በፓሪስ ኦሎምፒክ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በተካሄደው የወንዶች 1500ሜ ማጣሪያ ኢትዮጵያዊው ኤርሚያስ ግርማ 1ኛ በመሆን ወደ ቀጣይ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
ሳሙኤል ተፈራ ከምድቡ 6ኛ በመውጣት ወደ ቀጣይ ዙር ያለፈ ሲሆን፣ በሌላ በኩል አብዲሳ ፈይሳ ከምድቡ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።
-----
#OlympicGames in #Paris2024 - Men's 1500m Round 1
Ermias Girma 🇪🇹 (3:35:21) of #TeamEthiopia qualifies to next round after finishing 1st in Heat 2
Samuel Tefera 🇪🇹 (3:37.34) of #TeamEthiopia qualifies to next round after finishing 6th in Heat 3
Meanwhile in Heat 1, Abdisa Fayisa was unable to qualify
(📷: Getty Images)
በአዲስ አበባ ከተማ የ50 አመት እድሜ ያላቸው ዘመናዊ ጎጆ ቤቶች በኮሪደር ልማት ምክንያት ሊፈርሱ ነው
በአዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኙ የሃምሳ ዓመት እድሜ ያላቸው 31 ጎጆ ቤቶች በከተማይቱ አስተዳደር ትዕዛዝ ሊፈርሱ ነው። ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን የሆኑት ጎጆ ቤቶቹ የሚፈርሱት፤ ቦታው “ለኮሪደር ልማት” ስለሚፈለግ እንደሆነ ተገልጿል።
ጎጆ ቤቶቹ የተሰሩት፤ የኢትዮጵያ ሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር በመስከረም 1966 ዓ.ም. ባስመረቀው ባለ ዘጠኝ ወለል ህንጻ አካል በመሆን ነበር። ህንጻው የተገነባው “ለሀገር እና ለወገናቸው በጎ ስራ ሰርተው ያለፉ ኢትዮጵያውያት እንዲታሰቡበት፣ መጪዎችም ይገነዙበት ዘንድ፣ ስራቸውም ለትውልድ ተላልፎ ዘላቂነት እንዲኖረው በማሰብ” እንደሆነ በህንጻው መግቢያ ላይ የተለጠፈው መረጃ ያሳያል።
በስተኋላ ላይ ለኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን የተላለፈው ይህ ህንጻ “በዲዛይን ልህቀቱ፣ በቦታ አጠቃቀሙ፣ ባህላዊ እሳቤን በዘመናዊ አሰራር ያወሃደ” በመሆኑ ተጠቃሽ እንደሆነ የኪነ ህንጻ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ባለሙያዎቹ ህንጻውን እና የእርሱ አካል የሆኑትን ጎጆ ቤቶች፤ “የአዲስ አበባ ምልክት ከሆኑ” ግንባታዎች መካከል ይመድቧቸዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
መንግሥት የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲወሰን ያሳለፈው ውሳኔ ወቅቱን ያልጠበቀ እና አገራዊ ምስቅልቅልን የሚያስከትል ነው _ ኢዜማ
የ ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) መንግሥት የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲወሰን ያሳለፈው ውሳኔ በየትኛውም መለኪያ ወቅቱን ያልጠበቀ እና ሃገራዊ ምስቅልቅልን የሚያስከትል ነው ሲል ገለጸ::
ፓርቲው መንግስት ተግባራዊ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አስመልክቶ ትላንት ባወጣው የአቋም መግለጫ፤ የኢኮኖሚ ማሻሻያው "የኑሮ ውድነትን በማባባስ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖች አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ሲል ገልጿል::
“የውጭ ምንዛሬን በገበያ መወሰንን በሚመለከት በተወሰነው ውሳኔ የሚመጣውን ማንኛውም በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚደርስ የምጣኔ ሀብት፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ውሳኔውን ያሳለፈው መንግሥት ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል” ሲልም ኢዜማ አስገንዝቧል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
አነጋጋሪውን የመንግስት የፖሊሲ ለውጥ አስመልክቶ ከኢዜማ የተሰጠ መግለጫ
-----
ፖሊሲ የማውጣት ሉዓላዊነትን የሚገድብ ማሻሻያ ውጤቱ ቀውስ ጋባዥ ትርፉም ሀገራዊ ዕዳ ነው!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ)
ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም.
