fanualesefr | Unsorted

Telegram-канал fanualesefr - ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

275

ኢትዮጽያ ስጋችን ናት ቤተክርስትያን ደሞ ነፍሳችን!!!! ስለ ቻናላችን ያሎትን አስተያየት @Nati080 ያስተያየት ትንሽ የለውም። ፫

Subscribe to a channel

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ደባትረ ብርሀን ኅበ ተተክሉ ለገነተ ጽባህ በማእከሉ ውድስት አንቲ ወስብሕት በአፈ ኩሉ እምነ ጻድቃን ዘታህቱ ወእምትጉሃን ዘላዕሉ ማርያም ለኪ ስብሐተ አደሉ።

@fanualesefer

@fanualesefer

@fanualesefer

# ፪፩

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

ታማችኋል....በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተዉታላችሁ ። ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ ፤ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ... የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ ፤ የረገጣችሁትን ትይዙታላችሁ ፤ ምኞታችሁ ልክ የለውም ፣ አምሮታችሁ ብዙ ነው ፣ ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል ፣ ተው የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፣ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፣ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ ። ...ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደፊት ቤተመቅደሱን በመስታወት ሰርታችሁ መቅደስ ባትገቡ እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ፣ ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም... ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ ። ኃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም ጥበብን ሀ-ግእዝ ብዬ ላስተምር ብሞክር መንደር ውስጥ በቃረምካት እወቀት ተመክተህ ሆ-ሳብህ ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ...የግል ታሪካችሁ ቢታይ ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተልከፈከፈ የተማሪ ኮፋዳ ውስጥ ያለ እህል ይመስላል...ተምራችሁ እወቀት ስታገኙ ሰርታችሁ ሀብት ስታፈሩ ከላይ የሆናችሁበት ሃገር ለቃችሁ ሰፋ ወዳለው እንድረስ ብላችሁ ከታች ትጀምራላችሁ፤ ትቀጥላላችሁ ፣በመጨረሻም ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ፤ ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ፤ ወዲያው ትፀፀታላችሁ ። በፅኑህ ታማችኋል.. አንዴ ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ። ከዛም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ። እናም ስለታሪካችሁና ስለቅርሳችሁ ባሰባችሁ ቁጥር ፍርሀትና ሀፍረት ይሰማቸዋል። ስለሆነም ከሞላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ "በዚህ አለም ጥድፊያ ታማችኋ።" የምትፈልጉትን አታዉቁም።

እመጓ

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@fanualesefr

@fanualesefr

╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
4 any comment
@jangile
❥❥________⚘_______❥❥

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

ቀጣዩን ለማንብ
@fanualesefr


@jangile

@Nati080

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

አንድ አባት ፆም ሳይገባ የንስሐ ልጆቻቸውን ሰብስበው ስለፆም መክረው እንዳይሳደቡ ከሰው እንዳይጣሉ በንፅሕና ቢፆሙዋጋ እንደሚያገኙ አስተምረው አሰናበቷቸው ታዲያ አንዷሴትዮ ተሳዳቢ ነገረኛ የምንላቸው ሰዎች አይነት ናት የአካባቢውን ሰውለምን አያችሁኝ እያለችእንኳ በስድብ ታስጨንቃቸው ነበር የዛኔ ፆሙየገባና አባ የመከሯት ሰሞን ዝምአለች የመጀመሪያ ቀንቤተክርስቲያን ሂዳ የሷ ቢጤዎች በነገር ለኮፍ ሲያረጓት ብትናደድ ዝምብላቸው መጣች 2ተኛ ቀንምእንዲሁ ዝምብላ ፊቷን ከስክሳ ገባች በ3ተኛው ቀን ግን አልቻለችም ስድቡም ሲናፍቃት ቆይ ብቻ ይህች ፆም ትውጣ ብቻ በየቤትሽ እየመጣው ነው የማጥረገርግሽ አለች ይባላል፡፡
✍እና ቤተሰቦቼ ፆሙን በመጠጥ በጭፈራ አፈታለሁ እያልን የያዝናቸው ቀጠሮዎች ስግደታችንን ፆማችንን በዜሮ እንዳያባዛብን ዋጋ እንዳያሳጣን እንጠንቀቅ!!!! ቢያንስ ለ5
ጓደኞቻችሁ ሼር ሼር
@fanualesefr 👈ይጫኑት
@fanualesefr አጫጭርታሪክ
@fanualesefr ትምህርቶች
👆👆 ይጫኑት👆 ይቀላቀሉን
share &join

