✍️ "የግብፅ ሪሞት ኮንትሮል በኢትዮጵያ እጅ ገብቷል!"
🔹 ሁለተኛውን ሙሊት የፀጥታው ምክር ቤትም ሆነ ማንም መከልከልና ማስቆም አይችልም።~ግብፃዊው የውሃ ሀብት ምሑር ዶክተር አባስ አል-አሸረቂ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
ኢትዮጵያ ጠል የሆኑት የካይሮ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሳይንስ ልሂቅ አባስ አል አሽራቂ ትላንት ምሽት ከግብፅ ቴሌቪዥን ጋር በስልክ በነበረው ቆይታ ከተናገሩት፦
"ስለ ግድብ ደህንነት ዋስትና በአለም ማንም ሀገር አይወስድም ። አሜሪካ ሆነች ቻይና ማንም ሀገር ።
የህዳሴው ግድብ የመፍረስ አደጋው ችግር ከሚሊዮን 1 ብቻ ነው።
የሁለተኛውን ሙሊት የፀጥታው ምክር ቤትም ሆነ ማንም መከልከልና ማስቆም አይችልም። ኢትዮጵያ ራሷ ብትፈልግም እንኳ አትችልም። የግብፅ የመንቀሳቀሻ ሪሞት ኮንትሮል አሁን በኢትዮጵያ እጅ ሆኗል"
የዕርቀ ሰላም መድረክ🕊ሸዋሮቢት ከተማ !
በአጣዬና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት የተሳተፉ ወንጀለኞችን የመለየት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ደስታ አብቼ ገለፁ።
በ2ቱ ዞኖች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የሚያስችል የዕርቀ ሰላም መድረክ በሸዋሮቢት ከተማ ተካሂዷል።
በዚሁ ጊዜ ሌተናል ጄነራል ደስታ አብቼ ፣ በሁለቱ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ተዋናይ የነበሩ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ኮማንድ ፖስቱ በቅርብ ጊዜ ወንጀለኞችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ወንጀለኞችን ለመለየት በሚሰራው ስራ ላይ ወንጀለኞችን የመደበቅና ያለማጋለጥ ፣ ምስክሮችን የማስፈራራትና የሃሰት ምስክሮችን የማቅረብ ችግሮች የምርመራ ሂደቱን እንዳዘገዬውም ሌተናል ጄነራሉ ተናግረዋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ነው።
ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከስልጣናቸው ተነሱ።
እስራኤልን ለ12 ዓመታት የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በዛሬው እለት ከስልጣናቸው ተነስተዋል።
ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከስልጣናቸው የተነሱት የሀገሪቱ ከኔስት (ፓርላማ) ጥምረት የፈጠሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመሰረቱትን መንግስትን መቀበሉን ተከትሎ ነው።
የግራ ዘመሙ የያማኒያ ፓርቲው ናፍታሊ ቤንት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስፍራውን ተረክበዋል።
ናፍታሊ ቤንት በዛሬው ዕለት ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን፣ እስከ 2023 ድረስ እስራኤልን የሚመሩ ይሆናል።
ከ2023 በሁዋላም ስልጣኑን ለያዴህ አቲድ ፓርቲ መሪው ያኢር ላፒድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስፍራውን የሚያስረክቡ ይሆናል።
ይህ ጥምር መንግስት የመሰረቱት ፓርቲዎች ስልጣን ለመጋራት በደረሱት ስምምነት መሰረት እንደሚፈጸም ተነግሯል።
ኔታንያሁ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በርካታ እስራኤላውያን አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን እየገለጹ ነው።
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
#TigrayReport!
የሚደርሱን ሪፖርቶች በምግብ እጥረት የተጎዱ የህፃናት ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ያመላክታሉ" - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ደረጃ ምደባ (Integrated Food Security Phase Classification) በቅርቡ ባወጣው ረፖርት እንደተጠቀሰው በትግራይ ክልል ያለው አሳዛኝ ሰብዓዊ ቀውስ ከፍተኛ የድንገተኛ አደጋ ስጋት ላይ መድረሱ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ዛሬ ገልጿል።
ኮሚሽኑ ከክልሉ ከሚገኙ የጤና ተቋማት ደረሱኝ ባላቸው ሪፖርቶች በምግብ እጥረት የተጎዱ የህፃናት ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ያመላክታሉ ብሏል።
ኮሚሽኑ የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት በአፋጣኝ የማረጋገጥ አስፈላጊነትን እና በአብዛኛው ተደራሽ በሆኑ አካባቢዎች ጭምር ያለው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እጥረት ለሟሟላት ተገቢ ጥረት መደረግ እንዳለበት በአፅንዎት አሳስቧል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ያደረጋቸውን ጥሪዎች አስታውሰው "ሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ መቆየት የማይችለው አስቸኳይ ጉዳይ ግን አስፈላጊውን አቅምና ሀብት ሁሉ በማሰባሰብ የሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽነት ማረጋገጥ እና ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እርዳታ ማድረግ እንደሆነ" ገልፀዋል።
