ethopoeia | Unsorted

Telegram-канал ethopoeia - ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

588

🇪🇹ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት ማክበር ባትችል አታዋርዳት ማራመድ ባትችል አታዘግያት መጠበቅ ባትችል አትበትናት። ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም። 🇪🇹 ሼር በማድረግ ትክክለኛ መረጃ ከምንጩ ያግኙ

Subscribe to a channel

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ምሽት በetv ቀርበው ስለህዳሴው ግድብ ከተናገሩት ፦

- DRC ኮንጎ አመራርነቱን ከተረከበች በኃላ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ እስካሁን አንድ ጊዜ ለሶስትዮሽ ድርድር ተቀምጠዋል።

- የሶስትዮሽ ድርድሩ በሁለቱ ሀገራት ምክንያት (ግብፅ እና ሱዳን) ፍላጎት ማነስ ተቋርጧል።

- ኢትዮጵያ ሁል ጊዜም ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ መቀጠል ነው።

- ኢትዮጵያ ሁሌም የምትለውን ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ አቋም ላይ እንድረስ የሚል ነው። በዋናነት በሙሌቱና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እንስማማ እያለች ነው።

- የሙሌት ስምምነቱን በተመለከተ ግን ሱዳን እና ግብፅ አጠቃላይ ስምምነቱን ካልደረስን ካልተፈራረምን በሚል ፣ ሌሎች አደራዳሪዎችን በመፈለግ ሂደቱን እያፈረሱት ነው።

- ኢትዮጵያ አጠቃላይ ስምምነቱ በሂደት ይመጣል ብላለች። በአንዴ የሚሆን አይደለም ጊዜ ይወስዳል። በበርካታ ጉዳዮች ላይ መነጋጋረ አለብን ብላለች።

- አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ዝናብ ነው፣ ብዙ ውሃ አለ፣ ከሚመጣው ውሃ እንኳን አብዛኛውን እየተያዘ አይደለም ፤ ሙሌቱ ላይ እንስማማ የሚል አቋም ነው ያለው በኢትዮጵያ በኩል። እነሱ ግን አልተቀበሉትም።

- ግድቡ የሚሰራው ሊሞላ ነው ፤ አምና የመጀመሪያው ሙሌት ሄዷል ዘንድሮ ሁለተኛው ይሄዳል፤ ይሄ በ2015 የሶስትዮሽ ስምምነት ላይ ያለ ነው ፤ ነገር ግን ይሄንንም እየተቃወሙ ነው።

- ኢትዮጵያ ሙሌቱ እና አጠቃላይ ፕሮጀክቱ እንደማይጎዳቸው እየገለፀች ነው።

- አሁን በተለይ ሱዳኖቹ ጥያቄዎቻቸው የተመለሱላቸው ይመስላል ፤ ድብቅ ፍላጎታቸው ሌላ ቢሆንም፤አንዴ የአፍሪካ ህብረትን ሚና እያሳነሱ ሌላ አደራዳሪ እየፈለጉ፤ አንዴ ሚናዎችን እንዲበረዙ መሰናክሎች እየደረደሩ ነው።

- ኢትዮጵያ ወደሁለተኛው ሙሌቱ መሄዷ የማይቀር ነው።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

"የዘንድሮው የፊቼ ጫምባላላ በዓል በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በአደባባይ አይከበርም" - አቶ ደስታ ሌዳሞ

የዘንድሮውን የፊቼ ጫምባላላ በዓል የኮሮና ወረርሽኝ መስፋፋትን ለመከላከል ሲባል በአደባባይ እንደማይከበር የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ።

ህብረተሰቡ በዓሉን ሲያከብር ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመርዳትና እርስ በእርስ በመደጋገፍ ሊሆን እንደሚገባውም ርዕሰ መስተዳደሩ ዛሬ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ገልጸዋል።

የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ የሆነው“ ፊቼ ጫምባላላ ” ከጥንት ጀምሮ ሲከበር የቆየ መሆኑን አስታውሰው፤ በዓሉ የተጣሉትን በማስታረቅ ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና ለሰው ልጆችና እንስሳት ክብር በመስጠት የሚከበር ታላቅ በዓል መሆኑን አስረድተዋል።

“ለበዓሉ ሲባል እንስሳት የማይታረዱበትና በቀያቸው በእንክብካቤ የሚያሳልፉበት እንዲሁም ዛፍ የማይቆረጥበት በመሆኑም እለቱን ልዩ ያደርገዋል” ብለዋል።

በአሁን ወቅት በፍጥነት እየተዛመተና በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያሰከተለ ባለው የኮሮና ወረርሽኝ ተዕዕኖ ምክንያት በዓሉ እንደወትሮው በአደባባይ በመሰባሰብ እንደማይከበርም ገልጸዋል።

ሆኖም በዓሉ ባህላዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ዘንድሮ ሁሉም የብሄሩ ተወላጅ በየቤቱ ሆኖ የሚያከብረው መሆኑን አመላክተዋል።

ህብረተሰቡ የዘንድሮውን ፊቼ ጫምባላላ በአልን ሲያከብር እራሱን ከኮሮና ወረርሽኝ በመከላከል ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተለይ ከተጣላው ጋር ይቅር በመባባልና ከመዋደድ ባሻገር እርስ በእርስ በመደጋገፍ እንዲሆንም አቶ ደስታ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የዘንድሮው የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል ከንክኪ በራቀ መልክ ሚያዝያ 29 እና 30 እንደሚከበርም ጨምረው ገልፀዋል። #ENA

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

#Update

የኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስከሬን ባህርዳር ገባ።

በድንገተኛ ህመም ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀው የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስክሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ተልኮ እንደነበር ይታወሳል።

በአሁኑ ሰዓት ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር አለም አቀፍ ኤርፖርት አየገባ ይገኛል።

በስፍራው ፦

- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር
- የጠ /ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
- ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች
- አዲሱ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ
- ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች መገኘታቸውን ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

የአውሮፓ ህብረት ለምንድነው ታዛቢ አልክም ያለው ?

