fasilsc | Unsorted

Telegram-канал fasilsc - ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

21567

የአፄዎቹ ፈጣን የመረጃ ምንጭ 🔴 ለአስተያየት ፣ለጥቆማ ፣ ለማስታወቂያ ➠ @FASILKFCBOT https://t.me/+TY2Jn5HJdPL1cMuk

Subscribe to a channel

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

55'ናቲ አሪፍ ኳስ ሞክሮ ነበር አልተሳካም

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

ሱራ አሪፍ ኳስ አግኝቶ ነበር አልተሳካም

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

እረፍት
ፋሲል 0-0 መድን

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

34' ፋሲል 0- 0መድን
እናሸንፋለን በአፄው ሙሉ እምነት አለን

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

24' ፋሲል 0-0 መድን
ፋሲል ኳስ ተቆጣጥሮ ለመጫወተሰ እየሞከሩ ነው

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

ጨዋታ ተጀምሯል
ፋሲል0-0 መድን

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

ሪፖርት


ወላይታ ድቻ ፋሲል ከነማን አሸንፏል።
ወላይታ ድቻ በቅዱስ ጊዮርጊስ ከተሸነፈበት ጨዋታ አንፃር በግብ ጠባቂነት ቢኒያም ገነቱን በወንድወሰን አሸናፊ ምትክ ሲጠቀም ያሬድ ዳዊት እና ዘላለም አባተም በደጉ ደበበ እና ንጋቱ ገብረስላሴ ተተክተዋል። ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ ለጨዋታው የቀረቡት ፋሲል ከነማዎች ደግሞ በአስቻለው ታመነ ፣ አምሳሉ ጥላሁን እና ታፈሰ ሰለሞን ቦታ መናፍ ዐወል ፣ ወንድምአገኝ ማርቆስ እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስን ወደ ቀዳሚው አሰላለፍ አስገብተዋል።

በኳስ ቁጥጥር ጨዋታውን ለመቆጣጠር ያሰቡት ፋሲል ከነማዎች ገና ጨዋታው እንደተጀመረ በፈጣን ቅብብል የወላይታ ድቻ ግብ ክልል ደርሰው ነበር። በዚህም ፍቃዱ ዓለሙ በተከላካዮች መካከል በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ የደረሰውን ኳስ ለመጠቀም ሲጥር መልካሙ ቦጋለ ከደጉ ደበበ ጋር ታግሎ አምክኖበታል። በተቃራኒው ወደ ራሳቸው ግብ ወረድ ብለው መንቀሳቀስን የመረጡት ወላይታ ድቻዎች ዘለግ ያለውን ደቂቃ በራሳቸው ሜዳ ቢያሳልፉም በቀጥተኛ አጨዋወት እና ፈጣን ሽግግር ፋሲልን ለመፈተን ጥረዋል። በ17ኛው ደቂቃም ሳሙኤል ተስፋዬ በሞከረው የቅጣት ምት ለመጀመሪያ ጊዜ ጠንከር ያለ ሙከራ ያስመዘገቡበትን ሁነት አስመልክተዋል።

በዚህኛው የጨዋታ አጋማሽ እምብዛም የጠሩ የግብ ሙከራዎች ባይስተናገዱም በቀጣዩ ደቂቃ ግብ አስቆጣሪ የሚመስለው ቡድን ፋሲል ከነማ ነበር። ምንም እንኳን ቡድኑ የፈጠራ አቅማቸው የተሻሉ ተጫዋቾችን አብዝቶ ወደ ሜዳ ቢገባም ጠጣሩን የድቻ የኋላ መስመር መስበር አልቻለም። ይህንን ተከትሎም ከሳጥን ውጪ በርካታ ጥቃቶችን ሲሰነዝር ታይቷል። በተለይ ቡድኑን በአምበልነት እየመራ የነበረው ሱራፌል ሁለት ጥሩ ዒላማቸውን የጠበቁ ጥቃቶችን ቢሰነዝርም ግብ ጠባቂው ቢኒያም አድኖበታል። እንደተገለፀው ቀጥተኛ አጨዋወትን ሲተገብሩ የታዩት ድቻዎች ከግማሽ ሰዓት በኋላ የተሻለ ለግብ የቀረቡበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር። በቅድሚያ በ31ኛው ደቂቃ ሀብታሙን ቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ቃልኪዳን ሲሞክር በ44ኛው ደቂቃ ደግሞ ስንታየሁ ከሳጥን ውጪ ጥቃት ሰንዝሮ መክኖበታል።

