ይህ ጥንታዊ ፍልፍል ቤተ መንግሥት በመዲናችን በአዲስ አበባ እንደሚገኝ ያውቁ ኖሯል?
======================
አንድ ወጥ ድንጋይን በመፈልፈል ከቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ጋር በእጅጉ ተቀራራቢነት ባለው ኹኔታ ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ የቀረው ይኽ ቤተ መንግሥት ታዲያ ዛሬ ላይ 1692 ዓመታት የእድሜ ባለጸጋ ኾኖ ይገኛል።
መገናኛ አካባቢ የሚገኘው ይህ ቤተ መንግሥት ታዲያ የታሪካዊ ጉዟችን መነሻ እንዲኾን መርጠነዋልና ጉዟችንን ከእዛ እንጀምራለን።
መድረሻችንን የምናደርገውም እንጦጦ ተራራ ላይ ነው።
የቅርብ ሩቁ ታሪካችን ማሕተም ወደኾነውና ታላቁ የአዲሳባ ቤተ መንግሥት እስከሚገነባበት ጊዜ ድረስ በመንግሥት መቀመጫነት ወዳገለገው ወደ አፄ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት።
======================
ከጥንታዊው ፍልፍል ቤተ መንግሥት እስከ ዘመናዊው የሚኒሊክ ቤተ ነንግሥት ማለትም ከመገናኛ አካባቢ እስከ እንጦጦ ቤተ መንግሥት ድረስ ያለውን 17 ኪሎሜትር ስንጓዝ ታዲያ በአገር በቀል ዛፎች እና በባሕርዛፍ ጥቅጥቅ ደኖች የተሸፈነውን ኮረብታ እየረመረምን የአፍሪካ መዲናዋን አዲሳባን ቁልቁል እየተመለከትን ሐሩሩን እየሠነጠቅን አንዳንዴም ነፋሻውን አየር እየማግን በጉዞው ላይ የምናገኛቸው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን ጋር ተፈጥሮን እያደነቅን እና ማሕበራዊ ቁርኝቶቻችንን እያሰፋን በጉዟችን አጋማሽም እጅግ ውብ በኾነ ኮረብታ ላይ ምሣችንን በልተን እንደገና ማራኪውን ስነ ምህዳር አቆራርጠን ከጥንቱ ተነስተን ወደ ትናንቱ እንንደረደራለን።
=========================
ታሪክ እና ተፈጥሮ ተቆራኝተው የዛሬ ማንነቶቻችንን ከነ ነጸብራቆቻቸው በጉልህ ያስመለክቱናል።
እንዝናናበታለን በተጨማሪም እንማርበታለን እና ጉዟችን ፋይዳው ግዙፍ ነውና እነኾ ብለናል።
========================
ከእኛ ጋር ይጓዛሉ?
አህሪቡ ብለናል።
እኛም አብረውን ስለሚጓዙም ምሥጋናችን ታላቅ ነው።
ዛሬውኑ ይመዝገቡ
========================
ይህችን ዕለት ከእኛ ጋር ሲያሳልፉ ታዲያ እጅግ ተመጣጣኝ በኾነ ዋጋ ነው።
ሦስት መቶ ሃምሣ ብር ብቻ።
የከፈሉት 350 ብር ታዲያ
👉ምሣዎን
👉በጉዞ ላይ የሚቀርብልዎትን እሽግ ውኃ
👉ወደ ታሪካዊ ቦታዎቹን የሚደረጉ የመግቢያ ክፍያዎችን እንዲሁም
👉የአስጎብኚ እና ሌሎች መሰል ወጪዎችን ያካተተ ስለኾነ ተጨማሪ ክፍያ አንጠይቀዎትም።
======================
ቡና ባንክ
አካውንት ቁጥር
#2029505000300
ክፍያውን ቅድሚያ በባንክ ፈጽመው ደረሰኙን ብቻ ይዘው በመገኘት ከእኛ ጋር መጓዝ ይችላሉ
======================
ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ተጓዦች 15 $ ይከፍላሉ
=======================
አዘጋጁ #ሌጀንድስ_ፋሚሊ_አክሲዮን_ማሕበር ነው።
ኑ አብረን እንጓዝ......ኑ አብረን እንድረስ!!
ሌጄንድስ
========================
ለበለጠ መረጃ ፦
ይደውሉ......
0967234118
0911889372
0922368868
0903132888
#ዛሬን_ለነገ
👉 በዓይነቱ ለየት ያለ ፕሮግራም!
አዘጋጅ፦ #ሌጀንድስ_ፋሚሊ_አክሲዮን_ማሕበር!!!!!!
#ሌጀንድስ_ፋሚሊ_አክሲዮን_ማሕበር #ከኢንስፓዬር_ኢትዮጵያ እና #ከቢፀ_ተስፋዬ እንዲሁም ከሙዚቃ ባለሞያው #ከጊታሪስት_ካሌብ_አላሁ ጋር በመተባበር እና በዓይነቱ ለየት ያለ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ሲጋብዝዎ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል!!!!!!
ዕለቱ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ.ም ሲኾን
ቦታው ካዛንቺስ የሚገኘው #የኦዳ_ታወር አዳራሽ ነው።
በእለቱ የተለያዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ፕሮግራሞች የሚቀርቡ ሲኾን በዋዛ እና ቁም ነገሮቻቸውን የማይጠገቡ የመድረክ ፈርጦችም በተጋባዥነት ተገኝተው እያዝናኑ ያስተምሩናል።
#ሌጀንድስ_ፋሚሊ ይኽንን የባለ ራእይ ወጣቶች ድግስ በማዘጋጀት ዕለተ እሑድን ካዛንቺስ ኦዳ ታወር ተገኝተው እየተዝናኑ ያተርፉባት ዘንድ በክብር ሲጋብዝዎ ታዲያ በታላቅ ደስታም ጪምር ነው!!!!
✍ ፕሮግራሙ ከቀኑ 7 ሠዓት ጀምሮ ይካሔዳል!!!!!
👉 እሑድ ካዛንቺስ ኦዳ ታወር አይቀርም!!!!!!
የመግቢያ ዋጋ ኹለት መቶ ብር ብቻ!!!
ለተጨማሪ መረጃ በሥልክ ቁጥሮቻችን
#0965607666 ወይም #0913295685 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
#ሌጀንድስ_ፋሚሊ
" አንቺ ሁሉም ስለራሱ ሲያወራ ለዘመናት ዝም ያልሽ
ልጉም ሙዳይ፤ ቫቲካን
ስታቅራራ፣ ቆጵሮስ ስትጮህ፣ እስክንድርያ ስታመሰጥር፣
እየሩሳሌም በፀፀት
ስትቃትት፣ ለንደን ያለስጦታዋ ስትቦተልክ፣ የፈረንሰይዋ
ማርሴይ በምኞት ስትቃዥ
ምንም የማይመስልሽ አርምሞን የመረጥሽ አሳቻ
ታዛቢ.... የእኅቶችሽን
የአክሱምን፣ የግሸንን፣ የላሊበላን፣ የጣና ቂርቆስን ያክል
እንኳን ፊትሽ የማይፈታ
የተቋጠርሽ ሸማ!"
እመጓ!!!
ምንጭ ፦ #እመጓ_ገፅ_177
አማራ ባንክ ሄኖክ ከበደን መስራች ፕሬዚዳንቱ አድርጎ ሾሟል
5.9 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ይዞ የተመሠረተው አማራ ባንክ ሄኖክ ከበደን መስራች ፕሬዚዳንቱ አድርጎ ሾሟል። የለንደኑ ኖርዊች ዩኒቨርሲቲ ምሩቁ ሄኖክ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በዳሽን ባንክ ከፍተኛ አመራር በመሆን የሰራና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለቦታው የሚጠይቀውን በመስኩ ከ12 ዓመታት በላይ የስራ ልምድ ያለው የሚለውን መስፈርት የሚያሟላ በመሆኑ በቅርቡ የተቋቋመውን የአማራ ባንክ በወርሃዊ 300 ሺህ ብር ደመወዝ ለመምራት ስምምነት ላይ ደርሷል።
🎈Welcome to Tele Birr Bot
➣ ቴሌ ብር Botን ሲጠቀሙ
📋 ሲመዘገቡ 15.00 ብር Bonus
🎁 በየ 48:00 ሰሀት(2 ቀን) 3.00 ብር ጉርሻ
🔗 ጓደኛ በመጋበዝ 5.00 ብር ያገኛሉ።
TeleBirr Botን ይቀላቀሉ
🔗 /channel/TeleBirrProBot?start=Bot6078634
ስለ አገራችን የተለያዩ መረጃዎችን እና ቁምነገሮችን በቋሚነት የምንነጋገርባት የዩቲዩብ ጎጆ ቀልሰን #ቶጳዝዮን_ዕንቁ_ሚዲያ በሚል ስያሜ ሥራ አስጀምረናታል።
ቁም ነገር አይታጣባትምና ቤተሰብ መኾን ለምትሹ እንካችሁ ሙከራችንን በ125ኛው የአድዋ ድል ዝክረ በዓል ላይ ተገኝተን አጋጣሚ የቀረጽናትን አጠር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጨዋታ ብጤ ጀባ ብለናችኋል ❤️ https://youtu.be/jU1NV_G1gHM
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
እነኾ እመለስበታለሁ ያልኩት የመዝጊያ መልእክት እና ድምዳሜ!
(በተከታታይ ያቀረብኩት ሓሳብ የፀሓፊው የግል ምልከታ ትንጂ የማንም ሦስተኛ ወገን እንዳልኾነ ይታወቅ)
#ቶቶቶቶቶቶቶ
"the man who saw tomorrow" ይሉታል ከአይሁድ የዘር ግንድ እንደሚመዘዝ የሚነገርለትን ፈረንሣያዊው የጥበብ ሰው "ኖስትራዳመስ"ን
የስነፈለክ ባለሞያ ብቻ ሳይሆን የሕክምና ልህቀቱም ለወቅቱ የስፔን ንግስት የግል ሐኪም እስከመሆን ያደረሰው "ሚካኤል ዲ ኖስትራ ዳሞስ"ን ብዙዎች ታውቁታላችሁ ብዬ እገምታለሁ።
ነገን ማየት (ማወቅ) የቻለው ሰው እንደማለት ነው "ዘማን ሁ ሶው ቱሞሮው" የሚለው በእንግሊዞች አፍ የተጠራበት መለያው።
በነገራችን ላይ የዚሁ ግለሰብ መጠሪያ የሆነው "ኖስትራዳመስ" የሚለው ቃል ጣልያንኛ ቃል ጠቢብ (አዋቂ) ማለት እንደሆነ የሥራ ባልደረባየ ብቻ ሳይሆን ወዳጄም የሆነው (ዲጄ ጆ) አጫውቶኛል።
ይህቺን ትርጓሜ ከሰማሁ በኋላም እኔ በግሌ እናት እና አባቱ ሲወለድ ያወጡለት ስያሜው ይኽ ድንቅ ስም መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ጉጉት አድሮብኝ ባደረግሁት ፍለጋ የመጀመሪያ መጠሪያው ማለትም #ሚካኤል_ዲ_ኖስትራዳም የሚለውን ነባር ስሙን ወደ ላቲንኛ ትርጓሜው በመለወጥ ኖስትራዳመስ ሲል እንዳሻሻለው የሚገልፁ ፅሑፎች ብቻ ነው ማግኘት የቻልኩት።
በዚህች ጦማር በዋናነት ላነሳው የወደድኩት ቁም ነገር በሰውየው ዙሪያ ሳይኾን በትንቢቶቹ ዙሪያ በትኩረት ያላየናቸው የመሰለኝን ሃቆች ለመጥቀስ ያህል ነው።
#አላርም ነገር ለማሠማትም ጪምር.........
በ16ኛው ክ/ዘመን ኖሮ የሞተው ይህ አዋቂ እንደሚከተለው ያስመጣትን ወሳኝ ትንቢት ፍጻሜዋ ምን እንደመሰለ ጠቁሜ ይህቺኑ ክስተት የሐሳቤ መንደርደሪያ በማድረግ ዘመናችንን ለመፈተሽ እንድንሞክር አደራ እላለሁ።
"#የዓመቱ_የወሩ_የሣምንቱ_የዕለቱም_መጀመሪያ በሆነች ቀን የአሜሪካ #መንታ_ሕንፃዎች (ፔንታጎን) በፍንዳታ ተንጠው ይወድማሉ" ሲል ነበር ኖስትራዳመስ እ.ኤ.አ በ1555 ዓ.ም በአራት በአራት ስንኞች እየከፋፈለ በጻፈውና ዘ አልማናክ (the almanac) በተሰኘው መጽሓፉ ከተነበያቸው እጅግ በርካታ እና ረቂቅ ትንቢቶች አንዷን የገለፃት።
እናም..........
ከ500 ዓመታት በኋላ (እሱ ከሞተ ከ446 ዓመታት በኋላ ትንቢቱ ተፈፀመ።
እኛም እንደ ትውልድ ምስክሮች ሆንን......
እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 11, 2011 ዓ.ም።
9,11 (ናይን ኢለቨን)
ትንቢቱ የተፈፀመባት ዕለት እና የኖስትራዳመስ ቋንቋ ሲጋጭ (ሲቃረን) ላሳያችሁማ........
እንደ ጎርጎርሳውያኑ አቆጣጠር ዕለቱ ሲተነተን እንደሚከተለው ነው።
የዓመቱ 243ኛ የወሩ ደግሞ 11ኛ ቀን
የዓመቱ 9ኛ ወር ነበር #በአውሮፓውያኑ (ጎርጎርሳውያኑ) አቆጣጠር።
(september ለፈረንጆቹ 9ኛው ወር እንደኾነ ልብ ይሏል)
ታዲያ ክስተቱ ከትንቢቱ ጋር አብሮ ይሄዳል?
በፍፁም!
እናስ?
እናማ ትንቢቱ የተፈፀመበት ቀን በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ዕሁድ #መስከረም 1 ቀን 1994 ዓ.ም መሆኑን ልብ ይሏል።
እንዴት?
ለእኛ ለኢትዮጵያውያን መስከረም= #የዓመቱ 1ኛ (የመጀመሪያ) ወር ነው።
መስከረም 1 ደሞ=የዓመቱ የመጀመሪያ ቀን
መስከረም አንድ 1994 (የክስተቱ ዕለት) ደግሞ እሁድ ቀን ነበር የዋለው።
ዕሁድ= #የዓመቱ የመጀመሪያ ሣምንት
መስከረም 1= #የሣምንቱ የመጀመሪያ ዕለት ስለሆነ።
የዓመቱ የወሩ የሣንቱ የዕለቱ መጀለሪያዎች በኾኑበት አጋጣሚ። በፈረንጆቹ 7:00
(በእኛ በኢትዮጵያኑ መደበኛ ሠዓት ጠዋት 1 ሠዓት ላይ)
ስለዚህ ኖስትራዳሞስ #የኢትዮጵያውያኑን_መለኮታዊ_የዘመን_መቁጠሪያ የትንቢቱ ቋንቋ አድርጎት ነበር ማለት ነው።
እና ዛሬ ላይ ይህንን ማንሳት ለምን አስፈለገህ አትሉኝም?
በርግጥ ይህ ከላይ የጠቀስኩት አሜሪካ በአልቃኢዳ ተደረገብኝ ያለችው ትንቢታዊ ክስተት የሽብር ድርጊት ነው መባሉን ተከትሎ ጦሱ ለእኛም ያልቀረልንን የፀረ ሽብር ሕግ ዓለም በተግባር ላይ እንድታውል ፈር ቀደደላት ከማለት ውጭ የትለየ ምልከታ አላደረግንበት ይሆናል።
በትኩረት መመርመር ግን ነበረብን!
ከዚህ የፖለቲካ ፍጆታነት አልፎ ትኩረትን መሳብ የነበረበት ጉዳይ ግን አሁንም ሰውየው ከመንታዎቹ የፔንታጎን ሕንፃዎች ውድመት 18 ዓመታት በኋላም ሚዛን የሚደፋ ትንቢት ተንብዮ ማለፉ ላይ ነበር።
ትንቢቱን ተከትሎም የአሜሪካው የፊልም ኢንዱስትሪ ሆሊውድ ሳይቀር በከፍተኛ በጀት ወደ ፊልምነት የቀየረበት ብዙ የዓለማችን ሕዝብም የዛሬ 8 ዓመት አካባቢ በጭንቀት መደበቂያ ያጣበት ትንቢት ነበር።
እ.ኤ.አ ዲሴምበር 21, 2012 የዓለማችን መሠረት እንደሚናጋ ነበር ኖስትራዳመስ ለዚህ ትውልድ በሌላው ትንቢቱ ከ500 ዓመታት በፊት የማስጠንቀቂያ ደወሉን የተወልን።
የጎርጎርሳውያኑ ታኅሣስ 21 ቀን ሲመሽ መልሶ የማይነጋ የመሰላት ዓለም ታኅሣስ 21 ሲነጋ ያልተሳካ ትንቢት ነበር ብለው አልፈውታል።
ታዲያ ይህ የማያውያን ጥበብ ባሕር ተሻግሮ የኼደው ከኢትዮጵያ የወሰዱትም ኢትዮጵያውያን እንደኾኑ በሰሞኑ ጽሑፎቼ በስፋት ያነሳኹትን የማያ ካላንደር ተመርኩዘው የኖስትራ ዳመስን ትንቢት ሊፈቱት የሞከሩት ምእራባውያን ከ8 ዓመታት በኋላ የጠበቁት ክስተት በድጋሚ ከኢትዮጵያውያኑ ዘመን ጋር እጅግ ተሣስሮ ተፈጸመ።
በአስራ አራተኛው ዓውደ ቀመር ፍፃሜ በስድስተኛው ማኅተም በአራተኛው ንዑስ ዓውደ ቀመር ማለት ነው።
ለግንዛቤ ትንሽ ማብራሪያ፦
የማያውያኑ 13ኛ የ144,000 ቀናት ዑደት በ2012 መጨረሻ ተፈጽሞ አዲሱን ዓመት ስንቀበል ኢትዮጵያውያኑ በባሕረ ሓሳብ መዝግበው እንዳስተላለፉልን በዓብይ ዓውደ ቀመር መዝጊያ ብቻ ሳይኾን እጅግ አስደናቂ በኾነ ኹኔታ የዓብይ ዓውደ ቀመሩ የመጨረሻ ንዑስ ቀመር ላይ ጁፒተር ሣተርን እና ማርስ ትልቁን የጋራ መነሻ ዙር እንደጀመሩት የናሳ ሊቃውንት አረጋገጡ።
አንድ ዓብይ ዓውደ ቀመር ማለት እንግዲህ 532 ዓመታትን የያዘ ሲኾን እርሱም በአራት ማሕተሞች እና በ28 ዓውደ ቀመሮች የሚከፋፈል ነው።
አንድ ዓውደ ቀመር=19 ዓመት
ዓውደ ቀመር የተባለበትም ምክንያት ፀሓይ እና ጨረቃ በየ 19 ዓመቱ በተመሳሳይ ጊዜ በተመሳሳይ ቦታ በምሥራቅ በኩል መስከረም አንድ ቀን ስለሚወጡ እና እኩል ዙር ስለሚጀምሩ (conjunction) ስለሚፈጥሩ ነው።
አራቱ ዓውደ ቀመሮችም በአንድ ላይ ተጠቅልለው አንድ ማኅተም ይባላሉ።
እነዚህ ዓውደ ማኅተሞች ሰባት ጊዜ ሲደጋገሙ ነው እንግዲህ ትልቁ የፀሓይና የጨረቃ ዙር ኮንጃንክሺኑን የሚፈጥር በመኾኑ እጅግ ጉልህ የሰው ልጅ የታሪክ የስነ ልቦና እና የፍልስፍና ለውጥ ሊከሰት እንደሚችል የሚነገረው።
ይህንን ዓውደ ቀመር ኢትዮጵያውያኑ እንደጻፉልን በ1500 ዓ.ም የጀመርነው በመኾኑም የሚጠናቀቅበት ጊዜ 1500+532=2032 ኾኖ በመኻል በመኻል የንዑስ ቀመር እና የማኅተም ጊዜዎች በሥሌት የሚገኙ ይኾናል።
እናም የፈጸምነው 2012 የስድስቱ 76 ዓመታት ፍፃሜ በ1956 ዓ.ም ተከናውኖ ከመጨረሻው 76 ዓመት ላይ ማለትም ከ4×19 ዓመታት ላይ ሦስት 19 ዓመታትን ተሻግሮ አራተኛው የዓውደ ቀመር ተራ ከ2013 ጋር አብረን የተቀበልነው።
ይህ ማለት 2013 ጨምሮ ሲቆጠሩ ዓብይ ዓውደ ቀመር ሊጠናቀቅ 19 ዓመታት የቀሩት መኾኑ እና አዲሱ ዓመት 2032 ሲጠባ ዓውደ ዕለት፣ ዓውደ ሰንበት ዓውደ ዓመት፣፣ ዓውደ ንዑስ ቀመር፤ ዓውደ ፀሓይ፣ ዓውደ ማኅተም፣ዓውደ ዓብይ ቀመር (ኹሉም) የሚጠናቀቁ ይኾናል ማለት ነው።
የኢትዮጵያውያን ሥነ ሰማ
(ዘረኛ፣ ጎጠኛ፣ ቋንቋ ተኮር አሳቢ፣ የዘውግ በሺታ ተጠቂ፣ ፌደራሊስት ወዘተ የኾናችሁ ግለሰዎች………የዚህ ዓይነት ጽሑፍ እንቅልፍ እንቅልፍ ይላችኋል አትጀምሩት፤ አልፎ ተርፎ የዝግመተ ለውጥ እድገታችሁ እንዲህ ዓይነት ቁምነገሮችን ለመገንዘብ አልደረሰምና ከገፄ ላይ በፍጥነት ጡርግ በሉ😅)
✍✍✍✍✍✍✍✍✍
ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውት የአገሬ ልጆች አርበኞቹ፣ ጀግኖቹ፣ ፈላስማዎቹ፣ መሣፍንተ ኢትዮጵያ ግን ይህቺን ጽሑፍ ለማዘጋጀት ከፍተኛ ትኩረት መስጠትና እንደ አባቶቻችን እንደ ኢትዮጵያኑ ወግ የክብር ግብዣ አሰናድቻለሁና ይህቺን ከትናንት የቀጠለች የአባቶቻችሁን ድንቅ ጥበብ የምትተርክ አጪር ጽሑፍ ተጋበዙልኝ።
✍✍✍✍✍✍✍✍✍
ኢትዮጵያ
ዓለምን በሥሌት ደግማ የረታችበት የጥበብ ማሕጸንነቷን ዳግም ያረጋገጠችበት ክስተት!