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በትላንት መግለጫቸው :

#Ethiopia : የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚፃረሩ ፣ የኢትዮጵያን ነፃነት የሚዳፈሩ፣ የኢትዮጵያን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው የጠየቋቸው ጥያቄዎች።

አንደኛ VSAT የተባለ ከኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ውጪ ይዤ ካልገባሁ የሚል ነው፤ ይሄ 6ኛ ምርጫ ነው ከዚህ በፊት በተደረጉ ምርጫዎች እንዲህ አይነት ጥያቄ ከታዛቢዎች ቀርቦ አያውቅም።

አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የምርጫ ታዛቢዎች የሚሄዱባቸው ቦታዎች በሙሉ በናሽናል ቴሌኮሚኒኬሽን ሲስተም ተደራሽ ናቸው ፤ እሱን መጠቀም ይችላሉ።

ከዚህ ውጪ የኛ የቴሌኮሚኒኬሽን ሲስተም ቴክኒካሊ የማይቆጣጠረውን መሳሪያ ይዤ ልግባ ማለት ላስተዳደርህ ማለት ነው ሌላ ምንም ጥያቄ የለውም፤ለምን እንደሆነ ጥቅሙም አይታወቅም።

ለምርጫ መታዘብ ከሆነ ደህንነት አለ፤ተደራሽነት፣ ቴሌኮሚኒኬሽን ይኖራል ኑና እዩ ተብሏል ስለዚህ VSAT የሚባል የራሱን ጭኖት የሚመጣው ነገር አለ እሱን ጭኜ ካልመጣሁ የሚል ነው አንደኛው።

ሁለተኛ በየትኛውም ሀገር የምርጫ ህግ ከዚህ በፊት በእኛም ሀገር ሌላም ሀገር፥ በፍፁም በነሱ ሀገር ጭራሽ የማያስቡትን የምርጫን ውጤት መግለጫ የሚሰጠው የምርጫ ኮሚሽን ነው፤ የምርጫ ኮሚሽን መግለጫ ከመስጠቱ በፊት እኔ መግለጫ ሰጣለሁ ነው ያለው።

ይሄን አትችልም፤ ሲጀመር ምርጫችንን የሚያረጋግጥልን/የሚመሰክርልን በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፣ ቀጥሎ የኢትዮጵያ ምርጫ ኮሚሽን ነው ፤ ገለልተኛ ተብሎ ነው የተቋቋመው። እኔ ያልፈቀድኩት ምርጫ አይሆንም ነው የሚለው።

በፊትም እመጣለሁ ብሎ የጠየቀው እሱ፤ ቡድን አደራጅቻለሁ ያለው እሱ አሁን በመጨረሻ በዚህ በዛም አርጎ እነዚህን ሁለት ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ነው አልመጣም ያለው።"

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

ለትግራይ ጊዜው ያለፈበት ዘይት እና ዱቄት ተልኳል ?

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው መቐለ "ማይወይኒ" መጠለያ የሚገኙ ዜጎች ከቀናት በፊት የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት የስንዴ ዱቄትና የመጠቀሚያ ጊዜ የሚያልፍበት ቀን የታተመበት አጠራጣሪ ዘይት 'ቀይ መስቀል' አቅርቧል በሚል እንደማይጠቀሙ ገልፀው ነበር።

የቀይ መስቀል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን አሊ ፥ በመቐለም ሆነ በሌላ የትኛውም አካባቢ የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት ምግብ እንደላቀርቡ እና እንደማያቀርቡ ገልፀዋል።

የጥርጣሬው መነሻ የሀገሪቱ ስንዴ አምራች ኩባንያዎች የመጠቀሚያ ጊዜ የሚየልፍበትን ጊዜ ማሸጊያው ላይ የሚያትም ዘመናዊ አሰራር ስለሌላቸው መሆኑን አስረድተዋል።

ቀይ መስቀል ያቀረበው ስንዴ እና ዘይት የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት አይደለም ብለዋል።

ዶ/ር ሰለሞን ፦

"የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን በአ/አ እና መቐለ ባለው ተረጋግጧል። እነዚህ ምልክቶች በወረቀት ተለጥፈው ነው የሚሄዱት እነዚህ ምልክቶች የሚያሳስቱ መስሏቸው ስለተጠራጠሩ አንወስድም ፤ ይሄ ተለጥፎ ነው የመጣው፤ ቀኑም ልክ አይደልም ብለዋል።

የእኛ ሀገር ዱቄት ይሄን ሁሉ መንገድ አጓጉዘን፤ ዱቄቶቹ ከቃጫ የሚሰሩ ናቸው ከማሌዢያ ወይም ከፊሊፒንስ የሚመጡ አይደለም ፤ እነዚህን ሲያዩ አንዳንድ ተፈናቃይ ወገኖቻችን እነዚህን ነገሮች ተጠራጥረዋል።

መጠራጠራቸውን ትክክል ነው ፤ እነዚህ ነገሮች ይታዩ ፤ ይፈተሹ ተባለ ፤ ናሙናው ተወስዶ ታዩ ዱቄቱ በሙሉ ንፁህ ነው ፤ ለምግብነት መዋል ይችላል የሚል የፅሁፍ ማረገገጫ ነው ያገኘነው።

ዘይቶቹ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚያገለግሉ ዘይቶች ናቸው። ነገር ግን ምርመራ ሲደረግ የአዮዲን መጠናቸውን አነስተኛ ሆነው ነው የተገኘው"

ያንብቡ : telegra.ph/ERCS-05-05 [ቪኦኤ]

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማደናቀፍ በህቡዕ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖችን እኩይ ሴራ ማክሸፉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ
*********