#Ethiopia #IMF #WorldBank #AfricanEconomy #EthiopianEconomy
ብሔራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው በአለምአቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን ገለጸ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ ለሚያቀርቡ አምራቾች እና አቅራቢዎች ክፍያ የሚፈጸመው በሚያወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን ተሰልቶ መሆኑን አስታውቋል።
የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ የሚመራ መደረጉን ተከትሎ ብሔራዊ ባንክ በወርቅ መግዣ ላይ አዲሱን አሰራር ተግባራዊ እንደሚያደርግ የገለጸ ሲሆን ለማንኛውም ወርቅ አቅራቢ ክፍያ የሚፈጸመዉ የእለቱን ዓለም ዓቀፍ የወርቅ ዋጋ በእለቱ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣዉ የውጭ ምንዛሪ ተመን ተባዝቶ ይሆናል ሲልም ነው በማብራሪያው የጠቆመው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ስርአት መሸጋገሩ ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ማስታወቁ ይታወቃል፡፡
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአንድ ዶላር
👉 መግዣ ዋጋ ዛሬ 77.12 ገብቷል።
👉መሸጫውም 78.67 ሆኗል።
👉 1 የኩዌት ዲናር ዛሬ 240.34 ገብቷል።
👉 ዩሮ ደግሞ 83.37 ሆኗል።
ስድስት የግል ባንኮች በአዲሱ የውጭ ምንዛሬ ግብይት መጠቀም አልጀመሩም
የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ “በገበያ ላይ የተመሰረተ” እንደሚሆን ቢያስታውቅም፤ ስድስት የግል ባንኮች የውጭ ገንዘቦችን የሚገዙበትን እና የሚሸጡበትን የተሻሻለ ተመን እስከ እኩለ ቀን ድረስ ይፋ አለማድረጋቸውን ገልፀዋል።
የየባንኮቹ ኃላፊዎች በተመኑ ላይ ለመነጋገር ዛሬ ረፋዱን በየፊናቸው ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
እስከ ዛሬ ድረስ በነበረው አሰራር ባንኮች የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዙበት እና የሚሸጡበትን ተመን የሚያወጣላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነበር።
ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ጠዋት ባወጣው መግለጫ፤ የውጭ ምንዛሬ ተመኑ “በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ስርአት መሸጋገሩን” አስታውቋል።
ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በኋላ “ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ” እንደሚሆንም ገልጿል። ይህን የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ለውጥ ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ከሁሉም አስቀድሞ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው።
የግል ባንኮች ያወጣሉ ተብሎ የሚጠበቀው የውጭ ምንዛሬ ተመን፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተመን ጋር “ተመሳሳይ ይሆናል” ብለው እንደሚጠብቁ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነገረቻቸው የአንድ የግል ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ ተናግረዋል። ባንኮች ተመኑን የሚወስኑት ያላቸውን የውጭ መገበያያ ገንዘብ ክምችት መሰረት አድርገው መሆኑንም አክለዋል።
Via:- Ethiopian Insider
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
አንድ የአሜሪካ ዶላር ከ76 ብር በላይ መሸጥ ተጀመረ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእለቱን የዉጪ ምንዛሪን ይፋ አድርጓል ። አንድ የአሜሪካ ዶላር በ 74.7364 ተገዝቶ በ 76.2311 ብር እንዲሸጥ ተወስኗል።
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ሰኞ ሐምሌ 22፤ 2016 ጀምሮ፤ “በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ስርአት እንደተሸጋገረ” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።
በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ58 ብር ከ64 ሳንቲም ገደማ ይሸጥ የነበረውን አንድ የአሜሪካን ዶላር፤ በዛሬው ዕለት ወደ 76.23 ብር አስገብቶቷል። በተጨማሪ በዩሮ ፣ እና ፓዉንድን በመሰሉት የዉጪ ምንዛሪዎች ላይም ጭማሪ ተደርጎባቸዋል።
ምን አልባትም ይህ ዋጋ አዲስ የወጣውን ህግ መሠረት አድርጎ ያደረገው ለውጥ መሆኑን ለመረዳት ያስችላል።
መቀነት : Meqenet : በዚህ ሳምንት ሴት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ደህንነት ይሰማቸዋል? በሚል ርዕስ ያቀረብነውን ፕሮግራም ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ ።