(ዋናው ማጠንጠኛችን ነው)
መንደርደሪያ
ፀሓያችን የ1,872,000 ዕለታት ጉዞዋን ስትፈጽም ሊከሰቱ የሚችሉ ሣይንሳዊ እና መንፈሳዊ ጉዳዮች።
ይህ እውቀት በኢትዮጵያውያን ዘንድ በስፋት እና በጥልቀት የተተነተነ በመኾኑ የአባቶቻችንን ጥበብ መልሳችሁ መመርመር የምትፈልጉ አንባቢያን ብትኖሩ ዋና ዋናዎቹን መጻሕፍት በየመሓሉ እጠቁማችኋላሁ።
(7578 × 19) + (18) ቀናት=144,000 ቀናት።
144,000 ቀናት ×13 ዓውድ= 1,872,000 ዕለታት።
ምሥጢር 1፦
ከዘመነ አዳም እስከ ዘመነ መሲህ ኢየሱስ ድረስ የነበሩት አምሥት ቀን ተኩል ተብለው የተገለፁልን ዘመናትም በዚህ የጊዜ ርዝመት ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
ለመኾኑ እለዚህ አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ ዕለታት ምንድን ናቸው?
ዕለታቱ በማያውየን የጥንት የጊዜ ቀመር ውስጥ በስፋት በሚታወቀው የረጅም ዘመን ልኬት ስያሜ መ ሰረት ባክቱን ይባላሉ። እናም ማያውያን የፀሓይ ዓውድ (ዙር) ፍፃሜ የሚኾነው 13 ባክቱን ሲጠናቀቅ ነው ሲሉ ቀመሩን አስቀምጠውልን አልፈዋል።
13 ባክቱን ማለት፦
(7578 የኢትዮጵያ ንዑስ ቀመር ማለት ነው)
አንድ የኢትዮጵያውያን ንዑስ ቀመር 19 ዓመት ሲኾን 4 ንዑስ ቀመር አንድ የኢትዮጵያ ማኅተም (76 ዓመት) ይሰጠናል።
(1894×76) + (56) ቀናት= 144,000 ቀናት። ይህም ማለት 1894 የኢትዮጵያ ዓውደ ማኅተም ማለት ነው።
" በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ በወርቅም ፈርጥ አድርግ።"
(ኦሪት ዘጸአት 28:11)
" በአክዓብም ስም ደብዳቤ ጻፈች፥ በማኅተሙም አተመችው፤ በከተማው ወደ ነበሩትና ከናቡቴም ጋር ወደ ተቀመጡት ሽማግሌዎችና ከበርቴዎች ደብዳቤውን ላከች።"
(መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 20:8)
" ለእኔም። ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።"
(የዮሐንስ ራእይ 22:10)
#ማሳሰቢያ፦
እነዚህን ከላይ ያኖርኳቸውን ቅዱስ መጽሓፋዊ የመለኮት ቋንቋዎች ማስቀመጤ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ከዘመናት መካከል የሚፈፀምባቸውን ዓውዶች ለወደዳቸው ለአባቶቻችን እርሱ ራሱ ልዑል እግዚአብሔር ፈቅዶ እንደገለጠላቸው ለመጠቆም ብቻ መኾኑ ይታወቅ!!!!!
144,000 × 13=1,872,000 (13 የማያ ባክቱን)
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
በትናንትናው ጽሑፌ ለማስረዳት እንደሞከርኩት ፀሓይ በሚልክዌ ክፍለ ሰማይ ላይ በምድራውያን አቆጣጠር 5125.25 ዓ.መታት ገደማ ተጉዛ ወደ መነሻ ሥፍራዋ እንደምትደርስ ለመጥቀስ ሞክሬአለሁ።
ይህ ከመኾኑ በፊት ግን በምንኖርባት ምድርም ይኹን በሌሎች ፀሓይን ማዕከል አድርገው በሚሽከረከሩ የሰማይ አካላት (ፕላኔቶቻችንን ጨምሮ) ከፍተኛ የኾነ ፈተና ውስጥ ይገባሉ።
እንዴት?
ፀሓይ አውራ ኾና ግልገሎቿ የሚመስሉ ፕላኔቶቻችን ዙሪያዋን ሲያደርጉት የነበረው ዑደት ከፍተኛ ተጽዕኖ ውስጥ ይገባሉ። የተጽዕኖው መነሻም ጥልቁ ጉድጓድ (black hole) እና ፀሓይ ከሚያደርጉት ትንቅንቅ የሚመነጭ ይኾናል።
ጥቁሩ ጉድጓድ (black hole) ምንድን ነው?
ጥልቁ፦ በሰው ልጅ አእምሮ ሊገመት የማይችል የቀረበውን ኹሉ ውጦ አላየኹም የሚል የተፈጥሮ ከርስ ሲኾን የቀረበውን ኹሉ ውጦ የማስቀረቱ ምስጢር ደግሞ ከፍተኛ የኾነ የሰብሳቢነት የስበት ተፈጥሮው ነው።
ለጥልቁ አካል ይኹን ድምጽ፣ ብርሐን ይኹን የአተሞች ቅንጣት በቀረቡት ልክ እንደ መረጃ የሚያነፈንፋቸውና በአካባቢው የሚገኘው መረጃ እየጨመረ በመጣ ቁጥር መጠኑ እጅግ እየተለቀ የሚመጣ ወደ ውሥጥ ስቦ ያስገባቸው ነገሮች በሙሉ በጥልቁ ከርስ ከተዋጡ በኋላ ምን ሊኾኑ እንደሚችሉ የመረዳት ዕድሉን አላገኘም።
ምክንያቱም ጥልቁ የዋጠው ነገር በሙሉ ደብዛው የሚጠፋ መኾኑና የጥልቁ ስፋት ይኹን ጥልቀት ይህ ነው ተብሎ ሊለካ ባለመቻሉ ነው።
እናም ፀሓይ ለጥልቁ (ለብላክ ኾል) እጅግ እየቀረበች የምትመጣበትን ዘመን ለመረዳት ይህንን በማያውያን የተቀመረውን የጊዜ ሥሌት መረዳት ግዴታ ይኾናል። አልያም የዓውደ ፀሓይ ዓውደ ቀመር ዓውደ ማሕተም ዓውደ ዓብይ ቀመር ተብለው ከማያውያኑ የሥርዓተ ጊዜ ልኬት ጋር እጅግ ተመሳሳይ ኾኖ ከትውልድ ትውልድ ተሻግሮ የአኹኑ የእኔ እና የእናንተ ዘመን ድረስ የዘለቀውን ባሕረ ሓሳብ (ሓሳበ ኢትዮጵያ) ፤ ሓሳበ ዳዊት፤ ሓሳበ ድሜጵጥሮስ፤ መጽሓፈ ኩፋሌ ዘኢትዮጵያ እንዲኹም መጽሓፈ ሖኖክ የመሳሰሉ እጅግ ረቂቃን እና ህቡአን ትምሕርተ መጻሕፈትን የመረዳት ግዴታ ይኖርብናል።
በዚህ ወቅት ፕላኔቶቻችን በሙሉ ህልውናቸው በፀሓይ ህልውና ላይ የሚወድቅ ይኾናል።
ሌሎች ቁስ አካሎችን በሙሉ ለዘለዓለም ሲውጥ እንደሚሞረው ተሳክቶለት ፀሓይንም በከፍተኛ ስበቱ ጎትቶ መዋጥ ከቻለ ምድራችንን ጨምሮ ፕላኔቶችን ኹሉ ለዘለዓለሙ የሚያከትምላቸው ይኾናል።
ፀሓይ ጥልቁን ማሸነፍ ስትችል ብቻ ሌሎች በዙሪያዋ የሚባዝኑ ዓለማትም ለአሸናፊነት ይበቃሉ።
እናም ይህ የተፈጥሮ ትልቅ ከርስ በከፍተኛ ስበቱ ፀሓይንና ተከታዮቿን ውጦ ድምጥማጣቸውን ለማጥፋት የ7 ዓመታት ፍልሚያ ሲያደርግ እንደገና ለመወለድ ጉዞዋን በአሸናፊነት ልትወጣ 1,872,000 ዕለታት ገደማ የተጓዘችው ፀሓይም እጅግ ግዙፍ በኾነ በአካለ መጠኗ ዋስትናነት በጥልቁ ላይ የማለፍ ግዴታዋን በድፍረት ትገባበታለች።
ፀሓያችን በጥልቁ ላለመዋጥ ለ7 ዓመታት የምታደርገውን ትንቅንቅ ተከትሎ እንደ ቀድሞው በፀሓይ ዙሪያ ሳይደረደሩ በተለየ ኹኔታ ፀሓይን ከፊት ለፊት አስቀድመው እንደ ጭራ እየተከተሏት በጥልቁ ላይ ሊሻገሩ የሚገደዱት ዓለማትም ከስበቱ የተነሳ በሚፈጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ (ርግብግቢት) በእሳተ ጎሞራ መናወጥ ይጀምራሉ።
እኛ የምንኖርባት መሬት ደግሞ በተለየ ኹኔታ የያዘችው ውኃ የነውጡ አንድ አካል ስለሚኾን ሕያው ፍጥረታት በሙሉ የአደጋው ሰለባ ለመኾን እንገደዳለን።
በዚህ ሒደትም በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ብቻ በዕድል (probablity) ስሌት ከጥልቁ እና ከሥርዓተ ፀሓያችን ትንቅንቅ በኋላ በሕይወት ሊኖሩ እና በጥፋት ባዶ የምትኾንን ዓለም ዳግም በሰው ዘር የመሙላት ግዴታ ሊቀበሉ እንደሚችሉ ሊቃውንቱ በትንበያቸው ደጋግመው ነግረውናል።
ይህ የጊዜ ስሌት ቀድሞ የተደረሰበት ደግሞ በኢትዮጵያውያንና በማያውያን የጊዜ ሠሌዳ ቀመር ሥሌት ብቻ ነው።
ከኢትዮጵያውያኑን ሥሌት ከመመልከታችን በፊት ስለ ማያውያን እና ስለ ማያ ካለንደር ግንዛቤ ለመጨበጥ እንዲረዳን #ሓሳበ_ማያውያን በሚል አጪር ዳሰሳ ለማብራራት ልሞክር።
ለመኾኑ የማያውያን ጥበብ ብቻ ሳይኾን ራሳቸው ማያውያኑ የአሁኗን አሜሪካ የተባለች ክፍለ ዓለም ከብዙ ሺህ ዘመናት በፊት እንደረገጧትና ምድሪቱንም ወርሰው በዋናነት ግዛታቸው አድር
እንኳን ለግሪጎሪያን ዘመን 2021 ዓ.ም በሠላም አደረሳችሁ።
የዓለማችን 2020 ዓ.ም እነኾ ተፈጸመ።
አለም ወደ 2021 ተሻገረች!
2020 ዓ.ም ሥልጡኗ ዓለም በጥንታዊቷ በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ዳግም የተረታችበት ዓመት ነበር!
(ሓሳበ ኢትዮጵያ)
አንድ ሚሊዮን ሥምንት መቶ ሰባ ኹለት ሺህ ቀናትን (1,872,000 ቀናት) በአንድ አጪቆ የያዘ እና በብዙ ምሥጢራት ሠምና ወርቅ የተገመደ የግዙፍ ዘመን መዝጊያ እና የአዲስ ዘመን መክፈቻ ለመኾን ታሪክ ዕድል የሠጠን ትውልድ!
#የማያ_ካለንደር ፍጻሜ።
144,000×13=1,872,000
93,600×20=1,872,000
260×7200=1,872,000
ይህ የማያውያን የዘመናት መለዋወጫ ቀመር ነው።
ሓሳበ ማያውያን
ማያውያን ጥንታውያን የሥነ ከዋክብት ምጡቅ ታሪክ ያላቸው ጥቁር ሕዝቦች ናቸው።
እነዚህ ጥቁር ዕንቁዎችም የኢትዮጵያችን ጠበብት ልጆች እንደኾኑ በርካታ የታሪክ አሻራዎች ያረጋገጡ መኾኑንስ ስንቶቻችን እናውቃለን?
አዚህ ጽሑፍ ዓላማ የጥበብ ኹሉ የኾነችው ኢትዮጵያ በዓለም የሥልጣኔ ጉዞ ላይ ያበረከተችውን አልፋ እና ኦሜጋ ውለታዎች መዘርዘር በመኾኑ ምንጮቼን ለአንባቢ ጠቅሼ ወደ ዋናው መነሻ ሐሳቤ ለማለፍ እወዳለሁ።
በመኾኑም ይህንን ሐቅ ማረጋገጥ የሚፈልግ የዛሬ ዘመን የታሪክ አሳሽ ይህንን ጽሑፍ ሲመለከት ምንጭ ከምን ቢል They Game before colombus, The African princes in ancient America የተሰኘውን የኢቫን ቫን ሰርቲማ (ivan van sertima) ድንቅ የታራክ መዝገብ መመልከት አልያም ሼክ አንታ ዲዮፕ (Cheikh Anta Diop) የጻፈውንና ሜርሠር ኩክ (Mercer Cook) ወደ እንግሊዝኛ የተረጎመውን "The African origin of civilization, myth or reality" የተሰኘ መጽሓፍ እንዲሁም John.G Jackson (ጆን ጂ ጃክሰን) "Ethiopia the origin of civilization" ሲል በጥልቅ ጥናታዊ ትንታኔ የጻፈውን ጨምሮ መጻሕፍትን ማገላበጥ የበለጠ ጥርት ብሎ የሚታይ ጉልህ ማስረጃዎችን ለመመልከት ይጠቅማሉ እላለሁ።
በተጨማሪም እነዚህ ማያ የተባሉ ሕዝቦች መጠሪያ ስማቸው ማያ(መመልከቻ) ከሚለው ማሕበረሰባዊ ስያሜያቸው ባሻገር ይጠቀሟቸው የነበሩ በርካታ ቃላትም ከእኛው ግእዝ አማርኛ ትግርኛ ወዘተ ሴማዊ ቋንቋዎች ጋር ተመሳሳይ ሥነ ልሳን እንደነበራቸው ለመረዳትም በተለይ ለኢትዮጵያዊ አጥኚዎች ማያውያን የተባሉ ሕዝቦችን ታሪክ ማጥናት ብቻ በቂ ግንዛቤ ይሰጣል።
ወደ ማያ ሕዝቦች የዘመን ቀመር ስንመለስ ምናልባትም እነዚህ ሕዝቦች ለዘመናት ከቀሪው ዓለም ተነጥላ እና ተሠውራ ኖራ ክርስቶፈር ኮሎምበስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሰሣ አግኝቷታል ተብሎ በታሪክ ድርሣናት ላይ የተጻፈላትን የዛሬዋን ታላቅ አህጉር (አሜሪካን) ከክርስቶፈር ኮሎምበስ እጅግ ብዙ ሺህ ዘመናትን ቀድመው የረገጧት የኖሩባትና ትንግርታዊ የሥነ ከዋክብት ጥበባቸውን በድንጋይ ላይ ቀርጸው ያኖሩባት ሕዝቦች ናቸው።
ይህ የማያውያን የቀን አቆጣጠር ቀመር በዚህ ዘመን ልሂቃን ላይ በምን ያህል ደረጃ ተጽእኖ የፈጠረ መኾኑን ለመገንዘብ ደግሞ በመገናኛ ብዙሃኖች ከፍተኛ ትኩረት ስቦ የነበረውንና የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ ይፋ የኾነውን "2012" የተሰኘውን የአሜሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ ሆሊውድ የሠራውን መሠረቱም የእነዚሁ የማያ ሕዝቦች ካላንደር የኾነውን እጅግ ከፍተኛ ገቢም ለኢንዱስትሪው ያበረከተውን ፊልም መመልከት ነው።
2012......