ፋሲሎች ሁለተኛውን አጋማሽም በፈጣን ጥቃት ነበር የጀመሩት። በ48ኛው ደቂቃም ሽመክት ረጅም ርቀት ኳስ እየገፋ ተጫዋች በመቀነስ ሳጥን ውስጥ በመግባት የሞከረው የጨዋታው ግልፅ የግብ ማግባት አጋጣሚ መጨረሻው መረብ ሳይሆን ቀርቷል። ድቻዎች በአንፃሩ የአጨዋወት ለውጥ ሳያደርጉ በሚደነቅ የመከላከል ዲሲፕሊን መንቀሳቀሳቸውን ቀጥለዋል።

ከመጀመሪያው የሽመክት ሙከራ በኋላ ጨዋታው ቀጣዩን ሙከራ ለማስተናገድ በርከት ያሉ ደቂቃዎች ወስደውበታል። ነገር ግን ቀጣዩ ሙከራ ግብ ሆኖ መሪ ተገኝቷል። በዚህም በ67ኛው ደቂቃ በኃይሉ ተሻገርን ቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ዘላለም አባቴ የሜዳውን ሳር ከረገጠ ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ከግራ መስመር የተሻማን ኳስ በአንድ ንክኪ ከመረብ ጋር አዋህዶት ድቻ ቀዳሚ ሆኗል። ድቻ ይህቺን ግብ ካስቆጠረ በኋላም በሚገርም ተነሳሽነት በእጁ የገባውን ሦስት ነጥብ ላለማጣት ሲጣጣር ተስተውሏል።

ፋሲል ከነማዎች ከጨዋታው አንዳች ነገር ለማግኘት ወዲያው የማጥቃት ባህሪ ያላቸውን ተጫዋቾች በማስገባት በተሻለ ወደፊት ለማምራት ቢጥሩም ውጤታማ መሆን አልቻሉም። ሙሉ የጨዋታ ክፍለ ጊዜው ሊጠናቀቅ አንድ ደቂቃ ሲቀረው ግን ከመዓዘን ምት መነሻን ያደረገ ኳስ ወደ ግብነት ሊቀይሩ ተቃርበው አናጋው ባደግ ውጥናቸውን አምክኗል። ፍልሚያው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አካላዊ ጉሽሚያዎች በዝተውበት የነበረ ሲሆን ቃልኪዳን እና ኪሩቤልም በሁለቱም ቡድኖች በኩል በጭማሪው ደቂቃ መባቻ በቀይ ካርድ ከሜዳ እንዲወጡ ሆኗል። ጨዋታውም በወላይታ ድቻ አንድ ለምንም አሸናፊነት ተጠናቋል።
©soccerethiopia

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

በጨዋታው ላይ ያላችሁን አስተያየት ጨዋነት በተሞላው መልኩ ግሩፓችን ላይ ፃፉልን ✍️

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

85' ወላይታ ድቻ 1-0 ፋሲል ከነማ

71' ዘላለም አባቴ

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

2ኛ አጋማሽ | ወላይታ ድቻ 0-0 ፋሲል ከነማ 64’


🗓️ እሁድ ህዳር 25/2015
🕙 10:00
🏟 ድሬዳዋ አለማቀፍ ስታዲየም

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

1ኛ አጋማሽ | ወላይታ ድቻ 0-0 ፋሲል ከነማ 30’


🗓️ እሁድ ህዳር 25/2015
🕙 10:00
🏟 ድሬዳዋ አለማቀፍ ስታዲየም

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 10ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 9ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች አራት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አራት ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቁ 22 ጎሎች በ20 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ አራት በፍፁም ቅጣት ምት ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 29 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ ሶስት ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል።

