ዳይሬክተሯ 87 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ለዜጎች ተደራሽ መደረጉንም አብራርተዋል።

ህትመትን አስመልክቶም ቀደም ሲል በቀን 2ሺሕ ሲታተም የነበረው አሁን ወደ 14ሺሕ ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልጸው ውጤቱ የተመዘገበው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት በተከወነ ጠንካራ ስራ ነው ብለዋል።

የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጎሳ ደምሴ በበኩላቸው 820 ሺሕ ለሚሆኑ የውጭ ዜጎች በተለያዩ አገልግሎት መስጭያ አመራጮች ቪዛ መሰጠቱንና ከ51ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን መታወቂያ መሰጠቱን አንስተዋል።

ከ34ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የውጭ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የመኖርያ ፍቃድ የተሰጠ መሆኑንና 18ሺሕ የሚሆኑና ሀሰተኛ የመኖርያ ፍቃድና ቪዛን ጨምሮ ሌሎች መረጃ የተገኘባቸው አካላትን ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ለቱሪስትም ሆነ ለቢዝነስ የሚገቡትን በስፋት ለማስተናገድም እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አያይዘው በአመቱ በአይር ኬላ 4 ነጥብ 9 ሚሊየን በየብስ ደግሞ 580 ሺሕ በድምሩ 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎችን ማስተናገድ ተችሏል ብለዋል።

በህግ ላይ መሰረት በማድረግ ተደራሽ አገልግሎትን መስጠት፣ ተደራሽነትን ማስፋት በተለይም 12 የነበሩ ቅርንጫፎችን ወደ 2 ማሳደግ፣ ምቹ የስራ አከባቢን መፍጠር፣ በልዩ ሁኔታ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማመቻቸትና ሌሎችም የ2017 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እቅድ መሆኑም በመግለጫው ተጠቁሟል ሲል አዲስ ዋልታ ነው የዘገበው።

Читать полностью…

EthioTube

«ኡስታዝ አቡበከር ሁሴንን በማገት ሊብሬውን በመቀየር መኪናውን ሊነጥቁ ነበር» የተባሉ አምስት ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ።

የዐቃቤ ህግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ ብይን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹም÷ 1ኛ የሁለተኛ ተከሳሽ ወኪል የሆነው ፍፁም ተክሉ አፅብሀ፣ 2ኛ የኡስታስ አቡበከር ሁሴንን ተሽከርካሪ በስሙ አዙሯል የተባለው አበራ ነጋሳ ሆርዶፋ፣ በአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውስጥ የተሽከርካሪ አገልግሎት ባለሙያ ናቸው የተባሉት አብዮት አበራ፣ ልየው አሰፋ አንዱአለም፣ አለሙ ኦልጅራ ናቸው።

በተራ ቁጥር 6 እና 7 ላይ የተጠቀሱት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ቡድን ኃላፊ ዋና ሳጅን መኳንንት ተመስገን እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኢንተለጀንስ ቡድን አባል የሆነው ዋና ሳጅን ገመቹ ብርሃኑን በሚመለከት በወቅቱ ታዘው በስራ ላይ ተመድበው እንደነበር ተጠቅሶ ተቋሞቻቸው ማረጋገጫ በማቅረባቸው ምክንያት ነጻ ተብለዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ በአጠቃላይ በሰባት ተከሳሾች ላይ የወንጀል የተሳትፎ ደረጃቸውን ጠቅሶ ዝርዝር ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በአጠቃላይ የተሳትፎ ደረጃን ጠቅሶ ዐቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ ዝርዝር ላይ ተከሳሾቹ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ ኡስታዝ አቡበከር ሁሴን መሀመድ የሆነውንና የዋጋ ግምቱ 7 ሚሊየን ብር የሆነ ቪ8 ተሽከርካሪ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ማህደሩን በመለወጥና በሽያጭ በማስተላለፍ ለመውሰድ ሲሉ የተያዙ መሆኑ ተጠቅሶ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን  ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ነበር የተከሰሱት።