በተለያዩ የውጭ ሀገራት በሚኖሩ አንድ አንድ ጽንፈኛ የዳያስፖራ አባላት የፋይናንስ፣የሃሳብ የሎጀስቲክስ ድጋፎችን በሀገር ውስጥ የአመጽና የግጭት ተልዕኮ ሰጥተው እንዲፈፅሙ በህቡዕ ላደራጇቸው አካላት ስምሪት ሰጥተው ሁከትና ግርግር በመፍጠር 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በማደናቀፍ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በእነዚህ በህቡዕ በተደራጁ የአመጽና የግጭት ቡድኖች ላይ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ክትትልም አደረጃጀታቸው፣ አመራሮቹ፣ ለጥፋት ተልዕኮው የተዘጋጁ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች፣ የተለያዩ ቁሶች፣ የገንዘብ ድጋፍና ዝውውር የተደረገባቸው ማስረጃዎች፤ተልዕኳቸውን የተመለከቱ የተለያዩ መረጃዎችና ማስረጃዎች ተጠናቅረው እርምጃ አየተወሰደ እንደሚገኝም መግለጫው አመልክቷል፡፡
በሀገር ውስጥና በውጭ በህቡዕ የተደራጁት ቡድኖቹ ሀገራዊ ምርጫውን ለማደናቀፍ ያወጡትን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ከአንድ አንድ የመንግሥት የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅር አባላትና አመራሮች ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት በመፍጠር ኢላማ የተደረጉ ቁልፍ አመራሮችን ለይቶ በመግደል ሀገራዊ ትርምስ ለመፍጠር የሚያስችል ሴራ በመጠንሰስ በድብቅ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን የጋራ ግብረ ሃይሉ በመግለጫው አብራርቷል ፡፡ በዘረጉት የግንኙነት መረብም አመጽና ሁከት በመፍጠር ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ እንዲደናቀፍና በሂደትም የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት እቅድ ይዘው ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን አመልክቷል።
እንደ መግለጫው ‹‹ስለ አዲስ አበባ ዝም አንልም›› በሚል በውጭና በሀገር

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

#Tigray

የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን የትግራይ ሪፖርት :

- በከፍተኛ ሁኔታ በምግብ እጥረት የተጎዱ ታዳጊዎችን ማግኘቱን ገልጿል።

- ገጠራማ አካባቢ በሚገኙ ክልኒኮች ክትትል ከተደረገላቸው ሕጻናት መካከል ሶስት እጅ የሚሆኑት በምግብ እጥረት ተጎድተዋል።

- የእለት እርዳታ ከዋና ከተማዎች በዘለለ ወደ ገጠሪቱ የትግራይ ክፍል የሚደርሰው በአነስተኛ መጠን ነው።

- አንዳንድ ቤተሰቦች በቀን አንዴ ይመገባሉ ፤ በብዛት ዳቦ ብቻ ነው የሚበሉት።

- የዝናቡ ወቅት እየደረሰ ሲመጣ የሚካሄደው ጦርነት ገበሬዎችን ወደ ማሳቸው ከመሄድ በመከልከል ሁኔታው እየከፋ ሊመጣ ይችላል ሲል ገምቷል።

- የሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከቦታ ቦታ ቢለያይም ባለፉት ወራቶች አጣዳፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በትግራይ እየጨመረ መጥቷል። ብዙ ቤተሰቦች የሚገኙበት የምግብ ጥራት እና ብዛት መቀነሱ ብዙዎች በቀን አንድ ጊዜ ብቻ መመገባቸውን በምክንያትነት ቀርቧል።

- የሰብአዊ ዕርዳታን ለማሳደግ እና ተደራሽነቱን ለማስፋፋት የሚጠይቅ አስቸኳይ ፍላጎት አለ።

MSF አሁን ላይ ምን እየሰራ ነው ?

ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን በአሁኑ ወቅት በዓዲግራት ፣ በኣክሱም ፣ በዓድዋ ፣ አቢ አዲ፣ ሽረ ፣ ሸራሮ ፣ ሁመራ እና ዳንሻ ከተሞች የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ከ2021 መጀመሪያ ጀምሮ የተንቀሳቃሽ ቡድኖቹን እንቅስቃሴ ወደ ገጠር ከተሞች እና ተራራማ አካባቢዎች እያስፋፋ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

አሶሳ ከቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ተቆፍሮ የወጣው ተተኳሽ ጥይት ጉዳይ ፦

በአሶሳ መንበረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ካቴዴራል ግቢ ውስጥ ከ35 ዓመታት በላይ ተቀብሮ የኖረ ከ624 በላይ የዙ 23 ተተኳሽ ጥይት ተገኝቷል።

ከ35 ዓመት በላይ ተቀብሮ የኖረ ጥይት በልማት ስራ ቁፋሮ ላይ ነው የተገኘው።

• የአሶሳ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መልዓከ ጸሀይ ቆሞስ አባ ዘካርያስ ጸጋው ይህን ብለዋል ፦

"አካባቢው ከዘመነ ደርግ በፊትም ሆነ በኋላ የጦር ሰፈር ነበር። የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ማከማቻ ቦታም ነበር። ከሚመለከተዉ የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ቦታዉ ለቤተ-ክርስቲያን አምልኮት ተሰጥቷል።

ቤተክርስቲያኗ ቦታዉን አስከብራ በመቆየቷ ከ35 አመት በላይ ተቀብሮ የቆየ ጥይት ነው።

ጥይቱ በዚህ መንገድ የተገኘ መሆኑን ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል"

• የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮ/ር ቡሽራ አልቀሪብ ስለጉዳዩ ሲያብራሩ ይህን ብለዋል ፦

"ቦታዉ ለቤተክርስቲያን ልማት ከመዋሉ በፊት የደርግ 47ኛ ክፍለ ጦር የነበረበት ቦታ ነው፤ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ማከማቻ ሰፈር ነበር።