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ህዳር 23/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋቾች በሳምንቱ መርሃግብር
ቡታቃ ሸመና(አርባምንጭ ከተማ)፣
ባዬ ገዛኸኝ (ሀዲያ ሆሳዕና) እና
አምሳሉ ጥላሁን(ፋሲል ከነማ) 
ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው ቀይ ካርድ አይተው ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ 1 ጨዋታ እንዲታገዱ ሲወሰን እንዲሁም ባዬ ገዛኸኝ  ከጨዋታ ሜዳ በተወገደበት ወቅት የዕለቱን ዳኛ አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት የቀረበበት በመሆኑ ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት ከተቀጣው ቅጣት በተጨማሪ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3/ሶስት/ ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3000/ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

በክለቦች ፋሲል ከነማ ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ሲወሰን ድሬዳዋ ከተማ ክለቡ ከ ከወልቂጤ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛንና የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበባቸው ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

እሁድ ህዳር 25/2015 ዓ.ም የሚካሄደው የሁለተኛ ሳምንት የወላይታ ድቻ እና የፋሲል ከነማ ተስተካካይ ጨዋታን በተመለከተ ጨዋታው ከ10 ወደ 12፡00 ሰዓት ተለውጧል። በተጨማሪነትም ፋሲል ከነማ በ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን 30ኛ ሳምንት በነበረ ቅጣት የሊጉ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ያለ ደጋፊ እንደሚካሄድ የተላለፈው ውሳኔ በእንግዳ ቡድኑ(በፋሲል ከነማ) በኩል ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልፇል።

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

🏆#የኢትዮጵያ_ፕሪሚየር_ሊግ_የ2ኛ_ሳምንት_ተስተካካይ_ጨዋታ ⚽BetKing Ethiopian Premier League..

. ወላይታ ድቻ 🆚 ፋሲል ከነማ

🗓️ እሁድ ህዳር 25/2015
🕙 10:00
🏟 ድሬዳዋ አለማቀፍ ስታዲየም
🏆 ድል ለአፄዎቹ!!


. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

🇦🇹#ማሳሰቢያ🇦🇹
🇦🇹አፄዎቹ ከ ወላይታ ዲቻ

ለመላው የአሸናፊው ክለባችን ደጋፊዎች በሙሉ በኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ የ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን ፋሲል ከነማ ከድሬ ዳዋ በነበረን የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ አወዳዳሪ አካሉ ባስተላለፈው ውሳኔ ምክንያት የ2015 ዓ.ም የውድድር ዘመን ሁለት ጨዋታዎችን ክለባችን ያለ ደጋፊ እንዲጫወት መቀጣቱ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የፊታችን ህዳር 25/2015 ዓ.ም ከወላይታ ዲቻ ጋር በድሬ ዳዋ ስቴዲየም የምናደርገው ተስተካካይ ጨዋታ ላይ ደጋፊ የማይገባ በመሆኑ ከድሬ ዳዋ ውጭ ያሉ ደጋፊዎች ለዚህ ጨዋታ ሲባል ጉዞ እንዳያደርጉ እንዲሁም ድሬ ዳዋ የምትገኙ ደጋፊዎች የክለቡን ማልያ እና ሌሎች የክለቡን አርማ የያዙ ቁሳቁሶችን ይዞ ማዳ እንዳትገቡ እናሳስባለን።

ማስጠንቀቂያ:- በጥሩ መነሳሳት ላይ ያለውን ክለባችንን ላለማስቀጣት ሲባል ማንኛውም የክለባችን ደጋፊ ወደ ሜዳ እንዳይገባ እናሳስባለን።


🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ🇦🇹
🇦🇹#ሼርShare_በማድረግ_መረጃውን_ለደጋፊዎች_ያጋሩ 🇦🇹

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

ለቻን ውድድር ቅድመ ዝግጅት ለ42 እጩ ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአልጄርያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ለሚያደርገው ተሳትፎ ቅድመ ዝግጅት ለ42 ተጫዋቾች የመጀመርያ ዙር ጥሪ ተደረገ።