ተከሳሾች የክስ ዝርዝር ከደረሳቸው በኋላ የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም በማለት የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ህግም የግል ተበዳዩን ኡስታስዝ አቡበከርን ጨምሮ ሌሎችንም ምስክሮች አቅርቦ የምስክር ቃላቸውን በችሎት አሰምቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም የምስክር ቃል መርምሮ ከ6ኛ እና ከ7 ኛ ተራ ቁጥር ከተጠቀሱ የፖሊስ አባላት ውጪ ያሉ ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።

ሆኖም በክስ መዝገቡ በተራ ቁጥር 6 እና 7 ላይ የተጠቀሱትን በሚመለከት በወቅቱ ታዘው በስራ ላይ ተመድበው እንደነበር ተጠቅሶ ተቋሞቻቸው ማረጋገጫ በማቅረባቸው ምክንያት ነጻ ተብለዋል።

ተከላከሉ የተባሉትን የመከላከያ ማስረጃ ለመጠባበቅም ከሐምሌ 19 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
(በታሪክ አዱኛ)

Читать полностью…

EthioTube

1,036 የአዲስ አበባ ስቴዲየም ወንበሮች ተሰብረዋል

ባለፈው ዕሁድ በኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻ መካከል በተደረገው የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታ 1,036 የአዲስ አበባ ስታዲየም ወንበሮች መሰበራቸው ተገልጿል።

በጨዋታው ከሽንፈት ያስተናገደው ወላይታ ድቻ ደጋፊዎች የተቀመጡበት አካባቢ 840 ወንበሮች መሰበራቸው ታውቋል።

የዋንጫው አሸናፊ ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የተቀመጡበት አካባቢ ደግሞ 196 ወንበሮች ተሰብረዋል ተብሏል።

የተሰበሩ ወንበሮችን ቆጥሮ ይፋ ያደረገው ጋዜጠኛ ቴዲ ባጫ ነው።

ወንበሮች በእጅ ከመሰበራቸው በተጨማሪ ተመልካች ቆሞባቸው እንደተሰበሩ ለመመልከት ተችሏል።
ከደረሰው ጥፋት እንዳለ ሆኖ የወንበሮቹ ጥራት ጉዳይም አነጋጋሪ ሆኗል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በአዲስ አበባ በግንባታ ላይ የነበረ ህንፃ በመኖሪያ ቤት ላይ ተደርምሶ በመኝታ ላይ የነበረ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ

ዛሬ ሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም  ከንጋቱ 11:45 ሰዓት ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 አርሴማ ቤተክርስቲያን አካባቢ እየተገነባ ያለ ህንፃ ከስሩ ባለ መኖሪያ ቤት ላይ ተደርምሶ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ህይወታቸዉ ያለፈዉ ግለሰብ በቤት ዉስጥ ተኝተዉ የነበሩ በጾታ ወንድ የሆኑ የ50 ዓመት ዕድሜ የተገመቱ መሆናቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።

በስፍራዉ ፈጥነዉ የደረሱት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረጉት ርብርብ ሶስት ሰዎችን ከአደጋዉ መታደግ ችለዋል።

በአዲስ አበባ የግንባታ ስራ ላይ በተለይም በግለሰቦች የሚገነቡ ግንባታዎች የደህንነት መስፈርቶችን ጠብቆ ባለመስራታቸዉ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ በተደጋጋሚ አደጋዎች እያጋጠሙ ይገኛል።

የግንባታ ስራዎች በሚከናወኑበት ጉዳዩ የሚመለከታቸዊ አካላት ግንባታዎቹ የአደጋ ደህንነት መስፈርት ተጠብቀዉ ስለመሰራታቸዉ የተጠናከረ ቁጥጥር በማድረግ የማስተካከያ እርምጃዎችን መዉሰድና የህግ ተጠያቂነትን ማስፈን ያስፈልጋል ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።

Читать полностью…

EthioTube

የአሜሪካ የሚስጥራዊ ደህንነት(ሰክሬት ሰርቪስ) ኃላፊ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ።

የዲሞክራት እና ሪፐብሊካን የተወካዮች ምክርቤት አባላት የአሜሪካ ሚስጥራዊ ደህንነት ኃላፊ ክምብርሊ ቻትል ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል።