https://youtu.be/_qoLBDnG0GY
ዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
***
ቴዲ አፍሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድምፃዊው በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፉን በማድረግ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለማገዝ የተለያዩ አካላት ድጋፋቸውን እያደረጉ ይገኛል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን ማወጁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያስታወቀ ሲሆን፤ ብሔራዊ ሐዘኑ የታወጀው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ የዜጎች ሕይወት በማለፉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
(ምንጭ፦ ETV)
ቤንች ሸኮ ዞን : በመሬት ናዳ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል
👉 ሁለት ቀበሌዎች የሚደረግ የትራንስፖርት እንስቃሴ ተቋርጧል
የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና ደንና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ እንደተናገሩት ከቀን 15/11/2016 ጀምሮ በጉራፈርዳ ወረዳ ኮመታ ሰፈራ ፣ ነባሩ ኮመታ ቀበሌ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ 3 ሄክታር የሚሆን ደን በናዳው ምክንያት መውደሙን ገልጸዋል።
ናዳው በነባሩ ኮመታ 2 ህጻናት እንዲሁም ከባዲቃ የመጣች አንዲት ሴት በድምሩ 3 ሰዎች የተወሰዱ ሲሆን ዜናው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በፍለጋ አለመገኘታቸውን ገልጸዋል። በቀበሌው የበቆሎ ፣ ጎደሬና የሙዝ ማሳ ላይ ጉዳት መድረሱን የገለጹት አቶ መስፍን ከመምሪያው የተላኩ አመራሮችና ባለሙያዎች በስፍራው ተገኝተው ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።
አቶ መስፍን እንደተናገሩት በናዳውና በከፍተኛ ሁኔታ የወንዝ ሙላት የተነሳ ወደ ነባሩ ኮመታና ኡይቃ ቀበሌዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና ሰሞኑን እየጣለ ባለው ከፍተኛ ዝናብ ሰቢያ በሸኮ ወረዳ ሻይታና ቦይታ ቀበሌዎች 4 መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለፀ ሲሆን የችግሩ ስጋት አለባቸው በሚባሉት ሼይ ቤንች ወረዳን ጨምሮ በሁሉም መዋቅሮች የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
በካፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸዉ አለፈ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ሞዲዮ ጎምበራ ቀበሌ ሐምሌ 17 ቀን ከሌሊቱ 8:00 በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ነው አደጋ የተከሰተው።
በመሬት መንሸራተት አደጋው እናት እና አባት እንዲሁም የ8 አመት ታዳጊ በአጠቃላይ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው ሲያልፍ ፣ በአንድ ሰው ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን የክልሉ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በተጨማሪም 24 ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።በቀጣይ ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስ ተራራማ አከባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
በክልሉ ከሶስት አመት በፊት በዳውሮ ፣በኮንታ እና በካፋ ዞኖች የመሬት መንሸራተት አደጋዎች እንዳጋጠመ ተገልጿል።
ባሳለፍነው ሰኞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት መንሽራተት የበርካቶች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።
ጎፋ በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ
በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን በደረሰው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
ጽህፈት ቤቱ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ ባወጣው የሁኔታዎች መግለጫ ላይ ነው በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል ያመለከተው።
እሁድ ሐምሌ 14 እና ሰኞ ሐምሌ 15/ 2016 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ተቀብረው የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ዛሬም ለአራተኛ ቀን እየተካሄደ ነው።
በአደጋው ስፍራ የሚገኙት የቢቢሲ ዘጋቢዎች እንደገለጹት ዛሬን ጨምሮ በአካባቢው እየጣለ ባለው ዝናብ ውስጥ ጭምር ከተንሸራተተው መሬት ስር ለማውጣት የሚደረገው የነፍስ አድን ጥረት ቀጥሏል።
ባለፉት ቀናት በተደረጉት የፍለጋ ጥረቶች በአደጋው ሕይወታቸው አልፎ የተገኙ ሰዎች ቁጥር 257 የደረሰ ሲሆን፣ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ስጋታቸውን መግለጻቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) አመልክቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በማህበር ተደራጅተው ቤት የሚገነቡበትን አሰራር አፀደቀ።
በከተማዋ የሚኖሩና የቤት ችግር ያለባቸውን ነዋሪዎች ችግር በሚቀርፍ አግባብ የከተማ አስተዳደሩ መሬት፣ የሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ህንፃዎች ዲዛይን፣ ማህበራቱን የማደራጀትና ግንባታው በሚጀመርበት ጊዜ የመቆጣጠር ሀላፊነት የሚወስድ ሆኖ በማህበር ተደራጅተው የጋራ ህንጻ የሚገነቡ ሰራተኞች፣ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች የፀጥታ አካላት ከተደራጁ በኋላ ቁጠባ በአግባቡ መቆጠብ የሚችሉና አስተዳደሩ በሚያዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ከፍታቸውን የጠበቁ ህንፃዎች ለመገንባት ዝግጁ የሆኑ ወደ ግንባታ እንዲገቡ ማድረግ የሚያስችል ደንብ ትናንት ምክር ቤቱ ያፀደቀ ሲሆን ዝርዝር የአፈፃፀም ሂደቱ በከተማዋ ካለው የቤት አቅርቦት ማህቀፍ ጋር ተጣጥሞ እንዲፈፀም ውሳኔ አሳልፏል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም በኋላ ወደ አሥመራ እንዳይበር አገደ
የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዋና ከተማዋ አሥመራ የሚያደርገው በረራዎች ከመስከረም አጋማሽ በኋላ እንዲቋረጡ ወሰነ።በኤርትራ የትራንስፖርት እና ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስቴር የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዛሬ በታተመው በመንግሥታዊው “ሓዳስ ኤርትራ” ጋዜጣ ላይ ባወጣው ማስታወቂያ ላይ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ መታገዱን የገለጸው።
ባለሥልጣኑ በጋዜጣው ላይ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከመስከረም 20/2017 ዓ.ም. በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርጋቸው በረራዎችን በሙሉ ማገዱን አስታውቋል።የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣኑ በጋዜጣ ላይ ባወጣው መግለጫ አየር መንገዱ እንዲታገድ የተወሰነው በኤርትራውያን መንገደኞች ላይ “የተደራጀ እና ስልታዊ” የሆነ በደል በማድረሱ ነው ብሏል።
አየር መንገዱ አግባብ ባልሆነ ሂደት ሆነ ብሎ “የተጓዦች ሻንጣዎች ላይ ስርቆት ይፈጸማል”፣ በተደጋጋሚ የበረራዎች እና የሻንጣዎች መዘግየት እንደሚያጋጥም ጠቅሶ፤ አየር መንገዱ ለተጓዦች ካሳ ሳይሰጥ ቆይቷል ብሏል።ጉዳዩን በተመለከተ ቢቢሲ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም።
የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አየር መንገዱን ለማገድ ከወሰነበት ምክንያቶች ሌላኛው የበረራ ቲኬቶች ዋጋ ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በመደረጉ ነው ብሏል።“ከላይ የተጠቀሱ ችግሮች እንዲቀረፉ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጡ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች ውጤት ማስገኘት ባለመቻላቸው ከመስከረም 20/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ኤርትራ የሚደረጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች እንዲታገዱ ተደርገዋል” ብሏል።
የኤርትራ መንግሥት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦች ባወጣው መልዕክት ከመስከረም 20 በኋላ በአየር መንገዱ በረራ ለማድረግ ያቀዱ መንገደኞች ቀድመው ማስተካከያ እንዲያደርጉ አሳስቧል።የኤርትራ መንግሥት አየር መንገዱን ከመስረም 20 በኋላ አግጃለሁ ቢልም አየር መንገዱ ግን አሁንም በድረ-ገጹ እና በቲኬት መሸጫ ቢሮዎቹ ከመስከረም 21 በኋላ ለሚደረጉ በረራዎች የአየር ቲኬቶችን እየሸጠ ይገኛል።
ቢቢሲ
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
አዋሽ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በዘጠና ብር እየገዛ ነው
ከግል ባንኮች አንዱ የሆነው አዋሽ ባንክ በዛሬ ምንዛሬ ተመኔ ዶላር በ90 ብር ከ0009 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 94 ብር ከ5011 እሸጣለሁ ብሏል።
ፓውንድ ስተርሊንግንም እጅግ ከፍ ባለ ዋጋ በ110 ብር ከ6446 ሳንቲም ገዝቼ በ116 ብር ከ1768 ሳንቲም እሸጣለሁኝ ብሏል።
ዩሮንም ቢሆን ጨመር አድርጌ በ97 ብር ከ5882 ሳንቲም እገዛለሁ፤ መሸጫዬ ደግሞ 102 ብር ከ4776 ሳንቲም ነው ብሏል።