የብሔራዊ ቡድናችን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በጥር ወር ለሚካሄደው ውድድር ቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ እና ተጫዋቾች በየክለባቸው በውድድር ላይ እያሉ ተገቢውን ክትትል እና ዝግጅት ለማከናወን እንዲረዳ እጩ የተጨዋቾች ዝርዝር ማቅረብ አስፈላጊ በመሆኑ ለ42 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን የገለፁ ሲሆን በቀጣይ የ28 ተጨዋቾችን ዝርዝር እንደሚያሳውቁ እና እጩ ተጫዋቾችም የዝግጅት ጊዜው እስኪጀምር ድረስ አቋማቸውን በመጠበቅ ውድድራቸውን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር እስከ ታህሳስ 17 እየተካሄደ እንደሚቀጥል የተገለፀ ሲሆን ከታህሳስ 18 ጀምሮ ብሔራዊ ቡድኑ ለቻን ውድድር ቅድመ ዝግጅቱን የሚጀምር ይሆናል።

ጥሪ የተደረገላቸው 42 ተጫዋቾች ዝርዝር ይህንን ይመስላል፦

ግብ ጠባቂዎች...

ፋሲል ገ/ሚካኤል ባህር ዳር ከተማ
በረከት አማረ ኢትዮጵያ ቡና
ዳግም ተፈራ መቻል
ባህሩ ነጋሽ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዳንኤል ተሾመ ድሬዳዋ ከተማ

ተከላካዮች...

አስራት ቱንጆ ኢትዮጵያ ቡና
ሱሌማን ሀሚድ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ረመዳን የሱፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሄኖክ አዱኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዓለምብርሃን ይግዛው ፋሲል ከነማ
ጊት ጋትኩት ሲዳማ ቡና
አስቻለው ታመነ ፋሲል ከነማ
ምኞት ደበበ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ብርሃኑ በቀለ ሃዲያ ሆሳዕና
ያሬድ ባየ ባህር ዳር ከተማ
ፍሬዘር ካሣ ሃዲያ ሆሳዕና
ፈቱዲን ጀማል ባህር ዳር ከተማ
ገዛኸኝ ደሳለኝ ኢትዮጵያ ቡና

አማካዮች...

አማኑኤል ዮሐንስ ኢትዮጵያ ቡና
ጋቶች ፓኖም ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይሁን እንዳሻው ፋሲል ከነማ
ከነዓን መርክነህ መቻል
መስኡድ መሐመድ አዳማ ከተማ
በዛብህ መለዮ ፋሲል ከነማ
ናትናኤል ሰለሞን ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ቢኒያም በላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፍሬው ሰለሞን ሲዳማ ቡና
ታፈሰ ሰለሞን ፋሲል ከነማ
ፉአድ ፈረጃ ባህር ዳር ከተማ

አጥቂዎች...

በረከት ደስታ መቻል
ቸርነት ጉግሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይገዙ ቦጋለ ሲዳማ ቡና
አማኑኤል ገ/ሚካኤል ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዳዋ ሆቴሳ አዳማ ከተማ
ብሩክ በየነ ኢትዮጵያ ቡና
ኪቲካ ጀማ ኢት. መድን ድርጅት
ዱሬሳ ሹቢሳ ባህር ዳር ከተማ
ቢኒያም ጌታቸው ድሬዳዋ ከተማ
ጌታነህ ከበደ ወልቂጤ ከተማ
ሽመክት ጉግሳ ፋሲል ከነማ
ምንይሉ ወንድሙ መቻል
ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ፋሲል ከነማ

@EFF!!

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

52'መድን ከባድ ኳስ ሞክሮ ነበር ሳማኪ አወጣው

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሮል
ፋሲል 0-0 መድን

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

ሱራ አሪፍ ኳስ አግኝቶ ነበር ከጨዋታ ውጭ ሆነ

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

ናቲ አሪፍ ኳስ አግኝቶ አልተሳካም

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

መድኖች አርፊ ቦታ ቅጣት ምት አግኝተው ነበር
አስቼ አስወጥቶታል

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

https://vm.tiktok.com/ZMFbagq3J/

https://vm.tiktok.com/ZMFbagq3J/

https://vm.tiktok.com/ZMFbagq3J/

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የ2ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታውን ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረገው ክለባችን ፋሲል ከነማ በመሸነፉ ደረጃውን ማሻሻል ሳይችል ቀርቷል።

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

የሙሉ ሰዓት ውጤት

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

ጎልልል!

71' ዘላለም አባቴ

(ወላይታ ድቻ 1-0 ፋሲል ከነማ)

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

እረፍት !

ወላይታ ድቻ 0-0 ፋሲል ከነማ

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

https://vm.tiktok.com/ZMFVjfefX/

https://vm.tiktok.com/ZMFVjfefX/

https://vm.tiktok.com/ZMFVjfefX/

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

🇦🇹#የፋሲል_ከነማ ደጋፊዎች በስታዲየም አይታደሙም...

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሜየር ሊግ የ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን ፋሲል ከነማ ከድሬ ዳዋ በነበረን የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ማለትም አወዳዳሪ አካሉ ባስተላለፈው ውሳኔ ምክንያት የ2015 ዓ.ም የውድድር ዘመን ሁለት ጨዋታዎችን ያለ ደጋፊ እንዲጫወት ቅጣት እንደተላለፈበት ይታወሳል።

አፄዎቹ የፊታችን እሁድ ህዳር 25/2015 ዓ.ም ከወላይታ ድቻ ጋር በድሬ ዳዋ ስታዲየም የሚያደርጉት የሁለተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ላይ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም መግባት እንደማይችሉ የተገለፀ በመሆኑ ወደ ድሬዳዋ ጉዞ ለማድረግ ያሰባችሁ እና በቦታው የምትገኙ ደጋፊዎቻችን ክለባችን ሌላ ቅጣት እንዳይጣልበት ማሊያ ባንዲራና መሰል ክለባችን የሚገልፁ ነገሮችን ይዛችሁ እንዳትገኙ ስንል እናሳስባለን።

መልዕክቱ ለደጋፊዎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉት!

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ከ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በኃላ ፋሲል ከነማ 2 ተስተካይይ ጨዋታዎች እየቀሩት 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል::

@FASILSC

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

https://vm.tiktok.com/ZMF4SQS5n/

https://vm.tiktok.com/ZMF4SQS5n/

https://vm.tiktok.com/ZMF4SQS5n/

Читать полностью…

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

 
የጨዋታው ሪፖርት

ምሽት 01፡00 ላይ የሲዳማ ቡና እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ ሲደረግ ሲዳማዎች በዘጠነኛው ሳምንት መቻልን 2-0 ሲረቱ ከተጠቀሙት አሰላለፍ ሙሉዓለም መስፍንን በጉዳት ከስብስብ ውጪ በሆነው ሙሉቀን አዲሱ ተክተዋል። ዐፄዎቹ በበኩላቸው በዘጠነኛው ሳምንት ለገጣፎ ለገዳዲን 3-0 ከተረቱበት አሰላለፍ ሱራፌል ዳኛቸውን በበዛብህ መለዩ ቦታ ተክተው ቀርበዋል።

ጨዋታው ገና እንደተጀመረ ፋሲል ከነማዎች ለማጥቃት ወደ ሲዳማ የግብ ክልል ይዘውት የሄዱት ኳስ ሳጥን ውስጥ የግራ መስመር ተከላካዩ ሰለሞን በእጅ በመንካቱ የፍፁም ቅጣት ተሰጥቷቸዋል። የፍፁም ቅጣት ምቱንም ፍቃዱ ዓለሙ ግብ አድርጎት ፋሲል ከነማ መምራት ጀምሯል። በጊዜ ግብ ያስተናገዱት ሲዳማዎች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ኳሱን ተቆጣጥረው ለመጫወት ቢጥሩም ውጤታማ መሆን አልቻሉም። በ14ኛው ደቂቃም ቡልቻ ሹራ ሳጥኑ መግቢያ ላይ ቡድኑን አቻ የማድረጊያ የመጀመሪያ ጥቃት ሰንዝሮ ወጥቶበታል።


ፋሲሎች የኳስ ቁጥጥሩን ወደ ራሳቸው ለማድረግ እየጣሩ የሚያገኟቸውን ኳሶች በዓላማ ወደ ላይኛው ሜዳ እየወሰዱ ለተጨማሪ የግብ ምንጭነት ለመጠቀም ሲሞክሩ ታይቷል። በ19ኛው ደቂቃም ከቀኝ የሳጥኑ ክፍል ሽመክት የመታው ኳስ የግቡን ቋሚ ነክቶ ሲመለስ የመጀመሪያው ግብ ባለቤት ፍቃዱ አግኝቶይ ለቡድኑ ሁለተኛ ጎል አድርጎታል። ከስድስት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ሽመክት ከፍቃዱ ጋር አንድ ሁለት ተቀባብሎ ተከላካዮችን በፍጥነት በማለፍ በቀኝ እግሩ የመታው ኳስ ሦስተኛ ጎል ሆኗል።