ዛሬ ድረስ ያልደበዘዘ ይልቅስ እያደር ገናና የሚኾን የጥበብ ቅኔን ተቀኝተው በደረሰባቸው ከፍተኛ እና ተከታታይ የዘር ፍጂት ለፍጻሜ የተዳረጉ ሕዝቦች ናቸው።
እነዚህን ጥንታዊ ጠቢባን ምድራቸውን በኃይል ቀምታ ለመጨረሻ ጊዜ ከምድረ ገጽ ያጠፋቺው የዘመናችን ኃያል አገር ደግሞ አሳፋሪዋና አሳዛኟ አሜሪካ ነች።
የማያውያን የቀን ቆጠራ ሥርዓት (ሓሳበ ማያ) ፤ መጽሐፈ ኩፋሌ፥ ሓሳበ ሙሴ ፥ ሓሳበ ዳዊት፥ ሓሳበ ዲሜጵጥሮስ የመሳሰሉ ቀመሮችን አቀናጅቶ የዘመናት ምልክቶችን ሲያጤኑ የ ሰምና ወርቆቻችን ሥር መሠረቶች ምን ያህል ሩቅ እንደኾኑ መረዳት ብቻ ሳይኾን የዚህች አገር ጥበብ ርቀቱ እስከምን እንደኾነ ተገንዝቦ እጅን በአፍ ላይ ለመጫን ለገደድ ሳይወዱ በግድ የሚጎነጩት ጽዋ ይኾናል።
የማያ ካላንደርን (ሓሳበ ማያ) ከዓለማዊና መንፈሣዊ እሳቤዎች ጋር ያለውን ቁርኚትና የጥንታዊያኑን አስደናቂ የሒሳብ ልህቀት በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት በ2021 ዓ.ም የመጀመሪያ ዕለት (በነገው ዕለት) አጠር ባለች ጽሑፍ ላስቃኛችሁ እሞክራለሁ።
(ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም)
በተረፈ ባቃል ኪዳኖቹ ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያውያትና ኢትዮጵያውያን ቸር እደሩልኝ!
በነገራችን ላይ.....
በታሪክ አጋጣሚ ግብጽ ህወሓትን፥ ሻእቢያን፥ ሶማሌን....ብቻ የኢትዮጵያ መከራ ሊኾኑ የሚፈልጉ ኃይሎችን ኹሉ በመርዳት ሦስት ትልልቅ ህልሞቿን መተግበር ችላለች።
አንደኛው ኤርትራን ከእናት አገሯ በመነጠልና ኢትዮጵያን የማዳከም ሴራ ሲኾን ኹለተኛው በመንፈስ ልጇ በመለስ ዜናዊ በኩል ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብ ባለቤትነቷን እንድታጣ እና የባሕር በር አልባ ሐገር እንድትኾን ማድረጓ ነው።
የግብጽ ሦስተኛው ውጤታማ ሤራ ደግሞ በኹለት በወንድማማች ሕዝቦች መካከል እሳት በመጫር ደም አፋሳሽ የነበረውን የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መተግበሯ በዚህ ምክንያትም ኹለቱ ሕዝቦች የዘላለም ባላንጣ እንዲኾኑ ማድረግ ሲኾን ይህ በከፊል የተሳካ ጥረቷ ነበር።
ዛሬስ?
ከኦነግ እና ከኦነግ ሸኔ ጀርባ ህወሓት ተደብቃ ብዙ መከራ አሳይታናለች፣ አሁን ደግሞ ከቤኒሻንጉል (መተከል) ነፍሰ በላዎችና ከሱዳብ የጦር ኃይል ጀርባ ከህወሓት ጀርባ የነበረችው ግብጽ የተለመደ ሴራዋን በኢትዮጵያ ላይ እየተበተበች ትገኛለች።
የማይቀረው የቀጠናው ጦርነትም እንደ ጽንስ እየገፋ መጥቷል።
ይህ ማለት ደግሞ ህወሓት፥ ኦነግ፥ ኦነግ ሸኔ፥ የመተከል ነፍሰ ገዳዮች፥ ሱዳን፥ሶማሌ ወዘተ የተባሉ የጀርባ ቅማሎቻችን በሙሉ የግብጽ ቆሻሻ/እድፍ ውጤቶች ናቸው ማለት ነው።
ለመኾኑ ግብጽን የልብ ልብ የሠጣት ማን ነው?
ከመጋረጃው ጀርባ ያለችውን ግብጽ በሦስተኛ ወገንነት የጀርባ አጥንት ኾና የኢትዮጵያን የመከራ ቀንበር ዘላለማዊ ለማድረግ እና ኢትዮጵያ የምትባል አገር ከምድረ ገጽ ትጠፋ ዘንድ ሳታሠልስ ሸፍጥ የምትሰራው ደግሞ የ78 ዓመቷ ጎልማሳ አገር ነች።
እሥራኤል።
ለምን?
እሥራኤል ማለት ከጆርጂያ/ሙት ባሕር በመነሳት ዓለምን ጠቅልሎ ለመግዛት የወጣው አውሬ (አስካናዚ) ድርሰት ስትኾን የዓለምን ፖለቲካ ከሦስቱ የአብርሃም ዘሮች ኃይማኖቶች አንጻር በመተንተን ቅዱስ መጻሕፍትን በኑፋቄ ተርጉማ በታሪክ የሌለ አገርን የመሠረተች የቫቲካን ታላቅ እህት ነች።
እዚህ ጋር በየትኛውም ቅዱስ መጽሐፍ ላይ እሥራኤል የሚባል ሕዝብ እንጂ እሥራኤል የሚባል አገር ኖሮ እንደማያውቅ ልብ ይሏል።
" እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።"
(የዮሐንስ ራእይ 3:9)
እሥራኤል የሚባለው ሕዝብም የዚህችው የቅድስቲቱ አገር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲኾን ስያሜውን በወሰደበት በግእዙ ቋንቋ እሥራ ማለት ኻያ፤ ኤል ማለትም ቅዱስ አባት ማለትብነው። ይኸውም እሥራኤል የተባለው አባታችን ያዕቆብ ከአዳም ጀምሮ ሲቆጠር ኻያኛው ቅዱስ አባት በመኾኑ የተሰጠው ሥም ነው።
እናም ይህቺ በአስካናዚ አይሁዶች ምናብ ተደርሳ በረቀቀ እባባዊ የዲያብሎሳዊ ተንኮል በ1948 አገር ኾና መቋቋም የቻለችው የዛሬዋ እሥራኤልን ደራሲዎቹ የአስካናዚ አይሁዶች በበላይነት የሚዘውሯት ሲኾን በዋናነት የማንነታቸው ውቅየኖስ የሚቀዳው ደግሞ እንደ እንግሊዝ ጣልያን ፈረንሳይ ጀርመን ቤልጂየም ፖርቹጋል ስፔን አሜሪካ ከተባሉ ከዛሬዎቹ የጭን ገረድ ግዛቶቿ ነው።
" እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።"
(የዮሐንስ ራእይ 3:9)
እናም ከሕዝበ እሥራኤል (ኢትዮጵያውያን) ላይ ሥም ተውሳ ዓለምን የምትዘውረው ውሸታሟ እሥራኤል የፍልስጤማዊያንን ዘር በግፍ ጨፍጪፋ ዛሬ ላይ ያለ ከልካይ የዓለም እማወራ የኾነቺው ይህቺ የዚህ ዓለም ጋለሞታ አገር አሜሪካ ካምፕ ዴቪዳ ላይ ከግብጽ ጋር በመመሳጠር ስምምነት ተፈራርማ በሠራችው የሰላም ቦይ (peace canal) አማካኝነት ከግዮን ምንጭ የሚፈስሰውን የገነት ውኃ በነጻ መጠጣት የቻለች ሠላቢ አገር ነች።
እናም ከግብጽ እና ከኢትዮጵያ ፖለቲካ በስተጀርባ የተንኮል ሴራ ጠንሳሽ እና ደጋሿ ይህቺው የግፈኞች እናት የኾነችዋ ጋለሞታዋ የአስካናዚዎች አገር ናት!
" የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።"
" በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።"
" ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤"
(የዮሐንስ ራእይ 17:2- 4)
ለዚህም ነው ዛሬ ላይ የዓለም አገራት በሙሉ ያለ የሌለ ኃይላቸውን በሙሉ አስተባብረው ኢትዮጵያ የምትባልን ቀደምት እና ቅድስት ግዛት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከዓለም ካርታ ላይ ሊያጠፏት እየተዘጋጁ የሚገኙት።
ይህንን ከንቱ ምኞታቸውን ለመፈጸምም በአፍሪቃ ቀንድ ላይ 32 የዓለም ኃያል አገራት የጦር ካምፖቻቸውን አቋቁመው ጦርነቱ የሚጀመርበትን መንገድ በማመቻቸት በግብጽ በኩል አድርገው ሱዳንን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንድትገባ በማድረግ ላይ የሚገኙት።
እነዚህ 32 አገራት ኤርትራ (ምጽዋ) ላይ፤ ጅቡቲ (ዱሜራ) ሶማሊያ (በርበራ) ላይ ለዘመናት የገነቧቸውን የጦር ካምፖች የዘመኑ ቴክኖሎጂ በፈቀደላቸው ልክ የጦር መሣሪያዎቻቸውን አከማችተው ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ድምጽ ሳያሰሙ በመክበብ በአገሪቱ ውስጥ እርስ በርስ ጦርነት እንዲከሰትና የሰላም አስከባሪ ኾነው በመግባት የወረራ ህልማቸውን ለማሳካት ሲቋምጡ ኖረዋል። የእርስ በርስ ጦርነቱ በፈለጉት መጠን መፈጠር ካልቻለም ሱዳን የተባለች የግብጽ የጡት ልጅ የኾነች ጎረቤታችንን በድምበር ሰበብ ጦርነት እንድትገጥመን በማድረግ በሰላም አስከባሪነት (በፕላን B) መሠረት ወረራቸውን ለመተግበር ምናልባትም የመጨረሻው መጨረሻ ላይ ይመስላሉ።
ቃሉ ይፈጸም ዘንድ ግድ ነውና
" ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ፤ አሕዛብን አባረርህ እርስዋንም ተከልህ።"
" ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ።"
" በፊትዋም ስፍራን አዘጋጀህ፥ ሥሮችዋንም ተከልህ ምድርንም ሞላች።"
" ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ።"
" ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥ ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።"
" አጥርዋን ለምን አፈረስህ? መንገድ አላፊም ሁሉ ይቀጥፋታል።"
" የዱር እርያ አረከሳት፥ የአገር አውሬም ተሰማራባት።"
(መዝሙረ ዳዊት 80:8-13)
ግና ቢኾንም ቢኾንም የምድያም ድንኳኖች ይጨነቃሉ፤ ከዛም ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
ረዳቷ እና ረድኤቷም ስለ ክብሩ ስለ ቃል ኪዳኑም ሕዝበ እሥራኤልን ይታደጋል።
ጠላት በቆፈረው ጉድጓድ ገብቶ የዓለሙን የበላይ ገዢነት ሳይወድድ በግዱ ለኢትዮጵያዬ ያስረክባል።
ይህቺ ምድርም መሐሏ ገነት ዳሯ እሳት እንደኾነ የዓለም አውራ ኾና ለዘላለም ትኖራለች።
" አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለዚህ ትንቢት ተናገር ጎግንም እንዲህ በለው። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል ሳይፈራ በተቀመጠ ጊዜ አንተ አታውቀውምን?"
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 38:14)
#ቶ
ልባቻው በሃዘን ስብር ብሏል፡፡
አዝነዋል!
ቢኾንም እንደ ኀይማኖታቸው ሥርዓት አንገታቸውን አቀርቅረው ፀሎተ ፍትሓት እያደረጉ ባለበት ሠዓት እንግዳ ነገር ጆሯቸውን ሳበው፡፡
ያልተጠበቀ ክስተት!
በንጉሱ ጦር ከተማረኩት የደርቡሽ ጭፍራዎች መካከል አንዱ 'ኧረ ባካችሁ ውሃ አቅምሱኝ . . . ' ሲል ጮኸ።
በአማርኛ ነው ጩኸቱን ያቀለጠው!
አፄው ግርምታቸውን በኾዳቸው ይዘው ቆይተው ኖሮ ሥርዓተ ኀይማኖቱን እንደጨረሱ ምርኮኛውን አስጠርተው አነጋገሩት።
በፖለቲካ ህይወታቸው እንደዛን ቀን ደንግጠው አያውቁም፡፡
'እንዴት፣በል?' ጮሁ፡፡
ከፊታቸው እንደቆመ አንዲህ ነበር የጠየቁት፡፡
' . . . የኛ ሰው ነህ እንዴ?' ሲሉ ነበር በመገረም የጠየቁት፡፡
'አዎ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ከደርቡሽ ጋር ጅሀድ ወጥቼ ነው። ግን ማረካችሁኝ!' ሲል መለሰላቸው፡፡
ኢትዮጵያውያን ራሳችን ኢትዮጵያን ጠንቅቀን ባለማወቃችን የት ድረስ ዋጋ እየከፈለን እንደምንገኝና በገዛ ወገኖቻችን መካከል በሚዘራው የሸፍጥ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት በከንቱ የፈሰሰው ደም አሳዘኗቸው ይኹን እርሳቸው ራሳቸው የወሎን ሙስሊሞች ቦሩ ሜዳ ላይ ሰብስበው ኀይማኖታችሁን ለውጡ ወይም አገር ልቀቁ እና ሒዱ በማለት የፈጸሙት ጠርዝ የሌለው አምባገነንነት የኋላ ኋላ መዘዙ ምን ሊኾን እንደሚችል ተገንዝበው በመጸጸት ባይታቀቅም ግን ንጉሠ ነገሥቱ በዚህ ገጠመኝ አዘኑ.....ዐይኖቻቸውም እንባ አቀረሩ፡፡ ፊታቸውን በእጃቸው ሸፈን ሲያደርጉት ጺማቸውን እንባ አርሦታል፡፡
ኹለተኛው እና የመጨረሻቸው የንጉሡ እንባ ደግሞ ፍጻሜአቸው ጫፍ ላይ በነበሩበት ጊዜ መተማ ላይ ያለቀሱት መራራ ልቅሶ ነው፡፡ ደጋግመው ክንዳቸውን ባሳዩአቸው ደርቡሾች ጥይት ተመትተው በጽኑ ቆስለው እያቃሰቱ በነበሩበት በመጨረሻዋ ሰዓት፡፡
ንጉሡ ልጃቸው መንገሻ በትረ መንግሥታቸውን እንዲያስቀጥልና ዘውዱንም እንዲዎርስ በመናዘዝ ላይ ሳሉ ድንገት እንባቸው መንታ መንታ እየኾነ ፈሰሰ፡፡
ለኢትዮጵያ ብለው ብዙ ደክመዋል፤ ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ብለውም ብዙ ተሳስተዋል ግን ያሰቡትን ሳያሳኩ የጀመሩትን ሳይፈጽሙ ሪቮሉሲዮናቸው መተማ ላይ እንደተፈጸመ ሲገነዘቡ አፄ ዮሐንስ አለቀሱ።
አፄ ዮሐንስ ከአክራሪ የእስልምና ኃይላት ጋር (አክራሪዎቹ ጸረ ኢምፔሪያሊስት ቢኾኑም) ለመዋጋት ወደ መተማ በዘለቁ ጊዜ እልህ እንደነበረባቸውና ከቶውንም እንባ አውጥተው እንዳለቀሱ ይነገራል። የአፄ ዮሐንስ ልቅሶ ታዲያ የፍርሃት ልቅሶ አልነበረም። ንጉሡ አንዴ በተድአሊ፣ አንዴ በጉንዴት እና በጉንዳጉንዴ፣ አንዴ በጉራዕ ጦራቸውን እየላኩ የአገራቸውን ጠላቶች አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ መልሰዋቸዋል። መተማ አካባቢ የተከማቸውን የፈንዳሞንታሊስቶች ኃይል በተመለከተ ግን "እኔው ራሴ ሔጄ እጄን ላሳየው" በእልህ በቁጭትና በተደፈርሁ ባይነት ስሜት እየነደዱ ሔዱላቸው።
ሰማእት ኾኑ።
ኹለት የኢትዮጵያ መሪዎች በተከታታይ በጠላት ሳይማረኩ መስዋእትነትን ተቀበሉ!
ሃሌ ሉያ
በሞታቸውም አስከብረውን አለፉ። ሩጫውን እስከፍጻሜው ሮጠን ድል ማድረግ ለማይሆንልን ዜጎች ምናልባት እንዲህ ያለውን ድል እያሰብን ውርደትንም እያሰላሰልን እንደ ኃይሌ ገ/ሥላሴ፣ እንደ ቴዎድሮስ እንደ ዮሐንስ ልናለቅስ እንችላለን።
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴም በአርባ አራት ዓመታት አገዛዛቸው ግዙፍ ግዙፍ ሥራዎችን እንደሠሩ ይታወቃል። እድሜ ከድቷቸው ወቅቱም ሌላ ዘመን ኾነባቸውና የወትሮ ሕልማቸውን ለመቀጠል አልተቻላቸውም። ከሥልጣን ሲወገዱም "እኛ በዘመናችን የቻልነውን ኹሉ ሠርተናል፤ አኹን ደግሞ እናንተ ሞክሩት። እኛ ለኢትዮጵያ ያላደረግነው ነገር አልነበረም።" በማለት ለአዳዲሶቹ ሰዎች መልካሙን ኹሉ ተመኝተው ወደ እስራት ዓለም ሔዱ። ኹለት ዘለላ እንባ አውርደው!
በረጅሙ የሥልጣን ዘመናቸው ስህተቶችን የሠሩ ቢኾንም የተጣለባቸው ቅጣት ግን ይበዛባቸው ነበር። እናም በሕይወት በቆዩባቸው የእሥራት ዘመናቸውም አልቅሰዋል።
ያውም በስተ እርግና!
የግል ሕይወት ብታሳሳና ብታስለቅስም የአገር ዕድል ግን የበለጠ ያስለቅሳል። ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተለይ ዙፋናቸውን ለቅቀው በቤተ መንግሥት ታስረው በነበረበት ወቅት ያለቀሱት ልቅሶ ኾድ አስብሶ ያስለቅሳል።
የተማደበላቸው ጠባቂ መርዝ አብልቶ ሊገድላቸው እርሳቸው ደግሞ የቀረበላቸውን መርዝ ዓይናቸው እያየ ላለመብላት ከፍተኛ ትግል አደረጉ። በደካማ ዘመናቸው በ82/83 ዓመት የሽምግልና እድሜያቸው ራሳቸውን ለማዳን ከጠብደል ጠባቂያቸው ጋር ትንቅንቅ ላይ በነበሩበት ሰዓት ሰው ደርሶላቸው ጽዋዋ ለጊዜውም ቢኾን አለፈቻቸው።
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ የልብ ስብራታቸው ምን ያህል እንደነበር በሚያሳይ ኹኔታ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ።
አዎ....ለኢትጵያማ ዘላለም ይለቀሳል
መቼም አብዮተኛ ማለት ማርክሲስት ሌኒኒስት ማለት ነው የሚል ሙግት ካልቀረበ በስተቀር ቴዎድሮስም፣ ዮሐንስም፣ ሚኒሊክም፣ ኃይለ ሥላሴም አብዮተኞች ነበሩ።
ምናልባትም ይኽንን የለመድነውንና አንዳንዶች ጨርሶ የጠሉትን አብዮት የሚለውን ቋንቋ እንተወውና ቴዎድሮስ ሚኒሊክና ኃይለ ሥላሴ በየራሳቸው መንገድ ሪቮሊሲዮናውያን ነበሩ ማለት ይቻላል። ከኹሉም በላይ ግን በኢትዮጵያ ታሪክ ቴዎድሮስ ትልቁ ሪቮሊሺነሪ ነበር ለማለት እደፍራለሁ።
ለአገሩ ታላላቅ ለውጦችን ለማምጣት ሰፋፊ እና ጠቃሚ ሕልሞቹን ከግብ እንዳያደርስ ግን አያሌ አወናባጆች፤ ፀረ ሪቮሉሺነሪዎች፤ ጎትጓቾች እና ኾዳሞች ከፊቱ በመቆማቸው የቴዎድሮስ ሪ ቮሉሽን ከሸፈ። ይኹንና ዛሬም የቴዎድሮስን ሪ ቮሉሽን ያልተረዳን ሚሊዮኖች አለን። በ1966 ዓ.ም የተቀሰቀሰውን የሪቮሊሲዮን መንፈስ አሁንም ድረስ ያልተረዳንና ለዛሬው ፀረ አብዮት አቋም ያደረስነውም አለን። ቴዎድሮስን በዛ ዘመን የከዳው ዓይነት ደካማ የሕዝብ ክፍል በመገኘቱ ለዛሬው ፀረ ሪቮሉሲዮን ኃይል በመመቻቸት ለሕዝብ ይገባ የነበረውን ሥልጣንና መብት ለቡድኖች አስረክበናል።
Team took over the revolution of citizens!