የUAE ድርሃም የዛሬው መግዣዬ 22 ብር ከ1751 ሳንቲም ነው ፤ መሸጫዬ 23 ብር ከ2837 ነው ሲል አውጇል። ዛሬ ከግል ባንኮች ቀደም ብሎ ዕለታዊ የምንዛሬ ተመን ያሳወቀው አዋሽ ባንክ ነው።
በኦሊምፒክ ተሳትፎ ታሪካችን በእርምጃ ውድድር አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት ለሃገራችን ተመዘገበ
ዛሬ ማለዳ በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ በተጀመረው የአትሌቲክስ ስፖርት የመክፈቻ ውድድር ላይ በእርምጃ ወንዶች 20 ኪሎ ሜትር ብቸኛ ተወዳዳሪያችን አትሌት ምስጋና ዋቁማ በ1:19:31 የሃገራችን የርቀቱ ሪከርድና የግሉ የተሻለ ሰዓት በማስመዝገብ ጭምር 6ኛ ደረጃን በመያዝ በኦሊምፒክ ተሳትፎ ታሪካችን በእርምጃ ውድድር እጅግ አበረታችና ለወደፊት ተስፋ ሰጪ የሆነ ውጤት አስመዝግቧል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ተአምረ ማርያም መጽሐፍ ወደ ኦሮምኛ ተተረጎመ
-----
(#EOTCTV ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም)
በሰሜን አሜሪካ የሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል እና ዲያቆን እንዳለው መለሰ አዘጋጅነት በኦሮምኛ ፣ በግእዝና በአማርኛ ቋንቋዎች የተጻፈው ተአምረ ማርያም መጽሐፍ ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ ላይ ተመርቋል።
መጽሐፉ በማኅበረ ቅዱሳን የኤዲቶርያል አገልግሎት ተመርምሮ ለኅትመት የበቃ ሲሆን አሳታሚና አከፋፋይ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በሰሜን አሜሪካ የሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቤተ ክርስቲያን በቋንቋ ማገልገልና መገልገልን ከሐዋርያት ተቀበላ እያስቀጠለች መሆኗን ገልጸው እኛም የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኦርቶዶክሳውያንን መሠረት ያደረገውን መጽሐፍ እንደ አቅማችን ተርጉመን ለኅትመት አብቅተናል ብለዋል፡፡
ብዙ ከማውራት ትንሽ መሥራት የተሻለ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ይህንን አድርገናል፣ በቀጣይ ደግሞ የትርጉም ሥራዎችን ከዚህ በበለጠ ለመሥራት መጽሐፍትን እየመረጥንና እየተመካከርን ነው ብለዋል፡፡
ቋንቋ ተግባብተን የምንለወጥበትና የምንስማማበት እንጅ መንግሥተ ሰማያት የምንገባበት አይደለም ሲሉም አጽዕኖት ሰጥተዋል።
ብፁዕነታቸው ጨምረው እንደገለጹት መጽሐፉ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ምእመናንን መሠረት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እኛ ይህንን የትርጉም ሥራ ለመሥራት ያነሳሳን ምክንያት የቤተ ክርስትያንን ተደራሽነት በመረዳት ምእመናን በቋንቋቸው እንዲገለገሉ በማሰብ ነው ያሉት ዲያቆን እንዳለው ቋንቋን ምክንያት በማድረግ በአጉል ትርክት የተጠቁ ሁሉ ሊማሩበት የሚገባ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካን ዶላርን በ80 ብር መግዛት መጀመሩን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ቀትር ላይ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ የአሜሪካን ዶላርን በ80 ብር መግዛት መጀመሩን አስታውቋል፤ መሸጫው ደግሞ 81 ብር ከ61 ሳንቲም መሆኑን ገልጿል።
መንግስት ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም አንድ የአሜሪካ ዶላርን ይገዛበት ከነበረበት 57.48 ብር ወደ 74.73 ብር ከፍ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል።
ዛሬ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ተመን መግለጫ ላይ በሁለት ቀናት ውስጥ የስድስት ብር ጭማሪ የተደረገበትን 80 ብር መግዣ ዋጋ ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወስንበት የገበያ ሥርዓት ማሸጋገሩን ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና፣ ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እድሜ ልክ እና 15 ዓመት ከሚያስፈርዱ ሁለት ክሶች ነፃ ተባለ !
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሐምሌ 2014 ዓ.ም. “ጥብቅ የመከላከያ ሠራዊትን ምስጢር ማባከን”፣ “መከላከያ ሠራዊቱን መከፋፈል” እና “የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋት” የሚሉ ሦስት ክሶች ተመስርተውበት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆኖ ለስድስት ወራት በእስር ላይ ነበር።
ሆኖም ግን ፤ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሕገ-መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ችሎት ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ ዳኛ ዘላለም ተስፋዬ እና የተከበሩ የቀኝ ዳኛ ወ/ሮ ሐረገውይን ተክሉ ተሰይመው የመጀመሪያ እና ሁለተኛውን ክስ ውድቅ አድርገው፣ ሦስተኛው ክስ ደግሞ አንቀጽ ተቀይሮ እንዲከላከል በመወሰናቸው ከወህኒ ቤት በዋስ መፈታቱ ይታወሳል፡፡