ethio_mereja_news
ethiomereja_news
በታች አርማጭሆ ወረዳ ህገ-ወጥ ሽጉጥ ተያዘ።
ዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ሲሆን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ከተማ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ የታርጋ ቁጥር አማ 31398 በሆነ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) 98 (ዘጠና ስምንት) ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ተጭኖ ከአብራሀጅራ ወደ ጎንደር ሲጓጓዝ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ ነው መሆኑን ሲሉ የታች አርማጭሆ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳውቋል።
መረጃው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ ሚድያ ዋና ክፍል ነው።
#ሞጣ
ዛሬ "ሕብር እና ፍቅር ከሰባቱ ዋርካ ስር" በሚል መሪ ቃል በሞጣ ከተማ አስተዳደር እና በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አዘጋጅነት የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ፣ የአብሮነት፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት መርሃ ግብር በሞጣ ሁለገብ ስታዲየም እየተካሄድ ነው።
ከ2 ቀናት በፊት "በፍቅር እንኖራለን፤ በአንድነት እንሻገራለን” በሚል መሪ ቃል የሞጣ ከተማ ነዋሪዎች የይቅርታ መድረክ አካሂደዋል።
መረጃው የሞጣ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።
ሰሞነኛው የግብፅ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ዙሪያ :
#Djibouti
• የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ከጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ለመወያየት ዛሬ ማለዳ ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል፡፡
- የፕሬዚዳንቱ የጅቡቲ ጉብኝት በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል።
- የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ ትብብር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ታውቋል። በተለይም በፀጥታ ፣ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር የውይይቱ ዓላማ መሆኑ ተጠቁሟል።
- የግብፅና የጅቡቲ መሪዎች የጋራ በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እና ሀሳቦችን ለመለዋወጥም አቅደዋል፡፡
#Kenya
• ግብፅ እና ኬንያ በትናንትናው እለት ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
- በናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት ዓላማ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር አካል ነው።
- ግብፅ ከኬንያ ጋር ያደረገችው ወታደራዊ ስምምነት እ.ኤ.አ. በ2021 በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ጋር ያደረገችው አራተኛ ስምምነት ነው፡፡
- ከኬንያ በተጨማሪ ከሱዳን ፣ ከኡጋንዳ እን ከብሩንዲ ጋር ግብፅ ወታደራዊ ስምምነት ፈርማለች፡፡
#Sudan
• ግብፅ እና ሱዳን በትናንትናው ዕለት ለ 6 ቀናት የሚቆይ ሁለገብ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በሱዳን ጀምረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት የሚካሔደው ይህ ልምምድ ፣ የናይል ጠባቂዎች (Nile Protectors/ናይል ፕሮቴክተርስ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
#አልአይን
ምርጫ ቦርድ ለባልደራስ የሰጠው ምላሽ ምንድነው ?
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በህግ ጥላ ስር ያሉ የፓርቲው ዕጩዎች የሆኑት አባላት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 207000 ግንቦት 13 ባሳለፈው የፍርድ ውሳኔ መሰረት እንዲመዘገቡለትና ቦርዱ እስከ ግንቦት 19 ድረስ ተገቢውን ትዕዛዝ ለምርጫ ወረዳዎች አስተላልፎ እንደ ፍርዱ እንዲፈፀም ጥያቄ ማቅረቡን ምርጫ ቦርድ ገልጿል።
የዕጩዎች ምዝገባ የካቲት 30 በመጠናቀቁ እና አንዳንድ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖረውን ስፍራ የሚወስን የሎተሪ ዕጣ በመውጣትና በዚሁ መሰረት የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ህትመትም ተጠናቆ ወደ ምርጫ ጣቢያ የመላኩ ተግባር በቅርብ ጊዜ የሚጀመር በመሆኑ እንደውሳኔው ለመፈፀም ቦርዱ የሚቸገር መሆኑን ገልጿል።
"... እኛ እዚህ የመጣነው ከተፈረደብን ለመቀጣት ፤ ነጻ ከተባልን ደግሞ ለመውጣት ነው። ከዛሬ ጀምሮ በገዛ ፍቃዳችን ፍርድ ቤት አንቀርብም" - አቶ ጃዋር መሀመድ