ጨዋታው ከቁጥጥራቸው ውጪ እየሆነባቸው የመጣው ሲዳማዎች ሁለተኛ ግብ እንደተቆጠረባቸው ለፍፁም ቅጣት ምቱ መነሻ የሆነው ሰለሞን እና አማካዩ ቴዎድሮስን በማስወጣት ከባዱን ፈተና መጋፈጥ ይዘዋል። ይህ ቢሆንም ግን በ32ኛው ደቂቃ ከቀኝ መስመር ከቅጣት ምት በተሻማና ሽመክት በቅርቡ ቋሚ ሆኖ በሞከረው አጋጣሚ ለሌላ ግብ ተዳርገው ነበር። ከደቂቃ በኋላ ደግሞ በተመሳሳይ ከቆመ ኳስ በተፈጠረ አጋጣሚ ጊት ቡድኑን ሊያነሳሳ የሚችል የግንባር አጋጣሚ ፈጥሮ ለጥቂት ወጥቶበታል።

ጨዋታው ከቁጥጥራቸው ውጪ እየሆነባቸው የመጣው ሲዳማዎች ሁለተኛ ግብ እንደተቆጠረባቸው ለፍፁም ቅጣት ምቱ መነሻ የሆነው ሰለሞን እና አማካዩ ቴዎድሮስን በማስወጣት ከባዱን ፈተና መጋፈጥ ይዘዋል። ይህ ቢሆንም ግን በ32ኛው ደቂቃ ከቀኝ መስመር ከቅጣት ምት በተሻማና ሽመክት በቅርቡ ቋሚ ሆኖ በሞከረው አጋጣሚ ለሌላ ግብ ተዳርገው ነበር። ከደቂቃ በኋላ ደግሞ በተመሳሳይ ከቆመ ኳስ በተፈጠረ አጋጣሚ ጊት ቡድኑን ሊያነሳሳ የሚችል የግንባር አጋጣሚ ፈጥሮ ለጥቂት ወጥቶበታል።

ዐፄዎቹ ሁለተኛውን አጋማሽም በፈጣን ሁኔታ ጀምረዋል። ገና በ48ኛው ደቂቃም ሀብታሙ ገዛኸኝ ከተከላካይ ጋር ታግሎ በግራ መስመር ላይ ያገኘውን ኳስ አክርሮ በመምታት አራተኛ ግብ ተቆጥሯል። አሠልጣኝ ሥዩም የአጥቂ መስራቸውን በማደስ ከጨዋታው አንዳች ነገር ለማግኘት ቢወጥኑም ጠንካራውን የፋሲል የኋላ መስመር በቀላሉ ማስከፈት አልቻሉም። በእንቅስቃሴ ረገድ ግን የተሻለ እድገት አሳይተው ነበር። በ63ኛው ደቂቃም ከመዓዘን ምት የተሻማ ኳስ ሙሉዓለም ተጨራርፎ ደርሶት ግብ ለማድረግ ቢሞክርም ሳማኬ ይዞበታል።

በዚህ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ቀዝቀዝ ያለው የሁለቱ ቡድኖች ፍልሚያ ቀጣዩን ሙከራ ለማስተናገድ መገባደጃው አካባቢ መጠበቅ ግድ ብሏል። በዚህም 85ኛው ደቂቃ ላይ አስቻለውን ቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው መናፍ ዐወል የሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተገኘን የቅጣት ምት ፍሬው ሰለሞን በቀጥታ መረብ ላይ አሳርፎታል። ሙሉ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተጨመሩት 6 ደቂቃዎች ማብቂያ ላይ አምሳሉ ጥላሁን ሳጥን ውስጥ ጥፋት ሰርቶ ሲዳማ የፍፁም ቅጣት ምት አግኝቷል። የፍፁም ቅጣት ምቱንም ይገዙ ቦጋለ የማሳረጊያ ጎል አድርጎት ጨዋታው 4ለ2 ተጠናቋል።
©soccerethiopia

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC

Читать полностью…
Subscribe to a channel