ይሁንና፣ የፌደራል መንግሥት ዓቃቢ ሕግ ጋዜጠኛው ነፃ የተባለባቸው ከ15 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እና ከ10 እስከ 15 ዓመት ከሚያስፈርዱበት ሁለት ክሶች “ነፃ መባል አልነበረበትም” በሚል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡ ጋዜጠኛውም በጠበቃዎቹ ቤተማርያም አለማየሁ እና ሄኖክ አክሊሉ በኩል ሲከራከር ቢቆይም፣ ጉዳዩን እየመረመረው በነበረው በአቶ ሽምሱ ሲርጋጋ ሰብሳቢነት የሚመራው ችሎት ላይ “የዳኛ ይቀየርልኝ” ጥየቄ አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበት ነበር፡፡
ይህም ሆኖ፣ በወርሃ ሚያዚያ 2016 ዓ.ም ሦስቱም ዳኞች ተቀይረው፣ በምትካቸው ሰብሳቢ የተከበሩ ዳኛ ምጽላል ኃይሌ፣ እንዲሁም የተከበሩ ዳኛ ከበቡሽ ወርቁ እና የተከበሩ ዳኛ ኡመር መሐመድ የግራ እና ቀኝ ዳኛ ሆነው ተመድበዋል፡፡
በትናንትናው እለት ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም በተከበሩ ዳኛ ምጽላል ኃይሌ ሰብሳቢነት የሚመራው ችሎት “የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክልና የሚነቀፍ ሆኖ ስላላገኘነው ጋዜጠኛው በነፃ እንዲሰናበት የተሰጠው ውሳኔ ጽንቷል” በሚል ፍርድ ሰጥተዋል፡፡
ይህን ተከትሎ፣ የዚህ ዜና ዘጋቢ ጋዜጠኛውን “ውሳኔው የፍርድ ቤቶችን ገለልተኝነት ያሳያል ወይ?” ብሎ ላቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ “ፈጽሞ አያሳይም” ካለ በኋላ፤ “ለእኔ እውነተኛ ዳኝነት የሰጡኝ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞችም ሆኑ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ለህሊናቸው ታማኝ እና ፍትሃዊ በመሆናቸው፣ እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ጠንካራ በመሆናቸው ብቻ የመጣ ውጤት ነው፡፡ በተረፈ፣ ከእነዚህ ጥቂት ዳኞች በቀር፣ ፍርድ ቤት ላይ ፈጽሞ እምነት የለኝም፤ ገለልተኛም ነው ብዬ አላምንም፡፡ እንደተቋም ብዙ የሚያሳዝኑ ጉዳዮች አሉ፤” ብሏል፡፡
ይድነቃቸው ከበደ
“በህወሓት አመራር መካከል የተፈጠረው ክፍፍል፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የትግራይን ቀውስ እያባባሰው ነው” - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ በፓርቲያቸው አመራር ላይ የሰላ ትችት የሰነዘሩበት ገለጻ አድርገዋል፤ ለጊዜያዊ አስተዳደሩን ዕቅድ መበላሸት እና ለክልሉ ጸጥታ መደፍረስ የህወሓት አመራር ተጠያቂ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ከድምጽ ወያነ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባካሄዱት የትግርኛ ቃለምልልስ ክልሉ እየተጋፈጠ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ክልሉ በቀውስ ውስጥ እየታመሰ ይገኛል ያሉት አቶ ጌታቸው ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የህወሓት አመራር ከህዝቡ ሰላም እና ደህንነት ይልቅ ለግላዊ ፍላጎቱ ቅድሚያ መስጠቱ ነው ሲሉ ተችተዋል።
በክልሉ እየተባባሰ ላለው የጸጥታ ችግር ዋነኛ ምክንያቶቹ “በተዋረድ ያለው አስተዳደር አለመናበብ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ በጸጥታ ሀይሉ እና በፍትህ ተቋማት መካከል አለመናበብ” መሆኑን አመላክተዋል።
“በህወሓት አመራር ላይ እየተስተዋለ ያለው ክፍፍል ሁኔታው እንዲባባስ አድርጓል” ብለዋል።
በወርቅ ዘረፋው ላይ ከሴኔጋል፣ ናይጀሪያ እና ቻይና ዜጎች የተሳተፉበት፣ ወርቁን ለማውጣት መርዛማ ኬሚካልም ጭምር ጥቅም ላይ የዋለበት ነው ሲሉ ገልጸው በክልሉ በስፋት እየተካናወነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
via Addis Standard
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ዘንድሮ በተሰጠው የመውጫ ፈተና 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አላሳለፋም ተባለ
የግል የከፍተኛ ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከል ያሳለፋት 13 በመቶ እንደሆነ ተነግሯል።
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ አሳልፈዋል ተብሏል።
202 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዘንድሮ የመውጫ ፈተና ተማሪዎቻቸውን ቢያስፈትኑም 22ቶቹ አንድም ተማሪ ማሳለፍ እንዳልቻሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ኘ/ር) ተናግረዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የፓሪስ ኦሊምፒክ አዘጋጆች በመጨረሻው እራት ላይ ባስተላለፉት አፀያፊ መልዕክት ይቅርታ ጠየቁ