[ በ www.ethiopiainsider.com የቀረበ ]
በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱ 24 ተከሳሾች ከዛሬ ጀምሮ ጉዳያቸውን ለመከታተል ወደ ፍ/ቤት አንቀርብም አሉ።
ውሳኔያቸውን ያሳወቁት መደበኛ የክስ ሂደታቸውን እየተመለከተ ላለው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ-ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 18 በጽሁፍ ባቀረቡት አቤቱታ ነው።
በችሎቱ ንግግር ያደረጉት አቶ ጃዋር ፥ የኮሎኔል ገመቹ አያናና የሌሎች ተከሳሶችን ጉዳይ በመጥቀስ የፍርድ ቤት ውሳኔ በተገቢው መንገድ ተፈጻሚ እየሆነ አይደለም ብለዋል።
አክለው ፥“እኛ እዚህ የመጣነው ከተፈረደብን ለመቀጣት፤ ነጻ ከተባልን ለመውጣት ነው” ያሉት አቶ ጃዋር፤ “ከዛሬ ጀምሮ በገዛ ፍቃዳችን ፍርድ ቤት አንቀርብም” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።
ይህንን ውሳኔ ደግፈው የተናገሩት አቶ በቀለ ገርባ በበኩላቸው “በግድ ተጎትተን እና ተደብድበን ካልሆነ በቀር ወደዚህ ፍርድ ቤት አንመጣም ሲሉ ተደምጠዋል።
አቶ ጃዋር ወደ ፍ/ቤት ላለመምጣት መወሰናቸውን ከማስታወቃቸው በተጨማሪም በትግራይ ክልል እየተከሰተ ላለው ሁኔታ የትግራይ ህዝብ የረሃብ አድማ ላይ በመሆኑ፤ እነርሱም ለሁለት ቀናት ምግብ እንደማይበሉ ተናግረዋል።
የረሃብ አድማው በትግራይ እየታየ ያለውን “የጅምላ ግድያና ኢ-ፍትሃዊ አገዛዝ ለመቃወም” መሆኑን ተከሳሹ አስረድተዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/EthiopiaInsider-05-26
ኢትዮ ቴሌኮም ከመጭው ጥር ወር በኋላ ኢትዮጵያን የ5G የላቀ ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚያደርጋት መናገሩን ሸገር ዘግቧል፡፡ ኩባንያው ይህን ዕቅዱን ያስታወቀው፣ ትናንት በምሥራቅ ኢትዮጵያ ቀጠና ለድሬዳዋ፣ ጭሮ እና አይሻ ከተሞች የ4ኛው ትውልድ የላቀ ኢንተርኔት አገልግሎትን ባስጀመረበት ስነ ሥርዓት ላይ ነው፡፡
[Wazema]
* ሬይካቪክ
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የፊላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ብሊንከን እና ሃርቬስቶ ትላንት ሬይካቪክ ላይ በተገናኙበት ወቅት ነው ስለሁለቱ ሃገራት ጉዳይ የመከሩት።
ውይይቱን ተከትሎ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት መግለጫ አውጥቷል።
በወጣው መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ፥ ትግራይ ጉዳይም ተነስቷል።
አንቶኒ ብሊንከን እና ፔካ ሃርቪስቶ ትግራይን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ሃሳብ ስለመለዋወጣቸው በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል።
ፔካ ሃርቪስቶ ከዚህ ቀደም የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ወደኢትዮጵያ መጥተው ጉብኝት አድርገው ባለስልጣናትን አነጋገረው መመለሳቸው አይዘነጋም።
ሪይካቪክ (አይስላንድ) ላይ ምን አለ ?
የአየር ለውጥ ጉባኤ እና 12ኛው የአርክቲክ ካውንስል የሚኒስትሮች ስብሰባ አለ። ከስብሰባው ጎን ለጎንም ሀገራት በሁለትዮች ጉዳዮቻቸው ላይ እየመከሩ ነው። አባል ሀገራቱ ፦ ዴንማርክ፣ ካናዳ፣ ፊንላንድ፣ አይስላንድ፣ አሜሪካ፣ ስውዲን፣ ሩስያ፣ ኖርዌይ ናቸው።
አርክቲክ ካውንስል የሚባለው የአርክቲክ አካባቢ መንግሥታትና ህዝቦች ጉዳዮች ላይ የሚመክር የህብረ መንግሥታዊ ስብስብ ጉባዔ ነው።
ዛሬ ቂሊንጦ በር ላይ ምን ተፈጠረ ?
ትላንት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኮለኔል ገመቹ አያናና በአቶ ኪሲ ቂጡማ የሚጠሩ 13 ሰዎችን ልደታ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት በነፃ አሰናብቷቸው ነበር።
ኮ/ል ገመቹ አያና የሚገኙበት በአቶ ኪሲ ቂጡማ የሚጠራው መዝገብ ላይ የተከሰሱት ግለሰቦች የሽብር ጥቃት አድርሰዋል፣ አስተባብረዋል እና አሰማርተዋል ተብለው ነበር የተከሰሱት።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ የፀረሽብር እና የህገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቶ ከ2 ዓመት በኋላ ትላንት ተከሳሾቹ በነፃ እንዲለቀቁ ብይን ሰጥቶ እንደነበር ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቪኦኤ ተናግረው ነበር።
ዛሬ ቤተሰቦቻቸው ከእስር ቤት ይለቀቁ የሚል የመፍቻ ትዕዛዝ ይዘው ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሄደው እንደነበር ጠበቃ ቱሊ ባይሳ ለኦ ኤም ኤን ማምሻውን ተናግረዋል።
በወቅቱ "የስም ስህተት አለ" በማለት ወዲያና ወዲህ ሲያመላልሷቸው ቆይተው 11 ሰዓት ላይ ኮ/ል ገመቹን ጨምሮ 9 ሰዎች ከእስር እንዲወጡ ከተደረገ በኃላ በር ላይ የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱና በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ የፀጥታ ኃይሎች 9ኙን ሰዎች ከበው በመኪና ወስደዋቸው ከአባቢው እንደተሰወሩ ቤተሰቦቻቸው እንደነገሯቸው አስረድተዋል።