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

★መንግስትህ ትምጣ★?!?!
በአንድ ወቅት አንድየተናገሩት ነገር ለኛ ትምህርት ነው በዘወትርት ፀሎታችን የምንፀልየው አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ ብለን #መንግስትህ ትምጣ እንላለን ይህማለት መንግስትህን እንወርስ ዘንድ በስጋዊ ሞት ነፍሳችንን ለያት ውሰዳት መንግስትህን አውርሳት እንደማለት ነው፡፡ ታዲያ አንዲት ሴትዮ የዕለት ከዕለት ፀሎቷ ዕድሜ ስጠኝ፣ዕድሜ ስጠኝ፣ ዕድሜ ስጠኝ ብቻነው በቃ ታዲያ አንድቀን እግዚአብሔር ከመንበሩ በድምፅ ያናግራታል አንቺ ሴት እቤቴ ድረስ መተሽ አንድቀን እንኳን እሰከዛሬ ለኖርሽውም ሆነ ላአኖርኩሽ አመስገነሽኝ አታውቂም ቆይ ይህን ያህል ስንትዓመት መኖር ብትፈልጊ ነው? ብሎ ቢጠይቃት አንድሺህ ልበለው አይ ነገደግሞ አንድ ሺዓመት ሲሞላኝ ይቆጨኛል አንድ ሚሊዮን ልበለው ሲያስቡ ከዛበላይ ቁጥር አያቁም አንድ ሚሊዮኑም ቢሆን ያንሰኛል ብለው አሰቡ መጨረሻ ላይ ቢጨንቃቸው ጌታዬ ምን አለበት አንድ እኔን ብትተወኝ፡፡ አሉ ይባላል
✍እና ምን ልላቹነው መንግስት ትመጣ በብለን ስንፀልይ ንስሐ ገብተን ስጋወደሙን እየተቀበልን መሆን አለበት አለዚያ እንደዛች ሴትዮአንድ እኔንተወኝ እያልን የሞኝ ፀሎት አብረን መፀለይ ይኖርብናል፡፡
★እድሜን ግን ለንስሐ ባርኮ ይስጠን★
አስተያየት ጥያቄ @Nati080 ፃፉልኝ
@fanualesefr አጫጭርታሪክ
@fanualesefr ትምህርቶች
@fanualesefrገድለ ቅዱሳን
👆👆ይንኩት👆👆 ይቀላቀሉን

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

#ከክፋት_ስትርቅ_ሰላም_ትሆናለህ፡፡

ለሰዎች መልካም ስታስብ ውስጥህ የተረጋጋ ይሆናል፡፡በሰዎች ደስታ ስትደሰት ጤናማ አስተሳሰብን እየገነባህ ትመጣለህ፡፡የዛኔ ውስጥህ ከ ጭንቀት እና ከ ፀፀት የፀዳ ይሆናል፡፡


ቻናላችንን ለመቀላቀል @fanualesefr
@jangile


ለማንኛውም አስተያየት @Nati080

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

Masale yemtfelgu @Nati080 yeteleyayu selocen enselalen

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

@fanualesefr

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

ይነበብ ከገድላት አንደበት ገፅ 108 -109-110 ላይ ይገኛል

ከንጉሡ ቶዎድሮስ ጋር እና አሁን ጊዜ ጋር የተያያዘ ነው

ሙሉውን ለማንበብ @fanualesefr


መፅሀፉን ለማግኘት @Nati080

ራፋኤል ዘ ኢትዮጵያ

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

#እጅግ_አሳዛኝ_ዜና!
እባካችሁ በእመብርሃን #ሸርርርርር...አድርጉት...❗

የዲያቆን ቢኒያም ፍሬው ስቃይ በዚህ ይብቃ❗❗❗
የምታቁት ሰዎች ታቁታላችሁ፤ የማታቁት ግን ለዲያቆን ቢኒያም ማለት ስለክርስቶስ አምላክነት ነጥብ በነጥብ እያብራራ አህዛብን መልስ የሚያሳጣ የዘመኑ እንቁ ሀዋርያ ነው።

በዚህ ትልቅ እውቀቱም ብዙ ጊዜ ስለክርስቶስ አምላክነት ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ሙስሊሞች በተለያዩ ሲዲዎች ሲጠይቁትና ትችት ሲያቀርቡበት እሱ ግን ስለክርስቶስ አምላክነት ነጥብ በነጥብ፤ ግልጽ በግልፅ እያብራራ መልስ ከማሳጣቱም በላይ የቁራንን ምንነትና የመሀመድን አስተምህሮ በማያሻማ ማስረጃ እየተነተነ ያቀርብላቸው ነበር።
በዚህ ተግባሩ ግራ የተጋቡትና አንገታቸውን የደፉት ሙስሊሞችና ኡስታዞቻቸው (በተለይ #ሳዲቅ የተባለው ኡስታዝ) በመኪና አደጋና በተለያዩ የጥቃት መንገዶች የመግደል ሙከራ ቢያደርጉበትም፤ በእግዚአብሔር ድንቅ ጥበቃ ጥቃቱ አልተሳካላቸውም።

አሁን ግን በሙስሊሞች የግድያ ርብርብ ምክንያት ዲያቆን ቢኒያም ቤቱን ለቆ ከአገልግሎት ርቆ በጫካ ከቤተሰቦቹ ጋር እየተንገላታ እንዳለና ቤተሰቦቹም አብረውት በስቃይ ውስጥ እንደሆኑ ተናግሯል።

የሚያሳዝነው ነገር ይህንን ጉዳይ እንኳንስ ሲኖዶሱ መንግስትም እንደሚያውቀው በማስረዳት፤ በምዕመናን ደረጃ ግን ከጥቂቶች በስተቀር አብዛኛዎቹ ምዕመናን ያለበትን ሁኔታ እንደማያውቁት ያስረዳል።

†††ይህንን ጉዳይ እያወቃችሁ ቃል ያልተነፈሳችሁ አገልጋዮችና አባቶች ግን እግዚአብሔር ቢያውቀውም አዝነንባችኋል፤ እሱም ይፈርዳል❗😭

ይህንን መረጃ የምታነቡ ወገኖች፤ በእግዚአብሔር ስም ለመምህራችን #ሼር በማድረግ ድምፅ እንሁንለት፡ ያለበትን ሁኔታ የህግ አካላት እንዲያውቁትና የሀይማኖት አባቶችም እንዲነቁ እናድርግ ! አለበለዛ መናገር እየቻልን ዝም በማለታችን በክርስቶስ ክርስቲያን የሆነ ወንድማችን ድምጽ ካልሆንለት በሰማይ ቤት ይፋረደናል...በየጉሩፖች በእየአካውንቶች #ሼር_ሼር አድርጉት በአዛኝቷ😭