ዛሬ የተገኘዉ የዙ 23 ተተኳሽ ጥይት በቁጥር 624 በላይ የሚሆንና ከ35 ዓመት በላይ በመሬት ዉስጥ ተቀብሮ የተገኘ የበሰበሰ እና አገልግሎትም የማይሰጥ ነው።

አካባቢዉ የቀድሞ ጦር ሰፈር መሆኑን በመረዳት ህብረተሰቡ እዉነቱን ሊረዳ ይገባል ፤ ሁኔታውንም በሌላ መንገድ ሊወስደው አይገባም።"

መረጃው የአሶሳ ከተማ አስተዳድር ኮሙዩኒኬሽን ነው።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

የአሜሪካ ሴናተሮች ከሱዳን መሪዎች ጋር ተወያዩ።

በአሜሪካው ሰኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባል በሆኑት በሴናተር ክሪስ ኩን የተመራ ልዑክ ከሱዳን ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ እና ከአብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ትላንት በካርቱም ወይይት አድርገዋል።

አሜሪካ የሱዳንን የሽግግር መንግስት እንደምትደግፍ ሴናተር ክሪስ ኩን ማረጋገጣቸውን ሱናን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ዘግቧል።

የኮንግረስ ልዑክን በመምራት በካርቱም ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ሴናተር ክሪስ ኩንስ ፥ ጉብኝታቸው የአሜሪካ እና የሱዳን ወዳጅነት የሚያረጋግጥ እንደሆነ ተገልጿል።

ሴናተር ክሪስ ኩንስ ከሱዳን የፋይናንስና ምጣኔ ሀብት ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ታውቋል።

ከውይይቱ በኃላ ሴናተር ኩንስ በሰጡት አስተያየት ፥ አሜሪካ እሰካሁን 700 ሚልዮን ዶላር ለሱዳን ድጋፍ እንዳደረገች በመግለፅ በቀጣይ ለሱዳናውያንን ሁለንተናዊ መረጋጋት፣ ደህንነትና ሰላም የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

ሴናተር ክሪስ ቫን ሆለን በበኩላቸው በሱዳን ያለውን የሽግግር በማድነቅ “ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ ፣ የሰላም እና የፍትህ በምታደርገው ጉዞ አሜሪካ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ናት” ብለዋል።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

የኮቪድ-19 ስርጭትን በተመለከተ ሀገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ ነው።

የጤና ሚኒስቴር ፣ የኢትዮጵየ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ፣ የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (CDC) እና የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመተባበር በሃገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በከተማ እና በገጠር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭት ሁኔታ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ጥናት ሊጀመር መሆኑን በዛሬው እለት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መገለጫ አስታውቀዋል።

የጥናቱ ዋና አላማ በሀገር አቀፍ ደረጃ ፣ በክልሎችና በከተማ መስተዳድሮች የበሽታው ስርጭት በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ምን እንደሚመስል ጥናት በማካሄድ በሽታውን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራ ላይ መፍትሄ ለማስቀመጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via EPHI

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

💥💥💥💥💥💥💥

📚THINK & GROW RICH/ አስተውሎ መበልፀግ

4ኛው ምስጢር

ልዩ እውቀት/ SPECIALIZED KNOWLEDGE

💥💥💥💥💥💥💥

🎯እውቀት ሀይል አደለም። ሀይል የመሆን ብቃት ግን አለው።

🎯 እውቀት ሀይል የሚሆነው ምን ምን ማድረግ ስንችል ነው?

👇👇👇👇👇
he_secret_p34


👂👂👂👂👇👇👇👇

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

ለሞት ሽረት ፍልሚያ አቢጃን የደረሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጀመሪያ ልምምድን ሰርቷል።

ዋልያዎቹ በቀጣይ ማክሰኞ ከአይቮሪኮስት ጋር አቻ መውጣት ወይም የማዳጋስካር ነጥብ መጣል እና ሽንፈት በቀጥታ ከ8 አመት በኋላ ለአፍሪካ መድረክ ያበቃቸዋል።

መልካም ዕድል ለዋልያዎቹ🇪🇹

@Bisrat_Sport_Fm Bisrat_Sport_Fm

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

🌿የመኖር ተስፋ !

ማዳን ባትችል ቢያንስ ለህመም መንስኤ አትሁን!!
ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል።
ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ
እንዲል ይደረጋል። አልጋው የሚገኘው
በክፍሉ ብቸኛ ከሆነው መስኮት አጠገብ ነው። ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ
በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው ፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት
እንደሚያሳልፉ... ወዘተ አውርተዋል።
ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ
እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል።
".....በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል፣... በሀይቁ ላይ
ዳኪዬዎች ይዋኛሉ...... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች
በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ... ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው
አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ፣... ከሀይቁ ባሻገር ውብ
የሆነ ከተማ ይታየኛል....." በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ
ይተርክለታል። በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።
አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት
አጠገብ ያለው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች።
ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች
ጠራች። ያ ብቻውን የቀረው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ
ሊወስዱለት ይችሉ እንደሆነ ጠየቀ። ወሰዱለት። በመስኮት ለማየት
በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር
ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ!!! "ምን
ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ። "ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ
መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት። "ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል
አይነስውር ነበር አለችው።" ልብ የሚነካ ነገር.... ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።
ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር
ፈጥሮ የሚያወራው።
==========================
አንዳንድ ሠዎች እንዲህ ናቸው እነሡ እየሞቱ የሠውን የህይወት ብርሀን
ያለመልማሉ ::
አንተስ እስከመቼ የራስህ ብርሀን እያለህ የሠው ጭላንጭል ያስቀናሀል ፡፡
እስኪ ለ 1 ደቂቃ ዝም ብለህ አስብ መልካምነት እኮ አያስከፍልም ፡፡
የሠው ህይወት ማዳን ባትችል እንኳን ቢያንስ ለሠው ተስፋ ስጥ ይሄም
የመልካምነት ኢትዮጲያዊነት አንዱ ገፅ ነው ፡
👇👇👇👇👇👇
The_secret_power
👇👇👇
@ETHOPOEIA @ETHOPOEIA