ከእስር የተለቀቁት እነኮ/ሌ ገመቹ አያና ለምን እና ወዴት እንደተወሰዱ አይታወቅ ብለዋል።
ትላንት እንዲለቀቁ ከተባሉት መካከል 3 ታሳሪዎች ዋና ሳጅን እንጉላ ፣ አቶ አማኑኤል እጅጉ ፣ አቶ ኪሲ ቂጡማ የስም ስህተት ስላለ ተብሎ አልተለቀቁም ፤ አሁንም ቂሊንጦ ይገኛሉ።
ጠበቃ ቱሊ ፥ "በስም ስህተት ሳይወጡ ቀሩ እንጂ ቢወጡ የእነሱም እጣ ፋንታ የነኮሎኔል ገመቹ አያና እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለንም" ብለዋል።
#Update
የብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት በደብረ ታቦር ደብረልዑላን መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ዛሬ ተፈፅሟል።
ከቀብር ስርዓቱ በፊት በደብረ ታቦር አጅባር ሜዳ የጀግና አሸኛኘት መደረጉ ተገልጿል።
የብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ አስከሬን ትላንት ከባሕርዳር ወደ ደብረታቦር መሸኘቱ ይታወሳለል።
ምንጭ ፦ የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሚኒኬሽን
* Update
የአውሮፓ ህብረት በፍልስጤም እና በእስራኤል ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ሊቀመጥ መሆኑ ተሰምቷል።
የህብረቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የፊታችን ማክሰኞ በቪድዮ ስብሰባቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ግጭቱ በሚቆምበት መንገድ ዙሪያ ማድረግ ስላለባቸው አስተዋፆ እንደሚወያዩና እንደሚመክሩ ጆሴፕ ቦሬል ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ዛሬ ጥዋት እስራኤል በጋዛ የሚገኘውን የሀማስ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ክንፍ መሪው ዬይያ አል-ሲንዋር መኖሪያ ቤትን በአየር ጥቃት መደብደቧን የሀማስ ቲቪ ገልጿል።
በተጨማሪ እስራኤል ዛሬ በጋዛ በፈጸመችው የአየር ድብደባ የ26 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ በርካቶች መቁሰላቸው እና ህንጸዎች መውደማቸው ታውቋል።
ትላንት ለሊቱን ከሀማስ ወደ እስራኤል ከተሞች የሚወነጨፉት ሮኬቶች የቀጠሉ ሲሆን ያደረሱት ጉዳት እንደሌለና እስራኤል በአየርን ዶም መከላከል እንደቻለች ተገልጿል።
ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገራቸው ጦር በጋዛ የሚፈፅመው የአየር ጥቃት አስፈላጊ እስከሆኑ ድረስ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ንሑሀን ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸውም የቻሉትን ሁሉ እያደረጉ እንደሆነም ተናግረዋል።
ኔታንያሁ፥ ‘’አሁን ለተፈጠረው ፍጥጫ ጥፋተኞቹ እኛ አይደለንም፤ እኛ ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት ናቸው’’ ሲሉ ተደምጠዋል።
አሁንም ባልበረደው እና መፍትሄ ባላገኘው የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት በፍልስጤም በኩል የሟቾች ቁጥር 170 ደርሷል፤ ከነዚህ ውስጥ 41ዱ ህፃናት ናቸው። በእስራኤል በኩል ሁለት ህፃናትን ጨምሮ 10 ሰዎች ተገድለዋል።
በዌስት ባንክ የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በትንሹ 13 ፍልስጤማውንን መግደላቸው ተሰምቷል።
የተመድ የፀጥታው ም/ቤት ዛሬ በእስራኤልና በፍልስጤም ጉዳይ ስብሰባ ይካሄዳል።
መረጃው የተሰባሰበው ከቢቢሲ፣ አልጀዚራ፣ ቲአርቲ ወርልድ ነው።
#DrTedrosAdhanom
በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በተከታታይ ለዘጠነኛ ሳምንት ፣ በበሽታው ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ለስድተኛ ሳምንት ማሻቀቡን መቀጠሉን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አደሃኖም ይህን ያሳወቁት ትናንት በአባል ሃገራቱ የመረጃ ልውውጥ ጉባኤ ላይ ነው።
ዶ/ር ቴድሮስ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተመዘገበው የኮሮና ቫይረስ ተያዦች ቁጥር በወረርሽኙ የመጀመሪያ 6 ወር ውስጥ ከተመዘገቡት ይበልጣል ብለዋል።
በመሆኑም ወቅቱ የቫይረሱ ስርጭት እየቀነሰላቸው ባሉትም ሃገሮች ጭምር ከመጠንቀቅ ወደኋላ የሚባልበት አይደለም ሲሉ ማሳሰባቸውን ቪኦኤ በድረ ገፁ አስነብቧል።
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ሳያቋርጡ እያከናወኑ እንደሆነ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ትግራይ ከሚገኙ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ጋር ባደረገው ክትትል ትምህርት አለመቋረጡን አረጋግጫለው ብሏል።
የጀርመን ድምፅን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተማሪዎቹን ድምፅ በመቅረጽ ለተማሪዎች ቤተሰብ እና ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ማሰማታቸው ይታወቃል። #MoSHE
#UPDATE_NEWS
✅ እስከአሁን ለፍሬሾች ጥሪ ያደረጉ ዩንቨርሲቲ👇👇👇👇