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

*ድንቅ ተአምር*
# ሼር
ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን 2013 ዓም በቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል አዲስ አበባ ታቦቱ ቆሞ የተሰጠ ምስክርነት!
መስካሪዋ እናት ናቸው። የሁለት ልጆች እናት። ሁለተኛው ልጃቸው የአራት አመት ልጅ ሆኖ በድንገት ራሴን ወጋኝ አይኔንም አቃጠለኝ ብሎ አለቀሰ።
ልጁ ህመሙ ጸናበት በአራተኛው ቀን ሁለት አይኖቹ ታወሩ። ሁለት ጆሮቹም ደንቆሩ። ከዚህ ይሰውረን! ጤነኛ ልጅ ወልዶ በአንድ ጊዜ እንዲህ አይነት ችግር ውስጥ መውደቅ ያሳዝናል።
አሜሪካን አገር የሚኖረው የዳንኤል አባት ፍጹም ሀዘን እና ጭንቀት ውስጥ ወደቀ። እናት ሥራቸውን ለቀቁ በርካታ ገንዘብ እየተከፈለ የዳንኤል ህክምናው በየአቅጣጫው ቀጠለ። አልተ ሳካም።
ወላጅ እናት ሕጻን ዳንኤልን ይዘው በየጠበሉ ጉዞ ሆነ። አራት አመት ሙሉ በጸሎት ታገሉ በጠበል ታገሉ በእምነት ታገሉ። ለአራት አመታት ሙሉ ልጅ ዳንኤል አይኑ እንደታወረ ጆሮውም መስማት እንደተሳነው ኑሮ ቀጠለ። የአባት እና እናት ጸሎትና ተማጽኖ ቀጠለ።
ትናንትና ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓም እናት ልጅ ዳንኤልን በመኪናቸው ይዘው አራት ኪሎ ቅድሥት ሥላ ሴ ካቴድራል መጡ።
ቅዳሴ የተቀደሰበትን እምነት ግቢው ውስጥ ባለው የቅድስት ሥላሴ ጠበል በጥብጠው ልጃቸው ዳንኤልን በሥመ ሥላሴ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ብለው የታወሩ አይኖቹን በእምነቱ ለቀለቋቸው። ሁለት ጆሮቹን እምነቱን ለቀለቋቸው።
እንዲህ ብለውም ተማጸኑ፦ አጋዕዝተ አለም ሥላሴ እርዱኝ ልጄ ቢያንስ ድምጼን ስምቶ እንድንግባባ ባይሆን ጆሮውን እንኳን ክፈቱልኝ ብለው ተማጸኑ። ከዚያም ልጃቸውን ይዘው መኪናቸውን እየነዱ ወደቤታቸው ሄዱ።
ትናንትና ሌሊቱን ሐምሌ 6 ቀን 2013 ከሌሉቱ 7:00 ሰዓት ላይ ህጻን ዳንኤል በአልጋው ሆኖ እናቱን ተጣራ። ምነው ልጄ ደሞ አዕምሮውን ታመመብ ኝ ይሆን በሌሊት የሚጠራኝ ብለው ወደ ህጻኑ ሄዱ።
እማዬ አይታይሽም? አይታይሽም? አይታይሽም? ብሎ ጮኽ ህጻን ዳንኤል። የሚሰማኝ ይመስል ምንድነው ሥለው: ልጄ ዳንኤል ድምጼን ሰማኝ! እማ እማ አለ.....ጆሮው ተከፍቶ ድምጼን ሰምቶ! እይው እይው... ያንን መስቀል አለኝ።
ለእኔ የሚታየኝ ነገር አልነበረም ፈዝዤ ቀረሁ። እይው የሚያበራ መስቀል እና መስቀሉ ላይ ያሉትን ሦስት ትልልቅ ሰዎች እያቸው እያቸው እያቸው አለኝ። እነዚህ ሦስት ሰዎች መስቀሉ ላይ ሆነው አይኔን አበሩልኝ ጆሮዬንም አዳኑኝ ብሎ ተናገረ።
እናት እ እ እ... ልጄ..ድምጼን እየሰማህ ነው? እእእ እኔ እኔ እታይሃለሁ አዎ አዎ እማዬ። እናት እንዲህ አሉ...ልብስ ደረብኩ እና ምን አይነት ልብስ ነው የለበስኩት? አልኩት ልጄን እናቴ ነጭ እኮ ነው ብሎ በትክክል ነገረኝ።
እናትና ልጅ ተቃቅፈው በለቅሶ ተዋጡ። ከአራት አመታት በኋላ ልጅ የእናቱን ድምጽ ሰማ! የእናቱን ፊት አየ.....
ወዲያው እናት እና ልጅ ልብሳቸውን ለብሰው ሌሊቱን እናት መኪናቸውን እየነዱ ወደ ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል መጡ። ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሲገቡ ልጅ የቅድሥት ሥላሴን ሥዕል አየ። እማዬ እነዚህ ናቸው እኮ ማታ መስቀሉ ላይ ያየዋቸው! እነዚህ ናቸው እኮ ያዳኑኝ ብሎ በገሀድ ተናገረ። እልልታ እና ለቅሶ ቀጠለ....
ምሥክርነቱ ተሰጠ። አሁን ደግሞ ከ40 ደቂቃ በፊት ታቦቱ ዞሮ እንደቆመ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደቆሙ እኛ ሁላችን እንደቆምን ምስክርነቱ በገሃድ ለህዝበ ክርስቲያን ታወጀ።
አይኖቻቸው በእንባ የረጠቡ አዕላፍ ምዕመናን በማያቋርጥ እልልታ ግቢውን አናጉት። እልልልልልልልልልልልል እልልልልልልልልልልልልልእ
ልልልልልልልልልልል........የደስታ እንባ ከሁላችንም አይኖች ፈሰሰ....ምን ልበላችሁ!?! እባካችሁ ወገኖቼ በእምነታችሁ ጽኑ!
ምሥጋና ለአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሥላሴ!
ይህንን ተአምር ታቦቱ ፊት ቆሜ እንደሰማሁ ወዲያውኑ ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን 2013 ከጠዋቱ 5:05 ሰዓት ላይ ጻፍኩት።
የሥላሴ ቤተሰቦች ደስ ይላችሁ ዘንድም ለሁላችሁም ላኩላችሁ። ሥላሴን አመስግኑ!
|+ ዘአክሎግ+