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

FOR YOUR GENERAL INFORMATION *Top 10 Sites for your career:*

1. LinkedIN
2. Indeed
3. Naukri
4. Monster
5. JobBait
6. Careercloud
7. Dice
8. CareerBuilder
9. Jibberjobber
10. Glassdoor

*Top 10 Tech Skills in demand:*

1. Machine Learning
2. Mobile Development
3. SEO/SEM Marketing
4. Data Visualization
5. Data Engineering
6. UI/UX Design
7. Cyber-security
8. Cloud Computing/AWS
9. Blockchain
10. IOT

*Top 10 Sites for Free Online Education:*

1. Coursera
2. edX
3. Khan Academy
4. Udemy
5. iTunesU Free Courses
6. MIT OpenCourseWare
7. Stanford Online
8. Codecademy
9. Open Culture Online Courses

*Top 10 Sites to learn Excel for free:*

1. Microsoft Excel Help Center
2. Excel Exposure
3. Chandoo
4. Excel Central
5. Contextures
6. Excel Hero
7. Mr. Excel
8. Improve Your Excel
9. Excel Easy
10. Excel Jet

*Top 10 Sites to review your resume for free:*

1. Zety Resume Builder
2. Resumonk
3. Resume dot com
4. VisualCV
5. Cvmaker
6. ResumUP
7. Resume Genius
8. Resumebuilder
9. Resume Baking
10. Enhancv

*Top 10 Sites for Interview Preparation:*

1. Ambitionbox
2. AceTheInterview
3. Geeksforgeeks
4. Leetcode
5. Gainlo
6. Careercup
7. Codercareer
8. InterviewUp
9. InterviewBest
10. Indiabix

*Top 3 Sites for Pharma Jobs:*
1. Daily Pharma Jobs
2. Pharma Wisdom
3. Pharma Job Alert
Source logisticsethiopia

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

አስራ ሦስት የሲሚንቶ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

የሲሚንቶ ምርትን በመደበቅ፣ በማከማቸት፣ አየር በአየር እና ከንግድ አድራሻ ውጪ በመሸጥ ላይ የነበሩ 13 የሲሚንቶ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ነጋዴዎቹ ምርቱን በመደበቅ፣ በማከማቸት፣ አየር በአየር በመሸጥ፣ ከንግድ አድራሻ ውጪ በመሸጥ፣ እንዲያከፋፍሉ ወይም እንዲሸጡ ከተፈቀደላቸው ውጪ ለሌላ አካል በመሸጥ የተለያዩ አሻጥሮችን ሲሰሩ በመገኘታቸው ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል፡፡

በቀጣይ ከፋብሪካ የሲሚንቶ ምርት የሚረከቡ ጅምላና ቸርቻሪ ነጋዴዎች በተፈቀደው አሠራር ብቻ በትክክለኛው ዋጋ በሽያጭ እንዲያስተላልፉ እና የሥርጭትና ሽያጭን በተመለከተ ከፋብሪካ ከማንሳታቸው በፊት ለቢሮው ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው ቢሮው አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም በሲሚንቶ ችርቻሮ ንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ነጋዴዎች በክፍለ ከተማ ከተመደቡ ጅምላ ነጋዴዎች ምርቱን በመረካከብ በተመጣጣኝ ዋጋ በደረሰኝ ለተጠቃሚዎች እንዲሸጡ ስለተረከቡት ምርትና ሽያጭ ከጅምላ ነጋዴዎች ከመረከባቸው በፊት ለክፍለከተማቸው ንግድ ጽ/ቤት ሪፖርት ማድረግ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

ይህን የሲሚንቶ ስርጭት መመሪያ እና ሕግን ተላልፈው በሚገኙ ማንኛውም በሲሚንቶ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 መሠረት እርምጃ እንደሚወስድ ቢሮው አሳስቧል፡፡

ነዋሪዎችም በሲሚንቶ ምርት ላይ ህገ-ወጥ ተግባር የሚፈጽሙ አካላትን ለመከላከል 8588 ነፃ የስልክ ቁጥር ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ቢሮው ጥሪውን አቅርቧል፡፡

#liyu_merja

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

#Egypt

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ከግብጹ ፕሬዝዳንት ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ መነጋገራቸው ተሰምቷል።

ማክሰኞ ግብጽ የገቡት ልዑኩ ጄፍሪ ፌልትማን ትናንት ነው የግብጹን ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲን ያነጋገሩት።

አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አሜሪካ በግድቡ ምክንያት ለተነሳው ውዝግብ መፍትሄ ለማግኘት ውጤታማ ሚና እንድትጫወት ጠይቀዋል ተብሏል።

ግድቡ የሃገራቸው ህልውና ጉዳይ መሆኑን ተናግረው ግብጽ የውሃ ፍላጎቷን የሚጎዳን ማንንም እንደማትቀበል እንዳስታወቁ ተሰምቷል።

በተጨማሪ ፌልትማን የግብጹን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያነጋገሩ ሲሆን ፥ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ጥንቃቄ ለሚፈልገው ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ለመሻት ከልብ እንዳሰበበት ተናግረዋል።

ፌልትማን ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳንን በቀጣይ እንደሚጎበኙ ዶቼ ቨለ አሶሼትድ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ መግለጫ ፦

- መንግስት ከዚህ በኋላ ከትግራይ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ውስጥ በ14 በመቶው ብቻ ድጋፍ ያደርጋል ፤ ቀሪው 86 በመቶው የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ተቋማት ይሸፈናል። ከዚህ ቀደም 70% ሲሸፈን የነበረው በኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ነበር።

- ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው ለመመለስ በ3 መንገድ እየተሰራ ነው።

ሶስቱ መንገዶች ፦

• ሰላም በተረጋገጠባቸው ቦታዎች ላይ ህዝቡን በማወያየት መመለስ፣
• ሙሉ ሰላም ያልተረጋገጠባቸው ቦታዎች ላይ ስነልቦናዊ ችግሮችን ለማቅለል ወደዘመድ እንዲሄዱ መርዳት
• ሰላም ካልተረጋገጠባቸው ቦታዎች ለተፈናቀሉት ደግሞ ጊዜያዊ መጠለያን ማዘጋጀት የሚሉ ናቸው።

- ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ተጨማሪ 4 ተቋማት ፈቃድ አግኝተዋል፡፡

- ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረግ አልተቻለም በሚል የሚቀርቡ ክሶችና ወቀሳዎች ከአሁን በኋላ ተቀባይነት የላቸውም።

- እርዳታዎችን ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ተከፍተዋል።

- “በረሀብ የሞተ ሰው የለም”፤ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ተቋማት “እርዳታ ለማግኘት ሲሉ ጉዳዩን እያስጮሁት” ነው። “ልክ እንደ የመን እና ሶሪያ እርዳታ ለማግኘት ጉዳዩን እየተደረገ ያለ ሩጫ ነው።

በሌላ በኩል ፦

በሀገሪቱ ያለው የተፈናቃይ ብዛት 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሲሆን 40 በመቶ ያህሉን ለመመለስ መታሰቡን ተጠቁሟል።

አጣየ በተመለከተ፦ አማራ ክልል ውስጥ ለ50ሺ ተረጂዎች ድጋፍ እንዲደረግ ችግሩ በተፈጠረበት ወቅት ወዲያውኑ መጠየቁን ተከትሎ ድጋፉ በማግስቱ (ቅዳሜ ተጠይቆ እሁድ) እንዲደርስ ተደርጓል።

ምንጭ፦ አል ዓይን

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያዩ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ እንደገለጸው ምክትል ጠቅላይ
ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በፕሪቶሪያ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያይተዋል።በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ተወያይተዋል።በውይይቱም በኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሠሩ ተገልጿል።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ተወሰነ።

#Ethiopia : የአዲስ አበባ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች በከተማዋ አስተዳደር ስር ባሉ የጤና ተቋማት በሙሉ ነፃ ህክምና እንዲሰጥ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ 80ኛውን የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ከነፃ ህክምና አገልግሎቱም በተጨማሪ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የጠየቀው መሬት እንዲሰጠው መወሰኑኑን ወ/ሮ አዳነች መግለፃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

#Ethiopia😷

ባለፉት 24 ሰዓት 23 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 5,733 የላብራቶሪ ምርመራ 785 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 729 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 260,139 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,795 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 203,408 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 777 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,215,934 ደርሷል።

#Purpose

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

ዶ/ር አብርሃም በላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ !

ዶክተር አብርሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ዶክተር አብርሃም ላለፉት 6 ወራት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩትን ዶ/ር ሙሉ ነጋን በመተካት ነው በዋና ስራ አስፈጻሚነት የተሾሙት።

ዶ/ር ሙሉ ለምን ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ የተገለፀ ነገር የለም።

ዶ/ር አብርሃም የኢኖቬሽን እና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትም ናቸው።

የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሔር "መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልዎት እመኛለሁኝ" ሲሉ ለዶ/ር አብርሃም መልካም ምኞታቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።

ዶክተር ሙሉ ነጋ ባሳለፍነው ወርሃ ህዳር መባቻ ነበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተሾሙት፡፡

ሹመቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት በክልሉ የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ ባጸደቀው ደንብ መሠረት የተሰጠ ነበር።

ሆኖም እስካሁን ድረስ የዶክተር አብርሃም ሹመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለመሰጠቱ የተገለፀ ነገር የለም፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

ወጣት ጉሌድ በሰራው መልካምና በጎ ተግባር ለሽልማት በቃ !

ከ4 ወር በፊት በጅግጅጋ ከተማ በሚያሽከረክረው ባጃጅ ውስጥ 300 ሺ ብር ጥለው ለወረዱ እናት በታማኝነት ብሩን የመለሰው ወጣት ጉሌድ በሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እውቅና ተሰጥቶ ነበር።

በወቅቱ ለመልካም አርአያነቱ ሽልማት አንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት እንደነበር አይዘነጋም።

በተገባው ቃል መሰረት ለወጣቱ የክልሉ መንግስት በዛሬው እለት በጅግጅጋ ከተማ በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፍ ሙሁመድ በኩል ዘመናዊ የህዝብ ማመላለሻ ቶዮታ መኪና መረከቡን የሱማሊ ክልል ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ አሳውቋል።

ብሩን የጣሉት እናት ገንዘቡን ልጃቸውን ለማሳከም ብለው ከብቶችን ሽጠው ያመጡት እንደነበር በግዜው ሲገለፅ እንደነበር አይዘነጋም።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

የኮቪድ-19 አጫጭር መረጃዎች ፦

[ በPurpose የቀረበ ]

- ትላንት በዓለም አቀፍ ደረጃ 776,696 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 13,667 ሰዎች ሞተዋል።

- ህንድ ትላንት 382,691 አዲስ ታማሚዎች ሪፖርት አድርጋለች፤ በ24 ሰዓት 3,786 ሰዎች ሞተዋል።

- በብራዚል በ24 ሰዓታት ውስጥ 3,786 ሰዎች ሲሞቱ ፤ 69,378 አዲስ ታማሚዎችን ሪፖርት አድርጋለች።

- በ24 ሰዓት በርካታ ሰዎችን ከሞቱባቸው ሀገራት መካከል ፦ አሜሪካ 853 ፣ አርጀንቲና 410 ፣ ኢራን 344 ፣ ጀርመን 365 ፣ ፔሩ 299 ፣ ራሽያ 337፣ ፈረንሳይ 247 ፣ ጣልያን 305 ፣ ቱርክ 336 ፣ ኮሎምቢያ 463 ይጠቀሳሉ።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች 154,998,238 ደርሰዋል፤ ከነዚህ መካከል 3,241,462 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል 132,485,040 አገግመዋል።