አባላቱ ኃላፊዋ ከስልጣናቸው እንዲለቁ የጠየቁት የሪፑብሊካኑ ፕሬዝደንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ እንዲፈጸም ምክንያት ለሆነው የጸጥታ ክፍተት ተጠያቂ በማድረግ ነው።

ነገርግን ኃላፊዋ ጥሪውን ውድቅ ከማድረጋቸው ባሻገር ተጨማሪ ማብራሪያም ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

በብዙ ጉዳዮች የተለያየ አቋም በማንጸባረቅ የሚታወቁት የተወካዮች ምክር ቤት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የሪፐብሊካን ሊቀመንበር ጄምስ ኮመር እና የዲሞክራቱ ከፍተኛ ፖለቲከኛ ጄሚ ራስኪን ቻትል ከስልጣን ይነሱ የሚል ተመሳሳይ ድምጽ አሰምተዋል።

"ይህ ኮሚቴ የሚታወቀው የተለያየ አቋም በመያዝ ነው፣ ዛሬ ግን ወደ አንድ መጥተናል" ሲሉ ኮመር ለቻትል ነግረዋቸዋል።

"በአንቺ አመራርነት እምነት የለንም"
ራስኪን በበኩላቸው ቻትል "በሀገራችን ታሪክ የኮንግረሱን እምነት አጥታለች፤ ስለሆነም በፍጥነት ከዚህ በላይ መሄድ አለብን" ሲሉ ተናግረዋል።  

ቻትል 4 1/2 ሰአት በፈጀው የኮንግረስ ቆይታቸው በፈረንጆቹ ሐምሌ 13 የተፈጸመውን የግድያ ሙከራ በ1981 በቀድሞው ፕሬዝደንት ሮናልድ ሪገን ላይ ከተፈጸመው ግድያ ጋር በማወዳደር "በአስር አመታት ውስጥ ጉልህ የሚባል የጸጥታ ክፍተት ነው"ሲሉ ገልጸውታል።

ነገርግን ከኃላፊነት እንዲነሱ የበረበላቸውን ጥያቄ አልተቀበሉትም፤ "በዚህ ሰአት ሚስጥራዊ የደህንነት አገልግሎቱን ለመምራት የተሻልኩ ሰው ነኝ ብየ አስባለሁ" ሲሉም አክለዋል።

ቻትል ትራምፕ በፔንስልቬንያ የምርጫ ቅስቀሳው እያደረጉ በነበረበት ወቅት ስለተደረገባቸው የግድያ መከራ ጋር በተያያዘ በተወካዮች ፊት ቀርበው ሲያስረዱ የትናንትናው የመጀመሪያቸው ነው።

ትራምፕ በጆሯቸው ላይ የመቁሰል አደጋ ሲያጋጥማቸው፣ ከድጋፍ ሰልፉ ተሳታፋዎች ደግሞ አንድ መገደሉ እና ሌላ አንድ መቁሰሉ ይታወሳል። ግድያውን በማድረስ የተጠረጠረው የ20 አመቱ ቶማስ ክሩክስ በጸጥታ አካላት ተገድሏል። ተኩስ የከተፈው ወጣት አላማ ምን እንደሆነ አልታወቀም።

ምንጭ፦ አል አይን

Читать полностью…

EthioTube

በደረሰ የመሬት ናዳ ከ 20 በላይ ሰዎች ሞቱ

ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ፤ በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የወረዳው ዋና አስተዳደር ፥  እሰካሁን በተደረገው ፍለጋ ከ 20 በላይ አስከሬን መገኘቱን አመልክቷል።

የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል።

በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ  የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን ተሰምቷል።

በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙ ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

መረጃው ከገዜ ጎፋ ወረዳ ነው የተገኘው።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በሚገኘው አውላላ የሥደተኞች መጠለያ ጣቢያ አከባቢ ሰፍረው በነበሩ ስደተኞች ላይ ቅዳሜ ዕለት በተፈፀመ ጥቃት የሁለት ሱዳናውያን ስደተኞች ህይወት ማለፉና 10 ስደተኞች መቁሰላቸውር ተገለጸ::

ጥቃቱ የደረሰው የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኮሚሽን ተወካዮች አካባቢውን ጎብኝተው ከሄዱ በኋላ መሆኑ ተነግሯል::

ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም በአማራ ክልል በሱዳናውያን መጠለያ ካምፕ አቅራቢያ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች እና በታጣቂዎች መካከል በተደረገ ውጊያ ዘጠኝ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መገደላቸውንና ስደተኞች መጎዳታቸውን ይታወቃል::

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የታጋች ተማሪዎች ደኅንነት እንዳሳሰባቸው በቤዛ ክፍያ የተለቀቁ ተማሪዎች ገለፁ

ከሁለት ሳምንት በፊት፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በገርበ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ እስከ አሁን በታጣቂዎች ታግተው የሚገኙ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደኅንነት እንደሚያሳስባቸው፣ በቅርቡ “የቤዛ ገንዘብ ከፍለን ተለቀናል” ያሉ ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡

ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማችን እንዳይጠቀስ ያሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት ተማሪዎች፣ “ሸኔ” ብለው በጠሩት ታጣቂ ቡድን ታግተው መቆየታቸውንና ከ50 ሺሕ እስከ 300ሺሕ ብር የቤዛ ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በታጣቂ ቡድኑ ቁጥጥር ሥር በነበሩባቸው ቀናት፣ “ብዙ ድብደባ እና እንግልት ይደርስብን ነበር፤” ያሉት ተማሪዎቹ፣ አሁንም በታጣቂዎቹ እጅ እንደሚገኙ የጠቆሟቸው 67 ታጋቾች፣ “በከፍተኛ ሥቃይ ውስጥ መኾናቸው በእጅጉ አሳስቦናል፤” ሲሉም አመልክተዋል፡፡

via VOA

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

አፋር እና ሶማሌ ግጭቱን በዘላቂነት ለመፍታ እንደተስማሙ ተሰምቷል

የአፋር ክልል እና የሶማሌ ክልል በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚታዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ስምምነት አደረጉ።

ባለፉት ጊዜያት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በእርቅና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ነው ስምምነት ያደረጉት፡፡

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ በጋራ በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ አልፎ አልፎ እየተነሳ ያለውን ችግር ከስር መሰረቱ ለመፍታት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።

ግጭቶች  ተመልሶ እንዳይነሱና የሰው ሕይወት መጥፋት ስለሌለበት ከስምምነት በመድረሳቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ስምምነት ላይ መደረሱ ዘለቂ ሰላም በአዋሳኝ አካባቢዎች እንዲኖር ክልሉ በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።

የግጭቱ መነሻ የሆኑ ጥያቄዎች በህጋዊ፣ ህገ መንግስታዊ  እና ሰላማዊ በሆነ አግባብ ብቻ እንዲመለሱ በፌዴራል ባለድርሻ አካላት የሚመራ መሆኑን ገልፀው ሰላም እንዲመጣ እንሰራለን ነው ያሉት።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የታዩ አለመግባባቶችን ወደ ጎን በመተው አሳታፊ የሆነ የህዝብ ውይይቶች በማድረግ ልዩነቶችን በውይይት ብቻ ለመፍታት ከስምምነት ደርሰናል ብለዋል።

ግጭቶችን በመተው መግባባት ላይ የተደረሱባቸውን ጉዳዮች በመለየት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ መገባቱንም አስታውቀዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube

Читать полностью…

EthioTube

ለጡት ካንሰር ተብሎ በገበያ የሚገኘው ሄርሴፕቲን 440 ሚሊ ግራም መድሀኒት ሀሰተኛ መሆኑ ተነገረ

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በኢትዮጵያ ከሆፍማን ሮቼ የንግድ ተወካይ ጽህፈት ቤት የተላከለትን መልዕክትና በኬንያ የተሰራጨውን ማስጠንቀቂያ ዋቢ በማድረግ ባደረገው ማጣራት ሄርሴፕቲን 440 ሚሊ ግራም የተሰኘውን ሀሰተኛ መድኃኒት ገበያ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል፡፡