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

ዘ ኢትዮጵያ lewde tektatayicu ymilekacewni ፁፎች bemanbebe ewketacenine enasfa
ተዋህዶ ፫ yawe esume lay leyu leyu ewkte ascebace negroce alubet tetekemubete
@fanualesefr ፫ @jangile
ሰላም ለኢትዮጵያ💚💛❤️
ዘ ፋኑኤል

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

በክርስቶስ አምናለሁ የሚል ብሄርተኛ ቢያጋጥመኝ የክርስቶስ ሰው እንዳልሆነ አውቃለሁ።

ረቂቅ ምርመራም አያስፈልግም እሱን ለማወቅ ቀኖና ትውፊት መመርመር ግድ አይደለም።

ሺህ ግዜ እንጥልህ በመዝሙርና በቅዳሴ ቢነድ ብሄርተኛ(ጎሰኛ) ነህ?በቃ

ክርስቲያን አይደለህም።


[ አዳም ረታ ]



ቻናላችንን ለመቀላቀል @fanualesefr
@jangile


ለማንኛውም አስተያየት @Nati080

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

"​​ልጄ ሆይ ወዳጅ ማለት ሰው አይምሰልህ። ነገር ግን ወዳጅ ማለት ጊዜ ነውና በጊዜህ ሁሉ ይወድሃል አለ ጊዜህ ግን ወዳጅህ እንኳን ይጠላሃል። ጊዜ ማለትም ቀንና ሌሊት አይምሰልህ። ነገር ግን ጊዜ ማለት የእግዚአብሔር አሳብ የሚፈፀምበት ነው ስለዚህ በሆነውም በሚሆነውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁን እያልህ ተቀመጥ።"


[ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ]



ቻናላችንን ለመቀላቀል @fanualesefr
@jangile


ለማንኛውም አስተያየት
@fanualesefr

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

ሱፊዎች እንዲህ ሲሉ ይመክራሉ፦

"ከዓለም ሀብት ጋር እራሱን ያጣመረ ዕውቀቱን ያጠፋል፤ ከብዙ ሰዎች ጋር የተዋዳጀ እርሱ ብቸኛ ነው፤ በሥራ ብቻ የተጠመደ ሰው እርሱ ሌላ ነገር ለማሰብ ጊዜ አይኖረውም፤ ከፈጣሪው ጋር የተወዳጀ ግን እርሱ ታላቅ ህብረትን የፈጠረ ነው።"



ቻናላችንን ለመቀላቀል @fanualesefr


@fanualesefr






ለማንኛውም አስተያየት
@Nati080

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ደባትረ ብርሀን ኅበ ተተክሉ ለገነተ ጽባህ በማእከሉ ውድስት አንቲ ወስብሕት በአፈ ኩሉ እምነ ጻድቃን ዘታህቱ ወእምትጉሃን ዘላዕሉ ማርያም ለኪ ስብሐተ አደሉ።

@fanualesefer
@Nati080

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

አውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ አውደ ዓመት
ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል

ማርያም ሆይ ለምሕረትና ለይቅርታ
አውደዓመቱን ለመባረክ ነይ

🎤 ዘማሪ ዲ/ን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

#ኢትዮጵያን_አናውቃትም!

[ ደራሲ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ ]

ኢትዮጵያን አናውቃትም። አውቃታለሁ የሚል ደፋር ነው። ከምናስባት ሁሉ በላይ የማትገመት ሀገር ናት።

እኛኮ ያልሞከርነው ክፋት የለም። እንደ ሂትለር ዘር ተኮር ስብከትን አስፋፍተናል። እንደ አይሁድ ሰውን እርቃኑን ሰቅለናል፤ በድንጋይ ወግረን ገድለናል። እንደ ስታሊን ቁልቁል ሰቅለን ገርፈናል፤ አሰቃይተናል።

እኛ ኢትዮጵያውያን ሩዋንዳን ከበተነው የዘር ተኮር ጥላቻ ስብከት በላይ ተሰብከናል፤ ሶማሊያን መንግሥት አልባ ካደረገው በላይ ችግር ተፈጽሞብናል፤ ሶሪያን ካፈራረሰው በላይ ሴራና ግጭት ተከናውኖብናል። ተከፋፍለንና ተበታትነን እንድንጠፋ እስከመገንጠል መብት ተሰጥቶናል። ይህ ሁሉ ተሞክሮም ግን አለን። ይህችን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ልዩ ምሥጢር ካልሆነ በቀር ማነው የሚያኖራት?