- በአፍሪካ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 4,627,444 የደረሰ ሲሆን ከፍተኛ የኮቪድ-19 ኬዝ በማስመዝገብ ደቡብ አፍሪካ በ1,586,148 ቀዳሚ ናት፣ ሞሮኮ በ512,285፣ ቱኒዝያ በ314,152፣ ኢትዮጵያ በ259,354 ይከተላሉ።

- ከፍተኛ የሞት መጠን የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፥ ደቡብ አፍሪካ 54,511 ፣ ግብፅ 13,591 ፣ ቱኒዝያ 11,016፣ ሞሮኮ 9,038 ናቸው።

- አሜሪካ እድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ላሉት ታዳጊዎች የኮቪድ -19 ክትባት ልትሰጥ ነው። ታዳጊዎች ክትባቱ በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሳቸው ይደረጋል ተብሏል። የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር 70 % ለሚሆኑ አዋቂ አሜሪካዊው እስከ ሰኔ 27 ድረስ ክትባት ለመስጠት አቅጃለሁ ማለቱን ቢቢሲ አስነብቧል።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

የቤልጂየም ድጋፍ : በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የ4 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጋለች።

ቤልጅየም በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ [ICRC] በኩል ነው በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች 4 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ያደረገችው።

ቤልጂየም ከሰብዓዊ እርዳታ በተጨማሪ ትግራይ ውስጥ ስለተፈፀሙ ወንጀሎች ገለልተኛ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አሳውቃለች።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

" #ፍርሀትህን_ለማሸነፍ_የምትፈራውን_ነገር_ደጋግመህ_አድርገው "

አንድ ፈረስ አንድ ቀን ከአሳዳሪው ጋር ሲጎዝ መን ገድ ጠርዝ ላይ ከተቀበረ ጉቶ ስር አንድ እባብ ሲመጣ ተመልክቶ በርግጎ ጮኸ ። ከዛን ቀን
ወዲህ እዛች ቦታ ሲደርስ ይበረግጋል፣ ይጮሀል። የፈረሱ ባለቤት ቢቸግረው ጉቶዉን ፈንቅሎ አነደደው። መሬቱንም በሚገባ ደለደለው ይሁንና ይህ ምንም ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም።የፈረሱ ድርጊት ለአመታት ዘለቀ ። ፈረሱ የሚጮኸውና የሚበረግገው ይህን በአእምሮው የተቀረፀ ነገር ነገር እዛች ቦታ ሲደርስ ስለሚያስታውስ ነው።

እናንተስ እንደ ፈረሱ ፍርሃትና ስጋት ወደፊት እንዳ ትራመዱ አስሯችኃል?ፍርሀት በአዕምሮአችሁ ውስጥ ሊኖር የሚችል ሀሳብ ነው። ይህ ሃሳብ በጠንካራ እምነት፣በስኬትና በድል አድራጊነት ሃሳቦች በመተካት ከስሩ ፈንቅላቹ ልታወጡት ትችላላችሁ። ሁል ጊዜም በራሳችን ላይ እምነትን ካሳደርን ፣የማናሸንፍበትና ደስተኞች የማንሆንበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም። እናም ደስታህን በራስህ ፈልገው።
🕯ደስታህን ከሻማ በላይ አድርገው!
👇👇👇👇👇👇
The_secret_power
The_secret_power
እርሶ በአመለካከት መቀየር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ያግኙን፡ ያማክሩን ብዙ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ።👇👇👇

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

ሜሲ እና ሮናልዶ ከ2009/10 እስከ 2017/18


📊ላሊጋ የነበራቸው ቁጥር

ሜሲ: ✅ 309 ጨዋታ አደረገ
✅ 329 ጎል አስቆጠረ
✅ በየጨዋታው 1.06 ጎል ያስቆጥራል

ሮናልዶ: ✅ 292 ጨዋታ አደረገ
✅ 311 ጎል አስቆጠረ
✅ በየጨዋታው 1.07 ጎል ያስቆጥራል

📊በቻምፒየንስ ሊግ የነበራቸው ቁጥር

ሜሲ: ✅ 92 ጨዋታ አደረገ
✅ 83 ጎል አስቆጠረ
✅ በየጨዋታው 0.9 ጎል ያስቆጥራል

ሮናልዶ: ✅ 101 ጨዋታ አደረገ
✅ 105 ጎል አስቆጠረ
✅ በየጨዋታው 1.04 ጎል ያስቆጥራል

📊በአለም ክለቦች ጨዋታ፣ ኮፓ ድሬ እና ሱፐር ካፕ፣ ስፓንሽ ሱፐር ካፕ


ሜሲ: ✅ 75 ጨዋታ አደረገ
✅ 60 ጎል አስቆጠረ
✅ በየጨዋታው 0.8 ጎል ያስቆጥራል

ሮናልዶ: ✅ 45 ጨዋታ አደረገ
✅ 34 ጎል አስቆጠረ
✅ በየጨዋታው 0.75 ጎል ያስቆጥራል


📊በሁሉም ውድድር አጠቃላይ ሲታይ

ሜሲ: ✅ 476 ጨዋታ አደረገ
✅ 472 ጎል አስቆጠረ
✅ በየጨዋታው 0.99 ጎል ያስቆጥራል

ሮናልዶ: ✅ 438 ጨዋታ አደረገ
✅ 450 ጎል አስቆጠረ
✅ በየጨዋታው 1.027 ጎል ያስቆጥራል


ላሊጋ ግን የጎል ሊግ ስለሆነ ነው ወይስ ሁለቱም አሪፍ የሆኑበት ግዜ ስለነበረ 😁


@Bisrat_sport_fm

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

ከትንሽነት አመለካከት ውጣ!