በዚህ መሠረት ባለሥልጣኑ በጥያቄ ውስጥ ያሉትን ምርቶች የገበያ ፈቃድ በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ግምገማ ተደርጓል ። ተቋሙ ምርቱ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ የተመዘገበ የምርት ስሙ ሄርሴፕቲን 440 ሚሊ ግራም ፣ በዩናይትድ ስቴትስ  የተመረተ ስለመሆኑ ፣ የተሰራበት መንገድ ፓውደር የሆነ በመርፌ መልክ የሚሰጥ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ይዛ ።ይሁን እንጂ በኬንያ 05830083 መለያ ቁጥር የተሰጠው ሀሰተኛ መድኃኒት ስለመሆኑ እና በኢትዮጵያ የመለያ ቁጥር ኤች 5170 በሚል እንደተሰጠው የተረጋገጠ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል ።

በተጨማሪም የመድኃኒቱ ምርት በተፈቀደላቸው አስመጪዎችና አከፋፋዮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዳልመጣ በባለስልጣኑ የመድሃኒት አምራቾች ኢንስፔክሽንና ህግ ማስፈፀም ዴስክ ሃላፊ አ/ቶ ደጄኔ ጣባ  የሆኑት ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ  አንድ ታካሚ ምንጩ ያልተረጋገጠውን የሄርሴፕቲን 440 ሚሊ ግራም መድሃኒት መግዛቱ እንዳረጋገጠ ገልጿል ። ይኸው የመድኃኒቱ ማቀፊያ ሳጥን በከፊል የሚያሳየው ምስል እና የመድኃኒት ጠርሙስ ምስል ቁጥር ኤች 5170 ሐሰተኛ የመድኃኒት ምርት በኬንያ ውስጥ እየተሰራጨ መሆኑ ተረጋግጧ ።

መድሃኒቱ የጡት ካንሰርን ለማከም  የሚሰጥ መድሃኒት ሲሆን በሆስፒታል ደረጃ የሚታዘዝ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ እንደሆነ የገለፁት አ/ቶ ደጄኔ መድሃኒቱን እንዲያስመጣ ፈቃድ የተሰጠው አካል ወደ ሀገር ውስጥ ያላስገባው እንዲሁም ከሌላ መድሃኒት ጋር ተመሳስሎ የተሰራ እንደሆነ ለተቋሙ ጥቆማ እንደደረሰው ገልፀዋል ።

ከመድኃኒቱ ምርት መረዳት እንደሚቻለው ምንም እንኳን ይህ የተጭበረበረ ምርት በኬንያ ቢታወቅም በኢትዮጵያ የተሰራጨው በኢ-መደበኛ ገበያ ሊሆን እንደሚችል ተቋሙ ገልጿል ። ስለሆነም በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል ከስርጭት ውስጥ መለየት እና ማስወገድ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተቋሙ አስገንዝቧል ።

በተለይም መድኃኒት አስመጪዎች፣ አከፋፋዮች፣ ችርቻሮ ነጋዴዎች እና ጤና አጠባበቅ አቅራቢዎች የሀሰተኛ ወይም የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ የመድኃኒት ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ፣ እንዳይከፋፈሉ፣ እንዳይሸጡ እና እንዳይገዙ እንዲሁም ከአቅርቦት ሰንሰለት ጋር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል ።ሁሉም የሕክምና ምርቶች ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መገኘት እንዳለባቸው ያሳሰበው ተቋሙ የምርቶቹ ትክክለኛነት እና አካላዊ ሁኔታ በጥንቃቄ መገምገም እንዳለባቸው አስታውቋል ። ከዚህ በተጨማሪ የጤና ባለሙያዎች እና ሸማቾች አጠራጣሪ ከደረጃ በታች የሆኑ እና ሀሰተኛ መድኃኒቶችን በአቅራቢያቸዉ ወደሚገኝ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጽህፈት ቤት ማሳወቅ እንደሚገባቸዉ ጥሪ ቀርቧል ።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የስርቆት ወንጀል የፈጸመው የጥበቃ ሰራተኛ በእስራት ተቀጣ
                           
ተከሳሽ ቃቁሽ ከበደ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጋዜቦ አደባባይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኝ አንድ ህንፃ ውስጥ ነው።

የደምበል አካባቢ ፖሊስ ወንጀል መርማሪ ዋና ሳጅን አበበ ደሳለኝ እንደተናገሩት ተከሳሹ የህንጻው የጥበቃ ሰራተኛ ሲሆን የተሰጠውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከሚጠብቀው ድርጅት ውስጥ ሁለት ኮምፒውተሮችን ሰርቆ ሲንቀሳቀስ በአካባቢው ስራ ላይ በነበሩ ፖሊሶች እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ ከተጣራበት በኋላ ክስ ተመስርቶበታል።