በቴዎድሮስ ዘመን የነበረው ችግር የጥቂቶች ንቃትና የብዙሐን ወገኖች የግንዛቤ ችግር እንደነበረ ይሰማኛል። አኹን በ2010 ደግሞ የ1966ቱ የሪቮሉሺን ጭንገፋ ተመልሶ ነፍስ በመዝራት ታሪክ ራሱን ሲደግም የተመለከትን ግን ያላስተዋልን ትውልዶች እንገኘን።
የሕዝብ ሪቮሉሺን በቡድንን የማስጠለፍ አዙሪት።
ዛሬም ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት መኾኑን ሳያረጋግጥ በመጨረሻ ሠዓት የተከሰቱ ቡድኖች የሪቮሉሲዮኑ ባለቤት እንዲኾኑ ዕድል በመሥጠት የዚህ ዘመን ልሂቃን የኢትዮጵያን ሕዝብ የመከራ ዘመን አራዘሙበት!!!
ያስለቅሳል!
እውነትም ለኢትዮጵያ ዘላለም ይለቀሳል።
ቴዎድሮስን በተመለከተ ጥፋቶቹንና የሥልት ጉድለቶቹን ትተን ኢትዮጵያን ማፍቀሩንና ኢትዮጵያን ከሩቅ አሻግሮ ማየቱን ዋናው ቁምነገር ነውና ውለታ አድርገን እንውሰድለት። ፈጣን ለውጡን፤ ታላቅ የኾነ ሕዝባዊ ዓላማውን፤ የአንድነት አቋሙን፤ በጠውላላው ኢትዮጵያ እንድትኾን የአኘላትን ሥዕል ስናስብ አጠገቡ የነበሩት ብዙ ሰዎች ምንኛ የአገር ጠንቅ እንደነበሩ እንረዳለን። ቴዎድሮስን የሚጎትቱት አያሌ ነበሩ። የእንግሊዙን ጆሮ ጠቢ ቢትወደድ ዮሐንስ ቤልን ጨምሮ። በዚያ የሪቮሉሽን ነውጥ ውስጥ ደግሞ በግዴለሽነት የተኙም ነበሩ። ባይተኙም ዓይናቸውም አፍጥጠው እጅ እግራቸውን አጣጥፈው የተቀመጡም ነበሩ። "በሪቮሉሲዮን ወቅት ነቅቶ መገኘት (remaining awake through revolution )" ከሚለው ማርቲን ሉተርንኪንግ ጁኒየር በዋናነት ከሚያነሳው ምክርና አብዮትን ከተፈለገው ግብ ለማድረስ ወሳኝ
ርጉም ምን እንደኾነ እስከማይለዩበት ድረስ ዝቅ ብላው ቅኝ መገዛት ነበረብን ብለው የሚቆጩባት አገር......
ለውጥ እርሟ ኾኖ የሪቮሉሲዮን ሾተላይ ደጋግሞ ቡአ የመታት ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ ትንሳኤ ይኾንላት ዘንድ ።
ለውጥ ጽንስ ለምእተ ዓመታት ለሚጨነግፍባት ኢትዮጵያ እንደ ቁልቢው ገጸ ባሕሪ እንደ ተስፋዬ ዛሬም ብዙዎች ያለቅሱላታል፤ ያለቅሱባታልም።
ምክንያቱን እንደ ግል መረዳቴ ስመረምር ሩቅ ኾኖ አላገኘኹትም።
እንደ አገር ከመጠቀችው የሳይንሥ ዓለም ጋር ስንነጻጸር ከሚታየው ከኋላ ቀርነታችን በላይ ከሠይጣን ገላ የተቆረጠ መንግሥታዊ ሥርዓት በቅጣት መልክ ከፈጣሪ ስለተሰጠን ከቶውንም በዛሬው ወቅት መቀራረቡ ይባስ እየጠፋ የወንድማማችነቱ መረሳት ሲገርመን ጉርብትናውም እየሻከረና እየከሰመ መጥቶ መጪውን ታሪክችንን የጠላትነት ገጾች እያበዛንለት መጥተናል።
ይልቁንም በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ዓለምን ለመቅጣት ኮሮናን በተለይም ኢትዮጵያን በግል ለመቅጣት ፈልጎ ይኽን መንግሥት ሰጥቶን ይኾን??
ያ እንደየግል አመለካከታችን የሚትረጎም ሲኾን በእኔ በኩል የዚህ ኹሉ ምክንያት በድሮዎቹ ነገሥታት እና መሣፍንት እግር የተተኩት የዘመኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መሪዎቻቸው ናቸው።የአንዳንዶቹ ግልጽ ተልእኮ የአገርን ክብር እና ዝና ማፍረ ስ እንዲሁም ወዳጅነትንና ወንድማማችነትን ማጥፋት መኾኑን ለመረዳት ጊዜ ፈጅቶብናል። ማንም መጣ ማንም ሔደ ወደፊት በወንድማማችነትና በፍቅር ተባብረን አብረን እንድንኖር የአኹኑን የተበላሸ ሥርዓት በመዋጋት ረገድ ብዙ ብዙ ምሁራን አገር ወዳዶችና ጀግኖችን ብዙም አናይም። በዚህ ረድፍ የሚገኙትና የሶቅራጠስን ሔምሎክ (መርዝ) የሚጋቱ ሔምሎኳን ለመጋትም ሕይወታቸው ሳያሳሳቸው ላአገር አንድነት ለትውልድ ክብር ለባንዲራ ፍቅር ከራሳቸው ይልቅ ቅድሚያ ሠጥተው በግንባር ቀደምነት የሚሟገቱት በእኛ ዘመን በጣት አይቆጠሩም። በኢትዮጵያ በየትኛውም ቅጽበት ሊወርድ የሚችለው የጥፋት ደመና ብሎም የመከራ ዶፍ ለመግፈፍ ሕይወታቸውን እንደ ጧፍ የሚያቃጥሉ አብዮተኞች ያስፈልጉን ነበር። ይኽ ትውልድ በውዥንብር ውስጥ እያለፈ ይገኛል። መጭዎቹም ትውልዶች በዚህ ዓይነት ቱማታ ውስጥ ሊያልፍ አይገባውም።
ሥለዚህ የዛሬውን ትውልድ አበሳ ለማቃለል ሲባል የነገው ትውልድ የሌላ ዙር አበሳ ተሸካሚ እንዳይኾን እንደ ቢድሂስት መነኮሳት ራሱን የሚያቃጥል ቢያንስ ቢያንስ የሙያለቅስ ቴዎድሮስ፥የሚያለቅስ በላይ ዘለቀ፥ የሚያለቅስ ገርማሜ ነዋይ፥ የሚያለቅስ አሥራት ወልደየስ ያስፈልገናል።
እንዴት?
ይቀጥላል
@eyori
ኢራኑ ሼህ ኤንድ ሻህ ፓህላቪ የታላላቆቹን የነ ዳርየስን እና ሳይረስን ዙፋን እንደወረሱ ወዲያው ንጉሠ ነገሥታት መባልን አልፈለጉም ነበር።
ፓህላቪ "አኹን ዘውድ አልደፋም። ድሃ እና ጎስቋላ ሕዝብ መግዛት የኩራት ምንጭ ሊኾን አይችልም። መጀመሪያ የሕዝቤን አኗኗር ለመለወጥ ከሞከርኩ በኋላ ዘውድ መጫን- ዙፋን ላይ መቀመጡ ይደርሳል።" ማለታቸው ይጠቀሳል።
በተመሣሣይ ኹኔታ የሚኒሊክ አልጋ ወራሽ አቤቶ ኢያሱ (ልጅ ኢያሱ) "ፈረሴን ከቀይ ባሕር ሳላጠጣ፤ አባቴም (ራስ ዓሊ) ንጉሥ ሳይባል እኔ ንጉሠ ነገሥታት ለመባል እና ዘውድ ለመጫን አልፈልግም ብለዋል።"
ፓህላቪም ይኹኑ አቤቶ ኢያሱ ለእናት ሀገራቸው አንዳች ብጽዓት ለማምጣት ከራሳቸው ወይም ከአምላካቸው ጋር ስእለት ገብተው ነበር።
አንድ ነገር ለመፈጸም.....አንድ ውጤት ለማስገኘት......
ሸህ ኤንድ ሻህ ፓህላቪ የደረሱበት የታሪክ ምእራፍ አገርን በትንሹም ቢኾን የመለወጥ ትውልዱንም ብርሐን ወደምትታይበት የተሻለች ዓለም የማሻገር ግዴታን የጣለባቸው እንደነበር ተገንዝበው ነበር ወደ ሥልጣን የመጡት።
ምን ዋጋ አለው?
የሰው ልጆች ጠባይ በአመዛኙ ተመሣሣይ ነው!
በተለይም አንድ ጊዜ ሥልጣን ከቀመሱ ወደህ ወንበሯ ስለምትጣፍጥ ቃል እና ተግባር አብሮ አይሔድም።
ፓህላቪ ወደ መንግሥትነት ሲመጡ የነበራቸውን አቋም ለውጠው ትሕትናው እና ብጽአቱ ቀረና ቀስ በቀስ በስለላ እና በአፈና አማካኝነት ለመግዛት ሞከሩ።
#ሳቫክ የተባለው ያስለላ እና የአፈና ድርጅታቸው እያደር ከጀርመኑ ኤስ ኤስ ከሩስያው ኬጂቢ ከሮማንያው....... ከምሥራቅ ጀርመኑ...... የስለላ እና የዐፈና ድርጅቶች ጋር ተፎካካሪ ኾኖ ዐረፈው።
ፓህላቪ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የተረዳውን የሕዝብን ፍቅር ወሳኝነት ገና አልተገነዘቡም ነበር አልያም ወንበር ላይ ከወጡ በኋላ ወሳኝነቱ አልታይህ ብሏቸዋል።
ልክ እንደ ዛሬዎቹ እኛው አገር ምስለ'ኔዎች ማለት ነው!
የሕዝብን ስሜት በፍቅር ሳይገዙ የሕዝብን አካል በዐፈና መግዛት ፈለጉ የኢራኑ ፓህላቪ!
ፓህላቪ ተሸንፈው ቦታቸውን ለቀቁ።
ጀግናው ኃይሌ ገንረሥላሴ ግን ሲያሸንፍ አለቀሰ።
ኃይሌ ለኢትዮጵያ ሠንደቅ አለቀሰላት!
በነገራችን ላይ አፄ ቴዎድሮስም ለኢትዮጵያ አልቅሰዋል!!
ይቀጥላል!
#በታሪክ_ምንጣፍ_ከዛሬ_ደጃፍ
ታኅሣስ 17 ቀን 2014 ዓ.ም
#ጉዞ_በታሪክ_ምንጣፍ_ከዛሬ_ደጃፍ
======================
መነሻችን፦ በ322 ዓ.ም ጥንታውያኑ ወንድማማች ኢትዮጵያዊያን ነገሥታት ቤተ መንግሥትነት ለማነጽ ጀምረውት የነበረ ጥንታዊ የዋሻ ቤተ መንግሥት ነው።
#ኢትዮጵያዊ_ኤራቅሊጰስ_ስለ_ኢትዮጵያዊ_አቤሜሌክ
ኤራቅሊጰስ በነብዩ ኤርምያስ ዘመን የነበረ ታሪክን በዓይኑ ተመልክቶ በልሳነ ግዕዝ የተየበ ሊቅ ነበር፡፡ ኤራቅሊጰስ የታሪክ ጸሃፊ ብቻ አልነበረም፡፡ቴልስ ከተባለዉ የግሪክ ፈላስፋ ጋር በዓለም ታሪክ የመጀመሪያዉን ዓለም አቀፍ የፍልስፍና እሰጥ አገባ በማድረግ በታሪክ ዕዉቅና ከሚሰጠዉ ንጉሥ ዘግዱር (ለግዕዝ ፊደላት አናባቢዎችን የፈጠረ ሊቅ) በመቀጠል በዓለም የፍልስፍና ታሪክ ዉስጥ ተጠቃሽ መሆን የቻለ የፍልስፍና ሊቅም ነበር፡፡
ኤራቅሊጰስ ከዚህ ጊዜም ቀደም ብሎ ከሀገሩ ከኢትዮጵያ ተጉዞ በመካከለኛዉ ምስራቅ ታሪክመን መመዝገቡ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 38 ቁጥር 6 እና በዚሁ በትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 38 ከቁጥር 12-13 የተጻፈዉን ታሪክ ሳይዛነፍ ለመጻፍ የቻለ ጥንታዊ የታሪክ ጸሀፊ ነበር፡፡ ኤራቅሊጰስ የታሪክ መጽሐፉንም በራሱ ስም ኤራቅሊጰስ ሲል ነበር የሰየመዉ፡፡ የኤራቅሊጰስ መጽሐፍ ይዘቱ ለየት የሚልበት እና ከጥንታዊያ የታሪክ መዛግብት በአንጻሩ ተመራጭ የሚሆንበት ምክንያት ጥታዊ ህይወት ምን ይመስል እንደነበር እና የዘመናችንን ስልጣኔዎች ከጥቱ ስጣኔ ጋር ለማነጻፀር እንድንችል በዉብ የእጅ ስዕሎቹ አሥፍሮልን ማለፉ ነዉ፡፡
ኤራቅሊጰስ በታሪክ ዘገባዉ በጥንት ዘመን ከኢትዮጵያ ተነስተዉ ባሕር አቋርጠዉ የተጓዙ እና ስልጣኔን ባሕር ማሻገር የቻሉ የኢትዮጵያ ሊቃዉንት በርካታ ቢሆኑም በመጽሐፍ ቅዱስ ሳይቀር በእግዚአብሔር በነገስታት እና በሰዉ ፊት በቅድስና እና በጥበብ ተነስቶ ነብዩ ኤርምያስን ሳይቀር ከጉድጓድ በማዉጣት ሞቱን ወደ ህይወት ማሸጋገር ስለቻለዉ መፅሐፍ ቅዱስም በስፋት ስለተረከለት ስለ አቤሜሌክ በግዕዝ ሲገልጽ አቤሜሌክ እናቱ #ላቀች የምትባል በመንፈሳዊ ተግባራት የታወቀች ሴት እንደሆነች እና ቀደም ባሉ ዘመናት #አገረ_አማራ (ዛሬ ወሎ) በሚባለዉ ዋድላ ደላንታ ዉስጥ ወገደት በሚባለዉ መንደር የተወለደች ሴት ናት፡፡
አቤሜሌክ ለላቀች ብቸኛ ልጇ ነበር፡፡
የአቤሜሌክ አባትም ስሙ #አልቦዳ ሲሆን የትዉልድ አገሩ በጥንት መጠሪያዉ እናሪያ የዛሬዉ ከፋ ጊሚራ (ቤንች ማጂ) ነዉ፡፡የአቤሜሌክ አባት አልቦዳ ለማሳሔርታ (በዘመኑ ለነበረዉ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት) የሰላም ጠባቂ ኃይል ጠቅላይ አዛዥ ሆኖ ይሰራ ነበር፡፡
የዘመኑ የሠላም ጠባቂ ኃይል አሰማች የሚል መጠሪያ እንደነበረዉም ኤራቅሊጰስ በታሪክ መጽሐፉ ላይ አስፍሮታል፡፡
ንጉሠ ነገስቱም የኢትዮጵያን ህዝብ ለ20 ዓመታት መርቶ ያለፈ ታላቅ ጥበበኛ እና ቅን ፈራጅ ንጉሥ ነበር እንደ ኤራቅሊጰስ ይሁን ሌሎች የታሪክ ጠበብት ዘገባ፡፡
ይህ ከላይ የጠቀስነዉ ማሳሔርታ የተባለዉ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት በ2500 ዓ.ዓ ገደማ (ከክርስቶስ ልደት በፊት) እነደነበረ ቢገልጽም አንዳንድ የታሪክ ሊቃዉንት ይህ ጊዜ ከ1037-1057 ዓ›ዓ (ከክርስቶስ ልደት በፊት) እንደነበር ጽፈዋል፡፡
አቤሜሌክ አልቦዳ ገና የ9 ወር ጨቅላ ሲሆን አባቱ አልቦዳ በመሞቱ ንጉስ ማሳሔርታ ወስዶ ከልጆቹ እንደ አንዱ አድርጎ በቤተ መንግስቱ አሳደገዉ፡፡
ነግር ግን ብዙም ሳይቆይ አቤሜሌክ ገና የአንድ ዓመት ከ9 ወር ልጅ ሳለ ንጉስ ማሳሔርታ ሞተ፡፡ በመቀጠል የነገሰዉ ንጉሥ ራሜን ቀጣዩን የአቤሜሌክን የልጅነት ዕድሜ በኃላፊነት ተቀብሎ ብላቴናዉን እንደ ቀድሞዉ ንጉስ ማሳሔርታ በመንከባከብ ያሳድገዉ ነበር፡፡ ከንጉስ ራሜን ቀጥላ የነገሰችዉ ንግስት ማክዳም ብላቴናዉን አቤሜሌክን ተቀብላ በራሷ በንግሥቷ እልፍኝ ዉስጥ ለሚያድጉ ብላቴናዎች አዛዥ አድርጋ በታላቅ ክብር ያዘችዉ፡፡
አቤሜሌክ ከቤተ መንግስት ቤተ መንግስት እየተዘዋወረ በከፍተኛ ትምህርት እና እዉቀት አደገ፡፡ በመቀጠልም ንግሥት ኒኮትራስ ቅንደኬ 6ኛ በነገሰች ጊዜ ከቤተ መንግሥቱ ሳይለይ የኢትዮጵያ ሰላም ጠባቂ ኃይል (የአሰማች ሠራዊት) ኃላፊ ከመሆኑም በላይ በወቅቱ የነበረዉን ከፍተኛ ማዕረግ አግኝቷል፡፡
በዚህ ዘመን በንግሥቲቱ ኒኮትራስ ቅንደኬ 6ኛ ላይ ያመጸዉን ሩስሂል የተባለዉ የሜርዌ አስተዳዳሪ በማመፁ ምክንያት አስተዳዳሪዉን ይዞ እንዲመጣ በንግሥቲቱ ቢታዘዝም አቤሜሌክ በከፍተኛ የማግባባት ችሎታዉ ተጠቅሞ ሩስሂል ንግስቲቱን ይቅርታ አንዲጠይቅ እና ሰላም እንዲወርድ በማድረጉ ችሎታዉ እና ዝናዉ እጅግ ከፍ ብሎ ነበር፡፡
በዚህም ከፍተኛ ችሎታ እና ዝናዉ ምክንያት በወቅቱ በነበሩት የዕብራዊያን ህዝቦች ጋር የነበረዉን መራራቅ አስወግዶ በህዝብ እና በመንግስታቱ መካከል መቀራረብን እንዲያመጣ ታስቦ ወደ ዕብራዊያን አገር በእንደራሴነት (አምባሳደርነት) ሹመት ተልኮ ለብዙ ዘመናት እዛዉ ኖረ፡፡
በዚህ ወቅትም ሴዴቅ ለተባለዉ የዕብራዉያን ንጉሥ አማካሪ በመሆን ህዝቡን እምነት እንዲሁም መንግስትን የፖለቲካ ትምህርት በማስተማር ለከፍተኛ ደረጃ ማብቃት የቻለ ተደማጭ እንደራሴ (ዲፕሎማት/አምባሳደር) ለመሆን በቅቷል፡፡
በዚህ ዘመን በነብዩ ኤርምያስ ላይ የተደረገዉን አስነዋሪ ተግባር በማስወገድ የፈጸመውን ከፍተኛ የፍትሕ ተግባርም ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 38 ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
ኢትዮጵያዊዉ አቤሜሌክ አልቦዳ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ በጠቅላላ 55 ጊዜ ስሙ ተጠቅሶ የሚገኝ የእግዚአብሔር ሰዉ ነዉ፡፡
ምንጭ፡-ይህንን በራሴ አገላለጽ አጠር አድርጌ ያቀረብኩትን ጽሁፍ ሙሉ ታሪክ:-
እንደወረደ በግዕዝ ቋንቋ ማንበብ ለምትፈልጉ ዋግ ዝቋላ ሳይኮ አይጠገብ ብራንቋ ገብርዔል የሚገኘዉን መጽሐፈ ኤራቅሊጰስ ልሳነ ግዕዝ ከገጽ 99-600 ታገኙታላችሁ፡፡
በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 38፤6 እና ምዕራፍ 38፤12-13 ላይ ከነ ሃይማኖታዊ ይዘቱ ማግኘት ቻልኩ፡፡
#አትሳሳቱ!!!
የዓለማቀፉ ኃያላን በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ላይ ክፉ ማድረጋቸውን ቀጥለውበታል።
በእነርሱ ሴራ ምክንያት ብዙ ኢትዮጵያውያን ዕለት ዕለት የሞትን ጽዋ ይጎነጫሉ።
ሠላማዊ ዜጎች በግፍ ይገደላሉ።
ነገር ግን በሼረቡት ሴራ ለሞትን ለእኛው ተቆርቋሪ መስለው ሲያሸረግዱ ከትዝብት ሌላ ምን ይባላል?
ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያውያን የቆምንበት የሞራል የበላይነትም የያዝንበት ሐቅ ቢገባቸው ሰብአዊነትን ከእኛ በተማሩ ነበር።
ሕዝባችን በአምልኮተ ፈጣሪ ሕግ የሚኖር ከወታደር እስከ ሲቪል ፤ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ፈጣሪውን የሚፈራ ሕዝብ ነው እንጂ ወንድሙብ በግፍ የሚገድል አረማዊ ማንነት ያለው ሕዝብ አይደለም።
✍✍✍✍✍✍✍✍✍
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ወታደር ይኹን ሲቪል ልሂቅ ይኹን ደቂቅ የቅዱስ ቁርዓን አስተምህሮ የሚኖር ፤ ለሕግጋቱም የሚገዛ እንጂ ከፈጣሪው ትእዛዝ አፈንግጦ ወንድሙን በከንቱ አይገድልም።
አይጠላምም!!!
﷽﷽﷽
ﮨ ﮩ ﮪ ﮫ ﮬ ﮭ ﮮ ﮯ ﮰ ﮱ ﯓ ﯔ ﯕ ﯖ ﯗ ﯘ ﯙ ﯚ ﯛ ﯜ ﯝ ﯞ ﯟ ﯠ ﯡ ﯢ ﯣ
ﯤ ﯥ ﯦ ﯧ
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡"
#ሱረቱ አል-ማኢዳህ 5:8
✍✍✍✍✍✍✍✍✍
እንዲኹም ማንኛውም ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ ከዚህ በታች በሚነበበው የቅዱስ ዳዊት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ አፈንግጦ ጊዜ እና ጉልበትን ተገን አድርጎ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ከመልአክትም የላቀ ክብር የተሰጠውን የንፁህ ሰው ደም በከንቱ አያፈስስም።
“ሰዎቹንም፦ እግዚአብሔር የቀባው ነውና እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር አደርግ ዘንድ እጄንም እጥልበት ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው አላቸው።”
1ኛ ሳሙኤል 24፥6
እናም ንገሩልን ለኃያላኑ ፤ ሕግ የሚከበርባት አጥፊዎችም የሚቀጡባት የሠላም ምድር የኾነች ኢትዮጵያ ለዓለም ሕዝቦች ኹሉ በልዩነት አንድ ኾኖ የመኖርን ጥበብ ታስተምርላችኹ ዘንድ የአሻጥር እጆቻችኹን አሳርፉ ፤ በወንድማማች ሕዝቦች መካከል ጸብን ከመዝራትም ተቆጠቡ በሉልኝ።
ሠናይ ምሺት!!!
ያት ጥበብ ትክክለኛነት እና የቅዱስ መጻሕፍት የጊዜ ልኬት መሠረትነቱ ብቻ ሳይኾን በመለኮት ፈቃድ ትንቢትን ይናገሩ የነበሩ ጥንታውያን በሙሉ በተመሳሳይ ሊቃውንት አባቶቻችን ዛሬ ድረስ ይሻገር ዘንድ ያወረሱንን ሓሳበ ኢትዮጵያ የሒሳብ ሥሌት ትክክለኛነት በመመስከር ዳግም አሸናፊነታችንን የመሰከረበት እውነት!!!!!!!
ለመሆኑ ሰውየው ሌሎች ምን ምን አሳማኝ ጉዳዮችን ተንብዮ አልፏል? ለምትሉኝ እነኾ ትንሽ እውነታዎችን ላካፍላችሁ።
ይህ ሰውዬ እ.ኤ.አ እስከ 3797 ዓ.ም.ም ምን ሊከሰት እንደሚችል በመፅሐፍ ጽፎ አስቀምጧል።
እርሱ እግዚአብሔር አይደለምና ሁሉን ያውቃል ባይባልም።
የዚህን ሰውዬ ትንቢት ለየት የሚያደርገው ድርጊቶቹ የሚፈፀሙበትን ትክክለኛ ቀን፣ቦታ እና አንዳንዴ ደግሞ የሰዎችን ስም መጥቀሱ ነው።
ለምሳሌ፦ሂትለር እንደሚመጣና የስዋስቲካን ምልክት (ጠልሰም) እንደሚጠቀምበት ጭምር ገልፃል።
ስለ ፔንስሊን መድኃኒት መፈጠር ይናገራል።
ስለኤች አይቪ ቫይረስ፣ ከላይ ስላነሳሁት ስለ 9/11 እና ስለጆን ኦፍ ኬኔዲ አሟሟት፣ ስለፈረንሳይ አብዮትና ስለ ጉልቶኒ አሟሟት ያለ እንከን እንደተነበያቸው ተፈፅመዋል ከሚባሉለት ትንቢቶቹ መካከል ተጠቃሾች ናቸው።
ማሳሰቢያ፦
ይህ እውነት ከምእራባውያኑ የካሌንደር ቀመር ጋር ተጣጥሞ ቢፈጸም ኖሮ እየንዳንዱ ሚዲያ በምን ያህል ደረጃ ሺፋን ይሰጠው የነበረ ስለመኾኑ ለአንባቢያን ልተወውና የዘመኑን ነባራዊ ኹኔታ በአስተዋይ ልቦና ትመረምሩ ዘንድ ዘመኑ በሰጠን የመገናኛ ስርዓት ይህቺን ተከታታይ ጽሑፍ ሳቀርብላችሁ ምናልባትም በጣት የሚቆጠሩ ዓመታት የቀሩትን የኢትዮጵያ ትንሣኤ እና የከፍታ ዘመን ሊመለከቱ ተመኝተው ለዚህ ዕድል መብቃት ያልቻሉ የአገር ባለውለታዎች እልፍ ኾነው ሳለ ያለ ማስተዋል የተጓዝን እኛ በዋዜማው ላይም ቢኾን ኖረናልና ምን ያኽል እድለኞች እንደኾንን እናስተውል ዘንድ ነው።
"ይህን የሚመሰክር። አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። #ዓሜን_ማራናታ_ጌታ_ኾይ_ቶሎ_ና! ።"
የዮሐንስ ራእይ 22:20
ገዋት እንደነበር ይህንን ኹሉ ጥበብም ባሕር ማዶ አሻግረው የዛሬውን ዓለም በከባድ እንቆቅልሽ ውስጥ ዘፍቀውት የተሻገሩ ድንቅ ሕዝቦች እንደነበሩ በጥናት ተረጋግጧል?
#ሓሳበ_ማያውያን
ማያውያን ጥንታውያን የሥነ ከዋክብት ምጡቅ ታሪክ ያላቸው ጥቁር ሕዝቦች ናቸው።
እነዚህ ጥቁር ዕንቁዎችም የኢትዮጵያችን ጠበብት ልጆች እንደኾኑ በርካታ የታሪክ አሻራዎች ያረጋገጡ መኾኑንስ ስንቶቻችን እናውቃለን?
አዚህ ጽሑፍ ዓላማ የጥበብ ኹሉ የኾነችው ኢትዮጵያ በዓለም የሥልጣኔ ጉዞ ላይ ያበረከተችውን አልፋ እና ኦሜጋ ውለታዎች መዘርዘር በመኾኑ ምንጮቼን ለአንባቢ ጠቅሼ ወደ ዋናው መነሻ ሐሳቤ ለማለፍ እወዳለሁ።
በመኾኑም ይህንን ሐቅ ማረጋገጥ የሚፈልግ የዛሬ ዘመን የታሪክ አሳሽ ይህንን ጽሑፍ ሲመለከት ምንጭ ከምን ቢል They Game before colombus, The African princes in ancient America የተሰኘውን የኢቫን ቫን ሰርቲማ (ivan van sertima) ድንቅ የታራክ መዝገብ መመልከት አልያም ሼክ አንታ ዲዮፕ (Cheikh Anta Diop) የጻፈውንና ሜርሠር ኩክ (Mercer Cook) ወደ እንግሊዝኛ የተረጎመውን "The African origin of civilization, myth or reality" የተሰኘ መጽሓፍ እንዲሁም John.G Jackson (ጆን ጂ ጃክሰን) "Ethiopia the origin of civilization" ሲል በጥልቅ ጥናታዊ ትንታኔ የጻፈውን ጨምሮ መጻሕፍትን ማገላበጥ የበለጠ ጥርት ብሎ የሚታይ ጉልህ ማስረጃዎችን ለመመልከት ይጠቅማሉ እላለሁ።
በተጨማሪም እነዚህ ማያ የተባሉ ሕዝቦች መጠሪያ ስማቸው ማያ(መመልከቻ) ከሚለው ማሕበረሰባዊ ስያሜያቸው ባሻገር ይጠቀሟቸው የነበሩ በርካታ ቃላትም ከእኛው ግእዝ አማርኛ ትግርኛ ወዘተ ሴማዊ ቋንቋዎች ጋር ተመሳሳይ ሥነ ልሳን እንደነበራቸው ለመረዳትም በተለይ ለኢትዮጵያዊ አጥኚዎች ማያውያን የተባሉ ሕዝቦችን ታሪክ ማጥናት ብቻ በቂ ግንዛቤ ይሰጣል።
ወደ ማያ ሕዝቦች የዘመን ቀመር ስንመለስ ምናልባትም እነዚህ ሕዝቦች ለዘመናት ከቀሪው ዓለም ተነጥላ እና ተሠውራ ኖራ ክርስቶፈር ኮሎምበስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሰሣ አግኝቷታል ተብሎ በታሪክ ድርሣናት ላይ የተጻፈላትን የዛሬዋን ታላቅ አህጉር (አሜሪካን) ከክርስቶፈር ኮሎምበስ እጅግ ብዙ ሺህ ዘመናትን ቀድመው የረገጧት የኖሩባትና ትንግርታዊ የሥነ ከዋክብት ጥበባቸውን በድንጋይ ላይ ቀርጸው ያኖሩባት ሕዝቦች ናቸው።
ይህ የማያውያን የቀን አቆጣጠር ቀመር በዚህ ዘመን ልሂቃን ላይ በምን ያህል ደረጃ ተጽእኖ የፈጠረ መኾኑን ለመገንዘብ ደግሞ በመገናኛ ብዙሃኖች ከፍተኛ ትኩረት ስቦ የነበረውንና የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ ይፋ የኾነውን "2012" የተሰኘውን የአሜሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ ሆሊውድ የሠራውን መሠረቱም የእነዚሁ የማያ ሕዝቦች ካላንደር የኾነውን እጅግ ከፍተኛ ገቢም ለኢንዱስትሪው ያበረከተውን ፊልም መመልከት ነው።
2012......
2012ን በተመለከተ ከተያያዥ ኩነቶች ጋር አያይዤ የምነግራችሁ ትንሺዬ መረጃ ብጤ ትኖረኛለች እመለስበታለሁ.....
በተረፈ ባለቃልኪዳኖቹ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ቸር እደሩልኝ!
(ዘረኛ፣ ጎጠኛ፣ ቋንቋ ተኮር አሳቢ፣ የዘውግ በሺታ ተጠቂ፣ ፌደራሊስት ወዘተ የኾናችሁ ግለሰዎች………የዚህ ዓይነት ጽሑፍ እንቅልፍ እንቅልፍ ይላችኋል አትጀምሩት፤ አልፎ ተርፎ የዝግመተ ለውጥ እድገታችሁ እንዲህ ዓይነት ቁምነገሮችን ለመገንዘብ አልደረሰምና ከገፄ ላይ በፍጥነት ጡርግ በሉ😅)
✍✍✍✍✍✍✍✍✍
ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውት የአገሬ ልጆች አርበኞቹ፣ ጀግኖቹ፣ ፈላስማዎቹ፣ መሣፍንተ ኢትዮጵያ ግን ይህቺን ጽሑፍ ለማዘጋጀት ከፍተኛ ትኩረት መስጠትና እንደ አባቶቻችን እንደ ኢትዮጵያኑ ወግ የክብር ግብዣ አሰናድቻለሁና የአባቶቻችሁን ድንቅ ጥበብ ተጋበዙልኝ።
በነጮቹ አዲስ ዘመን መባቻ ዕለት ስለ ማያውያን የተወሰኑ መረጃዎችን ላካፍላችሁ ቃል ገብቼም አልነበር?
ይህቺን ላካፍላችሁ ያሰብኳትን መረጃ ላደርሳችሁ የምችለው ደሞ በማሕበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጽ ከመኾኑ አንጻርና መሠረታዊ ግንዛቤ ያለው ሰው አነስተኛ ይኾናል ከሚል ግምት በመነሳት መሠረታዊ ግንዛቤ ሳይኖር ይኽንን ጽሑፍ ለመረዳትም እጅግ ውስብስብ የሚኾንባቸውን አንባቢያን በቂ በኾነ የግንዛቤ መሠረት የማስረዳት የሞራል ግዴታ ፈጥሮብኝ ከመሠረታዊ የጋራ ግንዛቤአችን ልጀምር።
ወደ ዋነኛው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ዘመን የማይሽረው ፍልስፍና አብረን እንንደረደር ዘንድም እንደ መግቢያ አጠር ያለች ሃተታ ብቻ ለማቅረብ ግዴታ ኾኖብኝ እነኾ አጪሯን መንደርደሪያችንን እንደ በአል ሥጦታ ተጋበዙልኝ
✍✍✍✍✍✍✍✍✍
ኢትዮጵያ
ዓለምን በሥሌት ደግማ የረታችበት የጥበብ ማሕጸንነቷን ዳግም ያረጋገጠችበት ክስተት!
(ዋናው ማጠንጠኛችን ነው)
የሰው ልጅ አእምሮ እውቀትን የመቀበል ደረጃው እጅግ መጥቋል በምንልበት በዚህ ዘመን ኹሉንም በየደረጃው የሚያግባቡ ብዙ ግንዛቤዎች እንዳሉ ይታወቃል።
ከእነዚህ የጋራ ግንዛቤዎቻችን መካከልም አንዱ የምንኖርባት መሬት እጅግ ግዙፍ በኾነ ሕዋ ላይ ከሚገኙ ፕላኔቶች አንዷ ስለመኾኗ ነው።
መሬት ብቻ አይደለችም።
ኹሉም የሰማይ አካላት ማለትም ፕላኔቶች ኮሜቶች ከዋክብት (ሕዋ ከብት) ወዘተ በየራሳቸው ምሕዋር የሚንቀሳቀሱ እና የየራሳቸውን ምሕዋር ለመዞርም የተለያየ የጊዜ ብዛት የሚፈጅባቸው ናቸው።
ይህ በራሳቸው ምሕዋር የመሽከርከር ተፈጥሯዊ ዑደት እንዳለ ኾኖ ከላይ የጠቀስኳቸው ምድራችን እና የከዋክብት ክምችቶቻችን ጨምሮ ሌሎችም እህትና ወንድሞቻቸው በአብዛኛው በፀሓይ ዙሪያ የሚሽከረከሩ እረፍት አልባ ባተሌ ፍጥረታት እንደኾኑ ግልጽ ነው።
ነገር ግን ይኽ ኹሉ ግዝፈተ ዓለም በዙሪያዋ የሚሾር የሚሽከረከርላት ፀሓይ የተባለች የእሳት ኳስ የኹሉ ማእከል የኾነችው ያለ ምንም እንቅስቃሴ ነው ወይንስ እሷም ሌላ የሚበልጣትን አካል ትዞራለች?
nothing is at rest, everything is in a constant motion ይለናል ፊዚክሱ።
የቆመ ብሎ ነገር በተፈጥሮ ውስጥ የለም። ኹሉም ነገር በዘላለማዊ እንቅስቃሴ ላይ ዐለ። ይኖራልም። ይህ ማለት ታዲያ ፀሓይም ትሽከረከራለች ማለት ነው።
በምን ዙሪያ?
በራሷ ምሕዋር?
የራሷ ምሕዋር ምንድን ነው?
ወተታማው ሕብረ ሰማይ (ሚልኪዌ) ጋላክሲ።
ሥርዓተ ፀሓያችን ኅልቆ መሣፍርት ከኾኑ ሥርሥዓተ ፀሓዮች አንዱ ሲኾን የእኛ ሥርዓተ ፀሓይ ዋና ማእከልም ይኸው ሚልኪዌ ክፍለ ሰማይ እንደኾነ እና በዚህ ክፍለ ሰማይ ማእከላዊነት ሳታቋርጥ ለዘለዓለም የምትሽከረከረው የሕይዎቶቻችን ኹሉ የኾነችው ፀሓያችን በምሕዋሩ ላይ አንድ ዙር ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ደግሞ አንድ ሚሊዮን ሥምንት መቶ ሰባ ኹለት ሺህ የእኛ የምድራዊያኑ ቀናት (1,872,000 ቀናት) ያህል ነው።
አጃኢብ አትሉም።
ስንት ዓመት ማለት ነው?
1872000፥365.25 ብሎ ማስላት ነው።
ከ5125.25 ምድራዊ ዓመታት በላይ ማለት ነው።
ይኽም ማለት የእኛዋ መሬት 5125.25 ጊዜ በፀሓይ ዙሩያ ስትዞር ፀሓይ ደግሞ በማእከሏ በሚልኪዌ ላይ አንድ ጊዜ ትዞራለች ማለት ነው።
ገደማ ለፀሓይ አንድ ዓመት እንደማለት ነው።
ይህ የፀሓይ ዙር የሚጠናቀቀውም እያንዳንዳቸው 20 ቀናትን በያዙ 13 ዓውዶች (ዙሮች) በመጀመር እና 13ቱ ዓውዶች ሌላ 27 ዓውድ ፈጥረው 7200 ዕለታት ከተቆጠሩ በኋላ 7200ዎቹን ዕለታ በሌላ 20 ዓውድ (ዙር) አባዝተን 144,000 ዕለታትን በመቁጠር ነው።
እነዚህ 144,000 ዕለታትም በራሳቸው እንደ ዘመን እየተቆጠሩ 13 ጊዜ 144,000 ቀናትን ቆጥረን ስንፈጽም ጠቅላላው የሕዋ ታሪክ የሚዘዎርበትንና የሚለወጥበትን 1,872,000 ቀናት እናገኛለን ማለት ነው።
20*13=260
260*27~7200
(19*365.25 ማለት ሲኾን ይኽም የባሕረ ሓሳቡ አውደ ቀመር ጋር ተመሳሳይ ጊዜን ይሰጠናል።)
7200*20=144,009
144,000*13=1,872,000
#ምስጢረ 144,000 (አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ)
የዮሐንስ ራእይ 7፥4
የዮሐንስ ራእይ 14፥1
የዮሐንስ ራእይ 14፥3
የዮሐንስ ራእይ 21፥17
ከላይ ያኖርኳቸው ጥቅሶች ቅዱስ ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት ላይ በነበረ ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ከተማረው መለኮታዊ ቅኔ ጋር ቁጥሮቹ የተቀመሩ መኾናቸውን የሚያስረዱ ጸሓፍት በመኖራቸው በዚሁ ጥቆማ ሰጥቼ ለማለፍ ነው።
ሌላው በግብጽ ፒራሚድ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ምሁራን ፒራሚዶች በእያንዳንዱ ገጽ ላይ እኩል መጠንና እፍግታ ያላቸው 144,000 ድንጋዮች እየተነባበሩ ጠቅላላውን 13 ማእዘን የሚፈጥሩ ስለማኾናቸው መጻፋቸውም ቁጥሩን አስገራሚ ያደርገዋል።
በተጨማሪም በቅዱስ መጽሓፍ ተርጓሚያን ዘንድ በተለይ የግእዝ ሊቃውን የሰው ኹሉ አባት የኾነው አባታችን አዳም የስሙ ቁጥር 144 እንደኾነ እና ዳግማዊ አዳም ኾኖ ወደ ምድር የወረደው የአብ ልጅ ልዑሉ መሲሕ ኢየሱስም የስሙቁጥር 144 መኾኑ ኢየሱስ=አዳም (አምላክ ሰው ኾነ) የሚል ረቂቅ ቅኔ ያስተምራሉ።
አዳም (አ=40 ደ=100 መ=4)
ድምር 144= (12*12)
ኢየሱስ (አ=40 የ=90 ሰ=7 ሰ=7) ድምር 144= (12*12)
ኢትዮጵያ እና #የማያ_ካለንደር ቁርኙት ከምን እስከ ምን የሚለውን ግሃዳዊ ሃቅ እንዲኹም የፀሓይ 1,872,000 ቀናት ጉዞ መፈጸም ሣይንሳዊና መንፈሳዊ ምስጢራት ምን ምን እንደሚመስሉ በግርድፉ የምመለስበት ይኾናል።
በተረፈ ባለቃልኪዳኖቹ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ቸር እደሩልኝ!
መድብሌን በሰላም ለመገላገል ከጫፍ መድረሴን እያበሰርኩ በዚህም የተሰማኝን ታላቅ ደሰታ ልገልፅላችሁ እወዳለሁ።
እናም እንኳን ማርያም ማረችሽ/ህ የመባባሉ ባህላችን እንዳለ ኾኖ #ዲዮጋን ስል የሰየምኳትን የበኩር መድብሌን ገዝታችሁ በማንበብ (የዓይን አባት) በመሆን የአገራችን ጌጥ የኾነውን የሥነ ግጥም ዘርፍ የማሳደግ ጥበባዊ ግዴታ እንዳለባችሁ ይዘነጋል ብዬ አላምንምና ይኸቺን ከጥበብ ምጥ ግልግል በኋላ የተገኘች እፎይታና ደስታዬን ላልሰሙ የጥበብ አፍቃሪያን ታደርሱልኝ ዘንድ እነኾ የፊት እና የኋላ የሺፋን ገጿን ዋቢ አድርጌ ከፊታችሁ አቀረብኩ።
እናም መልዕክቴን ለሌሎች ትደርስ ዘንድ በተቻላችሁ መጠን እንድታጋሩልኝ (share) እንድታደርጉልኝ ስል በእክብሮት እጠይቃለሁ።
ከምስጋና ጋር
ከ ዲ ዮ ጋ ን አባት
ከበእምነት ተስፋዬ ታደሰ
ከኾነው ስልት በተቃርኒ ማለት ነው። ከሪቮሉሽኑም ከመንደሩም ከሕዝቡም ተለይተው ያሉትን ማለቴ ነው። ቴዎድሮስ በዚህ ዓይነት ረዳት አጥቶ ብቻውን ባዝኖ ከተራራው ላይ ወጥቶ ሽጉጡን እንዳጉረሰ ለአገሩ አልቅሶ ለራሱ ግን ራሱ በእጁ ያጎረሰውን ሽጉጥ ጎረሰው።
ከ1945-48 አካባቢ ከዋሽንግተን አር ቪንግ ውብ ብዕር ያፈለቀ ሪፕ ቫን ዊንክል (Rip Van Winkle) የተባለ መጽሐፍ ነበር።
መጽሐፉ ሪፕ ቫን ዊንክል ለኻያ ዓመታት መተኛቱን ይተርክልናል። ለመተኛትም የመረጠው አንድ ትልቅ ተራራን ነበር። ሪፕ ላኻያ ዓመት እንቅልፉ ወደመረጠው አንድ ትልቅ ተራራ ጫፍ ሲሔድ አንድ ትልቅ ምልክት አዬ። በምልክቱ ላይ ከዚህ በፊት የነበረውል ሥዕል ሪፕ ቫን ዊንክል ያስታውሳል። የእንግሊዙን ንጉሥ የጆርጅ ሣልሳዊን ምስል ነበር እዚህ ቦታ ላይ የሚያውቀው። ጆርጅ ቫን ዊንክል ለ20 ዓመታት እንቅልፉን ለጥጦ ከተራራው ላይ ሲወርድ ግን ወደ ተራራው ጫፍ ሲወጣ የተመለከተውን የእንግሊዙ ንጉሥ የጆርጅ 3ኛ ምስል በቦታው የለም። ይባስ ብሎ በቦታው ቫን ዊንክል የማያውቀው የአዲስ ሰው ምስል ተለጥፎበታል። (የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት የጆርጅ ዋሽንግተን ምስል)
ይኽ ደግሞ ማን ነው ሲል ራሱን ይጠይቃል ቫን ዊንክል።
ድንግርግር አለው። ተገረመ። ማን እንደኾነ አላወቀም። እሱ በእንቅልፍ ዓለም በቆየባቸው ኻያ ዓመታት በአሜሩካ ታላቅ ሪ ቮሉሲዮን ተቀስቅሶ ኖሮ አሜሪካ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ወጥታ አዲስ መሪ አግኝታ አዲስ አቅጣጫ መያዟንና ወደ አዲስ ዓለም መግባቷን አላወቀም ነበር። ይህ የሚያሳየም ሪፕ ቫን ዊንክል ለኻያ ዓመታት መተኛቱን ብቻ አይደለም። ወደ ታላቅ ሪ ቮሉሲዮን (አብዮት!) ውስጥ እየገባች በነበረች አገር ውስጥ እየኖረ ለኻያ ዓመታት ወደሚተኛበት የተራራ ጫፍ መሰደዱን ነው ዋሽንግተን አርቪንግ በመጽሐፉ ያሳዬን።
ቫን ዊንክል በተራራ ላይ ኾኖ የስንፍና እንቅልፍ ውስጥ ገብቶ ሲያንኮራፋ በሚኖርባት አሜሪካ ውስጥ ትልቅ ሪቮሉሲዮን እየተካሔደ ነበር።
ለዛውም የአሜሪካን ብቻ ሳይኾን የዓለምን ገጽታ በእጅጉ የሚለውጥ አብዮት ውስጥ፤ ታሪክ እየተሰራ በነበረበት ሪቮሉሲዮን ውስጥ ቫን ዊንክል ያንኮራፋ ነበር!
ልክ እንደ እኛ!
እንደ ዛሬዎቹ ኢጵያውያን።
ይቀጥላል......
@eyori
ባሳለፍነው የጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ተከታታይ የኾኑ ጽሑፎችን ጋብዣችኋለሁ።
በዋናነትም ከራስ ጋር በተደረገ ቃልኪዳን የተቀጣጠለው የኃይሌ ገ/ሥላሴ የአትሌቲክስ ሪቮሉሲዮን አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ድረስ ገናናነቱ ያልተደፈረ የበላይነት እንድትይዝ ማስቻሉን እና ኢትዮጵያውያን ጀምረን አሳክተናቸዋል ብለን ልንጠራቸው ከምንችላቸው ሪቮሉሲዮኖች ምናልባትም አቻ የሌለው እንደሆነ......
ኃይሌ ያለቀሰላት ሰንደቅ ዛሬም ከከፍታዋ ዝቅ ያላለች የዓለም አትሌቲክስ ጌጥ ስለመኾኗ ለማሳየት ሞክሬ ነበር።
ጎን ለጎንም በፍትህና ርትእ ጉዳይ ግን ኢትዮጵያ የብዙዎችን እንባ ጠጥታ ዝም ያለች የጀግኖች እንባ የአብዮተኞች ልቅሶ እፎይታን ያላመጣለት አገር እንደኾነች ለማንሳት ሞክሬ ነበር።
ለመደምደሚያነት የመረጥኩትም "ይኽ ትውልድ በውዥንብር ውስጥ እያለፈ ይገኛል። መጭዎቹም ትውልዶች በዚህ ዓይነት ቱማታ ውስጥ ሊያልፍ አይገባውም። ሥለዚህ የዛሬውን ትውልድ አበሳ ለማቃለል ሰባ የነገው ትውልድ የሌላ ዙር አበሳ ተሸካሚ እንዳይኾን እንደ ቢድሂስት መነኮሳት ራሱን የሚያቃጥል ቢያንስ ቢያንስ የሙያለቅስ ቴዎድሮስ፥የሚያለቅስ በላይ ዘለቀ፥ የሚያለቅስ ገርማሜ ነዋይ፥ የሚያለቅስ አሥራት ወልደየስ ያስፈልገናል።" በማለት ነበር።
አዎ....ኢትዮጵያ ዛሬ ድረስ ልቅሶ የምትሻ እና እያነባች ያለች አገር ነች።
ይኽ ልቅሶ የኹሉም ልቅሶ ነው።
ዘመኑ እየከፋ ሽማግሌ በአገር እየጠፋ ለጊዜውም ቢኾን እውነት ለሐሰት ቦታዋን ለቀቀች እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ከአንድነታችን ያፈነገጠ አማራጭም ምርጫም ያለን ሕዝቦች አይደለንም።
ይኸ ጥንት ድረስ ሔደን እናጥና ብንል መሠረቱን የማናገኘው ሕዝብ ልጆች ነንና ወደድንም ጠላንም አንድ ሕዝብ ነን። ሕዝቡ አንድ የእድላችንም ኮኮብ ያው አንድ ትልቅ ኮኮብ የኾንን ሕዝብ፤ የሕልማችን ሻማ አንድ ደማቅ ሻማ፤ ተስፋችንም በአንድ ክር የተሰፋ ሕዝብ ነን። እንደ አንድ የምንነድ እንደ አንድ የምናበራ ውሕድ የኾንን የተጋመድን ሕዝብ!
ያለፉት አባቶች በዚህ እምነት ኖረው አልፈዋል የሚመጣውም ትውልድ በዚኹ እምነት ይቀጥላሉ። አንድ ከመኾን ውጪ ተፈጥሮ ሌላ ምርጫም ተፈጥሮአዊ ማንነትም ያልፈጠረችበት አንድ ትልቅ ሕዝብ!
ለዚህም እምነት አባቶች እንደታገሉት የዛሬዎቹ እኛ እንታገላለን። እኛ በአግባቡ ካታገል-በአንዳንድ ደካማ እና ሰነፍ ፖለቲከኞች፤ በአጠቃላይ በጊዜው በሰፈነው የግርግር ፖለቲካ ካልተሳነፍን- መጪዎቹም ትውልዶቻችን ለዚሁ ኢትዮጵያዊ እምነት ይታገላሉ።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ ትውልድ አባላት የግፍና የፍዳን ሸክም ተሸክመን ኖረናል። ኦሮሞው ተሸክሞ ኖሯል። አማራው ተሸክሞ ኖሯል። እስካሁን ድረስ ምናልባትም በባሰ ኹኔታ ግፉን ኹሉም ተሸክሞታል። ይሳደዳል፣ ይታሰራል፣ ይገረፋል፣ በጥይት አረር ይቆላል፤ ምን ያልታሸከመው አበሳ ይገኛል የኢትየጵያ ሕዝብ?
ግዙፉን ግፍማ መግለጥም አይኖርብንም። ዓለም እያወቀው ሔዷልና። የዛሬውን ግፍ እና ሕዝባዊ ሰቆቃ ለማጠቃለል ካስፈለገ "ሥቃያችን ኹሉ-ሸክማችን ኹሉ የገዢዎቻችንን የውርደት መጠን አመላካች ነው" ለማለት እንችላለን።
በኋላ ላይ እምባገነንነታቸው ወደር የሌለው መኾኑ የሚነገርላቸው የኢራኑ ሼህ ኤንድ ሻህ ፓህላቪ እንደተናገሩት "ለአንድ መንግሥት ጎስቋላ እና ድሀ ሕዝብ መግዛቱና መንዳቱ የኩራት ምንጭ ሊኾን አይችልም።" ይበልጥ ደግሞ በሰደፍ የሚገዛ መንግሥት ወደ ሽፍትነትና ሌብነት ማምራት ሲጀምር የሞራል ኅይልና ኩራት (የሰልፍ ፕራይድ) እንዲሁም የክብር (የዲግኒቲ) ድሀ እየኾነ ይሔዳል። እዚያ ደረጃ ላይ ነው እኛ ያለነው? ወይስ የተሻለ ደረጃ ላይ? ወይስ አንድ የዝቅጠት ዙር ፈጽመን የሌላ ዝቅጠታችን ጎዳና የመጀመሪያ ወራት ላይ እንገኛለን?
ግልጽ ነው!
ኢትዮጵያውያን የሌላኛው ዙር የዝቅጠታችን ጎዳና የመጀመሪያ ወራት ላይ እንገኛለን?
ለምንድነው ታዲያ ቢያንስ ቴዎድሮስ የተመኘልን ዓይነት ኢትዮጵያ ዛሬ ድረስ መፍጠር ያልቻልነው?
እውነት በአገረ መንግሥት ምስረታው ረገድ አንድ የኃይሌ ገ/ስላሴ ዓይነት አርበኛ አልዋጣልን ብሎ ነው?
ኃይሌን ደጋግሜ ያነሳሁት ለከንቱ ውዳሴ አይደለም!
በአንድ ወቅት የኃይሌን ሕይወት ተመልሼ ስመለከት በራሴ እፍረት ተሰምቶኝ ያውቃል።
ብሔራዊ ጀግኖች ሲባል እነ ገበየሁ፣ እነ ባልቻ ሳፎ፣ እነ አሉላ ቁምቢ፣ እነ ዘርአይ ድረስ፣ እነ አብዲሳ አጋ እነ አበበ አረጋይ፣ እነ ኃይለማርያም ማሞ፣ እነ በላይ ዘለቀ፤ እነ ሙሉጌታ ቡሊ፣ እነጃገማ ኬሎ፣ እነ ጣይቱ ብጡል፤ እነ ስንዱ ገብሩ ወዘተ ብቻ ይመስሉኝ ነበር።
ነገር ግን እነ አበበ ቢቂላ፣ ማሞ ወልዴ፣ ምሩጽ ይፍጠር፣ በላይነህ ዲንሳሞ፣ ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮና፣ ብርሀኔ አደሬ......የመሳሰሉ አገራቸውን ከራሳቸው አስቀድመው፤ ኢትዮጵያን ከፊት አድርገው ጀብድ የፈፀሙም ከአርበኞቻችን ከአርበኞቻችን እኩል ብሔራዊ ጀግኖች ናቸው!
ቴዎድሮስ ይህንን ዘመን አስቦ ይኾን ያለቀ ሰው? ቴዎድሮስ በፍቅር የተለሰነ ነፋስ የማይገባው አንድነትና በእኩልነት የቆመች ኢትዮጵያ ለመመሥረት የዘመነ መሣፍንት ጊዜ በማሕተም ይዘጋ ዘንድ (ያከትም ዘንድ) የተቻለውን ያኽል ጥረት አደረገ። ነገር ግን ዘመኑን ቀድሞ የተፈጠረውን ቴዎድሮስን መረዳትና መርዳት ያልቻሉት ፊውዳሎች፣ ቀሳውስት፣ የቅርብና የሩቅ መሣፍንቶቹ ሳይቀሩ ክህደት አደረጉበት። ከቶውንም በሕልሙ የሳላትን በምናቡ የቀረጻትን ኢትዮጵያ ሊያንጻት ደፋ ቀና ሲል ብቻውን ቆሞ መቅረቱንና ያቺን የምናቡን ኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን መቶ አምሣ ዓመታት ያህል ችግር ያልተለያትን ነባራዊዋን ኢትዮጵያ ሳይቀር የዘውድ ተስፈኛውም ባለ ትልልቅ ሆዱ ዜጋም እንደከዳት የሥጋ ዓይኑን ጨፈን አድርጎ በሕሊና ዓይኑ ተመለከታት ቴዎድሮስ። ቴዎድሮስ የ1860ዋን ኢትዮጵያ ብቻ አልነበረም በሕሊና ዓይኑ አሻግሮ የተመለከታት። የ1960፣ የ2060፣ የ2160ዋንም ኢትዮጵያ ጨምሮ እንጂ! ምናልባትም እስከ ፍፃሜተ ዓለም ያለዥውን ኢትዮጵያ ሳይቀር በፍጥነት በፍጥነት በፍጥነት ገጾቿን እየገለጠ ለማየት ሞከረ።
አለቀሰ!
ደም!
እስቲ አንድ የዛሬ የፖለቲካ ሰው ምናልባትም አንድ ከፍተኛ የአገር መሪ እናስብ። "የነበረኝን ራእይ ትንሽ እንኳን ተፍባራዊ ሳላደርግ፤ ይኸንን ሕዝብ ከችግር እገላግለዋለሁ እያልኩ ስጨነቅ-የኢትዮጵያን መልክ እለውጠዋለሁ ስል፣ እንዲህ ኾኜ ልቀር ነው?" ብሎ ያለቅሳል?
በፍጹም!
ለማልቀስ የጀግና ልብ፤ እውነት ያደረበት ልብ፤ ፍቅር ያደረበት ንጹሕ ልብ፤ ሞራል እና ኀይማኖት የሚገዙት ተፈጥሯዊ የሰው ልብ ያስፈልጋል።
ለኢትዮጵያ ቀና አጀንዳ ትክክለኛም ራእይ አላቸው ተብለው (ተቃራኒው ካልኾነ) የማይታሙት ወገኖች እንባም ኾነ በልባቸው ሥር ደም ያላቸው አይመስለኝም።
የአፄ ዮሐንስን ልቅሶዎችእንደ መረጃ ጠቁሜ በፖለቲካው ረገድ የምናደርጋቸው ሩጫዎች አሟሟታቸው ለምን አስቀያሚ እንደኾነ እንመለከታለን።
አፄ ዮሐንስ (በዝብዝ ካሣ) በገናናነታቸው ዘመን ኹለቴ አንብተዋል፡፡
ኩፊት ላይ ከፈንዳሜንታሊስቶቹ አክራሪ የደርቡሾች ጋር ተዋግተው እንደነበርና አክራሪውን ፈንዳሜንታሊስቱን አንጃ አይቀጡ ቅጣት ወጥተውት እንደነበር የታሪክ ሰነዶች ይናገራሉ፡፡
ቢኾንም አስከፊው ጦርነት ከኹለቱም ወገን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን ሕይወት የነጠቀ መራራ ጦርነት ነበር ይባላል።
አፄ ዮሐንስ ግን ጠላቶቻቸውን ማርከው እንደበግ አስነዷቸው፡፡
ዣንኾይ ዮሐንስ ታዲያ ኢትዮጵያችንን አስከብረው ጦርነቱን በድል ቢፈጽሙም ከኹላቱም ወገን ያለቀውን የሰው ቁጥር ባሰቡ ጊዜ
#ኃይሌን_ያስለቀሰች_ኢትዮጵያ
#የመጨረሻው_ተራ_ለዜግነት
#the_least_priority_for_citizenship!
የመጨረሻው ተራ ለዜግነት (ክፍል 3)
ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን በወርቃማ የተውኔት ብእሩ የጀግናው የመጨረሻ ቃል ገልጾታል። እውነትም ኢትዮጵያ ምንኛ የሚለቀስላት አገር እንደኾነች የቴዎድሮስ ስንብት በጸጋዬ ገብረ መድኅን ልህቀት ተከሽኖ ቀርቧል።
የጀግናውን የመጨረሻ ቃል ለጀግናው ተውለት ይላል ታዲያ ጋሽ ጸጋዬ ምንጭ ጠቅሶ
“አይ ኢትዮጵያ......
…ይልቅስ ተረት ልንገርሽ -
የተላከ ከእንግሊዝ ዘንድ
እጅህን ስጥ አለኝ ፈረንጅ -
እጅ ተይዞ ሊወሰድ፤
ምን እጅ አለና የ'ሣት ሰደድ?
አያውቅም ክንዴ እንደሚያነድ?”......
ታዲያ ማን አባቱ ነው የመይሳውን እጅ የሚይዝ?
እ'ሣትን በእጁ የሚጨብጥ????
ናፖሊዮን ግን እንደ ቴዎድሮስ አያስብም!
ቴዎድሮስም እንደ ናፖሊዮን ቦናፓርቲ ለማሰብ በሚያስችል ኬሚስትሪ አልተቀመመም።
ኢትዮጵያን ወደኋላ ማንበብ ያሳዝናል
በሳይንሣዊ አመክንዮ የወደፊት መዳረሻዋን መተንበይም አብዝቶ ያቆስላል። ያስለቅሳል!
እውነትም ደራሲያኖቻችን በዚህች አገር የተመላለሱ ትውልዶች በሠፊውም በጠባቡም የመሯቸውን አንዳንድ መሪዎች በማጣት እጓለ ማውታ (ኦርፋንስ) እየኾኑ መቅረታቸውንና የተጀመረ ለውጥ ኹሉ እየመከነ መሔዱን ያመለክታሉ። ይልቁንም የአንድነት እና የዳር ድንበር ጥያቄ በየዘመኑ እንደ አዲስ እየመጣ የአገሪቱ የጎን ውጋት፣ የጅዝባችንም የእግር እሣት መኾኑን ያሳዩናል። ክህደትን፣ የጥቂቶችን የመስዋእትነት ሥቃይ፤ የአንዳንዶችን መኝታ እና ይልቍንም ምን እየተካኼደ እንዳለ አለማወቅን..............
የትግሉ ጀማሪዎች ተስፋ በመቁረጥ-ያሰቡት ሳይሳካና ትግሉንም ለቀጣዩ ሳያስረክቡ የመኼድን ትራጄዲ ያሳየናል።
በርግጥ የአንድነት ነገር ከተነሳ ከቴዎድሮስ ወዲህ ኢትዮጵያ መቀራረቧ አይካድም። ትግራይ ከሸዋ ጎጃም ከከፋ ወለጋ ከወሎ ሲዳሞ ከጎንደር ወላይታ ከላስታ ወዘተ ወዘተ ጋር (እድሜ ለመንገድ እድሜ ለስልክ እድሜ ለጢያራ[ኤሮፕላን] የሚኒሊክ እና የተፈሪን ነፍስ ይማርልንና) ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያዊያን ጋር ተገናኝተዋል። አለበለዚያማ ለትግራዋዩ ለሸዌው ለላስታ ለወሎ ለጎጃሙ ሰው አርሲ ማለት "ዳር አገር" ወይም የዓለም ዳርቻ ከአድማስ ባሻገር በመሰለው ነበር።
ያስቸጋራው እና ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያንን ፈተና የኾነብን ነገር አንዳንዶቻችን እህትማማች/ወንድማማች ሕዝቦች መኾናችንን ሳይኾን እንደ ጎረቤት የምንተያይ መኾናችን ነው።
ታዲያ ዛሬም ኹለት ምእተ ዓመታትን ከሚጠጋ ዘመን በኋላ ቴዎድሮስ ወደ ሕልውና ዓለም እንደገና ቢመለስና አዙሪታችንን ቢመለከት ሌላ ዙር ለቅሶ አይገባውምን?
የኢትዮጵያ አባቶችን ልቅሶ ካነሳን ዘንዳ እጅግ ብልኹ እጅግ ሩህሩኹ እና እጅግ ታላቅ የዲፕሎማሲ ክህሎት ባለቤት የኾኑት እና ከእሳቸው በፊትም ይኹን ከእሳቸው በኋላ እንደ እሳቸው አብዮቱን ማሳካት የቻለ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ አልተገኘም የሚባልላቸውን አጤ ሚኒሊክን እናገኛለን።
ልክ እምደቴዎድሮስ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን ቢመለከቱ ሌላ ኹለተኛ ዙር እንባ ሊያነቡ ከሚችለ ንጉሥ.....
*####**************
የሠዓት መጠቆሚያችንን ተከትለን ወደ ሚኒሊክ ዘመን ስናማትር እምዬ ምኒሊክ ሆደ ቡቡው እና አልቃሻ ንጉሥ ተብሎ በተደጋጋሚ የተጻፈላቸው የኀይማኖት እና የሞራል ልዕልናቸው ከሌሎች በእጅጉ ከፍ ያለ ንጉሥ ምኒሊክ እንደነበሩ ታሪክ ያወጋናል፡፡ በ1881/82 የተከሰተውና "ክፉ ቀን" የሚል ስያሜ የተሰጠው ርሃብ ኢትዮጵያውያንን አገል አጉል አድጎ በቀጣበት ወቅት አንዲት ሴት በከፍተኛ ወንጀል ተከስሳ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ችሎት ትቀርባለች። ወደ እምዬው ችሎት።
በከፍተኛ ወንጀለኝነት ያስከሰሳት ወንጀል ደግሞ ስምንት ሕጻናትን በልታለች የሚል የሰው ልጅ አውሬያዊ ተግባር ፈጽሞ ከሰውነት ተርታ እንደወረደ የመያሳይ ወንጀል ነበር።
ሕጻናቱን አርዳ በላቻቸው ተባለ፡፡
ጥፋተኛዋም ተይዛ እፊታቸው ቀረበች፡፡
"ልጀ እውነት ሰው በልተሻል?" አፄ ሚኒሊክ ጠየቋት፡፡
ሴትዮዋ ቅንጣት አላመነታችም፡፡
"ታዲያ ሲርበኝ ምን ላድርግ፤ ልጆቼ በርሃብ ሲሰቃዩ ምን ላብላቸው?
አዎ ጃንሆይ ግጥም አድርጌ በልቻቸዋለሁ" ስትል መለሰች።
እምዬ በዚህች ሴት ላይ የሚፈርዱበት ሞራል ሟሸሸ።
ቁጣ ከዳቸው።
ከፈጣሪ ጋር ሙግት ገጠሙ።
ምን አድርጌ ምን በድዬህ በዘመኔ እና በሕዝቤ ላይ እንዲህ ጨከንህ??
ይግባኝ ወደ ላይ......
ንጉሡ ክርክራቸው ከተፈጥሮ ጌታ ጋር ኾነ........
እንባቸውም ከመቅፅበት ፈሰሰ፡፡
በችሎት አደባባይ እንደ ሴት አምርረው አለቀሱ.......
እናት የኾኑት ንጉሥ ከንጉሥነታቸው ካባ ስር እናትነታቸው እና ሆደ ቡቡነታቸው ገንፍሎ ወጣ........
ከእሳቸው ሌላ እምዬ የተባለ ንጉሥ በታሪክ አላገኘኹም። በጣም የሚቀርበውን ስብእና ከኢትዮጵያ ነገሥታት ፈልጎ ለማግኘት ምናልባትም ወደ ጎንደር ዘመን ወደ ደጉ ንጉሥ ዮሐንስ ማማተር ግድ ይኾን ይመስለኛል።
ይኽ ብቻ አይደለም......
ታላቁ ጥቁር ኹለት አንጄት የሚበሉ የለቅሶ ታሪኮችን ትተውልን አልፈዋል።
ከአድዋ ድል በኋላ ጀግኖች የኢትዮጵያ የጦር ባለሟሎች እና ጀብደኞች ዣንኾይ ሜዳ (ዣን ሜዳ) የጀግና አቃባበል በሚያደርግላቸው ሕዝብ እና በንጉሠ ነገሥቱ ፊት በድል አድራጊነት በጀግና ወግ በብሔራዊ ኩራት በማለፍ ላይ ነበሩ።
በፈረስ በፈረሳቸው እየኾኑ ደንገላሳ እየመቱ።
እነ ባልቻ ሳፎ (አባ ነፍሶ)....እነ ሐብተጊዮርጊስ ዲነግዴ(አባ መላ).......እነ ራስ ሚካኤል (አባ ሻንቆ) እነ ራስ መንገሻ እነ አሉላ ቁንቢ (አሉላ አባ ነጋ) ብቻ የኢትዮጵያን ጠላት አድዋ ላይ ድባቅ የመቱት ጀግኖቻችን በፈረሶቻቸው ላይ ኾነው በቄጠኛ ግልቢያ ዣን ሜዳን በፉከራ እና በቀረርቶ አድምቀውታል።
በዚህ መሃል እምዬ ሚኒሊክ ከክብር ቦታቸው ላይ እንደተሰየሙ ዓይናቸው አንድ ሕፃን ልጅ ላይ አረፈ።
የ9 ዓመት ሕፃን ልጅ በፈረስ ላይ ተቀምጦ በሕዝብ መኻል ከጀግኖች አርበኞች ጋር ሲያልፍ እምዬ ሚኒሊክ ተመለከቱት።
#የገበየሁ ልጅ ነበር።
የ9 ዓመት ብላቴና......
ሸዊት ማርያም ላይ ከጠላትን ጦር ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቆ የዋደቀው የጀግናው ገበየኹ ፈረስ እንደ ወትሮው ገበየሁ አልተቀመጠባትም።
የ9 ዓመት ልጁ እንጂ......
እምዬ ዳግም መራራ ለቅሶአቸው በአደባባይ ታዬ.....
ሕዝብ አብሯቸው አነባ......
ከድል አድራጊነት ቀረርቶው እና ከፉከራው ባልተናነሰ መልኩ ከንጉሥ እስከ ተርታ ሕዝብ ከመኳንንት እስከ ተራ ጡሩምቡሌ በእንባ ዣንሜዳን በእንባ ተራጨባት።
ውስጣቸውን ፈንቅሎ ለወዳጃቸው ለአገልጋያቸው ለአጋራቸው ለጀግናቸው ለገበየሁ የቀረበችው ጽዋ ምን ያህል መራራ እንደነበረች አስበው የእምዬ አምርረው አለቀሱለት።
አልቅሰው ሕዝቡን ሆድ አስባሱት.......
ዣንሜዳ ምስክር ነች.....
ኢትዮጵያ ድል አድርጋ ቢደሰቱም ኢትዮጵያ ትልቅ ሰው አጥታለች።
"ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ......"
የባለቅኔው የሀሰን አማኑ ዝክረ ነገር ገበየሁን ህያው ለማድረግ ውለታውን ለመዘከር በሕዝብ ልብ ውስጥ ሰርጾ ገብቶ ለገበየሁ ከንፈር ይመጠጥለታል።
ለኢትዮጵያማ ይለቀሳል!!!!!
የጀግኖች ሰማእትነት ልጆቿ የነጻነት ዐየርን ይተነፍሱ ዘንድ ዋስትና ያልኾነላት እልፍ የነጻነት ታጋዮች አጥንት እና ደም ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ትኖር ዘንድ ቤዛ የኾነላት አገር በገዛ ልጆቿ የመከራ ቀንበርን ተሸክማ ዜጎቿ በባእድ ያለመገዛት ት
#ኃይሌን_ያስለቀሰች_ኢትዮጵያ
#የመጨረሻው_ተራ_ለዜግነት
#the_least_priority_for_citizenship!
የመጨረሻው ተራ ለዜግነት (ክፍል 2)
እፁብ ድንቅ የተባለለት ጋዜጣኛ እና ደራሲ የነበረው ብርሐኑ ዘሪሁን "የቴዎድሮስ እንባ" በሚለው ዝነኛ መጽሐፉ ታላቁን ንጉሠ ነገሥት ወደ መቅደላ አምባ ያወጣዋል።
በናፔር የሚመራው የእንግሊዝ ኤክስፔዲሺን (ዘመቻ) ንጉሠ ነገሥቱ ካሉበት ሥፍራ ተጠግቷል። ቴዎድሮስ በመቅደላ አምባ ላይ እንደ ወትሮው ሁሉ በአጭር ታጥቆ፤ ሽጉጡን አቀባብሎ የሴቫስታፖል መድፉ አንዳች ግዳይ ለመዋጥ እንደታዘጋጀ ዘንዶ እንደተራበም አንበሣ አፉን ከፍቶ አውሬ ኾኖ.........
ቴዎድሮስ በግርማ ሞገስ ተንጎራደደ።
ለወትሮውማ መይሣው ካሣ ንጉሡ ቴዎድሮስ መሬት ራሷ ያረገደችለት ምድር የገበረችለት ጎበዛዝት የእንብርክክ የሰገዱለት የጀግኖች ጀግና ነበር!
አሁን ግን ጀግኖች ወንድሞቹ እነ ገብርዬ ሳይቀሩ ወድቀዋል።
"ቴዎድሮስ ይሙት" እያለ በሥሙ የሚምልበት እንግሊዛዊው የቴዎድሮስ ቢትወደድ ሊቀመኳስ ዮሐንስ (ቤል) ሳይቀር አሁን ላይ ቴዋድሮስን ከድቶ ሔዷል።
በዝብዝ ካሣ ለናፔር ድጋምፍ የመስጠቱ ዜናም መቅደላ ከቴዎድሮስ ጆሮ ደርሷል።
ለማይሣው ኹሉም ነገር ክሕደት በክሕደት ኾኖበታል። መቅደላ አምባ ላይ የቆማው ቴዎድሮስ ግራ ቀኙን አማተረ።
ኢትዮጵያን በምናቡ ቃኛት!
ወደ ላይ ተራሮቹን ወደ ታች ሜዳውን ዝቅዝቅ አረህ ተረተሩን ተመለከተ።
ለኢትዮጵያ የነበረውን ሕልም.....
የአንድነት ጉዞውን.....
የአንዲት ኢትዮጵያን ጉዳይ....
የፊውዳሉ ሴራ የነቃፊዎቹ ጎታችነት እና ኋላ ቀርነት ከቴዎድሮስ የተሳሳተ ሥልት ጋር ተደማምረው ቴዎድሮስ ያቀጣጠለው አብዮት እንዳይሳካ እንከን ኾነው ጠልፈው ጣሉት።
በቴዎድሮስ ጭንቅላት ውስጥ ጥያቄ ተፈጠረ!
ኢትዮጵያ በእኔ ምክንያት የእንግሊዝ ቅኝ ተገዢ ልትኾን ነው?????
መይሣውን ቁጭት አሳበደው።
"የኢትዮጵያ ባል የኢየሩሳሌም እጮኛ" የሚለው ፉከራው ሲከሽፍ ዓይኑ ተገልጣ ተመለከተች።
ኢትዮጵያ ወደ ዘመነ መሣፍንት ትመለስ ይኾን? የሚል ስጋት ቴዎድሮስን የእግር እሳት ኾኖ አቅሉን አስሣተው።
ቴዎድሮስ አለቀሰ!!!!
መይሳው እንባውን አፈሰሰ!
ጀግናው መቅደላ አምባ ላይ አ..ለ..ቀ...ሰ
ተስፋ ቆረጠ ቴዎድሮስ።
መይሳው ካሣ አንድ ለእናቱ ሺህ ለጠላቱ....
ጥይት ያጎረሰውን ሽጉጡን ራሱ ጎረሰው.....
አዎ በእጁ ያጎረሰውን ሽጉጥ ራሱ በድፍረት ጎረሰው........
በቴዎድሮስ እጅ ከጎረሱ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ እንኳን በዚህ ሠዓት ከጎኑ አልነበሩም።
ከሽጉጡ በስተቀር
አለቀሰ
እናም ቴዎድሮስ ጥይት ያጎረሰውን ሽጉጡን በእልህ ጎረሰው.....
ቴዎድሮስ የጀግኖች ጀግና መኾኑን መቅደላ አምባ እያየች ጠላቶቹ እየመአከሩ የጀግና ሞት ሞተ!
የትግሬውን ንጉስ ሲንቁ ሲንቁ
የየጁውን ንጉሥ ሲንቁ ሲንቁ
የሰሜኑን ንጉሥ ሲንቁ ሲንቁ
ወንድ ያለ ራስዎ ገድለውም አያውቁ.....
ተባለለት የወንዶች ቁናውን አፄ ቴዎድሮስን ራሱ ቴዎድሮስ ቢገድለው።
እሱ ብቻ ቢደፍረው!