1. ደብረታቦር ═ሰኔ 26-29
2.ጎንደር════ ሰኔ 23-24
3.ሰመራ════ሰኔ 26-27
4. ወላይታሶዶ══ሰኔ 26-27
5. ወሎ═════ ሰኔ 28_29
6. ደብረብርሃን══"" 25-30
7. አሶሳ═════ "" 26-30
8. አዲስ አበባ═══"" 19-20
9. አምቦ═════ "" 24-25
10.ሐዋሳ═════"" 21-22
11. ባህር ዳር ═══"" 22-23
12.ደባርቅ═════"" 26-30
13. ወለጋ═════ "" 28-30
14. AASU════ "" 24-25
15. ዋቻሞ════"" 29-30
16. ወልቂጤ══"" 28 እና 29
17.መቅደላ አምባ═ "" 27-29
18. ድሬደዋ════ "" 27- 29
19. ዲላ══════"" 22-23
20.ጅማ ═══════"" 24-25
21. ASTU══════"" 24-25
22. ጋምቤላ ═════"" 28-29
23. እንጅባራ═════"" 28-29
24. ወልድያ══════""29-30
25. ሰላሌ═══════""24-25
26.ጂጂጋ═══════""28-30
26 universityዎች መግቢያ ቀን አሳውቀዋል 🙌
19 Universityዎች ይቀራሉ
ስለዚህ ተማሪዎች በርታ በርታ በሉ።
ለተጨማሪ መረጃ ይሄን የቴሌግራም ቻናል JOIN ማድረግ ትችላላችሁ
#ለትምህርት ነክ መረጃ ለማግኘት👇👇
Ethio_Entrance_preparation_Exam
Ethio_Entrance_preparation_Exam
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
#Update
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ሰኔ 14 እንደማይካሄድ ካሳወቀ በኋላ የተለያዩ ቅሬታዎች በተለይ ከዞንና ከወረዳ አመራሮች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ ቦርዱ ዛሬ ከዞንና ከወረዳ አመራሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ቦርዱ ሰኔ 14/2013 ህዝበ ውሳኔውን ለማድረግ ያስቸግራል ያለበትን ምክንያት በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎችም ህዝበ ውሳኔው ሰኔ 14 እንዲደረግ ኃሳቦችን አቅርበዋል።
ከውይይቱ በኋላ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከዞን እና ከወረዳ አስተዳዳሪዎቹ የተነሱ ኃሳቦችን ከቦርዱ ኃሳቦች ጋር አቻችሎ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
ህዝበ ውሳኔውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች ካሉም ዝርዝር አፈጻጸሙን በአጭር ጊዜ የሚገልጽ እንደሆነ ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
/channel/ETHOPOEIA
/channel/ETHOPOEIA
#Update
በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ ከሚገኙ ካምፖች በወታደሮች ተወስደው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ዜጎች ውስጥ አብዛኞቹ ትላንት ሀሙስ ምሽት መለቀቃቸውን ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ ምንጮች ነገሩኝ በማለት CNN ዘግቧል።
አንድ የእርዳታ ሰራተኛ ለCNN እንደገለፁት ፥ ወታደሮቹ እስረኞቹን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላት ናችሁ በማለት እንደያዟቸው ተናግሯል።
የእርዳታ ሰራተኛው ወታደሮቹ ይህን ያደረግነው ሰዎቹ የህወሓት አባላት ስለነበሩ ነው ብለው ሲነግሩን ነበር በማለት ለCNN አስረድተዋል።
ከእስር የተለቀቀ አንድ ተፈናቃይ ፥ ተይዘው በቆዩበት ወቅት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ወታደሮች አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ገልጿል።
UNHCR በትግራይ ከተፈናቃዮች መጠለያ ወታደሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወስደዋል መባሉ እጅግ እንዳሳሰበው ስጋቱን ዛሬ ገልጿል።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ባባር ባሎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ "ሁሉም ወገኖች በኃይል የተፈናቀሉትን ጨምሮ የሰላማዊ ሰዎችን ደሕንነት እንዲያረጋግጡ ከዚህ ቀደም ያቀረብንውን ጥሪ አሁንም እንደግማለን" ብለዋል።
ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ከተያዙት የተወሰኑት መለቀቃቸውን ቢናገሩም ቁጥራቸውን ግን አልጠቀሱም።
የተቀሩት ወጣቶች አሁንም በእስር ላይ ይሁኑ ይለቀቁ ግልጽ እንዳልሆነ አክለዋል። ባሎች ፥ "ለጠፉ ሰዎች ዘመዶች ብቻ ሳይሆን በሽረ ለሚገኙ ተፈናቃዮች በሙሉ ሁኔታው አሳዛኝና አሳሳቢ ነው ብለዋል።
ወ/ሮ ኬሪያ ምስክርነታቸው ተነስቶ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የምስክርነት ጥበቃቸው ተነስቶ ዳግም ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለጸ።
ወ/ሮ ኬሪያ ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።
የጠቅላይ አቃቤ ሕግ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን እንደገለጹት፤ ወ/ሮ ኬሪያ ከተከሳሽነት ወደ ምስክርነት ተቀይረው ነበር ብለዋል።
ተጠርጣሪዋ በጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 በገቡት ሥምምነት መሠረት ዝርዝር የምስክርነት ቃላቸውን በፈቃዳቸው ሰጥተው ነበር ብለዋል።
በገዛ ፈቃዳቸው በጽሑፍና በሲዲ ምስክርነታቸውን ሰጥተው በኃላም በፍ/ቤት ውሳኔ ከእስር እንደተለቀቁና ጎን ለጎንም ለግለሰቧ አስፈላጊውን የምስክርነት ጥበቃ ሲደረግላቸው ነበር ብለዋል።
ይሁንና ወ/ሮ ኬሪያ ቆይተው ምስክር የመሆን ፍላጎት እንደሌላቸው እና ምስክርነት ሲሰጡ የቆዩት ተገደው እንደነበር በመግለፅ ምስክረነታቸው መቋረጡን አስረድተዋል።
በምስክሮችና ጠቋሚዎች አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀፅ 11 መሰረት የጥበቃ ተጠቃሚው ሥምምነቱንና ግዴታውን የማያከብር ከሆነ የጥበቃ ስምምነት ውሉ ስለሚቋረጥ አቃቤ ሕግም ለወ/ሮ ኬሪያ ምስክር በመሆናቸው ይሰጣቸው የነበረውን ጥበቃ ለማንሳት መገደዱን ነው የተናገሩት።
"ከዚህም በኋላ ወይዘሮ ኬሪያ ከዚህ ቀደም በተጠረጠሩበት ወንጀል የቅድመ ምርመራ ስራ እንዲጀመር አቃቤ ሕግ ዛሬ ለፍ/ቤት ጥያቄ አቅርቧል" ብለዋል።
የተጠርጣሪዋ ጠበቆች በጉዳዩ ላይ ለመከራከር አልተዘጋጀንም በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ወ/ሮ ኬሪያ በመጪው ሰኞ ዳግም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አዟል።
ወ/ሮ ኬሪያ እስከ ሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ፍ/ቤቱ መወሰኑን ኢዜአ ዘግቧል።
4G LTE በማዕከላዊ ምሥራቅ ሪጅን ጀመረ።
ኢትዮ-ቴሌኮም ማዕከላዊ ምሥራቅ ሪጅን ለ227 ሺህ ደንበኞችን አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን 4G LTE Advanced ፈጣን ኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሩን ኢፕድ ዘግቧል።
በማዕከላዊ ምሥራቅ ሪጅን ፦
- ሐረር፣
- አወዳይ
- ሀሮማያ ከተሞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
የተጀመረው የኢንተርኔት አገልግሎት በሪጅኑ የነበረውን የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት በ14 እጥፍ እንደሚያሻሽለው ተገልጻል።
#Ethiopia
ከሁለት ዓመት በፊት በአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው።
አደጋው የደረሰበት የግምቢቹ ወረዳ ቱሉፈራ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ አራት ፕሮጀክቶች ሊተገበሩ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ፅሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አባ ተሾመ ፍቅሬ እንዳሉት ቦይንግ ኩባንያ ለተጎጂ ቤተሰቦች በሰጠው ድጋፍ መሰረት በኢትዮጵያ ጉዳት የደረሰባቸው 18 ሰዎች ቤተሰቦች አደጋው በደረሰበት ስፍራ ያሉ ነዋሪዎች ላደረጉት ሰብዊነት በስፍራው ሐውልት እንዲሰራ ይሁንታ ሰጥተዋል።
የሰውነት ተምሳሌት የሆኑ ነዋሪዎች በአደጋው ለተጎዱት ዜጎች ያደረጉት ክብር አድንቀው፤ አደጋ በደረሰበት ስፍራ ነዋሪዎች በአደጋው ያለፉ ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ተጎጂዎች ያደረጉት ተግባር ከቦይንግ በተገኘ ገንዘብ ድጋፍ አምስት አይነት ፕሮጀክቶች እንዲተገበሩ ተወስኗል።
ፕሮጀክቶቹ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ልማት ድርጅት አማካኝት ነው የሚተገበረው።
የፕሮጀክቶችን ክንውን የሚቆጣጠር ከኦሮሚያ ክልልና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሯል።
በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፈፃሚነት ስራዎች ተጀመሩ ሲሆን ፦
- ፕሮጀክቶች ሶስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች፣
- እያንዳንዳቸው 5 ብሎክ ህንፃዎች ያላቸው ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
- 1 ጤና ኬላ ግንባታና
- ሰባት ድልድዮች የፕሮጀክቱ አካል ናቸው ተብሏል።
ፕሮጀክቶቹ በግቢቹ ወረዳ 4 ቀበሌዎች የሚኖሩ 13,852 አባውራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል።
በቦይንግ ኩባንያ 106 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ መገኘቱን ገልጸው ፕሮጀክቶቹ በ1 ዓመት ከ6 ወር ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል። #ኢዜአ
#Update
"...ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አላከብርም ብሏል" - ባልደራስ ፓርቲ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት እነ አቶ እስክንድር ነጋን በተመለከተ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ እንዳይሆኑ ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር እንዲመዘገቡ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።
በውሳኔው መሰረት የባልደራ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በዕጩነት ለማስመዝገብ እና እንደ ፍርዱ እንዲፈፀም ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ የተጠየቀም ቢሆንም ምርጫ ቦርድ ውሳኔ እንደማይፈፅም በደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል።
ይህን ተከትሎም የባልደራስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል ሲል ፓርቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።
#Update
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ ጠዋት ውሎው የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትትን የመክፈቻ መልእክት ያዳመጠ ሲሆን፦
- ብጹዕ አቡነ ኤልያስ
- ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ
- ብጹዕ አቡነ ማርቆስ
- ብጹዕ አቡነ አብርሃምን
- ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ
- ብጹዕ አቡነ ፊልጶስ
- ብጹዕ አቡነ ሩፋኤልን አጀንዳ ቀርጸው እንዲያቀርቡ መድቧል። በዚህ መሰረት የተመረጡት ብጹአን አባቶች አዘጋጅተው የሚያቀርቧቸውን አጀንዳዎች ምልዐተ ጉባኤው መርምሮ ካጸደቃቸው በኋላ አንድ በአንድ እየተወያየ ያጸድቃቸዋል።
መረጃው የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሪፖርት ፦
- በትግራይ አክሱም ከተማ ህዳር 19 እና 20፣ 2013 ዓ.ም በነበረው ውጊያ የኤርትራ ወታደሮች 110 ንጹሃን ሰዎች ገድለዋል።
• 70 ሰዎች በአክሱም ከተማ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መንገድ ላይ እያሉ ተደገድለዋል ከሟቾቹ ውስጥ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱም በጦርነቱ የተሳተፉ ሰዎች ነበሩ።
• 40 ንጹሃን ሰዎች የኤርትራ ወታደሮች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሰሳ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገው እና በቤታቸው ውስጥ ተገድለዋል።
- በከተማዋ በርከት ያሉ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ደርሷል፥ ከእነዚህም ውስጥ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች፣ ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ብራና ሆቴል ይገኙበታል።
- ጠቅላይ አቃቤ ህግ በትግራይ በንጹሃን ግድያና በጾታ ጥቃት ላይ ትኩረት በማድረግ ባካሄደው ምርመራ፣ የወታደራዊ ግዴታ በሌለበት ወቅት በግድያ የተጠረጠሩ 28 የኢትዮጵያ ወታሮች ላይ ክስ መስርቷል።
- የጾታ ጥቃት እና አስገድዶ መድፈር የፈጸሙ 25 ወታደሮች ክስ ተመስርቶባቸዋል።
* ሙሉ የአቃቤ ህግ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።
#አል_ዓይን #የፌዴራል_ጠቅላይ_አቃቤ_ህግ
"...ምርጫ አልፎ መንግሥት ከተረጋጋ በኋላ በ2015 ወይንም ደግሞ በ2016 ጉዳያችን ይታይ" - እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ለፍርድ ቤት የተናገሩት
ዛሬ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 20 ተከሳሾች ልደታ የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ችሎት በአካል ቀርበው ነበር።
በዛሬው ቀጠሮ እነአቶ ጃዋር ፥ ቀጠሯቸው ከሁለት ዓመት በኋላ እንዲያዝ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤት የእነ አቶ ጃዋርን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
እነአቶ ጃዋር ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የሚታይ ሳይሆን የፖለቲካ ውሳኔ የሚፈልግ መሆኑን በመግለጽ ፣ ፍርድ ቤት በመመላለስ የተከሳሾችን፣ የሕግ ባለሙያዎችን፣ የጠቅላይ አቃቤ ሕግን እና የጠበቆችን ጊዜ ከማጥፋት ረዥም ቀጠሮ ለሁለት ዓመት እንዲሰጣቸው ነው የጠየቁት።
"ምርጫ አልፎ መንግሥት ከተረጋጋ በኋላ በ2015 ወይንም ደግሞ በ2016 ጉዳያችን ይታይ" ሲሉ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል።
የኮሎኔል ገመቹ እና የሌሎችን ተከሳሾችን ጉዳይ እንደማስረጃ ያቀረቡት እነ አቶ ጃዋር፣ ፍርድ ቤት ነጻ ቢለቀን እንኳ መንግሥት አይለቀንም ሲሉ ተደምጠዋል።
ከእነአቶ ጃዋር መሀመድ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ የሰጠቱትን ቃለ ምልልስ በዚህ ይገኛል ፦ https://telegra.ph/BBC-05-20
' አርባምንጭ ደብረ መድሃኒት መድሃኒዓለም ካቴድራል '
(የጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን)
ለአርባምንጭ ደብረ መድሃኒት መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን የካቴድራል ማዕረግ መሰጠቱ ተገለጸ።
ከጋሞ ጎፋ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤሊያስ ሚያዚያ 23/2013 ዓ.ም በቀረበ ጥያቄ መሠረት ባለአምስት ጉልላት ሕንፃ ቤተክርስቲያን ተሰርቶ በመጠናቀቁ ፣ ከትልቅነቱ እንዲሁም ማራኪነቱ አንጻር ከግንቦት 1/2013 ዓ.ም ጀምሮ ካቴድራል ሆኖ እንዲሰየም አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተወካያቸው ሊቀ ሊቃውንት ኃይሌ ሥላሴ ዘማርያም አማካይነት ገልጸዋል።