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰው እና በሰነድ ማስረጃ  የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመ መሆኑን በማረጋገጥ ተከሳሹን ያርማል ሌሎችን የስጠነቅቃል  በማለት በ8 ዓመት ከ5 ወር  እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በሀገሪቱ የሚገኘዉ ሆቴሎች ለዉጪ ሀገር ዜጎች የአገልግሎት ክፍያቸውን በድጋሚ ሙሉ በሙሉ በዶላር ብቻ እንዲፈፅሙ ማድረግ ጀመሩ!

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም የዉጪ ሀገር ፖስፖርት ያላቸው ዜጎች በሆቴሎች ለተጠቀሙበት አገልግሎቶች ክፍያ በዶላር እንዲፈፅሙ የሚያዝ ህግ ቢኖረዉም ለዓመታት ገቢራዊ ሳይሆን መቅረቱ ተሰምቷል።

ሆቴሎች በዶላር ክፍያ እንዳይቀበሉ ተግዳሮት ሆኖባቸው ቆይቷል ከተባሉት ምክንያቶች መካከል በጥቁር ገበያዉ ( Black Market ) እና በመደበኛው የዉጪ ምንዛሪ መካከል ያለዉ ልዩነት እየሰፋ መሄዱ እንዲሁም ብሔራዊ ባንክ የሚያደርገው ቁጥጥር ዝቅተኛ ሊሆን በመቻሉ ነዉ  ተብሏል።

የአዲስ አበባ ሆቴሎች ማህበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት " መመሪያው ከዚህ ቀደም በህግ ደረጃ የነበረ ቢሆንም ቁጥጥሩ ዝቅተኛ ነበር በዚህ ምክንያት የዉጪ ሀገር ዜግነት ያላቸዉ ቱሪስቶች ማረፊያቸውን በሚያደርጉበት ሆቴሎች ለተጠቀሙበት አገልግሎቶች ክፍያቸዉን በሂደት በብር ብቻ እንዲፈፅሙ" ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል።

አሁን ግን ብሔራዊ ባንክ በድጋሚ ቁጥጥሩን በማጠናከር በሰጠው አዲሱ ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ ክፍያቸውን በአሜሪካ ዶላር እንዲፈፅሙ እና ሆቴሎችም ይህንኑ መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ መጀመራቸው ለማወቅ ተችሏል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ለዓለም አቀፍ በረራ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ መንገደኞች ትኬት በዶላር ብቻ እንደሚሸጥ አስታውቋል።

ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶችም ወደ አገራቸው ሲመለሱ በብር ሳይሆን በዶላር ብቻ ነው የትኬት አገልግሎት ማግኝት የሚችሉት ተብሏል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተደረገው የግድያ መከራ የአሜሪካ የፓለቲካ ምህዳር ያለበትን የከፋ ሁኔታ ማሳያ ነው ሲሉ የፓለቲካ ተንታኞች መግለፃቸው ተሰምቷል።

ትራምፕ የተቃጣባቸው ጥቃት በምርጫ ክርክር ወቅት በጆ ባይደን ላይ የወሰዱት ብልጫ መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ ነው የተነገረው ።

ጥቃት አድራሹ ወጣት የትራምፕ ፓለቲካዊ እርምጃ ከሚነቅፉ መካከል ሊሆን ይችላልም ተብሏል።
የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸው በኋላም ጠባቂዎቻቸው ወደ ተሸከርካሪ ውስጥ ቢያስገቧቸውም ትራምፕ አይበሬነታቸውን ለማሳየት ሲሞክሩ ነው የተሰተዋሉት፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ላይ ጥቃት ያደረሰው ግለሰብ በጊዜው በጸጥታ ኃይሎች የተገደለ ሲሆን ወጣቱ ለጥቃቱ ምን እንዳነሳሳው ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን የፀጥታ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ሆኖም ፣ ትራምፕ ላይ የተቃጣው ጥቃት መንስኤ ምን እንደሆነ የተባለ ነገር ባይኖርም ፤ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነም የግድያ ሙከራው የአሜሪካን የፓለቲካ አቅጣጫ የሚቀይር ነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ቢቢሲ

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

ስፔን እንግሊዝን 2 ለ 1 በመርታት የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊ ሆኑ

#EURO2024 #England #Spain

Читать полностью…

EthioTube

የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አማካሪን ጨምሮ 8 ተከሳሾች ከይዞታ ምዝበራ ጋር ተያይዞ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ።

1ሺህ 800 ካሬ ሜትር ይዞታን በተለያዩ መጠኖች ግለሰቦች ያለአግባብ እንዲወስዱ በማድረግና በየደረጃው ይዞታውን ተቀብሎ በመሸጥ ከ80 ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል ተብለው በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞ የከተማ ከንቲባ አማካሪን ጨምሮ 8 ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቷል።

ሌሎች በክስ መዝገቡ ተካተትው በሌሉበት ጉዳያቸው የታዩ 15 ተከሳሾች በሚመለከት የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ብይኑን የሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና የወንጀል ችሎት በክስ መዝገቡ የተካተተ አንድን ተከሳሽም በቂ ማስረጃ እንዳልቀረበበት ጠቅሶ ከቀረበበት ክስ ነጻ ብሎታል።

እንዲከላከሉ ብይን ከተሰጠባቸው ተከሳሾች መካከል የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽ/ቤት የካሳ ግምትና ምትክ ባለሙያ አፈወርቅ ሀይሌ ገ/ስላሴ፣የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አማካሪ ቶሎሳ ተስፋዬ እና የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ቢሮ የሰው ኃይል ዳይሬክቶሬት ባለሙያ አበበ ደጋ እና የኮንስትራክሽን ሰራተኛ የሆነው ኢዶሳ ነገራ ስንኩሬ ይገኙበታል።

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በ11 የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞችና 13 ግለሰቦች በአጠቃላይ በ24 ተጠርጣሪዎች ላይ የወንጀል የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ በዋና ወንጀል አድራጊነት እና በልዩ የሙስና ወንጀል ተካፋይነት በመሆን ስልጣንን አላግባብ መገልገል የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

በዚህም በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1(ሀ) ፣ንዑስ ቁጥር 3 እና አንቀጽ 33 እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና (ለ) እንዲሁም ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተጠቀሰውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ክስ ነው የቀረበባቸው።

በክሱ ላይ ከ1ኛ እስከ 9ኛ እንዲሁም 23ኛ እና 24ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሱት ተከሳሾች የመንግስት የስራ ኃላፊነት ላይ ተመድበው ሲሰሩ በልዩ ወንጀል አድራጊነት የሙስና ወንጀል ተካፋይ ከሆኑት ከ10ኛ እስከ 22ኛ ከተጠቀሱት በግል ስራ ከሚተዳደሩት ተከሳሾች ጋር በጥቅም በመመሳጠር በልማት ተነሺ ስም ከመስከረም 23 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት የተለያዩ ቀናት ውስጥ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 እና በልደታ ወረዳ 3 በይዞታ ክልል ውስጥ በአርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጆች በሚል ምክንያት ብቻ ተገቢ ያልሆነ የካሳና ምትክ በተለያዩ መጠኖች አጠቃላይ 1 ሺህ 800 ካሬ ሜትር ይዞታን በሕገ ወጥ መንገድ ግለሰቦች እንዲወሰድ መደረጉ በክሱ ተጠቅሷል።

ሌሎቹ ተከሳሾች ላይም ቦታውን ወስዶ በመሸጥ ለራሳቸው የማይገባ ብልፅግና በማግኘትና በመንግስት ላይም የመሬቱ ሊዝ ዋጋ የሆነውን እና ካሳ የተከፈለውን 80 ሚሊየን 755 ሺህ 508 ብር ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ በዋና ወንጀል አድራጊነት እና በልዩ የሙስና ወንጅል ተካፋይ በመሆን የስልጣን አላግባብ መገልገል የሚል የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ ነበር የቀረበው።

በዚህ መልኩ ዝርዝር ክስ ከቀረበባቸው ተከሳሾች መካከል የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽ/ቤት የካሳ ግምትና ምትክ ባለሙያ አፈወርቅ ሀይሌ ገ/ስላሴ፣የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አማካሪ ቶሎሳ ተስፋዬ እና የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ቢሮ የሰው ኃይል ዳይሬክቶሬት አበበ ደጋ እና የኮንስትራክሽን ሰራተኛ የሆነው ኢዶሳ ነገራ ስንኩሬ ጨምሮ 8 ተከሳሾች ክሱ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

እነዚህ ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ ዝርዝር በንባብ ከተሰማ በኋላ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የተደረጉ ሲሆን፤ከዚህም በኋላ ተከሳሾቹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው በሰጡት የዕምነት ክህደት ቃል መነሻ ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዳሉ ያላቸውን የሰው ምስክሮች አቅርቦ የምስክርነት ቃላቸውን አሰምቷል፡፡
ፍርድ ቤቱም የምስክር ቃል መርምሮ ወንጀሉ መፈጸሙን መረጋገጡን በመጥቀስ 8 ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡

በተደጋጋሚ በመጥሪያና በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ችሎት ያልቀረቡ 15 ተከሳሾችን በሚመለከት ጥፋተኛ ተብለዋል።

በሌላ በኩል በክስ መዝገቡ በሌለበት የተከሰሰው 21 ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰ ተከሳሽን በሚመለከት በቀረበበት ክስ ላይ ማስረጃ እንዳልቀረበበት ተጠቅሶ ነጻ ተብሏል።

ፍርድ ቤቱ ተከላከሉ የተባሉ ተከሳሾችን የመከላከያ ማስረጃ ለመጠባበቅ ወደ ሕዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም በማሸጋገር ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

Читать полностью…

EthioTube

የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ አይነቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ እና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

አገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል

ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት ነው እየተሰጠ ያለው።

የመጀመሪያ ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ትላንት ሐምሌ 2 በቀድሞ ትምህርት ካሪኩሉም ትምህርታቸውን የተከታተሉ የትግራይ ክልል ተማሪዎች አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጀመራቸው ይታወሳል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…

EthioTube

የፒያሳው ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሕንጻ ለንግድ ቤቶች ኪራይ ክፍት ተደረገ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት ይገኝበት የነበረው ሕንጻ ከዚህ ቀደም በፒያሳ ዙሪያ ሲሰሩ ለነበሩ ነጋዴዎች ለኪራይ ክፍት መደረጉ ተገለጸ።

ከዚህ በፊት ፒያሳ አካባቢ የተለያዩ  የንግድ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ
➘የወርቅ መሸጫ ሱቆች፣
➘ባቅላባ ቤት፣
➘ የመዋቢያ እቃ መሸጫ ሱቆች፣
➘ የእጅ ሰዓት መሸጫ፣
➘ አልባሳት መሸጫ ቤቶች፣
➘ኬክ ቤቶች፣
የቡና ቤቶች እና ሌሎች በአካባቢው የንግድ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ ድርጅቶች ቅድሚያ በመስጠት ሕንጻውን ማከራየት ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት ሜክሲኮ አካባቢ ወደሚገኘው የንብ ባንክ ሕንጻ እንደተዘዋወረም ታውቋል።

በፒያሳ አካባቢ ከላይ በተገለጹት የንግድ ዘርፍ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ከሚመለከተው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ በማቅረብ ከሐምሌ 8 እስከ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፒያሳ በሚገኘው ኤሌክትሪክ ህንጻ ምድር ወለል ቢሮ ቁጥር 001 መከራየት የምትፈልጉትን የቦታ ስፋትና ወለል በመጥቀስ በንግድ ቤቱ ባለቤት/ህጋዊ ወኪል የተፈረመ የኪራይ ፍላጎት ማሳወቂያ ደብዳቤ እንዲያስገቡ ተጠይቋል።

ተቋሙ የሚቀርበውን የተከራዮች ብዛትና የቦታ ኪራይ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከሐምሌ 12 ቀን በኋላ ቀጣይ ሂደቱን እንደሚያሳውቅ አስታውቋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L

Читать полностью…
Subscribe to a channel