ከትንሽ አመለካከት መውጣት ማለት ስለማንነቴ ከሌሎች ምንጮች የምሰማውን ጤና ቢስ መልእክት ችላ በማለት ትክክለኛውንና ሚዛናዊውን ብቻ ወደ ማመን መሸጋገር ማለት ነው፡፡

ከትንሽነት አመለካከት የመውጣትን ሚዛናዊ ምልከታ ካላዳበርን እንኳን ጎድሎብን፣ አብዛኛው ነገር ሙሉ ሆኖልን ሳለ እንኳን፣ አንዲትን የጎደለች ነገር በመጠቆም ትንሽነትን የሚሰብከን ዓለም ውስጥ እንኖራለን፡፡

ዓለም በትልቁና በትንሹ፣ በአዋቂውና በማያውቀው፣ በሃብታሙና በድሃው … ከፋፍላና እኛንም አንዱ ጋር መድባ ማስቀመጥ ትችልበታለች፡፡ እኛም ብንሆን ሚዛናዊ አስተሳሰብ ካላዳበርን ዝም ብለን ይህንን ሁኔታ ልናስተናግድ እንችላለን፡፡

በአለማችን ላይ ምንም ነገር ላይገድባቸው ቆርጠው በመነሳት ከትንሽነት አመለካከት የወጡ ሰዎች በርካታ ናቸው፡፡ አንተም እንደነሱ ይህንን ለመለማመድ ከፈለክ ማስታወስ የሚኖርብህ እውነታዎች አሉ፡፡

1. ሰዎች አይገድቡህ
ሰዎች ስለአንተ ምንም ነገር የማሰብብ ሆነ አንተን መናቅም መብታቸው ነው፡፡ ሆኖም አንተ እስካልፈቀድክላቸው ድረስ አመለካከታቸው ማንነትህን ሊቀናንሰው አይችልም፡፡ የአንተን ትልቅነትና ትንሽነት የሚወስነው የራስህው አመለካከትና ማንነትህን የመቀበልህና ያለመቀበልህን ሁኔታ መሆኑን አትዘንጋ፡፡

@ETHOPOEIA
@ETHOPOEIA
2. ራስህን አትገድበው
አንዳንድ ሰዎች ሌሎች የሚሰጧቸውን የወረደ ስምና ምደባ ስፍራ ያለመቀበል ችግር የለባቸውም፡፡ ሆኖም ግን በራሳቸው ላይ ይህ ነው የማይባል የወረደ አመለካከት አላቸው፡፡ ትንሽ እንደሆኑ፣ በአካባቢያቸው ካለው ሰውና ሁኔታ ጋር የማይመጥን ማንነት እንዳላቸውና ገና ብዙ እንደሚቀራቸው ካለማቋረጥ ለራሳቸው ይሰብኩታል፡፡ አንተ ግን ራስህን እስካልገደበክ ድረስ ምንም ነገር ሊገድብህ እንደማይችል እወቅ፡፡
3. ራስህን በሁኔታህ መነጽር አትመልከተው👇
@ETHOPOEIA

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

የሴናተር ክሪስ ኩንስ የኢትዮጵያ ቆይታ ማብራሪያ ፦

By : Al Ain News Agency

ከአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ወደ ኢትዮጵያ ተልከው ፣ በኢትዮጵያ የነበሩት ሴናተር ክሪስ ኩንስ የኢትዮጵያ ቆይታቸው ስኬታማ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ሴናተር ኩንስ ወደአሜሪካ ከተመለሱ በኋላ ከአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ላይ ፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የዓለማቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሴኔቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ በሚያሳልፈው ውሳኔ ላይ ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል ሀሳብ እንዲሰጡ በውጭ ግንኙነት ኮሚቴው እንደተፈቀደላቸው ጠቅሰው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚመለከታቸው አካላት ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጻቸው ፣ በኢትዮጵያ ግዛት የኤርትራ ወታደሮች ስለመኖራቸው በይፋ መናገራቸውን ሴናተር ኩንስ በስብሰባው ላይ በአዎንታዊነት ጠቅሰዋል፡፡

ከሱዳን ጋር ላለው የድንበር ውዝግብ ዕልባት ለማምጣት እንዲሁም የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አለመግባባት ለመፍታት የኢትዮጵያን ዝግጁነትም በአዎንታዊነት ነው ሴናተሩ ያነሱት፡፡

ይሁንና “አሁንም መፈታት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ” ያሉት ሴናተሩ እነዚህም “የተሟላ የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነት፣ ግጭት ማቆም እና ነጻ፣ ፍትሀዊ ምርጫ የማድረግ ሽግግር” መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በነዚህ ጉዳዮች ላይ ከሴኔቱ ኮሚቴ ጋር በጋራ እንደሚሰሩና የተሻለ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያላቸውን ተስፋም ገልጸዋል፡፡

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ

ኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ፅኑ ታማሚዎች 752 ደርሰዋል።

ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ አንስቶ ይህን ያህል የፅኑ ታማሚ ቁጥር አልተመዘገበም።

ባለፉት 24 ሰዓት የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉትን ከአቶ ያዕቆም ሰማን (MoH) ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሁኔታው ወደ አስከፊ ደረጃ እየተሸጋጋረ ስለሆነ በምትችሉት አቅም ሁሉ እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችን ከወረርሽኙ ጠብቁ እንላለን።

Читать полностью…

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

#AlertEthiopia😷

በኢትዮጵያ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 653 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከተደረገው 6,922 የላብራቶሪ ምርመራ 1,537 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 15 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 1,119 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 188,902 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,674 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 148,571 ሰዎች አገግመዋል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel