faiza_kiza | Unsorted

Telegram-канал faiza_kiza - ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

1551

ማወቅን ማወቅ ፣አለማወቅን ማወቅ ፣አለማወቅን አለማወቅ ፣ማወቅን አለማወቅ፣ አለማወቅን ማወቅ ነዉ፡፡ (sokrats ) @faiza_kiza በብዕር እንነሳለን በብዕር እንዘቅጣለን በብዕር እናድጋለን 👍🥰 አስተያየቶቻችሁን በ @mornin_bot አድርሱኝ

Subscribe to a channel

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

Faiza🌚


He was an angel who show up when I wasn't askin for him....he was the sun shine for me when I get my comfort in the fukin dark clouds....he was the one to make me smile when I failed to elicit one...he is just a flaw full perfect creature who make me belive and try again ...he draw stars around my scars✨




╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
             @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

📝📝📝


Why is it happening again? I thought I was fine ....but at some point am not ...I was laughing min before and for now am breaking in tears in side my bed....why am I coming back after I feel like am far from there ...why am getting my self at the same state after doing and trying alot am tired am tired for real......

By faiza🫡




╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
             @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

Am on ig @faiza_kiza dm to share story or maybe some advice or if you want to just talk to am halfway psychologist after all😁 and as some of you asked I will start english letters and some quotes stay tuned and share it please 😊

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

በፋኢዛ✍

ለአንቺ☺️


አንዳንድ ጊዜያቶች አሉ ብትናገሪ ሰዉ የማይረዳሽ ....ብታለቅሽ የማይወጣልሽ.......ምን አጥፍቼ ነዉ ብለሽ የምታማርሪበት .....ህይወት የምትጨልብሽና ብርታት የምታጭበት...የሆነ ጊዜ አለ ብቻ ...እናም የኔ ቆንጆ ብቻሽን አይደለሽም ...ይሄ አንች ማንም አይገባውም የምትይዉ ስሜት ብዙ ሰዎች አይተዉት ነበር....ብዙ ሰዎች ደሞ እያዩት ነዉ ....ሌሎች ብዙ ሰዎች ደሞ ወደፊት ያዩታል ...እናም ለችግርሽ ከራስሽ በላይ ቦታ አትስጭዉ.....የምወደዉ አንድ ፈረንጅኛ ነገር አለ " when you focus on you , you grow ..when you focus on your shit , shit grows" ቀላል ሎጂክ ማተኮር ያለብሽ ማደግ ያለበት ላይ ነዉ ...እና እማኮ .....አንቺ ዉስጥ ያለችዉን ትልቅ ሴት አትግደያት ...ታገይ ...እመኝ...አሸንፊ ....ደሞም ...ት..ች..ያ..ለ..ሽ


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
             @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share❗️❗️

😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
😍   Join @faiza_kiza     😍
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ሰላም ህዝባ ህዝቦች ፋኢዛ ነኝ....ያዉ ይቺን ሁለት ቀን እንደመፃፍ እያደረገኝም አይደል አንዳንድ የጠፉ ወዳጆች እንዴት ነሽ የት ነሽ ምን ሁነሽ ነበር እያሉ አስጨነቁኝ እናጠቃለዉ በሚለዉ😁.....ደና ነኝ አልሃምዱሊላሂ በጣም ደና ነኝ...አሁን ለጊዜዉ ከወሎ ወጥቻለሁ ...ያዉ ብዙዎቻችሁ እንደምታዉቁት ዩኒቨርስቲ ወራቤ ደርሶኝ የስልጤተ በሬደታ ሁኛለሁ (ዘፈን ላይ ሰምቼዉ ነዉ ትርጉሙን እንጃ😂) ...ህልሜ ሳይኮሎጂስት መሆን እንደነበር ብዙዎቻችሁ ታዉቃላችሁ እናም አሁን ላይ ሁለተኛ አመት የሳይኮሎጂ ተማሪ ሁኛለሁ ..አላሳፍራችሁም አሁንም ሰቃይ ነኝ🫡 ...ከመፃፍ ጋር በተያያዘ እኔም ለራሴ የምሰጠዉ በቂ ምክንያት የለኝም ብቻ ምንም አይነት መነቃቃት ዉስጥ አልነበርኩም...ብዕር ለማንሳትም ጉልበት አልነበረኝም...ተጨማሪ ሀላፊነቶች እና አዲስ ማንነት እየገነባሁ ስለነበርም ይሆናል ...ብቻ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም የመፃፍ አቅም መልሼ አግኝቻለሁ እናም ጥሩ ስራዎችን አቀርባለሁ ተይህ ወዲያ😂 ....እና ታሪኮቻችሁን እየላካችሁልኝ በ@mornin_bot ...እና ሼር አድርጉ ኘሊስ 3k ሊገባ ሲል የተዉክት ቻናል ይሄዉ ከአንድ ሺ ሊወርድ ነዉ እና ፍሊስ ሼር☹️



╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
             @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share❗️❗️

😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
😍   Join @faiza_kiza     😍
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ታሪካችሁን አጋሩን @mornin_bot

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ታማኛለህ አሉ.....

በፋኢዛ🫡


ነይ ብያት ነበር...ፍቅራችንን እናድሰዉ ብያት ነበር እሷ ግን አልፈለገችም...ስለኔ ግድ አይሰጣትም...ፍቅራችንን አትፈልገዉም ...ሌላ ሳትለምድም አትርም....እያልክ ታማኛለክ አሉ....እዉነት ነዉ ጓድ? .....አልተሳሳትክምኮ ልክ ነህ አልፈልግህም.....ፍቅራችንን አልፈልገዉም....ስላንተ ግድ አይሰጠኝም....አዎ ብቸኝነት የሚባል ሌላ ሰዉ ለምጃለሁ ካንተ አብሮነት በላይም ሰላም አለዉ....ግን አንተ ሰዉ ሀሜት ከጀመርክ አይቀር ይሄንን ማንነት እንዴት እንደፈጠርከዉ ንገራቸዉ.....ከይቅርታ በላይ ይቅርታን ስሰጥክ ከህመም በላይ ህመም እንዳሸከምከኝ ንገራቸዉ.....ከፍቅር በላይ ንፁህ ፍቅር ስሰጥክ የምጠላብህን ምክንያቶች እንደሰጠኸኝ ንገራቸዉ....ከራሴ በላይ ሳከብርህ ከማንም በላይ እንደናከኝ ንገራቸዉ.....ጥፋትህን ...ንቀትህን...ሁሉንም ችዬ የምሄድበት ሽ ምክንያት እያለኝ አንድ ፍቅርህን ብቻ ይዤ መቆየትን መርጬ እንደነበር ንገራቸዉ ....ግን ሰዉ ናት በላቸዉ ...ጠንካራ የሚባሉ ስሜቶች በጊዜ በበደል በትዕግስት ጫና ይናዳሉ ተስፋ ቆረጥኩ በቃ! እናም ንገራቸዉ ይሄንን እኔን እና እሷን ያጣላን ይሄ ነበር ... የሷ ይቀየራል ብላ ማሰብ እና የኔ አትቀየርም ብሎ ማሰብ....እኔ አንተን ለመቀየር ደፋ ቀና ስል ተስፋዬ አለቀ ...አንተ አትቀየርም ብለክ ጊዜ ስትወስድ እኔ ርቄያለሁ ....እና ግድ የለም እማኝ ግን ሁሉንም ንገራቸዉ.....


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
             @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share❗️❗️

😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
😍   Join @faiza_kiza     😍
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ርዕስም ትርጉምም የለዉም........


አንዳንዴ ነገሮችን ለማብራራት ከየት እንደምንጀምር ግራ ይገባናል....አለ አይደል አሳቢ እና ታዛዥ ከመሆን ......ምን አገባህ... ምን አገባሽ... አይመለከትህም አይመለከትሽም... ወደማለት እንዴት እንደተሻገርን እኛም አናዉቀዉም ...እናዉቀዋለን ግን እንዴት ነዉ የምናስረዳዉ? ...በቤተሰብና ጓደኛ መከበብን ጨዋታና ወከባ ከመዉደድ .....ለብቻ መቀመጥን እና ወከባ መጥላትን እንዴት ልምድ እንዳደረግን አናዉቅም...ብቻ አንዳንድ ሁኔታዎች ቅርፅ ይሰጡናል ...አንዳንድ ሰዎች ሰብረዉ ራስን መዉደድ ያስተምሩናል....አንዳንድ ጨለማ ምሽቶች ፅልመት ጋር ያወዳጁናል ...አንዳንድ ቀዝቃዛ ጊዜያት ዉስጣችን የተቀጣለዉን ፍቅር እና የሰዉ ተስፋ አጥፍተዉ አቀዝቅዘዉት ይሄዳሉ ....እናም ደና ነን ...ደና ነኝ

@faiza_kiza
❤️❤️❤️❤️❤️please join and.share family

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

jami.bio/faiza
Hey there! Exciting news - I'm now on Jami and I'd love for you to check out my profile!, See you on the other side! 🤘😎

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

........................................

✍faiza


አይፈጠሩም ብለን ያሰብናቸዉ ተፈጥረዋል....አይቀየሩም ያልናቸዉ ተቀይረዋል.....የተከራከርንላቸዉ የማልንባቸዉ ሰዎች ከጎናችን የሉም.......አያልፉም ያልናቸዉ ህመሞች አልፈዉ ድሮ ሁነዋል.....ማን ቀረ? እኛ እና የማይጠፋዉ የሀሳብ ገመድ ትዝታ.....በእርግጥ እኛም የሆነቀን እናልፋለን ትዝታችንም አብሮን አፈር ይለብሳል ግን....እነዛ በጣር ያለፍናቸዉ ትናንትናዎች ...አይናችንን ጎርፍ ያለበሱት ሰዎችና ገጠመኞች.....ስናስባቸዉ የሚያሙን ...የሚያሳፍሩን ትዝታዎች ....ዛሬና ነገን እንዲያጨልሙብን እድል ልንሰጣቸዉ አይገባም😊

Just sayin🥹

@faiza_kiza join please

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

አንድ ሳቅ አላት

መስከረም ጥቅምት:
ከላፍቶ ዳገት - እንደሚነሳ፥
ልብ የሚያሳቅል - ቀልብ የሚነሳ፥
የጽጌ ሰሞን...
የአደይ አበባ - የጸደይ ሽታ...
አንድ ሳቅ አላት - አንድ ፈገግታ።

የናፍቆት አፀድ - የፍቅር ሰፈር፥
አንገት የሚስም - ልክ እንደከንፈር፥
እንደመልዐክ - በግራ በቀኝ፥
እያረበበ..
ከዘመን ክፉ - የሚደብቀኝ - የሚጠብቀኝ፥
አንድ ሳቅ አላት።

ከእሷ አፍ ብቻ - የሚስገመገም፥
በምድር እድሜ - የማይደገም፥
የማይቻለን - የሚቻልላት፥
አንድ ሳቅ አላት።

የሰማይ ደረት - ተሸነቆረ፤
እንደጣቃ ጨርቅ - ተተረተረ፤
ትርትሩ መሐል - ዐይኔ ቢከተኝ፥
ቅዱስ ቅዱሱን - አመላከተኝ፥
አመላከተኝ - ተስፋ መቅደሱን፤
አንድ ሳቅ አላት...
ከሆነ ቦታ - ስቃለች እሱን።

Micky Minassie

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

"ከጊዜ ስጓተት መዳፌ ቢላላም
ዓይኖቼን መድቤ ቁማር አልበ'ላም"

/Play me a memory/

ሄዶን

እውነት ሀሰት ተቃለጠ
በሬ ካ'ራጁ ሲያዘግም
እንባዬም በሳቅ ታጠበ
ሰባራ እምነቴን ላይደግም
ለካዱኝ ዘረጋሁ ክንዴን
ባልዝልም ያሻኛል ድጋፍ
እስከማይ ታንቀው ሲረግፉ
ደግፈው በሸኙት መዳፍ
ባመንኩት እምነት ብ'ሰዋ
ደሜ ነው ያነቃኝ ከእንቅልፍ
ለካደኝ አዋስኩት ዓይኔን
ከጥርጊያው ጀርባ ልሰለፍ
ደግነት ባያጣው ክፋት
ሙታንም ህይወት ያውሳል
ለደሙ ደም አይገብርም
ህያው ግዛቱን ይወርሳል፡፡


21/01/2023
Sat

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ሁሉም እግሩ ለመሄድ ያኮበኮበ አይመስልም..ድንገት..ዛሬንም እንደዘበት በነበርንበት የምሽት ንቃት ላይ እያለን የተሸከፈ ጓዙን ጠቅልሎ ለስንብት ይጎበኘናል..እኛም የመንገድ ነገር ያስፈራን ይመስል ልባችን እንደመራድ አድርጓት ታብጣለች..ይገርመናል ደሞ..እኛ ተጓዥ የሆንን ሰዎች ካኮበኮበ እግር አልፈን ያኮበኮበ ልብን ማየት ተስኖን ነበርን?..እንላለን..መልስ ሰጭውም እኛው ጋ እንዳለ አይነት ይናገራል.."ንቃታችሁ ሲገለጥ መደንዘዝ ነውና..ድንዛዜአችሁም ከሱ በቀር በዙሪያችሁ ላለው ቦታ አይሰጥምና ካለማወቅ ባልተሻለ ማወቅ ቸልታችሁን ተከናንባችሁ ነበር.."..መልሱንም በዚህ እውቀታችን ቀድመን ስለምናውቀው አይገርመንም..ይልቁንም ወደ ጭለማው ንቃታችን ደግመን እንገሰግሳለን..ከብዙ ሸክማችን ለጥቂት አፍታ እንገላገላለን..አዙሪቱ አያቆምም..ደሞ መልኩን ቀይሮ እንዳ'ዲስ ያስጎነብሰናል..እንዳ'ዲስ እንዳቃናን ሆኖ..

      "በመንገዳችን መካከል የጉዞ ውሀ
ሲጠማ
      ብርታት ነው የጥርስሽ ድርድር ፅዋ ነው
የሳቅሽ ዜማ.."

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

...የቀጠለ

ገቢር አንድ

ትእይንት አንድ

( እሱ የብስራቱን ዜማ ለልብ እያቀነቀነ እሷን ለማግኘት "መቼቱ"ላይ ተደላድሎ በስልኩ ነይልኝ ተማፅኖ ...)

እሱ:-  አንቺ ሴት( ከትናንቷ "እሷ"  ስለተለየች)  የመምጣትሽን ዳና የጠበኩ ነው፡ትመጪብኝ ይሆን እባክሽ አትቅሪ( የሰደደው የስልክ መልክት ነበር)

ያቺ ሴት(እሷነት ስለሸሻት):- ሮጥኩ፣አመለጥኩህ ዘገየህ፣በጊዜ ዳናዬ ሌላ ደጅ ላይ ተራግፏል፡ትናንት የሚያቀው፡ዛሬ ላልጠፋው ደጅ አደርኩ፡እናም ላይህ አልሻም...(የተቀበለው )

እሱ:-(ሳቅ ደስታ እና ፍራት ራስወዳድነት ባሉበት)  አውቃለው፡እወቂው ትናንትን ልመልስ ደጅሽ ድረስ አረገጥኩም፣ዛሬንም እንደትናንት ልኖር፡እሰይ ተመስገን ባለመቆምሽ ወደኋላም መሄድ ይሁን ወደፊት መሄድላይ አዲስ ነገር አለ(...ሰደደው)

እሱ:- (ደገመ)መቅናቱ ላንቺ ተመስገን ነው: ግን አንዴ ነይ እና ለመሄድሽ ምቾት የሚሆን ከስሜትም፡ ከእምነትም ነፃ የሆነ እውነት ቃል ላካፍልሽ፡ትናንታችንን እንዳንቺ የማይክድ፡ለዛሬ እኛነታችን ትርጉም የሌለው(ስለረፈደ)፡ለመንገዳችን ግን ስንቅ...የሆነ ቃል

ያቺ ሴት:- (ሳቅ ቧልት ያለበት ይመስላል) ትገርማለክ ማየት የማልፈልገው ሰው በምድር አንተ ነክ እያልኩህ ላግኝሽ! ደግሞ ለፍቅሬ ጊዜ እሻለሁ!...

ያቺ ሴት:- ፍቅሬ ጋር ነኝ ተወኝ ...!(መረር ያለ)

እሱ:- (ግርምት :-ከላግኝህ/እንዳላይህ የወሰደ መንፈስ የተወጋ ይሁን የሚል ይመስላል)  ፍቅርሽን አገናኝኝ ሰላም ልበለው...

ያቺ ሴት:-  ማለት
እሱ:-  ላግኝው
ያቺ ሴት:-  አብደሀል በል ቻው በቃህ ጊዜየን አትሻማ...



እሱ:- ( ያበድኩት ትናንት አፈቀርኩህ ስትይኝ ሳምን ዛሬም አፍቅሪያለው ስትይኝ እንደማምንሽ ሲገባኝ ነው)
መልካም ጠብቅሻለሁ ከቻልሽ ዛሬን ብቻ!...(ሰ.ደ.ደ.ው)


( ብቻውን ለግርምት ቅርብ ሁኖ ለምሬት እየተጠጋ "የመቼቱ" ምቾት ከብርዱ ቁር ጋር ተዳብሎ አዲስ ውልደት ሲነፍስ) እንዲህ የሚል ቃል እኔን ወደሰማይ ነጠቀኝ( መናኝ ሂድ ተሰደድ በስደተኛው የማሳይህን የምነግርህን ክተብ...)

አየሁ :- የጊዜ ግጥምጥሞሽ ከመሆን እንደሚበልጡ፡ እኛ የምንለውን ማንነት ለማስካድ ኢምንት እንደሚበቃቸው፡እንዲሁ እንደዘበት፣እንዲሁ እንደወረት ማለቅ እንደሚመጣ፡መወለድ እንደሚገኝ፣ማፍቀር እንደሚነጥፍ፣መጥላት እንደሚሰርፅ...

አየሁ:- ክርስቶስ ይሁዳን ሁኖ እንደነበር፡እሱ እሷን ክዶ እንደነበር...

አየሁ:- የመሆን በር ሲሰበር፣የተስፋ በድን ሲቀበር፡ መላእክት ጥቁር ሲለብሱ ፣ሉሲፈሮች ለፍቅር ፅዋ ሲያነሱ፡የመበለቲቱ ደም በራሱ ሲቆም...

አየሁ:- ሱታፌወች ሲነጥፉ፣ሱራፌሎች ከመንበራቸው ሲረግፉ፡ያሬድ ዜማውን ሲያበላሽ፣ሰሎሞን ጥበብን ሲያኮላሽ፡ዳዊት ንግስናን ሲቀማ፣አብርሀም ለንብረት ሲያነባ...

አየሁ:- መምጣት በመሄድ ሲያከትም ንጋት በራሱ ሲጨልም አየሁ በዚሁሉ መሀል በየፊናቸው አንድ እሷ እና አንድ እሱ ነበሩ እንደተለያዩ....

እንዲህ ብለህ ተርጉም አለኝ:  ልብን አስችል በሉት እና መሆንን ተለማመዱት በቀልን ለጊዜ ተውት!... በርባን እና ክርስቶስ ከይሁዳ እኩል መቀጣታቸውን አትዘንጉ እንግዲህ ማን አሸነፈ ማንስ ተበቀለ...

አያልቅም..

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ፊትና ጀርባ

📝 ኒራን

የሰጠሽኝ ጣፋጭ ፍሬ :
እያየሁት በሰበሰ :
የሰጠሁሽ ጥቁር መቅረዝ :
ምስጥ በላው ፈራረሰ


                 ሄዶን

ክፍል ፩

መብላት አይቻልም እሺ! አልጋህ ላይ ስትሆን በደንብ ሊታይህ የሚችልበትን ቦታ ምረጥና ብርጭቆ ውስጥ ውሀ አርገህ አስቀምጠው። ታዲያ ጠዋት ስትነሳና ማታ ስትተኛ አብሬህ ሆንኩ ማለት አይደለ? ያው ቀን ቀን በአካል አለሁልህ! ብላ ጉንጬን ስማኝ ሄደች። መዳፌ ላይ ያለችውን ቀይ የፖም ፍሬ እያየሁ...


ጉንጩን መሳሟ ምን ይገርማል? ያኔ አታስታውሺም ጆኒ ጋር ተጣልተው በስልክ ሲሰዳደቡ? ከዛ አቲ ደውሎ በኔ ጥፍት ነው የተጣላችሁት እና ሶሪ ምናምን አላት። ከዛ ስለደወልክልኝ ደስ ብሎኛል ነገ ላግኝህ ምናምን አላለችም መሰለሽ? እኔ በሳቅ ልሞት! ከዛ በማግስቱ ስታገኘው አንገቱ ላይ ተጠምጥማ ያን ሰፊ ከንፈሯን ጉንጩ ላይ አለጠፈችበትም? ከሩቅ ለሚያያቸው እኮ የከረሙ ፍቅረኛሞች ነው የሚመስሉት! በመጀመሪያ ትውውቅ መሳሳም ሼም ነው በጣም!! እኔን አይታ እንኳን አላፈረችም። አቲ ግን ስትስምህ ደንግጠህ ነበር ኣ? ሂሂሂ...ለነገሩ ማንስ ይሄን ይጠብቃል? እኔ ግን የገረመኝ ይሄ ሳይሆን የአፕሉ ነገር ነው። በሷ ቤት እኮ ሮማንስ ሮማንስ እያጫወተችህ ነው!! ሂሂሂ....


ታውቃለህ በጣም ተጎድቻለሁ!! ግን ባንተ ልካስ ነው አይደል ለዘመናት ያለቀስኩት? ታውቃለህ(ታበዛለች) ድንግልናዬን ያጣሁት መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ እያለሁ ነበር። ካፈቀርኩት ልጅ ለፍቅሬ ምላሽ ፍቅርን ስጠብቅ በጉብዝናዬ እና በሰቃይ ተማሪነቴ ቀንቶ አስደገመብኝ። ክብሬን አሳልፌ ስለሠጠሁት በምናምኑ ተበተበኝ። በጣም ታመምኩ!! ትምህርቴን አቋርጬ ፈውስ ፍለጋ ማርቆስ ድረስ ሄድኩኝ። አዋቂ የተባለው ሠው ክንዴን በምላጭ እየተለተለ ደሜን ሲያፈሰው ሰነበተ። አየህ?!...(ክንዶቿን ዘርግታ ሰንበሯን እያሳየችኝ...) በስንት መከራ ድኜ እናቴ ጋር ደብረብርሃን ተመለስኩ።...

-አቲ ግን ዩኒቨርስቲ ገብቻለሁ አላለችህም?
-ኧረ ብላኛለች! መቀሌ አይደል የተማረችው?
(ተያይተው በሳቅ ፈረሱ)
-አላልኩሽም? ይህች ሳክሰኛ የሳክስ ንግስት!! ሸሌነቷን ስታስተባብል ዩኒቨርስቲ ቅብርጥሶ ትላለች። አላውቃትም እንዴ በዋለችበት ስትታለብ! ይህች ላም!ሂሂሂ...

ያ ከሀዲ ጉድ ከሰራኝ በኋላ ወንድ ማመን ከበደኝ። ግን በጊዜ ሂደት ሌላ ወንድ ለመድኩ። ናታን ይባላል። በጣም ደስ የሚል ልጅ ነው! ግን አንድ የማልወደው ባህሪ ነበረው። አቲዬ የሚገርምህ ከአባቱ ብር እየሰረቀ ጫማ ይገዛ ነበር። ተው ብለው አልሰማም አለ። ግን እሱን ማፍቀሬን መተው አልቻልኩም። ከእናቴ ተጣልቼ ከቤት አባራኝ ስለነበር ተከራይቼ ነበር የምኖረው።  ከርሞ ፍቅሬ ሲበረታ የነበርኩበትን ቤት ለቅቄ ናታን የሚኖርበት ሠፈር ሌላ ቤት ፈልጌ ተከራየሁ። ሌሊት ቤተሰቦቹ ሲተኙ ጠብቆ በመስኮት ዘሎ እየመጣ  ለረዥም ጊዜ ወጣን። ግን እያደር ጭኔን ለመደውና ፍቅሩ ቀነሰ መሰል በሆነው ባልሆነው መጋጨት ጀመርን። ይባስ ብሎ እንለያይ አለኝ!! ቢያንስ ምክንያቱን እንኳን ቢነግረኝ ደስ ይለኝ ነበር።(ካይኖቿ ውሀ መፍለቅ ጀመረ)... ማርያምን አቲዬ የሠፈር ሰዎች እያዩኝ ነው እግሩ ላይ ወድቄ የለመንኩት ማርያምን...(ድምጿ ሰለለ)


-ስማ ናቲ! አንተ ናታን!! 
-ወዬ ጄሪዬ
-አንተ ግን ያ ሁሉ የሰፈር ሰው እያየ ጭራሽ እግርህ ላይ ወድቃ ጥለሀት ትሄዳለህ? አቤት ወንዶች ስትባሉ ግን...
-ኧረ በእግዚአብሔር የሷን ነገር እያወቃችሁ አትነዝንዙኝ!! ስማ አቲ እሷ እኮ ማለት ከሆነ ሰው መኪና ስትወርድ አይቻት ደውዬ የት ነሽ ስላት ቢሮ ነኝ ብላ የዋሸችኝ ሴት ናት። ደሞኮ አብሯት የነበረውንም ልጅ በደንብ አይቼዋለሁ። የሆነ ነገርማ ነበራት። ግን ሰዎች ይቅርታ አድርጉልኛ ሳይዳ ውስጧ ቢከፈት ደም ሳይሆን ውሸት የሚፈሳት ነው የሚመስለኝ።

-ግን ለምን እንለያይ አለሽ?(እንባዋን በመዳፌ አበስኩላት)...
- በጊዜው ምንም ምክንያት የለኝም ነበር ያለኝ። ቆይቶ ግን ከሆነ ሰው መኪና ስትወርጂ አይቼሽ ደውዬ የት ነሽ ብልሽ ቢሮ ብለሽ ዋሸሺኝ አለኝ። ታውቃለህ? ልዋሸሁ ፈልጌ እኮ አልነበረም! ልጁ የስራ ባልደረባዬ ቢሆንም አልፎ አልፎ ልጋብሽ፣ ልሸኝሽ ይለኝ ነበር። የዛን ቀንም ስራ ጨርሰን ቤት ካላደረስኩሽ ብሎ ሲያስጨንቀኝ እሺ አልኩት። ናታንም ሲደውል ለማይረባ ነገር አጉል ጥርጣሬ ከሚሰማው ብዬ ስራ ቦታ ነኝ አልኩት።...

-ደግሞ የዛች የፌክ ስኳር በሽታዋ ነገርስ?ሂሂሂሂ...በጣም እኮ ነው የምትገርመኝ! ፌክ መሆኑን እንዴት እንደነቃሁባት ታውቃለህ? የሆነ ቀን ጠዋት አመመኝ ብላ ደውላልኝ ቁርስ ልሰራላት ቤቷ ሄድኩኝ። ቁርሷን በልታ ስትጨርስ መድሀኒቴን ልዋጥ ብላ ተነሳች እኔም የሞባይል ካርድ ገዝቼ ልምጣ ብዬ ተነሳሁ። በብርጭቆ ውሀ ቅጅሊኝ ብላ ክኒኗን ከቦርሳዋ ልታመጣ ሄደች። ውሀውን ቀድቼ ስሰጣት ክኒኑን ፊቴ ዋጠችና ብርጭቆውን ሰጥታኝ ፍራሿ ላይ ተጋደመች። ብርጭቆውን እቃ ማጠቢያው ላይ አስቀምጬ ካርዴን ልገዛ ወጣሁ። የሽንኩት ልጣጭ ስጥል ባዶ የነበረው የቆሻሻ ቅርጫት ካርዱን ገዝቼ ስመለስ አንድ ክኒን ውስጡ ተጥሎ አየሁ። ወደ ቤት እየገባሁ መድሀኒትሽን ዋጥሽ ሳይድ ስላት ደንግጣ ኧረ ውጬዋለሁ!! አላለችኝም! ሂሂሂ እኔ መች አልዋጥሽውም ወጣኝ? ሂሂሂሂ....

-በጣም መሸ አይደል? ወደ ቤት እንግባ! ዛሬማኮ መድሀኒቴን ጨርሼ ጉድ ሆኜልሀለሁ!
-የምን መድሀኒት?
- ስኳር እንዳለብኝ ነግሬህ የለ? አንድ ክኒን ነበር የቀረኝ! ጠዋት ልውጥ ስዘጋጅ ከእጄ አምልጦ አልወደቀም መሰለህ? አውጥቼ ጣልኩ።
- እና ምን ተሻለ? ዛሬ ሙሉ ቀን ላትውጪ ነው ማለት ነው?
- ጠዋትማ ውጫለሁ እኮ!
- እንዴ አሁን ወድቆ..
- እ ሁለት ነበር እኮ የቀረኝ! በቃ መሸ እንግባ! የልብ ጓደኛ ምኑን እንደሚሳም ታውቃለህ?
- አላውቅም!
- እጅህን ስጠኝ!
(
መዳፉን ስማው ሄደች)....


<< ሰርቆኛል>> ብትልም: እንደ ፈራጅ አይታን
ስለምናውቃቸው መርጠናል ዝምታን...
እሱ ሰርቆን ነበር : እሷ ደግሞ ዋሽታን።


                    ረድኤት አሰፋ


ይቀጥላል...




ⒸNIRAN2015

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ፋኢዛ🫡

አንዳንዶች ያፈቀሩትን መርሳት ዉስጥ ስላለዉ ህመም ያወራሉ ......አንዳንዶች ደሞ ያፈቀሩትን መጠበቅ ዉስጥ ስላለዉ ስብራት .....ግን የቱ እንደሚያም ታዉቃላችሁ መጠበቅ ይሁን መርሳት ያለባችሁ ግራ ሲገባችሁ.....





╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
             @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

By faiza🫡


Never lose hope in one person.....never doubt one person....never lie one person....never stop to communicate with one person.....never put down one person....never get ashamed of one person .....cause that person is the only one who will be there at the end of the day....and that person is you😊




╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
             @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share❗️❗️

😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
😍   Join @faiza_kiza     😍
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

jami.bio/faiza
Hey there! Exciting news - I'm now on Jami and I'd love for you to check out my profile!, See you on the other side! 🤘😎

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

በፋኢዛ...✍

ህይወት አለዉ ....ሰላም አለዉ.....ሳየዉ ደስታ አይሰማኝም ....ሲያቅፈኝም እንደዛዉ ....በደስታ አልፈነጥዝም....በቃ ዝም ያለ ስሜት ...አብሮነቱ ለብቻ የመሆን ያህል ሰላም አለዉ....ምን ላዉራ አልልም ቃል ሳናወጣ የምንግባባቸዉ ብዙ ቃላቶች አሉ....ፍቅር ይሆናል ....ወይ ከፍቅርም በላይ ...ብቻ ሰላሜ ነዉ ...ሰላም አለዉ ....




╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
             @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share❗️❗️

😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
😍   Join @faiza_kiza     😍
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

እየሄዳችሁ🚶

በፋኢዛ🥱


መንገድ መንገድ ነዉ እስከሄድክበት ድረስ አያልቅም ......እስከሄድክበት ያደርሳል....ግን ስለ ስኬት ንገሪኝ ካልከኝ መንገድ ያሰብክበት እንደማያደርስ ነዉ የምነግርህ....መሄድህ ሳይሆን እየሄድክበት ያለዉ አቅጣጫ ነዉ ስኬትህን የሚያረጋግልህ....ያለ አቅጣጫህ ከሄድክ ምንም ያህል ከቅያሱ ብትርቅ መመለስህ አይቀርም ወይ ደግሞ ጠፍተህ መቅረትህ....እና ጓደ በያዝከዉ መንገድ መፍጠንህን ቀንሰህ አቅጣጫህን ፈትሽ .........እየሄዳችሁ🚶🚶🚶


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
             @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share❗️❗️

😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
😍   Join @faiza_kiza     😍
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

Simple reminder 😁


ዛሬን ለማየት ያልታደሉት ብዙ ናቸዉና አመስግን...እናም ትናንት ከነበርከዉ የተሻለ ሁነህ አሳልፈዉ😊


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
        @faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

      For any comment    
       @mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥


😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
😍   Join @faiza_kiza     😍
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ሰላም ህዝባ ህዝቦች ፋኢዛ ነኝ😄 ከአመት ከምናምን እረፍት በሇላ ብዕር እንደመያዝ እያደረገኝ ነዉ እና እንዲፃፍላችሁ የምትፈልጉት ወይ አሁን የምሰራበትን ይዘትና እንዲቀርብላችሁ የምትፈልጉትን content በተለመደዉ ቦት ከረሳችሁትም @mornin_bot አድርሱኝ እና ሼር በማድረግ አስደስቱኝ😁

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

remedan kerim ahbab🌙

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

Tip of the day🫣

✍faiza

አልቅሰን እንደማናዉቅ ፈገግ እንበል 😊
ወድቀን እንደማናዉቅ እንታገል 💪
ተጎድቶ እንደማያዉቅ እናፍቅር👩‍❤️‍💋‍👨
ነገ እንደሌለ አድርገን እንኑር🫵

@faiza_kiza
@faiza_kiza

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ውበት እና አበባ

✍🏼 ሄዶን


" አንቺን ሳስብ ውበት ፤ ውበት መልኩ አበባ "


ስላንቺ ሳስብ የውበት ትርጉሙ በአበቦች አምሳል ከምናቤ ይፀድቃል። በመጨረሻዎቹ ሠዓታት ካሸለበኝ ግማሽ ሞት ቀስቅሶ የመኖርን ትንፋሽ የተጋራኝ ውብት በሴትነትሽ አውድ ተቀንብቦ ሰዋዊ እንስሳነቴን ሲያጎላው፤ ድካሜን ንቄ ለሽኝትሽ ተሳልኩ እንጂ የምድር አምሳል ምስቅልቅል ገላዬ ላይ የፀደቅሽ አበባዬን እንደቀጠፍኩ መቼ አስተዋልኩ?


" ያለ ስምሽ ማን ነሽ? ያለ ቦታሽ የት ነሽ? "

ስላንቺ ሳስብ የውበት ትርጉሙ በአበቦች አምሳል ከምናቤ ይፀድቃል። ሁሌም ባይሆን በዙሪያሽ ያሉ ሰዎች ስምሽን ሲጠሩት አደምጥና ቃሉ ስለሚከስትላቸው ምስልሽ አስባለሁ። ሁሌም ባይሆን የት ናት? ብለው ሊፈልጉሽ የት ሲሄዱ ባበቀሉሽ ነፍሶች ልኬት የታነፀው ቤትሽን በልኬታቸው እንደሠፉልሽ አስተውልና ቅጥርሽ ስለጋረደባቸው ነፃነትሽ አስባለሁ።
በተጋሩት ጠረኖችሽ ያልታወደ : ማናት? ብሎ ማነሽ ቢልሽ፤ የት ናት? ብሎ የት ነሽ ቢልሽ በነገሽ ላይ ቤቱን ያንፅ በሠፈረሽ ልክ ይለካሽ እንጂ ዛሬዎችሽን ቀይጦ ቀለምሽን ይቀምር ዘንድ እንደማይቻለው እኔ ህያው ምስክር ነኝ።


ውበት

" wild poetry on our lips when we kiss "
– butterflies rising


ስላንቺ ሳስብ የውበት ትርጉሙ በአበቦች አምሳል ከምናቤ ይፀድቃል። አንዳንዱ ቀን እብድ ነው! ራስን ለራስ ሠውቶ ፤ በራስ ዙፋን የሚነግሥ! ለኔም ከእብደቱ ቢጀባኝ ከመንገዴ ተካክጄ አዲስ መንገድ ስለማለም ዓመታትን አንቀላፋሁ።
ስነቃ; ልብሶቼ ቆሸሹ፣ ገላዬን እከክ ወረሰው፣ ጥርሶቼ ወየቡ፣ ከንፈሬን ጭስ አጠቆረው። ታዲያ ቀኔ በቀንሽ ቢማረክ፤ ዙሪያዬን ባፍታ ዘንግቼ ወደ ጥጋትሽ ተሰበሰብኩ። ሳቄ ያስጨነቃቸው ምን አድርጋህ ነው? ብለው ተቆጡ!!

ባጨስኩበት ሳመችኝ !!


አበባ

ስላንቺ ሳስብ የውበት ትርጉሙ በአበቦች አምሳል ከምናቤ ይፀድቃል።

- ደግሞ በአካል ስንገናኝ የምነግርሽ ብዙ ነገር አለ...
- አሁን ንገረኝ...

ለወራት ካራራቀን እውነት አገግመን እንደ ፈቃዳቸው ዳግም ተወዳጀን።

- እኔ የምልህ...
- ወዬ ፍቅር
- ባለፈው እነግርሻለሁ ያልከኝን ነገር አትነግረኝም?

ሀሳብን በሀሳብ ስለመሻር ስጠበብ ከተመስጦዬ ደጋግሞ የሚያነቃኝ ያልነገርኳት አንድ እውነት ይህ ነው...

ውበቴ ነበርሽ !!




©Hedon2023

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

✍🏽ሕያው

ያንገቴ ላይ ማህተም ያንገቴ ላይ ንቅሳት
የከናፍርሽ አሻራ ያ'ይኖችሽ ነበልባል እሳት
ያ'ይኖችሽ ተስፋ አቆራረጥ የቃልሽ ቃላት ፍለጋ
ብትንትን ያልሽበት መደብ እርጋታን በ'ምነትሽ ማጥመድ..እዛጋ..

አንዳንዴ

ፈዝዤ የቀረሁ አይነት ዘላለም እዛ እንደመቆም
ብትንትንሽን መሰብሰብ ነገዬን ለነገሽ ማቆም
ያ'ፍታ ምኞቴን አያለሁ በ'ምነትሽ ጥላ ሰክኜ
ለህይዎት ምሰሶ ማገር ለሞትሽ ከለላ ሆኜ

አንዳንዴ

እናፍቃለሁ እንደዚህ ሰው መሆን ባንቺ ጎዳና
ምናለ..
ሁልጊዜ አንዳንዴ ቢሆን ዛሬም ባንዳንዴ ቢፀና..

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

✍️ ሄዶን

የአቦጊዳ ጥቁር ቀለም
የውብ ገፆች ች'ኮ ብዕር
ክብሩን ረግጦ የሰበረ
መንገድ አልባ ተራማጅ እግር...

ከልቡ ዳስ ውብ ማህሌት
ከፍቅር ካብ ከመቅደሱ
መንገድ ልኮት የመጣ እንደሁ
ወሰን አልባው ሰው ንፋሱ...

ፅፎ መቅደድ
ጭሮ ማንደድ

በስሪቱ ነበር ስቃይ...

ወድቆ ማንገስ
ነትቦ ማበስ

በከንቱ ዓለም የተስፋ ጣ'ይ...

ባ'ዙሪት ህግ ድግግሞሽ
በመሰልቸት ህያው ጥለት
መዳከሙ ያበረታቸው
ቅፅር ካቡን የናዱት ለ'ት
ለመውደቁ ልቡ ሲያምፅ
እየሾመ ለአፈርሳታ
ይክሱት ዘንድ ሲከ'ሳቸው
ስለናዱት ቅዱስ ቦታ...
ልቡን ስሎ ልብን ሲያድ'ን
በመሰሉ ፊቱን ጋርዶ
የዘነጋህ ይምሰል እንጂ
ያነፀውን እምነት ንዶ

"መች ይዘነጋሀል?"

ሌላው ቢቀር የዚያችን ለ'ት...
ሌላው ቢቀር ያ'ንዲቷን ለት...
ያፈካውን የጥርስህ ላይ የምሽት ጣ'ይ
እግዜር ሳቀ ብሎ ያማህ መልክህን ሲያይ

ያ'ንዲት ታ'ምር
   ያ'ንዲት ጨረር
ያ'ንዲት ምስጢር
   ያ'ንዲት ቀመር

ምን ብታጥር  ...
   አይኮንኑት ጊዜ ዳሷን
ምንስ ብታንስ ...
   ምንስ አለ ሚ'ያህል እሷን?

ብቻ...

መንጠቅ በቀማነው የነበር መሰረት
እንኳን ባላፊ ሀቅ የሌት ጥላ ክስረት
በሞት ንፋስ ቢናድ ያስጠለለን ዋርካ
ካ'ንተ የሆነን ነገር ምን አለ የሚተካ?

ምንም!!




   

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

✍ መናኝ

የሚቀጥል



ትእይነት ሁለት

( የህይወት መጋረጃው ሲገለጥ: እሱ ከትናንቱ መዞ እንደ ሸንኮራ እያኘከ ፈገግ ሲል ይታያል)

ምልሰት!
ድሮ ድሮ እኔ ሳውቃት
ልብ ነበራት
             ቀልብ ያበጀ
በሀይማኖት የታጠረ
በባህል ወግ የደረጀ
ከእለታት አንድ ቀን ይሉኝታ ስናጣ ልቧን ብፈልገው
እንደኔው አጣሁት አጥፍቶ ጠፊ ነው...


( አመዳም ሳቅ አመዳም ፊቱላይ)( ፀጉሩን እያከከ ስለግጥሙ ማሰብ ጀመረ፤ ቀለሙን ሊሰድር፡ ቃል ሊመርጥለት አሰኝው!። በድንገት ሌላ ውልብታ: የሱ የመኖር ቀለም ስደራውን በአንፃር የሚያስቃኝ፤ የሱን የእምነት ቃል በንፅፅር የሚያጎላ:( ፈገግ አለ ያንኑ አመዳም ሳቅ)፡ የባሰ አይደል! ፡ ለግጥሙ ተመስገን ነው! "ከኔ የኑረት ግጥ'ም የሚሻል" ይል ይመስላል።)

ትእግስቷ ቻይ እንደመሬት፣ ምህረቷ ነገን ያኖራል
አፏ እንደ ህፃን አንደበት፣ ይጣፍጣል ይናፍቃል።


( "ይጣፍጣል"  ላይ ምናብ ረገጥ አድርጎ: እንዲህ አይነት 'ትዝታ' አወጣ ለራሱ በራሱ: 'ትዝታዬ': መቼ ይሆን እግርሽን በሞቀ ውሀ የማጥብልሽ? የታጠቡትን እነዛን ስስ ለመዳፍ ቅርብ የሆኑ እግሮችሽን በቅባት በወረዛ እጆቼ ከላይ ታች የምዳስሳችው?( መቼ ይሆን የሞተን አካል ነበስ መዝራት በሚችል ድምፅሽ 'ትናንቴ' ብለሽ ጠርተሽኝ ደስ እንደሚልሽ የምትነግሪኝ?)
የኔ እረፍት መቼ ይሆን የገነትን ምስራቅ ይዘሽ የኪሩቤል መንበር እስኪመስለኝ በማከብረው መኝታችን ላይ ሳለሽ ነብስ በሚዘራው እይታሽ በፍቅር እየናጥሽኝ ትናንቴ እራት አታሰራልኝም የምትይኝ?)

መቼም!(ሲጠይቅ የሚፈልገው አይመስልም አለመፈለጉን ሽሽት የሚያወጣው ኩሸት መሆኑ ጠፋን!(ከባለ ፀሀፊው)

መቼም አትናፍቅ አትለኝም፣ ፈልጌ ደግሞ አልናፍቅ
ማነው ትዝታ የማይኖረው የኖረበትን ቀዬ ቢርቅ?
እናፍቃለሁ እናፍቃለሁ
ትዝታ አለኝ የማይመዘን የማይለካ
እዚህጋ ይሻላል እዛጋ ሰው አለ የለም ቦታ መረጣ በጫካ
ይህ ጉቶ ይሻላል ያ ዛፍ መቆሚያ መቀመጫ ዱካ
ሳልል...
(ከራስ ጋር ትግል ነበረው
ውልብታውን ማን ሊያስጥለው?

እዲህ የሚለውን: ዛሬ ውል ብለሽኝ ነበር። ባለ ማተብ የሱስ ጌታ ለንጋቱ የከንፈሩ ቅድ ቅጥል ጭስን መማግ ነብስ እንደሚዘራበት አይነት። ናፍቆት አይመስለኝም!

ዛሬ ታይተሽኝ ነበር። የህልም አለም አጋፋሪ በነበር ውቅያኖሱ ላይ የስብራት ወጀብ ሲንጠው ከትናንት ለትናንት የተላከለት መሲህ ግዞት ወጀቡን ሲገስፀው አይነት። ትዝታ አይመስለኝም!)

ያኔ ያኔ እኔ ሳውቃት ክንፍም ነበራት...
የቱ ጋር ነህ ብላ መልስህን ሳትጨርስ
ከተፍ ትላለች እንደማርያም ፈረስ
ከዛ ነፍስ ውጪ ነብስ ግቢ
ላምላክ ከበሮ ለወዲያኛው ድቢ
እንዳልሞት እንዳልድን አድርጋ ደግሞ ትሄዳለች
ከፍ እያለች ከፍ እያለች
ከፍ እያለች እየተሽኮረመመች
አሁን ባንተ ጊዜ ሴትዬዋ እንዴት ነች
በኔ ጊዜ አለም ነበር....

ባንተ ጊዜ እንዴት ናት ግን?( ይደርሰው ይመስል የሀሳብ ሸንኮራወን ምጥጥ ያደርጋል ለባለ ምልክቱ...!)

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

✍ መናኝ

ወደ መንገድ ሰወች 

እውቂያ

ጊዜው
  ደስ የሚል ምሽት: የሰሜን ቀዝቃዛ ንፋስ አቅጣጫውን ስቶ የሚነፈስበት፤የሆ አይነት የለም: ትንቢት ለመንገር ያኮበኮበ  ድምናዊ፡ሰማይ የተጫነው፤ የስርቻው ፍጥረታት፡ አኩቴት ለምንም ፈጣሪያቸው ይሰድሩ ይመስል፡ኦናውን ጥቁረት እያናጉ፡የሚያለዝቡት ድምፅ ብቻውን ገኖ የሚሰማበት፤ ዳናን የማንገስ አቅም ተሰቶት፡እርምጃን በጆሮ ሽፋሽፍት፡መለካት እስኪያስችል፡ በዝምታ የተሰደረ: ደግሞ ለክፋታቸው አማልክቱ የምድሪቷን ጉሮሮ፣በጠብታ ለማራስ፣በእንቁልልጭ መልክ ከማሰሯቸው ከፍተው የሚለቁት እርጥብ ፈሳሽ፡ በስልችት አቅም ቁልቁል ሲወርድ፣ለንዴቱ ምድሪቱን መቅጣት ባይችል ለገላ አለንጋ የሚሆን የብርድ ቁር አብሮቶ የሚያለቅስበት ምሽት ነበረ...

እሱ
   እድፋም፡አብረቅራቂ እጆች፣ለማቀፍ የማይቦዝኑ፤ ጥላሸት የከለለው፡ዳውላ ስፋት ያለው፣ጭንቅላት ከማሰብ የማይቦዝን፤ ነጠላ ልኬት ያለው፡በስሱ የተዳወረ፣አፍቃሪ ልብ፤ የተቸረው መፃጉ: ከንአንን ሽሽት ካራን ላይ በድንኳን ቤት የሰራ፤ "አብራምነት" ያልጎደለው፤ የቀኝ ግራ፣የጥቁር ነጭ፣የጥሩ መጥፎ የሆነ ነበረ...

የትእይንት መግለጫ...
  ቅንፍ አንድ(

♠እሱ ከተጠራበት አንስታ ላልተጠራበት በረከት የሆነችውን ወንጌሉን ከእጁ ተንሽራታ ለጳውሎስ ስታደላ ያያት ዴማስ...

♠እሱ "አለምን ወዶ ክዶኛል እና" እስኪባል መጠራቱን ትቶ  ጥቂት ጊዚያትን :በዘመናት የሸሸገባት ተሶሎንቄው ልጅነቱ ላይ(ጅልነቱ ላይ) ከእቅፏ ፍቅሬን መጠጥክ አይነት ነውር የተሸሸው ዴማስ...


♠ እሱ ይችልበት ፀጋ፣ይደፍርበት ብርታት የተቀባው፤ ይቀመጥበት ንግስና፣ይመራበት ብኩርና የተላበሰው፤ ሁሉ ከደማስቆ(ከህይወት ሀገሩ) ባንዲት መሰመር(እሷ) የተለወጠው(የተነጠቀው(የጣለው)) ሶምሶም...

♠ እሱ ለከንቱነት(ለአለም) ብኩርና የታጨበትን፡የንግስና ፀጉር ለመንግስቱ(ለፍቅር) ሲያስረክብ፡በልቧ ቦታ ተደላድሎ ሊነግስ፡ለአለም መድከሙን(መስነፉን) ቢያበስር ገሊላ ከፀጉሩ ጋር የሸሸችው ሶምሶም...

♠ እሱ ለአይሁዶች ግዞት(የዘመን ኑረት ጣእም) ቸልታን ሰቶ፡በደማስቆ ታሪኳ(እሷ)፡እስርቤት እንዳለ፡ስለ አዳኙ፣ስለ መሲሁ(እሷ) የዘመረው፣የኖረው ጳውሎስ...

♠እሱ ስለ...(ፍቅሯ) መከራን መቀበል ሙዚቃው የሆነ፤
የለትእለት መንገዱ ወደሰሊሆም የሚያቀና ፤ገዳይ፣ አሳዳጅ፣እስራኤላዊው( ሰዋዊው) በጌታው የብርሀን ጥሪ( በእሷ) ከመንገዱ የሸሸው ሳኡል(ጳውሎስ)...

እሱ በጥሏ በመሰቀል ፍቅርን የገደለው የቀራኒዮው ጉልበተኛ

ቅንፉ ይዘጋል)

መቼት

(የሆነ ቀን ነው አርብ ቀን፣ ሰኞ ቀን፣ ሮብ፣ሀሙስ፣ቅዳሜ ቀን ብቻ እሁድ ያልሆነ እረፍት የሌለበት(የህሊና)፤ የሆነ ሰአት ላይ አንድ፣ሁለት፣ሶስት...፣ሀያ ሶስት ምናምን ብቻ ሀያ አራት ያልሞላው መደላደል የሌለበት(የልብ)፤የሆነ ቦታ ነው እኔ፣እሷ፣ሳቅ፣ ጨዋታ፣ ተስፋ፣ትዝታ...ስሜት ምናምን ያረፉበት ጎጆ፡ብቻ አሁን የሌለበት(የፍቅር) መቼቱ ተመለሰ(ከጅምሩ ጋር ይስማማል))

የትእይንት መግለጫ...

   እሱ ላለቀችበት(በሷ በኩል ከሱ በኩል ወይም በሱ በኩል ከሷ በኩል) የስሪቱ ግማድ: "መሄዴ ነው" እያለች ነጋሪት ጉሰማዋን ከሩቅ ስታሰማ፤"ልሸሽህ ነው" አይነት ሙሾዋን ስትቀፅል፤'እየሱሳዊ' ምልከታው 'ከይሁዳዊ(ከልብ') ፀፀቱ እኩል ሲሰግሩ ዳናዋን ፈትሾ ለመሸኝት ዝግጅት ላይ በነበረ ( አቤት የፍቅር ሮሚዮነት(ውሸት አለበት))፤እሷ ሽሽቷ ከንፋስ ሩጫ ይቀድም ነበር እና ለእዝነቱ እንዲህ ይል ቃቶት ነበር(መዘክር)
       ግ'ጥም
ወዲያ ማዶ ሁኖ ፣ገዳይሽ ቢጣቀስ
ቸኩለሽ፣
ይሄው ጆሮሽ ደማ፣ ጌጥ እሰካ ብለሽ።
እኳላለሁ ብለሽ አይንሽን ወጋሽው
ሽቱ እቀባ ብለሽ ፣ ፍሊት ተቀባሽው
ኧረ ቀስ!
እግሮችሽ ተጋጩ ፣ ከሞትሽ ለመድረስ።
እረ ተግ አንቺዬ ፣ ቀስ ብለሽ ሂጂ
ባይሆን በመንገድሽ ፣እድሜሽ ይርዘም እንጂ
( ውሸትነት ላ/አያጣውም 'ኢጎ' ስለሚሆን የሱ)

ማሳሰቢያ አንድ:-  ከዚህ በላይ እሱ እሷን ከመሄዷ መንገድ ላይ ሳለች መሄዷን ሳይጣላ በክብር ሰረገላ የእውቀት ስንቅ አሰንቆ ወደፍቃዷ እንድትነጉድ የሞከረው የተውኔቱ የመግለጫ ክፍል ነው...

ማሳሰቢያ ሁለት :- ከዚህ በታች የሚቀርበው ትእይንተ ታሪክ ከእውነተኛው አለም ጋር በስምም ሆነ በተግባር አንድ ቢሆኑባቹ እንዳይገርማቹ " መኖርን እየተወንን የኖርን እኛ ነን እና" ልክ ናቹ ግን በእውነተኛው አለም የሉም ውሸት ስለሆኑ....

Читать полностью…

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

✍🏽ሕያው

አየሽ..በትናንት የትዝታችን ጨረፍታ ነው የቆምነው..የኖርናት ጥቂት..አሁናችንን አቅልማልን..እንጂ ወደቀድሟችን ተመልሰናል..የትናንቷ እሳት..ሽርፍራፊ ኮረብታ ነዳጆች ወደተቀላቀለበት አመድነቷ ሳትመለስ አልቀረችም..ዛሬአችን እንደ በፊቱ ተናግታለች..ልዩነቱ..የበፊቱን ያህል መፈራረሷ አይታይም..ተቃቅፎ እንዳለመገናኘት ያለች ናት..እንዴት ያለ ነገር ነው..አቅፌሽ ያላገኘሁሽ..ናፍቄሽ የማትፈልጊኝ..አንላቀቅ ነገር..ሂደቱ ስር መሰረታችንን አንግሶ መጣበቅ ጎብኝቶናል..አንጣበቅ ነገር..ሂደቱ የገባችውን ንፋስ አግዝፎ መራራቅ ፀንቶብናል..
.
.
እንዴት ላርግሽ..

Читать полностью…
Subscribe to a channel