የፓሪስ 2024 አዘጋጅ ኮሚቴ የሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ የመጨረሻው እራት ሥዕል ከድራግ ንግሥቶች እና ከግሪክ አምላክ እንዲሁም አማልክት ጋር አያይዞ በማሳየት የሠራውን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ በተፈጠረው ትዕይንት የተናደዱ ካቶሊኮችን እና ሌሎች የክርስቲያን ቡድኖችን ይቅርታ ጠይቋል።
በሴይን ወንዝ ዳራ ላይ የተካሄደው የመጽሐፍ ቅዱስ ትዕይንት ትርኢት ዳዮኒሰስን ለመተርጎም እና “በሰዎች መካከል የሚፈጸመውን ዓመፅ ከንቱነት” ለማስገንዘብ ታስቦ ነበር ሲሉ አስተባባሪዎች በኤክስ ላይ ጽፈዋል።
ኮሚቴው ይቅርታ ለመጠየቅ የተገደደው ትርኢቱ በካቶሊኮች፣ በክርስቲያን ቡድኖች እና በአለም ዙሪያ ባሉ ወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች ዘንድ ቁጣን ከፈጠረ በኋላ ነው።በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ለማንም የሃይማኖት ቡድን ክብር ለመንፈግ አልነበረም ሲሉ የፓሪስ 2024 ቃል አቀባይ አን ዴስካምፕስ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተናግረዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የድምጻዊ ያሬድ ነጉ የሀዘን መግለጫ ከጎፋ ሳውላ
በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ውድ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን ምክኒያት የተሰማን ሀዘን ጥልቅ መሆኑን እየገለጽኩ፦ አቅም በፈቀደ መልኩ ለወገኖቻችን ድጋፍ ይሆን ዘንድ ከጓደኞቼ ጋ በመተባበር ይሄ ቢመጣ የተባልነውን አስጭነን በስፍራው ተገኝተናል።
ይሄ ድጋፋችን በዚህ ብቻ የማይቆም መሆኑን በመግለጽ ወገኖቻችን በፈለጉን ሁሉ ቅጽበት አቤት ብለን የምንገኝ ልጆቻቸው መሆናችንን ስንገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው።
ነፍስ ይማር!!
ያሬድ ነጉ እና ጓደኞቹ፦ ትውልደ ኤርትራዊው፥ አዎት እንድሪያስ፣ አዲስ ጌቱ፣ አብዲ፣ ታታ አፍሮ እና ኡጁሉ ፌራ በአንድ በመተባበር
ከጎፋ ሳውላ ከተማ
ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን አውጇል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ኢትዮጵያ በ39 ስፖርተኞች የምትሳተፍበት የ #ፓሪስ_ኦሊምፒክ ዛሬ ይጀመራል
በፓሪስ የሚካሄደው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ስነ ስርዓት ዛሬ ሐምሌ 19 ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ30 በይፋ ይጀመራል።
ከ100 ዓመታት በኋላ ለ3ኛ ጊዜ ታላቁን የስፖርት መድረክ የማስተናገድ ዕድል ያገኘችው ፓሪስ፤ የዘንድሮው ኦሊምፒክ መክፈቻ በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስታዲየም ውጪ በወንዝ ላይ ታደርጋለች።
ይህ የመክፈቻ መርሃግብር በፓሪስ ሰሜናዊ ክፍል ዘወትር የመዝናኛ ጀልባዎች በሚንሸራሸሩበት ሴን ወንዝ ላይ የሚከናወን ሲሆን፤ ተሳታፊ ሃገራትም ባንዲራቸውን ይዘው የሚታዩት በተዘጋጁላቸው 94 ጀልባዎች ላይ ሆነው የ3 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር ጉዞ ያደርጋሉ፡፡
በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከ203 ሀገራት የተወጣጡ 10 ሺህ 500 አትሌቶች በ32 የስፖርት አይነቶች እንደሚወዳደሩ የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ በዋናነት በተለያዩ ርቀቶች በሚደረጉ የአትሌቲክስ የስፖርት ውድድሮች በ39 ስፖርተኞች የምትካፈል ሲሆን አትሌቶቹ ከሚያዚያ 2016 ዓ.ም አንስቶ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ፈረንሳይ የኦሊምፒክ ተሳታፊ ሀገራትን ቀይ ምንጣፍ በመዘርጋት እየተቀበለቻቸው ሲሆን ለታላቁ ድግስ 9 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ያደረገች ሲሆን በአጠቃላይ እስከ 12 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ታገኛለች ተብሎም ይጠበቃል፡፡
የማሊና የፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላት የ29 ዓመቷ ድምጻዊና የዜማ ደራሲ አያ ናካሙራ በመክፈቻው ስነ ስርዓት ስራዋን ታቀርባለች። አሜሪካዊቷ ሌዲ ጋጋና ካናዳዊቷ ኮከብ ሴሊን ዲዮን የሙዚቃ ስራቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
መረጃው ከኢዜአ እና ከኢፕድ የተቀናጀ ነው።
ፕሬዚዳንት ፑቲን እና አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ
ፕሬዝዳንት ፑቲን እና አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢትዮጵያ መንግስት ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ዜጎች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን መግለጻቸውንም በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል፡፡