የጋሞ ጎፋ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤሊያስ ለሕንፃው ግንባታ አስተዋፅኦ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያበረከቱ አካላትን አመስግነው ቤተክርስቲያኑ ወደ ካቴድራል ማዕረግ በማደጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ፥ ካቴድራሉ ለከተማዋ ቅርስና ውበት በመሆን ሌላ መስዕብ መሆኑ ገልፀዋል።
የሕንጻ ቤተክርስቲያኑ የግንባታ ቁሳቁስ በስጦታና የማህበረሰብ ተሳትፎ የቤተክርስቲያን ሕንጻ ወጪ እስከ መጋቢት 30/2013 ዓ.ም ድረስ 34 ሚሊዮን 192 ሺ 481 ሲሆን የቤተልሔም ጀርባ ክትር ሥራ ፣ የመግቢያ አጥር እና የውስጥ ቁሳቁስ ጨምሮ አጠቃላይ ወጪው 50 ሚሊዮን ብር እንደሚደርስ የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ ቁጥጥር ክፍል አሳውቀዋል።
የአርባምንጭ ደብረ መድሃኒት መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ግንባታው የተጀመረው ግንቦት/2004 ዓ.ም የዛሬ 8 ዓመት ነው።
ያንብቡ : telegra.ph/ArbaMinch-05-16
Natinael Mekonnen
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቀጣይ 3ወራት ተግባራት ዙሪያ ከክልል አመራሮች ጋር የሚያደርጉት ውይይት ተጀመረ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቀጣይ 3ወራት ተግባራት ዙሪያ ከክልል አመራሮች ጋር የሚያደርጉት ውይይት ተጀምሯል፡፡
በሀገራዊ ጉዳዮች እና በቀጠና ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና ከክልል አመራሮች ጋር የሚካሄድ የሁለት ቀናት ስብሰባ ዛሬ መጀመሩን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ስብሰባው መንግሥት በቀጣይ ሦስት ወራት የሚያከናውናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለመወያየት እና ዕቅድ ለማውጣት ያለመ ነው።
ለትግራይ ክልል የጦርነት ተፈናቃዮች ለመጭው ክረምት ጊዜያዊ መጠለያዎችን እየገነባ እንደሆነ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ መጠለያዎቹን በ20 ከተሞች ለመገንባት እና ቁሳቁሶችን ለማቅረብ 50 ሚሊዮን ዶላር ከተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና ሌሎች ረድዔት ድርጅቶች ተገኝቷል፡፡ አስተዳደሩ መጠለያዎቹን በግንቦት እና ሰኔ ወራት ሰርቶ ለማጠናቀቅ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ እና እያንዳንዱ መጠለያ 15 ሺህ ተፈናቃይ እንደሚይዝ ለኢዜአ ተናግሯል፡፡
ምን ያህል መራጮች ተመዘገቡ ?
እስከ ሚያዚያ 29/2013 ዓ/ም ድረስ 31,724,947 መራጮች በ43,017 የምርጫ ጣቢያዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት አሳውቋል።
• ኦሮሚያ - 14,301,855
• አማራ - 5,205,011
• ሶማሌ - 3,844,129
• ደቡብ - 3,496,892
• አፋር - 1,712,991
• ሲዳማ - 1,329,490
• አዲስ አበባ - 1,212,073
• ጋምቤላ - 272,810
• ድሬዳዋ - 177,519
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ - 155,913
• ሐረሪ - 16,264
እስካሁን ከተመዝጋቢዎቹ መካከል 54 % ወንዶች ሲሆኑ 46 % ሴቶች ናቸው።
ምንጭ፦ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምስል ባለቤት : ethiopianinsider.com
#Update
ፌልትንማን ከኤርትራ ፕሬዜዳንት ጋር ተወያዩ።
በጁፍሪ ፌልትማን የሚመራው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ኤርትራ አስመራ ገብቷል።
የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈረወርቂ ልዑኩን በደንደን የእንግዳ መቀበያ ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።
ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ከአሜሪካ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን እንዳስረዱ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ የማነ ገ/መስቀል በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።
አምባሳደር ፌልማን በበኩላቸው በአፍሪካ ቀንድ እየታዩ ባሉ ችግሮች ዙሪያ የአሜሪካ አስተዳደር ያለውን አመለካከትና እይታ ለፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንዳብራሩላቸው የኤርትራው ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ገልፀዋል።
የነበረው ውይይት 4:00 ሰዓት ገደማ የወሰደ እንደነበረ የተሰማ ሲሆን ከላይ ከተገለፀው መረጃ ውጭ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች እስካሁን ይፋ አልሆኑም።