ቴዎድሮስ ስለ ኢትዮጵያ አልቅሷል
እውነትም ለኢትዮጵያ ዘላለም ይለቀሳል! እንዲሉ ጸሐፍት።
ለምን?
ኤድመንድ መሪ የተባለ አሜሪካዊ አማካሪ በኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ሲሠራ በነበረበት ጊዜ አንድ መጽሐፍ ጽፎ ነበር።
#ቁልቢ ለመጽሐፉ የሰጠው ርእስ ነበር።
ታሪክ ቀመስ ልብ ወለድ ነው ኤድመንድ መሪ የጻፈው።
እናም በዚህ መጽሐፉ ተስፋዬ የሚባል ጀግና ገጸባሕሪ ይፈጥራል ጸሐፊው።
ኤድመንድ በንጉሡ እርጅና ምክንያት እየመጣ የነበረው ለውጥ በግልጽ የታየው ሰው ነበር። በአሜሪካዊ ንቃተ ሕሊናው ታግዞ የዘውድ ሥርዓቱ ፍጻሜው እንደተቃረበ እና በምትኩ የኢትዮጵያን ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እሴቶች የማያውቅ ቢያውቅም የማያከብር ካፒታሊስቶችንም የሰው ዘር ጣላት እንደኾኑ አድርጎ የሚፈርጅ የአራዊት ሥርዓት እንደሚመጣ፤ ሐገሪትነ ኢትዮጵያ ደም በደም ልትኾን እንደተቃረበች መጪውን ጊዜ እንደ ራእይ አይቶት ነበር።
ኤድመንድ ታዲያ ተስፋዬ ሲል የሰየመውን የመጽሐፉን ጀግና ከተራራ ላይ ያወጣዋል።
ተስፋዬ ኢትዮጵያ ስትቃጠል ያያል። ያላቅሳል።
ምርር ብሎ ያለቅሳል።
ተስፋዬ ያልቅሳል።
በኢትዮጵያ ሞት ያለቅሳል!
የመጽሐፉ የመጨረሻ ቃላትም እኒሁ ናቸው።
የታንያን ለቅሶ የሚመስል የሰቆቃ ለቅሶ!
ታንያ......
ከኹለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ በየአገሩ ይሸጥ የነበራ የአንዲት ሩሲያዊት ሕፃን ሥዕል እንደነበር ይነገራል።
ልጅቷ በጦርነቱ ወላጆቿ በናዚዎች ቦምብ እና የእልቂት ዝናም አልቀውባታል።መንደሩ በሙሉ ጋይቷል። ቀና ስትል የሚታያት ጥቁር ሰማይ ነው። ጎንበስ ስትል ደሞ ጥቁር መሬት። የምትተገንበት ሥፍራ የምትቀምሰው የምትልሰው እህል አልነበራትም። በዓለም ላይ ብቻዋን የተጣለች ምስኪን ፍጡር ትመስላለች። ታንያ የቀራት ብቸኛ ወዳጅ እንባዋ ነበር።
ይኽ አሳዛኝ ተውኔት በብዙ የሩሲያ ሥነ ጽሑፎች የተስተጋባ ሲኾን የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ሪቻርድ ኒክሰን የቀድሞዋን ሶቬት ሕብረት ሲጎበኙ ይህቺን የዓለም ከርታታ (የታንያን) ታሪክ አንስተው በሬዲዮ ሲናገሩ ሕዝቡን እንባ በእንባ አደረጉት። ታኒያ ዛሬም በየአገሩ ታለቅሳለች። በኢትዮጵያም ወገኖቻቸው በእርስ በርስ ጦርነት እና በፖለቲካ አሻጥር ያለቁባቸው፤ በፖሊሲ ተቀርጾ በገዢዋቻቸው ቅንብር በዘግናኝ የወገን ጭካኔ መፈናቀላቸው ሳያንስ በአሰቃቂ ኹኔታ የሞቱባቸው ዜጎች በሻሸመኔ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሐረር፣ በጎንደር፣ በአሶሳ፣ በዝዋይ፣ በከሚሴ፣ በትግራይ፣ በወልቃይት፣ በራያ፣ በጉጂ፣በጋሞ፣ በጊምቢ ወዘተ የታኒያን ዓይነት ለቅሶ ያለቅሳሉ።
አዎ....ኢትዮጵያውያን ዛሬም ያለቅሳሉ።
ብቻ የማያለቅስ የለም።
ፕሬዘዳንት ኒክሰን በትዝታ መጽሐፋቸው ስለ ታንያ ያነሡትን አንብቦ የማያለቅስ ይገኛል ማለት ዘበት ነው። በዚህች ልጅ ታሪክ ያላለቀሰ በእውነት እርሱ ጥሩ ድንጋይ ልብ ያለው ይመስለኛል።
እነዚህ ደራሲያን በቆንጆ ቋንቋ የሳሉልን (የሳሉብን) ታዲያ በእግዚአብሔር እና በወገን የማመን-በወደፊቱ ተስፋ ሰጪነት የመተማመን ዓለም መንኮታኮቱንና በጭንቀትና በፍርኅት በተሞላ ሌላ ዓለም መተካቱን ነው።
ቴዎድሮስ ያልተፈጸመ አብዮቱን ይዞ ወደ ሞት ዓለም ይሔዳል። ከዛ በፊት ግን አንድ ዘለላ ሳይሆን መንታ መንታ እንባ ይረጫል። ለራሱ አይደለም። ቴዎድሮስ ለራሲ ቢያስብ ኖሮ በእንግሊዝ መንግሥት ተልከው በመጡ ሕንዳውያን ወታደሮች ሊማረክ ይችል ነበር። እንደ ናፖሊዮን ቦናፓርቲ። ቴዎድሮስ ግን እንደ ናፖሊዮን አያስብም። ናፖሊዮን ከትራስፋጋር እና ከወተርሉ ጦርነቶች በኋላ ተማርኳል። ከወተርሉ ጦርነት በኋላ ተማርኮ ወደ ሴንት ሔሊና ደሴት በግዞት ተወስዷል። ነገር ግን ከዛ አምልጦ ለ100 ቀናት ፈረንሣይን እንደገና ለመግዛት ችሏል።
ቴዎድሮስ ግን መማረክ የሚባለውን ውርደት የሚሸከም ጫንቃ አልነበረውም። ማን አባቱ ነው የመይሳውን እጅ የሚይዝ።
ቴዎድሮስ ስለ ኢትዮጵያ እንባውን ካፈሰሰ በኋላ ግን በጠላት ላይ ተሳልቆ ሞትን እንደ ከንቱ ነገር ንቆ አልፏል.............
አብዝቶ ቀልብ በሚገዛ ንጉሣዊ እና ኢትዬጵያዊ ጀብደኝነት።
"ዓለም በሥልጣኔ መጥቆ ሰማየ ሰማያትን ሲነካ
እጅ መስጠት ማለት ምን ማለት እንደኾነ የማያውቅ.....
እንግሊዝ መሃይም ነው ለካ!
እንኳን የማርያም ልጅ ከትቢያ ላይ አንስቶ #ለኢዛና እና #ለካሌብ መንበር ላበቃው ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ይቅርና........
ከሥጋው የተዋኻደች ደሙ አበሻዊ ቅይጥ እንዳላት ላወቀ ሕፃንም እጅ መስጠት ማለት ሞት ነው!
#ኃይሌን_ያስለቀሰች_ኢትዮጵያ 🇪🇹
👉የመጨረሻው ተራ ለዜግነት
👉#least_priority_for_citizenship!
የመጨረሻው ተራ ለዜግነት
ይህቺን የመጨረሻው ተራ ለዜግነት (The least priority for citizenship) በሚል ርእስ ያዘጋጀኋትን ጽሑፍ እንድሞነጫጭር ምክንያት የኾነኝ
በቅርቡ (ባሳለፍነው ክረምት) አገራችንን ከገጠሟት ምስቅልቅሎች እጅግ በጣም አሳፋሪው እና የመጨረሻውን ተራ ለዜግነት የሰጠው ሥርዓት ያሸከመንን የመከራችንን ክብደትና የገዢዎቻችንን የውርደት ልክ ቁልጭ አድርገው አሳይተውን ካለፉ ክስተቶች መካከል አንዱ በኃይሌ ገብረሥላሴ ድርጅቶችና ንብረቶች ላይ የተነጣጠረው ጥቃት ነበር።
ለምን?
ኃይሌ ኢትዮጵያዊ ነዋ።
ዜግነት ማለት ምን ማለት እንደኾነ አሳምሮ የሚውቅ የአገር እና የባንዲራ ፍቅር ምን ማለት እንደኾነ ለዓለም ያስተማረ እንጂ ከዓለም ያልተማረ ብሔራዊ ጀግና።
በጣም አሳፋሪው ነገር ግን ኃይሌ ያለቀሰላት አገር ስለ ክብሯ እንባውን በሰንደቋ ፊት በዓለም አደባባይ ያፈሰሰላት ኢትዮጵያ ዛሬ ለውለታው የሰጠችው ምላሽ ምን እንደኾነ ማዬትና መስማት ብቻ በቂ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ኃይሌ ያልተፈራ ኃይሌ ያልተከበረ ማን ሊፈራ ማንስ ሊከበር ይችላል?
ኢትዮጵያ እና ኃይሌ ገ/ሥላሴ ምንና ምን ናቸው?
ይኽንን ባሰብኩ ጊዜ አንድዳች ነገር ሰውነቴን ውርር አደረገኝ። ደምግሞ መልሶ የመቅዝቅዝ ዓይነት ስሜት ተሰማኛና ቁጭት ይሁን እልህ ብቻ የመጨረሻው ተርታ ላይ ያስቀመጥነውን ኢትዮጵያዊነት ከየት አንስተን የት እንዳደረስነው መጻፍ አሰኘኝ።
ጻፍ ጻፍ አለኝ!
የማውቃትን ጥቂት ሃቅ ማካፈል ፈለግሁ።
ከዛም ከዛም የቃረምኩትን በቻልኩት መጠን አነበብኩ ያልኳትን የገባችኝንም ያልገባኝንም መጻፍ አማረኝ።
ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝና አንብባችሁ በሃቅ ሞግቱኝ። እቀበላለሁ።
እንደተለመደው ተነበበልኝ ብዬ ጻፍ ጻፍ እንዲለኝ አስባችሁ ለምታነቡልኝ ወዳጆቻም ከወዲሁ ምስጋናየ ይድረሳችሁ።
ለመኾኑ ኢትዮጵያ እና ኃይሌ ገ/ሥላሴ ምንና ምን ናቸው?
አንዴ ተከተሉኝ ወደ 1988 መጨረሻ ሐምሌ ወር (ክረምት) ልውሰዳችሁማ!
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያ እና ኃይሌ ገ/ሥላሴ
በአሥር ሺህ ሜትር ሩጫ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ኃይሌ ገ/ሥላሴ አትላንታ ላይ (ሐምሌ 1988 ዓ.ም) የወርቅ ሜዳል ሲሸለም ከጎን እና ከጎኑ ከቆሙት ማለትም ኹለተኛ እና ሦስተኛ ከወጡት ተወዳዳሪዎቹ ላቅ-ከፍ ካለ መቆሚያ ላይ ኾኖ በአንገቱ ወርቅ ተጠለቀለት።
በኃይሌ አማካይነት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚም ባይኾን፣ በፖለቲካም በትምሕርትም በቴክኖሎጂም በሣይንስም ባይኾን፤ በ10ሺህ ሜትር ሩጫ ዓለምን እየመራች ነበር።
ኢትዮጵያ በፋጡማ ሮባ የማራቶን ሩጫም ዓለምን ወሬሳ መትታላች።
ረሃብታኛዋ እና የግፍ ኹሉ ተሸካሚዋ ኢትዮጵያ ባዚህ እንኳ እንዲትታወቅ በመደረጉ በእጅጉ ኮርተናል።
ኃይሌ ገብረሥላሴ ግን ድል ካደረገ በኋላ አለቀሰ።
እንባው ጣምራ ጣምራ እየኾነ በፊቱ ላይ ቦይ ቦይ እየሠራ ወረደ።
ሆደ ባሻናት፥ሲቃ፥የደስታ ይኹን የአንዳች ነገር ናፍቆት.....ብቻ ኃይሌ አለቀሰ።
ከዚህ በፊት ኃይሌ ሩጫ አሸንፎ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ከፍ አድርጎ አውለብልቧል።
ያን ዕለት በሚሮጥበት ጊዜ ግን ከድፍን አሜሪካ ከየ እስቴቱ (ከየ ክፍላተ አሜሪካ) ወደ አትላንታ የጎረፉ የአገር ልጆችና አብረውት የሔዱት አሠልጣኝ ሌሎች አትሌቶችና ሐኪሞች ሳይቀሩ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ይዘው ከኃይሌ ጋር ይሮጡ ነበር።
እኩል ይሮጡ ነበር።
ያቺ የሳመማትና የተሳለማት አጎንብሶ የሰገደላት ሠንደቅ ዓላማ ለኃይሌ ግፊት ሰጠችው!!!!
የኢትዮጵያ ሠንዳቅ ዓላማ ለኃይሌ ኃይል ኾነችው......
🟩 አረንጓዴ
🟨 ብጫ
🟥 ቀይ
እናም ኃይሌ አሸነፈና አለቀሰ።
ጀግናው ኃይሌ ገ/ሥላሴ መንታ መንታ እንባውን አፈሰሰ!
ድል አድራጊዎች ያለቅሳሉ እንዴ?
ጀግኖችና ብርቱ ሰዎች ያለቅሳሉ?
አዎ ጀግኖች እንደ ኃይሌ ያለቅሳሉ።
ጀግኖች ብቻ አይደሉም ሥጋ የለበሰው መለኮት ኢየሱስም'ኮ አልቅሷል!
ከአፄ ቴዎድሮስ ጀምሮ እስከ መለስ ዜናዊ ድረስ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ መሪዎች በሥልጣናቸው ላይ በነበሩበት ወቅት ወይም ተፍፃሜተ መንግሥታቸው ሲቃረብ አልቅ�ሰዋል። እንደየ አስፈላጊነቱ ኹሉንም እንዴት እና በምን እንዳለቀሱ ታሪክን እየዳሰስን ንባባችንን እንቀጥላለን።
የኢትዮጵያዊያኑ ጀግኖች ብቻ አይደሉም፤ የዓለም ጀግኖች በተለያዩ ወቅቶች ለራሳቸው ለሕዝባቸው አልያም ለአገራቸው ያለቀሱበት ጊዜ በርካታ ነው።
በትንሿ የታሪክ ክትትሌ እና ንባቤ እንደማውቀውም በኹለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት ጀግኖች የኾኑት ባለ አራት ኮኮብ ማእረግ ያላቸው የአሜሪካ የጦር አዛዦች እነ ጀነራል ፓተንና ጄነራል ማካርተር ያለቀሱበት ወቅት ነበር።
ኦሽዊትዝ፣ ቡከንወልድ፣ ዳቻ የተባሉ ዋነኛ የኮንሰንትሬሽን ካምፖቻቸውን አይተው ከለቅሶም ያለፈ ሥሜት ንጧቸዋል።
የበሉት አልረጋ ብሏቸው ወጥቷል!
የሕዝብ ስቃይ አሳዝኗቸው እነ ጄነራል ፓተንና ጀነራል ማካርተር አልቅሰዋል።
ጀግኖች ጓዶቻቸው ከጎናቸው ሲወድቁ አይተው አልቅሰዋል።
ኃይሌ ገብረሥላሴም የሐገሩ የኢትጵያ ሠንደቅ የአትላንታን ነፋስ አሸንፋ.....ከቶውንም የአትላንታው ከባድ ነፋስ ግርማ ሞገስ ጨምሮላት በባእድ አገር ሰማይ ላይ ስትደንስ አያት!
ሩጫውን በድል የፈጸመው ጀግናው የኢትዮጵያ ልጅ ኃይሌ ትክ ብሎ ሠንደቁን ተመለከታት....
አለቀሰ።
ምናባልባት "እግዚአብሔር እኔን መሣሪያ አድርጎ ይቺን አገርና ይቺን ሠንደቅ ዓላማ እንዳስከብር ታሪክ ዕድል ሠጠኝ?" በማለትና በመገረም ይኾናል ወይም የአገር እና የሠንደቅ ዓላማ ሩቅ እና ጥልቅ ትርጉም ሳያስበው ድንገት አእምሮውን ሞልቶት ወይም ለሕዝብ እና ለራሱ ቃል ገብቶ የተሳለው ስእለት አትላንታ ላይ ሲሰምር የተለዬ ስሜት ፈጥሮባት ይኹን.....
ብቻ አይታወቅም......
ኃይሌ ገ/ሥላሴ የጀግኖችን ለቅሶ አለቀሰ።
በተለይ ኃይሌ ድንቅ የአገር ፍቅር ግንዛቤ ያለው ሰው መኾኑን እናውቃለን!
ኃይሌ ከድል ማግስት ቦሌ አየር ማረፊያ እንደደረሰ አቀባበል ሲደረግለት ማሸነፍ ብቻውን ትርጉም አልባ እንደኾነ እና ከድሉ ጋር የሕዝብ ፍቅር ማግኘት ትልቁና ዋናው ጉዳይ እንደኾነ ጭምር ጆሮ ላለው ገልጧል።
ኃይሌ እስከ አትላንታ ኦሎምፒክ ድረስ በአውሮፓ እና በሌሎች የተለያዩ ሐገራት ሮጦ በማሸነፍ በሽልማት መልክ ያገኛቸውን አውቶሞቢሎች ቤቱ ውስጥ ሸፍኖ አስቀምጦ ነበር።
ኃይሌ ለራሱ ቃል የገባ ሰው ነበር። እነዚያን ዘመናዊ አውቶሞቢሎች የማሽከረክረው ሀገሬን ወክዬ አትካንታ ላይ ሮጬ ድል ካደረግሁ በኋላ ነው ሲል ነበር ኃይሌ ከራሱ ጋር ቃል ኪዳን ያሰረው።
እነኾ ኃይሌ በቃል ኪዳኑ መሠረት አትላንታ ሔደ.....ሮጠ....አሸነፈ......
"መጣኹ....አየሁ.....ማረክኹ....." እንዳለው ዮልዮስ ቄሣር።
መጣኹ....አየሁ.....ማረክኹ.....ከባድ እና ዘላለማዊ ተጠቃሽ ቃል ነበር!
የኃይሌ ስእለት እና እምነት ከባድ ነበር። "እግዚአብሔር በለገሰኝ የተፈጥሮ ሥጦታ አትላንታ ላይ አገሬን ካስጠራኹ በኋላ እነዚህን መኪናዎች እነዳለሁ" ብሎ ተስሏል ኃይሌ።
እናም እኛ ዛሬ ለኃይሌ ገብረሥላሴ ውለታ ሕንፃዎቹን አጋዬን ንብረቱን አወደምን ኃይሌን በጎሣ ሚዛን ላይ አስቀምጠን የመንጋ ፍርድ ፈረድንበት!
ኃይሌ ያለቀሰላት አገር ለውለታው ምላሽ ኃይሌን ገፍታ አስለቀሰች!
አገር እንደሌለው እንደ ባእድ ኃይሌ.......
በከባድ ሕዝባዊ የቁጣ ማእበል ምክንያት ገናናነታቸውና ኃያልነታቸው በአንዲት ጀንበር ተሽሮ ከሥልጣናቸው የተባረሩት የ