ሳስበው ክፋትን ሁሉ ሞክረን ስለጨረስን አሁን መልካም ነገር የሚሞከርበት ጊዜ ላይ ነው። ካሁን በኋላ በዚህች ሀገር ላይ ያልተሞከረ አዲስ ክፋት ፈልጎ ሊያገኝ የሚችል ስለማይኖር ሁሉም በጎ በጎውን ማሰብና መሥራት መጀመሩ አይቀርም። ለኢትዮጵያ የተሻለ ጊዜ እየመጣ ነው።

"ኢትዮጵያን አውቃታለሁ" የሚል ሰው ድፍረቱ ይገርመኛል። እኔ እንደማላውቃት ነው ማውቀው። ኢትዮጵያን አናውቃትም። ፈጽሞ አላስተዋልናትም።
ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት ሀገር ስለሆነች ከሌላ ሀገር በተቀዳ ሐሳብ ልትመራ አትችልም። ማንም ሀገር የሌለው የራሷ የሆነ ጥበብና እውቀት አላት። በድህነት መነፅር ስለምናያት ነው እንጅ... ልዩና ማንም የሚመኛት ሀገር ናት።

አንዳንዱ "የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀኛል፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የምታገለው፣ ሕዝቡ ከእኔ ጋር ነው..." ሲል ይሰማል። ምን ማለቱ ነው? የትኛው ሕዝብ? ፌስቡክ ላይ ያለው? ሚዲያ ያለውና ? ፖለቲከኛው? ሃይማኖተኛው? ወይስ የቱ? መለየት አለበት። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀውም የሚሰማውም ሰው ያለ አይመስለኝም።


ቻናላችንን ለመቀላቀል @fanualesefr
@fanualesefr


ለማንኛውም አስተያየት @Nati080

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

በአንድ ወቅት መፀሐፍ አንብቦ የማያወቅ ሰውዬ ከጎደኞቹ ጋር ተቀምጦ ሳለ ስላነበቧቸው መፃሐፍት እየተነጋገሩ እሱ ብቻዝም ማለቱ በጣም ተሰማው በተለይደግሞ የመፀሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እያነሱ የተጫወቷቸው ጨዋታቸው ባይገባውም ውስጡን ግን ደስደስ አሰኝቶታል ከዛ አንዱን ጓደኛውን መፀሐፍ ቅዱስ ማንበብ እፈልጋለሁ ይለው ና ይቀበለዋል ከዛም ቤቱገብቶ ይቀመጥና መፀሐፍ አንብቦ ስለማያውቅ ዝምብሎ ከመሀል ገፅ ይገልጥና ሲመለከት ይሁዳም ራሱን አጠፋ.....ይላል ደንግጦ ዘጋው ምን አይነት ነገርነው ብሎ ኸረጉዱን ልየው ብሎመልሶ ከመሀል ቢገለጠው ....እናንተም እንዲሁ አድርጉ....የሚልሀረግ ያገኛል ከመጀመሪያው ይበልጥ ደነገጠ ከመቀመጫው ብድግ ቁጭ አለ ይሄንንነው መፅሐፍ ቅዱስ የሚሉት ድንቄመ ቅዱስ እያለ ሊመልስለት ሄደ፡፡
✍የዚ ዘመንም ዋናው ችግር ብሉይን ሳያነቡ ሀዲስ መፃፈነብያትን ሳያነቡ ወንጌልን ወንጌልን ሳያነቡ መልዕክታቱን እያነበቡ ያንዱን ንባብ ከሌላኛው ጋር እየጨረሱ ይመስለኛል የመነፈቁት ሰዉንም ያመነፈቁት፡፡ ለጓደኞቻችሁ ሼር Share join
@fanualesefr አጫጭርታሪክ
@jangile ገድለ ቅዱሳን
@fanualesefr ኦርቶዶክሳዊ
@fanualesefr ትምህርቶች
👆👆ይንኩት👆👆 ይቀላቀሉን


አስተያየት @Nati080 ፃፉልኝ

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

ሁለት አይነት ሰዎች አሉ።

አንዱ መልካም ነው ብሎ በመልካምነትህ ብቻ ይወድሀል።

አንዱ መልካም እና የዋህ ነህ ብሎ ይነግድብሀል ይጠቀምብሀል።

አንተ ለሰዎች ከየቱ ነህ?? ሰዎችስ ለአንተ ከየቱ ናቸው??


ቻናላችንን ለመቀላቀል @fanualesefr
@jangile


ለማንኛውም አስተያየት @Nati080

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

💚💛❤️ ሰላም ለኢትዮጵያ

@fanualesefr

@jangile
መልካም ፆም ይሁንል የበረከት ፆም ያርግልን ። የአባቶች የነገሩንን በማሰብ እንፁም !!!!!!!

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

👉👉👉ይህንን አስታውሱ👈👈👈

🤔ሀጢዓት ስትሰሩ.....የምትሞቱበትን ቀን
🤔ስትሾሙ........የምትሻሩበትን
🤔በጠገባችሁ ጊዜ.....የተራባችሁበትን
🤔ጤነኛ ስትሆኑ......የታመማችሁበትን ዘመን
🤔ፈጣሪ ከፍ ሲያረጋቹ....አፈር መሆናችሁን
🤔ባለፀጋ ስትሆኑ.....የችግራችሁን ጊዜ
🤔በደስታችሁ ዕለት....ያዘናችሁበትን
ወራት አስታውሱና አሁን በዛ ውስጥ ያሉትን ለመርዳት ሞክሩ!