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ጥልቅ ሃዘን አንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡
በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደስር እንደሚችል ኦቻ መግለጹን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተጎጅዎች ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርጓል
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬቾ ቀበሌ ለደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወጎኖቻችን ግምታቸው 45 ነጥብ 5 ሚሊዮን የ ገንዘብ ፤የህክምና ግብአቶች የአስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ቦታው መላኩን አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በድጋፉ ሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት ለወገን ቀድሞ መድረስ ቀዳሚ ተግባራችን ነው ያሉት በከተማው ህዝብና አስተዳደር ስም ከጎናቸው መሆናችንን ለመግለፅ የከተማው አመራሮችን ወደ ቦታው በአካል የሄዱ ሲሆን የጉዳቱን ልክ በቦታው በአካል በማየት ድጋፉን ለመቀጠል እንስራለን ሲሉም አብሮነታቸውን ተናግረዋል።
ከተላኩት የድጋፍ አይነቶቹ ውስጥ አንቡላንስ፣ የህፃናት አልሚ ምግቦች ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ህክምና እርዳታ መስጫ መሣሪያዎች ፣ መድሀኒቶች ፣ እንሶላዎች፣ በርድልብሶች ሲሆኑ በገንዘብ 25 ሚሊየን እና በቁሳቁስ ደግሞ 20 ሚሊዮን ግምት እንዳላቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በጋምቤላ ክልል ከተፈጸመ የንፁሃን ግድያ ጋር በተያያዘ የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነርን ጨምሮ የተከሰሱ ግለሰቦች በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ
በጋምቤላ ክልል ተፈጽሟል ከተባለ የንፁሃን ግድያ ጋር ተያይዞ ክስ የቀረበባቸው የክልሉ የቀድሞ ም/ኮሚሽነር የነበሩትን ቱት ኮር ጨምሮ ሌሎች የፖሊስ እና የልዩ ሃይል አመራር አባላት ከ14 እስከ 22 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ ተገለጸ።
የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የህገ መንግስትና በህገ መንግስት ስርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት መሆኑም ተጠቁሟል።
ችሎቱ ከዚህ በፊት በነበረ ቀጠሮ በክሱ ተራ ቁጥር 1 የተከሰሱትን የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከላቸውን ጠቅሶ በነጻ ማሰናበቱ ይታወሳል።
መረጃ ሰጥተዋል በሚል ማንነታቸው የተለዩ 35 የሚሆኑ ሰዎች እና ሌሎች ማንነታቸው ያልተለዩ ንጹሐን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው በክሱ ተጠቅሷል።
በዚህም ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ባለመቻላቸው 2ኛ ተከሳሽ የክልሉ የቀድሞ ም/ኮሚሽነር የነበሩት ቱት ኮር፣ 3ኛ ተከሳሽ የክልሉ የቀድሞ የልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኮንግ ሬክ እና 4ኛ ተከሳሽ የክልሉ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡጀዲ ባሬ እያንዳንዳቸው በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል። ሌሎች በሌሉበት ጉዳያቸው የታየው 14ኛ እና 15ኛ ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው በ22 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ከፋና ያገኘነው ዘገባ ያሳያል።
የቀደመ ህጋዊ ሰውነት እንዲመለስ እንጂ እንደ አዲስ ፓርቲ መመዝገብ አልፈልግም:-ህወሀት
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በፖለቲካዊ ውሳኔ የነበረው ሕጋዊ ሰውነት እንዲመለስለት እንጂ እንደ አዲስ መመዝገብ እንደማይፈልግ የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ።
አቶ አማኑኤል ባለፈው ግንቦት ወር በምርጫ ሕጉ ላይ የተደረገው ማሻሻያ፤ “የተሰረዘውን የህወሓት ሕጋዊ ሰውነት ለመመለስ የሚያስችል ሳይሆን በልዩ ሁኔታ እንደ አዲስ ለመመዝብ የሚያስችል ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ኃይልን መሠረት ባደረገ የአመጽ ተግባር ተሳትፎ የነበረ የፖለቲካ ቡድን በፓርቲነት የሚመዘገብበትን ሂደት በዝርዝር ያስቀመጠ ነው።
የአዋጅ ማሻሻያው፤ የፖለቲካ ቡድኑ “ሕገ መንግሥታዊ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግሥት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል” ሲል ይደነግጋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L