✍✍እንኳን ተዋህዶ ሆንኩ✍✍

እንኳን ተዋህዶ ሆንኩ እንኳንም ተጠመኩ
ሁሌም አመስጋኝ ነኝ ኦርቶዶክስ ስለሆንኩ

ገና በልጅነት በኮልታፋ አንደበት
እርሱን ላገለግል መቅደሱ ባለበት
ተመርጬ መጣሁ ከብዙ ሕጻናት
በቅድስና አድባር በጺዮን ተራራ
እርሱን እንዳመልከው ከቅዱሳን ጋራ
መርጦ ስልጣን ሰጠኝ በስሙ እንድጠራ
አዎን
አዎን ልጅ ነኝ አሁን እንቁ አባት ያለኝ
አባዬ የምለው እርሱም ልጄ ሚለኝ
ሳዝን በእቅፉ አርጎ ሁሌም የሚያጽናናኝ
ከጭንቀት መከራ ዘወትር ሚጠብቀኝ
ስራብ የሚያበላኝ ስጠማ ሚያጠጣኝ
ለኔ ሲል በመስቀል ደም ያፈሰሰልኝ

አሁን እናት አለኝ ጋሻና መከታ
በምልጃዋ ፍቅር ማትለየኝ ላፍታ
ፈጣሪ ልጅ ያላት የምታማልደኝ

አሁን ብዙ መላዕክት አሉ በዙሪያዬ
መጋቢ ጠባቂ መከታ አሌንታዬ
ከሁሉም የተሻልኩ እኔ እድለኛ ነኝ
እንኳን ተዋህዶ ሆንክ እንኳን ተመረጥኩኝ

ማነው እንደኔ እድለኛ?
ይህን ያህል ሚቀርበን አባት ሮሜ 8፡15
ይህን ያህል የተሰጠችን እናት ዮሐ 19፡26
ይህን ያህል ሚጠብቁን መላዕክት መዝ 91፡10-12
ስላለን እግዚአብሔር ይመስገn

መንፈሳዊ ጥበብ
@fanualesefr
@jangile

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

@fanualesefr

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

በዚህ ዓለም ላይ እንደኔ ያለ ሀጥያተኛ የለም ሀጢያቴም በዝቶ አትማረኝ ብለው እሱም አለ የማልችለው እሱን ነው አለኝ



ራፋኤል ዘ ኢትዮጵያ


@fanualesefr

@jangile #፫
Join&share ተዋህዶ ሀይማኖቴ

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

#እጅግ_አሳዛኝ_ዜና!
እባካችሁ በእመብርሃን #ሸርርርርር...አድርጉት...❗

የዲያቆን ቢኒያም ፍሬው ስቃይ በዚህ ይብቃ❗❗❗
የምታቁት ሰዎች ታቁታላችሁ፤ የማታቁት ግን ለዲያቆን ቢኒያም ማለት ስለክርስቶስ አምላክነት ነጥብ በነጥብ እያብራራ አህዛብን መልስ የሚያሳጣ የዘመኑ እንቁ ሀዋርያ ነው።

በዚህ ትልቅ እውቀቱም ብዙ ጊዜ ስለክርስቶስ አምላክነት ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ሙስሊሞች በተለያዩ ሲዲዎች ሲጠይቁትና ትችት ሲያቀርቡበት እሱ ግን ስለክርስቶስ አምላክነት ነጥብ በነጥብ፤ ግልጽ በግልፅ እያብራራ መልስ ከማሳጣቱም በላይ የቁራንን ምንነትና የመሀመድን አስተምህሮ በማያሻማ ማስረጃ እየተነተነ ያቀርብላቸው ነበር።
በዚህ ተግባሩ ግራ የተጋቡትና አንገታቸውን የደፉት ሙስሊሞችና ኡስታዞቻቸው (በተለይ #ሳዲቅ የተባለው ኡስታዝ) በመኪና አደጋና በተለያዩ የጥቃት መንገዶች የመግደል ሙከራ ቢያደርጉበትም፤ በእግዚአብሔር ድንቅ ጥበቃ ጥቃቱ አልተሳካላቸውም።

አሁን ግን በሙስሊሞች የግድያ ርብርብ ምክንያት ዲያቆን ቢኒያም ቤቱን ለቆ ከአገልግሎት ርቆ በጫካ ከቤተሰቦቹ ጋር እየተንገላታ እንዳለና ቤተሰቦቹም አብረውት በስቃይ ውስጥ እንደሆኑ ተናግሯል።

የሚያሳዝነው ነገር ይህንን ጉዳይ እንኳንስ ሲኖዶሱ መንግስትም እንደሚያውቀው በማስረዳት፤ በምዕመናን ደረጃ ግን ከጥቂቶች በስተቀር አብዛኛዎቹ ምዕመናን ያለበትን ሁኔታ እንደማያውቁት ያስረዳል።

†††ይህንን ጉዳይ እያወቃችሁ ቃል ያልተነፈሳችሁ አገልጋዮችና አባቶች ግን እግዚአብሔር ቢያውቀውም አዝነንባችኋል፤ እሱም ይፈርዳል❗😭

ይህንን መረጃ የምታነቡ ወገኖች፤ በእግዚአብሔር ስም ለመምህራችን #ሼር በማድረግ ድምፅ እንሁንለት፡ ያለበትን ሁኔታ የህግ አካላት እንዲያውቁትና የሀይማኖት አባቶችም እንዲነቁ እናድርግ ! አለበለዛ መናገር እየቻልን ዝም በማለታችን በክርስቶስ ክርስቲያን የሆነ ወንድማችን ድምጽ ካልሆንለት በሰማይ ቤት ይፋረደናል...በየጉሩፖች በእየአካውንቶች #ሼር_ሼር አድርጉት በአዛኝቷ😭

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

✥ የተቆለፈ ሳጥን

#ልዩ_ልዩ

አንድ በተቆለፈ ሳጥን ላይ ተቀምጦ የሚለምን ለማኝ ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀንም በዚያ መንገድ የሚያልፍ ሰው ወደሱ ጠጋ ብሎ ለመሆኑ የተቀመጥክበትን ሳጥን ከፍተህ ውስጡን አይተህ ታውቃለህን ? ብሎ ጠየቀው። ለማኙም አረ አላቅም አለና ከፍቶ ቢያየው ሳጥኑ በወርቅ በብር የተሞላ ነበር። እኛም እንደዛ ነን እኔ ዋጋ የለኝም አልረባም ብኖር ባልኖር። አልጠቅምም እንላለን። ግን አንድም ቀን ውስጣችንን አይተን አናውቅም። ውስጣችን ግን ወርቅ በመሰሉ አላማዎች እንቁ በመሰሉ በጎ ሀሳቦች የተሞላ ነው። ማይልስ እንዳለው የአለም ውድ ሀብት ያለው በአረብ ሀገራት የነዳጅ ቦታ ውስጥ አይደለም የአለም ውድ ሀብት ያለው በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ቦታዎች ውስጥም አይደለም ።የአለም ውድ ሀብት ያለው የመቃብር ቦታዎች ውስጥ ነው።

ምክኒያቱም ብዙዎች ወደዚህ አለም ይዘው የመጡትን አላማና ራዕይ አውጥተው ሳይኖሩትና ለአለም ሳያበረክቱት ስለሚሞቱ ነው። ማግኘት ማጣት የጊዜ ጉዳይ ነው። ማንም ባዶ የለም ምንአልባት አሁን ባዶ እጃችንን እንሆን ይሆናል ነገር ግን ባዶ ልባችንን አልተፈጠርንም። ለዝች አለም የምናበረክተው አንዳች ነገር በውስጣችን አለ። እኛ ምን አልባት ለቤተሰቦቻችን በስህተት የተወለድን ይመስላቸው ይሆናል። ነገር ግን በስላሴ ዘንድ መለኮታዊ አጀንዳ ተይዞልን ለአለማ ተወልደናል። አለም ላይ ላሉ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ የያዝን አለን: ለተዘበራረቀው ፖለቲካችን የተስተካከለ የአመራር ብቃት ያለን አለን ፡ እየጠፉ ላለው ስነፅሁፋችን የተባ ትንቱግ ብዕር የጨበጥን አለን ፡ ብቻ ሁላችንም ውስጥ ውድ ሀብት አለ። እኛ ግን ቆልፈንበት ተቀምጠናል እናውጣው እንጠቀምበት

#መልካም_ቅዳሜ
________________________

#ሼር
#share
@fanualesefr

@jangile

ራፋኤል

ዘ-ኢትዮጵያ 💚💛❤️

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

አንዳንዴ ምንም ያህል ጥሩ ሰው ቢሆንም እንኳን ትንሽ ጥሩ ያልሆነ ጎን ሊኖረው ይችላልና ችሎ ማሳለፍ ነው አለበለዚያ ግን ለትንሹ ጥሩ ላልሆነው ነገር ብለን ትልቁን መልካም ነገር እናጣለንና።

ምክንያቱም እጅግ የሚያምረው የፅጌሬዳ አበባ እንኳን ያለ እሾህ አልተፈጠረምና።



ቻናላችንን ለመቀላቀል @fanualesefr
@jangile


ለማንኛውም አስተያየት @Nati080

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

#የዕለቱ_በረከት

በዛሬዋ ዕለት ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ መከራን ተቀብለው በሰማዕትነት ያረፉባት ዕለት ናት::

ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ፈጣሪ አምላክ ያድለን::

#አሜን
_______________________

#ሼር
#share
@fanualesefr

@jangile 💚💛❤️

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

የትኛውን ነሽ??

በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና አንዱን ችግር ስትፈታ ሌላ ችግር እንደሚገጥማት፤ መኖር እንደከበዳታ እና ከዚህ በላይ ችግሮቿን መቋቋም እንደማትችል አቤቱታዋን ለአባቷ አቀረበች፡፡
_
አባቷ የምግብ ሰራተኛ ነው፤ እናም ወደ ማብሰያ ክፍል ይዟት ሄደ፡፡ ሶስት ድስቶችን ውሃ ሞልቶ እሳት ላይ ጣዳቸው፡፡
____
በድስቶቹ ውስጥ ያለው ውሃ መፍላት ሲጀምር በአንዱ ድስት ውስጥ ድንች፤ በሌላኛው ውስጥ እንቁላል፤ በሶስተኛው ውስጥ ደሞ ቡና ጨመረባቸው እና ከደነው፡፡ እናም ምንም ሳይናገር መጠበቅ ጀመረ፡፡ ልጁ መነጫነጭና ትዕግስት በጎደለው መልኩ ምን ሊያረግ እንደሆነ ለማየት መጠበቅ ጀመረች፡፡
____
ከ20 ደቂቃ በኀላ እሳቱን አጥፍቶ ድንቹን፣ እንቁላሉን አውጥቶ በአንድ ሰሃን አስቀመጠ፡፡ ቡናውን በሲኒ ቀድቶ አስቀመጠ፡፡
____
"ልጄ አሁን ምን ይታይሻል? በማለት ጠየቃት፡፡ ልጅ "በቁጣ ስሜት ሁና ድንች፣ እንቁላል፣ ቡና" አለች፡፡
____
"በደንብ ተመልከች፤ ድንቹን ንኪው" አላት፡፡ እንዳላት አድርጋ ድንቹ ጥንካሬውን እንዳጣ ተገነዘበች፡፡
____
"እንቁላሉንም ስበሪው" አላት፡፡ ሰበረችው ነገር ግን አስኳሉ ሌላ ጠንካራ እና የሚያቃጥል አካል ሰርቷል፡፡
____
በስተመጨረሻ ከቡናው ፉት እንድትል አዘዛት፡፡ እሷም ቀምሳ ደስ የሚለው ጣዕሙ የፊቷን ፈገግታ ሲቀይረው ታወቃት፡፡
____
👉"አባቴ ይህ ምንድን ነው?" አለች፡፡

አባት ማብራራት ጀመረ፡፡ "ድንቹ፣ እንቁላሉ እንዱሁም የቡናው ዱቄት ሁሉም እኩል የፈላ ውሃ ውስጥ ነው የገቡት፡፡ ነገር ግን ሁሉም ለፈላው ውሃ የሰጡት ምላሽ የተለያየ ነበር፡፡

👉 ድንቹ በፊት ጠንካራ ነበር፤ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ጥንካሬውን አጥቶ ልፍስፍስ ሆነ፡፡

👉እንቁላሉ በፊት በቀላሉ ከተሰበረ ሜዳ ላይ የሚፈስ ልፍስፍስ አስኳል ነበር፡፡ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ውስጡን አጠንክሮ መጣ፡፡

👉ከሁሉም የሚገርመው ግን የቡና ዱቄቱ ነው፡፡ በፈላ ውሃ ሲፈተን እራሱ ውሃውን ወደ ጣፋጭን መልካም ጠረን ቀይሮ አዲስ ነገር ፈጠረ፡፡
__

✍አንቺ የትኛው ነሽ?" ችግር ሲገጥማችሁ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው? እንደ ድንቹ መልፈስፈስ? ወይስ እንደ እንቁላሉ ውስጥን ማጠንከር? አልያም ችግሩን ለአዲስ ነገር መፍጠሪያ መጠቀም?"
____
✍በህይወት ውስጥ ነገሮች በአካባቢያችን ይከናወናሉ፤ ነገሮች በእኛ ላይ ይደርሳሉ፤ ነገር ግን ትልቁና ወሳኙ በእኛ ውስጥ የሚከናወነው ነገር ነው!"

የትኛው ነህ? ነሽ??

አስተማሪ ታሪክ ነውና ለወዳጅዎ ያጋሩ

Join👇
@fanualesefr
@fanualesefr

Читать полностью…

ተዋህዶ ሀይማኖቴ ፫

"#ደኅና_ነው" መጽሐፈ ነገስት ካልዕ 4:23

ሱነም ተብላ በምትጠራ መንደር ትኖር የነበረች "ሱነማዊት" ለእግዚአብሔር ሰው ነብዩ ኤልሳዕ መልካም በማድረግ ከባሏ ጋር ትተባበር ነበር። ይህች ደግ ሴት ልጅ አልነበራትም። ነገር ግን ከወገኖቿ መሐል ስለምትኖር ታመሰግናለች እንጂ አታማርርም።

እግዚአብሔር በነብዩ ኤልሳዕ አማካኝነት የመካንነት ጥማቷን በልጅ አረካና ጎዶሎዋን ሞላላት። ልጇን በደስታ እያሳደገች ባለበት ሁኔታ ከቀናት በአንዱ ቀን በራስ ህመም ታሞ በክንዷ ላይ ሞተ። መሞቱን ከእርሷ ውጪ ያየ ስላልነበረ በፃዲቁ ሰው አልጋ ላይ አስተኝታው በር ቆልፋበት የእግዚአብሔርን ሰው ልትዋቀሰው እግሮቿን አፀናች።

ይህች ሴት ነብዩ ኤልሳዕን እስክታገኘው ድረስ በመንገድ ስለ ልጇ ደኅንነት ለሚጠይቋት ሁሉ "ደኅና ነው" እያለች ትሄድ ነበር። ነብዩ ኤልሳዕን ስታገኘው ግን የሆነውን ብትነግረው የሚሆነውን አደረገላት። የሞተው ልጇ ተነስቶ እንደቃሏ "ደኅና" ሆነላት።

"ለሁሉም ካብራራህ ችግርህን ታገዝፈዋለህ"

ከልጅ ሞት በላይ የጠነከረ ደንዳና ሀዘን ምን አለ? እንዲህ በገዘፈ ሀዘን ውስጥ ሆኖ የሞተን ሰው "ደኅና ነው" ማለት ጠላትን ማስደገጥ ያክል ነው። ጠላት ማሸነፉን ከሚያረጋግጥባቸው ነገሮች አንዱ ደኅና አይደለሁም የሚል ቃል ከአፋችን ማዳመጡ ነው። ቅዱሳንን ሁሉ "እግዚአብሔር በደኅና አኑሮአቸዋል፥ "መጽሐፈ ኢዮብ 24:23

ነገሮች ባይሳኩልኝም እኔ ደኅና ነኝ። አለኝ ያልኩት ባይኖረኝም እኔ ደኅና ነኝ። ወዳጅ እንደ ተልባ ስፍር ተንሸራቶ ቢወርድም እኔ ደኅና ነኝ። ሃብት ንብረቴ
በሰው የሚቆጠር ባይሆንም እኔ ደኅና ነኝ። አግኝቼ ባልስቅም እኔ ደኅና ነኝ።
ከሳሾቼ እንደ ፈረስ ኮቴ እርምጃቸው ቢያስፈራም ደኅና ነኝ። በጋጥ ውስጥ ከብቶች ባይኖሩኝም እኔ ደኅና ነኝ።

"አስተውሉኝ የእኔ ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ደኅና ነኝ ማለትን በሕይወት እንደ ሱነማዊቷ ስንለምድ የጠላትን ምሽግ የማፍረስ አቅም ይኖረናል"

እግዚአብሔር ሁሉን ደኅና ያድርግልን።
_____________________________

#ሼር
#share
@fanualesefr
@fanualesefr
@fanualesefr

#፫ 🔯

Читать полностью…
Subscribe to a channel